text
stringlengths 4
267
|
---|
ልበ ንጹሕ መሆን የምንችለው እንዴት ነው? |
ውስጣችንን ንጹሕ በማድረግና ማንኛውንም መጥፎ ምግባር በማስወገድ ነው። |
መንፈሳዊነታችን ይበልጥ እየተጠናከረ ሲሄድና ትክክለኛ ምግባር ስናሳይ አምላክን ማየት ከሚችሉ ሰዎች መካከል እንሆናለን። |
ጴጥሮስ በውኃው ላይ ሲራመድ በዙሪያው የነበረው ነፋስና ማዕበል ክርስቲያኖች ከሚያጋጥሟቸው ፈተናዎችና መከራዎች ጋር ሊመሳሰል ይችላል። |
ፈተናውና መከራው እጅግ ከባድ ቢሆንም እንኳ በይሖዋ እርዳታ ጸንተን መቆም እንችላለን። |
ጴጥሮስ መስመጥ የጀመረው ከኃይለኛ ነፋሱ ወይም ሞገዱ የተነሳ አለመሆኑን አስታውስ። |
የተከሰተውን ሁኔታ በቅደም ተከተል ለማሰብ ሞክር፤ ጴጥሮስ አውሎ ነፋሱን ሲያይ ፈራ። |
ጴጥሮስ ትኩረቱን በኢየሱስ ላይ ማድረግ ባቃተው ጊዜ እምነቱ ተናወጠ። |
እኛም አውሎ ነፋሱን ማየት ከጀመርን በሌላ አባባል በማዕበሉ ኃይለኝነት ላይ ካተኮርንና ይሖዋ እንደሚደግፈን ከተጠራጠርን መስመጥ ልንጀምር እንችላለን። |
መጽሐፍ ቅዱስ የእምነት መዳከምን ወይም እምነት ማጣትን በቀላሉ ተብትቦ የሚይዘን ኃጢአት ብሎ ይጠራዋል፤ ይህም እምነታችንን ሊያዳክም የሚችልን የትኛውንም ሁኔታ አቅልለን ማየት እንደሌለብን ያስገነዝበናል። |
ጴጥሮስ ከደረሰበት ሁኔታ ማየት እንደሚቻለው ትኩረታችን በተሳሳተ ነገር ላይ ካረፈ እምነታችን በቀላሉ ሊዳከም ይችላል። |
የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ከመካከላቸው ማን ታላቅ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይከራከሩ የነበረ ቢሆንም ኢየሱስ ተስፋ አልቆረጠባቸውም። |
የሰጣቸውን ምክር እንዳልሠሩበት ሲያይም ሁኔታውን በቸልታ አላለፈውም። |
ኢየሱስ አመቺ ጊዜና ቦታ መርጦ በፍቅርና በደግነት እርማት ሰጥቷቸዋል። |
እናንተም ለልጆቻችሁ ተግሣጽ በመስጠት እንደምትወዷቸው አሳዩአቸው። |
አንዳንድ ጊዜ፣ አንድ ድርጊት ትክክል ወይም ስህተት የሆነበትን ምክንያት ማስረዳቱ ብቻ በቂ ሊሆን ይችላል። |
በእርግጥ ልጆቻችሁ የነገራችኋቸውን ተግባራዊ ሳያደርጉ የሚቀሩበት ጊዜ ይኖራል። |
እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥማችሁ የኢየሱስን ምሳሌ ተከተሉ። |
ተስማሚ ጊዜና ቦታ መርጣችሁ ልጆቻችሁን ገሥጿቸው፤ ይህን የምታደርጉት በፍቅር፣ በደግነት ብሎም በትዕግሥት መመሪያ፣ ሥልጠናና እርማት በመስጠት ነው። |
በደቡብ አፍሪካ የምትኖር ኢሌን የተባለች እህት ወላጆቼ በቁጣ ወይም ምክንያቱን ሳያስረዱኝ ተግሣጽ ሰጥተውኝ አያውቁም ብላለች። |
ይህም ሳልፈራ ተረጋግቼ እንድኖር አድርጎኛል። |
ማለፍ የሌለብኝ ገደብ ምን እንደሆነ እንዲሁም ከእኔ ምን እንደሚጠበቅ አውቃለሁ። |
የይሖዋ ምሥክሮችን የሚደግፉም ሆነ አምርረው የሚቃወሙ ሰዎች ሊክዱ የማይችሉት አንድ ሐቅ አለ፤ ይኸውም የይሖዋ ምሥክሮች በስብከቱ ሥራቸው በቡድን ደረጃ በስፋት የታወቁ መሆናቸው ነው። |
