label
class label
4 classes
headline
stringlengths
17
80
text
stringlengths
1
16.8k
headline_text
stringlengths
28
16.8k
url
stringlengths
36
49
2health
በቀጣይ በዓለም ላይ የሚከሰቱ ወረርሸኞች ከኮቪድ በላይ ገዳይ ሊሆኑ ይችላሉ ተባለ
በዓለማችን ከዚህ በኋላ የሚከሰቱ ወረርሽኞች ከኮሮረናቫይረስ በላይ የከፉ ገዳይ ሊሆኑ እንደሚችሉ የኦክስፎርድ አስትራዜኔካ ክትባትን ከፈጠሩት ተመራማሪዎች መካከል አንዷ ባለሙያ ተናገሩ። ፕሮፌሰር ሳራህ ጊልበርት እንደሚሉት ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ዝግጁነት ለመደገፍ መንግሥታት በቂ ድጋፍ ማድረግ ያለባቸው ሲሆን አሁን የተገኙ ስኬቶችንም ማስቀጠል አስፈላጊ ነው። ፕሮፌሰሯ አክለውም ጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙት ክትባቶች አዲሱን የቫይረስ አይነት ኦሚክሮን ለመከላከል ብዙም አቅም ላይኖራቸው እንደሚችልም ጠቁመዋል። ስለአዲሱ ቫይረስ በቂ መረጃ እስከሚገኝ ድረስ ሰዎች በጥንቃቄ እንዲንቀሳቀሱም መክረዋል። "ወረርሽኝ ሕይወታችንን እና አኗኗራችንን አደጋ ላይ ሲጥል ይህ የመጨረሻው የሚሆን አይመስለኝም። እውነታው ቀጣዩ ወረርሽኝ በጣም ከባድ ሊሆን እንደሚችል ነው። በፍጥነት የሚዛመት፣ በከፍተኛ ሁኔታ ገዳይ አልያም ሁለቱንም ያጣመረ ሊሆን ይችላል" ብለዋል። "በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ያለፍነውን ችግር መርሳት የለብንም። ወረርሽኙ በምጣኔ ሀብታችን ላይ ያሳደረው ጫና ወደፊት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን እንዳንቆጣጠር ሊያደርገን አይገባም'' ሲሉ ያሳስባሉ። ፕሮፌሰር ሳራህ ጊልበርት ስለአዲሱ ኦሚክሮን ቫይረስ ሲናገሩ "አዲሱ ቫይረስ እራሱን አሻሽሎ ስለመጣ በክትባት መልክ ወይም በኮሮረናቫይረስ ስንያዝ የምናዳብረው በሽታ የመከላከል አቅም ብዙም ላይጠቅመን ይችላል" ብለዋል። አክለውም ስለአዲሱ ቫይረስ በቂ መረጃ እስከሚገኝና ምርምሮች እስከሚደረጉ ድረስ ሰዎች ስርጭቱን ለመቀነስ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። በኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የተገኘው ትምህርትና ክትባቶችን በፍጥነት የማድረስ ልማድ ሊቀጥል እንደሚገባ ያሳሰቡት ፕሮፌሰሯ ከዚህ በኋላ መሰል እርምጃዎች የተለመዱ መሆን አለባቸው ብለዋል። የኦሚክሮን ስርጭትን ለመቆጣጠር እንዲቻል በማለት ቅዳሜ ዕለት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የሚጓዙ ሰዎች ከበረራቸው አስቀድመው የኮሮረናቫይረስ ምርምራ እንዲያደርጉ መንግሥት አሳስቧል። በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) እስካሁን 246 ሰዎች በአዲሱ ኦሚክሮን መያዛቸው የተረጋተጠ ሲሆን ትናንት ዕሁድ ዕለት ብቻ 86 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን መንግሥት አስታውቋል። ነገር ግን የዩኬን መንግሥት የሚያማክሩ አንድ ተመራማሪ የጉዞ እገዳውና ሌሎች መመሪያዎች የዘገዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ፕሮፌሰር ማርክ ዉልሐውስ እንደሚሉት የመንግሥት ውሳኔ የዘገየ ሲሆን እዚህ ግባ የሚባል ለውጥ ያመጣል ብለው እንደማያምኑም ተናግረዋል።
በቀጣይ በዓለም ላይ የሚከሰቱ ወረርሸኞች ከኮቪድ በላይ ገዳይ ሊሆኑ ይችላሉ ተባለ በዓለማችን ከዚህ በኋላ የሚከሰቱ ወረርሽኞች ከኮሮረናቫይረስ በላይ የከፉ ገዳይ ሊሆኑ እንደሚችሉ የኦክስፎርድ አስትራዜኔካ ክትባትን ከፈጠሩት ተመራማሪዎች መካከል አንዷ ባለሙያ ተናገሩ። ፕሮፌሰር ሳራህ ጊልበርት እንደሚሉት ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ዝግጁነት ለመደገፍ መንግሥታት በቂ ድጋፍ ማድረግ ያለባቸው ሲሆን አሁን የተገኙ ስኬቶችንም ማስቀጠል አስፈላጊ ነው። ፕሮፌሰሯ አክለውም ጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙት ክትባቶች አዲሱን የቫይረስ አይነት ኦሚክሮን ለመከላከል ብዙም አቅም ላይኖራቸው እንደሚችልም ጠቁመዋል። ስለአዲሱ ቫይረስ በቂ መረጃ እስከሚገኝ ድረስ ሰዎች በጥንቃቄ እንዲንቀሳቀሱም መክረዋል። "ወረርሽኝ ሕይወታችንን እና አኗኗራችንን አደጋ ላይ ሲጥል ይህ የመጨረሻው የሚሆን አይመስለኝም። እውነታው ቀጣዩ ወረርሽኝ በጣም ከባድ ሊሆን እንደሚችል ነው። በፍጥነት የሚዛመት፣ በከፍተኛ ሁኔታ ገዳይ አልያም ሁለቱንም ያጣመረ ሊሆን ይችላል" ብለዋል። "በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ያለፍነውን ችግር መርሳት የለብንም። ወረርሽኙ በምጣኔ ሀብታችን ላይ ያሳደረው ጫና ወደፊት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን እንዳንቆጣጠር ሊያደርገን አይገባም'' ሲሉ ያሳስባሉ። ፕሮፌሰር ሳራህ ጊልበርት ስለአዲሱ ኦሚክሮን ቫይረስ ሲናገሩ "አዲሱ ቫይረስ እራሱን አሻሽሎ ስለመጣ በክትባት መልክ ወይም በኮሮረናቫይረስ ስንያዝ የምናዳብረው በሽታ የመከላከል አቅም ብዙም ላይጠቅመን ይችላል" ብለዋል። አክለውም ስለአዲሱ ቫይረስ በቂ መረጃ እስከሚገኝና ምርምሮች እስከሚደረጉ ድረስ ሰዎች ስርጭቱን ለመቀነስ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። በኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የተገኘው ትምህርትና ክትባቶችን በፍጥነት የማድረስ ልማድ ሊቀጥል እንደሚገባ ያሳሰቡት ፕሮፌሰሯ ከዚህ በኋላ መሰል እርምጃዎች የተለመዱ መሆን አለባቸው ብለዋል። የኦሚክሮን ስርጭትን ለመቆጣጠር እንዲቻል በማለት ቅዳሜ ዕለት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የሚጓዙ ሰዎች ከበረራቸው አስቀድመው የኮሮረናቫይረስ ምርምራ እንዲያደርጉ መንግሥት አሳስቧል። በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) እስካሁን 246 ሰዎች በአዲሱ ኦሚክሮን መያዛቸው የተረጋተጠ ሲሆን ትናንት ዕሁድ ዕለት ብቻ 86 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን መንግሥት አስታውቋል። ነገር ግን የዩኬን መንግሥት የሚያማክሩ አንድ ተመራማሪ የጉዞ እገዳውና ሌሎች መመሪያዎች የዘገዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ፕሮፌሰር ማርክ ዉልሐውስ እንደሚሉት የመንግሥት ውሳኔ የዘገየ ሲሆን እዚህ ግባ የሚባል ለውጥ ያመጣል ብለው እንደማያምኑም ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59545549
3politics
የነዳጅ አምራች አገራት ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ ምርታቸውን እምብዛም እንደማይጨምሩ አስታወቁ
ምንም እንኳን የዓለም የነዳጅ ዋጋ በሰባት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ በሚባል ደረጃ ከፍ ቢልም ትልልቅ የሚባሉት ነዳጅ አምራች አገራት ግን የነዳጅ ምርታቸውን መጠን በትንሹ ብቻ እንደሚጨምሩ አስታውቀዋል። በሩሲያ የሚመራው የነዳጅ ላኪ አገራት ድርጅት ኦፔክ እና አጋሮቹ በምንም አይነት ሁኔታ ከድንበራቸው የሚወጣ ነዳጅ እምብዛም ከፍ እንደማያደርጉ ነው የተገለጸው። 23 አባል አገራት ያሉት ድርጅቱ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ በየቀኑ ተጨማሪ 400 ሺ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ብቻ ለገበያ እንደሚያቀርቡ ተገልጿል። ድርጅቱ በአውሮፓውያኑ 2021 አባል አገራት በተስማሙበት የምርት ሂደትን ይከተላል። አገራቱ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ቀንሶ የነበረውን ምርት ቀስ በቀስ ለማስተካከል ነበር የተስማሙት። በወቅቱ የነዳጅ ፍላጎት በመቀነሱ አገራት የምርት መጠናቸውን ለመቀነስ ተገድደው ነበር። ነገር ግን ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ የአንድ ድፍድፍ በርሜል ነዳጅ ዋጋ 113 ዶላር ደርሷል። ኦፔክ+ የሰሞኑን የነዳጅ ዋጋ መጨመርና ስጋት በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ላይ በአሁኑ ወቅት የነዳጅ ምርት እጥረት እንደሌለ ገልጿል። በሌላ በኩል የዓለም አቀፉ ኢነርጂ ኤጀንሲ አባል አገራት በበኩላቸው ከወሳኝ መጠባበቂያዎቻቸው ተጨማሪ ነዳጅ 60 ሚሊየን በርሜል ነዳጅ ለመልቀቅ ተስማምተዋል። ከዚህ ነዳጅ ግማሽ የሚሆነው የሚመጣው ከአሜሪካ እንደሚሆን ይጠበቃል። ነገር ግን ይህ ውሳኔ እንኳን የስቶክ ገበያውንም ሆነ እየጨመረ የመጣውን የነዳጅ ዋጋ ግሽበት በአፋጣኝ ያስተካክለዋል ተብሎ አይጠበቅም። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት የነዳጅ ዋጋ በቅርብ ወራት ውስጥ ወደነበረበት የመመለስ ዕድሉ ጠባብ ነው። እንደ ቢፒ እና ሼል ያሉ ትልልቅ የነዳጅ አጣሪና አከፋፋይ ድርጅቶች ከሩሲያ ለቅቀው እንደሚወጡ ማስታወቃቸው ደግሞ ገበያው እንዳይረጋጋ እንደሚያደርገው ተገልጿል። እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት የሩሲያ የነዳጅ ደንበኞች ትልቅ ችግር እየገጠማቸው ነው። የምዕራቡ ዓለም አገራት ሩሲያ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ ተከትሎ ድርጅቶቹ ክፍያ መፈጸም ሆነ መቀበል እንዲሁም የነዳጅ ዝውውር ላይ ከፍተኛ ጫና እያጋጠማቸው ነው። ''በአጭር ጊዜ ውስጥ የነዳጅ ዋጋ ሲጨምር እየተመለከትን ነው። ከሩሲያ ጋር በተያያዘ ያለው ግራ መጋባት የነዳጅ ገበያው እንዳይረጋጋ አድርጎታል'' ይላሉ በዋሽንግተን የስትራቴጂክ እና ዓለም አቀፍ ጥናት ባለሙያው ቤን ካሂል። ነዳጅ አምራች አገራት ምርታቸውን ለምን መጨመር አልፈለጉም? ቁልፍ የሚባሉት ነዳጅ አምራች አገራት አሁን ላይ ያለውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር በሚል ምርት ብንጨምር በሚቀጥለው ዓመት ላይ ከፍተኛ የሆነ የነዳጅ ምርት ገበያው ላይ ሊትረፈረፍ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። ይህ ደግሞ የነዳጅ ዋጋና በእጅጉ ያወርደዋል። ምንም እንኳን አንዳንድ የነዳጅ ላኪ ድርጅቶች ከሩሲያ የሚመጣውን አንደኛ ደረጃ ነዳጅ በርካሽ ዋጋ ለማሸጥ ቢሞክሩም ገዢ እንደጠፋ እየተነገረ ነው። ሩሲያ ከአሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ በመቀጠል የዓለማችን ሶስተኛዋ የነዳጅ አምራች አገር ነች። በዚህም ከዓለማችን የነዳጅ ፍላጎት ከ8 እስከ 10 በመቶ የሚሆነውን የምታሟላው ሩሲያ ነች። ከዚህ በተጨማሪ አብዛኛው አውሮፓ 40 በመቶ የሚሆነውን የተፈጥሮ ጋዝ የሚያገኘው ከሩሲያ ነው። ለዚህም ይመስላል የምዕራቡ ዓለም አገራት ሩሲያ ላይ ከነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ጋር በተያያዘ ጠንካራ ማዕቀብ መጣል የከበዳቸው። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት የኦፔክ+ አባል አገራት በዩክሬን ሩሲያ ቀውስ ምክንያት ወደፊት ሊከሰት የሚችለውን ቀውስ ከማየት ይልቅ አሁን ላይ ገበያው ምን ይመስላል የሚለውን ከግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚፈልጉ ይገልጻሉ። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እየጨመረ በመጣው የነዳጅ ዋጋ ምክንያት ትንሽ የተደናገጡ ይመስላል። እንደ ሳኡዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ያሉ የኦፔክ+ አባል አገራት ላይ ጫና ለማሳደር ቢሞክሩም እምብዛም አልተሳካለቸውም። በሌላ በኩል ደግሞ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከአቡ ዳቢ ልዑል ሼክ ሞሀመድ ቢን ዛይድ ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸውም የኦፔክ+ አባል አገራት የወሰኑት በወሰኑት ውሳኔ ላይ ስለመጽናት ተነጋግረዋል። እስካሁን ድረስ በርካታ የመካከለኛው ምስራቅ ነዳጅ አምራች አገራት ከዩክሬን ጉዳይ ጋር በተያያዘ ዝምታን የመረጡ ይመስላል። ባሳለፍነው ሳምንት የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት የሩሲያን ወረራ የሚቃወም የአቋም መግለጫ ሲያወጣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በድምጸ ታቅቦ አልፋለች። ተንታኞች እንደሚሉት ዩኤኢ እና ሳኡዲ አረቢያ በጉዳዩ ላይ የገለልተኝነት ውሳኔ እየተከተሉ ነው ብለዋል።
የነዳጅ አምራች አገራት ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ ምርታቸውን እምብዛም እንደማይጨምሩ አስታወቁ ምንም እንኳን የዓለም የነዳጅ ዋጋ በሰባት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ በሚባል ደረጃ ከፍ ቢልም ትልልቅ የሚባሉት ነዳጅ አምራች አገራት ግን የነዳጅ ምርታቸውን መጠን በትንሹ ብቻ እንደሚጨምሩ አስታውቀዋል። በሩሲያ የሚመራው የነዳጅ ላኪ አገራት ድርጅት ኦፔክ እና አጋሮቹ በምንም አይነት ሁኔታ ከድንበራቸው የሚወጣ ነዳጅ እምብዛም ከፍ እንደማያደርጉ ነው የተገለጸው። 23 አባል አገራት ያሉት ድርጅቱ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ በየቀኑ ተጨማሪ 400 ሺ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ብቻ ለገበያ እንደሚያቀርቡ ተገልጿል። ድርጅቱ በአውሮፓውያኑ 2021 አባል አገራት በተስማሙበት የምርት ሂደትን ይከተላል። አገራቱ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ቀንሶ የነበረውን ምርት ቀስ በቀስ ለማስተካከል ነበር የተስማሙት። በወቅቱ የነዳጅ ፍላጎት በመቀነሱ አገራት የምርት መጠናቸውን ለመቀነስ ተገድደው ነበር። ነገር ግን ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ የአንድ ድፍድፍ በርሜል ነዳጅ ዋጋ 113 ዶላር ደርሷል። ኦፔክ+ የሰሞኑን የነዳጅ ዋጋ መጨመርና ስጋት በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ላይ በአሁኑ ወቅት የነዳጅ ምርት እጥረት እንደሌለ ገልጿል። በሌላ በኩል የዓለም አቀፉ ኢነርጂ ኤጀንሲ አባል አገራት በበኩላቸው ከወሳኝ መጠባበቂያዎቻቸው ተጨማሪ ነዳጅ 60 ሚሊየን በርሜል ነዳጅ ለመልቀቅ ተስማምተዋል። ከዚህ ነዳጅ ግማሽ የሚሆነው የሚመጣው ከአሜሪካ እንደሚሆን ይጠበቃል። ነገር ግን ይህ ውሳኔ እንኳን የስቶክ ገበያውንም ሆነ እየጨመረ የመጣውን የነዳጅ ዋጋ ግሽበት በአፋጣኝ ያስተካክለዋል ተብሎ አይጠበቅም። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት የነዳጅ ዋጋ በቅርብ ወራት ውስጥ ወደነበረበት የመመለስ ዕድሉ ጠባብ ነው። እንደ ቢፒ እና ሼል ያሉ ትልልቅ የነዳጅ አጣሪና አከፋፋይ ድርጅቶች ከሩሲያ ለቅቀው እንደሚወጡ ማስታወቃቸው ደግሞ ገበያው እንዳይረጋጋ እንደሚያደርገው ተገልጿል። እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት የሩሲያ የነዳጅ ደንበኞች ትልቅ ችግር እየገጠማቸው ነው። የምዕራቡ ዓለም አገራት ሩሲያ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ ተከትሎ ድርጅቶቹ ክፍያ መፈጸም ሆነ መቀበል እንዲሁም የነዳጅ ዝውውር ላይ ከፍተኛ ጫና እያጋጠማቸው ነው። ''በአጭር ጊዜ ውስጥ የነዳጅ ዋጋ ሲጨምር እየተመለከትን ነው። ከሩሲያ ጋር በተያያዘ ያለው ግራ መጋባት የነዳጅ ገበያው እንዳይረጋጋ አድርጎታል'' ይላሉ በዋሽንግተን የስትራቴጂክ እና ዓለም አቀፍ ጥናት ባለሙያው ቤን ካሂል። ነዳጅ አምራች አገራት ምርታቸውን ለምን መጨመር አልፈለጉም? ቁልፍ የሚባሉት ነዳጅ አምራች አገራት አሁን ላይ ያለውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር በሚል ምርት ብንጨምር በሚቀጥለው ዓመት ላይ ከፍተኛ የሆነ የነዳጅ ምርት ገበያው ላይ ሊትረፈረፍ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። ይህ ደግሞ የነዳጅ ዋጋና በእጅጉ ያወርደዋል። ምንም እንኳን አንዳንድ የነዳጅ ላኪ ድርጅቶች ከሩሲያ የሚመጣውን አንደኛ ደረጃ ነዳጅ በርካሽ ዋጋ ለማሸጥ ቢሞክሩም ገዢ እንደጠፋ እየተነገረ ነው። ሩሲያ ከአሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ በመቀጠል የዓለማችን ሶስተኛዋ የነዳጅ አምራች አገር ነች። በዚህም ከዓለማችን የነዳጅ ፍላጎት ከ8 እስከ 10 በመቶ የሚሆነውን የምታሟላው ሩሲያ ነች። ከዚህ በተጨማሪ አብዛኛው አውሮፓ 40 በመቶ የሚሆነውን የተፈጥሮ ጋዝ የሚያገኘው ከሩሲያ ነው። ለዚህም ይመስላል የምዕራቡ ዓለም አገራት ሩሲያ ላይ ከነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ጋር በተያያዘ ጠንካራ ማዕቀብ መጣል የከበዳቸው። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት የኦፔክ+ አባል አገራት በዩክሬን ሩሲያ ቀውስ ምክንያት ወደፊት ሊከሰት የሚችለውን ቀውስ ከማየት ይልቅ አሁን ላይ ገበያው ምን ይመስላል የሚለውን ከግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚፈልጉ ይገልጻሉ። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እየጨመረ በመጣው የነዳጅ ዋጋ ምክንያት ትንሽ የተደናገጡ ይመስላል። እንደ ሳኡዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ያሉ የኦፔክ+ አባል አገራት ላይ ጫና ለማሳደር ቢሞክሩም እምብዛም አልተሳካለቸውም። በሌላ በኩል ደግሞ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከአቡ ዳቢ ልዑል ሼክ ሞሀመድ ቢን ዛይድ ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸውም የኦፔክ+ አባል አገራት የወሰኑት በወሰኑት ውሳኔ ላይ ስለመጽናት ተነጋግረዋል። እስካሁን ድረስ በርካታ የመካከለኛው ምስራቅ ነዳጅ አምራች አገራት ከዩክሬን ጉዳይ ጋር በተያያዘ ዝምታን የመረጡ ይመስላል። ባሳለፍነው ሳምንት የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት የሩሲያን ወረራ የሚቃወም የአቋም መግለጫ ሲያወጣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በድምጸ ታቅቦ አልፋለች። ተንታኞች እንደሚሉት ዩኤኢ እና ሳኡዲ አረቢያ በጉዳዩ ላይ የገለልተኝነት ውሳኔ እየተከተሉ ነው ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60598934
2health
ከአራስ እስከ 114 ዓመት ዕድሜ የኮቪድ-19 ሕሙማንን ያከመው የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ውለታ
ላለፉት ሁለት ዓመታት መላውን ዓለም አዳርሶ 15 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተከሰተበት የመጀመሪያ ወቅት ሥራ የጀመረው ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በኢትዮጵያ የወረርሽኑ ጥረት ውስጥ ጉልህ ቦታን ይዟል። ስለ ወረርሽኙ ምንነትና አጠቃላይ ሁኔታ ዝርዝር መረጃ ባልነበረበት ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕሙማንን ተቀብሎ ያስተናገደው ሆስፒታሉ፣ ባለፈው ሐሙስ በእንክብካቤው ስር የነበሩት ብቸኛ ታካሚ አገግመው ወደ ቤታቸው በመሄዳቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ሆስፒታሉ ውስጥ የኮቪድ ታማሚ እንደሌለ አሳውቋል። የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ ታካሚው አገግመው ወደ ቤታቸው በመሸኘታቸው ላለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ የኮቪድ-19 የሕክምና ማዕከል ሆኖ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለው ሆስፒታል ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ታካሚ ውሎ አድሯል። የሕክምና ማዕከሉ የኮሮናቫይረስ ወረርሽን በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በሁሉም የበሽታው ማዕበል ደረጃዎች ወቅት ሕምና የሚያስፈልጋቸውን ሕሙማን ሲያገለግል ቆይቷል። አገሪቱን ባጋጠሟት አራት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ማዕበሎች ውስጥ ባለፉት ሁለት ዓመታት ምንም ታካሚ ሳይኖር ያሳለፉበት ጊዜ እንዳልነበረ ዶ/ር ያሬድ አስታውሰዋል። በአራተኛው ማዕበል ተቀብለው ሕክምና ሲሰጧቸው ከነበሩ ሕሙማን መካከል የሕክምና ባለሙያ የሆኑት ታካሚ አስፈላጊውን ድጋፍ አግኝተው በማገገማቸው ነው ሐሙስ መጋቢት 27/2041ዓ. ም. ከሆስፒታሉ የተሸኙት። በዚህም ሆስፒታሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ሕክምና የሚያስፈልገው አንድም ታማሚ ሳይረኖረው 24 ሰዓታትን አሳልፏል። "ሕክምናውን በተሳካ ሁኔታ ጨርሶ የተሸኘው ሰው፣ በወረርሽኙ አራተኛ ማዕበል አገግሞ ከሆስፒታሉ የወጣ የመጨረሻው ሰው ይሆናል ብለን ተስፋ እንዳርጋለን" ሲሉ ዶ/ር ያሬድ ለቢቢሲ ምኞታቸውን ተናግረዋል። ኮቪድ-19 መጋቢት 04/2012 ዓ. ም. በኢትዮጵያ ውሰጥ መገኘቱ ሲረጋገጥ በአገሪቱ የተገኘ የመጀመሪያውን ጃፓናዊ ታማሚ በመቀበል ሥራ የጀመረው የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል፣ ከሁለት ዓመታት ያልተቋረጠ አገልግሎት በኋላ ስማቸው ያልተገለጹትን ለአሁኑ የመጨረሻው ሊባሉ የሚችሉትን ሕመምተኛ አክሞ ለመሸኘት በቅቷል። በሁለት ዓመታት ውስጥ ሐሙስ ዕለት አገግመው እስከወጡት ታካሚ ድረስ ሆስፒታሉ 6546 የኮሮናቫይረስ ሕሙማንን ያስተናገደ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ ወይም 87 በመቶ የሚሆኑት ባገኙት ሕክምና አገግመው መውጣታቸውን ዶ/ር ያሬድ ገልጸዋል። ከዚህ ባሻገር ከ800 በላይ የሚሆኑት ወይም አጠቃላይ ሆስፒታሉ ካስተናገዳቸው ሕሙማን መካከል 13 በመቶው ደግሞ በወረርሽኙ ሰበብ ለህልፈት ተዳርገዋል። የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ይህንን አገልግሎት በሰጠባቸው ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ወረርሽኙ የተለያዩ ጫናዎች ባለሙያዎች ላይ አሳድሮ እንደነበር የሚያስታውሱት ዶ/ር ያሬድ "በተለይ በመጀመሪያው ጊዜ ላይ ስለ በሽታው ዝርዝር ሁኔታ ከነበረው ዝቅተኛ መረጃ አንጻር ባለሙያዎች ከፍተኛ የሥነ ልቦና ጫና ገጥሟቸው ነበር" ይላሉ። ነገር ግን የሕክምና ባለሙያዎቹ ቃል ኪዳናቸውን ጠቀብቀው አገራቸውንና ሕዝባቸውን በማስቀደም በዚያ አስፈሪና አስቸጋሪ ወቅት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ባለፉት ሁለት ዓመታት ያለማቋረጥ ለመወጣት ችለዋል። በተለይ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሕሙማን ወደ ሆስፒታሉ በብዛት መምጣት በጀመሩበት በሁለተኛው እና በሦስተኛ ዙር የወረርሽኑ ማዕበል ወቅት፣ የሰው ሠራሽ መተንፈሻ ድጋፍ የሚፈልጉ እና ወደ ጽኑ ሕሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች መጨመሩ ከባድ ጫናን በሆስፒታሉ ላይ አስከትሎ ነበር። በተጨማሪ ደግሞ ለሌሎች ሕክምናዎች ከሚሰጡ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች መካከልም በበሽታው የሚያዙ ስለነበሩ ከባድ ሥራና ኃላፊነትን ከሚወጡት ባለሙያዎች ሲቀነሱ የሰው ኃይል እጥረት ገጥሟቸው የነበረበት ጊዜ እንደነበር ዶ/ር ያሬድ ይጠቅሳሉ። ከባለሙያዎቹ መካከል በተደጋጋሚ ጭምር በበሽታው የመያዝ ሁኔታ የገጠማቸው ቢኖሩም ለሞት የተዳረገ የሆስፒታሉ ባልደረባ አልነበረም። የመጀመሪያው የኮቪድ-19 ሕክምና ማዕከል የሆነው የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ከወረርሽኙ መከሰት ጀምሮ በሆስፒታል ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን፣ የመተንፈሻ ድጋፍ የሚያሻቸውን እንዲሁም የጽኑ ሕሙማን ሕክምና ድጋፍ የሚፈልጉ የኮቪድ-19 ሕሙማንን አስተናግዷል። በተጨማሪም በኮሮናቫይረስ ተይዘው ተጓዳኝ ሕመም ኖሮባቸው የሐኪም የቅርብ ክትትልና ድጋፍ የሚያስፍለጋቸው፣ ነፍሰ ጡሮችና የመውለጃ ጊዜያቸው የደረሱ ሕሙማንን ጭምር በመቀበል ከወረርሽኙ ጋር የተያያዙ ዘርፈ ብዙ የሕክምና አገልግሎቶችን ሲሰጥ ቆይቷል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ሆስፒታሉ በሰጠው አገልግሎት ከወረርሽኙ የዳኑ ሰዎች በተለያየ የዕድሜ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። እዚያው የተወለዱ የአንድ ቀን ዕድሜ ካላቸው አራስ ሕጻናት አንስቶ አስከ 114 ዓመት ዕድሜ ያላቸው አዛውንት ድረስ የኮቪድ ሕሙማንን ሆስፒታሉ አስተናግዷል። ከአንድ ወር በታች ዕድሜ ያላቸው በበሽታው ተይዘው ለሕክምና የገቡት ሁሉም ጨቅላ ሕጻናት አገግመው እንደወጡ ዶ/ር ያሬድ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በሁለት ዓመታት ውስጥ በርካታ መልካምና አሳዛኝ አጋጣሚዎች በሆስፒታሉ ውስጥ ማጋጠሙን በመጥቀስ፣ እነዚህን የሆስፒታሉን ክስተቶች እና ሌሎች የሚነገሩ ታሪኮችን በመጽሐፍ የማቅረብ ሐሳብ እንዳላቸው ዶ/ር ያሬድ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ መገኘቱን ተከትሎ በአገሪቱ ውስጥ በተደረጉ ምርመራዎች ከ470 ሺህ በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ከ7500 በላይ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሰበብ ለሞት መዳረጋቸውን ከጤና ሚኒስቴር የወጣው ወቅታዊ መረጃ ያመለክታል።
ከአራስ እስከ 114 ዓመት ዕድሜ የኮቪድ-19 ሕሙማንን ያከመው የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ውለታ ላለፉት ሁለት ዓመታት መላውን ዓለም አዳርሶ 15 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተከሰተበት የመጀመሪያ ወቅት ሥራ የጀመረው ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በኢትዮጵያ የወረርሽኑ ጥረት ውስጥ ጉልህ ቦታን ይዟል። ስለ ወረርሽኙ ምንነትና አጠቃላይ ሁኔታ ዝርዝር መረጃ ባልነበረበት ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕሙማንን ተቀብሎ ያስተናገደው ሆስፒታሉ፣ ባለፈው ሐሙስ በእንክብካቤው ስር የነበሩት ብቸኛ ታካሚ አገግመው ወደ ቤታቸው በመሄዳቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ሆስፒታሉ ውስጥ የኮቪድ ታማሚ እንደሌለ አሳውቋል። የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ ታካሚው አገግመው ወደ ቤታቸው በመሸኘታቸው ላለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ የኮቪድ-19 የሕክምና ማዕከል ሆኖ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለው ሆስፒታል ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ታካሚ ውሎ አድሯል። የሕክምና ማዕከሉ የኮሮናቫይረስ ወረርሽን በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በሁሉም የበሽታው ማዕበል ደረጃዎች ወቅት ሕምና የሚያስፈልጋቸውን ሕሙማን ሲያገለግል ቆይቷል። አገሪቱን ባጋጠሟት አራት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ማዕበሎች ውስጥ ባለፉት ሁለት ዓመታት ምንም ታካሚ ሳይኖር ያሳለፉበት ጊዜ እንዳልነበረ ዶ/ር ያሬድ አስታውሰዋል። በአራተኛው ማዕበል ተቀብለው ሕክምና ሲሰጧቸው ከነበሩ ሕሙማን መካከል የሕክምና ባለሙያ የሆኑት ታካሚ አስፈላጊውን ድጋፍ አግኝተው በማገገማቸው ነው ሐሙስ መጋቢት 27/2041ዓ. ም. ከሆስፒታሉ የተሸኙት። በዚህም ሆስፒታሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ሕክምና የሚያስፈልገው አንድም ታማሚ ሳይረኖረው 24 ሰዓታትን አሳልፏል። "ሕክምናውን በተሳካ ሁኔታ ጨርሶ የተሸኘው ሰው፣ በወረርሽኙ አራተኛ ማዕበል አገግሞ ከሆስፒታሉ የወጣ የመጨረሻው ሰው ይሆናል ብለን ተስፋ እንዳርጋለን" ሲሉ ዶ/ር ያሬድ ለቢቢሲ ምኞታቸውን ተናግረዋል። ኮቪድ-19 መጋቢት 04/2012 ዓ. ም. በኢትዮጵያ ውሰጥ መገኘቱ ሲረጋገጥ በአገሪቱ የተገኘ የመጀመሪያውን ጃፓናዊ ታማሚ በመቀበል ሥራ የጀመረው የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል፣ ከሁለት ዓመታት ያልተቋረጠ አገልግሎት በኋላ ስማቸው ያልተገለጹትን ለአሁኑ የመጨረሻው ሊባሉ የሚችሉትን ሕመምተኛ አክሞ ለመሸኘት በቅቷል። በሁለት ዓመታት ውስጥ ሐሙስ ዕለት አገግመው እስከወጡት ታካሚ ድረስ ሆስፒታሉ 6546 የኮሮናቫይረስ ሕሙማንን ያስተናገደ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ ወይም 87 በመቶ የሚሆኑት ባገኙት ሕክምና አገግመው መውጣታቸውን ዶ/ር ያሬድ ገልጸዋል። ከዚህ ባሻገር ከ800 በላይ የሚሆኑት ወይም አጠቃላይ ሆስፒታሉ ካስተናገዳቸው ሕሙማን መካከል 13 በመቶው ደግሞ በወረርሽኙ ሰበብ ለህልፈት ተዳርገዋል። የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ይህንን አገልግሎት በሰጠባቸው ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ወረርሽኙ የተለያዩ ጫናዎች ባለሙያዎች ላይ አሳድሮ እንደነበር የሚያስታውሱት ዶ/ር ያሬድ "በተለይ በመጀመሪያው ጊዜ ላይ ስለ በሽታው ዝርዝር ሁኔታ ከነበረው ዝቅተኛ መረጃ አንጻር ባለሙያዎች ከፍተኛ የሥነ ልቦና ጫና ገጥሟቸው ነበር" ይላሉ። ነገር ግን የሕክምና ባለሙያዎቹ ቃል ኪዳናቸውን ጠቀብቀው አገራቸውንና ሕዝባቸውን በማስቀደም በዚያ አስፈሪና አስቸጋሪ ወቅት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ባለፉት ሁለት ዓመታት ያለማቋረጥ ለመወጣት ችለዋል። በተለይ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሕሙማን ወደ ሆስፒታሉ በብዛት መምጣት በጀመሩበት በሁለተኛው እና በሦስተኛ ዙር የወረርሽኑ ማዕበል ወቅት፣ የሰው ሠራሽ መተንፈሻ ድጋፍ የሚፈልጉ እና ወደ ጽኑ ሕሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች መጨመሩ ከባድ ጫናን በሆስፒታሉ ላይ አስከትሎ ነበር። በተጨማሪ ደግሞ ለሌሎች ሕክምናዎች ከሚሰጡ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች መካከልም በበሽታው የሚያዙ ስለነበሩ ከባድ ሥራና ኃላፊነትን ከሚወጡት ባለሙያዎች ሲቀነሱ የሰው ኃይል እጥረት ገጥሟቸው የነበረበት ጊዜ እንደነበር ዶ/ር ያሬድ ይጠቅሳሉ። ከባለሙያዎቹ መካከል በተደጋጋሚ ጭምር በበሽታው የመያዝ ሁኔታ የገጠማቸው ቢኖሩም ለሞት የተዳረገ የሆስፒታሉ ባልደረባ አልነበረም። የመጀመሪያው የኮቪድ-19 ሕክምና ማዕከል የሆነው የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ከወረርሽኙ መከሰት ጀምሮ በሆስፒታል ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን፣ የመተንፈሻ ድጋፍ የሚያሻቸውን እንዲሁም የጽኑ ሕሙማን ሕክምና ድጋፍ የሚፈልጉ የኮቪድ-19 ሕሙማንን አስተናግዷል። በተጨማሪም በኮሮናቫይረስ ተይዘው ተጓዳኝ ሕመም ኖሮባቸው የሐኪም የቅርብ ክትትልና ድጋፍ የሚያስፍለጋቸው፣ ነፍሰ ጡሮችና የመውለጃ ጊዜያቸው የደረሱ ሕሙማንን ጭምር በመቀበል ከወረርሽኙ ጋር የተያያዙ ዘርፈ ብዙ የሕክምና አገልግሎቶችን ሲሰጥ ቆይቷል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ሆስፒታሉ በሰጠው አገልግሎት ከወረርሽኙ የዳኑ ሰዎች በተለያየ የዕድሜ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። እዚያው የተወለዱ የአንድ ቀን ዕድሜ ካላቸው አራስ ሕጻናት አንስቶ አስከ 114 ዓመት ዕድሜ ያላቸው አዛውንት ድረስ የኮቪድ ሕሙማንን ሆስፒታሉ አስተናግዷል። ከአንድ ወር በታች ዕድሜ ያላቸው በበሽታው ተይዘው ለሕክምና የገቡት ሁሉም ጨቅላ ሕጻናት አገግመው እንደወጡ ዶ/ር ያሬድ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በሁለት ዓመታት ውስጥ በርካታ መልካምና አሳዛኝ አጋጣሚዎች በሆስፒታሉ ውስጥ ማጋጠሙን በመጥቀስ፣ እነዚህን የሆስፒታሉን ክስተቶች እና ሌሎች የሚነገሩ ታሪኮችን በመጽሐፍ የማቅረብ ሐሳብ እንዳላቸው ዶ/ር ያሬድ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ መገኘቱን ተከትሎ በአገሪቱ ውስጥ በተደረጉ ምርመራዎች ከ470 ሺህ በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ከ7500 በላይ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሰበብ ለሞት መዳረጋቸውን ከጤና ሚኒስቴር የወጣው ወቅታዊ መረጃ ያመለክታል።
https://www.bbc.com/amharic/news-61346541
2health
ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች ሥራውን ማቋረጡን አስታወቀ
የፈረንሳዩ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ኤምኤስኤፍ ሠራተኞቹ ትግራይ ውስጥ ከተገደሉ በኋላ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የሚያከናውነውን ሥራ ማቋረጡን ገለጸ። ሰኔ 17/2013 ዓ.ም ትግራይ ክልል ውስጥ ለሥራ እየተጓዙ ሳለ ማንነታቸው ባልታወቁ ጥቃት ፈጻሚዎች የተገደሉት የእርዳታ ድርጅቱ ሠራተኞች ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንዷ ደግሞ የስፔን ዜግነት ያላት ናት። ድርጅቱ እንዳለው በሠራተኞቹ ላይ በተፈጸመው ጭካኔ የተሞላበት ግድያ ዙሪያ አስቸኳይ ምርመራ እንዲደረግና በክልሉ ውስጥ የእርዳታ ሠራተኞች ደኅንነታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ እንዲፈቀድ ጠይቋል። በሠራተኞቹ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በመቃወም ኤምኤስኤፍ በትግራይ ክልል ማዕከላዊና ምሥራቃዊ ክፍል በሚገኙት አቢ አዲ፣ አዲግራትና አክሱም ውስጥ የሚያከናውነውን ሥራ ማቋረጡን አስታውቋል። ነገር ግን ከእነዚህ አካባቢዎች ውጪ ባሉ ሌሎች አካባቢዎች አባላቱ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ነዋሪዎች ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ሥራቸውን ማከናወን እንደሚቀጥሉ ገልጿል። "በባልደረቦቻችን ላይ ግድያው ከተፈጸመ ሁለት ሳምንት ሊሆነው ቢቃረብም ማንም ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን የሌለ ሲሆን በተጨማሪም በግድያው ዙሪያ ስላለው ሁኔታ ምንም ግልጽ ያለ ነገር የለም" ሲሉ የድርጅቱ ኃላፊ ቴሬሳ ሳንክሪስቶቫል ተናግረዋል። ጨምረውም በባልደረቦቻቸው ላይ በተፈጸመው ግድያ ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ ምርመራ አድርገው ምን እንደተከሰተና ተጠያቂው ማን እንደሆነ ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። በዚህም ሳቢያ "በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ በጣም ከባድ ነገር ግን አስፈላጊ የሆነውን በበርካታ የትግራይ አካባቢዎች የምናካሂዳቸውን ሥራዎቻችንን ለማቋረጥ ወስነናል" ብለዋል። የእርዳታ ሠራተኞቹ ሰኔ ወር አጋማሽ ላይ በትግራይ ክልል ውስጥ በጉዞ ላይ እንዳሉ የነበራቸው ግንኙነት መቋረጡንና በተከታዩ ቀን የሁለቱ ኢትዮጵያውያንና የስፔናዊቷ አስከሬን ይጓዙበት ከነበረው መኪና ጥቂት ሜትሮች ራቅ ብሎ መገኘቱንም የድንበር የለሽ ሐኪሞች በወቅቱ ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቶ ነበር። በጥቃቱ የተገደሉት የህክምና እርዳታ ድርጅቱ ባልደረቦች በየካቲት ወር ላይ በድርጅቱ በረዳት አስተባባሪነት ሥራ የጀመረው የ31 ዓመቱ ዮሐንስ ሃለፎም፣ በግንቦት ወር ለግብረ ሰናይ ድርጅቱን መሥራት የጀመረው የ31 ዓመቱ ሹፌር ቴድሮስ ገብረ ማሪያም እና ለዓመታት በድንገተኛ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪነት የሠራችው የ34 ዓመቷ ስፔናዊት ማሪያ ኽርናንዴዝ ናቸው። አስካሁን ድረስ ለሦስቱ የድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን ሠራተኞች ግድያ ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን የሌለ ሲሆን ስለግድያው የወጣ ምንም አይነት ተጨመሪ መረጃ የለም። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግድያውን ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ የተሰማውን ሐዘን ገልጾ፤ ጥቃቱ የተፈጸመው አቢ አዲ ተብሎ በሚጠራ "ህወሓት በሚንቀሳቀስበት አካባቢ" መሆኑን አመልክቷል። ጨምሮም እንዲህ አይነቱን "ኃላፊነት በማይሰማው ቡድን የሚፈጸምን ጥቃት ለማስቀረት የእርዳታ ድርጅቶች በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ወታደራዊ እጀባ እንዲደረግላቸው መንግሥት ያቀረበው ጥሪ ትክክል መሆኑን ያመለክታል" ብሏል። ከመንግሥት ሠራዊት ጋር ለስምንት ወራት በጦርነት ውስጥ የቆየው የህወሓት ኃይልም በበኩሉ በእርዳታ ሠራተኞቹ ላይ የተፈጸመውን ግድያ አውግዞ ድርጊቱ በመንግሥት ወታደሮች የተፈጸመ ነው ሲል ገልጾ ነበር። ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) በትግራይ ክልል ውስጥ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት በመደገፍና በማቋቋም እንዲሁም የህክምና ድጋፍ ለሚሹ ሰዎች እርዳታን እያደረገ ያለ ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው። ድርጅቱ በባልደረቦቹ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በመቃወም አገልግሎቱን አሁን ለማቋረጥ በወሰነባቸው አካባቢዎች ውስጥ ለሚገኙ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች የተለያየ አይነት የጤና አገልግሎቶች ሲያርብ መቆየቱን ገልጿል። የአገልግሎቱ መቋረጥም በርካታ ሰዎች ከረድኤት ድርጅቱ ሲያገኙት የነበረውን የሰብአዊና የጤና ድጋፎችን እንዲያጡ ያደርጋቸዋል ተብሏል።
ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች ሥራውን ማቋረጡን አስታወቀ የፈረንሳዩ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ኤምኤስኤፍ ሠራተኞቹ ትግራይ ውስጥ ከተገደሉ በኋላ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የሚያከናውነውን ሥራ ማቋረጡን ገለጸ። ሰኔ 17/2013 ዓ.ም ትግራይ ክልል ውስጥ ለሥራ እየተጓዙ ሳለ ማንነታቸው ባልታወቁ ጥቃት ፈጻሚዎች የተገደሉት የእርዳታ ድርጅቱ ሠራተኞች ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንዷ ደግሞ የስፔን ዜግነት ያላት ናት። ድርጅቱ እንዳለው በሠራተኞቹ ላይ በተፈጸመው ጭካኔ የተሞላበት ግድያ ዙሪያ አስቸኳይ ምርመራ እንዲደረግና በክልሉ ውስጥ የእርዳታ ሠራተኞች ደኅንነታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ እንዲፈቀድ ጠይቋል። በሠራተኞቹ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በመቃወም ኤምኤስኤፍ በትግራይ ክልል ማዕከላዊና ምሥራቃዊ ክፍል በሚገኙት አቢ አዲ፣ አዲግራትና አክሱም ውስጥ የሚያከናውነውን ሥራ ማቋረጡን አስታውቋል። ነገር ግን ከእነዚህ አካባቢዎች ውጪ ባሉ ሌሎች አካባቢዎች አባላቱ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ነዋሪዎች ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ሥራቸውን ማከናወን እንደሚቀጥሉ ገልጿል። "በባልደረቦቻችን ላይ ግድያው ከተፈጸመ ሁለት ሳምንት ሊሆነው ቢቃረብም ማንም ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን የሌለ ሲሆን በተጨማሪም በግድያው ዙሪያ ስላለው ሁኔታ ምንም ግልጽ ያለ ነገር የለም" ሲሉ የድርጅቱ ኃላፊ ቴሬሳ ሳንክሪስቶቫል ተናግረዋል። ጨምረውም በባልደረቦቻቸው ላይ በተፈጸመው ግድያ ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ ምርመራ አድርገው ምን እንደተከሰተና ተጠያቂው ማን እንደሆነ ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። በዚህም ሳቢያ "በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ በጣም ከባድ ነገር ግን አስፈላጊ የሆነውን በበርካታ የትግራይ አካባቢዎች የምናካሂዳቸውን ሥራዎቻችንን ለማቋረጥ ወስነናል" ብለዋል። የእርዳታ ሠራተኞቹ ሰኔ ወር አጋማሽ ላይ በትግራይ ክልል ውስጥ በጉዞ ላይ እንዳሉ የነበራቸው ግንኙነት መቋረጡንና በተከታዩ ቀን የሁለቱ ኢትዮጵያውያንና የስፔናዊቷ አስከሬን ይጓዙበት ከነበረው መኪና ጥቂት ሜትሮች ራቅ ብሎ መገኘቱንም የድንበር የለሽ ሐኪሞች በወቅቱ ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቶ ነበር። በጥቃቱ የተገደሉት የህክምና እርዳታ ድርጅቱ ባልደረቦች በየካቲት ወር ላይ በድርጅቱ በረዳት አስተባባሪነት ሥራ የጀመረው የ31 ዓመቱ ዮሐንስ ሃለፎም፣ በግንቦት ወር ለግብረ ሰናይ ድርጅቱን መሥራት የጀመረው የ31 ዓመቱ ሹፌር ቴድሮስ ገብረ ማሪያም እና ለዓመታት በድንገተኛ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪነት የሠራችው የ34 ዓመቷ ስፔናዊት ማሪያ ኽርናንዴዝ ናቸው። አስካሁን ድረስ ለሦስቱ የድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን ሠራተኞች ግድያ ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን የሌለ ሲሆን ስለግድያው የወጣ ምንም አይነት ተጨመሪ መረጃ የለም። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግድያውን ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ የተሰማውን ሐዘን ገልጾ፤ ጥቃቱ የተፈጸመው አቢ አዲ ተብሎ በሚጠራ "ህወሓት በሚንቀሳቀስበት አካባቢ" መሆኑን አመልክቷል። ጨምሮም እንዲህ አይነቱን "ኃላፊነት በማይሰማው ቡድን የሚፈጸምን ጥቃት ለማስቀረት የእርዳታ ድርጅቶች በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ወታደራዊ እጀባ እንዲደረግላቸው መንግሥት ያቀረበው ጥሪ ትክክል መሆኑን ያመለክታል" ብሏል። ከመንግሥት ሠራዊት ጋር ለስምንት ወራት በጦርነት ውስጥ የቆየው የህወሓት ኃይልም በበኩሉ በእርዳታ ሠራተኞቹ ላይ የተፈጸመውን ግድያ አውግዞ ድርጊቱ በመንግሥት ወታደሮች የተፈጸመ ነው ሲል ገልጾ ነበር። ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) በትግራይ ክልል ውስጥ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት በመደገፍና በማቋቋም እንዲሁም የህክምና ድጋፍ ለሚሹ ሰዎች እርዳታን እያደረገ ያለ ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው። ድርጅቱ በባልደረቦቹ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በመቃወም አገልግሎቱን አሁን ለማቋረጥ በወሰነባቸው አካባቢዎች ውስጥ ለሚገኙ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች የተለያየ አይነት የጤና አገልግሎቶች ሲያርብ መቆየቱን ገልጿል። የአገልግሎቱ መቋረጥም በርካታ ሰዎች ከረድኤት ድርጅቱ ሲያገኙት የነበረውን የሰብአዊና የጤና ድጋፎችን እንዲያጡ ያደርጋቸዋል ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57714392
2health
ኤርትራውያን በካንሰር ለሚሰቃይ ግለሰብ በ24 ሰዓታት ውስጥ ግማሽ ሚሊዮን ዶላር አሰባሰቡ
በውጭ አገራት የሚኖሩ ኤርትራውያን እና ትውልደ ኤርትራውያን ዲያስፖራዎች በሕመም ለሚሳቃይ አንድ ኤርትራዊ ግለሰብ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን የካናዳ ዶላር በላይ አሰባሰቡ። በኤርትራ ነዋሪ የሆነው እና የስድስት ልጆች አባት የሆነው ዮናስ ፀጋይ፤ ባለፈው አንድ ዓመት ሆድኪን ሊምፎማ በተባለ የደም ካንሰር አይነት ሲሰቃይ ቆይቷል። 'ዮናስ ፀጋይን እና ቤተሰቡን ይርዱ' በሚል በተከፈተው የጎፈንድሚ አካውንት በ24 ሰዓታት ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የካናዳ ዶላር ማሰባሰብ ተችሏል። ለዮናስ የተሰባሰበው መዋጮ ማክሰኞ ጥር 09 ከሰዓት ላይ 637 ሺህ የካናዳ ዶላር (ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ) ደርሷል። በጎፈንድሚ ገጽ ላይ ተያይዞ በወጣው የእርዳታ ተማጽኖ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ፤ ዮናስ ፀጋይ በደም ካንሰር ምክንያት ከፍተኛ ሕመም ውስጥ እንደሚገኝ እና ሰዎች ለሕክምና ወጪ መዋጮ እንዲያደርጉለት ሲማጸን ይታያል። በስድስት ልጆቹ ተከቦ የሚታየው ዮናስ፤ በሕመሙ ምክንያት ሰውነቱ አብጦ እና እጆቹን በኃይል ሲያሽ ይታያል። ለዮናስ የቀረበው የእርዳታ አድርጉ ጥሪ በርካታ ምላሾችን በማግኘት በጎፈንዲሚ ገጽ ላይ ቀዳሚ ደረጃን ይዟል። ዮናስ በኤርትራ ወደ ጤና ተቋማት ቢሄድም ለተጨማሪ ሕክምና ከአገር ውጭ መጓዝ እንዳለበት ተነግሮታል። በድህነት ውስጥ የሚኖረው ዮናስ የሕክምና ወጪውን መሸፈን አለመቻሉን በመግለጽ አንድ የዩቲዩብ ገጽ የስድስት ልጆቹ አባት የሆነው ግለሰብ ያለበት ሁኔታ ለሌሎች አጋርቷል። ዮናስን ለማገዝ የጎፈንድሚ ገጽ በተከፈተ በመጀመሪያዎቹ 12 ሰዓታት ውስጥ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኤርትራውያን ከ350 ሺህ የካናዳ ዶላር በላይ በማዋጣት ፈጣን ምላሽ ሰጥተዋል። የእርዳታ ገንዘብ አሰባሳቢዎች መካከል አንዱ የሆነው ዮሴፍ ወርቄ እንዲህ በፍጥነት በርካቶችን ያሳተፈ መዋጮ አጋጥሞት እንደማያውቅ ለቢቢሲ ትግርኛ ክፍል ተናግሯል። አስተባባሪው እንደሚለው በሕመም የሚሰቃየው የዮናስ ተማጽእኖ የበርካታ ሰዎችን ልብ ተነክቷል። እንድ የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ የጤና አግልግሎት (ኤንኤችኤስ) ድረ-ገጽ ከሆነ ዮናስ የሚሰቃይበት ሆድኪን ሊምፎማ ብዙ ጊዜ የሚያጋጥም ከነጭ የደም ሴል ጋር የተገናኘ የደም ካንስር አይነት ነው። ተቋሙ እንደሚለው ከሆነ ይህ የካንሰር ሕመም በጨረር ሕክምና (በኬሞቴራፒ) እንዲሁም በራዲዮቴራፒ ሕክምና ሊድን ይችላል።
ኤርትራውያን በካንሰር ለሚሰቃይ ግለሰብ በ24 ሰዓታት ውስጥ ግማሽ ሚሊዮን ዶላር አሰባሰቡ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኤርትራውያን እና ትውልደ ኤርትራውያን ዲያስፖራዎች በሕመም ለሚሳቃይ አንድ ኤርትራዊ ግለሰብ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን የካናዳ ዶላር በላይ አሰባሰቡ። በኤርትራ ነዋሪ የሆነው እና የስድስት ልጆች አባት የሆነው ዮናስ ፀጋይ፤ ባለፈው አንድ ዓመት ሆድኪን ሊምፎማ በተባለ የደም ካንሰር አይነት ሲሰቃይ ቆይቷል። 'ዮናስ ፀጋይን እና ቤተሰቡን ይርዱ' በሚል በተከፈተው የጎፈንድሚ አካውንት በ24 ሰዓታት ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የካናዳ ዶላር ማሰባሰብ ተችሏል። ለዮናስ የተሰባሰበው መዋጮ ማክሰኞ ጥር 09 ከሰዓት ላይ 637 ሺህ የካናዳ ዶላር (ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ) ደርሷል። በጎፈንድሚ ገጽ ላይ ተያይዞ በወጣው የእርዳታ ተማጽኖ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ፤ ዮናስ ፀጋይ በደም ካንሰር ምክንያት ከፍተኛ ሕመም ውስጥ እንደሚገኝ እና ሰዎች ለሕክምና ወጪ መዋጮ እንዲያደርጉለት ሲማጸን ይታያል። በስድስት ልጆቹ ተከቦ የሚታየው ዮናስ፤ በሕመሙ ምክንያት ሰውነቱ አብጦ እና እጆቹን በኃይል ሲያሽ ይታያል። ለዮናስ የቀረበው የእርዳታ አድርጉ ጥሪ በርካታ ምላሾችን በማግኘት በጎፈንዲሚ ገጽ ላይ ቀዳሚ ደረጃን ይዟል። ዮናስ በኤርትራ ወደ ጤና ተቋማት ቢሄድም ለተጨማሪ ሕክምና ከአገር ውጭ መጓዝ እንዳለበት ተነግሮታል። በድህነት ውስጥ የሚኖረው ዮናስ የሕክምና ወጪውን መሸፈን አለመቻሉን በመግለጽ አንድ የዩቲዩብ ገጽ የስድስት ልጆቹ አባት የሆነው ግለሰብ ያለበት ሁኔታ ለሌሎች አጋርቷል። ዮናስን ለማገዝ የጎፈንድሚ ገጽ በተከፈተ በመጀመሪያዎቹ 12 ሰዓታት ውስጥ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኤርትራውያን ከ350 ሺህ የካናዳ ዶላር በላይ በማዋጣት ፈጣን ምላሽ ሰጥተዋል። የእርዳታ ገንዘብ አሰባሳቢዎች መካከል አንዱ የሆነው ዮሴፍ ወርቄ እንዲህ በፍጥነት በርካቶችን ያሳተፈ መዋጮ አጋጥሞት እንደማያውቅ ለቢቢሲ ትግርኛ ክፍል ተናግሯል። አስተባባሪው እንደሚለው በሕመም የሚሰቃየው የዮናስ ተማጽእኖ የበርካታ ሰዎችን ልብ ተነክቷል። እንድ የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ የጤና አግልግሎት (ኤንኤችኤስ) ድረ-ገጽ ከሆነ ዮናስ የሚሰቃይበት ሆድኪን ሊምፎማ ብዙ ጊዜ የሚያጋጥም ከነጭ የደም ሴል ጋር የተገናኘ የደም ካንስር አይነት ነው። ተቋሙ እንደሚለው ከሆነ ይህ የካንሰር ሕመም በጨረር ሕክምና (በኬሞቴራፒ) እንዲሁም በራዲዮቴራፒ ሕክምና ሊድን ይችላል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60041868
3politics
ፑቲን በአገራቸው ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ከጦርነት አዋጅ ጋር አመሳሰሉ
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ወረራ ምክንያት በምዕራባውያን ሀገራት የተጣሉትን ማዕቀቦች "ጦርነት ከማወጅ ጋር ተመሳሳይ ነው" ሲሉ ገልጸዋል ። "ነገር ግን አምላክ ይመስገን ወደዛ አልደረሰም" ሲሉም አክለዋል። ዩክሬን ከበረራ ቀጠና ውጭ መደረግ አለባት በሚል የዩክሬን ባለስልጣናት ከፍተኛ ግፊት እያደረጉ ሲሆን ይህንንም አስመልክቶ ፕሬዚዳንት ፑቲን የበረራ ክልከላ ሙከራ በጦርነቱ ውስጥ ቀጥታ ተሳትፎ እንደሚታይ አስጠንቅቀዋል። ከጦርነቱም ጋር ተያይዞ በሩሲያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊያውጁ ይችላሉ የሚለውን ሃሳብ ውድቅ አድርገውታል። ፕሬዚዳንት ፑቲን ይህንን ያሉት በሞስኮ አቅራቢያ በሚገኘው የኤሮፍሎት ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ ሴት የበረራ አስተናጋጆች ቡድን ባነጋገሩበት ወቅት ነው። አስራ አንደኛ ቀኑን ባስቆጠረው የሩስያ ወረራን ተከትሎ ምዕራባውያን ሃገራት በሩስያ የሚያደርጉትን ማዕቀብ አጠናክረው ቀጥለዋል። እስካሁን ከተጣሉ ማዕቀቦች መካከል የፕሬዚዳንት ፑቲን የውጭ ሃብት ማገድን ጨምሮ የሩስያ ባንኮችን ስዊፍት ከተሰኘው ዓለም አቀፍ የክፍያ ስርዓት ማስወጣት ይገኙበታል። በተጨማሪም በርካታ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በሩሲያ ውስጥ ያለውን ሥራቸውን አቁመዋል ። በያዝነው ሳምነት ቅዳሜ ፣ ዛራ ፣ ፔይፓል እና ሳምሰንግ የተሰኙት ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በሩሲያ ያለውን ንግዳቸውን በቅርብ ጊዜ ያቆሙ ድርጅቶች ሆነዋል። በአገሪቱ ላይ የተጣለው ማዕቀብ የአገሪቱን መገበያያ ገንዘብ ሩብል በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሽቆለቆል ያደረገው ሲሆን የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የወለድ ተመኖችን በእጥፍ እንዲጨምር አስገድዶታል። ፕሬዚዳንት ፑቲን በቅርቡ በሰጡት አስተያየት፣ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስረዳት ሞክረዋል። የሩሲያ ቋንቋ ተናጋሪ ማህበረሰቦችን በሀገሪቱ እየተደረገ ካለው "ከፍተኛ ወታደራዊነትና ናዚነት" ጥፋት ለመከላከል እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። የምዕራባውያን የመከላከያ ተንታኞች የሩሲያ ወታደራዊ ዘመቻ እንደተጠበቀው እየሄደ አይደለም ለሚሉት አስተያየትም ፕሬዚዳንቱ ምላሽ ሰጥተዋል "ሠራዊታችን ሁሉንም ተግባራት ይፈጽማል። ምንም ጥርጥር የለኝም። ሁሉም ነገር በእቅድ እየሄደ ነው" ብለዋል። በጦርነቱ ላይ የሚሳተፉት በሙያቸው ወታደሮች የሆኑ ብቻ መሆናቸውን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ ምንም አይነት ተቃራኒ ዘገባዎች ቢኖሩም ዜጎች በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ ውትድርና አለመግባታቸውን ገልጸዋል። የሩሲያው መሪ በዩክሬን ሰማይ ላይ በረራ ለመከልከል የሚደረገው ጥረት ወታደራዊ ግጭቱን አንድ እርምጃ ወደፊት እንደሚወስደውና ተሳታፊዎቹም እንደ ጠላት ተዋጊ እንደሚወሰዱ ተናግረዋል። "አሁን ያለው አመራር በአሁኑ ተግባራቸው ከቀጠሉ የዩክሬንን የወደፊት እድል አደጋ ላይ እንደሚጥሉ ሊገነዘቡ ይገባል" ሲሉም አክለዋል።
ፑቲን በአገራቸው ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ከጦርነት አዋጅ ጋር አመሳሰሉ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ወረራ ምክንያት በምዕራባውያን ሀገራት የተጣሉትን ማዕቀቦች "ጦርነት ከማወጅ ጋር ተመሳሳይ ነው" ሲሉ ገልጸዋል ። "ነገር ግን አምላክ ይመስገን ወደዛ አልደረሰም" ሲሉም አክለዋል። ዩክሬን ከበረራ ቀጠና ውጭ መደረግ አለባት በሚል የዩክሬን ባለስልጣናት ከፍተኛ ግፊት እያደረጉ ሲሆን ይህንንም አስመልክቶ ፕሬዚዳንት ፑቲን የበረራ ክልከላ ሙከራ በጦርነቱ ውስጥ ቀጥታ ተሳትፎ እንደሚታይ አስጠንቅቀዋል። ከጦርነቱም ጋር ተያይዞ በሩሲያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊያውጁ ይችላሉ የሚለውን ሃሳብ ውድቅ አድርገውታል። ፕሬዚዳንት ፑቲን ይህንን ያሉት በሞስኮ አቅራቢያ በሚገኘው የኤሮፍሎት ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ ሴት የበረራ አስተናጋጆች ቡድን ባነጋገሩበት ወቅት ነው። አስራ አንደኛ ቀኑን ባስቆጠረው የሩስያ ወረራን ተከትሎ ምዕራባውያን ሃገራት በሩስያ የሚያደርጉትን ማዕቀብ አጠናክረው ቀጥለዋል። እስካሁን ከተጣሉ ማዕቀቦች መካከል የፕሬዚዳንት ፑቲን የውጭ ሃብት ማገድን ጨምሮ የሩስያ ባንኮችን ስዊፍት ከተሰኘው ዓለም አቀፍ የክፍያ ስርዓት ማስወጣት ይገኙበታል። በተጨማሪም በርካታ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በሩሲያ ውስጥ ያለውን ሥራቸውን አቁመዋል ። በያዝነው ሳምነት ቅዳሜ ፣ ዛራ ፣ ፔይፓል እና ሳምሰንግ የተሰኙት ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በሩሲያ ያለውን ንግዳቸውን በቅርብ ጊዜ ያቆሙ ድርጅቶች ሆነዋል። በአገሪቱ ላይ የተጣለው ማዕቀብ የአገሪቱን መገበያያ ገንዘብ ሩብል በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሽቆለቆል ያደረገው ሲሆን የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የወለድ ተመኖችን በእጥፍ እንዲጨምር አስገድዶታል። ፕሬዚዳንት ፑቲን በቅርቡ በሰጡት አስተያየት፣ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስረዳት ሞክረዋል። የሩሲያ ቋንቋ ተናጋሪ ማህበረሰቦችን በሀገሪቱ እየተደረገ ካለው "ከፍተኛ ወታደራዊነትና ናዚነት" ጥፋት ለመከላከል እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። የምዕራባውያን የመከላከያ ተንታኞች የሩሲያ ወታደራዊ ዘመቻ እንደተጠበቀው እየሄደ አይደለም ለሚሉት አስተያየትም ፕሬዚዳንቱ ምላሽ ሰጥተዋል "ሠራዊታችን ሁሉንም ተግባራት ይፈጽማል። ምንም ጥርጥር የለኝም። ሁሉም ነገር በእቅድ እየሄደ ነው" ብለዋል። በጦርነቱ ላይ የሚሳተፉት በሙያቸው ወታደሮች የሆኑ ብቻ መሆናቸውን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ ምንም አይነት ተቃራኒ ዘገባዎች ቢኖሩም ዜጎች በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ ውትድርና አለመግባታቸውን ገልጸዋል። የሩሲያው መሪ በዩክሬን ሰማይ ላይ በረራ ለመከልከል የሚደረገው ጥረት ወታደራዊ ግጭቱን አንድ እርምጃ ወደፊት እንደሚወስደውና ተሳታፊዎቹም እንደ ጠላት ተዋጊ እንደሚወሰዱ ተናግረዋል። "አሁን ያለው አመራር በአሁኑ ተግባራቸው ከቀጠሉ የዩክሬንን የወደፊት እድል አደጋ ላይ እንደሚጥሉ ሊገነዘቡ ይገባል" ሲሉም አክለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60636847
2health
በዩኬ ኮቪድ-19 በህሙማን ላይ የቆየበት ረጅሙ ጊዜ ከ16 ወር በላይ መሆኑን ምርመራዎች አመለከቱ
የዩናይትድ ኪንግደም ሐኪሞች ኮቪድ-19 በህሙማን ላይ የቆየበትን ረጅም ጊዜ መዝገበዋል። ሐኪሞቹ በኮቪድ-19 ተይዘው ሕክምና ያደረጉላቸው ህመምተኛ ከቫይረሱ ነጻ ሳይሆኑ በአጠቃላይ ለ16 ወራት ወይም ለ505 ቀናት እንደቆዩ ምርመራዎች እንዳመለከቱ ገልጸዋል። ስማቸው ያልተጠቀሰው እኝህ ግለሰብ ሌላ ተጓዳኝ በሽታዎች የነበሩባቸው ሲሆን እአአ በ2021 ሆስፒታል ውስጥ ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ይህችን ዓለም ተሰናብተዋል። እኝህ ግለሰብ ለ16 ወራት ያህል በተመረመሩ ቁጥር ቫይረሱ ይገኝባቸው ነበር። የለንደን የሕክምና ባለሙያዎች ለረጅም ጊዜ በቫይረሱ ተይዞ መቆየት እምብዛም የተለመደ አይደለም ይላሉ። አብዛኛው ሰው በተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅም ከቫይረሱ ነጻ ይሆናሉ። ነገር ግን ቀደም ሲል የተጠቀሱት ግለሰብ የነበራቸው በተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅም እጅግ የተዳከመ ነበር። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደዚህ ያሉ ስር የሰደዱ የሰውነት መቆጣቶችን ስለኮቪድ ያለን ግንዛቤ እና ሊያመጣ የሚችለውን አደጋ ለማሻሻል ጥናት እንደሚያስፈልግ ይጠቁማሉ ብለዋል። ህመምተኛው ለመጀመሪያ ጊዜ በኮቪድ-19 የተያዙት በ2020 መጀመሪያ ላይ ነበር። የበሽታው ምልክትም የነበራቸው ሲሆን በፒሲአር ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከ72 ሳምንታት ለሚበልጥ በርካታ ጊዜ ለመደበኛ ምርመራ እና ለእንክብካቤ ሆስፒታል ሲገቡ እና ሲወጡ ነበር። በአጠቃላይ ለ50 ጊዜ ያህል ምርመራ አድርገው ከቫይረሱ ነጻ አለመሆናቸው በምርመራ ተረጋግጧል። የኪንግስ ኮሌጅ ለንደን እና ጋይስ ኤንድ ሴንት ቶማስ ኤንኤችኤስ ፋውንዴሽን ትረስት ሐኪሞች እንዳሉት ግለሰቡ በተደጋጋሚ በቫይረሱ የተያዙ ሳይሆን አንድ ጊዜ ተይዘው ለረዥም ጊዜ ከቫይረሱ ሳያገግሙ መቆየታቸውን ዝርዝር የሆነ ላብራቶሪ ምርምራ ትንታኔ አሳይቷል። ህመምተኛው የፀረ ቫይረስ መድሃኒቶች ከወሰዱ በኋላ እንኳን ከበሽታው ማገገም አልቻሉም ነበር። ይህ አንድ ግለሰብ ከቫይረሱ ነጻ መሆኑ ተረጋግጦ ምልክቶቹ ከማይጠፉበትና በቫይረሱ ለረዥም ጊዜ ተይዞ መቆየት ጋር የተለየ ነው። በሕክምና ጉባዔ ላይ ስለግኝቶቹ ከሚያቀርቡት ሐኪሞቹ አንዱ በአውሮፓ ኮንግረንስ ክሊኒካል ማይክሮባዮሎጂ እና ተላላፊ በሽታዎች ሐኪም የሆኑት ዶክተር ሉኬ ብላግዶን ስኔል ናቸው። ዶክተር ሉኬ "ከጉሮሮ የሚወሰድ ናሙና ምርመራ ይደረግ ነበር። ግለሰቡ ሁል ጊዜ በተመረመሩ ቁጥር ከቫይረሱ ነጻ አለመሆናቸውን ያሳይ ነበር። ህመምተኛው ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን የሚያሳይ የምርመራ ውጤት ኖሯቸው አያውቅም። እናም ይህ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ በሽታ እንደሆነ መናገር እንችላለን። ምክንያቱም የቫይረሱ ዘረ መል ላይ ያደረግነው ተከታታይ ምርመራ ቫይረሱ በህመምተኛው ላይ የተለየ እና ወጥ የሆነ እንደሆነ አመላክቷል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዶክተር ሉኬ "ሰዎች ለረጅም ጊዜ በቫይረሱ ተይዘው ሲቆዩ ቫይረሱ ከሰውነታቸው ጋር ይላመዳል። ይህም አዳዲስ ዝርያዎችን ለመከላከል አቅም እንዲያዳብሩ ሊያግዝ ይችላል" ብለዋል። ምርመራ ካደረጉላቸው ዘጠኝ ታካሚዎች መካከልም አንዳቸውም በሌላ የቫይረስ ዝርያ አለመያዛቸውን ዶክተር ሉኬ ተናግረዋል። ስር በሰደደ ኢንፌክሽን የተያዘ ሰው ቫይረሱን ለሌሎች ላያስተላልፍ እንደሚችልም ዶክተር ሉኬ አክለዋል።
በዩኬ ኮቪድ-19 በህሙማን ላይ የቆየበት ረጅሙ ጊዜ ከ16 ወር በላይ መሆኑን ምርመራዎች አመለከቱ የዩናይትድ ኪንግደም ሐኪሞች ኮቪድ-19 በህሙማን ላይ የቆየበትን ረጅም ጊዜ መዝገበዋል። ሐኪሞቹ በኮቪድ-19 ተይዘው ሕክምና ያደረጉላቸው ህመምተኛ ከቫይረሱ ነጻ ሳይሆኑ በአጠቃላይ ለ16 ወራት ወይም ለ505 ቀናት እንደቆዩ ምርመራዎች እንዳመለከቱ ገልጸዋል። ስማቸው ያልተጠቀሰው እኝህ ግለሰብ ሌላ ተጓዳኝ በሽታዎች የነበሩባቸው ሲሆን እአአ በ2021 ሆስፒታል ውስጥ ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ይህችን ዓለም ተሰናብተዋል። እኝህ ግለሰብ ለ16 ወራት ያህል በተመረመሩ ቁጥር ቫይረሱ ይገኝባቸው ነበር። የለንደን የሕክምና ባለሙያዎች ለረጅም ጊዜ በቫይረሱ ተይዞ መቆየት እምብዛም የተለመደ አይደለም ይላሉ። አብዛኛው ሰው በተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅም ከቫይረሱ ነጻ ይሆናሉ። ነገር ግን ቀደም ሲል የተጠቀሱት ግለሰብ የነበራቸው በተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅም እጅግ የተዳከመ ነበር። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደዚህ ያሉ ስር የሰደዱ የሰውነት መቆጣቶችን ስለኮቪድ ያለን ግንዛቤ እና ሊያመጣ የሚችለውን አደጋ ለማሻሻል ጥናት እንደሚያስፈልግ ይጠቁማሉ ብለዋል። ህመምተኛው ለመጀመሪያ ጊዜ በኮቪድ-19 የተያዙት በ2020 መጀመሪያ ላይ ነበር። የበሽታው ምልክትም የነበራቸው ሲሆን በፒሲአር ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከ72 ሳምንታት ለሚበልጥ በርካታ ጊዜ ለመደበኛ ምርመራ እና ለእንክብካቤ ሆስፒታል ሲገቡ እና ሲወጡ ነበር። በአጠቃላይ ለ50 ጊዜ ያህል ምርመራ አድርገው ከቫይረሱ ነጻ አለመሆናቸው በምርመራ ተረጋግጧል። የኪንግስ ኮሌጅ ለንደን እና ጋይስ ኤንድ ሴንት ቶማስ ኤንኤችኤስ ፋውንዴሽን ትረስት ሐኪሞች እንዳሉት ግለሰቡ በተደጋጋሚ በቫይረሱ የተያዙ ሳይሆን አንድ ጊዜ ተይዘው ለረዥም ጊዜ ከቫይረሱ ሳያገግሙ መቆየታቸውን ዝርዝር የሆነ ላብራቶሪ ምርምራ ትንታኔ አሳይቷል። ህመምተኛው የፀረ ቫይረስ መድሃኒቶች ከወሰዱ በኋላ እንኳን ከበሽታው ማገገም አልቻሉም ነበር። ይህ አንድ ግለሰብ ከቫይረሱ ነጻ መሆኑ ተረጋግጦ ምልክቶቹ ከማይጠፉበትና በቫይረሱ ለረዥም ጊዜ ተይዞ መቆየት ጋር የተለየ ነው። በሕክምና ጉባዔ ላይ ስለግኝቶቹ ከሚያቀርቡት ሐኪሞቹ አንዱ በአውሮፓ ኮንግረንስ ክሊኒካል ማይክሮባዮሎጂ እና ተላላፊ በሽታዎች ሐኪም የሆኑት ዶክተር ሉኬ ብላግዶን ስኔል ናቸው። ዶክተር ሉኬ "ከጉሮሮ የሚወሰድ ናሙና ምርመራ ይደረግ ነበር። ግለሰቡ ሁል ጊዜ በተመረመሩ ቁጥር ከቫይረሱ ነጻ አለመሆናቸውን ያሳይ ነበር። ህመምተኛው ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን የሚያሳይ የምርመራ ውጤት ኖሯቸው አያውቅም። እናም ይህ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ በሽታ እንደሆነ መናገር እንችላለን። ምክንያቱም የቫይረሱ ዘረ መል ላይ ያደረግነው ተከታታይ ምርመራ ቫይረሱ በህመምተኛው ላይ የተለየ እና ወጥ የሆነ እንደሆነ አመላክቷል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዶክተር ሉኬ "ሰዎች ለረጅም ጊዜ በቫይረሱ ተይዘው ሲቆዩ ቫይረሱ ከሰውነታቸው ጋር ይላመዳል። ይህም አዳዲስ ዝርያዎችን ለመከላከል አቅም እንዲያዳብሩ ሊያግዝ ይችላል" ብለዋል። ምርመራ ካደረጉላቸው ዘጠኝ ታካሚዎች መካከልም አንዳቸውም በሌላ የቫይረስ ዝርያ አለመያዛቸውን ዶክተር ሉኬ ተናግረዋል። ስር በሰደደ ኢንፌክሽን የተያዘ ሰው ቫይረሱን ለሌሎች ላያስተላልፍ እንደሚችልም ዶክተር ሉኬ አክለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/61132951
2health
ከ 1 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን 8 ሰዎችን ብቻ የሚያጠቃው አስገራሚ በሽታ
አንዳንድ በሽታዎች ግራ ናቸው። ለታማሚም ለአስታማሚም፤ ለአካሚም ለታካሚም። ሐኪሞች እንዲህ ግራ የሆኑትን ደዌዎች ኢዲዮፓቲክ (idiopathic) ሲሉ ይጠሯቸዋል። ግራ የሚባሉት ግራ ስለሚያጋቡ ነው። መንስኤያቸው ስለማይታወቅ። ይህ ዛሬ የምንነግራችሁ በሽታ ከዚህ ይመደባል። 60 ከመቶ በምን እንደሚመጣ አይታወቅም። ሲመጣ ግን እግር ተወርች ያስራል። አስሮ ቤት ያስቀምጣል። የአማርኛ ስም የለውም። በእንግሊዝኛ ‘ትራንስቨረስ ማያሊቲስ’ ይባላል። በቅጽል ስሙ (TM) ይሉታል። በደምሳሳው የሕብለ ሰረሰር (የነርቭ) በሽታ ነው። ቀደም ሲል እንዳልነው 60 ከመቶው በምን እንደሚመጣ አይታወቅም። በቃ አያድርስ ነው የሚባለው። 40 ከመቶ ግን ምንጩ ይታወቃል። ይህን ዘርዘር አድርገው የሚያስረዱን ዶ/ር ዳዊት ክብሩ ናቸው። ዶ/ር ዳዊት የነርቭ ሕክምና ከፍተኛ ስፔሻሊስት ናቸው። አሁን በሰሜን አሜሪካ፣ በዊስኮንስን እና በሚቺጋን ግዛቶች በተለያዩ ሆስፒታሎች ይሠራሉ። “በሽታው የሕብለ ሰረሰር አንዱን ክፍል በድንገት ያጠቃል” ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። ቀጥሎ ከተጠቃው ሕብለ ሰረሰር በታች ያለውን የነርቭ ሥርዓት ይስተጓጎላል። ይስተጓጎላል ሲባል ምን ማለት ነው? ለምሳሌ እጅና እግርን ማዘዝ ይቸግራል። ሽንት መቆጣጠርም ሊያስቸግር ይችላል። “ከእንቅልፌ ስነሳ ድንገት መራመድ አቃተኝ፤ እግሬ ሰነፈብኝ” የሚሉ ታማሚዎች ያጋጥማሉ። ማንኛውም ነገር ሲነካን ቆዳችን ንክኪን የሚረዳበትን መንገድም ይቀየራል። ይህ የሚሆነው ከአእምሮ የሚላክ መልዕክት እየተቀየረ ለነርቭ ጫፍ ስለሚደርስ ነው። ለምሳሌ አንሶላ ጣል ቢደረግብን አሸዋ የተደፋብን ያህል ሊሰማን ይችላል። የሸሚዝ ቁልፍ ሲነካን በመርፌ የተወጋን ያህል ሊሰማን ይችላል። “በሽታው ያልተለመደ የሚባል ነው’’ ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። ያልተለመደ ያስባለው ደግሞ ምልክቶቹ አይደሉም። ጥቂት ሰዎችን ብቻ ስለሚያጠቃ ነው። በዓለም ከአንድ ሚሊዮን ሰው ቢበዛ 8 ሰዎችን ቢይዝ ነው። ይህን አሃዝ ወደ እኛ አገር እንመንዝረው። ለስሌት እንዲመቸን የኢትዮጵያን ሕዝብን 100 ሚሊዮን ነው እንበል። በዓመት በዚህ በሽታ የሚያዙት 800 ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ እንደማለት ነው። ምንም ስላደረግን አይደለም የሚመጣው። ምንም ሳላላደረግንም አይደለም። በቃ አንዳንድ ጊዜ መከላከያችን በስህተት ራሱን ያጠቃል። ይህ ከባዕድ ተህዋሲዎች ጋር የሚያያዝ ሊሆን ይችላል። በሽታው በምን በምን ይመጣል? ስንል ዶ/ር ዳዊትን ጠየቅን። “ብዙውን ጊዜ ያለምንም ምክንያት በድንገት ይመጣል።” “ሌላ ጊዜ ደግሞ የአንጀት መቁሰል (ጋስትሮ ስትራይተስ) ሲያመን ሊመጣ ይችላል” ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። “አንዳንድ ሰዎች በአንጀት መቁሰል ከታመሙ ከ2 ሳምንት ወይም ከ3 ሳምንት በኋላ በዚህ በሽታ ይያዛሉ።” እንደ ጉንፋን ዓይነት ወይም ኮቪድ ወይም ኤችአይቪም ይህን ድንገቴ በሽታ ሊስከትሉ ይችላል። አንዳንድ ሰዎች አንዳች ቫይረስ ከያዛቸው ከ2 እና ከ3 ሳምንት በኋላ ይህ በሽታ ይከሰትባቸዋል። ክሮኒክ በሽታዎች የሚባሉ በቋሚነት ሰውን የሚያጠቁ በሽታዎች አሉ። ለምሳሌ የመገጣጠሚያ ሕመም ያለባቸው ሰዎች ይህ በሽታ አንዳንዴ ይከሰትባቸዋል። በአመዛኙ ግን ይህ በሽታ ግራ የሚያጋባና ምክንያቱ የማይታወቅ፣ መነሻው በውል የማይለይ እና ያልተለመደ ደዌ ነው። ዶ/ር ዳዊት እንደሚሉት ይህ በሽታ የሚያሳያቸው ምልክቶች ውስን ናቸው። አንዱና ዋንኛው የእግር መስነፍ ነው። የጡንቻ መልፈስፈስ ነው። ታማሚዎች አንድ እርምጃ መራመድ ተራራ የመውጣት ያህል ሊሰማቸው ይችላል። ይህ የሚሆነው ደግሞ በብዛት በአጭር ቀናት ውስጥ ነው። ፋታም አይሰጥም። የእግር መስነፍ ብቻ ሳይሆን ከአንገት በታች ወይም ከወገብ በታች ያለ የሰውነት ክፍል በጠቅላላ አለመታዘዝ ይኖራል። ሽንት እምቢኝ፣ አልወጣ ሊል ይችላል። ቀስ ብሎ ደግሞ የሽንት እና ሰገራ ሙሉ ቁጥጥር ማጣት ይመጣል። ምልክቶቹ በትንሹ እንኳ ሲታዩ ቶሎ ሐኪም ማየት እንጂ ሌላ መላ የለም። “ቶሎ ከታከመ ነው ማገገም የሚቻለው። ከዘገዩ አደጋ ነው” ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። በዚህ በሽታ ድንገተኛ (acute) እና መለስተኛ ድንገተኛ (sub-acute) የሚባሉ ደረጃዎች አሉ። ድንገተኛ የምንለው በቀናት ውስጥ የሚመጣ ነው። መለስተኛ ድንገተኛ የሚባለው ደግሞ በ2 ሳምንት አካባቢ የሚባባስ ነው። ድንገተኛው በቀናት ውስጥ አጣድፎ ለሞት ሊያደርስ ይችላል። በተለይ ቶሎ ሐኪም ዘንድ ካልተሄደ አደገኛ ነው። ከፊል ድንገቴ ከሆነ ግን ፋታ ይሰጣል። ይህ የሚታወቀው በኤምአይአር እና በተጨማሪ ደም ምርመራዎች ነው። ዶ/ር ዳዊት በሽታውን በቀላሉ ለማስረዳት የኤሌክትሪክ መስመርን እንደ ምሳሌ ይጠቀማሉ። ነርቮች የእኛ የኤሌክትሪክ መስመር ሽቦዎች ናቸው። ሕብለ ሰረሰር ውስጥ ልክ እንደ ኤሌክትሪክ መስመር ሽቦዎች የሚያልፉበት አንድ የነርቭ መስመር አለ። እሱ የነርቭ መስመር ብግነት ሲገጥመው ነው ይህ በሽታ የሚጀምረው። የነርቭ መስመሩ ብግነት ደረጃ ደግሞ የበሽታውን ደረጃ ይወስናል። ብግነቱን ማቆም ነው የመጀመሪያው ጥረት። ሁለት ዓይነት ሕክምናዎች ይሰጣሉ። የመጀሪመያው ሕክምና ስቴሮይድ ይባላል። በደም ሥር ይሰጣል። ለተወሰኑ ቀናት። ይህም ብግነቱን ይቀንሳል። ሌላኛው ደግሞ ‘ኢሚኖሞግሎቢን’ የሚባለው ነው። የተቀመሙ አንቲቦዲዎች በደም ሥር ይሰጣል። ይህ በኢትዮጵያ ውስጥ አይገኝም። ውድም ነው። ከዚህ በኋላ ኦኮፔሽናልናል ፊዚዮቴራፒ ነው የሚቀጥለው። ጡንቻ መሰልጠን የሚችል ነገር ነው። አገልግሎቱን አቁሞ ከቀረ በዚያው ይሰንፋል፤ ይረሳል ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። ስለዚህ ሰውነታችን በፊዚካል ቴራፒ መሰልጠን አለበት። ይህ በሽታ በዘር አይተላለፍም። አንዳንድ ጊዜ ግን ክትባት ያመጣዋል። በኮቪድ በተያዙ ሰዎች ላይም አልፎ አልፎ ሊከሰት ይችላል። ሆኖም ግን ከስንት አንዴ ነው ይህ የሚሆነው። የኮቪድ ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ተህዋስ ይህን የሕብለ ሰረሰር ብግነትን ሊያመጡ ይችላሉ። ሰውነታችን ባክቴሪያዎቹንና ቫይረሶቹን ለማጥፋት ከሰውነታችን የሚሠራቸው አንቲቦዲ የምንላቸው ንጥረ ነገሮች አሉ። እነርሱ በስህተት የራሳችንን መከላከያ ሲያጠቁ ይህ በሽታ ይከሰታል። በተመሳሳይ ኮቪድም ቫይረስ ነው። ይህን በሽታ ሊያመጣ ይችላል። እስካለፈው ዓመት መጨረሻ ድረስ በ22 አገሮች እንዲህ ዓይነት አጋጣሚዎች ሪፖርት ተደርገዋል። ግን ብዙ አይደሉም። በመቶ ሚሊዮኖች ከሚቆጠሩ በኮቪድ ከተያዙ ሰዎች ውስጥ ይህ የተከሰተባቸው ሰዎች ከመቶ በታች ናቸው። “ከ140 ሚሊዮን ሰው ነው 100 ሰዎች ሪፖርት የተደረገው። የኮቪድ ክትባትም ተመሳሳይ ነው። ክትባቶች ለዚህ የሕብለ ሰረሰር በሽታ ቢያጋልጡም ቁጥራቸው ግን እዚህ ግባ የሚባል አይደለም” ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። ስለዚህ የኮቪድ ክትባት ይህን ሕመም ያመጣል ወይስ አያመጣም? ዶ/ር ዳዊት ለዚህ የሚሰጡት ምላሽ ጥንቃቄ የተሞላበት ነው። “የኮቪድ ክትባት ይህን በሽታ ያመጣል ብሎ መናገር ትክክል አይሆንም።” ይህ ሲባል የሕብለ ሰረሰር በሽታው ከከትባት ጋር አይያያዝም ማለት ሳይሆን፣ በዚህ የመከሰት አጋጣሚው እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነው። “እንደ ሕብረተሰብ ሦስትና አራት አጋጣሚዎች (cases) ስላሉ ክትባት በሽታውን ያመጣል ብለን መናገር ፍጹም ስህተት ነው” ይላሉ። ዶ/ር ዳዊት እንደሚያወሱት ከሆነ ይህ በሽታ በእኛ አገር በብዛት ከቲቢ ጋር እንደሚምታታ ይናገራሉ። ብዙ ሰው ቲቢ በአገራችን ከሳምባ ጋር ብቻ አያይዞ ነው የሚያየው። ነገር ግን ቲቢ ሳንባን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን ያጠቃል። ከእነዚህም መካከል ሕብለ ሰረሰር ይገኝበታል። ይህን በሽታ ከሌሎች ተመሳሳይ በሽታዎች የሚለየው ታዲያ በቀናት ውስጥ ነገሮች መባባሳቸው ነው። በተለይ ዶ/ር ዳዊት አገር ቤት ለሚገኙ ጠቅላላ ሐኪሞች ማስገንዘብ የሚሹት አንድ ነገር አለ። በሽተኞቻቸው ላይ ምልክቶችን ካዩ ሳይውሉ ሳያድሩ በፍጥነት ወደ ነርቭ ሐኪም እንዲልኳቸው። ይህም በተለይ በገጠርና ጤና ጣቢያ አካባቢ መዘግየት ሊኖር ከቻለ በሽታው ወዲያው ስለሚባባስ ነው። ከአንድ ወር እስከ ሦስት ወር ባለ ጊዜ ታማሚዎች ለውጥ ማየት ይጀምራሉ። ይሁንና ነገሮች በአንድ እና በሁለት ቀን ውስጥ ከተከሰቱ የማገገም ዕድሉም እየጠበበ ይመጣል። ረዘም ያለ ቀን የታመመ ሰው የማገገም ዕድሉ ከፍ ይላል። በዚህ ሕመም የ 1/3ኛ ሕግ የሚባል ነገር አለ ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። ከታማሚዎቹ ውስጥ አንድ እጁ ሙሉ በሙሉ ይድናሉ። ይህም እስከ ሦስት ወራት ሊወስድ ይችላል። አንድ ሦስተኛዎቹ ደግሞ አዝጋሚ ለውጥ ያያሉ። ይህ ለውጥ ዓመታት ሊወስድም ይችላል። ቀሪዎቹ አንድ ሦስተኞቹ ደግሞ ቋሚ ችግር ይኖርባቸዋል ማለት ነው። እንደ ዶ/ር ዳዊት መረዳት ከሆነ ከዚህ በሽታ ለማገገም ጊዜ ይወስዳል። የማገገም ዕድሎችን የሚጨምሩ ሌሎች ነገሮች ግን አሉ። ለምሳሌ በአፋጣኝ ሕክምና ማግኘት፤ ለምሳሌ አጋዥ ሕክምናዎች ኦኮፔሽናል እና ፊዚካል ቴራፒን ቶሎ መጀመር። በተለይ በሽተኞቹ ወጣት ከሆኑ ደግሞ የማገገም ዕድላቸው በዚያው ደረጃ ይጨምራል። ዶ/ር ዳዊት የነርቭን ተግባር በቀላል ቋንቋ ለማስረዳት የኤሌክትሪክ መስመርን ማሰብ ይበጃል እንዳሉ ከላይ ገልጠናል። በቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ ሽቦዎችን የሚሸፍን ኮንዲት አለ። በሰውነት ደግሞ ነርቮችን የሚሸፍን ነገር አለ፤ ማይሊን ይባላል። ብዙ ጊዜ ብግነቱ ይህን ሽፋኑን ነው የሚያጠቃው። ብግነቱ ከፍተኛ ሲሆን ግን ወደ ነርቭም ይገባል። በዚህ ጊዜ ነርቮች መልዕክት ለማስተላለፍ ይቸገራሉ። መልዕክት የሚተላለፈው በኬሚካል መስተጋብር ነው። ለምሳሌ ጭንቅላታችን “ተራመድ!” ብሎ ሲያዝ እኛ አናውቀውም እንጂ በነርቭ በኩል በሕብለ ሰረሰር አልፎ ወደ እግር ይሄዳል። ሕብለ ሰርሰር ላይ ብግነት ሲኖር መልዕክቱ በትክክል አይተላለፍም። በዚህን ጊዜ የነርቭ ሥራ ተስተጓጎለ እንላለን። በዚህ በሽታ ሦስት ዓይነት ምልክቶች አሉ ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። አንደኛ ‘ሞተር’ የምንለው የእንቅስቃሴ መስተጓጎል ነው። በቅጽበት ሰውነት ድንዝዝ ይላል። ስንፍ ይላል። እግር ታጥፎ አለመዘርጋት፣ ተዘርግቶ አለመታጠፍ ወይም ግትር የማለት ፀባይ ያሳያል። ሁለተኛ ‘ሴንሰሪ’ የምንለው ነው። ይህም የውሸት ምልክቶች እና ስሜቶች ማየት ስንጀምር ነው። እግሬ ትልቅ የሆነ ይመስለኛል። እግሬ በረዶ ውስጥ የገባ ይመስለኛል፤ የምንለው ለዚህ ነው። በሕክምና ዲስቴዥያ እንለዋለን። የተሳሳተ መልዕክት ሲተላለፈ እንደማለት ነው። ሦስተኛው ደግሞ ‘ኦቶኖሚክ ዲስፈንክሽን’ የሚባለው ነው። ይህም ማለት የእኛ ቁጥጥር ሳይኖረው አእምሯችን ካለማወቅ በራሱ የሚሠራቸው ነገሮች አሉ። ለምሳሌ ሽንታችን እንደመጣ የምናውቀው መሽናት እንዳለብን አስበንበት አብሰልስለን ሳይሆን ሰውነታችን ስለሚነግረን ነው። የ‘ሰብ ኮንሽየስ’ አእምሮ ክፍል “ሽንት ወጥሮሃል ሂድና ሽና” ይለናል። ይህ በሽታ እሱን መልዕክት ያዛባውና ሽንት እንደመጣብን አይነግረንም። ከዚያ ፊኛችን ተጠራቅሞ ተጠራቅሞ በራሱ ጊዜ ይወጣል። እኛ ሳናውቀው። ይህን ክስተት ‘ኦቶኖሚክ ዲስፈንክሽን’ እንለዋለን ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ በዚህ በሽታ ስንፈተ ወሲብ ይገጥማቸዋል። ዶ/ር ዳዊት ይህን በሽታ በተለየ ሁኔታ መከላከል እንደማይቻል ይጠቁማሉ። ይልቅ ደጋግመው የሚያሰምሩበት ምልክት በታየ ፍጥነት ቶሎ ሐኪም ማየትን ነው። ለታመሙ ሰዎች የሚሰጡት ምክር ሁለት ነው። አንዳንድ ታማሚዎች ካገገሙ በኋላ በተራዘመ ጊዜ የኩላሊት ኢንፌክሽን ሊገጥማቸው ይችላል። ይህን መከታተል ይኖርባቸዋል። ሌሎች ታማሚዎች ደግሞ መንቀሳቀስ ስለሚያቅታቸው አልጋ ላይ ይውላሉ። ይህንን ተከትሎ መቀመጫና ጀርባ አካባቢ ቁስል ይከሰታል። ይህ ሌላ ኢንፌክሽን ሊመጣ ይችላል። በዚህ ሁኔታ በሽተኛውን በየሁለት ሰዓቱ ማገላበጥ ያስፈልጋል ይላሉ። ከዚህ ሁሉ በላይ የሚያሰምሩበት ግን አንድ ነገር ነው። ሰዎች ምልክት ካዩ ሐኪም ለማየት መዘግየት እንደሌለባቸው። በዚህ በሽታ መዘግየት ማለት ሞት ነው።
ከ 1 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን 8 ሰዎችን ብቻ የሚያጠቃው አስገራሚ በሽታ አንዳንድ በሽታዎች ግራ ናቸው። ለታማሚም ለአስታማሚም፤ ለአካሚም ለታካሚም። ሐኪሞች እንዲህ ግራ የሆኑትን ደዌዎች ኢዲዮፓቲክ (idiopathic) ሲሉ ይጠሯቸዋል። ግራ የሚባሉት ግራ ስለሚያጋቡ ነው። መንስኤያቸው ስለማይታወቅ። ይህ ዛሬ የምንነግራችሁ በሽታ ከዚህ ይመደባል። 60 ከመቶ በምን እንደሚመጣ አይታወቅም። ሲመጣ ግን እግር ተወርች ያስራል። አስሮ ቤት ያስቀምጣል። የአማርኛ ስም የለውም። በእንግሊዝኛ ‘ትራንስቨረስ ማያሊቲስ’ ይባላል። በቅጽል ስሙ (TM) ይሉታል። በደምሳሳው የሕብለ ሰረሰር (የነርቭ) በሽታ ነው። ቀደም ሲል እንዳልነው 60 ከመቶው በምን እንደሚመጣ አይታወቅም። በቃ አያድርስ ነው የሚባለው። 40 ከመቶ ግን ምንጩ ይታወቃል። ይህን ዘርዘር አድርገው የሚያስረዱን ዶ/ር ዳዊት ክብሩ ናቸው። ዶ/ር ዳዊት የነርቭ ሕክምና ከፍተኛ ስፔሻሊስት ናቸው። አሁን በሰሜን አሜሪካ፣ በዊስኮንስን እና በሚቺጋን ግዛቶች በተለያዩ ሆስፒታሎች ይሠራሉ። “በሽታው የሕብለ ሰረሰር አንዱን ክፍል በድንገት ያጠቃል” ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። ቀጥሎ ከተጠቃው ሕብለ ሰረሰር በታች ያለውን የነርቭ ሥርዓት ይስተጓጎላል። ይስተጓጎላል ሲባል ምን ማለት ነው? ለምሳሌ እጅና እግርን ማዘዝ ይቸግራል። ሽንት መቆጣጠርም ሊያስቸግር ይችላል። “ከእንቅልፌ ስነሳ ድንገት መራመድ አቃተኝ፤ እግሬ ሰነፈብኝ” የሚሉ ታማሚዎች ያጋጥማሉ። ማንኛውም ነገር ሲነካን ቆዳችን ንክኪን የሚረዳበትን መንገድም ይቀየራል። ይህ የሚሆነው ከአእምሮ የሚላክ መልዕክት እየተቀየረ ለነርቭ ጫፍ ስለሚደርስ ነው። ለምሳሌ አንሶላ ጣል ቢደረግብን አሸዋ የተደፋብን ያህል ሊሰማን ይችላል። የሸሚዝ ቁልፍ ሲነካን በመርፌ የተወጋን ያህል ሊሰማን ይችላል። “በሽታው ያልተለመደ የሚባል ነው’’ ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። ያልተለመደ ያስባለው ደግሞ ምልክቶቹ አይደሉም። ጥቂት ሰዎችን ብቻ ስለሚያጠቃ ነው። በዓለም ከአንድ ሚሊዮን ሰው ቢበዛ 8 ሰዎችን ቢይዝ ነው። ይህን አሃዝ ወደ እኛ አገር እንመንዝረው። ለስሌት እንዲመቸን የኢትዮጵያን ሕዝብን 100 ሚሊዮን ነው እንበል። በዓመት በዚህ በሽታ የሚያዙት 800 ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ እንደማለት ነው። ምንም ስላደረግን አይደለም የሚመጣው። ምንም ሳላላደረግንም አይደለም። በቃ አንዳንድ ጊዜ መከላከያችን በስህተት ራሱን ያጠቃል። ይህ ከባዕድ ተህዋሲዎች ጋር የሚያያዝ ሊሆን ይችላል። በሽታው በምን በምን ይመጣል? ስንል ዶ/ር ዳዊትን ጠየቅን። “ብዙውን ጊዜ ያለምንም ምክንያት በድንገት ይመጣል።” “ሌላ ጊዜ ደግሞ የአንጀት መቁሰል (ጋስትሮ ስትራይተስ) ሲያመን ሊመጣ ይችላል” ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። “አንዳንድ ሰዎች በአንጀት መቁሰል ከታመሙ ከ2 ሳምንት ወይም ከ3 ሳምንት በኋላ በዚህ በሽታ ይያዛሉ።” እንደ ጉንፋን ዓይነት ወይም ኮቪድ ወይም ኤችአይቪም ይህን ድንገቴ በሽታ ሊስከትሉ ይችላል። አንዳንድ ሰዎች አንዳች ቫይረስ ከያዛቸው ከ2 እና ከ3 ሳምንት በኋላ ይህ በሽታ ይከሰትባቸዋል። ክሮኒክ በሽታዎች የሚባሉ በቋሚነት ሰውን የሚያጠቁ በሽታዎች አሉ። ለምሳሌ የመገጣጠሚያ ሕመም ያለባቸው ሰዎች ይህ በሽታ አንዳንዴ ይከሰትባቸዋል። በአመዛኙ ግን ይህ በሽታ ግራ የሚያጋባና ምክንያቱ የማይታወቅ፣ መነሻው በውል የማይለይ እና ያልተለመደ ደዌ ነው። ዶ/ር ዳዊት እንደሚሉት ይህ በሽታ የሚያሳያቸው ምልክቶች ውስን ናቸው። አንዱና ዋንኛው የእግር መስነፍ ነው። የጡንቻ መልፈስፈስ ነው። ታማሚዎች አንድ እርምጃ መራመድ ተራራ የመውጣት ያህል ሊሰማቸው ይችላል። ይህ የሚሆነው ደግሞ በብዛት በአጭር ቀናት ውስጥ ነው። ፋታም አይሰጥም። የእግር መስነፍ ብቻ ሳይሆን ከአንገት በታች ወይም ከወገብ በታች ያለ የሰውነት ክፍል በጠቅላላ አለመታዘዝ ይኖራል። ሽንት እምቢኝ፣ አልወጣ ሊል ይችላል። ቀስ ብሎ ደግሞ የሽንት እና ሰገራ ሙሉ ቁጥጥር ማጣት ይመጣል። ምልክቶቹ በትንሹ እንኳ ሲታዩ ቶሎ ሐኪም ማየት እንጂ ሌላ መላ የለም። “ቶሎ ከታከመ ነው ማገገም የሚቻለው። ከዘገዩ አደጋ ነው” ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። በዚህ በሽታ ድንገተኛ (acute) እና መለስተኛ ድንገተኛ (sub-acute) የሚባሉ ደረጃዎች አሉ። ድንገተኛ የምንለው በቀናት ውስጥ የሚመጣ ነው። መለስተኛ ድንገተኛ የሚባለው ደግሞ በ2 ሳምንት አካባቢ የሚባባስ ነው። ድንገተኛው በቀናት ውስጥ አጣድፎ ለሞት ሊያደርስ ይችላል። በተለይ ቶሎ ሐኪም ዘንድ ካልተሄደ አደገኛ ነው። ከፊል ድንገቴ ከሆነ ግን ፋታ ይሰጣል። ይህ የሚታወቀው በኤምአይአር እና በተጨማሪ ደም ምርመራዎች ነው። ዶ/ር ዳዊት በሽታውን በቀላሉ ለማስረዳት የኤሌክትሪክ መስመርን እንደ ምሳሌ ይጠቀማሉ። ነርቮች የእኛ የኤሌክትሪክ መስመር ሽቦዎች ናቸው። ሕብለ ሰረሰር ውስጥ ልክ እንደ ኤሌክትሪክ መስመር ሽቦዎች የሚያልፉበት አንድ የነርቭ መስመር አለ። እሱ የነርቭ መስመር ብግነት ሲገጥመው ነው ይህ በሽታ የሚጀምረው። የነርቭ መስመሩ ብግነት ደረጃ ደግሞ የበሽታውን ደረጃ ይወስናል። ብግነቱን ማቆም ነው የመጀመሪያው ጥረት። ሁለት ዓይነት ሕክምናዎች ይሰጣሉ። የመጀሪመያው ሕክምና ስቴሮይድ ይባላል። በደም ሥር ይሰጣል። ለተወሰኑ ቀናት። ይህም ብግነቱን ይቀንሳል። ሌላኛው ደግሞ ‘ኢሚኖሞግሎቢን’ የሚባለው ነው። የተቀመሙ አንቲቦዲዎች በደም ሥር ይሰጣል። ይህ በኢትዮጵያ ውስጥ አይገኝም። ውድም ነው። ከዚህ በኋላ ኦኮፔሽናልናል ፊዚዮቴራፒ ነው የሚቀጥለው። ጡንቻ መሰልጠን የሚችል ነገር ነው። አገልግሎቱን አቁሞ ከቀረ በዚያው ይሰንፋል፤ ይረሳል ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። ስለዚህ ሰውነታችን በፊዚካል ቴራፒ መሰልጠን አለበት። ይህ በሽታ በዘር አይተላለፍም። አንዳንድ ጊዜ ግን ክትባት ያመጣዋል። በኮቪድ በተያዙ ሰዎች ላይም አልፎ አልፎ ሊከሰት ይችላል። ሆኖም ግን ከስንት አንዴ ነው ይህ የሚሆነው። የኮቪድ ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ተህዋስ ይህን የሕብለ ሰረሰር ብግነትን ሊያመጡ ይችላሉ። ሰውነታችን ባክቴሪያዎቹንና ቫይረሶቹን ለማጥፋት ከሰውነታችን የሚሠራቸው አንቲቦዲ የምንላቸው ንጥረ ነገሮች አሉ። እነርሱ በስህተት የራሳችንን መከላከያ ሲያጠቁ ይህ በሽታ ይከሰታል። በተመሳሳይ ኮቪድም ቫይረስ ነው። ይህን በሽታ ሊያመጣ ይችላል። እስካለፈው ዓመት መጨረሻ ድረስ በ22 አገሮች እንዲህ ዓይነት አጋጣሚዎች ሪፖርት ተደርገዋል። ግን ብዙ አይደሉም። በመቶ ሚሊዮኖች ከሚቆጠሩ በኮቪድ ከተያዙ ሰዎች ውስጥ ይህ የተከሰተባቸው ሰዎች ከመቶ በታች ናቸው። “ከ140 ሚሊዮን ሰው ነው 100 ሰዎች ሪፖርት የተደረገው። የኮቪድ ክትባትም ተመሳሳይ ነው። ክትባቶች ለዚህ የሕብለ ሰረሰር በሽታ ቢያጋልጡም ቁጥራቸው ግን እዚህ ግባ የሚባል አይደለም” ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። ስለዚህ የኮቪድ ክትባት ይህን ሕመም ያመጣል ወይስ አያመጣም? ዶ/ር ዳዊት ለዚህ የሚሰጡት ምላሽ ጥንቃቄ የተሞላበት ነው። “የኮቪድ ክትባት ይህን በሽታ ያመጣል ብሎ መናገር ትክክል አይሆንም።” ይህ ሲባል የሕብለ ሰረሰር በሽታው ከከትባት ጋር አይያያዝም ማለት ሳይሆን፣ በዚህ የመከሰት አጋጣሚው እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነው። “እንደ ሕብረተሰብ ሦስትና አራት አጋጣሚዎች (cases) ስላሉ ክትባት በሽታውን ያመጣል ብለን መናገር ፍጹም ስህተት ነው” ይላሉ። ዶ/ር ዳዊት እንደሚያወሱት ከሆነ ይህ በሽታ በእኛ አገር በብዛት ከቲቢ ጋር እንደሚምታታ ይናገራሉ። ብዙ ሰው ቲቢ በአገራችን ከሳምባ ጋር ብቻ አያይዞ ነው የሚያየው። ነገር ግን ቲቢ ሳንባን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን ያጠቃል። ከእነዚህም መካከል ሕብለ ሰረሰር ይገኝበታል። ይህን በሽታ ከሌሎች ተመሳሳይ በሽታዎች የሚለየው ታዲያ በቀናት ውስጥ ነገሮች መባባሳቸው ነው። በተለይ ዶ/ር ዳዊት አገር ቤት ለሚገኙ ጠቅላላ ሐኪሞች ማስገንዘብ የሚሹት አንድ ነገር አለ። በሽተኞቻቸው ላይ ምልክቶችን ካዩ ሳይውሉ ሳያድሩ በፍጥነት ወደ ነርቭ ሐኪም እንዲልኳቸው። ይህም በተለይ በገጠርና ጤና ጣቢያ አካባቢ መዘግየት ሊኖር ከቻለ በሽታው ወዲያው ስለሚባባስ ነው። ከአንድ ወር እስከ ሦስት ወር ባለ ጊዜ ታማሚዎች ለውጥ ማየት ይጀምራሉ። ይሁንና ነገሮች በአንድ እና በሁለት ቀን ውስጥ ከተከሰቱ የማገገም ዕድሉም እየጠበበ ይመጣል። ረዘም ያለ ቀን የታመመ ሰው የማገገም ዕድሉ ከፍ ይላል። በዚህ ሕመም የ 1/3ኛ ሕግ የሚባል ነገር አለ ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። ከታማሚዎቹ ውስጥ አንድ እጁ ሙሉ በሙሉ ይድናሉ። ይህም እስከ ሦስት ወራት ሊወስድ ይችላል። አንድ ሦስተኛዎቹ ደግሞ አዝጋሚ ለውጥ ያያሉ። ይህ ለውጥ ዓመታት ሊወስድም ይችላል። ቀሪዎቹ አንድ ሦስተኞቹ ደግሞ ቋሚ ችግር ይኖርባቸዋል ማለት ነው። እንደ ዶ/ር ዳዊት መረዳት ከሆነ ከዚህ በሽታ ለማገገም ጊዜ ይወስዳል። የማገገም ዕድሎችን የሚጨምሩ ሌሎች ነገሮች ግን አሉ። ለምሳሌ በአፋጣኝ ሕክምና ማግኘት፤ ለምሳሌ አጋዥ ሕክምናዎች ኦኮፔሽናል እና ፊዚካል ቴራፒን ቶሎ መጀመር። በተለይ በሽተኞቹ ወጣት ከሆኑ ደግሞ የማገገም ዕድላቸው በዚያው ደረጃ ይጨምራል። ዶ/ር ዳዊት የነርቭን ተግባር በቀላል ቋንቋ ለማስረዳት የኤሌክትሪክ መስመርን ማሰብ ይበጃል እንዳሉ ከላይ ገልጠናል። በቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ ሽቦዎችን የሚሸፍን ኮንዲት አለ። በሰውነት ደግሞ ነርቮችን የሚሸፍን ነገር አለ፤ ማይሊን ይባላል። ብዙ ጊዜ ብግነቱ ይህን ሽፋኑን ነው የሚያጠቃው። ብግነቱ ከፍተኛ ሲሆን ግን ወደ ነርቭም ይገባል። በዚህ ጊዜ ነርቮች መልዕክት ለማስተላለፍ ይቸገራሉ። መልዕክት የሚተላለፈው በኬሚካል መስተጋብር ነው። ለምሳሌ ጭንቅላታችን “ተራመድ!” ብሎ ሲያዝ እኛ አናውቀውም እንጂ በነርቭ በኩል በሕብለ ሰረሰር አልፎ ወደ እግር ይሄዳል። ሕብለ ሰርሰር ላይ ብግነት ሲኖር መልዕክቱ በትክክል አይተላለፍም። በዚህን ጊዜ የነርቭ ሥራ ተስተጓጎለ እንላለን። በዚህ በሽታ ሦስት ዓይነት ምልክቶች አሉ ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። አንደኛ ‘ሞተር’ የምንለው የእንቅስቃሴ መስተጓጎል ነው። በቅጽበት ሰውነት ድንዝዝ ይላል። ስንፍ ይላል። እግር ታጥፎ አለመዘርጋት፣ ተዘርግቶ አለመታጠፍ ወይም ግትር የማለት ፀባይ ያሳያል። ሁለተኛ ‘ሴንሰሪ’ የምንለው ነው። ይህም የውሸት ምልክቶች እና ስሜቶች ማየት ስንጀምር ነው። እግሬ ትልቅ የሆነ ይመስለኛል። እግሬ በረዶ ውስጥ የገባ ይመስለኛል፤ የምንለው ለዚህ ነው። በሕክምና ዲስቴዥያ እንለዋለን። የተሳሳተ መልዕክት ሲተላለፈ እንደማለት ነው። ሦስተኛው ደግሞ ‘ኦቶኖሚክ ዲስፈንክሽን’ የሚባለው ነው። ይህም ማለት የእኛ ቁጥጥር ሳይኖረው አእምሯችን ካለማወቅ በራሱ የሚሠራቸው ነገሮች አሉ። ለምሳሌ ሽንታችን እንደመጣ የምናውቀው መሽናት እንዳለብን አስበንበት አብሰልስለን ሳይሆን ሰውነታችን ስለሚነግረን ነው። የ‘ሰብ ኮንሽየስ’ አእምሮ ክፍል “ሽንት ወጥሮሃል ሂድና ሽና” ይለናል። ይህ በሽታ እሱን መልዕክት ያዛባውና ሽንት እንደመጣብን አይነግረንም። ከዚያ ፊኛችን ተጠራቅሞ ተጠራቅሞ በራሱ ጊዜ ይወጣል። እኛ ሳናውቀው። ይህን ክስተት ‘ኦቶኖሚክ ዲስፈንክሽን’ እንለዋለን ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ በዚህ በሽታ ስንፈተ ወሲብ ይገጥማቸዋል። ዶ/ር ዳዊት ይህን በሽታ በተለየ ሁኔታ መከላከል እንደማይቻል ይጠቁማሉ። ይልቅ ደጋግመው የሚያሰምሩበት ምልክት በታየ ፍጥነት ቶሎ ሐኪም ማየትን ነው። ለታመሙ ሰዎች የሚሰጡት ምክር ሁለት ነው። አንዳንድ ታማሚዎች ካገገሙ በኋላ በተራዘመ ጊዜ የኩላሊት ኢንፌክሽን ሊገጥማቸው ይችላል። ይህን መከታተል ይኖርባቸዋል። ሌሎች ታማሚዎች ደግሞ መንቀሳቀስ ስለሚያቅታቸው አልጋ ላይ ይውላሉ። ይህንን ተከትሎ መቀመጫና ጀርባ አካባቢ ቁስል ይከሰታል። ይህ ሌላ ኢንፌክሽን ሊመጣ ይችላል። በዚህ ሁኔታ በሽተኛውን በየሁለት ሰዓቱ ማገላበጥ ያስፈልጋል ይላሉ። ከዚህ ሁሉ በላይ የሚያሰምሩበት ግን አንድ ነገር ነው። ሰዎች ምልክት ካዩ ሐኪም ለማየት መዘግየት እንደሌለባቸው። በዚህ በሽታ መዘግየት ማለት ሞት ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c16xpxknlw6o
2health
ኮሮናቫይረስ፡ በእንግሊዝ 10 አዳዲስ የኮቪድ-19 ክትባት መስጫ ማዕከላት ሊከፈቱ ነው
እንግሊዝ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ አዳዲስ የኮሮናቫይረስ ክትባት መስጫ ማዕከላትን ልትከፍት እንደሆነ አስታውቃለች። ይህ የሆነው መንግሥት ከአንድ ወር በኋላ በዩናይትድ ኪንግደም 15 ሚሊዮን ሕዝብ ለመከተብ ያቀደውን ግብ ለማሳካት ነው። ብላክበርን ካቴድራል እና ቅዱስ ሄለንስ ራግቢ ግራውንድ (ሜዳ) አሁን አገልግሎት እየሰጡ ያሉትን ሰባት ማዕከላት ይቀላቀላሉ። የእንግሊዝ ብሔራዊ ጤና አገልግሎት [ኤንኤችኤስ] ማዕከላቱ በሳምንት በሺዎች የሚቆጠሩ ክትባቶችን እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በብሔራዊ የክትባት ዘመቻው የተሳተፉትን አመስግነዋል። በዩናይትድ ኪንግደም እስካሁን በቫይረሱ ከተያዙት 3.3 ሚሊዮን ሰዎች ቁጥር በላይ ማለትም 3.5 ሚሊዮን ሰዎች ክትባቱን ወስደዋል። ሆኖም ከተመዘገበው ቁጥር በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች እንደሚኖሩ ይታመናል። መንግሥት ቁጥራቸው 15 ሚሊዮን ለሚሆኑ፤ ከ70 ዓመት ዕድሜ በላይ ለሆኑ፣ ለበሽታው ተጋላጭ ለሆኑ የሕክምና ባለሙያዎች እና የእንክብካቤ ማዕከላት ሰራተኞችን በሙሉ በየካቲት ወር አጋማሽ ክትባቱን ለመስጠት ቃል ገብቷል። በእንግሊዝ ታሪክ ሰፊው በሆነው በዚህ የክትባት መርሃ ግብር ሕዝቡ አረጋዊያንን በመርዳትና በቀጠሯቸው እንዲገኙ በማገዝ ድርሻውን እንዲወጣ መንግሥት አሳስቧል።
ኮሮናቫይረስ፡ በእንግሊዝ 10 አዳዲስ የኮቪድ-19 ክትባት መስጫ ማዕከላት ሊከፈቱ ነው እንግሊዝ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ አዳዲስ የኮሮናቫይረስ ክትባት መስጫ ማዕከላትን ልትከፍት እንደሆነ አስታውቃለች። ይህ የሆነው መንግሥት ከአንድ ወር በኋላ በዩናይትድ ኪንግደም 15 ሚሊዮን ሕዝብ ለመከተብ ያቀደውን ግብ ለማሳካት ነው። ብላክበርን ካቴድራል እና ቅዱስ ሄለንስ ራግቢ ግራውንድ (ሜዳ) አሁን አገልግሎት እየሰጡ ያሉትን ሰባት ማዕከላት ይቀላቀላሉ። የእንግሊዝ ብሔራዊ ጤና አገልግሎት [ኤንኤችኤስ] ማዕከላቱ በሳምንት በሺዎች የሚቆጠሩ ክትባቶችን እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በብሔራዊ የክትባት ዘመቻው የተሳተፉትን አመስግነዋል። በዩናይትድ ኪንግደም እስካሁን በቫይረሱ ከተያዙት 3.3 ሚሊዮን ሰዎች ቁጥር በላይ ማለትም 3.5 ሚሊዮን ሰዎች ክትባቱን ወስደዋል። ሆኖም ከተመዘገበው ቁጥር በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች እንደሚኖሩ ይታመናል። መንግሥት ቁጥራቸው 15 ሚሊዮን ለሚሆኑ፤ ከ70 ዓመት ዕድሜ በላይ ለሆኑ፣ ለበሽታው ተጋላጭ ለሆኑ የሕክምና ባለሙያዎች እና የእንክብካቤ ማዕከላት ሰራተኞችን በሙሉ በየካቲት ወር አጋማሽ ክትባቱን ለመስጠት ቃል ገብቷል። በእንግሊዝ ታሪክ ሰፊው በሆነው በዚህ የክትባት መርሃ ግብር ሕዝቡ አረጋዊያንን በመርዳትና በቀጠሯቸው እንዲገኙ በማገዝ ድርሻውን እንዲወጣ መንግሥት አሳስቧል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55693948
2health
ኮሮናቫይረስ፡ የትኞቹ የአፍሪካ ሃገራት ክትባት ጀመሩ? ሌሎቹስ መች ይጀምራሉ?