በምናምንባቸው ነገሮች ባይስማሙም በምናከናውነው ሥራ እንደሚያከብሩን የሚናገሩ ሰዎች በአገልግሎት ላይ አጋጥመውህ ያውቁ ይሆናል። |
ኢየሱስ የመንግሥቱ ምሥራች በመላው ምድር እንደሚሰበክ አስቀድሞ እንደተናገረ እናውቃለን። |
ወንጌሉን ወይም ምሥራቹን እየሰበኩ እንዳሉ የሚሰማቸው በርካታ ሃይማኖታዊ ቡድኖች አሉ። |
አብዛኛውን ጊዜ ግን የሚያከናውኑት የስብከት ሥራ ስለ ራሳቸው ተሞክሮ ምሥክርነት ከመስጠት፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከመስበክ አሊያም በመገናኛ ብዙኃን ይኸውም በቴሌቪዥን ወይም በኢንተርኔት አማካኝነት ፕሮግራም ከማቅረብ ያለፈ አይደለም። |
ሌሎች ደግሞ የሚያከናውኗቸውን የበጎ አድራጎት ሥራዎች አሊያም በሕክምና እና በትምህርት መስኮች የሚያደርጉትን እርዳታ ይጠቅሳሉ። |
ጽናት የሚፈጽመው ሥራ ምንድን ነው? |
ጽናት በሁሉም ረገድ ምንም የማይጎድለን ፍጹማንና እንከን የለሽ እንድንሆን ይረዳናል። |
አብዛኛውን ጊዜ ፈተናዎች፣ ምን ድክመት እንዳለብን እንዲሁም ልናሻሽላቸው የሚገቡን ባሕርያት የትኞቹ እንደሆኑ እንድንገነዘብ ያደርጋሉ። |
የሚደርሱብንን ፈተናዎች በጽናት የምንወጣ ከሆነ ክርስቲያናዊ ባሕርያትን ይበልጥ በተሟላ መንገድ ማዳበር እንችላለን። |
ለምሳሌ ያህል፣ ይበልጥ ታጋሾች፣ አድናቂዎችና ሩኅሩኆች እንድንሆን ሊረዱን ይችላሉ። |
ጽናት ጥሩ ክርስቲያኖች እንድንሆን በመቅረጽ ረገድ አስፈላጊ የሆነ ሥራ ይፈጽማል፤ በመሆኑም የሚደርሱብንን ፈተናዎች ለማስቆም ስንል ቅዱስ ጽሑፋዊ መሠረታዊ ሥርዓቶችን ከመጣስ ልንቆጠብ ይገባል። |
ለምሳሌ ያህል፣ ርኩስ የሆኑ ሐሳቦች ወደ አእምሮህ እየመጡ ቢያስቸግሩህ ምን ታደርጋለህ? |
በፈተናው ከመሸነፍ ይልቅ እነዚህን ምኞቶች ለማስወገድ እንዲረዳህ ወደ ይሖዋ ጸልይ። |
እንዲህ በማድረግ፣ ራስን የመግዛት ባሕርይ ታዳብራለህ። |
ከማያምን የቤተሰብህ አባል ተቃውሞ እየደረሰብህ ነው? |
በተጽዕኖው ከመሸነፍ ይልቅ በሙሉ ልብህ ይሖዋን ማምለክህን ለመቀጠል ቁርጥ ውሳኔ አድርግ። |
የአምላክን ሞገስ ለማግኘት፣ መጽናት እንዳለብን አስታውስ። |
ስለ ዘር፣ ባሕል ወይም አገር ተገቢ ያልሆነ ኩራት ማዳበር ይሖዋ ለሰብዓዊ አገዛዝና ለሰው ዘር ካለው አመለካከት ጋር እንደሚጋጭ እናውቃለን። |
እርግጥ ነው፣ አምላክ ያደግንበትን ባሕል እንድንተው አይጠብቅብንም። |
እንዲያውም የተለያዩ ባሕሎች መኖራቸው በሰብዓዊው ቤተሰብ መካከል ያለውን አስደናቂ ልዩነት ያጎላል። |
ያም ቢሆን በአምላክ ዓይን ሁሉም ሰው እኩል መሆኑን ማስታወስ ይገባናል። |
ከትውልድ ቦታችን ጋር በተያያዘ ተገቢ ያልሆነ ኩራት ማዳበር ብሔራዊ ስሜት እንዲያድርብን ያደርጋል፤ ይህ ደግሞ አቋማችንን ወደማላላት ሊመራን ይችላል። |
ክርስቲያኖችም ቢሆን እንዲህ ዓይነት ኩራት ወጥመድ ሊሆንባቸው ይችላል፤ በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበረው ጉባኤ አንዳንድ አባላት እንኳ ከእነሱ የተለየ ዜግነት ባላቸው ወንድሞቻቸው ላይ አድልዎ ፈጽመዋል። |
ተገቢ ያልሆነ ኩራት በልባችን ውስጥ እያቆጠቆጠ መሆኑን እንዴት ማወቅ እንችላለን? |
ለምሳሌ የሌላ አገር ዜጋ የሆነ ክርስቲያን አንድ ሐሳብ አቀረበልን እንበል። |
እኛ ነገሮችን የምናከናውንበት መንገድ የተሻለ ነው በማለት ሐሳቡን ወዲያውኑ ውድቅ እናደርገዋለን? |
የተሻለው አካሄድ ሁላችንም በዛሬው የዕለት ጥቅስ ላይ ያለውን በመንፈስ መሪነት የተሰጠ ምክር ተግባራዊ ማድረጋችን ነው። |
ለወጣቶች በሚዘጋጁ ጽሑፎች ላይ የሚጠቀሱት አብዛኞቹ ችግሮች ሌሎቻችንንም ያጋጥሙናል። |
ሁላችንም ለእምነታችን ጥብቅና መቆም፣ ስሜታችንን መቆጣጠር፣ ጎጂ የሆነ የእኩዮች ተጽዕኖን መቋቋም እንዲሁም ከመጥፎ ጓደኛና መዝናኛ መራቅ ይኖርብናል። |
እነዚህና ሌሎች በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ለወጣቶች በተዘጋጁት ጽሑፎች ላይ ተብራርተዋል። |
በዕድሜ ከፍ ያሉ ክርስቲያኖች፣ ለወጣቶች የተዘጋጁ ጽሑፎች ለእነሱ እንደማይመጥኑ ሊሰማቸው ይገባል? |
በፍጹም! ትምህርቱ የተዘጋጀው ወጣቶችን በሚማርክ መልኩ ቢሆንም ምክሩ የተመሠረተው ጊዜ በማይሽራቸው የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ላይ ነው፤ ስለዚህ ሁላችንም ከዚህ መንፈሳዊ ዝግጅት ጥቅም ማግኘት እንችላለን። |
ጽሑፎቻችን ወጣቶች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች እንዲቋቋሙ የሚያግዟቸው ከመሆኑም ሌላ መንፈሳዊ እድገት እንዲያደርጉና ወደ ይሖዋ እንዲቀርቡ ይረዷቸዋል። |
በዕድሜ ከፍ ያሉ ክርስቲያኖችም በዚህ ረገድ ጥቅም ማግኘት ይችላሉ። |
አምላካችን ይሖዋ አንድ ይሖዋ ነው። |
ይህ ትልቅ ትርጉም ያዘለ ጥቅስ ነው! ይህ ሐሳብ እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲገቡና ምድሪቱን ሲቆጣጠሩ ያጋጠሟቸውን ተፈታታኝ ሁኔታዎች ለመቋቋም የሚያስችል ብርታት ሰጥቷቸዋል። |
እኛም ይህን ጥቅስ ልብ ማለታችን፣ ከፊታችን የሚጠብቀንን ታላቅ መከራ ለማለፍ የሚያስችል ብርታት እንድናገኝና ገነት በምትሆነው ምድር ላይ ለሚኖረው ሰላምና አንድነት አስተዋጽኦ እንድናደርግ ይረዳናል። |
ይሖዋን በሙሉ ነፍሳችን በመውደድና በማገልገል እንዲሁም በወንድማማች ማኅበራችን መካከል ያለው አንድነት ተጠብቆ እንዲኖር ልባዊ ጥረት በማድረግ፣ እሱን ብቻ ማምለካችንን እንቀጥል። |
እንዲህ የምናደርግ ከሆነ ኢየሱስ በግ እንደሆኑ ለሚፈርድላቸው ሰዎች የተናገረው የሚከተለው ሐሳብ የሚፈጸምበትን ጊዜ በልበ ሙሉነት መጠባበቅ እንችላለን፦ እናንተ አባቴ የባረካችሁ ኑ፤ ዓለም ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። |
ኢየሱስን ያዳምጡ የነበሩ ሰዎች፣ ሊያስጨንቃቸው ስለማይገባ ነገር ይጨነቁ ነበር። |