በአህጉረ አፍሪካ ቢያንስ 100 ሺህ ያክል ሰዎች እስካሁን በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። አህጉሪቱ የኮሮናቫይረስ ክትባትን በተገቢው መንገድ እየሰጠች አይደለም እየተባለች ትታማለች። ለመሆኑ የትኞቹ የአህጉሪቱ ሃገራት ናች ክትባት መስጠት የጀመሩት? የዓለም ሃገራት የኮቪድ-19 ክትባት ለማግኘት ፉክክር ላይ ናቸው። የአፍሪካ ሃገራት ግን ሃብታም ከሚባሉት ሃገራት ጋር ሲነፃፀር ወደኋላ የቀሩ ይመስላሉ። "በጣም ተጋላጭ የሆኑ የአፍሪካ ሃገራት ክትባት የማግኘት ተራቸው እስኪደርስ ድረስ እየጠቁ ነገር ግን እምብዛም ተጋላጭ ያልሆኑ ሃብታም ሃገራት ክትባቱን ሲያገኙ ማየት ፍትሃዊ አይደለም" ይላሉ በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ማትሺዲሶ ሞዬቲ። የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማኽሮ የአውሮፓና ሃገራትና አሜሪካ ከክትባቶቻቸው ቀንሰው ለአፍሪካ ሃገራት መስጠት አለባቸው ሲሉ ምክረ ሐሳብ አመንጭተው ነበር። የተወሰኑ ክትባቶች ለአፍሪካ ሃገራት በፍጥነት ሊዳረሱ ይገባል ይላሉ ፕሬዝደንቱ። አፍሪካ ውስጥ እስካሁን ድረስ ክትባት ማግኘት የቻሉት ከፋብሪካዎች በቀጥታ መግዛት የቻሉና ከሩስያ፣ ቻይና፣ ሕንድና ዩናይትድ አራብ ኤሜሬትስ በእርዳታ መልክ ያገኙ ሃገራት ናቸው። የአፍሪካ ሃገራት በዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ፕሮግራሞች ክትባት ለማግኘት ተስፋ አድርገዋል። አንደኛው ፕሮግራም ኮቫክስ የተሰኘው ነው። ይህ ፕሮግራም ሁሉም ሃገራት ክትባት ያገኙ ዘንድ ያለመ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት ከያዝነው የፈረንጆች ወር መጨረሻ ጀምሮ የአፍሪካ ሃገራት ክትባት ማግኘት ይጀምራሉ ብሎ ይገምታል። በዚህ ወቅት የሚሠራጩ 90 ሚሊዮን ክትባቶች የአህጉሪቱን 3 በመቶ ሕዝብ ይከትባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ክትባት በጣም ተጋላጭ ለሆኑና በቫይረሱ ምክንያት የበለጠ አደጋ ለሚደርስባቸው እንደ ጤና ባለሙያዎች ላሉ የሕብረተሰብ አካላት የሚከፋፈል ነው። የኮቫክስ ዓላማ 600 ሚሊዮን ክትባት ማግኘት ነው። ይህ የክትባት መጠን በፈረንጆቹ 2021 መጨረሻ ባለው የአህጉሪቱን 20 በመቶ ሰው ይከትባል። የአፍሪካ በሽታ ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል ኃላፊ ጆን ንኬንጋሶንግ ግን ይህ የክትባት መጠን በሽታውን ከአፍሪካ ነቅሎ ለማስወጣት በቂ ነው ብለው አያምኑም። እሳቸው እንደሚሉት የአፍሪካ ሃገራት ቢያንስ 60 በመቶ የሚሆነውን ሕዝባቸውን መከተብ አለባቸው። የአፍሪካ ሕብረትም በሃምሳ አምስቱ የአፍሪካ ሃገራት ስም ክትባት ለማግኘት ደፋ ቀና እያለ ነው። የአፍሪካ ሞባይል ኔትወርክ አቅራቢ ድርጅት የሆነው ኤምቲኤን 25 ሚሊዮን ዶላር በማዋጣት ለአፍሪካ የጤና ባለሙያዎች የሚሆን ሰባት ሚሊዮን ክትባት ለማግኘት እየጣረ ነው። የበሽታ ቁጥጥር ማዕከሉ እንደሚለው በኤምቲኤን በኩል የተገኘ አንድ ሚሊዮን ክትባት ለ20 ሃገራት በያዝነው ወር መጨረሻ ይከፋፈላል። የትኞቹ ሃገራት ቀድመው ክትባቱን እንደሚያገኙ ግን የተባለ ነገር የለም። ዜጎቻቸውን መከተብ የቻሉ ሃገራት የትኞቹ ናቸው? ምንም እንኳ ጥቂት ሃገራት ባለፈው ወር ክትባት መስጠት ቢጀምሩም አብዛኛዎቹ ሃገራት ግን ገና አልጀመሩም። በሰሜን አፍሪካ ክትባት መስጠት የጀመሩት ሃገራት ሞሮኮ፣ አልጄሪያና ግብፅ ናቸው። ከሰሃራ በታች ባሉ አፍሪካ አገራት ደግሞ ደቡብ አፍሪካ፣ ሲሼልስ፣ ሩዋንዳ፣ ሞሪሺዬስና ዚምባቡዌ ይገኛሉ። እንደ ኢኳቶሪያል ጊኒና ሴኔጋል ያሉ ሃገራት የመጀመሪያውን ዙር የሳይኖፋርም ክትባት ተቀብለዋል፤ መከተብ ግን አልጀመሩም። በአህጉሪቱ በወረርሽኙ ክፉኛ የተጠቃችው ደቡብ አፍሪካ አስትራዜኔካ የተሰኘውን ክትባት ለመከተብ ዕቅድ ይዛ ነበር። ነገር ግን ክትባቱ በአዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ላይ ያለው ኃያልነት አናሳ ነበው በሚል ሰርዛዋለች። ነገር ግን አሁን ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ከተሰኘው ፋብሪካ የተገኘው ክትባት ለአዲሱ ዝርያ ፍቱን ነው በሚል መከተብ ጀምራለች። ደቡብ አፍሪካ ከሕንዱ አቅራቢ ያገኘችውን አድን ሚሊዮን የአስትራዜኔካ ክትባት ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት መጠቀም ከፈለጉ በሚል ለአፍሪካ ሕብረት ሰጥታለች።
ኮሮናቫይረስ፡ የትኞቹ የአፍሪካ ሃገራት ክትባት ጀመሩ? ሌሎቹስ መች ይጀምራሉ? በአህጉረ አፍሪካ ቢያንስ 100 ሺህ ያክል ሰዎች እስካሁን በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። አህጉሪቱ የኮሮናቫይረስ ክትባትን በተገቢው መንገድ እየሰጠች አይደለም እየተባለች ትታማለች። ለመሆኑ የትኞቹ የአህጉሪቱ ሃገራት ናች ክትባት መስጠት የጀመሩት? የዓለም ሃገራት የኮቪድ-19 ክትባት ለማግኘት ፉክክር ላይ ናቸው። የአፍሪካ ሃገራት ግን ሃብታም ከሚባሉት ሃገራት ጋር ሲነፃፀር ወደኋላ የቀሩ ይመስላሉ። "በጣም ተጋላጭ የሆኑ የአፍሪካ ሃገራት ክትባት የማግኘት ተራቸው እስኪደርስ ድረስ እየጠቁ ነገር ግን እምብዛም ተጋላጭ ያልሆኑ ሃብታም ሃገራት ክትባቱን ሲያገኙ ማየት ፍትሃዊ አይደለም" ይላሉ በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ማትሺዲሶ ሞዬቲ። የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማኽሮ የአውሮፓና ሃገራትና አሜሪካ ከክትባቶቻቸው ቀንሰው ለአፍሪካ ሃገራት መስጠት አለባቸው ሲሉ ምክረ ሐሳብ አመንጭተው ነበር። የተወሰኑ ክትባቶች ለአፍሪካ ሃገራት በፍጥነት ሊዳረሱ ይገባል ይላሉ ፕሬዝደንቱ። አፍሪካ ውስጥ እስካሁን ድረስ ክትባት ማግኘት የቻሉት ከፋብሪካዎች በቀጥታ መግዛት የቻሉና ከሩስያ፣ ቻይና፣ ሕንድና ዩናይትድ አራብ ኤሜሬትስ በእርዳታ መልክ ያገኙ ሃገራት ናቸው። የአፍሪካ ሃገራት በዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ፕሮግራሞች ክትባት ለማግኘት ተስፋ አድርገዋል። አንደኛው ፕሮግራም ኮቫክስ የተሰኘው ነው። ይህ ፕሮግራም ሁሉም ሃገራት ክትባት ያገኙ ዘንድ ያለመ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት ከያዝነው የፈረንጆች ወር መጨረሻ ጀምሮ የአፍሪካ ሃገራት ክትባት ማግኘት ይጀምራሉ ብሎ ይገምታል። በዚህ ወቅት የሚሠራጩ 90 ሚሊዮን ክትባቶች የአህጉሪቱን 3 በመቶ ሕዝብ ይከትባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ክትባት በጣም ተጋላጭ ለሆኑና በቫይረሱ ምክንያት የበለጠ አደጋ ለሚደርስባቸው እንደ ጤና ባለሙያዎች ላሉ የሕብረተሰብ አካላት የሚከፋፈል ነው። የኮቫክስ ዓላማ 600 ሚሊዮን ክትባት ማግኘት ነው። ይህ የክትባት መጠን በፈረንጆቹ 2021 መጨረሻ ባለው የአህጉሪቱን 20 በመቶ ሰው ይከትባል። የአፍሪካ በሽታ ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል ኃላፊ ጆን ንኬንጋሶንግ ግን ይህ የክትባት መጠን በሽታውን ከአፍሪካ ነቅሎ ለማስወጣት በቂ ነው ብለው አያምኑም። እሳቸው እንደሚሉት የአፍሪካ ሃገራት ቢያንስ 60 በመቶ የሚሆነውን ሕዝባቸውን መከተብ አለባቸው። የአፍሪካ ሕብረትም በሃምሳ አምስቱ የአፍሪካ ሃገራት ስም ክትባት ለማግኘት ደፋ ቀና እያለ ነው። የአፍሪካ ሞባይል ኔትወርክ አቅራቢ ድርጅት የሆነው ኤምቲኤን 25 ሚሊዮን ዶላር በማዋጣት ለአፍሪካ የጤና ባለሙያዎች የሚሆን ሰባት ሚሊዮን ክትባት ለማግኘት እየጣረ ነው። የበሽታ ቁጥጥር ማዕከሉ እንደሚለው በኤምቲኤን በኩል የተገኘ አንድ ሚሊዮን ክትባት ለ20 ሃገራት በያዝነው ወር መጨረሻ ይከፋፈላል። የትኞቹ ሃገራት ቀድመው ክትባቱን እንደሚያገኙ ግን የተባለ ነገር የለም። ዜጎቻቸውን መከተብ የቻሉ ሃገራት የትኞቹ ናቸው? ምንም እንኳ ጥቂት ሃገራት ባለፈው ወር ክትባት መስጠት ቢጀምሩም አብዛኛዎቹ ሃገራት ግን ገና አልጀመሩም። በሰሜን አፍሪካ ክትባት መስጠት የጀመሩት ሃገራት ሞሮኮ፣ አልጄሪያና ግብፅ ናቸው። ከሰሃራ በታች ባሉ አፍሪካ አገራት ደግሞ ደቡብ አፍሪካ፣ ሲሼልስ፣ ሩዋንዳ፣ ሞሪሺዬስና ዚምባቡዌ ይገኛሉ። እንደ ኢኳቶሪያል ጊኒና ሴኔጋል ያሉ ሃገራት የመጀመሪያውን ዙር የሳይኖፋርም ክትባት ተቀብለዋል፤ መከተብ ግን አልጀመሩም። በአህጉሪቱ በወረርሽኙ ክፉኛ የተጠቃችው ደቡብ አፍሪካ አስትራዜኔካ የተሰኘውን ክትባት ለመከተብ ዕቅድ ይዛ ነበር። ነገር ግን ክትባቱ በአዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ላይ ያለው ኃያልነት አናሳ ነበው በሚል ሰርዛዋለች። ነገር ግን አሁን ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ከተሰኘው ፋብሪካ የተገኘው ክትባት ለአዲሱ ዝርያ ፍቱን ነው በሚል መከተብ ጀምራለች። ደቡብ አፍሪካ ከሕንዱ አቅራቢ ያገኘችውን አድን ሚሊዮን የአስትራዜኔካ ክትባት ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት መጠቀም ከፈለጉ በሚል ለአፍሪካ ሕብረት ሰጥታለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-56144583
5sports
ማንቸስተር ሲቲ ከቶተንሃም፣ አርሴናል ከኤቨርትን. . . የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት
ባለፈው ሳምንት ዌስት ሃም እና ኒውካስል በአወዛጋቢው በቪዲዮ በታገዘ ዳኝነት (ቫር) መጎዳታቸውን የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን ይገልጻል። እንደሱቶን ከሆነ ዌስትሃም ከቼልሲ ጋር አቻ መለያየት ይችል ነበር። ከፓላስ ጋር በነበረው ጨዋታ ኒውካስልም ሦስት ነጥባ ማሳካት ይችል ነበር። “ያለፈው ሳምንት ለእኔ ጥሩ አይደለም። ያለፈው ሳምንት ግምቴ በቫር ውሳኔ ሳይሳካ ቀርቷል” ብሏል። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ፣ እሑድ እና ሰኞ ይከናወናሉ። ለዚህ ሳምንትም ሱቶን የሊጉን ጨዋታዎች  ግምት አስቀምጧል። ፉልሃም ከ ቼልሲ ቼልሲ በዚህ ውድድር ዓመት ወጥ አቋም ማሳየት አልቻለም። ከአሰልጣኝ ቶማስ ቱህል መሰናበት በኋላስ ቡድኑ ምን ዓይነት አቋም ያሳያል? አዲሱ አሰልጣኝ ግርሃም ፖተር ቡድኑን ለማዘጋጀት በቂ ጊዜ ያላቸው አይመስልም። ቼልሲ ከፉልሃም የተሻሉ ተጫዋቾችን ይዟል። ቢሆንም ፉልሃም በሜዳው ማግኘት ከነበረበት ዘጠኝ ነጥብ ሰባቱን ማሳካት ችሏል። ግምት፡ 1 – 1 የግራም ፖተርን መልቀቅ ተከትሎ ብራይተን ወዴት ያመራ ይሆን? ብርንማውዝም አሰልጣኙ ስኮት ፓርከርን ካሳበተ በኋላ በጊዜያዊው አሰልጣኝ ጋሪ ኦኔል ይመራል። ኖቲንግሃም ፎረስትን ካሸነፉ በኋላ ሥራውን በቋሚነት ለመያዝ ማለሙ ጥፋት አይደለም። ፓርከር አንዳንድ ተጫዋቾቹ ለሊጉ ይመጥናሉ ብሎ የሚያስብ አይመስለኝም። ኦኔል ግን በተቃራኒው የሚያስብ ይመስለኛል። ይህ ነው ልዩነቱም። የፖተር መልቀቅም የተጫዋቾችን እምነት በመሸርሸር ለበርንማውዝ የሚጠቅም ይመስለኛል። ከፖተር ውጭም በራይተን ይህን ጨዋታ በበላይነት የሚያጠናቅቅ ይመስለኛል። ግምት፡ 1 – 2 ይህ ጨዋታ በመሰናበት አጣብቂኝ ውስጥ የሚገኙ ሁለት አሰልጣኞች የሚገናኙበት ነው። በብራይተን ከተሸነፉ በኋላ ብሬንዳን ሮጀርስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ከቡድኑ ጋር መቀጠል የሚፈልጉ አይመሰልም። ስቴቨን ዤራርድም ጫና ውስጥ ቢወድቅም ከማንቸስተር ሲቲ ጋር አቻ መውጣቱ ቡድን እየገነባ ለመሆኑ ምልክት ሊሆን ይችላል። ሮጀርስ አሰልጣኝ ሆነው ዤራርድ ተጫዋች ሆነው በሊቨርፑል ይተዋወቃሉ። ሁለቱም አሰልጣኞች የተለያዩ ቡድኖችን ይዘውም በስኮትላንድ ሊግ ተገናኝተዋል። ይህን ሁሉ ከግምት በማስገባት ቡድኖቹ ለመፋለም ብዙ ምክንያት እንዳላቸው አምናለሁ። ሆኖም ቪላ የሚያሽነፍ ይሰምለኛል። ግምት፡ 1 – 2 የሊቨርፑል ተከላካይ መስመር እንደቀድሞው አይደለም። ረቡዕ ምሽት በናፖሊ በተደጋጋሚ ሲፈተን አምሽቷል። ከዚህ ቀደም ሊቨርፑል ከመጥፎ ውጤቱ እንደሚያገግም በተደጋጋሚ እገምት ነበር። አሁን ግን በተቃራኒው እቆማለሁ። ሊቨርፑል ጎል እንደሚያስቆጥር ባምንም ዎልቭስ ጫና ያሳድርባቸዋል። ዎልቭሶች ችግራቸው ጎል ማስቆጠር ነው። ዲዬጎ ኮስታ ለዚህ መፍትሔ ስለመሆኑ ብጠራጠርም አንፊልድ ላይ የተወሰኑ ዕድሎችን እንደሚፈጥሩ አምናለሁ። ግምት፡ 1 – 2 ይህንን ጨዋታ ለመገመት ከባድ ነው። ባለፈው ዓመት ሴንት ሜሪ ላይ ሳውዝሃምፕት 4-1 ሲያሸንፍ በመልሱ ጨዋታ ብሬንትፎርድ 3-0 አሸንፏል። ጫና ያለው በአሰልጣኝ ራልፍ ሃሰንሃልት ላይ ቢሆን ጨዋታዎችን አሸንፈው በሊጉ እንደሚቆዩ አምናለሁ። ብሬንትፎርድ ጎል የማስቆጠር ችግር እንደሌለበት በሊድስ ጨዋታ አሳይቷል። አቻ ብዬ መገመት ባልወድም ከዚህ ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች አንድ አንድ ነጥብ ያገኛሉ። ግምት፡ 2 – 2 በሊጉ ምርጡ የመልሶ ማጥቃት ቡድን ቶተንሃም ነው። የሲቲ አጨዋወት ለቶተንሃም እንደሚመች ባለፈው የካቲት ኢትሃድ ላይ ተመልክተናል። የቅዳሜው ጨዋታ ክፍት እንደሚሆን እጠበቃለሁ። ሶን በዚህ ጨዋታ ጎል ያስቆጥራል ብዬ አስባለሁ። ሃላንድም ኳስና መረብን ያገናኛል። ግምት፡ 3 – 3 አርሴናል ከ ኤቨርትን አርሴናል ባለፈው ሳምንት በማንቸስተር ዩናይትድ ከደረሰበት ሽንፈት አንድ ነገር ማግኘት ነበረበት። አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአንድ ጊዜ ሦስት ተጫዋቾችን በቀየረበት አጋጣሚ ሲተች ተመልክቻለሁ። ለእኔ ግን ተገቢ ውሳኔ ነበር። ይህ ጨዋታ ለአርሴናል ቀላል አይሆንም። ኤቨርተን በጥሩ መንፈስ ላይ ይገኛል። ይህ የላምፓርድ ቡድን ነጥብ እንዲያገኝ በቂው ነው? ቡድኑ ጥሩ ኳስ ፈጣሪ ተጫዋቾች ያሉት ሲሆን ጋብርኤል ጄሱስን ካሰለፈ የእሑዱን ጨዋታ በድል ያጠናቅቃል። ግምት፡ 2 - 1 ዌስት ሃም በቼልሲ ሜዳ ባጋጠመው ነገር አዝኛለሁ። ማክስዌል ኮርኔት ያስቆጠረው ኳስ መሻሩ ከመጥፎ ውሳኔዎች አንዱ ነው። ኒውካስልም በተመሳሳይ መጥፎ ውሳኔ ተላልፎበታል። ሁለቱም ቡድኖች ማስመስከር የሚፈልጉት ጉዳይ ስላለ ጥሩ ጨዋታ ይሆናል። ኒውካስል ማጥቃትን የሚመርጥ ሲሆን ይህ አጨዋወት ለዌስት ሃም መልሶ ማጥቃት የተመቸ ነው። ግምት፡ 2 – 1 በሦስት ሳምንታት ውስጥ ማንቸስተር ዩናይትድ ለብዙዎች ከዓለማችን መጥፎው ቡድን ወደ ሃገሪቱ ድንቅ ቡድንነት ተቀይሯል። እውነታውን ካየበደረጃ ሰንጠረዡ መሐል ላይ ነው የሚገኙት። ያለፉትን አራት ጨዋታዎች ሲያሸንፉ ጥሩ ቢሆኑም በመሐል መሰናክል ያጋጥማቸዋል። ባለፈው ዓመት ዩናይትድን በሜዳው ያሸነፈው ክሪስታል ፓላስ በዚህም ጨዋታ ጥሩ ውጤት የሚያመጡለት ድንቅ ተጫዋቾች አሉት። የዩናይትድ ተከላካይ ክፍል ጫናን የሚቋቋምበት መንገድ የተመቸኝ ሲሆን በዚህ ጨዋታም የማሸነፍ ጉዟቸውን ይቀጥላሉ። ግምት፡ 0 – 1 ሊድስ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት በእነዚህ ሁለት ቡድኖች ምክንያት ከደጋፊዎች ከፍተኛ ትችት ገጥሞኛል።  ይህ የሆነው ደግሞ ሁለቱም እንደሚወርዱ እና ፎረስት በመጀመሪያዎቹ ሁለት ጨዋታዎች እንደሚሸነፍ በመገመቴ ነበር። በዚህ ጨዋታ ምን እንደሚፈጠር እንመልከት። በሜዳቸው እንደመጫወታቸው ሊድሶች የሚጠቀሙ ይሆናል። ፎረስት ያስመጣቸውን ተጫዋቾች እስኪያዋህድ ጊዜ ያስፈልገዋል። ፎረስት ባለፈው ሳምንተ 2 ለ 0 ከመምራት በበርንማውዝ መሸነፉ ቡድኑን ይጎዳዋል። ግምት፡ 3 – 1
ማንቸስተር ሲቲ ከቶተንሃም፣ አርሴናል ከኤቨርትን. . . የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት ባለፈው ሳምንት ዌስት ሃም እና ኒውካስል በአወዛጋቢው በቪዲዮ በታገዘ ዳኝነት (ቫር) መጎዳታቸውን የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን ይገልጻል። እንደሱቶን ከሆነ ዌስትሃም ከቼልሲ ጋር አቻ መለያየት ይችል ነበር። ከፓላስ ጋር በነበረው ጨዋታ ኒውካስልም ሦስት ነጥባ ማሳካት ይችል ነበር። “ያለፈው ሳምንት ለእኔ ጥሩ አይደለም። ያለፈው ሳምንት ግምቴ በቫር ውሳኔ ሳይሳካ ቀርቷል” ብሏል። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ፣ እሑድ እና ሰኞ ይከናወናሉ። ለዚህ ሳምንትም ሱቶን የሊጉን ጨዋታዎች  ግምት አስቀምጧል። ፉልሃም ከ ቼልሲ ቼልሲ በዚህ ውድድር ዓመት ወጥ አቋም ማሳየት አልቻለም። ከአሰልጣኝ ቶማስ ቱህል መሰናበት በኋላስ ቡድኑ ምን ዓይነት አቋም ያሳያል? አዲሱ አሰልጣኝ ግርሃም ፖተር ቡድኑን ለማዘጋጀት በቂ ጊዜ ያላቸው አይመስልም። ቼልሲ ከፉልሃም የተሻሉ ተጫዋቾችን ይዟል። ቢሆንም ፉልሃም በሜዳው ማግኘት ከነበረበት ዘጠኝ ነጥብ ሰባቱን ማሳካት ችሏል። ግምት፡ 1 – 1 የግራም ፖተርን መልቀቅ ተከትሎ ብራይተን ወዴት ያመራ ይሆን? ብርንማውዝም አሰልጣኙ ስኮት ፓርከርን ካሳበተ በኋላ በጊዜያዊው አሰልጣኝ ጋሪ ኦኔል ይመራል። ኖቲንግሃም ፎረስትን ካሸነፉ በኋላ ሥራውን በቋሚነት ለመያዝ ማለሙ ጥፋት አይደለም። ፓርከር አንዳንድ ተጫዋቾቹ ለሊጉ ይመጥናሉ ብሎ የሚያስብ አይመስለኝም። ኦኔል ግን በተቃራኒው የሚያስብ ይመስለኛል። ይህ ነው ልዩነቱም። የፖተር መልቀቅም የተጫዋቾችን እምነት በመሸርሸር ለበርንማውዝ የሚጠቅም ይመስለኛል። ከፖተር ውጭም በራይተን ይህን ጨዋታ በበላይነት የሚያጠናቅቅ ይመስለኛል። ግምት፡ 1 – 2 ይህ ጨዋታ በመሰናበት አጣብቂኝ ውስጥ የሚገኙ ሁለት አሰልጣኞች የሚገናኙበት ነው። በብራይተን ከተሸነፉ በኋላ ብሬንዳን ሮጀርስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ከቡድኑ ጋር መቀጠል የሚፈልጉ አይመሰልም። ስቴቨን ዤራርድም ጫና ውስጥ ቢወድቅም ከማንቸስተር ሲቲ ጋር አቻ መውጣቱ ቡድን እየገነባ ለመሆኑ ምልክት ሊሆን ይችላል። ሮጀርስ አሰልጣኝ ሆነው ዤራርድ ተጫዋች ሆነው በሊቨርፑል ይተዋወቃሉ። ሁለቱም አሰልጣኞች የተለያዩ ቡድኖችን ይዘውም በስኮትላንድ ሊግ ተገናኝተዋል። ይህን ሁሉ ከግምት በማስገባት ቡድኖቹ ለመፋለም ብዙ ምክንያት እንዳላቸው አምናለሁ። ሆኖም ቪላ የሚያሽነፍ ይሰምለኛል። ግምት፡ 1 – 2 የሊቨርፑል ተከላካይ መስመር እንደቀድሞው አይደለም። ረቡዕ ምሽት በናፖሊ በተደጋጋሚ ሲፈተን አምሽቷል። ከዚህ ቀደም ሊቨርፑል ከመጥፎ ውጤቱ እንደሚያገግም በተደጋጋሚ እገምት ነበር። አሁን ግን በተቃራኒው እቆማለሁ። ሊቨርፑል ጎል እንደሚያስቆጥር ባምንም ዎልቭስ ጫና ያሳድርባቸዋል። ዎልቭሶች ችግራቸው ጎል ማስቆጠር ነው። ዲዬጎ ኮስታ ለዚህ መፍትሔ ስለመሆኑ ብጠራጠርም አንፊልድ ላይ የተወሰኑ ዕድሎችን እንደሚፈጥሩ አምናለሁ። ግምት፡ 1 – 2 ይህንን ጨዋታ ለመገመት ከባድ ነው። ባለፈው ዓመት ሴንት ሜሪ ላይ ሳውዝሃምፕት 4-1 ሲያሸንፍ በመልሱ ጨዋታ ብሬንትፎርድ 3-0 አሸንፏል። ጫና ያለው በአሰልጣኝ ራልፍ ሃሰንሃልት ላይ ቢሆን ጨዋታዎችን አሸንፈው በሊጉ እንደሚቆዩ አምናለሁ። ብሬንትፎርድ ጎል የማስቆጠር ችግር እንደሌለበት በሊድስ ጨዋታ አሳይቷል። አቻ ብዬ መገመት ባልወድም ከዚህ ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች አንድ አንድ ነጥብ ያገኛሉ። ግምት፡ 2 – 2 በሊጉ ምርጡ የመልሶ ማጥቃት ቡድን ቶተንሃም ነው። የሲቲ አጨዋወት ለቶተንሃም እንደሚመች ባለፈው የካቲት ኢትሃድ ላይ ተመልክተናል። የቅዳሜው ጨዋታ ክፍት እንደሚሆን እጠበቃለሁ። ሶን በዚህ ጨዋታ ጎል ያስቆጥራል ብዬ አስባለሁ። ሃላንድም ኳስና መረብን ያገናኛል። ግምት፡ 3 – 3 አርሴናል ከ ኤቨርትን አርሴናል ባለፈው ሳምንት በማንቸስተር ዩናይትድ ከደረሰበት ሽንፈት አንድ ነገር ማግኘት ነበረበት። አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአንድ ጊዜ ሦስት ተጫዋቾችን በቀየረበት አጋጣሚ ሲተች ተመልክቻለሁ። ለእኔ ግን ተገቢ ውሳኔ ነበር። ይህ ጨዋታ ለአርሴናል ቀላል አይሆንም። ኤቨርተን በጥሩ መንፈስ ላይ ይገኛል። ይህ የላምፓርድ ቡድን ነጥብ እንዲያገኝ በቂው ነው? ቡድኑ ጥሩ ኳስ ፈጣሪ ተጫዋቾች ያሉት ሲሆን ጋብርኤል ጄሱስን ካሰለፈ የእሑዱን ጨዋታ በድል ያጠናቅቃል። ግምት፡ 2 - 1 ዌስት ሃም በቼልሲ ሜዳ ባጋጠመው ነገር አዝኛለሁ። ማክስዌል ኮርኔት ያስቆጠረው ኳስ መሻሩ ከመጥፎ ውሳኔዎች አንዱ ነው። ኒውካስልም በተመሳሳይ መጥፎ ውሳኔ ተላልፎበታል። ሁለቱም ቡድኖች ማስመስከር የሚፈልጉት ጉዳይ ስላለ ጥሩ ጨዋታ ይሆናል። ኒውካስል ማጥቃትን የሚመርጥ ሲሆን ይህ አጨዋወት ለዌስት ሃም መልሶ ማጥቃት የተመቸ ነው። ግምት፡ 2 – 1 በሦስት ሳምንታት ውስጥ ማንቸስተር ዩናይትድ ለብዙዎች ከዓለማችን መጥፎው ቡድን ወደ ሃገሪቱ ድንቅ ቡድንነት ተቀይሯል። እውነታውን ካየበደረጃ ሰንጠረዡ መሐል ላይ ነው የሚገኙት። ያለፉትን አራት ጨዋታዎች ሲያሸንፉ ጥሩ ቢሆኑም በመሐል መሰናክል ያጋጥማቸዋል። ባለፈው ዓመት ዩናይትድን በሜዳው ያሸነፈው ክሪስታል ፓላስ በዚህም ጨዋታ ጥሩ ውጤት የሚያመጡለት ድንቅ ተጫዋቾች አሉት። የዩናይትድ ተከላካይ ክፍል ጫናን የሚቋቋምበት መንገድ የተመቸኝ ሲሆን በዚህ ጨዋታም የማሸነፍ ጉዟቸውን ይቀጥላሉ። ግምት፡ 0 – 1 ሊድስ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት በእነዚህ ሁለት ቡድኖች ምክንያት ከደጋፊዎች ከፍተኛ ትችት ገጥሞኛል።  ይህ የሆነው ደግሞ ሁለቱም እንደሚወርዱ እና ፎረስት በመጀመሪያዎቹ ሁለት ጨዋታዎች እንደሚሸነፍ በመገመቴ ነበር። በዚህ ጨዋታ ምን እንደሚፈጠር እንመልከት። በሜዳቸው እንደመጫወታቸው ሊድሶች የሚጠቀሙ ይሆናል። ፎረስት ያስመጣቸውን ተጫዋቾች እስኪያዋህድ ጊዜ ያስፈልገዋል። ፎረስት ባለፈው ሳምንተ 2 ለ 0 ከመምራት በበርንማውዝ መሸነፉ ቡድኑን ይጎዳዋል። ግምት፡ 3 – 1
https://www.bbc.com/amharic/articles/cw0njlx21x3o
2health
ኮሮናቫይረስ፡ አውሮፕላኖች እንዴት ነው በፀረ- ተህዋሲያን የሚፀዱት?
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ቀጥ ብሎ የነበረውን የአለም የንግድ እንቅስቃሴን ለመመለስ በርካታ ጥረቶች እየተደረገ ነው። በተለያዩ አገራትም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ጥለዋቸው የነበሩ መመሪያዎችን እያላሉ ይገኛሉ። የወረርሽኝ ስርጭቱን ለመግታት አገራት አስተላልፈዋቸው ከነበሩ መመሪያዎች መካከል ዓለም አቀፍ በረራዎችን ማቆም፣ አየር ማረፊያዎቻቸውንና ድንበሮቻቸውን መዝጋት ይገኙበታል። በዚህም የተነሳ በርካታ የኢንዱስትሪ ዘርፎች በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ሲሆን በተለይም የአየር ትራንስፖርት ዘርፉ እንዲሽመደመድ ምክንያት ሆኗል። ከሰሞኑ አገራቱ ዘግተዋቸው የነበሩ ድንበሮቻቸውን ከፍተዋል፤ አለም አቀፍ አየር መንገዶቹም በረራዎችን ጀምረዋል። የአለም አቀፉ አቪየሽን ድርጅት የአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ እንዲያንሰራራና ተጓዦችም ደህንነታቸቸው በተጠበቀ መልኩ እንዲጓዙ ለማድረግ እንደ መመሪያነት የሚያገለግል አንድ ሰነድ አውጥቷል። በዚህም መመሪያ ውስጥ ከተካተቱት ጉዳዮች መካከል አውሮፕላኖች በምን መንገድ በፀረ- ተህዋሲያን መፀዳት እንዳለባቸውና የፅዳት ድግግሞሽንም ይመለከታል። እንዲሁ ከላይ ከላይ ሲታይ የአየር በረራና አካላዊ ርቀትን መጠበቅ የሚጣጣሙ አይመስሉም ። ነገር ግን ተቆጣጣሪ አካላት የተለያዩ ፕሮቶኮሎችን በማውጣት አስፈላጊ የሚባሉ የፅዳት መመሪያዎችን ለመተግበር ቀን ተሌት ደፋ ቀና በማለት ላይ ናቸው። ለአየር በረራዎች በዋነኝነት የሚያስፈልገው ፈጣንና፣ በቅልጥፍና የተሞላ ውጤታማ ፀረ- ተህዋሲያን የፅዳት ስርዓት መዘርጋት ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ ፍቃድ ያላቸው የፀረ- ተህዋሲያን ፅዳት በሚታዩና፣ ተደራሽ በሆኑ አካላት ላይ ጨርቅን እንዲሁም ተንቀሳቃሽ መርጫን በመጠቀም ማፅዳት ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ። ነገር ግን ሁለቱም የማፅጃ መንገዶች በሰዎች አማካኝነት የሚካዱ ከመሆናቸው አንፃር ውጤታማነታቸውን የሚቀንስ ሲሆን መደረስ የማይችሉ የአውሮፕላኑ አካላትም ላይ ክፍተትን ይፈጥራሉ ተብሏል። ኦክስጅንና ኦዞን በሌላ መልኩ "አቶሚክ ኦክስጅንን" እንደ ፀረ-ተህዋሲያነት በመጠቅም አካባቢን ለማፅዳት ተጀምሯል። ከዚህም በተጨማሪ አምቡላንሶችን ለማፅዳት የሚጠቀሙበትን ፀረ ተህዋሲያንንም ለአውሮፕላን የውስጥ ክፍል ለማፅዳት እየታሰበበት ነው። ነገር ግን እነዚህ ማፅጃዎች ባላቸው የንጥረ ነገር በተለይም 'ኦክሳይድ' ባለው ባህርይ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች ላይ ጉዳት ሊፈጥሩ ይችሉ ይሆን በሚለው ስምምነት ላይ አልተደረሰም። መቶ በመቶ ውጤታማ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ በሌለበት ሁኔታ ሌላኛው አማራጭ "የኦዞን" ንጥረ ነገሮችን መጠቀም ነው። በአሁኑ ወቅት ኦዞን በአውሮፕላን አካላት ላይ አገልግሎት ላይ ባይውልም በመጠጥ ቤቶችና በተለያዩ የንግድ ተቋማት ላይ በፀረ-ተህዋሲያን ማፅጃነት እያገለገለ ይገኛል። አካባቢውን የኦዞን ንጥረ ነገሮችን በመርጨት ውጤታማ የሆነ ፅዳትን ማግኘት ይቻላል። ነገር ግን ይህ ንጥረ ነገር በከፍተኛ መጠን ሲሆን ለሰዎች ጎጅ በመሆኑ ባለሙያን በመጠቀም መንገደኞች በሌሉበት ሁኔታ ሊረጭ ይገባል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ኦዞን ላይ ያለው ዋነኛ ጥያቄም የኦክሳይድ ንጥረ ነገር መጠኑ ነው፤ 'በአውሮፕላን የውስጥ አካልና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ላይ ያለው ተፅእኖ ላይ መስማማት አልተቻለም። 'አየኖችና የአልትራቫዮሌት ጨረር ' በላብራቶሪ ውስጥ ተሞክሮ ውጤታማ የሆነው ከከባቢ አየር የሚለቀቀውን የውሃ ትነት ውስጥ የኦክስጅንና ሃይድሮጅን ንጥረ ነገሮችን ለይቶ በማውጣት ፀረ ተህዋሲያንን መፍጠር ነው። ይህ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ መንገድ በጣም አድካሚና ለሁለት ሰዓታት ያህልም የሚወስድ ጊዜን ይፈጃል። ሆኖም ይሄ መንገድ በከፍተኛ ሁኔታ ውጤታማና መቶ በመቶ የሚተማመኑበት ነው። ከዚህም በተጨማሪ ፀረ ተህዋሲያኑ ቀላልና ተንቀሳቃሽ በሆነ መልኩ ትልልቅ የአውሮፕላን አካሎችን ማፅዳት ቢቻልም ለማፅዳት ግን ረዘም ያለ ጊዜ መውሰድ ያስፈልጋል። ሌላኛው ደግሞ ሲ የሚባለው የአልትራቫዮሌት ጨረር ሲሆን ይህ ጨረር ሳርስ የተባለውን የኮሮናቫይረስ አይነት ማጥፋት ይችላል። ለዚያም ነው ከፍተኛ ወጪ የሌላቸው ጨረሮች የአውሮፕላን አካላትን ለማፅዳት እየተነደፉ እንዲሁም እየተመረቱ ያሉት። ይህንም ተከትሎ በገበያው ላይ የነዚህ ጨረሮች ፍላጎት በመጨመሩ ምክንያት የአልትራቫዮሌት ጨረሮችን የሚያመርቱ ኩባንያዎች ምርታቸው በሚቀጥሉት አራት አመታት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምርም ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በርካታ አማራጮች በርካታ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ አማራጮች ከመኖራቸው አንፃር በተለያየ ሂደትም ላይ ናቸው። አሁንም ቢሆን የትኛው የበለጠ ተስማሚ እንደሆነም እስካሁንም አይታወቅም። የትኛው የፀረ ተህዋሲያን ስርአት የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን መለየት ከተቻለ በኋላ ምን ያህል ጊዜም ይወስዳል የሚለውን ማየት አስፈላጊ እንደሆነም እየተነገረ ነው። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አሁንም ስጋት ሆኖ ባለበት ወቅት በርካታ አየር መንገዶች በረራ መጀመራቸው ጋር ተያይዞ ቫይረሱ እንዳይሰራጭ የማድረግ ከፍተኛ ኃላፊነትና ሸክም ተጥሏባቸዋል። የአውሮፕላኑ ሰራተኞች፣ መንገደኞችን ደህንነት በሚያስጠብቅ መልኩ አውሮፕላኖቹ በፀረ ተህዋሲያን መፀዳትም ግዴታ ነው። እነዚህ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ ዘዴዎች ቫይረሱን መግታት ብቻ ሳይሆን የአየር መንገድ ኃላፊዎችም ሆነ ተቆጣጣሪዎች የሚያስወጣቸውን ዋጋና እንዲሁም ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ መንገድ መፅዳት የሚችሉበትን ሁኔታ መገምገም ይጠበቅባቸዋል። በአንድ መልኩ የአየር ትራንስፖርቱ ወደቀደመ ሁኔታ እንዲመለሱ ግፊት እያደረጉ ሲሆን በሌላ መልኩ በዚህ ወረርሽኝ መካከል የተጓዦች ደህንነት በተጠበቀ መልኩ አገልግሎታቸውን መመለስና በወረርሽኙ ምክንያት ያጡትን ገቢ ለማግኘትም አጣጥመው መሄድ ይጠበቅባቸዋል። በተለይም አውሮፕላኖቹ የሚፀዱበትን ደረጃና ያለውን የስጋት መጠንን መቀነስና፤ የሚፀዳበትን ጊዜ አጣጥመው መሄድም ይጠበቅባቸዋል። የመንገደኞችን ጤንትና ደህንነት ቅድሚያ በመስጠትም አየር መንገዶቹ እነዚህን ተግባራት እንዲያከናውኑም አለም አቀፉ አቪየሽንም መመሪያ ሰጥቷል። ከአለም አቀፉ አቪየሽን ቡድንና፣ የትራንስፖርት ዘርፍ ተመራማሪዎች የተውጣጡ ግለሰቦችም ውጤታማ የሆኑትን የፀረ ተህዋሲያን የማፅጃ ዘዴዎችንም ለመቀየስ ከፍተኛ ምርምሮችን እያደረጉም ነው፤ የተለያዩ መመሪያዎችንም በማውጣትም ላይ ይገኛሉ።
ኮሮናቫይረስ፡ አውሮፕላኖች እንዴት ነው በፀረ- ተህዋሲያን የሚፀዱት? የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ቀጥ ብሎ የነበረውን የአለም የንግድ እንቅስቃሴን ለመመለስ በርካታ ጥረቶች እየተደረገ ነው። በተለያዩ አገራትም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ጥለዋቸው የነበሩ መመሪያዎችን እያላሉ ይገኛሉ። የወረርሽኝ ስርጭቱን ለመግታት አገራት አስተላልፈዋቸው ከነበሩ መመሪያዎች መካከል ዓለም አቀፍ በረራዎችን ማቆም፣ አየር ማረፊያዎቻቸውንና ድንበሮቻቸውን መዝጋት ይገኙበታል። በዚህም የተነሳ በርካታ የኢንዱስትሪ ዘርፎች በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ሲሆን በተለይም የአየር ትራንስፖርት ዘርፉ እንዲሽመደመድ ምክንያት ሆኗል። ከሰሞኑ አገራቱ ዘግተዋቸው የነበሩ ድንበሮቻቸውን ከፍተዋል፤ አለም አቀፍ አየር መንገዶቹም በረራዎችን ጀምረዋል። የአለም አቀፉ አቪየሽን ድርጅት የአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ እንዲያንሰራራና ተጓዦችም ደህንነታቸቸው በተጠበቀ መልኩ እንዲጓዙ ለማድረግ እንደ መመሪያነት የሚያገለግል አንድ ሰነድ አውጥቷል። በዚህም መመሪያ ውስጥ ከተካተቱት ጉዳዮች መካከል አውሮፕላኖች በምን መንገድ በፀረ- ተህዋሲያን መፀዳት እንዳለባቸውና የፅዳት ድግግሞሽንም ይመለከታል። እንዲሁ ከላይ ከላይ ሲታይ የአየር በረራና አካላዊ ርቀትን መጠበቅ የሚጣጣሙ አይመስሉም ። ነገር ግን ተቆጣጣሪ አካላት የተለያዩ ፕሮቶኮሎችን በማውጣት አስፈላጊ የሚባሉ የፅዳት መመሪያዎችን ለመተግበር ቀን ተሌት ደፋ ቀና በማለት ላይ ናቸው። ለአየር በረራዎች በዋነኝነት የሚያስፈልገው ፈጣንና፣ በቅልጥፍና የተሞላ ውጤታማ ፀረ- ተህዋሲያን የፅዳት ስርዓት መዘርጋት ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ ፍቃድ ያላቸው የፀረ- ተህዋሲያን ፅዳት በሚታዩና፣ ተደራሽ በሆኑ አካላት ላይ ጨርቅን እንዲሁም ተንቀሳቃሽ መርጫን በመጠቀም ማፅዳት ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ። ነገር ግን ሁለቱም የማፅጃ መንገዶች በሰዎች አማካኝነት የሚካዱ ከመሆናቸው አንፃር ውጤታማነታቸውን የሚቀንስ ሲሆን መደረስ የማይችሉ የአውሮፕላኑ አካላትም ላይ ክፍተትን ይፈጥራሉ ተብሏል። ኦክስጅንና ኦዞን በሌላ መልኩ "አቶሚክ ኦክስጅንን" እንደ ፀረ-ተህዋሲያነት በመጠቅም አካባቢን ለማፅዳት ተጀምሯል። ከዚህም በተጨማሪ አምቡላንሶችን ለማፅዳት የሚጠቀሙበትን ፀረ ተህዋሲያንንም ለአውሮፕላን የውስጥ ክፍል ለማፅዳት እየታሰበበት ነው። ነገር ግን እነዚህ ማፅጃዎች ባላቸው የንጥረ ነገር በተለይም 'ኦክሳይድ' ባለው ባህርይ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች ላይ ጉዳት ሊፈጥሩ ይችሉ ይሆን በሚለው ስምምነት ላይ አልተደረሰም። መቶ በመቶ ውጤታማ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ በሌለበት ሁኔታ ሌላኛው አማራጭ "የኦዞን" ንጥረ ነገሮችን መጠቀም ነው። በአሁኑ ወቅት ኦዞን በአውሮፕላን አካላት ላይ አገልግሎት ላይ ባይውልም በመጠጥ ቤቶችና በተለያዩ የንግድ ተቋማት ላይ በፀረ-ተህዋሲያን ማፅጃነት እያገለገለ ይገኛል። አካባቢውን የኦዞን ንጥረ ነገሮችን በመርጨት ውጤታማ የሆነ ፅዳትን ማግኘት ይቻላል። ነገር ግን ይህ ንጥረ ነገር በከፍተኛ መጠን ሲሆን ለሰዎች ጎጅ በመሆኑ ባለሙያን በመጠቀም መንገደኞች በሌሉበት ሁኔታ ሊረጭ ይገባል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ኦዞን ላይ ያለው ዋነኛ ጥያቄም የኦክሳይድ ንጥረ ነገር መጠኑ ነው፤ 'በአውሮፕላን የውስጥ አካልና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ላይ ያለው ተፅእኖ ላይ መስማማት አልተቻለም። 'አየኖችና የአልትራቫዮሌት ጨረር ' በላብራቶሪ ውስጥ ተሞክሮ ውጤታማ የሆነው ከከባቢ አየር የሚለቀቀውን የውሃ ትነት ውስጥ የኦክስጅንና ሃይድሮጅን ንጥረ ነገሮችን ለይቶ በማውጣት ፀረ ተህዋሲያንን መፍጠር ነው። ይህ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ መንገድ በጣም አድካሚና ለሁለት ሰዓታት ያህልም የሚወስድ ጊዜን ይፈጃል። ሆኖም ይሄ መንገድ በከፍተኛ ሁኔታ ውጤታማና መቶ በመቶ የሚተማመኑበት ነው። ከዚህም በተጨማሪ ፀረ ተህዋሲያኑ ቀላልና ተንቀሳቃሽ በሆነ መልኩ ትልልቅ የአውሮፕላን አካሎችን ማፅዳት ቢቻልም ለማፅዳት ግን ረዘም ያለ ጊዜ መውሰድ ያስፈልጋል። ሌላኛው ደግሞ ሲ የሚባለው የአልትራቫዮሌት ጨረር ሲሆን ይህ ጨረር ሳርስ የተባለውን የኮሮናቫይረስ አይነት ማጥፋት ይችላል። ለዚያም ነው ከፍተኛ ወጪ የሌላቸው ጨረሮች የአውሮፕላን አካላትን ለማፅዳት እየተነደፉ እንዲሁም እየተመረቱ ያሉት። ይህንም ተከትሎ በገበያው ላይ የነዚህ ጨረሮች ፍላጎት በመጨመሩ ምክንያት የአልትራቫዮሌት ጨረሮችን የሚያመርቱ ኩባንያዎች ምርታቸው በሚቀጥሉት አራት አመታት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምርም ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በርካታ አማራጮች በርካታ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ አማራጮች ከመኖራቸው አንፃር በተለያየ ሂደትም ላይ ናቸው። አሁንም ቢሆን የትኛው የበለጠ ተስማሚ እንደሆነም እስካሁንም አይታወቅም። የትኛው የፀረ ተህዋሲያን ስርአት የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን መለየት ከተቻለ በኋላ ምን ያህል ጊዜም ይወስዳል የሚለውን ማየት አስፈላጊ እንደሆነም እየተነገረ ነው። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አሁንም ስጋት ሆኖ ባለበት ወቅት በርካታ አየር መንገዶች በረራ መጀመራቸው ጋር ተያይዞ ቫይረሱ እንዳይሰራጭ የማድረግ ከፍተኛ ኃላፊነትና ሸክም ተጥሏባቸዋል። የአውሮፕላኑ ሰራተኞች፣ መንገደኞችን ደህንነት በሚያስጠብቅ መልኩ አውሮፕላኖቹ በፀረ ተህዋሲያን መፀዳትም ግዴታ ነው። እነዚህ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ ዘዴዎች ቫይረሱን መግታት ብቻ ሳይሆን የአየር መንገድ ኃላፊዎችም ሆነ ተቆጣጣሪዎች የሚያስወጣቸውን ዋጋና እንዲሁም ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ መንገድ መፅዳት የሚችሉበትን ሁኔታ መገምገም ይጠበቅባቸዋል። በአንድ መልኩ የአየር ትራንስፖርቱ ወደቀደመ ሁኔታ እንዲመለሱ ግፊት እያደረጉ ሲሆን በሌላ መልኩ በዚህ ወረርሽኝ መካከል የተጓዦች ደህንነት በተጠበቀ መልኩ አገልግሎታቸውን መመለስና በወረርሽኙ ምክንያት ያጡትን ገቢ ለማግኘትም አጣጥመው መሄድ ይጠበቅባቸዋል። በተለይም አውሮፕላኖቹ የሚፀዱበትን ደረጃና ያለውን የስጋት መጠንን መቀነስና፤ የሚፀዳበትን ጊዜ አጣጥመው መሄድም ይጠበቅባቸዋል። የመንገደኞችን ጤንትና ደህንነት ቅድሚያ በመስጠትም አየር መንገዶቹ እነዚህን ተግባራት እንዲያከናውኑም አለም አቀፉ አቪየሽንም መመሪያ ሰጥቷል። ከአለም አቀፉ አቪየሽን ቡድንና፣ የትራንስፖርት ዘርፍ ተመራማሪዎች የተውጣጡ ግለሰቦችም ውጤታማ የሆኑትን የፀረ ተህዋሲያን የማፅጃ ዘዴዎችንም ለመቀየስ ከፍተኛ ምርምሮችን እያደረጉም ነው፤ የተለያዩ መመሪያዎችንም በማውጣትም ላይ ይገኛሉ።
https://www.bbc.com/amharic/53627279
5sports
ሜሲ ወይስ ሞድሪች? ፈረንሳይ አሊያ ሞሮኮ? አዲስ ታሪክ የሚፃፍበት የዓለም ዋንጫ ወደየት ያመራ ይሆን?
እንግሊዝ ቅዳሜ ምሽት በፈረንሳይ ተረትታ በበነጋው አውሮፕላን ተሳፍራ ከዶሃ ወጥታለች። አሁን አራት ብሔራዊ ቡድኖች ቀርተዋል - ፈረንሳይ፣ ሞሮኮ፣ ክሮሺያ እና አርጀንቲና። ከአራቱ አንዱ በሚቀጥለው እሑድ ወርቃማውን ዋንጫ ያነሳል። እኚህ አራት ቡድኖች ለግማሽ ፍፃሜ ይደርሳሉ ብሎ የገመተ ጥቂት ነው። አራቱም ብሔራዊ ቡድኖች አዲስ ታሪክ ሊፅፉ ከጫፍ ደርሰዋል። አርጀንቲናዊው ኮከብ በእግር ኳስ ሕይወቱ የመጀመሪያው እና የመጨረሻውን የዓለም ዋንጫ ሊያነሳ ይችላል። ሜሲ ለዋንጫ ብርቅ አይደለም። 10 የስፔን ላሊ ጋ ዋንጫ፣ አራት ጊዜ ቻምፒዮንስ ሊግ፣ አንድ ጊዜ የፈረንሳይ ሊግ እንዲሁም ከአገሩ አርጀንቲና ጋር ኮፓ አሜሪካን አንስቷል። ሜሲ የእግር ኳስ ከዋክብት ጉምቱው ሽልማት የሚባለውን ባሎን ዶር ሰባት ጊዜ በማንሳት ክብረ-ወሰን ጨብጧል። ነገር ግን የ35 ዓመቱን የእግር ኳስ ተዓምረኛ ከማራዶና እና ከፔሌ የሚለየው የዓለም ዋንጫን አለማንሳቱ ነው። አርጀንቲና በዲዬጎ ማራዶና እየተመራች የዓለም ዋንጫ ካነሳች 36 ዓመታት ተቆጥረዋል። ሜሲ ይህን ይደግመው ይሆን? የዓለም ዋንጫ ማንሳቱስ የዘመናችን ድንቁ ተጫዋች የተሰኘውን ስያሜ ያሰጠው ይሆን? ሞሮኮ ከወዲሁ ታሪክ ሰርታ፤ እንዲሁም ጨምራ ሌላ ታሪክ እየፃፈች እዚህ ደርሳለች። ሞሮኮ ከአህጉረ አፍሪካ፣ አልፎም ከአረቡ ዓለም ለግማሽ ፍፃሜው የደረሰች የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። ምንም እንኳ ሞሮኮ እንደ አሽራፍ ሐኪሚ እና ሐኪም ዚዬች ያሉ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች ቢኖሯትም እዚህ ትደርሳለች ብለው የገመቱ ጥቂት ናቸው። ክሮሺያ እና ቤልጂዬም የነበሩበትን ምድብ አልፋ፣ ኃያሏ ስፔንን አስወግዳ፣ ፖርቹጋልን አሰናብታ ነው እዚህ የደረሰችው። የአትላስ አናብስት የጎል መስመራቸውን ሲከላከሉ ያለ እረፍት ነው። በኳታር የዓለም ዋንጫ ማንም የሞሮኮን መረብ አልደፈረም። ከአንድ ጎል በቀር። እሱም በራስ ላይ የተቆጠረ ነው። ሞሮኮ የዓለም ዋንጫ ድምቀት ሆናለች። ደጋፊዎች ስታደየሙን ከጫፍ ጫፍ ሞልተው ያለማቋረጥ ቡድናቸውን ይደግፋሉ። ሞሮኮ ረቡዕ ዕለት አዲስ ታሪክ ትፅፍ ይሆን? ፈረንሳይ የዓለም ዋንጫ በተከታታይ ሁለት ጊዜ ታነሳ ይሆን? አውሮፓዊቷ አገር የዓለም ዋንጫውን በተከታታይ ሁለት ጊዜ እንዳታነሳ ታሪክ ሠሪዋ ሞሮኮ ልታግዳት ትችላለች። 'ሌ ብሉ' በሚለው ቅጽል ስማቸው የሚታወቁት ፈረንሳዮች፣ ከስድሳ ዓመታት በኋላ አዲስ ታሪክ ለመፃፍ ይሞክራሉ። ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ በተከታታይ የዓለም ዋንጫ ያነሳችው ብራዚል ስትሆን፣ ይህ ከሆነ 60 ዓመታት ተቆጥረዋል። ጣልያን፣ ስፔን፣ ጀመርን ባለፉት 12 ዓመታት ዋንጫ አንስተው በሚቀጥለው የዓለም ዋንጫ ውድድሩን በጊዜ የተሳነበቱ አገራት ናቸው። ባለፈው ቅዳሜ እንግሊዝን የረታችው ፈረንሳይ ከብራዚል ቀጥላ ዋንጫ ባነሳች ተከታ የዓለም ዋንጫ ውድድር ለግማሽ ፍፃሜ የበቃች አገር ሆናለች። አሠልጣኝ ዲዲዬ ዴሾ አሁን ትኩረታቸው ሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮ ሆናለች። የ2018 ዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታን ደግመን ልናየው እንችል ይሆናል። ፈረንሳይ ሞሮኮን፤ ክሮሺያ ደግሞ አርጀንቲናን ካሰናበቱ በሩሲያ ያሳዩንን የፍፃሜ ጨዋታ በኳታር ምድር ይደግሙታል። ክሮሺያ በዙር 16 ጃፓንን፤ በሩብ ፍፃሜው ደግሞ ብራዚልን በመርታት ነው ከመጨረሻዎቹ አራት ቡድኖች ተርታ መሰለፍ የቻለችው። ክሮሺያ ለመጨረሻ ጊዜ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ በ90 ደቂቃ ተጫውታ ያለፈችው ከ24 ዓመታት በፊት ጀርመንን በረታች ወቅት ነው። የክሮሺያ አምበል እና የመሃል መስመሩ ሞተር፤ ሉካ ሞድሪች ዕድሜው 37 ደርሷል። ነገር ግን 120 ደቂቃ ተጫውቶ አገሩን ለዚህ አብቅቷል። ባለፈው የዓለም ዋንጫ በምድብ ጨዋታ በክሮሺያ 3 ለምንም የተረታችው አርጀንቲና ለሞድሪች ቡድን ንቀት እንደማታሳይ ይጠበቃል። አርጀንቲና ከክሮሺያ ማክሰኞ ምሽት 4 ሰዓት ይገናኛሉ፤ ፈረንሳይ ከሞሮኮ ደግሞ ረቡዕ በተመሳሳይ ሰዓት ይፋለማሉ። አዲስ ታሪክ ይመዘገብ ይሆን?
ሜሲ ወይስ ሞድሪች? ፈረንሳይ አሊያ ሞሮኮ? አዲስ ታሪክ የሚፃፍበት የዓለም ዋንጫ ወደየት ያመራ ይሆን? እንግሊዝ ቅዳሜ ምሽት በፈረንሳይ ተረትታ በበነጋው አውሮፕላን ተሳፍራ ከዶሃ ወጥታለች። አሁን አራት ብሔራዊ ቡድኖች ቀርተዋል - ፈረንሳይ፣ ሞሮኮ፣ ክሮሺያ እና አርጀንቲና። ከአራቱ አንዱ በሚቀጥለው እሑድ ወርቃማውን ዋንጫ ያነሳል። እኚህ አራት ቡድኖች ለግማሽ ፍፃሜ ይደርሳሉ ብሎ የገመተ ጥቂት ነው። አራቱም ብሔራዊ ቡድኖች አዲስ ታሪክ ሊፅፉ ከጫፍ ደርሰዋል። አርጀንቲናዊው ኮከብ በእግር ኳስ ሕይወቱ የመጀመሪያው እና የመጨረሻውን የዓለም ዋንጫ ሊያነሳ ይችላል። ሜሲ ለዋንጫ ብርቅ አይደለም። 10 የስፔን ላሊ ጋ ዋንጫ፣ አራት ጊዜ ቻምፒዮንስ ሊግ፣ አንድ ጊዜ የፈረንሳይ ሊግ እንዲሁም ከአገሩ አርጀንቲና ጋር ኮፓ አሜሪካን አንስቷል። ሜሲ የእግር ኳስ ከዋክብት ጉምቱው ሽልማት የሚባለውን ባሎን ዶር ሰባት ጊዜ በማንሳት ክብረ-ወሰን ጨብጧል። ነገር ግን የ35 ዓመቱን የእግር ኳስ ተዓምረኛ ከማራዶና እና ከፔሌ የሚለየው የዓለም ዋንጫን አለማንሳቱ ነው። አርጀንቲና በዲዬጎ ማራዶና እየተመራች የዓለም ዋንጫ ካነሳች 36 ዓመታት ተቆጥረዋል። ሜሲ ይህን ይደግመው ይሆን? የዓለም ዋንጫ ማንሳቱስ የዘመናችን ድንቁ ተጫዋች የተሰኘውን ስያሜ ያሰጠው ይሆን? ሞሮኮ ከወዲሁ ታሪክ ሰርታ፤ እንዲሁም ጨምራ ሌላ ታሪክ እየፃፈች እዚህ ደርሳለች። ሞሮኮ ከአህጉረ አፍሪካ፣ አልፎም ከአረቡ ዓለም ለግማሽ ፍፃሜው የደረሰች የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። ምንም እንኳ ሞሮኮ እንደ አሽራፍ ሐኪሚ እና ሐኪም ዚዬች ያሉ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች ቢኖሯትም እዚህ ትደርሳለች ብለው የገመቱ ጥቂት ናቸው። ክሮሺያ እና ቤልጂዬም የነበሩበትን ምድብ አልፋ፣ ኃያሏ ስፔንን አስወግዳ፣ ፖርቹጋልን አሰናብታ ነው እዚህ የደረሰችው። የአትላስ አናብስት የጎል መስመራቸውን ሲከላከሉ ያለ እረፍት ነው። በኳታር የዓለም ዋንጫ ማንም የሞሮኮን መረብ አልደፈረም። ከአንድ ጎል በቀር። እሱም በራስ ላይ የተቆጠረ ነው። ሞሮኮ የዓለም ዋንጫ ድምቀት ሆናለች። ደጋፊዎች ስታደየሙን ከጫፍ ጫፍ ሞልተው ያለማቋረጥ ቡድናቸውን ይደግፋሉ። ሞሮኮ ረቡዕ ዕለት አዲስ ታሪክ ትፅፍ ይሆን? ፈረንሳይ የዓለም ዋንጫ በተከታታይ ሁለት ጊዜ ታነሳ ይሆን? አውሮፓዊቷ አገር የዓለም ዋንጫውን በተከታታይ ሁለት ጊዜ እንዳታነሳ ታሪክ ሠሪዋ ሞሮኮ ልታግዳት ትችላለች። 'ሌ ብሉ' በሚለው ቅጽል ስማቸው የሚታወቁት ፈረንሳዮች፣ ከስድሳ ዓመታት በኋላ አዲስ ታሪክ ለመፃፍ ይሞክራሉ። ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ በተከታታይ የዓለም ዋንጫ ያነሳችው ብራዚል ስትሆን፣ ይህ ከሆነ 60 ዓመታት ተቆጥረዋል። ጣልያን፣ ስፔን፣ ጀመርን ባለፉት 12 ዓመታት ዋንጫ አንስተው በሚቀጥለው የዓለም ዋንጫ ውድድሩን በጊዜ የተሳነበቱ አገራት ናቸው። ባለፈው ቅዳሜ እንግሊዝን የረታችው ፈረንሳይ ከብራዚል ቀጥላ ዋንጫ ባነሳች ተከታ የዓለም ዋንጫ ውድድር ለግማሽ ፍፃሜ የበቃች አገር ሆናለች። አሠልጣኝ ዲዲዬ ዴሾ አሁን ትኩረታቸው ሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮ ሆናለች። የ2018 ዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታን ደግመን ልናየው እንችል ይሆናል። ፈረንሳይ ሞሮኮን፤ ክሮሺያ ደግሞ አርጀንቲናን ካሰናበቱ በሩሲያ ያሳዩንን የፍፃሜ ጨዋታ በኳታር ምድር ይደግሙታል። ክሮሺያ በዙር 16 ጃፓንን፤ በሩብ ፍፃሜው ደግሞ ብራዚልን በመርታት ነው ከመጨረሻዎቹ አራት ቡድኖች ተርታ መሰለፍ የቻለችው። ክሮሺያ ለመጨረሻ ጊዜ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ በ90 ደቂቃ ተጫውታ ያለፈችው ከ24 ዓመታት በፊት ጀርመንን በረታች ወቅት ነው። የክሮሺያ አምበል እና የመሃል መስመሩ ሞተር፤ ሉካ ሞድሪች ዕድሜው 37 ደርሷል። ነገር ግን 120 ደቂቃ ተጫውቶ አገሩን ለዚህ አብቅቷል። ባለፈው የዓለም ዋንጫ በምድብ ጨዋታ በክሮሺያ 3 ለምንም የተረታችው አርጀንቲና ለሞድሪች ቡድን ንቀት እንደማታሳይ ይጠበቃል። አርጀንቲና ከክሮሺያ ማክሰኞ ምሽት 4 ሰዓት ይገናኛሉ፤ ፈረንሳይ ከሞሮኮ ደግሞ ረቡዕ በተመሳሳይ ሰዓት ይፋለማሉ። አዲስ ታሪክ ይመዘገብ ይሆን?
https://www.bbc.com/amharic/articles/czq327npyvpo
5sports
ቶኪዮ ኦሎምፒክ፡ የአትሌቲክስ ቡድን አባላት ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጁ ነን አሉ
ከነገ ወዲያ በሚጀመረው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ውድድር ላይ ከዚህ ቀደም ከተመዘገበው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጁ መሆናቸውን አትሌቶች እና አሰልጣኞች ለቢቢሲ ተናገሩ። በጃፓን መዲና የሚካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ የፊታችን ዓርብ ሐምሌ 16 ጀምሮ ነሐሴ 8 ይጠናቀቃል። ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ከአትሌቲክሱ በተጨማሪ በውሃ ዋና፣ በብስክሌት ውድድር እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ በቴኳንዶ ውድድር ትወከላለች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 35 አትሌቶችን ይዞ ወደ ቶኪዮ የሚያመራ ሲሆን አትሌቶች በ7 የተለያዩ ርቀቶች ተወዳዳሪ ሆነው ይቀርባሉ። በኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ቡድን ውስጥ የወቅቱ የ5ሺህ እና 10ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ይዛ የምትገኘው ለተሰንበት ግደይ ትገኝበታለች። በኮቪድ-19 ስርጭት ምክንያት በአንድ ዓመት ዘግይቶ ለሚከናወነው የኦሎምፒክ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ያለፉትን 8 ወራት በሆቴል ቆይተው ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል። የአትሌቲክስ ቡድኑ ዝግጅት ምን ይመስል ነበር? ሕዝቡ ምን አይነት ውጤት ይጠብቅ? ለሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት በዝግጅት ላይ የነበሩ አትሌቶችን ጠይቀናል። ሰለሞን ባረጋ አገሩን ወክሎ በ10ሺህ ሜትር ተወዳዳሪ ሆኖ ይቀርባል። ''ጥሩ ነጥብ እናመጣለን ብዬ አስባለሁ። እስካሁን 5ሺህ ሜትር ስወዳደር ነበር። በ10ሺህ ከእኔ ጋር ከሚወዳደሩት ጋር ተወዳድሬ ባላውቅም አሯሯጣቸውን ግን አውቃለሁ። ባለ ሪከርድ ከሆኑ የኬንያ እና ኡጋንዳ አትሌቶች ጋር ነው የምወዳደረው" በማለት አትሌት ሰለሞን ባረጋ ለቢቢሲ ተናግሯል። የ10ሺህ ሜትር ውድድር ዓርብ ሐምሌ 23 ይካሄዳል። በዚህ ውድድር ከሰለሞን ባረጋ በተጨማሪ ዮሚፍ ቀጄልቻ እና በሪሁ አረጋዊ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ። ባለፉት ሁለት የኦሎምፒክ ውድድሮች ማለትም በሪዮ እና ለንደን ኦሎምፒክ በ5ሺህ እና በ10ሺህ ኦሎምፒክ የወርቅ ተሸላሚው መሐመድ ፋራህ መስፈርት ማሟላት ባለመቻሉ ከመድረኩ ቀርቷል። አትሌት ሹራ ቂጣታ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሎምፒክ ይወዳደራል። አትሌት ሹራ ኢትዮጵያን በማራቶችን የሚወክል ሲሆን፤ "በዚህ ውድድር ለአገርም ለግልም ወርቅ ማምጣት አለብን በሚል ነው እየተዘጋጀን ያለነው" በማለት ይናገራል። ከአንድ ዓመት በፊት በለንደን ማራቶን የኬንያውን ኢሊዩድ ኪፕቼጌን ያሸነፈው ሹራ፤ በቶኪዮ ኦሎምፒክም የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ኪፕቼጌ ጋር ይወዳደራል። ከአትሌት ሹራ ጋር አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ እና ሲሳይ ለማ አገራቸውን ወክለው በማራቶን ይሳተፋሉ። የረዥም ርቀት ዋና አሰልጣኝ ኮማንደር ሁሴን ሺቦ በኦሎምፒክ ውድድር ላይ ተሳታፊ ሲሆኑ የቶኪዮ ኦሎምፒክ 6ኛው ሆኖ ይመዘገባል። "ለአገራችን ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ አትሌቶቻችንም፤ እኛም በአካልም በአእምሮም ዝግጁ ሆነናል" በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል። አሰልጣኝ ሁሴን በ5ሺህ እና 10ሺህ ሜትር ውድድሮች የሚሳተፉ አትሌቶችን ይመራሉ። "አራት ቡድን እመራለሁ። የሴቶች እና የወንዶች 5ሺህ እና 10ሺህ ሜትር ውድድሮችን። 1ኛ እና 2ኛ ደረጃን ለመያዝ አቅደን እየሰራን እንገኛለን" የሚሉት አሰልጣኙ፤ ከዚህ ቀደም ከተመዘገበ ውጤት በቶኪዮ ኦሎምፒክ ውጤት ይመዘገባል ብዬ እገምታለሁ ብለዋል። አሰልጣኝ ሁሴን በዘንድሮ የቶኪዮ ኦሎምፒክ የሚሳተፉት አብዛኛዎቹ አትሌቶች በኦሎምፒክ ውድድር ሲሳተፉ የመጀመሪያቸው እንደሆነ ያስረዳሉ። "ከአጠቃላይ አትሌቶች 98 በመቶ የሚሆኑት ከዚህ ቀደም በኦሎምፒክ ውድድር ተሳትፈው የሚያውቁ ስላልሆኑ በከፍተኛ ተነሳሽነት በውድድሩ ተሳትፈው አመርቂ ውጤት ያስመዘግባሉ የሚል እምነት አለኝ" ብለዋል። አትሌት ደራርቱ ከሰሃራ በረሃ በታች ከሚገኙ አገራት የኦሎምፒክ ወርቅ ያገኘች የመጀመሪያዋ ጥቁር አትሌት ነች። ዘንድሮ ደግሞ ደራርቱ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽንን እየመራች ወደ ቶኪዮ ታቀናለች። "አንዳንድ ችግሮች አይታጡም ግን ዝግጅታችን በጣም ጥሩ ነው። ዓለም ለማሸነፍ ይዘጋጃል። እኛም እንደ አንድ ትልቅ አገር ለማሸነፍ ተዘጋጅተናል" በማለት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሸን ፕሬዝደንት ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለፉት ስምንት ወራት ፌዴሬሽኑ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ ሦስት ውድድሮችን አከናውኖ አትሌቶችን ለመመልመል እድል አግኝቷል። "ፈጣሪ ከረዳን ጥሩ ውጤት እናመጣለን ብለን እናስባለን። እንደ ልባችን እንዳንሰራ የረበሸን ነገር ኮቪድ-19 ወረርሸኝ ነው" ብላለች አትሌት ደራርቱ።
ቶኪዮ ኦሎምፒክ፡ የአትሌቲክስ ቡድን አባላት ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጁ ነን አሉ ከነገ ወዲያ በሚጀመረው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ውድድር ላይ ከዚህ ቀደም ከተመዘገበው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጁ መሆናቸውን አትሌቶች እና አሰልጣኞች ለቢቢሲ ተናገሩ። በጃፓን መዲና የሚካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ የፊታችን ዓርብ ሐምሌ 16 ጀምሮ ነሐሴ 8 ይጠናቀቃል። ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ከአትሌቲክሱ በተጨማሪ በውሃ ዋና፣ በብስክሌት ውድድር እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ በቴኳንዶ ውድድር ትወከላለች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 35 አትሌቶችን ይዞ ወደ ቶኪዮ የሚያመራ ሲሆን አትሌቶች በ7 የተለያዩ ርቀቶች ተወዳዳሪ ሆነው ይቀርባሉ። በኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ቡድን ውስጥ የወቅቱ የ5ሺህ እና 10ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ይዛ የምትገኘው ለተሰንበት ግደይ ትገኝበታለች። በኮቪድ-19 ስርጭት ምክንያት በአንድ ዓመት ዘግይቶ ለሚከናወነው የኦሎምፒክ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ያለፉትን 8 ወራት በሆቴል ቆይተው ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል። የአትሌቲክስ ቡድኑ ዝግጅት ምን ይመስል ነበር? ሕዝቡ ምን አይነት ውጤት ይጠብቅ? ለሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት በዝግጅት ላይ የነበሩ አትሌቶችን ጠይቀናል። ሰለሞን ባረጋ አገሩን ወክሎ በ10ሺህ ሜትር ተወዳዳሪ ሆኖ ይቀርባል። ''ጥሩ ነጥብ እናመጣለን ብዬ አስባለሁ። እስካሁን 5ሺህ ሜትር ስወዳደር ነበር። በ10ሺህ ከእኔ ጋር ከሚወዳደሩት ጋር ተወዳድሬ ባላውቅም አሯሯጣቸውን ግን አውቃለሁ። ባለ ሪከርድ ከሆኑ የኬንያ እና ኡጋንዳ አትሌቶች ጋር ነው የምወዳደረው" በማለት አትሌት ሰለሞን ባረጋ ለቢቢሲ ተናግሯል። የ10ሺህ ሜትር ውድድር ዓርብ ሐምሌ 23 ይካሄዳል። በዚህ ውድድር ከሰለሞን ባረጋ በተጨማሪ ዮሚፍ ቀጄልቻ እና በሪሁ አረጋዊ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ። ባለፉት ሁለት የኦሎምፒክ ውድድሮች ማለትም በሪዮ እና ለንደን ኦሎምፒክ በ5ሺህ እና በ10ሺህ ኦሎምፒክ የወርቅ ተሸላሚው መሐመድ ፋራህ መስፈርት ማሟላት ባለመቻሉ ከመድረኩ ቀርቷል። አትሌት ሹራ ቂጣታ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሎምፒክ ይወዳደራል። አትሌት ሹራ ኢትዮጵያን በማራቶችን የሚወክል ሲሆን፤ "በዚህ ውድድር ለአገርም ለግልም ወርቅ ማምጣት አለብን በሚል ነው እየተዘጋጀን ያለነው" በማለት ይናገራል። ከአንድ ዓመት በፊት በለንደን ማራቶን የኬንያውን ኢሊዩድ ኪፕቼጌን ያሸነፈው ሹራ፤ በቶኪዮ ኦሎምፒክም የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ኪፕቼጌ ጋር ይወዳደራል። ከአትሌት ሹራ ጋር አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ እና ሲሳይ ለማ አገራቸውን ወክለው በማራቶን ይሳተፋሉ። የረዥም ርቀት ዋና አሰልጣኝ ኮማንደር ሁሴን ሺቦ በኦሎምፒክ ውድድር ላይ ተሳታፊ ሲሆኑ የቶኪዮ ኦሎምፒክ 6ኛው ሆኖ ይመዘገባል። "ለአገራችን ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ አትሌቶቻችንም፤ እኛም በአካልም በአእምሮም ዝግጁ ሆነናል" በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል። አሰልጣኝ ሁሴን በ5ሺህ እና 10ሺህ ሜትር ውድድሮች የሚሳተፉ አትሌቶችን ይመራሉ። "አራት ቡድን እመራለሁ። የሴቶች እና የወንዶች 5ሺህ እና 10ሺህ ሜትር ውድድሮችን። 1ኛ እና 2ኛ ደረጃን ለመያዝ አቅደን እየሰራን እንገኛለን" የሚሉት አሰልጣኙ፤ ከዚህ ቀደም ከተመዘገበ ውጤት በቶኪዮ ኦሎምፒክ ውጤት ይመዘገባል ብዬ እገምታለሁ ብለዋል። አሰልጣኝ ሁሴን በዘንድሮ የቶኪዮ ኦሎምፒክ የሚሳተፉት አብዛኛዎቹ አትሌቶች በኦሎምፒክ ውድድር ሲሳተፉ የመጀመሪያቸው እንደሆነ ያስረዳሉ። "ከአጠቃላይ አትሌቶች 98 በመቶ የሚሆኑት ከዚህ ቀደም በኦሎምፒክ ውድድር ተሳትፈው የሚያውቁ ስላልሆኑ በከፍተኛ ተነሳሽነት በውድድሩ ተሳትፈው አመርቂ ውጤት ያስመዘግባሉ የሚል እምነት አለኝ" ብለዋል። አትሌት ደራርቱ ከሰሃራ በረሃ በታች ከሚገኙ አገራት የኦሎምፒክ ወርቅ ያገኘች የመጀመሪያዋ ጥቁር አትሌት ነች። ዘንድሮ ደግሞ ደራርቱ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽንን እየመራች ወደ ቶኪዮ ታቀናለች። "አንዳንድ ችግሮች አይታጡም ግን ዝግጅታችን በጣም ጥሩ ነው። ዓለም ለማሸነፍ ይዘጋጃል። እኛም እንደ አንድ ትልቅ አገር ለማሸነፍ ተዘጋጅተናል" በማለት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሸን ፕሬዝደንት ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለፉት ስምንት ወራት ፌዴሬሽኑ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ ሦስት ውድድሮችን አከናውኖ አትሌቶችን ለመመልመል እድል አግኝቷል። "ፈጣሪ ከረዳን ጥሩ ውጤት እናመጣለን ብለን እናስባለን። እንደ ልባችን እንዳንሰራ የረበሸን ነገር ኮቪድ-19 ወረርሸኝ ነው" ብላለች አትሌት ደራርቱ።
https://www.bbc.com/amharic/news-57904032
2health
ዜና ማየት ቢቀርብንስ? ሌላው ቢቀር ለአእምሯችን ጤና ስንል!
እኛ ራሳችን ዜና አቅራቢ ሆነን ይህን ማለታችን ወለፈንዲ ሊሆን ይችላል። ትዝብት ላይ ሊጥለንም ይችላል። ያም ሆኖ ግን ነገሩ አሳሳቢ ነው። ቀኑን ሙሉ የዜና ቆሎ መቆርጠም ቢቀርብንስ? ሌላው ቢቀር ለአእምሯችን ጤና ስንል። መረጃ ትንፋሽ አሳጣን እኮ፡፡ የመረጃ ሱናሚ ጠራርጎ ወሰደን እኮ… በኮቪድ ዘመን ደግሞ ቤት ተዘግቶ መዋል የዜና ሸመታችንን ሰማይ አድርሶታል፡፡ በብዙ ዓለም ይህ ነገር እውነት ነው፡፡ እስኪ አስቡት… እጃችሁ ላይ የቲቪ ትዕይንት መዘርዝር መዘወርያ አለ እንበል፡፡ ሪሞት! ሌላኛው እጃችሁ ላይ ደግሞ ስልካችሁ ይኖራል፤ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ በዚህ ዘመን ከስልካችን ከራቅን ጭንቅ ነው የሚሆንብን፡፡ ምናልባትም ይህን ጽሑፍ በስልካችሁ እያነበባችሁት ይሆናል፡፡ ከንባብ የሚያናጥቡ ተከታታይ መልእክቶች እየደረሷችሁም ይሆናል፡፡ በፌስቡክ…በቴሌግራም…በዋትስአፕ…በትዊተር… በዚያ ላይ ‹ይቺን አንብባትማ በሞቴ!› የሚለው ሰው ብዛቱ… "ጉርሻ ይመስል!" ለምን እንደሆነ ባይታወቅም ሁሉም ሰው የያዘውን ንባብ እንኳ ሳይጨርስ የማጋራት ሱስ አለበት፡፡ አንዳንዱ አጭሬ የቧልት ቪዲዮ ዓይቶ፣ ስቆ እንኳ ሳይጨርስ አጋርቶ ይጨርሳል፡፡ ጊዜ የለም፡፡ የመረጃ ግሽበት አለ፡፡ ስለዚህ ወደሚቀጥለው፡፡ ሳቅን ለማጣጣም ቀርቶ ፈገግታን ለመጨረስ የሚሆን ጊዜ የለም፡፡ እጃችሁ ላይ የቲቪ 'ሪሞት' አለ ብለናል፡፡ ሲኤንኤን፣ አልጀዚራ፣ ቢቢሲ ሰበር ዜና እየላኩ የአእምሮ ጫና ይፈጥራሉ፡፡ ፈነዳ፣ አፈነዳ፣ ፈነዱ….ገደለ፣ ገደሉ…ተገደለ፣ አስገደለ፣ ሞቱ፣ ቆሰሉ…አቆሰለ…ቆሰለ፡፡ ጂኒ ጃንካ ቅብርጥሶ… ሪሞቱን ይዛችሁታል ብለናል….፡፡ እንዳትለቁት፡፡ ዓለምን በቲቪ መስኮት እየሾፈራችኋት ነው፡፡ በቲቪ የትእይንቶች መዘርዝር ውስጥ 300 ቻናሎች አሉ፡፡ 300 ምርጫዎች አሏችሁ ማለት ነው፡፡ የትኛውን ማየት ይሻላል? ይህ የምርጫ መብዛት ራሱ ለአእምሮ ጤና መልካም አይደለም፡፡ ከቲቪ መዘርዝሩ ጎን የራዲዮ መዘርዝር አለ፡፡ ከሱ ጎን ላፕቶፕ አለ፡፡ ላፕቶፑ ውስጥ እልፍ ፊልሞች አሉበት፡፡ በዚህ ላይ ከጎረቤት የሆነ ራዲዮ ጣቢያው ላንቃው እስኪሰነጠቅ ይጮኻል፡፡ ከወዲያ በኩል ሼልፍ ላይ ያላነበቧችኋቸው መጻሕፍት እያዛጉ ነው፡፡ ዓለም ትጨንቃለች፡፡ መረጃ ይንዠቀዠቃል፡፡ ሰቆቃ…ዜና…ሰቆቃ…መረጃ…ገደሉ፣ ተገደለ፣ ቆሰሉ አቆሰለ፡፡ ጂኒ ጃንካ ቁልቋል…. በዚሁ ሁሉ መሀል ሌላ መልእክት ይመጣል፡፡ ከወዳጅ፣ ከቴሌ፣ ከቴሌግራም ጉጅሌ፣ ከፌስቡክ ክበብ… መረጃውን እንቀበላለን፤ እንጎርሳለን፡፡ ደግሞ መረጃውን አላምጠን አይደለም የምንጎርሰው፡፡ ምኑ ይላመጥና፡፡ ማስቲካ…ይላመጣል? ይዋጣል? መረጃ ማስቲካ ላንቲካ ሆኗል፡፡ ማመንዠግ ነው እንጂ ሌላ አማራጭ የለም፡፡ ዝምብሎ ማቀበል ነው፣ የሰማው ላልሰማው፡፡ የሰማው ለሰማው፡፡ ወዘተ፡፡ ወዘተ ራሱ ድሮ አጭር ቃል ነበር፡፡ አሁን ወዘተ ረዥም ቃል ሆኗል፡፡ መረጃ ያታክታል፡፡ የዚህ ጽሑፍ እንደ አንጀት መርዘም ራሱ አታካች ነው፡፡ ለምን እዚህ ጋ አናቆመውም፡፡ ምክንያቱም ጸሐፊው ተስፋ ያደርጋላ…ጠቃሚ መረጃ እያቀበለ እንደሆነ ይሰማዋላ፡፡ ስለዚህ አያቆምም ይቀጥላል፡፡ ማንም ደንታው ባይሆንም ይቀጥላል፡፡ ለመረጃ ግሽበት የራሱን አስተዋጽኦ ማድረግ አለበት፡፡ በዓይንና ጆሮ የምንሸምተው ዜና ካሎሪ ቢሆን እኮ አለመጠን ወፍረን ፈንድተናል፣ ይሄኔ፡፡ ስኳር፣ ጨጓራ፣ ደም ብዛት፣ ደም ግፊት ነበረብን እኮ ይሄኔ፡፡ ሽንታችን ቀለሙ ቢጫ፣ ሽታው ዜና ዜና የሚል ይሆን ነበር ይሄኔ፡፡ ደግነቱ ዜና ካሎሪ የለውም፡፡ ካሎሪ የለውም ማለት ግን ጭንቅላታችን ላይ አይወጣም ማለት ነው እንዴ? አይደለም፡፡ ልክ እንደ ቢጫ ወባ ዘሎ ጭንቅላታችን ላይ ይወጣል፡፡ ይህን የምንረዳው ግን ዘግይተን ነው፡፡ ፓሮል ጎሽ የ32 ዓመት ወጣት ናት፡፡ በዜና ጎርፍ ተወሰደች፡፡ እንደ ቀልድ ሪሞቱን ታነሳዋለች፡፡ አንዱ ዜና ለሌላው ሲያቀብላት፣ ሌላው ለሌላ ሲያሻግራት እንዲሁ እንደ ቅሪላ እየተለጋች ቀኑ መሽቶ ይነጋል፣ ነግቶ ይመሻል፡፡ ‹‹ወንድ ልጅ ቆረጠ፣ ሴት ልጅ ወሰነች›› አልኩ በሆዴ ትላለች ፓሮል፣ የሆነ ቀን፡፡ ፓሮል ቤተሰቦቿ ሕንድ ናቸው፡፡ እሷ ስዊድን ነው የምትኖረው፡፡ ስዊድን ነው የምኖረው ትበል እንጂ እውነተኛ ሕይወቷ ቲቪ ውስጥ ነው፤ ኢንተርኔት ውስጥ ነው፡፡ ስለ ሕንድ አንዱን ዜና ጀምራ ሌላውን ስትገልጥ በሕንድ የወጣች ፀሐይ በስዊድን ትጠልቃለች፡፡ ይህ ሁልጊዜ የሚሆን ነው፡፡ በቀን በቀን፡፡ በመጨረሻ ካሮል ጭንቅላቷ መደንዘዝ ጀመረ፡፡ ‹‹ሕንድ እየሆነ ያለው ነገር ቤተሰቤን የሚጨርስ ስለሚመስለኝ ለተደጋጋሚ ጭንቀት ተዳረኩ›› ብላለች ካሮል፣ ለቢቢሲ፡፡ ክሪስ ክላንሲ ደግሞ አለ፡፡ 33 ዓመቱ ነው፡፡ በአውስትራሊያ፣ ቪክቶሪያ ነው የሚኖረው፡፡ የርሱ ሱስ ጫት አይደለም፡፡ ዜና ነው፡፡ ዜና-ሱስ የሚባል ነገር ታሟል፡፡ ዜና ማየት ብቻ አይደለም ችግሩ፡፡ የዓለም ጋዜጠኞችን ልቅም አድርጎ ይከተላል፡፡ በትዊተር፣ በፌስቡክ እግር በእግር ይከተላቸዋል፡፡ አንዲት ቅንጣት ዜና አታልፈውም፡፡ ከዜና በፊት ዜና ያገኛል፡፡ በቀኑ መጨረሻ ግን ይደነዝዛል፡፡ ይታክታል፡፡ ለካንስ ሳያስበው ዓለም ላይ የተፈጠረ ክፉ ነገሮችን በሙሉ በዐይኑ በኩል ሲጠጣቸው ነው የዋለው፡፡ ልክ ማታ ላይ ጭንቅላቱን ሲወቅረው ነው ይህን የሚረዳው፡፡ ቲቪውንና ስልኩን ሲዘጋ ነው የሚታወቀው፡፡ ወደ መኝታው ሲሄድ ሕልሙ ዜና በዜና፡፡ ሽብር በሽብር፡፡ ደግሞ አያስችለውም፣ ጠዋት መልሶ ይከፍተዋል፡፡ ዜናው ደግሞ አይቀየርም፡፡ መልሶ መላልሶ ያው ጉዳይ ይታኘካል፣ ይመነዠጋል፡፡ ማስቲካ ላንቲካ፡፡ ‹‹ለጤናዬ ሰጋሁ፤ እየታመምኩ መጣሁ፤ እርምጃ ወሰድኩ፡፡ ዜና በሳምንት አንድ ጊዜ ብቻ ማየት ጀመርኩ፡፡›› ይላል ክሪስ ጤናው እንዴት እንደተመለሰለት ሲናገር፡፡ ጎሽ እና ክሪስ ብቻቸውን አይደሉም ይላል ስታትስቲክስ፡፡ ሚሊዮኖች እንደነሱ እየተሰቃዩ ነው፡፡ ምናልባትም ቢሊዮኖች፡፡ ምንም እንኳ በዚህ ክፉ የወረርሽኝ ዘመን ቤት ተዘግቶ መዋል የቲቪ ተጠቃሚዎችን ቁጥር እንዲያሻቅብ ቢያደርግም፤ በብዙ አገራት ግን የዜና ግሽበት ተከስቷል፡፡ ለምሳሌ በዩናይትድ ኪንግደም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በከፍተኛ ሁኔታ የተመልካቾቻቸው ቁጥር ቀንሷል፡፡ በአውስራሊያ ደግሞ ከዜና ቻናሎች ይልቅ መዝናኛዎች የተሻለ ተመልካች ቁጥር አስመዝግበዋል፡፡ ፒው የሪሰርች ሴንተር በሰራው አንድ ጥናት ደግሞ በርካታ ሰዎች ስለ ኮሮና ዜና በጭራሽ መስማት አይፈልጉም፡፡ ለምን? አታክቷቸዋላ፡፡ ለምሳሌ በአሜሪካ ከ10 ሰዎች ሰባቱ ስለ ኮሮና ምንም ዓይነት ዜና መስማት ጠላን ብለዋል፡፡ የአእምሮ ጤና አዋቂዎች ሁለት ነገር ያነሳሉ፡፡ አንዱ የበዛ መረጃ ወደ ታዳሚዎች እየተወነጨፈ የሰዎችን አእምሮ ቀስ በቀስ እየበጠበጠ መሆኑን፡፡ ሁለተኛው ዜና ምን ያህል እንደሚጎዳን አለመገንዘባችን፡፡ ለምሳሌ ስለ ኮሮና ቢጠራቀም አንድ ሜጋ ባይት የሚወጣው ዜና በቀን በቀን ሰምተን ይሆናል፡፡ ግንዛቢያችን ግን በአንድ ኪሎ ባይት እንኳ ጨምሯል? አልጨመረም፡፡ እንደ መረጃው ብዛቱ የመረጃ ጥራት አለን ማለት አይደለም፡፡ የሚመስለን ግን ብዙ በሰማን፣ ባየን፣ ባነበብን ቁጥር ብዙ ማወቃችን ነው፡፡ ለምሳሌ የኮሮና ዜና ዕለታዊ ቢሆንም የሰዎች በበሽታው ላይ ያላቸው ግንዛቤ ግን ተቀራራቢ ነው፡፡ ብዙ ዜና በመስማታቸው ከበሽታው የተፈወሱ የሉም፡፡ ብዙ የዜና እንጀራ በመመገባቸው የተህዋሲውን ክትባት ያገኙ የሉም፡፡ ዛሬ በዚህ አገር እንዲህ ያህል ሰዎች ተያዙ፣ ተመረዙ የሚል ዜና እየወቀረን ስንውል ግን አእምሯችን ላይ ጉዳት እያደረስን ነው፤ እንወቀውም አንወቀውም፡፡ ለምሳሌ ሰዎች ጭምብል ማጥለቅ አለባቸው ተብሏል፣ 2 ሜትር መራራቅ አለባቸው ተብሏል፤ እጃቸውን መታጠብ አለባቸው ተብሏል፡፡ ይህንኑ መረጃ በተለያየ መንገድ ለመቶ ሺ ጊዜ መስማት ትርፉ ምንድነው? ጆን ፖል ዴቪስ ሳይኮቴራፒስት ናቸው፡፡ ደንበኞቻቸው በመረጃ ሱናሚ ምክንያት ብቻ ለድብታ እና ለጭንቀት እንደተዳረጉ ደርሰውበታል፡፡ ጆን ፖል እንደሚሉት ከሆነ በሌላ የዓለም ጥግ የደረሰ አደጋ በዜና መልክ አእምሯችን ከቀሰመው በኋላ የዘነጋነው ይመስለናል፡፡ አእምሮ ግን ውስብስብ ነው፡፡ ባይታወቀንም የሰማነው መጥፎ ዜና ቀናችንን ያገረጣዋል፡፡ በፌስቡክ ሸርተቴ ሲንሸራተቱ፣ በመረጃ ሲንከላወሱ የሚውሉ ሰዎች አሉታዊነት እንደሚያጠቃቸው ብዙ ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡ እነሱ የድብታ መጫወቻዎች ነው የሚሆኑት፡፡ ዱካክ ከነ ሠራዊቱ እላያቸው ላይ ይሰፍራል፡፡ ሰዎች ነን፤ የመረጃ ዘመን ላይ ነን፡፡ ያለ መረጃ መኖር አንችል ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መረጃ የአእምሮ ጤናን ያውካል እየተባልን ነው፡፡ ስለዚህ ምን ተሻለ? ፕሮፌሰር ዴቪስ የአእምሮ ጤና ተመራማሪ ናቸው፡፡ በቀን አንድ ጊዜ ዋና ዋና ዜናዎችን አለፍ አለፍ እያሉ ማየት በቂ ነው ይላሉ፡፡ በዜና ሱስ ለሚሰቃዩ ሰዎች ግን ሚዲያ ቅኝት በሳምንት አንድ ጊዜ በቂ ነው ብለዋል፡፡ ፕሮፌሰር ዴቪስ ሌላው ምክራቸው ዜናን ብቻ ሳይሆን ዜና ጣቢያን ማጋበስ አደገኛ እንደሆነ ነው፡፡ የዜና ምንጫችን ከሚታመኑ አንድ ወይም ሁለት ሚዲያዎች ብቻ ብናደርግ ለአእምሯችን ውለታ ዋልንለት ማለት ነው፡፡ ሚዲያዎች ሁሉ መጥፎ አይደሉም፤ ሁሉም ደግሞ ለጤናዎ በጎ አይደሉም፡፡ በረብ የለሽ የመረጃ ጥይት የማያቆስልዎትን ሚዲያዎች መምረጥ የርስዎ ፋንታ ነው፡፡ አሰስ ገሰሱን የሚያቀርብልዎት ማኅበራዊ ሚዲያ ለአእምሮ መቃወስ ሊዳርግ ይችላል፡፡ ፕሮፌሰር ጆን ፖል ዴቪስ ለሁሉም ነገር ድንበር ማበጀት እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ያሰምሩበታል፡፡ ለምሳሌ በቀን ውስጥ ጠዋት ወይም ምሳ ሰዓት ላይ አንድ ጊዜ ብቻ ለ15 ደቂቃዎች መረጃ ቃርመን ከዚያ ግን በምንም መልኩ አለመመለስ፡፡ ይህ ግን ይቻላል? እንደሚባለው ቀላል ነው? በዲጂታል ዓለም ችግሩ የሚጀምረው የመጀመርያዋን ዜና ከማየቱ ላይ ነው፡፡ ከዚያማ እያሳሳቀ ይወስደናል፡፡ በመጨረሻ የጥፋተኝነት ስሜቱ አእምሯችን ይቀውራል፡፡ ምናልባት ራስን በጊዜ የሽቦ አጥር ማጠር አስፈላጊ የሚሆነው ለዚህ ነው፡፡ ስልክን አንድ ጊዜ አይቼ እዘጋዋለሁ ብለው የሚከፍቱ የዋሆች ናቸው፡፡ በመረጃ ሱናሚ ተጥረግርገው የማይወሰዱት ስንቶቹ ናቸው? ፓራል ጎሽ ሰዎችን በሰዓት ገድቦ መረጃን መቆጣጠር እንደሚችሉ መንገር ቀልድ ነው ትላለች፡፡ እሷ ሞክራው አልተሳካላትም፡፡ ለእሷ መፍትሄ የሆነላት መረጃን ከሰዎች አፍ መቀበልን ነው፡፡ ለሻይ ከሰዎች ጋ ስትገናኝ ሰዎች ያወሩላታል፡፡ መረጃ ከአፍ አፋቸው ትቀልባለች፡፡ ከዚያ ውጭ ያለው መንገድ አልሰራላትም፡፡ አንድ ጊዜ ወደ ስልኬ ከገባሁማ መውጫ የለኝም ትላለች፡፡ የሷ ታሪክ የሚሊዮኖች ታሪክ ነው፡፡ ‹‹አሁን ነጻ ወጥቻለሁ፤ በዕለታዊ ቅራቅንቦ ዜና አልታለልም፤ ልቦለድ ማንበብ ነው የምወደው፤ ለሱ ጊዜ በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ ትላለች፡፡›› ይስመርላት!
ዜና ማየት ቢቀርብንስ? ሌላው ቢቀር ለአእምሯችን ጤና ስንል! እኛ ራሳችን ዜና አቅራቢ ሆነን ይህን ማለታችን ወለፈንዲ ሊሆን ይችላል። ትዝብት ላይ ሊጥለንም ይችላል። ያም ሆኖ ግን ነገሩ አሳሳቢ ነው። ቀኑን ሙሉ የዜና ቆሎ መቆርጠም ቢቀርብንስ? ሌላው ቢቀር ለአእምሯችን ጤና ስንል። መረጃ ትንፋሽ አሳጣን እኮ፡፡ የመረጃ ሱናሚ ጠራርጎ ወሰደን እኮ… በኮቪድ ዘመን ደግሞ ቤት ተዘግቶ መዋል የዜና ሸመታችንን ሰማይ አድርሶታል፡፡ በብዙ ዓለም ይህ ነገር እውነት ነው፡፡ እስኪ አስቡት… እጃችሁ ላይ የቲቪ ትዕይንት መዘርዝር መዘወርያ አለ እንበል፡፡ ሪሞት! ሌላኛው እጃችሁ ላይ ደግሞ ስልካችሁ ይኖራል፤ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ በዚህ ዘመን ከስልካችን ከራቅን ጭንቅ ነው የሚሆንብን፡፡ ምናልባትም ይህን ጽሑፍ በስልካችሁ እያነበባችሁት ይሆናል፡፡ ከንባብ የሚያናጥቡ ተከታታይ መልእክቶች እየደረሷችሁም ይሆናል፡፡ በፌስቡክ…በቴሌግራም…በዋትስአፕ…በትዊተር… በዚያ ላይ ‹ይቺን አንብባትማ በሞቴ!› የሚለው ሰው ብዛቱ… "ጉርሻ ይመስል!" ለምን እንደሆነ ባይታወቅም ሁሉም ሰው የያዘውን ንባብ እንኳ ሳይጨርስ የማጋራት ሱስ አለበት፡፡ አንዳንዱ አጭሬ የቧልት ቪዲዮ ዓይቶ፣ ስቆ እንኳ ሳይጨርስ አጋርቶ ይጨርሳል፡፡ ጊዜ የለም፡፡ የመረጃ ግሽበት አለ፡፡ ስለዚህ ወደሚቀጥለው፡፡ ሳቅን ለማጣጣም ቀርቶ ፈገግታን ለመጨረስ የሚሆን ጊዜ የለም፡፡ እጃችሁ ላይ የቲቪ 'ሪሞት' አለ ብለናል፡፡ ሲኤንኤን፣ አልጀዚራ፣ ቢቢሲ ሰበር ዜና እየላኩ የአእምሮ ጫና ይፈጥራሉ፡፡ ፈነዳ፣ አፈነዳ፣ ፈነዱ….ገደለ፣ ገደሉ…ተገደለ፣ አስገደለ፣ ሞቱ፣ ቆሰሉ…አቆሰለ…ቆሰለ፡፡ ጂኒ ጃንካ ቅብርጥሶ… ሪሞቱን ይዛችሁታል ብለናል….፡፡ እንዳትለቁት፡፡ ዓለምን በቲቪ መስኮት እየሾፈራችኋት ነው፡፡ በቲቪ የትእይንቶች መዘርዝር ውስጥ 300 ቻናሎች አሉ፡፡ 300 ምርጫዎች አሏችሁ ማለት ነው፡፡ የትኛውን ማየት ይሻላል? ይህ የምርጫ መብዛት ራሱ ለአእምሮ ጤና መልካም አይደለም፡፡ ከቲቪ መዘርዝሩ ጎን የራዲዮ መዘርዝር አለ፡፡ ከሱ ጎን ላፕቶፕ አለ፡፡ ላፕቶፑ ውስጥ እልፍ ፊልሞች አሉበት፡፡ በዚህ ላይ ከጎረቤት የሆነ ራዲዮ ጣቢያው ላንቃው እስኪሰነጠቅ ይጮኻል፡፡ ከወዲያ በኩል ሼልፍ ላይ ያላነበቧችኋቸው መጻሕፍት እያዛጉ ነው፡፡ ዓለም ትጨንቃለች፡፡ መረጃ ይንዠቀዠቃል፡፡ ሰቆቃ…ዜና…ሰቆቃ…መረጃ…ገደሉ፣ ተገደለ፣ ቆሰሉ አቆሰለ፡፡ ጂኒ ጃንካ ቁልቋል…. በዚሁ ሁሉ መሀል ሌላ መልእክት ይመጣል፡፡ ከወዳጅ፣ ከቴሌ፣ ከቴሌግራም ጉጅሌ፣ ከፌስቡክ ክበብ… መረጃውን እንቀበላለን፤ እንጎርሳለን፡፡ ደግሞ መረጃውን አላምጠን አይደለም የምንጎርሰው፡፡ ምኑ ይላመጥና፡፡ ማስቲካ…ይላመጣል? ይዋጣል? መረጃ ማስቲካ ላንቲካ ሆኗል፡፡ ማመንዠግ ነው እንጂ ሌላ አማራጭ የለም፡፡ ዝምብሎ ማቀበል ነው፣ የሰማው ላልሰማው፡፡ የሰማው ለሰማው፡፡ ወዘተ፡፡ ወዘተ ራሱ ድሮ አጭር ቃል ነበር፡፡ አሁን ወዘተ ረዥም ቃል ሆኗል፡፡ መረጃ ያታክታል፡፡ የዚህ ጽሑፍ እንደ አንጀት መርዘም ራሱ አታካች ነው፡፡ ለምን እዚህ ጋ አናቆመውም፡፡ ምክንያቱም ጸሐፊው ተስፋ ያደርጋላ…ጠቃሚ መረጃ እያቀበለ እንደሆነ ይሰማዋላ፡፡ ስለዚህ አያቆምም ይቀጥላል፡፡ ማንም ደንታው ባይሆንም ይቀጥላል፡፡ ለመረጃ ግሽበት የራሱን አስተዋጽኦ ማድረግ አለበት፡፡ በዓይንና ጆሮ የምንሸምተው ዜና ካሎሪ ቢሆን እኮ አለመጠን ወፍረን ፈንድተናል፣ ይሄኔ፡፡ ስኳር፣ ጨጓራ፣ ደም ብዛት፣ ደም ግፊት ነበረብን እኮ ይሄኔ፡፡ ሽንታችን ቀለሙ ቢጫ፣ ሽታው ዜና ዜና የሚል ይሆን ነበር ይሄኔ፡፡ ደግነቱ ዜና ካሎሪ የለውም፡፡ ካሎሪ የለውም ማለት ግን ጭንቅላታችን ላይ አይወጣም ማለት ነው እንዴ? አይደለም፡፡ ልክ እንደ ቢጫ ወባ ዘሎ ጭንቅላታችን ላይ ይወጣል፡፡ ይህን የምንረዳው ግን ዘግይተን ነው፡፡ ፓሮል ጎሽ የ32 ዓመት ወጣት ናት፡፡ በዜና ጎርፍ ተወሰደች፡፡ እንደ ቀልድ ሪሞቱን ታነሳዋለች፡፡ አንዱ ዜና ለሌላው ሲያቀብላት፣ ሌላው ለሌላ ሲያሻግራት እንዲሁ እንደ ቅሪላ እየተለጋች ቀኑ መሽቶ ይነጋል፣ ነግቶ ይመሻል፡፡ ‹‹ወንድ ልጅ ቆረጠ፣ ሴት ልጅ ወሰነች›› አልኩ በሆዴ ትላለች ፓሮል፣ የሆነ ቀን፡፡ ፓሮል ቤተሰቦቿ ሕንድ ናቸው፡፡ እሷ ስዊድን ነው የምትኖረው፡፡ ስዊድን ነው የምኖረው ትበል እንጂ እውነተኛ ሕይወቷ ቲቪ ውስጥ ነው፤ ኢንተርኔት ውስጥ ነው፡፡ ስለ ሕንድ አንዱን ዜና ጀምራ ሌላውን ስትገልጥ በሕንድ የወጣች ፀሐይ በስዊድን ትጠልቃለች፡፡ ይህ ሁልጊዜ የሚሆን ነው፡፡ በቀን በቀን፡፡ በመጨረሻ ካሮል ጭንቅላቷ መደንዘዝ ጀመረ፡፡ ‹‹ሕንድ እየሆነ ያለው ነገር ቤተሰቤን የሚጨርስ ስለሚመስለኝ ለተደጋጋሚ ጭንቀት ተዳረኩ›› ብላለች ካሮል፣ ለቢቢሲ፡፡ ክሪስ ክላንሲ ደግሞ አለ፡፡ 33 ዓመቱ ነው፡፡ በአውስትራሊያ፣ ቪክቶሪያ ነው የሚኖረው፡፡ የርሱ ሱስ ጫት አይደለም፡፡ ዜና ነው፡፡ ዜና-ሱስ የሚባል ነገር ታሟል፡፡ ዜና ማየት ብቻ አይደለም ችግሩ፡፡ የዓለም ጋዜጠኞችን ልቅም አድርጎ ይከተላል፡፡ በትዊተር፣ በፌስቡክ እግር በእግር ይከተላቸዋል፡፡ አንዲት ቅንጣት ዜና አታልፈውም፡፡ ከዜና በፊት ዜና ያገኛል፡፡ በቀኑ መጨረሻ ግን ይደነዝዛል፡፡ ይታክታል፡፡ ለካንስ ሳያስበው ዓለም ላይ የተፈጠረ ክፉ ነገሮችን በሙሉ በዐይኑ በኩል ሲጠጣቸው ነው የዋለው፡፡ ልክ ማታ ላይ ጭንቅላቱን ሲወቅረው ነው ይህን የሚረዳው፡፡ ቲቪውንና ስልኩን ሲዘጋ ነው የሚታወቀው፡፡ ወደ መኝታው ሲሄድ ሕልሙ ዜና በዜና፡፡ ሽብር በሽብር፡፡ ደግሞ አያስችለውም፣ ጠዋት መልሶ ይከፍተዋል፡፡ ዜናው ደግሞ አይቀየርም፡፡ መልሶ መላልሶ ያው ጉዳይ ይታኘካል፣ ይመነዠጋል፡፡ ማስቲካ ላንቲካ፡፡ ‹‹ለጤናዬ ሰጋሁ፤ እየታመምኩ መጣሁ፤ እርምጃ ወሰድኩ፡፡ ዜና በሳምንት አንድ ጊዜ ብቻ ማየት ጀመርኩ፡፡›› ይላል ክሪስ ጤናው እንዴት እንደተመለሰለት ሲናገር፡፡ ጎሽ እና ክሪስ ብቻቸውን አይደሉም ይላል ስታትስቲክስ፡፡ ሚሊዮኖች እንደነሱ እየተሰቃዩ ነው፡፡ ምናልባትም ቢሊዮኖች፡፡ ምንም እንኳ በዚህ ክፉ የወረርሽኝ ዘመን ቤት ተዘግቶ መዋል የቲቪ ተጠቃሚዎችን ቁጥር እንዲያሻቅብ ቢያደርግም፤ በብዙ አገራት ግን የዜና ግሽበት ተከስቷል፡፡ ለምሳሌ በዩናይትድ ኪንግደም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በከፍተኛ ሁኔታ የተመልካቾቻቸው ቁጥር ቀንሷል፡፡ በአውስራሊያ ደግሞ ከዜና ቻናሎች ይልቅ መዝናኛዎች የተሻለ ተመልካች ቁጥር አስመዝግበዋል፡፡ ፒው የሪሰርች ሴንተር በሰራው አንድ ጥናት ደግሞ በርካታ ሰዎች ስለ ኮሮና ዜና በጭራሽ መስማት አይፈልጉም፡፡ ለምን? አታክቷቸዋላ፡፡ ለምሳሌ በአሜሪካ ከ10 ሰዎች ሰባቱ ስለ ኮሮና ምንም ዓይነት ዜና መስማት ጠላን ብለዋል፡፡ የአእምሮ ጤና አዋቂዎች ሁለት ነገር ያነሳሉ፡፡ አንዱ የበዛ መረጃ ወደ ታዳሚዎች እየተወነጨፈ የሰዎችን አእምሮ ቀስ በቀስ እየበጠበጠ መሆኑን፡፡ ሁለተኛው ዜና ምን ያህል እንደሚጎዳን አለመገንዘባችን፡፡ ለምሳሌ ስለ ኮሮና ቢጠራቀም አንድ ሜጋ ባይት የሚወጣው ዜና በቀን በቀን ሰምተን ይሆናል፡፡ ግንዛቢያችን ግን በአንድ ኪሎ ባይት እንኳ ጨምሯል? አልጨመረም፡፡ እንደ መረጃው ብዛቱ የመረጃ ጥራት አለን ማለት አይደለም፡፡ የሚመስለን ግን ብዙ በሰማን፣ ባየን፣ ባነበብን ቁጥር ብዙ ማወቃችን ነው፡፡ ለምሳሌ የኮሮና ዜና ዕለታዊ ቢሆንም የሰዎች በበሽታው ላይ ያላቸው ግንዛቤ ግን ተቀራራቢ ነው፡፡ ብዙ ዜና በመስማታቸው ከበሽታው የተፈወሱ የሉም፡፡ ብዙ የዜና እንጀራ በመመገባቸው የተህዋሲውን ክትባት ያገኙ የሉም፡፡ ዛሬ በዚህ አገር እንዲህ ያህል ሰዎች ተያዙ፣ ተመረዙ የሚል ዜና እየወቀረን ስንውል ግን አእምሯችን ላይ ጉዳት እያደረስን ነው፤ እንወቀውም አንወቀውም፡፡ ለምሳሌ ሰዎች ጭምብል ማጥለቅ አለባቸው ተብሏል፣ 2 ሜትር መራራቅ አለባቸው ተብሏል፤ እጃቸውን መታጠብ አለባቸው ተብሏል፡፡ ይህንኑ መረጃ በተለያየ መንገድ ለመቶ ሺ ጊዜ መስማት ትርፉ ምንድነው? ጆን ፖል ዴቪስ ሳይኮቴራፒስት ናቸው፡፡ ደንበኞቻቸው በመረጃ ሱናሚ ምክንያት ብቻ ለድብታ እና ለጭንቀት እንደተዳረጉ ደርሰውበታል፡፡ ጆን ፖል እንደሚሉት ከሆነ በሌላ የዓለም ጥግ የደረሰ አደጋ በዜና መልክ አእምሯችን ከቀሰመው በኋላ የዘነጋነው ይመስለናል፡፡ አእምሮ ግን ውስብስብ ነው፡፡ ባይታወቀንም የሰማነው መጥፎ ዜና ቀናችንን ያገረጣዋል፡፡ በፌስቡክ ሸርተቴ ሲንሸራተቱ፣ በመረጃ ሲንከላወሱ የሚውሉ ሰዎች አሉታዊነት እንደሚያጠቃቸው ብዙ ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡ እነሱ የድብታ መጫወቻዎች ነው የሚሆኑት፡፡ ዱካክ ከነ ሠራዊቱ እላያቸው ላይ ይሰፍራል፡፡ ሰዎች ነን፤ የመረጃ ዘመን ላይ ነን፡፡ ያለ መረጃ መኖር አንችል ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መረጃ የአእምሮ ጤናን ያውካል እየተባልን ነው፡፡ ስለዚህ ምን ተሻለ? ፕሮፌሰር ዴቪስ የአእምሮ ጤና ተመራማሪ ናቸው፡፡ በቀን አንድ ጊዜ ዋና ዋና ዜናዎችን አለፍ አለፍ እያሉ ማየት በቂ ነው ይላሉ፡፡ በዜና ሱስ ለሚሰቃዩ ሰዎች ግን ሚዲያ ቅኝት በሳምንት አንድ ጊዜ በቂ ነው ብለዋል፡፡ ፕሮፌሰር ዴቪስ ሌላው ምክራቸው ዜናን ብቻ ሳይሆን ዜና ጣቢያን ማጋበስ አደገኛ እንደሆነ ነው፡፡ የዜና ምንጫችን ከሚታመኑ አንድ ወይም ሁለት ሚዲያዎች ብቻ ብናደርግ ለአእምሯችን ውለታ ዋልንለት ማለት ነው፡፡ ሚዲያዎች ሁሉ መጥፎ አይደሉም፤ ሁሉም ደግሞ ለጤናዎ በጎ አይደሉም፡፡ በረብ የለሽ የመረጃ ጥይት የማያቆስልዎትን ሚዲያዎች መምረጥ የርስዎ ፋንታ ነው፡፡ አሰስ ገሰሱን የሚያቀርብልዎት ማኅበራዊ ሚዲያ ለአእምሮ መቃወስ ሊዳርግ ይችላል፡፡ ፕሮፌሰር ጆን ፖል ዴቪስ ለሁሉም ነገር ድንበር ማበጀት እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ያሰምሩበታል፡፡ ለምሳሌ በቀን ውስጥ ጠዋት ወይም ምሳ ሰዓት ላይ አንድ ጊዜ ብቻ ለ15 ደቂቃዎች መረጃ ቃርመን ከዚያ ግን በምንም መልኩ አለመመለስ፡፡ ይህ ግን ይቻላል? እንደሚባለው ቀላል ነው? በዲጂታል ዓለም ችግሩ የሚጀምረው የመጀመርያዋን ዜና ከማየቱ ላይ ነው፡፡ ከዚያማ እያሳሳቀ ይወስደናል፡፡ በመጨረሻ የጥፋተኝነት ስሜቱ አእምሯችን ይቀውራል፡፡ ምናልባት ራስን በጊዜ የሽቦ አጥር ማጠር አስፈላጊ የሚሆነው ለዚህ ነው፡፡ ስልክን አንድ ጊዜ አይቼ እዘጋዋለሁ ብለው የሚከፍቱ የዋሆች ናቸው፡፡ በመረጃ ሱናሚ ተጥረግርገው የማይወሰዱት ስንቶቹ ናቸው? ፓራል ጎሽ ሰዎችን በሰዓት ገድቦ መረጃን መቆጣጠር እንደሚችሉ መንገር ቀልድ ነው ትላለች፡፡ እሷ ሞክራው አልተሳካላትም፡፡ ለእሷ መፍትሄ የሆነላት መረጃን ከሰዎች አፍ መቀበልን ነው፡፡ ለሻይ ከሰዎች ጋ ስትገናኝ ሰዎች ያወሩላታል፡፡ መረጃ ከአፍ አፋቸው ትቀልባለች፡፡ ከዚያ ውጭ ያለው መንገድ አልሰራላትም፡፡ አንድ ጊዜ ወደ ስልኬ ከገባሁማ መውጫ የለኝም ትላለች፡፡ የሷ ታሪክ የሚሊዮኖች ታሪክ ነው፡፡ ‹‹አሁን ነጻ ወጥቻለሁ፤ በዕለታዊ ቅራቅንቦ ዜና አልታለልም፤ ልቦለድ ማንበብ ነው የምወደው፤ ለሱ ጊዜ በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ ትላለች፡፡›› ይስመርላት!
https://www.bbc.com/amharic/news-54179474
3politics
በሙስሊም አሜሪካውያን የምትመራው የአሜሪካ ከተማ
በአሜሪካዋ ሚቺጋን ግዛት በምትገኘው ሐምትራምክ ዋና ጎዳና መረማመድ በዓለም ያሉ ከተሞችን እንደጎበኙ የሚያደርግ ስሜትን ይፈጥራል። ከተማዋን ያደመቁት የፖላንድ የቋሊማ መሸጫ መደብር፣ የምሥራቅ አውሮፓ ዳቦ ቤት፣ የየመን መገበያያ መደብር እና የቤንጋሊ ልብስ ቤት ከተማዋን የበርካታ ሕዝቦችና ባህሎች መናኸሪያ አድርገዋታል። የቤተ ክርስቲያን ደወልና የሙስሊሞች የፀሎት ጥሪ (አዛን) በተመሳሳይ ወቅት ይሰሙባታል። "ዓለምን በሁለት ስኩዌር ማይል" በሚል መፈክሯ የምትታወቀው ሐምትራምክ በአምስት ስኩዌር ኪሎሜትር የቆዳ ስፋቷ ውስጥ ወደ 30 የሚጠጉ ቋንቋዎች የሚነገሩባት በመሆን እውነትም "ትንሿ ዓለም" የሚል ስያሜ አሰጥቷታል። በመካከለኛውም ምዕራብ የምትገኘውና የ28ሺህ ሕዝብ መኖሪያ የሆነችው ይህች ከተማ በዚህ ወር ደግሞ በታሪኳ ለየት ጉዳይ ተሰምቶባታል። በሐምትራምክ ሁሉም አባላት የእስልምና ተከታይ የሆኑበት የከተማ ምክር ቤትና የሙስሊም ከንቲባ መርጣለች። በአሜሪካ ውስጥ የሙስሊሞች አስተዳደር ሲመሰረት ይህ የመጀመሪያ እንደመሆኑ መጠን ታሪካዊ ክስተት ነው ተብሏል። በአንድ ወቅት በከተማይቱ የሚደርስባቸውን መድሎና መገለል ሲታገሉ የነበሩት ሙስሊም ነዋሪዎች የዚህች የብዙ ባህሎች መናኸሪያ ከተማ ዋና አካል ሆነዋል፤ ከሕዝቡም ከግማሽ በላይ የሚሆነውንም ቁጥር ይዘዋል። ምንም እንኳን ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች እና ከፍተኛ የባህል ክርክሮች ቢኖሩም፣ ሐምትራምክ ከተለያዩ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ መሰረቶች የመጡ ነዋሪዎች ተስማምተው አብረው የሚኖሩባት ሆናለች። ይህም በአሜሪካ ውስጥ እየጨመረ ለመጣው ብዝኃነት የወደፊት ዕጣ ፈንታ ትርጉም ያለው የጥናት መነሻም ልትሆን እንደምትችል ተነግሯል። ሆኖም በሐምትራምክ ያለው ታሪካዊ ክስተት በሌሎች የሚደገም ወይስ የተለየ ሆኖ የሚቀር የሚል ጥያቄም እያጫረ ነው። በበርካታ የጀርመን ሰፋሪዎች ጥንታዊ ታሪኳ የሚጀምረው የሐምትራምክ ከተማ በአሁኑ ወቅት ደግሞ በርካታ ሙስሊሞች የሚኖሩባት ስትሆን ይህ ከጥንት እስካሁን ያለው ገፅታዋም በጎዳናዎቿ ባሉ ኪነ ጥበቦች በግልፅ ይንጸባረቃል። መደብሮቿ በአረብኛና በቤንጋሊ ቋንቋዎች በተጻፉ ስሞች ያጌጡ ሲሆን፣ የባንግላዴሽ ባለ ጥልፍ አልባሳት፣ ከየመን የመጣው አጭር ጥምዝ ቢላ (ጃምቢያስ) በበርካታ መደብሮቿ መስኮቶች ውስጥ ይታያሉ። የከተማዋ ሙስሊም ነዋሪዎች ፓክዝኪ የሚባለውን የፖላንድ ዶናት ለመግዛት ወረፋ ይዘውና ተሰልፈው ይታያሉ። "አጫጭር ቀሚስ የለበሱና ሰውነታቸው በንቅሳት ያጌጠ እንዲሁም ሙሉ ፊታቸውንና ሰውነታቸውን የሚሸፍን ልብስ ለብሰው በተመሳሳይ መንገድ ሲሄዱ ማየት የተለመደ ነው። ይህ ሁሉ የኛ አካል ነው" በማለት በከተማዋ መሃል የካፌ ባለቤት የሆነው የቦስኒያ ስደተኛ ዝላታን ሳዲኮቪች ይናገራል። በዲትሮይት በአብዛኛው የተከበበችው ሐምትራምክ በአንድ ወቅት የአሜሪካ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ማዕከል ነበረች። የመኪና አምራቹ ጄኔራል ሞተርስ ፋብሪካ የሚገኘውም በከተማዋና 'ሞተር ሲቲ' ተብላ በምትጠራው ዲትሮይት ድንበር ላይ ነው። የመጀመሪያው ካዲላክ ኤልዶራዶም መገጣጠሚያውን በሐምትራምክ በ1980ዎቹ ከፈተ። በ20ዎቹ ክፍለ ዘመን የፓላንድ ስደተኞች በገፍ መግባታቸውን ተከትሎም ከተማዋ "ትንሿ ዋርሶ" የሚል ስያሜ አገኘች። የፖላንድ ተወላጁ የቀድሞው የሮም ሊቃነ ጳጳስ ጆን ፖል በአውሮፓውያኑ 1987 በአሜሪካ ጉብኝት ካደረጉባቸው ከተሞች መካከል አንዷ ናት። በአውሮፓውያኑ 1970 አካባቢም የከተማዋ 90 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ የፖላንድ ዝርያ ነበረው። በእነዚያ አስርት ዓመታት ውስጥም የአሜሪካ የመኪና ምርት ኢንዱስትሪ ማሽቆልቆሉን ተከትሎ ወጣትና ሃብታም ፖላንድ አሜሪካውያን ኑሯቸውን ወደ ሌሎች ከተሞች ማድረግ ጀመሩ። ይህ ለውጥም ሐምትራምክን በሚቺጋን ካሉ ግዛቶች በጣም ድሃ ከተሞች ውስጥ አንዷ አድርጓታል። ሆኖም በከተማው የነበረው የተመጣጠነ የመግዛት አቅም ስደተኞችን መሳብ ጀመረ። ባለፉት 30 ዓመታት ሐምትራምክ በከፍተኛ ለውጥ ያለፈች ሲሆን ለአረብ እና ለእስያ ስደተኞች በተለይም ከየመን እና ከባንግላዴሽ ለመጡት ዋነኛ ተመራጭ ማረፊያ ሆናለች። በአሁኑ ጊዜ ካሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ውስጥ 42 በመቶ የውጭ አገራት ተወላጆች ናቸው። ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ደግሞ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንደሆኑ ይታመናል። አዲስ የተመረጡትን የምክር ቤት አባላት አወቃቀርም በሐምትራምክ ያለውን ተለዋዋጭ የሥነ ሕዝብ ሁኔታ የሚያንጸባርቅ ነው። የከተማው ምክር ቤት አባላት ሁለት ቤንጋሊ አሜሪካውያን፣ ሦስት የመን አሜሪካውያን እና እምነቷን ወደ እስልምና የቀየረች ፖላንዳዊ-አሜሪካዊ ናቸው። 68 በመቶ ድምጽ በማሸነፍ ኡመር ጋሊብ በአሜሪካ የመጀመሪያው የመን አሜሪካዊ ከንቲባ ሆነዋል። "ክብር እና ኩራት ይሰማኛል፣ ነገር ግን ትልቅ ኃላፊነት እንደሆነ አውቃለሁ" በማለት የ41 አመቱ ከንቲባ ተናግረዋል። በየመን አንዲት መንደር ውስጥ የተወለዱት የአሁኑ ከንቲባ ወደ አሜሪካ የመጡት በ17 ዓመታቸው ነው። በወቅቱም ሐምትራምክ አቅራቢያ በሚገኝ ፋብሪካ ውስጥ የፕላስቲክ መኪና መለዋወጫም እንዲሰሩ ተቀጠሩ። በኋላም እንግሊዝኛ ተምረው በህክምና ባለሙያነት የተመረቁ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በጤና ባለሙያነት እያገለገሉ ይገኛሉ። "የሐምትራምክ ሕዝቦች በመጡበት በራሳቸው ባህል ይኮራሉ። እንዋሃድ ካልን ልዩነታችንን እናጣለን። የእያንዳንዳንችንን ልዩነት እናከብራለን" ሲሉ በአሁኑ ወቅት ለከተማዋ ምክር ቤት አባል የተመረጡት የ29 ዓመቷ አማንዳ ጃክዝኮውስኪ ተናግረዋል። አክለውም "እርስ በርሳችን ተቀራርበን ስንኖር በልዩነታችን ላይ ላለማተኮር እንገደዳለን" ብለዋል። ሆኖም ሁሉ ነገር አልጋ ባልጋ እንዳልሆነ ለ15 ዓመታት ያህል በከንቲባነት ያገለገሉትና በቅርቡ የተተኩት ካረን ማጄውስኪ ይናገራሉ። "ትንሽ ቦታ ነው፤ ግጭቶችም አሉ" ይላሉ። በተለይም በአውሮፓውያኑ 2004 የእስላማዊ የፀሎት ጥሪ (አዛን) በድምፅ ማጉያ በአደባባይ እንዲሰማ ድምጽ መሰጠቱን ተከትሎ ውጥረቶች ነግሰው ነበር። አንዳንድ ነዋሪዎች በመስጊድ አቅራቢያ ያሉ ቡና ቤቶችን መከልከል የአካባቢውን ኢኮኖሚ ይጎዳል ሲሉ ተከራክረዋል። ከስድስት ዓመት በፊትም በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ሙስሊም አብላጫውን የያዘበት ምክር ቤት ስታቋቁምም ከመላው ዓለም የተውጣጡ ሚዲያዎች ሁኔታውን ለመታዘብ ወደ ሐምትራምክ ጎረፉ። አንዳንድ የመገናኛ ብዙኃን ባወጧቸው ዘገባዎችም በርካታ ሙስሊሞች በመኖራቸው "ውጥረት የበዛባት" የሚል ምስልም ለመስጠት ሞክረዋል። የብሔራዊ ቴሌቪዥን አቅራቢም የወቅቱን ከንቲባ ማጄውስኪን ከንቲባ መሆን ያስፈራቸው እንደሆነ ሁሉ ጠይቋል። ይባስ ብሎ ሙስሊሞች በሚቆጣጠሩት ምክር ቤት ውስጥ የሸሪዓ ሕጎች በሕዝቡ ላይ ሊጫኑ ይችላሉ የሚሉ አስተያየቶች ከአንዳንዶች ተነስቷል። "በሐምትራምክ ነዋሪዎች ለእንደዚህ አይነት ንግግሮች ጆሯቸውን አይሰጡም" ይላሉ ማጄውስኪ። የሐምትራምክ ሕዝብ እንግዳ ተቀባይ በመሆኑ በጣም የሚያስደስታቸው ጉዳይ ነው እናም አዲስ ነዋሪዎች ባህላቸውንና ቋንቋቸውን ለሚረዱ ተወካዮች ድምፃቸውን ቢሰጡ "ተፈጥሯዊ" ነው በማለት ያስረዳሉ። የአሜሪካ የሕዝብ ቆጠራ ቢሮ ስለ ሃይማኖት መረጃ ባይሰበስብም፣ ነገር ግን ፒው የተሰኘ የምርምር ማዕከል በአውሮፓውያኑ 2020 በአሜሪካ ውስጥ ወደ 3.85 ሚሊዮን የሚጠጉ ሙስሊሞች እንዳሉ ግምቱን አስቀምጧል። ይህም አሃዝ ከጠቅላላይ ሕዝቡ 1.1 በመቶ ያህል ነው። በአውሮፓውያኑ 2040 እስልምና በአሜሪካ ውስጥ ከክርስትና በመቀጠል ሁለተኛ ተከታይ ያለው እምነት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ምንም እንኳን የሃይማኖቱ ተከታዮች ቁጥር እያደገ ቢሄድም ሙስሊሞች በአሜሪካ ውስጥ አሁንም ቢሆን ጥላቻ ይደርስባቸዋል። በአሜሪካ ከደረሰው 9/11 ጥቃት ከሁለት አስርት ዓመታትም በኋላ በአገሪቱ ያሉ ሙስሊሞች እንዲሁም ሌሎች አረብ አሜሪካውያን ከፍተኛ ጥላቻን እያስተናገዱ ይገኛሉ። የያኔው ዕጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በርካታ ሕዝባቸው ሙስሊም ከሆኑ አገሮች የሚመጡ ስደተኞች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ሃሳብ ባቀረቡበት ወቅት ግማሹ ሙስሊም አሜሪካውያን መድልዎና መገለል እንደደረሰባቸው በአውሮፓውያኑ 2016 ለፒው ተናግረዋል። በተጨማሪም ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሁሉም የሃይማኖት ቡድኖች መካከል ሙስሊሞች አሁንም ቢሆን በአሜሪካ ሕዝብ ዘንድ በአሉታዊ ሁኔታ ነው የሚታዩት። ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አሜሪካውያን በግላቸው የእስልምና ተከታይ የሆኑ ሰዎችን ባያውቁም፣ እናውቃለን የሚሉ አሜሪካውያን በበኩላቸው እስልምና ከሌሎች ሃይማኖቶች በበለጠ ሁከትን ያበረታታል ብለው እንደማያስቡ ተናግረዋል። ስለ እስልምናም ሆነ ሙስሊሞችን ማወቅ ከእስልምና ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥላቻዎች ትርጉም እንደሌላቸው የሐምትራምክ ከተማ ዋና ማሳያ ናት። ሻሃብ አህመድ የ9/11 ጥቃትን ተከትሎ ለከተማው ምክር ቤት አባልነት ሲወዳደሩ ትልቅ ፈተና ነበር የገጠማቸው። "ወደ አውሮፕላኑ ያልደረስክ 20ኛው ጠላፊ ነህ የሚሉ በራሪ ወረቀቶች በከተማዋ ሁሉ ተበትነው ነበር" ሲሉ ቤንጋሊ አሜሪካዊው ሻሃብ ተናግረዋል። በአውሮፓውያኑ 2001 በተካሄደው ምርጫም ተሸነፉ። ሆኖም ተስፋ አልቆረጡም ከሁለት ዓመታት በኋላ በነበረው የምረጡኝ ዘመቻ እንቅስቃሴ የጎረቤቶቻቸውን በር እያንኳኩ ድምፅ ስጡኝ አሉ። የከተማዋም ነዋሪ ሰማቸው፣ ድምፅም ሰጣቸው በዚህም የሐምትራምክ የመጀመሪያው ሙስሊም ከንቲባም ሆነው ተመረጡ። በአውሮፓውያኑ 2017 የትራምፕ አስተዳደር በሙስሊም አገራት ላይ እገዳውን ሲጥል ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን ለመግለፅ ተሰብስበው በከተማዋ ወጥተዋል። "በሐምትራምክ ውስጥ ለመኖር የሌሎች ሰዎችን ዕምነትና ባህልን ማክበር እንዳለብን በማሳወቅ አንድነታችን እንዲያጠናክር ረድቶናል" በማለት "ሐምትራምክ፣ ዩኤስኤ" የተሰኘ ፊልም በተባባሪ ዳይሬክተርነት የሰራው ራዚ ጃፍሪ ይናገራል። በአገር አቀፍ ደረጃም ቢሆን ሙስሊም አሜሪካውያን በፖለቲካው ዘንድ ጎልተው የሚታዩ ሆነዋል። በአውሮፓውያኑ 2007 የሚኒሶታ ዲሞክራት ኪት ኤሊሰን የመጀመሪያው ሙስሊም የምክር ቤት አባል ሆኑ። በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ ምክር ቤት አራት ሙስሊም አባላት አሉት ። ባለፈው ወር በነበረው የሐምትራምክ ምርጫ በርካታ ነዋሪዎች በምርጫ ጣቢያዎች ፊት ለፊት ተሰብስበው ሰላምታ ሲለዋወጡ ብዙዎችም "መርጫለሁ" የሚል ወረቀት ሲያሳዩም ነበር። "ሰዎችን አንድ ላይ ማሰባሰብ የአሜሪካዊነት መገለጫ ነው። አንደኛውም እሴታችን ነው" በማለት የሚናገሩት ጃክኮቭስኪ ስደተኞች በዲሞክራሲ ሂደት ውስጥ በመሳተፋቸው የነበራቸውንም ደስታ ገልጸዋል። ነገር ግን እንደሌላው የአገሪቱ ክፍል በከተማው ውስጥ ከፍተኛ የባህል ክርክሮች መካሄዳቸው አልቀረም። በሰኔ ወር የከተማው አስተዳደር የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች መለያ የሆነው ሰንደቅ አላማ በከተማው አዳራሽ ፊት ለፊት እንዲውለበለብ ሲፈቅድ አንዳንድ ነዋሪዎችን አስቆጥቷል። በተጨማሪም በግል የንግድ ተቋማትና ቤቶች ውጭ የተሰቀሉ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ሰንደቅ አላማዎች ተቀዳደዋል። ከነዚህም መካከል ከማጄውስኪ ልብስ መደብር ውጪ የተሰቀለው ሰንደቅ አላማም ተቀዶ ተጥሏል። ይህንንም ተከትሎም "ይህ ለሰዎች በጣም አስደንጋጭ መልዕክት ያስተላልፋል" ብለዋል። ዕፀ ፋርስም (ማሪዋና) የውዝግብ መንስኤ ሆኗል። በሐምትራምክ የተከፈቱ ሦስት የዕጸ ፋርስ ማከፋፈያዎች በአንዳንድ የሙስሊም እና የፖላንድ-ካቶሊክ ማኅበረሰቦች ቁጣን ቀስቅሰዋል። ሌሎች ነዋሪዎች በበኩላቸው በወግ አጥባቂ ሙስሊም ማኅበረሰቦች ውስጥ ያለው የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ማነስ እንዳሳሰባቸው ሲናገሩ ይሰማሉ። በምርጫው ምሽት ተመራጩ ከንቲባ ጋሊብ ከድምፅ መስጫው በኋላ በደስታ በፈነጠዙና ባቅላቫና 'ክባብ' በሚያከፋፍሉ የመን አሜሪካውያን ተከበው ነበር። የከበቧቸው ከ100 በላይ ደጋፊዎች ሁሉም ወንዶች ናቸው። በምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻቸው ውስጥ ሴቶች እንደተሳተፉ የሚናገሩት ከንቲባው ሆኖም በባህሉ መሰረት ፆታዎች አንዳይቀላቀሉ ተደርጓል። ምንም እንኳን ራሳቸውን እንደ አሜሪካዊ በሚያዩት ወጣቶች ዘንድ ይህንን ሃሳብ ቢገዳደሩትም ከንቲባው ባህሉ መቀጠል አለበት ይላሉ። ሐምትራምክ ከዚህ ባለፈ ደግሞ በተበላሹ መሰረተ ልማቶችና ውስን በሆኑ የምጣኔ ሃብት ዕድሎች በርካታ ችግሮች ተደቅኖባታል። በበጋው የጣለው ከባድ ዝናብ የከተማውን የፍሳሽ ማስወገጃዎች ሞልቶ በርካታ ቤቶችን አጥለቅልቋል። ለመጠጥ የሚውለው ውሃ በኬሚካል መበከሉ ሁኔታውን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎታል። የከተማዋ ግማሽ የሚጠጋው ሕዝብ የሚኖረው ከድህነት ወለል በታች ነው። እነዚህ ችግሮች ለአዲሱ የከተማ አስተዳደርም ለዓመታት ሲንከባለሉ የቆዩ አንገብጋቢ የቤት ሥራዎች ናቸው። "በአብዛኛው ሙስሊም በሚበዛበት ከተማ ዲሞክራሲ ምን ዓይነት መልክ አለው? እንደሌላው ቦታ ሁሉ የተዘበራረቀ እና የተወሳሰበ ነው" ሲል ዘጋቢ ፊልም ሰሪው ጃፍሪ የተናገረ ሲሆን አክሎም "አሁን ያለው የደስታ ስሜት ሲቀዘቅዝ ሥራው መሰራት አለበት" በማለትም ያስረዳል።
በሙስሊም አሜሪካውያን የምትመራው የአሜሪካ ከተማ በአሜሪካዋ ሚቺጋን ግዛት በምትገኘው ሐምትራምክ ዋና ጎዳና መረማመድ በዓለም ያሉ ከተሞችን እንደጎበኙ የሚያደርግ ስሜትን ይፈጥራል። ከተማዋን ያደመቁት የፖላንድ የቋሊማ መሸጫ መደብር፣ የምሥራቅ አውሮፓ ዳቦ ቤት፣ የየመን መገበያያ መደብር እና የቤንጋሊ ልብስ ቤት ከተማዋን የበርካታ ሕዝቦችና ባህሎች መናኸሪያ አድርገዋታል። የቤተ ክርስቲያን ደወልና የሙስሊሞች የፀሎት ጥሪ (አዛን) በተመሳሳይ ወቅት ይሰሙባታል። "ዓለምን በሁለት ስኩዌር ማይል" በሚል መፈክሯ የምትታወቀው ሐምትራምክ በአምስት ስኩዌር ኪሎሜትር የቆዳ ስፋቷ ውስጥ ወደ 30 የሚጠጉ ቋንቋዎች የሚነገሩባት በመሆን እውነትም "ትንሿ ዓለም" የሚል ስያሜ አሰጥቷታል። በመካከለኛውም ምዕራብ የምትገኘውና የ28ሺህ ሕዝብ መኖሪያ የሆነችው ይህች ከተማ በዚህ ወር ደግሞ በታሪኳ ለየት ጉዳይ ተሰምቶባታል። በሐምትራምክ ሁሉም አባላት የእስልምና ተከታይ የሆኑበት የከተማ ምክር ቤትና የሙስሊም ከንቲባ መርጣለች። በአሜሪካ ውስጥ የሙስሊሞች አስተዳደር ሲመሰረት ይህ የመጀመሪያ እንደመሆኑ መጠን ታሪካዊ ክስተት ነው ተብሏል። በአንድ ወቅት በከተማይቱ የሚደርስባቸውን መድሎና መገለል ሲታገሉ የነበሩት ሙስሊም ነዋሪዎች የዚህች የብዙ ባህሎች መናኸሪያ ከተማ ዋና አካል ሆነዋል፤ ከሕዝቡም ከግማሽ በላይ የሚሆነውንም ቁጥር ይዘዋል። ምንም እንኳን ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች እና ከፍተኛ የባህል ክርክሮች ቢኖሩም፣ ሐምትራምክ ከተለያዩ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ መሰረቶች የመጡ ነዋሪዎች ተስማምተው አብረው የሚኖሩባት ሆናለች። ይህም በአሜሪካ ውስጥ እየጨመረ ለመጣው ብዝኃነት የወደፊት ዕጣ ፈንታ ትርጉም ያለው የጥናት መነሻም ልትሆን እንደምትችል ተነግሯል። ሆኖም በሐምትራምክ ያለው ታሪካዊ ክስተት በሌሎች የሚደገም ወይስ የተለየ ሆኖ የሚቀር የሚል ጥያቄም እያጫረ ነው። በበርካታ የጀርመን ሰፋሪዎች ጥንታዊ ታሪኳ የሚጀምረው የሐምትራምክ ከተማ በአሁኑ ወቅት ደግሞ በርካታ ሙስሊሞች የሚኖሩባት ስትሆን ይህ ከጥንት እስካሁን ያለው ገፅታዋም በጎዳናዎቿ ባሉ ኪነ ጥበቦች በግልፅ ይንጸባረቃል። መደብሮቿ በአረብኛና በቤንጋሊ ቋንቋዎች በተጻፉ ስሞች ያጌጡ ሲሆን፣ የባንግላዴሽ ባለ ጥልፍ አልባሳት፣ ከየመን የመጣው አጭር ጥምዝ ቢላ (ጃምቢያስ) በበርካታ መደብሮቿ መስኮቶች ውስጥ ይታያሉ። የከተማዋ ሙስሊም ነዋሪዎች ፓክዝኪ የሚባለውን የፖላንድ ዶናት ለመግዛት ወረፋ ይዘውና ተሰልፈው ይታያሉ። "አጫጭር ቀሚስ የለበሱና ሰውነታቸው በንቅሳት ያጌጠ እንዲሁም ሙሉ ፊታቸውንና ሰውነታቸውን የሚሸፍን ልብስ ለብሰው በተመሳሳይ መንገድ ሲሄዱ ማየት የተለመደ ነው። ይህ ሁሉ የኛ አካል ነው" በማለት በከተማዋ መሃል የካፌ ባለቤት የሆነው የቦስኒያ ስደተኛ ዝላታን ሳዲኮቪች ይናገራል። በዲትሮይት በአብዛኛው የተከበበችው ሐምትራምክ በአንድ ወቅት የአሜሪካ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ማዕከል ነበረች። የመኪና አምራቹ ጄኔራል ሞተርስ ፋብሪካ የሚገኘውም በከተማዋና 'ሞተር ሲቲ' ተብላ በምትጠራው ዲትሮይት ድንበር ላይ ነው። የመጀመሪያው ካዲላክ ኤልዶራዶም መገጣጠሚያውን በሐምትራምክ በ1980ዎቹ ከፈተ። በ20ዎቹ ክፍለ ዘመን የፓላንድ ስደተኞች በገፍ መግባታቸውን ተከትሎም ከተማዋ "ትንሿ ዋርሶ" የሚል ስያሜ አገኘች። የፖላንድ ተወላጁ የቀድሞው የሮም ሊቃነ ጳጳስ ጆን ፖል በአውሮፓውያኑ 1987 በአሜሪካ ጉብኝት ካደረጉባቸው ከተሞች መካከል አንዷ ናት። በአውሮፓውያኑ 1970 አካባቢም የከተማዋ 90 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ የፖላንድ ዝርያ ነበረው። በእነዚያ አስርት ዓመታት ውስጥም የአሜሪካ የመኪና ምርት ኢንዱስትሪ ማሽቆልቆሉን ተከትሎ ወጣትና ሃብታም ፖላንድ አሜሪካውያን ኑሯቸውን ወደ ሌሎች ከተሞች ማድረግ ጀመሩ። ይህ ለውጥም ሐምትራምክን በሚቺጋን ካሉ ግዛቶች በጣም ድሃ ከተሞች ውስጥ አንዷ አድርጓታል። ሆኖም በከተማው የነበረው የተመጣጠነ የመግዛት አቅም ስደተኞችን መሳብ ጀመረ። ባለፉት 30 ዓመታት ሐምትራምክ በከፍተኛ ለውጥ ያለፈች ሲሆን ለአረብ እና ለእስያ ስደተኞች በተለይም ከየመን እና ከባንግላዴሽ ለመጡት ዋነኛ ተመራጭ ማረፊያ ሆናለች። በአሁኑ ጊዜ ካሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ውስጥ 42 በመቶ የውጭ አገራት ተወላጆች ናቸው። ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ደግሞ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንደሆኑ ይታመናል። አዲስ የተመረጡትን የምክር ቤት አባላት አወቃቀርም በሐምትራምክ ያለውን ተለዋዋጭ የሥነ ሕዝብ ሁኔታ የሚያንጸባርቅ ነው። የከተማው ምክር ቤት አባላት ሁለት ቤንጋሊ አሜሪካውያን፣ ሦስት የመን አሜሪካውያን እና እምነቷን ወደ እስልምና የቀየረች ፖላንዳዊ-አሜሪካዊ ናቸው። 68 በመቶ ድምጽ በማሸነፍ ኡመር ጋሊብ በአሜሪካ የመጀመሪያው የመን አሜሪካዊ ከንቲባ ሆነዋል። "ክብር እና ኩራት ይሰማኛል፣ ነገር ግን ትልቅ ኃላፊነት እንደሆነ አውቃለሁ" በማለት የ41 አመቱ ከንቲባ ተናግረዋል። በየመን አንዲት መንደር ውስጥ የተወለዱት የአሁኑ ከንቲባ ወደ አሜሪካ የመጡት በ17 ዓመታቸው ነው። በወቅቱም ሐምትራምክ አቅራቢያ በሚገኝ ፋብሪካ ውስጥ የፕላስቲክ መኪና መለዋወጫም እንዲሰሩ ተቀጠሩ። በኋላም እንግሊዝኛ ተምረው በህክምና ባለሙያነት የተመረቁ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በጤና ባለሙያነት እያገለገሉ ይገኛሉ። "የሐምትራምክ ሕዝቦች በመጡበት በራሳቸው ባህል ይኮራሉ። እንዋሃድ ካልን ልዩነታችንን እናጣለን። የእያንዳንዳንችንን ልዩነት እናከብራለን" ሲሉ በአሁኑ ወቅት ለከተማዋ ምክር ቤት አባል የተመረጡት የ29 ዓመቷ አማንዳ ጃክዝኮውስኪ ተናግረዋል። አክለውም "እርስ በርሳችን ተቀራርበን ስንኖር በልዩነታችን ላይ ላለማተኮር እንገደዳለን" ብለዋል። ሆኖም ሁሉ ነገር አልጋ ባልጋ እንዳልሆነ ለ15 ዓመታት ያህል በከንቲባነት ያገለገሉትና በቅርቡ የተተኩት ካረን ማጄውስኪ ይናገራሉ። "ትንሽ ቦታ ነው፤ ግጭቶችም አሉ" ይላሉ። በተለይም በአውሮፓውያኑ 2004 የእስላማዊ የፀሎት ጥሪ (አዛን) በድምፅ ማጉያ በአደባባይ እንዲሰማ ድምጽ መሰጠቱን ተከትሎ ውጥረቶች ነግሰው ነበር። አንዳንድ ነዋሪዎች በመስጊድ አቅራቢያ ያሉ ቡና ቤቶችን መከልከል የአካባቢውን ኢኮኖሚ ይጎዳል ሲሉ ተከራክረዋል። ከስድስት ዓመት በፊትም በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ሙስሊም አብላጫውን የያዘበት ምክር ቤት ስታቋቁምም ከመላው ዓለም የተውጣጡ ሚዲያዎች ሁኔታውን ለመታዘብ ወደ ሐምትራምክ ጎረፉ። አንዳንድ የመገናኛ ብዙኃን ባወጧቸው ዘገባዎችም በርካታ ሙስሊሞች በመኖራቸው "ውጥረት የበዛባት" የሚል ምስልም ለመስጠት ሞክረዋል። የብሔራዊ ቴሌቪዥን አቅራቢም የወቅቱን ከንቲባ ማጄውስኪን ከንቲባ መሆን ያስፈራቸው እንደሆነ ሁሉ ጠይቋል። ይባስ ብሎ ሙስሊሞች በሚቆጣጠሩት ምክር ቤት ውስጥ የሸሪዓ ሕጎች በሕዝቡ ላይ ሊጫኑ ይችላሉ የሚሉ አስተያየቶች ከአንዳንዶች ተነስቷል። "በሐምትራምክ ነዋሪዎች ለእንደዚህ አይነት ንግግሮች ጆሯቸውን አይሰጡም" ይላሉ ማጄውስኪ። የሐምትራምክ ሕዝብ እንግዳ ተቀባይ በመሆኑ በጣም የሚያስደስታቸው ጉዳይ ነው እናም አዲስ ነዋሪዎች ባህላቸውንና ቋንቋቸውን ለሚረዱ ተወካዮች ድምፃቸውን ቢሰጡ "ተፈጥሯዊ" ነው በማለት ያስረዳሉ። የአሜሪካ የሕዝብ ቆጠራ ቢሮ ስለ ሃይማኖት መረጃ ባይሰበስብም፣ ነገር ግን ፒው የተሰኘ የምርምር ማዕከል በአውሮፓውያኑ 2020 በአሜሪካ ውስጥ ወደ 3.85 ሚሊዮን የሚጠጉ ሙስሊሞች እንዳሉ ግምቱን አስቀምጧል። ይህም አሃዝ ከጠቅላላይ ሕዝቡ 1.1 በመቶ ያህል ነው። በአውሮፓውያኑ 2040 እስልምና በአሜሪካ ውስጥ ከክርስትና በመቀጠል ሁለተኛ ተከታይ ያለው እምነት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ምንም እንኳን የሃይማኖቱ ተከታዮች ቁጥር እያደገ ቢሄድም ሙስሊሞች በአሜሪካ ውስጥ አሁንም ቢሆን ጥላቻ ይደርስባቸዋል። በአሜሪካ ከደረሰው 9/11 ጥቃት ከሁለት አስርት ዓመታትም በኋላ በአገሪቱ ያሉ ሙስሊሞች እንዲሁም ሌሎች አረብ አሜሪካውያን ከፍተኛ ጥላቻን እያስተናገዱ ይገኛሉ። የያኔው ዕጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በርካታ ሕዝባቸው ሙስሊም ከሆኑ አገሮች የሚመጡ ስደተኞች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ሃሳብ ባቀረቡበት ወቅት ግማሹ ሙስሊም አሜሪካውያን መድልዎና መገለል እንደደረሰባቸው በአውሮፓውያኑ 2016 ለፒው ተናግረዋል። በተጨማሪም ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሁሉም የሃይማኖት ቡድኖች መካከል ሙስሊሞች አሁንም ቢሆን በአሜሪካ ሕዝብ ዘንድ በአሉታዊ ሁኔታ ነው የሚታዩት። ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አሜሪካውያን በግላቸው የእስልምና ተከታይ የሆኑ ሰዎችን ባያውቁም፣ እናውቃለን የሚሉ አሜሪካውያን በበኩላቸው እስልምና ከሌሎች ሃይማኖቶች በበለጠ ሁከትን ያበረታታል ብለው እንደማያስቡ ተናግረዋል። ስለ እስልምናም ሆነ ሙስሊሞችን ማወቅ ከእስልምና ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥላቻዎች ትርጉም እንደሌላቸው የሐምትራምክ ከተማ ዋና ማሳያ ናት። ሻሃብ አህመድ የ9/11 ጥቃትን ተከትሎ ለከተማው ምክር ቤት አባልነት ሲወዳደሩ ትልቅ ፈተና ነበር የገጠማቸው። "ወደ አውሮፕላኑ ያልደረስክ 20ኛው ጠላፊ ነህ የሚሉ በራሪ ወረቀቶች በከተማዋ ሁሉ ተበትነው ነበር" ሲሉ ቤንጋሊ አሜሪካዊው ሻሃብ ተናግረዋል። በአውሮፓውያኑ 2001 በተካሄደው ምርጫም ተሸነፉ። ሆኖም ተስፋ አልቆረጡም ከሁለት ዓመታት በኋላ በነበረው የምረጡኝ ዘመቻ እንቅስቃሴ የጎረቤቶቻቸውን በር እያንኳኩ ድምፅ ስጡኝ አሉ። የከተማዋም ነዋሪ ሰማቸው፣ ድምፅም ሰጣቸው በዚህም የሐምትራምክ የመጀመሪያው ሙስሊም ከንቲባም ሆነው ተመረጡ። በአውሮፓውያኑ 2017 የትራምፕ አስተዳደር በሙስሊም አገራት ላይ እገዳውን ሲጥል ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን ለመግለፅ ተሰብስበው በከተማዋ ወጥተዋል። "በሐምትራምክ ውስጥ ለመኖር የሌሎች ሰዎችን ዕምነትና ባህልን ማክበር እንዳለብን በማሳወቅ አንድነታችን እንዲያጠናክር ረድቶናል" በማለት "ሐምትራምክ፣ ዩኤስኤ" የተሰኘ ፊልም በተባባሪ ዳይሬክተርነት የሰራው ራዚ ጃፍሪ ይናገራል። በአገር አቀፍ ደረጃም ቢሆን ሙስሊም አሜሪካውያን በፖለቲካው ዘንድ ጎልተው የሚታዩ ሆነዋል። በአውሮፓውያኑ 2007 የሚኒሶታ ዲሞክራት ኪት ኤሊሰን የመጀመሪያው ሙስሊም የምክር ቤት አባል ሆኑ። በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ ምክር ቤት አራት ሙስሊም አባላት አሉት ። ባለፈው ወር በነበረው የሐምትራምክ ምርጫ በርካታ ነዋሪዎች በምርጫ ጣቢያዎች ፊት ለፊት ተሰብስበው ሰላምታ ሲለዋወጡ ብዙዎችም "መርጫለሁ" የሚል ወረቀት ሲያሳዩም ነበር። "ሰዎችን አንድ ላይ ማሰባሰብ የአሜሪካዊነት መገለጫ ነው። አንደኛውም እሴታችን ነው" በማለት የሚናገሩት ጃክኮቭስኪ ስደተኞች በዲሞክራሲ ሂደት ውስጥ በመሳተፋቸው የነበራቸውንም ደስታ ገልጸዋል። ነገር ግን እንደሌላው የአገሪቱ ክፍል በከተማው ውስጥ ከፍተኛ የባህል ክርክሮች መካሄዳቸው አልቀረም። በሰኔ ወር የከተማው አስተዳደር የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች መለያ የሆነው ሰንደቅ አላማ በከተማው አዳራሽ ፊት ለፊት እንዲውለበለብ ሲፈቅድ አንዳንድ ነዋሪዎችን አስቆጥቷል። በተጨማሪም በግል የንግድ ተቋማትና ቤቶች ውጭ የተሰቀሉ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ሰንደቅ አላማዎች ተቀዳደዋል። ከነዚህም መካከል ከማጄውስኪ ልብስ መደብር ውጪ የተሰቀለው ሰንደቅ አላማም ተቀዶ ተጥሏል። ይህንንም ተከትሎም "ይህ ለሰዎች በጣም አስደንጋጭ መልዕክት ያስተላልፋል" ብለዋል። ዕፀ ፋርስም (ማሪዋና) የውዝግብ መንስኤ ሆኗል። በሐምትራምክ የተከፈቱ ሦስት የዕጸ ፋርስ ማከፋፈያዎች በአንዳንድ የሙስሊም እና የፖላንድ-ካቶሊክ ማኅበረሰቦች ቁጣን ቀስቅሰዋል። ሌሎች ነዋሪዎች በበኩላቸው በወግ አጥባቂ ሙስሊም ማኅበረሰቦች ውስጥ ያለው የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ማነስ እንዳሳሰባቸው ሲናገሩ ይሰማሉ። በምርጫው ምሽት ተመራጩ ከንቲባ ጋሊብ ከድምፅ መስጫው በኋላ በደስታ በፈነጠዙና ባቅላቫና 'ክባብ' በሚያከፋፍሉ የመን አሜሪካውያን ተከበው ነበር። የከበቧቸው ከ100 በላይ ደጋፊዎች ሁሉም ወንዶች ናቸው። በምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻቸው ውስጥ ሴቶች እንደተሳተፉ የሚናገሩት ከንቲባው ሆኖም በባህሉ መሰረት ፆታዎች አንዳይቀላቀሉ ተደርጓል። ምንም እንኳን ራሳቸውን እንደ አሜሪካዊ በሚያዩት ወጣቶች ዘንድ ይህንን ሃሳብ ቢገዳደሩትም ከንቲባው ባህሉ መቀጠል አለበት ይላሉ። ሐምትራምክ ከዚህ ባለፈ ደግሞ በተበላሹ መሰረተ ልማቶችና ውስን በሆኑ የምጣኔ ሃብት ዕድሎች በርካታ ችግሮች ተደቅኖባታል። በበጋው የጣለው ከባድ ዝናብ የከተማውን የፍሳሽ ማስወገጃዎች ሞልቶ በርካታ ቤቶችን አጥለቅልቋል። ለመጠጥ የሚውለው ውሃ በኬሚካል መበከሉ ሁኔታውን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎታል። የከተማዋ ግማሽ የሚጠጋው ሕዝብ የሚኖረው ከድህነት ወለል በታች ነው። እነዚህ ችግሮች ለአዲሱ የከተማ አስተዳደርም ለዓመታት ሲንከባለሉ የቆዩ አንገብጋቢ የቤት ሥራዎች ናቸው። "በአብዛኛው ሙስሊም በሚበዛበት ከተማ ዲሞክራሲ ምን ዓይነት መልክ አለው? እንደሌላው ቦታ ሁሉ የተዘበራረቀ እና የተወሳሰበ ነው" ሲል ዘጋቢ ፊልም ሰሪው ጃፍሪ የተናገረ ሲሆን አክሎም "አሁን ያለው የደስታ ስሜት ሲቀዘቅዝ ሥራው መሰራት አለበት" በማለትም ያስረዳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59868775
5sports
እግር ኳስ፡ የአውሮፓ ዋንጫ እሑድ ምሽት ፍጻሜውን ያገኛል፤ ማን ያሸንፋል?
የበርካታ እግር ኳስ አፍቃሪያንን ልብ ሰቅዞ ይዞ የከረመው የአውሮፓ ዋንጫ ነገ እሑድ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ፍጻሜውን ያገኛል። በፍጻሜ ጨዋታው ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ ዋንጫ ለፍጻሜ የደረሰችው እንግሊዝ እና ምንም ሳትጠበቅ እዚህ የደረሰችው ጣልያን ይፋለማሉ። ጣልያኖች ገና ከምድብ ጨዋታዎች ጀምሮ በርካታ ጎሎችን እያስቆጠሩና እስካሁንም ድረስ ምንም አይነት ሽንፈትም ሆነ አቻ ውጤት ሳያስተናግዱ ነው ለፍጻሜው ጨዋታ የደረሱት። እንግሊዝ ደግሞ በምድብ ጨዋታዎች ግብ ማስቆጠር ተስኗት ነበር። ቀስ በቀስ ግን እነ ሀሪ ኬንን የያዘው ቡድን ወደ ግብ ማግባት መመለስ ችሏል። በግማሽ ፍጻሜው ጨዋታ ጣልያን ስፔንን በፍጹም ቅጣት ምት በማሸነፍ ለፍጻሜ መድረሷን አረጋግጣለች። በእንግሊዙ ዌምብሌይ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዘጠና ደቂቃው እና ተጨማሪ ደቂቃ አንድ አቻ በመጠናቀቁ ሁለቱ ቡድኖች በፍጽም ቅጣት ምት እንዲለያዩ ሆኗል። የጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ በፈጣን እንቅስቃሴና በስፔን የተበላይነት የተሞላ ቢሆንም ግብ ግን ሳይቆጠር ነበር የተጠናቀቀው። ሁለተኛው አጋማሽ ላይ የጣልያኑ ፌደሪኮ ኪዬዛ አስገራሚ ግብ አስቆጥሮ ጣልያንን መሪ ማድረግ ችሏል። ነገር ግን ጨዋታው ሊጠናቀቅ እየተቃረበ በነረበት ሰዓት የስፔን ተጫዋቾች በጥሩ ጨዋታ ጣልያን የግብ ክልል ውስጥ የተቀባበሏትን ኳስ ተቀይሮ የገባው አልቫሮ ሞራታ በግሩም ሁኔታ ወደ ግብነት በመቀየር አገሩን አቻ ማድረግ ችሎ ነበር። የጣልያኑ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ ያዋቀሩት ቡድን እስካሁን ድረስ ብዙም ሳይቸገር ነበር ለግማሽ ፍጻሜው መድረስ የቻለው። ነገር ግን ከስፔን ጋር የተደረገው ጨዋታ ጣልያኖችን የፈተነ ነበር። ጣልያን ከምድብ ድልድል ጀምሮ ባልተለመደ መልኩ ማጥቃት ላይ መሠረት ያደረገና ብዙ ግቦችን ማስቆጠር የሚያስችል አጨዋወት ነበር ይዛ የመጣችው። አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ ብሔራዊ ቡድኑን ከተረከቡ ወዲህ ለ2018ቱ የዓለም ዋንጫ እንኳን ጣልያንን ማሳለፍ አቅቷቸው የነበረ ቢሆንም በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ግን በደንብ የተደራጀና ውጤታማ ቡድን ሠርተው ለፍጻሜ መድረስ ችለዋል። እንግሊዝ ደግሞ በግማሽ ፍጻሜው ዴንማርክን በመርታት ከ55 ዓመት በኋላ ለአንድ ትልቅ የእግር ኳስ ውድድር ፍጻሜ ደርሳለች። በርካታ ተመልካች በሚይዘው የለንደኑ ዌምብሊ ስታዲየም የተካሄደው ጨዋታ ፈጣንና በግብ ሙከራዎች የታጀበ ነበር። እንግሊዝ በፈረንጆቹ 1966 ምዕራብ ጀርመንን በመርታት ካነሳችው የዓለም ዋንጫ ውጭ ሌላ ውድድር አሸንፋም ይሁን ለፍጻሜ ደርሳ አታውቅም። ረቡዕ ምሽት ዴንማርክን የገጠመችው እንግሊዝ አንድ ለባዶ ስትመራ ብትቆይም ከ120 ደቂቃዎች ፍልሚያ በኋላ 2-1 መርታት ችላለች። ምንም እንኳ ዴንማርክ በወጣቱ ዳምስጋርድ ግሩም ቅጣት ምት አማካይነት ጨዋታውን ስትመራ ብትቆይም የኋላ ኋላ እጇን ሰጥታለች። የመጀመሪያው አጋማሽ ከመጠናቀቁ በፊት የእንግሊዙ ቡካዮ ሳካ ወደ ጎል የላካትን ኳስ የዴንማርኩ ሳይመን ኬር በራሱ መረብ ላይ በማሳረፉ ጨዋታው አቻ ሆነ። የዴንማርኩ ግብ ጠባቂ ካስፐር ሽማይክል ከሃገሪ ማጓየርና ሃሪ ኬን የተቃጡበትን የጎል ሙከራዎች ማዳን ቢችልም 103ኛው ደቂቃ ላይ ራሂም ስተርሊንግ ፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ተጠልፎ ዳኛው ቅጣት ሰጥተዋል። የእንግሊዙ ግብ አዳኝ ሃሪ ኬን ፍጹም ቅጣት ምቱን ሲመታ በረኛው ተወርውሮ ቢያድነውም ሃሪ ኬን ግን ተመልሶ ኳሷን ወደ መረብ በመጠለዝ እንግሊዝ ሁለት ለአንድ እንድታሸንፍ አስችሏል። የጣልያኑ ተከላካይ ሊዮናርዶ ቦኑቺ የፍጻሜ ጨዋታው በእንግሊዙ ዌምብሌይ ስታዲየም መካሄዱ ምንም አይነት ፍርሀት እንደማይፈጥርባቸው ተናግሯል። "ምንም እንኳን በስታዲየሙ ከሚገኙት ደጋፊዎች መካከል አብዛኛዎቹ እንግሊዛውያን እንደሚሆኑ ብናውቅም ምንም አይነት ስጋት ግን አይገባንም። እንደውም ይሄ ተጨማሪ መነሳሳትን ነው የሚፈጥርልን" ብሏል። በለንደኑ ዌምብሌይ ስታዲየም የሚካሄደውን የፍጻሜ ጨዋታ እስከ 1 ሺህ የሚደርሱ ጣልያናውያን ደጋፊዎች ገብተው እንደሚከታተሉት ይጠበቃከል። የዩቬንቱስ የመሀል ተካለካይ ቦኑቺ ከ36 ዓመቱ ጆርጂዮ ኪዬሊኒ ጋር በመጣመር እንግሊዝ ግብ እንዳታስቆጥር ከፍተኛ ሥራ ይጠበቅባቸዋል። ነገር ግን አማካይ እድሜው 25 የሆነው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አንጋፋዎቹን ተከላካዮች ሥራ እንዳያበዛባቸው ተሰግቷል። ''በጣም ፈጣን የፊት መስመር ተጫዋቾች አሏቸው። ሙሉ ቡድናቸውንና በተለይ አጥቂዎቹን በትልቅ ትኩረት ነው የምንጠብቃቸው። ምን አይነች ችግር ሊፈጥሩብን እንደሚችሉ እናውቃለን። ፍጥነታቸውን ከግምት ውስጥ አስገብተን ተጠንቅቀን እንጫወታለን'' ብሏል ቦኑቺ። የእንግሊዙ አምበል ሃሪ ኬን በበኩሉ ''ይሄ በእግር ኳስ ሕይወቴ ትልቁ አጋጣሚ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ። ምናልባት ይህ ለሁሉም የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች የሚሠራ ይመስለኛል''ብሏል። ''ልጅ ሆነን እንዲህ አይነት ህልሞችን እናልማለን። አገርን ወክሎ ተጫውቶ ዋንጫ ማሸነፍ። አሁን ይህንን ህልም የመኖር እድል አግኝተናል። ይሄን የመሰለ እድል በቀላሉ አሳልፈን አንሰጥም።'' እንግሊዞች የግማሽ ፍፃሜ እርግማን አለባቸው ይባል ነበር። በወጣት ተጫዋቾች የተሞላችው እንግሊዝ በ2018ቱ የዓለም ዋንጫ ለግማሽ ፍጻሜ ደርሳ በክሮሺያ መሸነፏ ይታወሳል። ጣልያን በተካሄደው የ1990 ዓለም ዋንጫ ላይ እንዲሁ ለግማሽ ፍጻሜ ደርሰው ተሸንፈዋል። በድጋሚ ጣልያን ባስተናገደችው የ1996 አውሮፓ ዋንጫ ላይ ለግማሽ ፍጻሜ የደረሰችው እንግሊዝ ሽንፈት አስተናግዳ ነበር። አሁን ግን ይህንን መጥፎ ጠባሳ ሽራ ለፍጻሜ ማለፍ ችላለች። አሁን ጥያቄው እንግሊዝ ከነዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላ በዓለም መድረክ ትልቅ ዋንጫ ማንሳት ትችላለች ወይ የሚለው ነው። እሑድ ምሽት 4 ሰዓት በለንደኑ ዌምብሊ ስታድየም በአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ እንግሊዝ ከጣልያን የውድድሩን የመጨረሻ ጨዋታ ያደርጋሉ። ሁለቱም ቡድኖች ባሳዩት አቋም ምክንያት ይሄኛው ቡድን የተሻለ እድል አለው ለማለት እንኳን ከባድ አድርጎታል። ለማንኛውም ግን አሸናፊው ነገ ምሽት የሚታወቅ ይሆናል።
እግር ኳስ፡ የአውሮፓ ዋንጫ እሑድ ምሽት ፍጻሜውን ያገኛል፤ ማን ያሸንፋል? የበርካታ እግር ኳስ አፍቃሪያንን ልብ ሰቅዞ ይዞ የከረመው የአውሮፓ ዋንጫ ነገ እሑድ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ፍጻሜውን ያገኛል። በፍጻሜ ጨዋታው ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ ዋንጫ ለፍጻሜ የደረሰችው እንግሊዝ እና ምንም ሳትጠበቅ እዚህ የደረሰችው ጣልያን ይፋለማሉ። ጣልያኖች ገና ከምድብ ጨዋታዎች ጀምሮ በርካታ ጎሎችን እያስቆጠሩና እስካሁንም ድረስ ምንም አይነት ሽንፈትም ሆነ አቻ ውጤት ሳያስተናግዱ ነው ለፍጻሜው ጨዋታ የደረሱት። እንግሊዝ ደግሞ በምድብ ጨዋታዎች ግብ ማስቆጠር ተስኗት ነበር። ቀስ በቀስ ግን እነ ሀሪ ኬንን የያዘው ቡድን ወደ ግብ ማግባት መመለስ ችሏል። በግማሽ ፍጻሜው ጨዋታ ጣልያን ስፔንን በፍጹም ቅጣት ምት በማሸነፍ ለፍጻሜ መድረሷን አረጋግጣለች። በእንግሊዙ ዌምብሌይ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዘጠና ደቂቃው እና ተጨማሪ ደቂቃ አንድ አቻ በመጠናቀቁ ሁለቱ ቡድኖች በፍጽም ቅጣት ምት እንዲለያዩ ሆኗል። የጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ በፈጣን እንቅስቃሴና በስፔን የተበላይነት የተሞላ ቢሆንም ግብ ግን ሳይቆጠር ነበር የተጠናቀቀው። ሁለተኛው አጋማሽ ላይ የጣልያኑ ፌደሪኮ ኪዬዛ አስገራሚ ግብ አስቆጥሮ ጣልያንን መሪ ማድረግ ችሏል። ነገር ግን ጨዋታው ሊጠናቀቅ እየተቃረበ በነረበት ሰዓት የስፔን ተጫዋቾች በጥሩ ጨዋታ ጣልያን የግብ ክልል ውስጥ የተቀባበሏትን ኳስ ተቀይሮ የገባው አልቫሮ ሞራታ በግሩም ሁኔታ ወደ ግብነት በመቀየር አገሩን አቻ ማድረግ ችሎ ነበር። የጣልያኑ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ ያዋቀሩት ቡድን እስካሁን ድረስ ብዙም ሳይቸገር ነበር ለግማሽ ፍጻሜው መድረስ የቻለው። ነገር ግን ከስፔን ጋር የተደረገው ጨዋታ ጣልያኖችን የፈተነ ነበር። ጣልያን ከምድብ ድልድል ጀምሮ ባልተለመደ መልኩ ማጥቃት ላይ መሠረት ያደረገና ብዙ ግቦችን ማስቆጠር የሚያስችል አጨዋወት ነበር ይዛ የመጣችው። አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ ብሔራዊ ቡድኑን ከተረከቡ ወዲህ ለ2018ቱ የዓለም ዋንጫ እንኳን ጣልያንን ማሳለፍ አቅቷቸው የነበረ ቢሆንም በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ግን በደንብ የተደራጀና ውጤታማ ቡድን ሠርተው ለፍጻሜ መድረስ ችለዋል። እንግሊዝ ደግሞ በግማሽ ፍጻሜው ዴንማርክን በመርታት ከ55 ዓመት በኋላ ለአንድ ትልቅ የእግር ኳስ ውድድር ፍጻሜ ደርሳለች። በርካታ ተመልካች በሚይዘው የለንደኑ ዌምብሊ ስታዲየም የተካሄደው ጨዋታ ፈጣንና በግብ ሙከራዎች የታጀበ ነበር። እንግሊዝ በፈረንጆቹ 1966 ምዕራብ ጀርመንን በመርታት ካነሳችው የዓለም ዋንጫ ውጭ ሌላ ውድድር አሸንፋም ይሁን ለፍጻሜ ደርሳ አታውቅም። ረቡዕ ምሽት ዴንማርክን የገጠመችው እንግሊዝ አንድ ለባዶ ስትመራ ብትቆይም ከ120 ደቂቃዎች ፍልሚያ በኋላ 2-1 መርታት ችላለች። ምንም እንኳ ዴንማርክ በወጣቱ ዳምስጋርድ ግሩም ቅጣት ምት አማካይነት ጨዋታውን ስትመራ ብትቆይም የኋላ ኋላ እጇን ሰጥታለች። የመጀመሪያው አጋማሽ ከመጠናቀቁ በፊት የእንግሊዙ ቡካዮ ሳካ ወደ ጎል የላካትን ኳስ የዴንማርኩ ሳይመን ኬር በራሱ መረብ ላይ በማሳረፉ ጨዋታው አቻ ሆነ። የዴንማርኩ ግብ ጠባቂ ካስፐር ሽማይክል ከሃገሪ ማጓየርና ሃሪ ኬን የተቃጡበትን የጎል ሙከራዎች ማዳን ቢችልም 103ኛው ደቂቃ ላይ ራሂም ስተርሊንግ ፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ተጠልፎ ዳኛው ቅጣት ሰጥተዋል። የእንግሊዙ ግብ አዳኝ ሃሪ ኬን ፍጹም ቅጣት ምቱን ሲመታ በረኛው ተወርውሮ ቢያድነውም ሃሪ ኬን ግን ተመልሶ ኳሷን ወደ መረብ በመጠለዝ እንግሊዝ ሁለት ለአንድ እንድታሸንፍ አስችሏል። የጣልያኑ ተከላካይ ሊዮናርዶ ቦኑቺ የፍጻሜ ጨዋታው በእንግሊዙ ዌምብሌይ ስታዲየም መካሄዱ ምንም አይነት ፍርሀት እንደማይፈጥርባቸው ተናግሯል። "ምንም እንኳን በስታዲየሙ ከሚገኙት ደጋፊዎች መካከል አብዛኛዎቹ እንግሊዛውያን እንደሚሆኑ ብናውቅም ምንም አይነት ስጋት ግን አይገባንም። እንደውም ይሄ ተጨማሪ መነሳሳትን ነው የሚፈጥርልን" ብሏል። በለንደኑ ዌምብሌይ ስታዲየም የሚካሄደውን የፍጻሜ ጨዋታ እስከ 1 ሺህ የሚደርሱ ጣልያናውያን ደጋፊዎች ገብተው እንደሚከታተሉት ይጠበቃከል። የዩቬንቱስ የመሀል ተካለካይ ቦኑቺ ከ36 ዓመቱ ጆርጂዮ ኪዬሊኒ ጋር በመጣመር እንግሊዝ ግብ እንዳታስቆጥር ከፍተኛ ሥራ ይጠበቅባቸዋል። ነገር ግን አማካይ እድሜው 25 የሆነው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አንጋፋዎቹን ተከላካዮች ሥራ እንዳያበዛባቸው ተሰግቷል። ''በጣም ፈጣን የፊት መስመር ተጫዋቾች አሏቸው። ሙሉ ቡድናቸውንና በተለይ አጥቂዎቹን በትልቅ ትኩረት ነው የምንጠብቃቸው። ምን አይነች ችግር ሊፈጥሩብን እንደሚችሉ እናውቃለን። ፍጥነታቸውን ከግምት ውስጥ አስገብተን ተጠንቅቀን እንጫወታለን'' ብሏል ቦኑቺ። የእንግሊዙ አምበል ሃሪ ኬን በበኩሉ ''ይሄ በእግር ኳስ ሕይወቴ ትልቁ አጋጣሚ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ። ምናልባት ይህ ለሁሉም የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች የሚሠራ ይመስለኛል''ብሏል። ''ልጅ ሆነን እንዲህ አይነት ህልሞችን እናልማለን። አገርን ወክሎ ተጫውቶ ዋንጫ ማሸነፍ። አሁን ይህንን ህልም የመኖር እድል አግኝተናል። ይሄን የመሰለ እድል በቀላሉ አሳልፈን አንሰጥም።'' እንግሊዞች የግማሽ ፍፃሜ እርግማን አለባቸው ይባል ነበር። በወጣት ተጫዋቾች የተሞላችው እንግሊዝ በ2018ቱ የዓለም ዋንጫ ለግማሽ ፍጻሜ ደርሳ በክሮሺያ መሸነፏ ይታወሳል። ጣልያን በተካሄደው የ1990 ዓለም ዋንጫ ላይ እንዲሁ ለግማሽ ፍጻሜ ደርሰው ተሸንፈዋል። በድጋሚ ጣልያን ባስተናገደችው የ1996 አውሮፓ ዋንጫ ላይ ለግማሽ ፍጻሜ የደረሰችው እንግሊዝ ሽንፈት አስተናግዳ ነበር። አሁን ግን ይህንን መጥፎ ጠባሳ ሽራ ለፍጻሜ ማለፍ ችላለች። አሁን ጥያቄው እንግሊዝ ከነዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላ በዓለም መድረክ ትልቅ ዋንጫ ማንሳት ትችላለች ወይ የሚለው ነው። እሑድ ምሽት 4 ሰዓት በለንደኑ ዌምብሊ ስታድየም በአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ እንግሊዝ ከጣልያን የውድድሩን የመጨረሻ ጨዋታ ያደርጋሉ። ሁለቱም ቡድኖች ባሳዩት አቋም ምክንያት ይሄኛው ቡድን የተሻለ እድል አለው ለማለት እንኳን ከባድ አድርጎታል። ለማንኛውም ግን አሸናፊው ነገ ምሽት የሚታወቅ ይሆናል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57787750
0business
ኢትዮጵውያንን እየፈተነ ያለው የኑሮ ውድነት መፍትሄው ምን ይሆን?
አቶ አብዲሳ ገቢሳ ከባለቤታቸው እና ከሁለት ልጆቻቸው ጋር በአዲስ አበባ ከተማ መኖሪያ ቤት ተከራይተው ይኖራሉ። የመንግሥት ሠራተኛ የሆኑት አቶ አብዲ፤ ወርሃዊ ደመወዛቸው 5ሺህ ብር ሲሆን የባለቤታቸው ገቢ ሲጨመር የቤተሰቡ ወርሃዊ ገቢ 8 ሺህ ብር ይደርሳል። ይሁን እንጂ ይህን ቤተሰብ በ8ሺህ ብር ወርሃዊ ገቢ ማስተዳደር እጅጉን ለአቶ አብዲ ከብዷቸዋል። "5ሺህ ብር ወር ጠብቄ ነው የማገኘው ነው። ወጪ እና የማገኘው ገንዘብ አይመጣጠንም። የቤት ኪራይ አለ፣ ቀለብ አለ፣ ለልጆች ትምህር ቤት ወጪ አለ። ልጆች ትምህር ቤት ሲሄዱ ምሳ ይዘው ነው የሚሄዱት። ትራንስፖርት፣ ልብስ እንዲሁም ለሠራተኛ የሚከፈል አለ። ሕይወት በጣም እየጎዳን ነው" ይላሉ። በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የዋጋ ግሽበት በተከታታይ ጭማሪ ሲያሳይ ቆይቷል። በተለይም ኀብረተሰቡ በዕለት ተዕለት በሚጠቀምባቸው መሰረታዊ ፍጆታዎች፣ በግንባታ እቃዎችና በሌሎች ላይ እየታየ ያለው የዋጋ ንረት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዜጎችን ህይወት እጅግ እየተፈታተነው ይገኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በቅርቡ መንግሥት የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረጉ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ በኑሮ ውድነቱ ላይ ከፍተኛ ጫና ሊያሳርፍ እንደሚችል ነዋሪዎች እና የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የሚናገሩት ነው። የበርካታ አገራት ፈተና የሆነው የኑሮ ውድነት በያዝነው አውሮፓውያኑ 2022 በርካታ የዓለማችን አገራት ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አጋጥሟቸዋል። በዩናትድ ኪንግደም ባለፈው ወር በ30 ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የኑሮ ውድነት በ7 በመቶ ተመዝግቧል። ኬንያውያንም በምግብ ዘይት፣ በእህል እና በአትክልት እና ፍራፍሬ ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ አስቆጥቷቸዋል። ከቀናት በፊት የብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ፤ "አሁንም በኢኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ፈተና እየገጠመን ያለው ከዋጋ ግሽበት ጋር በተገናኘ ሲሆን፥ከአምናው የሚያዚያ ወር ጋር ሲነጻጸር የዋጋ ግሽበቱ 36.6 በመቶ ደርሷል። ነገሩን ይበልጥ ከባድ የሚያደርገው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እየተመዘገበ ያለው የምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ መሆኑ ነው፡፡" በማለት አትቷል። አቶ አብዲ ገቢያ የምርቶች ዋጋ 'በየቀኑ እና በየሰዓቱ' በሚባል ደረጃ እየጨመረ ነው ይላሉ። "በየቀኑ፤ በየሰዓቱ ይጨምራል። ለምሳሌ ባለፈው እሁድ ለልጅ ታሽጋ የምትሸጥ ወተት በ20 ብር ነበር የገዛሁት። ማታ ለልጅ ገዝቼ ልግባ ስል ዋጋው 30 ብር ሆኗል። 10 ብር ጨመረ ማለት ነው ! " በማለት ይናገራሉ። ይህ የመዲናዋ ከተማ ነዋሪ የኑሮ ውድነቱ መቋቋም ከምንችለው በላይ ሆኖብናል ይላሉ። "የኑሮ ሁኔታ ይህ ነው ማለት የሚቻል አይደለም። በጣም እየከበደ ነው። ከኔ በታች ሆኖ የሚኖር ደግሞ አለ። ከኔ በታች ያለ ሰው በምን ተዓር እንደሚኖር አላውቅም" በማለት የተጫናቸውን የኑሮ ክብደት ይናገራሉ። የአገሪቱ መንግሥት ለዋጋ ግሽበቱና ላስከተለው የኑሮ ውድነት እንደምክንያት አድርጎ የሚያቀርበው አገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን ነው። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የጥሬ ግብዓት ውድነት፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እያጋጠሙ ያሉ አለመረጋጋቶች እንዲሁም የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነት ለዋጋ ግሽበቱና ለኑሮ ውድነት እንደ ምክንያት የሚጠቀሱ ናቸው። ከጎረቤት ጋር እየተረዳዳን አብረን እንኖራለን አቶ አብዲ ገቢሳ 8 ሺህ ብር ገቢያቸውን በብልሃት ወጪ ያደርጋሉ። በባለቤታቸው ገቢ የቤት ኪራይ ከከፈሉ በኋላ በቀሪው ገንዘብ ቀሪ ወጪዎች እንደሚሸፈኑ ይናገራሉ። "እሷ ቤት ኪራይ ከቻለች እኔ ደግሞ እንደ ቀለብ፣ ትራንስፖርት፣ የትምህር ቤት ክፍያ፣ ለቤት ሠራተኛ ደመወዝ እክፍላለሁ። ከእነዚህ ወጪዎች የተረፈ ካለ ሌሎች ነገሮች አደርግበታለሁ" ይላሉ። "ካልበቃን ደግሞ ከሰው እንበደራለን። ደመወዝ እስኪደርስ ከሰው እንበደራለን። ከጎረቤት ጋር እየተረዳዳን አብረን እንኖራለን" ይላሉ የኑሮ ውድነቱን ለመቆጣጠር ምን እርምጃ መወሰድ አለበት? መንግሥት የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ አልያም ለመቆጣጠር እየወሰዳቸው ያሉት እርምጃዎች አጥጋቢ አደሉም በሚል ተደጋጋሚ ትችቶች ይቀርቡበታል። ምርት በማከማቸት ዋጋ እንዲንር ምክንያት በሚሆኑ ነጋዴዎች ላይ፣ በሸማች እና አምራች መካከል በመግባት የኑሮ ውድነት የሚያስከትሉ ነጋዴዎች ላይ በቂ እርምጃ አልተወሰደም የሚለው አንዱ መንግሥት ላይ የሚነሳ ቅሬታ ነው። በጅማ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት ለታ ሴራ (ዶ/ር) የአንድ ምርት ዋጋ ከፍ የሚለው ፍላጎት ከአቅርቦት ሲያንስ እንደሆነ አስታውሰው፤ መሠረታዊ አቅርቦቶች በገበያ እንዲኖሩ መንግሥት አምራቾችን መደገፍ አለበት ይላሉ። መምህሩ ምጣኔ ሃብታዊ ምክንያት በሌላው ሳይኖር በአንድ ለሊት የምርቶች ዋጋ የሚጨምርበት አጋጣሚ እንዳለ ይናገራሉ። "አንዳንድ ጊዜ በአገራችን በአንድ ለሊት 'ከገበያ ጠፍቷል' ሲሉ ይሰማል። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ትናንት የነበረ ዕቃ በአንድ ለሊት ጠፍቶ አደራ ሲባል ምርቱን ደበቀው ዋጋውን ከፍ አድርገው መሸጥ የሚፈልጉ ሰዎች መኖራቸውን ያሳያል" ይላሉ። ይህን የመቆጣጠር ኃላፊነት የመንግሥት መሆኑን የምጣኔ ሃብት መምህሩ ይናገራሉ። አቶ አብዲ ገቢሳ በተመሳሳይ "መንግሥት ታች ወርዶ ዋጋቸውን እየጨመሩ ያሉ ነገሮችን አይቶ መፍትሄ መስጠት ይችላል" ይላሉ የብር የውጭ ምንዛሬ የመግዛት አቅም መዳከም የተፈለገውን ያህል ውጤት በምጣኔ ሀብቱ ላይ እንዳላመጣ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በሌላ በኩል በምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች የሚነሳው የአገሪቱ የወጪና የገቢ ንግድን ማመጣጠን አልመቻሉ ነው። የባለፈውን ዓመት ስንመለከት አገሪቱ ከወጪ ንግድ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ስታገኝ በገቢ ንግድ ደግሞ 15 ቢሊዮን ዶላር ወጪ አድርጋለች፤ ይህንንም ከፍተኛ ልዩነት ማመጣጠን አለመቻሉ ከፍተኛ ማነቆ መፍጠሩን ባለሙያዎች የሚያስረዱት ነው። በተጨማሪም ከወጪ ንግዷ በላይ በከፍተኛ ሁኔታ ምርቶች ከውጭ አገር የምታስገባው ኢትዮጵያ የብር ምንዛሬ ማሽቆልቆል ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትን ማስከተሉና ይህም በዜጎች ላይ እያሳረፈ ያለው ኢኮኖሚያዊ ጫና ከፍተኛ ሆኗል። ከዋጋ ግሸበትም ጋር ተያይዞ መሰረታዊ የሚባሉ ሸቀጦች ዋጋ መናርም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። እነዚህ የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች በዋነኝነት የሚጠቅሱት መፍትሄ አገሪቷ የገቢና ወጪ ንግዷን አመጣጥና የንግድ ሚዛን ጉድለቷን ማስተካከል ነው። ይህንንም ለማድረግ ከግብርና ግብዓቶችና ቁሳቁሶች በመውጣት ወደ ማኑፋክቼሪንግ ዘርፉ መገባት መንግሥት በከፍተኛ ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራው የሚገባው ጉዳይ ነው ይላሉ። በተጨማሪም መንግሥት የወጪ ንግዱን ለማጠናከር በባለሙያ፣ የፋይናንስ ተቋማቱን እንዲሁም ሌሎች ማሻሻያዎችን በመስራት ችግሩን ሊቀርፍ እንደሚገባም የዘርፉ ባለሙያዎች የሚሰጡት አስተያየት ነው። ብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ምክር ቤት በበኩሉ በአገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይ ጫና የሚፈጥሩ ጉዳዮችን ለመቅረፍ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን እና እርምጃው ቀጣይነት እንደሚኖረው ይገልጻል። ከእነዚህ እርምጃዎች መካከል ግለቦች እንደ ስንዴ፣ ዘይት፣ የሕጻናት ወተት እና ስኳር ያሉ ምርቶች በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ ወደ አገር እንዲያስገቡ መፍቀድ አንዱ ነው። የማክሮ ኢኮኖሚ ምክር ቤቱ፤ "በቀጣይ ጊዜያት በኢኮኖሚያችን ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ጫናዎችን ለመቀነስ የተለያዩ አንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛሉ። የመድኃኒት፣ ነዳጅ፣ ማዳበርያ፣ ዘይት፣ እና ሌሎችም መሠረታዊ ሸቀጦች ግዥን በተገቢው ሁኔታ እንዲካሄድ፣ በእነዚህ ሸቀጦች አቅርቦት ላይ መንዛዛት እንዳይኖር በግዥ ሥርዓቱ ላይ አስፈላጊው ማስተካከያ ይወሰዳል" ብሏል።
ኢትዮጵውያንን እየፈተነ ያለው የኑሮ ውድነት መፍትሄው ምን ይሆን? አቶ አብዲሳ ገቢሳ ከባለቤታቸው እና ከሁለት ልጆቻቸው ጋር በአዲስ አበባ ከተማ መኖሪያ ቤት ተከራይተው ይኖራሉ። የመንግሥት ሠራተኛ የሆኑት አቶ አብዲ፤ ወርሃዊ ደመወዛቸው 5ሺህ ብር ሲሆን የባለቤታቸው ገቢ ሲጨመር የቤተሰቡ ወርሃዊ ገቢ 8 ሺህ ብር ይደርሳል። ይሁን እንጂ ይህን ቤተሰብ በ8ሺህ ብር ወርሃዊ ገቢ ማስተዳደር እጅጉን ለአቶ አብዲ ከብዷቸዋል። "5ሺህ ብር ወር ጠብቄ ነው የማገኘው ነው። ወጪ እና የማገኘው ገንዘብ አይመጣጠንም። የቤት ኪራይ አለ፣ ቀለብ አለ፣ ለልጆች ትምህር ቤት ወጪ አለ። ልጆች ትምህር ቤት ሲሄዱ ምሳ ይዘው ነው የሚሄዱት። ትራንስፖርት፣ ልብስ እንዲሁም ለሠራተኛ የሚከፈል አለ። ሕይወት በጣም እየጎዳን ነው" ይላሉ። በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የዋጋ ግሽበት በተከታታይ ጭማሪ ሲያሳይ ቆይቷል። በተለይም ኀብረተሰቡ በዕለት ተዕለት በሚጠቀምባቸው መሰረታዊ ፍጆታዎች፣ በግንባታ እቃዎችና በሌሎች ላይ እየታየ ያለው የዋጋ ንረት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዜጎችን ህይወት እጅግ እየተፈታተነው ይገኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በቅርቡ መንግሥት የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረጉ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ በኑሮ ውድነቱ ላይ ከፍተኛ ጫና ሊያሳርፍ እንደሚችል ነዋሪዎች እና የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የሚናገሩት ነው። የበርካታ አገራት ፈተና የሆነው የኑሮ ውድነት በያዝነው አውሮፓውያኑ 2022 በርካታ የዓለማችን አገራት ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አጋጥሟቸዋል። በዩናትድ ኪንግደም ባለፈው ወር በ30 ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የኑሮ ውድነት በ7 በመቶ ተመዝግቧል። ኬንያውያንም በምግብ ዘይት፣ በእህል እና በአትክልት እና ፍራፍሬ ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ አስቆጥቷቸዋል። ከቀናት በፊት የብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ፤ "አሁንም በኢኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ፈተና እየገጠመን ያለው ከዋጋ ግሽበት ጋር በተገናኘ ሲሆን፥ከአምናው የሚያዚያ ወር ጋር ሲነጻጸር የዋጋ ግሽበቱ 36.6 በመቶ ደርሷል። ነገሩን ይበልጥ ከባድ የሚያደርገው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እየተመዘገበ ያለው የምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ መሆኑ ነው፡፡" በማለት አትቷል። አቶ አብዲ ገቢያ የምርቶች ዋጋ 'በየቀኑ እና በየሰዓቱ' በሚባል ደረጃ እየጨመረ ነው ይላሉ። "በየቀኑ፤ በየሰዓቱ ይጨምራል። ለምሳሌ ባለፈው እሁድ ለልጅ ታሽጋ የምትሸጥ ወተት በ20 ብር ነበር የገዛሁት። ማታ ለልጅ ገዝቼ ልግባ ስል ዋጋው 30 ብር ሆኗል። 10 ብር ጨመረ ማለት ነው ! " በማለት ይናገራሉ። ይህ የመዲናዋ ከተማ ነዋሪ የኑሮ ውድነቱ መቋቋም ከምንችለው በላይ ሆኖብናል ይላሉ። "የኑሮ ሁኔታ ይህ ነው ማለት የሚቻል አይደለም። በጣም እየከበደ ነው። ከኔ በታች ሆኖ የሚኖር ደግሞ አለ። ከኔ በታች ያለ ሰው በምን ተዓር እንደሚኖር አላውቅም" በማለት የተጫናቸውን የኑሮ ክብደት ይናገራሉ። የአገሪቱ መንግሥት ለዋጋ ግሽበቱና ላስከተለው የኑሮ ውድነት እንደምክንያት አድርጎ የሚያቀርበው አገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን ነው። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የጥሬ ግብዓት ውድነት፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እያጋጠሙ ያሉ አለመረጋጋቶች እንዲሁም የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነት ለዋጋ ግሽበቱና ለኑሮ ውድነት እንደ ምክንያት የሚጠቀሱ ናቸው። ከጎረቤት ጋር እየተረዳዳን አብረን እንኖራለን አቶ አብዲ ገቢሳ 8 ሺህ ብር ገቢያቸውን በብልሃት ወጪ ያደርጋሉ። በባለቤታቸው ገቢ የቤት ኪራይ ከከፈሉ በኋላ በቀሪው ገንዘብ ቀሪ ወጪዎች እንደሚሸፈኑ ይናገራሉ። "እሷ ቤት ኪራይ ከቻለች እኔ ደግሞ እንደ ቀለብ፣ ትራንስፖርት፣ የትምህር ቤት ክፍያ፣ ለቤት ሠራተኛ ደመወዝ እክፍላለሁ። ከእነዚህ ወጪዎች የተረፈ ካለ ሌሎች ነገሮች አደርግበታለሁ" ይላሉ። "ካልበቃን ደግሞ ከሰው እንበደራለን። ደመወዝ እስኪደርስ ከሰው እንበደራለን። ከጎረቤት ጋር እየተረዳዳን አብረን እንኖራለን" ይላሉ የኑሮ ውድነቱን ለመቆጣጠር ምን እርምጃ መወሰድ አለበት? መንግሥት የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ አልያም ለመቆጣጠር እየወሰዳቸው ያሉት እርምጃዎች አጥጋቢ አደሉም በሚል ተደጋጋሚ ትችቶች ይቀርቡበታል። ምርት በማከማቸት ዋጋ እንዲንር ምክንያት በሚሆኑ ነጋዴዎች ላይ፣ በሸማች እና አምራች መካከል በመግባት የኑሮ ውድነት የሚያስከትሉ ነጋዴዎች ላይ በቂ እርምጃ አልተወሰደም የሚለው አንዱ መንግሥት ላይ የሚነሳ ቅሬታ ነው። በጅማ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት ለታ ሴራ (ዶ/ር) የአንድ ምርት ዋጋ ከፍ የሚለው ፍላጎት ከአቅርቦት ሲያንስ እንደሆነ አስታውሰው፤ መሠረታዊ አቅርቦቶች በገበያ እንዲኖሩ መንግሥት አምራቾችን መደገፍ አለበት ይላሉ። መምህሩ ምጣኔ ሃብታዊ ምክንያት በሌላው ሳይኖር በአንድ ለሊት የምርቶች ዋጋ የሚጨምርበት አጋጣሚ እንዳለ ይናገራሉ። "አንዳንድ ጊዜ በአገራችን በአንድ ለሊት 'ከገበያ ጠፍቷል' ሲሉ ይሰማል። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ትናንት የነበረ ዕቃ በአንድ ለሊት ጠፍቶ አደራ ሲባል ምርቱን ደበቀው ዋጋውን ከፍ አድርገው መሸጥ የሚፈልጉ ሰዎች መኖራቸውን ያሳያል" ይላሉ። ይህን የመቆጣጠር ኃላፊነት የመንግሥት መሆኑን የምጣኔ ሃብት መምህሩ ይናገራሉ። አቶ አብዲ ገቢሳ በተመሳሳይ "መንግሥት ታች ወርዶ ዋጋቸውን እየጨመሩ ያሉ ነገሮችን አይቶ መፍትሄ መስጠት ይችላል" ይላሉ የብር የውጭ ምንዛሬ የመግዛት አቅም መዳከም የተፈለገውን ያህል ውጤት በምጣኔ ሀብቱ ላይ እንዳላመጣ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በሌላ በኩል በምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች የሚነሳው የአገሪቱ የወጪና የገቢ ንግድን ማመጣጠን አልመቻሉ ነው። የባለፈውን ዓመት ስንመለከት አገሪቱ ከወጪ ንግድ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ስታገኝ በገቢ ንግድ ደግሞ 15 ቢሊዮን ዶላር ወጪ አድርጋለች፤ ይህንንም ከፍተኛ ልዩነት ማመጣጠን አለመቻሉ ከፍተኛ ማነቆ መፍጠሩን ባለሙያዎች የሚያስረዱት ነው። በተጨማሪም ከወጪ ንግዷ በላይ በከፍተኛ ሁኔታ ምርቶች ከውጭ አገር የምታስገባው ኢትዮጵያ የብር ምንዛሬ ማሽቆልቆል ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትን ማስከተሉና ይህም በዜጎች ላይ እያሳረፈ ያለው ኢኮኖሚያዊ ጫና ከፍተኛ ሆኗል። ከዋጋ ግሸበትም ጋር ተያይዞ መሰረታዊ የሚባሉ ሸቀጦች ዋጋ መናርም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። እነዚህ የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች በዋነኝነት የሚጠቅሱት መፍትሄ አገሪቷ የገቢና ወጪ ንግዷን አመጣጥና የንግድ ሚዛን ጉድለቷን ማስተካከል ነው። ይህንንም ለማድረግ ከግብርና ግብዓቶችና ቁሳቁሶች በመውጣት ወደ ማኑፋክቼሪንግ ዘርፉ መገባት መንግሥት በከፍተኛ ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራው የሚገባው ጉዳይ ነው ይላሉ። በተጨማሪም መንግሥት የወጪ ንግዱን ለማጠናከር በባለሙያ፣ የፋይናንስ ተቋማቱን እንዲሁም ሌሎች ማሻሻያዎችን በመስራት ችግሩን ሊቀርፍ እንደሚገባም የዘርፉ ባለሙያዎች የሚሰጡት አስተያየት ነው። ብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ምክር ቤት በበኩሉ በአገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይ ጫና የሚፈጥሩ ጉዳዮችን ለመቅረፍ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን እና እርምጃው ቀጣይነት እንደሚኖረው ይገልጻል። ከእነዚህ እርምጃዎች መካከል ግለቦች እንደ ስንዴ፣ ዘይት፣ የሕጻናት ወተት እና ስኳር ያሉ ምርቶች በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ ወደ አገር እንዲያስገቡ መፍቀድ አንዱ ነው። የማክሮ ኢኮኖሚ ምክር ቤቱ፤ "በቀጣይ ጊዜያት በኢኮኖሚያችን ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ጫናዎችን ለመቀነስ የተለያዩ አንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛሉ። የመድኃኒት፣ ነዳጅ፣ ማዳበርያ፣ ዘይት፣ እና ሌሎችም መሠረታዊ ሸቀጦች ግዥን በተገቢው ሁኔታ እንዲካሄድ፣ በእነዚህ ሸቀጦች አቅርቦት ላይ መንዛዛት እንዳይኖር በግዥ ሥርዓቱ ላይ አስፈላጊው ማስተካከያ ይወሰዳል" ብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-61418643
2health
ኮሮናቫይረስ ፡ ሲሼልስ የኮቪድ -19 ክትባት መስጠት ጀመረች
በርካቶች ለመዝናናት የሚመርጧት አፍሪካዊቷ ደሴታማ አገር፣ ሲሼልስ የኮሮናቫይረስ ክትባት መስጠት መጀመሯን አስታወቀች። ይህንን በማድረግም ከጊኒ ቀጥላ ሁለተኛዋ አፍሪካዊት አገር ሆናለች። ጊኒ የሩሲያውን ስፑትኒክ ቪ ክትባት አነስተኛ ዶዝ ያገኘችው ባለፈው ወር ነበር። የሲሼልስ ፕሬዚደንት ዋቨል ራምካላዋን ዕሁድ እለት የመጀመሪያውን ክትባት በቀጥታ ቴሌቪዥን ሥርጭት እየታዩ ተከትበዋል። ፕሬዚደንቱ "የተሰማኝ ልክ እንደማንኛውም ክትባት ነው" በማለት ሌሎች ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ አበረታተዋል። ደሴታማዋ አገር ሲሼልስ ቻይና ያበለፀገችውን ክትባት ከተባበሩት አርብ ኤምሬትስ 50 ሺህ ዶዝ [መጠን] በእርዳታ አግኝታለች። ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ዛሬ የጤና ባለሙያዎች መከተብ እንደሚጀምሩ እና ከዚያ በኋላ ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ክትባቱን እንደሚወስዱ ተናግረዋል። ይህ ሲጠናቀቅም ክትባቱ ለሌሎች ሕዝቦቿ ይዳረሳል ተብሏል። አገሪቷ ከሁለት ወር እስከ ሦስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ካሏት 98 ሺህ ሕዝብ 70 በመቶውን ለመከተብ አቅዳለች። ይህንን ለማሳካትም በአንድ ቀን 1 ሺህ ሰዎችን መከተብ ይጠይቃል። ሲሼልስ እስካሁን 508 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን የመዘገበች ሲሆን ያስተናገደችው አንድ ሞት ብቻ ነው። ይሁን እንጂ ባለሥልጣናት በቅርቡ የታየው የቫይረሱ ሥርጭት አስግቷቸዋል። ቅዳሜ ዕለት ብቻ በአገሪቷ 57 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተገልጿል።
ኮሮናቫይረስ ፡ ሲሼልስ የኮቪድ -19 ክትባት መስጠት ጀመረች በርካቶች ለመዝናናት የሚመርጧት አፍሪካዊቷ ደሴታማ አገር፣ ሲሼልስ የኮሮናቫይረስ ክትባት መስጠት መጀመሯን አስታወቀች። ይህንን በማድረግም ከጊኒ ቀጥላ ሁለተኛዋ አፍሪካዊት አገር ሆናለች። ጊኒ የሩሲያውን ስፑትኒክ ቪ ክትባት አነስተኛ ዶዝ ያገኘችው ባለፈው ወር ነበር። የሲሼልስ ፕሬዚደንት ዋቨል ራምካላዋን ዕሁድ እለት የመጀመሪያውን ክትባት በቀጥታ ቴሌቪዥን ሥርጭት እየታዩ ተከትበዋል። ፕሬዚደንቱ "የተሰማኝ ልክ እንደማንኛውም ክትባት ነው" በማለት ሌሎች ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ አበረታተዋል። ደሴታማዋ አገር ሲሼልስ ቻይና ያበለፀገችውን ክትባት ከተባበሩት አርብ ኤምሬትስ 50 ሺህ ዶዝ [መጠን] በእርዳታ አግኝታለች። ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ዛሬ የጤና ባለሙያዎች መከተብ እንደሚጀምሩ እና ከዚያ በኋላ ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ክትባቱን እንደሚወስዱ ተናግረዋል። ይህ ሲጠናቀቅም ክትባቱ ለሌሎች ሕዝቦቿ ይዳረሳል ተብሏል። አገሪቷ ከሁለት ወር እስከ ሦስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ካሏት 98 ሺህ ሕዝብ 70 በመቶውን ለመከተብ አቅዳለች። ይህንን ለማሳካትም በአንድ ቀን 1 ሺህ ሰዎችን መከተብ ይጠይቃል። ሲሼልስ እስካሁን 508 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን የመዘገበች ሲሆን ያስተናገደችው አንድ ሞት ብቻ ነው። ይሁን እንጂ ባለሥልጣናት በቅርቡ የታየው የቫይረሱ ሥርጭት አስግቷቸዋል። ቅዳሜ ዕለት ብቻ በአገሪቷ 57 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55614499
3politics
በሚየንማር ተቃዋሚዎች ላይ እንደተተኮሰ ተመድ ገለጸ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዑክ የሚየንማር የጸጥታ ኃይሎች ተቃዋሚዎች ላይ እንደተኮሱ ገለጹ። ይህም ዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰ ነው። በጄኔቫ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ልዑኩ ቶማስ አንድሪውስ የመፈንቅለ መንግሥቱን ጠንሳሾች ወቅሰዋል። በአገሪቱ ያልተገቡ ድርጊቶች እየተፈጸሙ እንደሚገኙ የፎቶ ማስረጃ እንዳለም ጠቅሰዋል። ልዑኩ ሚየንማር ላይ የመሣሪያ ማዕቀብ እንዲጣልም ጠይቀዋል። የወታደራዊ ኃይሉ ኃላፊ ተቃውሞ እንዲቆም ቢጠይቁም ለተከታታይ ቀናት ሰልፉ እንደቀጠለ ነው። በሚየንማር የአንድነት ቀን ሲከበር ኃላፊው ጀነራል ሚን አውግ ህላግ "አገራዊ አንድነት ያስፈልገናል" ቢሉም ሕዝቡ አን ሳን ሱ ቺን ጨምሮ ሌሎችም አመራሮች ከቁም እስር እንዲለቀቁ እየጠየቀ ነው። በሚየንማር የአንድነት ቀን ሲከበር ወታደራዊ ኃይሉ 55 የውጪ ዜጎችን ጨምሮ 23,000 ታራሚዎችን ከእስር ለቋል። የአንድነት ቀን የሚከበረው እአአ በ1947 በአን ሳን ሱ ቺ አባት አማካይነት የተፈረመውን ስምምነት በማስታወስ ነው። ስዛኣር ሳን የተባለ ተማሪና የመብት ተሟጋች ለቢቢሲ እንደተናገረው ታራሚዎች የተፈቱት ተቃዋሚዎች ላይ ጥቃት ሊያደርሱ ነው ብሎ ይሰጋል። የተመድ ልዑክ እንዳሉት የድርጅቱ የሰብዓዊ መብት መርማሪዎች ሚየንማር ለመግባት ፍቃድ አላገኙም። ሆኖም ግን ተቃዋሚዎች ላይ ጥይት እንደተተኮሰ ማስረጃ ተገኝቷል። ተመድ የቃል መግለጫ ከማውጣት በዘለለ የመሣሪያ ሽያጭ ላይ ማዕቀብ እንዲጥልና ወታደራዊ ኃላፊዎች የጉዞ ክልከላ እንዲወጣባቸውም ጠይቀዋል። የሳምንቱ መባቻ ላይ ሚያ ትዌ ተዌ ካሂግ የተባለች የ19 ዓመት ወጣት በጥይት ጭንቅላቷን መመታቷ አይዘነጋም። ለሕይወቷ አስጊ ሁኔታ ውስጥም ትገኛለች። ፓሊሶች ተቃዋሚዎችን ለመበተን ውሃ፣ የፕላስቲክ ጥይትና መሣሪያ ተጠቅመዋል። አንድ የቀይ መስቀል ኃላፊ ለሮይተርስ እንደገለጹት ሦስት ሰዎች በፕላስቲክ ጥይት ጉዳት ደርሶባቸዋል። አሜሪካን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች ሚየንማር ውስጥ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፣ መሪዎች እንዲለቀቁ እየጠየቁ ነው። ወታደራዊ ኃይሉ የብሔራዊ ምርጫ ውጤት ተጭበርብሯል ብሎ መፈንቅለ መንግሥት ካካሄደ 12 ቀናት ተቆጥረዋል። ወታደራዊ ኃይሉ ተቃዋሚዎችን የሚደግፍ ሲሆን፤ አዲስ ፓርላማ መመሥረት ጀምሯል። አን ሳን ሱ ቺ እና ሌሎች መሪዎች በቁም እስር ላይ ሲሆኑ፤ በሕግ ወጥ መንገድ አገር ውስጥ የገባ የራድዮ መገናኛ (ዋኪ-ቶኪ) በመያዝ ክስ ተመሥርቶባቸዋል።
በሚየንማር ተቃዋሚዎች ላይ እንደተተኮሰ ተመድ ገለጸ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዑክ የሚየንማር የጸጥታ ኃይሎች ተቃዋሚዎች ላይ እንደተኮሱ ገለጹ። ይህም ዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰ ነው። በጄኔቫ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ልዑኩ ቶማስ አንድሪውስ የመፈንቅለ መንግሥቱን ጠንሳሾች ወቅሰዋል። በአገሪቱ ያልተገቡ ድርጊቶች እየተፈጸሙ እንደሚገኙ የፎቶ ማስረጃ እንዳለም ጠቅሰዋል። ልዑኩ ሚየንማር ላይ የመሣሪያ ማዕቀብ እንዲጣልም ጠይቀዋል። የወታደራዊ ኃይሉ ኃላፊ ተቃውሞ እንዲቆም ቢጠይቁም ለተከታታይ ቀናት ሰልፉ እንደቀጠለ ነው። በሚየንማር የአንድነት ቀን ሲከበር ኃላፊው ጀነራል ሚን አውግ ህላግ "አገራዊ አንድነት ያስፈልገናል" ቢሉም ሕዝቡ አን ሳን ሱ ቺን ጨምሮ ሌሎችም አመራሮች ከቁም እስር እንዲለቀቁ እየጠየቀ ነው። በሚየንማር የአንድነት ቀን ሲከበር ወታደራዊ ኃይሉ 55 የውጪ ዜጎችን ጨምሮ 23,000 ታራሚዎችን ከእስር ለቋል። የአንድነት ቀን የሚከበረው እአአ በ1947 በአን ሳን ሱ ቺ አባት አማካይነት የተፈረመውን ስምምነት በማስታወስ ነው። ስዛኣር ሳን የተባለ ተማሪና የመብት ተሟጋች ለቢቢሲ እንደተናገረው ታራሚዎች የተፈቱት ተቃዋሚዎች ላይ ጥቃት ሊያደርሱ ነው ብሎ ይሰጋል። የተመድ ልዑክ እንዳሉት የድርጅቱ የሰብዓዊ መብት መርማሪዎች ሚየንማር ለመግባት ፍቃድ አላገኙም። ሆኖም ግን ተቃዋሚዎች ላይ ጥይት እንደተተኮሰ ማስረጃ ተገኝቷል። ተመድ የቃል መግለጫ ከማውጣት በዘለለ የመሣሪያ ሽያጭ ላይ ማዕቀብ እንዲጥልና ወታደራዊ ኃላፊዎች የጉዞ ክልከላ እንዲወጣባቸውም ጠይቀዋል። የሳምንቱ መባቻ ላይ ሚያ ትዌ ተዌ ካሂግ የተባለች የ19 ዓመት ወጣት በጥይት ጭንቅላቷን መመታቷ አይዘነጋም። ለሕይወቷ አስጊ ሁኔታ ውስጥም ትገኛለች። ፓሊሶች ተቃዋሚዎችን ለመበተን ውሃ፣ የፕላስቲክ ጥይትና መሣሪያ ተጠቅመዋል። አንድ የቀይ መስቀል ኃላፊ ለሮይተርስ እንደገለጹት ሦስት ሰዎች በፕላስቲክ ጥይት ጉዳት ደርሶባቸዋል። አሜሪካን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች ሚየንማር ውስጥ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፣ መሪዎች እንዲለቀቁ እየጠየቁ ነው። ወታደራዊ ኃይሉ የብሔራዊ ምርጫ ውጤት ተጭበርብሯል ብሎ መፈንቅለ መንግሥት ካካሄደ 12 ቀናት ተቆጥረዋል። ወታደራዊ ኃይሉ ተቃዋሚዎችን የሚደግፍ ሲሆን፤ አዲስ ፓርላማ መመሥረት ጀምሯል። አን ሳን ሱ ቺ እና ሌሎች መሪዎች በቁም እስር ላይ ሲሆኑ፤ በሕግ ወጥ መንገድ አገር ውስጥ የገባ የራድዮ መገናኛ (ዋኪ-ቶኪ) በመያዝ ክስ ተመሥርቶባቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56041930
5sports
ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ ከዓለም ዋንጫ ውጭ ሆነ
ሴኔጋላዊው አጥቂ ሳዲዮ ማኔ ለክለቡ ባየር ሙኒክ ሲጫወት በደረሰበት ጉዳት ምንክያት የጉልበት ቀዶ ህክምና በማከናወኑ ከዓለም ዋንጫ ውጭ ሆነ። ማክሰኞ ዕለት የሴኔጋል እግር ኳስ ፌደሬሽን ማኔ ከዓለም ዋንጫው “መጀመሪያ ጨዋታችን” ውጭ ይሆናል ብሎ ነበር። ሐሙስ በተደረገለት ተጨማሪ ምርመራም ቀዶ ህክምና እንደሚያስፈለገው ተረጋግጧል። ባየር ሙኒክ ወርደር ብሬመንን ባሸነፈበት ጨዋታ ነበር ሴኔጋላዊው ጉዳት ደርሶበት ከሜዳ የወጣው። ባየር ሙኒክ ተጫዋቹ ስኬታማ ቀዶ ጥገና ማከናወኑን አስታውቋል። “ተጫዋቹ በጥቂት ቀናት ማገገም ይጀምራል” ብሏል ክለቡ። ሴኔጋል በዓለም ዋንጫው የመጀመሪያ ጨዋታዋን ሰኞ ዕለት ከኔዘላንናድስ ጋር ትጀምራለች። በቀጣይም ከአስተናጋጇ ኳታር ቀጥሎ ደግሞ ኤኳዶር ጋር ትገናኛለች። ለሁለት ጊዜ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋች ለመሆን የበቃው ማኔ የብሔራዊ ቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች ነው። ባለፈው የካቲት ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያውን የአፍሪካ ዋንጫ እንዲያነሳ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በፍጻሜው ጨዋታ ግብጽን ሲያሸንፉ ወሳኟን የመለያ ምት አስቆጥሮ ነበር። ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ በድጋሚ ከግብጽ ጋር ሲገናኙም ማኔ ለቡድኑ ባለውለታ መሆኑን አረጋግጧል።
ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ ከዓለም ዋንጫ ውጭ ሆነ ሴኔጋላዊው አጥቂ ሳዲዮ ማኔ ለክለቡ ባየር ሙኒክ ሲጫወት በደረሰበት ጉዳት ምንክያት የጉልበት ቀዶ ህክምና በማከናወኑ ከዓለም ዋንጫ ውጭ ሆነ። ማክሰኞ ዕለት የሴኔጋል እግር ኳስ ፌደሬሽን ማኔ ከዓለም ዋንጫው “መጀመሪያ ጨዋታችን” ውጭ ይሆናል ብሎ ነበር። ሐሙስ በተደረገለት ተጨማሪ ምርመራም ቀዶ ህክምና እንደሚያስፈለገው ተረጋግጧል። ባየር ሙኒክ ወርደር ብሬመንን ባሸነፈበት ጨዋታ ነበር ሴኔጋላዊው ጉዳት ደርሶበት ከሜዳ የወጣው። ባየር ሙኒክ ተጫዋቹ ስኬታማ ቀዶ ጥገና ማከናወኑን አስታውቋል። “ተጫዋቹ በጥቂት ቀናት ማገገም ይጀምራል” ብሏል ክለቡ። ሴኔጋል በዓለም ዋንጫው የመጀመሪያ ጨዋታዋን ሰኞ ዕለት ከኔዘላንናድስ ጋር ትጀምራለች። በቀጣይም ከአስተናጋጇ ኳታር ቀጥሎ ደግሞ ኤኳዶር ጋር ትገናኛለች። ለሁለት ጊዜ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋች ለመሆን የበቃው ማኔ የብሔራዊ ቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች ነው። ባለፈው የካቲት ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያውን የአፍሪካ ዋንጫ እንዲያነሳ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በፍጻሜው ጨዋታ ግብጽን ሲያሸንፉ ወሳኟን የመለያ ምት አስቆጥሮ ነበር። ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ በድጋሚ ከግብጽ ጋር ሲገናኙም ማኔ ለቡድኑ ባለውለታ መሆኑን አረጋግጧል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c28371j103wo
2health
ኮሮናቫይረስ፡ አሜሪካ "የከፋ ፈተና" ሊገጥማት እንደሚችል ከፍተኛ የጤና ባለሙያ አስጠነቀቁ
በአሜሪካ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ እና ታምመው ወደ ሆስፒታል የሚሄዱ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ አገሪቱ "የከፋ ፈተና" ሊገጥማት እንደሚችል አንድ ከፍተኛ ሳይንቲስት አስጠነቀቁ። ሰኞ ዕለት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተለያዩ ግዛት ፖለቲከኞችን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግን መልሰው እንደ ግዴታ እንዲያስቀምጡ ጥሪ አቅርበው ነበር። በሚያዚያ ወር አጋማሽ ላይም 90 በመቶ የሚሆኑ አሜሪካውያን አዋቂዎችም የወረርሽኙን መከላከያ እንደሚከተቡም ቃል ገብተዋል። አሜሪካ ባለፈው ሳምንት ብቻ 60,000 ያህል ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን በምርመራ አረጋግጣለች። የአሜሪካ ሕብረተሰብ ጤና ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶ/ር ሮሼሌ ዋሌኒስኪ በዋይት ሐውስ በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ "የከፋ ችግር ሊገጥመን እንደሚችል እየተሰማኝ ስላለው ስሜት አስተያየት መስጠት እፈልጋለሁ" ያሉ ሲሆን አክለውም "ተስፋ ለማድረግ በርካታ ምክንያቶች አሉን ነገር ግን አሁን በጣም ፈርቻለሁ" ብለዋል። ባለፉት ሳምንታት በቫይረሱ የተያዙ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር በቀን 60 ሺህ ደርሷል። ዶ/ር ዋሌንስኪ አሜሪካ ዳግም ሌላ የኮቪድ-19 ስርጭት እንድታስመዘግብ አልያም በበርካታ አውሮፓ አገራት እንደሆነው ከፍተኛ ሞትን እንድታይ እንደማይፈልጉ ተናግረዋል። በሚቺጋን እና ኒውዮርክ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፍጥነት እየተስፋፋ ይገኛል። በቴሌቪዥን ቀርበው ንግግር ያደረጉት ባይደን የግዛት አስተዳዳሪዎች ነዋሪዎቻቸው የአፍ መሸፈኛ ጭምብል እንዲያደርጉ በድጋሚ እንዲያስገድዱ ጠይቀዋል። በአሜሪካ የኮሮናቫይረስ መከላከያ መመሪያዎች ከግዘት ግዛት ይለያያል። ባይደን "አሁን መመሪያዎቻችንን ካላላን ቫይረሱ ከመቀነስ ይልቅ ወደ ከፋ ደረጃ ሲሸጋገር እናየዋለን" ብለዋል። ባይደን አሜሪካ ክትባቱን በማዳረስ ረገድ ያሳያችውን ውጤት በመጥቀስ ከእቅዷ ቀድማለች ብለዋል። በሚያዚያ ወር ክትባት ለመውሰድ ከሚችሉ አዋቂዎች መካከል 90 በመቶዎቹ ከቤታቸው በቅርብ ርቀት አገልግሎቱን እንዲያገኙ ለማድረግ ቃል ገብተዋል። ባይደን አክለውም በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ ሁሉም አዋቂ አሜሪካውያን አንዱን ክትባት ለመውሰድ ይመዘገባሉ ሲሉ እቅዳቸውን ይፋ አድርገዋል። የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣተሪያ ማዕከል እድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ ከሆነው መካከል ከአምስት አዋቂ አሜሪካውያን መካከል አንዱ ሙሉ ሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ተከትበዋል ሲል አስታውቋል። ክትባቱን ለማግኘት የሚችለው ማን ነው? የሚለው ከግዛት ግዛት ይለያያል። ነገር ግን በሁሉም ግዛቶች በቅድሚያ የጤና ባለሙያዎች፣ ከዚያ በመቀጠል አድሜያቸው ከ65 በላይ ከሆኑት ግለሰቦች ክትባቱን ያገኛሉ። በጆርጂያ እና አሪዞና ደግሞ እድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ የሆነ ክትባቱን ማግኘት ይችላሉ። ባይደን አሜሪካውያን አካላዊ ርቀታቸውን እንዲጠብቁ እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ኮሮናቫይረስ፡ አሜሪካ "የከፋ ፈተና" ሊገጥማት እንደሚችል ከፍተኛ የጤና ባለሙያ አስጠነቀቁ በአሜሪካ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ እና ታምመው ወደ ሆስፒታል የሚሄዱ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ አገሪቱ "የከፋ ፈተና" ሊገጥማት እንደሚችል አንድ ከፍተኛ ሳይንቲስት አስጠነቀቁ። ሰኞ ዕለት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተለያዩ ግዛት ፖለቲከኞችን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግን መልሰው እንደ ግዴታ እንዲያስቀምጡ ጥሪ አቅርበው ነበር። በሚያዚያ ወር አጋማሽ ላይም 90 በመቶ የሚሆኑ አሜሪካውያን አዋቂዎችም የወረርሽኙን መከላከያ እንደሚከተቡም ቃል ገብተዋል። አሜሪካ ባለፈው ሳምንት ብቻ 60,000 ያህል ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን በምርመራ አረጋግጣለች። የአሜሪካ ሕብረተሰብ ጤና ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶ/ር ሮሼሌ ዋሌኒስኪ በዋይት ሐውስ በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ "የከፋ ችግር ሊገጥመን እንደሚችል እየተሰማኝ ስላለው ስሜት አስተያየት መስጠት እፈልጋለሁ" ያሉ ሲሆን አክለውም "ተስፋ ለማድረግ በርካታ ምክንያቶች አሉን ነገር ግን አሁን በጣም ፈርቻለሁ" ብለዋል። ባለፉት ሳምንታት በቫይረሱ የተያዙ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር በቀን 60 ሺህ ደርሷል። ዶ/ር ዋሌንስኪ አሜሪካ ዳግም ሌላ የኮቪድ-19 ስርጭት እንድታስመዘግብ አልያም በበርካታ አውሮፓ አገራት እንደሆነው ከፍተኛ ሞትን እንድታይ እንደማይፈልጉ ተናግረዋል። በሚቺጋን እና ኒውዮርክ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፍጥነት እየተስፋፋ ይገኛል። በቴሌቪዥን ቀርበው ንግግር ያደረጉት ባይደን የግዛት አስተዳዳሪዎች ነዋሪዎቻቸው የአፍ መሸፈኛ ጭምብል እንዲያደርጉ በድጋሚ እንዲያስገድዱ ጠይቀዋል። በአሜሪካ የኮሮናቫይረስ መከላከያ መመሪያዎች ከግዘት ግዛት ይለያያል። ባይደን "አሁን መመሪያዎቻችንን ካላላን ቫይረሱ ከመቀነስ ይልቅ ወደ ከፋ ደረጃ ሲሸጋገር እናየዋለን" ብለዋል። ባይደን አሜሪካ ክትባቱን በማዳረስ ረገድ ያሳያችውን ውጤት በመጥቀስ ከእቅዷ ቀድማለች ብለዋል። በሚያዚያ ወር ክትባት ለመውሰድ ከሚችሉ አዋቂዎች መካከል 90 በመቶዎቹ ከቤታቸው በቅርብ ርቀት አገልግሎቱን እንዲያገኙ ለማድረግ ቃል ገብተዋል። ባይደን አክለውም በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ ሁሉም አዋቂ አሜሪካውያን አንዱን ክትባት ለመውሰድ ይመዘገባሉ ሲሉ እቅዳቸውን ይፋ አድርገዋል። የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣተሪያ ማዕከል እድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ ከሆነው መካከል ከአምስት አዋቂ አሜሪካውያን መካከል አንዱ ሙሉ ሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ተከትበዋል ሲል አስታውቋል። ክትባቱን ለማግኘት የሚችለው ማን ነው? የሚለው ከግዛት ግዛት ይለያያል። ነገር ግን በሁሉም ግዛቶች በቅድሚያ የጤና ባለሙያዎች፣ ከዚያ በመቀጠል አድሜያቸው ከ65 በላይ ከሆኑት ግለሰቦች ክትባቱን ያገኛሉ። በጆርጂያ እና አሪዞና ደግሞ እድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ የሆነ ክትባቱን ማግኘት ይችላሉ። ባይደን አሜሪካውያን አካላዊ ርቀታቸውን እንዲጠብቁ እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56563215
5sports
እግር ኳስ፡ 'ከዘረኝነት መልዕክት' እስካልተጠበቁ ውጤቶች ያስመዘገበው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ
ትናንት ምሽት ፒኤስጂ እና ኢስታንቡል ባሻክሺር በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ሊያደርጉት የነበረው የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ በዕለቱ አራተኛ ዳኛ የዘረኝነት መልዕክት ተላልፏል በሚል ተጫዋቾች ሜዳውን ለቅቀው በመውጣታቸው ጨዋታው በድጋሚ ዛሬ ሊካሄድ እንደሆነ ተገልጿል። ኢስታንቡል ባሻክሺር እግር ኳስ ክለብ እንዳስታወቀው አራተኛ ዳኛው ሴባስቺያን ኮልትስኩ ስለምክትል አሰልጣኙ ፒዬር ዌብ ሲናገሩ ዘረኛ የሆነ መልዕክት አስተላልፈዋል ብሏል። የቀድሞ የካሜሩን ተጫዋቹ ዌቦ ከሜዳ ውጪ የቀይ ካርድ ሰለባ ሆኖም ነበር። ይህንን ተከትሎ የኢስታንቡል ባሻክሺር ተጫዋቾች ሜዳውን ለቅቀው የወጡ ሲሆን የፒኤስጂ ተጫዋቾችም ተከትለዋቸው ወደ መልበሻ ክፍል ገብተዋል። ክስተቱ የተፈጠረው የመጨረሻ የምድብ ጨዋታው ተጀምሮ 14 ደቂቃዎች ያክል ከተጫወቱ በኋላ ሲሆን ተጫዋቾቹ ሜዳውን ለቅቀው እስከሚወጡ ድረስ ደግሞ ምንም አይነት ግብ አልተቆጠረም ነበር። ጨዋታው ዛሬ ምሽት በድጋሚ እንደሚካሄድ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ያስታወቀ ሲሆን ትናንት ምሽት ማንቸስተር ዩናይትድ በአርቢ ላይፕሲዥ መሸነፉን ተከትሎ ደግሞ ፒኤስጂዎች ከጨዋታው በፊት ወደ ጥሎ ማለፍ ድልድል ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ባወጣው መግለጫ '' ከሁለቱም ቡድኖች ጋር ከተነጋገርን በኋላ ጨዋታው በድጋሚ ከቆመበት እንዲጀምርና ሌሎች ዳኛዎች ጨዋታውን እንዲመሩት ወስነናል'' ብሏል። አክሎም ''በዚህ ጉዳይ ዙሪያ እጅግ ፈጣንና ጥልቅ ምርመራ ይካሄዳል፤ የተጣሰ ህግ ካለም ተገቢው እርምጃ ይወሰዳል'' ሲል አስታውቋል። ተቀያሪ ወንበር ላይ የነበረው የኢስታንቡል ባሻክሺር አጥቂው ዴምባ ባ ከአራተኛው ዳኛ ጋር ''ለምን ያኛው ጥቁር ሰው'' ብለህ መጥቀስ አስፈለገህ እያለ ሲከራከር ተስተውሏል። በሌላ ምስል ደግሞ የፒኤስጂው ተከላካይ ''ይህ ሰው የምሩን ነው? በቃ እንሂድ'' ሲል ታይቷል። ምንም እንኳን የፒኤስጂ ተጫዋቾች ለረጅም ሰአት መልበሻ ክፍሉ አካባቢ ሰውነታቸውን እያሟሟቁ ቢጠብቁም የኢስታንቡል ባሻክሺር ተጫዋቾች ባለመመለሳቸው ምክንያት ጨዋታው ለመቋረጥ ግድ ሆኗል። የፒኤስጂው አጥቂ ኪሊያን ምባፔም በበኩሉ በትዊተር ገጹ ላይ ባስተላለፈው መልዕክት ''ዘረኝነት ይብቃ። ዌብ አብረንህ ነን'' ሲል ጽፏል። በሌሎች ጨዋታዎች በጉጉት ሲጠበቅ የማንቸስተር ዩናይትድና አር ቢ ላይፕሲዥ ጨዋታ በአርቢ ላእፕሲዥ 3 ለ2 አሸናፊነት ተጠናቋል። ምንም እንኳን ማንቸስተር ዩናይትዶት ከምድቡ ለማለፍ አቻ ብቻ የሚቃቸው የነበረ ቢሆንም በመጀመሪያዎች 20 ደቂቃዎች አርቢ ላይፕሲዦችን መቋቋም አቅቷቸው ተስተውሏል። ጨዋታው በተጀመረ 13 ደቂቃዎች ውስጥም ሁለት ግቦችን አስተናግደው የመጀመሪያው አጋማሽ 2 ለባዶ የተጠናቀቀ ቢሆንም በሁለተኛው አጋማሽ ሌላ ሶስተኛ ግብ አስተናግደዋል። በጨዋታው መጠናቀቂያ አካባቢ ማንቸስተር ዩናይትዶች ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ቢችሉም አቻ ማድረግ ግን ሳይችሉ ቀርተዋል። በዚህም ከምድቡ አለማለፋቸውን አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል በሌላኛው የተጠበቀ ጨዋታ ጁቬንቱስ ባርሴሎናን 3 ለባዶ ማሸነፍ ችሏል። ሁለቱን ግቦች ክርስቲያኖ ሮናልድ በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠረ ሲሆን ሶስተኛዋ ግብ ደግሞ ማክኬኒ በጨዋታ ማስቆጠር ችሏል። ይህን ውጤት ተከትሎ ሁለቱም ቡድኖች ከምድባቸው አንደኛና ሁለተኛ ሆነው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። ዛሬም የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ቀጥለው የሚካሄዱ ሲሆን አትሌቲኮ ማድሪድ ከሬድ ቡል ሳልዝበርግ እንዲሁም ሪያል ማድሪድ ከቦርሺያ ሞንቼግላድባክ የሚያደርጉት ወሳኝ ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል። እስካሁን በተደረጉ ጨዋታዎች የጁቬንቱሱ አልቫሮ ሞራታ፣ የቦርሺያ ዶርትሞንዱ ኢርሊንግ ሃላንድ እና የማንቸስተር ዩናይትዱ ማርከስ ራሽፎርድ በ6 ግቦች ኮኮብ ጎል አግቢነቱን እየመሩት ነው።
እግር ኳስ፡ 'ከዘረኝነት መልዕክት' እስካልተጠበቁ ውጤቶች ያስመዘገበው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ትናንት ምሽት ፒኤስጂ እና ኢስታንቡል ባሻክሺር በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ሊያደርጉት የነበረው የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ በዕለቱ አራተኛ ዳኛ የዘረኝነት መልዕክት ተላልፏል በሚል ተጫዋቾች ሜዳውን ለቅቀው በመውጣታቸው ጨዋታው በድጋሚ ዛሬ ሊካሄድ እንደሆነ ተገልጿል። ኢስታንቡል ባሻክሺር እግር ኳስ ክለብ እንዳስታወቀው አራተኛ ዳኛው ሴባስቺያን ኮልትስኩ ስለምክትል አሰልጣኙ ፒዬር ዌብ ሲናገሩ ዘረኛ የሆነ መልዕክት አስተላልፈዋል ብሏል። የቀድሞ የካሜሩን ተጫዋቹ ዌቦ ከሜዳ ውጪ የቀይ ካርድ ሰለባ ሆኖም ነበር። ይህንን ተከትሎ የኢስታንቡል ባሻክሺር ተጫዋቾች ሜዳውን ለቅቀው የወጡ ሲሆን የፒኤስጂ ተጫዋቾችም ተከትለዋቸው ወደ መልበሻ ክፍል ገብተዋል። ክስተቱ የተፈጠረው የመጨረሻ የምድብ ጨዋታው ተጀምሮ 14 ደቂቃዎች ያክል ከተጫወቱ በኋላ ሲሆን ተጫዋቾቹ ሜዳውን ለቅቀው እስከሚወጡ ድረስ ደግሞ ምንም አይነት ግብ አልተቆጠረም ነበር። ጨዋታው ዛሬ ምሽት በድጋሚ እንደሚካሄድ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ያስታወቀ ሲሆን ትናንት ምሽት ማንቸስተር ዩናይትድ በአርቢ ላይፕሲዥ መሸነፉን ተከትሎ ደግሞ ፒኤስጂዎች ከጨዋታው በፊት ወደ ጥሎ ማለፍ ድልድል ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ባወጣው መግለጫ '' ከሁለቱም ቡድኖች ጋር ከተነጋገርን በኋላ ጨዋታው በድጋሚ ከቆመበት እንዲጀምርና ሌሎች ዳኛዎች ጨዋታውን እንዲመሩት ወስነናል'' ብሏል። አክሎም ''በዚህ ጉዳይ ዙሪያ እጅግ ፈጣንና ጥልቅ ምርመራ ይካሄዳል፤ የተጣሰ ህግ ካለም ተገቢው እርምጃ ይወሰዳል'' ሲል አስታውቋል። ተቀያሪ ወንበር ላይ የነበረው የኢስታንቡል ባሻክሺር አጥቂው ዴምባ ባ ከአራተኛው ዳኛ ጋር ''ለምን ያኛው ጥቁር ሰው'' ብለህ መጥቀስ አስፈለገህ እያለ ሲከራከር ተስተውሏል። በሌላ ምስል ደግሞ የፒኤስጂው ተከላካይ ''ይህ ሰው የምሩን ነው? በቃ እንሂድ'' ሲል ታይቷል። ምንም እንኳን የፒኤስጂ ተጫዋቾች ለረጅም ሰአት መልበሻ ክፍሉ አካባቢ ሰውነታቸውን እያሟሟቁ ቢጠብቁም የኢስታንቡል ባሻክሺር ተጫዋቾች ባለመመለሳቸው ምክንያት ጨዋታው ለመቋረጥ ግድ ሆኗል። የፒኤስጂው አጥቂ ኪሊያን ምባፔም በበኩሉ በትዊተር ገጹ ላይ ባስተላለፈው መልዕክት ''ዘረኝነት ይብቃ። ዌብ አብረንህ ነን'' ሲል ጽፏል። በሌሎች ጨዋታዎች በጉጉት ሲጠበቅ የማንቸስተር ዩናይትድና አር ቢ ላይፕሲዥ ጨዋታ በአርቢ ላእፕሲዥ 3 ለ2 አሸናፊነት ተጠናቋል። ምንም እንኳን ማንቸስተር ዩናይትዶት ከምድቡ ለማለፍ አቻ ብቻ የሚቃቸው የነበረ ቢሆንም በመጀመሪያዎች 20 ደቂቃዎች አርቢ ላይፕሲዦችን መቋቋም አቅቷቸው ተስተውሏል። ጨዋታው በተጀመረ 13 ደቂቃዎች ውስጥም ሁለት ግቦችን አስተናግደው የመጀመሪያው አጋማሽ 2 ለባዶ የተጠናቀቀ ቢሆንም በሁለተኛው አጋማሽ ሌላ ሶስተኛ ግብ አስተናግደዋል። በጨዋታው መጠናቀቂያ አካባቢ ማንቸስተር ዩናይትዶች ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ቢችሉም አቻ ማድረግ ግን ሳይችሉ ቀርተዋል። በዚህም ከምድቡ አለማለፋቸውን አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል በሌላኛው የተጠበቀ ጨዋታ ጁቬንቱስ ባርሴሎናን 3 ለባዶ ማሸነፍ ችሏል። ሁለቱን ግቦች ክርስቲያኖ ሮናልድ በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠረ ሲሆን ሶስተኛዋ ግብ ደግሞ ማክኬኒ በጨዋታ ማስቆጠር ችሏል። ይህን ውጤት ተከትሎ ሁለቱም ቡድኖች ከምድባቸው አንደኛና ሁለተኛ ሆነው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። ዛሬም የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ቀጥለው የሚካሄዱ ሲሆን አትሌቲኮ ማድሪድ ከሬድ ቡል ሳልዝበርግ እንዲሁም ሪያል ማድሪድ ከቦርሺያ ሞንቼግላድባክ የሚያደርጉት ወሳኝ ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል። እስካሁን በተደረጉ ጨዋታዎች የጁቬንቱሱ አልቫሮ ሞራታ፣ የቦርሺያ ዶርትሞንዱ ኢርሊንግ ሃላንድ እና የማንቸስተር ዩናይትዱ ማርከስ ራሽፎርድ በ6 ግቦች ኮኮብ ጎል አግቢነቱን እየመሩት ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-55242915
5sports
የወደፊቱ የአርሰናል አምበል ይሆናል የተባለለት ቡካዮ ሳካ ለምን የተለየ ሆነ?