ስለዚህ ኢየሱስ መጨነቃቸውን እንዲተዉ እያሳሰባቸው ነው፤ ይህን ያለው ያለ ምክንያት አይደለም። |
ሊያሳስቡን ስለሚገቡ ነገሮችም እንኳ ከልክ በላይ መጨነቅ፣ ትኩረታችን እንዲሰረቅና ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑ መንፈሳዊ ነገሮችን ችላ እንድንል ሊያደርገን ይችላል። |
ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ከልብ ስለሚያስብ፣ በተራራ ስብከቱ ላይ ይህን አደገኛ ዝንባሌ በተመለከተ አራት ጊዜ ማሳሰቢያ ሰጥቷቸዋል። |
ኢየሱስ ሰዎች በየዕለቱ ምን እንደሚያስፈልጋቸው በሚገባ ያውቃል። |
ከዚህም በላይ ለመቋቋም የሚያስቸግር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመን በተባለው በዚህ የመጨረሻ ቀን ውስጥ የሚኖሩ ተከታዮቹ ምን ዓይነት አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንደሚያጋጥሟቸው ይረዳል። |
ብዙዎች ከሚያጋጥሟቸው ነገሮች መካከል እንደ ሥራ ማጣት፣ የኑሮ ውድነት፣ የምግብ እጥረትና የከፋ ድህነት ያሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ይገኙበታል። |
ያም ሆኖ ኢየሱስ ሕይወት ከምግብ፣ ሰውነት ከልብስ እንደሚበልጥ ተገንዝቦ ነበር። |
መንፈሳዊ ገነት የሚለው ሐሳብ ከምንጠቀምባቸው ቲኦክራሲያዊ አገላለጾች አንዱ ሆኗል። |
ይህ አገላለጽ ከአምላክና ከወንድሞቻችን ጋር ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖረን የሚያደርገውን ልዩ የሆነና በመንፈሳዊ የበለጸገ ሁኔታ ያመለክታል። |
እርግጥ ነው፣ መንፈሳዊ ገነት እና መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ የሚሉት ሐሳቦች አንድ እንደሆኑ አድርገን ልንደመድም አይገባም። |
መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ የሚባለው አምላክ ከእውነተኛው አምልኮ ጋር በተያያዘ ያደረገው ዝግጅት ነው። |
በሌላ በኩል ደግሞ መንፈሳዊው ገነት አምላክ ሞገሱን የሚያሳያቸውን እንዲሁም በመንፈሳዊው ቤተ መቅደሱ እሱን የሚያገለግሉትን ሰዎች በግልጽ ለመለየት ይረዳል። |
ጋብቻ በታሪክ ዘመናት ሁሉ የነበረ ነገር ነው። |
ጋብቻ እንዴት እንደተጀመረና ዓላማው ምን እንደሆነ መመርመራችን፣ የጋብቻን ጥምረት በተመለከተ ትክክለኛ አመለካከት እንዲኖረንና የሚያስገኛቸውን በረከቶች ይበልጥ ማጣጣም እንድንችል ይረዳናል። |
አምላክ የመጀመሪያውን ሰው አዳምን ከፈጠረ በኋላ ለእንስሳቱ ስም እንዲያወጣላቸው ወደ እሱ አመጣቸው። |
ለሰው ግን ማሟያ የሚሆን ረዳት አልነበረውም። |
በመሆኑም አምላክ፣ አዳም ከባድ እንቅልፍ እንዲወስደው ካደረገ በኋላ ከጎድን አጥንቶቹ አንዷን ወስዶ ሴት አድርጎ ሠራት፤ ከዚያም ወደ አዳም አመጣት። |
ከዚህ ማየት እንደሚቻለው የጋብቻ መሥራች አምላክ ነው። |