ቡካዮ ሳካ በተማረበት ግሪንፊልድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የእሱ ሥራዎች የኩራት ምንጭ ናቸው። በትምህርት ቤቱ የእንግዳ መቀበያ አካባቢ በሚገኘው ግድግዳ ላይ ቡካዮ ሳካ የፈረመበት አርሰናል እግር ኳስ ክለብ መለያ ተሰቅሏል። ከስሩ ደግሞ የ19 ዓመቱ እግር ኳሰኛ "አመሰግናለሁ" የሚል ጽሁፍ አስፍሯል። በትምህርት ቤቱ የሚገኙ ተማሪዎችም ሆነ አስተማሪዎች ስለ ቡካዮ ሳካ ሲያወሩ በኩራት ሲሆን አሁንም ድረስ የወሬ ርዕስ ሆኖ እንደቀጠለ ነው። "ሳካ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ሲመረጥ ሁሉም ሰው በጣም ተገርሞ ነበር'' ይላል የሳካ የቀድሞ የሰውነት ማጎልመሻ መምህርና ምክትል አሰልጣኝ ማርክ ሃርቪ። "በእድሜ ከፍ የሚሉት ተማሪዎች የእሱን ህይወት በሚገባ ይከታተላሉ። ሁሌም ቢሆን እሱ የሆነ ነገር ሲያደርግ፣ ግብ ሲያስቆጥር አልያም ለጎል አመቻችቶ ሲያቀብል በትምህርት ቤቱ የዋትስአፕ ቡድን ላይ ሁሉም ሰው የሚያጋረው እሱን ነው። እንደውም ትንንሾቹ ተማሪዎች እሱ በትምህርት ቤታችን ይማር እንደነበር አያምኑም" የሚለው ደግሞ የሳካ የቀድሞ አሰልጣኝ የነበረው ዲፔሽ ፓቴል ነው። አርሰናል ሳካን ፍለጋ ወደ ትምህርት ቤቱ የመጣው የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ከመውሰዱ በፊት ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2018 ላይ ትምህርት ቤቱን ሲለቅ በፈተናው አራት ትምህርቶች ላይ ኤ አምጥቷል። ገና በልጅነቱም በእግር ኳን ትምህርት ቤቱን ወክሎ በክልላዊና አገራዊ ውድድሮች ላይ ተሳትፏል። በእሱ ምክንያትም ቡድኑ በርካታ ስኬቶችን አግኝቷል። "በዚህ ትምህርት ቤት ለበርካታ ዓመታት ቆይቻለሁ፤ ነገር ግን ገና ከመጀመሪያው ነበር ሳካ የተለየ ችሎታ እንዳለው ያስተዋልኩት" ይላል ዲፔሽ ፓቴል። አክሎም "ሜዳ ላይ የሚያደርገው እንቅስቃሴ፣ ጨዋታውን የሚመለከትበት መንገድ፣ እንዲሁም የሚወስናቸው ውሳኔዎች በጣም የተለዩ ነበሩ። በጣም የሚያስገርም የቡድን ተጫዋች ነበር።'' "በትምህርት ቤታችን ቆይታው ሰባተኛው ዓመት ላይ በአንድ ውድድር ላይ ለዋንጫ አልፈን 4 ለ 3 የተሸነፍንተበትን ጨዋታ አስታውሳለሁ። በጨዋታው በርካታ የጎል እድሎችን አግኝቶ አልተጠቀመባቸውም ነበር። ከሜዳ ሲወጣ አስታውሳለው በጣም ተበሳጭቶ ነበር። ለመሸነፋችን ምክንያት እሱ እንደሆነ ነበር ያሰበው። 'ከዚህ በኋላ እግር ኳስ ደግሜ አልጫወትም' አለኝ።" "ወደ መጨረሻው ጨዋታ ያለፈነው በቀላሉ ነበር። በአብዛኛዎቹ ጨዋታዎች አስገራሚ ብቃቱን ሲያሳይ ነበር። አንዳንድ ጊዜ ለሌሎቹ ተጫዋቾች እድል ለመስጠት ስል የጨዋታው ግማሽ ላይ አቀይረው ነበር። ስምንተኛው ዓመት ላይ ግን ሁሉንም ውድድር ማሸነፍ ችለናል። በርካታ ዋንጫዎችን አንስተን ነበር። ሁሌም ቢሆን ስለቡድኑ ነበር የሚያስበው።" የክንፍ መስመር አጥቂው ሳካ ከሰባት ዓመቱ ጀምሮ ከመድፈኞቹ ጋር የነበረ ሲሆን ለዋናው ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ የተጫወተው በአውሮፓውያኑ 2018 ላይ በአውሮፓ ሊግ ውድድር ነበር። በመቀጠል ደግሞ ጥር ወር ላይ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ለመጀመሪያ ጊዜ መጫወት ችሏል። ነገር ግን ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ከአርሰናል ጋር የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል። በኤምሬትስ የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራትም ፈርሟል። ከሁለት ወራት በኋላ ደግሞ ከ16 ዓመት በታች ሲጫወት ከነበረበት ተነስቶ በዋናው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጫወተ። በጨዋታው እንግሊዝ ዌልስን አሸንፋለች። ምንም እንኳን ሳካ በአርሰናል ቤት የቋሚነት ቦታውን ለመረከብ እና በብሔራዊ ቡድኑ ሰአልጣኝ ጋሬዝ ሳውዝጌት ቡድን ውስጥ ሰብሮ ለመግባት ብዙ ኢዜ ባይፈጅበትም የመጣበትን ግን አልረሳም። "ለብዙ ዓመታት የትምህርት ቤቱ ኃላፊ ከነበሩት ጋር ጥሩ የሆነ ግንኙነት አለው። የቼልሲ ደጋፊ ከሆኑት የክፍል ኃላፊውም ጋር ቢሆን በጣም የጠበቀ ወዳጅነት አላቸው'' ይላል ሃርቪ። "በጣም ቅርብ የሆኑ ጥቂት ጓደኞች ነበሩት። ምናልባት ከአምስት እስከ ስምነት የሚሆኑ ልጆች ነበሩ። ሁሉም በጣም ጥሩ ተማሪዎች ነበሩ። ስፖርቱ ላይ ብቻ ሳይሆን ትምህርት ላይም ቢሆን ጎበዞች ነበሩ።" የሳካ የቀድሞ ክፍል ኃላፊ ከሁለት ዓመታት በፊት በጡረታ ሲገለሉ የሽኝት ዝግጅቱ ላይ ያለውን ክብር በአካል ተገኝቶ አሳይቷል። "በሽኝት ዝግጅቱ ላይ ከአባቱ ጋር በመገኘት ለሰዓታት ያክል ቆይቶ ነው ተመለሰው። ከቀድሞ ጓደኞቹንና ከአስተማሪዎቹ ጋር ሲጫወትም ነበር" ይላል ሃርቪ። "ሁሉም ሰው ያውቀዋል። ከእንግዳ ተቀባዮቹ እስከ ጥበቃ ድረስ ሁሉም ጋር ጥሩ ግንኙነት አለው።" ቡካዮ ሳካ ከልጅነቱ ጀምሮ ያልተለየው ነገር ቢኖር ለስኬት ያለው ከፍተኛ ፍላጎት ነው። በአርሰናልና በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ተቀናቃኞቹን የሚሸውድበትና የማይገመቱ ውሳኔዎቹ ሁሌም ልዩ ያደርጉታል። "በጣም ዝምተኛ ልጅ ነበር። ሁሉንም ሰው የሚያከብርና በጣም ጥሩ አድማጭ ነው። ሰዎችን ለማስደሰት የሚጥርና በሁሉም ነገር ምርጥ መሆን የሚፈልግ አይነት ሰው ነው" ይላል ከ18 ዓመት በታች የቀድሞ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኙ ኒል ዴውስኒፕ። "4-4-3 አሰላለፍ ተጠቅመን ስንጫወት ሁሌም በግራ ተከላካይ መስመር በኩል እንዲጫወት እንዳርገዋለን። ከሜሰን ግሪንዉድ ጋር ተመሳሳይ ቦታ ነው። ሳካ እንደ አንደ መስመር አጥቂም መጫወት ይችላል። በተጨማሪም በቀኝ በኩልም ይጫወታል። በጣም አስገራሚ ተጫዋች ነው።'' "ከኳሷ ጋርም ሆነ ያለኳስ ሩጫው በጣም ያምራል። ተጫዋቾችንም በቀላሉ ማለፍ ይችላል። ከተከላካዮች ጋር ለአንድ ሲገናኝም ኳሷን ሚገፋበት መንገድ ይለያል፤ ግብ ማስቆጠርም አይከብደውም።'' "በሁለቱም እግሮቹ መጫወት ይችላል። አጨዋወቱ ማጥቃት ላይ የተመሰረተ ነው'' ይላል የአርሰናል የቀድሞ ተጫዋች መልማይ የነበረው ማርቲን ታይለር። "ተጫዋቾችን በቀላሉ የማለፍ፣ ግብ የማስቆጠርና ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ላይ በጣም ጥሩ የሆነ ችሎታ አለው። የሚያስገርመው ደግሞ እነዚህን ነገሮች የሚያደርገው ብዙም ሳይጨነቅ ነው። እንደ ቀልድ ነው የሚያደርጋቸው'' "ገና የ7 እና የ8 ዓመት ህጻን እያለ እንኳን የእግር ኳስ ችሎታውን አለማስተዋል አይቻልም። ይህን አይነት ችሎታ በትምህርት የሚገኝ አይደለም'' ይላል ሀርቪ። ''አንድ ቀን የአርሰናል አምበል ይሆናል'' የሥነልቦና ጥንካሬ እና አካላዊ ብቃት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሁሉ ተጫዋቾች የሚጠበቅ ነገር እየሆነ የመጣ ሲሆን እነዚህን ነገሮች ካሟሉ እድገታቸው ፈጣን እንደሚሆን ማርቲን ያምናል። "ትምህርት ዋናውና ወሳኙ ነገር ነው። በተለይ ደግሞ ታዳጊ ተጫዋቾች። እነዚህ ወጣት ተጫዋቾች በርካታ የማኅበራዊ ኃላፊነት የሚጠይቁ ዝግጅቶች ላይ ይሳተፋሉ። ቡካዩ ሳካ እና ጓደኞቹ በእነዚህ ቦታዎች ላይ ንግግር ሲያደርጉ በከፍተኛ ብስለትና ማስተዋል ነው።'' "ከቤተሰቦቹ እና ከአርሰናል ጋር በመሆን እድገቱን ስንከታተል ነበር። ወደ ትምህርት ቤቱ ሄጄም የቀድሞ መዝገቡን ተመልክቻለሁ። በጣም የሚያስገርም ታዳጊ ነው።'' "ሁሌም ቢሆን ሰው አክባሪ ነው። እንደ ሳካ አይነት የእግር ኳስ ብቃት ኖሮህ የቡድን አጋሮችህ እና ተቀናቃኞችህ ተመጣጣኝ ያልሆነ ብቃት ሲኖራቸው አንዳንዴም ቢሆን ከእነሱ ጋር መመሳሰል ያስፈልጋል፤ በተለይ ታዳጊ እያሉ። ይህ ወጣት ሁሉም አይነት በጎ ምግባር የሚታይበት ነው። ወደፊት የአርሰናል አምበል እንደሚሆን አስባለሁ።'' ታይለር እንደሚለው የሳካ ጠንካራ ሥነልቦናው ነው ለዚህ ሁሉ ስኬት ያበቃው። "እንደ ኦባምያንግ እና ላካዜት ካሉ ኮከብ ተጫዋቾች ጋር ነው የሚጫወተው። በእድሜም በልምድም ከሚበልጡት ተጫዋቾች ጋር ነው የሚጫወተው፤ በዚህ ታዳጊ እድሜው።" "ሁሌም የመጀመሪያ ሀሳቡ ወደፊት መሄድ ነው። በርካታ ተጫዋቾች ይህ ችሎታ የላቸውም። እንደ ቡካዮ ሳካ አይነት በራስ መተማመን ያለው ተጨዋች ማንም ሊያስቆመው አይችልም። በእግሩ ብቻ ሳይሆን በጭንቅላቱም ነው የሚጫወተው። እንዲህ አይነት ችሎታ አብሮህ ይወለዳል እንጂ በልምድ ወይም በትምህርት አይመጣም። ምናልባት በትምህርትና በልምድ ችሎታው ሊዳብር ይችል ይሆናል እንጂ ውስጡ ያለው ብቃት ግን አብሮት የተወለደ ነው።'' በያዝነው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዓመት በጣም ምርጥ በነበረው ጨዋታው ላይ ሳውዝሃምፕተንን 3 ለ 1 ሲያሸንፉ አንድ ግብ አስቆጥሮ ሌላ ደግሞ አመቻችቶ ሰጥቷል። "አሁንም ቢሆን ገና የእግር ኳስ ሕይወቱ ጅማሮ ላይ ነው ያለው። ምንም እንኳን በክለብም ሆነ በበብሔራዊ ቡድን አስገራሚ ጉዞ እያደረገ ቢሆንም ብዙ የሚቀሩት ነገሮች አሉ። በጣም ወጣት ታዳጊ ነው'' ይላል ዴውስኒፕ። "በብሔራዊ ቡድን ደረጃ የሚጫወት ተጫዋች ማሰልጠን ለክለብ አሰልጣኞች የማይገኝ እድል ነው። የመጫወት ፍላጎት፣ ብቃት፣ ድፍረትና ተስፋ ያለው ተጫዋች ነው።''
የወደፊቱ የአርሰናል አምበል ይሆናል የተባለለት ቡካዮ ሳካ ለምን የተለየ ሆነ? ቡካዮ ሳካ በተማረበት ግሪንፊልድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የእሱ ሥራዎች የኩራት ምንጭ ናቸው። በትምህርት ቤቱ የእንግዳ መቀበያ አካባቢ በሚገኘው ግድግዳ ላይ ቡካዮ ሳካ የፈረመበት አርሰናል እግር ኳስ ክለብ መለያ ተሰቅሏል። ከስሩ ደግሞ የ19 ዓመቱ እግር ኳሰኛ "አመሰግናለሁ" የሚል ጽሁፍ አስፍሯል። በትምህርት ቤቱ የሚገኙ ተማሪዎችም ሆነ አስተማሪዎች ስለ ቡካዮ ሳካ ሲያወሩ በኩራት ሲሆን አሁንም ድረስ የወሬ ርዕስ ሆኖ እንደቀጠለ ነው። "ሳካ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ሲመረጥ ሁሉም ሰው በጣም ተገርሞ ነበር'' ይላል የሳካ የቀድሞ የሰውነት ማጎልመሻ መምህርና ምክትል አሰልጣኝ ማርክ ሃርቪ። "በእድሜ ከፍ የሚሉት ተማሪዎች የእሱን ህይወት በሚገባ ይከታተላሉ። ሁሌም ቢሆን እሱ የሆነ ነገር ሲያደርግ፣ ግብ ሲያስቆጥር አልያም ለጎል አመቻችቶ ሲያቀብል በትምህርት ቤቱ የዋትስአፕ ቡድን ላይ ሁሉም ሰው የሚያጋረው እሱን ነው። እንደውም ትንንሾቹ ተማሪዎች እሱ በትምህርት ቤታችን ይማር እንደነበር አያምኑም" የሚለው ደግሞ የሳካ የቀድሞ አሰልጣኝ የነበረው ዲፔሽ ፓቴል ነው። አርሰናል ሳካን ፍለጋ ወደ ትምህርት ቤቱ የመጣው የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ከመውሰዱ በፊት ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2018 ላይ ትምህርት ቤቱን ሲለቅ በፈተናው አራት ትምህርቶች ላይ ኤ አምጥቷል። ገና በልጅነቱም በእግር ኳን ትምህርት ቤቱን ወክሎ በክልላዊና አገራዊ ውድድሮች ላይ ተሳትፏል። በእሱ ምክንያትም ቡድኑ በርካታ ስኬቶችን አግኝቷል። "በዚህ ትምህርት ቤት ለበርካታ ዓመታት ቆይቻለሁ፤ ነገር ግን ገና ከመጀመሪያው ነበር ሳካ የተለየ ችሎታ እንዳለው ያስተዋልኩት" ይላል ዲፔሽ ፓቴል። አክሎም "ሜዳ ላይ የሚያደርገው እንቅስቃሴ፣ ጨዋታውን የሚመለከትበት መንገድ፣ እንዲሁም የሚወስናቸው ውሳኔዎች በጣም የተለዩ ነበሩ። በጣም የሚያስገርም የቡድን ተጫዋች ነበር።'' "በትምህርት ቤታችን ቆይታው ሰባተኛው ዓመት ላይ በአንድ ውድድር ላይ ለዋንጫ አልፈን 4 ለ 3 የተሸነፍንተበትን ጨዋታ አስታውሳለሁ። በጨዋታው በርካታ የጎል እድሎችን አግኝቶ አልተጠቀመባቸውም ነበር። ከሜዳ ሲወጣ አስታውሳለው በጣም ተበሳጭቶ ነበር። ለመሸነፋችን ምክንያት እሱ እንደሆነ ነበር ያሰበው። 'ከዚህ በኋላ እግር ኳስ ደግሜ አልጫወትም' አለኝ።" "ወደ መጨረሻው ጨዋታ ያለፈነው በቀላሉ ነበር። በአብዛኛዎቹ ጨዋታዎች አስገራሚ ብቃቱን ሲያሳይ ነበር። አንዳንድ ጊዜ ለሌሎቹ ተጫዋቾች እድል ለመስጠት ስል የጨዋታው ግማሽ ላይ አቀይረው ነበር። ስምንተኛው ዓመት ላይ ግን ሁሉንም ውድድር ማሸነፍ ችለናል። በርካታ ዋንጫዎችን አንስተን ነበር። ሁሌም ቢሆን ስለቡድኑ ነበር የሚያስበው።" የክንፍ መስመር አጥቂው ሳካ ከሰባት ዓመቱ ጀምሮ ከመድፈኞቹ ጋር የነበረ ሲሆን ለዋናው ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ የተጫወተው በአውሮፓውያኑ 2018 ላይ በአውሮፓ ሊግ ውድድር ነበር። በመቀጠል ደግሞ ጥር ወር ላይ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ለመጀመሪያ ጊዜ መጫወት ችሏል። ነገር ግን ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ከአርሰናል ጋር የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል። በኤምሬትስ የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራትም ፈርሟል። ከሁለት ወራት በኋላ ደግሞ ከ16 ዓመት በታች ሲጫወት ከነበረበት ተነስቶ በዋናው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጫወተ። በጨዋታው እንግሊዝ ዌልስን አሸንፋለች። ምንም እንኳን ሳካ በአርሰናል ቤት የቋሚነት ቦታውን ለመረከብ እና በብሔራዊ ቡድኑ ሰአልጣኝ ጋሬዝ ሳውዝጌት ቡድን ውስጥ ሰብሮ ለመግባት ብዙ ኢዜ ባይፈጅበትም የመጣበትን ግን አልረሳም። "ለብዙ ዓመታት የትምህርት ቤቱ ኃላፊ ከነበሩት ጋር ጥሩ የሆነ ግንኙነት አለው። የቼልሲ ደጋፊ ከሆኑት የክፍል ኃላፊውም ጋር ቢሆን በጣም የጠበቀ ወዳጅነት አላቸው'' ይላል ሃርቪ። "በጣም ቅርብ የሆኑ ጥቂት ጓደኞች ነበሩት። ምናልባት ከአምስት እስከ ስምነት የሚሆኑ ልጆች ነበሩ። ሁሉም በጣም ጥሩ ተማሪዎች ነበሩ። ስፖርቱ ላይ ብቻ ሳይሆን ትምህርት ላይም ቢሆን ጎበዞች ነበሩ።" የሳካ የቀድሞ ክፍል ኃላፊ ከሁለት ዓመታት በፊት በጡረታ ሲገለሉ የሽኝት ዝግጅቱ ላይ ያለውን ክብር በአካል ተገኝቶ አሳይቷል። "በሽኝት ዝግጅቱ ላይ ከአባቱ ጋር በመገኘት ለሰዓታት ያክል ቆይቶ ነው ተመለሰው። ከቀድሞ ጓደኞቹንና ከአስተማሪዎቹ ጋር ሲጫወትም ነበር" ይላል ሃርቪ። "ሁሉም ሰው ያውቀዋል። ከእንግዳ ተቀባዮቹ እስከ ጥበቃ ድረስ ሁሉም ጋር ጥሩ ግንኙነት አለው።" ቡካዮ ሳካ ከልጅነቱ ጀምሮ ያልተለየው ነገር ቢኖር ለስኬት ያለው ከፍተኛ ፍላጎት ነው። በአርሰናልና በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ተቀናቃኞቹን የሚሸውድበትና የማይገመቱ ውሳኔዎቹ ሁሌም ልዩ ያደርጉታል። "በጣም ዝምተኛ ልጅ ነበር። ሁሉንም ሰው የሚያከብርና በጣም ጥሩ አድማጭ ነው። ሰዎችን ለማስደሰት የሚጥርና በሁሉም ነገር ምርጥ መሆን የሚፈልግ አይነት ሰው ነው" ይላል ከ18 ዓመት በታች የቀድሞ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኙ ኒል ዴውስኒፕ። "4-4-3 አሰላለፍ ተጠቅመን ስንጫወት ሁሌም በግራ ተከላካይ መስመር በኩል እንዲጫወት እንዳርገዋለን። ከሜሰን ግሪንዉድ ጋር ተመሳሳይ ቦታ ነው። ሳካ እንደ አንደ መስመር አጥቂም መጫወት ይችላል። በተጨማሪም በቀኝ በኩልም ይጫወታል። በጣም አስገራሚ ተጫዋች ነው።'' "ከኳሷ ጋርም ሆነ ያለኳስ ሩጫው በጣም ያምራል። ተጫዋቾችንም በቀላሉ ማለፍ ይችላል። ከተከላካዮች ጋር ለአንድ ሲገናኝም ኳሷን ሚገፋበት መንገድ ይለያል፤ ግብ ማስቆጠርም አይከብደውም።'' "በሁለቱም እግሮቹ መጫወት ይችላል። አጨዋወቱ ማጥቃት ላይ የተመሰረተ ነው'' ይላል የአርሰናል የቀድሞ ተጫዋች መልማይ የነበረው ማርቲን ታይለር። "ተጫዋቾችን በቀላሉ የማለፍ፣ ግብ የማስቆጠርና ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ላይ በጣም ጥሩ የሆነ ችሎታ አለው። የሚያስገርመው ደግሞ እነዚህን ነገሮች የሚያደርገው ብዙም ሳይጨነቅ ነው። እንደ ቀልድ ነው የሚያደርጋቸው'' "ገና የ7 እና የ8 ዓመት ህጻን እያለ እንኳን የእግር ኳስ ችሎታውን አለማስተዋል አይቻልም። ይህን አይነት ችሎታ በትምህርት የሚገኝ አይደለም'' ይላል ሀርቪ። ''አንድ ቀን የአርሰናል አምበል ይሆናል'' የሥነልቦና ጥንካሬ እና አካላዊ ብቃት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሁሉ ተጫዋቾች የሚጠበቅ ነገር እየሆነ የመጣ ሲሆን እነዚህን ነገሮች ካሟሉ እድገታቸው ፈጣን እንደሚሆን ማርቲን ያምናል። "ትምህርት ዋናውና ወሳኙ ነገር ነው። በተለይ ደግሞ ታዳጊ ተጫዋቾች። እነዚህ ወጣት ተጫዋቾች በርካታ የማኅበራዊ ኃላፊነት የሚጠይቁ ዝግጅቶች ላይ ይሳተፋሉ። ቡካዩ ሳካ እና ጓደኞቹ በእነዚህ ቦታዎች ላይ ንግግር ሲያደርጉ በከፍተኛ ብስለትና ማስተዋል ነው።'' "ከቤተሰቦቹ እና ከአርሰናል ጋር በመሆን እድገቱን ስንከታተል ነበር። ወደ ትምህርት ቤቱ ሄጄም የቀድሞ መዝገቡን ተመልክቻለሁ። በጣም የሚያስገርም ታዳጊ ነው።'' "ሁሌም ቢሆን ሰው አክባሪ ነው። እንደ ሳካ አይነት የእግር ኳስ ብቃት ኖሮህ የቡድን አጋሮችህ እና ተቀናቃኞችህ ተመጣጣኝ ያልሆነ ብቃት ሲኖራቸው አንዳንዴም ቢሆን ከእነሱ ጋር መመሳሰል ያስፈልጋል፤ በተለይ ታዳጊ እያሉ። ይህ ወጣት ሁሉም አይነት በጎ ምግባር የሚታይበት ነው። ወደፊት የአርሰናል አምበል እንደሚሆን አስባለሁ።'' ታይለር እንደሚለው የሳካ ጠንካራ ሥነልቦናው ነው ለዚህ ሁሉ ስኬት ያበቃው። "እንደ ኦባምያንግ እና ላካዜት ካሉ ኮከብ ተጫዋቾች ጋር ነው የሚጫወተው። በእድሜም በልምድም ከሚበልጡት ተጫዋቾች ጋር ነው የሚጫወተው፤ በዚህ ታዳጊ እድሜው።" "ሁሌም የመጀመሪያ ሀሳቡ ወደፊት መሄድ ነው። በርካታ ተጫዋቾች ይህ ችሎታ የላቸውም። እንደ ቡካዮ ሳካ አይነት በራስ መተማመን ያለው ተጨዋች ማንም ሊያስቆመው አይችልም። በእግሩ ብቻ ሳይሆን በጭንቅላቱም ነው የሚጫወተው። እንዲህ አይነት ችሎታ አብሮህ ይወለዳል እንጂ በልምድ ወይም በትምህርት አይመጣም። ምናልባት በትምህርትና በልምድ ችሎታው ሊዳብር ይችል ይሆናል እንጂ ውስጡ ያለው ብቃት ግን አብሮት የተወለደ ነው።'' በያዝነው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዓመት በጣም ምርጥ በነበረው ጨዋታው ላይ ሳውዝሃምፕተንን 3 ለ 1 ሲያሸንፉ አንድ ግብ አስቆጥሮ ሌላ ደግሞ አመቻችቶ ሰጥቷል። "አሁንም ቢሆን ገና የእግር ኳስ ሕይወቱ ጅማሮ ላይ ነው ያለው። ምንም እንኳን በክለብም ሆነ በበብሔራዊ ቡድን አስገራሚ ጉዞ እያደረገ ቢሆንም ብዙ የሚቀሩት ነገሮች አሉ። በጣም ወጣት ታዳጊ ነው'' ይላል ዴውስኒፕ። "በብሔራዊ ቡድን ደረጃ የሚጫወት ተጫዋች ማሰልጠን ለክለብ አሰልጣኞች የማይገኝ እድል ነው። የመጫወት ፍላጎት፣ ብቃት፣ ድፍረትና ተስፋ ያለው ተጫዋች ነው።''
https://www.bbc.com/amharic/news-56755322
2health
ኮሮናቫይረስ፡ክትባት ለመከተብ አጭበርብረዋል የተባሉ ኃላፊ ከስራቸው ለቀቁ
ከ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የካዚኖ ቁማር ኩባንያ የሚመሩት ዋና ስራ አስፈፃሚ የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት አጭብርብረዋል መባሉን ተከትሎ ከስራቸው ለቀቁ። ኃላፈውና ባለቤታቸው ባለስልጣናቱን አታለዋል በሚል ተከሰዋል። ግሬት ካናዲያን ጌሚንግ የተባለ የካዚኖ ቁማር ድርጅት የሚመሩት ሮድ ቤከርና ባለቤታቸው ኢካትሪና ገጠራማ ወደሆነው ዩኮን ግዛት ክትባት ለመከተብ አቅንተው ነበር። ግዛቱ የቀደምት ካናዳውያን መኖሪያ ሲሆን ከሌሎች የካናዳ ክፍሎች በበለጠ ፈጣን የሆነ የክትባት አሰጣጥ ስርአት እንዳለው መረጃዎች ያሳያሉ። ባለትዳሮቹ ወደ ቦታው ሲያመሩም የሆቴል ሰራተኞች ነን በሚል ሽፋን ነው። በባለፈው ሳምንት በግዛቲቱ ውስጥ በምትገኝ ቢቨር ክሪክ በምትባል መንደር ውስጥ ተከትበው ከጨረሱ በኋላ ወደ አየር ማረፊያ ውሰዱን ማለታቸውን ተከትሎ ነው የተጋለጡት። " በዚህ ራስ ወዳድ በሆነ ባህርያቸው በጣም ተበሳጭቻለሁ" በማለት የዩኮን ማህበረሰብ አገልግሎት ሚኒስትር ጆን ስትሬይከር ተናግረዋል። "በዚህ መንገድ ሰው አጭበርብሮ እንዲህ አይነት ተግባር ይፈፅማል የሚል ነገር በጭራሽ አላሰብንም" ብለዋል አክለውም። ከዚሁ ጋር ተያያይዞ የዋይት ሪቨር ፈርስት ኔሽን፣ የአካባቢው የቀደምት ህዝቦች ኃላፊ አንጄላ ዴሚት በበኩላቸው "የእድሜ ባለፀጎቻችንና ተጋላጭ ማህበረሰቦቻችንን ስጋት ውስጥ የሚከቱ የአንዳንድ ግለሰቦች ድርጊት በጣም አሳስቦናል። ተራን ባለመጠበቅ እንዲህ አይነት አስነዋሪ ስራ መፈፀም ራስ ወዳድነት ነው" ብለዋል። ሮድ ቤከርና ባለቤታቸው ከቫንኮቨር ግዛት ወደ ዩኮን በሄዱበት ወቅት አስገዳጅ የሆነውን የ14 ቀናት ለይቶ ማቆያ ባለማክበር ተቀጥተዋል።
ኮሮናቫይረስ፡ክትባት ለመከተብ አጭበርብረዋል የተባሉ ኃላፊ ከስራቸው ለቀቁ ከ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የካዚኖ ቁማር ኩባንያ የሚመሩት ዋና ስራ አስፈፃሚ የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት አጭብርብረዋል መባሉን ተከትሎ ከስራቸው ለቀቁ። ኃላፈውና ባለቤታቸው ባለስልጣናቱን አታለዋል በሚል ተከሰዋል። ግሬት ካናዲያን ጌሚንግ የተባለ የካዚኖ ቁማር ድርጅት የሚመሩት ሮድ ቤከርና ባለቤታቸው ኢካትሪና ገጠራማ ወደሆነው ዩኮን ግዛት ክትባት ለመከተብ አቅንተው ነበር። ግዛቱ የቀደምት ካናዳውያን መኖሪያ ሲሆን ከሌሎች የካናዳ ክፍሎች በበለጠ ፈጣን የሆነ የክትባት አሰጣጥ ስርአት እንዳለው መረጃዎች ያሳያሉ። ባለትዳሮቹ ወደ ቦታው ሲያመሩም የሆቴል ሰራተኞች ነን በሚል ሽፋን ነው። በባለፈው ሳምንት በግዛቲቱ ውስጥ በምትገኝ ቢቨር ክሪክ በምትባል መንደር ውስጥ ተከትበው ከጨረሱ በኋላ ወደ አየር ማረፊያ ውሰዱን ማለታቸውን ተከትሎ ነው የተጋለጡት። " በዚህ ራስ ወዳድ በሆነ ባህርያቸው በጣም ተበሳጭቻለሁ" በማለት የዩኮን ማህበረሰብ አገልግሎት ሚኒስትር ጆን ስትሬይከር ተናግረዋል። "በዚህ መንገድ ሰው አጭበርብሮ እንዲህ አይነት ተግባር ይፈፅማል የሚል ነገር በጭራሽ አላሰብንም" ብለዋል አክለውም። ከዚሁ ጋር ተያያይዞ የዋይት ሪቨር ፈርስት ኔሽን፣ የአካባቢው የቀደምት ህዝቦች ኃላፊ አንጄላ ዴሚት በበኩላቸው "የእድሜ ባለፀጎቻችንና ተጋላጭ ማህበረሰቦቻችንን ስጋት ውስጥ የሚከቱ የአንዳንድ ግለሰቦች ድርጊት በጣም አሳስቦናል። ተራን ባለመጠበቅ እንዲህ አይነት አስነዋሪ ስራ መፈፀም ራስ ወዳድነት ነው" ብለዋል። ሮድ ቤከርና ባለቤታቸው ከቫንኮቨር ግዛት ወደ ዩኮን በሄዱበት ወቅት አስገዳጅ የሆነውን የ14 ቀናት ለይቶ ማቆያ ባለማክበር ተቀጥተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55807191
3politics
የእስራኤል ተቃዋሚዎች አዲስ የአንድነት መንግሥት ለማቋቋም ተስማሙ
የእስራኤል ተቃዋሚ ፓርቲዎች የቤንጃሚን ኔታንያሁን የ 12 ዓመታት ጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚያከትም አዲስ መንግሥት ለማቋቋም ከስምምነት ደረሱ፡፡ የየሽ አቲድ ፓርቲ መሪው ያይር ላፒድ በስምንት ቡድኖች የተቋቋመ ጥምረት መመስረቱን አስታውቀዋል፡፡ ሥልጣን በዙር በሚከፋልበት በዚሁ ስምምነት መሠረት የያሚና ፓርቲው አለቃ ናፍታሊ ቤኔት በቀዳሚነት ጠቅላይ ሚንስትር ይሆናሉ። በቀጣይ ላፒድ ሥልጣኑን ይረከቧቸዋል። መንግሥት ለመመስረት ቃለ መሐላ ከመፈጸሙ በፊት የፓርላማዉ ይሁንታ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል፡፡ ላፒድ በሰጡት መግለጫ ስለስምምነቱ ለፕሬዚዳንት ሬውቨን ሪቭሊን ማሳወቃቸውን ገልጸዋል። "ይህ መንግስት ሁሉንም የእስራኤል ዜጎች፣ የመረጡትንም ሆነ ያልመረጡትን ለማገልገል እንደሚሠራ ቃል እገባለሁ" ብለዋል፡፡ "ተቃዋሚዎቻቸውን የሚያከብር ሲሆን ሁሉንም የእስራኤልን የህብረተሰብ ክፍሎች አንድ ለማድረግ እና ለማገናኘት የቻለውን ሁሉ ያደርጋል" ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በእስራኤል የመገናኛ ብዙሃን በተሰራጨ ምስል ላፒድ፣ ቤኔት እና የአረብ ኢስላሚስት ራም ፓርቲ ሊቀመንበር ማንሱር አባስ ስምምነቱን ሲፈርሙ ቢታዩም ብዙዎች የማይቻል መስሏቸው ነበር፡፡ አባስ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት "ውሳኔው ከባድ እና በርካታ ክርክሮች ነበሩት። ስምምነቶቹ ላይ መድረስ ግን አስፈላጊ ነበር፡፡ በዚህ ስምምነት ለአረብ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚጠቅም ብዙ ነገሮች አሉት" ብለዋል ፡፡ ላፒድ ለፕሬዚዳንቱ በላኩት ማስታወሻ እአአ ነሐሴ 27/2023 ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እስከሚሾሙ ድረስ ከቤኔት ጋር በመሆን መንግስትን እመራለሁ ብለዋል፡፡ ሪቭሊን በጉዳዩ ላይ የመተማመኛ ድምጽን በተመለከተ ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ፓርላማው በተቻለ ፍጥነት እንዲሰበሰብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ህብረቱ በ 120 መቀመጫዎች ባሉት ክኔሴት (የእስራኤል ፓርላማ) የአብላጫውን ድጋፍ ማግኘት ካልቻለ ሃገሪቱ በሁለት ዓመታት ውስጥ ለአምስተኛ ጊዜ ምርጫ ለማካሄድ ትገደዳለች፡፡ ጥምረት የፈጠሩት ፓርቲዎች የእስራኤልን ፖለቲካ ሙሉ ገጽታ ያሳያሉ ተብሏል፡፡ ፓርቲዎቹ ኔታንያሁን ለመተካት ከማቀድ ውጭ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ብዙም የሚያመሳስላቸው ነገር የለም፡፡ ረቡዕ ዕለት ረዥም ሰዓታትን የወሰደው ውይይት በቴሌ አቪቭ አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ሆቴል የተካሄደ ሲሆን ዕፀ ፋርስን ህጋዊ ከማድረግ ጀምሮ በርካታ ጉዳዮች አጀንዳ ሆነው ተነስተዋል። የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ሁሉም ሃሳቦች ተነስተው ከስምምነት አልተደረሰም ያሉ ሲሆን ይህም ጥምረቱ የመተማመኛ ድምጹን ያሸንፋል በሚለው ላይ ጥርጣሬ ጭሯል፡፡ የኔታንያሁ ሊኩድ ፓርቲ ከወራት በፊት በተደረገው ምርጫ ብዙ ወንበር ቢያገኝም ስልጣን የሚያስገኝለትን ጥምረት መመስረት አልቻለም። ኔታንያሁ የታቀደው አዲስ መንግስት "የክፍለ ዘመኑ ማጭበርበር" ሲሉ ገልጸው የእስራኤልን መንግሥት እና ህዝቡን አደጋ ላይ የሚጥል ብለውታል፡፡
የእስራኤል ተቃዋሚዎች አዲስ የአንድነት መንግሥት ለማቋቋም ተስማሙ የእስራኤል ተቃዋሚ ፓርቲዎች የቤንጃሚን ኔታንያሁን የ 12 ዓመታት ጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚያከትም አዲስ መንግሥት ለማቋቋም ከስምምነት ደረሱ፡፡ የየሽ አቲድ ፓርቲ መሪው ያይር ላፒድ በስምንት ቡድኖች የተቋቋመ ጥምረት መመስረቱን አስታውቀዋል፡፡ ሥልጣን በዙር በሚከፋልበት በዚሁ ስምምነት መሠረት የያሚና ፓርቲው አለቃ ናፍታሊ ቤኔት በቀዳሚነት ጠቅላይ ሚንስትር ይሆናሉ። በቀጣይ ላፒድ ሥልጣኑን ይረከቧቸዋል። መንግሥት ለመመስረት ቃለ መሐላ ከመፈጸሙ በፊት የፓርላማዉ ይሁንታ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል፡፡ ላፒድ በሰጡት መግለጫ ስለስምምነቱ ለፕሬዚዳንት ሬውቨን ሪቭሊን ማሳወቃቸውን ገልጸዋል። "ይህ መንግስት ሁሉንም የእስራኤል ዜጎች፣ የመረጡትንም ሆነ ያልመረጡትን ለማገልገል እንደሚሠራ ቃል እገባለሁ" ብለዋል፡፡ "ተቃዋሚዎቻቸውን የሚያከብር ሲሆን ሁሉንም የእስራኤልን የህብረተሰብ ክፍሎች አንድ ለማድረግ እና ለማገናኘት የቻለውን ሁሉ ያደርጋል" ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በእስራኤል የመገናኛ ብዙሃን በተሰራጨ ምስል ላፒድ፣ ቤኔት እና የአረብ ኢስላሚስት ራም ፓርቲ ሊቀመንበር ማንሱር አባስ ስምምነቱን ሲፈርሙ ቢታዩም ብዙዎች የማይቻል መስሏቸው ነበር፡፡ አባስ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት "ውሳኔው ከባድ እና በርካታ ክርክሮች ነበሩት። ስምምነቶቹ ላይ መድረስ ግን አስፈላጊ ነበር፡፡ በዚህ ስምምነት ለአረብ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚጠቅም ብዙ ነገሮች አሉት" ብለዋል ፡፡ ላፒድ ለፕሬዚዳንቱ በላኩት ማስታወሻ እአአ ነሐሴ 27/2023 ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እስከሚሾሙ ድረስ ከቤኔት ጋር በመሆን መንግስትን እመራለሁ ብለዋል፡፡ ሪቭሊን በጉዳዩ ላይ የመተማመኛ ድምጽን በተመለከተ ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ፓርላማው በተቻለ ፍጥነት እንዲሰበሰብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ህብረቱ በ 120 መቀመጫዎች ባሉት ክኔሴት (የእስራኤል ፓርላማ) የአብላጫውን ድጋፍ ማግኘት ካልቻለ ሃገሪቱ በሁለት ዓመታት ውስጥ ለአምስተኛ ጊዜ ምርጫ ለማካሄድ ትገደዳለች፡፡ ጥምረት የፈጠሩት ፓርቲዎች የእስራኤልን ፖለቲካ ሙሉ ገጽታ ያሳያሉ ተብሏል፡፡ ፓርቲዎቹ ኔታንያሁን ለመተካት ከማቀድ ውጭ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ብዙም የሚያመሳስላቸው ነገር የለም፡፡ ረቡዕ ዕለት ረዥም ሰዓታትን የወሰደው ውይይት በቴሌ አቪቭ አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ሆቴል የተካሄደ ሲሆን ዕፀ ፋርስን ህጋዊ ከማድረግ ጀምሮ በርካታ ጉዳዮች አጀንዳ ሆነው ተነስተዋል። የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ሁሉም ሃሳቦች ተነስተው ከስምምነት አልተደረሰም ያሉ ሲሆን ይህም ጥምረቱ የመተማመኛ ድምጹን ያሸንፋል በሚለው ላይ ጥርጣሬ ጭሯል፡፡ የኔታንያሁ ሊኩድ ፓርቲ ከወራት በፊት በተደረገው ምርጫ ብዙ ወንበር ቢያገኝም ስልጣን የሚያስገኝለትን ጥምረት መመስረት አልቻለም። ኔታንያሁ የታቀደው አዲስ መንግስት "የክፍለ ዘመኑ ማጭበርበር" ሲሉ ገልጸው የእስራኤልን መንግሥት እና ህዝቡን አደጋ ላይ የሚጥል ብለውታል፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-57333188
0business
ከአሜሪካና ከቻይና ቢሊየነሮች በሀብት ማን ይበልጣል?
የዓለም ሕዝብ መከራውን እየበላ ነው። የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ሚሊዮኖች ሳይሆኑ ቢሊዮኖች ናቸው። ቢሊየነሮች ግን ሀብታቸው ሰማይ እየነካ በተድላ 'እየተሰቃዩ' ነው። በሀብት የሚያዋኙት የዓለም ቢሊየነሮች በቁጥር ከዓለም ሕዝብ ጋር ሲነጻጸሩ ጥቂቶች ናቸው። በጣም ጥቂቶች። ኧረ በጣም በጣም ጥቂቶች። ተዝቆ የማያልቅ አዱኛን ካካበቱት መካከል የአማዞን ባለቤት ጄፍ ቤዞስ ይገኝበታል። ኮሮናቫይረስ ከተከሰተ ወዲህ የቢሊየነሮች ሀብት በአማካይ በ27.5 ከመቶ ተመንድጓል። ወይም ደግሞ የ10.2 ትሪሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል፤ ይህም ከመጋቢት ወር ወዲህ ብቻ መሆኑ ነው። መረጃውን ያወጣው የስዊዘርላንዱ ዩቢኤስ ባንክ ነው። የቢሊየኖች ብዛት ከኮሮናቫይረስ በፊት ቀድሞም ቢሆን ከዓመት ዓመት ጭማሪ እያሳየ ነው የመጣው። በ2017 ዓ.ም በዓለም ያሉ ቢሊየነሮች በድምሩ ቁጥራቸው 2 ሺህ 158 ነበር። አሁን ስንት ደረሱ? በድምሩ 2 ሺህ 189 ደርሰዋል። በሦስት ዓመት ውስጥ የቢሊየነሮቹ ቁጥር በ31 ከፍ ብሏል። በጣም ብዙ ነው። ባንኩ እንዳወጣው መረጃ ከሆነ በዚህ ዓመት የሃብት በረከት ከዘነበላቸው ቢሊየነሮች ዋንኞቹ ኢንደስትሪያሊስቶች ናቸው። በሦስት ወር ብቻ ሀብታቸው በ44 ከመቶ አድጓል። ቀጥለው የሚገኙት የቴክኖሎጂ ቢሊየነሮች ናቸው። የተሰማሩበት መስክ የኮቪድ-19 ክስተትን ለመጠቀም የተስማማ በመሆኑ ሀብታቸው 41 ከመቶ ጨምሯል። ይህ ዘርፍ የሚያቀርበው የአብዛኛው አገልግሎት ፍላጎት ኮቪድ-19 አመጣሽ ነው። ሰዎች በአካል መገናኘት አደጋ እንደሆነ ሲረዱ ወደ በይነ መረብ ዞረዋል። ይህም ለቴክኖሎጂ ቢሊየነሮች ተጨማሪ ቢሊየኖችን ይዞላቸው መጥቷል። ከጤና ጋር በተያያዙ ምርቶች ላይ የተመሰረቱት ቢሊየነሮችም ኮቪድ-19ን ወደውታል። የሕክምና ቁሳቁስ እንዲሁም የመድኃኒት አምራች ቢሊየነሮች ንግድ ጦፎልናል ብለዋል። ቁጥር አንድ የፕላኔቷ ቢሊየነር የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ እና የቴስላ ኩባንያ መሥራች ኤሎን መስክ የኩባንያዎቻቸው የአክሲዮን ዋጋ ሰማይ በመንካቱ ሀብታቸው ላይ በላይ እየተከመረ ነው ብሏል ባንኩ። የቻይና ቢሊየነሮች ባለፉት 11 ዓመታት የቻይና ቢሊየነሮች ቁጥር እያሻቀበ ነው። ሀብታቸው የሚጨምርበት ፍጥነትም አስደንጋጭ ነው። በድምሩ የቻይና ቢሊየነሮች ሀብት በ1 ሺ 146 በመቶ ጨምሯል። ይህም በፈረንጆች ከ2009 ጀምሮ ሲታይ ነው፤ እንደ ባንኩ መረጃ። ለምሳሌ የታላቋ ብሪታኒያ ቢሊየነሮችን ከቻይና ቢሊየነሮች ጋር ብናነጻጽር የእንግሊዞቹ ቢሊየነሮች ሀብታቸው የጨመረው 168 በመቶ ብቻ ነው። ያም ሆኖ በቢሊየነሮች ክምችት አሜሪካንን የሚያህል የለም። ቻይናና አሜሪካንን ብናነጻጽር ለምሳሌ አሜሪካዊ ቢሊየነሮች በድምሩ 3.5 ትሪሊዮን ዶላር ሲያካብቱ ቻይናዎች ግን በድምሩ 1.7 ትሪሊዮን ዶላር ሀብት ነው ያፈሩት። ሆኖም የቻይና ቢሊየነሮች አመጣጥ ለአሜሪካ አስፈሪ ይመስላል። በአጭር ጊዜ እየተቃረቡ ነው። የታላቋ ብሪታኒያ ቢሊየነሮች ሀብት ተለቅ ያለ ካልኩሌተር ፈልገን ብንደምረው 205 ቢሊየን ዶላር ቢሆን ነው። የጀርመኖች 595 ቢሊየን ዶላር ደርሷል። የፈረንሳይ ቢሊየነሮች ድምር ሀብት ደግሞ 443 ቢሊየን ዶላር ብቻ ነው። ስለዚህ ቻይናና አሜሪካ ከአውሮፓዊያኑ ቢሊየነሮች ጋር ሲነጻጸሩ 'ምን ብልተው ነው የሚያድሩት?' ያስብላል። ማን ለጋስ ነው? ዩቢኤስ ባንክ እንደሚለው ብዙ ቢሊየነሮች ከኮቪድ-19 በኋላ ደግ፣ ቸር፣ እና ለጋስ ሆነዋል። "በእኛ ጥናት መሰረት 209 የዓለም ቢሊየነሮች በይፋ ተናግረው የለገሱት ብር ድምር 7.2 ቢሊየነር ዶላር ነው" ይላል ባንኩ። ይህ አሐዝ ከመጋቢት እስከ ሰኔ 2020 ብቻ ቃል ተገብቶ የተለገሰ ነው። የዚህ ልግስና ባህሪ ከስከዛሬው የሚለየው በፍጥነት መሆኑና ተለጋሽ ተቋማትም ገንዘቡን ለፈለጉት አገልግሎት በፈለጉት መንገድ እንዲያውሉት መደረጉ ነው ይላል ባንኩ። ጥናቱ የታላቋ ብሪታኒያ ቢሊየነሮች ከብዙ አገሮች አንጻር ትንሹን ልግስና ማሳየታቸው አስገርሞል። በአሜሪካ ለምሳሌ 98 ቢሊየነሮች 4.5 ቢሊዮን ዶላር ለግሰዋል። በቻይና 12 ቢሊየነሮች 679 ሚሊዮን ዶላር ልግሰዋል። በታላቋ ብሪታኒያ ግን 9 ቢሊየነሮች ብቻ ናቸው መለገስ የቻሉት። ድምሩም 300 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ብቻ ነው።
ከአሜሪካና ከቻይና ቢሊየነሮች በሀብት ማን ይበልጣል? የዓለም ሕዝብ መከራውን እየበላ ነው። የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ሚሊዮኖች ሳይሆኑ ቢሊዮኖች ናቸው። ቢሊየነሮች ግን ሀብታቸው ሰማይ እየነካ በተድላ 'እየተሰቃዩ' ነው። በሀብት የሚያዋኙት የዓለም ቢሊየነሮች በቁጥር ከዓለም ሕዝብ ጋር ሲነጻጸሩ ጥቂቶች ናቸው። በጣም ጥቂቶች። ኧረ በጣም በጣም ጥቂቶች። ተዝቆ የማያልቅ አዱኛን ካካበቱት መካከል የአማዞን ባለቤት ጄፍ ቤዞስ ይገኝበታል። ኮሮናቫይረስ ከተከሰተ ወዲህ የቢሊየነሮች ሀብት በአማካይ በ27.5 ከመቶ ተመንድጓል። ወይም ደግሞ የ10.2 ትሪሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል፤ ይህም ከመጋቢት ወር ወዲህ ብቻ መሆኑ ነው። መረጃውን ያወጣው የስዊዘርላንዱ ዩቢኤስ ባንክ ነው። የቢሊየኖች ብዛት ከኮሮናቫይረስ በፊት ቀድሞም ቢሆን ከዓመት ዓመት ጭማሪ እያሳየ ነው የመጣው። በ2017 ዓ.ም በዓለም ያሉ ቢሊየነሮች በድምሩ ቁጥራቸው 2 ሺህ 158 ነበር። አሁን ስንት ደረሱ? በድምሩ 2 ሺህ 189 ደርሰዋል። በሦስት ዓመት ውስጥ የቢሊየነሮቹ ቁጥር በ31 ከፍ ብሏል። በጣም ብዙ ነው። ባንኩ እንዳወጣው መረጃ ከሆነ በዚህ ዓመት የሃብት በረከት ከዘነበላቸው ቢሊየነሮች ዋንኞቹ ኢንደስትሪያሊስቶች ናቸው። በሦስት ወር ብቻ ሀብታቸው በ44 ከመቶ አድጓል። ቀጥለው የሚገኙት የቴክኖሎጂ ቢሊየነሮች ናቸው። የተሰማሩበት መስክ የኮቪድ-19 ክስተትን ለመጠቀም የተስማማ በመሆኑ ሀብታቸው 41 ከመቶ ጨምሯል። ይህ ዘርፍ የሚያቀርበው የአብዛኛው አገልግሎት ፍላጎት ኮቪድ-19 አመጣሽ ነው። ሰዎች በአካል መገናኘት አደጋ እንደሆነ ሲረዱ ወደ በይነ መረብ ዞረዋል። ይህም ለቴክኖሎጂ ቢሊየነሮች ተጨማሪ ቢሊየኖችን ይዞላቸው መጥቷል። ከጤና ጋር በተያያዙ ምርቶች ላይ የተመሰረቱት ቢሊየነሮችም ኮቪድ-19ን ወደውታል። የሕክምና ቁሳቁስ እንዲሁም የመድኃኒት አምራች ቢሊየነሮች ንግድ ጦፎልናል ብለዋል። ቁጥር አንድ የፕላኔቷ ቢሊየነር የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ እና የቴስላ ኩባንያ መሥራች ኤሎን መስክ የኩባንያዎቻቸው የአክሲዮን ዋጋ ሰማይ በመንካቱ ሀብታቸው ላይ በላይ እየተከመረ ነው ብሏል ባንኩ። የቻይና ቢሊየነሮች ባለፉት 11 ዓመታት የቻይና ቢሊየነሮች ቁጥር እያሻቀበ ነው። ሀብታቸው የሚጨምርበት ፍጥነትም አስደንጋጭ ነው። በድምሩ የቻይና ቢሊየነሮች ሀብት በ1 ሺ 146 በመቶ ጨምሯል። ይህም በፈረንጆች ከ2009 ጀምሮ ሲታይ ነው፤ እንደ ባንኩ መረጃ። ለምሳሌ የታላቋ ብሪታኒያ ቢሊየነሮችን ከቻይና ቢሊየነሮች ጋር ብናነጻጽር የእንግሊዞቹ ቢሊየነሮች ሀብታቸው የጨመረው 168 በመቶ ብቻ ነው። ያም ሆኖ በቢሊየነሮች ክምችት አሜሪካንን የሚያህል የለም። ቻይናና አሜሪካንን ብናነጻጽር ለምሳሌ አሜሪካዊ ቢሊየነሮች በድምሩ 3.5 ትሪሊዮን ዶላር ሲያካብቱ ቻይናዎች ግን በድምሩ 1.7 ትሪሊዮን ዶላር ሀብት ነው ያፈሩት። ሆኖም የቻይና ቢሊየነሮች አመጣጥ ለአሜሪካ አስፈሪ ይመስላል። በአጭር ጊዜ እየተቃረቡ ነው። የታላቋ ብሪታኒያ ቢሊየነሮች ሀብት ተለቅ ያለ ካልኩሌተር ፈልገን ብንደምረው 205 ቢሊየን ዶላር ቢሆን ነው። የጀርመኖች 595 ቢሊየን ዶላር ደርሷል። የፈረንሳይ ቢሊየነሮች ድምር ሀብት ደግሞ 443 ቢሊየን ዶላር ብቻ ነው። ስለዚህ ቻይናና አሜሪካ ከአውሮፓዊያኑ ቢሊየነሮች ጋር ሲነጻጸሩ 'ምን ብልተው ነው የሚያድሩት?' ያስብላል። ማን ለጋስ ነው? ዩቢኤስ ባንክ እንደሚለው ብዙ ቢሊየነሮች ከኮቪድ-19 በኋላ ደግ፣ ቸር፣ እና ለጋስ ሆነዋል። "በእኛ ጥናት መሰረት 209 የዓለም ቢሊየነሮች በይፋ ተናግረው የለገሱት ብር ድምር 7.2 ቢሊየነር ዶላር ነው" ይላል ባንኩ። ይህ አሐዝ ከመጋቢት እስከ ሰኔ 2020 ብቻ ቃል ተገብቶ የተለገሰ ነው። የዚህ ልግስና ባህሪ ከስከዛሬው የሚለየው በፍጥነት መሆኑና ተለጋሽ ተቋማትም ገንዘቡን ለፈለጉት አገልግሎት በፈለጉት መንገድ እንዲያውሉት መደረጉ ነው ይላል ባንኩ። ጥናቱ የታላቋ ብሪታኒያ ቢሊየነሮች ከብዙ አገሮች አንጻር ትንሹን ልግስና ማሳየታቸው አስገርሞል። በአሜሪካ ለምሳሌ 98 ቢሊየነሮች 4.5 ቢሊዮን ዶላር ለግሰዋል። በቻይና 12 ቢሊየነሮች 679 ሚሊዮን ዶላር ልግሰዋል። በታላቋ ብሪታኒያ ግን 9 ቢሊየነሮች ብቻ ናቸው መለገስ የቻሉት። ድምሩም 300 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ብቻ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-54456858
3politics
በሱዳን ዳርፉር ግዛት በተነሳ ግጭት ከ100 በላይ ሰዎች ተገደሉ
በምዕራብ ሱዳን ዳርፉር ግዛት ለቀናት በዘለቀ የብሄር ግጭት ከ100 በላይ ሰዎች ተገደሉ። በአረብ ጎሳዎች እና በቀድሞ አማፂያን የሚደገፉት የአፍሪካ ማሳሊት ማህበረሰብ ተዋጊዎች መካከል ውጊያ ለቀናት ሲደረግ ቆይቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደገለጸው በክሪኒክ ግዛት አካባቢ ባለው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። የተወሰኑትም ድንበር አቋርጠው ወደ ጎረቤት አገር ቻድ መግባታቸው ተገልጿል። ከግጭቱ የተረፉ ግለሰቦች እንደተናገሩት ታጣቂዎች ከክሬኒክ በስተምዕራብ በሚገኝ መንደር ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል፤ እንዲሁም ቤቶችን ከማቃጠላቸው በፊት ተኩስ ከፍተዋል። በዋናው መንገድ ላይም አድፍጠው ህዝቡ ወደሌሎች ቦታዎች እንዳይሻገር ዘግተው ነበር ተብሏል። ከዚህም ጋር በተያያዘ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ማግኘት አልቻሉም። በባለፈው ሳምንት መጨረሻ እሁድ እለት በተለያዩ ማህበረሰቦች መካከል በተቀሰቀሰ አዲስ ግጭት በትንሹ 55 ሰዎች ተገድለዋል። ማክሰኞ እለት በአካባቢው በሚገኝ ቁጥቋጦ ውስጥ ተጨማሪ አስከሬኖች የተገኙ ሲሆን የሟቾችንም ቁጥር ከ100 በላይ አድርሶታል። ከዚህም በተጨማሪ በደርዘን የሚቆጠሩ ደብዛቸው የደረሰበት አልታወቀም። ባለፈው ወር በምእራብ ዳርፉር በተለያዩ አካባቢዎች 43 ሰዎች ተገድለዋል። በግጭት በምትናጠው ዳርፉር ደቡባዊ ግዛትም ብሄር ተኮር ግጭቶች መከሰታቸውም ታውቋል። መንግስት ብጥብጡን ለመቆጣጠር የመከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ኃይልና፣ የፖሊስ ጥምር ሃይል ወደ ምዕራብ እና ደቡብ ዳርፉር አሰማርቷል።
በሱዳን ዳርፉር ግዛት በተነሳ ግጭት ከ100 በላይ ሰዎች ተገደሉ በምዕራብ ሱዳን ዳርፉር ግዛት ለቀናት በዘለቀ የብሄር ግጭት ከ100 በላይ ሰዎች ተገደሉ። በአረብ ጎሳዎች እና በቀድሞ አማፂያን የሚደገፉት የአፍሪካ ማሳሊት ማህበረሰብ ተዋጊዎች መካከል ውጊያ ለቀናት ሲደረግ ቆይቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደገለጸው በክሪኒክ ግዛት አካባቢ ባለው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። የተወሰኑትም ድንበር አቋርጠው ወደ ጎረቤት አገር ቻድ መግባታቸው ተገልጿል። ከግጭቱ የተረፉ ግለሰቦች እንደተናገሩት ታጣቂዎች ከክሬኒክ በስተምዕራብ በሚገኝ መንደር ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል፤ እንዲሁም ቤቶችን ከማቃጠላቸው በፊት ተኩስ ከፍተዋል። በዋናው መንገድ ላይም አድፍጠው ህዝቡ ወደሌሎች ቦታዎች እንዳይሻገር ዘግተው ነበር ተብሏል። ከዚህም ጋር በተያያዘ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ማግኘት አልቻሉም። በባለፈው ሳምንት መጨረሻ እሁድ እለት በተለያዩ ማህበረሰቦች መካከል በተቀሰቀሰ አዲስ ግጭት በትንሹ 55 ሰዎች ተገድለዋል። ማክሰኞ እለት በአካባቢው በሚገኝ ቁጥቋጦ ውስጥ ተጨማሪ አስከሬኖች የተገኙ ሲሆን የሟቾችንም ቁጥር ከ100 በላይ አድርሶታል። ከዚህም በተጨማሪ በደርዘን የሚቆጠሩ ደብዛቸው የደረሰበት አልታወቀም። ባለፈው ወር በምእራብ ዳርፉር በተለያዩ አካባቢዎች 43 ሰዎች ተገድለዋል። በግጭት በምትናጠው ዳርፉር ደቡባዊ ግዛትም ብሄር ተኮር ግጭቶች መከሰታቸውም ታውቋል። መንግስት ብጥብጡን ለመቆጣጠር የመከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ኃይልና፣ የፖሊስ ጥምር ሃይል ወደ ምዕራብ እና ደቡብ ዳርፉር አሰማርቷል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59580108
5sports
የሱቶን ግምት፡ አርሰናል ሊቨርፑልን 4 ለ 1 ሊያሸንፍ ይችላል?
የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የማንቸስተር ደርቢ ሲቲ በበላይነት ያጠናቅቃል ማለቱ ተሳክቶለታል። በዚህ ሳምንትም በአርሰናል እና በሊቨርፑል ጨዋታ ትልቅ ግምት አስቀምጧል። “ላውሮ ቀድሞ ግምቱን ያስቀምጥ ነበረው የስፖርት ተንታኝ) ሊቨርፑል ይሸነፋል ብሎ አይገምትም። እኔ ግን ይሸነፋሉ ሳይሆን ይቀጠቀጣሉ ነው የምለው” ይላል ሱቶን። የሊጉ የዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ እሑድ እና ሰኞ ይከናወናሉ። ሱቶን እንደተለመደው በዚህ ሳምንትም እንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ ጨዋታዎችን ግምት አስቀምጧል። በርንማውዝ ከ ሌስተር በየሳምንቱ በርንማውዝ ይሸነፋል እያልኩ ያለፉትን አራት ጨዋታዎች አልተሸነፉም። ጎልም አላስተናገዱም። ከቆመ ኳስ ሌስተር ላይ ስጋት ቢፈጥሩም ቀበሮዎቹ ምን መስራት እንደሚችሉ ከፎረስተ ጋር አሳይተዋል። ፉክክር ያለበት ጨዋታ ይሆናል። በዚህ ጨዋታም በርንማውዝ ግምቴን የሚያፈርስ ውጤት ያስመዘግባል? ግምት፡ 1 – 2 ዎልቭሶች አሰልጣኝ በሩኖ ላዥን በጊዜ ማሰናበቱ ትንሽ ጭካኔ የሞላው ነው። ጎል ማስቆጠር አለመቻላቸው የአሰልጣኙ ጥፋት ሳይሆን የአጥቂዎቹ መጎዳት ነው። ዎልቭስ አሰልጣኝ ያልተሾመላቸው ሲሆን ይህንን ጨዋታም አያሸንፉም። ቼልሲም ከግርሃም ፖተር ጋር ህይወት የጀመረበት ወቅት ነው። ፒዬር-ኤምሪክ ኦባመያንግ ጎል ማስቆጠር ጀምሯል። ስለዚህ በቀላሉ ሦስት ነጥብ ያሳካሉ። ግምት፡ 2 – 0 የሳውዝሃምፕተኑ አለቃ ራልፍ ሃሰንሃትል ይባረራሉ የሚል ወሬ አለ። ከሲቲ ጋር መጫወት ደግሞ ትልቅ ዕድል ነው። ቡድኑ ባለፈው ዓመት በሁለቱም ጨዋታ አቻ ቢለያዩም ዘንድሮ ግን ኢትሃድ ላይ አያሳኩትም። የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን የጎሎቹን መጠን የቅርጫት ኳስ ሊያስመስለው ይችላል። ካለው የጨዋታ መደራረብ ግን በቂ ጎሎች ላይ ሲደርስ ቡድኑ ይቀዘቅዛል። በዚህ ምክንያት ብዙ ጎል አልገምትም። ሲቲ በፍጥነት አራት ጎሎችን አስቆጥሮ ጨዋታውን መቆጣጠር የሚጀመር ይመስለኛል። ግምት፡ 4 – 0 ባለፈው ሳምንት ኒውካስል ፉልሃምን ሲያሸንፍ ወደ ፊት የሚሄዱበት መንገድ አስገራሚ ነበር። ካለም ዊልሰን ከጉዳት ተመልሶ ምርጥ ብቃት ላይ ሲገኝ ሚጌዌል አልሚሮን ደግሞ ካለፈው ዓመት ተሻሽሏል። ኒውካስል ጨዋታውን በመቆጣጠር እና ዕድሎችን በመፍጠር ያሸንፋል። የብሬንትፎርዱ አጥቂ ኢቫን ቶኒ ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ ሲመለስ ማረጋገጥ የሚፈለገው ነጥብ ይኖራል። ግምት፡ 2 – 1 ብራይትን ድንቅ አቋም ላይ ስለሚገኝ ይህን ጨዋታ ለመገመት ከባድ ነው። ሊያንድሮ ትሮሳድ አንፊልድ ላይ አስደናቂ ሆኖ ሲያመሽ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ደ ዜብሪም ማጥቃት የሚወዱ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ቶተንሃም ዘንድሮ ማጥቃት ላይ የተመሠረተ አጨዋወት የሚመርጥ አይመስልም። የብራይተን አጨዋወት ግን ይመቻቸዋል። ግምት፡ 1 – 1 ክሪስታል ፓላስ ከ ሊድስ ይህን ጨዋታ ባለፈው ዓመት ዘግቤዋለሁ። ጨዋታው ሳቢ ካለመሆኑም በላይ 0 ለ 0 ነበር የተጠናቀቀው። ይህም ድንቅ ጨዋታ አይሆንም። ውጤቱን በጣም የሚፈልጉት ፓላሶች ያሸነፋሉ ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 1 – 0 ዌስት ሃም ከ ፉልሃም ዌስተሃም ባለፈው ሳምንት አስፈላጊ ነጥቦችን ከዎልቭስ ላይ ሰብስቧል። መዶሻዎቹ በጥሩ አቋም ላይ ስለመሆናቸው ይህ ጨዋታ የሚፈተሹበት ይሆናል። የፉልሃም ነገር የሚወሰነው በተጎዳው አጥቂያቸው አሌክሳንደር ሚትሮቪች ጤንነት ላይ ነው። ግምት፡ 2 – 1 አርሰናል ባለፈው ሳምንት ከቶተንሃም ጋር ነበረው ጨዋታ ላይ ሳቢ ነበር። በዚህ ጨዋታም በተመሳሳይ ይደግመዋል። መድፈኞቹ በጥሩ አጨዋወት እና ልበ ሙሉነት ላይ ሲገኙ ቀያዮቹ ግን ነገሮች ገና አልተሰካኩላቸውም። የርገን ክሎፕ ቡድን በቻምፒዮንስ ሊጉ ከሬንጀርስ ጋር ጥሩ ቢሆንም የተከላካይ መስመሩ አልተፈተነም። ማርቲኔሊ፣ ሳካ እና ጂሰስ ግን ፋታ የሚሰጧቸው አይመስልም። ሊቨርፑል ጎል ማስቆጠር ቢችልም አርሰናል ባለው የማጥቃት መስመር ጥንካሬ የበላይ ሆኖ ያጠናቅቃል። ግምት፡ 4 – 1 ኤቨርተን ባለፈው ሳምንት ጥሩ ብቃት ላይ ሳይሆንም ሳውዝሃምፕተንን ማሸነፍ ችሏል። ብዙ ጎል ስለማይቆጠርባቸው ዕድሎችን ባይፈጥሩም በጨዋተ መቆየት ይችላሉ። ማንቸስተር ዩናይትድ ባለፈው ሳምንት በሲቲ የደረሰበት ሽንፈት ሁሉንም የሚያጋጥም ነው። ቡድኑ በኤሪክ ቴን ሃግ ስር የተወሰነ መሻሻል አሳይቷል። ከአራት ድሎቻቸው በኋላ ይሰናከላሉ ብዬ አልጠብቅም። ሲቲን በመሰለ ቡድን በመሸነፋቸውም ችግር ውስጥ ናቸው አልልም። ኤቨርተን በሜዳው የሚያጠቃ ቢመስለኝም ሁለቱም ቡድኖች ነጥብ ይጋራሉ። ግምት፡ 1 – 1 ኖቲንግሃም ፎረስት ከ አስቶን ቪላ የፎረስቱ አለቃ ስቲቭ ኩፐር በኃላፊነታቸው ቢቀጥሉም ነገሮች ጥሩ እየሄዱላቸው አይደለም። በሌላ በኩል በአስር ተጫዋች ለ45 ደቂቃ ያህል የተጫወተውን ሊድስን ማሸነፍ ባለመቻሉ አስቶን ቪላ የሚገኝበትን ለማወቅ ያዳግታል። ቡድኑ በሚጠበቀው ደረጃ አለመሻሻሉን የሚገልጹ ደጋፊዎች አሉ። ፊሊፔ ኮቲንሆም ዘንድሮ ጥሩ አቋም ላይ አይገኝም። የፎረስት በራስ መተማመን ዝቀትኛ በመሆኑ ቪላ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ። ግምት፡ 0 – 1
የሱቶን ግምት፡ አርሰናል ሊቨርፑልን 4 ለ 1 ሊያሸንፍ ይችላል? የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የማንቸስተር ደርቢ ሲቲ በበላይነት ያጠናቅቃል ማለቱ ተሳክቶለታል። በዚህ ሳምንትም በአርሰናል እና በሊቨርፑል ጨዋታ ትልቅ ግምት አስቀምጧል። “ላውሮ ቀድሞ ግምቱን ያስቀምጥ ነበረው የስፖርት ተንታኝ) ሊቨርፑል ይሸነፋል ብሎ አይገምትም። እኔ ግን ይሸነፋሉ ሳይሆን ይቀጠቀጣሉ ነው የምለው” ይላል ሱቶን። የሊጉ የዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ እሑድ እና ሰኞ ይከናወናሉ። ሱቶን እንደተለመደው በዚህ ሳምንትም እንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ ጨዋታዎችን ግምት አስቀምጧል። በርንማውዝ ከ ሌስተር በየሳምንቱ በርንማውዝ ይሸነፋል እያልኩ ያለፉትን አራት ጨዋታዎች አልተሸነፉም። ጎልም አላስተናገዱም። ከቆመ ኳስ ሌስተር ላይ ስጋት ቢፈጥሩም ቀበሮዎቹ ምን መስራት እንደሚችሉ ከፎረስተ ጋር አሳይተዋል። ፉክክር ያለበት ጨዋታ ይሆናል። በዚህ ጨዋታም በርንማውዝ ግምቴን የሚያፈርስ ውጤት ያስመዘግባል? ግምት፡ 1 – 2 ዎልቭሶች አሰልጣኝ በሩኖ ላዥን በጊዜ ማሰናበቱ ትንሽ ጭካኔ የሞላው ነው። ጎል ማስቆጠር አለመቻላቸው የአሰልጣኙ ጥፋት ሳይሆን የአጥቂዎቹ መጎዳት ነው። ዎልቭስ አሰልጣኝ ያልተሾመላቸው ሲሆን ይህንን ጨዋታም አያሸንፉም። ቼልሲም ከግርሃም ፖተር ጋር ህይወት የጀመረበት ወቅት ነው። ፒዬር-ኤምሪክ ኦባመያንግ ጎል ማስቆጠር ጀምሯል። ስለዚህ በቀላሉ ሦስት ነጥብ ያሳካሉ። ግምት፡ 2 – 0 የሳውዝሃምፕተኑ አለቃ ራልፍ ሃሰንሃትል ይባረራሉ የሚል ወሬ አለ። ከሲቲ ጋር መጫወት ደግሞ ትልቅ ዕድል ነው። ቡድኑ ባለፈው ዓመት በሁለቱም ጨዋታ አቻ ቢለያዩም ዘንድሮ ግን ኢትሃድ ላይ አያሳኩትም። የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን የጎሎቹን መጠን የቅርጫት ኳስ ሊያስመስለው ይችላል። ካለው የጨዋታ መደራረብ ግን በቂ ጎሎች ላይ ሲደርስ ቡድኑ ይቀዘቅዛል። በዚህ ምክንያት ብዙ ጎል አልገምትም። ሲቲ በፍጥነት አራት ጎሎችን አስቆጥሮ ጨዋታውን መቆጣጠር የሚጀመር ይመስለኛል። ግምት፡ 4 – 0 ባለፈው ሳምንት ኒውካስል ፉልሃምን ሲያሸንፍ ወደ ፊት የሚሄዱበት መንገድ አስገራሚ ነበር። ካለም ዊልሰን ከጉዳት ተመልሶ ምርጥ ብቃት ላይ ሲገኝ ሚጌዌል አልሚሮን ደግሞ ካለፈው ዓመት ተሻሽሏል። ኒውካስል ጨዋታውን በመቆጣጠር እና ዕድሎችን በመፍጠር ያሸንፋል። የብሬንትፎርዱ አጥቂ ኢቫን ቶኒ ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ ሲመለስ ማረጋገጥ የሚፈለገው ነጥብ ይኖራል። ግምት፡ 2 – 1 ብራይትን ድንቅ አቋም ላይ ስለሚገኝ ይህን ጨዋታ ለመገመት ከባድ ነው። ሊያንድሮ ትሮሳድ አንፊልድ ላይ አስደናቂ ሆኖ ሲያመሽ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ደ ዜብሪም ማጥቃት የሚወዱ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ቶተንሃም ዘንድሮ ማጥቃት ላይ የተመሠረተ አጨዋወት የሚመርጥ አይመስልም። የብራይተን አጨዋወት ግን ይመቻቸዋል። ግምት፡ 1 – 1 ክሪስታል ፓላስ ከ ሊድስ ይህን ጨዋታ ባለፈው ዓመት ዘግቤዋለሁ። ጨዋታው ሳቢ ካለመሆኑም በላይ 0 ለ 0 ነበር የተጠናቀቀው። ይህም ድንቅ ጨዋታ አይሆንም። ውጤቱን በጣም የሚፈልጉት ፓላሶች ያሸነፋሉ ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 1 – 0 ዌስት ሃም ከ ፉልሃም ዌስተሃም ባለፈው ሳምንት አስፈላጊ ነጥቦችን ከዎልቭስ ላይ ሰብስቧል። መዶሻዎቹ በጥሩ አቋም ላይ ስለመሆናቸው ይህ ጨዋታ የሚፈተሹበት ይሆናል። የፉልሃም ነገር የሚወሰነው በተጎዳው አጥቂያቸው አሌክሳንደር ሚትሮቪች ጤንነት ላይ ነው። ግምት፡ 2 – 1 አርሰናል ባለፈው ሳምንት ከቶተንሃም ጋር ነበረው ጨዋታ ላይ ሳቢ ነበር። በዚህ ጨዋታም በተመሳሳይ ይደግመዋል። መድፈኞቹ በጥሩ አጨዋወት እና ልበ ሙሉነት ላይ ሲገኙ ቀያዮቹ ግን ነገሮች ገና አልተሰካኩላቸውም። የርገን ክሎፕ ቡድን በቻምፒዮንስ ሊጉ ከሬንጀርስ ጋር ጥሩ ቢሆንም የተከላካይ መስመሩ አልተፈተነም። ማርቲኔሊ፣ ሳካ እና ጂሰስ ግን ፋታ የሚሰጧቸው አይመስልም። ሊቨርፑል ጎል ማስቆጠር ቢችልም አርሰናል ባለው የማጥቃት መስመር ጥንካሬ የበላይ ሆኖ ያጠናቅቃል። ግምት፡ 4 – 1 ኤቨርተን ባለፈው ሳምንት ጥሩ ብቃት ላይ ሳይሆንም ሳውዝሃምፕተንን ማሸነፍ ችሏል። ብዙ ጎል ስለማይቆጠርባቸው ዕድሎችን ባይፈጥሩም በጨዋተ መቆየት ይችላሉ። ማንቸስተር ዩናይትድ ባለፈው ሳምንት በሲቲ የደረሰበት ሽንፈት ሁሉንም የሚያጋጥም ነው። ቡድኑ በኤሪክ ቴን ሃግ ስር የተወሰነ መሻሻል አሳይቷል። ከአራት ድሎቻቸው በኋላ ይሰናከላሉ ብዬ አልጠብቅም። ሲቲን በመሰለ ቡድን በመሸነፋቸውም ችግር ውስጥ ናቸው አልልም። ኤቨርተን በሜዳው የሚያጠቃ ቢመስለኝም ሁለቱም ቡድኖች ነጥብ ይጋራሉ። ግምት፡ 1 – 1 ኖቲንግሃም ፎረስት ከ አስቶን ቪላ የፎረስቱ አለቃ ስቲቭ ኩፐር በኃላፊነታቸው ቢቀጥሉም ነገሮች ጥሩ እየሄዱላቸው አይደለም። በሌላ በኩል በአስር ተጫዋች ለ45 ደቂቃ ያህል የተጫወተውን ሊድስን ማሸነፍ ባለመቻሉ አስቶን ቪላ የሚገኝበትን ለማወቅ ያዳግታል። ቡድኑ በሚጠበቀው ደረጃ አለመሻሻሉን የሚገልጹ ደጋፊዎች አሉ። ፊሊፔ ኮቲንሆም ዘንድሮ ጥሩ አቋም ላይ አይገኝም። የፎረስት በራስ መተማመን ዝቀትኛ በመሆኑ ቪላ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ። ግምት፡ 0 – 1
https://www.bbc.com/amharic/articles/cqe742z20d1o
3politics
አውሮፓዊቷ አገር ቤላሩስ የፈረንሳይ አምባሳደርን አባረርች
በቤላሩስ የፈረንሳይ አምባሳደር አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ በታዘዙት መሠረት ወደ መጡበት መመለሳቸውን ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። የኤምባሲው ቃል አቀባይ ለፈረንሳይ ዜና ወኪል እንደተናገሩት አምባሳደር ኒኮላስ ደ ላስት ቤላሩስን ለቀው የወጡት እሑድ ዕለት ነው። የቤላሩስ መንግሥት አምባሳደሩ ዋና ከተማዋ ሚኒስክን ለቀው እንዲወጡ እስከ ሰኞ ድረስ ቀነ ገደብ ሰጥቶ ነበር። የ57 ዓመቱ አምባሳደር ኒኮላስ ባለፈው ዓመት ነበር በቤላሩስ የፈረንሳይ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት። የቤላሩስ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት አምባሳደሩ የሥራ ፈቃዳቸውን ለፕሬዝደንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ አላቀረቡም። ፈረንሳይ ልክ እንደሌሎቹ የአውሮፓ አገራት የቤላሩሱ መሪ ሉካሼንኮ ባለፈው ዓመት ነሐሴ የተደረገውን ምርጫ አሸንፍኩ ብለው ለስድስተኛ ጊዜ ፕሬዝደንት ሆነው መመረጣቸው አልተዋጠላትም። አምባሳደሩ ባለፈው ታኅሣሥ ፕሬዝደንቱን በማግኘት ፈንታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቭላድሚር ማኬይን ነው ያገኙት። ለኤኤፍፒ በተላከ መግለጫ የፈረንሳይ ኤምባሲ ቃል አቀባይ "የቤላሩስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደሩ ከሰኞ በፊት ለቀው እንዲወጡ ነው ያዘዘው" ብለዋል። "ሁሉንም የኤምባሲውን ሠራተኞች ተሰናብተው ነው የሄዱት። ለቤላሩስ ሕዝብ በተንቀሳቃሽ ምስል ቀድተው ያስቀመጡት መልዕክት በኤምባሲው ድረ-ገፅ ይለቀቃል።" የአውሮፓ ሕብረት በተደጋጋሚ ባለፈው ነሐሴ የተካሄደው ምርጫ "ነፃና ፍትሐዊ" ነው ብሎ እንደማያምን አሳውቋል። ሕብረቱ አልፎም በፕሬዝደንት ሉካሼንኮ አገዛዝ ላይ ማዕቀብ መጣሉ የሚዘነጋ አይደለም። ፕሬዝደንቱ ከምርጫው በኋላ ለዓመታት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ተቃውሞ እያሰሙ ያሉ ዜጎች ላይ ከፍተኛ የኃይል እርምጃ ወስደዋል። ምንም እንኳ የምዕራቡ ዓለም ማዕቀብ ቢጥልባቸውም ሉካሼንኮ ሥልጣናቸውን ተቆናጠው እንደያዙ ናቸው። የ67 ዓመቱ የቤላሩስ መሪ አገራቸውን በፈረንጆቹ ከ1994 ጀምሮ ገዝተዋል። ዘንድሮ ከአውሮፓ አገራት በደረሰባቸው ጫና ምክንያት ከአብዛኛዎቹ ጋር ያላቸውን ግንኙነት አቋርጠዋል። የፕሬዝደንቱ ዋነኛ ደጋፊ የሚባሉት የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። ባለፈው መጋቢት የቤላሩስ መንግሥት የላትቪያ አምባሳደርን ጨምሮ ሁሉንም የኤምባሲ ሠራተኞች ማባረሩ ይታወሳል። ይህ የሆነው በላትቪያ በተካሄደ የበረዶ መንሸራተት ጨዋታ ላይ የቤላሩስ ተቃውሞን የሚያንፀባርቅ ባንዲራ በመታየቱ ነው። የቀድሞ የሶቪዬት ግዛት የነበረችው አገር ባለፈው ነሐሴ ደግሞ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ወደ ቤላሩስ ሊጓዙ ለነበሩት ጁሊ ፊሸር የሥራ ፈቃድ እንደማትሰጥ አሳውቃ ነበር።
አውሮፓዊቷ አገር ቤላሩስ የፈረንሳይ አምባሳደርን አባረርች በቤላሩስ የፈረንሳይ አምባሳደር አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ በታዘዙት መሠረት ወደ መጡበት መመለሳቸውን ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። የኤምባሲው ቃል አቀባይ ለፈረንሳይ ዜና ወኪል እንደተናገሩት አምባሳደር ኒኮላስ ደ ላስት ቤላሩስን ለቀው የወጡት እሑድ ዕለት ነው። የቤላሩስ መንግሥት አምባሳደሩ ዋና ከተማዋ ሚኒስክን ለቀው እንዲወጡ እስከ ሰኞ ድረስ ቀነ ገደብ ሰጥቶ ነበር። የ57 ዓመቱ አምባሳደር ኒኮላስ ባለፈው ዓመት ነበር በቤላሩስ የፈረንሳይ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት። የቤላሩስ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት አምባሳደሩ የሥራ ፈቃዳቸውን ለፕሬዝደንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ አላቀረቡም። ፈረንሳይ ልክ እንደሌሎቹ የአውሮፓ አገራት የቤላሩሱ መሪ ሉካሼንኮ ባለፈው ዓመት ነሐሴ የተደረገውን ምርጫ አሸንፍኩ ብለው ለስድስተኛ ጊዜ ፕሬዝደንት ሆነው መመረጣቸው አልተዋጠላትም። አምባሳደሩ ባለፈው ታኅሣሥ ፕሬዝደንቱን በማግኘት ፈንታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቭላድሚር ማኬይን ነው ያገኙት። ለኤኤፍፒ በተላከ መግለጫ የፈረንሳይ ኤምባሲ ቃል አቀባይ "የቤላሩስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደሩ ከሰኞ በፊት ለቀው እንዲወጡ ነው ያዘዘው" ብለዋል። "ሁሉንም የኤምባሲውን ሠራተኞች ተሰናብተው ነው የሄዱት። ለቤላሩስ ሕዝብ በተንቀሳቃሽ ምስል ቀድተው ያስቀመጡት መልዕክት በኤምባሲው ድረ-ገፅ ይለቀቃል።" የአውሮፓ ሕብረት በተደጋጋሚ ባለፈው ነሐሴ የተካሄደው ምርጫ "ነፃና ፍትሐዊ" ነው ብሎ እንደማያምን አሳውቋል። ሕብረቱ አልፎም በፕሬዝደንት ሉካሼንኮ አገዛዝ ላይ ማዕቀብ መጣሉ የሚዘነጋ አይደለም። ፕሬዝደንቱ ከምርጫው በኋላ ለዓመታት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ተቃውሞ እያሰሙ ያሉ ዜጎች ላይ ከፍተኛ የኃይል እርምጃ ወስደዋል። ምንም እንኳ የምዕራቡ ዓለም ማዕቀብ ቢጥልባቸውም ሉካሼንኮ ሥልጣናቸውን ተቆናጠው እንደያዙ ናቸው። የ67 ዓመቱ የቤላሩስ መሪ አገራቸውን በፈረንጆቹ ከ1994 ጀምሮ ገዝተዋል። ዘንድሮ ከአውሮፓ አገራት በደረሰባቸው ጫና ምክንያት ከአብዛኛዎቹ ጋር ያላቸውን ግንኙነት አቋርጠዋል። የፕሬዝደንቱ ዋነኛ ደጋፊ የሚባሉት የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። ባለፈው መጋቢት የቤላሩስ መንግሥት የላትቪያ አምባሳደርን ጨምሮ ሁሉንም የኤምባሲ ሠራተኞች ማባረሩ ይታወሳል። ይህ የሆነው በላትቪያ በተካሄደ የበረዶ መንሸራተት ጨዋታ ላይ የቤላሩስ ተቃውሞን የሚያንፀባርቅ ባንዲራ በመታየቱ ነው። የቀድሞ የሶቪዬት ግዛት የነበረችው አገር ባለፈው ነሐሴ ደግሞ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ወደ ቤላሩስ ሊጓዙ ለነበሩት ጁሊ ፊሸር የሥራ ፈቃድ እንደማትሰጥ አሳውቃ ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/news-58951085
2health
እስራኤል የማትሪክ ፈተና ለሚቀመጡ ተማሪዎቿ ክትባት መስጠት ጀመረች
እስራኤል ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 18 የሚሆኑ ወጣቶችን ኮቪድ ክትባት መስጠት ጀመረች። ለነዚህ ወጣቶች ክትባቱ እንዲሰጠት የሆነው የማትሪክ ፈተና ሊቀመጡ ስለሆነ ነው። እስራኤል 9 ሚሊዮን ከሚሆነው ሕዝቧ ውስጥ ሩብ ያህሉ የመጀመርያውን የክትባት ጠብታ ወስዷል። የክትባቱ አይነትም ፋይዘር ሰራሹ መሆኑ ታውቋል። እስራኤል ለዜጎቿ ክትባት መስጠት የጀመረችው ባለፈው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ አካባቢ ከዲሴምበር 19 ጀምሮ ነው። ክትባቱ ሲጀመር ቅድሚያ የተሰጣቸው እድሜያቸው ለገፉ አዛውንቶች ሲሆን ከዚያም ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች ነበር። አሁን ዕድሜያቸው ከ40 በላይ የሆኑ ዜጎች ክትባቱን በመወሰድ ላይ ናቸው። እስራኤል ኢኮኖሚዋን በየካቲት ወር ሙሉ በሙሉ ለመክፈት እየታተረች ነው። የእስራኤል የትምህርት ሚኒስትር እንዳሉት አሁን ወጣት ተማሪዎችን መከተብ የተጀመረው ወደ ትምህርት እንዲመለሱና ፈተና እንዲቀመጡ ለማስቻል ነው። ወጣት ተማሪዎቹ ክትባቱን የሚወስዱት በወላጆቻቸው ፈቃድ ነው። እስራኤል ያሉ ተማሪዎች የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ሲጨርሱ የሚወስዱት የማትሪክ ፈተና ወደ ዩኒቨርስቲ ለመግባት አለመግባት የሚለዩበት ነው። የሚያመጡት ውጤትም በውትድርና ተሳትፏቸው ላይ ወሳኝ ሚና አለው። በእስራኤል ዜጎች ለተወሰነ ጊዜ የግዴታ የውትድርና አገልግሎትን ይሰጣሉ። የአገሪቱ የትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ክትባቱ መሰጠቱን እየቀጠለ ቢሆንም በሚቀጥለው ወር ትምህርት ስለመጀመር አለመጀመሩ ለመናገር ጊዜው ገና ነው። እስራኤል ክትባት በመስጠት ከአለም ፈጣኗ አገር ሆና ነው በዲሴምበር 19 የጀመረችው። በፈረንጆቹ 2020 መገባደጃ የሕዝቧን 10 እጅ ከትባ ጨርሳለች። እስራኤል 600ሺህ በተህዋሲው የተያዙ ዜጎች ያሏት ሲሆን 4ሺ የሚሆኑት ሞተውባታል። ትናንት የእሰራኤል መንግሥት ባወጣው አዲስ መመርያ የመንገደኞች በረራን ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ የጥር ወርን ሙሉ ማገዱን አስታውቋል። ይህም ተህዋሲውን ለመቆጣጠር የሚደረግ ጥረት አንድ አካል ነው። ቤንያሚን ኔትንያሁ እንደተናገሩት ይህ የበረራ እገድ አዲሱ የኮቪድ ዝርያ ወደ እስራኤል እንዳይገባ ለማድረግ የሚወሰድ ጥብቅ እርምጃ ነው ብለዋል። በአሁኑ ጊዜ የውጭ ዜጎች ወደ እስራኤል እንዲገቡ እየተፈቀደላቸው አይደለም። እስራኤል በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ 9 ሚሊዮን ዜጎቿን ጸረ ኮቪድ ክትባት በመከተብ የዓለም የመጀመርያዋ አገር ለመሆን ቀን ተሌት እየሰራች ትገኛለች።
እስራኤል የማትሪክ ፈተና ለሚቀመጡ ተማሪዎቿ ክትባት መስጠት ጀመረች እስራኤል ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 18 የሚሆኑ ወጣቶችን ኮቪድ ክትባት መስጠት ጀመረች። ለነዚህ ወጣቶች ክትባቱ እንዲሰጠት የሆነው የማትሪክ ፈተና ሊቀመጡ ስለሆነ ነው። እስራኤል 9 ሚሊዮን ከሚሆነው ሕዝቧ ውስጥ ሩብ ያህሉ የመጀመርያውን የክትባት ጠብታ ወስዷል። የክትባቱ አይነትም ፋይዘር ሰራሹ መሆኑ ታውቋል። እስራኤል ለዜጎቿ ክትባት መስጠት የጀመረችው ባለፈው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ አካባቢ ከዲሴምበር 19 ጀምሮ ነው። ክትባቱ ሲጀመር ቅድሚያ የተሰጣቸው እድሜያቸው ለገፉ አዛውንቶች ሲሆን ከዚያም ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች ነበር። አሁን ዕድሜያቸው ከ40 በላይ የሆኑ ዜጎች ክትባቱን በመወሰድ ላይ ናቸው። እስራኤል ኢኮኖሚዋን በየካቲት ወር ሙሉ በሙሉ ለመክፈት እየታተረች ነው። የእስራኤል የትምህርት ሚኒስትር እንዳሉት አሁን ወጣት ተማሪዎችን መከተብ የተጀመረው ወደ ትምህርት እንዲመለሱና ፈተና እንዲቀመጡ ለማስቻል ነው። ወጣት ተማሪዎቹ ክትባቱን የሚወስዱት በወላጆቻቸው ፈቃድ ነው። እስራኤል ያሉ ተማሪዎች የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ሲጨርሱ የሚወስዱት የማትሪክ ፈተና ወደ ዩኒቨርስቲ ለመግባት አለመግባት የሚለዩበት ነው። የሚያመጡት ውጤትም በውትድርና ተሳትፏቸው ላይ ወሳኝ ሚና አለው። በእስራኤል ዜጎች ለተወሰነ ጊዜ የግዴታ የውትድርና አገልግሎትን ይሰጣሉ። የአገሪቱ የትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ክትባቱ መሰጠቱን እየቀጠለ ቢሆንም በሚቀጥለው ወር ትምህርት ስለመጀመር አለመጀመሩ ለመናገር ጊዜው ገና ነው። እስራኤል ክትባት በመስጠት ከአለም ፈጣኗ አገር ሆና ነው በዲሴምበር 19 የጀመረችው። በፈረንጆቹ 2020 መገባደጃ የሕዝቧን 10 እጅ ከትባ ጨርሳለች። እስራኤል 600ሺህ በተህዋሲው የተያዙ ዜጎች ያሏት ሲሆን 4ሺ የሚሆኑት ሞተውባታል። ትናንት የእሰራኤል መንግሥት ባወጣው አዲስ መመርያ የመንገደኞች በረራን ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ የጥር ወርን ሙሉ ማገዱን አስታውቋል። ይህም ተህዋሲውን ለመቆጣጠር የሚደረግ ጥረት አንድ አካል ነው። ቤንያሚን ኔትንያሁ እንደተናገሩት ይህ የበረራ እገድ አዲሱ የኮቪድ ዝርያ ወደ እስራኤል እንዳይገባ ለማድረግ የሚወሰድ ጥብቅ እርምጃ ነው ብለዋል። በአሁኑ ጊዜ የውጭ ዜጎች ወደ እስራኤል እንዲገቡ እየተፈቀደላቸው አይደለም። እስራኤል በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ 9 ሚሊዮን ዜጎቿን ጸረ ኮቪድ ክትባት በመከተብ የዓለም የመጀመርያዋ አገር ለመሆን ቀን ተሌት እየሰራች ትገኛለች።
https://www.bbc.com/amharic/55792458
3politics
መርማሪ ቡድኑ በትራምፕ ላይ መጥሪያ እንዲቆረጥባቸው ወሰነ
ባለፈው ዓመት የአሜሪካ ምርጫን ተከትሎ የተነሳውን ነውጥ ለመመርመር በሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት የተዋቀረውና 9 አባላት ያሉት መርማሪ ኮሚሽን ትናንት ምሽት ምርመራውን አጠናቋል። በዚህ የመጨረሻ ነው በተባለ የምርመራ ውጤት የመርማሪ ኮሚሽኑ አባላት በትራምፕ ላይ መጥሪያ እንዲቆረጥና ስለሆነው ነገር ሁሉ ቃል እንዲሰጡ በሙሉ ድምጽ ወስነዋል። ‘ለፈጸመው ተግባር ምላሽ እንዲሰጥ ግድ ይላል’ ብለዋል የሚሲሲፒው ዲሞክራት ወኪልና የመርማሪ ሸንጎው ሊቀ መንበር የሆኑት ቤኒ ቶምሰን። ትራምፕ መጥሪያውን ቸል ካሉ ክስና እስር ይጠብቃቸዋል። ይህ መርማሪ ሸንጎ የትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች ካፒቶል ሒልን ሰብረው ያደረሱትን ጥፋት ሲመረምር ድፍን ዓመት አልፎታል። በዚህ ሸንጎ ከ 9 አባላት ሁለቱ ሪፐብሊካን፣ 7ቱ ደግሞ ዲሞክራቶች ናቸው። የመርማሪ ኮሚሽኑ አባላት ትራምፕ መጥሪያ ተቆርጦላቸው ቃላቸውን እንዲሰጡ የወሰኑት ያለምንም ተቃውሞና ድምጸ ተአቅቦ በሙሉ ድምጽ ነው። ለትራምፕ መጥሪያ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ተቆርጦ ይሰጣቸዋል። የዋዮሚንግ ግዛትና የሪፐብሊካን ተወካይ እንዲሁም የመርማሪው ሸንጎ ምክትል የሆኑት ሊዝ ቼኒ እንዳሉት አሜሪካዊያን ለዚሁ ሁሉ ጥፋት መሠረት ነው ከሚባለው ሰው ሐቁን የመስማት መብት አላቸው። ትናንት በኢትዮጵያ አቆጣጠር ማታ 2፡00 ሰዓት የጀመረው የመርማሪ ቡድኑ 9ኛ ሸንጎ የመጨረሻ ምርመራ ሰነዶችና የቪዲዮ ማስረጃዎች የቀረቡበት ነበር። በርካታ አስደንጋጭ የተባሉ መረጃዎችም ለሕዝብ በቀጥታ ቴሌቪዥን እንዲታዩ ሆነዋል። በዚህ የቪዲዮ ማስረጃ በተለይካፒቶል ሒል ውስጥ የነበሩ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት፣ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፒሎሲን ጨምሮ ከቢሮ ቢሮ ሲሯሯጡ፣ ለዶናልድ ትራምፕ የቅርብ ሰዎች ስልክ ሲደውሉና በከፍተኛ ጭንቅ ከነውጠኞቹ ለማምለጥ ሲሞክሩ የሚያሳዩ አዳዲስ ቪዲዮዎች ለሕዝብይፋ ተደርገዋል። እንደራሴዎቹ በተለይ የጋዝ መከላከያ ጭንብል ሲለብሱና በነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ሁኔታ ሆነው ሲንቀሳቀሱ የቪዲዮ ማስረጃዎች የቀረቡበት ነበር የትናንቱምስክርነት። ዶናልድ ትራምፕ ይህን የመርማሪ ኮሚሽኑን ውሳኔ ፖለቲካዊ ብለውታል። ‘አሜሪካዊያን በዲሞክራቶች ቀሽም አመራር በተማረሩበት ወቅት የፖለቲካ ነጥብ ለማስቆጠር የተቀናበረ ነው፤ የእኔን ምስክርነትከፈለጉ ለምን በምርመራው መጀመርያ አልጠየቁኝም?’ ብለዋል ትራምፕ። ዶናልድ ትራምፕ በ2024 በድጋሚ ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው ፍንጭ ሰጥተዋል። አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ይህ የምርመራ ቡድኑ ውሳኔ ከወር በኋላ ከሳምንታት በኋላ  የሚደረገው ‘ሚድተርም’ ምርጫ ላይ ዲሞክራቶች ሊደርስባቸው የሚችለውን ሽንፈት በመስጋት መራጮችን ለማማለል ሆን ተብሎ የተደረገ ነው ይላሉ። ይህ በሕዝብ እንደራሴዎች የተቋቋመው መርማሪ ቡድን ሙሉ የምርመራ ውጤቱን ከሁለት ወራት በኋላ ይፋ ያደርጋል። ለዓመት ያህል በዘለቀው ምርመራ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን፣ የደህንነት ሰዎችን፣ ሚኒስትሮችን፣ የዶናልድ ትራምፕ የቀድሞ ረዳቶችን፣ የጸጥታ አካላትን ጨምሮ ከአንድ ሺህ አሜሪካዊያን በላይ ምስክርነት ሰምቶ መርምሯል። በዚህ መርማሪ ቡድን ሁለቱ ብቸኛ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል የሆኑት ሊዝ ቼኒ እና አዳም ኪዚንግር ትናንት ትራምፕ የምስክርነት ማዘዣ ተቆርጦባቸው ቃላቸውን እንዲሰጡ ድምጽ በመስጠታቸው በፓርቲያቸው ዘንድ ከፍተኛ ውግዘት ደርሶባቸዋል። በባለፈው ዓመት የትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች የካፒቶል ሒል አመጽ 850 አሜሪካዊያን ክስ ተመስርቶባቸዋል።
መርማሪ ቡድኑ በትራምፕ ላይ መጥሪያ እንዲቆረጥባቸው ወሰነ ባለፈው ዓመት የአሜሪካ ምርጫን ተከትሎ የተነሳውን ነውጥ ለመመርመር በሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት የተዋቀረውና 9 አባላት ያሉት መርማሪ ኮሚሽን ትናንት ምሽት ምርመራውን አጠናቋል። በዚህ የመጨረሻ ነው በተባለ የምርመራ ውጤት የመርማሪ ኮሚሽኑ አባላት በትራምፕ ላይ መጥሪያ እንዲቆረጥና ስለሆነው ነገር ሁሉ ቃል እንዲሰጡ በሙሉ ድምጽ ወስነዋል። ‘ለፈጸመው ተግባር ምላሽ እንዲሰጥ ግድ ይላል’ ብለዋል የሚሲሲፒው ዲሞክራት ወኪልና የመርማሪ ሸንጎው ሊቀ መንበር የሆኑት ቤኒ ቶምሰን። ትራምፕ መጥሪያውን ቸል ካሉ ክስና እስር ይጠብቃቸዋል። ይህ መርማሪ ሸንጎ የትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች ካፒቶል ሒልን ሰብረው ያደረሱትን ጥፋት ሲመረምር ድፍን ዓመት አልፎታል። በዚህ ሸንጎ ከ 9 አባላት ሁለቱ ሪፐብሊካን፣ 7ቱ ደግሞ ዲሞክራቶች ናቸው። የመርማሪ ኮሚሽኑ አባላት ትራምፕ መጥሪያ ተቆርጦላቸው ቃላቸውን እንዲሰጡ የወሰኑት ያለምንም ተቃውሞና ድምጸ ተአቅቦ በሙሉ ድምጽ ነው። ለትራምፕ መጥሪያ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ተቆርጦ ይሰጣቸዋል። የዋዮሚንግ ግዛትና የሪፐብሊካን ተወካይ እንዲሁም የመርማሪው ሸንጎ ምክትል የሆኑት ሊዝ ቼኒ እንዳሉት አሜሪካዊያን ለዚሁ ሁሉ ጥፋት መሠረት ነው ከሚባለው ሰው ሐቁን የመስማት መብት አላቸው። ትናንት በኢትዮጵያ አቆጣጠር ማታ 2፡00 ሰዓት የጀመረው የመርማሪ ቡድኑ 9ኛ ሸንጎ የመጨረሻ ምርመራ ሰነዶችና የቪዲዮ ማስረጃዎች የቀረቡበት ነበር። በርካታ አስደንጋጭ የተባሉ መረጃዎችም ለሕዝብ በቀጥታ ቴሌቪዥን እንዲታዩ ሆነዋል። በዚህ የቪዲዮ ማስረጃ በተለይካፒቶል ሒል ውስጥ የነበሩ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት፣ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፒሎሲን ጨምሮ ከቢሮ ቢሮ ሲሯሯጡ፣ ለዶናልድ ትራምፕ የቅርብ ሰዎች ስልክ ሲደውሉና በከፍተኛ ጭንቅ ከነውጠኞቹ ለማምለጥ ሲሞክሩ የሚያሳዩ አዳዲስ ቪዲዮዎች ለሕዝብይፋ ተደርገዋል። እንደራሴዎቹ በተለይ የጋዝ መከላከያ ጭንብል ሲለብሱና በነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ሁኔታ ሆነው ሲንቀሳቀሱ የቪዲዮ ማስረጃዎች የቀረቡበት ነበር የትናንቱምስክርነት። ዶናልድ ትራምፕ ይህን የመርማሪ ኮሚሽኑን ውሳኔ ፖለቲካዊ ብለውታል። ‘አሜሪካዊያን በዲሞክራቶች ቀሽም አመራር በተማረሩበት ወቅት የፖለቲካ ነጥብ ለማስቆጠር የተቀናበረ ነው፤ የእኔን ምስክርነትከፈለጉ ለምን በምርመራው መጀመርያ አልጠየቁኝም?’ ብለዋል ትራምፕ። ዶናልድ ትራምፕ በ2024 በድጋሚ ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው ፍንጭ ሰጥተዋል። አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ይህ የምርመራ ቡድኑ ውሳኔ ከወር በኋላ ከሳምንታት በኋላ  የሚደረገው ‘ሚድተርም’ ምርጫ ላይ ዲሞክራቶች ሊደርስባቸው የሚችለውን ሽንፈት በመስጋት መራጮችን ለማማለል ሆን ተብሎ የተደረገ ነው ይላሉ። ይህ በሕዝብ እንደራሴዎች የተቋቋመው መርማሪ ቡድን ሙሉ የምርመራ ውጤቱን ከሁለት ወራት በኋላ ይፋ ያደርጋል። ለዓመት ያህል በዘለቀው ምርመራ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን፣ የደህንነት ሰዎችን፣ ሚኒስትሮችን፣ የዶናልድ ትራምፕ የቀድሞ ረዳቶችን፣ የጸጥታ አካላትን ጨምሮ ከአንድ ሺህ አሜሪካዊያን በላይ ምስክርነት ሰምቶ መርምሯል። በዚህ መርማሪ ቡድን ሁለቱ ብቸኛ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል የሆኑት ሊዝ ቼኒ እና አዳም ኪዚንግር ትናንት ትራምፕ የምስክርነት ማዘዣ ተቆርጦባቸው ቃላቸውን እንዲሰጡ ድምጽ በመስጠታቸው በፓርቲያቸው ዘንድ ከፍተኛ ውግዘት ደርሶባቸዋል። በባለፈው ዓመት የትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች የካፒቶል ሒል አመጽ 850 አሜሪካዊያን ክስ ተመስርቶባቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c998p5kdkn1o
3politics
ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ በአፍሪካ ህብረት ንግግር ለማድረግ በድጋሚ ጠየቁ
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በአፍሪካ ህብረት መሪዎችን ለማነጋገር በድጋሚ ጥያቄ እንዳቀረቡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ አስታውቀዋል። ሊቀ መንበሩ በትዊተር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ጥያቄው የመጣው ከዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ነው። በዚህ ውይይት ላይ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ "ከአፍሪካ ኅብረት ጋር የጠበቀ ግንኙነት የመፍጠር ፍላጎት" እንዳላቸውም መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸው ተገልጿል። ፋኪ የፕሬዚዳንቱ ጥያቄ ተቀባይነት ይኖረው እንደሆነ ያልገለጹ ሲሆን ነገር ግን "ከሩሲያ ጋር ላለው ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ አጥብቀው መናገራቸውን" በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ለሴኔጋሉ አቻቸውና ለወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ማኪ ሳል የአፍሪካ መሪዎችን ለማነጋገር ጥያቄ አቅርበው ነበር። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሩሲያ ከተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት እንድትታገድ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ድምጽ ያልሰጡ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ የአፍሪካ ሀገራት የበላይነቱን መያዛቸው ይታወሳል። ውሳኔው በ93 ድጋፍ፣ በ24 ተቃውሞ እና በ58 ድምጸ ተአቅቦ ጸድቋል። በአህጉሪቱ ከሚገኙት 54 ሀገራት አንጎላ፣ ግብፅ፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል እና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ 24ቱ ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል። ከሩሲያ ጋር በታሪክ ጥሩ ግንኙነት የነበራቸው አልጄሪያ እና ኢትዮጵያን ጨምሮ ዘጠኙ እርምጃውን ተቃውመዋል። ሌሎች 11 አገራት ድምፃቸውን ሳይሰጡ ቀርተዋል። 10 ሃገራት ብቻ የሩሲያን ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት መታገድ ደግፈዋል። እነዚህም ቻድ፣ ኮሞሮስ፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ሊቢያ፣ ማላዊ እና ሲሼልስ ነበሩ። አፍሪካ ሩሲያን ለመደገፍ ዝንባሌ የምታሳየው ለምንድነው? በተባበሩት ጠቅላላ ጉባኤው ሩስያን በመቃወም ሁለት ጊዜ ድምጽ ከመስጠት የተቆጠበችው የአህጉሪቱ ትልቁ ኢኮኖሚ ደቡብ አፍሪካ በኩል የተሰጡት አስተያየቶች በተወሰነ መልኩ ያለውን ሁኔታ ያስረዳሉ። "ግጭቱ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት የአለም አቀፉን ሰላምና ደህንነትን የማስጠበቅ ተልዕኮውን መወጣት አለመቻሉን አጋልጧል" ሲል የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳን ጠቅሶ ኤኤፍፒ ዘግቧል። ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ሩሲያ፣ እንግሊዝ እና አሜሪካን ያካተተውና አምስት ቋሚ አባላት ያሉት የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት አባልነት "ጊዜ ያለፈበት እና የማይወክል ነው" ብለዋል። የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶርም የአገራቸውን ገለልተኝነት አቋም አስመልክቶ በመደገፍ የተከራከሩ ሲሆን ግጭቱ "የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ኢ-ፍትሃዊነት" አሳይቷል ሲሉም ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ በአፍሪካ ህብረት ንግግር ለማድረግ በድጋሚ ጠየቁ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በአፍሪካ ህብረት መሪዎችን ለማነጋገር በድጋሚ ጥያቄ እንዳቀረቡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ አስታውቀዋል። ሊቀ መንበሩ በትዊተር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ጥያቄው የመጣው ከዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ነው። በዚህ ውይይት ላይ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ "ከአፍሪካ ኅብረት ጋር የጠበቀ ግንኙነት የመፍጠር ፍላጎት" እንዳላቸውም መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸው ተገልጿል። ፋኪ የፕሬዚዳንቱ ጥያቄ ተቀባይነት ይኖረው እንደሆነ ያልገለጹ ሲሆን ነገር ግን "ከሩሲያ ጋር ላለው ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ አጥብቀው መናገራቸውን" በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ለሴኔጋሉ አቻቸውና ለወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ማኪ ሳል የአፍሪካ መሪዎችን ለማነጋገር ጥያቄ አቅርበው ነበር። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሩሲያ ከተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት እንድትታገድ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ድምጽ ያልሰጡ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ የአፍሪካ ሀገራት የበላይነቱን መያዛቸው ይታወሳል። ውሳኔው በ93 ድጋፍ፣ በ24 ተቃውሞ እና በ58 ድምጸ ተአቅቦ ጸድቋል። በአህጉሪቱ ከሚገኙት 54 ሀገራት አንጎላ፣ ግብፅ፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል እና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ 24ቱ ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል። ከሩሲያ ጋር በታሪክ ጥሩ ግንኙነት የነበራቸው አልጄሪያ እና ኢትዮጵያን ጨምሮ ዘጠኙ እርምጃውን ተቃውመዋል። ሌሎች 11 አገራት ድምፃቸውን ሳይሰጡ ቀርተዋል። 10 ሃገራት ብቻ የሩሲያን ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት መታገድ ደግፈዋል። እነዚህም ቻድ፣ ኮሞሮስ፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ሊቢያ፣ ማላዊ እና ሲሼልስ ነበሩ። አፍሪካ ሩሲያን ለመደገፍ ዝንባሌ የምታሳየው ለምንድነው? በተባበሩት ጠቅላላ ጉባኤው ሩስያን በመቃወም ሁለት ጊዜ ድምጽ ከመስጠት የተቆጠበችው የአህጉሪቱ ትልቁ ኢኮኖሚ ደቡብ አፍሪካ በኩል የተሰጡት አስተያየቶች በተወሰነ መልኩ ያለውን ሁኔታ ያስረዳሉ። "ግጭቱ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት የአለም አቀፉን ሰላምና ደህንነትን የማስጠበቅ ተልዕኮውን መወጣት አለመቻሉን አጋልጧል" ሲል የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳን ጠቅሶ ኤኤፍፒ ዘግቧል። ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ሩሲያ፣ እንግሊዝ እና አሜሪካን ያካተተውና አምስት ቋሚ አባላት ያሉት የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት አባልነት "ጊዜ ያለፈበት እና የማይወክል ነው" ብለዋል። የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶርም የአገራቸውን ገለልተኝነት አቋም አስመልክቶ በመደገፍ የተከራከሩ ሲሆን ግጭቱ "የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ኢ-ፍትሃዊነት" አሳይቷል ሲሉም ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-61272797
2health
ኮሮናቫይረስ፡ አሜሪካ የተከተቡ ዜጎቿ ጭምብል ሳያደርጉ መሰባሰብ ይችላሉ አለች
የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ) የኮሮናቫይረስ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ወደቀደመ ህይወታቸው መመለስ ይችላሉ የሚል መመሪያ አውጥቷል። በዚህም መሰረት ክትባቱን የተከተቡ ሰዎች ጭምብል (ማስክ) ሳያደርጉ በቤት ውስጥ መሰብሰብ ይችላሉ ተብሏል። ሲዲሲ እንዳስታወቀው የመጨረሻውን ክትባት ከተከተቡ ከሁለት ሳምንት በኋላ ከኮሮናቫይረስ ስጋት ነፃ ናቸው ብሏል። እስካሁን ድረስ አሜሪካ ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿን ከትባለች። የአገሪቱ የጤና ባለስልጣናት አዲሱን የደህንነት መመሪያ ይፋ ያደረጉት በትናንንትናው እለት ዋይት ሃውስ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ግብረ- ኃይል መግለጫ ላይ ነው። መመሪያው የኮሮናቫይረስ ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ማድረግ ይችላሉ ብሎ ካስቀመጣቸው መካከል፦ "ከኮቪድ-19 በኋላ ሊኖር የሚችለውን አለም ማየት ጀምረናል። የበለጠ ዜጎቻችን በተከተቡ ቁጥር ማከናወን የምንችላቸውን ተግባራትም ይጨምራሉ" በማለት የዋይት ሃውስ ከፍተኛ አማካሪ አንዲ ስላቪት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ክትባቱን የተከተቡ ሰዎች ህዝባዊ በሆነ ቦታ ላይ ጭምብል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤ እንዲሁም አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማስወገድና የተጣሉ የጉዞ ገደቦችን መከተል ይኖርባቸዋል ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ መመሪያው ያልተከተቡና ለኮሮናቫይረስ በበለጠ ተጋላጭ ከሆኑ ማህበረሰቦችም በተለይ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አስቀምጧል። አሜሪካ በቅርቡ የምትከትባቸውን ዜጎቿን ቁጥር በከፍተኛ እየጨመረ መሆኑን ያስታወቀች ሲሆን እስካሁን ድረስ 90 ሚሊዮን ሰዎች ተከትበዋል። በተለይም የጆንሰን ጆንሰን የአንድ ጊዜ ክትባት እውቅና ማግኘቱ አቅርቦቱን ጨምሮታል ተብሏል። ነገር ግን በኮሮናቫይረስ ክፉኛ በተመታችው አሜሪካ ኮቪድ-19 የማህበረሰቡ የጤና ጠንቅ መሆኑ ቀጥሏል። አገሪቱ እስካሁን ድረስ 29 ሚሊዮን ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ያስታወቀች ሲሆን 525 ሺህ ዜጎቿንም አጥታለች።
ኮሮናቫይረስ፡ አሜሪካ የተከተቡ ዜጎቿ ጭምብል ሳያደርጉ መሰባሰብ ይችላሉ አለች የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ) የኮሮናቫይረስ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ወደቀደመ ህይወታቸው መመለስ ይችላሉ የሚል መመሪያ አውጥቷል። በዚህም መሰረት ክትባቱን የተከተቡ ሰዎች ጭምብል (ማስክ) ሳያደርጉ በቤት ውስጥ መሰብሰብ ይችላሉ ተብሏል። ሲዲሲ እንዳስታወቀው የመጨረሻውን ክትባት ከተከተቡ ከሁለት ሳምንት በኋላ ከኮሮናቫይረስ ስጋት ነፃ ናቸው ብሏል። እስካሁን ድረስ አሜሪካ ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿን ከትባለች። የአገሪቱ የጤና ባለስልጣናት አዲሱን የደህንነት መመሪያ ይፋ ያደረጉት በትናንንትናው እለት ዋይት ሃውስ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ግብረ- ኃይል መግለጫ ላይ ነው። መመሪያው የኮሮናቫይረስ ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ማድረግ ይችላሉ ብሎ ካስቀመጣቸው መካከል፦ "ከኮቪድ-19 በኋላ ሊኖር የሚችለውን አለም ማየት ጀምረናል። የበለጠ ዜጎቻችን በተከተቡ ቁጥር ማከናወን የምንችላቸውን ተግባራትም ይጨምራሉ" በማለት የዋይት ሃውስ ከፍተኛ አማካሪ አንዲ ስላቪት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ክትባቱን የተከተቡ ሰዎች ህዝባዊ በሆነ ቦታ ላይ ጭምብል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤ እንዲሁም አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማስወገድና የተጣሉ የጉዞ ገደቦችን መከተል ይኖርባቸዋል ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ መመሪያው ያልተከተቡና ለኮሮናቫይረስ በበለጠ ተጋላጭ ከሆኑ ማህበረሰቦችም በተለይ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አስቀምጧል። አሜሪካ በቅርቡ የምትከትባቸውን ዜጎቿን ቁጥር በከፍተኛ እየጨመረ መሆኑን ያስታወቀች ሲሆን እስካሁን ድረስ 90 ሚሊዮን ሰዎች ተከትበዋል። በተለይም የጆንሰን ጆንሰን የአንድ ጊዜ ክትባት እውቅና ማግኘቱ አቅርቦቱን ጨምሮታል ተብሏል። ነገር ግን በኮሮናቫይረስ ክፉኛ በተመታችው አሜሪካ ኮቪድ-19 የማህበረሰቡ የጤና ጠንቅ መሆኑ ቀጥሏል። አገሪቱ እስካሁን ድረስ 29 ሚሊዮን ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ያስታወቀች ሲሆን 525 ሺህ ዜጎቿንም አጥታለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-56330257
2health
በኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ቀናት ብቻ ከ22 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ታወቀ
በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፈው ሳምንት ውስጥ በተደረገ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ሰዎች ላይ ወረርሽኙ መገኘቱን የተደረጉ የምርመራ ውጤቶች አመለከቱ። ካለፈው ሰኞ አስከ ትናንት እሁት ድረስ ባለፉት ሰባት ቀናት በ77,083 ናሙናዎች ላይ በተደረጉ ምርመራዎች በ22,321ዱ ላይ ቫይሱ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር በየዕለቱ የሚያወጣቸው የወረርሽኙ ሪፖርቶች ያመለክታሉ። ይህም አስካሁን በአንድ ሳምንት ከተመዘገቡ ከፍተኛ ቁጥር ካላቸው በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ውስጥ የሚመደብ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት ሚኒስቴሩ እንዳለው እየተመዘገበ ያለው የበሽታው የመስፋፋት መጠን አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ቀደም ሲል በነበሩ ሳምንታት ምርመራ ከሚያደርጉ ሰዎች መካከል በየዕለቱ ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ከአምስት መቶ በላይ፣ ነገር ግን አንድ ሺህ እንኳን የማይደርስ ነበር። ባለፈው ሳምንት ግን ሰኞ ዕለት ከተመዘገበው 681 ውጪ በሌሎቹ ቀናት አሃዙ ከፍተኛ ነበር። በዚህም መሠረት በየዕለቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር በ2300 እና 5000 መካከል ይገኛል። ዝቅተኛው ማክሰኞ ዕለት የተመዘገበው 2,323 ሲሆን፣ ከፍተኛ ደግሞ ቅዳሜ ዕለት 5,013 የተመዘገበው ሲሆን፣ በሳምንቱ ውስጥ በአጠቃላይ በ22,321 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። የወረርሽኙ ቫይረስ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር ከሚመረመሩት ሰዎች ብዛት አንጻር ከፍና ዝቅ የሚል ቢሆንም ያለፈው ሳምንት አሃዝ ግን ከፍተኛ እንደሆነ ቀደም ካሉት ሳምንታት ጋር የተደረገው ንጽጽር ያመለክታል። ቀደም ሲል በነበረው ሳምንት ውስጥ ከተመረመሩ 53 ሺህ ሰዎች መካከል 8500 ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት የተመዘገበው ቁጥር ግን በእጅጉ ከፍተኛ ነው። በቀደሙት ሳምንታት ምርመራ ካደረጉ ሰዎች መካከል ሦስት በመቶ ያህሉ ላይ ብቻ የኮሮናቫይረስ ይገኝባቸው የነበረ ሲሆን፤ ከአንድ ሳምንት በፊት ግን ቁጥሩ ወደ 28 በመቶ ከፍ ብሎ ነበር። ባለፈው ሳምንት ደግሞ በእጀጉ አሻቅቧል። የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ባለፈው ሳምንት ለቢቢሲ እንደተናገሩት "እስካሁን የነበረው አካሄድ ጥሩ ነበር። ነገር ግን ከታኅሣሥ 07/2014 ዓ. ም. ወዲህ ባሉት ቀናት በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው" ብለዋል። ጨምረውም በአሁኑ ወቅት የኮቪድ-19 ምርመራ ከሚያደርጉ ሰዎች መካከል "አንድ ሦስተኛው ቫይረሱ እየተገኘባቸው ስለሆነ የጥንቃቄ እርምጃ መወሰድ አለበት። ለዚህም ማስክ በአግባቡ ማድረግና የመከላከያ ክትባት መውሰድ ይገባል" ሲሉ መክረዋል። በበርካታ የዓለም አገራት መገኘቱ የተረጋገጠውና ከሰው ወደ ሰው የመዛመት አቅሙ ከፍተኛ የሆነው አዲሱ የኦሚክሮን ቫይረስ ዝርያ በኢትዮጵያ ውስጥ መኖር አለመኖሩ ገና ያልተረጋገጠ ሲሆን ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ሚኒስትሩ ለቢቢሲ ገልጸዋል። "በሌሎች አገሮች የሚታየው የኦሚክሮን ዝርያ በኢትዮጵያም ምልክቶቹ ታይተዋል። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአስጊ ሁኔታ ጨምሯል። አሁን ናሙና እየመረመርን ነው። እስክናረጋግጥ ድረስ ኦሚክሮን መግባቱን ለመናገር አስቸጋሪ ነው" ብለዋል ዶ/ር ደረጄ። የኮሮናቫይረስ በኢትዮጵያ መኖሩ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ አስከ ትናንት ድረስ 4 ሚሊዮን 52ሺህ 568 ሰዎች ተመርምረው 400 ሺህ በሚጠጉት ላይ ቫይረሱ የተገኘ ሲሆን፣ 6 ሺህ 898 ደግሞ ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን አጥተዋል። በሽታውን ለመከላከል የሚረዳው ክትባት በአገሪቱ መሰጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የተከተቡ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ካላት አጠቃላይ ሕዝብ አንጻር ይህ አሃዝ ዝቅተኛ እንደሆነ ይነገራል። የበሽታውን መስፋፋት ለመቆጣጠር የተለመዱትን የመከላከያ ዘዴዎች በአግባቡ ዘወትር ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የሚመክሩት የጤና ሚኒትር ዲኤታው ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ክትባት መውሰድም አስፈላጊ መሆኑን መክረዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የጤና ሚኒስቴር የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የጤና ባለሙያዎች በአስገዳጅ ሁኔታ ክትባት እንዲወስዱ ማድረግ እና ያልተከተቡ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ የመንግሥት የነጻ ሕክምና ተጠቃሚ እንይሆኑ እንደሚደረግ ጨምረው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ቀናት ብቻ ከ22 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ታወቀ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፈው ሳምንት ውስጥ በተደረገ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ሰዎች ላይ ወረርሽኙ መገኘቱን የተደረጉ የምርመራ ውጤቶች አመለከቱ። ካለፈው ሰኞ አስከ ትናንት እሁት ድረስ ባለፉት ሰባት ቀናት በ77,083 ናሙናዎች ላይ በተደረጉ ምርመራዎች በ22,321ዱ ላይ ቫይሱ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር በየዕለቱ የሚያወጣቸው የወረርሽኙ ሪፖርቶች ያመለክታሉ። ይህም አስካሁን በአንድ ሳምንት ከተመዘገቡ ከፍተኛ ቁጥር ካላቸው በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ውስጥ የሚመደብ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት ሚኒስቴሩ እንዳለው እየተመዘገበ ያለው የበሽታው የመስፋፋት መጠን አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ቀደም ሲል በነበሩ ሳምንታት ምርመራ ከሚያደርጉ ሰዎች መካከል በየዕለቱ ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ከአምስት መቶ በላይ፣ ነገር ግን አንድ ሺህ እንኳን የማይደርስ ነበር። ባለፈው ሳምንት ግን ሰኞ ዕለት ከተመዘገበው 681 ውጪ በሌሎቹ ቀናት አሃዙ ከፍተኛ ነበር። በዚህም መሠረት በየዕለቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር በ2300 እና 5000 መካከል ይገኛል። ዝቅተኛው ማክሰኞ ዕለት የተመዘገበው 2,323 ሲሆን፣ ከፍተኛ ደግሞ ቅዳሜ ዕለት 5,013 የተመዘገበው ሲሆን፣ በሳምንቱ ውስጥ በአጠቃላይ በ22,321 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። የወረርሽኙ ቫይረስ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር ከሚመረመሩት ሰዎች ብዛት አንጻር ከፍና ዝቅ የሚል ቢሆንም ያለፈው ሳምንት አሃዝ ግን ከፍተኛ እንደሆነ ቀደም ካሉት ሳምንታት ጋር የተደረገው ንጽጽር ያመለክታል። ቀደም ሲል በነበረው ሳምንት ውስጥ ከተመረመሩ 53 ሺህ ሰዎች መካከል 8500 ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት የተመዘገበው ቁጥር ግን በእጅጉ ከፍተኛ ነው። በቀደሙት ሳምንታት ምርመራ ካደረጉ ሰዎች መካከል ሦስት በመቶ ያህሉ ላይ ብቻ የኮሮናቫይረስ ይገኝባቸው የነበረ ሲሆን፤ ከአንድ ሳምንት በፊት ግን ቁጥሩ ወደ 28 በመቶ ከፍ ብሎ ነበር። ባለፈው ሳምንት ደግሞ በእጀጉ አሻቅቧል። የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ባለፈው ሳምንት ለቢቢሲ እንደተናገሩት "እስካሁን የነበረው አካሄድ ጥሩ ነበር። ነገር ግን ከታኅሣሥ 07/2014 ዓ. ም. ወዲህ ባሉት ቀናት በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው" ብለዋል። ጨምረውም በአሁኑ ወቅት የኮቪድ-19 ምርመራ ከሚያደርጉ ሰዎች መካከል "አንድ ሦስተኛው ቫይረሱ እየተገኘባቸው ስለሆነ የጥንቃቄ እርምጃ መወሰድ አለበት። ለዚህም ማስክ በአግባቡ ማድረግና የመከላከያ ክትባት መውሰድ ይገባል" ሲሉ መክረዋል። በበርካታ የዓለም አገራት መገኘቱ የተረጋገጠውና ከሰው ወደ ሰው የመዛመት አቅሙ ከፍተኛ የሆነው አዲሱ የኦሚክሮን ቫይረስ ዝርያ በኢትዮጵያ ውስጥ መኖር አለመኖሩ ገና ያልተረጋገጠ ሲሆን ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ሚኒስትሩ ለቢቢሲ ገልጸዋል። "በሌሎች አገሮች የሚታየው የኦሚክሮን ዝርያ በኢትዮጵያም ምልክቶቹ ታይተዋል። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአስጊ ሁኔታ ጨምሯል። አሁን ናሙና እየመረመርን ነው። እስክናረጋግጥ ድረስ ኦሚክሮን መግባቱን ለመናገር አስቸጋሪ ነው" ብለዋል ዶ/ር ደረጄ። የኮሮናቫይረስ በኢትዮጵያ መኖሩ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ አስከ ትናንት ድረስ 4 ሚሊዮን 52ሺህ 568 ሰዎች ተመርምረው 400 ሺህ በሚጠጉት ላይ ቫይረሱ የተገኘ ሲሆን፣ 6 ሺህ 898 ደግሞ ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን አጥተዋል። በሽታውን ለመከላከል የሚረዳው ክትባት በአገሪቱ መሰጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የተከተቡ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ካላት አጠቃላይ ሕዝብ አንጻር ይህ አሃዝ ዝቅተኛ እንደሆነ ይነገራል። የበሽታውን መስፋፋት ለመቆጣጠር የተለመዱትን የመከላከያ ዘዴዎች በአግባቡ ዘወትር ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የሚመክሩት የጤና ሚኒትር ዲኤታው ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ክትባት መውሰድም አስፈላጊ መሆኑን መክረዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የጤና ሚኒስቴር የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የጤና ባለሙያዎች በአስገዳጅ ሁኔታ ክትባት እንዲወስዱ ማድረግ እና ያልተከተቡ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ የመንግሥት የነጻ ሕክምና ተጠቃሚ እንይሆኑ እንደሚደረግ ጨምረው ገልጸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59796707
3politics
"ፖለቲከኞች የሶማሌን ሕዝብ እንደ ኢትዮጵያዊ አያስቡትም" የኦብነግ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አህመድ መሐመድ
ከሦስት ዓመታት በፊት ለውጡን ተከትሎ ለሰላማዊ ትግል ወደ አገር ውስጥ ከገቡ ፓርቲዎች መካከል አንዱ ነው። ቢቢሲ ስለ ምርጫና ስለ ፓርቲው እንቅስቃሴ ከኦብነግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የፌደራል መንግሥት ግንኙነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ መሐመድ ጋር ቆይታ አድርጓል። ስለኦብነግ እምብዛምም ከማይታወቁ ነገሮች እንጀምር። አፈጣጠሩ ከዚያድባሬ ወረራ ጋር የሚያያዝ ታሪክ አለው። በሽግግሩ ጊዜ ተሳትፋችኋል። ከምዕራብ ሶማሊያ ነጻነት ግንባር ወጣት ሊግ ነው ኦብነግ የተፈጠረው ይባላል። ክልሉን ለሁለት ዓመት ያህል አስተዳድራኋል። ልክ ነኝ? የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) የተመሰረተው (እአአ) ነሐሴ 15 ቀን 1984 ነው። በወቅቱ የነበረው የምዕራብ ሶማሌ ነጻ አውጭ ግንባር (WSLF) በኢትዮጵያ ውስጥ በነበረችው ሶማሌዎች በሚኖሩበት አገር ከተዳከመ በኋላ የግንባሩ ወጣቶች ዘርፍ የነበሩ አባሎች ተሰባስበው የመሠረቱት ግንባር ነው። የምዕራብ ሶማሌ ነጻ አውጭ ግንባር በኢትዮጵያ ሶማሌዎች የተቋቋመው ነው። ሆኖም በሶማሊያ መንግሥት ይደገፍ የነበረ ድርጅት ነበር። ወጣቶቹ ተሰባስበው፣ ተጠያይቀው ትግላችን እየተዳከመ ስለሆነ ምን እናድርግ በማለት የመሠረቱት ድርጅት ነው- ኦብነግ። እነዚህ ወጣቶች ትግላቸው ከሶማሊያ መንግሥት ነጻ አለመሆኑንና ጣልቃ ገብነት እንዳለው ተረድተው የመሠረቱት ነው። ኦብነግ በሶማሊያም በኢትዮጵያም ክልክል ስለነበርና ተቀባይነት ስላልነበራቸው በድብቅ ለዓመታት ሲሠሩ ቆይተዋል። ድርጅቱ ሲመሠረት አቶ አብዱረህማን መህዲ ነበሩ ሊቀመንበር። ከዚያም መሐመድ አብዲ መገኒ ለሁለት ወር ያህል ሊቀመንበር ሆነዋል። ከዚያም አቶ ሼህ ኢብራሂም አብደላህ ቋሚ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠው ድርጅቱን ለረዥም ጊዜ መርተዋል። እርሳቸው አሁን በሕይወት የሉም። የኦብነግ ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሶማሌዎች ኦጋዴን ተብሎ የሚጠራውን አገር ነጻ ማውጣት ነበር። የደርግ መንግሥት ከወደቀ በኋላ የኦብነግ መሪዎች እና ኃላፊዎች አገር ውስጥ ገብተው በመጎብ ዞን፣ ገርቦ በምትባል ወረዳ ሕዝብ ሰብስበው፤ ብሔራዊ ውይይት አድርገው ሸህ ኢብራሂም አብደላ እንደገና ተመርጠው በሽግግር መንግሥቱ ተሳትፏል። በመጀመሪያው ምርጫም ተሳትፎ በ84 በመቶ ድምፅ አብላጫ ድምጽ አግኝተው በክልሉ መንግሥት መሥርተዋል። ኢህአዴግ/ሕወሓት ምን ዓይነት የሕዝብ ድጋፍ፣ ዓለማና አቋም እንዳለን ካየ በኋላ ግን ወረረን። በዚህ ምክንያት ለትጥቅ ትግል ጫካ ተገባ፡፡ ፍላጎታችን በዲሞክራሲ መሳተፍ ነበር፤ ተገደን፣ ተገፍተን ጫካ ገባን። ለምን ያህል ጊዜ ነው ክልሉን? ለተወሰነ ጊዜ ነበር። አንድ ዓመት ከአሥር ወር ገደማ አስተዳድረናል። አሁን ያለው የክልሉ ሰንደቅ ዓላማ እንዲሁም እስካሁን ያለው በሶማሊኛ የተጻፈ መርሐ ሥርዓተ ትምህርት [ካሪኩለም] በኦብነግ በተመራው ክልላዊ መንግሥት ነበር የተጀመረው። መሠረታዊ የሆኑ ሥራዎችን ከጀመርን በኋላ የሕዝብ ድጋፋችን በጣም ከፍተኛ ስለነበር ጦርነት ተከፈተብን። ኃላፊዎችን መግደል ጀመሩ በዚህ ምክንያት ወደ ጫካ ገባን። ላለፉት 36 ዓመታት የቆየ አንጋፋ ድርጅት ነው። በዋናነት ለራስ ገዝ [self determination] ሲዋጋ የኖረ የፖለቲካ ድርጅት ነው። ለውጡን ተከትሎ በተደረሰ ስምምነት ወደ አገር ቤት መጥታችኋል። ነገር ግን አሁንም ስማችሁ የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ነው። እንዴት ይህን ስም ይዛችሁ ትቀጥላላችሁ? በአሁኒቷ ኢትዮጵያ ስሜት ይሰጣል? ጥሩ ጥያቄ ነው። በለውጥ ስማችን አይለወጥም። በሕዝብ ፍላጎት ነው ይህ ስም የተሰየመው። አቋም የያዘውም በሕዝብ ፍላጎት ነው። ዝም ብሎ በመሪዎች፣ በሁለት. . . በሦስት. . . በሃምሳ በመቶ ሰዎች የሚወሰን አይደለም። የመገንጠልም ሆነ ወደ ኢትዮጵያ ለመሳተፍ የሚወሰነው በሕዝብ ድምፅ ነው። ይህ ሕዝብ ምን ዓይነት ድርጅት እንደሚፈልግና ምን ዓይነት አቋም እንደሚይዝ ድርጅቱ የሚወሰነው በሕዝብ ድምፅ ነው። እኛ ከለውጡ ሰዎች ጋራ ስለተግባባን የድርጅቱን ስም፣ አቋምና ዓላማ መለወጥ አንችልም። እንደዚህ ዓይነት ባህርይም የለንም። በሕዝብ የተቋቋመ ድርጅት፣ ለሕዝብ የተቋቋመ ዓላማ ስለሆነ፤ አንቀይርም። መቀየርም አንችልም። ሕዝብ ተጠይቆ፣ ተሰብስቦ፣ ብሔራዊ ስብሰባ ተካሂዶ ነው ዓላማችን የሚቀየረው። የኢትዮጵያ መሪዎች ደግሞ ሕዝብን የመሳብ ጠባይ ካላሳዩ ዝም ብሎ በቀላል የሚቀየር ነገር አይደለም። ታዲያ ኮንፈረንሱን የማታደርጉት ለምንድን ነው? የመቀየር ጊዜው አሁን አይደለም ብላችሁ ስለምታምኑ ነው? ነጻ አውጭ ግንባር ብሎ ራሱን ከማዕከላዊ መንግሥት ለመገንጠል የሚያስብን ድርጅት ስም ይዞ ከሌሎች ፓርቲዎችስ ጋር እንዴት ነው የምትሠሩት? እኔ ግራ የገባኝ፣ እኔ ግራ የሚገባኝ ይሄ ጥያቄያችሁ ነው። ብዙ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ይሄን ጥያቄ ሲጠይቁኝ ቆይተዋል። የመገንጠል [self determination] ጉዳይ ብዙ ጋዜጠኞች …፤ ምንድነው ችግራችሁ? ከዚህ ነጥብ ማለፍ ያቃታችሁስ ለምንድነው? እንዴ! የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ራሱ እስከ መገንጠል ይፈቅዳል። ለምን ይሄ ነገር ለጋዜጠኞች ራስ ምታት (stress) ሆነባችሁ? ለምን የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ላይዋጥላችሁ ቻለ? ለምን ይሄ ነገር ጉሮሯችሁ ውስጥ ተቀርቅሮ እንደቀረ እኔ ግራ ገባኝ። ሕጋዊ የሆነ ነገር ነው፤ ሕዝብ ይሆንልኛል ባለው መሄድ አለበት። ኢትዮጵያ ከሆነችላቸው በኢትዮጵያዊነት መቆየት ይችላሉ፤ ካልሆነችላቸው ደግሞ የራሳቸውን መንግሥት መፍጠር ይችላሉ። ይህ በዓለም ሕግጋትም ያለ ነው። በኢትዮጵያም ሕገ መንግሥት ያለ ነው። ለምን ደግማችሁ ደጋግማችሁ የእኛን ድርጅት ይሄን ጥያቄ እንደምትጠይቁ ግራ ይሆንብኛል። ጋዜጠኞች ግን ከዚህ ጥያቄ ማለፍ ለምን አቃታችሁ? ከዓመታት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት ዋና ፀሐፊያችሁ አቶ አብዱራህማን መህዲ በአንድ ቃለ ምልልሳቸው ላይ "ሶማሌ በማዕከላዊ መንግሥቱ የተናቀና የተረሳ ክልል ነው። እኛ ኢትዮጵያዊነት አይሰማንም፤ በቅኝ ነው ማዕከላዊ መንግሥቱ የያዘን" ሲሉ ተደምጠዋል። ይህ ቀደም ሲል ያለ ስሜት ነው። ከለውጡ በኋላ ይህ ስሜታችሁ በምን ያህል መጠን ተፈውሷል? በእርግጥ ይህ የመሪዎች ስሜት ሳይሆን የሕዝብ ስሜት ነው። እውነቱን ንገረኝ ካልከኝ የእኛ ሕዝብ፣ የሶማሌው ሕዝብ፣ የኦጋዴኑ ሕዝብ የእኔ መንግሥት የሚል ስሜት አሁንም ያለው አይመስለኝም። ምክንያቱም መንግሥት የራስ የሚሆነው ስለ ራስህ ሲያስብ ነው። ከአጤ ቴዎድሮስ፣ ከአጤ ምንሊክ፣ ከአጤ ኃይለ ሥላሴ፣ ከኮሎኔል መንግሥቱ እና አቶ መለስ ዜናዊ እስከ ዛሬ ድረስ የሶማሌ ሕዝብ ምን ተደረገለት? ምንስ ይደረግ ነበር? የሶማሌ ሕዝብ በፌደራል መንግሥት ምን ያህል ተሳትፎ ተሰጣቸው? ወይም ምን ያህል ጥቅም አገኙ? እንዴትስ ነው የሚታዩት? ዛሬ እኮ የኢትዮጵያን ብር እና የኢትዮጵያን መንግሥት የማያውቁ ሰዎች በክልላችን ውስጥ አሉ። ይሄ ምን ይነግርሃል? ለምን? በምንድን ነው የሚገበያዩት ታዲያ? ለምን? መንግሥት ስላልደረሳቸው ነዋ። የሶማሌ ሕዝብ ወታደር ተልኮ፣ ወታደር ሲጨፈጭፋቸውና ሲገድላቸው ነው የሚያውቁት። ይህን ነገር መቀየር ያለብን እኛ ሳንሆን የኢትዮጵያ መንግሥትና መሪዎች ናቸው። እኔ ልንገርህ ለምሳሌ…በቅርቡ በፌደራል የተዘጋጀ ውይይት ላይ በቢሾፍቱ ተሳትፌ አንድ ሰው ምን ብሎ ጠራኝ መሰለህ። በውይይት ላይ ነው የምልህ…አንድ ሰው "ወንድሜ ሶማሌው እንደገለፀው" ይለኛል። ተመልከት እንግዲህ! ምንድነው ችግሩ ታዲያ፣ አልገባኝም? እኔ በማንነቴ እኮራለሁ ችግር የለብኝም። ግን ለምሳሌ ሌላው ተሳታፊ የኦሮሞው ወንድሜ፣ የሃዲያው፣ የጉራጌው እየተባለ በብሔሩ ተሰይሞ ስሙን ከብሔሩ ጋር አያይዞ አልተነሳም። ወንድሜ ኦሮሞው፣ ወንድሜ ሃዲያው አልተባለም። እኔ ለምን ልዩ ሆንኩ? ይህ ምን ያሳይኻል? ይህንን መቀየር ያለብን ደግሞ ፖለቲከኞች፣ ምሁራንና መሪዎች ናቸው። ይህ ልዩነት ከጥንት ጀምሮ እስከዛሬ ያለ ነው። እንደ ሁለተኛ ዜጋ ነው የሚያዩን። ፖለቲከኞች የሶማሌን ሕዝብ እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ አያስቡትም። ይህንን አለ የምትሉትን የተንሸዋረረ አመለካከት ለማቃናት እናንተስ እንደ አንድ ፓርቲ ምን ያህል ጥረት አድርጋችኋል ብዬ ለጥይቅዎ? ከጥንት እስከ ዛሬ ኢትዮጵያዊ መሆናችን አልቀረም። በድርጅት ብቻ ሳይሆን በሶማሌ ባለሥልጣናት እንደ ሶማሌ ብሔረሰብ ተወያይተው በመሆኑም ድርሻችን ምን ያህል መሆን እንዳለበት መወያየት አለብን። ትልቁ ሚና መጫወት የነበረባቸው በሥልጣን ላይ ያሉ የሶማሌ ባለሥልጣናት ነበሩ። ምን እንዳጡ፣ ምን እንደሚያንሳቸው መጠየቅ ነበረባቸው። እኛ እንደዚህ ብለን ስንጠይቃቸው እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ ነው የሚያዩን። በመሆኑም ለዚህ ከፍ ያለ ሚና መጫወት ያለባቸው በሶማሌ ክልል ያሉ ባለሥልጣናት ነበሩ። እኛ ተወያይተን ምን ማድረግ እንዳለብን ለመወሰን እንደ የቤት ሥራ እናስብበታለን። ድርጅታችንም ያስብበታል። በዚች አገር ኢትዮጵያ ውስጥ እስካለን ድረስ የድርሻችንን ማግኘት አለብን። የድርሻችንን መጫዎች እና የድርሻችንን መካፈል አለብን የሚል እምነት ነው ያለን። በአሁኗ ኢትዮጵያ ውስጥ አፋሩም፣ ሐረሪውም ፣ ሶማሌውም፣ ደቡቡም . . . እኔ ተገፍቻለሁ፤ እኔ እንደ ኢትዮጵያ አልቆጠርም እኔ ሁለተኛ ዜጋ ነኝ እያለ ነው። ይህ የስሜት መጎዳት ሁሉም ሕዝብ ላይ እንደሆነ ይታወቃል። ሁሉም አኩራፊ ከሆነ እንዴት ነው ኢትዮጵያን መጠበቅና ወደፊት ማራመድ የሚቻለው? እኔ ተጎድቻለሁ የሚለው ሕዝብስ ወደ መሀል መምጣትና የድርሻውን መወጣት የለበትም ወይ? ይህ ስሜት የማይሰማውስ ብሔር አለ ወይ ኦሮሞው፣ ወላይታው፣ አማራው፣ ሲዳማው . . . በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው ያነሳኸው። በዓለም ላይ እኔ ነኝ ጎጂው፣ እኔ ነኝ በዳዩ፣ እኔ ነኝ አጥፊው የሚል ሰው የለም። ጎጂውም ተጎጂውም እንደዛ ነው የሚቀጥሉት። ባለፉት ሥርዓቶች ምን ዓይነት ችግሮች ነበሩ ብለን እንደ አንድ አገር ዜጋ ተወያይተን፣ ስህተታችንን ተጠያይቀን፤ እርቅ ተቀብለን፤ ወደፊት ምን ይሻለናል? ማለት አለብን ብዬ አንስቻለሁ። ነገሩ የአዞ እንባ እንዳይሆን፤ ማን ነው ይህን የሚያመጣው? ሥርዓቶቹ ናቸው። በመለስ ዜናዊ አስተዳደር የህወሓት፣ የትግራይ ጊዜ ይባላል። በደርግም ጊዜ የአማራው ጊዜ ይባላል። እነርሱም ግን ተበድለናል እያሉ ነው። ስለዚህ ቆሻሻችንን ከመቆፈር አሁን ምን ማድረግ አለብን? የሚለው ላይ መምጣት ያስፈልጋል። መጀመሪያ ይቅርታ መጠያየቅ፣ ሕዝብን ማስተማር፣ መቻቻልና፥ አንድ ሰው ተበድያለሁ ካለ ይቅርታ ማለት ያስፈልጋል። አሁን ባለችው ኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትና ሥነ ሥርዓት ተከባብረን እየተጓዝን፤ ጥያቄዎች ካሉ በሕጋዊ መሠረት እንዲፈቱ፣ ማንኛውም የወደፊት ዕጣ በሕጋዊ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ነው የማስበው። እኛም እንደዛ ዓይነት አቋም ነው ያለን። ይቅርታ መጠያየቅ ላይ ብዙዎች ጥያቄ የላቸውም። ጥያቄው ይቅርታ የሚጠይቀው ማን ነው? የሚጠየቀውስ ማን ነው? አጥፊው ማነው? ተጎጂው ማነው? የሚለው ነው። የደርግ መንግሥት ብለዋል ደርግ የትኛውን ብሔር ነው የሚወክለው? ከዚያ በፊት ያሉ አስተዳደርና መንግሥታትን ስንቆጥር የትኛውን ብሔር ነው የምናነሳው? የመሪውን ብሔር ነው የምናነሳው? የወከሉት ሕዝብስ ራሱ ሲበደል አልነበር ወይ? እውነት ብለሃል። በተወሰነ መልኩ ካነሳኸው ነጥብ ጋር እስማማለሁ። ምክንያቱም በሥልጣን ላይ የነበረ ሰው ወይም ሰዎች ናቸው ሥርዓቱን ያጠፉት ይባላል። እውነት ነው የአማራ ሕዝብ ተሰብስቦ የሶማሌን ሕዝብ እንበድል አላለም። የትግራይም ሕዝብ እንደዚያው ተነስቶ የሶማሌ ሕዝብ ወይም ሌላውን እንበድል ብሎ አልተነሳም። ግን በመለስ ዜናዊ ጊዜ አራት ድርጅቶች ነበሩ። በኢህአዴግ ሥር የተሰበሰቡ ድርጅቶች። ነገረ ግን ብዙ ጊዜ ሰው ሲናገር በህወሓት የተመራው መንግሥት ነው የሚለው? በህወሓት እነማን ነበሩ ሲባል ትግራዮች ነበሩ እንላለን። በደርግ ጊዜም እነማን ነበሩ ሲባል የአማራው ነበሩ ይባላል። ያው በተወሰነ ደረጃ ካንተ ጋር እስማማለሁ ምክንያቱም ሥርዓቱ ነበር አጥፊው። በተወሰነ ደረጃ ደግሞ ከሥርዓቱ በስተጀርባ የትኛው ብሔር ነበረ? አፍሪካዊያን እኮ ብሔርተኞች ነን ሁላችንም። ይህንን መካድ አንችልም። ኬንያ ብትሄድ ተመሳሳይ ነገር ነው ያለው። ኬንያ ብታነሳ የኪኩዩ መንግሥት ነው የምትለው። እዚህም እንደዛ ዓይነት ነገር አለ። እና መካድ የለብንም፡፡ ይህን መቀበል አለብን ብዬ አስባለሁ። ከአራት ዓመታት በፊት ሊቀመንበራች አቶ አብዱራህማን መኽዲ ከአልጀዚራ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ "በመቶ ዓመት ውስጥ ኦጋዴን ውስጥ አንድ ሃይስኩልና አንድ ሆስፒታል ነው ያለን። ሴቶቻችን ሊወልዱ ሲሉ ወይም ሲታመሙ ሞቃዲሹ ነበር የሚሄዱት" ብለዋል። በአንጻሩ ሶማሌ በተለይም ሰፊ ድጋፍ ባላችሁ ኦጋዴን በጋዝ ሃብት ትልቅ ተስፋ የተጣለበትና ትልቅ ሃብት ያለው አካባቢ ነው። አሁን ሕዝባችሁ በልማት እየተጠቀመ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? በዚያ አካባቢ ባለው እንቅስቃሴ ተስፋ ይታያችኋል? ተስፋ አለን። እንደ እንድ ሙስሊም በቁርዓን ላይ (ላ ታቅናጡ ቢራሕማቲላህ) "በፈጣሪ ፀጋና ሲሳይ ተስፋ አትቁረጡ" የሚል አንቀጽ አለ። ሁልጊዜም ተስፋ አለን። ምንም እንኳ ብንተችም አሁን ያለው የሶማሌ አስተዳደር በመጠኑ እያደረገ ነው። ጥሩ ነው። ትምህርት ቤቶች በቁጥር አነስተኛ ቢሆኑም በመጠኑ እየተሠሩ ነው፤ ከዚህ በላይ መሆን ነበረበት ማለታችን ባይቀርም ማለቴ ነው። ይህ ማለት ግን እንዳትሳሳት። አሁንም በእሳት ብርሃን (በኩራዝ ብርሃን) የሚወልዱ የሶማሌ እናቶች አሉ። ከ60 በመቶ በላይ የሶማሌ ሴቶች አሁንም እንደዚያው እየወለዱ ነው ያሉት። ጥራታቸው ዝቅተኛ ቢሆንም ትምህርት ቤቶች አሉ። ጥራታቸው በጣም ዝቅተኛ ቢሆኑም ሆስፒታሎችም ክሊኒኮችም በመጠኑ አሉ። እየተሠሩም ነው። ወደፊትም እንዲሠራ፣ እኛም ካሸነፍን ቅድሚያ ሰጥተን የምንሠራው ይህንን ነው። ሌላም ቢያሸንፍ መሠረታዊ የሆኑት እነዚህ ላይ ትኩረት መስጠት እንዳለበት እናምናለን። የጋዝ ሃብቱ ላይ የምታነሱት የተለየ ጥያቄ አለ? አንድ የሶማሌ ተረት አለ። "Dhariba ninkii u dhow baa dhuunigiisa leh" ጭብጡ ምንድነው? "ምግብ ሲበስል ለቀረበው ሰው ነው ቅድሚያ መሰጠት ያለበት" የሚል አባባል ነው። የሶማሌው ሕዝብ ከጋዝና ነዳጅ ንብረቱ እንደዚህ ሩቅ መሆን የለበትም። የተሰጠው ድርሻም በቂ አይደለም ብለን እናምናለን። ከዚያ በላይ ነው ማግኘት ያለባቸው ብለን እናምናለን። በፌደራል መንግሥት ያላቸው ድርሻም በቂ አይደለም እንላለን። የፌደራል ሃብትም የሚደርሳቸው ከዚያ በላይ ማግኘት አለባቸው ብለን እናምናለን። አቶ አብዱራሕማን እንዳሉት ሕዝባችን ድሮም በጫካ ያለ ሐኪምና መድኃኒት ሲሞት እንደነበረው አሁንም እየሞተ ነው ያለው። ይህ ግን በእኛም ይሁን በሌላ እንደዚህ ሆኖ መቀጠል የለበትም ብለን እናምናለን። እናንተ ጫካ በነበራችሁበት ዘመን የሶማሌ ሕዝብ በቀድሞ የሶማሌ አስተዳዳሪ አቶ አብዲ ኢሌ ቁም ስቅሉን ሲያይ እንደነበረው እናንተም ፍዳውን ስታበሉት ነበር። አሁን አቶ ሙስጠፌ ከመጡ ወዲህ ግን ክልሉ ከሌሎች ክልሎች አንጻር ብዙም ኮሽታ የሌለበት፣ ሰላም ያለበት እንደሆነ ነው የምናየው፤ ፕሬዝዳንት ሙስጠፌም በዚህ የሚሞካሹ ናቸው። እናንተ እንዴት ነው የምትገመግሙት? አቶ ሙስጠፌ ከመጣ ሰላም መጣ ከማለት እናንተ ከመንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት ከፈረማችሁ በኋላ ሰላም መጣ ብትሉ ይመረጣል ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም አቶ ሙስጠፌ እኛ አዲስ አበባ እያለን፤ እኛ የሰላም አቅጣጫ ከመንግሥት ጋር ከተስማማን በኋላ ነው የተሾሙት። ሰላም በአቶ ሙስጠፌ አሊያም በብልጽግና ፓርቲ ሳይሆን፤ በእኛና በኢህአዴግ ነው የተፈፀመው። ሰላም በኦብነግ ነው የመጣው፤ ሰላም በእኛ ውሳኔ ነው የመጣው ብለን እናምናለን። ምክንያቱም ከመንግሥት ጋር ስንፋለም ነበር። እኛ እስከተፋለምን ድረስ 'እነሱን ሕዝብ ይደግፋቸዋል' በሚል ሕዝብ ሲጨፈጭፉ ከእኛም ጋር ሲዋጉ ነበር። አቶ ሙስጠፌ በመሀል ገብቶ ነው እንጂ በእርሱ ሰላም አልመጣም። በእኛ ነው ሰላም የመጣው። አሁንም በእኛ ካልሆነ በሰላም አይቆይም ነበር። ምክንያቱም ድርጊታቸው፣ ጸባያቸው፣ አነጋገራቸው እና ሁሉ ነገራቸው ወደ ሰላማዊ የሚወስደን አይደለም ብዬ አምናለሁ። ሰላም በእኛ ነው የመጣው፤ በእኛ ነው የተመሠረተው። አሁንም በእኛ ነው ያለው። ነገር ግን ሰላም ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲነጻጸር ጥሩ ነው። የሕዝባችን ውሳኔ ነው። ሌሎች ኢትዮጵያውያን ሁለተኛ ዜጋ ሆነው በያሉበት ቦታ እየተገደሉ ነው። ሶማሌው የሰላምንም የጦርነትንም ዋጋ ስለሚያውቅ፤ እኛ ስለወሰንን ነው ዛሬ ሰላም የሆነው። ዛሬ የሰላም ቀን ነው። የፈለግነውን በሰላም እንፈልግ ከሌሎች ጋር በሰላም እንወያይ፣ በሰላም እንሂድ ብለን የኦብነግ ውሳኔ ስለሆነ ነው በዚያ እየሄድን ያለው። አሁንም እንቀጥላለን። ሰላም ለሕዝባችን ለአፍሪካ ቀንድም እንዲወርድ አላህን እንጠይቃለን። እናንተ ጫካ በነበራችሁ ጊዜ በትጥቅ ትግሉ ጊዜ ፤ አንዳንድ የፈጸማችኋቸው ጥቃቶች አሉ። ግንቦት 2007 እአአ 65 ኢትዮጵያያዊ የጉልበት ሠራተኞች እና ዘጠኝ ቻይናዊያን በማዕድን ቁፋሮ ላይ ሳሉ አቦሌ ላይ ጥቃት አድርሳችሁ ገድላችኋቸዋል። ንጹሃን ሞተዋል። ጅግጅጋም ላይ እንደዚሁ የሰዎች ሕይወት አልፏል። ይህም በእናንተ የሆነ ነው። አሁን ለሰላም ትግል ከመጣችሁ በኋላ ይቅርታ መጠየቅ ያለባችሁ አይመስላችሁም? ሁለት ዝሆኖች ሲጣሉ ብዙ ሳር ይወድማል ይባላል። የትኛውም አገር ጦርነት ሲከሰት የሰላማዊ ሰው ሕይወት ያልፋል። ያለ ነገር ነው። እኛ ዓላማችን ሰላማዊ ሰዎችን እናጥቃ ብለን አልነበረም። ቻይናውያን በማን ጥቃት ነው የሞቱት? ማንን ጠይቀው ነው የኦጋዴን ግዛት የገቡት? ከመግባታቸው በፊትና ከገቡም በኋላ አስጠንቅቀናቸው ሰላም አለመሆኑን እየነገርናቸው 'እምቢ' ብለው ስለገቡ እኛ የመንግሥት ሠራዊትን ዒላማ ስናደርግ ቻይናውያኑ ስለሞቱ መንግሥት ነው ይቅርታ መጠየቅ ያለበት። አምጪው ነው ይቅርታ መጠየቅ ያለበት። ግን ገዳዮቹ እናንተ ናችሁ እኮ? የተገደሉት በእናንንተ አይደለም እንዴ? በሁለቱም በኩል ጥይት ተተኩሷል። በማን ጥይት እንደሞቱ አይታወቅም። በማን ጥይት እንደተገደሉ ማን ይናገራል? በእኛ ብቻ የሚላከክ አይደለም። የእኛ እጅ የለበትም ብለን አንክድም። ነገር ግን ማን ነው ያመጣቸው? ሁለተኛ ደግሞ በማን ኃላፊነት ነው የመጡት? በእኛ ኃላፊነት አልመጡም። እኛ እንደውም ማስጠንቀቂያ ሰጥተን ነበር 'እምቢ' አሉ። በመሆኑም እኛ ይቅርታ የምንጠይቅበት ሰበብ የለም። በእኛ ፍቃድና ኃላፊነት አልመጡም፡፡ ጽፈንላቸው ይቅርባችሁ ብለን ነው እምቢ ያሉት። አገራችንና ሃብታችንን ሊወስዱ ነበር የገቡት። ስለቻይናውያኑን ይህን ካሉ ኢትዮጵያውያን የጉልበት ሠራተኞች ደም ፈሶ ይቅርታ ለመጠየቅ ለምን ጉልበት ያንሳችኋል? በዚህ ጦርነት ስንት ኢትዮጵያዊያን ሞተዋል? በዚህ ጦርነት ኃላፊው ማን ነበር? እኛ በሰላም ሕዝባችንን እየመራን በነበረበት ሰዓት አመጹን ቀስቅሶ ሕዝብ የጨረሰ ማን ነው? ጦርነቱን ያነሳሳ አካል ነው ለሁሉም ይቅርታ መጠየቅ ያለበት። ከእኛ ጦር ለሞቱት፣ ከመንግሥት ጦር ለሞቱት፣ ለንፁሃን ዜጎች ሁሉ ኃላፊነቱን መወሰድ ያለበት የኢትዮጵያ መንግሥት፤ የኢትዮጵያ መሪዎች ናቸው። ምክንያቱም በሰላም እንዲያወያየንና ችግራችን በሰላም እንዲፈታ ያልሄድንበት የለም። ኢትዮጵያውያንን ከዚህም ከዚያም የሚያዋጉት ኃላፊነት የሚወስዱት አነሱ ናቸው ብለን እናምናለን። ፓርቲያችሁ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ለብቻው ተገናኝቶ ያውቃል? ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኛችሁት መቼ ነበር? ምን ተወያያችሁ? ይህን ቀን ነው ብዬ ልነግርህ አልችልም። ግን ከስድስት ወር በፊት አንዴ በቤተ መንግሥት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ከአቶ አብዱራህማን ጋር ነበር የተወያዩት፤ እስከማውቀው ድረስ። ስለ አገራዊ ሁኔታ፣ ስለመጪው ምርጫ፣ ስለሠላም፣ ስለ ዲሞክራሲ እና ስለተለያዩ ጉዳዮች ነበር ያነሱት። በጥሩ ሁኔታ ነበር የተወያዩት። ይህን ያህል ነው የማውቀው። ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ግንቦት ወር ላይ ይካሄዳል። እናንተም ትሳተፋላችሁ። በቅርቡ ጥቃት እየፈፀመብን ነው።አባላት ታስረውብኛል። ዶሎ፣ ቸረረ፣ ሸበሌና ቆራሄ ዞኖች ሰብዓዊ ጥሰት አለ። እየተንገላቱብኝ ነው ብላችኋል። አሁንም ችግር አለ ማለት ነው? ይህ ችግርስ ከምርጫ እንድትወጡ ሊያደርጋችሁ ይችላል? በዚህ ላይ ትኩረት ማድረግ እፈልጋለሁ። ዛሬ ከሚደርሱን መረጃዎችና ከምናያቸው ነገሮች በምርጫው እንደምንሳተፍ ሙሉ ቃል መስጠት አልችልም። ጫፍ ላይ የደረስን ይመስለኛል። ነገሮች እየተደማመሩ ነው። ለምሳሌ አሁን ላይ የመራጮች ምዝገባ ጊዜ ነው። የመራጮች ምዝገባ ጊዜው ተራዝሟል። በቴክኒካል ችግር ሊሆን ይችላል። ሆነ ተብሎም ሊሆን ይችላል። ዛሬ ከሚደርሱን መረጃዎች ነገሮች እየተባባሱ ነው። ለምሳሌ ለመራጮች የሚሰጠው ካርድ ለሶማሌ ክልል ምን ያህል ካርድ እንደሚላክ የምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎቹ ማሳወቅ አለበት። ወደ ምርጫ ጣቢያዎቹ የሚላከውን ካርድ ተወዳዳሪዎች ማወቅ አለባቸው። በምርጫው ምዝገባ ጊዜም ፓርቲዎቹ ወይም ተወዳዳሪዎቹ ታዛቢ ወይም ወኪል መስጠት አለባቸው፤ ነገር ግን ዝም ብለው በተለያዩ ቦታዎች ሳጥኖችን አራገፉ። ሳጥኑ ደግሞ ክፍት ነው። እስካሁን ለእኛ የተሰጠን ካርድ ቁጥር የለም። እና የተያያዘ ነገር እየመጣ ነው። ብዙ ምልክቶች እየታዩ ነው። በሚቀጥሉት ቀናት ድርጅቱ ተሰብስቦ ይወያይበታል። ሠራተኞቹም መጀመሪያ ሲቀጠሩ ከዘመድ፣ ከመንግሥት ሠራተኛ ሲሆኑ መቶ በመቶ በሶማሌ ክልል ሠራተኞች የብልጽግና ተከፋይ ናቸው። 99 በመቶ የመንግሥት ተከፋይ ናቸው። በመሆኑም በቀላሉ ለመንግሥት ሊገዙ ይችላሉ። በመሆኑም ምንም በሌለን መረጃ መቀጠል የምንችል አይመስለኝም። ሆን ተብሎ የተደረገ ነገርም ይመስላል። በተጨማሪም ብልጽግና በመንግሥት ሃብትና ንብረት እየተጠቀመ ነው ያለው። ሥልጣኑንም እየተጠቀመ ነው። ተወዳዳሪ ልናስመዘግብ አልቻልንም። እዚህ አዲስ አበባ ነው እያስመዘገብናቸው ያለው። ይህንን ስናመለክት እናስተካክላለን ሲሉን ነበር። ምንም የተስተካከለ ነገር የለም። የእኛ ተወዳዳሪዎች ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው። በመንግሥት መኪና ዘመቻ እያደረጉ ነው። ለምን ስንላቸው ደግሞ ታርጋ መፍታት ጀምረዋል። ስለዚህ ሁኔታው በዚህ የሚቀጥል ከሆነ በምርጫው የምንሳተፍ አይመስለኝም። ምን ያህል ዕጩዎችን የት አስመዝግባችኋል? በሶማሌ ክልልም በሌላ የሶማሌ ማኅበረሰብ ባለባቸው አጎራባች ክልሎች እና አዲስ አበባ ለመወዳደር አስበን ነበር። ግን በተሳሳተ በዕጩዎቻችን የተሳሳተ አረዳድ እና ቴክኒካል ችግር ምክንያት አዲስ አበባ መመዝገብ አልቻሉም። ድሬዳዋ እንዳናስመዘግብ ደግሞ በብልፅግና ተከልክለናል። ተከልክለናል ሲሉ ምንድን ነው ማስረጃዎት? የእኛ ዕጩዎች እንዳይመዘገቡ ተከልክለዋል። በምርጫ ቢሮ ኃላፊዎች አትመዘገቡም ተብለዋል። በገርባ ኢሴ፣ በፊቲ፣ ሃደጋላ ያሉ ዕጩዎችም እንደዚሁ ተብለው አስፈርመዋቸው ከሦስት ቀን እስራት በኋላ ተባረዋል። በሞያሌ፣ በካሱርቱ፣ በዞላአጦ ምርጫ ኮሚሽን ተገናኝተን ለምን አታስመዘግቡም ሲሉ፤ ኦብነግን እንዳናስመዘገብ በመንግሥት ታዘናል የሚል ምላሽ የሰጡ ነበሩ። ብዙ የተከለከልንባቸው ቦታዎች አሉ። እስካሁን 237 የክልል እና 15 ድሬዳዋ ላይ ከዚህ ላይ አምስቱ ዛቻና ማስፈራሪያ ስለደረሰባቸው ወጥተዋል። ከምርጫ ቦርድ ጋር በክልል ሆነ በፌደራል ደረጃ ይህን ያህል ለማስተጋባት ምን ያህል ርቀት ሄዳችኋል? የምርጫ ቦርድ አቅማቸው እስከሚፈቅድ ችግሩን ለመፍታት ሞክረው ነበር። መፍታት ያልቻሉትን ደግሞ አዲስ አበባ መጥተን እንድናስመዘገብ አድርገዋል። ለዚህም እናመሰግናቸዋለን። ይህንን ችግር እንዲፈታ ወ/ሪት ብርቱካን ከክልል መንግሥት ጋር እናገናኛችኋለን ጂግጅጋ እመጣለሁ ብላን ነበር እስካሁን እየጠበቅናት ነው። ችግሩ ይፈታል ብለን እናምናለን። አሁንም ከምርጫ እንቀራለን ማለት አይደለም። ችግሩ ከተፈታ ምርጫ እንካፈላለን፤ ካልተፈታ ግን ውጤቱ መጥፎ ነው። ምርጫ ትሳተፋላችሁ ብለን ተስፋ እናድርግና እናንተ በክልላችሁ አብላጫ ድምፅ የማግኘት ዕድላችሁ ምን ያህል ነው? የሕዝብ ድጋፋችሁን ስትገመግሙት? ከፍተኛ ድጋፍ ያላችሁ በኦጋዴን ጎሳ ነው። የምትወክሉትም ኦጋዴን ጎሳን ብቻ ነው ይሏችኋል። ከኦጋዴን ጎሳ ውጭ ያሉትንስ ትወክላላችሁ? ይቀበሏችኋል? [ሳቅ] እኛ እንደ ጎሳ አይደለንም። እንደዚያ ዓይነት ቃላት የሚናገሩ አስተሳሰባቸው ጠባብ ነው ብለን ነው የምናምነው። እኛ የታገልነው፤ አሁንም የምንታገልለት ለሶማሌው ሕዝብ ነው። በሞያሌ፣ ነገሌ፣ ፊልቱ፣ በጎዱ ኡኩር፣ በጂግጅጋ፣ በድሬዳዋ ባለው የሶማሌ ሕዝበ ተወዳድረናል፤ ደግሞም እንወዳደራለን። ከፍተኛ የማሸነፍ ተስፋ ነው ያለን፤ ነገሩ የምርም በሕዝብ ድምፅ የሚወሰን ከሆነ። እንደዚያ ግን አይመስልም። ለምን በለኝ። ነገሩ በሕዝብ ድምጽ የሚወሰን ከሆነ ለምንድነው ዕጩ እንዳናመዘግብ የሚከለክሉን። ነገሩ በሕዝብ ድምጽ የሚወሰን ከሆነ ለምንድነው አባሎቻችን የሚታሰሩት? እኛ በሕዝብ ልብ ውስጥ ያለን ፓርቲ ነን ብለን እናምናለን። አንድ ሰውም አላሰርንም፤ አንድም ሰውም አላባረርንም በሕዝብ ምርጫ ስለምናምን። ስለዚህ ምርጫው ካልተጭበረበረ 89 በመቶ በላይ ድምፅ እናገኛለን ብለን እናስባለን። ከተጭበረበረ ግን መቶ በመቶ አሸንፈናል ሲል ነበር አቶ መለስ፤ አሁንም እንደዚያ ሊሉን ይችላሉ። እንደው በምርጫው ብትሸነፉ የምርጫውን ውጤት ተቀብሎ ወደፊት ደግሞ ለተሻለ ውጤት ለመሄድ ያላችሁ ዝግጁነት ምን ያህል ነው? መቶ በመቶ ዝግጁ ነን! ምክንያቱም እኛ ከጫካ ትግል መጥተን እንደ ጋዜጠኛ ምን ያህል ሕዝብ አቀባባል እንዳደረገልን ብታይ ጥሩ ነበር፤ አሁንም በቀብሪደሃር፣ በዋርዴር፣ በነገሌ ያለው እንቅስቃሴ ብታይ ጥሩ ነበር። ሕዝባችን እንደሚመርጠን እናምናለን። እንደ ፓርቲ ከተሸነፍንም እንቀበላለን። ከአሸናፊው ጋር አብረን እንሠራለን። ለሕዝብ ልማት ትግላችንን እንቀጥላለን። ለመጪው ምርጫ እንዘጋጃለን። ይህ የሚሆነው ግን ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ሲካሄድ ብቻ ነው። አሁን ባለው ሁኔታ ግን "አሸንፈናል ኑ ፈርሙልን" ቢሉ ግን "አጭበርብራችኋል እንጂ አላሸነፋችሁም" ነው የምንላቸው። ዘ ጋርዲያን በሶማሌ ክልል ጋዝ በማውጣት ላይ የተሰማሩ እንደ ፖሊ እና ሲጂኤል ያሉ ድርጅቶች እንቅስቃሴ ሳቢያ የተፈጠረ አካባቢያዊ ብክለትን ተከትሎ በርካቶች እየሞቱ እንደሆነ ዘግቧል። እአአ በ2014 እስከ 2ሺህ 400 ሰዎች ሞተዋል ብሏል። ይህንን የሚመለከተው የፌደራል መንግሥትን ቢሆንም ስለዚህ ጉዳይ ፓርቲያችሁ ያውቃል? ፌደራል መንግሥቱ ትኩረት እንዲሰጥ ያደረጋችሁት እንቅስቃሴ አለ? ድርጅታችን ይህንን ያውቃል። ችግር እንዳለ እናውቃለን። እኔ ከቆራሂ ዞን ነኝ። ዞኔ ስለሆነ ነገሩን በጥልቀት አውቃለሁ። ዶዶይን፣ ሽላቦ እና ሌሎች ቦታዎች ሄጃለሁ። ሰው በማይታወቅ በሽታ እየሞተ ነው። ሆዳቸው አብጦ በአፍንጫቸው ደም ፈሶ ይሞታሉ። ሐኪም ቤት ሲሄዱም 'ምንም ያገኘነው ነገር የለም ነው' የሚሉት ሐኪሞቹ። እንስሳትም እየሞቱ ነው። የፌደራል መንግሥት መፍትሔ ማድረግ አለበት። ኩባንያዎቹ ምን ዓይነት እንቅስቀሴ እያደረጉ እንደሆነ ማወቅ አለበት። ምን ተበላሽቶ እንደሄደ ማወቅ አለበት። በዓለም ነዳጅ ይወጣል፣ ናፍጣ ይወጣል፣ ቤንዚል ይወጣል። ነገር ግን አካባቢን እንዳይበከል የሚያስችሉ መደረግ ያለባቸው ቅድመ ዝግጅቶች አሟልቷል ወይ የሚለውን ፌደራል መንግሥት የራሱን ኃላፊነት መወጣት አለበት። በተጨማሪም የሶማሌ ክልል መንግሥት ኃላፊነት መወጣት አለበት ብለን እናምናለን። ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይተናል፤ ግን ምንም ግብረ መልስ አላገኘንም። አሁንም እንጽፋለን። ሕዝብ ምንም ማድረግ አይችልም። አንድ ግመል እየጠበቀ ያለ እረኛ ግመሉ ስትሞት ቤተሰቡ ሲሞት ምን ማድረግ ይችላል? ይህ ኃላፊነት የፌደራል መንግሥትና የክልሉ መንግሥት ነው። አሁንም ጥያቄያችንን እንቀጥላል። በቀድሞው አስተዳደር አብዲ ኢሌ ብዙ ጥፋቶች ተፈፅመዋል ከእናንተ ጋር በተያያዘ። የአቶ አብዲ ኢሌን የፍርድ ሂደት ተከታትላችሁ ታውቃለችሁ? ለደረሰባችሁ ጥቃት፣ በደልና ሕዝባችሁ ላይ ለደረሰ ጥፋት ራሳችሁን ችላችሁ ክስ የመመስረት ሐሳብስ አላችሁ? እኛ በአብዲ ኢሌም ሆነ ከእሱ በፊት በነበሩት፣ ከእርሱ ጋር የነበሩትን ጠቅላይ ሚኒስትሮችና የኢህአዴግ መሪዎች በአፍሪካም በዓለም ፍርድ ቤትም ከሰናል። በሶማሌም በሌሎችም ሕዝቦች ላይ ባደረሱት በደል ተጠያቂ እንዲሆኑ ከሰናል። አሁንም እንከታተላለን። ነገር ግን ከሚያሳዝኑን እና ከሚያናድዱን ነገሮች አብዱ ኢሌ እና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በፍርድ ቤት የሚጠየቁት በሶማሌ ሕዝብ ላይ ባደረሱት በደል እና ግፍ ሳይሆን እአአ በነሐሴ 4 በጂግጅጋ የሶማሌ ተወላጅ ባልሆኑ ሰዎች ላይ ባደረሱት በደል እና በቤተክርስቲያን መቃጠል ብቻ ነው። ይህ ትክክል አይደለም ማለቴ ሳይሆን ከዚያ በፊት ሲያደርግ በነበረውም ጭምር ሊጠየቅ ይገባል። አሁንም የታሰሩትና ያሉት የህወሓት አመራሮች በሶማሌ ሕዝብ ላይ ባደረሱት ግፍና በደል መጠየቅ አለባቸው ብለን እናምናለን። እንከታተላለን። ፍትሕ እስከምናገኝ ድረስ አይደክመንም፤ አይሰለቸንም። የመጨረሻው ጥያቄ የሚሆነው፣ አሁኗን ኢትዮጵያን ድርጅታችሁ እንዴት ነው የሚገመግማት? አገሪቷ ለመፍረስ ቋፍ ላይ ነው ያላችው ከሚለው ጀምሮ አገሪቷ የተሻለ የአንድነት ተስፋ የሚጣልበት ጊዜ ነው የሚሉም አሉ። በብዙ ክልሎች የሚሰማው ዜና ደግሞ የሚረብሽ ነው። እናንተ ደግሞ ድምጻችሁም አይሰማም። ሌላ ቦታ በሚታዩት ነገሮች አይመለከተንም ብላችሁ ነው? በአገር ጉዳይ ለምን ዳር ያዛችሁ? ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው ያለችው። በዚህ ወቅት ገዥው ፓርቲ የሚጫወተው ሚና እጅግ ወሳኝ ነው ብዬ አምናለሁ። እናምናለን። የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ደግሞ እንዲሁ ከፍተኛ ሚና አለው። ይህች አገር እኛ እንደሚመስለን ለምርጫ ከመሮጥ ብሔራዊ መግባባት ያስፈልጋታል ብለን እናምናለን። ለምን? ትላልቅ ፓርቲዎች በዚህ ምርጫ አይሳተፉም ማለት ይቻላል። ለምን? አሁን አዲስ አበባ ነው ያለሁት። ለምርጫው ጥቂት ጊዜ ነው የሚቀረው። ግን ይህን አታይም። ዛሬ እንደከዚህ ቀደሙ የምርጫ ፖስተሮችና ምልክቶች አይታዩም። ሕዝብ ደንታ አይሰጥም ለምርጫ ማለት ነው። ለምን? ብለን መጠየቅ አለብን። በሶማሌና በአፋር ጦርነት አለ። በአማራና በኦሮሞ ሽኩቻ አለ። በትግራይም ያለው ይኸው ነው። ይህ ሁሉ ነገር እያለ፤ ብሔራዊ ውይይት ተደርጎ ሳንስማማ ወደ ምርጫ መሮጣችን ወደ ከፋ ሁኔታ ይወስደናል ብለን እናምናለን። በሁሉም ነገር ባንስማማ በአንድ ነገር ቢያንስ በምርጫ ሂደትና ተሳታፊነት እንኳን ብንስማማ ይመረጣል ብዬ አምናለሁ። እኔ በግሌ አገሪቷ በከፋ፣ በከፋ ሁኔታ ላይ ነው ያለችው ብዬ አምናለሁ። ስለ ነገ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ እርግጠኛ አይደሉም? አይደለሁም። እኔንጃ ወደየት እየሄድን እንደሆነ?
"ፖለቲከኞች የሶማሌን ሕዝብ እንደ ኢትዮጵያዊ አያስቡትም" የኦብነግ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አህመድ መሐመድ ከሦስት ዓመታት በፊት ለውጡን ተከትሎ ለሰላማዊ ትግል ወደ አገር ውስጥ ከገቡ ፓርቲዎች መካከል አንዱ ነው። ቢቢሲ ስለ ምርጫና ስለ ፓርቲው እንቅስቃሴ ከኦብነግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የፌደራል መንግሥት ግንኙነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ መሐመድ ጋር ቆይታ አድርጓል። ስለኦብነግ እምብዛምም ከማይታወቁ ነገሮች እንጀምር። አፈጣጠሩ ከዚያድባሬ ወረራ ጋር የሚያያዝ ታሪክ አለው። በሽግግሩ ጊዜ ተሳትፋችኋል። ከምዕራብ ሶማሊያ ነጻነት ግንባር ወጣት ሊግ ነው ኦብነግ የተፈጠረው ይባላል። ክልሉን ለሁለት ዓመት ያህል አስተዳድራኋል። ልክ ነኝ? የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) የተመሰረተው (እአአ) ነሐሴ 15 ቀን 1984 ነው። በወቅቱ የነበረው የምዕራብ ሶማሌ ነጻ አውጭ ግንባር (WSLF) በኢትዮጵያ ውስጥ በነበረችው ሶማሌዎች በሚኖሩበት አገር ከተዳከመ በኋላ የግንባሩ ወጣቶች ዘርፍ የነበሩ አባሎች ተሰባስበው የመሠረቱት ግንባር ነው። የምዕራብ ሶማሌ ነጻ አውጭ ግንባር በኢትዮጵያ ሶማሌዎች የተቋቋመው ነው። ሆኖም በሶማሊያ መንግሥት ይደገፍ የነበረ ድርጅት ነበር። ወጣቶቹ ተሰባስበው፣ ተጠያይቀው ትግላችን እየተዳከመ ስለሆነ ምን እናድርግ በማለት የመሠረቱት ድርጅት ነው- ኦብነግ። እነዚህ ወጣቶች ትግላቸው ከሶማሊያ መንግሥት ነጻ አለመሆኑንና ጣልቃ ገብነት እንዳለው ተረድተው የመሠረቱት ነው። ኦብነግ በሶማሊያም በኢትዮጵያም ክልክል ስለነበርና ተቀባይነት ስላልነበራቸው በድብቅ ለዓመታት ሲሠሩ ቆይተዋል። ድርጅቱ ሲመሠረት አቶ አብዱረህማን መህዲ ነበሩ ሊቀመንበር። ከዚያም መሐመድ አብዲ መገኒ ለሁለት ወር ያህል ሊቀመንበር ሆነዋል። ከዚያም አቶ ሼህ ኢብራሂም አብደላህ ቋሚ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠው ድርጅቱን ለረዥም ጊዜ መርተዋል። እርሳቸው አሁን በሕይወት የሉም። የኦብነግ ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሶማሌዎች ኦጋዴን ተብሎ የሚጠራውን አገር ነጻ ማውጣት ነበር። የደርግ መንግሥት ከወደቀ በኋላ የኦብነግ መሪዎች እና ኃላፊዎች አገር ውስጥ ገብተው በመጎብ ዞን፣ ገርቦ በምትባል ወረዳ ሕዝብ ሰብስበው፤ ብሔራዊ ውይይት አድርገው ሸህ ኢብራሂም አብደላ እንደገና ተመርጠው በሽግግር መንግሥቱ ተሳትፏል። በመጀመሪያው ምርጫም ተሳትፎ በ84 በመቶ ድምፅ አብላጫ ድምጽ አግኝተው በክልሉ መንግሥት መሥርተዋል። ኢህአዴግ/ሕወሓት ምን ዓይነት የሕዝብ ድጋፍ፣ ዓለማና አቋም እንዳለን ካየ በኋላ ግን ወረረን። በዚህ ምክንያት ለትጥቅ ትግል ጫካ ተገባ፡፡ ፍላጎታችን በዲሞክራሲ መሳተፍ ነበር፤ ተገደን፣ ተገፍተን ጫካ ገባን። ለምን ያህል ጊዜ ነው ክልሉን? ለተወሰነ ጊዜ ነበር። አንድ ዓመት ከአሥር ወር ገደማ አስተዳድረናል። አሁን ያለው የክልሉ ሰንደቅ ዓላማ እንዲሁም እስካሁን ያለው በሶማሊኛ የተጻፈ መርሐ ሥርዓተ ትምህርት [ካሪኩለም] በኦብነግ በተመራው ክልላዊ መንግሥት ነበር የተጀመረው። መሠረታዊ የሆኑ ሥራዎችን ከጀመርን በኋላ የሕዝብ ድጋፋችን በጣም ከፍተኛ ስለነበር ጦርነት ተከፈተብን። ኃላፊዎችን መግደል ጀመሩ በዚህ ምክንያት ወደ ጫካ ገባን። ላለፉት 36 ዓመታት የቆየ አንጋፋ ድርጅት ነው። በዋናነት ለራስ ገዝ [self determination] ሲዋጋ የኖረ የፖለቲካ ድርጅት ነው። ለውጡን ተከትሎ በተደረሰ ስምምነት ወደ አገር ቤት መጥታችኋል። ነገር ግን አሁንም ስማችሁ የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ነው። እንዴት ይህን ስም ይዛችሁ ትቀጥላላችሁ? በአሁኒቷ ኢትዮጵያ ስሜት ይሰጣል? ጥሩ ጥያቄ ነው። በለውጥ ስማችን አይለወጥም። በሕዝብ ፍላጎት ነው ይህ ስም የተሰየመው። አቋም የያዘውም በሕዝብ ፍላጎት ነው። ዝም ብሎ በመሪዎች፣ በሁለት. . . በሦስት. . . በሃምሳ በመቶ ሰዎች የሚወሰን አይደለም። የመገንጠልም ሆነ ወደ ኢትዮጵያ ለመሳተፍ የሚወሰነው በሕዝብ ድምፅ ነው። ይህ ሕዝብ ምን ዓይነት ድርጅት እንደሚፈልግና ምን ዓይነት አቋም እንደሚይዝ ድርጅቱ የሚወሰነው በሕዝብ ድምፅ ነው። እኛ ከለውጡ ሰዎች ጋራ ስለተግባባን የድርጅቱን ስም፣ አቋምና ዓላማ መለወጥ አንችልም። እንደዚህ ዓይነት ባህርይም የለንም። በሕዝብ የተቋቋመ ድርጅት፣ ለሕዝብ የተቋቋመ ዓላማ ስለሆነ፤ አንቀይርም። መቀየርም አንችልም። ሕዝብ ተጠይቆ፣ ተሰብስቦ፣ ብሔራዊ ስብሰባ ተካሂዶ ነው ዓላማችን የሚቀየረው። የኢትዮጵያ መሪዎች ደግሞ ሕዝብን የመሳብ ጠባይ ካላሳዩ ዝም ብሎ በቀላል የሚቀየር ነገር አይደለም። ታዲያ ኮንፈረንሱን የማታደርጉት ለምንድን ነው? የመቀየር ጊዜው አሁን አይደለም ብላችሁ ስለምታምኑ ነው? ነጻ አውጭ ግንባር ብሎ ራሱን ከማዕከላዊ መንግሥት ለመገንጠል የሚያስብን ድርጅት ስም ይዞ ከሌሎች ፓርቲዎችስ ጋር እንዴት ነው የምትሠሩት? እኔ ግራ የገባኝ፣ እኔ ግራ የሚገባኝ ይሄ ጥያቄያችሁ ነው። ብዙ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ይሄን ጥያቄ ሲጠይቁኝ ቆይተዋል። የመገንጠል [self determination] ጉዳይ ብዙ ጋዜጠኞች …፤ ምንድነው ችግራችሁ? ከዚህ ነጥብ ማለፍ ያቃታችሁስ ለምንድነው? እንዴ! የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ራሱ እስከ መገንጠል ይፈቅዳል። ለምን ይሄ ነገር ለጋዜጠኞች ራስ ምታት (stress) ሆነባችሁ? ለምን የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ላይዋጥላችሁ ቻለ? ለምን ይሄ ነገር ጉሮሯችሁ ውስጥ ተቀርቅሮ እንደቀረ እኔ ግራ ገባኝ። ሕጋዊ የሆነ ነገር ነው፤ ሕዝብ ይሆንልኛል ባለው መሄድ አለበት። ኢትዮጵያ ከሆነችላቸው በኢትዮጵያዊነት መቆየት ይችላሉ፤ ካልሆነችላቸው ደግሞ የራሳቸውን መንግሥት መፍጠር ይችላሉ። ይህ በዓለም ሕግጋትም ያለ ነው። በኢትዮጵያም ሕገ መንግሥት ያለ ነው። ለምን ደግማችሁ ደጋግማችሁ የእኛን ድርጅት ይሄን ጥያቄ እንደምትጠይቁ ግራ ይሆንብኛል። ጋዜጠኞች ግን ከዚህ ጥያቄ ማለፍ ለምን አቃታችሁ? ከዓመታት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት ዋና ፀሐፊያችሁ አቶ አብዱራህማን መህዲ በአንድ ቃለ ምልልሳቸው ላይ "ሶማሌ በማዕከላዊ መንግሥቱ የተናቀና የተረሳ ክልል ነው። እኛ ኢትዮጵያዊነት አይሰማንም፤ በቅኝ ነው ማዕከላዊ መንግሥቱ የያዘን" ሲሉ ተደምጠዋል። ይህ ቀደም ሲል ያለ ስሜት ነው። ከለውጡ በኋላ ይህ ስሜታችሁ በምን ያህል መጠን ተፈውሷል? በእርግጥ ይህ የመሪዎች ስሜት ሳይሆን የሕዝብ ስሜት ነው። እውነቱን ንገረኝ ካልከኝ የእኛ ሕዝብ፣ የሶማሌው ሕዝብ፣ የኦጋዴኑ ሕዝብ የእኔ መንግሥት የሚል ስሜት አሁንም ያለው አይመስለኝም። ምክንያቱም መንግሥት የራስ የሚሆነው ስለ ራስህ ሲያስብ ነው። ከአጤ ቴዎድሮስ፣ ከአጤ ምንሊክ፣ ከአጤ ኃይለ ሥላሴ፣ ከኮሎኔል መንግሥቱ እና አቶ መለስ ዜናዊ እስከ ዛሬ ድረስ የሶማሌ ሕዝብ ምን ተደረገለት? ምንስ ይደረግ ነበር? የሶማሌ ሕዝብ በፌደራል መንግሥት ምን ያህል ተሳትፎ ተሰጣቸው? ወይም ምን ያህል ጥቅም አገኙ? እንዴትስ ነው የሚታዩት? ዛሬ እኮ የኢትዮጵያን ብር እና የኢትዮጵያን መንግሥት የማያውቁ ሰዎች በክልላችን ውስጥ አሉ። ይሄ ምን ይነግርሃል? ለምን? በምንድን ነው የሚገበያዩት ታዲያ? ለምን? መንግሥት ስላልደረሳቸው ነዋ። የሶማሌ ሕዝብ ወታደር ተልኮ፣ ወታደር ሲጨፈጭፋቸውና ሲገድላቸው ነው የሚያውቁት። ይህን ነገር መቀየር ያለብን እኛ ሳንሆን የኢትዮጵያ መንግሥትና መሪዎች ናቸው። እኔ ልንገርህ ለምሳሌ…በቅርቡ በፌደራል የተዘጋጀ ውይይት ላይ በቢሾፍቱ ተሳትፌ አንድ ሰው ምን ብሎ ጠራኝ መሰለህ። በውይይት ላይ ነው የምልህ…አንድ ሰው "ወንድሜ ሶማሌው እንደገለፀው" ይለኛል። ተመልከት እንግዲህ! ምንድነው ችግሩ ታዲያ፣ አልገባኝም? እኔ በማንነቴ እኮራለሁ ችግር የለብኝም። ግን ለምሳሌ ሌላው ተሳታፊ የኦሮሞው ወንድሜ፣ የሃዲያው፣ የጉራጌው እየተባለ በብሔሩ ተሰይሞ ስሙን ከብሔሩ ጋር አያይዞ አልተነሳም። ወንድሜ ኦሮሞው፣ ወንድሜ ሃዲያው አልተባለም። እኔ ለምን ልዩ ሆንኩ? ይህ ምን ያሳይኻል? ይህንን መቀየር ያለብን ደግሞ ፖለቲከኞች፣ ምሁራንና መሪዎች ናቸው። ይህ ልዩነት ከጥንት ጀምሮ እስከዛሬ ያለ ነው። እንደ ሁለተኛ ዜጋ ነው የሚያዩን። ፖለቲከኞች የሶማሌን ሕዝብ እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ አያስቡትም። ይህንን አለ የምትሉትን የተንሸዋረረ አመለካከት ለማቃናት እናንተስ እንደ አንድ ፓርቲ ምን ያህል ጥረት አድርጋችኋል ብዬ ለጥይቅዎ? ከጥንት እስከ ዛሬ ኢትዮጵያዊ መሆናችን አልቀረም። በድርጅት ብቻ ሳይሆን በሶማሌ ባለሥልጣናት እንደ ሶማሌ ብሔረሰብ ተወያይተው በመሆኑም ድርሻችን ምን ያህል መሆን እንዳለበት መወያየት አለብን። ትልቁ ሚና መጫወት የነበረባቸው በሥልጣን ላይ ያሉ የሶማሌ ባለሥልጣናት ነበሩ። ምን እንዳጡ፣ ምን እንደሚያንሳቸው መጠየቅ ነበረባቸው። እኛ እንደዚህ ብለን ስንጠይቃቸው እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ ነው የሚያዩን። በመሆኑም ለዚህ ከፍ ያለ ሚና መጫወት ያለባቸው በሶማሌ ክልል ያሉ ባለሥልጣናት ነበሩ። እኛ ተወያይተን ምን ማድረግ እንዳለብን ለመወሰን እንደ የቤት ሥራ እናስብበታለን። ድርጅታችንም ያስብበታል። በዚች አገር ኢትዮጵያ ውስጥ እስካለን ድረስ የድርሻችንን ማግኘት አለብን። የድርሻችንን መጫዎች እና የድርሻችንን መካፈል አለብን የሚል እምነት ነው ያለን። በአሁኗ ኢትዮጵያ ውስጥ አፋሩም፣ ሐረሪውም ፣ ሶማሌውም፣ ደቡቡም . . . እኔ ተገፍቻለሁ፤ እኔ እንደ ኢትዮጵያ አልቆጠርም እኔ ሁለተኛ ዜጋ ነኝ እያለ ነው። ይህ የስሜት መጎዳት ሁሉም ሕዝብ ላይ እንደሆነ ይታወቃል። ሁሉም አኩራፊ ከሆነ እንዴት ነው ኢትዮጵያን መጠበቅና ወደፊት ማራመድ የሚቻለው? እኔ ተጎድቻለሁ የሚለው ሕዝብስ ወደ መሀል መምጣትና የድርሻውን መወጣት የለበትም ወይ? ይህ ስሜት የማይሰማውስ ብሔር አለ ወይ ኦሮሞው፣ ወላይታው፣ አማራው፣ ሲዳማው . . . በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው ያነሳኸው። በዓለም ላይ እኔ ነኝ ጎጂው፣ እኔ ነኝ በዳዩ፣ እኔ ነኝ አጥፊው የሚል ሰው የለም። ጎጂውም ተጎጂውም እንደዛ ነው የሚቀጥሉት። ባለፉት ሥርዓቶች ምን ዓይነት ችግሮች ነበሩ ብለን እንደ አንድ አገር ዜጋ ተወያይተን፣ ስህተታችንን ተጠያይቀን፤ እርቅ ተቀብለን፤ ወደፊት ምን ይሻለናል? ማለት አለብን ብዬ አንስቻለሁ። ነገሩ የአዞ እንባ እንዳይሆን፤ ማን ነው ይህን የሚያመጣው? ሥርዓቶቹ ናቸው። በመለስ ዜናዊ አስተዳደር የህወሓት፣ የትግራይ ጊዜ ይባላል። በደርግም ጊዜ የአማራው ጊዜ ይባላል። እነርሱም ግን ተበድለናል እያሉ ነው። ስለዚህ ቆሻሻችንን ከመቆፈር አሁን ምን ማድረግ አለብን? የሚለው ላይ መምጣት ያስፈልጋል። መጀመሪያ ይቅርታ መጠያየቅ፣ ሕዝብን ማስተማር፣ መቻቻልና፥ አንድ ሰው ተበድያለሁ ካለ ይቅርታ ማለት ያስፈልጋል። አሁን ባለችው ኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትና ሥነ ሥርዓት ተከባብረን እየተጓዝን፤ ጥያቄዎች ካሉ በሕጋዊ መሠረት እንዲፈቱ፣ ማንኛውም የወደፊት ዕጣ በሕጋዊ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ነው የማስበው። እኛም እንደዛ ዓይነት አቋም ነው ያለን። ይቅርታ መጠያየቅ ላይ ብዙዎች ጥያቄ የላቸውም። ጥያቄው ይቅርታ የሚጠይቀው ማን ነው? የሚጠየቀውስ ማን ነው? አጥፊው ማነው? ተጎጂው ማነው? የሚለው ነው። የደርግ መንግሥት ብለዋል ደርግ የትኛውን ብሔር ነው የሚወክለው? ከዚያ በፊት ያሉ አስተዳደርና መንግሥታትን ስንቆጥር የትኛውን ብሔር ነው የምናነሳው? የመሪውን ብሔር ነው የምናነሳው? የወከሉት ሕዝብስ ራሱ ሲበደል አልነበር ወይ? እውነት ብለሃል። በተወሰነ መልኩ ካነሳኸው ነጥብ ጋር እስማማለሁ። ምክንያቱም በሥልጣን ላይ የነበረ ሰው ወይም ሰዎች ናቸው ሥርዓቱን ያጠፉት ይባላል። እውነት ነው የአማራ ሕዝብ ተሰብስቦ የሶማሌን ሕዝብ እንበድል አላለም። የትግራይም ሕዝብ እንደዚያው ተነስቶ የሶማሌ ሕዝብ ወይም ሌላውን እንበድል ብሎ አልተነሳም። ግን በመለስ ዜናዊ ጊዜ አራት ድርጅቶች ነበሩ። በኢህአዴግ ሥር የተሰበሰቡ ድርጅቶች። ነገረ ግን ብዙ ጊዜ ሰው ሲናገር በህወሓት የተመራው መንግሥት ነው የሚለው? በህወሓት እነማን ነበሩ ሲባል ትግራዮች ነበሩ እንላለን። በደርግ ጊዜም እነማን ነበሩ ሲባል የአማራው ነበሩ ይባላል። ያው በተወሰነ ደረጃ ካንተ ጋር እስማማለሁ ምክንያቱም ሥርዓቱ ነበር አጥፊው። በተወሰነ ደረጃ ደግሞ ከሥርዓቱ በስተጀርባ የትኛው ብሔር ነበረ? አፍሪካዊያን እኮ ብሔርተኞች ነን ሁላችንም። ይህንን መካድ አንችልም። ኬንያ ብትሄድ ተመሳሳይ ነገር ነው ያለው። ኬንያ ብታነሳ የኪኩዩ መንግሥት ነው የምትለው። እዚህም እንደዛ ዓይነት ነገር አለ። እና መካድ የለብንም፡፡ ይህን መቀበል አለብን ብዬ አስባለሁ። ከአራት ዓመታት በፊት ሊቀመንበራች አቶ አብዱራህማን መኽዲ ከአልጀዚራ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ "በመቶ ዓመት ውስጥ ኦጋዴን ውስጥ አንድ ሃይስኩልና አንድ ሆስፒታል ነው ያለን። ሴቶቻችን ሊወልዱ ሲሉ ወይም ሲታመሙ ሞቃዲሹ ነበር የሚሄዱት" ብለዋል። በአንጻሩ ሶማሌ በተለይም ሰፊ ድጋፍ ባላችሁ ኦጋዴን በጋዝ ሃብት ትልቅ ተስፋ የተጣለበትና ትልቅ ሃብት ያለው አካባቢ ነው። አሁን ሕዝባችሁ በልማት እየተጠቀመ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? በዚያ አካባቢ ባለው እንቅስቃሴ ተስፋ ይታያችኋል? ተስፋ አለን። እንደ እንድ ሙስሊም በቁርዓን ላይ (ላ ታቅናጡ ቢራሕማቲላህ) "በፈጣሪ ፀጋና ሲሳይ ተስፋ አትቁረጡ" የሚል አንቀጽ አለ። ሁልጊዜም ተስፋ አለን። ምንም እንኳ ብንተችም አሁን ያለው የሶማሌ አስተዳደር በመጠኑ እያደረገ ነው። ጥሩ ነው። ትምህርት ቤቶች በቁጥር አነስተኛ ቢሆኑም በመጠኑ እየተሠሩ ነው፤ ከዚህ በላይ መሆን ነበረበት ማለታችን ባይቀርም ማለቴ ነው። ይህ ማለት ግን እንዳትሳሳት። አሁንም በእሳት ብርሃን (በኩራዝ ብርሃን) የሚወልዱ የሶማሌ እናቶች አሉ። ከ60 በመቶ በላይ የሶማሌ ሴቶች አሁንም እንደዚያው እየወለዱ ነው ያሉት። ጥራታቸው ዝቅተኛ ቢሆንም ትምህርት ቤቶች አሉ። ጥራታቸው በጣም ዝቅተኛ ቢሆኑም ሆስፒታሎችም ክሊኒኮችም በመጠኑ አሉ። እየተሠሩም ነው። ወደፊትም እንዲሠራ፣ እኛም ካሸነፍን ቅድሚያ ሰጥተን የምንሠራው ይህንን ነው። ሌላም ቢያሸንፍ መሠረታዊ የሆኑት እነዚህ ላይ ትኩረት መስጠት እንዳለበት እናምናለን። የጋዝ ሃብቱ ላይ የምታነሱት የተለየ ጥያቄ አለ? አንድ የሶማሌ ተረት አለ። "Dhariba ninkii u dhow baa dhuunigiisa leh" ጭብጡ ምንድነው? "ምግብ ሲበስል ለቀረበው ሰው ነው ቅድሚያ መሰጠት ያለበት" የሚል አባባል ነው። የሶማሌው ሕዝብ ከጋዝና ነዳጅ ንብረቱ እንደዚህ ሩቅ መሆን የለበትም። የተሰጠው ድርሻም በቂ አይደለም ብለን እናምናለን። ከዚያ በላይ ነው ማግኘት ያለባቸው ብለን እናምናለን። በፌደራል መንግሥት ያላቸው ድርሻም በቂ አይደለም እንላለን። የፌደራል ሃብትም የሚደርሳቸው ከዚያ በላይ ማግኘት አለባቸው ብለን እናምናለን። አቶ አብዱራሕማን እንዳሉት ሕዝባችን ድሮም በጫካ ያለ ሐኪምና መድኃኒት ሲሞት እንደነበረው አሁንም እየሞተ ነው ያለው። ይህ ግን በእኛም ይሁን በሌላ እንደዚህ ሆኖ መቀጠል የለበትም ብለን እናምናለን። እናንተ ጫካ በነበራችሁበት ዘመን የሶማሌ ሕዝብ በቀድሞ የሶማሌ አስተዳዳሪ አቶ አብዲ ኢሌ ቁም ስቅሉን ሲያይ እንደነበረው እናንተም ፍዳውን ስታበሉት ነበር። አሁን አቶ ሙስጠፌ ከመጡ ወዲህ ግን ክልሉ ከሌሎች ክልሎች አንጻር ብዙም ኮሽታ የሌለበት፣ ሰላም ያለበት እንደሆነ ነው የምናየው፤ ፕሬዝዳንት ሙስጠፌም በዚህ የሚሞካሹ ናቸው። እናንተ እንዴት ነው የምትገመግሙት? አቶ ሙስጠፌ ከመጣ ሰላም መጣ ከማለት እናንተ ከመንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት ከፈረማችሁ በኋላ ሰላም መጣ ብትሉ ይመረጣል ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም አቶ ሙስጠፌ እኛ አዲስ አበባ እያለን፤ እኛ የሰላም አቅጣጫ ከመንግሥት ጋር ከተስማማን በኋላ ነው የተሾሙት። ሰላም በአቶ ሙስጠፌ አሊያም በብልጽግና ፓርቲ ሳይሆን፤ በእኛና በኢህአዴግ ነው የተፈፀመው። ሰላም በኦብነግ ነው የመጣው፤ ሰላም በእኛ ውሳኔ ነው የመጣው ብለን እናምናለን። ምክንያቱም ከመንግሥት ጋር ስንፋለም ነበር። እኛ እስከተፋለምን ድረስ 'እነሱን ሕዝብ ይደግፋቸዋል' በሚል ሕዝብ ሲጨፈጭፉ ከእኛም ጋር ሲዋጉ ነበር። አቶ ሙስጠፌ በመሀል ገብቶ ነው እንጂ በእርሱ ሰላም አልመጣም። በእኛ ነው ሰላም የመጣው። አሁንም በእኛ ካልሆነ በሰላም አይቆይም ነበር። ምክንያቱም ድርጊታቸው፣ ጸባያቸው፣ አነጋገራቸው እና ሁሉ ነገራቸው ወደ ሰላማዊ የሚወስደን አይደለም ብዬ አምናለሁ። ሰላም በእኛ ነው የመጣው፤ በእኛ ነው የተመሠረተው። አሁንም በእኛ ነው ያለው። ነገር ግን ሰላም ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲነጻጸር ጥሩ ነው። የሕዝባችን ውሳኔ ነው። ሌሎች ኢትዮጵያውያን ሁለተኛ ዜጋ ሆነው በያሉበት ቦታ እየተገደሉ ነው። ሶማሌው የሰላምንም የጦርነትንም ዋጋ ስለሚያውቅ፤ እኛ ስለወሰንን ነው ዛሬ ሰላም የሆነው። ዛሬ የሰላም ቀን ነው። የፈለግነውን በሰላም እንፈልግ ከሌሎች ጋር በሰላም እንወያይ፣ በሰላም እንሂድ ብለን የኦብነግ ውሳኔ ስለሆነ ነው በዚያ እየሄድን ያለው። አሁንም እንቀጥላለን። ሰላም ለሕዝባችን ለአፍሪካ ቀንድም እንዲወርድ አላህን እንጠይቃለን። እናንተ ጫካ በነበራችሁ ጊዜ በትጥቅ ትግሉ ጊዜ ፤ አንዳንድ የፈጸማችኋቸው ጥቃቶች አሉ። ግንቦት 2007 እአአ 65 ኢትዮጵያያዊ የጉልበት ሠራተኞች እና ዘጠኝ ቻይናዊያን በማዕድን ቁፋሮ ላይ ሳሉ አቦሌ ላይ ጥቃት አድርሳችሁ ገድላችኋቸዋል። ንጹሃን ሞተዋል። ጅግጅጋም ላይ እንደዚሁ የሰዎች ሕይወት አልፏል። ይህም በእናንተ የሆነ ነው። አሁን ለሰላም ትግል ከመጣችሁ በኋላ ይቅርታ መጠየቅ ያለባችሁ አይመስላችሁም? ሁለት ዝሆኖች ሲጣሉ ብዙ ሳር ይወድማል ይባላል። የትኛውም አገር ጦርነት ሲከሰት የሰላማዊ ሰው ሕይወት ያልፋል። ያለ ነገር ነው። እኛ ዓላማችን ሰላማዊ ሰዎችን እናጥቃ ብለን አልነበረም። ቻይናውያን በማን ጥቃት ነው የሞቱት? ማንን ጠይቀው ነው የኦጋዴን ግዛት የገቡት? ከመግባታቸው በፊትና ከገቡም በኋላ አስጠንቅቀናቸው ሰላም አለመሆኑን እየነገርናቸው 'እምቢ' ብለው ስለገቡ እኛ የመንግሥት ሠራዊትን ዒላማ ስናደርግ ቻይናውያኑ ስለሞቱ መንግሥት ነው ይቅርታ መጠየቅ ያለበት። አምጪው ነው ይቅርታ መጠየቅ ያለበት። ግን ገዳዮቹ እናንተ ናችሁ እኮ? የተገደሉት በእናንንተ አይደለም እንዴ? በሁለቱም በኩል ጥይት ተተኩሷል። በማን ጥይት እንደሞቱ አይታወቅም። በማን ጥይት እንደተገደሉ ማን ይናገራል? በእኛ ብቻ የሚላከክ አይደለም። የእኛ እጅ የለበትም ብለን አንክድም። ነገር ግን ማን ነው ያመጣቸው? ሁለተኛ ደግሞ በማን ኃላፊነት ነው የመጡት? በእኛ ኃላፊነት አልመጡም። እኛ እንደውም ማስጠንቀቂያ ሰጥተን ነበር 'እምቢ' አሉ። በመሆኑም እኛ ይቅርታ የምንጠይቅበት ሰበብ የለም። በእኛ ፍቃድና ኃላፊነት አልመጡም፡፡ ጽፈንላቸው ይቅርባችሁ ብለን ነው እምቢ ያሉት። አገራችንና ሃብታችንን ሊወስዱ ነበር የገቡት። ስለቻይናውያኑን ይህን ካሉ ኢትዮጵያውያን የጉልበት ሠራተኞች ደም ፈሶ ይቅርታ ለመጠየቅ ለምን ጉልበት ያንሳችኋል? በዚህ ጦርነት ስንት ኢትዮጵያዊያን ሞተዋል? በዚህ ጦርነት ኃላፊው ማን ነበር? እኛ በሰላም ሕዝባችንን እየመራን በነበረበት ሰዓት አመጹን ቀስቅሶ ሕዝብ የጨረሰ ማን ነው? ጦርነቱን ያነሳሳ አካል ነው ለሁሉም ይቅርታ መጠየቅ ያለበት። ከእኛ ጦር ለሞቱት፣ ከመንግሥት ጦር ለሞቱት፣ ለንፁሃን ዜጎች ሁሉ ኃላፊነቱን መወሰድ ያለበት የኢትዮጵያ መንግሥት፤ የኢትዮጵያ መሪዎች ናቸው። ምክንያቱም በሰላም እንዲያወያየንና ችግራችን በሰላም እንዲፈታ ያልሄድንበት የለም። ኢትዮጵያውያንን ከዚህም ከዚያም የሚያዋጉት ኃላፊነት የሚወስዱት አነሱ ናቸው ብለን እናምናለን። ፓርቲያችሁ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ለብቻው ተገናኝቶ ያውቃል? ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኛችሁት መቼ ነበር? ምን ተወያያችሁ? ይህን ቀን ነው ብዬ ልነግርህ አልችልም። ግን ከስድስት ወር በፊት አንዴ በቤተ መንግሥት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ከአቶ አብዱራህማን ጋር ነበር የተወያዩት፤ እስከማውቀው ድረስ። ስለ አገራዊ ሁኔታ፣ ስለመጪው ምርጫ፣ ስለሠላም፣ ስለ ዲሞክራሲ እና ስለተለያዩ ጉዳዮች ነበር ያነሱት። በጥሩ ሁኔታ ነበር የተወያዩት። ይህን ያህል ነው የማውቀው። ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ግንቦት ወር ላይ ይካሄዳል። እናንተም ትሳተፋላችሁ። በቅርቡ ጥቃት እየፈፀመብን ነው።አባላት ታስረውብኛል። ዶሎ፣ ቸረረ፣ ሸበሌና ቆራሄ ዞኖች ሰብዓዊ ጥሰት አለ። እየተንገላቱብኝ ነው ብላችኋል። አሁንም ችግር አለ ማለት ነው? ይህ ችግርስ ከምርጫ እንድትወጡ ሊያደርጋችሁ ይችላል? በዚህ ላይ ትኩረት ማድረግ እፈልጋለሁ። ዛሬ ከሚደርሱን መረጃዎችና ከምናያቸው ነገሮች በምርጫው እንደምንሳተፍ ሙሉ ቃል መስጠት አልችልም። ጫፍ ላይ የደረስን ይመስለኛል። ነገሮች እየተደማመሩ ነው። ለምሳሌ አሁን ላይ የመራጮች ምዝገባ ጊዜ ነው። የመራጮች ምዝገባ ጊዜው ተራዝሟል። በቴክኒካል ችግር ሊሆን ይችላል። ሆነ ተብሎም ሊሆን ይችላል። ዛሬ ከሚደርሱን መረጃዎች ነገሮች እየተባባሱ ነው። ለምሳሌ ለመራጮች የሚሰጠው ካርድ ለሶማሌ ክልል ምን ያህል ካርድ እንደሚላክ የምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎቹ ማሳወቅ አለበት። ወደ ምርጫ ጣቢያዎቹ የሚላከውን ካርድ ተወዳዳሪዎች ማወቅ አለባቸው። በምርጫው ምዝገባ ጊዜም ፓርቲዎቹ ወይም ተወዳዳሪዎቹ ታዛቢ ወይም ወኪል መስጠት አለባቸው፤ ነገር ግን ዝም ብለው በተለያዩ ቦታዎች ሳጥኖችን አራገፉ። ሳጥኑ ደግሞ ክፍት ነው። እስካሁን ለእኛ የተሰጠን ካርድ ቁጥር የለም። እና የተያያዘ ነገር እየመጣ ነው። ብዙ ምልክቶች እየታዩ ነው። በሚቀጥሉት ቀናት ድርጅቱ ተሰብስቦ ይወያይበታል። ሠራተኞቹም መጀመሪያ ሲቀጠሩ ከዘመድ፣ ከመንግሥት ሠራተኛ ሲሆኑ መቶ በመቶ በሶማሌ ክልል ሠራተኞች የብልጽግና ተከፋይ ናቸው። 99 በመቶ የመንግሥት ተከፋይ ናቸው። በመሆኑም በቀላሉ ለመንግሥት ሊገዙ ይችላሉ። በመሆኑም ምንም በሌለን መረጃ መቀጠል የምንችል አይመስለኝም። ሆን ተብሎ የተደረገ ነገርም ይመስላል። በተጨማሪም ብልጽግና በመንግሥት ሃብትና ንብረት እየተጠቀመ ነው ያለው። ሥልጣኑንም እየተጠቀመ ነው። ተወዳዳሪ ልናስመዘግብ አልቻልንም። እዚህ አዲስ አበባ ነው እያስመዘገብናቸው ያለው። ይህንን ስናመለክት እናስተካክላለን ሲሉን ነበር። ምንም የተስተካከለ ነገር የለም። የእኛ ተወዳዳሪዎች ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው። በመንግሥት መኪና ዘመቻ እያደረጉ ነው። ለምን ስንላቸው ደግሞ ታርጋ መፍታት ጀምረዋል። ስለዚህ ሁኔታው በዚህ የሚቀጥል ከሆነ በምርጫው የምንሳተፍ አይመስለኝም። ምን ያህል ዕጩዎችን የት አስመዝግባችኋል? በሶማሌ ክልልም በሌላ የሶማሌ ማኅበረሰብ ባለባቸው አጎራባች ክልሎች እና አዲስ አበባ ለመወዳደር አስበን ነበር። ግን በተሳሳተ በዕጩዎቻችን የተሳሳተ አረዳድ እና ቴክኒካል ችግር ምክንያት አዲስ አበባ መመዝገብ አልቻሉም። ድሬዳዋ እንዳናስመዘግብ ደግሞ በብልፅግና ተከልክለናል። ተከልክለናል ሲሉ ምንድን ነው ማስረጃዎት? የእኛ ዕጩዎች እንዳይመዘገቡ ተከልክለዋል። በምርጫ ቢሮ ኃላፊዎች አትመዘገቡም ተብለዋል። በገርባ ኢሴ፣ በፊቲ፣ ሃደጋላ ያሉ ዕጩዎችም እንደዚሁ ተብለው አስፈርመዋቸው ከሦስት ቀን እስራት በኋላ ተባረዋል። በሞያሌ፣ በካሱርቱ፣ በዞላአጦ ምርጫ ኮሚሽን ተገናኝተን ለምን አታስመዘግቡም ሲሉ፤ ኦብነግን እንዳናስመዘገብ በመንግሥት ታዘናል የሚል ምላሽ የሰጡ ነበሩ። ብዙ የተከለከልንባቸው ቦታዎች አሉ። እስካሁን 237 የክልል እና 15 ድሬዳዋ ላይ ከዚህ ላይ አምስቱ ዛቻና ማስፈራሪያ ስለደረሰባቸው ወጥተዋል። ከምርጫ ቦርድ ጋር በክልል ሆነ በፌደራል ደረጃ ይህን ያህል ለማስተጋባት ምን ያህል ርቀት ሄዳችኋል? የምርጫ ቦርድ አቅማቸው እስከሚፈቅድ ችግሩን ለመፍታት ሞክረው ነበር። መፍታት ያልቻሉትን ደግሞ አዲስ አበባ መጥተን እንድናስመዘገብ አድርገዋል። ለዚህም እናመሰግናቸዋለን። ይህንን ችግር እንዲፈታ ወ/ሪት ብርቱካን ከክልል መንግሥት ጋር እናገናኛችኋለን ጂግጅጋ እመጣለሁ ብላን ነበር እስካሁን እየጠበቅናት ነው። ችግሩ ይፈታል ብለን እናምናለን። አሁንም ከምርጫ እንቀራለን ማለት አይደለም። ችግሩ ከተፈታ ምርጫ እንካፈላለን፤ ካልተፈታ ግን ውጤቱ መጥፎ ነው። ምርጫ ትሳተፋላችሁ ብለን ተስፋ እናድርግና እናንተ በክልላችሁ አብላጫ ድምፅ የማግኘት ዕድላችሁ ምን ያህል ነው? የሕዝብ ድጋፋችሁን ስትገመግሙት? ከፍተኛ ድጋፍ ያላችሁ በኦጋዴን ጎሳ ነው። የምትወክሉትም ኦጋዴን ጎሳን ብቻ ነው ይሏችኋል። ከኦጋዴን ጎሳ ውጭ ያሉትንስ ትወክላላችሁ? ይቀበሏችኋል? [ሳቅ] እኛ እንደ ጎሳ አይደለንም። እንደዚያ ዓይነት ቃላት የሚናገሩ አስተሳሰባቸው ጠባብ ነው ብለን ነው የምናምነው። እኛ የታገልነው፤ አሁንም የምንታገልለት ለሶማሌው ሕዝብ ነው። በሞያሌ፣ ነገሌ፣ ፊልቱ፣ በጎዱ ኡኩር፣ በጂግጅጋ፣ በድሬዳዋ ባለው የሶማሌ ሕዝበ ተወዳድረናል፤ ደግሞም እንወዳደራለን። ከፍተኛ የማሸነፍ ተስፋ ነው ያለን፤ ነገሩ የምርም በሕዝብ ድምፅ የሚወሰን ከሆነ። እንደዚያ ግን አይመስልም። ለምን በለኝ። ነገሩ በሕዝብ ድምጽ የሚወሰን ከሆነ ለምንድነው ዕጩ እንዳናመዘግብ የሚከለክሉን። ነገሩ በሕዝብ ድምጽ የሚወሰን ከሆነ ለምንድነው አባሎቻችን የሚታሰሩት? እኛ በሕዝብ ልብ ውስጥ ያለን ፓርቲ ነን ብለን እናምናለን። አንድ ሰውም አላሰርንም፤ አንድም ሰውም አላባረርንም በሕዝብ ምርጫ ስለምናምን። ስለዚህ ምርጫው ካልተጭበረበረ 89 በመቶ በላይ ድምፅ እናገኛለን ብለን እናስባለን። ከተጭበረበረ ግን መቶ በመቶ አሸንፈናል ሲል ነበር አቶ መለስ፤ አሁንም እንደዚያ ሊሉን ይችላሉ። እንደው በምርጫው ብትሸነፉ የምርጫውን ውጤት ተቀብሎ ወደፊት ደግሞ ለተሻለ ውጤት ለመሄድ ያላችሁ ዝግጁነት ምን ያህል ነው? መቶ በመቶ ዝግጁ ነን! ምክንያቱም እኛ ከጫካ ትግል መጥተን እንደ ጋዜጠኛ ምን ያህል ሕዝብ አቀባባል እንዳደረገልን ብታይ ጥሩ ነበር፤ አሁንም በቀብሪደሃር፣ በዋርዴር፣ በነገሌ ያለው እንቅስቃሴ ብታይ ጥሩ ነበር። ሕዝባችን እንደሚመርጠን እናምናለን። እንደ ፓርቲ ከተሸነፍንም እንቀበላለን። ከአሸናፊው ጋር አብረን እንሠራለን። ለሕዝብ ልማት ትግላችንን እንቀጥላለን። ለመጪው ምርጫ እንዘጋጃለን። ይህ የሚሆነው ግን ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ሲካሄድ ብቻ ነው። አሁን ባለው ሁኔታ ግን "አሸንፈናል ኑ ፈርሙልን" ቢሉ ግን "አጭበርብራችኋል እንጂ አላሸነፋችሁም" ነው የምንላቸው። ዘ ጋርዲያን በሶማሌ ክልል ጋዝ በማውጣት ላይ የተሰማሩ እንደ ፖሊ እና ሲጂኤል ያሉ ድርጅቶች እንቅስቃሴ ሳቢያ የተፈጠረ አካባቢያዊ ብክለትን ተከትሎ በርካቶች እየሞቱ እንደሆነ ዘግቧል። እአአ በ2014 እስከ 2ሺህ 400 ሰዎች ሞተዋል ብሏል። ይህንን የሚመለከተው የፌደራል መንግሥትን ቢሆንም ስለዚህ ጉዳይ ፓርቲያችሁ ያውቃል? ፌደራል መንግሥቱ ትኩረት እንዲሰጥ ያደረጋችሁት እንቅስቃሴ አለ? ድርጅታችን ይህንን ያውቃል። ችግር እንዳለ እናውቃለን። እኔ ከቆራሂ ዞን ነኝ። ዞኔ ስለሆነ ነገሩን በጥልቀት አውቃለሁ። ዶዶይን፣ ሽላቦ እና ሌሎች ቦታዎች ሄጃለሁ። ሰው በማይታወቅ በሽታ እየሞተ ነው። ሆዳቸው አብጦ በአፍንጫቸው ደም ፈሶ ይሞታሉ። ሐኪም ቤት ሲሄዱም 'ምንም ያገኘነው ነገር የለም ነው' የሚሉት ሐኪሞቹ። እንስሳትም እየሞቱ ነው። የፌደራል መንግሥት መፍትሔ ማድረግ አለበት። ኩባንያዎቹ ምን ዓይነት እንቅስቀሴ እያደረጉ እንደሆነ ማወቅ አለበት። ምን ተበላሽቶ እንደሄደ ማወቅ አለበት። በዓለም ነዳጅ ይወጣል፣ ናፍጣ ይወጣል፣ ቤንዚል ይወጣል። ነገር ግን አካባቢን እንዳይበከል የሚያስችሉ መደረግ ያለባቸው ቅድመ ዝግጅቶች አሟልቷል ወይ የሚለውን ፌደራል መንግሥት የራሱን ኃላፊነት መወጣት አለበት። በተጨማሪም የሶማሌ ክልል መንግሥት ኃላፊነት መወጣት አለበት ብለን እናምናለን። ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይተናል፤ ግን ምንም ግብረ መልስ አላገኘንም። አሁንም እንጽፋለን። ሕዝብ ምንም ማድረግ አይችልም። አንድ ግመል እየጠበቀ ያለ እረኛ ግመሉ ስትሞት ቤተሰቡ ሲሞት ምን ማድረግ ይችላል? ይህ ኃላፊነት የፌደራል መንግሥትና የክልሉ መንግሥት ነው። አሁንም ጥያቄያችንን እንቀጥላል። በቀድሞው አስተዳደር አብዲ ኢሌ ብዙ ጥፋቶች ተፈፅመዋል ከእናንተ ጋር በተያያዘ። የአቶ አብዲ ኢሌን የፍርድ ሂደት ተከታትላችሁ ታውቃለችሁ? ለደረሰባችሁ ጥቃት፣ በደልና ሕዝባችሁ ላይ ለደረሰ ጥፋት ራሳችሁን ችላችሁ ክስ የመመስረት ሐሳብስ አላችሁ? እኛ በአብዲ ኢሌም ሆነ ከእሱ በፊት በነበሩት፣ ከእርሱ ጋር የነበሩትን ጠቅላይ ሚኒስትሮችና የኢህአዴግ መሪዎች በአፍሪካም በዓለም ፍርድ ቤትም ከሰናል። በሶማሌም በሌሎችም ሕዝቦች ላይ ባደረሱት በደል ተጠያቂ እንዲሆኑ ከሰናል። አሁንም እንከታተላለን። ነገር ግን ከሚያሳዝኑን እና ከሚያናድዱን ነገሮች አብዱ ኢሌ እና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በፍርድ ቤት የሚጠየቁት በሶማሌ ሕዝብ ላይ ባደረሱት በደል እና ግፍ ሳይሆን እአአ በነሐሴ 4 በጂግጅጋ የሶማሌ ተወላጅ ባልሆኑ ሰዎች ላይ ባደረሱት በደል እና በቤተክርስቲያን መቃጠል ብቻ ነው። ይህ ትክክል አይደለም ማለቴ ሳይሆን ከዚያ በፊት ሲያደርግ በነበረውም ጭምር ሊጠየቅ ይገባል። አሁንም የታሰሩትና ያሉት የህወሓት አመራሮች በሶማሌ ሕዝብ ላይ ባደረሱት ግፍና በደል መጠየቅ አለባቸው ብለን እናምናለን። እንከታተላለን። ፍትሕ እስከምናገኝ ድረስ አይደክመንም፤ አይሰለቸንም። የመጨረሻው ጥያቄ የሚሆነው፣ አሁኗን ኢትዮጵያን ድርጅታችሁ እንዴት ነው የሚገመግማት? አገሪቷ ለመፍረስ ቋፍ ላይ ነው ያላችው ከሚለው ጀምሮ አገሪቷ የተሻለ የአንድነት ተስፋ የሚጣልበት ጊዜ ነው የሚሉም አሉ። በብዙ ክልሎች የሚሰማው ዜና ደግሞ የሚረብሽ ነው። እናንተ ደግሞ ድምጻችሁም አይሰማም። ሌላ ቦታ በሚታዩት ነገሮች አይመለከተንም ብላችሁ ነው? በአገር ጉዳይ ለምን ዳር ያዛችሁ? ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው ያለችው። በዚህ ወቅት ገዥው ፓርቲ የሚጫወተው ሚና እጅግ ወሳኝ ነው ብዬ አምናለሁ። እናምናለን። የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ደግሞ እንዲሁ ከፍተኛ ሚና አለው። ይህች አገር እኛ እንደሚመስለን ለምርጫ ከመሮጥ ብሔራዊ መግባባት ያስፈልጋታል ብለን እናምናለን። ለምን? ትላልቅ ፓርቲዎች በዚህ ምርጫ አይሳተፉም ማለት ይቻላል። ለምን? አሁን አዲስ አበባ ነው ያለሁት። ለምርጫው ጥቂት ጊዜ ነው የሚቀረው። ግን ይህን አታይም። ዛሬ እንደከዚህ ቀደሙ የምርጫ ፖስተሮችና ምልክቶች አይታዩም። ሕዝብ ደንታ አይሰጥም ለምርጫ ማለት ነው። ለምን? ብለን መጠየቅ አለብን። በሶማሌና በአፋር ጦርነት አለ። በአማራና በኦሮሞ ሽኩቻ አለ። በትግራይም ያለው ይኸው ነው። ይህ ሁሉ ነገር እያለ፤ ብሔራዊ ውይይት ተደርጎ ሳንስማማ ወደ ምርጫ መሮጣችን ወደ ከፋ ሁኔታ ይወስደናል ብለን እናምናለን። በሁሉም ነገር ባንስማማ በአንድ ነገር ቢያንስ በምርጫ ሂደትና ተሳታፊነት እንኳን ብንስማማ ይመረጣል ብዬ አምናለሁ። እኔ በግሌ አገሪቷ በከፋ፣ በከፋ ሁኔታ ላይ ነው ያለችው ብዬ አምናለሁ። ስለ ነገ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ እርግጠኛ አይደሉም? አይደለሁም። እኔንጃ ወደየት እየሄድን እንደሆነ?