ይሖዋ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ይለያል፤ ከሚስቱም ጋር ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ ብሎ ተናግሮ ነበር፤ ኢየሱስም ይህንኑ መሠረታዊ ሥርዓት በድጋሚ ተናግሯል። |
አምላክ የመጀመሪያዋን ሴት ሔዋንን የፈጠራት ከአዳም የጎድን አጥንት መሆኑ፣ ባልና ሚስት ምን ያህል የጠበቀ ጥምረት እንዳላቸው ለመጀመሪያዎቹ ጥንዶች አስገንዝቧቸው መሆን አለበት። |
አምላክ፣ ባልና ሚስት እንዲፋቱ ወይም በትዳር ጓደኛቸው ላይ ሌላ ደርበው እንዲያገቡ ዓላማው አልነበረም። |
አንድ ባልና ሚስት በትዳራቸው ውስጥ እልባት ያላገኘ ከባድ ችግር በሚኖርበት ጊዜ ከሁለት አንዳቸው አሊያም ሁለቱም ለመለያየት ወይም ለመፋታት ሊያስቡ ይችላሉ። |
ባለትዳሮች ከትዳር ጓደኛቸው ጋር መለያየትን እንደ ቀላል ነገር ሊያዩት አይገባም። |
በትዳር ውስጥ ከባድ ችግሮች በሚኖሩበት ጊዜ መለያየት መፍትሔ ቢመስልም እንዲህ ማድረጉ በአብዛኛው ተጨማሪ ችግሮች ያስከትላል። |
ይሖዋ፣ ሰው አባትና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር እንደሚጣበቅ ተናግሯል፤ ኢየሱስም ይህን ሐሳብ በድጋሚ ከተናገረ በኋላ አምላክ ያጣመረውን ማንም ሰው አይለያየው ብሏል። |
ይህ ጥቅስ ባልና ሚስት ራሳቸውም ቢሆኑ አምላክ ያጣመረውን መለያየት እንደሌለባቸው ያጎላል። |
በይሖዋ ፊት ጋብቻ የዕድሜ ልክ ጥምረት ነው። |
ማናችንም ብንሆን በአምላክ ፊት ተጠያቂዎች ነን፤ ባለትዳሮች ይህን ማስታወሳቸው፣ ችግሮች ተባብሰው ከባድ ደረጃ ከመድረሳቸው በፊት ዛሬ ነገ ሳይሉ መፍትሔ ለማግኘት ከልባቸው ጥረት እንዲያደርጉ ይረዳቸዋል። |
ዳንኤልና ጓደኞቹ በግዞት በተወሰዱበት ወቅት ባቢሎናውያን፣ እነዚህን ወጣቶች የከለዳውያንን ቋንቋ በማስተማር ከባሕሉ ጋር እንዲዋሃዱ ለማድረግ ሞክረው ነበር። |
ከዚህም ሌላ እንዲያሠለጥናቸው የተመደበው የቤተ መንግሥት ባለሥልጣን የባቢሎናውያን ስም አወጣላቸው። |
ለዳንኤል የተሰጠው ስም የባቢሎን ዋነኛ አምላክ ከሆነው ከቤል ጋር የተያያዘ ነበር። |
ንጉሥ ናቡከደነጾር ይህን ያደረገው በዳንኤል አስተሳሰብ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ይኸውም አምላኩ ይሖዋ፣ ለባቢሎን አምላክ እንደተገዛ ሆኖ እንዲሰማው ለማድረግ ፈልጎ ሊሆን ይችላል። |
ዳንኤል የንጉሡ ምርጥ ምግብ ቢቀርብለትም በዚህ ምግብ ላለመርከስ በልቡ ቁርጥ ውሳኔ አድርጓል። |
ዳንኤል ቅዱሳን መጻሕፍትን በአፍ መፍቻ ቋንቋው ያጠና ስለነበር በሌላ አገር ቢኖርም መንፈሳዊነቱን ሊጠብቅ ችሏል። |
ግርጌ በመሆኑም ወደ ባቢሎን ከተወሰደ ከ70 ዓመታት ገደማ በኋላም እንኳ የሚታወቀው በዕብራይስጥ ስሙ ነበር። |
ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ምሥራቹን ለመስበክ የትኞቹን ዘዴዎች ተጠቅመዋል? |
ምሥራቹን ለማድረስ፣ ሰዎች በብዛት ወደሚገኙባቸው ቦታዎችና ከቤት ወደ ቤት ሄደዋል። |