https://www.bbc.com/amharic/news-56795580
5sports
ቦክሰኛው ማይክ ታይሰን አውሮፕላን ውስጥ ተሳፋሪን በቦክስ ዘረረ
የቀድሞው ባለ ከባድ ሚዛን ሻምፒዮና ማይክ ታይሰን አውሮፕላን ውስጥ አንድን ተሳፋሪ በቦክስ ደብድቧል፡፡ የታይሰን ቃል አቀባይ እንዳለው ታይሰን ግለሰቡን በቦክስ ለመምታት የተገደደው የውሃ ላስቲክ ስለወረወረበት ነው፡፡ ከአውሮፕላኑ ውስጥ የተቀረጸ ተንቀሳቃሽ ምሥል ማይክ ታይሰን ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደ ግለሰቡ በመሄድ ይህ ማንነቱ ለጊዜው ያልተለየን ግለሰብ በጡጫ ሲነርተው በከፊል ይታያል፡፡ ቃል አቀባዩ እንዳለው ታይሰን ለዚህ መጥፎ አጋጣሚ የተጋበዘው ተሳፋሪው በተደጋጋሚ ሳለስቸገረው ነው፡፡ ፖሊስ ከዚሁ ክስተት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን ሁለት ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡ አንዱ ግለሰብ በሳንፍራንሲስኮ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ሕክምና እየተደረገለት ሲሆን ጉዳቱ ለሕይወቱ አስጊ አይደለም ተብሏል፡፡ ፖሊስ በትክክል ምን ተከስቶ እንደነበረ ከተጎጂዎች በቂ መረጃን እንዳላገኘ የሳንፍራንሲስኮ ፖሊስ ቃል አቀባይና ባልደረባ ተናግራለች፡፡ በዚህም የተነሳ ምርመራው እንደሚቀጥል፣ ነገር ግን ለጊዜው የተያዙት ሁለት ሰዎችም ከእስር እንደተለቀቁ ገልጻለች፡፡ ፖሊስ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በዚህ ክስተት ውስጥ ይኑሩበት አይኑሩበት ገና እርግጠኛ መሆን አልቻለም፡፡ ይህ የማይክ ታይሰን የአውሮፕላን የቡጢ ክስተት የተፈጠረው ረቡዕ ዕለት ሲሆን አውሮፕላኑ ከሳንፍራንሲስኮ ወደ ፍሎሪዳ ለመጓዝ ገና ደንበኞችን በማሳፈር ላይ ሳለ ነበር፡፡ ክስተቱን ያሳያል የተባለው ተንቀሳቃሽ ምሥል የተቆራረጠና ታሪኩን ለመረዳት በቂ መረጃን የማይሰጥ ሲሆን ሆኖም ግን ግለሰቡ የውሃ ላስቲክ በማይክ ታይሰን ላይ ሲወረውርበት አያሳይም፡፡ ቲኤምዜድ፣የዕውቅ ሰዎችን ጉዳይ በመዘገብ የሚታወቅ ሚዲያ፣ እንዳለው ታይሰን በቅድሚያ ከዚህ ጸብ ውስጥ ከገባው ግለሰብ ጋር ፎቶ ለመነሳት ፈቅዶ ነበር፡፡ ነገር ግን ግለሰቡ ታይሰንን ያልተገባ ነገር እየተናገረ ትዕግስቱን ተፈታትኖታል፡፡ ማይክ ታይሰንም ግለሰቡን ‹ተረጋጋ› ሲል አስቀድሞ መልካም ምክርን ሰጥቶት ነበር፡፡ ማይክ ታይሰን ግለሰቡን በቡጢ ከደበደበው በኋላ ሰዎችን ለመገላገል ሲሞክሩ በተንቀሳቃሽ ምሥሉ ይታያል፡፡ በመጨረሻ ምሥሉ የተደብዳቢው ግንባር ደም በደም ሆኖ ያሳያል፡፡ ማይክ ታይሰን ለእንደዚህ ዓይነት ክስተቶች ሲጋለጥ የመጀመርያው አይደለም፡፡ እንደ አውሮጳዊያኑ በ1992 ዓ/ም ሴት በመድፈር ተወንጅሎ 3 ዓመት ተፈርዶበት ነበር፡፡ በ1997 ዓ/ም ደግሞ የተጋጣሚውን ሆሊፊልድን ጆሮ በመዘንጠሉ ከቦክስ ለጊዜው ገለል እንዲል መደረጉ ይታወሳል፡፡
ቦክሰኛው ማይክ ታይሰን አውሮፕላን ውስጥ ተሳፋሪን በቦክስ ዘረረ የቀድሞው ባለ ከባድ ሚዛን ሻምፒዮና ማይክ ታይሰን አውሮፕላን ውስጥ አንድን ተሳፋሪ በቦክስ ደብድቧል፡፡ የታይሰን ቃል አቀባይ እንዳለው ታይሰን ግለሰቡን በቦክስ ለመምታት የተገደደው የውሃ ላስቲክ ስለወረወረበት ነው፡፡ ከአውሮፕላኑ ውስጥ የተቀረጸ ተንቀሳቃሽ ምሥል ማይክ ታይሰን ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደ ግለሰቡ በመሄድ ይህ ማንነቱ ለጊዜው ያልተለየን ግለሰብ በጡጫ ሲነርተው በከፊል ይታያል፡፡ ቃል አቀባዩ እንዳለው ታይሰን ለዚህ መጥፎ አጋጣሚ የተጋበዘው ተሳፋሪው በተደጋጋሚ ሳለስቸገረው ነው፡፡ ፖሊስ ከዚሁ ክስተት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን ሁለት ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡ አንዱ ግለሰብ በሳንፍራንሲስኮ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ሕክምና እየተደረገለት ሲሆን ጉዳቱ ለሕይወቱ አስጊ አይደለም ተብሏል፡፡ ፖሊስ በትክክል ምን ተከስቶ እንደነበረ ከተጎጂዎች በቂ መረጃን እንዳላገኘ የሳንፍራንሲስኮ ፖሊስ ቃል አቀባይና ባልደረባ ተናግራለች፡፡ በዚህም የተነሳ ምርመራው እንደሚቀጥል፣ ነገር ግን ለጊዜው የተያዙት ሁለት ሰዎችም ከእስር እንደተለቀቁ ገልጻለች፡፡ ፖሊስ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በዚህ ክስተት ውስጥ ይኑሩበት አይኑሩበት ገና እርግጠኛ መሆን አልቻለም፡፡ ይህ የማይክ ታይሰን የአውሮፕላን የቡጢ ክስተት የተፈጠረው ረቡዕ ዕለት ሲሆን አውሮፕላኑ ከሳንፍራንሲስኮ ወደ ፍሎሪዳ ለመጓዝ ገና ደንበኞችን በማሳፈር ላይ ሳለ ነበር፡፡ ክስተቱን ያሳያል የተባለው ተንቀሳቃሽ ምሥል የተቆራረጠና ታሪኩን ለመረዳት በቂ መረጃን የማይሰጥ ሲሆን ሆኖም ግን ግለሰቡ የውሃ ላስቲክ በማይክ ታይሰን ላይ ሲወረውርበት አያሳይም፡፡ ቲኤምዜድ፣የዕውቅ ሰዎችን ጉዳይ በመዘገብ የሚታወቅ ሚዲያ፣ እንዳለው ታይሰን በቅድሚያ ከዚህ ጸብ ውስጥ ከገባው ግለሰብ ጋር ፎቶ ለመነሳት ፈቅዶ ነበር፡፡ ነገር ግን ግለሰቡ ታይሰንን ያልተገባ ነገር እየተናገረ ትዕግስቱን ተፈታትኖታል፡፡ ማይክ ታይሰንም ግለሰቡን ‹ተረጋጋ› ሲል አስቀድሞ መልካም ምክርን ሰጥቶት ነበር፡፡ ማይክ ታይሰን ግለሰቡን በቡጢ ከደበደበው በኋላ ሰዎችን ለመገላገል ሲሞክሩ በተንቀሳቃሽ ምሥሉ ይታያል፡፡ በመጨረሻ ምሥሉ የተደብዳቢው ግንባር ደም በደም ሆኖ ያሳያል፡፡ ማይክ ታይሰን ለእንደዚህ ዓይነት ክስተቶች ሲጋለጥ የመጀመርያው አይደለም፡፡ እንደ አውሮጳዊያኑ በ1992 ዓ/ም ሴት በመድፈር ተወንጅሎ 3 ዓመት ተፈርዶበት ነበር፡፡ በ1997 ዓ/ም ደግሞ የተጋጣሚውን ሆሊፊልድን ጆሮ በመዘንጠሉ ከቦክስ ለጊዜው ገለል እንዲል መደረጉ ይታወሳል፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-61195175
3politics
'ለኤርትራ ነጻነት 30 ዓመት ተዋደቅን፤ ለ30 ዓመት ዲሞክራሲን ጠበቅን፤ አልመጣም' የቀድሞው የቢቢሲ ትግርኛ አርታኢ
ኤርትራ ነጻነቷን ካገኘች 30 ዓመት ደፈነች። የቀድሞው የቢቢሲ ትግርኛ አርታኢ የነበረው ሳሙኤል ገብረሕይወት ለነጻነቱ ነፍጥ አንግበው ከተዋደቁ ኤትራዊያን አንዱ ነበረ። ስለ ትግሉ እና እንደ ጉም ስለተነነው ኤርትራዊያን የነጻነትና ዲሞክራሲ ተስፋ እንዲሁም አገሪቱ እንዴት በአምባገነን እጅ ስር እንደወደቀች እንዲህ ይተርካሉ። ለሰላሳ ዓመታት ነፍጥ አንስተን ለነጻነት ተዋጋን፣ እያንዳንዱ ቀንና ሰዓት በጦርነት የሚያልፍ ነበር። ስቃይንና መስዋዕት መሆንን ለመድነው። አብዛኞቻችን ሁለት ወይም ለሦስት ጊዜ ቆስለናል። ይህ ብርቅ አይደለም። እንደነገሩ ታክመን ወደ ሌላ ጦርነት እንዘምት ነበር። በሰሜን ኤርትራ ቃሮራ ግንባርን እንዴት እንደታደግን ይገርመኛል። በደቡብ ኤርትራ ዱሜራን እንዴት እንደተከላከልን ይደንቀኛል። ምሽግ ለምሽግ እየተሳብን፣ እዚያው እያደርን፣ ተራራ እየቧጠጥን፣ ከሸለቆ ሸለቆ እየዘለልን…። ብቻ እኔ ከዕድለኞቹ እመደባለሁ። 65 ሺህ ጓዶቻችን በጦርነቱ ሞተዋል። የነጻነት ግንባሩን የተቀላቀልኩት በፈረንጆች 1982 ላይ ገና በ16 ዓመቴ ነበር። ስለነጻነት ተዋጊ ኤርትራዊያን ብዙ እሰማ ነበር። ቁምጣቸው፣ ረዥም ጸጉራቸው፣ የሚይዙት ኤኬ 47 ጠመንጃ …፣ ይህ ሁሉ ታሪካቸው ያጓጓኝ ነበር። በአራግ ሸለቆ ለጥቂት ወራት ስልጠና ተሰጠኝ። እንዴት ጥቃት መሰንዘር እንደምንችልና እንዴት ማፈግፈግ እንደሚቻል ተማርን። እንዴት ራሳችንን ከአካባቢው ጋር ማመሳሰል እንደምንችል፣ እንዴት መደበቅ እንደምንችል፣ እንዴት ቦምብ ፈቶ መግጠም፣ ነቅሎ መጣል እንደሚቻል፣ አርፒጂ መሣሪያ አጠቃቀምን ሁሉ ሰለጠንን። ስልጠናችን መጥፎ የሚባል አልነበረም። ጎን ለጎን ደግሞ የፖለቲካ ትምህርት እንደወስድ ነበር። ከዚህ መሀል እንዴት ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ማቋቋም እንደምንችል ጭምር ተምረናል። ከዚህ ስልጠና በኋላ በበርካታ ጦርነቶች ውስጥ ተሳትፊያለሁ። መደምደሚያው የነበረው በ1990 (እአአ) በምጽዋ ወደብ ላይ የተደረገው 'የፈንቅል ዘመቻ' ነበር። ያ ድል እጅግ ወሳኝ ነበር። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን ከኤርትራ እንዲወጣም ያስገደደ ቁልፍ ወታደራዊ ድል ነበር። ያን ጊዜ ያለማቋረጥ ለ72 ሰዓታት ተዋግተናል። እጅግ ወሳኝ የነበረችውን ምጽዋን ለመያዝ ያልሆነው የለም ማለት ይቻላል። ከዚያ በኋላ ደግሞ ለመከላከል 100 ኪሎ ሜትር ምሽግ ቆፍረን ከአንድ ዓመት በላይ ቆይተናል። በዚህ ውጊያ ጭንቅላቴ ላይ እንዲሁም እጄ ላይ ቆስያለሁ። ከዚያ ሆስፒታል ታክሜ ዳንኩ። ታዲያ ወዲያውኑ ወደ ውጊያ ነበር የተመለስኩት። በ1980ዎቹ መጨረሻ ወደ ኪነትና ባሕል ክፍል ተዛወርኩ። የዚህ ክፍል ዋና ዓላማ ወታደሩን በሙዚቃና ድራማ ሞራሉን ከፍ ማድረግ፣ ማነሳሳት ነበር። በ1991 (እአአ) ከምጽዋ ቅርብ ርቀት በዳሕላክ ደሴት ላይ ነበርን። ዳሕላክ ሳለን ነበር በሕይወታችን እጅግ ጣፋጩን ዜና የሰማነው። ኤርትራ ነጻነቷን እንደተቀዳጀች ተነገረን። የፈንጠዚያ ቀናት በደስታ ሰክረን በጀልባ ወደ ምጽዋ ተጓዝን። እዚያ ስንደርስ ከባድ ተሸከርካሪ ላይ ተጭነን ወደ ዋና ከተማ አሥመራ ጉዞ ጀመርን። ጉዞው ሦስት ሰዓታትን የፈጀ ነበር። የኢትዮጵያ ሠራዊት ደቡባዊ ቀጠናን አለፍነው። ሰው የሚባል አልነበረም። የኢትዮጵያ ወታደሮች ጥለውት ሄደዋል። በአሥመራ ውስጥ ሕልም የሚመስል አውድ ነበር። ነዋሪዎች እኛን የነጻነት ታጋዮችን ለመቀበል ጨርቄን ማቄን ሳይሉ አደባባይ ወጥተው ነበር። በጓይላ ጭፈራ ራሳቸውን ስተው ነበር። ጎዳናው በሙሉ ሕዝብ ፈሶበት አስታውሳለሁ። ይህ በአሥመራ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ከተሞችና መንደሮችም የታየ ኩነት ነበር። ይህ ቀን ከመምጣቱ በፊት አሥመራ ሙሉ በሙሉ ጭንቅ ውስጥ ነበረች። አየር ማረፊያው በተከታታይ በተኩስ ሲናጥ ነበር የሰነበተው። ጥብቅ ሰዓት እላፊም ታውጆ ነበር። ልክ በግንቦት 24 (እአአ) ሁሉ ነገር ተለወጠ። እናቶች የጣዱትን ጀበና ትተው፣ የለኮሱትን ሞጎጎ እንጀራ መጋገሪያቸውን ጥለው፣ የቡና ሥነ ሥርዓታቸውን ጣጥለው ግልብጥ ብለው አደባባይ ወጥተው ነበር። ይህም እኛን ታጋዮችን ለመቀበል ነበር። ብዙ ኤርትራውያን የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ይታዩ ነበር። ወጣቶች እየዘለሉ ታንክ ላይ ይወጡ እንደነበረና የዘንባባ ዝንጣፊ እያውለበለቡ ሲቀበሉንም አስታውሳለሁ። ይህ ፈንጠዝያ ለቀናት ቀጠለ። ምሽቶቹም ደማቅ ነበሩ። በእርግጥ በዚህ ደማቅ ስሜት መሀል ጭንቅም ነበረ። ወላጆች የልጆቻቸውን ፎቶ ይዘው በመውጣት በሕይወት ይኖሩ እንደሁ ይጠይቁ ነበር። "ልጄ ተርፎልኝ ይሆን? ልጄ ሞታ ይሆን?" የሚል የማያባራ ጥያቄ። በኛ ምድብ ገድለና አባየይ የሚባሉ ጓዶች ነበሩ። ሁለቱ ጓዶች ፊት ለፊት በመኪና ላይ ተጭነው ቤተሰባቸውን ባዩ ጊዜ የሆኑት ትዝ ይለኛል፤ ሲጮኹ፣ ሲስቁ፣ የደስታ እንባ ሲያነቡ። የገድለ አባት "ልጄን አገኘሁት! ልጄን አገኘሁት!" እያለ ወደኛ መኪና ሲሮጥ ትዝ ይለኛል። አባየይ ደግሞ ሴት ታጋይ ነበረች። ጋቢና ነበር የተቀመጠችው። የባለቤቷን እናት ስታይ ጊዜ ድንገት እየሄደ ከነበረ መኪና ዘላ ልትወርድና ራሷን ለከፍተኛ አደጋ ልታጋልጥ ስትል ነበር በተአምር የዳነችው። በኋላ ላይ በአዛዦቻችን ፈቃድ ተሰጠን፤ ፈቃዱ ወጥተን ቤተሰባችንን እንድናገኝ ነበር። በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ቤተሰብን ማግኘት ቀልድ አልነበረም። ለእነዚያ ሁሉ ዓመታት የተለዩትን ማግኘት እንዲህ የዋዛ አልነበረም። ሆኖም ብዙዎቻችን ዘመድ አላጣንም። በዚያ ቅጽበት ሁላችንም እናስብ የነበረው ከዚህ ሁሉ በኋላ ኤርትራ በልጽጋ፣ ችግር ከኤርትራ ምድር ጠፍቶ እያንዳንዱ ኤርትራዊ በደስታና በፍሰሐ መኖር ይጀምራል የሚል ነበር። ነገር ግን ይህ ተስፋችን እንደ ጉም ሊተን ብዙ ጊዜ አልወሰደበትም። የነበረንን ሁሉ ሰጠን፣ ለነጻነት ስንል። ወጣትነታችንን፣ ሕይወታችንን…። ብዙዎቻችን ከነጻነት በኋላ ከውትድርና ተሰናብተን ቤተሰባችንን ተቀላቅለን፣ ትምህርታችንን ቀጥለን፣ ወደ ግል ሥራና ኑሮ ለመመለስ ነበር ዕቅዳችን። ሆኖም ሠራዊቱን እንኳ ለመልቀቅ እንደማንችል ስናውቅ ተደነቅን። ወታደራዊ አዛዦቻችን የፖለቲካ መሪዎች ሆኑ። አዲሲቷ አገር በእጇ ምንም ቤሳቤስቲ እንደሌላት ነገሩን። ኤርትራ ያላት ብቸኛ ሀብት የያዝናቸው የጦር መሣሪያዎች እንደሆኑ ተነገረን። ከዚያ ሁሉ የጦርነት ፍዳና መከራ በኋላ የቀድሞ ተዋጊዎች ቀበቷችንን ይበልጥ እንድናጠብቅ በድጋሚ አረዱን። ማንኛውንም ሥራ ያለ ክፍያ እንድንምንሰራ ነገሩን። ምግብ ብቻ ይሰጡናል። በነጻ እናገለግላለን። ይህ ሁኔታ ለሁለት ዓመት ቀጠለ። ከዚያ በኋላ ነው ትንሽ ገንዘብ ማግኘት የጀመርነው። በትግሉ ጊዜ ልክ እንደ አንድ ቤተሰብ ይተሳሰቡ የነበሩ ታጋዮች የመሪዎቹን እውነተኛ ባሕሪ ሲረዱ ተከፉ። ብዙዎቹ ወታደራዊ መሪዎች አገሪቱ ልክ ነጻ ከመውጣቷ አስረሽ ምቺው ውስጥ ገብተው ነበር። በርካታ ታላላቅ አመራሮች በየመሸታ ቤቱ ይታዩ ነበር። ራሳቸውን እስኪስቱ ይጠጡም ነበር። በዚህ ወቅት ታጋዩ ኑሮው አለት ሆኖበት ነበር። የዕዝ ሰንሰለቱ እየላላ፣ መደበኛ ስብሰባዎች እየተረሱ መጡ። መደበኛ ታጋዮች ነገሮች ከዛሬ ነገ ይስተካከላሉ ሲሉ ተስፋ አደረጉ፤ ገፋ ብለው ጠበቁ፣ ጠየቁ። አዲስ ነገር አልነበረም። ከጎረቤት ጋር አዲስ ጦርነት እንደ አውሮፓውያኑ በ1993፣ የኤርትራ ነጻነት 2ኛ ዓመት ሊከበር ዋዜማ፣ የቀድሞ ተዋጊዎች አመጹ። መሪዎቻቸው ብሶታቸውን እንዲያዳምጡም ተማጸኑ። መሪዎቻቸው ታላቅ ስብሰባ በአሥመራ ስታዲየም እንዲጠሩ አስገደዷቸው። የተሰጠው ምላሽ ግን፣ "ችግራችሁ ይገባናል፣ የተለደመ ችግር ነው፤ ሁሉንም በቅርብ እንፈታዋለን" የሚል ነበር። ልክ ይህ ስብሰባ እንዳበቃ ታዲያ መሪዎቹ የአመጹን አስተባባሪዎች አፍነው ወሰዱ። አንድ በአንድ። በጥቂት ጊዜ ውስጥ ከአንድ ዓመት እስከ 15 ዓመት እንደተፈረደባቸው ሰማን። የታጋዩን ችግር በይፋ በመናገራቸው ትልቅ ዋጋ ከፈሉ። ብዙ "ሰዎች በቃ መሪዎቻችን ወደ አምባገነንነት ሊለወጡ ነው" ማለት ጀመሩ። ሌሎች ግን ትንሽ መታገስና ማየት እንደሚገባ መከሩ። ኤርትራ እያረቀቀችው ያለው ሕገ መንግሥት ሲጠናቀቅ አገራችን ወደ ዲሞክራሲ እንደምታመራ ተነገረን። ይህ ሁሉ ግን መና ቀረ። ኤርትራ በአንድ ፓርቲ የምትመራ፣ ምርጫ አካሄዳ የማታውቅ አገር ሆና ቀረች። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለን ኤርትራ ከሁሉም ጎረቤቶቿ ጋር ጦርነት ውስጥ ገባች። ከየመን በ1995፣ ከሱዳን በ1996፣ ከኢትዮጵያ በ1998 እና ከጂቡቲ ጋር በ2008። አዲሷ አገራችን ኤርትራ ሌሎች ተጨማሪ 10ሺህ ወጣቶቿን ሕይወት አስቀጠፈች። አሁን የኤርትራ ወታደሮች ከነጻነት በኋላ በ5ኛው ዙር ጦርነት ውስጥ ይገኛሉ። አሁን የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ነው። ከህወሓት ጋር ጦርነት ላይ ናቸው። ህወሓት ኤርትራ ነጻነቷን ባወጀች ጊዜ ሥልጣን ላይ የነበረ ነው። ከ1998 እስከ 2000 ከኢትዮጵያ ጋር በተደረገው ጦርነት ወቅትም የነበረ ነው። ከነጻነት በኋላ በነበረው ጊዜ ከገዢው ፓርቲ የባሕል ክፍል ውስጥ ገባሁ። ለታጋዮች የሚገባቸውን ሞገስ ለማሰጠት ብሎም አገሪቱን ለመገንባት ብዙ ሥራ እሠራለሁ በሚል ነበር። በርካታ ተውኔቶችን፣ ሙዚቃዎችን ደረስኩኝ። ተሳትፌባቸዋለሁም። ተወዳጇ ሔለን መለስ 'ምጽዋ' የሚለውን የኔን ሙዚቃ ተጫወተችው። ሙዚቃው 'ምጽዋ ወድ ልጆችሽ የት ገቡ?' የሚል ነበር። ለውጥ አይቀሬ ነው ትንሽም ቢሆን ጭል ጭል ትል የነበረችው የፖለቲካ ምህዳር ተስፋ የኢትዮጵያ-ኤርትራ ጦርነት ማግስት ከሰመች። መንግሥት ልወረር ነው የሚል ሥነልቦና በሕዝቡ ዘንድ ገዢ ሐሳብ እንዲሆን አደረገ። ይህ ጦርነት በጠረጴዛ ዙርያ ንግግር ብቻ እንዲቀር ማድረግ ይቻል እንደነበር ብዙዎች ያምናሉ። በመስከረም 2001 (እአአ) ደግሞ መንግሥት ያልተጠበቀ እርምጃ እንዲወሰድ አዘዘ። አሥራ አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና መካከለኛ ካድሬዎች ድንገት ዘብጥያ ወረዱ። ለዚህ የተዳረጉት ታዲያ አንዳንድ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ስለጠየቁ ብቻ ነው። ከዚያች ዕለት ጀምሮ ሰዎቹ የት እንዳሉ ምንም አልተሰማም። እነዚህን መሻሻል እንዲደረግ የጠየቁ ባለሥልጣናትን ያናገሩ፣ ስለነሱ የጻፉ 11 ጋዜጠኞችም ታስረዋል። ከነዚህ መሐል ወዳጄና ጓደኛዬ ስዩም ይገኝበታል። ስዩም ያኔ በድል ስንገባ ፎቶ ሲያነሳ የነበረ ልጅ ነው። እነዚህ ሁሉ እስረኞች አንዳቸውም ፍርድ ቤት አልቀረቡም። አንዳቸውም ያሉበት አይታወቅም። ኤርትራ አሁንም የአንድ ፓርቲ አገር ናት። ከነጻነት ወዲህ ለ30 ዓመት ምርጫ የሚባል ነገር አድርጋ አታውቅም። ነጻ ፕሬስ የለም። ነጻ አደረጃጀት የለም። ሁሉም ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም ሆኑ የአገር ውስጥ ሲቪክ ድርጅቶች ታግደዋል። ይፋ የሚደረጉ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከነጻነት ወዲህ በአገሪቱ ውስጥ የጤናና የትምህርት አገልግሎት እንደተሻሻሉ ያሳያሉ። ይህን ማመን ግን ከባድ ነው። ካለው ጥቂት የሥራ ዕድል እና አስገዳጅ እንዲሁም ክፍያ አልባ የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ጋር ተያይዞ በርካታ ወጣቶች አገሪቱን እየለቀቁ ነው። በርካታ ወጣቶች በሌሎች የአፍሪካ አገሮችና በአውሮፓ ተጠልለው ይኖራሉ። ይህ ሁሉ ሆኖ ግን አሁንም ብዙዎቻችን ተስፋ አልቆረጥንም። ለውጥ አይቀሬ እንደሆነ በጽኑ እናምናለን። ኤርትራ አንድ ቀን በሰማዕታት ቃል የተገባላትን የዲሞክራሲ ሕልም ትኖረዋለች።
'ለኤርትራ ነጻነት 30 ዓመት ተዋደቅን፤ ለ30 ዓመት ዲሞክራሲን ጠበቅን፤ አልመጣም' የቀድሞው የቢቢሲ ትግርኛ አርታኢ ኤርትራ ነጻነቷን ካገኘች 30 ዓመት ደፈነች። የቀድሞው የቢቢሲ ትግርኛ አርታኢ የነበረው ሳሙኤል ገብረሕይወት ለነጻነቱ ነፍጥ አንግበው ከተዋደቁ ኤትራዊያን አንዱ ነበረ። ስለ ትግሉ እና እንደ ጉም ስለተነነው ኤርትራዊያን የነጻነትና ዲሞክራሲ ተስፋ እንዲሁም አገሪቱ እንዴት በአምባገነን እጅ ስር እንደወደቀች እንዲህ ይተርካሉ። ለሰላሳ ዓመታት ነፍጥ አንስተን ለነጻነት ተዋጋን፣ እያንዳንዱ ቀንና ሰዓት በጦርነት የሚያልፍ ነበር። ስቃይንና መስዋዕት መሆንን ለመድነው። አብዛኞቻችን ሁለት ወይም ለሦስት ጊዜ ቆስለናል። ይህ ብርቅ አይደለም። እንደነገሩ ታክመን ወደ ሌላ ጦርነት እንዘምት ነበር። በሰሜን ኤርትራ ቃሮራ ግንባርን እንዴት እንደታደግን ይገርመኛል። በደቡብ ኤርትራ ዱሜራን እንዴት እንደተከላከልን ይደንቀኛል። ምሽግ ለምሽግ እየተሳብን፣ እዚያው እያደርን፣ ተራራ እየቧጠጥን፣ ከሸለቆ ሸለቆ እየዘለልን…። ብቻ እኔ ከዕድለኞቹ እመደባለሁ። 65 ሺህ ጓዶቻችን በጦርነቱ ሞተዋል። የነጻነት ግንባሩን የተቀላቀልኩት በፈረንጆች 1982 ላይ ገና በ16 ዓመቴ ነበር። ስለነጻነት ተዋጊ ኤርትራዊያን ብዙ እሰማ ነበር። ቁምጣቸው፣ ረዥም ጸጉራቸው፣ የሚይዙት ኤኬ 47 ጠመንጃ …፣ ይህ ሁሉ ታሪካቸው ያጓጓኝ ነበር። በአራግ ሸለቆ ለጥቂት ወራት ስልጠና ተሰጠኝ። እንዴት ጥቃት መሰንዘር እንደምንችልና እንዴት ማፈግፈግ እንደሚቻል ተማርን። እንዴት ራሳችንን ከአካባቢው ጋር ማመሳሰል እንደምንችል፣ እንዴት መደበቅ እንደምንችል፣ እንዴት ቦምብ ፈቶ መግጠም፣ ነቅሎ መጣል እንደሚቻል፣ አርፒጂ መሣሪያ አጠቃቀምን ሁሉ ሰለጠንን። ስልጠናችን መጥፎ የሚባል አልነበረም። ጎን ለጎን ደግሞ የፖለቲካ ትምህርት እንደወስድ ነበር። ከዚህ መሀል እንዴት ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ማቋቋም እንደምንችል ጭምር ተምረናል። ከዚህ ስልጠና በኋላ በበርካታ ጦርነቶች ውስጥ ተሳትፊያለሁ። መደምደሚያው የነበረው በ1990 (እአአ) በምጽዋ ወደብ ላይ የተደረገው 'የፈንቅል ዘመቻ' ነበር። ያ ድል እጅግ ወሳኝ ነበር። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን ከኤርትራ እንዲወጣም ያስገደደ ቁልፍ ወታደራዊ ድል ነበር። ያን ጊዜ ያለማቋረጥ ለ72 ሰዓታት ተዋግተናል። እጅግ ወሳኝ የነበረችውን ምጽዋን ለመያዝ ያልሆነው የለም ማለት ይቻላል። ከዚያ በኋላ ደግሞ ለመከላከል 100 ኪሎ ሜትር ምሽግ ቆፍረን ከአንድ ዓመት በላይ ቆይተናል። በዚህ ውጊያ ጭንቅላቴ ላይ እንዲሁም እጄ ላይ ቆስያለሁ። ከዚያ ሆስፒታል ታክሜ ዳንኩ። ታዲያ ወዲያውኑ ወደ ውጊያ ነበር የተመለስኩት። በ1980ዎቹ መጨረሻ ወደ ኪነትና ባሕል ክፍል ተዛወርኩ። የዚህ ክፍል ዋና ዓላማ ወታደሩን በሙዚቃና ድራማ ሞራሉን ከፍ ማድረግ፣ ማነሳሳት ነበር። በ1991 (እአአ) ከምጽዋ ቅርብ ርቀት በዳሕላክ ደሴት ላይ ነበርን። ዳሕላክ ሳለን ነበር በሕይወታችን እጅግ ጣፋጩን ዜና የሰማነው። ኤርትራ ነጻነቷን እንደተቀዳጀች ተነገረን። የፈንጠዚያ ቀናት በደስታ ሰክረን በጀልባ ወደ ምጽዋ ተጓዝን። እዚያ ስንደርስ ከባድ ተሸከርካሪ ላይ ተጭነን ወደ ዋና ከተማ አሥመራ ጉዞ ጀመርን። ጉዞው ሦስት ሰዓታትን የፈጀ ነበር። የኢትዮጵያ ሠራዊት ደቡባዊ ቀጠናን አለፍነው። ሰው የሚባል አልነበረም። የኢትዮጵያ ወታደሮች ጥለውት ሄደዋል። በአሥመራ ውስጥ ሕልም የሚመስል አውድ ነበር። ነዋሪዎች እኛን የነጻነት ታጋዮችን ለመቀበል ጨርቄን ማቄን ሳይሉ አደባባይ ወጥተው ነበር። በጓይላ ጭፈራ ራሳቸውን ስተው ነበር። ጎዳናው በሙሉ ሕዝብ ፈሶበት አስታውሳለሁ። ይህ በአሥመራ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ከተሞችና መንደሮችም የታየ ኩነት ነበር። ይህ ቀን ከመምጣቱ በፊት አሥመራ ሙሉ በሙሉ ጭንቅ ውስጥ ነበረች። አየር ማረፊያው በተከታታይ በተኩስ ሲናጥ ነበር የሰነበተው። ጥብቅ ሰዓት እላፊም ታውጆ ነበር። ልክ በግንቦት 24 (እአአ) ሁሉ ነገር ተለወጠ። እናቶች የጣዱትን ጀበና ትተው፣ የለኮሱትን ሞጎጎ እንጀራ መጋገሪያቸውን ጥለው፣ የቡና ሥነ ሥርዓታቸውን ጣጥለው ግልብጥ ብለው አደባባይ ወጥተው ነበር። ይህም እኛን ታጋዮችን ለመቀበል ነበር። ብዙ ኤርትራውያን የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ይታዩ ነበር። ወጣቶች እየዘለሉ ታንክ ላይ ይወጡ እንደነበረና የዘንባባ ዝንጣፊ እያውለበለቡ ሲቀበሉንም አስታውሳለሁ። ይህ ፈንጠዝያ ለቀናት ቀጠለ። ምሽቶቹም ደማቅ ነበሩ። በእርግጥ በዚህ ደማቅ ስሜት መሀል ጭንቅም ነበረ። ወላጆች የልጆቻቸውን ፎቶ ይዘው በመውጣት በሕይወት ይኖሩ እንደሁ ይጠይቁ ነበር። "ልጄ ተርፎልኝ ይሆን? ልጄ ሞታ ይሆን?" የሚል የማያባራ ጥያቄ። በኛ ምድብ ገድለና አባየይ የሚባሉ ጓዶች ነበሩ። ሁለቱ ጓዶች ፊት ለፊት በመኪና ላይ ተጭነው ቤተሰባቸውን ባዩ ጊዜ የሆኑት ትዝ ይለኛል፤ ሲጮኹ፣ ሲስቁ፣ የደስታ እንባ ሲያነቡ። የገድለ አባት "ልጄን አገኘሁት! ልጄን አገኘሁት!" እያለ ወደኛ መኪና ሲሮጥ ትዝ ይለኛል። አባየይ ደግሞ ሴት ታጋይ ነበረች። ጋቢና ነበር የተቀመጠችው። የባለቤቷን እናት ስታይ ጊዜ ድንገት እየሄደ ከነበረ መኪና ዘላ ልትወርድና ራሷን ለከፍተኛ አደጋ ልታጋልጥ ስትል ነበር በተአምር የዳነችው። በኋላ ላይ በአዛዦቻችን ፈቃድ ተሰጠን፤ ፈቃዱ ወጥተን ቤተሰባችንን እንድናገኝ ነበር። በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ቤተሰብን ማግኘት ቀልድ አልነበረም። ለእነዚያ ሁሉ ዓመታት የተለዩትን ማግኘት እንዲህ የዋዛ አልነበረም። ሆኖም ብዙዎቻችን ዘመድ አላጣንም። በዚያ ቅጽበት ሁላችንም እናስብ የነበረው ከዚህ ሁሉ በኋላ ኤርትራ በልጽጋ፣ ችግር ከኤርትራ ምድር ጠፍቶ እያንዳንዱ ኤርትራዊ በደስታና በፍሰሐ መኖር ይጀምራል የሚል ነበር። ነገር ግን ይህ ተስፋችን እንደ ጉም ሊተን ብዙ ጊዜ አልወሰደበትም። የነበረንን ሁሉ ሰጠን፣ ለነጻነት ስንል። ወጣትነታችንን፣ ሕይወታችንን…። ብዙዎቻችን ከነጻነት በኋላ ከውትድርና ተሰናብተን ቤተሰባችንን ተቀላቅለን፣ ትምህርታችንን ቀጥለን፣ ወደ ግል ሥራና ኑሮ ለመመለስ ነበር ዕቅዳችን። ሆኖም ሠራዊቱን እንኳ ለመልቀቅ እንደማንችል ስናውቅ ተደነቅን። ወታደራዊ አዛዦቻችን የፖለቲካ መሪዎች ሆኑ። አዲሲቷ አገር በእጇ ምንም ቤሳቤስቲ እንደሌላት ነገሩን። ኤርትራ ያላት ብቸኛ ሀብት የያዝናቸው የጦር መሣሪያዎች እንደሆኑ ተነገረን። ከዚያ ሁሉ የጦርነት ፍዳና መከራ በኋላ የቀድሞ ተዋጊዎች ቀበቷችንን ይበልጥ እንድናጠብቅ በድጋሚ አረዱን። ማንኛውንም ሥራ ያለ ክፍያ እንድንምንሰራ ነገሩን። ምግብ ብቻ ይሰጡናል። በነጻ እናገለግላለን። ይህ ሁኔታ ለሁለት ዓመት ቀጠለ። ከዚያ በኋላ ነው ትንሽ ገንዘብ ማግኘት የጀመርነው። በትግሉ ጊዜ ልክ እንደ አንድ ቤተሰብ ይተሳሰቡ የነበሩ ታጋዮች የመሪዎቹን እውነተኛ ባሕሪ ሲረዱ ተከፉ። ብዙዎቹ ወታደራዊ መሪዎች አገሪቱ ልክ ነጻ ከመውጣቷ አስረሽ ምቺው ውስጥ ገብተው ነበር። በርካታ ታላላቅ አመራሮች በየመሸታ ቤቱ ይታዩ ነበር። ራሳቸውን እስኪስቱ ይጠጡም ነበር። በዚህ ወቅት ታጋዩ ኑሮው አለት ሆኖበት ነበር። የዕዝ ሰንሰለቱ እየላላ፣ መደበኛ ስብሰባዎች እየተረሱ መጡ። መደበኛ ታጋዮች ነገሮች ከዛሬ ነገ ይስተካከላሉ ሲሉ ተስፋ አደረጉ፤ ገፋ ብለው ጠበቁ፣ ጠየቁ። አዲስ ነገር አልነበረም። ከጎረቤት ጋር አዲስ ጦርነት እንደ አውሮፓውያኑ በ1993፣ የኤርትራ ነጻነት 2ኛ ዓመት ሊከበር ዋዜማ፣ የቀድሞ ተዋጊዎች አመጹ። መሪዎቻቸው ብሶታቸውን እንዲያዳምጡም ተማጸኑ። መሪዎቻቸው ታላቅ ስብሰባ በአሥመራ ስታዲየም እንዲጠሩ አስገደዷቸው። የተሰጠው ምላሽ ግን፣ "ችግራችሁ ይገባናል፣ የተለደመ ችግር ነው፤ ሁሉንም በቅርብ እንፈታዋለን" የሚል ነበር። ልክ ይህ ስብሰባ እንዳበቃ ታዲያ መሪዎቹ የአመጹን አስተባባሪዎች አፍነው ወሰዱ። አንድ በአንድ። በጥቂት ጊዜ ውስጥ ከአንድ ዓመት እስከ 15 ዓመት እንደተፈረደባቸው ሰማን። የታጋዩን ችግር በይፋ በመናገራቸው ትልቅ ዋጋ ከፈሉ። ብዙ "ሰዎች በቃ መሪዎቻችን ወደ አምባገነንነት ሊለወጡ ነው" ማለት ጀመሩ። ሌሎች ግን ትንሽ መታገስና ማየት እንደሚገባ መከሩ። ኤርትራ እያረቀቀችው ያለው ሕገ መንግሥት ሲጠናቀቅ አገራችን ወደ ዲሞክራሲ እንደምታመራ ተነገረን። ይህ ሁሉ ግን መና ቀረ። ኤርትራ በአንድ ፓርቲ የምትመራ፣ ምርጫ አካሄዳ የማታውቅ አገር ሆና ቀረች። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለን ኤርትራ ከሁሉም ጎረቤቶቿ ጋር ጦርነት ውስጥ ገባች። ከየመን በ1995፣ ከሱዳን በ1996፣ ከኢትዮጵያ በ1998 እና ከጂቡቲ ጋር በ2008። አዲሷ አገራችን ኤርትራ ሌሎች ተጨማሪ 10ሺህ ወጣቶቿን ሕይወት አስቀጠፈች። አሁን የኤርትራ ወታደሮች ከነጻነት በኋላ በ5ኛው ዙር ጦርነት ውስጥ ይገኛሉ። አሁን የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ነው። ከህወሓት ጋር ጦርነት ላይ ናቸው። ህወሓት ኤርትራ ነጻነቷን ባወጀች ጊዜ ሥልጣን ላይ የነበረ ነው። ከ1998 እስከ 2000 ከኢትዮጵያ ጋር በተደረገው ጦርነት ወቅትም የነበረ ነው። ከነጻነት በኋላ በነበረው ጊዜ ከገዢው ፓርቲ የባሕል ክፍል ውስጥ ገባሁ። ለታጋዮች የሚገባቸውን ሞገስ ለማሰጠት ብሎም አገሪቱን ለመገንባት ብዙ ሥራ እሠራለሁ በሚል ነበር። በርካታ ተውኔቶችን፣ ሙዚቃዎችን ደረስኩኝ። ተሳትፌባቸዋለሁም። ተወዳጇ ሔለን መለስ 'ምጽዋ' የሚለውን የኔን ሙዚቃ ተጫወተችው። ሙዚቃው 'ምጽዋ ወድ ልጆችሽ የት ገቡ?' የሚል ነበር። ለውጥ አይቀሬ ነው ትንሽም ቢሆን ጭል ጭል ትል የነበረችው የፖለቲካ ምህዳር ተስፋ የኢትዮጵያ-ኤርትራ ጦርነት ማግስት ከሰመች። መንግሥት ልወረር ነው የሚል ሥነልቦና በሕዝቡ ዘንድ ገዢ ሐሳብ እንዲሆን አደረገ። ይህ ጦርነት በጠረጴዛ ዙርያ ንግግር ብቻ እንዲቀር ማድረግ ይቻል እንደነበር ብዙዎች ያምናሉ። በመስከረም 2001 (እአአ) ደግሞ መንግሥት ያልተጠበቀ እርምጃ እንዲወሰድ አዘዘ። አሥራ አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና መካከለኛ ካድሬዎች ድንገት ዘብጥያ ወረዱ። ለዚህ የተዳረጉት ታዲያ አንዳንድ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ስለጠየቁ ብቻ ነው። ከዚያች ዕለት ጀምሮ ሰዎቹ የት እንዳሉ ምንም አልተሰማም። እነዚህን መሻሻል እንዲደረግ የጠየቁ ባለሥልጣናትን ያናገሩ፣ ስለነሱ የጻፉ 11 ጋዜጠኞችም ታስረዋል። ከነዚህ መሐል ወዳጄና ጓደኛዬ ስዩም ይገኝበታል። ስዩም ያኔ በድል ስንገባ ፎቶ ሲያነሳ የነበረ ልጅ ነው። እነዚህ ሁሉ እስረኞች አንዳቸውም ፍርድ ቤት አልቀረቡም። አንዳቸውም ያሉበት አይታወቅም። ኤርትራ አሁንም የአንድ ፓርቲ አገር ናት። ከነጻነት ወዲህ ለ30 ዓመት ምርጫ የሚባል ነገር አድርጋ አታውቅም። ነጻ ፕሬስ የለም። ነጻ አደረጃጀት የለም። ሁሉም ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም ሆኑ የአገር ውስጥ ሲቪክ ድርጅቶች ታግደዋል። ይፋ የሚደረጉ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከነጻነት ወዲህ በአገሪቱ ውስጥ የጤናና የትምህርት አገልግሎት እንደተሻሻሉ ያሳያሉ። ይህን ማመን ግን ከባድ ነው። ካለው ጥቂት የሥራ ዕድል እና አስገዳጅ እንዲሁም ክፍያ አልባ የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ጋር ተያይዞ በርካታ ወጣቶች አገሪቱን እየለቀቁ ነው። በርካታ ወጣቶች በሌሎች የአፍሪካ አገሮችና በአውሮፓ ተጠልለው ይኖራሉ። ይህ ሁሉ ሆኖ ግን አሁንም ብዙዎቻችን ተስፋ አልቆረጥንም። ለውጥ አይቀሬ እንደሆነ በጽኑ እናምናለን። ኤርትራ አንድ ቀን በሰማዕታት ቃል የተገባላትን የዲሞክራሲ ሕልም ትኖረዋለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-57222401
0business
ኤርትራ፡ የአሰብና ምጽዋ ወደቦች ምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ?
ስድሳ ከመቶ በላይ የዓለም ነዳጅ በሚመላለስበት የንግድ መስመር ቀይ ባሕር በኤርትራ ውስጥ ከሰሜን ወደ ደቡብ 1 ሺህ ኪሎ ሜትር ይሸፍናል። ኤርትራ ከ300 በላይ ትላልቅና አነስተኛ ደሴቶች አሏት። በዚህ ምጽዋና አሰብ ተብለው የሚጠሩ ሁለት የወደብ ከተሞች አሉ። ወደቦቹ ከ60 ዓመታት በፊት ብዙ የወጪና የገቢ ንግድ የሚመላለስባቸው ነበሩ። በኤርትራ ትጥቅ ትግል ወቅት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ወደቦች ጥገና ተደርጎላቸው ከ1983 እስከ 1990 ድረስ አገልግሎት ይሰጡ ነበር። የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ግን ኢትዮጵያ የጅቡቲ ወደብን መጠቀም ጀመረች። በዚህ ምክንያት ተዳክመው የቆዩት ወደቦች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ዳግም መነቃቃት ያሳያሉ ተብሎ ተስፋ ተጥሎባቸዋል። በአሁኑ ወቅት በንግድ መርከብ የሚሰራው የኤርትራ ባሕረኞች ማኅበር አባል የሆነው ካፒቴን መሪሕ ሃብተ የኤርትራ ወደቦችን ከባሕር ትራንስፖርት፣ ከአሳ፣ ከቱሪዝምና ከማዕድን አንጻር ከፋፍሎ ማየት ይቻላል ይላል። የአሰብና የምጽዋ ወደቦች እቃዎችን የመጫንና የማራገፍ፣ የመጋዝን እና ሌሎች አገልግሎቶች የሚሰጡ ሲሆን በአሰብ እስከ 94 በመቶ የሚገባውና የሚወጣው ንብረት የኢትዮጵያ ንግድ እንደነበረ ቺፍ ኢንጅነር ፓውሎ አንቶንዮ ይጠቅሳል። ከ1983 እስከ 1988 ዓ.ም 3.06 ቶን የሚደርስ ጭነት በወደቦቹ እንደተጓጓዘና እስከ 802 መርከቦች ማስተናገዱንም ይናገራል። ከ1986 እስከ 1989 ዓ.ም ባሉት ዓመታት ደግሞ ወደቦቹ እስከ 1150 መርከቦች አስተናግደዋል፤ 3.287 ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ ጭነትም አራግፈዋል። በ1989 ብቻ 2695 መርከቦች ሲያስተናግዱ 3̋95 ሚሊየን ቶን እቃ እንደተጫነና እንደተራገፈ ቺፍ ኢንጅነር ፓውሎ ይናገራል። የወደቦቹ አቅም የወደቦቹ አቅም ከጎረቤት አገሮች ጋር ሲነጻጸር የኤርትራ ወደቦች ከጂቡቲ ወደቦች ጋር ሲነጻጸሩ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ይህ አገራቱ ከሚከተሉት ፖሊሲ ጋር የሚያያዝ ሲሆን ጂቡቲ የብዙ አገሮች የወደብ ማዕከል በመሆንዋ፣ በተለይ ከ1990 በኋላ ለኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት ስትጀምር አገልግሎት የመስጠት አቅሟ በእጥፍ እንዳደገ የኤርትራ ባሕረኛ የነበረው ካፒቴን ተስፋይ ኢትባረኽ ይናገራል። ማሪታይም ሲልክ ሮድ በመባል የሚታወቀው የቻይና ፕሮጀክት አካል የሆነው ፖርት ሱዳንም ዘመናዊ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ በኋላ እያደገ መሆኑ ይነገራል። የኤርትራ ወደቦች በተለይ ባለፉት ዓመታት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከየመን ጋር ለምታደርገው ጦርነት ብትጠቀምበትም ምንም አይነት ማሻሻያ አለማሳየታቸው የባሕር እንቅስቃሴ የሚከታተለው አህመድ አብዱ ይገልጻል። ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአንድ ወቅት ለአገሪቷ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ቃለ መጠይቅ "የባሕር እንቁ የሚትባለው ምጽዋ ግን አለች? የባሕር እንቁም አይደለችም፤ ምንም አይደለችም" በማለት የምጽዋ ወደብ አቅም እንደወረደ ገልጸው ነበር። በአሁን ወቅት በስዊድን አገር በአንድ መርከብ ላይ እየሰራ የሚገኘው ኦፊሰር ቢንያም ታደሰ "የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝቦች በድንበር ጦርነት ምክንያት በወደብ አገልግሎት ብቻ በቢሊየን ዶላር ከስረዋል" ይላል። ኦፊሰር ቢንያም "የኤርትራ ባሕር ግን የወደብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ብቻ የሚውል አይደለም" በማለት የተለያዩ የአሳ አይነቶች፣ የባህር እንቁ፣ የጨው ማዕድንና ሌሎች የውጭ ምንዛሪ ማስገኘት የሚችሉ ሃብቶች እንዳሉት ያስረዳል። ኤርትራ ስንት መርከቦች አሏት? በ2002 በተደረገው ጥናት መሰረት በኤርትራ 8 የሚደርሱ ትልልቅ መርከቦች ተመዝግበው ነበር። መርከቦቹም ዮሃና፣ በይሉል፣ ሰላም፣ አንጀሎስ፣ ደንደን፣ መረብ ጋሽ፣ ሳሊናና ኤስሮምና የሚል መጠሪያ አላቸው። መርከቦቹ በአጠቃላይ 31245 ቶን እንደሚመዘኑ የኤርትራ ባሕረኞች ይናገራሉ። ኤስሮም ትላቋ የጭነት መርከብ ስትሆን 12333 ቶን ትመዘናለች። ዲኤምቲ የተባለው ኩባኒያም የመርከቧ ባለቤት ነው። በይሉል የቦት መርከብ ስትሆን መረብ ጋሽ ደግሞ በከረን ሺፒን ላይን የምትተዳደረው የነዳጅ ጫኝ መርከብ ናት። ሳሊና መርከብ የጭነት አገልግሎት የምትሰጥ በግል የምትተዳደር መርከብ ስትሆን ዛፈ ሺፒንግ ሊይን ባለቤትዋ ነው። "ይሁን እንጂ" ይላል ኦፊሰር ቢንያም "በአሁኑ ወቅት ተጨማሪ አገልግሎት የሚሰጡ በመንግሥትና በተለያዩ ማኅበራት የሚተዳደሩ መርከቦች ሙሉ ለሙሉ ቆመው፤ ሠራተኞቻቸው በስደት በተለያዩ አገራት መርከቦች እየሰሩ ይገኛሉ።" ከዚህ ቀደም ብዙ ወደ ሆላንድ፣ ሕንድና ፓኪስታን ተልከው የሰለጠኑ በርካታ ባሕረኞች እንደነበሩ የሚገልጸው ካፒቴን ተስፋይ በበኩሉ "ከነጻነት በኋላ በርካታ ወደ ታንዛኒያ፣ ዱባይና ኤምሬትስ ተልከው ሰልጥነው ነበር" ሲል ያስታውሳል። ሆኖም ይህ ቀጣይነት ማጣቱን የሚናገረው ካፒቴን ተስፋይ "የኤርትራ ባሕረኞች አቅም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ነው ያለው" ሲል ያስረዳል። የመጀመሪያው የኤርትራ ባሕረኞች ማኅበር በ1975 በምጽዋ ተመስርቶ ነበር። ይህ በተለያዩ ምክንያቶች መቀጠል ስላልቻለ በ2015 በስደት የተቋቋመው የኤርትራ ባሕረኞች ማኅበር እስከ 1500 የሚደርሱ አባላት አሉት።
ኤርትራ፡ የአሰብና ምጽዋ ወደቦች ምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ? ስድሳ ከመቶ በላይ የዓለም ነዳጅ በሚመላለስበት የንግድ መስመር ቀይ ባሕር በኤርትራ ውስጥ ከሰሜን ወደ ደቡብ 1 ሺህ ኪሎ ሜትር ይሸፍናል። ኤርትራ ከ300 በላይ ትላልቅና አነስተኛ ደሴቶች አሏት። በዚህ ምጽዋና አሰብ ተብለው የሚጠሩ ሁለት የወደብ ከተሞች አሉ። ወደቦቹ ከ60 ዓመታት በፊት ብዙ የወጪና የገቢ ንግድ የሚመላለስባቸው ነበሩ። በኤርትራ ትጥቅ ትግል ወቅት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ወደቦች ጥገና ተደርጎላቸው ከ1983 እስከ 1990 ድረስ አገልግሎት ይሰጡ ነበር። የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ግን ኢትዮጵያ የጅቡቲ ወደብን መጠቀም ጀመረች። በዚህ ምክንያት ተዳክመው የቆዩት ወደቦች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ዳግም መነቃቃት ያሳያሉ ተብሎ ተስፋ ተጥሎባቸዋል። በአሁኑ ወቅት በንግድ መርከብ የሚሰራው የኤርትራ ባሕረኞች ማኅበር አባል የሆነው ካፒቴን መሪሕ ሃብተ የኤርትራ ወደቦችን ከባሕር ትራንስፖርት፣ ከአሳ፣ ከቱሪዝምና ከማዕድን አንጻር ከፋፍሎ ማየት ይቻላል ይላል። የአሰብና የምጽዋ ወደቦች እቃዎችን የመጫንና የማራገፍ፣ የመጋዝን እና ሌሎች አገልግሎቶች የሚሰጡ ሲሆን በአሰብ እስከ 94 በመቶ የሚገባውና የሚወጣው ንብረት የኢትዮጵያ ንግድ እንደነበረ ቺፍ ኢንጅነር ፓውሎ አንቶንዮ ይጠቅሳል። ከ1983 እስከ 1988 ዓ.ም 3.06 ቶን የሚደርስ ጭነት በወደቦቹ እንደተጓጓዘና እስከ 802 መርከቦች ማስተናገዱንም ይናገራል። ከ1986 እስከ 1989 ዓ.ም ባሉት ዓመታት ደግሞ ወደቦቹ እስከ 1150 መርከቦች አስተናግደዋል፤ 3.287 ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ ጭነትም አራግፈዋል። በ1989 ብቻ 2695 መርከቦች ሲያስተናግዱ 3̋95 ሚሊየን ቶን እቃ እንደተጫነና እንደተራገፈ ቺፍ ኢንጅነር ፓውሎ ይናገራል። የወደቦቹ አቅም የወደቦቹ አቅም ከጎረቤት አገሮች ጋር ሲነጻጸር የኤርትራ ወደቦች ከጂቡቲ ወደቦች ጋር ሲነጻጸሩ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ይህ አገራቱ ከሚከተሉት ፖሊሲ ጋር የሚያያዝ ሲሆን ጂቡቲ የብዙ አገሮች የወደብ ማዕከል በመሆንዋ፣ በተለይ ከ1990 በኋላ ለኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት ስትጀምር አገልግሎት የመስጠት አቅሟ በእጥፍ እንዳደገ የኤርትራ ባሕረኛ የነበረው ካፒቴን ተስፋይ ኢትባረኽ ይናገራል። ማሪታይም ሲልክ ሮድ በመባል የሚታወቀው የቻይና ፕሮጀክት አካል የሆነው ፖርት ሱዳንም ዘመናዊ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ በኋላ እያደገ መሆኑ ይነገራል። የኤርትራ ወደቦች በተለይ ባለፉት ዓመታት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከየመን ጋር ለምታደርገው ጦርነት ብትጠቀምበትም ምንም አይነት ማሻሻያ አለማሳየታቸው የባሕር እንቅስቃሴ የሚከታተለው አህመድ አብዱ ይገልጻል። ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአንድ ወቅት ለአገሪቷ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ቃለ መጠይቅ "የባሕር እንቁ የሚትባለው ምጽዋ ግን አለች? የባሕር እንቁም አይደለችም፤ ምንም አይደለችም" በማለት የምጽዋ ወደብ አቅም እንደወረደ ገልጸው ነበር። በአሁን ወቅት በስዊድን አገር በአንድ መርከብ ላይ እየሰራ የሚገኘው ኦፊሰር ቢንያም ታደሰ "የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝቦች በድንበር ጦርነት ምክንያት በወደብ አገልግሎት ብቻ በቢሊየን ዶላር ከስረዋል" ይላል። ኦፊሰር ቢንያም "የኤርትራ ባሕር ግን የወደብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ብቻ የሚውል አይደለም" በማለት የተለያዩ የአሳ አይነቶች፣ የባህር እንቁ፣ የጨው ማዕድንና ሌሎች የውጭ ምንዛሪ ማስገኘት የሚችሉ ሃብቶች እንዳሉት ያስረዳል። ኤርትራ ስንት መርከቦች አሏት? በ2002 በተደረገው ጥናት መሰረት በኤርትራ 8 የሚደርሱ ትልልቅ መርከቦች ተመዝግበው ነበር። መርከቦቹም ዮሃና፣ በይሉል፣ ሰላም፣ አንጀሎስ፣ ደንደን፣ መረብ ጋሽ፣ ሳሊናና ኤስሮምና የሚል መጠሪያ አላቸው። መርከቦቹ በአጠቃላይ 31245 ቶን እንደሚመዘኑ የኤርትራ ባሕረኞች ይናገራሉ። ኤስሮም ትላቋ የጭነት መርከብ ስትሆን 12333 ቶን ትመዘናለች። ዲኤምቲ የተባለው ኩባኒያም የመርከቧ ባለቤት ነው። በይሉል የቦት መርከብ ስትሆን መረብ ጋሽ ደግሞ በከረን ሺፒን ላይን የምትተዳደረው የነዳጅ ጫኝ መርከብ ናት። ሳሊና መርከብ የጭነት አገልግሎት የምትሰጥ በግል የምትተዳደር መርከብ ስትሆን ዛፈ ሺፒንግ ሊይን ባለቤትዋ ነው። "ይሁን እንጂ" ይላል ኦፊሰር ቢንያም "በአሁኑ ወቅት ተጨማሪ አገልግሎት የሚሰጡ በመንግሥትና በተለያዩ ማኅበራት የሚተዳደሩ መርከቦች ሙሉ ለሙሉ ቆመው፤ ሠራተኞቻቸው በስደት በተለያዩ አገራት መርከቦች እየሰሩ ይገኛሉ።" ከዚህ ቀደም ብዙ ወደ ሆላንድ፣ ሕንድና ፓኪስታን ተልከው የሰለጠኑ በርካታ ባሕረኞች እንደነበሩ የሚገልጸው ካፒቴን ተስፋይ በበኩሉ "ከነጻነት በኋላ በርካታ ወደ ታንዛኒያ፣ ዱባይና ኤምሬትስ ተልከው ሰልጥነው ነበር" ሲል ያስታውሳል። ሆኖም ይህ ቀጣይነት ማጣቱን የሚናገረው ካፒቴን ተስፋይ "የኤርትራ ባሕረኞች አቅም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ነው ያለው" ሲል ያስረዳል። የመጀመሪያው የኤርትራ ባሕረኞች ማኅበር በ1975 በምጽዋ ተመስርቶ ነበር። ይህ በተለያዩ ምክንያቶች መቀጠል ስላልቻለ በ2015 በስደት የተቋቋመው የኤርትራ ባሕረኞች ማኅበር እስከ 1500 የሚደርሱ አባላት አሉት።
https://www.bbc.com/amharic/news-57193973
2health
ኮቪድ-19፡ በስህተት የ16 ሺህ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ውጤት ሳይገለጽ ቀረ
ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በገጠመ የቴክኒክ ስህተት ወደ 16 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሳይገለጽ ቀረ። ይህም በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለመለየት የሚደረገውን ጥረት አጓቷል። የአገሪቱ የሕብረተሰብ ጤና ተቋም እንዳለው ከመስከረም 25 እስከ ጥቅምት 2 ድረስ 15,841 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በእለታዊ ሪፖርት ሳይካተት ቀርቷል። ሪፖርት ያልተደረጉት ሰዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ እና እሁድ በወጡት እለታዊ ሪፖርቶች ተካተዋል። • የኮቪድ-19 ፀር ሳሙና ወይስ ፀረ-ቫይረስ ፈሳሽ? • ትራምፕ ደጋፊዎቻቸውን ለማየት ሆስፒታል ጥለው ወጡ • ልብስ ሳያረጥብ በፀረ ተህዋስ የሚያፀዳው የኢትዮጵያዊው ፈጠራ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ውጤታቸው ቢነገራቸውም ከእነሱ ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች መረጃው እንዳልደረሳቸው ተቋሙ አስታውቋል። በገጠመው የቴክኒክ ስህተት ምክንያት ባለፈው ሳምንት የወጡ ሪፖርቶች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርን አሳንሰዋል። በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በቫይረሱ እንደተያዙ የተገለጸው 7,000 ሰዎች ቢሆንም፤ ትክክለኛው ቁጥር ወደ 11,000 ይጠጋል። ሪፖርት ካልተደረጉት ሰዎች አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት የሰሜን ምዕራብ ኢንግላንድ ነዋሪዎች ናቸው። በርካታ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የሚኖሩት በሊቨርፑል እና በማንችስተር ነው። ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች በአጠቃላይ እንደተነገራቸው ገልጸዋል። የክትባት ምርምር ግብረ ኃይል ኃላፊ ኬት ቢንግሀም ለፋይናንሽያል ታይምስ እንደተናገሩት፤ ከዩኬ ዜጎች ከፊሉ ይከተባሉ። “ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ሰዎች ክትባት አይሰጥም። ክትባቱ ከ50 ዓመት በላይ ለሆኑና በዋናነትም ለጤና ባለሙያዎችና አረጋውያንን ለሚንከባከቡ ሰዎች ይሰጣል” ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ወረርሽኙን የማሸነፍ ተስፋ እንዳለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ማኅበረሰቡ “ጥንቃቄ ማድረግ እንጂ መፍራት የለበትም” ሲሉም አክለዋል። በአገሪቱ የምርመራ ውጤት መዘግየቱ መንግሥትን እያስተቸ ባለበት ወቅት፤ በስህተት ውጤታቸው ያልተገለጸ ሰዎች የመኖራቸው ዜና ነገሮችን አባብሷል። በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች መረጃውን አለማግኘታቸው ሌላው አሳሳቢ ነገር ነው። ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦች በ48 ሰዓታት ውስጥ ሊነገራቸው ይገባል። ስህተቱ የኮምፒውተር እንደሆነና አሁን መስተካከሉ ተገልጿል። መንግሥት ትላንት ባወጣው ሪፖርት ተጨማሪ 22,961 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸውና አጠቃላይ በበሽታው የተያዙ ቁጥር 502,978 መድረሱን ገልጿል። የሕብረተሰብ ጤና ተቋም ኃላፊው ማይክል ብሮይድ እንዳሉት፤ አብዛኞቹ ሪፖርት ያልተደረጉ ቁጥሮች የቅርብ ጊዜ የምርመራ ውጤት ናቸው። “ችግሩን በአፋጣኝ ለመቅረፍና የምርመራ ውጤቶቹን ለመግለጽ ሞክረናል። ስህተቱ ሊፈጥር የሚችለውን ስጋት እንረዳለን። በቀጣይ ተመሳሳይ ነገር እንዳይፈጠር ጥብቅ እርምጃ ወስደናል” ብለዋል።
ኮቪድ-19፡ በስህተት የ16 ሺህ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ውጤት ሳይገለጽ ቀረ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በገጠመ የቴክኒክ ስህተት ወደ 16 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሳይገለጽ ቀረ። ይህም በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለመለየት የሚደረገውን ጥረት አጓቷል። የአገሪቱ የሕብረተሰብ ጤና ተቋም እንዳለው ከመስከረም 25 እስከ ጥቅምት 2 ድረስ 15,841 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በእለታዊ ሪፖርት ሳይካተት ቀርቷል። ሪፖርት ያልተደረጉት ሰዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ እና እሁድ በወጡት እለታዊ ሪፖርቶች ተካተዋል። • የኮቪድ-19 ፀር ሳሙና ወይስ ፀረ-ቫይረስ ፈሳሽ? • ትራምፕ ደጋፊዎቻቸውን ለማየት ሆስፒታል ጥለው ወጡ • ልብስ ሳያረጥብ በፀረ ተህዋስ የሚያፀዳው የኢትዮጵያዊው ፈጠራ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ውጤታቸው ቢነገራቸውም ከእነሱ ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች መረጃው እንዳልደረሳቸው ተቋሙ አስታውቋል። በገጠመው የቴክኒክ ስህተት ምክንያት ባለፈው ሳምንት የወጡ ሪፖርቶች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርን አሳንሰዋል። በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በቫይረሱ እንደተያዙ የተገለጸው 7,000 ሰዎች ቢሆንም፤ ትክክለኛው ቁጥር ወደ 11,000 ይጠጋል። ሪፖርት ካልተደረጉት ሰዎች አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት የሰሜን ምዕራብ ኢንግላንድ ነዋሪዎች ናቸው። በርካታ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የሚኖሩት በሊቨርፑል እና በማንችስተር ነው። ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች በአጠቃላይ እንደተነገራቸው ገልጸዋል። የክትባት ምርምር ግብረ ኃይል ኃላፊ ኬት ቢንግሀም ለፋይናንሽያል ታይምስ እንደተናገሩት፤ ከዩኬ ዜጎች ከፊሉ ይከተባሉ። “ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ሰዎች ክትባት አይሰጥም። ክትባቱ ከ50 ዓመት በላይ ለሆኑና በዋናነትም ለጤና ባለሙያዎችና አረጋውያንን ለሚንከባከቡ ሰዎች ይሰጣል” ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ወረርሽኙን የማሸነፍ ተስፋ እንዳለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ማኅበረሰቡ “ጥንቃቄ ማድረግ እንጂ መፍራት የለበትም” ሲሉም አክለዋል። በአገሪቱ የምርመራ ውጤት መዘግየቱ መንግሥትን እያስተቸ ባለበት ወቅት፤ በስህተት ውጤታቸው ያልተገለጸ ሰዎች የመኖራቸው ዜና ነገሮችን አባብሷል። በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች መረጃውን አለማግኘታቸው ሌላው አሳሳቢ ነገር ነው። ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦች በ48 ሰዓታት ውስጥ ሊነገራቸው ይገባል። ስህተቱ የኮምፒውተር እንደሆነና አሁን መስተካከሉ ተገልጿል። መንግሥት ትላንት ባወጣው ሪፖርት ተጨማሪ 22,961 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸውና አጠቃላይ በበሽታው የተያዙ ቁጥር 502,978 መድረሱን ገልጿል። የሕብረተሰብ ጤና ተቋም ኃላፊው ማይክል ብሮይድ እንዳሉት፤ አብዛኞቹ ሪፖርት ያልተደረጉ ቁጥሮች የቅርብ ጊዜ የምርመራ ውጤት ናቸው። “ችግሩን በአፋጣኝ ለመቅረፍና የምርመራ ውጤቶቹን ለመግለጽ ሞክረናል። ስህተቱ ሊፈጥር የሚችለውን ስጋት እንረዳለን። በቀጣይ ተመሳሳይ ነገር እንዳይፈጠር ጥብቅ እርምጃ ወስደናል” ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54423275
2health
ዩናይትድ ኪንግደም ጤነኛ ሰዎችን በኮቪድ ተህዋሲ 'ልትለክፋቸው' ነው
የኮቪድ ክትባትን በማግኘት ጥረት ውስጥ ከፊት ከሆኑ አገራት አንዷ የሆነችው ዩናይትድ ኪንግደም የተለየ አይነት የክትባት ሙከራ ለማድረግ ቀዳሚዋ አገር ልትሆን ነው። በጥር ወር ላይ 90 ጤነኛ ሰዎች ሆን ተብለው ለኮቪድ ተህዋሲ እንዲጋለጡ በማድረግ ነው አዲሱ ሙከራ የሚደረገው። ይህም ቶሎ ክትባት ለማግኘት ይረዳል ተብሏል። መንግሥት ከወዲሁ 33.6 ሚሊዮን ፓውንድ ለዚሁ ሙከራ መድቧል። ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግበታል የተባለው ይህ አዲስ የሙከራ ዘዴ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ከአገሪቱ መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ይሁንታን ማግኘት ይኖርበታል። በመድኃኒት ቅመማ ሂደት ‹ሂዩማን ቻሌንጅ› በሚል የሚታወቀው ይህ ጤነኞች ላይ በሽታ አምጪ ተህዋስን ሆን ብሎ በማጋባት ሙከራ ማድረግ ብዙም የተለመደ አይደለም። ነገር ግን ከዚህ ቀደም በወባና በኢንፍሉዌዛ የመድኃኒት ግኝቶች ሂደት ውስጥ ተሞክሮ ውጤት ማስገኘቱን ኔቸር መጽሔት ዘግቧል። ሳይንቲስቶች በጥር ወር መጀመርያ ተግባራዊ ያደርጉታል በተባለው በዚህ ሂደት ውስጥ የሚሳተፉት ሰዎች ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 30 የሚሆን ፍጹም ጤነኛ የሆኑ በጎ ፈቃደኞች ብቻ ናቸው። ሙከራው አንድን ሰው ምን ያህል የተህዋሲው መጠን ነው ለበሽታ የሚያጋልጠው የሚለውንም ለማወቅ ይረዳል ተብሏል። ለበጎ ፈቃደኞቹ በቅድሚያ ተህዋሲው በትንሽ መጠን ይሰጣቸዋል። ፍጹም ጤነኛ ሰዎችን እንደ አይጥ መሞከርያ ማድረግ ቶሎ ውጤት ለማግኘት አስፈላጊ ነው የሚሉ በርካታ ቢሆንም መድኃኒት በሌለው በሽታ ሰዎችን ሆን ብሎ መበከል ከሕክምና ሥነ ምግባር አንጻር ተገቢ አይደለም ሲሉ ነገሩን የሚተቹትም በርካታ ናቸው። ተህዋሲው ለበጎ ፈቃደኞቹ የሚሰጣቸው በአፍንጫቸው በኩል ይሆናል ተብሏል። ለ24 ሰዓታትም ጥብቅ ክትትል ይደረግላቸዋል። በጎ ፈቃደኞቹ ለከፋ አደጋ የመጋለጥ እድላቸው አነስተኛ ነው፤ ምክንያቱም ጤነኞችና ወጣቶች በመሆናቸውና በጥንቃቄ ስለሚመረጡ ነው ይላሉ ተመራማሪዎች። ቅድመ ጥንቃቄው አስተማማኝ በሚባል ደረጃ ላይ ሲደርስ በበጎ ፈቃደኞቹ በአንዳንዶቹ ላይ ሙከራ ላይ የሚገኙ ክትባቶች ይሰጧቸዋል። ለኮቪድ ተህዋሲው ከመገላጣቸው በፊትም ክትባት እንዲወስዱ የሚደረጉ ይኖራሉ። ክትባቱን የወሰዱት ለተህዋሲው ተጋልጠው ተህዋሲው ይይዛቸዋል ወይስ አይዛቸውም የሚለውም ምላሽ ያገኛል። የዚህ ምርምር መሪ የኢምፔሪያል ኮሌጁ ዶ/ር ክሪስ ቺዩ ሰዎች ያን ያህልም ሐሳብ ሊገባቸው አይገባም ይላሉ። ‹‹እኔና ባልደረቦቼ በዚህ መንገድ ላለፉት 10 ዓመታት በርካታ ጤነኛ ሰዎች ላይ ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያያዙ ቫይረሶችን በመስጠት ስንሰራ ቆይተናል። እርግጥ ነው የትኛውም ጥናት ቢሆን የራሱ አደጋ የለውም አይባልም። ነገር ግን አደጋውን ለመቀነስ እንታገላለን›› ብለዋል። ረዳታቸው ፕሮፌሰር ፒተር ኦፔን ሻው በበኩላቸው ጤነኛ ሰዎችን በተህዋሲ ሆን ብሎ በመበከል ምርምር ማካሄድ በቀላሉ የሚታይ ነገር ባይሆንም ውጤት ለማግኘት ግን ወሳኝ ነው፤ ያግዛል ብለዋል። በአሁን ሰዓት በመቶዎች የሚቆጠሩ የኮቪድ ክትባቶች በመጨረሻ ምዕራፍ ሙከራ ላይ ሲሆኑ ውጤት ያስገኛሉ ተብለው በጉጉት እየተጠበቁ ካሉት መካከል የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው ተጠቃሽ ነው። በጥር ወር ጤነኛ ሰዎችን በተህዋሲው በመበከል የሚደረገው ምርምር ሌላ ፍቱን መድኃኒት ቀድሞ ቢገኝም የሚቋረጥ አይሆንም። ክትባቶች ከተገኙ በኋላ የትኛው ክትባት እጅግ ውጤታማ ነው የሚለው ጥናት ይቀጥላል። ተህዋሲውን በገዛ ፈቃዳቸው ለመውሰድ የፈቀዱ የታላቋ ብሪታኒያ ዜጎች ለጊዜያቸውና ለደፋር ውሳኔያቸው የሚመጥን ነው የሚባል ገንዘብ ይከፈላቸዋል። ሙከራው ከተደረገባቸው በኋላም ቢያንስ ለአንድ ዓመት ያለማቋረጥ የቅርብ ክትትል ይደረግባቸዋል።
ዩናይትድ ኪንግደም ጤነኛ ሰዎችን በኮቪድ ተህዋሲ 'ልትለክፋቸው' ነው የኮቪድ ክትባትን በማግኘት ጥረት ውስጥ ከፊት ከሆኑ አገራት አንዷ የሆነችው ዩናይትድ ኪንግደም የተለየ አይነት የክትባት ሙከራ ለማድረግ ቀዳሚዋ አገር ልትሆን ነው። በጥር ወር ላይ 90 ጤነኛ ሰዎች ሆን ተብለው ለኮቪድ ተህዋሲ እንዲጋለጡ በማድረግ ነው አዲሱ ሙከራ የሚደረገው። ይህም ቶሎ ክትባት ለማግኘት ይረዳል ተብሏል። መንግሥት ከወዲሁ 33.6 ሚሊዮን ፓውንድ ለዚሁ ሙከራ መድቧል። ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግበታል የተባለው ይህ አዲስ የሙከራ ዘዴ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ከአገሪቱ መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ይሁንታን ማግኘት ይኖርበታል። በመድኃኒት ቅመማ ሂደት ‹ሂዩማን ቻሌንጅ› በሚል የሚታወቀው ይህ ጤነኞች ላይ በሽታ አምጪ ተህዋስን ሆን ብሎ በማጋባት ሙከራ ማድረግ ብዙም የተለመደ አይደለም። ነገር ግን ከዚህ ቀደም በወባና በኢንፍሉዌዛ የመድኃኒት ግኝቶች ሂደት ውስጥ ተሞክሮ ውጤት ማስገኘቱን ኔቸር መጽሔት ዘግቧል። ሳይንቲስቶች በጥር ወር መጀመርያ ተግባራዊ ያደርጉታል በተባለው በዚህ ሂደት ውስጥ የሚሳተፉት ሰዎች ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 30 የሚሆን ፍጹም ጤነኛ የሆኑ በጎ ፈቃደኞች ብቻ ናቸው። ሙከራው አንድን ሰው ምን ያህል የተህዋሲው መጠን ነው ለበሽታ የሚያጋልጠው የሚለውንም ለማወቅ ይረዳል ተብሏል። ለበጎ ፈቃደኞቹ በቅድሚያ ተህዋሲው በትንሽ መጠን ይሰጣቸዋል። ፍጹም ጤነኛ ሰዎችን እንደ አይጥ መሞከርያ ማድረግ ቶሎ ውጤት ለማግኘት አስፈላጊ ነው የሚሉ በርካታ ቢሆንም መድኃኒት በሌለው በሽታ ሰዎችን ሆን ብሎ መበከል ከሕክምና ሥነ ምግባር አንጻር ተገቢ አይደለም ሲሉ ነገሩን የሚተቹትም በርካታ ናቸው። ተህዋሲው ለበጎ ፈቃደኞቹ የሚሰጣቸው በአፍንጫቸው በኩል ይሆናል ተብሏል። ለ24 ሰዓታትም ጥብቅ ክትትል ይደረግላቸዋል። በጎ ፈቃደኞቹ ለከፋ አደጋ የመጋለጥ እድላቸው አነስተኛ ነው፤ ምክንያቱም ጤነኞችና ወጣቶች በመሆናቸውና በጥንቃቄ ስለሚመረጡ ነው ይላሉ ተመራማሪዎች። ቅድመ ጥንቃቄው አስተማማኝ በሚባል ደረጃ ላይ ሲደርስ በበጎ ፈቃደኞቹ በአንዳንዶቹ ላይ ሙከራ ላይ የሚገኙ ክትባቶች ይሰጧቸዋል። ለኮቪድ ተህዋሲው ከመገላጣቸው በፊትም ክትባት እንዲወስዱ የሚደረጉ ይኖራሉ። ክትባቱን የወሰዱት ለተህዋሲው ተጋልጠው ተህዋሲው ይይዛቸዋል ወይስ አይዛቸውም የሚለውም ምላሽ ያገኛል። የዚህ ምርምር መሪ የኢምፔሪያል ኮሌጁ ዶ/ር ክሪስ ቺዩ ሰዎች ያን ያህልም ሐሳብ ሊገባቸው አይገባም ይላሉ። ‹‹እኔና ባልደረቦቼ በዚህ መንገድ ላለፉት 10 ዓመታት በርካታ ጤነኛ ሰዎች ላይ ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያያዙ ቫይረሶችን በመስጠት ስንሰራ ቆይተናል። እርግጥ ነው የትኛውም ጥናት ቢሆን የራሱ አደጋ የለውም አይባልም። ነገር ግን አደጋውን ለመቀነስ እንታገላለን›› ብለዋል። ረዳታቸው ፕሮፌሰር ፒተር ኦፔን ሻው በበኩላቸው ጤነኛ ሰዎችን በተህዋሲ ሆን ብሎ በመበከል ምርምር ማካሄድ በቀላሉ የሚታይ ነገር ባይሆንም ውጤት ለማግኘት ግን ወሳኝ ነው፤ ያግዛል ብለዋል። በአሁን ሰዓት በመቶዎች የሚቆጠሩ የኮቪድ ክትባቶች በመጨረሻ ምዕራፍ ሙከራ ላይ ሲሆኑ ውጤት ያስገኛሉ ተብለው በጉጉት እየተጠበቁ ካሉት መካከል የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው ተጠቃሽ ነው። በጥር ወር ጤነኛ ሰዎችን በተህዋሲው በመበከል የሚደረገው ምርምር ሌላ ፍቱን መድኃኒት ቀድሞ ቢገኝም የሚቋረጥ አይሆንም። ክትባቶች ከተገኙ በኋላ የትኛው ክትባት እጅግ ውጤታማ ነው የሚለው ጥናት ይቀጥላል። ተህዋሲውን በገዛ ፈቃዳቸው ለመውሰድ የፈቀዱ የታላቋ ብሪታኒያ ዜጎች ለጊዜያቸውና ለደፋር ውሳኔያቸው የሚመጥን ነው የሚባል ገንዘብ ይከፈላቸዋል። ሙከራው ከተደረገባቸው በኋላም ቢያንስ ለአንድ ዓመት ያለማቋረጥ የቅርብ ክትትል ይደረግባቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/54617479
0business
የናይጄሪያው ሼል ላደረሰው ብክለት ለአርሶ አደሮች ካሳ እንዲከፍል ተወሰነበት
የኔዘርላንድስ ፍርድ ቤት በኒጀር ዴልታ ተፋሰስ የነዳጅ ብክለት አስከትሏል በሚል በናይጄሪያ የሚገኘውን የሼል ኩባንያ ቅርንጫፍ ጥፋተኛ አድርጎታል፤ ካሳም እንዲከፍል አዞታል። ፍርድ ቤቱ የናይጄሪያው ሼል ጉዳት ለደረሰባቸው ናይጄሪያዊ አርሶ አደሮች ካሳ እንዲከፍል እንዲሁም ተቋራጩ የሆነው የእንግሊዙ-ደች ኩባንያ ለወደፊቱ የሚፈጠርን ጉዳት ለመከላከል አስፈላጊ የሚባለውን ቁሳቁስ እንዲገጥም ትዕዛዝ ተላልፎለታል። በአውሮፓውያኑ 2008 ሼል አካባቢያችንን በክሎታል በሚል አርሶ አደሮቹ ክስ መመስረታቸው ይታወሳል። ሼል በበኩሉ "ሆን ብሎ የተጠነሰሰብኝ ሴራ ነው" ይላል። በዛሬው እለት የደች ሼል ባወጣው መግለጫ በውሳኔው "አዝነናል"ብሏል። ኩባንያው ይግባኝ የመጠየቅ መብት አለው ተብሏል። ፍርድ ቤቱ በበኩሉ "ጎይና ኦሩማ በሚባሉ መንደሮች ላይ ነዳጁ ፈስሶ ለደረሰው ጉዳት ኩባንያው ሴረኞች የፈፀሙት ነው ቢልም ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም። ኩባንያው ከነበረው ደካማ አሰራር ጋር የተያያዘ ነው" ብሏል ችሎቱ። "በነዚህ አካባቢዎች ተንጠባጥቦና ፈስሶ ለደረሰው ብክለትና ጉዳት ሼል ናይጄሪያ ተጠያቂ ነው" በማለት ፍርድ ቤቱ አስምሯል። የካሳው መጠንም ከዚህ በኋላ የሚወሰን ይሆናል። ኢኮት አዳ ኡዶ በተባለው መንደር ኩባንያው እንዳለው ሆን ተብሎ የተፈፀመ ለመሆኑ አንዳንድ ፍንጮች በመኖራቸው የበለጠ እመረምረዋለሁ በማለት ፍርድ ቤቱ ለጊዜው ይዞታል። ከሳሾቹ አራት አርሶ አደሮች ከመሬት ስር የተቀበረው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፈስሶ ውሃቸው እንዲሁም መሬታቸው እንደተበከለና መላ ህይወታቸውን ግልብጥብጡን እንዳወጣው ገልፀዋል። ከከሳሾቹ ውስጥ ሁለቱ መሞታቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው አስነብቧል። አርሶ አደሮቹን ፍሬንድስ ኦፍ ዘ ኧርዝ የተባለ የከባቢ ጥበቃ ቡድን ደግፏቸዋል። "የደስታ እንባ ነው የማነባው፤ ከአስራ ሶስት አመታት በኋላ አሸነፍን" በማለት የቡድኑ ኔዘርላንድስ ቅርንጫፍ ተወካይ በውሳኔው የተሰማቸውን ደስታ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። በዛሬው እለት የተላለፈው ውሳኔ ከናይጄሪያ አልፎ የኩባንያዎች ኃላፊነት እስከምን ድረስ ሊሆን ይገባል በሚለው ጉዳይ ላይ ሌሎች አገራት ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል ተብሏል። በዚህ ክስ ላይ የነዳጁ ፍሰት የተፈጠረው ከ2004-2007 ቢሆንም በአሁኑም ወቅት በኒጀር ደልታ ከነዳጅ መተላለፊያ ቧንቧዎች የሚወጣው ብክለት ትልቅ ችግር ነው ተብሏል።
የናይጄሪያው ሼል ላደረሰው ብክለት ለአርሶ አደሮች ካሳ እንዲከፍል ተወሰነበት የኔዘርላንድስ ፍርድ ቤት በኒጀር ዴልታ ተፋሰስ የነዳጅ ብክለት አስከትሏል በሚል በናይጄሪያ የሚገኘውን የሼል ኩባንያ ቅርንጫፍ ጥፋተኛ አድርጎታል፤ ካሳም እንዲከፍል አዞታል። ፍርድ ቤቱ የናይጄሪያው ሼል ጉዳት ለደረሰባቸው ናይጄሪያዊ አርሶ አደሮች ካሳ እንዲከፍል እንዲሁም ተቋራጩ የሆነው የእንግሊዙ-ደች ኩባንያ ለወደፊቱ የሚፈጠርን ጉዳት ለመከላከል አስፈላጊ የሚባለውን ቁሳቁስ እንዲገጥም ትዕዛዝ ተላልፎለታል። በአውሮፓውያኑ 2008 ሼል አካባቢያችንን በክሎታል በሚል አርሶ አደሮቹ ክስ መመስረታቸው ይታወሳል። ሼል በበኩሉ "ሆን ብሎ የተጠነሰሰብኝ ሴራ ነው" ይላል። በዛሬው እለት የደች ሼል ባወጣው መግለጫ በውሳኔው "አዝነናል"ብሏል። ኩባንያው ይግባኝ የመጠየቅ መብት አለው ተብሏል። ፍርድ ቤቱ በበኩሉ "ጎይና ኦሩማ በሚባሉ መንደሮች ላይ ነዳጁ ፈስሶ ለደረሰው ጉዳት ኩባንያው ሴረኞች የፈፀሙት ነው ቢልም ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም። ኩባንያው ከነበረው ደካማ አሰራር ጋር የተያያዘ ነው" ብሏል ችሎቱ። "በነዚህ አካባቢዎች ተንጠባጥቦና ፈስሶ ለደረሰው ብክለትና ጉዳት ሼል ናይጄሪያ ተጠያቂ ነው" በማለት ፍርድ ቤቱ አስምሯል። የካሳው መጠንም ከዚህ በኋላ የሚወሰን ይሆናል። ኢኮት አዳ ኡዶ በተባለው መንደር ኩባንያው እንዳለው ሆን ተብሎ የተፈፀመ ለመሆኑ አንዳንድ ፍንጮች በመኖራቸው የበለጠ እመረምረዋለሁ በማለት ፍርድ ቤቱ ለጊዜው ይዞታል። ከሳሾቹ አራት አርሶ አደሮች ከመሬት ስር የተቀበረው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፈስሶ ውሃቸው እንዲሁም መሬታቸው እንደተበከለና መላ ህይወታቸውን ግልብጥብጡን እንዳወጣው ገልፀዋል። ከከሳሾቹ ውስጥ ሁለቱ መሞታቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው አስነብቧል። አርሶ አደሮቹን ፍሬንድስ ኦፍ ዘ ኧርዝ የተባለ የከባቢ ጥበቃ ቡድን ደግፏቸዋል። "የደስታ እንባ ነው የማነባው፤ ከአስራ ሶስት አመታት በኋላ አሸነፍን" በማለት የቡድኑ ኔዘርላንድስ ቅርንጫፍ ተወካይ በውሳኔው የተሰማቸውን ደስታ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። በዛሬው እለት የተላለፈው ውሳኔ ከናይጄሪያ አልፎ የኩባንያዎች ኃላፊነት እስከምን ድረስ ሊሆን ይገባል በሚለው ጉዳይ ላይ ሌሎች አገራት ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል ተብሏል። በዚህ ክስ ላይ የነዳጁ ፍሰት የተፈጠረው ከ2004-2007 ቢሆንም በአሁኑም ወቅት በኒጀር ደልታ ከነዳጅ መተላለፊያ ቧንቧዎች የሚወጣው ብክለት ትልቅ ችግር ነው ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55859771
5sports
ኢሊዩድ ኪፕቾጌ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች አጠናቀቀ
ኢሊዩድ ኪፕቾጌ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች በመሮጥ የመጀመሪያው አትሌት ሆነ። ኪፕቾጌ ሩጫውን ለመጨረስ አንድ ሰዓት ከ59 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ ፈጅቶበታል። የ34 ዓመቱ ኬኒያዊ አትሌት 42.2 ኪሎ ሜትር ለመሮጥ የፈጀበት ሰዓት እንደ ዓለም ክብረ ወሰን እንደማይመዘገብለት የተገለጠ ሲሆን፣ ለዚህም ምክንያት ነው የተባለው የተጠቀማቸው አሯሯጮች፤ እየተፈራረቁ የሚያሯሩጡት አትሌቶች መሆናቸውና ለሁሉም ክፍት የሆነ ውድድር ባለመሆኑ ነው። ኪፕቾጌ ውጤቱን አስመልክቶ ሲናገር "ይህ የሚያሳየው ማንም ሰው ሊያሳካው እንደሚችል ነው" ብሏል። "አሁን እኔ አሳክቸዋለሁ፤ ከአሁን በኋላ ሌሎችም እንዲያሳኩት እፈልጋለሁ" ብሏል። • ኪፕቾጌን በሩጫ ይገዳደሩታል? • ከባህር ዳር - አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ዛሬም አልተከፈተም • ነገ በአዲስ አበባ የሚደረግ ሠልፍም ሆነ ስብሰባ የለም-የአዲስ አበባ ፖሊስ ይሀ የኦሎምፒክ ሻምፒዮና የአለም አቀፉን የማራቶን ክብረወሰን በአውሮፓዊያኑ 2018 ጀርመን በርሊን ላይ በሁለት ሰዓት ከ01 ደቂቃ 39 ሰከንድ በእጁ አስገብቶ ነበር። የለንደን ማራቶንን አራት ጊዜ በማሸነፍ ስሙን የተከለው ኪፕቾጌ፤ ከድሉ በኋላ ባለቤቱ ግሬስን ተጠምጥሞ በመሳም የሀገሩን ባንዲራ ለብሶ በአሯሯጮቹ ተከብቦ ደስታውን ገልጧል። ኪፕቾጌ በሚሮጥበት ወቅት ከፊት ከፊቱ በመሆን ሰዓቱን የሚጠቁመው መኪና የነበረ ሲሆን 100 ሜትሩን 17 ደቂቃ ከ08 ሰከንድ በመሮጥ ለስኬት በቅቷል። ኪፕቾጌን 42 አሯሯጮች ያሯሯጡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የ1500 ሜትር ሻምፒዮናው ማቲው ቹንትሮ ዊትዝ፣ የ5000 ሜትር የመዳብ ባለቤቱ ፓል ቼሊሞና ኖርዌጂያን ወንድማማቾቹ ጃኮብ፣ ፍሊፕና ሄንሪክ ይገኙበታል። እነዚህ አሯሯጮች እያረፉ ያሯሯጡት ሲሆን የ1500 እና የ5000 ዓለም ሻምፒዮና የሆነው በርናንርድ ላጋት የመጨረሻዎቹን ርቀቶች አሯሩጦታል። ኪፕቾጌም "እነዚህ በዓለም አሉ የሚባሉ ዝነኛ አትሌቶች ናቸው፤ አመሰግናለሁ" በማለት፤ አክሎም "ይህንን ሥራ ስለተቀበሉ አመሰግናለሁ። ያሳካነው በጋራ ነው" ብሏል። • "የማራቶን ሯጮቹ ላይ የተላለፈው እገዳ አይደለም" ዱቤ ጂሎ • 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፡ የእኛ ሠው በዶሃ የኪፕቾጌ አሰልጣኝ አትሌቱ ልክ እንደ ሌላ ጊዜው የሚጠጣው ውሃ ከጠረጴዛ ላይ አንስቶ ከሚጠቀም ይልቅ በብስክሌት በመሆን ውሃና ኃይል ሰጪ ጄል ሲያቀብሉት ነበር። እንዲህ ዓይነት እገዛ ግን በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕግ መሰረት አይፈቀድም። ኪፕቾጌ የሮጠበት ሥፍራ የተመረጠው የአየር ጠባዩ ምቹ ስለሆነ መሆኑ ተነግሯል። ይህንን ሰዓት ለማሻሻል የተደረገውን ጥረት በገንዘብ የደገፉት እንግሊዛዊው ባለሀብት ሰር ጂም ራትክሊፍ በኩባንያቸው ፔትሮ ኬሚካልስ ስም ነው። ናይክም አምስት የዓለማችን ፈጣን የማራቶን ሯጮች ብቻ ያደረጉት አዲስ ሞዴል ጫማ አበርክቶለታል። የመጨረሻዎቹን ኪሎ ሜትሮች ያጠናቀቀበት ፍጥነት "አስደማሚ ነበር" ያሉት ራትክሊፍ ሲሆኑ የኪፕቾጌ አሰልጣኝ በበኩላቸው " በዚህ ሙከራችን ሁሉም ነገር እንዳሰብነው ሄዷል" ብለዋል። "ሁላችንንም ነው ያነቃቃው፤ በሕይወታችን አቅማችንን በመለጠጥ መፈተሽ እንደምንችል አሳይቶናል" ካሉም በኋላ "በስፖርቱ ዓለም ለሌሎች አትሌቶች ከሚያስቡት በተሻለ መሮጥ እንደሚችሉ ያሳየ፤ በሌላ ሕይወት መስክ ደግሞ ሌላ ከፍታ መውጣት እንደሚችል ያስተማረ ነው" በማለት ድሉን አሞካሽተውታል። "በአጠቃላይ ታሪክ ተሠርቷል፤ የማይታመን ነገር ነው" ብለዋል።
ኢሊዩድ ኪፕቾጌ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች አጠናቀቀ ኢሊዩድ ኪፕቾጌ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች በመሮጥ የመጀመሪያው አትሌት ሆነ። ኪፕቾጌ ሩጫውን ለመጨረስ አንድ ሰዓት ከ59 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ ፈጅቶበታል። የ34 ዓመቱ ኬኒያዊ አትሌት 42.2 ኪሎ ሜትር ለመሮጥ የፈጀበት ሰዓት እንደ ዓለም ክብረ ወሰን እንደማይመዘገብለት የተገለጠ ሲሆን፣ ለዚህም ምክንያት ነው የተባለው የተጠቀማቸው አሯሯጮች፤ እየተፈራረቁ የሚያሯሩጡት አትሌቶች መሆናቸውና ለሁሉም ክፍት የሆነ ውድድር ባለመሆኑ ነው። ኪፕቾጌ ውጤቱን አስመልክቶ ሲናገር "ይህ የሚያሳየው ማንም ሰው ሊያሳካው እንደሚችል ነው" ብሏል። "አሁን እኔ አሳክቸዋለሁ፤ ከአሁን በኋላ ሌሎችም እንዲያሳኩት እፈልጋለሁ" ብሏል። • ኪፕቾጌን በሩጫ ይገዳደሩታል? • ከባህር ዳር - አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ዛሬም አልተከፈተም • ነገ በአዲስ አበባ የሚደረግ ሠልፍም ሆነ ስብሰባ የለም-የአዲስ አበባ ፖሊስ ይሀ የኦሎምፒክ ሻምፒዮና የአለም አቀፉን የማራቶን ክብረወሰን በአውሮፓዊያኑ 2018 ጀርመን በርሊን ላይ በሁለት ሰዓት ከ01 ደቂቃ 39 ሰከንድ በእጁ አስገብቶ ነበር። የለንደን ማራቶንን አራት ጊዜ በማሸነፍ ስሙን የተከለው ኪፕቾጌ፤ ከድሉ በኋላ ባለቤቱ ግሬስን ተጠምጥሞ በመሳም የሀገሩን ባንዲራ ለብሶ በአሯሯጮቹ ተከብቦ ደስታውን ገልጧል። ኪፕቾጌ በሚሮጥበት ወቅት ከፊት ከፊቱ በመሆን ሰዓቱን የሚጠቁመው መኪና የነበረ ሲሆን 100 ሜትሩን 17 ደቂቃ ከ08 ሰከንድ በመሮጥ ለስኬት በቅቷል። ኪፕቾጌን 42 አሯሯጮች ያሯሯጡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የ1500 ሜትር ሻምፒዮናው ማቲው ቹንትሮ ዊትዝ፣ የ5000 ሜትር የመዳብ ባለቤቱ ፓል ቼሊሞና ኖርዌጂያን ወንድማማቾቹ ጃኮብ፣ ፍሊፕና ሄንሪክ ይገኙበታል። እነዚህ አሯሯጮች እያረፉ ያሯሯጡት ሲሆን የ1500 እና የ5000 ዓለም ሻምፒዮና የሆነው በርናንርድ ላጋት የመጨረሻዎቹን ርቀቶች አሯሩጦታል። ኪፕቾጌም "እነዚህ በዓለም አሉ የሚባሉ ዝነኛ አትሌቶች ናቸው፤ አመሰግናለሁ" በማለት፤ አክሎም "ይህንን ሥራ ስለተቀበሉ አመሰግናለሁ። ያሳካነው በጋራ ነው" ብሏል። • "የማራቶን ሯጮቹ ላይ የተላለፈው እገዳ አይደለም" ዱቤ ጂሎ • 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፡ የእኛ ሠው በዶሃ የኪፕቾጌ አሰልጣኝ አትሌቱ ልክ እንደ ሌላ ጊዜው የሚጠጣው ውሃ ከጠረጴዛ ላይ አንስቶ ከሚጠቀም ይልቅ በብስክሌት በመሆን ውሃና ኃይል ሰጪ ጄል ሲያቀብሉት ነበር። እንዲህ ዓይነት እገዛ ግን በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕግ መሰረት አይፈቀድም። ኪፕቾጌ የሮጠበት ሥፍራ የተመረጠው የአየር ጠባዩ ምቹ ስለሆነ መሆኑ ተነግሯል። ይህንን ሰዓት ለማሻሻል የተደረገውን ጥረት በገንዘብ የደገፉት እንግሊዛዊው ባለሀብት ሰር ጂም ራትክሊፍ በኩባንያቸው ፔትሮ ኬሚካልስ ስም ነው። ናይክም አምስት የዓለማችን ፈጣን የማራቶን ሯጮች ብቻ ያደረጉት አዲስ ሞዴል ጫማ አበርክቶለታል። የመጨረሻዎቹን ኪሎ ሜትሮች ያጠናቀቀበት ፍጥነት "አስደማሚ ነበር" ያሉት ራትክሊፍ ሲሆኑ የኪፕቾጌ አሰልጣኝ በበኩላቸው " በዚህ ሙከራችን ሁሉም ነገር እንዳሰብነው ሄዷል" ብለዋል። "ሁላችንንም ነው ያነቃቃው፤ በሕይወታችን አቅማችንን በመለጠጥ መፈተሽ እንደምንችል አሳይቶናል" ካሉም በኋላ "በስፖርቱ ዓለም ለሌሎች አትሌቶች ከሚያስቡት በተሻለ መሮጥ እንደሚችሉ ያሳየ፤ በሌላ ሕይወት መስክ ደግሞ ሌላ ከፍታ መውጣት እንደሚችል ያስተማረ ነው" በማለት ድሉን አሞካሽተውታል። "በአጠቃላይ ታሪክ ተሠርቷል፤ የማይታመን ነገር ነው" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-50027271
5sports
የሉሲዎቹና የአዳማ ክለብ ጎል አዳኝ ሴናፍ ዋቁማ
የሉሲዎቹና የአዳማ ክለብ ጎል አዳኝ የፊት መስመር ተጫዋች ነች፤ ሴናፍ ዋቁማ። ትውልድና እድገቷ በነቀምት ነው። ለእግር ኳስ ያላትን ፍቅር ስትገልጽ "ትምህርት ቤት እያለሁ ለኳስ ካለኝ ፍቅር የተነሳ እጫወት የነበረው ከወንዶቹ ጋር ነበር" ትላለች። ትኩረቷን ሙሉ በሙሉ ለኳስ ከሰጠች በኋላ ነቀምት በሚገኙ የእግር ኳስ ፕሮጀክቶች ውስጥ ታቅፋ ስልጠናዎችን ወስዳለች። ከዚያም በነበራት አቋም ተመርጣ ወደ አሰላ በመሄድ ለአራት ዓመታት ስልጠና ወስዳለች። • "በሀገራችን ከሶስት ሴቶች አንዷ ላይ ጾታዊ ጥቃት ይደርሳል" • በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን አቃቤ ሕግ አስታወቀ • የሕዝብ እንደራሴዎችን ጎራ አስለይቶ ያሟገተው ሕግ "የሰዎች አመለካከት ጥሩ አልነበረም" የምትለው ሴናፍ፤ በእግር ኳስ ህይወቷ ማህበረሰቡ ሴቶች እግር ኳስ መጫወታቸውን በበጎ አለመመልከቱ የእግር ኳስ ህይወቷን ፈታኝ አድርጎባት እንደነበረ ታስረዳለች። "ሴቶች ከቤት መውጣት የለባቸውም የሚል አመለካከት ነበር። እግር ኳስ መጫወት ደግሞ እንደ ሃፍረት ነበር የሚቆጠረው" የምትለው ሴናፍ፤ የማህብረሰቡ አመለካከት በወላጆቿ ላይ ጭምር ጫና በማሳደሩ ወላጆቿ እግር ኳስ መጫወት ማቆም እንዳለባት ሲነግሯት እንደነበረ ታስታውሳለች። "እኔ ግን ይህ ሁሉ አመለካከት ወደ ኋላ አላስቀረኝም። ዓላማዬ አድርጌ ይዤው ስለነበረ ማንም ሊያስቆመኝ አልቻለም። ቤተሰቦቼም ይህን ሲረዱ እኔን መደገፍ ጀመሩ" ትላለች። ሴናፍ ተማሪ እያለች ፍቅሯ ለእግር ኳስ እንጂ ለትምህርት አልነበረም። በዚህም ብዙ ጊዜዋን የምታሳለፍው ኳስ በመጫወት ነበር። "አገርን ወክሎ እንደመሳተፍ የሚያስደስት ነገር የለም" የምትለው ሴናፍ፤ በ2011 በሁለት ዘርፎች የውድድር አሸናፊ ነበረች። በኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 21 ጎሎችን በማሰቆጠር ኮከብ ግብ አግቢ እና የውድድር ዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ተብላ ተሸልማለች። ክለቧ አዳማም፣ የውድድሩ ሻምፒዮን ሆኖ እንዲጨርስ የራሷን አስተዋጽኦ አበርክታለች። የ25 ዓመቷ እግር ኳሰኛ ሴናፍ፤ ወደፊት በእግር ኳሱ ዓለም ፕሮፌሽናል ተጫዋች ሆና መቀጠል ምኞቷ ነው። "አንድ ሰው ከቆረጠ እና በያዘው ላይ ካተኮረ ያሰበበትን ማሳካት አይሳነውም" በማለት ከራሷ የህይወት ተሞክሮ በመነሳት የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋችነት ህልሟን እንደምታሳካ በልበ ሙሉነት ትናገራለች። አንድነት ነገር ማሳካት እንደማይቻል የምናስብ ከሆነ ከስኬት መድረስ እንችልም ስለዚህ ያሰብነው እንዲሳካ በቁርጠኝነት መስራት ይኖርብናል ትላለች። ሴናፍ የኔይማር ጁኒየር አድናቂ መሆኗን ትናገራለች።
የሉሲዎቹና የአዳማ ክለብ ጎል አዳኝ ሴናፍ ዋቁማ የሉሲዎቹና የአዳማ ክለብ ጎል አዳኝ የፊት መስመር ተጫዋች ነች፤ ሴናፍ ዋቁማ። ትውልድና እድገቷ በነቀምት ነው። ለእግር ኳስ ያላትን ፍቅር ስትገልጽ "ትምህርት ቤት እያለሁ ለኳስ ካለኝ ፍቅር የተነሳ እጫወት የነበረው ከወንዶቹ ጋር ነበር" ትላለች። ትኩረቷን ሙሉ በሙሉ ለኳስ ከሰጠች በኋላ ነቀምት በሚገኙ የእግር ኳስ ፕሮጀክቶች ውስጥ ታቅፋ ስልጠናዎችን ወስዳለች። ከዚያም በነበራት አቋም ተመርጣ ወደ አሰላ በመሄድ ለአራት ዓመታት ስልጠና ወስዳለች። • "በሀገራችን ከሶስት ሴቶች አንዷ ላይ ጾታዊ ጥቃት ይደርሳል" • በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን አቃቤ ሕግ አስታወቀ • የሕዝብ እንደራሴዎችን ጎራ አስለይቶ ያሟገተው ሕግ "የሰዎች አመለካከት ጥሩ አልነበረም" የምትለው ሴናፍ፤ በእግር ኳስ ህይወቷ ማህበረሰቡ ሴቶች እግር ኳስ መጫወታቸውን በበጎ አለመመልከቱ የእግር ኳስ ህይወቷን ፈታኝ አድርጎባት እንደነበረ ታስረዳለች። "ሴቶች ከቤት መውጣት የለባቸውም የሚል አመለካከት ነበር። እግር ኳስ መጫወት ደግሞ እንደ ሃፍረት ነበር የሚቆጠረው" የምትለው ሴናፍ፤ የማህብረሰቡ አመለካከት በወላጆቿ ላይ ጭምር ጫና በማሳደሩ ወላጆቿ እግር ኳስ መጫወት ማቆም እንዳለባት ሲነግሯት እንደነበረ ታስታውሳለች። "እኔ ግን ይህ ሁሉ አመለካከት ወደ ኋላ አላስቀረኝም። ዓላማዬ አድርጌ ይዤው ስለነበረ ማንም ሊያስቆመኝ አልቻለም። ቤተሰቦቼም ይህን ሲረዱ እኔን መደገፍ ጀመሩ" ትላለች። ሴናፍ ተማሪ እያለች ፍቅሯ ለእግር ኳስ እንጂ ለትምህርት አልነበረም። በዚህም ብዙ ጊዜዋን የምታሳለፍው ኳስ በመጫወት ነበር። "አገርን ወክሎ እንደመሳተፍ የሚያስደስት ነገር የለም" የምትለው ሴናፍ፤ በ2011 በሁለት ዘርፎች የውድድር አሸናፊ ነበረች። በኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 21 ጎሎችን በማሰቆጠር ኮከብ ግብ አግቢ እና የውድድር ዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ተብላ ተሸልማለች። ክለቧ አዳማም፣ የውድድሩ ሻምፒዮን ሆኖ እንዲጨርስ የራሷን አስተዋጽኦ አበርክታለች። የ25 ዓመቷ እግር ኳሰኛ ሴናፍ፤ ወደፊት በእግር ኳሱ ዓለም ፕሮፌሽናል ተጫዋች ሆና መቀጠል ምኞቷ ነው። "አንድ ሰው ከቆረጠ እና በያዘው ላይ ካተኮረ ያሰበበትን ማሳካት አይሳነውም" በማለት ከራሷ የህይወት ተሞክሮ በመነሳት የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋችነት ህልሟን እንደምታሳካ በልበ ሙሉነት ትናገራለች። አንድነት ነገር ማሳካት እንደማይቻል የምናስብ ከሆነ ከስኬት መድረስ እንችልም ስለዚህ ያሰብነው እንዲሳካ በቁርጠኝነት መስራት ይኖርብናል ትላለች። ሴናፍ የኔይማር ጁኒየር አድናቂ መሆኗን ትናገራለች።
https://www.bbc.com/amharic/51505693
2health
ኮሮናቫይረስ፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለዓለም ያስገኛቸው አስር ትሩፋቶች
በአንድ ዓመት ውስጥ ከ115 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የያዘውና ከ2.5 በላይ ሰዎችን ደግሞ ለሞት ዳረገውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመጣል ሳይንስ፣ ዕውቀትና ትብብር ተጣምረው ብዙ ታግለዋል፤ እየታገሉም ይገኛሉ። ቫይረሱ አዲስ ዝርያ ማፍራቱን ተከትሎ በሚቀጥሉት ሳምንታትና ወራት ምን ሊከሰት እንደሚችል መገመት ቢያዳግትም አንድ ዓመት የሞላው ወረርሽኝ ብዙ አስተምሮናል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ብዙዎችን ቢቀጥፍም ከዚህ በፊት በአዕምሯችን ውል ያላሉ በጎ ትሩፋቶችን አስገኝቷል ይላሉ ባለሙያዎች። ከእዚህ ውስጥም እስቲ አስሩን ከኮቪድ-19 ትሩፋቶች እንመልከት። 1 - ኮቪድ-19 የወባን ማዕረግ መረከቡ ከአንድ ዓመት በፊት ማለትም ስለወረርሽኙ መዘገብ ከጀመረ ከአንድ ወር በኋላ በሕክምና መጽሔቶች ላይ ከ164 በላይ ፅሑፎች ስለኮቪድ-19 ታትሞ ወጥቷል። ከአንድ ዓመት በኋላ ዛሬ ስለወረርሽኙ የተፃፉ የጥናትና የምርምር ዘገባዎች ቁጥር በ600 እጥፍ ጨምሮ ከ100 ሺህ በላይ ሆኗል። ይህን ማዕረግ ቀድሞ ይዞ ነበር ወባ ነበር። ዘንድሮ ለወትሮው አብዝተን ከምንሰማቸው የበሽታ ዘገባዎች በላይ ስለ ኮቪድ-19 በብዛት ይነገራል። በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ ከወባ በላይ ስለኮቪድ-19 የበለጠ ዕውቀት አለ። 2 - ከ200 በላይ ክትባቶች ከአንድ ዓመት በፊት ኮሮናቫይረስን ለመከላከል ይረዳሉ ተብለው ጥናት ሲደረግባቸው የነበሩ ክትባቶች ቁጥር ስምንት ነበር። ባዮሬንደር የተሰኘው ድርጅት እንደሚለው አሁን ከ195 በላይ ክትባቶች በተለያዩ የሂደት ደረጃ ላይ ሲሆኑ 71 ያህሉ ደግሞ በሙከራ ደረጃ ላይ ናቸው። ፀረ-ኮሮናቫይረስ ክትባቶችን ለማምረት የወጣውን ወጪ፣ ትብብርና ጥናት ያክል ለሌሎች በሽታዎች ይህን የመሰለ ርብርብ አልተደረገም ይላሉ ባለሙያዎች። በዚህ ጥናት ላይ ሕዝቡ፣ የግል ድርጅቶች፣ አጥኚዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ መድኃኒት አምራቾች፣ እንዲሁም መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተሳትፈዋል። እርግጥ ነው አንዳንድ የጥናት ሂደቶች በእንጭጭ ቀርተዋል። ነገር ግን የዓለም ጤና ድርጅተ ያፀደቃቸው ደግሞ በርካታ ናቸው። ፋይዘር/ባዮንቴክ፣ ሞደርና፣ አስታራዜኔካ/ኦክስፎርድ፣ ስፑትኒክ 5 እንዲሁም የቻይናው ሲኖፋርምና ጎል ተብለው የሚጠቀሱ ክትባቶች ናቸው። ቢያንስ 20 ሌሎች ክትባቶች ደግሞ የሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ምናልባትም በሚቀጥሉት ሳምንታት አሊያም ወራት ውጤታቸው ተለይቶ ወደ ሥራ ሊገቡ ይችላሉ። 3 - የክትባቶች የጎንዮሽ ጉዳት አነስተኛ መሆን የክትባቶች ትልቁ ደንቃራ በሳይንስ ቋንቋ አናፊላክሲስ ይባላል። ይህም የክትባቶቹ ጎንዮሽ ጉዳት ሲሆን ክትባት ከተወሰደ በኋላ ወዲያው የሚከሰት ሲሆን እስከሞት ሊያደርስ ይችላል። አሜሪካ ውስጥ ክትባቱ በተሰጠበት የመጀመሪያው ወር ላይ የተሠራ ጥናት እንደሚጠቁመው 17.5 ሚሊየን ክትባቶች ተሰጥዋል። ከእነዚህ የፋይዘርና የሞደርና ክትባቶችን ከወሰዱ ሰዎች መካከል 66ቱ ብቻ ናቸው ይህ የጎንዮሽ ጉዳት የገጠማቸው። ይህ በሚሊዮንኛ ሲሰላ ከአንድ ሚሊዮን ሰው 4 ብቻ ነው ማለት ነው። በመቶኛ ሲሰላ ደግሞ 0.0003 ይሆናል። ከ66ቱ ሰዎች መካከል 21 ሰዎች ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ችግር ገጥሟቸው ያውቃል። በዚህ የጎንዮሽ ጉዳት ምክንያት እስከዛሬ ድረስ የሞተ ሰው የለም። የዚህ ጥናት ውጤት ለጊዜውም ቢሆን የሚጠቁመው ክትባቶች ከጉዳታቸው ጥቅማቸው በእጅጉ እንደሚያመዝን መሆኑ ነው። በተለይ ደግሞ የሞደርና ክትባት ከሌሎቹ በላቀ ደኅንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ ተነግሯል። 4 - ክትባቶች ውጤታማ ናቸው እስራኤል በርካታውን ዜጎቿን በመከተብ ከዓለም ቀዳሚ ናት። እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ ከ3.67 በላይ እስራኤላዊያን የፋይዘርን የመጀመሪያ ዙር ክትባት ወስደዋል። ይህ ከአገሪቱ ሕዝብ 40 በመቶውን የሚይዝ ነው። ከ28 በመቶ በላዩ ደግሞ ሁለተኛውን ዙር ክትባት ወስደዋል። ከ60 ዓመት በላይ ከሆናቸው ዜጎቿ መካከል ደግሞ 80 በመቶው ተከትበዋል። የክትባቶቹ የመጀመሪያ ዙር ውጤት እንደሚያሳየው ክትባቶች እስካሁን ድረስ ባለው ጥናት መሠረት ውጤታማ መሆናቸውን ነው። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም ከጊዜ ጊዜ እየቀነሰ መጥቷል፤ በለተይ ደግሞ ዕድሜያቸውን 60ና ከዚያ በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ። ሁለቱንም ዙር ክትባት ከወሰዱ 523 ሺህ እስራኤላዊያን መካከል 544 ሰዎች ላይ ብቻ ነው ኮቪድ-19 የተገኘው። እስካሁን ድረስ የተመዘገበ ሞት ግን የለም። ነገር ግን የክትባቱን ውጤታማነት ለማየት የግድ ወደ እስራኤል መሻገር አይጠበቅብንም። የክትባቶችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ በአዛውንቶች ማቆያ ማዕከላት የሚኖሩና አሁን ክትባቱ የደረሳቸውን ሰዎች ቁጥር ማየት ይቻላል። በአብዛኞቹ የአውሮፓ አገራት ያሉ በዕድሜ የገፉ ሰዎች አሁን ክትባቱን ካገኙ በኋላ የመያዝ ዕድላቸውና የሞት ቁጥር በእጅጉ እየቀነሰ ነው። 5 - በክትባት ላይ መተማመን መጨመር በዓለም ዙሪያ እስካሁን ድረስ ከ160 ሚሊዮን በላይ ብልቃጦች ጥቅም ላይ ውለዋል። የዚያኑ ያህል ሰዎች በክትባት ላይ ያላቸው መተማንም ከዕለት ዕለት እየጨመረ ነው። ለምሳሌ በአውሮፓ፣ እስያና አውስትራሊያ አገራት የሚኖሩ 13 ሺህ 500 ሰዎችን መሠረት አድርጎ አንድ ጥናት ተሠርቷል። ጥናቱ ከኅዳር እስከ ጥር ባለው ጊዜ የተሠራ ነው። ኅዳር ላይ አገራት ክትባት መስጠት ከመጀመራቸው በፊት 40 በመቶ ሰዎች ብቻ ነበሩ በክትባቱ ሙሉ እምነት የነበራቸው። ነገር ግን ጥር ላይ ከ50 በመቶ በላይ ሰዎች በክትባቶች ላይ ያላቸው እምነት ሲጨምር ክትባቱ የጎንዮሽ ጉዳት አለው ብለው የሚያምኑ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ቀንሷል። በዩናይት ኪንግደም ካሉ ሰዎች በተሰበሰበ መረጃ መሠረት ከ78 በመቶ በላይ ሰዎች ክትባቱን ለመውሰድ ዝግጁ ናቸው። 6 - በሽታን የመከላከል አቅም ከ8 ወራት በላይ አይዘልቅም አንድ ሰው በኮቪድ-19 ተይዞ ከተሻለው በኋላ የሚኖረው የመከላከል አቅም ምን ያህል ነው? የሚለውን ለመለየት የተሠሩ ጥናቶች ሙሉ ገፅታውን አያሳዩም። የበሽታ የመከላከል አቅም ምን ያህል ይቆያል የሚለውን መለየት እጅግ ጠቃሚ ነው። ይህ የክትባት የመከላከል አቅምን ለመለየትም ያስችላል። ምንም እንኳ የእያንዳንዱ ሰው በሽታን የመከላከል አቅም ቢለያይም በበርካታ አገራት የተሠሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቆይታው ከ6 አስከ 8 ወራት መሆኑን ነው። ይህ የመከላከል አቅም ቆይታ ሰዎች በበሽታው እጅጉን ተጠቁም አልተጠቁም ተመሳሳይ ነው። 7 - በጣም ለተጎዱ ሰዎች መድኃኒት ፍለጋ ኮቪድ-19 ከሳንባ ምች [ኒሞኒያ] በላይ የከፋ መሆኑን መረዳት ተችሏል። ምንም እንኳ ኮሮናቫይረስን ነጥሎ የሚያጠቃ መድኃኒት ባይኖርም በጣም ለተጎዱ ሰዎች ከሞት የሚታደጉ መድኃኒቶችን ደባልቆ መስጠት ተችሏል። እኒህን መድኃኒቶች ደባልቆ መስጠት ያለውን ሚና የሚለዩ ከ400 በላይ ጥናቶች የሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። በየቀኑ የኮሮናቫይረስ በሽታ ለጠናባቸው ሰዎች የሚሆኑ መድኃኒቶች ቅመማ ከጊዜ ጊዜ እየተሻሻለ መጥቷል። 8 - ጉንፋን መጥፋት ኮሮናቫይረስ ዓለምን ማዳረስ በጀመረበት ወቅት የነበረው አንዱ ፍራቻ በክረምት ወራት ከሚነሱ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ጋር እንዴት ያደርገናል የሚለው ነበር። እንደ ጉንፋን፣ ኢንፍሉዌንዛና አስም የመሳሰሉ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቁ በሽታዎች ወደ ሳንባ ምችና ብሮንካይትስ ሊያመሩ ይችላሉ። እነዚህ በሽታዎች በበርካታ የዓለማችን ክፍሎች በተለይ ደግሞ ተጋላጭ በሚባሉቱ አገራት እስከ ሞት የሚያደርሱ ናቸው። በኢንፍሉዌንዛና በኮሮናቫይረስ በአንድ ጊዜ የተጠቁ ሰዎች የመሞት ዕድል በኮቪድ-19 ብቻ ከተያዙት ላቅ ያለ ነው። በተለይ ደግሞ ዕድሜያቸው ከ70 ዓመት በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ አደጋው ይጨምራል። ነገር ግን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎችን መጠቀም እንደ ጉንፋን ያሉ በሽታዎች እንዲቀንሱ ትልቅ ምክንያት ሆኗል። መልካሙ ዜና በክረምት ወራት የሚከሰቱ በሽታዎች ጉዳት እንደሌላው ጊዜ አለመሆን ነው። ነገር ግን ይህ ጉዳይ በቀጣዩ ዓመት ክረምት ተመልሶ ሊመጣ እንደሚችል ይገመታል። ኢንፍሉዌንዛ ኮሮናቫይረስ በባሕሪ በጣም የተለያዩ በሽታዎች መሆናቸውን ልብ ማለት ያሻል። 9 - የበሽታውን ዕድገት በየደቂቃው መከታተል እንችላለን አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ጥቅም ላይ እየዋሉ ባሉ ክትባቶች ላይ ያለው ኃያልነት እስካሁን በውል አልተረጋገጠም። ቢሆንም አንድ መልካም ዜና አለ። አሁን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ላይ እያንዳንዱን ለውጥ በቅርበት መከታተል ይቻላል። ሳይንቲስቶች የበሽታውን ዕድገት የሚያጠኑበትን መንገድ አዳብረዋል። ጥናቶቹ ካለፈው ዓመት የካቲት እስካሁድ ድረስ ያለውን የበሽታውን ዕድገት ከሥር ከሥሩ የሚከታተሉ ናቸው። እኒህ ጥናቶች የበሽታውን አካሄድ አጥንቶ መፍትሄ ለማበጀት ይረዳሉ። የአንድን ወረርሽኝ እያንዳንዱ ዕድገትና ለውጥ በየደቂቃው ማጥናት የተቻለው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። 10 - የወረርሽኙ መቀዛቀዝ ተደጋግሞ እንደተጠቀሰው የኮሮናቫይረስ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል የሚለው አሁንም እርግጠኛ መልስ አልተገኘለትም። ነገር ግን እስካሁን የነበረውን አካሄድ በማየት በየጊዜ የወረርሽኙ ማዕበሎች ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት አያዳግትም። ቢሆንም ተፅዕኗቸው ከዚህ በፊት ከነበረው ዝቅ እያለ የሚመጣ ነው። አሁን እንደ መልካም ዜና እየተቆጠረ ያለው ወረርሽኙ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከዚህ በፊት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር መቀዛቀዝ ማሳየቱ ነው። ለዚህ እንደምክንያት ከሚጠቀሱ ነገሮች መካከል አንደኛው በሽታውን የመከላከል አቅም መዳበር ነው። ለመከላከል አቅም አንዱ አጋዥ መሣሪያ ደግሞ ክትባት ነው። ይህም የሽታውን መስፋፋት ለመግታት ትልቅ ተስፋን ሰጥቷል።
ኮሮናቫይረስ፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለዓለም ያስገኛቸው አስር ትሩፋቶች በአንድ ዓመት ውስጥ ከ115 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የያዘውና ከ2.5 በላይ ሰዎችን ደግሞ ለሞት ዳረገውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመጣል ሳይንስ፣ ዕውቀትና ትብብር ተጣምረው ብዙ ታግለዋል፤ እየታገሉም ይገኛሉ። ቫይረሱ አዲስ ዝርያ ማፍራቱን ተከትሎ በሚቀጥሉት ሳምንታትና ወራት ምን ሊከሰት እንደሚችል መገመት ቢያዳግትም አንድ ዓመት የሞላው ወረርሽኝ ብዙ አስተምሮናል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ብዙዎችን ቢቀጥፍም ከዚህ በፊት በአዕምሯችን ውል ያላሉ በጎ ትሩፋቶችን አስገኝቷል ይላሉ ባለሙያዎች። ከእዚህ ውስጥም እስቲ አስሩን ከኮቪድ-19 ትሩፋቶች እንመልከት። 1 - ኮቪድ-19 የወባን ማዕረግ መረከቡ ከአንድ ዓመት በፊት ማለትም ስለወረርሽኙ መዘገብ ከጀመረ ከአንድ ወር በኋላ በሕክምና መጽሔቶች ላይ ከ164 በላይ ፅሑፎች ስለኮቪድ-19 ታትሞ ወጥቷል። ከአንድ ዓመት በኋላ ዛሬ ስለወረርሽኙ የተፃፉ የጥናትና የምርምር ዘገባዎች ቁጥር በ600 እጥፍ ጨምሮ ከ100 ሺህ በላይ ሆኗል። ይህን ማዕረግ ቀድሞ ይዞ ነበር ወባ ነበር። ዘንድሮ ለወትሮው አብዝተን ከምንሰማቸው የበሽታ ዘገባዎች በላይ ስለ ኮቪድ-19 በብዛት ይነገራል። በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ ከወባ በላይ ስለኮቪድ-19 የበለጠ ዕውቀት አለ። 2 - ከ200 በላይ ክትባቶች ከአንድ ዓመት በፊት ኮሮናቫይረስን ለመከላከል ይረዳሉ ተብለው ጥናት ሲደረግባቸው የነበሩ ክትባቶች ቁጥር ስምንት ነበር። ባዮሬንደር የተሰኘው ድርጅት እንደሚለው አሁን ከ195 በላይ ክትባቶች በተለያዩ የሂደት ደረጃ ላይ ሲሆኑ 71 ያህሉ ደግሞ በሙከራ ደረጃ ላይ ናቸው። ፀረ-ኮሮናቫይረስ ክትባቶችን ለማምረት የወጣውን ወጪ፣ ትብብርና ጥናት ያክል ለሌሎች በሽታዎች ይህን የመሰለ ርብርብ አልተደረገም ይላሉ ባለሙያዎች። በዚህ ጥናት ላይ ሕዝቡ፣ የግል ድርጅቶች፣ አጥኚዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ መድኃኒት አምራቾች፣ እንዲሁም መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተሳትፈዋል። እርግጥ ነው አንዳንድ የጥናት ሂደቶች በእንጭጭ ቀርተዋል። ነገር ግን የዓለም ጤና ድርጅተ ያፀደቃቸው ደግሞ በርካታ ናቸው። ፋይዘር/ባዮንቴክ፣ ሞደርና፣ አስታራዜኔካ/ኦክስፎርድ፣ ስፑትኒክ 5 እንዲሁም የቻይናው ሲኖፋርምና ጎል ተብለው የሚጠቀሱ ክትባቶች ናቸው። ቢያንስ 20 ሌሎች ክትባቶች ደግሞ የሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ምናልባትም በሚቀጥሉት ሳምንታት አሊያም ወራት ውጤታቸው ተለይቶ ወደ ሥራ ሊገቡ ይችላሉ። 3 - የክትባቶች የጎንዮሽ ጉዳት አነስተኛ መሆን የክትባቶች ትልቁ ደንቃራ በሳይንስ ቋንቋ አናፊላክሲስ ይባላል። ይህም የክትባቶቹ ጎንዮሽ ጉዳት ሲሆን ክትባት ከተወሰደ በኋላ ወዲያው የሚከሰት ሲሆን እስከሞት ሊያደርስ ይችላል። አሜሪካ ውስጥ ክትባቱ በተሰጠበት የመጀመሪያው ወር ላይ የተሠራ ጥናት እንደሚጠቁመው 17.5 ሚሊየን ክትባቶች ተሰጥዋል። ከእነዚህ የፋይዘርና የሞደርና ክትባቶችን ከወሰዱ ሰዎች መካከል 66ቱ ብቻ ናቸው ይህ የጎንዮሽ ጉዳት የገጠማቸው። ይህ በሚሊዮንኛ ሲሰላ ከአንድ ሚሊዮን ሰው 4 ብቻ ነው ማለት ነው። በመቶኛ ሲሰላ ደግሞ 0.0003 ይሆናል። ከ66ቱ ሰዎች መካከል 21 ሰዎች ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ችግር ገጥሟቸው ያውቃል። በዚህ የጎንዮሽ ጉዳት ምክንያት እስከዛሬ ድረስ የሞተ ሰው የለም። የዚህ ጥናት ውጤት ለጊዜውም ቢሆን የሚጠቁመው ክትባቶች ከጉዳታቸው ጥቅማቸው በእጅጉ እንደሚያመዝን መሆኑ ነው። በተለይ ደግሞ የሞደርና ክትባት ከሌሎቹ በላቀ ደኅንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ ተነግሯል። 4 - ክትባቶች ውጤታማ ናቸው እስራኤል በርካታውን ዜጎቿን በመከተብ ከዓለም ቀዳሚ ናት። እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ ከ3.67 በላይ እስራኤላዊያን የፋይዘርን የመጀመሪያ ዙር ክትባት ወስደዋል። ይህ ከአገሪቱ ሕዝብ 40 በመቶውን የሚይዝ ነው። ከ28 በመቶ በላዩ ደግሞ ሁለተኛውን ዙር ክትባት ወስደዋል። ከ60 ዓመት በላይ ከሆናቸው ዜጎቿ መካከል ደግሞ 80 በመቶው ተከትበዋል። የክትባቶቹ የመጀመሪያ ዙር ውጤት እንደሚያሳየው ክትባቶች እስካሁን ድረስ ባለው ጥናት መሠረት ውጤታማ መሆናቸውን ነው። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም ከጊዜ ጊዜ እየቀነሰ መጥቷል፤ በለተይ ደግሞ ዕድሜያቸውን 60ና ከዚያ በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ። ሁለቱንም ዙር ክትባት ከወሰዱ 523 ሺህ እስራኤላዊያን መካከል 544 ሰዎች ላይ ብቻ ነው ኮቪድ-19 የተገኘው። እስካሁን ድረስ የተመዘገበ ሞት ግን የለም። ነገር ግን የክትባቱን ውጤታማነት ለማየት የግድ ወደ እስራኤል መሻገር አይጠበቅብንም። የክትባቶችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ በአዛውንቶች ማቆያ ማዕከላት የሚኖሩና አሁን ክትባቱ የደረሳቸውን ሰዎች ቁጥር ማየት ይቻላል። በአብዛኞቹ የአውሮፓ አገራት ያሉ በዕድሜ የገፉ ሰዎች አሁን ክትባቱን ካገኙ በኋላ የመያዝ ዕድላቸውና የሞት ቁጥር በእጅጉ እየቀነሰ ነው። 5 - በክትባት ላይ መተማመን መጨመር በዓለም ዙሪያ እስካሁን ድረስ ከ160 ሚሊዮን በላይ ብልቃጦች ጥቅም ላይ ውለዋል። የዚያኑ ያህል ሰዎች በክትባት ላይ ያላቸው መተማንም ከዕለት ዕለት እየጨመረ ነው። ለምሳሌ በአውሮፓ፣ እስያና አውስትራሊያ አገራት የሚኖሩ 13 ሺህ 500 ሰዎችን መሠረት አድርጎ አንድ ጥናት ተሠርቷል። ጥናቱ ከኅዳር እስከ ጥር ባለው ጊዜ የተሠራ ነው። ኅዳር ላይ አገራት ክትባት መስጠት ከመጀመራቸው በፊት 40 በመቶ ሰዎች ብቻ ነበሩ በክትባቱ ሙሉ እምነት የነበራቸው። ነገር ግን ጥር ላይ ከ50 በመቶ በላይ ሰዎች በክትባቶች ላይ ያላቸው እምነት ሲጨምር ክትባቱ የጎንዮሽ ጉዳት አለው ብለው የሚያምኑ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ቀንሷል። በዩናይት ኪንግደም ካሉ ሰዎች በተሰበሰበ መረጃ መሠረት ከ78 በመቶ በላይ ሰዎች ክትባቱን ለመውሰድ ዝግጁ ናቸው። 6 - በሽታን የመከላከል አቅም ከ8 ወራት በላይ አይዘልቅም አንድ ሰው በኮቪድ-19 ተይዞ ከተሻለው በኋላ የሚኖረው የመከላከል አቅም ምን ያህል ነው? የሚለውን ለመለየት የተሠሩ ጥናቶች ሙሉ ገፅታውን አያሳዩም። የበሽታ የመከላከል አቅም ምን ያህል ይቆያል የሚለውን መለየት እጅግ ጠቃሚ ነው። ይህ የክትባት የመከላከል አቅምን ለመለየትም ያስችላል። ምንም እንኳ የእያንዳንዱ ሰው በሽታን የመከላከል አቅም ቢለያይም በበርካታ አገራት የተሠሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቆይታው ከ6 አስከ 8 ወራት መሆኑን ነው። ይህ የመከላከል አቅም ቆይታ ሰዎች በበሽታው እጅጉን ተጠቁም አልተጠቁም ተመሳሳይ ነው። 7 - በጣም ለተጎዱ ሰዎች መድኃኒት ፍለጋ ኮቪድ-19 ከሳንባ ምች [ኒሞኒያ] በላይ የከፋ መሆኑን መረዳት ተችሏል። ምንም እንኳ ኮሮናቫይረስን ነጥሎ የሚያጠቃ መድኃኒት ባይኖርም በጣም ለተጎዱ ሰዎች ከሞት የሚታደጉ መድኃኒቶችን ደባልቆ መስጠት ተችሏል። እኒህን መድኃኒቶች ደባልቆ መስጠት ያለውን ሚና የሚለዩ ከ400 በላይ ጥናቶች የሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። በየቀኑ የኮሮናቫይረስ በሽታ ለጠናባቸው ሰዎች የሚሆኑ መድኃኒቶች ቅመማ ከጊዜ ጊዜ እየተሻሻለ መጥቷል። 8 - ጉንፋን መጥፋት ኮሮናቫይረስ ዓለምን ማዳረስ በጀመረበት ወቅት የነበረው አንዱ ፍራቻ በክረምት ወራት ከሚነሱ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ጋር እንዴት ያደርገናል የሚለው ነበር። እንደ ጉንፋን፣ ኢንፍሉዌንዛና አስም የመሳሰሉ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቁ በሽታዎች ወደ ሳንባ ምችና ብሮንካይትስ ሊያመሩ ይችላሉ። እነዚህ በሽታዎች በበርካታ የዓለማችን ክፍሎች በተለይ ደግሞ ተጋላጭ በሚባሉቱ አገራት እስከ ሞት የሚያደርሱ ናቸው። በኢንፍሉዌንዛና በኮሮናቫይረስ በአንድ ጊዜ የተጠቁ ሰዎች የመሞት ዕድል በኮቪድ-19 ብቻ ከተያዙት ላቅ ያለ ነው። በተለይ ደግሞ ዕድሜያቸው ከ70 ዓመት በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ አደጋው ይጨምራል። ነገር ግን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎችን መጠቀም እንደ ጉንፋን ያሉ በሽታዎች እንዲቀንሱ ትልቅ ምክንያት ሆኗል። መልካሙ ዜና በክረምት ወራት የሚከሰቱ በሽታዎች ጉዳት እንደሌላው ጊዜ አለመሆን ነው። ነገር ግን ይህ ጉዳይ በቀጣዩ ዓመት ክረምት ተመልሶ ሊመጣ እንደሚችል ይገመታል። ኢንፍሉዌንዛ ኮሮናቫይረስ በባሕሪ በጣም የተለያዩ በሽታዎች መሆናቸውን ልብ ማለት ያሻል። 9 - የበሽታውን ዕድገት በየደቂቃው መከታተል እንችላለን አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ጥቅም ላይ እየዋሉ ባሉ ክትባቶች ላይ ያለው ኃያልነት እስካሁን በውል አልተረጋገጠም። ቢሆንም አንድ መልካም ዜና አለ። አሁን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ላይ እያንዳንዱን ለውጥ በቅርበት መከታተል ይቻላል። ሳይንቲስቶች የበሽታውን ዕድገት የሚያጠኑበትን መንገድ አዳብረዋል። ጥናቶቹ ካለፈው ዓመት የካቲት እስካሁድ ድረስ ያለውን የበሽታውን ዕድገት ከሥር ከሥሩ የሚከታተሉ ናቸው። እኒህ ጥናቶች የበሽታውን አካሄድ አጥንቶ መፍትሄ ለማበጀት ይረዳሉ። የአንድን ወረርሽኝ እያንዳንዱ ዕድገትና ለውጥ በየደቂቃው ማጥናት የተቻለው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። 10 - የወረርሽኙ መቀዛቀዝ ተደጋግሞ እንደተጠቀሰው የኮሮናቫይረስ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል የሚለው አሁንም እርግጠኛ መልስ አልተገኘለትም። ነገር ግን እስካሁን የነበረውን አካሄድ በማየት በየጊዜ የወረርሽኙ ማዕበሎች ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት አያዳግትም። ቢሆንም ተፅዕኗቸው ከዚህ በፊት ከነበረው ዝቅ እያለ የሚመጣ ነው። አሁን እንደ መልካም ዜና እየተቆጠረ ያለው ወረርሽኙ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከዚህ በፊት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር መቀዛቀዝ ማሳየቱ ነው። ለዚህ እንደምክንያት ከሚጠቀሱ ነገሮች መካከል አንደኛው በሽታውን የመከላከል አቅም መዳበር ነው። ለመከላከል አቅም አንዱ አጋዥ መሣሪያ ደግሞ ክትባት ነው። ይህም የሽታውን መስፋፋት ለመግታት ትልቅ ተስፋን ሰጥቷል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56201441
3politics
የሰላም ጥረቱ እና የተስተጓጎለው የአፍሪካ ኅብረት ንግግር ፈተናዎች
ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም. በትግራይ ውስጥ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የተለያዩ ወገኖች ሰላም እንዲወርድ ጥሪ ሲያቀርቡ እና ጥረት ሲያደርጉ እነሆ ሁለት ዓመት ሊሞላ ነው። በተለይ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መቀላጠፍ በሚል መጋቢት 15/2014 ዓ.ም. ላልተወሰነ ጊዜ የሚጸና የተኩስ አቁም ሲያውጅና የትግራይ ኃይሎችም በዚሁ ውሳኔ ሲስማሙ ለድርድር በር ይከፍታል የሚል ተስፋን ፈጥሮ ነበር። ይህንን አጋጣሚ በመጠቀምም የአፍሪካ ኅብረት፣ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት እና የቀድሞው የኬንያ መሪ ድርድር እንዲጀመርና ጦርነቱ ማብቂያ እንዲያገኝ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። በተለይ የአፍሪካ ኅብረት እና አሜሪካ በተደጋጋሚ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት እንዲሁም ከትግራይ ኃይሎች መሪዎች ጋር በአዲስ አበባ እና በመቀለ ንግግር ቢያደርጉም ይህ ነው የተባለ ጦርነቱን የሚያስቆም ውጤት ሳያገኙ ቆይተዋል። የአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ ተወካይ እና የአሜሪካ መንግሥት ልዩ ልዑክ ያደረጓቸው ጥረቶች፣ ወደ ትግራይ የሚደርሰውን የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲሻሻል ያደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲጸና በማድረግ በዘላቂነት ጦርነቱን ለማስቆም ሳያስችል ቆይቷል። በተባበሩት መንግሥታት፣ በተለያዩ አገራት ያጋጠሙ ግጭቶችን ለማስቆም በተደረጉ ጥረቶች ውስጥ የሰሩት የሕግ ባለሙያ እና ዲፕሎማቱ አቶ ባይሳ ዋቅወያ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማብቃት ፈታኝ እና ውስብስብ ሁኔታዎች እንዳሉ ይናገራሉ። ነገር ግን የትኛውም ዓይነት ጦርነት በተለይም የእርስ በርስ ጦርነቶች የሚያበቁት በተፋላሚ ወገኖች መካከል በሚደረጉ ድርድሮች በመሆኑ “የቱንም ያህል ፈታኝ ሁኔታዎች ቢኖሩም ብቸኛው መፍትሔ ድርድር ነው” ይላሉ። ሁለቱም ወገኖች ጦርነቱ በድርድር እንዲያበቃ ፍላጎት እንዳላቸው በተደጋጋሚ የገለጹ ሲሆን፣ ንግግሩን ማን ይምራው በሚለው ላይ ግን ልዩነት ነበራቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት የአፍሪካ ኅብረትን ብቸኛ ምርጫው ሲያደርግ፣ የትግራይ ኃይሎች ደግሞ የቀድሞውን የኬንያ ፕሬዝዳንት በአደራዳሪነት መርጠው ነበር። ይህም ከመነሻው ለንግግር የነበረውን ዕድል እንዲጓተት በማድረግ፣ ለመነጋገር የነበረውን ተስፋ እንዲደናቀፍ እና ጊዜ እንዲባክን አድርጎ ነበር። ነገር ግን የትግራይ ኃይሎች ሐሳባቸውን ቀይረው ንግግሩ በአፍሪካ ኅብረት በኩል እንዲካሄድ በመስማማታቸው የሰላም ተስፋው መልሶ አንሰራራ። ከዚህ በፊት ግን ሁለቱ ወገኖች ይፋዊ ባልሆነ መንገድ በአሸማጋዮች አማካኝነት መገናኘታቸው ሲነገር ነበረ። የትግራይ ኃይሎች በአንድ ደብዳቤያቸው ላይ ይህንኑ የገለጹ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ይህንን በሚመለከት ያለው ነገር የለም። የአውሮፓ ኅብረት ልዩ ተወካይ የሆኑት አኔት ቬበር በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ለኅብረቱ አባል አገራት ባሰራጩት አንድ ሰነድ ላይ፣ ሁለቱ ወገኖች በአሜሪካ አመቻችነት በተለያዩ ጊዜያት ይፋዊ ባልሆነ ሁኔታ በጂቡቲ እና በሲሸልስ መገናኘታቸውን ጠቅሰዋል። ይህም ቢሆን ግን ለጦርነቱ ማብቃት የሚያግዝ መደበኛ ድርድር ለማድረግ የሚያስችል ውጤትን ለማምጣት ሳይችል ቀርቷል። የእርስ በርስ ጦርነት መቋጫው ድርድር ነው የሚሉት በድርድር እና በዲፕሎማሲ ዓለም አቀፍ ልምድ ያላቸው አቶ ባይሳ ዋቅወያ፣ ሁለቱም ወገኖች ንግግር ለመጀመር ፍላጎታቸውን እንዲያሳዩ የተለያዩ ወገኖች ጫና እንዳለ ሆኖ፣ አምነውበት የሚገቡበት ነው የሚል አዎንታዊ አመለካከት አላቸው። ቢሆንም ግን በጦርነቱ ጅማሬ ወቅት በዓለም ላይ የነበረው ተጨባጭ ሁኔታ በአሁኑ ወቅት የለም። በተለይ ምዕራባውያን ትኩረታቸው በዩክሬንና ሩሲያ ጦርነት መያዙ፣ እንዲሁም በዓለም ዙሪያ የተከሰተው ምጣኔ ሀብታዊ ጫና ነገሮችን ለውጧል። አቶ ባይሳም ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች እና በአገር ውስጥ ያሉ ክስተቶች ተፋላሚ ወገኖች ፊታቸውን ወደ ድርድር እንዲያዞሩ አድርጓቸዋል ይላሉ። “በጦርነቱ ጅማሬ ወቅት የነበረው የምዕራባውያን ወደ አንድ ወገን ያዘነበለ ድጋፍ መመናመን፣ በትግራይ ላይ የቆየው ከበባ፣ በአገሪቱ እየተባባሰ የመጣው የምጣኔ ሀብት ቀውስ እና የኑሮ ውድነት ሁለቱንም ወገን ንግግርን እንዲመርጡ አስገድዷቸዋል።” ባለፉት ሁለት ዓመታት ጦርነቱ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ነገር ግን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሞት ዳርጓል ተብሎ ይታመናል። የተከሰተው ሰብአዊ ቀውስ ከትግራይ ባሻገር በአማራና በአፋር ክልሎች ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እርዳታ ጠባቂ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። አቶ ባይሳ ሁለቱም ወገኖች የጦርነቱን ከባድ ዋጋ ከማንም በላይ ይገነዘቡታል የሚሉት አቶ ባይሳ፤ ከተጠቀሱት ገፊ ምክንያቶች በተጨማሪ ይህ ደም አፋሳሽ የእርስ በርስ ጦርነት “ማንም አሸናፊ ሆኖ የሚወጣበት ባለመሆኑ ሁለቱም ወገኖች በንግግር ችግራቸውን ይፈታሉ” የሚል ተስፋ አላቸው። ሁለቱም ወገኖች ንግግሩን እንዲመራ የተስማሙበት አህጉራዊው ድርጀት የሰላም ሂደቱን ለመጀመር ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ለመገናኘት ማቀዱን በመግለጽ የግብዣ ጥሪውን መስከረም 21/2015 ዓ.ም. ማቅረቡ ሲነገር ለበርካቶች ድንገተኛ ነበር። በኅብረቱ የተጻፈ የጥሪ ደብዳቤ እንደሚለው በሁለቱ ወገኖች መካከል ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ንግግር ለቀጣይ ድርድር አስፈላጊ የሆኑ ዝርዝር ጉዳዮች ትኩረት እንደሚደረግባቸው አመልክቷል። ንግግሩንም ለአንድ ዓመት የኅብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ሆነው ጥረት ሲያደርጉ የነበሩት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ እንደሚመሩትና የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የቀድሞዋ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት እንደሚሳተፉ ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥትም የአፍሪካ ኅብረት ግብዣ ከዚህ በፊት ካንጸባረቃቸው አቋሞቹ ጋር የሚጣጣሙ በመሆናቸው በንግግሩ ውስጥ እንዲሳተፍ የቀረበለትን ግብዣ እንደሚቀበለው አሳወቀ። ከትግራይ ኃይሎች በኩልም የቀረበላቸውን የሰላም ንግግር ግብዣን እንደተቀበሉት ገልጸው፣ ነገር ግን ይህ ጥሪ ከመቅረቡ በፊት ከኅብረቱ ጋር ምክክር ባለመደረጉ የሰላም ውይይቱ ተሳታፊዎች፣ ታዛቢዎች እና ዋስትና ሰጪዎች፣ የጉዞ  እና የደኅንነት ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ጠይቀው ነበር። ለሁለቱም ወገኖች የንግግር ጥሪ ከቀረበ ከሳምንት በኋላ ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ውስጥ ይካሄዳል የተባለው ንግግር፣ ሁለት ዓመት ሊሞላው በተቃረበው ጦርነት ውስጥ ከታዩት ሁሉ ጉልህ እመርታ ሊሆን እንደሚችልና ለቀጣይ ሰላም መሠረት ይጥላል የሚል ተስፋን በብዙዎች ዘንድ ፈጥሮ ነበር። የአፍሪካ ኅብረትም “በሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች መካከል የሚካሄደው ይህ የሰላም ውይይት ጦርነቱን በሰላም ለመቋጨት መሠረት የሚሆኑ መርሆች፣ የአጀንዳ ጉዳዮች፣ አሰራሮች እና የጊዜ ሰሌዳዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል” ብሏል። የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራይ ኃይሎች በንግግሩ ለመሳተፍ ፈቃደኛ መሆናቸውን መግለጻቸውን ተከትሎ፣ አፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ሁለቱም ወገኖች ለግብዣው አዎንታዊ ምላሽ መስጠታቸውን አድንቀው፣ ለሰላም ዕድል እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበው ነበር። ጨምረውም ንግግሩ በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ እና የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና በቀድሞዋ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፉምዚሌ ምላምቦ-ናግኩካ የሚመራ መሆኑን ይፋ አድርጓል። ውይይቱ የሚጀመርበት ዕለት አንድ ቀን ሲቀረው አርብ ከሰዓት በኋላ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ፣ ባጋጠመ የሎጂስቲክስ እክል ምክንያት ንግግሩ ወደ ሌላ ጊዜ መተላላፉን ዘገበ። ነገር ግን ምክንያት ሆነው የሎጂስቲክስ ችግር ምን እንደሆነ ዲፕሎማቶቹ በግልጽ ያሉት ነገር አልነበረም። ይህንን ተከትሎ ደግሞ ከአሸማጋዮቹ አንዱ የሆኑት የቀድሞው የኬንያው ፕሬዝዳንት ድርድሩ የሚጀመርበት ጊዜ ካላቸው ከሌላ ዕቅድ ጋር የሚደራረብ መሆኑን ጠቅሰው መገኘት እንደማይችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መጻፋቸው ይፋ ሆነ። ነገር ግን የኡሁሩ ጥያቄ የጊዜ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ያነሷቸው ጉዳዮች እንዳሉ ደብዳቤያቸው ላይ ጠቅሰዋል። ኡሁሩ በሌላ ጊዜ በሂደቱ ለመሳተፍ እንደሚችሉ፣ ነገር ግን ንግግሩ ስለሚካሄድበት ሂደት አወቃቀር እና አፈጻጸም፣ የተጋበዙ አሸማጋዮች መመሪያ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። እንዲሁም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ማድረግ ከንግግሩ ከአጀንዳዎች ሁሉ ቀዳሚው መሆን እንዳለበት እና ይህም ለንግግሩ ትክክለኛውን ሁኔታ ይፈጥራል በማለት ጥያቄ አቅርበዋል። ዲፕሎማቱ አቶ ባይሳ እንደሚሉት፣ በዚህ ንግግር ጦርነቱን የሚቋጭ ስምምነት ላይ አይደርሱም። ሁለቱ ወገኖች ንግግር መጀመራቸው ዋነኛው ጉዳይ ነው። በዚህም ለቀጣይ ድርድር የሚያስፈልገውን ተኩስ አቁም ላይ መስማማት እንዲሁም ለጦርነቱ መቋጫ ለሚያስፈልጉ ጉዳዮች ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት እና መስማማት ቀዳሚ እንደሚሆን ያምናሉ። ነገር ግን ይህንን ጦርነት ለማብቃት የሚደረገው ድርድር ቀላል እንደማይሆን የሚጠቅሱት አቶ ባይሳ “እንዲህ አይነት ውስብስብ ፖለቲካዊ ሁኔታ ያለበት ግጭት አይቼ አላውቅም” በማለት ጦርነቱ በቶሎ እንዲያበቃ ይመኛሉ። ባለፈው ነሐሴ የተቀሰቀሰው ጦርነት እየተካሄደ ባለበት፣ ከዚህ በፊት ከታየው በተለየ ሁለቱም ወገኖች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ንግግር ለመጀመር ፍላጎታቸውን ባሳዩበት ሁኔታ በአደራዳሪዎች በኩል ገጠሙ በተባሉ እንቅፋቶች ተስተጓጉሏል። የአፍሪካ ኅብረትም በመጨረሻው ሰዓት ላይ ገጠሙት የተባሉት የሎጂስቲክስ ችግሮችን በተመለከ እንዲሁም በኡሁሩ ኬንያታ በኩል የቀረቡ ጥያቄዎችን በተመለከተ እስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም። እንዲሁም የገጠሙ ችግሮች ተቀርፈው በቀጣይ ንግግሩ መቼ ሊደረግ እንደሚችል የሚለው እየተጠበቀ ነው።
የሰላም ጥረቱ እና የተስተጓጎለው የአፍሪካ ኅብረት ንግግር ፈተናዎች ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም. በትግራይ ውስጥ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የተለያዩ ወገኖች ሰላም እንዲወርድ ጥሪ ሲያቀርቡ እና ጥረት ሲያደርጉ እነሆ ሁለት ዓመት ሊሞላ ነው። በተለይ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መቀላጠፍ በሚል መጋቢት 15/2014 ዓ.ም. ላልተወሰነ ጊዜ የሚጸና የተኩስ አቁም ሲያውጅና የትግራይ ኃይሎችም በዚሁ ውሳኔ ሲስማሙ ለድርድር በር ይከፍታል የሚል ተስፋን ፈጥሮ ነበር። ይህንን አጋጣሚ በመጠቀምም የአፍሪካ ኅብረት፣ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት እና የቀድሞው የኬንያ መሪ ድርድር እንዲጀመርና ጦርነቱ ማብቂያ እንዲያገኝ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። በተለይ የአፍሪካ ኅብረት እና አሜሪካ በተደጋጋሚ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት እንዲሁም ከትግራይ ኃይሎች መሪዎች ጋር በአዲስ አበባ እና በመቀለ ንግግር ቢያደርጉም ይህ ነው የተባለ ጦርነቱን የሚያስቆም ውጤት ሳያገኙ ቆይተዋል። የአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ ተወካይ እና የአሜሪካ መንግሥት ልዩ ልዑክ ያደረጓቸው ጥረቶች፣ ወደ ትግራይ የሚደርሰውን የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲሻሻል ያደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲጸና በማድረግ በዘላቂነት ጦርነቱን ለማስቆም ሳያስችል ቆይቷል። በተባበሩት መንግሥታት፣ በተለያዩ አገራት ያጋጠሙ ግጭቶችን ለማስቆም በተደረጉ ጥረቶች ውስጥ የሰሩት የሕግ ባለሙያ እና ዲፕሎማቱ አቶ ባይሳ ዋቅወያ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማብቃት ፈታኝ እና ውስብስብ ሁኔታዎች እንዳሉ ይናገራሉ። ነገር ግን የትኛውም ዓይነት ጦርነት በተለይም የእርስ በርስ ጦርነቶች የሚያበቁት በተፋላሚ ወገኖች መካከል በሚደረጉ ድርድሮች በመሆኑ “የቱንም ያህል ፈታኝ ሁኔታዎች ቢኖሩም ብቸኛው መፍትሔ ድርድር ነው” ይላሉ። ሁለቱም ወገኖች ጦርነቱ በድርድር እንዲያበቃ ፍላጎት እንዳላቸው በተደጋጋሚ የገለጹ ሲሆን፣ ንግግሩን ማን ይምራው በሚለው ላይ ግን ልዩነት ነበራቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት የአፍሪካ ኅብረትን ብቸኛ ምርጫው ሲያደርግ፣ የትግራይ ኃይሎች ደግሞ የቀድሞውን የኬንያ ፕሬዝዳንት በአደራዳሪነት መርጠው ነበር። ይህም ከመነሻው ለንግግር የነበረውን ዕድል እንዲጓተት በማድረግ፣ ለመነጋገር የነበረውን ተስፋ እንዲደናቀፍ እና ጊዜ እንዲባክን አድርጎ ነበር። ነገር ግን የትግራይ ኃይሎች ሐሳባቸውን ቀይረው ንግግሩ በአፍሪካ ኅብረት በኩል እንዲካሄድ በመስማማታቸው የሰላም ተስፋው መልሶ አንሰራራ። ከዚህ በፊት ግን ሁለቱ ወገኖች ይፋዊ ባልሆነ መንገድ በአሸማጋዮች አማካኝነት መገናኘታቸው ሲነገር ነበረ። የትግራይ ኃይሎች በአንድ ደብዳቤያቸው ላይ ይህንኑ የገለጹ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ይህንን በሚመለከት ያለው ነገር የለም። የአውሮፓ ኅብረት ልዩ ተወካይ የሆኑት አኔት ቬበር በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ለኅብረቱ አባል አገራት ባሰራጩት አንድ ሰነድ ላይ፣ ሁለቱ ወገኖች በአሜሪካ አመቻችነት በተለያዩ ጊዜያት ይፋዊ ባልሆነ ሁኔታ በጂቡቲ እና በሲሸልስ መገናኘታቸውን ጠቅሰዋል። ይህም ቢሆን ግን ለጦርነቱ ማብቃት የሚያግዝ መደበኛ ድርድር ለማድረግ የሚያስችል ውጤትን ለማምጣት ሳይችል ቀርቷል። የእርስ በርስ ጦርነት መቋጫው ድርድር ነው የሚሉት በድርድር እና በዲፕሎማሲ ዓለም አቀፍ ልምድ ያላቸው አቶ ባይሳ ዋቅወያ፣ ሁለቱም ወገኖች ንግግር ለመጀመር ፍላጎታቸውን እንዲያሳዩ የተለያዩ ወገኖች ጫና እንዳለ ሆኖ፣ አምነውበት የሚገቡበት ነው የሚል አዎንታዊ አመለካከት አላቸው። ቢሆንም ግን በጦርነቱ ጅማሬ ወቅት በዓለም ላይ የነበረው ተጨባጭ ሁኔታ በአሁኑ ወቅት የለም። በተለይ ምዕራባውያን ትኩረታቸው በዩክሬንና ሩሲያ ጦርነት መያዙ፣ እንዲሁም በዓለም ዙሪያ የተከሰተው ምጣኔ ሀብታዊ ጫና ነገሮችን ለውጧል። አቶ ባይሳም ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች እና በአገር ውስጥ ያሉ ክስተቶች ተፋላሚ ወገኖች ፊታቸውን ወደ ድርድር እንዲያዞሩ አድርጓቸዋል ይላሉ። “በጦርነቱ ጅማሬ ወቅት የነበረው የምዕራባውያን ወደ አንድ ወገን ያዘነበለ ድጋፍ መመናመን፣ በትግራይ ላይ የቆየው ከበባ፣ በአገሪቱ እየተባባሰ የመጣው የምጣኔ ሀብት ቀውስ እና የኑሮ ውድነት ሁለቱንም ወገን ንግግርን እንዲመርጡ አስገድዷቸዋል።” ባለፉት ሁለት ዓመታት ጦርነቱ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ነገር ግን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሞት ዳርጓል ተብሎ ይታመናል። የተከሰተው ሰብአዊ ቀውስ ከትግራይ ባሻገር በአማራና በአፋር ክልሎች ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እርዳታ ጠባቂ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። አቶ ባይሳ ሁለቱም ወገኖች የጦርነቱን ከባድ ዋጋ ከማንም በላይ ይገነዘቡታል የሚሉት አቶ ባይሳ፤ ከተጠቀሱት ገፊ ምክንያቶች በተጨማሪ ይህ ደም አፋሳሽ የእርስ በርስ ጦርነት “ማንም አሸናፊ ሆኖ የሚወጣበት ባለመሆኑ ሁለቱም ወገኖች በንግግር ችግራቸውን ይፈታሉ” የሚል ተስፋ አላቸው። ሁለቱም ወገኖች ንግግሩን እንዲመራ የተስማሙበት አህጉራዊው ድርጀት የሰላም ሂደቱን ለመጀመር ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ለመገናኘት ማቀዱን በመግለጽ የግብዣ ጥሪውን መስከረም 21/2015 ዓ.ም. ማቅረቡ ሲነገር ለበርካቶች ድንገተኛ ነበር። በኅብረቱ የተጻፈ የጥሪ ደብዳቤ እንደሚለው በሁለቱ ወገኖች መካከል ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ንግግር ለቀጣይ ድርድር አስፈላጊ የሆኑ ዝርዝር ጉዳዮች ትኩረት እንደሚደረግባቸው አመልክቷል። ንግግሩንም ለአንድ ዓመት የኅብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ሆነው ጥረት ሲያደርጉ የነበሩት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ እንደሚመሩትና የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የቀድሞዋ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት እንደሚሳተፉ ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥትም የአፍሪካ ኅብረት ግብዣ ከዚህ በፊት ካንጸባረቃቸው አቋሞቹ ጋር የሚጣጣሙ በመሆናቸው በንግግሩ ውስጥ እንዲሳተፍ የቀረበለትን ግብዣ እንደሚቀበለው አሳወቀ። ከትግራይ ኃይሎች በኩልም የቀረበላቸውን የሰላም ንግግር ግብዣን እንደተቀበሉት ገልጸው፣ ነገር ግን ይህ ጥሪ ከመቅረቡ በፊት ከኅብረቱ ጋር ምክክር ባለመደረጉ የሰላም ውይይቱ ተሳታፊዎች፣ ታዛቢዎች እና ዋስትና ሰጪዎች፣ የጉዞ  እና የደኅንነት ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ጠይቀው ነበር። ለሁለቱም ወገኖች የንግግር ጥሪ ከቀረበ ከሳምንት በኋላ ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ውስጥ ይካሄዳል የተባለው ንግግር፣ ሁለት ዓመት ሊሞላው በተቃረበው ጦርነት ውስጥ ከታዩት ሁሉ ጉልህ እመርታ ሊሆን እንደሚችልና ለቀጣይ ሰላም መሠረት ይጥላል የሚል ተስፋን በብዙዎች ዘንድ ፈጥሮ ነበር። የአፍሪካ ኅብረትም “በሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች መካከል የሚካሄደው ይህ የሰላም ውይይት ጦርነቱን በሰላም ለመቋጨት መሠረት የሚሆኑ መርሆች፣ የአጀንዳ ጉዳዮች፣ አሰራሮች እና የጊዜ ሰሌዳዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል” ብሏል። የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራይ ኃይሎች በንግግሩ ለመሳተፍ ፈቃደኛ መሆናቸውን መግለጻቸውን ተከትሎ፣ አፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ሁለቱም ወገኖች ለግብዣው አዎንታዊ ምላሽ መስጠታቸውን አድንቀው፣ ለሰላም ዕድል እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበው ነበር። ጨምረውም ንግግሩ በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ እና የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና በቀድሞዋ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፉምዚሌ ምላምቦ-ናግኩካ የሚመራ መሆኑን ይፋ አድርጓል። ውይይቱ የሚጀመርበት ዕለት አንድ ቀን ሲቀረው አርብ ከሰዓት በኋላ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ፣ ባጋጠመ የሎጂስቲክስ እክል ምክንያት ንግግሩ ወደ ሌላ ጊዜ መተላላፉን ዘገበ። ነገር ግን ምክንያት ሆነው የሎጂስቲክስ ችግር ምን እንደሆነ ዲፕሎማቶቹ በግልጽ ያሉት ነገር አልነበረም። ይህንን ተከትሎ ደግሞ ከአሸማጋዮቹ አንዱ የሆኑት የቀድሞው የኬንያው ፕሬዝዳንት ድርድሩ የሚጀመርበት ጊዜ ካላቸው ከሌላ ዕቅድ ጋር የሚደራረብ መሆኑን ጠቅሰው መገኘት እንደማይችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መጻፋቸው ይፋ ሆነ። ነገር ግን የኡሁሩ ጥያቄ የጊዜ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ያነሷቸው ጉዳዮች እንዳሉ ደብዳቤያቸው ላይ ጠቅሰዋል። ኡሁሩ በሌላ ጊዜ በሂደቱ ለመሳተፍ እንደሚችሉ፣ ነገር ግን ንግግሩ ስለሚካሄድበት ሂደት አወቃቀር እና አፈጻጸም፣ የተጋበዙ አሸማጋዮች መመሪያ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። እንዲሁም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ማድረግ ከንግግሩ ከአጀንዳዎች ሁሉ ቀዳሚው መሆን እንዳለበት እና ይህም ለንግግሩ ትክክለኛውን ሁኔታ ይፈጥራል በማለት ጥያቄ አቅርበዋል። ዲፕሎማቱ አቶ ባይሳ እንደሚሉት፣ በዚህ ንግግር ጦርነቱን የሚቋጭ ስምምነት ላይ አይደርሱም። ሁለቱ ወገኖች ንግግር መጀመራቸው ዋነኛው ጉዳይ ነው። በዚህም ለቀጣይ ድርድር የሚያስፈልገውን ተኩስ አቁም ላይ መስማማት እንዲሁም ለጦርነቱ መቋጫ ለሚያስፈልጉ ጉዳዮች ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት እና መስማማት ቀዳሚ እንደሚሆን ያምናሉ። ነገር ግን ይህንን ጦርነት ለማብቃት የሚደረገው ድርድር ቀላል እንደማይሆን የሚጠቅሱት አቶ ባይሳ “እንዲህ አይነት ውስብስብ ፖለቲካዊ ሁኔታ ያለበት ግጭት አይቼ አላውቅም” በማለት ጦርነቱ በቶሎ እንዲያበቃ ይመኛሉ። ባለፈው ነሐሴ የተቀሰቀሰው ጦርነት እየተካሄደ ባለበት፣ ከዚህ በፊት ከታየው በተለየ ሁለቱም ወገኖች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ንግግር ለመጀመር ፍላጎታቸውን ባሳዩበት ሁኔታ በአደራዳሪዎች በኩል ገጠሙ በተባሉ እንቅፋቶች ተስተጓጉሏል። የአፍሪካ ኅብረትም በመጨረሻው ሰዓት ላይ ገጠሙት የተባሉት የሎጂስቲክስ ችግሮችን በተመለከ እንዲሁም በኡሁሩ ኬንያታ በኩል የቀረቡ ጥያቄዎችን በተመለከተ እስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም። እንዲሁም የገጠሙ ችግሮች ተቀርፈው በቀጣይ ንግግሩ መቼ ሊደረግ እንደሚችል የሚለው እየተጠበቀ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c0w5l1rrxz2o
3politics
በቡርኪናፋሶ በደረሰ ጥቃት ከ130 በላይ የአንዲት መንደር ነዋሪዎች ተገደሉ
በቡርኪናፋሶ በደረሰ ጥቃት ከ130 በላይ የአንዲት ነዋሪዎች መገደላቸው ተገልጿል። በሰሜን የአገሪቷ ግዛት የደረሰው ይህ ጥቃት በታጣቂዎች የተፈፀመ ሲሆን መንግሥትም እስካሁን ከደረሱት ከፍተኛው ነው ብሏል። ሶልሃን የተባለችውን መንደር ታጣቂዎች ከበው በርካታ ቤቶችንና የአካባቢውንም ገበያ በአንድ ምሽት አቃጥለዋል። ለዚህ ጥቃት ኃላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም በድንበር አካባቢ ፅንፈኛ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ጥቃት ያደርሳሉ ይባላል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ኃላፊ ጥቃቱን "አሰቃቂ" ሲሉ በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳዘናቸውም አስታውቀዋል። ኃላፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ "ይህንን አሰቃቂና አፀያፊ ጥቃት እናወግዛለን። ጥቃቱም ፍንትው አድርጎ ያሳየን አገራት የበርካቶችን ህይወት እየቀጠፈ ያለውን ፅንፈኝነት ለመዋጋት በሚያደርጉት ጥረት አለም አቀፉ ማህበረሰብ ከፍተኛ ርብርብና ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ነው" በማለት በቃለ አቀባያቸው በኩል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የቡርኪናፋሶ ፕሬዚዳንት ሮች ካባሬ በዚህ ጥቃት ህይወታቸውን ላጡት የሶስት ቀን ኃዘን ያወጁ ሲሆን በትዊተር ገፃቸውም ባስተላለፉት መልዕክት "አነዚህ የጥፋት ኢላማዎችን ለመቋቋም በአንድነት መቆም አለብን" ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ አክለውም የነዚህን ንፁኃን ህይወት የቀጠፉትን ታጣቂዎቸም በቁጥጥር ስር ለማዋል የፀጥታ ኃይሎች መሰማራታቸውን ነው። በያዝነው ሳምንት አርብ እንዲሁ በደረሰ ሌላ ጥቃት 14 ሰዎች በአንዲት መንደር ውስጥ ተገድለዋል። ጥቃቱ የደረሰው ታዳርያት በምትባል መንደር ሲሆን አሁን ጥቃቱ ከተፈፀመባት ሶልሃን በ150 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች። በባለፈው ወር እንዲሁ በምስራቅ ቡርኪናፋሶ 30 ሰዎች ተገድለዋል። አገሪቷ ከፍተኛ የሆነ የፀጥታና ደህንንነት ችግር የገጠማት ሲሆን ልክ እንደ ሌሎች ጎረቤቶቿ አገራትም የታጠቁ ቡድኖች መንደሮችን ከበው የንፁኃንን ዜጎች ይቀጥፋሉ እንዲሁም ሰዎችን ይጠልፋሉ። ይህንንም ለመግታት በሚል መንግሥት ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ዘመቻ በግንቦት ወር ቢጀምርም የንፁኃንን ዜጎች ህይወት ከመቀጠፍ አልታደጉትም። በባለፉት ሁለት አመታት በደረሱ ጥቃቶች ከሚሊዮን በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል።
በቡርኪናፋሶ በደረሰ ጥቃት ከ130 በላይ የአንዲት መንደር ነዋሪዎች ተገደሉ በቡርኪናፋሶ በደረሰ ጥቃት ከ130 በላይ የአንዲት ነዋሪዎች መገደላቸው ተገልጿል። በሰሜን የአገሪቷ ግዛት የደረሰው ይህ ጥቃት በታጣቂዎች የተፈፀመ ሲሆን መንግሥትም እስካሁን ከደረሱት ከፍተኛው ነው ብሏል። ሶልሃን የተባለችውን መንደር ታጣቂዎች ከበው በርካታ ቤቶችንና የአካባቢውንም ገበያ በአንድ ምሽት አቃጥለዋል። ለዚህ ጥቃት ኃላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም በድንበር አካባቢ ፅንፈኛ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ጥቃት ያደርሳሉ ይባላል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ኃላፊ ጥቃቱን "አሰቃቂ" ሲሉ በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳዘናቸውም አስታውቀዋል። ኃላፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ "ይህንን አሰቃቂና አፀያፊ ጥቃት እናወግዛለን። ጥቃቱም ፍንትው አድርጎ ያሳየን አገራት የበርካቶችን ህይወት እየቀጠፈ ያለውን ፅንፈኝነት ለመዋጋት በሚያደርጉት ጥረት አለም አቀፉ ማህበረሰብ ከፍተኛ ርብርብና ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ነው" በማለት በቃለ አቀባያቸው በኩል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የቡርኪናፋሶ ፕሬዚዳንት ሮች ካባሬ በዚህ ጥቃት ህይወታቸውን ላጡት የሶስት ቀን ኃዘን ያወጁ ሲሆን በትዊተር ገፃቸውም ባስተላለፉት መልዕክት "አነዚህ የጥፋት ኢላማዎችን ለመቋቋም በአንድነት መቆም አለብን" ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ አክለውም የነዚህን ንፁኃን ህይወት የቀጠፉትን ታጣቂዎቸም በቁጥጥር ስር ለማዋል የፀጥታ ኃይሎች መሰማራታቸውን ነው። በያዝነው ሳምንት አርብ እንዲሁ በደረሰ ሌላ ጥቃት 14 ሰዎች በአንዲት መንደር ውስጥ ተገድለዋል። ጥቃቱ የደረሰው ታዳርያት በምትባል መንደር ሲሆን አሁን ጥቃቱ ከተፈፀመባት ሶልሃን በ150 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች። በባለፈው ወር እንዲሁ በምስራቅ ቡርኪናፋሶ 30 ሰዎች ተገድለዋል። አገሪቷ ከፍተኛ የሆነ የፀጥታና ደህንንነት ችግር የገጠማት ሲሆን ልክ እንደ ሌሎች ጎረቤቶቿ አገራትም የታጠቁ ቡድኖች መንደሮችን ከበው የንፁኃንን ዜጎች ይቀጥፋሉ እንዲሁም ሰዎችን ይጠልፋሉ። ይህንንም ለመግታት በሚል መንግሥት ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ዘመቻ በግንቦት ወር ቢጀምርም የንፁኃንን ዜጎች ህይወት ከመቀጠፍ አልታደጉትም። በባለፉት ሁለት አመታት በደረሱ ጥቃቶች ከሚሊዮን በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57360811
2health
ኮሮናቫይረስ፡ ሁለት ጊዜ ከቡራዩ የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ያመለጡት እስረኞች እየተፈለጉ ነው
የምስራቅ ሸዋ ቦራ ወረዳ የሕግ ታራሚዎችና በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሁለት ወጣቶች ቡራዩ ወደሚገኘው የኮቪድ-19 የህክምና ማዕከል ከተወሰዱ በኋላ፤ ከህክምና ማዕከሉ ለሁለተኛ ጊዜ ማምለጣቸው እና ፖሊስ እየፈለጋቸው እንደሆነ ተነገረ። ሻሎ ፊታላ እና ኢሳቾ አበበ የተባሉት ሁለት ወጣቶች እና ሌሎች 3 ታራሚዎች በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦረ ወረዳ ባለ በእስር ቤት ሳሉ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ተከትሎ ለህክምና ወደ ቡራዩ ከተማ መወሰዳቸውን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ሚሊዮን ታፈሰ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ከላይ ስማቸው የተጠቀሰው ሁለቱ ወጣቶች፤ ወደ ቡራዩ በተወሰዱ በጥቂት ቀናቶች ውስጥ ከለይቶ ህክምና ማዕከሉ ማምለጣቸውን ኢንስፔክተር ሚሊዮን ተናግረዋል። ሁለቱ ወጣቶች ከለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከሉ ካመለጡ በኋላ ወደ ቤተሰቦቻቸው መኖሪያ ቀዬ መመለሳቸውን ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል። "ወጣቶቹ ከህክምና መስጫው አምልጠው ወደ ወረዳችን ነው የመጡት። በደረሰን ጥቆማ መሠረት ህዝቡን አስተባብረን አንድ የገጠር መንደር ውስጥ ከያዝናቸው በኋላ ወደ ቡራዩ መልሰናችዋል" ብለዋል። ወጣቶቹ ወደ ለይቶ ማቆያ ማዕከሉ እንዲመለሱ ከተደረጉ ከአራት ቀናት በኋላ ማለትም ቅዳሜ ነሐሴ 2 ለሁለተኛ ጊዜ ከማዕከሉ ማምለጣቸውን የፖሊስ አዛዡ ተናግረዋል። "ለሁለተኛ ጊዜ ማምለጣቸውን ከሰማን በኋላ ፍለጋችንን አጠናክረን እየሰራን ነው። ቤተሰቦቻቸው ጋር የሉም። ገጠር ድረስ የህብረሰብ ክፍል መረጃ አድርሰናል። እስካሁን ግን አለገኘናቸውም። ምናልባት ወደ ሌላ ወረዳዎች ውስጥ ተደብቀው ሳይቀሩ አይቀርም" ብለዋል። የቦራ ወረዳ ምክትል የጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፍጹም ወርቅነህ፤ በኮሮናቫይረስ ተይዘው "ከለይቶ ማከሚያ ማዕከል ያመለጡት ወጣቶች ጉዳይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሮብናል" ብለዋል።
ኮሮናቫይረስ፡ ሁለት ጊዜ ከቡራዩ የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ያመለጡት እስረኞች እየተፈለጉ ነው የምስራቅ ሸዋ ቦራ ወረዳ የሕግ ታራሚዎችና በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሁለት ወጣቶች ቡራዩ ወደሚገኘው የኮቪድ-19 የህክምና ማዕከል ከተወሰዱ በኋላ፤ ከህክምና ማዕከሉ ለሁለተኛ ጊዜ ማምለጣቸው እና ፖሊስ እየፈለጋቸው እንደሆነ ተነገረ። ሻሎ ፊታላ እና ኢሳቾ አበበ የተባሉት ሁለት ወጣቶች እና ሌሎች 3 ታራሚዎች በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦረ ወረዳ ባለ በእስር ቤት ሳሉ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ተከትሎ ለህክምና ወደ ቡራዩ ከተማ መወሰዳቸውን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ሚሊዮን ታፈሰ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ከላይ ስማቸው የተጠቀሰው ሁለቱ ወጣቶች፤ ወደ ቡራዩ በተወሰዱ በጥቂት ቀናቶች ውስጥ ከለይቶ ህክምና ማዕከሉ ማምለጣቸውን ኢንስፔክተር ሚሊዮን ተናግረዋል። ሁለቱ ወጣቶች ከለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከሉ ካመለጡ በኋላ ወደ ቤተሰቦቻቸው መኖሪያ ቀዬ መመለሳቸውን ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል። "ወጣቶቹ ከህክምና መስጫው አምልጠው ወደ ወረዳችን ነው የመጡት። በደረሰን ጥቆማ መሠረት ህዝቡን አስተባብረን አንድ የገጠር መንደር ውስጥ ከያዝናቸው በኋላ ወደ ቡራዩ መልሰናችዋል" ብለዋል። ወጣቶቹ ወደ ለይቶ ማቆያ ማዕከሉ እንዲመለሱ ከተደረጉ ከአራት ቀናት በኋላ ማለትም ቅዳሜ ነሐሴ 2 ለሁለተኛ ጊዜ ከማዕከሉ ማምለጣቸውን የፖሊስ አዛዡ ተናግረዋል። "ለሁለተኛ ጊዜ ማምለጣቸውን ከሰማን በኋላ ፍለጋችንን አጠናክረን እየሰራን ነው። ቤተሰቦቻቸው ጋር የሉም። ገጠር ድረስ የህብረሰብ ክፍል መረጃ አድርሰናል። እስካሁን ግን አለገኘናቸውም። ምናልባት ወደ ሌላ ወረዳዎች ውስጥ ተደብቀው ሳይቀሩ አይቀርም" ብለዋል። የቦራ ወረዳ ምክትል የጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፍጹም ወርቅነህ፤ በኮሮናቫይረስ ተይዘው "ከለይቶ ማከሚያ ማዕከል ያመለጡት ወጣቶች ጉዳይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሮብናል" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-53761489
2health
እስካሁን በኮሮናቫይረስ ያልተያዙ ሰዎች ለምን ሳይያዙ ቆዩ?
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተከስቶ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ በሁሉም አገራት የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለህመም፣ ከተወሳሰበ የጤና ችግር እና ለሞት ዳርጓል። ይህ በሽታ ከተከሰተ ሁለት ዓመት ያለፈው ሲሆን ከመተላለፊያ መንገዶቹ አመቺነት የተነሳ በአጭር ጊዜ መላውን ዓለም አዳርሷል። አንዳንዶች እንዲያውም አብዛኛው የዓለም ሕዝብ በበሽታው የመያዝ ዕድል አለው ይላሉ። ከወረርሽኙ የስርጭት ፍጥነት እና ስፋት አንጻር በርካቶች ለቫይረሱ የተጋለጡ ቢሆንም፣ ተጋላጭ ቢሆኑም በርካቶች አስካሁን በሽታው አልያዛቸውም ይባላል። ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው?
እስካሁን በኮሮናቫይረስ ያልተያዙ ሰዎች ለምን ሳይያዙ ቆዩ? የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተከስቶ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ በሁሉም አገራት የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለህመም፣ ከተወሳሰበ የጤና ችግር እና ለሞት ዳርጓል። ይህ በሽታ ከተከሰተ ሁለት ዓመት ያለፈው ሲሆን ከመተላለፊያ መንገዶቹ አመቺነት የተነሳ በአጭር ጊዜ መላውን ዓለም አዳርሷል። አንዳንዶች እንዲያውም አብዛኛው የዓለም ሕዝብ በበሽታው የመያዝ ዕድል አለው ይላሉ። ከወረርሽኙ የስርጭት ፍጥነት እና ስፋት አንጻር በርካቶች ለቫይረሱ የተጋለጡ ቢሆንም፣ ተጋላጭ ቢሆኑም በርካቶች አስካሁን በሽታው አልያዛቸውም ይባላል። ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው?
https://www.bbc.com/amharic/articles/ce9ne2g26qeo
2health
ረዥም ሰዓት መሥራት በዓመት የ 745 ሺህ ሰዎችን ህይወት እየነጠቀ ነው-ጥናት
ረዥም ሰዓት መሥራት በዓመት በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት እየነጠቀ ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡ በዓይነቱ የመጀመሪያ በሆነው ዓለም አቀፍ ጥናት መሠረት እአአ በ 2016 ከረዥም ሰዓታት ሥራ በሚከሰት ስትሮክ እና የልብ ህመም ምክንያት 745,000 ሰዎች መሞታቸውን ይፋ አደርጓል፡፡ ሪፖርቱ እንዳመለከተው በደቡብ ምስራቅ እስያ እና በምዕራብ ፓስፊክ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች በችግሩ በጣም የተጠቁ ናቸው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው ከሆነ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ችግሩ ሊባባስ ይችላል፡፡ ጥናቱ እንዳመለከተው በሳምንት ለ 55 ሰዓታት እና ከዚያ በላይ መሥራት በሳምንት 35 እስከ 40 ሰዓታት በሳምንት ከሚሠሩት ጋር ሲነፃፀር 35 በመቶ በስትሮክ እና 17 በመቶ ደግሞ በልብ ህመም የመሞት ዕድላቸው የጨመረ ነው፡፡ ከዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት (አይኤልኦ) ጋር የተደረገው ጥናቱ እንደሚያሳየው ረዘም ላለ ሰዓት በመሥራታቸው ከሞቱት መካከል ሶስት አራተኛ የሚሆኑት በመካከለኛ ዕድሜ ወይም ዕድሜያቸው የገፋ ወንዶች ናቸው፡፡ ብዙውን ጊዜ በዚህ ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡት ከብዙ አሥርት ዓመታት በኋላ ነው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ጥናት የተከሰተውን ወረርሽኝ ጊዜ አላካተተም። የድርጅቱ ባለሥልጣናት በቅርቡ ከቤት መሥራት እና የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ከረዥም የሥራ ሰዓታት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮችን ሳይጨምረው አይቀሩም ብለዋል ፡፡ "ሃገራት ወደ ብሄራዊ እንቅስቃሴ ገደብ ሲገቡ የሥራ ሰዓት በ 10 በመቶ ገደማ እንደሚጨምር የሚያሳዩ ጥቂት ማስረጃዎች አሉን" ያሉት የዓለም ጤና ድርጅት የቴክኒክ ባለሙያው ፍራንክ ፔጋ ናቸው። ሪፖርቱ እንደሚለው ከሥራ ጋር ተያያዥነት ካላቸው ህመሞች አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ከረዥም ሰዓት መሥራት ጋር እንደሚገናኙ ይገመታል፡፡ ተመራማሪዎቹ እንዳሉት ረዥም የሥራ ሰዓታት ለጤንነት መጥፎ ውጤት የሚያስከትሉባቸው ሁለት መንገዶች አሉ። አንደኛው ለጭንቀት የሚሰጠው ቀጥተኛ የፊዚዮሎጂ ምላሾች ናቸው። ሁለተኛው ደግሞ ረዥም ሰዓት የሚሠሩ ሠራተኞች እንደ ትምባሆ እና አልኮል መጠጣትን፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ካለማድረግ፣ ጤናማ ካልሆነ አመጋገብ እና የመሳሰሉ ጤናን የሚጎዱ ባህሪያትን የመልመድ ዕድላቸው ከፍተኛ በመሆኑ ነው። የሊድስ ነዋሪ የሆነው የ 32 ዓመቱ መሐንዲስ አንድሪው ፋልስ በቀድሞ ድርጅቱ ያሳለፈው ረዥም የሥራ ሰዓት በአዕምሮው እና በአካላዊ ጤንነቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ይናገራል፡፡ "ከሃምሳ እስከ 55 ሰዓት በሳምንት መሥራት የተለመደ ነበር፡፡ ለሳምንታትም ከቤቴ እርቅ ነበር" ብሏል፡፡ "ጭንቀት እና ድብርት ይመላለሱብኝ ነበር" ብሏል፡፡ "ወደታች በሚወርድበት የማያቋርጥ ሁኔታ ውስጥ ነበርኩ" ሲል ይገልጻል፡፡ ከአምስት ዓመታት በኋላ የሶፍትዌር መሐንዲስ ሆኖ ለመሥራት ሥራውን ለቀቀ፡፡ በዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሠረት ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት ለረጅም ሰዓታት የሚሠሩ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን ከጠቅላላው የዓለም ህዝብም ወደ 9 በመቶ ገደማ ናቸው፡፡ የዩኬ በብሔራዊ ስታትስቲክስ ቢሮ እንደሚለው በወረርሽኙ ወቅት ከቤት የሚሠሩ ሰዎች በሳምንት በአማካይ ስድስት ሰዓት ያለክፍያ የትርፍ ሰዓት ሥራዎችን ያከናውኑ ነበር ብሏል፡፡ ከቤታቸው የማይሠሩ ሰዎች በሳምንት በአማካይ በ 3.6 ሰዓታት የትርፍ ሰዓት ሥራ ብቻ ይሠራሉ ሲል ቢሮው አስታውቋል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት አሠሪዎች የሠራተኞቻቸውን የሥራ ጤና አደጋዎች ሲገመግሙ ይህንንም ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው ይላል፡፡ የቁርጥ ሰዓት ሥራ ምርታማነትን እንደሚያሳድግ በመታየቱ ለአሠሪዎች ጠቃሚ ይሆናል ሲሉ ፒጋ ገልጸዋል፡፡ "በኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ረዥም የሥራ ሰዓቶችን አለመጨመር የብልህ ምርጫ ነው" ብለዋል።
ረዥም ሰዓት መሥራት በዓመት የ 745 ሺህ ሰዎችን ህይወት እየነጠቀ ነው-ጥናት ረዥም ሰዓት መሥራት በዓመት በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት እየነጠቀ ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡ በዓይነቱ የመጀመሪያ በሆነው ዓለም አቀፍ ጥናት መሠረት እአአ በ 2016 ከረዥም ሰዓታት ሥራ በሚከሰት ስትሮክ እና የልብ ህመም ምክንያት 745,000 ሰዎች መሞታቸውን ይፋ አደርጓል፡፡ ሪፖርቱ እንዳመለከተው በደቡብ ምስራቅ እስያ እና በምዕራብ ፓስፊክ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች በችግሩ በጣም የተጠቁ ናቸው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው ከሆነ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ችግሩ ሊባባስ ይችላል፡፡ ጥናቱ እንዳመለከተው በሳምንት ለ 55 ሰዓታት እና ከዚያ በላይ መሥራት በሳምንት 35 እስከ 40 ሰዓታት በሳምንት ከሚሠሩት ጋር ሲነፃፀር 35 በመቶ በስትሮክ እና 17 በመቶ ደግሞ በልብ ህመም የመሞት ዕድላቸው የጨመረ ነው፡፡ ከዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት (አይኤልኦ) ጋር የተደረገው ጥናቱ እንደሚያሳየው ረዘም ላለ ሰዓት በመሥራታቸው ከሞቱት መካከል ሶስት አራተኛ የሚሆኑት በመካከለኛ ዕድሜ ወይም ዕድሜያቸው የገፋ ወንዶች ናቸው፡፡ ብዙውን ጊዜ በዚህ ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡት ከብዙ አሥርት ዓመታት በኋላ ነው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ጥናት የተከሰተውን ወረርሽኝ ጊዜ አላካተተም። የድርጅቱ ባለሥልጣናት በቅርቡ ከቤት መሥራት እና የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ከረዥም የሥራ ሰዓታት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮችን ሳይጨምረው አይቀሩም ብለዋል ፡፡ "ሃገራት ወደ ብሄራዊ እንቅስቃሴ ገደብ ሲገቡ የሥራ ሰዓት በ 10 በመቶ ገደማ እንደሚጨምር የሚያሳዩ ጥቂት ማስረጃዎች አሉን" ያሉት የዓለም ጤና ድርጅት የቴክኒክ ባለሙያው ፍራንክ ፔጋ ናቸው። ሪፖርቱ እንደሚለው ከሥራ ጋር ተያያዥነት ካላቸው ህመሞች አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ከረዥም ሰዓት መሥራት ጋር እንደሚገናኙ ይገመታል፡፡ ተመራማሪዎቹ እንዳሉት ረዥም የሥራ ሰዓታት ለጤንነት መጥፎ ውጤት የሚያስከትሉባቸው ሁለት መንገዶች አሉ። አንደኛው ለጭንቀት የሚሰጠው ቀጥተኛ የፊዚዮሎጂ ምላሾች ናቸው። ሁለተኛው ደግሞ ረዥም ሰዓት የሚሠሩ ሠራተኞች እንደ ትምባሆ እና አልኮል መጠጣትን፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ካለማድረግ፣ ጤናማ ካልሆነ አመጋገብ እና የመሳሰሉ ጤናን የሚጎዱ ባህሪያትን የመልመድ ዕድላቸው ከፍተኛ በመሆኑ ነው። የሊድስ ነዋሪ የሆነው የ 32 ዓመቱ መሐንዲስ አንድሪው ፋልስ በቀድሞ ድርጅቱ ያሳለፈው ረዥም የሥራ ሰዓት በአዕምሮው እና በአካላዊ ጤንነቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ይናገራል፡፡ "ከሃምሳ እስከ 55 ሰዓት በሳምንት መሥራት የተለመደ ነበር፡፡ ለሳምንታትም ከቤቴ እርቅ ነበር" ብሏል፡፡ "ጭንቀት እና ድብርት ይመላለሱብኝ ነበር" ብሏል፡፡ "ወደታች በሚወርድበት የማያቋርጥ ሁኔታ ውስጥ ነበርኩ" ሲል ይገልጻል፡፡ ከአምስት ዓመታት በኋላ የሶፍትዌር መሐንዲስ ሆኖ ለመሥራት ሥራውን ለቀቀ፡፡ በዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሠረት ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት ለረጅም ሰዓታት የሚሠሩ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን ከጠቅላላው የዓለም ህዝብም ወደ 9 በመቶ ገደማ ናቸው፡፡ የዩኬ በብሔራዊ ስታትስቲክስ ቢሮ እንደሚለው በወረርሽኙ ወቅት ከቤት የሚሠሩ ሰዎች በሳምንት በአማካይ ስድስት ሰዓት ያለክፍያ የትርፍ ሰዓት ሥራዎችን ያከናውኑ ነበር ብሏል፡፡ ከቤታቸው የማይሠሩ ሰዎች በሳምንት በአማካይ በ 3.6 ሰዓታት የትርፍ ሰዓት ሥራ ብቻ ይሠራሉ ሲል ቢሮው አስታውቋል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት አሠሪዎች የሠራተኞቻቸውን የሥራ ጤና አደጋዎች ሲገመግሙ ይህንንም ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው ይላል፡፡ የቁርጥ ሰዓት ሥራ ምርታማነትን እንደሚያሳድግ በመታየቱ ለአሠሪዎች ጠቃሚ ይሆናል ሲሉ ፒጋ ገልጸዋል፡፡ "በኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ረዥም የሥራ ሰዓቶችን አለመጨመር የብልህ ምርጫ ነው" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57159219
2health
በጊኒ ኢቦላ ተቀስቅሶ ሦስት ሰዎች ሞቱ
በጊኒ ኢቦላ ተቀስቅሶ 3 ሰዎች ሞቱ። ሌሎች አራት ሰዎች ደግሞ ተቅማጥ፣ ማስመለስና የመድማት ምልክቶችን እያሳዩ እንደሆነ ተነግሯል። አራቱ ሰዎች እነዚህን ምልክቶች ማሳየት የጀመሩት የአንድ በኢቦላ የሞተችን ነርስ ቀብር ከታደሙ በኋላ ነበር። ባለሥልጣናት አዲስ የተሰራ ክትባት በዓለም ጤና ድርጅት በኩል እንደሚገኝ እየተናገሩ ነው። በፈረንጆቹ ከ2013 እስከ 2016 ብቻ በምዕራፍ አፍሪካ ኢቦላ ወረርሽኝ የ11ሺ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። ወረርሽኙ ጊኒን ጨምሮ ጎረቤቶቿን ላይቤሪያንና ሴራሊዮንን በከፍተኛ ሁኔታ አጥቅቶ ነበር። ይህን ተከትሎም በርካታ ክትባቶች ተሞክረዋል። ክትባቶቹ ወረርሽኞቹን ለማቆም በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ አገልግሎት ላይ ሲውሉ ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት የጊኒ ተወካይ አልፍሬድ ጆርጅ ኪ ዜርቦ "አስፈላጊውን ክትባት ለማቅረብ የዓለም ጤና ድርጅት ከመድኃኒት አምራቾች ጋር እየተነጋገረ ነው ብለዋል። የኢቦላ ክትባት ለመጀመርያ ጊዜ በ2015 በጊኒ ሙከራ ተደርጎ ውጤት ማስገኘቱ ይታወሳል። ከክትባቱ ሌላ ታማሚው የመዳን እድሉን የሚጨምሩ መድኃኒቶች መፈብረካቸውም ይታወቃል። አሁን በጊኒ የተቀሰቀሰው ኢቦላ በአንድ ጤና ጣቢያ ትሰራ የነበረች ነርስ ታማ ከሞተች በኋላ በቀብሯ ላይ የተገኙ ሰዎች በተህዋሲው መጠቃታቸው ነው የተነገረው። ነርሷ ከሞተች ከ4 ቀናት በኋላ ነበር የተቀበረችው። ምናልባት አስክሬን በማጠብ ላይ የነበሩ ሰዎች ተህዋሲውን እንዳዛመቱ ይገመታል። ብዙውን ጊዜ በኢቦላ የሞቱ ሰዎች አስክሬን አደገኛና መርዛማ የኢቦላ ተህዋሲን የመሸከም አቅም አለው። የተህዋሲው እድሜም ከ2 ቀን እስከ 3 ሳምንት ይቆያል። ኢቦላ ቺምፓዚን ከመሰሉ እንሰሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ ተህዋሲ ነው። ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈውም በደም፣ በሰውነት ፈሳሽ ወይም ተህዋሲው ከነካው አካባቢ ሊሆን ይችላል። አሁን ሁሉም በተህዋሲው የተለከፉት እድሜያቸው ከ25 ዓመት በላይ የሆኑና የነርሷን ቀብር የታደሙት ናቸው። የወረርሽኙን መቀስቀስ ተከትሎ ሴራሊዯንና ላይቤሪያ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ። የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ለጤና ሚኒስትሮቻቸው ጉዳዩን በንቃት እንዲከታተሉ አዘዋል። የቢቢሲ ዘጋቢ ከሴራሊዯን እንደጻፈችው በአገሪቱ ከኮቪድ ተህዋሲ በላይ ሕዝቡ ስጋት ያለበት ለኢቦላ ወረርሽኝ ነው። ኢቦላ ተህዋሲ ድንገቴ ትኩሳት በመፍጠር በአጭር ሰዓት ታማሚውን በማዳከም የጡንቻ ከባድ ሕመም ፈጥሮ ጉሮሮን አቁሱሎ የሚገድል በሽታ ነው። ከዚህም ባሻገር ማስመለስ፣ ማስቀመጥ እና የውስጥና የውጭ መድማትን ያስከትላል። ታማሚዎች የሚሞቱት ብዙውን ጊዜ ፈሳሽ ከሰውነታቸው ተሟጦ ስለሚያልቅ ነው። ይህም የአንዳች ሰውነት አካል ሥራ ማቆምን ያስከትልና ለሞት ይዳርጋል።
በጊኒ ኢቦላ ተቀስቅሶ ሦስት ሰዎች ሞቱ በጊኒ ኢቦላ ተቀስቅሶ 3 ሰዎች ሞቱ። ሌሎች አራት ሰዎች ደግሞ ተቅማጥ፣ ማስመለስና የመድማት ምልክቶችን እያሳዩ እንደሆነ ተነግሯል። አራቱ ሰዎች እነዚህን ምልክቶች ማሳየት የጀመሩት የአንድ በኢቦላ የሞተችን ነርስ ቀብር ከታደሙ በኋላ ነበር። ባለሥልጣናት አዲስ የተሰራ ክትባት በዓለም ጤና ድርጅት በኩል እንደሚገኝ እየተናገሩ ነው። በፈረንጆቹ ከ2013 እስከ 2016 ብቻ በምዕራፍ አፍሪካ ኢቦላ ወረርሽኝ የ11ሺ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። ወረርሽኙ ጊኒን ጨምሮ ጎረቤቶቿን ላይቤሪያንና ሴራሊዮንን በከፍተኛ ሁኔታ አጥቅቶ ነበር። ይህን ተከትሎም በርካታ ክትባቶች ተሞክረዋል። ክትባቶቹ ወረርሽኞቹን ለማቆም በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ አገልግሎት ላይ ሲውሉ ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት የጊኒ ተወካይ አልፍሬድ ጆርጅ ኪ ዜርቦ "አስፈላጊውን ክትባት ለማቅረብ የዓለም ጤና ድርጅት ከመድኃኒት አምራቾች ጋር እየተነጋገረ ነው ብለዋል። የኢቦላ ክትባት ለመጀመርያ ጊዜ በ2015 በጊኒ ሙከራ ተደርጎ ውጤት ማስገኘቱ ይታወሳል። ከክትባቱ ሌላ ታማሚው የመዳን እድሉን የሚጨምሩ መድኃኒቶች መፈብረካቸውም ይታወቃል። አሁን በጊኒ የተቀሰቀሰው ኢቦላ በአንድ ጤና ጣቢያ ትሰራ የነበረች ነርስ ታማ ከሞተች በኋላ በቀብሯ ላይ የተገኙ ሰዎች በተህዋሲው መጠቃታቸው ነው የተነገረው። ነርሷ ከሞተች ከ4 ቀናት በኋላ ነበር የተቀበረችው። ምናልባት አስክሬን በማጠብ ላይ የነበሩ ሰዎች ተህዋሲውን እንዳዛመቱ ይገመታል። ብዙውን ጊዜ በኢቦላ የሞቱ ሰዎች አስክሬን አደገኛና መርዛማ የኢቦላ ተህዋሲን የመሸከም አቅም አለው። የተህዋሲው እድሜም ከ2 ቀን እስከ 3 ሳምንት ይቆያል። ኢቦላ ቺምፓዚን ከመሰሉ እንሰሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ ተህዋሲ ነው። ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈውም በደም፣ በሰውነት ፈሳሽ ወይም ተህዋሲው ከነካው አካባቢ ሊሆን ይችላል። አሁን ሁሉም በተህዋሲው የተለከፉት እድሜያቸው ከ25 ዓመት በላይ የሆኑና የነርሷን ቀብር የታደሙት ናቸው። የወረርሽኙን መቀስቀስ ተከትሎ ሴራሊዯንና ላይቤሪያ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ። የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ለጤና ሚኒስትሮቻቸው ጉዳዩን በንቃት እንዲከታተሉ አዘዋል። የቢቢሲ ዘጋቢ ከሴራሊዯን እንደጻፈችው በአገሪቱ ከኮቪድ ተህዋሲ በላይ ሕዝቡ ስጋት ያለበት ለኢቦላ ወረርሽኝ ነው። ኢቦላ ተህዋሲ ድንገቴ ትኩሳት በመፍጠር በአጭር ሰዓት ታማሚውን በማዳከም የጡንቻ ከባድ ሕመም ፈጥሮ ጉሮሮን አቁሱሎ የሚገድል በሽታ ነው። ከዚህም ባሻገር ማስመለስ፣ ማስቀመጥ እና የውስጥና የውጭ መድማትን ያስከትላል። ታማሚዎች የሚሞቱት ብዙውን ጊዜ ፈሳሽ ከሰውነታቸው ተሟጦ ስለሚያልቅ ነው። ይህም የአንዳች ሰውነት አካል ሥራ ማቆምን ያስከትልና ለሞት ይዳርጋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56066789
5sports
የጣልያኑ እግር ኳስ ኮከብ ቀብር ወቅት ቤቱ ተዘረፈ
በፈረንጆቹ 1982 የዓለም ዋንጫን ያነሳው የጣልያን ብሔራዊ ቡድን አባል የነበረው ፓውሎ ሮሲ ቀብር እየተፈፀመ ባለበት ወቅት ሌቦች ቤቱ ገብተው ዘረፉት። የጣልያን መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ትላንት [ቅዳሜ] የእግር ኳስ ኮከቡ ቀብር እየተፈፀመ መሆኑን አጥንተው የመጡ ሌባዎች ናቸው ቤቱን የመዘበሩት። ባፈለው ሐሙስ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ጣልያናዊው ፓውሎ ሮሲ ቀብር በሰሜን ምስራቋ ቪሴንዛ ከተማ ተፈፅሟል። አንሳ የተባለው የጣልያን ዜና ወኪል እንደዘገበው የሮሲ ባለቤት ፌዴሪካ ካፔሌቲ ከቀብር ስትመለስ ቤቷ ተበርብሮ ነው ያገኘችው። ሌቦቹ ከዘረፉት ንብረት መካከል የፓውሎ ሮሲ እጅ ሰዓትና ጥሬ ገንዘብ ይገኝበታል። ፖሊስ ጉዳዩን ምርምሬ ዘራፊዎች ማን እንደሆኑ እደርስበታለሁ ብሏል። ሮሲና ቤተሰቡ ፖጊዮ ሲዜና በተባለች የፍሎረንስ ገጠር አውራጃ ውስጥ ነው የሚኖሩት። ሮሲ በመኖሪያ አካባቢው አንድ የግብርና ኩባንያ አለው። ሮሲ በጣልያን እንደ ጀግና ነው የሚቆጠረው። ለዚህም ነው ሞቱ ብዙዎችን ያስደነገጠው። የጣልያን እግር ኳስ ወርቃማ ዘመን አባል የነበረው ሮሲ ሃገሪቱ ካፈራቻቸው ምርጥ አጥቂዎች መካከል አንዱ ተደርጎ ይቆጠራል። ለጣልያን ብሔራዊ ቡድን 48 ጊዜ ተሰልፎ 20 ኳሶችን ከመረብ አሳርፏል። በ1982ቱ የዓለም ዋንጫ ፓውሎ ሮሲ 6 ጎሎችን በማስቆጠር ሃገሩ ጣልያን ዋንጫ እንድታነሳ አግዟል። በክለብ ደረጃ ደግሞ ለቪሴንዛ እና ጁቬንቱስ ተጫውቷል። ሁለት ጊዜ የሴሪ አ ዋንጫ ማንሳትም ችሏል። ቅዳሜ ዕለት የነበረውን ቀብር በርካቶች ታድመውበታል። በተለይ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ የቪሴንዛ ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው ቀብሩን ታድመዋል። በ1982 ከሮሲ ጋር የዓለም ዋንጫን ያነሱ የቡድን አጋሮቹ የሮሲን አስከሬን ተሸክመው ወደ ሳንታ ማሪያ አኑሲያታ ካቴድራል ወስደዋል። ከቡድን አጋሮቹ መካከል ማርኮ ታርዴሊ፣ ጂያንካሪዬ አንቶጎኖኒ፣ አንቶኒዮ ካብሪኒ እንዲሁም ፉልቪዬ ኮሎቫቲ ይገኙበታል። "የቡድን አጋሬን ብቻ ሳይሆን ወንድሜን ነው ያጣሁት" ብሏል አንቶኒዮ ካብሪኒ። ከቀብሩ በፊት የሮሲ አስከሬን ቪሴንዛ ውስጥ ስታዲዮ ሮሜዬ ሜንቲ በተሰኘው ስታድየም እንዲቀመጥ ተደርጎ ነበር። የተጨዋቾቹ ደጋፊዎችና አድናቂዎች ወደ ስታደየሙ በማቅናት አበባ ሲያስቀምጡ ታይተዋል። ቅዳሜ ዕለት በተካሄዱ የሴሪ አ ጨዋታዎች ላይ ተጫዋቾች ለሟቹ ሮሲ ክብር ጥቁር አርማ ክንዳቸው ላይ አስረው ታይተዋል። ጨዋታዎቹ ከመጀመራቸው በፊትም የአንድ ደቂቃ የሕሊና ፀሎት ተካሂዶ ነበር። የሮሲ ፎቶ በስታድየሞቹ ግዙፍ ስክሪን ላይ ተሰቅሎም ታይቷል።
የጣልያኑ እግር ኳስ ኮከብ ቀብር ወቅት ቤቱ ተዘረፈ በፈረንጆቹ 1982 የዓለም ዋንጫን ያነሳው የጣልያን ብሔራዊ ቡድን አባል የነበረው ፓውሎ ሮሲ ቀብር እየተፈፀመ ባለበት ወቅት ሌቦች ቤቱ ገብተው ዘረፉት። የጣልያን መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ትላንት [ቅዳሜ] የእግር ኳስ ኮከቡ ቀብር እየተፈፀመ መሆኑን አጥንተው የመጡ ሌባዎች ናቸው ቤቱን የመዘበሩት። ባፈለው ሐሙስ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ጣልያናዊው ፓውሎ ሮሲ ቀብር በሰሜን ምስራቋ ቪሴንዛ ከተማ ተፈፅሟል። አንሳ የተባለው የጣልያን ዜና ወኪል እንደዘገበው የሮሲ ባለቤት ፌዴሪካ ካፔሌቲ ከቀብር ስትመለስ ቤቷ ተበርብሮ ነው ያገኘችው። ሌቦቹ ከዘረፉት ንብረት መካከል የፓውሎ ሮሲ እጅ ሰዓትና ጥሬ ገንዘብ ይገኝበታል። ፖሊስ ጉዳዩን ምርምሬ ዘራፊዎች ማን እንደሆኑ እደርስበታለሁ ብሏል። ሮሲና ቤተሰቡ ፖጊዮ ሲዜና በተባለች የፍሎረንስ ገጠር አውራጃ ውስጥ ነው የሚኖሩት። ሮሲ በመኖሪያ አካባቢው አንድ የግብርና ኩባንያ አለው። ሮሲ በጣልያን እንደ ጀግና ነው የሚቆጠረው። ለዚህም ነው ሞቱ ብዙዎችን ያስደነገጠው። የጣልያን እግር ኳስ ወርቃማ ዘመን አባል የነበረው ሮሲ ሃገሪቱ ካፈራቻቸው ምርጥ አጥቂዎች መካከል አንዱ ተደርጎ ይቆጠራል። ለጣልያን ብሔራዊ ቡድን 48 ጊዜ ተሰልፎ 20 ኳሶችን ከመረብ አሳርፏል። በ1982ቱ የዓለም ዋንጫ ፓውሎ ሮሲ 6 ጎሎችን በማስቆጠር ሃገሩ ጣልያን ዋንጫ እንድታነሳ አግዟል። በክለብ ደረጃ ደግሞ ለቪሴንዛ እና ጁቬንቱስ ተጫውቷል። ሁለት ጊዜ የሴሪ አ ዋንጫ ማንሳትም ችሏል። ቅዳሜ ዕለት የነበረውን ቀብር በርካቶች ታድመውበታል። በተለይ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ የቪሴንዛ ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው ቀብሩን ታድመዋል። በ1982 ከሮሲ ጋር የዓለም ዋንጫን ያነሱ የቡድን አጋሮቹ የሮሲን አስከሬን ተሸክመው ወደ ሳንታ ማሪያ አኑሲያታ ካቴድራል ወስደዋል። ከቡድን አጋሮቹ መካከል ማርኮ ታርዴሊ፣ ጂያንካሪዬ አንቶጎኖኒ፣ አንቶኒዮ ካብሪኒ እንዲሁም ፉልቪዬ ኮሎቫቲ ይገኙበታል። "የቡድን አጋሬን ብቻ ሳይሆን ወንድሜን ነው ያጣሁት" ብሏል አንቶኒዮ ካብሪኒ። ከቀብሩ በፊት የሮሲ አስከሬን ቪሴንዛ ውስጥ ስታዲዮ ሮሜዬ ሜንቲ በተሰኘው ስታድየም እንዲቀመጥ ተደርጎ ነበር። የተጨዋቾቹ ደጋፊዎችና አድናቂዎች ወደ ስታደየሙ በማቅናት አበባ ሲያስቀምጡ ታይተዋል። ቅዳሜ ዕለት በተካሄዱ የሴሪ አ ጨዋታዎች ላይ ተጫዋቾች ለሟቹ ሮሲ ክብር ጥቁር አርማ ክንዳቸው ላይ አስረው ታይተዋል። ጨዋታዎቹ ከመጀመራቸው በፊትም የአንድ ደቂቃ የሕሊና ፀሎት ተካሂዶ ነበር። የሮሲ ፎቶ በስታድየሞቹ ግዙፍ ስክሪን ላይ ተሰቅሎም ታይቷል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55292306
5sports
የዓለም ዋንጫ በየሁለት ዓመቱ እንዲካሄድ የቀረበው ሃሳብ ተቃውሞ ገጠመው
የዓለም ዋንጫ በየሁለት ዓመቱ መከናወኑ በሌሎች ስፖርቶች እና በሥርዓተ ፆታ እኩልነት ላይ ችግር ያስከትላል ይጥላል ሲል ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ተቃውሞውን ገለጸ። ፊፋ በየሁለት ዓመቱ የወንዶችን የዓለም ዋንጫ ለማካሄድ የያዘው ዕቅድ ለሌሎች ስፖርቶችና የሥርዓተ ፆታ እኩልነት ላይ ሥጋት ሊሆን ይችላል ብሎ እንደሚያምን የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (ኢይኦሲ) ገለጸ። በየሁለት ዓመቱ የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ እና በታላቁ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች መካከል በተመሳሳይ ጊዜ የመደረግ እና መደራረብ ሊፈጥር ይችላል። የኦሊምፒክ የሴቶች የእግር ኳስ ውድድርም ትልቅ ቦታ ያለው ነው። የአይኦሲ በመግለጫው ከሌሎች ውድድሮች ጋር የሚያጋጥም መደራረብ "የስፖርትን ብዝሃነት እና ልማት" ያዳክማል ብሏል። አክሎም ተጨማሪ የወንዶች ስፖርት መኖሩ ለሴቶች እግር ኳስ "ተግዳሮቶችን" ይፈጥራል ብሏል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር እና 10 የአውሮፓ ሴቶች ሊጎች በሰጡት የጋራ መግለጫ ዕቅዶቹ "በጣም ጎጂ" ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል። የሴቶች የዓለም ዋንጫ ከትልቅ የወንዶች ውድድር ጋር በተመሳሳይ ወቅት ይካሄዳል በማለት በመስከረም ወር ደግሞ የወንዶች ሊጎች የዓለም የእግር ኳስ የበላይ አካል ሃሳብን መቃወማቸውን አረጋግጠዋል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የተጫዋቾችን ደኅንነት ጨምሮ በሌሎች የስፖርት አካላት የተነሱትን ስጋቶችን እንደሚጋራ ገልጾ፣ የዓለም ዋንጫን ድግግሞሽ በእጥፍ ማሳየቱ "በተጫዋቾች አካላዊ እና አእምሯዊ ጤና ላይ የበለጠ ከባድ ጫና ይፈጥራል" ብሏል። የኦሊምፒክ የበላይ አካል ከስፖርተኛ ተወካዮች ጋር ሰፊ ምክክር እንዲደረግ የሚደረገውን ጥሪ እንደሚደግፍ ገልጾ ይህ "በግልጽ እንዳልተደረገ" አስታውቋል።
የዓለም ዋንጫ በየሁለት ዓመቱ እንዲካሄድ የቀረበው ሃሳብ ተቃውሞ ገጠመው የዓለም ዋንጫ በየሁለት ዓመቱ መከናወኑ በሌሎች ስፖርቶች እና በሥርዓተ ፆታ እኩልነት ላይ ችግር ያስከትላል ይጥላል ሲል ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ተቃውሞውን ገለጸ። ፊፋ በየሁለት ዓመቱ የወንዶችን የዓለም ዋንጫ ለማካሄድ የያዘው ዕቅድ ለሌሎች ስፖርቶችና የሥርዓተ ፆታ እኩልነት ላይ ሥጋት ሊሆን ይችላል ብሎ እንደሚያምን የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (ኢይኦሲ) ገለጸ። በየሁለት ዓመቱ የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ እና በታላቁ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች መካከል በተመሳሳይ ጊዜ የመደረግ እና መደራረብ ሊፈጥር ይችላል። የኦሊምፒክ የሴቶች የእግር ኳስ ውድድርም ትልቅ ቦታ ያለው ነው። የአይኦሲ በመግለጫው ከሌሎች ውድድሮች ጋር የሚያጋጥም መደራረብ "የስፖርትን ብዝሃነት እና ልማት" ያዳክማል ብሏል። አክሎም ተጨማሪ የወንዶች ስፖርት መኖሩ ለሴቶች እግር ኳስ "ተግዳሮቶችን" ይፈጥራል ብሏል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር እና 10 የአውሮፓ ሴቶች ሊጎች በሰጡት የጋራ መግለጫ ዕቅዶቹ "በጣም ጎጂ" ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል። የሴቶች የዓለም ዋንጫ ከትልቅ የወንዶች ውድድር ጋር በተመሳሳይ ወቅት ይካሄዳል በማለት በመስከረም ወር ደግሞ የወንዶች ሊጎች የዓለም የእግር ኳስ የበላይ አካል ሃሳብን መቃወማቸውን አረጋግጠዋል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የተጫዋቾችን ደኅንነት ጨምሮ በሌሎች የስፖርት አካላት የተነሱትን ስጋቶችን እንደሚጋራ ገልጾ፣ የዓለም ዋንጫን ድግግሞሽ በእጥፍ ማሳየቱ "በተጫዋቾች አካላዊ እና አእምሯዊ ጤና ላይ የበለጠ ከባድ ጫና ይፈጥራል" ብሏል። የኦሊምፒክ የበላይ አካል ከስፖርተኛ ተወካዮች ጋር ሰፊ ምክክር እንዲደረግ የሚደረገውን ጥሪ እንደሚደግፍ ገልጾ ይህ "በግልጽ እንዳልተደረገ" አስታውቋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58919819
2health
ኮሮናቫይረስ ፡ በቫይረሱ የተያዙ በመጀመሪያዎቹ ቀናት የማስተላለፍ እድላቸው ሰፊ መሆኑ ተጠቆመ
በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ምልክቶች በማያሳዩባቸው የመጀመሪያዎቹ አምስት ቀናት ውስጥ ቫይረሱን የማስተላለፍ ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን አንድ ጥናት ጠቆመ፡፡ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም ሳይንቲስቶች ከሆነ ቫይረሱ ያለባቸውን ቀደም ብሎ በለይቶ ማቆያ ማስገባት ስርጭቱን ለማስቆም ወሳኝ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ የጥናት ውጤቱ በላንሴት ማይክሮብ ላይ ታትሟል። ግለሰቦች የማስተላለፍ ዕድላቸው በብዙ ነገሮች ላይ የተመረኮዘ ሲሆን ራሱን የሚያባዛ ቫይረስ እና በሰውነታቸው ውስጥ ያለው የቫይረስ መጠን ስርጭቱን ከሚወስኑት መካከል ናቸው። አንዳንድ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ሰዎች የበሽታ ምልክቶች ከማሳየታቸው በፊት እና በቫይረሱ በተያዙ የመጀመሪያው ሳምንት በጣም አስተላላፊ ናቸው፡፡ በሆስፒታል ውስጥ የበሽታው ምልክት ያለባቸውንና ቫይረሱ የተገኘባቸውን ጨምሮ ሳይንቲስቶች በኮቪድ-19 ላይ 79 ዓለም አቀፍ ጥናቶችን መርምረዋል። ተመራማሪዎች ኢንፌክሽኑ ከጀመረ እስከ ዘጠኝ ቀናት ድረስ ከተወሰዱ የጉሮሮ ናሙናዎች ውስጥ ዋነኛ ቫይረሶችን መለየት እና ማባዛት ችለዋል፡፡ ምልክቶቹ በጀመሩበት ጊዜ ወይም በአምስት ቀናት ውስጥ ከፍተኛ የቫይረስ ስርጭት እንደሚኖር ከሰዎች የጉሮሮ ናሙና ማወቅ ችለዋል። ምልክቶቹ ከጀመሩ በአማካይ እስከ 17 ቀናት በአፍንጫ እና በጉሮሮ ናሙናዎች ንቁ ያልሆኑ የቫይረስ ቁርጥራጮች ተገኝተዋል፡፡ ተመራማሪዎቹ እነዚህ ቁርጥራጮቻቸው ከዘጠኝ ቀናት በላይ ቢቀጥሉም አብዛኛዎቹ ሰዎች የማስተላለፍ ዕድላቸው አነስተኛ ነው ብለዋል፡፡ የሴንት አንድሪውስ ዩኒቨርስቲ ባልደረባው ዶ/ር ሙጌ ሴቪክ ለቢቢሲ እንደገለጹት ግኝቶቹ ሰዎች ገና በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት በጣም አስተላላፊ እንደሆኑ አሳይተዋል፡፡ "ሰዎች የሕመም ምልክቶችን እንዳሳዩ እንዲለዩ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ምርመራ ውጤቶችን በሚያገኙበት ጊዜ በጣም አስተላላፊ የሚሆኑበትን ደረጃቸውን ያልፉ ይሆናል።" "ስለዚህ አንዳንድ ሰዎች ወዲያውኑ ራሳቸውን ያለዩበትን ምክንያት በመመልከት ይህንን እንዲያደርጉ ልንረዳቸው ይገባል" ብለዋል፡፡ ጥናቱ ምልክት የማያሳዩ ሰዎችን አላካተትም። ሆኖም ሌሎች ጥናቶችን እንደሚያስጠነቅቁት ሰዎች የበሽታ ምልክቶች ከማሳየታቸው በፊትም አስተላላፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ እና ምንም ዓይነት የበሽታ ምልክት ሳይኖር ቫይረሱ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ የእንግሊዝ ባለሥልጣናት እንደሚሉት ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ካላቸው ወዲያውኑ ራሳቸውን ቢያንስ ለ 10 ቀናት ማግለል አለባቸው፡፡
ኮሮናቫይረስ ፡ በቫይረሱ የተያዙ በመጀመሪያዎቹ ቀናት የማስተላለፍ እድላቸው ሰፊ መሆኑ ተጠቆመ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ምልክቶች በማያሳዩባቸው የመጀመሪያዎቹ አምስት ቀናት ውስጥ ቫይረሱን የማስተላለፍ ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን አንድ ጥናት ጠቆመ፡፡ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም ሳይንቲስቶች ከሆነ ቫይረሱ ያለባቸውን ቀደም ብሎ በለይቶ ማቆያ ማስገባት ስርጭቱን ለማስቆም ወሳኝ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ የጥናት ውጤቱ በላንሴት ማይክሮብ ላይ ታትሟል። ግለሰቦች የማስተላለፍ ዕድላቸው በብዙ ነገሮች ላይ የተመረኮዘ ሲሆን ራሱን የሚያባዛ ቫይረስ እና በሰውነታቸው ውስጥ ያለው የቫይረስ መጠን ስርጭቱን ከሚወስኑት መካከል ናቸው። አንዳንድ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ሰዎች የበሽታ ምልክቶች ከማሳየታቸው በፊት እና በቫይረሱ በተያዙ የመጀመሪያው ሳምንት በጣም አስተላላፊ ናቸው፡፡ በሆስፒታል ውስጥ የበሽታው ምልክት ያለባቸውንና ቫይረሱ የተገኘባቸውን ጨምሮ ሳይንቲስቶች በኮቪድ-19 ላይ 79 ዓለም አቀፍ ጥናቶችን መርምረዋል። ተመራማሪዎች ኢንፌክሽኑ ከጀመረ እስከ ዘጠኝ ቀናት ድረስ ከተወሰዱ የጉሮሮ ናሙናዎች ውስጥ ዋነኛ ቫይረሶችን መለየት እና ማባዛት ችለዋል፡፡ ምልክቶቹ በጀመሩበት ጊዜ ወይም በአምስት ቀናት ውስጥ ከፍተኛ የቫይረስ ስርጭት እንደሚኖር ከሰዎች የጉሮሮ ናሙና ማወቅ ችለዋል። ምልክቶቹ ከጀመሩ በአማካይ እስከ 17 ቀናት በአፍንጫ እና በጉሮሮ ናሙናዎች ንቁ ያልሆኑ የቫይረስ ቁርጥራጮች ተገኝተዋል፡፡ ተመራማሪዎቹ እነዚህ ቁርጥራጮቻቸው ከዘጠኝ ቀናት በላይ ቢቀጥሉም አብዛኛዎቹ ሰዎች የማስተላለፍ ዕድላቸው አነስተኛ ነው ብለዋል፡፡ የሴንት አንድሪውስ ዩኒቨርስቲ ባልደረባው ዶ/ር ሙጌ ሴቪክ ለቢቢሲ እንደገለጹት ግኝቶቹ ሰዎች ገና በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት በጣም አስተላላፊ እንደሆኑ አሳይተዋል፡፡ "ሰዎች የሕመም ምልክቶችን እንዳሳዩ እንዲለዩ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ምርመራ ውጤቶችን በሚያገኙበት ጊዜ በጣም አስተላላፊ የሚሆኑበትን ደረጃቸውን ያልፉ ይሆናል።" "ስለዚህ አንዳንድ ሰዎች ወዲያውኑ ራሳቸውን ያለዩበትን ምክንያት በመመልከት ይህንን እንዲያደርጉ ልንረዳቸው ይገባል" ብለዋል፡፡ ጥናቱ ምልክት የማያሳዩ ሰዎችን አላካተትም። ሆኖም ሌሎች ጥናቶችን እንደሚያስጠነቅቁት ሰዎች የበሽታ ምልክቶች ከማሳየታቸው በፊትም አስተላላፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ እና ምንም ዓይነት የበሽታ ምልክት ሳይኖር ቫይረሱ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ የእንግሊዝ ባለሥልጣናት እንደሚሉት ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ካላቸው ወዲያውኑ ራሳቸውን ቢያንስ ለ 10 ቀናት ማግለል አለባቸው፡፡
https://www.bbc.com/amharic/55026691
5sports
እንግሊዝ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ደረሰች
እንግሊዝ በዩሮ 2020 ፍልሚያ ዴንማርክን በመርታት ከ55 ዓመት በኋላ ለአንድ ትልቅ የእግር ኳስ ውድድር ፍፃሜ ደርሳለች። በርካታ ተመልካች በተሰበሰበበት በለንደኑ ዌምብሊ የተካሄደው ጨዋታው ልብን ሰቅዞ የሚይዝ ነበር። እንግሊዝ በፈረንጆቹ 1966 ምዕራብ ጀርመንን በመርታት ካነሳችው የዓለም ዋንጫ ውጭ ውድድር አሸንፋም ይሁን ለፍፃሜ በቅታ አታውቅም። ረቡዕ ምሽት ዴናማርክን የገጠመችው እንግሊዝ አንድ ለምንም ስትመራ ብትቆይም ከ120 ደቂቃዎች ፍልሚያ በኋላ 2-1 መርታት ችላለች። 66 ሺህ ሰዎች በታጩቀበት የተፋለሙት ሶስቱ አናብስት የተሰኘ ቅጥያ ያላቸው እንግሊዞች ይህን ጨዋታ በማሸነፋቸው በፍፃሜው ከጣልያን ጋር ይገናኛሉ። እንግሊዝ እሁድ ምሽት ጣልያን የምትገጥመው በገዛ ሜዳዋና ሕዝቧ ፊት ነው። ምንም እንኳ ዴንማርክ በወጣቱ ዳምስጋርድ ግሩም ቅጣት ምት አማካይነት ጨዋታውን ስትመራ ብትቆይም የኋላ ኋላ እጇን ሰጥታለች። ነገር ግን የመጀመሪያ አጋማሽ ከመጠናቀቁ በፊት የእንግሊዙ ቡካዮ ሳካ ወደ ጎል የላካትን ኳስ ሳይመን ኬር በራሱ መረብ ላይ በማሳረፉ ጨዋታው አቻ ሆነ። የዴንማርኩ ግብ ጠባቂ ካስፐር ሽማይክል የዳኒሾች ጎል ደጀን ሆኖ ቢያመሽም ከሽንፈት አልታደጋቸውም። ሽማይክል ከሃገሪ ማክጓዬርና ሃሪ ኬን የተቃጡበትን የጎል ሙከራዎች እያዳነ ቢያመሽም ጨዋታው ተጨማሪ 30 ደቂቃዎች ከታከሉበት በኋላ የተሰጥውት ፍፁም ቅጣት ምት ግን ማዳን አልቻለም። 103ኛው ደቂቃ ላይ ራሂም ስተርሊን ፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ተጠልፎ ወድቋል ሲሉ ዳኛው ቅጣት ምት ይሰጣሉ። በሺዎች የሚቆጠሩ የስታድየሙ ታዳሚያን በሁለት ተከፍለው ቅጣት ምቱን በጉጉት ይጠባበቃሉ። ሃሪ ኬን ኳሷን ወደ መረቡ ሲሰዳት ሽማይክል ያገኛታል። ነገር ግን ሲተፋት ተመልሳ የሃሪ ኬን እግር ላይ ታርፋለች። ይህን ወርቃማ ዕድል ያገኘው ኬን ኳሷን ከመረብ ያዋህዳል። ዴንማርክ የዳኛው ውሳኔ ትክክል አይደለም ብለው አቤቱታ ቢያቀርቡም ሰሚ አላገኙም። እንግሊዞች የግማሽ ፍፃሜ እርግማን አለባቸው ይባላል። ምክንያቱ ወዲህ ነው። በወጣት ተጫዋቾች የተሞላችው እንግሊዝ ባለፈው የዓለም ዋንጫ [2018] ለግማሽ ፍፃሜ ደርሳ መሸነፏ ይታወሳል። ጣልያን በተካሄደው የ1990 ዓለም ዋንጫ ላይ እንዲሁ ለግማሽ ፍፃሜ ደርሰው ተሸንፈዋል። በድጋሚ ጣልያን ባስተናገደችው የ1996 አውሮፓ ዋንጫ ላይ ለግማሽ ፍፃሜ የደረሰችው እንግሊዝ ሽንፈት ተከናንባ ነበር። ዘንድሮ ግን ይህንን ሽራ ለፍፃሜ ማለፍ ችላለች። የፍፃሜው ጨዋታ እሁድ ምሽት ይከናወናል። እንግሊዝ ከጣልያን እሁድ ምሽት 4 ሰዓት በለንደኑ ዌምብሊ ስታድዬም የአውሮፓ ዋንጫን ለማንሳት የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል።
እንግሊዝ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ደረሰች እንግሊዝ በዩሮ 2020 ፍልሚያ ዴንማርክን በመርታት ከ55 ዓመት በኋላ ለአንድ ትልቅ የእግር ኳስ ውድድር ፍፃሜ ደርሳለች። በርካታ ተመልካች በተሰበሰበበት በለንደኑ ዌምብሊ የተካሄደው ጨዋታው ልብን ሰቅዞ የሚይዝ ነበር። እንግሊዝ በፈረንጆቹ 1966 ምዕራብ ጀርመንን በመርታት ካነሳችው የዓለም ዋንጫ ውጭ ውድድር አሸንፋም ይሁን ለፍፃሜ በቅታ አታውቅም። ረቡዕ ምሽት ዴናማርክን የገጠመችው እንግሊዝ አንድ ለምንም ስትመራ ብትቆይም ከ120 ደቂቃዎች ፍልሚያ በኋላ 2-1 መርታት ችላለች። 66 ሺህ ሰዎች በታጩቀበት የተፋለሙት ሶስቱ አናብስት የተሰኘ ቅጥያ ያላቸው እንግሊዞች ይህን ጨዋታ በማሸነፋቸው በፍፃሜው ከጣልያን ጋር ይገናኛሉ። እንግሊዝ እሁድ ምሽት ጣልያን የምትገጥመው በገዛ ሜዳዋና ሕዝቧ ፊት ነው። ምንም እንኳ ዴንማርክ በወጣቱ ዳምስጋርድ ግሩም ቅጣት ምት አማካይነት ጨዋታውን ስትመራ ብትቆይም የኋላ ኋላ እጇን ሰጥታለች። ነገር ግን የመጀመሪያ አጋማሽ ከመጠናቀቁ በፊት የእንግሊዙ ቡካዮ ሳካ ወደ ጎል የላካትን ኳስ ሳይመን ኬር በራሱ መረብ ላይ በማሳረፉ ጨዋታው አቻ ሆነ። የዴንማርኩ ግብ ጠባቂ ካስፐር ሽማይክል የዳኒሾች ጎል ደጀን ሆኖ ቢያመሽም ከሽንፈት አልታደጋቸውም። ሽማይክል ከሃገሪ ማክጓዬርና ሃሪ ኬን የተቃጡበትን የጎል ሙከራዎች እያዳነ ቢያመሽም ጨዋታው ተጨማሪ 30 ደቂቃዎች ከታከሉበት በኋላ የተሰጥውት ፍፁም ቅጣት ምት ግን ማዳን አልቻለም። 103ኛው ደቂቃ ላይ ራሂም ስተርሊን ፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ተጠልፎ ወድቋል ሲሉ ዳኛው ቅጣት ምት ይሰጣሉ። በሺዎች የሚቆጠሩ የስታድየሙ ታዳሚያን በሁለት ተከፍለው ቅጣት ምቱን በጉጉት ይጠባበቃሉ። ሃሪ ኬን ኳሷን ወደ መረቡ ሲሰዳት ሽማይክል ያገኛታል። ነገር ግን ሲተፋት ተመልሳ የሃሪ ኬን እግር ላይ ታርፋለች። ይህን ወርቃማ ዕድል ያገኘው ኬን ኳሷን ከመረብ ያዋህዳል። ዴንማርክ የዳኛው ውሳኔ ትክክል አይደለም ብለው አቤቱታ ቢያቀርቡም ሰሚ አላገኙም። እንግሊዞች የግማሽ ፍፃሜ እርግማን አለባቸው ይባላል። ምክንያቱ ወዲህ ነው። በወጣት ተጫዋቾች የተሞላችው እንግሊዝ ባለፈው የዓለም ዋንጫ [2018] ለግማሽ ፍፃሜ ደርሳ መሸነፏ ይታወሳል። ጣልያን በተካሄደው የ1990 ዓለም ዋንጫ ላይ እንዲሁ ለግማሽ ፍፃሜ ደርሰው ተሸንፈዋል። በድጋሚ ጣልያን ባስተናገደችው የ1996 አውሮፓ ዋንጫ ላይ ለግማሽ ፍፃሜ የደረሰችው እንግሊዝ ሽንፈት ተከናንባ ነበር። ዘንድሮ ግን ይህንን ሽራ ለፍፃሜ ማለፍ ችላለች። የፍፃሜው ጨዋታ እሁድ ምሽት ይከናወናል። እንግሊዝ ከጣልያን እሁድ ምሽት 4 ሰዓት በለንደኑ ዌምብሊ ስታድዬም የአውሮፓ ዋንጫን ለማንሳት የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57760136
2health
የዩናይትድ ኪንግደም ጤና ሚኒስትር የኮቪድ-19ን ደንብ በመተላለፋቸው ከሥራ ለቀቁ
የዩናይትድ ኪንግደም ጤና ሚኒስትር ማት ሃንኮክ የኮቪድ-19 መመሪያ መጣሳቸውን ተከትሎ ከሥራቸው ለቀቁ። ሚኒስትሩ የአካላዊ ርቀትን ደንብ በመተላለፍ የሥራ ባልደረባቸውን መሳማቸውን ተከትሎ ነው ከሥራ የለቀቀቁት። ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሪስ ጆንሰን በፃፉት ደብዳቤ መንግሥት "በዚህ ወረርሽኝ ላይ መስዋዕትነት ለከፈሉ የማኅበረሰቡ ክፍሎች እኛም ስናጠፋ ተጠያቂ መሆናችንን ማሳየት አለብን" በማለት አስፍረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የሚኒስትሩን መልቀቂያ መቀበላቸው እንዳሳዘናቸው ገልፀዋል። ተሰናባቹን የጤና ሚኒስትርን በመተካት የቀድሞ የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ሳጂድ ጃቪድ የተሾሙ ሲሆን ለዚህ የሚኒስትርነት ቦታ በመመረጣቸው የተሰማቸውን ክብር ገልፀዋል። ማት ሃንኮክ ከረዳታቸው ጋር እየተሳሳሙ የሚያሳይ ቪዲዮ ሰን በተባለው ጋዜጣ ላይ መውጣቱን ተከትሎ ነው በርካቶች ኃላፊነታቸውን እንዲለቁ ግፊት ሲያደርጉባቸው የነበረው። ሁለቱም ያገቡና የሦስት ልጆች ወላጆች ናቸው። ጋዜጣው አክሎ እንደዘገበው ሁለቱንም ግለሰቦች ፎቶግራፉ የተነሳው ባለፈው የግንቦት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ላይ እዚያው የጤና ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ውስጥ ነው። ይህንንም ተከትሎ ሚኒስትሩ ለ15 ዓመታት በጋብቻ ከቆዩት ባለቤታቸው ጋር ተፋትተዋል። የሳሟት የሥራ ባልደረባቸው ጋር ያላቸው የፍቅር ግንኙነትም የጠነከረ እንደሆነ ተገልጿል። በርካታ የፓርላማ አባላት፣ የሠራተኛ፣ ማኅበራዊ ጉዳይና በኮቪድ-19 ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች የተቋቋመው የፍትህ ቡድን ሚኒስትሩ ከሥራ እንዲባረሩ ሲጠይቁ ነበር። እንዲሁም የፓርላማ አባላቱ ሚኒስትሩ ከሥራቸው እንዲለቁም መምከራቸውን ቢቢሲ ከአንዳንድ የፓርላማ አባላት ሰምቷል። ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሥራቸው እንዲለቁ ባይፈልጉም ሚኒስትሩ በራሳቸው ፈቃድ መልቀቃቸውን የቢቢሲ የፖለቲካ ዘጋቢ ላውራ ኩንስበርግ ዘግባለች። ከዚህም በተጨማሪ የሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ጂና ኮላዳንጌሎም እንዲሁ ከሥራቸው መልቀቃቸው ተዘግቧል።
የዩናይትድ ኪንግደም ጤና ሚኒስትር የኮቪድ-19ን ደንብ በመተላለፋቸው ከሥራ ለቀቁ የዩናይትድ ኪንግደም ጤና ሚኒስትር ማት ሃንኮክ የኮቪድ-19 መመሪያ መጣሳቸውን ተከትሎ ከሥራቸው ለቀቁ። ሚኒስትሩ የአካላዊ ርቀትን ደንብ በመተላለፍ የሥራ ባልደረባቸውን መሳማቸውን ተከትሎ ነው ከሥራ የለቀቀቁት። ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሪስ ጆንሰን በፃፉት ደብዳቤ መንግሥት "በዚህ ወረርሽኝ ላይ መስዋዕትነት ለከፈሉ የማኅበረሰቡ ክፍሎች እኛም ስናጠፋ ተጠያቂ መሆናችንን ማሳየት አለብን" በማለት አስፍረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የሚኒስትሩን መልቀቂያ መቀበላቸው እንዳሳዘናቸው ገልፀዋል። ተሰናባቹን የጤና ሚኒስትርን በመተካት የቀድሞ የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ሳጂድ ጃቪድ የተሾሙ ሲሆን ለዚህ የሚኒስትርነት ቦታ በመመረጣቸው የተሰማቸውን ክብር ገልፀዋል። ማት ሃንኮክ ከረዳታቸው ጋር እየተሳሳሙ የሚያሳይ ቪዲዮ ሰን በተባለው ጋዜጣ ላይ መውጣቱን ተከትሎ ነው በርካቶች ኃላፊነታቸውን እንዲለቁ ግፊት ሲያደርጉባቸው የነበረው። ሁለቱም ያገቡና የሦስት ልጆች ወላጆች ናቸው። ጋዜጣው አክሎ እንደዘገበው ሁለቱንም ግለሰቦች ፎቶግራፉ የተነሳው ባለፈው የግንቦት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ላይ እዚያው የጤና ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ውስጥ ነው። ይህንንም ተከትሎ ሚኒስትሩ ለ15 ዓመታት በጋብቻ ከቆዩት ባለቤታቸው ጋር ተፋትተዋል። የሳሟት የሥራ ባልደረባቸው ጋር ያላቸው የፍቅር ግንኙነትም የጠነከረ እንደሆነ ተገልጿል። በርካታ የፓርላማ አባላት፣ የሠራተኛ፣ ማኅበራዊ ጉዳይና በኮቪድ-19 ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች የተቋቋመው የፍትህ ቡድን ሚኒስትሩ ከሥራ እንዲባረሩ ሲጠይቁ ነበር። እንዲሁም የፓርላማ አባላቱ ሚኒስትሩ ከሥራቸው እንዲለቁም መምከራቸውን ቢቢሲ ከአንዳንድ የፓርላማ አባላት ሰምቷል። ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሥራቸው እንዲለቁ ባይፈልጉም ሚኒስትሩ በራሳቸው ፈቃድ መልቀቃቸውን የቢቢሲ የፖለቲካ ዘጋቢ ላውራ ኩንስበርግ ዘግባለች። ከዚህም በተጨማሪ የሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ጂና ኮላዳንጌሎም እንዲሁ ከሥራቸው መልቀቃቸው ተዘግቧል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57631461
3politics
ስለ የውጭ ጣልቃ ገብነት፣ ሰብአዊ እርዳታ፣ ውይይት. . . አቶ ደመቀ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ
የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአገራቸው የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚደረጉ ሙከራዎችን ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው ተናገሩ። በኒው ዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው በ76ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግሥታቸው የሰብአዊ እርዳታን በተመለከተ ያልተቆጠበ ቁርጠኝነት እንዳለው አመልክተው አገራቸው የትኛውንም ጣልቃ ገብነት አትቀበልም ብለዋል። ለነጻ፣ ለገለልተኝነትና ለሰብአዊነት ምርሆች ተገዢ ለሆኑ የእርዳታ አቅርቢ አጋሮች ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ መንግሥታቸው አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ የገለጹት አቶ ደመቀ፤ "ከዚህ ውጪ ግን የትኛውም ምክንያት በውስጥ ጉዳያችን ውስጥ ጣልቃ ለመግባት የሚደረግ ሙከራን ተቀባይ አያደርገውም" ብለዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን በመግሥታቱ ድርጅት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር በተለያዩ ኢትዮጵያ በሚመለከቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የመንግሥታቸውን አቋም አብራርተዋል። የሰብኢዊ እርዳታ አቅርቦት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሠሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ ስላለው ጦርነት ዝርዝር ያስረዱ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተደጋጋሚ የሚነሳውን የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትን በተመለከተ በንግግራቸው አንስተዋል። መንግሥታቸው የሚያስፈልገውን የሰብአዊ እርዳታ ለማሟላት ጥረት እያደረገ ባለበት ጊዜ "የጥፋት ቡድኑ ሰብዓዊ ቀውስ የመፍጠር እቅዱን ተግባራዊ ከማድረጉ ባሻገር ክፋት የተሞላበት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ተከፍቶብናል" ሲሉ ከሰዋል። ጨምረውም "አሁን በደረስንበት ምዕራፍ የሰብአዊ ድጋፍ የፖለቲካ ዓላማን ማስፈፀሚያ መሳሪያ እንደሆነ እየተገነዘብን ነው" ያሉት አቶ ደመቀ፤ የሐሰት መረጃን በማቀነባበር የተዛባ ግንዛቤ እንዲፈጠርና ሐሰተኛ ውንጀላ መቅረባቸውን ተናግረዋል። ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብአዊ ዕርዳታ አቅርቦት ግዴታውን መወጣቱ፣ የተናጠል ሰብአዊ የተኩስ አቁም ማወጁ እንዲሁም ጥሰቶችን በተመለከተ ምርመራ እንዲደረግና ተጠያቂነት ለማስፈን እርምጃዎችን መውሰዱን ጠቅሰው "ቢሆንም ግን የሐሰት ውንጀላዎቹን መቀልበስ አልተቻለም" ብለዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት ተቋማትና ሌሎች መንግሥታት የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ትግራይ ክልል ሰብአዊ እርዳታ እንዳይቀርብ እንቅፋት ሆኗል በማለት በተደጋጋሚ ሲከሱ ቆይተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በመንግሥታቱ ድርጅት ጉባኤ ላይ ይህን በተመለከተ ምላሽ ሰጥዋል። የውጭ ጫና ኢትዮጵያ ማዕቀቦች በሌሎች ላይ ሲጣሉ መቃወሟን አቶ ደመቀ አስታውሰው "በኢትዮጵያ ላይ የሚደረግ ፍትህና ፍትሕ የሚጎድለው አካሄድ ተግባራዊ እንዳይሆን እንመክራለን" ብለዋል። ጨምረውም "ምንም አይነት አላስፈላጊ ጫናዎች ቢኖሩብንም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነትና የፖለቲካ ነፃነትን የማስጠበቅ ግዴታችንን እንወጣለን" ብለዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገራቸው ከወዳጆቿ የሚቀርቡ ትብብር እና ቅን ሐሳብን እንደምትቀበል በመጥቀስ ነገር ግን ገንቢ፣ መተማመንን የሚያሰፍንና መግባባትን የሚፈጥር ሊሆን ይገባል ብለዋል። "በአንድ መንግሥት ውስጣዊ ጉዳይ ላይ ድጋፍን ወይም ሐሳብ ለመሰንዘር የሚደረግ ሙከራ ስለችግሩ ውስብስብነት ሙሉ ግንዛቤን ይጠይቃል" ሲሉ አሳስበዋል። በትግራይ ክልል ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ምዕራባውያን አገራት በተለይ አሜሪካ በጦርነቱ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ ወገኖች ላይ የተለያዩ ጫናዎችን ለማሳደር እየሞከሩ መሆኑ ይታወቃል። በቅርቡም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከግጭቱ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ዕቀባዎችን ለመጣል የሚያስችል ትዕዛዝ ላይ ፊርማቸውን ማኖራቸው ይታወሳል። ችግሮችን በውይይት ስለመፍታት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ ከተለያዩ ወገኖች የሚሰነዘሩ የውይይት ሐሳቦችን በተመለከተ በንግግራቸው ላይ እንዳነሱት፤ ሁልጊዜም ውይይት የመንግሥታቸው ተመራጭ መፍትሔ እንደሆነ ገልጸዋል። "ኢትዮጵያ ለሐቀኛ የሰላም ጥረቶች በሯ ክፍት ነው" በማለት ከአፍሪካ ሕብረትና ከሕብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ጋር ኢትዮጵያ መር ለሆነ ብሔራዊ ውይይት ለማካሄድ መንግሥታቸው እንደሚሰራ አመልክተዋል። ጨምረውም ኢትዮጵያ ለማንም የደኅንነት ስጋት ሆና እንደማታወቅተ በመጥቀስ "ኢትዮጵያ ሁሌም ሰላም ወዳድ አገር ሆና የምትኖርና ለቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ሰላም የበኩሏን አስተዋፅኦ ታበረክታለች" ብለዋል። ከሱዳን ጋር ስላለው ድንበር ጉዳይ በሠሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ የሱዳን ጦር በኢትዮጵያውያን እጅ የነበረና ይገባኛል የሚለውን የድንበር አካባቢን መቆጣጡ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት ተበላሽቶ ቆይቷል። ኢትዮጵያ ሱዳን ከተቆጣጠረችው አካባቢ ሠራዊቷን አስወጥታ ውይይት እንዲጀመር ብትጠይቅም ከሱዳን በኩል ተቀባይነት አላገኘችም። አቶ ደመቀ መኮንንም ይህንን ጉዳይ በመንግሥታቱ ድርጅት ስብሰባ ላይ አንስተው የአገሪቱ ግዛት በወረራ ስር መሆኑንና አሁንም ለሰላማዊ መፍትሔ በሯ ክፍት መሆኑን ገልጸዋል። "ኢትዮጵያ ችግር ውስጥ በነበረችበት ወቅት ጎረቤት አገር ዓለም አቀፍ ሕግን በመጣስ ግዛታችንን የወረረ ሲሆን ይህ ወረራ እስከዛሬ ድረስ ቀጥሏል። ኢትዮጵያ ይህንን ችግር ለመፍታት ዲፕሎማሲያዊ የመፍትሔ ሐሳቦችን ለመቀበል ዝግጁ ናት።" ብለዋል። የሕዳሴው ግድብ በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል ለዓመታት ያለመግባባት መንጭ ሆኖ የቆየው የታላቁ ሕዳሴን ግድብ በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እንደተናገሩት፤ ግድቡን ኢትዮጵያ በራሷ ሀብት የገነባችው መሆኑ ሌሎችም አገራት በራስ አቅም ለሚገነባ ለሚከናወኑ ተመሳሳይ ተግባራት ይፈጥራል ብለዋል። ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን በተመለከተ የገጠማትን ፈተና በተመለከተ አቶ ደመቀ መኮንን ለምክር ቤቱ ባስረዱበት ጊዜ እንዳሉት "የሚያሳዝነው ነገር ከራሳችን ውሃ እንዳንጠጣ መከልከላችን ነው" ብለዋል። አክለውም አገሪቱ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት ለመጠቀም ያለውን የትውልዶች ፍላጎት "በቅኝ ገዢዎች ውርስና በብቸኝነት ለመጠቀም ያለ ፍላጎት ምክንያት የሚገደብ አይሆንም" በማለት ጉዳዩ ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደርግና በአፍሪካ ሕብረት በሚመራ ሂደት ከመቋጫ ለማድረስ ዝግጁ ይሆናሉ ብላ አገራቸው ተስፋ እንደምታደርግ ገልጸዋል።
ስለ የውጭ ጣልቃ ገብነት፣ ሰብአዊ እርዳታ፣ ውይይት. . . አቶ ደመቀ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአገራቸው የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚደረጉ ሙከራዎችን ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው ተናገሩ። በኒው ዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው በ76ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግሥታቸው የሰብአዊ እርዳታን በተመለከተ ያልተቆጠበ ቁርጠኝነት እንዳለው አመልክተው አገራቸው የትኛውንም ጣልቃ ገብነት አትቀበልም ብለዋል። ለነጻ፣ ለገለልተኝነትና ለሰብአዊነት ምርሆች ተገዢ ለሆኑ የእርዳታ አቅርቢ አጋሮች ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ መንግሥታቸው አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ የገለጹት አቶ ደመቀ፤ "ከዚህ ውጪ ግን የትኛውም ምክንያት በውስጥ ጉዳያችን ውስጥ ጣልቃ ለመግባት የሚደረግ ሙከራን ተቀባይ አያደርገውም" ብለዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን በመግሥታቱ ድርጅት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር በተለያዩ ኢትዮጵያ በሚመለከቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የመንግሥታቸውን አቋም አብራርተዋል። የሰብኢዊ እርዳታ አቅርቦት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሠሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ ስላለው ጦርነት ዝርዝር ያስረዱ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተደጋጋሚ የሚነሳውን የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትን በተመለከተ በንግግራቸው አንስተዋል። መንግሥታቸው የሚያስፈልገውን የሰብአዊ እርዳታ ለማሟላት ጥረት እያደረገ ባለበት ጊዜ "የጥፋት ቡድኑ ሰብዓዊ ቀውስ የመፍጠር እቅዱን ተግባራዊ ከማድረጉ ባሻገር ክፋት የተሞላበት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ተከፍቶብናል" ሲሉ ከሰዋል። ጨምረውም "አሁን በደረስንበት ምዕራፍ የሰብአዊ ድጋፍ የፖለቲካ ዓላማን ማስፈፀሚያ መሳሪያ እንደሆነ እየተገነዘብን ነው" ያሉት አቶ ደመቀ፤ የሐሰት መረጃን በማቀነባበር የተዛባ ግንዛቤ እንዲፈጠርና ሐሰተኛ ውንጀላ መቅረባቸውን ተናግረዋል። ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብአዊ ዕርዳታ አቅርቦት ግዴታውን መወጣቱ፣ የተናጠል ሰብአዊ የተኩስ አቁም ማወጁ እንዲሁም ጥሰቶችን በተመለከተ ምርመራ እንዲደረግና ተጠያቂነት ለማስፈን እርምጃዎችን መውሰዱን ጠቅሰው "ቢሆንም ግን የሐሰት ውንጀላዎቹን መቀልበስ አልተቻለም" ብለዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት ተቋማትና ሌሎች መንግሥታት የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ትግራይ ክልል ሰብአዊ እርዳታ እንዳይቀርብ እንቅፋት ሆኗል በማለት በተደጋጋሚ ሲከሱ ቆይተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በመንግሥታቱ ድርጅት ጉባኤ ላይ ይህን በተመለከተ ምላሽ ሰጥዋል። የውጭ ጫና ኢትዮጵያ ማዕቀቦች በሌሎች ላይ ሲጣሉ መቃወሟን አቶ ደመቀ አስታውሰው "በኢትዮጵያ ላይ የሚደረግ ፍትህና ፍትሕ የሚጎድለው አካሄድ ተግባራዊ እንዳይሆን እንመክራለን" ብለዋል። ጨምረውም "ምንም አይነት አላስፈላጊ ጫናዎች ቢኖሩብንም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነትና የፖለቲካ ነፃነትን የማስጠበቅ ግዴታችንን እንወጣለን" ብለዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገራቸው ከወዳጆቿ የሚቀርቡ ትብብር እና ቅን ሐሳብን እንደምትቀበል በመጥቀስ ነገር ግን ገንቢ፣ መተማመንን የሚያሰፍንና መግባባትን የሚፈጥር ሊሆን ይገባል ብለዋል። "በአንድ መንግሥት ውስጣዊ ጉዳይ ላይ ድጋፍን ወይም ሐሳብ ለመሰንዘር የሚደረግ ሙከራ ስለችግሩ ውስብስብነት ሙሉ ግንዛቤን ይጠይቃል" ሲሉ አሳስበዋል። በትግራይ ክልል ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ምዕራባውያን አገራት በተለይ አሜሪካ በጦርነቱ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ ወገኖች ላይ የተለያዩ ጫናዎችን ለማሳደር እየሞከሩ መሆኑ ይታወቃል። በቅርቡም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከግጭቱ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ዕቀባዎችን ለመጣል የሚያስችል ትዕዛዝ ላይ ፊርማቸውን ማኖራቸው ይታወሳል። ችግሮችን በውይይት ስለመፍታት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ ከተለያዩ ወገኖች የሚሰነዘሩ የውይይት ሐሳቦችን በተመለከተ በንግግራቸው ላይ እንዳነሱት፤ ሁልጊዜም ውይይት የመንግሥታቸው ተመራጭ መፍትሔ እንደሆነ ገልጸዋል። "ኢትዮጵያ ለሐቀኛ የሰላም ጥረቶች በሯ ክፍት ነው" በማለት ከአፍሪካ ሕብረትና ከሕብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ጋር ኢትዮጵያ መር ለሆነ ብሔራዊ ውይይት ለማካሄድ መንግሥታቸው እንደሚሰራ አመልክተዋል። ጨምረውም ኢትዮጵያ ለማንም የደኅንነት ስጋት ሆና እንደማታወቅተ በመጥቀስ "ኢትዮጵያ ሁሌም ሰላም ወዳድ አገር ሆና የምትኖርና ለቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ሰላም የበኩሏን አስተዋፅኦ ታበረክታለች" ብለዋል። ከሱዳን ጋር ስላለው ድንበር ጉዳይ በሠሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ የሱዳን ጦር በኢትዮጵያውያን እጅ የነበረና ይገባኛል የሚለውን የድንበር አካባቢን መቆጣጡ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት ተበላሽቶ ቆይቷል። ኢትዮጵያ ሱዳን ከተቆጣጠረችው አካባቢ ሠራዊቷን አስወጥታ ውይይት እንዲጀመር ብትጠይቅም ከሱዳን በኩል ተቀባይነት አላገኘችም። አቶ ደመቀ መኮንንም ይህንን ጉዳይ በመንግሥታቱ ድርጅት ስብሰባ ላይ አንስተው የአገሪቱ ግዛት በወረራ ስር መሆኑንና አሁንም ለሰላማዊ መፍትሔ በሯ ክፍት መሆኑን ገልጸዋል። "ኢትዮጵያ ችግር ውስጥ በነበረችበት ወቅት ጎረቤት አገር ዓለም አቀፍ ሕግን በመጣስ ግዛታችንን የወረረ ሲሆን ይህ ወረራ እስከዛሬ ድረስ ቀጥሏል። ኢትዮጵያ ይህንን ችግር ለመፍታት ዲፕሎማሲያዊ የመፍትሔ ሐሳቦችን ለመቀበል ዝግጁ ናት።" ብለዋል። የሕዳሴው ግድብ በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል ለዓመታት ያለመግባባት መንጭ ሆኖ የቆየው የታላቁ ሕዳሴን ግድብ በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እንደተናገሩት፤ ግድቡን ኢትዮጵያ በራሷ ሀብት የገነባችው መሆኑ ሌሎችም አገራት በራስ አቅም ለሚገነባ ለሚከናወኑ ተመሳሳይ ተግባራት ይፈጥራል ብለዋል። ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን በተመለከተ የገጠማትን ፈተና በተመለከተ አቶ ደመቀ መኮንን ለምክር ቤቱ ባስረዱበት ጊዜ እንዳሉት "የሚያሳዝነው ነገር ከራሳችን ውሃ እንዳንጠጣ መከልከላችን ነው" ብለዋል። አክለውም አገሪቱ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት ለመጠቀም ያለውን የትውልዶች ፍላጎት "በቅኝ ገዢዎች ውርስና በብቸኝነት ለመጠቀም ያለ ፍላጎት ምክንያት የሚገደብ አይሆንም" በማለት ጉዳዩ ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደርግና በአፍሪካ ሕብረት በሚመራ ሂደት ከመቋጫ ለማድረስ ዝግጁ ይሆናሉ ብላ አገራቸው ተስፋ እንደምታደርግ ገልጸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58680780
3politics
ሩሲያ 10 የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን በማባረር አፀፋ መለሰች
ሩሲያ 10 የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ከአገሯ እንዲወጡ ትዕዛዝ የሰጠች ሲሆን ሌሎች ስምንት ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ደግሞ ወደ አገሯ እንዳይገቡ ጥቁር መዝገብ ውስጥ ማስገባቷ ተገለፀ። ሩሲያ ይህን ያደረገችው ማክሰኞ ዕለት አሜሪካ ለጣለችባት ማዕቀብ አፀፋዊ ምላሽ ነው። ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ከታገዱት መካከል የአሜሪካ ፌደራል ፖሊስ (ኤፍቢአይ) አባላትና የአሜሪካ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባለሥልጣናት ይገኙበታል። ዋይት ሐውስ ሩሲያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ባለፈው ዓመት በነበረው 'የሶላር ዊንድ' የሳይበር ጠለፋ እና ሌሎች "ጠብ አጫሪ" ድርጊቶች እንዲሁም በ2020 ምርጫ ጣልቃ ገብነቷ ምላሽ እንደሆነ አስታውቋል። ይህንን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ ቅራኔ ውስጥ የገቡት ሁለቱ አገራት፤ አሁን ደግሞ ወደ ባሰበት ውጥረት ውስጥ እየገቡ ነው። ሩሲያ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ያስጠጋች ሲሆን፤ የአሜሪካ የጦር መርከቦችም ወደ ጥቁር ባሕር እያመሩ መሆኑን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስጠንቅቋል። ባለፈው ወር መንግሥትን በሚተቸው አሌክሲ ናቫንሊይ መመረዝ ምክንያት አሜሪካ ሰባት የሩሲያ ባለሥልጣናትን እና በርካታ የመንግሥት ተቋማትን ኢላማ አድርጋለች። ሩሲያ ግን በአሌክሲ መመረዝ እጇ እንደሌለበት ገልጻለች። ሆኖም በዚህ ሳምንት የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ለሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ሁለቱ አገራት አብረው ሊሰሩባቸው የሚችሉባቸው ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ጥሪ አቅርበዋል። ሩሲያም ይህንን በበጎ እንደምትመለከተውና እያሰበችበት እንደሆነ ገልጻለች። ማዕቀቡ የተጣለበት ማነው? ሩሲያ 10 የአሜሪካ ዲፕሎማቶች አገሪቷን ለቀው እንዲወጡ ጠይቃለች። ከዚህ በተጨማሪም ስምንት የአሜሪካ ባለሥልጣናት ወደ አገሯ እንዳይገቡ አግዳለች። ከእነዚህም መካከል፡ • የአሜሪካ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጀነራል ሜሪክ ጋርላንድ፣ • የአሜሪካ ፌደራል ፖሊስ ዳሬክተር ክርስቶፈር ውሬይ እና • የአሜሪካ የውስጥ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪ ሱሳን ራይስ ይገኙበታል። ከዚህም ባሻገር ፖላንድ አምስት የሩሲያ ባለሥልጣናትን ማባረሯን ተከትሎ አምስት ፖላንዳዊ ዲፕሎማቶች አገሯን ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል። ሩሲያ በ2020 የአሜሪካ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ላይ ጫና ለማሳደር በመሞከሯ እና ሌሎች የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት አሜሪካ 10 የሩሲያ ዲፕሎማቶች ማባረርን ጨምሮ 32 ተቋማትና እና ባለሥልጣናትን ኢላማ አድርጋለች። የአሜሪካ የገንዘብ ተቋማትም ከሰኔ ወር ጀምሮ በውጭ ምንዛሪ ላይ መሰረት ያደረገ የውጭ ቦንድ ከሩሲያ ከመግዛት ታግደዋል።
ሩሲያ 10 የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን በማባረር አፀፋ መለሰች ሩሲያ 10 የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ከአገሯ እንዲወጡ ትዕዛዝ የሰጠች ሲሆን ሌሎች ስምንት ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ደግሞ ወደ አገሯ እንዳይገቡ ጥቁር መዝገብ ውስጥ ማስገባቷ ተገለፀ። ሩሲያ ይህን ያደረገችው ማክሰኞ ዕለት አሜሪካ ለጣለችባት ማዕቀብ አፀፋዊ ምላሽ ነው። ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ከታገዱት መካከል የአሜሪካ ፌደራል ፖሊስ (ኤፍቢአይ) አባላትና የአሜሪካ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባለሥልጣናት ይገኙበታል። ዋይት ሐውስ ሩሲያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ባለፈው ዓመት በነበረው 'የሶላር ዊንድ' የሳይበር ጠለፋ እና ሌሎች "ጠብ አጫሪ" ድርጊቶች እንዲሁም በ2020 ምርጫ ጣልቃ ገብነቷ ምላሽ እንደሆነ አስታውቋል። ይህንን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ ቅራኔ ውስጥ የገቡት ሁለቱ አገራት፤ አሁን ደግሞ ወደ ባሰበት ውጥረት ውስጥ እየገቡ ነው። ሩሲያ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ያስጠጋች ሲሆን፤ የአሜሪካ የጦር መርከቦችም ወደ ጥቁር ባሕር እያመሩ መሆኑን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስጠንቅቋል። ባለፈው ወር መንግሥትን በሚተቸው አሌክሲ ናቫንሊይ መመረዝ ምክንያት አሜሪካ ሰባት የሩሲያ ባለሥልጣናትን እና በርካታ የመንግሥት ተቋማትን ኢላማ አድርጋለች። ሩሲያ ግን በአሌክሲ መመረዝ እጇ እንደሌለበት ገልጻለች። ሆኖም በዚህ ሳምንት የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ለሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ሁለቱ አገራት አብረው ሊሰሩባቸው የሚችሉባቸው ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ጥሪ አቅርበዋል። ሩሲያም ይህንን በበጎ እንደምትመለከተውና እያሰበችበት እንደሆነ ገልጻለች። ማዕቀቡ የተጣለበት ማነው? ሩሲያ 10 የአሜሪካ ዲፕሎማቶች አገሪቷን ለቀው እንዲወጡ ጠይቃለች። ከዚህ በተጨማሪም ስምንት የአሜሪካ ባለሥልጣናት ወደ አገሯ እንዳይገቡ አግዳለች። ከእነዚህም መካከል፡ • የአሜሪካ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጀነራል ሜሪክ ጋርላንድ፣ • የአሜሪካ ፌደራል ፖሊስ ዳሬክተር ክርስቶፈር ውሬይ እና • የአሜሪካ የውስጥ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪ ሱሳን ራይስ ይገኙበታል። ከዚህም ባሻገር ፖላንድ አምስት የሩሲያ ባለሥልጣናትን ማባረሯን ተከትሎ አምስት ፖላንዳዊ ዲፕሎማቶች አገሯን ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል። ሩሲያ በ2020 የአሜሪካ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ላይ ጫና ለማሳደር በመሞከሯ እና ሌሎች የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት አሜሪካ 10 የሩሲያ ዲፕሎማቶች ማባረርን ጨምሮ 32 ተቋማትና እና ባለሥልጣናትን ኢላማ አድርጋለች። የአሜሪካ የገንዘብ ተቋማትም ከሰኔ ወር ጀምሮ በውጭ ምንዛሪ ላይ መሰረት ያደረገ የውጭ ቦንድ ከሩሲያ ከመግዛት ታግደዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56737751
2health
ከኮሮናቫይረስ በእጅጉ እያተረፉ ያሉት ትልልቅ ድርጅቶች
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የበርካታ አገራት ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ጫና እያደረሰ ቢሆንም ትልልቅ የሚባሉት የዓለማችን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ግን ጥሩ የሚባል ትርፍ እየሰበሰቡ ነው። በበይነ መረብ አማካይነት የተለያዩ አይት መገልገያዎችን የሚሸጠው አማዞን ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማግስት ባሉት ሶስት ወራት ብቻ ሽያጩ 40 በመቶ ከፍ እንዳለለት ያስታወቀ ሲሆን ታዋቂው የስልክና የላፕቶፕ አምራች አፕል ደግሞ የአይፎንና ሌሎች መቀየሪያ መሳሪያዎች በደንብ እንደተቸበቸቡለት ገልጿል። ፌስቡክ ደግሞ በስሬ በማስተዳድራቸው እንደ ዋትስአፕና ኢንስታግራም ባሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተጠቃሚዎች ቁጥር 15 በመቶ ከፍ ብሎልኛል ብሏል። • በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትርፉ መጨመሩን ሳምሰንግ አስታወቀ • ኮሮናቫይረስ የቀሰቀሳቸው የአና የሚበሉ ሥዕሎች • ከኮሮናቫይረስ የትኞቹ ድርጅቶች አተረፉ? እነማንስ ከሰሩ? የአማዞን የሩብ ዓመት ትርፍ 5.2 ቢሊየን ዶላር ሲሆን ድርጅቱ ከተቋቋመበት ከአውሮፓውያኑ 1994 ጀምሮ ይህ ከፍተኛው ነው ተብሏል። ድርጅቱ እንደውም ከኮሮናቫይረስ መከሰት በኋላ ለሰራተⶉቹ መከላከያ መሳሪያዎችን ለመግዛትና የመከላከያ ጥንቃቄዎችን ለማድረግ ከፍተኛ ወጪ ማውጣቱ ትርፉን ዝቅ ያደርገዋል ተብሎ ተፈርቶ ነበር። በአጠቃላይ በበይነ መረብ የሚካሄዱ ንግዶች የሽያጭ መጠኑ 40 በመቶ ከፍ ብሏል። እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ባሉት ሶስት ወራት ደግሞ በአጠቃላይ 88.9 ቢሊየን ዶላር አንቀሳቅሷል። ትርፍም ቢሆን በአስገራሚ ሁኔታ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 2.6 ቢሊየን ዶላር ወደ 5.2 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል። በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት ቤት ውስጥ ብዙ ጊዜያቸውን ማሳለፋቸውን ተከትሎ የበይነ መረብ ሽያጭ በእጅጉ ተጧጡፏል። አማዞንም ቢሆን የደንበኞቹን ፍላጎት ለማሟላት በሩብ ዓመቱ ብቻ ተጨማሪ 175 ሺ ሰራተኞችን ቀጥሯል። ፍላጎቱ በዚሁ መቀጠሉ ስለማይቀር በርካታ መጋዘኖችንና ሰራተኞችን ለመጨመርም እያሰበ ነው። የአፕል የሩብ ዓመት ትርፍ ደግሞ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 11 በመቶ በመጨመር 59.7 ቢሊየን ደርሷል። ሰዎች ስራቸውን ከቤታቸው ሆነው መስራታቸው የተለያዩ መገልገያዎችን እንዲጠቀሙ አድርጓቸዋል። በዚህም ምክንያት የማክ ላፕቶፖችና አይፓዶች በእጅጉ ተፈላጊ ነበሩ። ሁለቱም የአፕል ምርቶች ከወረርሽኙ መከሰት በኋላ ገበያቸው እንደደራ ድርጅቱ አስታውቋል። በዚህም ምክንያት ባለፈው ከነበረው 10 ቢሊየን ዶላር ትርፍ ወደ 11.25 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል። ፌስቡክ ደግሞ ከኮሮናቫይረስ በኋላ ትርፉ በእጅጉ እንደሚቀንስ ቢጠበቅም እንደውም የ 11 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። አነስተኛ ድርጅቶች ያሏቸው ሰዎች ለማስታወቂያ ወደ ፌስቡክ ላይሄዱ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ተንብየው ነበር። ነገር ግን ወረርሽኙን ተከትሎ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር በእጅጉ በመጨመሩ ምክንያት ለማስታወቂያ የሚመጡ ድርጅቶችም ቁጥር አብሮ ከፍ ብሏል። በዚህም ምክንያት የድርጅቱ የሩብ ዓመት ትርፍ 5.2 ቢሊየን ዶላር እንዲደርስ ሆኗል። ፌስቡክ እንደሚለው ባለፈው ሰኔ ወር ብቻ በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያዎቸ ላይ 2.4 ቢሊየን ተጠቃሚዎች የነበሩ ሲሆን ይህም የ15 በመቶ ጭማሪ አለው። ከአራቱ ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው አልፋቤትም ቢሆን እንደ ሌሎቹ ባይሆንም ትርፋማ ሆኗል። ድርጅቱ በስሩ ጉግልና ዩቲዩብን የያዘ ሲሆን እስካሁን ያገኘሁት ትርፍ 38.3 ቢሊየን ዶላር ነው ብሏል። ይህ ደግሞ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የሁለት በመቶ ቅናሽ ያሳያል።
ከኮሮናቫይረስ በእጅጉ እያተረፉ ያሉት ትልልቅ ድርጅቶች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የበርካታ አገራት ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ጫና እያደረሰ ቢሆንም ትልልቅ የሚባሉት የዓለማችን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ግን ጥሩ የሚባል ትርፍ እየሰበሰቡ ነው። በበይነ መረብ አማካይነት የተለያዩ አይት መገልገያዎችን የሚሸጠው አማዞን ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማግስት ባሉት ሶስት ወራት ብቻ ሽያጩ 40 በመቶ ከፍ እንዳለለት ያስታወቀ ሲሆን ታዋቂው የስልክና የላፕቶፕ አምራች አፕል ደግሞ የአይፎንና ሌሎች መቀየሪያ መሳሪያዎች በደንብ እንደተቸበቸቡለት ገልጿል። ፌስቡክ ደግሞ በስሬ በማስተዳድራቸው እንደ ዋትስአፕና ኢንስታግራም ባሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተጠቃሚዎች ቁጥር 15 በመቶ ከፍ ብሎልኛል ብሏል። • በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትርፉ መጨመሩን ሳምሰንግ አስታወቀ • ኮሮናቫይረስ የቀሰቀሳቸው የአና የሚበሉ ሥዕሎች • ከኮሮናቫይረስ የትኞቹ ድርጅቶች አተረፉ? እነማንስ ከሰሩ? የአማዞን የሩብ ዓመት ትርፍ 5.2 ቢሊየን ዶላር ሲሆን ድርጅቱ ከተቋቋመበት ከአውሮፓውያኑ 1994 ጀምሮ ይህ ከፍተኛው ነው ተብሏል። ድርጅቱ እንደውም ከኮሮናቫይረስ መከሰት በኋላ ለሰራተⶉቹ መከላከያ መሳሪያዎችን ለመግዛትና የመከላከያ ጥንቃቄዎችን ለማድረግ ከፍተኛ ወጪ ማውጣቱ ትርፉን ዝቅ ያደርገዋል ተብሎ ተፈርቶ ነበር። በአጠቃላይ በበይነ መረብ የሚካሄዱ ንግዶች የሽያጭ መጠኑ 40 በመቶ ከፍ ብሏል። እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ባሉት ሶስት ወራት ደግሞ በአጠቃላይ 88.9 ቢሊየን ዶላር አንቀሳቅሷል። ትርፍም ቢሆን በአስገራሚ ሁኔታ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 2.6 ቢሊየን ዶላር ወደ 5.2 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል። በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት ቤት ውስጥ ብዙ ጊዜያቸውን ማሳለፋቸውን ተከትሎ የበይነ መረብ ሽያጭ በእጅጉ ተጧጡፏል። አማዞንም ቢሆን የደንበኞቹን ፍላጎት ለማሟላት በሩብ ዓመቱ ብቻ ተጨማሪ 175 ሺ ሰራተኞችን ቀጥሯል። ፍላጎቱ በዚሁ መቀጠሉ ስለማይቀር በርካታ መጋዘኖችንና ሰራተኞችን ለመጨመርም እያሰበ ነው። የአፕል የሩብ ዓመት ትርፍ ደግሞ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 11 በመቶ በመጨመር 59.7 ቢሊየን ደርሷል። ሰዎች ስራቸውን ከቤታቸው ሆነው መስራታቸው የተለያዩ መገልገያዎችን እንዲጠቀሙ አድርጓቸዋል። በዚህም ምክንያት የማክ ላፕቶፖችና አይፓዶች በእጅጉ ተፈላጊ ነበሩ። ሁለቱም የአፕል ምርቶች ከወረርሽኙ መከሰት በኋላ ገበያቸው እንደደራ ድርጅቱ አስታውቋል። በዚህም ምክንያት ባለፈው ከነበረው 10 ቢሊየን ዶላር ትርፍ ወደ 11.25 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል። ፌስቡክ ደግሞ ከኮሮናቫይረስ በኋላ ትርፉ በእጅጉ እንደሚቀንስ ቢጠበቅም እንደውም የ 11 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። አነስተኛ ድርጅቶች ያሏቸው ሰዎች ለማስታወቂያ ወደ ፌስቡክ ላይሄዱ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ተንብየው ነበር። ነገር ግን ወረርሽኙን ተከትሎ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር በእጅጉ በመጨመሩ ምክንያት ለማስታወቂያ የሚመጡ ድርጅቶችም ቁጥር አብሮ ከፍ ብሏል። በዚህም ምክንያት የድርጅቱ የሩብ ዓመት ትርፍ 5.2 ቢሊየን ዶላር እንዲደርስ ሆኗል። ፌስቡክ እንደሚለው ባለፈው ሰኔ ወር ብቻ በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያዎቸ ላይ 2.4 ቢሊየን ተጠቃሚዎች የነበሩ ሲሆን ይህም የ15 በመቶ ጭማሪ አለው። ከአራቱ ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው አልፋቤትም ቢሆን እንደ ሌሎቹ ባይሆንም ትርፋማ ሆኗል። ድርጅቱ በስሩ ጉግልና ዩቲዩብን የያዘ ሲሆን እስካሁን ያገኘሁት ትርፍ 38.3 ቢሊየን ዶላር ነው ብሏል። ይህ ደግሞ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የሁለት በመቶ ቅናሽ ያሳያል።
https://www.bbc.com/amharic/news-53605349
2health
"ኮሮናቫይረስ በአዲሱ ዓመት ይረታል የሚል ተስፋ አለኝ" ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም
የዓለም የጤና ድርጀት ዋና ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም የዓለም አገራት በጋራ የሚሠሩ ከሆነ ኮሮናቫይረስ በአዲሱ የአውሮፓዊያኑ አዲስ ዓመት 2022 ይረታል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገለጹ። የዓለም የጤና ድርጅት በቻይና የተቀሰቀሰውን ቫይረስ በተመለከተ ሪፖርት ከደረሰው ሁለተኛ ዓመቱ በተቆጠረበት በዚህ ወቅት አዲሱን ዓመት በማስመልከት በሰጡት መግለጫ "ጠባብ ብሔርተኝነት እና ክትባትን ማከማቸት" አደጋ ናቸው ሲሉም አስጠንቅቀዋል። እስካሁን በመላው ዓለም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ287 ሚሊዮን የተሻገረ ሲሆን ከ5.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ዶ/ር ቴድሮስ አሁን ላይ ኮሮናቫይረስን ለማከም የተሻሉ መንገዶች መኖራቸውን ገልጸው፣ ፍትሐዊ የሆነ የክትባት ክፍፍል ባለመኖሩ ቫይረሱ ቅርጹን እየቀያየረ እንዲከሰት ዕድል ፈጥሯል ብለዋል። "በአንዳንድ አገሮች ጠባብ ብሔርተኝነት እና የክትባት ክምችት ፍትሐዊነትን አጓድሏል። እናም ለኦሚክሮን ዝርያ መፈጠር ተስማሚ ሁኔታዎችን ፈጥሯል። ቫይረሱ እየተለዋወጠ በመጣ ቁጥር የመቆጣጠር እና የመተንበይ አቅማችን እየቀነሰ ይሄዳል" ያሉት ዶ/ር ቴድሮስ "ኢ-ፍትሐዊነትን ከገታን ወረርሽኙን እንገታዋለን" ሲሉም አክለዋል። በአውሮፓ እና በአሜሪካ ሰዎች ቢያንስ አንድ ዙር የኮሮናቫይረስ ክትባት የወሰዱ ሲሆን የዓለም የጤና ድርጅት የአውሮፓዊያኑ 2021 ከመጠናቀቁ በፊት በመላው ዓለም ቢያንስ 40 በመቶ ሕዝብ ክትባት እንዲያገኝ ያቀደው ዕቅድ በተለይም በአብዛኛው የአፍሪካ አገራት ሳይሳካ ቀርቷል። ዶ/ር ቴድሮስ ከዚህ ቀደም የበለፀጉ አገራት የዓለም አቀፍ የክትባት አቅርቦትን "በማግበስበስ" አብዛኛው ሕዝባቸውን ሁለት ዙር ሲከትቡ ሌሎች የመጀመሪያውን ዙር ክትባት እየተጠባበቁ ይገኛሉ በማለት ወቅሰዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ለመጪው አዲስ ዓመት 2022 ባስቀመጠው አዲስ ግብ፣ ወረርሽኙን ለማጥፋት በሁሉም አገራት ቢያንስ እስከመጪው ነሐሴ ድረስ 70 በመቶ ክትባቱን ለማዳረስ አቅዷል።
"ኮሮናቫይረስ በአዲሱ ዓመት ይረታል የሚል ተስፋ አለኝ" ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም የዓለም የጤና ድርጀት ዋና ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም የዓለም አገራት በጋራ የሚሠሩ ከሆነ ኮሮናቫይረስ በአዲሱ የአውሮፓዊያኑ አዲስ ዓመት 2022 ይረታል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገለጹ። የዓለም የጤና ድርጅት በቻይና የተቀሰቀሰውን ቫይረስ በተመለከተ ሪፖርት ከደረሰው ሁለተኛ ዓመቱ በተቆጠረበት በዚህ ወቅት አዲሱን ዓመት በማስመልከት በሰጡት መግለጫ "ጠባብ ብሔርተኝነት እና ክትባትን ማከማቸት" አደጋ ናቸው ሲሉም አስጠንቅቀዋል። እስካሁን በመላው ዓለም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ287 ሚሊዮን የተሻገረ ሲሆን ከ5.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ዶ/ር ቴድሮስ አሁን ላይ ኮሮናቫይረስን ለማከም የተሻሉ መንገዶች መኖራቸውን ገልጸው፣ ፍትሐዊ የሆነ የክትባት ክፍፍል ባለመኖሩ ቫይረሱ ቅርጹን እየቀያየረ እንዲከሰት ዕድል ፈጥሯል ብለዋል። "በአንዳንድ አገሮች ጠባብ ብሔርተኝነት እና የክትባት ክምችት ፍትሐዊነትን አጓድሏል። እናም ለኦሚክሮን ዝርያ መፈጠር ተስማሚ ሁኔታዎችን ፈጥሯል። ቫይረሱ እየተለዋወጠ በመጣ ቁጥር የመቆጣጠር እና የመተንበይ አቅማችን እየቀነሰ ይሄዳል" ያሉት ዶ/ር ቴድሮስ "ኢ-ፍትሐዊነትን ከገታን ወረርሽኙን እንገታዋለን" ሲሉም አክለዋል። በአውሮፓ እና በአሜሪካ ሰዎች ቢያንስ አንድ ዙር የኮሮናቫይረስ ክትባት የወሰዱ ሲሆን የዓለም የጤና ድርጅት የአውሮፓዊያኑ 2021 ከመጠናቀቁ በፊት በመላው ዓለም ቢያንስ 40 በመቶ ሕዝብ ክትባት እንዲያገኝ ያቀደው ዕቅድ በተለይም በአብዛኛው የአፍሪካ አገራት ሳይሳካ ቀርቷል። ዶ/ር ቴድሮስ ከዚህ ቀደም የበለፀጉ አገራት የዓለም አቀፍ የክትባት አቅርቦትን "በማግበስበስ" አብዛኛው ሕዝባቸውን ሁለት ዙር ሲከትቡ ሌሎች የመጀመሪያውን ዙር ክትባት እየተጠባበቁ ይገኛሉ በማለት ወቅሰዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ለመጪው አዲስ ዓመት 2022 ባስቀመጠው አዲስ ግብ፣ ወረርሽኙን ለማጥፋት በሁሉም አገራት ቢያንስ እስከመጪው ነሐሴ ድረስ 70 በመቶ ክትባቱን ለማዳረስ አቅዷል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59845457
2health
ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ አለፈ
በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ ማለፉን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ህዳር 2/2013 ዓ.ም አስታወቀ። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በፌስቡክ ገፁ ላይ ይፋ እንዳደረገው በኢትዮጵያ ኮሮናቫይረስ መከሰቱ ከታወቀበት መጋቢት 4 /2012 ዓ.ም ጀምሮ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 100 ሺህ አልፏል። የኮቪድ-19 ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በቫይረሱ የተያዘ ሰው የተገኘው መጋቢት 4/ 2012 ዓ.ም ሲሆን እስካሁን ድረስ ለ1,534,470 ምርመራ ተደርጎ 100 ሺህ 327 በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በኢትዮጵያ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 1ሺህ 537 መሆናቸውን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መግለጫ ያትታል። አክሎም 61 ሺህ 516 ህሙማንም ከበሽታው አገግመዋል ሲል ገልጿል። የጤና ሚኒስቴሩ አክሎም "ኮሮና የለም" ከሚል የተሳሳተ አመለካከት በመውጣት ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በመከላከሉ ላይ ጠንክሮ እንዲሰራ ጥሪ አቅርቧል። የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትም "ማስክ ካልተደረገ አገልግሎት የለም" የሚለውን መርህ እንዲከተሉ አሳስቧል። በበርካታ አገራት በኮቪድ-19 የሚያዙ ከፍተኛ ቁጥር መመዝገቡን ተከለትሎ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን አልፏል። እንደጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ከሆነ ከ1.25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። በብዙ አገራት በቂ ምርመራ ባለመደረጉ እንጂ ይህን አሃዝ ከፍ ያለ ነው ተብሎ ይገመታል። በመላው አለም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁትር 51,554,166 መድረሱን የዩኒቨርስቲው መረጃ ያሳያል። በቫይረሱ በከፍተኛ ቁጥር ከተያዙት አገራት መካከል አሜሪካ፣ ሕንድ እና ብራዚል ከቀዳሚዎቹ ተርታ ይገኙበታል። እንደ አፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር መረጃ ከሆነ እስካሁን ድረስ በአፍሪካ 1,904,820 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 45,954 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን ከዚሁ ጋር በተያያዘ አጥተዋል።
ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ አለፈ በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ ማለፉን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ህዳር 2/2013 ዓ.ም አስታወቀ። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በፌስቡክ ገፁ ላይ ይፋ እንዳደረገው በኢትዮጵያ ኮሮናቫይረስ መከሰቱ ከታወቀበት መጋቢት 4 /2012 ዓ.ም ጀምሮ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 100 ሺህ አልፏል። የኮቪድ-19 ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በቫይረሱ የተያዘ ሰው የተገኘው መጋቢት 4/ 2012 ዓ.ም ሲሆን እስካሁን ድረስ ለ1,534,470 ምርመራ ተደርጎ 100 ሺህ 327 በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በኢትዮጵያ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 1ሺህ 537 መሆናቸውን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መግለጫ ያትታል። አክሎም 61 ሺህ 516 ህሙማንም ከበሽታው አገግመዋል ሲል ገልጿል። የጤና ሚኒስቴሩ አክሎም "ኮሮና የለም" ከሚል የተሳሳተ አመለካከት በመውጣት ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በመከላከሉ ላይ ጠንክሮ እንዲሰራ ጥሪ አቅርቧል። የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትም "ማስክ ካልተደረገ አገልግሎት የለም" የሚለውን መርህ እንዲከተሉ አሳስቧል። በበርካታ አገራት በኮቪድ-19 የሚያዙ ከፍተኛ ቁጥር መመዝገቡን ተከለትሎ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን አልፏል። እንደጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ከሆነ ከ1.25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። በብዙ አገራት በቂ ምርመራ ባለመደረጉ እንጂ ይህን አሃዝ ከፍ ያለ ነው ተብሎ ይገመታል። በመላው አለም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁትር 51,554,166 መድረሱን የዩኒቨርስቲው መረጃ ያሳያል። በቫይረሱ በከፍተኛ ቁጥር ከተያዙት አገራት መካከል አሜሪካ፣ ሕንድ እና ብራዚል ከቀዳሚዎቹ ተርታ ይገኙበታል። እንደ አፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር መረጃ ከሆነ እስካሁን ድረስ በአፍሪካ 1,904,820 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 45,954 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን ከዚሁ ጋር በተያያዘ አጥተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54874864
5sports
ኢትዮጵያ ባለፉት 20 ዓመታት በኦሊምፒክ ዝቅተኛውን ውጤት ያስመዘገበችው መቼ ነበር?
በኮሮናቫይረስ ምክንያት በአንድ ዓመት ተራዝሞ አምና ታቅዶ ዘንድሮ የተካሄደው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ውድድር ተጠናቋል። ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የዘንድሮውን ውድድር በ113 ሜዳሊያዎች በቁንጮነት ስታጠናቅቅ፣ ቻይና ሁለተኛ፣ አዘጋጇ ጃፓን ሦስተኛ፣ ጎረቤት አገር ኬንያ 19ኛ፤ ኢትዮጵያ ደግሞ 56ኛ ሆነው አጠናቀዋል። በዘንድሮው የኦሊምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ ያመጣችው ውጤት ዝቅተኛ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ኢትዮጵያ ጎልታ ከምትታይባቸው ዓለም አቀፍ የስፖርት መድረኮች መካከል ቀዳሚው በሆነው በኦሊምፒክ ውድድር ላይ የአገሪቱ አትሌቶች አኩሪ ውጤት እንዲያመጣ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በጉጉት ይጠብቃል። በኦሊምፒክ መድረክ ላይ በባዶ እግሩ ጭምር ሮጦ በተከታታይ በማራቶን ወርቅ በማግኘት ታሪክ የሰራው አበበ ቢቂላ በተወዳደረባት ቶኪዮ በተካሄደው ኦሊምፒክ ላይ ኢትዮጵያ ከፍያለ ድል ታገኛለች ብለው ጠብቀው ነበር። ነገር ግን የታሰበው ሳይሆን ልዑኩ ከመነሻው ባለመግባባት ውስጥ ሆኖ ኢትዮጵያ በዘንድሮው የኦሊምፒክ ጨዋታ 1 የወርቅ፣ አንድ የብር እና ሁለት የነሐስ በአጠቃላይ 4 ሜዳሊያዎች አግኝታ ባለፉት 20 ዓመታት ከተመዘገበው ዝቅተኛው ውጤት ሆኗል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ብቸኛውን ወርቅ ማግኘት የቻለው በ10 ሺህ ሜትር በአትሌት ሰለሞን ባረጋ አማካይነት ነው። በሦስት ሺህ ሜትር መሰናክል በአትሌት ግርማ ለሜቻ ብቸኛው ብር ሲገኝ ለተሰንበት ግደይና ጉዳፍ ፀጋይ እያንዳንዳቸው የነሐስ ሜዳሊያ አምጥተዋል። የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ቡድን በአትሌቲክስ 34 አትሌቶችን፣ በብስክሌት እሽቅድምድም አንዲት ሴት ተወዳዳሪ፣ በውሃ ዋና አንድ ተወዳዳሪ እንዲሁም በቴኳዋንዶ አንድ በድምሩ 37 ስፖርተኞችን ይዞ ነበር ወደ ቶኪዮ ያቀናው። ኢትዮጵያ ባለፈው ብራዚል የሪዮ ላይ በተካሄደው የ2016 ኦሊምፒክ 1 የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘች ቢሆንም በሦስት የብርና 4 የነሐስ በድምሩ 8 ሜዳሊዎች ማግኘት ችላ ነበር። ኢትዮጵያ ባለፉት 20 ዓመታት የዘንድሮው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ውጤት ባለፉት 20 ዓመታት ኢትዮጵያ ካስመዘገበቻቸው ውጤቶች ዝቅተኛው የሚባል ነው። የዛሬ 20 ዓመት በተደረገው የሲድኒ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴና በሻለቃ ደራርቱ ቱሉ በ10 ሺህ ሜትር በሁለቱም ፆታዎች እንዲሁም በሚሊዮን ወልዴና በገዛኸኝ አበራ 4 ወርቅ ማምጣቷ ይታወሳል። ከዚህም በተጨማሪ በጌጤ ዋሚ፣ በአሰፋ መዝገቡና በተስፋዬ ቶላ አራት ሜዳሊያዎችን በማከል ውድድሩን በ8 ሜዳሊያዎች ነበር ያጠናቀቀችው። ከሲድኒ ቀጥሎ የኦሊምፒክ ጨዋታዎችን ባዘጋጀችው የግሪኳ አቴንስም ኢትዮጵያ በአትሌቶቿ በሜዳሊያ ተንቆጥቁጣ ነበር። ኢትዮጵያን ወክሎ ወደ ግሪክ መዲና አቴንስ ያቀናው የኦሊምፒክ ቡድን በቀነኒሳ በቀለና በመሠረት ደፋር ሁለት ወርቆችና በሌሎች አትሌቶች ደግሞ ተጨማሪ 5 ሜዳሊያዎች በድምሩ 7 ሜዳሊያዎች ይዞ ተመልሷል። የውድድሩን አዘጋጅነት ከአቴንስ የተረከበችው የቻይናዋ ቤይጂንግም የኢትዮጵያ ባንዲራ ከፍ ብሎ መውለብለቡ ከአእምሮ የሚጠፋ አይደለም። በወቅቱ የቤይጂንግ ኦሊምፒክ ፈርጦች የተባሉት ቀነኒሳ በቀለና ጥሩነሽ ዲባባ እያንዳንዳቸው በ10 ሺህና 5 ሺህ ሜትር ውድድሮች ሁለት ሁለት ወርቅ በማምጣት ደምቀው ነበር። ከጥሩነሽና ቀነኒሳ በተጨማሪ በመሠረት ደፋር፣ በስለሺ ስህንና በፀጋዬ ከበደ ሜዳሊያዎች ታጅቦ ነው ቡድኑ አዲስ አበባ የገባው። በፈረንጆቹ 2012 በተካሄደው የለንደን ኦሊምፒክ ላይም ኢትዮጵያ ሜዳሊያ ብርቋ አልነበረም። በዚህ ውድድር ሦስቱ እንስት አትሌቶች ጥሩነሽ ዲባባ፣ መሠረት ደፋርና ቲኪ ገላና ወርቅ ማጥለቃቸው ይታወሳል። በለንደን ኦሊምፒክ ከሦስቱ አትሌቶች በተጨማሪ ሁለት ብርና ሦስት የነሐስ ሜዳሊያዎችን በአትሌቶቿ ያገኘችው ኢትዮጵያ ከእንግሊዝ የተመለሰችው በደመቀ ድል ነበር። በሪዮው ኦሊምፒክ ደግሞ አንድ ወርቅ፣ ሁለት ብርና 5 ነሐስ በማምጣት 8 ሜዳሊያዎችን ለማግኘት ችላ ነበር። የዘንድሮው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ውጤት ባለፉት 20 ዓመታት ኢትዮጵያ ከተመዘገበው የሜዳሊያ ብዛት ዝቅተኛው ነው። ቅድመ - 2000 ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ ውድድሮች መሳተፍ የጀመረችው ከፈረንጆቹ 1956 ጀምሮ ነው። እንደ አውሮፓውያኑ በ1956ቱ አውስትራሊያ ውስጥ በተካሄደው የሜልበርን ኦሊምፒክ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በውድድሩ ሜዳሊያ ማግኘት ሳይችል ተመልሷል። ነገር ግን በተከታይነት በተካሄደውና ኢትየጵያ ለሁለተኛ ጊዜ በተሳተፈችበት የሮም ኦሊምፒክ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ በአበበ ቢቂላ አማካይነት ለማግኘት ችላለች። ኢትዮጵያ በ1976 በካናዳው የሞንትሪያል ኦሊምፒክ ጨዋታዎች እንዲሁም በተከታታይ በአሜሪካ ሎስ አንጀለስና በደቡብ ኮሪያዋ ሴኡል በተካሄዱት ኦሊምፒኮች አልተሳተፈችም። ነገር ግን በፈረንጆቹ 1980 ሞስኮ ላይ በተካሄደው ኦሊምፒክ ተሳትፋ በሁለት የወርቅና በሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎች ከዓለም 17ኛ መውጣት ችላለች። ኢትዮጵያ ከመጀመሪያው የኦሊምፒክ ተሳትፎዋ አንስቶ እስከዛሬ ድረስ በተሳተፈችባቸው የኦሊምፒክ ውድድሮች በአትሌቲክስ 55 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። ይህ ውጤት ኢትዮጵያን ከኬንያና ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል በአፍሪካ በርካታ የኦሊምፒክ ሜዳሊያ ያላት ሦስተኛዋ አገር ያደርጋታል። በዘንድሮው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ደግሞ በሜዳሊያ ብዛት ከአፍሪካ አምስተኛ መሆን ችላለች።
ኢትዮጵያ ባለፉት 20 ዓመታት በኦሊምፒክ ዝቅተኛውን ውጤት ያስመዘገበችው መቼ ነበር? በኮሮናቫይረስ ምክንያት በአንድ ዓመት ተራዝሞ አምና ታቅዶ ዘንድሮ የተካሄደው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ውድድር ተጠናቋል። ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የዘንድሮውን ውድድር በ113 ሜዳሊያዎች በቁንጮነት ስታጠናቅቅ፣ ቻይና ሁለተኛ፣ አዘጋጇ ጃፓን ሦስተኛ፣ ጎረቤት አገር ኬንያ 19ኛ፤ ኢትዮጵያ ደግሞ 56ኛ ሆነው አጠናቀዋል። በዘንድሮው የኦሊምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ ያመጣችው ውጤት ዝቅተኛ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ኢትዮጵያ ጎልታ ከምትታይባቸው ዓለም አቀፍ የስፖርት መድረኮች መካከል ቀዳሚው በሆነው በኦሊምፒክ ውድድር ላይ የአገሪቱ አትሌቶች አኩሪ ውጤት እንዲያመጣ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በጉጉት ይጠብቃል። በኦሊምፒክ መድረክ ላይ በባዶ እግሩ ጭምር ሮጦ በተከታታይ በማራቶን ወርቅ በማግኘት ታሪክ የሰራው አበበ ቢቂላ በተወዳደረባት ቶኪዮ በተካሄደው ኦሊምፒክ ላይ ኢትዮጵያ ከፍያለ ድል ታገኛለች ብለው ጠብቀው ነበር። ነገር ግን የታሰበው ሳይሆን ልዑኩ ከመነሻው ባለመግባባት ውስጥ ሆኖ ኢትዮጵያ በዘንድሮው የኦሊምፒክ ጨዋታ 1 የወርቅ፣ አንድ የብር እና ሁለት የነሐስ በአጠቃላይ 4 ሜዳሊያዎች አግኝታ ባለፉት 20 ዓመታት ከተመዘገበው ዝቅተኛው ውጤት ሆኗል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ብቸኛውን ወርቅ ማግኘት የቻለው በ10 ሺህ ሜትር በአትሌት ሰለሞን ባረጋ አማካይነት ነው። በሦስት ሺህ ሜትር መሰናክል በአትሌት ግርማ ለሜቻ ብቸኛው ብር ሲገኝ ለተሰንበት ግደይና ጉዳፍ ፀጋይ እያንዳንዳቸው የነሐስ ሜዳሊያ አምጥተዋል። የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ቡድን በአትሌቲክስ 34 አትሌቶችን፣ በብስክሌት እሽቅድምድም አንዲት ሴት ተወዳዳሪ፣ በውሃ ዋና አንድ ተወዳዳሪ እንዲሁም በቴኳዋንዶ አንድ በድምሩ 37 ስፖርተኞችን ይዞ ነበር ወደ ቶኪዮ ያቀናው። ኢትዮጵያ ባለፈው ብራዚል የሪዮ ላይ በተካሄደው የ2016 ኦሊምፒክ 1 የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘች ቢሆንም በሦስት የብርና 4 የነሐስ በድምሩ 8 ሜዳሊዎች ማግኘት ችላ ነበር። ኢትዮጵያ ባለፉት 20 ዓመታት የዘንድሮው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ውጤት ባለፉት 20 ዓመታት ኢትዮጵያ ካስመዘገበቻቸው ውጤቶች ዝቅተኛው የሚባል ነው። የዛሬ 20 ዓመት በተደረገው የሲድኒ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴና በሻለቃ ደራርቱ ቱሉ በ10 ሺህ ሜትር በሁለቱም ፆታዎች እንዲሁም በሚሊዮን ወልዴና በገዛኸኝ አበራ 4 ወርቅ ማምጣቷ ይታወሳል። ከዚህም በተጨማሪ በጌጤ ዋሚ፣ በአሰፋ መዝገቡና በተስፋዬ ቶላ አራት ሜዳሊያዎችን በማከል ውድድሩን በ8 ሜዳሊያዎች ነበር ያጠናቀቀችው። ከሲድኒ ቀጥሎ የኦሊምፒክ ጨዋታዎችን ባዘጋጀችው የግሪኳ አቴንስም ኢትዮጵያ በአትሌቶቿ በሜዳሊያ ተንቆጥቁጣ ነበር። ኢትዮጵያን ወክሎ ወደ ግሪክ መዲና አቴንስ ያቀናው የኦሊምፒክ ቡድን በቀነኒሳ በቀለና በመሠረት ደፋር ሁለት ወርቆችና በሌሎች አትሌቶች ደግሞ ተጨማሪ 5 ሜዳሊያዎች በድምሩ 7 ሜዳሊያዎች ይዞ ተመልሷል። የውድድሩን አዘጋጅነት ከአቴንስ የተረከበችው የቻይናዋ ቤይጂንግም የኢትዮጵያ ባንዲራ ከፍ ብሎ መውለብለቡ ከአእምሮ የሚጠፋ አይደለም። በወቅቱ የቤይጂንግ ኦሊምፒክ ፈርጦች የተባሉት ቀነኒሳ በቀለና ጥሩነሽ ዲባባ እያንዳንዳቸው በ10 ሺህና 5 ሺህ ሜትር ውድድሮች ሁለት ሁለት ወርቅ በማምጣት ደምቀው ነበር። ከጥሩነሽና ቀነኒሳ በተጨማሪ በመሠረት ደፋር፣ በስለሺ ስህንና በፀጋዬ ከበደ ሜዳሊያዎች ታጅቦ ነው ቡድኑ አዲስ አበባ የገባው። በፈረንጆቹ 2012 በተካሄደው የለንደን ኦሊምፒክ ላይም ኢትዮጵያ ሜዳሊያ ብርቋ አልነበረም። በዚህ ውድድር ሦስቱ እንስት አትሌቶች ጥሩነሽ ዲባባ፣ መሠረት ደፋርና ቲኪ ገላና ወርቅ ማጥለቃቸው ይታወሳል። በለንደን ኦሊምፒክ ከሦስቱ አትሌቶች በተጨማሪ ሁለት ብርና ሦስት የነሐስ ሜዳሊያዎችን በአትሌቶቿ ያገኘችው ኢትዮጵያ ከእንግሊዝ የተመለሰችው በደመቀ ድል ነበር። በሪዮው ኦሊምፒክ ደግሞ አንድ ወርቅ፣ ሁለት ብርና 5 ነሐስ በማምጣት 8 ሜዳሊያዎችን ለማግኘት ችላ ነበር። የዘንድሮው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ውጤት ባለፉት 20 ዓመታት ኢትዮጵያ ከተመዘገበው የሜዳሊያ ብዛት ዝቅተኛው ነው። ቅድመ - 2000 ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ ውድድሮች መሳተፍ የጀመረችው ከፈረንጆቹ 1956 ጀምሮ ነው። እንደ አውሮፓውያኑ በ1956ቱ አውስትራሊያ ውስጥ በተካሄደው የሜልበርን ኦሊምፒክ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በውድድሩ ሜዳሊያ ማግኘት ሳይችል ተመልሷል። ነገር ግን በተከታይነት በተካሄደውና ኢትየጵያ ለሁለተኛ ጊዜ በተሳተፈችበት የሮም ኦሊምፒክ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ በአበበ ቢቂላ አማካይነት ለማግኘት ችላለች። ኢትዮጵያ በ1976 በካናዳው የሞንትሪያል ኦሊምፒክ ጨዋታዎች እንዲሁም በተከታታይ በአሜሪካ ሎስ አንጀለስና በደቡብ ኮሪያዋ ሴኡል በተካሄዱት ኦሊምፒኮች አልተሳተፈችም። ነገር ግን በፈረንጆቹ 1980 ሞስኮ ላይ በተካሄደው ኦሊምፒክ ተሳትፋ በሁለት የወርቅና በሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎች ከዓለም 17ኛ መውጣት ችላለች። ኢትዮጵያ ከመጀመሪያው የኦሊምፒክ ተሳትፎዋ አንስቶ እስከዛሬ ድረስ በተሳተፈችባቸው የኦሊምፒክ ውድድሮች በአትሌቲክስ 55 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። ይህ ውጤት ኢትዮጵያን ከኬንያና ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል በአፍሪካ በርካታ የኦሊምፒክ ሜዳሊያ ያላት ሦስተኛዋ አገር ያደርጋታል። በዘንድሮው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ደግሞ በሜዳሊያ ብዛት ከአፍሪካ አምስተኛ መሆን ችላለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-58162024
0business
በማልኮም ኤክስ ግድያ በስህተት ለ20 ዓመታት የታሰረው ግለሰብ 40 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ጠየቀ
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹን ማልኮም ኤክስን ገድለሃል ተብሎ በስህተት ጥፋተኛ ተብሎ 20 ዓመታትን በእስር ያሳለፈው ሙሃመድ አዚዝ ኒው ዮርክ ከተማ 40 ሚሊዮን ዶላር እንዲክሰው ጠየቀ። ሙሃመድ አዚዝ የማልኮም ኤክስን ግድያ ተከትሎ ከታሰረ ከ20 ዓመታት በኋላ ከእስር የተለቀቀው በ1985 ነበር። በ2021 ዐቃቤ ሕግ አዲስ ማስረጃ አግኝቻለሁ በሚል ሙሃመድ አዚዝ ወንጀሉን አልፈጸመም ብሏል። የቀድሞ የባሕር ኃይል አባሉ ሙሃመድ አዚዝ በ1965 ሲታሰሩ የ6 ልጆች አባት እና የ26 ዓመት ወጣት ነበሩ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ማልኮም ኤክስ የአደባባይ ንግግር ለማድረግ ዝግጅት ላይ እያለ በታጠቁ ሦስት ሰዎች በጥይት ተደብድቦ ነበር የተገደለው። በወቅቱ በግድያው ተጠርጥሮ ሙሃመድ አዚዝ ከካህሊል ኢስላም ጋር ነበር የታሰረው። 22 ዓመታትን በእስራት ያሳለፈው ኢስላም በ2009 ሕይወቱ አልፏል። ዐቃቤ ሕግ ተጨባጭ ማስረጃ ሳያቀርብ፤ የሚጣረስ ሃሳብ የሰጡ ምስክሮችን አሰምቶ በሁለቱ ግለሰቦች ላይ ብይን ያሰጠው። ግድያው በተፈጸመበት ቦታ በቁጥጥር ሥር የዋለው እና ማልኮም ኤክስን መግደሉን ያመነው ታለማደግ ሃዬር፤ በሁለቱ ግለሰቦች የፍርድ ሂደት ላይ ቀርቦ በወንጀሉ እጃቸው የለበትም ሲል ምስክርነቱን ሰጥቶ ነበር። በ1970ዎቹ ደግሞ በግድያው ሌሎች አራት ሰዎች መሳተፋቸውን ሃየር የጽሑፍ ቃለ መሃላ ፈጽሟል። በ2020 የእነ ሙሃመድ ጉዳይ ተጣርቶ ንጽህናቸው እንዲረጋገጥ ክሱን እንደገና ማየት ተጀምሮ ነበር።  የሁለቱን ተጠርጣሪዎች ጥብቅና የያዘው ዴቪድ ሻኒስ፣ በመንግሥት ግዴለሽ አሰራር ምክንያት ሁለቱ ሰዎች በስሕተት 42 ዓመታትን እስር ቤት እንዲያሳልፉ ተደርገዋል ብሏል። “የዘገየ ፍርድ እንደተነፈገ ይቆጠራል። ሙሃመድ አዚዝ 84 ዓመታቸው ነው። ኢስላም ደግሞ እንዳለመታደል ሆኖ ንጽህናቸው ሳይረጋገጥ ሕይወታቸው አልፏል” ብሏል ጠበቃው ዴቪድ። ባለፈው ዓመት የማልኮም ኤክስ ልጅ የአባቴ ጉዳይ እንደገና ይታይልኝ በማለት አመልክታ ነበር። የማልከም ኤክስ ሴት ልጅ በግድያው ወቅት ፖሊስ የነበረ ሰው ጽፎ አስቀምጦታል ያለችውን ደብዳቤ በመጥቀስ ግድያውን ያቀነባበሩት ኤፍቢአይ እና የኒው ዮርክ ፖሊስ ናቸው ብላለች። እነዚህ ማስረጃዎች ተደማምረው 20 ዓመታትን በእስር ያሳላፉት የ84 ዓመቱ ሙሃመድ አዚዝን በኒው ዮርክ ከተማ ላይ ክስ እንዲመሰርቱ አድርጓቸዋል። ያላአግባብ እና በመንግሥት ግዴለሽ አሰራር ምክንያት ለታሰሩበት ለሁለት አስርት ዓመታትም 40 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል።
በማልኮም ኤክስ ግድያ በስህተት ለ20 ዓመታት የታሰረው ግለሰብ 40 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ጠየቀ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹን ማልኮም ኤክስን ገድለሃል ተብሎ በስህተት ጥፋተኛ ተብሎ 20 ዓመታትን በእስር ያሳለፈው ሙሃመድ አዚዝ ኒው ዮርክ ከተማ 40 ሚሊዮን ዶላር እንዲክሰው ጠየቀ። ሙሃመድ አዚዝ የማልኮም ኤክስን ግድያ ተከትሎ ከታሰረ ከ20 ዓመታት በኋላ ከእስር የተለቀቀው በ1985 ነበር። በ2021 ዐቃቤ ሕግ አዲስ ማስረጃ አግኝቻለሁ በሚል ሙሃመድ አዚዝ ወንጀሉን አልፈጸመም ብሏል። የቀድሞ የባሕር ኃይል አባሉ ሙሃመድ አዚዝ በ1965 ሲታሰሩ የ6 ልጆች አባት እና የ26 ዓመት ወጣት ነበሩ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ማልኮም ኤክስ የአደባባይ ንግግር ለማድረግ ዝግጅት ላይ እያለ በታጠቁ ሦስት ሰዎች በጥይት ተደብድቦ ነበር የተገደለው። በወቅቱ በግድያው ተጠርጥሮ ሙሃመድ አዚዝ ከካህሊል ኢስላም ጋር ነበር የታሰረው። 22 ዓመታትን በእስራት ያሳለፈው ኢስላም በ2009 ሕይወቱ አልፏል። ዐቃቤ ሕግ ተጨባጭ ማስረጃ ሳያቀርብ፤ የሚጣረስ ሃሳብ የሰጡ ምስክሮችን አሰምቶ በሁለቱ ግለሰቦች ላይ ብይን ያሰጠው። ግድያው በተፈጸመበት ቦታ በቁጥጥር ሥር የዋለው እና ማልኮም ኤክስን መግደሉን ያመነው ታለማደግ ሃዬር፤ በሁለቱ ግለሰቦች የፍርድ ሂደት ላይ ቀርቦ በወንጀሉ እጃቸው የለበትም ሲል ምስክርነቱን ሰጥቶ ነበር። በ1970ዎቹ ደግሞ በግድያው ሌሎች አራት ሰዎች መሳተፋቸውን ሃየር የጽሑፍ ቃለ መሃላ ፈጽሟል። በ2020 የእነ ሙሃመድ ጉዳይ ተጣርቶ ንጽህናቸው እንዲረጋገጥ ክሱን እንደገና ማየት ተጀምሮ ነበር።  የሁለቱን ተጠርጣሪዎች ጥብቅና የያዘው ዴቪድ ሻኒስ፣ በመንግሥት ግዴለሽ አሰራር ምክንያት ሁለቱ ሰዎች በስሕተት 42 ዓመታትን እስር ቤት እንዲያሳልፉ ተደርገዋል ብሏል። “የዘገየ ፍርድ እንደተነፈገ ይቆጠራል። ሙሃመድ አዚዝ 84 ዓመታቸው ነው። ኢስላም ደግሞ እንዳለመታደል ሆኖ ንጽህናቸው ሳይረጋገጥ ሕይወታቸው አልፏል” ብሏል ጠበቃው ዴቪድ። ባለፈው ዓመት የማልኮም ኤክስ ልጅ የአባቴ ጉዳይ እንደገና ይታይልኝ በማለት አመልክታ ነበር። የማልከም ኤክስ ሴት ልጅ በግድያው ወቅት ፖሊስ የነበረ ሰው ጽፎ አስቀምጦታል ያለችውን ደብዳቤ በመጥቀስ ግድያውን ያቀነባበሩት ኤፍቢአይ እና የኒው ዮርክ ፖሊስ ናቸው ብላለች። እነዚህ ማስረጃዎች ተደማምረው 20 ዓመታትን በእስር ያሳላፉት የ84 ዓመቱ ሙሃመድ አዚዝን በኒው ዮርክ ከተማ ላይ ክስ እንዲመሰርቱ አድርጓቸዋል። ያላአግባብ እና በመንግሥት ግዴለሽ አሰራር ምክንያት ለታሰሩበት ለሁለት አስርት ዓመታትም 40 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cnl8ldxewvvo
0business
የናይጄሪያ ታጣቂዎች በባቡር ላይ ባደረሱት ጥቃት መንገደኞች ተገደሉ
በናይጄሪያ ርዕሰ መዲና አቡጃ እና ካዱና ከተማ በሚመላለስ ባቡር ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሰባት ተሳፋሪዎች መሞታቸውን የሆስፒታሉ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግሩ። ታጣቂዎቹ ሰኞ ምሽት ሃዲዱ ላይ ፍንዳታ በማድረስ 970 ተሳፋሪዎችን አሳፍሮ የነበረውን ባቡር አስገድደው አስቁመውታል። በመቀጠልም ታጣቂዎች ባቡሩን ከበው ተኩስ መክፈታቸውን አንድ ተሳፋሪ ለቢቢሲ ተናግሯል። ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ መንገደኞች ታፍነው ተወስደዋል። ባቡሩ በሁለቱ ከተሞች መካከል አስተማማኝ ነው ተብሎ በሚታሰበው የትራንስፖርት ዘዴ ነው። ለገንዘብ ሲሉ እገታ መፈጸም በመላ ናይጄሪያ የተለመደ ሆኗል። ታጣቂዎች በተለያየ ቦታ በመጠበቅ ተሽከርካሪዎችን ዒላማ ስለሚያደርጉ የአቡጃ-ካዱና አውራ ጎዳና በሃገሪቱ ካሉ አደገኛ መንገዶች አንዱ ሆኗል። ይህም መንገደኞች 150 ኪሜ የሚረዝመውን መንገድ በመተው ብዙዎች ፊታቸውን እአአ በ2016 ሥራ ወደ ጀመረው የባቡር መስመር እንዲያዞሩ ገፋፍቷቸዋል። ባለፉት ስድስት ወራት በሁለቱ ከተሞች መካከል ያለው የባቡር መስመር ዒላማ ሲደረግ ያሁኑ ለለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን እጅግ አሳሳቢውም አሳሳቢውም ነው ተብሏል። ሰኞ ማምሻውን ጥቃቱ የደረሰባቸው 22 ሰዎች ካዱና በሚገኘው ወታደራዊ ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ። በካዱና በሆስፒታል በጎ ፈቃደኝነት ሆና የምትሠራ አንዲት ሴት ለቢቢሲ እንደተናገረች በቦታው ከነበሩ ሰዎች እንደሰማችው ጥቃቱ "አስፈሪ" እና "አሰቃቂ" ነው። አንድ የባቡር መስመሩ ሠራተኛ እራሱን ጨምሮ "25 ሰዎችን ወደ ጫካ" ሲወስዱ ከአጋቾቹ ሮጦ ማምለጥ እንደቻለ ተናግሯል። ሌላኛዋ ደግሞ የተተኮሰባት "ጥይት በጉልበቷ አለፎ" በኋላም ወታደሮች እንደረሱላት ተናግራለች። አንድ ከፍተኛ የደህንነት ምንጭ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደገለፁት ወታደሮች በፍጥነት ወደ ስፍራው ደርሰዋል። "በፍጥነት በቦታው የደረሱት ወታደሮች ጥቃቱን መክተዋል። ወታደሮቹ ሲደርሱ ነው አሸባሪዎቹ የሸሹት። ባቡሩ ጥይት የማይበሳው በመሆኑ ወለሉ ላይ ተኝተው የነበሩትን ተሳፋሪዎች ከጉዳት ተከላክሏል" ብለዋል። የናይጄሪያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን (ኤንአርሲ) በሁለቱ ከተሞች መካከል ያለውን ሥራ አቁሟል። የካዱና ግዛት አስተዳዳሪ ጥቃቱን "የሽብር" ድርጊት ሲሉ አውግዘው ለተጎጂዎች ቤተሰቦችም መጽናናትን ተመኝተዋል። የባቡር መስመሩ ከሰሜን ምዕራብ ግዛቶች ወደ አቡጃ እና ወደ ደቡብ አቅጣጫ ለመጓዝ ለሚፈልጉ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች አገልግሎት ይሰጣል። የካዱና ግዛት ባለስልጣናት ሁሉም ተሳፋሪዎች የት እንዳሉ እና ማን በትክክል እንደጠፋ ለማወቅ ከኤንአርሲ ጋር ግንኙነት እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል ። ለገንዘብ ሲሉ ግድያና አፈና የሚፈጽሙ የታጠቁ ቡድኖች በሚገኙበት በሰሜን ናይጄሪያ ወታደሩ በአውሮፕላን ጭምር ጥቃት ቢፈጸምም ጥቃት ከማድረስ አላገዳቸውም። ባለፈው ቅዳሜ የካዱና ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ጥቃት ማድረሳቸው ይታወሳል።
የናይጄሪያ ታጣቂዎች በባቡር ላይ ባደረሱት ጥቃት መንገደኞች ተገደሉ በናይጄሪያ ርዕሰ መዲና አቡጃ እና ካዱና ከተማ በሚመላለስ ባቡር ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሰባት ተሳፋሪዎች መሞታቸውን የሆስፒታሉ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግሩ። ታጣቂዎቹ ሰኞ ምሽት ሃዲዱ ላይ ፍንዳታ በማድረስ 970 ተሳፋሪዎችን አሳፍሮ የነበረውን ባቡር አስገድደው አስቁመውታል። በመቀጠልም ታጣቂዎች ባቡሩን ከበው ተኩስ መክፈታቸውን አንድ ተሳፋሪ ለቢቢሲ ተናግሯል። ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ መንገደኞች ታፍነው ተወስደዋል። ባቡሩ በሁለቱ ከተሞች መካከል አስተማማኝ ነው ተብሎ በሚታሰበው የትራንስፖርት ዘዴ ነው። ለገንዘብ ሲሉ እገታ መፈጸም በመላ ናይጄሪያ የተለመደ ሆኗል። ታጣቂዎች በተለያየ ቦታ በመጠበቅ ተሽከርካሪዎችን ዒላማ ስለሚያደርጉ የአቡጃ-ካዱና አውራ ጎዳና በሃገሪቱ ካሉ አደገኛ መንገዶች አንዱ ሆኗል። ይህም መንገደኞች 150 ኪሜ የሚረዝመውን መንገድ በመተው ብዙዎች ፊታቸውን እአአ በ2016 ሥራ ወደ ጀመረው የባቡር መስመር እንዲያዞሩ ገፋፍቷቸዋል። ባለፉት ስድስት ወራት በሁለቱ ከተሞች መካከል ያለው የባቡር መስመር ዒላማ ሲደረግ ያሁኑ ለለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን እጅግ አሳሳቢውም አሳሳቢውም ነው ተብሏል። ሰኞ ማምሻውን ጥቃቱ የደረሰባቸው 22 ሰዎች ካዱና በሚገኘው ወታደራዊ ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ። በካዱና በሆስፒታል በጎ ፈቃደኝነት ሆና የምትሠራ አንዲት ሴት ለቢቢሲ እንደተናገረች በቦታው ከነበሩ ሰዎች እንደሰማችው ጥቃቱ "አስፈሪ" እና "አሰቃቂ" ነው። አንድ የባቡር መስመሩ ሠራተኛ እራሱን ጨምሮ "25 ሰዎችን ወደ ጫካ" ሲወስዱ ከአጋቾቹ ሮጦ ማምለጥ እንደቻለ ተናግሯል። ሌላኛዋ ደግሞ የተተኮሰባት "ጥይት በጉልበቷ አለፎ" በኋላም ወታደሮች እንደረሱላት ተናግራለች። አንድ ከፍተኛ የደህንነት ምንጭ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደገለፁት ወታደሮች በፍጥነት ወደ ስፍራው ደርሰዋል። "በፍጥነት በቦታው የደረሱት ወታደሮች ጥቃቱን መክተዋል። ወታደሮቹ ሲደርሱ ነው አሸባሪዎቹ የሸሹት። ባቡሩ ጥይት የማይበሳው በመሆኑ ወለሉ ላይ ተኝተው የነበሩትን ተሳፋሪዎች ከጉዳት ተከላክሏል" ብለዋል። የናይጄሪያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን (ኤንአርሲ) በሁለቱ ከተሞች መካከል ያለውን ሥራ አቁሟል። የካዱና ግዛት አስተዳዳሪ ጥቃቱን "የሽብር" ድርጊት ሲሉ አውግዘው ለተጎጂዎች ቤተሰቦችም መጽናናትን ተመኝተዋል። የባቡር መስመሩ ከሰሜን ምዕራብ ግዛቶች ወደ አቡጃ እና ወደ ደቡብ አቅጣጫ ለመጓዝ ለሚፈልጉ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች አገልግሎት ይሰጣል። የካዱና ግዛት ባለስልጣናት ሁሉም ተሳፋሪዎች የት እንዳሉ እና ማን በትክክል እንደጠፋ ለማወቅ ከኤንአርሲ ጋር ግንኙነት እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል ። ለገንዘብ ሲሉ ግድያና አፈና የሚፈጽሙ የታጠቁ ቡድኖች በሚገኙበት በሰሜን ናይጄሪያ ወታደሩ በአውሮፕላን ጭምር ጥቃት ቢፈጸምም ጥቃት ከማድረስ አላገዳቸውም። ባለፈው ቅዳሜ የካዱና ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ጥቃት ማድረሳቸው ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60923871
5sports
ሊዮኔል ሜሲ ለፓሪስ ሴንት ዠርሜን ለመጫወት ተስማማ
ሊዮኔል ሜሲ ከባርሴሎና በድንገት መውጣቱን ተከትሎ የፈረንሳዩ ክለብ ለመቀላቀል በሁለት ዓመት ኮንትራት መስማማቱን የቢቢሲ ስፖርት አምድ ጸሐፊው ጊለም ባላግ ተናገረ። ስምምነቱን ለማጠናቀቅ ሕክምና ማጠናቀቅ ብቻ ይቀረዋል። የ34 ዓመቱ የአርጀንቲና አምበል በላሊጋ የፋይናንስ ፍትሃዊ ጨዋታ ህግ መሰረት አዲስ ውል ለመፈረም ባለመቻሉ በብቸኝነት የተጫወተብትን ባርሳን ለመልቀቅ ተገዷል። የማውሪሲዮ ፖቸቲኖው ፒኤስጂ ባለፈው የውድድር ዘመን በሊግ 1 ከሊል በመቀጠል ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። ባላግ በቢቢሲ ሬዲዮ 5 ቀጥታ ስርጭት ላይ "ሁሉም ነገር ተረጋግጧል። ሊዮኔል ሜሲ የፒኤስጂ ተጫዋች ይሆናል። ይህ ነው። ባለፉት ጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የተከሰተ ነው" ብሏል። "ሃሳቡ የእግር ኳስ ህይወቱን በባርሴሎና ማድረግ ነበር። . . . ከዚያ በኳታር የዓለም ዋንጫ ጥሩ ነገር ማድረግ ነው።" ከዘመኑ ታላላቅ ተጫዋቾች አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት ሜሲ በ 13 ዓመቱ ለተቀላቀለበት ባርሳ 778 ጨዋታዎችን አከናውኖ 672 ግቦችን በስሙ አስመዝግቧል። የባላንዶርን ሽልማት ስድስት ጊዜ በማሸነፍ ባለክብረወሰን ሲሆን ከካታላኑ ክለብ ጋር 35 ዋንጫዎችን አንስቷል። ሜሲ በፒኤስጂ ከቀድሞው የክለቡ አጋሩ ኔይማር ጋር ይገናኛል። ሜሲ፤ ጆርጂንዮ ዋይናልደም፣ ሰርጂዮ ራሞስ እና ግብ ጠባቂው ጂያንሉጂ ዶናሩማ ተከትሎ የፒኤስጂ አራተኛው የነፃ ዝውውር ፈራሚ ይሆናል። ከፍተኛ ግምት የተሰጠው የቀኝ መስመር ተከላካዩ አክራክ ሃኪሚም ከኢንተር ሚላን የፓሪሱን ክለብ ተቀላቅሏል። ስምምነቱ በፍጥነት ከተጠናቀቀ ቅዳሜ የመጀመሪያውን የፒኤስጂ ጨዋታውን ከስትራስቡርግ ጋር ማድረግ ይችላል።
ሊዮኔል ሜሲ ለፓሪስ ሴንት ዠርሜን ለመጫወት ተስማማ ሊዮኔል ሜሲ ከባርሴሎና በድንገት መውጣቱን ተከትሎ የፈረንሳዩ ክለብ ለመቀላቀል በሁለት ዓመት ኮንትራት መስማማቱን የቢቢሲ ስፖርት አምድ ጸሐፊው ጊለም ባላግ ተናገረ። ስምምነቱን ለማጠናቀቅ ሕክምና ማጠናቀቅ ብቻ ይቀረዋል። የ34 ዓመቱ የአርጀንቲና አምበል በላሊጋ የፋይናንስ ፍትሃዊ ጨዋታ ህግ መሰረት አዲስ ውል ለመፈረም ባለመቻሉ በብቸኝነት የተጫወተብትን ባርሳን ለመልቀቅ ተገዷል። የማውሪሲዮ ፖቸቲኖው ፒኤስጂ ባለፈው የውድድር ዘመን በሊግ 1 ከሊል በመቀጠል ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። ባላግ በቢቢሲ ሬዲዮ 5 ቀጥታ ስርጭት ላይ "ሁሉም ነገር ተረጋግጧል። ሊዮኔል ሜሲ የፒኤስጂ ተጫዋች ይሆናል። ይህ ነው። ባለፉት ጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የተከሰተ ነው" ብሏል። "ሃሳቡ የእግር ኳስ ህይወቱን በባርሴሎና ማድረግ ነበር። . . . ከዚያ በኳታር የዓለም ዋንጫ ጥሩ ነገር ማድረግ ነው።" ከዘመኑ ታላላቅ ተጫዋቾች አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት ሜሲ በ 13 ዓመቱ ለተቀላቀለበት ባርሳ 778 ጨዋታዎችን አከናውኖ 672 ግቦችን በስሙ አስመዝግቧል። የባላንዶርን ሽልማት ስድስት ጊዜ በማሸነፍ ባለክብረወሰን ሲሆን ከካታላኑ ክለብ ጋር 35 ዋንጫዎችን አንስቷል። ሜሲ በፒኤስጂ ከቀድሞው የክለቡ አጋሩ ኔይማር ጋር ይገናኛል። ሜሲ፤ ጆርጂንዮ ዋይናልደም፣ ሰርጂዮ ራሞስ እና ግብ ጠባቂው ጂያንሉጂ ዶናሩማ ተከትሎ የፒኤስጂ አራተኛው የነፃ ዝውውር ፈራሚ ይሆናል። ከፍተኛ ግምት የተሰጠው የቀኝ መስመር ተከላካዩ አክራክ ሃኪሚም ከኢንተር ሚላን የፓሪሱን ክለብ ተቀላቅሏል። ስምምነቱ በፍጥነት ከተጠናቀቀ ቅዳሜ የመጀመሪያውን የፒኤስጂ ጨዋታውን ከስትራስቡርግ ጋር ማድረግ ይችላል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58161236
5sports
የኮቢ ብራያንት ባለቤት ኮቢ መሞቱን መጀመሪያ የሰማችው ከማኅበራዊ ሚዲያ እንደነበር ገለጸች
የኮቢ ብራያንት ባለቤት ቨኔሳ ብራያንት ባለቤቷ መሞቱን መጀመሪያ የሰማችው በማኅበራዊ ሚዲያ እንደነበር ገለጸች። "RIP Kobe" (ኮቢ ነፍስህ በሠላም ትረፍ) የሚል የስልክ የማኅበራዊ ሚዲያ መረጃዎች መልዕክት ጠቋሚ (ኖቲፊኬሽን) ሲደርሳት ነበር ባለቤቷ መሞቱን የተረዳችው። የቅርጫት ኳስ ኮከኩ ኮቢ እአአ ጥር 2020 በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ ከ13 ዓመቷ ሴት ልጁ ጂያና እና ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር ሕይወቱ አልፏል። ቨኔሳ ብራያንት በቸልተኝነት እና ግላዊነትን ባለመጠበቅ ምክንያት የሎስ አንጀለስ ፖሊስ መምሪያን ከሳለች። ኃላፊዎቹ የኮቢ እና የጂያናን አስከሬን ጨምሮ የአደጋውን አስከፊ ፎቶዎች አጋርተዋል ስትል ትከሳለች። ቨኔሳ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ አደጋው እንዴት እንዳወቀች ተጠይቃ ባለቤቷ እና ሴት ልጃቸው የሄሊኮፕተር አደጋ እንደደረሰባቸው ከቤተሰቡ ረዳት እንደተነገራት አስታውቃለች። ነገር ግን አምስት ሰዎች በሕይወት መትረፋቸው ስለተነገራት በሕይወት ከተረፉት መካከል ሊሆኑ እንደሚችሉ ማሰቧን ተናግራለች። ከዚያ በኋላ መልዕክቶች በስልኳ ይደርሷት ጀመር። ቨኔሳ "ስልኬን ይዤው ነበር። ምክንያቱም ለባለቤቴ ለመደወል እየሞከርኩ ነበር። RIP Kobe የሚሉ ማሳወቂያዎች ስልኬ ላይ ይጎርፉ ጀመር" ስትል ታስታውሳለች። አክላም "ያለ ባለቤቴ እና ልጄ ሕይወቴ መቼም እንደ ቀድሞው አይሆንም" ብላለች። በመጋቢት ወር ቨኔሳ የአደጋውን አስከፊ ፎቶዎችን አጋርተዋል ያለቻቸውን የሎስ አንጀለስ የፖሊስ መኮንኖችን ስም ይፋ አድርጋለች። ከፖሊስ መኮንኖች መካከል አንዱ የኮቢ ብራያንት አስከሬን ፎቶ ለመጠጥ ቤት አሳላፊ ሲያጋራ ሌሎቹ ደግሞ ሕይወታቸው ያለፈ ልጆችን፣ የወላጆችን እና የአሰልጣኞችን ፎቶዎች አሰራጭተዋል። የሎስ አንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ ባለፈው ዓመት የካቲት ወር እንደዘገበው፤ የፖሊስ የውስጥ ምርመራ እንደሚያሳየው ባለሥልጣናት የተጎጂዎችን ፎቶዎች አጋርተዋል። ቨኔሳ "ዛሬ እዚህ መጥቼ ለተጠያቂነት መታገሌ ተገቢ አይመስለኝም። ምክንያቱም ማንም ሰው እንደዚህ ዓይነቱን ስቃይ እና የቤተሰቡን ፍርሃት መታገስ የለበትም። ፎቶዎቹ መጋራታቸው ተገቢ አይደለም" ብላለች። ቨኔሳ ባለቤቷ እና ሴት ልጃቸው አደጋው ሲደርስ የለበሱትን ልብስ እንዳስቀመጠችው ተናግራለች። "አንድ ሰው እንዴት በጣም ጨካኝ ሊሆን እንደሚችል እና ለእነሱ ወይም ለጓደኞቻችን ምንም ደንታ እንደሌለው መገመት ይከብዳል። የመንገድ እንስሳት የሆኑ ይመስል ፎቶዎቻቸውን አጋርተዋል" ብላለች። ቨኔሳ በአደጋ ቦታው ማንም ፎቶ አለማንሳቱ እንዲረጋገጥ መጠየቋን የፖሊስ መኮንን አሌክስ ቪላኑዌቫን ተናግረዋል። የፖሊስ መምሪያው ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ባለው ክስ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።
የኮቢ ብራያንት ባለቤት ኮቢ መሞቱን መጀመሪያ የሰማችው ከማኅበራዊ ሚዲያ እንደነበር ገለጸች የኮቢ ብራያንት ባለቤት ቨኔሳ ብራያንት ባለቤቷ መሞቱን መጀመሪያ የሰማችው በማኅበራዊ ሚዲያ እንደነበር ገለጸች። "RIP Kobe" (ኮቢ ነፍስህ በሠላም ትረፍ) የሚል የስልክ የማኅበራዊ ሚዲያ መረጃዎች መልዕክት ጠቋሚ (ኖቲፊኬሽን) ሲደርሳት ነበር ባለቤቷ መሞቱን የተረዳችው። የቅርጫት ኳስ ኮከኩ ኮቢ እአአ ጥር 2020 በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ ከ13 ዓመቷ ሴት ልጁ ጂያና እና ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር ሕይወቱ አልፏል። ቨኔሳ ብራያንት በቸልተኝነት እና ግላዊነትን ባለመጠበቅ ምክንያት የሎስ አንጀለስ ፖሊስ መምሪያን ከሳለች። ኃላፊዎቹ የኮቢ እና የጂያናን አስከሬን ጨምሮ የአደጋውን አስከፊ ፎቶዎች አጋርተዋል ስትል ትከሳለች። ቨኔሳ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ አደጋው እንዴት እንዳወቀች ተጠይቃ ባለቤቷ እና ሴት ልጃቸው የሄሊኮፕተር አደጋ እንደደረሰባቸው ከቤተሰቡ ረዳት እንደተነገራት አስታውቃለች። ነገር ግን አምስት ሰዎች በሕይወት መትረፋቸው ስለተነገራት በሕይወት ከተረፉት መካከል ሊሆኑ እንደሚችሉ ማሰቧን ተናግራለች። ከዚያ በኋላ መልዕክቶች በስልኳ ይደርሷት ጀመር። ቨኔሳ "ስልኬን ይዤው ነበር። ምክንያቱም ለባለቤቴ ለመደወል እየሞከርኩ ነበር። RIP Kobe የሚሉ ማሳወቂያዎች ስልኬ ላይ ይጎርፉ ጀመር" ስትል ታስታውሳለች። አክላም "ያለ ባለቤቴ እና ልጄ ሕይወቴ መቼም እንደ ቀድሞው አይሆንም" ብላለች። በመጋቢት ወር ቨኔሳ የአደጋውን አስከፊ ፎቶዎችን አጋርተዋል ያለቻቸውን የሎስ አንጀለስ የፖሊስ መኮንኖችን ስም ይፋ አድርጋለች። ከፖሊስ መኮንኖች መካከል አንዱ የኮቢ ብራያንት አስከሬን ፎቶ ለመጠጥ ቤት አሳላፊ ሲያጋራ ሌሎቹ ደግሞ ሕይወታቸው ያለፈ ልጆችን፣ የወላጆችን እና የአሰልጣኞችን ፎቶዎች አሰራጭተዋል። የሎስ አንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ ባለፈው ዓመት የካቲት ወር እንደዘገበው፤ የፖሊስ የውስጥ ምርመራ እንደሚያሳየው ባለሥልጣናት የተጎጂዎችን ፎቶዎች አጋርተዋል። ቨኔሳ "ዛሬ እዚህ መጥቼ ለተጠያቂነት መታገሌ ተገቢ አይመስለኝም። ምክንያቱም ማንም ሰው እንደዚህ ዓይነቱን ስቃይ እና የቤተሰቡን ፍርሃት መታገስ የለበትም። ፎቶዎቹ መጋራታቸው ተገቢ አይደለም" ብላለች። ቨኔሳ ባለቤቷ እና ሴት ልጃቸው አደጋው ሲደርስ የለበሱትን ልብስ እንዳስቀመጠችው ተናግራለች። "አንድ ሰው እንዴት በጣም ጨካኝ ሊሆን እንደሚችል እና ለእነሱ ወይም ለጓደኞቻችን ምንም ደንታ እንደሌለው መገመት ይከብዳል። የመንገድ እንስሳት የሆኑ ይመስል ፎቶዎቻቸውን አጋርተዋል" ብላለች። ቨኔሳ በአደጋ ቦታው ማንም ፎቶ አለማንሳቱ እንዲረጋገጥ መጠየቋን የፖሊስ መኮንን አሌክስ ቪላኑዌቫን ተናግረዋል። የፖሊስ መምሪያው ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ባለው ክስ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59033821
0business
ዚምባብዌውያን በሃገሪቷ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ በመቃወም ሰልፍ አካሄዱ
በሺዎች የሚቆጠሩ ዚምባብዌውያን የአሜሪካና የአውሮፓ ህብረትን ማዕቀብ በመቃወም ሰልፍ አድርገዋል። መንግሥት ባዘጋጀው በዚህ ሰልፍ ማዕቀቡ ምን ያህል የዚምባብዌን ኢኮኖሚ እንዳሽመደመደው ተናግረዋል። በሌላ በኩል አሜሪካና የአውሮፓ ሕብረት የተጣለው ማዕቀብ በግለሰቦችና በኩባንያዎች ላይ በመሆኑ የሃገሪቷ ኢኮኖሚ ላይ ያመጣው ተፅእኖ እንደሌለ እየተናገሩ ነው። •የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? •የዋግ ኽምራ አርሶ አደሮች ለከፋ ችግር ተጋልጠናል እያሉ ነው ሰልፉን ምክንያት በማድረግም ዚምባብዌ ቀኑን ሕዝባዊ በዓል ስትል ያወጀች ሲሆን ለሰልፈኞቹም የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡም አውቶብሶች ተዘጋጅተው ነበር። በሰልፉ ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋም ለተሰበሰበው ሕዝብ ንግግር አድርገዋል። "ማዕቀቡ በያንዳንዱ ዚምባብዌውያን ላይ ያደረሰው ተፅእኖ የከፋ ነው፤ ማዕቀቡ ስህተት ነው የምንልበትም ምክንያት የሁሉንም ቤት ያንኳኳ በመሆኑ ነው" ማለታቸውን ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ንግግራቸውን ጠቅሶ ዘግቧል። •ኬንያዊው የፀረ ቅኝ ግዛት ነፃነት ታጋይ መካነ መቃብር ከ62 ዓመታት በኋላ ተገኘ •ማንዴላን ውትድርና ያሰለጠኑት ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚዎች "ማዕቀቡ መነሳት አለበት" የሚል ፅሁፍ ያለባቸውን ቲሸርቶች እንዲሁም "ማዕቀቡ በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል ነው" የሚል መፈክር ይዘው ነበር። የተለያዩ ቢዝነስ ባለቤቶችም ለቢቢሲ እንደተናገሩት ማዕቀቡ "ጠባሳን የተወ" ነው ብለውታል፤ ለዚህም እንደ ምክንያት የሚያነሱት ባንኮች ተመጣጣኝ በሆነ ወለድ ማበደር በማቆማቸው ሥራቸውን ቀጥ እንዳደረገው ይናገራሉ። በሰልፉ ላይ የነበሩ ተናጋሪዎችም ዚምባብዌ እያጋጠማት ያለው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መቆራረጥና የውሃ እጥረትም በማዕቀቡ ነው ብለዋል። ተችዎች በበኩላቸው ሃገሪቱ የገባችበትን የኢኮኖሚ አዘቅት እንዲሁም ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ያለውን ግሽበት በነዋሪው ላይ የፈጠረውን ንዴት አቅጣጫ ማስቀየሪያ ነው ይላሉ። የቢቢሲ ዘጋቢዎች እንደታዘቡትም የተጠበቀውን ያህል ሰልፈኞች አልመጡም ብለዋል፤ ስታዲየሙ 60ሺህ ሰዎችን የመያዝ አቅም ቢኖረውም የተገኘው ከ15ሺህ እስከ 20ሺህ የሚገመት ነው ተብሏል። •"ሌቱም አይነጋልኝ" የተባለላት የውቤ በረሃ ትዝታዎች የተቃዋሚ መሪ ኔልሰን ቻሚሳ በበኩላቸው ሰልፉ በሃገሪቱ ላይ የመሪዎችን ውድቀት ለመሸፈን የተደረገ ፕሮፓጋንዳ ነው ብለውታል። በዚምባብዌ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በበኩሉ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ መሽመድመድ "ደካማ ከሆኑ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች" ጋር የተያያዘ ነው በሚል በትዊተር ገፁ አስፍሯል። አሜሪካ ከገንዘብ ዝውውርና አለም አቀፍ ጉዞዎች ጋር በተገናኘ 85 ኃላፊዎች ላይ እንዲሁም 56 ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ ጥላለች። የሃገሪቱ ፕሬዚዳንትም ማዕቀብ ከተጣለባቸው መካከል ናቸው። •አቶ ታደሰ ካሳ፡ "…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው" ከዚህም በተጨማሪ የአሜሪካ ማዕቀብ ዚምባብዌ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ግዥ እንዳታደርግ የሚገድብም ነው። የአውሮፓ ህብረት ማዕቀብም በዚምባብዌ የመንግሥት ኃላፊዎችን እንቅስቃሴ መገደብ፣ የገንዘብ እንዲሁም የጦር መሳሪያ ዝውውርና ማገድን ያካትታል። ማዕቀቡ የተጣለው ከሃያ አመታት በፊት ሲሆን በዚህ አመትም የአሜሪካ መንግሥት ባለፈው አመት ከነበረው ተቃውሞ ጋር ተያይዞ በሞቱ ሰዎች ላይ እጃቸው አለበት ያላቸውንም ሰዎች በማዕቀብ ዝርዝሩ አካቷቸዋል።
ዚምባብዌውያን በሃገሪቷ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ በመቃወም ሰልፍ አካሄዱ በሺዎች የሚቆጠሩ ዚምባብዌውያን የአሜሪካና የአውሮፓ ህብረትን ማዕቀብ በመቃወም ሰልፍ አድርገዋል። መንግሥት ባዘጋጀው በዚህ ሰልፍ ማዕቀቡ ምን ያህል የዚምባብዌን ኢኮኖሚ እንዳሽመደመደው ተናግረዋል። በሌላ በኩል አሜሪካና የአውሮፓ ሕብረት የተጣለው ማዕቀብ በግለሰቦችና በኩባንያዎች ላይ በመሆኑ የሃገሪቷ ኢኮኖሚ ላይ ያመጣው ተፅእኖ እንደሌለ እየተናገሩ ነው። •የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? •የዋግ ኽምራ አርሶ አደሮች ለከፋ ችግር ተጋልጠናል እያሉ ነው ሰልፉን ምክንያት በማድረግም ዚምባብዌ ቀኑን ሕዝባዊ በዓል ስትል ያወጀች ሲሆን ለሰልፈኞቹም የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡም አውቶብሶች ተዘጋጅተው ነበር። በሰልፉ ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋም ለተሰበሰበው ሕዝብ ንግግር አድርገዋል። "ማዕቀቡ በያንዳንዱ ዚምባብዌውያን ላይ ያደረሰው ተፅእኖ የከፋ ነው፤ ማዕቀቡ ስህተት ነው የምንልበትም ምክንያት የሁሉንም ቤት ያንኳኳ በመሆኑ ነው" ማለታቸውን ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ንግግራቸውን ጠቅሶ ዘግቧል። •ኬንያዊው የፀረ ቅኝ ግዛት ነፃነት ታጋይ መካነ መቃብር ከ62 ዓመታት በኋላ ተገኘ •ማንዴላን ውትድርና ያሰለጠኑት ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚዎች "ማዕቀቡ መነሳት አለበት" የሚል ፅሁፍ ያለባቸውን ቲሸርቶች እንዲሁም "ማዕቀቡ በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል ነው" የሚል መፈክር ይዘው ነበር። የተለያዩ ቢዝነስ ባለቤቶችም ለቢቢሲ እንደተናገሩት ማዕቀቡ "ጠባሳን የተወ" ነው ብለውታል፤ ለዚህም እንደ ምክንያት የሚያነሱት ባንኮች ተመጣጣኝ በሆነ ወለድ ማበደር በማቆማቸው ሥራቸውን ቀጥ እንዳደረገው ይናገራሉ። በሰልፉ ላይ የነበሩ ተናጋሪዎችም ዚምባብዌ እያጋጠማት ያለው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መቆራረጥና የውሃ እጥረትም በማዕቀቡ ነው ብለዋል። ተችዎች በበኩላቸው ሃገሪቱ የገባችበትን የኢኮኖሚ አዘቅት እንዲሁም ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ያለውን ግሽበት በነዋሪው ላይ የፈጠረውን ንዴት አቅጣጫ ማስቀየሪያ ነው ይላሉ። የቢቢሲ ዘጋቢዎች እንደታዘቡትም የተጠበቀውን ያህል ሰልፈኞች አልመጡም ብለዋል፤ ስታዲየሙ 60ሺህ ሰዎችን የመያዝ አቅም ቢኖረውም የተገኘው ከ15ሺህ እስከ 20ሺህ የሚገመት ነው ተብሏል። •"ሌቱም አይነጋልኝ" የተባለላት የውቤ በረሃ ትዝታዎች የተቃዋሚ መሪ ኔልሰን ቻሚሳ በበኩላቸው ሰልፉ በሃገሪቱ ላይ የመሪዎችን ውድቀት ለመሸፈን የተደረገ ፕሮፓጋንዳ ነው ብለውታል። በዚምባብዌ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በበኩሉ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ መሽመድመድ "ደካማ ከሆኑ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች" ጋር የተያያዘ ነው በሚል በትዊተር ገፁ አስፍሯል። አሜሪካ ከገንዘብ ዝውውርና አለም አቀፍ ጉዞዎች ጋር በተገናኘ 85 ኃላፊዎች ላይ እንዲሁም 56 ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ ጥላለች። የሃገሪቱ ፕሬዚዳንትም ማዕቀብ ከተጣለባቸው መካከል ናቸው። •አቶ ታደሰ ካሳ፡ "…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው" ከዚህም በተጨማሪ የአሜሪካ ማዕቀብ ዚምባብዌ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ግዥ እንዳታደርግ የሚገድብም ነው። የአውሮፓ ህብረት ማዕቀብም በዚምባብዌ የመንግሥት ኃላፊዎችን እንቅስቃሴ መገደብ፣ የገንዘብ እንዲሁም የጦር መሳሪያ ዝውውርና ማገድን ያካትታል። ማዕቀቡ የተጣለው ከሃያ አመታት በፊት ሲሆን በዚህ አመትም የአሜሪካ መንግሥት ባለፈው አመት ከነበረው ተቃውሞ ጋር ተያይዞ በሞቱ ሰዎች ላይ እጃቸው አለበት ያላቸውንም ሰዎች በማዕቀብ ዝርዝሩ አካቷቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-50192157
2health
በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት መቀነሱ ተገለጸ
በኢትዮጵያ በየዓመቱ በኤችአይቪ ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነሱ ተገለጸ። በፌደራል ኤችአይቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግነኙነት እና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዳንኤል በስረ በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት መቀነሱን ጥናቶች ያመላክታሉ ብለዋል። በአገር አቀፍ ደረጃ አጠቃላይ የቫይረሱ የስርጭት ምጣኔ 0.86 በመቶ መሆኑን አቶ ዳንኤል ያስረዳሉ። "ይሄ ማለት በመላው አገሪቱ፤ በሁሉም ማሕበረሰብ ክፍል ተመሳሳይ ነው ማለት አይደለም። በገጠር እና በከተማ የስርጭት ምጣኔው የተለያየ ነው" የሚሉት ዳንኤል፤ በጋምቤላ ክልል እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስርጭት ምጣኔው ከፍተኛ መሆኑን ይናገራሉ። ዳንኤል የቫይረሱ ስርጭት በጋምቤላ 4.1 በመቶ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከ3 በመቶ በላይ መሆኑን ያስረዳሉ። 3 በመቶ ምጣኔ ምን ማለት እንደሆን ሲያስረዱ፤ በቀላል ቋንቋ ከመቶ ሰዎች ሦስት ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው አለ ማለት ነው ይላሉ። በሶማሌ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ በታች መሆኑን ይናገራሉ። የሶማሌ ክልል 0.01 በመቶ አነስተኛ የቫይረሱ ስርጭት የሚገኘበት ክልል መሆኑን ይናገራሉ። በአገሪቱ ክልሎች መካከል ከፍተኛ የሆነ የቫይረሱ ስርጭት ልዩነት እንዴት ሊፈጠረ ቻለ? ተብለው የተጠየቁት አቶ ዳንኤል፤ ለዚህ ጥያቄ ቁርጥ ያለ ምላሽ ለመስጠት በዝርዝር ጥናት ላይ መመርኮዝ እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የተሰራ ሥራ ልዩነት ፈጥሮ ሳይሆን ዋናው ምክንያት ከባህል እና ሃይማኖታዊ ጉዳይ ጋር ሊያያዝ ይችላል ይላሉ። አቶ ዳንኤል ከዓመታት በፊት በኢትዮጵያ አጠቃላይ የቫይረሱ ስርጭት ምጣኔ ከ6 በመቶ በላይ ደርሶ የሚያውቅበት አጋጣሚ እንዳለ ይናገራሉ። በከተሞች አካባቢ ደግሞ የስርጭት ምጣኔው እስከ 10 በመቶ ስለመድረሱ ተመዝግቦ ነበር ይላሉ። "በአንድ አገር አጠቃላይ የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫይረሱ ስርጭት ወረርሽኝ ነው የሚባለው" የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ ምንም እንኳ በአገር ደረጃ የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ በታች ቢሆንም የስርጭት መጠኑ ከ1 በመቶ በላይ የሆነባቸው ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች መኖራቸውን ይናገራሉ። የቫይረሱ ስርጭት በጾታ ተከፍሎ ሲታይ ደግሞ፤ ሴቶች ከወንዶች በላይ ተጋላጭ መሆናቸውን ይናገራሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሽታውን በመከላከል ረገድ የሚሰሩ ሥራዎች መቀነሳቸውን ዳንኤል አስረድተዋል። መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ቀደም ሲል ሲሰሩ በነበሩበት ልክ ቫይረሱን የመከላከል ሥራ እየሰሩ አይደለም ይላሉ። ለዚህም ምክንያቱ የስርጭቱ መጠን በየዓመቱ መቀነስ በማሳየቱ እና በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከመከላከሉ ይልቅ ሕክምናው ላይ ትኩረት በመሰጠቱ ነው ይላሉ። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች በአሁኑ ወቅት ከ622 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ይገኛል። ከእነዚህ መካከል ወደ 500 ሺህ የሚሆኑ ጸረ-ኤችአይቪ መድሃኒት እየወሰዱ እንደሚገኙ ጥናቶች ያሳያሉ ብለዋል ዳንኤል። በየዓመቱ ከ11 ሺህ በላይ አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች አሉ። "ይህን የከፋ የሚያደርገው ከእነዚህ ውስጥ 67 በመቶ ድርሻ የሚይዙት እድሜያቸው ከ30 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች መሆናቸው ነው" ይላሉ ዳንኤል። የቫይረሱን ስርጭት መከላከል አስፈላጊነትን ከሚያረጋግጡት መካከል አንዱ በበሽታው የሚያዙት አብዛኛዎቹ ወጣቶች መሆናቸው ነው ይላሉ። "አምራች ኃይል ነው። እንደ ሀገር ተስፋ የሚጣልበት ነው። በዚህ እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች ላይ የስርጭት ምጣኔው ከፍ ብሎ መታየቱ እንደ አገር አደጋ ውስጥ እንዳለን የሚያሳይ ነው" ብለዋል። ዳንኤል፤ ሴተኛ አዳሪዎች፣ ባሎቻቸውን በሞት ያጡ እና ትዳራቸውን የፈቱ ሴቶች ዘንድ የቫይረሱ ስርጭት መጠን ከፍተኛ ነው ይላሉ። "በሴተኛ አዳሪዎች የስርጭት ምጣኔው 18 በመቶ ነው። ባሎቻቸውን በሞት ያጡ እና ትዳራቸውን የፈቱ ሴቶች አካባቢ የስርጭት ምጣኔው ወደ 20 በመቶ ሆኖ እናያለን" ይላሉ። ሕይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ከ12 ሺህ ባለይ ሰዎች ደግሞ በየዓመቱ በኤድስ እና ተያያዥ በሽታዎች ሕይወታቸው እያለፈ ነው። በአገሪቱ ቫይረሱ በደማቸው ይገኘባቸዋል ከተባለው ከ622 ሺህ ባለይ ሰዎች 61 በመቶውን የሚይዙት ሴቶች ናቸው ይላሉ። በአሁኑ ሰዓት የስርጭት ምጣኔው ከ1 በታች መሆኑ የስርጭት መጠኑ አነስተኛ እንደሆነ ነው የሚያሳየን የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ የስርጭት መጠኑ ግን ሊያዘናጋን አይገባም ይላሉ። "መዘናጋቱ እና ቸልተኝነቱ በዚህ መንግድ የሚቀጥል ከሆነ፤ እንደ አገር ያልተገባ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል" የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ የልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የድርሻቸውን መወጣት አለባቸው ይላሉ። ኮቪድ እና ኤችአይቪ የኮሮናቫይረስ መከሰት ኤችአይቪ በደማቸው በሚገኝባቸው እና መድሃኒት በሚወስዱ ሰዎች ላይ ተጽእኖ ፈጥሯል ይላሉ። "ትልቁ ችግር የነበረው ስነ-ልቦናዊ ተጽእኖ ነው" የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ ኮቪድ-19 ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸውን ሰዎችን ይጎዳል በሚል በስጋት ወደ ጤና ተቋም ያለመምጣት ሁኔታዎች እንደነበሩ ይናገራሉ። ከዚህ በተጨማሪም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በማሰብ በመንግሥት የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን ተከትሎ ከሚኖሩበት ርቀው መድሃኒት ይወስዱ የነበሩ ሰዎች የትራንስፖርት አማራጭ ባለማግኘት መድሃኒታቸውን መውሰድ የማይችሉት ሁኔታ ነበር። "ለምሳሌ አዲስ አበባ ላይ ያለ ሰው አዳማ ሄዶ የሚወስድ ከሆነ . . . መንቀሳቀሱ ሲቆም መድሃኒቱን በትክክል ለመወሰድ መቸገር ነበር" ብለዋል።
በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት መቀነሱ ተገለጸ በኢትዮጵያ በየዓመቱ በኤችአይቪ ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነሱ ተገለጸ። በፌደራል ኤችአይቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግነኙነት እና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዳንኤል በስረ በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት መቀነሱን ጥናቶች ያመላክታሉ ብለዋል። በአገር አቀፍ ደረጃ አጠቃላይ የቫይረሱ የስርጭት ምጣኔ 0.86 በመቶ መሆኑን አቶ ዳንኤል ያስረዳሉ። "ይሄ ማለት በመላው አገሪቱ፤ በሁሉም ማሕበረሰብ ክፍል ተመሳሳይ ነው ማለት አይደለም። በገጠር እና በከተማ የስርጭት ምጣኔው የተለያየ ነው" የሚሉት ዳንኤል፤ በጋምቤላ ክልል እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስርጭት ምጣኔው ከፍተኛ መሆኑን ይናገራሉ። ዳንኤል የቫይረሱ ስርጭት በጋምቤላ 4.1 በመቶ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከ3 በመቶ በላይ መሆኑን ያስረዳሉ። 3 በመቶ ምጣኔ ምን ማለት እንደሆን ሲያስረዱ፤ በቀላል ቋንቋ ከመቶ ሰዎች ሦስት ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው አለ ማለት ነው ይላሉ። በሶማሌ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ በታች መሆኑን ይናገራሉ። የሶማሌ ክልል 0.01 በመቶ አነስተኛ የቫይረሱ ስርጭት የሚገኘበት ክልል መሆኑን ይናገራሉ። በአገሪቱ ክልሎች መካከል ከፍተኛ የሆነ የቫይረሱ ስርጭት ልዩነት እንዴት ሊፈጠረ ቻለ? ተብለው የተጠየቁት አቶ ዳንኤል፤ ለዚህ ጥያቄ ቁርጥ ያለ ምላሽ ለመስጠት በዝርዝር ጥናት ላይ መመርኮዝ እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የተሰራ ሥራ ልዩነት ፈጥሮ ሳይሆን ዋናው ምክንያት ከባህል እና ሃይማኖታዊ ጉዳይ ጋር ሊያያዝ ይችላል ይላሉ። አቶ ዳንኤል ከዓመታት በፊት በኢትዮጵያ አጠቃላይ የቫይረሱ ስርጭት ምጣኔ ከ6 በመቶ በላይ ደርሶ የሚያውቅበት አጋጣሚ እንዳለ ይናገራሉ። በከተሞች አካባቢ ደግሞ የስርጭት ምጣኔው እስከ 10 በመቶ ስለመድረሱ ተመዝግቦ ነበር ይላሉ። "በአንድ አገር አጠቃላይ የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫይረሱ ስርጭት ወረርሽኝ ነው የሚባለው" የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ ምንም እንኳ በአገር ደረጃ የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ በታች ቢሆንም የስርጭት መጠኑ ከ1 በመቶ በላይ የሆነባቸው ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች መኖራቸውን ይናገራሉ። የቫይረሱ ስርጭት በጾታ ተከፍሎ ሲታይ ደግሞ፤ ሴቶች ከወንዶች በላይ ተጋላጭ መሆናቸውን ይናገራሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሽታውን በመከላከል ረገድ የሚሰሩ ሥራዎች መቀነሳቸውን ዳንኤል አስረድተዋል። መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ቀደም ሲል ሲሰሩ በነበሩበት ልክ ቫይረሱን የመከላከል ሥራ እየሰሩ አይደለም ይላሉ። ለዚህም ምክንያቱ የስርጭቱ መጠን በየዓመቱ መቀነስ በማሳየቱ እና በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከመከላከሉ ይልቅ ሕክምናው ላይ ትኩረት በመሰጠቱ ነው ይላሉ። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች በአሁኑ ወቅት ከ622 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ይገኛል። ከእነዚህ መካከል ወደ 500 ሺህ የሚሆኑ ጸረ-ኤችአይቪ መድሃኒት እየወሰዱ እንደሚገኙ ጥናቶች ያሳያሉ ብለዋል ዳንኤል። በየዓመቱ ከ11 ሺህ በላይ አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች አሉ። "ይህን የከፋ የሚያደርገው ከእነዚህ ውስጥ 67 በመቶ ድርሻ የሚይዙት እድሜያቸው ከ30 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች መሆናቸው ነው" ይላሉ ዳንኤል። የቫይረሱን ስርጭት መከላከል አስፈላጊነትን ከሚያረጋግጡት መካከል አንዱ በበሽታው የሚያዙት አብዛኛዎቹ ወጣቶች መሆናቸው ነው ይላሉ። "አምራች ኃይል ነው። እንደ ሀገር ተስፋ የሚጣልበት ነው። በዚህ እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች ላይ የስርጭት ምጣኔው ከፍ ብሎ መታየቱ እንደ አገር አደጋ ውስጥ እንዳለን የሚያሳይ ነው" ብለዋል። ዳንኤል፤ ሴተኛ አዳሪዎች፣ ባሎቻቸውን በሞት ያጡ እና ትዳራቸውን የፈቱ ሴቶች ዘንድ የቫይረሱ ስርጭት መጠን ከፍተኛ ነው ይላሉ። "በሴተኛ አዳሪዎች የስርጭት ምጣኔው 18 በመቶ ነው። ባሎቻቸውን በሞት ያጡ እና ትዳራቸውን የፈቱ ሴቶች አካባቢ የስርጭት ምጣኔው ወደ 20 በመቶ ሆኖ እናያለን" ይላሉ። ሕይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ከ12 ሺህ ባለይ ሰዎች ደግሞ በየዓመቱ በኤድስ እና ተያያዥ በሽታዎች ሕይወታቸው እያለፈ ነው። በአገሪቱ ቫይረሱ በደማቸው ይገኘባቸዋል ከተባለው ከ622 ሺህ ባለይ ሰዎች 61 በመቶውን የሚይዙት ሴቶች ናቸው ይላሉ። በአሁኑ ሰዓት የስርጭት ምጣኔው ከ1 በታች መሆኑ የስርጭት መጠኑ አነስተኛ እንደሆነ ነው የሚያሳየን የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ የስርጭት መጠኑ ግን ሊያዘናጋን አይገባም ይላሉ። "መዘናጋቱ እና ቸልተኝነቱ በዚህ መንግድ የሚቀጥል ከሆነ፤ እንደ አገር ያልተገባ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል" የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ የልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የድርሻቸውን መወጣት አለባቸው ይላሉ። ኮቪድ እና ኤችአይቪ የኮሮናቫይረስ መከሰት ኤችአይቪ በደማቸው በሚገኝባቸው እና መድሃኒት በሚወስዱ ሰዎች ላይ ተጽእኖ ፈጥሯል ይላሉ። "ትልቁ ችግር የነበረው ስነ-ልቦናዊ ተጽእኖ ነው" የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ ኮቪድ-19 ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸውን ሰዎችን ይጎዳል በሚል በስጋት ወደ ጤና ተቋም ያለመምጣት ሁኔታዎች እንደነበሩ ይናገራሉ። ከዚህ በተጨማሪም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በማሰብ በመንግሥት የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን ተከትሎ ከሚኖሩበት ርቀው መድሃኒት ይወስዱ የነበሩ ሰዎች የትራንስፖርት አማራጭ ባለማግኘት መድሃኒታቸውን መውሰድ የማይችሉት ሁኔታ ነበር። "ለምሳሌ አዲስ አበባ ላይ ያለ ሰው አዳማ ሄዶ የሚወስድ ከሆነ . . . መንቀሳቀሱ ሲቆም መድሃኒቱን በትክክል ለመወሰድ መቸገር ነበር" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59515396
0business
የዶናልድ ትራምፕ ሀብት በአያሌው አሽቆለቆለ
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀብታቸው በ700 ሚሊዮን ዶላር ቀንሶባቸዋል ሲል ብሉምበርግ ዘገበ። አስገራሚው ነገር ሀብታቸው ያሽቆለቆለው ፕሬዝዳንት በሆኑባቸው ዘመናት መሆኑ ነው። አሁን የሰውየው ድምር ሀብት 2.3 ቢሊዮን ብቻ ነው። ለትራምፕ ሀብት መቀነስ ዋና ምክንያት ተደርጎ የተወሰደው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሲሆን የትራምፕ እውቅ ሆቴሎች፣ ጎልፍ ክለቦችና መዝናኛ ማዕከላቱ በደንበኞች ድርቅ መመታታቸው 700 ሚሊዮን ዶላር አሳጥቷቸዋል። ዶናልድ ትራምፕ አሁን ከቤተሰብ ቢዝነስና ከግብር ክፍያ ጋር በተያያዘ የወንጀል ምርመራ ፋይል ተከፍቶባቸዋል። ብሉምበርግ የሰውየውን ወጪና ገቢ ከግንቦት 2016 ጀምሮ እስከ ጥር 2021 ድረስ ሲያሰላው ቆይቷል። ፕሬዝዳንቱ ነጩ ቤተ መንግሥት ከመግባታቸው በፊትና በኋላ የሀብታቸውን ከፍና ዝቅ አስልቶታል። ትራምፕ የሀብታቸው ሦስት እጅ የሚይዘው የሪልስቴት ልማት ነው። ለቢሮ የሚውሉት የትራምፕ ፎቆች ገቢያቸው በከፍተኛ ሁኔታ ያሽቆለቆለ ሲሆን ይህም በወረርሽኙ ምክንያት ሰዎች ከቤታቸው መሥራት በመጀመራቸው የቢሮ አስፈላጊነት እየቀነሰ በመምጣቱ ነው። የገንዘብና ሀብት ሰነዶችን በማውጣት የሚታወቀው ብሉምበርግ እንደሚለው የዶናልድ ትራምፕን ስምና የንግድ ምልክታቸውን በመሸጥ የሚተዳደሩና በቀጥታ በራሳቸው ሥር የተቋቋሙ 19 ጎልፍ መጫወጫ ሜዳዎች አሏቸው። ከዚህ ሌላ 12 የሚሆኑ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ይገኛሉ። ምንም እንኳ ጎልፍ ተራርቆ በመቆም የሚጫወቱት ስፖርት በመሆኑ በወረርሽኑ ጊዜ ተመራጭ ስፖርት ሆኖ ቢቀጥልም የዶናልድ ትራምፕ በስኮትላንድ የነበሯቸው ሁለት ዕውቅ የጎልፍ ሜዳዎች ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶባቸዋል። በተለይም ነውጠኛ ደጋፊዎቻቸው ባለፈው ጥር ካፒቶል ሒልን መውረራቸውን ተከትሎ የአሜሪካ ፕሮፌሽናል ጎልፍ ተጫዋቾች ማኅበር በ2022 በኒው ጀርሲ በትራምፕ የጎልፍ ሜዳ ሊያዘጋጀው የነበረውን የጎልፍ ውድድር በመሰረዙ ትራምፕ ዳጎስ ያለ ትርፍ አምልጧቸዋል። ትራምፕ በ1990ዎቹ የቢዝነስ ክስረት በገጠማቸው ጊዜ ሊያበድራቸው ፈቅዶ የነበረው አጋራቸው ዶቼ ባንክም ከዚህ የካፒቶል ሒል ክስተት በኋላ "ከእርስዎ ጋር ለመሥራት ይከብደኛል" በሚል ጥሏቸው ሄዷል። ትራምፕ ከጎልፍ ሜዳዎችና ሆቴሎች እንዲሁም ሰማይ ጠቀስ የቢሮ ፎቆች በተጨማሪ በርከት ያሉ መለስተኛ አውሮፕላኖች አሏቸው። ከእነዚህ መካከል ቦይንግ 757 አውሮፕላኖች ይገኙበታል። ብሉምበርግ እንደሚለው አብዛኞቹ የትራምፕ አውሮፕላኖች አሁን እያረጁ በመሆናቸው ገበያቸው ተቀዛቅዟል። ከትራምፕ አውሮፕላኖች ውስጥ 7 የሚሆኑት በ2015 ግምታቸው 60 ሚሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን በ2020 ደግሞ 5 ሌሎች አውሮፕላኖች ግምታቸው 6 ሚሊዮን ብቻ ሆኗል። ይህም ከአውሮፕላኖቹ ዕድሜ ጋር የተያያዘ ነው። ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ሁሉ ሀብት ውስጥ የፋይናንስ ሰነዶቻቸው ጥርጣሬን የሚጭሩ በመሆናቸው ለምርመራ ተጋልጠዋል። ትራምፕ ምን ያህል ግብር እንደሚከፍሉ ለመግለጽ ሲተናነቃቸው ቆይቷል። ባለፈው ወር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዶናልድ ትራምፕን የግብር ሰነዶቻቸውን ለዐቃቢ ሕግ ይፋ እንዲያደርጉ አዟቸዋል። ይህ ምርመራ የተጀመረው በ2018 ቢሆነም እስከዛሬም አልተቋጨም። ብዙ የሚዲያ መረጃዎች ትራምፕ የግብር ማጭበርበርና የግብር ስወራ እንደፈጸሙ የሚጠቁሙ ናቸው። ትራምፕ ፕሬዝዳንት ሳሉ ያመለጣቸውን ትርፍ አሁን ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ ከቲቪና ከመጽሐፍ ስምምነቶች በሚያገኙት ገንዘብ ያካክሱታል ተብሎ ይገመታል፡። ባራክ ኦባማን ሚሼል ኦባማ ከአሳታሚዎች ጋር ባደረጉት ስምምነት በድምሩ 65 ሚሊዮን ዶላር ተከፍሏቸዋል። ቢል ክሊንተን በ2014 ለሚጽፉት መጽሐፍ 15 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ተከፍሏቸው ነበር። ትራምፕ የሚጽፉት መጽሐፍ አንባቢዎችን ይማርካል ተብሎ አይጠበቅም። የሰውየው ግንዛቤም ጥልቀት ይጎድለዋል ስለሚባል ትራምፕ ከመጽሐፍ የባራክ ኦባማን ያህል ትርፍ ያገኛሉ አይባልም። ሆኖም 74 ሚሊዮን የሚገመቱ ተከታዮቻቸውን ሊማርክ የሚችል ትዕይነት በቴሌቪዥንና በማኅበራዊ የትስስር መድረክ በማቅረብ ዳጎስ ያለ ትርፍ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የዶናልድ ትራምፕ ሀብት በአያሌው አሽቆለቆለ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀብታቸው በ700 ሚሊዮን ዶላር ቀንሶባቸዋል ሲል ብሉምበርግ ዘገበ። አስገራሚው ነገር ሀብታቸው ያሽቆለቆለው ፕሬዝዳንት በሆኑባቸው ዘመናት መሆኑ ነው። አሁን የሰውየው ድምር ሀብት 2.3 ቢሊዮን ብቻ ነው። ለትራምፕ ሀብት መቀነስ ዋና ምክንያት ተደርጎ የተወሰደው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሲሆን የትራምፕ እውቅ ሆቴሎች፣ ጎልፍ ክለቦችና መዝናኛ ማዕከላቱ በደንበኞች ድርቅ መመታታቸው 700 ሚሊዮን ዶላር አሳጥቷቸዋል። ዶናልድ ትራምፕ አሁን ከቤተሰብ ቢዝነስና ከግብር ክፍያ ጋር በተያያዘ የወንጀል ምርመራ ፋይል ተከፍቶባቸዋል። ብሉምበርግ የሰውየውን ወጪና ገቢ ከግንቦት 2016 ጀምሮ እስከ ጥር 2021 ድረስ ሲያሰላው ቆይቷል። ፕሬዝዳንቱ ነጩ ቤተ መንግሥት ከመግባታቸው በፊትና በኋላ የሀብታቸውን ከፍና ዝቅ አስልቶታል። ትራምፕ የሀብታቸው ሦስት እጅ የሚይዘው የሪልስቴት ልማት ነው። ለቢሮ የሚውሉት የትራምፕ ፎቆች ገቢያቸው በከፍተኛ ሁኔታ ያሽቆለቆለ ሲሆን ይህም በወረርሽኙ ምክንያት ሰዎች ከቤታቸው መሥራት በመጀመራቸው የቢሮ አስፈላጊነት እየቀነሰ በመምጣቱ ነው። የገንዘብና ሀብት ሰነዶችን በማውጣት የሚታወቀው ብሉምበርግ እንደሚለው የዶናልድ ትራምፕን ስምና የንግድ ምልክታቸውን በመሸጥ የሚተዳደሩና በቀጥታ በራሳቸው ሥር የተቋቋሙ 19 ጎልፍ መጫወጫ ሜዳዎች አሏቸው። ከዚህ ሌላ 12 የሚሆኑ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ይገኛሉ። ምንም እንኳ ጎልፍ ተራርቆ በመቆም የሚጫወቱት ስፖርት በመሆኑ በወረርሽኑ ጊዜ ተመራጭ ስፖርት ሆኖ ቢቀጥልም የዶናልድ ትራምፕ በስኮትላንድ የነበሯቸው ሁለት ዕውቅ የጎልፍ ሜዳዎች ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶባቸዋል። በተለይም ነውጠኛ ደጋፊዎቻቸው ባለፈው ጥር ካፒቶል ሒልን መውረራቸውን ተከትሎ የአሜሪካ ፕሮፌሽናል ጎልፍ ተጫዋቾች ማኅበር በ2022 በኒው ጀርሲ በትራምፕ የጎልፍ ሜዳ ሊያዘጋጀው የነበረውን የጎልፍ ውድድር በመሰረዙ ትራምፕ ዳጎስ ያለ ትርፍ አምልጧቸዋል። ትራምፕ በ1990ዎቹ የቢዝነስ ክስረት በገጠማቸው ጊዜ ሊያበድራቸው ፈቅዶ የነበረው አጋራቸው ዶቼ ባንክም ከዚህ የካፒቶል ሒል ክስተት በኋላ "ከእርስዎ ጋር ለመሥራት ይከብደኛል" በሚል ጥሏቸው ሄዷል። ትራምፕ ከጎልፍ ሜዳዎችና ሆቴሎች እንዲሁም ሰማይ ጠቀስ የቢሮ ፎቆች በተጨማሪ በርከት ያሉ መለስተኛ አውሮፕላኖች አሏቸው። ከእነዚህ መካከል ቦይንግ 757 አውሮፕላኖች ይገኙበታል። ብሉምበርግ እንደሚለው አብዛኞቹ የትራምፕ አውሮፕላኖች አሁን እያረጁ በመሆናቸው ገበያቸው ተቀዛቅዟል። ከትራምፕ አውሮፕላኖች ውስጥ 7 የሚሆኑት በ2015 ግምታቸው 60 ሚሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን በ2020 ደግሞ 5 ሌሎች አውሮፕላኖች ግምታቸው 6 ሚሊዮን ብቻ ሆኗል። ይህም ከአውሮፕላኖቹ ዕድሜ ጋር የተያያዘ ነው። ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ሁሉ ሀብት ውስጥ የፋይናንስ ሰነዶቻቸው ጥርጣሬን የሚጭሩ በመሆናቸው ለምርመራ ተጋልጠዋል። ትራምፕ ምን ያህል ግብር እንደሚከፍሉ ለመግለጽ ሲተናነቃቸው ቆይቷል። ባለፈው ወር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዶናልድ ትራምፕን የግብር ሰነዶቻቸውን ለዐቃቢ ሕግ ይፋ እንዲያደርጉ አዟቸዋል። ይህ ምርመራ የተጀመረው በ2018 ቢሆነም እስከዛሬም አልተቋጨም። ብዙ የሚዲያ መረጃዎች ትራምፕ የግብር ማጭበርበርና የግብር ስወራ እንደፈጸሙ የሚጠቁሙ ናቸው። ትራምፕ ፕሬዝዳንት ሳሉ ያመለጣቸውን ትርፍ አሁን ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ ከቲቪና ከመጽሐፍ ስምምነቶች በሚያገኙት ገንዘብ ያካክሱታል ተብሎ ይገመታል፡። ባራክ ኦባማን ሚሼል ኦባማ ከአሳታሚዎች ጋር ባደረጉት ስምምነት በድምሩ 65 ሚሊዮን ዶላር ተከፍሏቸዋል። ቢል ክሊንተን በ2014 ለሚጽፉት መጽሐፍ 15 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ተከፍሏቸው ነበር። ትራምፕ የሚጽፉት መጽሐፍ አንባቢዎችን ይማርካል ተብሎ አይጠበቅም። የሰውየው ግንዛቤም ጥልቀት ይጎድለዋል ስለሚባል ትራምፕ ከመጽሐፍ የባራክ ኦባማን ያህል ትርፍ ያገኛሉ አይባልም። ሆኖም 74 ሚሊዮን የሚገመቱ ተከታዮቻቸውን ሊማርክ የሚችል ትዕይነት በቴሌቪዥንና በማኅበራዊ የትስስር መድረክ በማቅረብ ዳጎስ ያለ ትርፍ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56441600
3politics
የአሜሪካ ምክር ቤት፡ ደጋፊዎቻቸው የአገሪቱ ምክር ቤትን ከወረሩ በኋላ ትራምፕ ከትዊተርና ከፌስቡክ ታገዱ
ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዋነኛዎቹ የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር ገጾች እንዲታገዱ ሆነዋል። ይህ እርምጃ የተወሰደባቸው ደጋፊዎቻቸው የካፒቶል ሂል ግቢን መውረራቸውና አደጋ ማድረሳቸውን ተከትሎ ነው። ዓለምን ባስገረመውና በአሜሪካ ምድር ይሆናል ተብሎ ባልተጠበቀ ነውጥ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የታችኛውና የላይኛው ምክር ቤት መሰብሰቢያ የሚገኝበትንና የመንግሥት መቀመጫ የሆነውን ካፒቶል ሒልን ጥሰው በመግባት አደጋ ያደረሱት ከሰዓታት በፊት ነው። ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎቻቸውን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ጠንካራ መልእክት ያስተላልፋሉ ተብሎ በሚጠበቅበት ሰዓት 'እወዳችኋለሁ' የሚል መልእክት አስተላልፈዋል። ይህ ብቻ ሳይሆን የተለመደውን ምርጫው ተጭበርብሯል የሚለውን ያልተጨበጠ ክስም በማኅበራዊ ገጻቸው አስተላልፈዋል። ትዊተር ሦስት የትራምፕ መልእክቶችን ከገጹ እንዲወገዱ እንደጠየቀ ይፋ ያደረገ ሲሆን ከፖሊሲያችን ጋር የሚጻረሩ መልእክቶች ስለሆኑ ነው መወገድ ያለባቸው ብሏል። ካልተወገዱ ግን ትራምፕን እስከመጨረሻው ከትዊተር አሰናብታቸዋለሁ ብሏል። ይህም ትዊተር ዶናልድ ትራምፕን እስከመጨረሻው ለማሰናበት በርካታ ቀናትን ላይጠብቅ ይችላል ማለት ነው። የትዊተር ውሳኔ በእንዲህ ሳለ ፌስቡክ በበኩሉ ትራምፕን ለ24 ሰዓታት እግድ ጥሎባቸዋል። ዩትዩብ በበኩሉ የትራምፕን ቪዲዯዎች ከገጹ እንዲወርዱ አድርጓል። ፌስቡክ ለምን ትራምፕን ለ24 ሰዓታት ከገጹ እንዳገደ በገለጸበት መግለጫው ምክንያቱም እየታየ ላለው ነውጥ ትራምፕ ማባባስ እንጂ ማብረድ ባለመቻላቸው ነው ብሏል። የትራምፕ ደጋፊዎች የአሜሪካ መንግሥት መቀመጫ የሆነውን ካፒቶል ሒልን ሰብረው በመግባት ከፖሊስ ጋር የተጋጩ ሲሆን በዚህ ዓለምን ጉድ ባሰኘው ነውጥ የአንዲት ሴት ሕይወት ማለፉም ተነግሯል። የትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶል ሒልን ጥሰው ጥቃት ሲፈጽሙ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት በጆ ባይደን ጉዳይና ድል እየተከራከረ ነበር። በሁለቱ ምክር ቤቶች ሪፐብሊካኖችና ዲሞክራቶች የኖቬምበሩን የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉትን ጆ ባይደንን ውጤት ማጽደቅና አለማጽደቅ ላይ እየተነጋገሩ በነበረበት ሰዓት ነው የትራምፕ ደጋፊዎች ያልተጠበቀ እርምጃ የወሰዱት። ይህ ነውጥ ከመከሰቱ በፊት ትራምፕ በዋሺንግተን ናሸናል ሞል ለደጋፊዎቻቸው ምርጫው ተዘርፏል ሲሉ ነበር። ይህ ከሆነ ከሰዓታት በኋላ ደጋፊዎቹ ካፒቶል ሒልን ጥሰው ገብተው ጉዳት ማድረስ ጀመሩ። ትራምፕ ድርጊቱን ያወግዛሉ ሲባል በቪዲዯ ቀርበው ምርጫው ተጨበርብሯል የሚለውን ንግግር ደገሙት። ይህ አልበቃ ብሎም ነውጠኞቹን እወዳችኋለሁ። ጀግኖች ናችሁ ያልዋቸው። ዩ ትዩብ ይህንን የፕሬዝዳንቱን ንግግር የኔን ፖሊሲ የማይከተል ስለሆነ አስወግጄዋለሁ ብሏል። ትዊተር በበኩሉ ይህንን ቪዲዮ ከማስወገድ ይልቅ ሰዎች እንዳያጋሩት እና መውደዳቸውን የሚያሳየውን ምልክት (ላይክ እንዳያደርጉት)፣ ከቪዲዯው ሥር አስተያየት እንዳይሰጡ በማድረግ የቪዲዯ መልእክቱ እንዳይዛመት አድርጎ ነበር። በኋላ ላይ ግን ቪዲዯውን ሙሉ በሙሉ አስወግዶ ፕሬዝዳንቱም ለጊዜው ከትዊተር እንዲሰናበቱ አድርጓቸዋል። ካፒቶል ሒልን የመውረሩ የነውጥ እንቅስቃሴ ሲስተባበር የነበረው በዋናነት እነዚህኑ ማኅበራዊ የትስስር መድረኮችን በመጠቀም ነበር።
የአሜሪካ ምክር ቤት፡ ደጋፊዎቻቸው የአገሪቱ ምክር ቤትን ከወረሩ በኋላ ትራምፕ ከትዊተርና ከፌስቡክ ታገዱ ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዋነኛዎቹ የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር ገጾች እንዲታገዱ ሆነዋል። ይህ እርምጃ የተወሰደባቸው ደጋፊዎቻቸው የካፒቶል ሂል ግቢን መውረራቸውና አደጋ ማድረሳቸውን ተከትሎ ነው። ዓለምን ባስገረመውና በአሜሪካ ምድር ይሆናል ተብሎ ባልተጠበቀ ነውጥ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የታችኛውና የላይኛው ምክር ቤት መሰብሰቢያ የሚገኝበትንና የመንግሥት መቀመጫ የሆነውን ካፒቶል ሒልን ጥሰው በመግባት አደጋ ያደረሱት ከሰዓታት በፊት ነው። ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎቻቸውን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ጠንካራ መልእክት ያስተላልፋሉ ተብሎ በሚጠበቅበት ሰዓት 'እወዳችኋለሁ' የሚል መልእክት አስተላልፈዋል። ይህ ብቻ ሳይሆን የተለመደውን ምርጫው ተጭበርብሯል የሚለውን ያልተጨበጠ ክስም በማኅበራዊ ገጻቸው አስተላልፈዋል። ትዊተር ሦስት የትራምፕ መልእክቶችን ከገጹ እንዲወገዱ እንደጠየቀ ይፋ ያደረገ ሲሆን ከፖሊሲያችን ጋር የሚጻረሩ መልእክቶች ስለሆኑ ነው መወገድ ያለባቸው ብሏል። ካልተወገዱ ግን ትራምፕን እስከመጨረሻው ከትዊተር አሰናብታቸዋለሁ ብሏል። ይህም ትዊተር ዶናልድ ትራምፕን እስከመጨረሻው ለማሰናበት በርካታ ቀናትን ላይጠብቅ ይችላል ማለት ነው። የትዊተር ውሳኔ በእንዲህ ሳለ ፌስቡክ በበኩሉ ትራምፕን ለ24 ሰዓታት እግድ ጥሎባቸዋል። ዩትዩብ በበኩሉ የትራምፕን ቪዲዯዎች ከገጹ እንዲወርዱ አድርጓል። ፌስቡክ ለምን ትራምፕን ለ24 ሰዓታት ከገጹ እንዳገደ በገለጸበት መግለጫው ምክንያቱም እየታየ ላለው ነውጥ ትራምፕ ማባባስ እንጂ ማብረድ ባለመቻላቸው ነው ብሏል። የትራምፕ ደጋፊዎች የአሜሪካ መንግሥት መቀመጫ የሆነውን ካፒቶል ሒልን ሰብረው በመግባት ከፖሊስ ጋር የተጋጩ ሲሆን በዚህ ዓለምን ጉድ ባሰኘው ነውጥ የአንዲት ሴት ሕይወት ማለፉም ተነግሯል። የትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶል ሒልን ጥሰው ጥቃት ሲፈጽሙ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት በጆ ባይደን ጉዳይና ድል እየተከራከረ ነበር። በሁለቱ ምክር ቤቶች ሪፐብሊካኖችና ዲሞክራቶች የኖቬምበሩን የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉትን ጆ ባይደንን ውጤት ማጽደቅና አለማጽደቅ ላይ እየተነጋገሩ በነበረበት ሰዓት ነው የትራምፕ ደጋፊዎች ያልተጠበቀ እርምጃ የወሰዱት። ይህ ነውጥ ከመከሰቱ በፊት ትራምፕ በዋሺንግተን ናሸናል ሞል ለደጋፊዎቻቸው ምርጫው ተዘርፏል ሲሉ ነበር። ይህ ከሆነ ከሰዓታት በኋላ ደጋፊዎቹ ካፒቶል ሒልን ጥሰው ገብተው ጉዳት ማድረስ ጀመሩ። ትራምፕ ድርጊቱን ያወግዛሉ ሲባል በቪዲዯ ቀርበው ምርጫው ተጨበርብሯል የሚለውን ንግግር ደገሙት። ይህ አልበቃ ብሎም ነውጠኞቹን እወዳችኋለሁ። ጀግኖች ናችሁ ያልዋቸው። ዩ ትዩብ ይህንን የፕሬዝዳንቱን ንግግር የኔን ፖሊሲ የማይከተል ስለሆነ አስወግጄዋለሁ ብሏል። ትዊተር በበኩሉ ይህንን ቪዲዮ ከማስወገድ ይልቅ ሰዎች እንዳያጋሩት እና መውደዳቸውን የሚያሳየውን ምልክት (ላይክ እንዳያደርጉት)፣ ከቪዲዯው ሥር አስተያየት እንዳይሰጡ በማድረግ የቪዲዯ መልእክቱ እንዳይዛመት አድርጎ ነበር። በኋላ ላይ ግን ቪዲዯውን ሙሉ በሙሉ አስወግዶ ፕሬዝዳንቱም ለጊዜው ከትዊተር እንዲሰናበቱ አድርጓቸዋል። ካፒቶል ሒልን የመውረሩ የነውጥ እንቅስቃሴ ሲስተባበር የነበረው በዋናነት እነዚህኑ ማኅበራዊ የትስስር መድረኮችን በመጠቀም ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/news-55561320
3politics
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር "አሜሪካ ጥቁሮች ላይ የምታደርሰውን የሰብአዊ መብት ጥሰት" እንድታቆም ጠየቁ
ጆ ባይደን ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በተደረገ የቻይና-አሜሪካ የንግድ ምክክር መድረክ በሁለቱ ኃያል አገሮች ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል ውይይት እየተደረገ ሲሆን ጠጣር የሐሳብ ልውውጦች መደረጋቸው ተሰማ፡፡ በዚህ የሁለትዮሽ ስብሰባ አንዱ ሌላውን አገር ያለ ርሕራሔ እየወቀሰ ይገኛል፡፡ የቻይና ከፍተኛ ባለሥልጣናት አሜሪካን ሌሎች አገሮች ቻይና ላይ ጦር እንዲሰብቁ ታበረታታለች ሲሉ ከሰዋል፡፡ አሜሪካ በበኩሏ ቻይና በዓለም አቀፍ ደረጃ አላስፈላጊ ትኩረትን ለመሳብ ትጥራለች ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ በሁለቱ አገሮች መካከል አሁን ያለው ግንኙነት የሻከረ የሚባል እንደሆነ ዲፕሎማቶች ያወሳሉ፡፡ አሜሪካ በዚህ ስብሰባ ላይ አጨቃጫቂ የሚባሉ ጉዳዮችን እንደምታነሳ ይጠበቃል፡፡ ከነዚህ አንዱ ቤጂንግ የኡህጉሩ ሙስሊሞችን በዢንዣንግ ካምፕ ውስጥ የምታደርስባቸውን ስቃይ እንድታቆም ይጠይቃሉ ተብሏል፡፡ ይህ በቃላት ጦርነት የታጀበ የከፍተኛ ባለሥልጣናት ስብሰባ እየተካሄደ ያለው በአላስካ ሲሆን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን እና የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጄክ ሰሊቫን ተገኝተውበታል፡፡ በቻይና በኩል ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ እና የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ባለሥልጣን ያንግ ጂቺ ተሳትፈዋል፡፡ በሁለትዮሹ ስብሰባ በጠንካራ ንግግር ውይይቱን ያስጀመሩት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን አሜሪካ በዚህ ስብሰባ የሚያሳስቧትን የዢንዣንግ ሙስሊሞች አፈና፣ የሆንግ ኮንግን እና የታይዋንን ጉዳይ እንዲሁም ከቻይና የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶችን ጉዳይ ታነሳለች ብለዋል፡፡ ለዚህ ምላሽ የሰጡት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያንግ ዋሺንግተን ባላት የፋይናንስና የወታደራዊ ኃያልነት የተነሳ ሌሎችን ትደፈጥጣለች ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ አክለውም አሜሪካ በብሔራዊ ደኅንነት አደጋ ስም በርካታ የንግድ ወንጀሎን ትፈጽማለች ብለዋል፡፡ ሌሎች አገራትም ቻይና ጋር ወዳጅ እንዳይሆኑ ታስፈራራለች ሲሉም ወቅሰዋል፡፡ የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአሜሪካ የሰብአዊ መብት ጥሰት መባባሱን ጠቅሰው ጥቁሮች በጠራራ ፀሐይ እየተገደሉ ነው ሲሉ አስገራሚ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ ይህ በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ የሚደረገው መተቻቸት የዓለም ሚዲያዎች በተገኙበት እየሆነ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል፡፡ ይህ አንድ ሁለት መባባል እየተካረረ ከሄደ በኋላ አሜሪካ ቻይናን ‹የተስማማነው 2 ደቂቃ የመክፈቻ ንግግር ለማድረግ ቢሆንም በዚህ ስብሰባ ቻይና መስመር አልፋ ወቅሳኛለች ስትል ከሳታለች፡፡ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን እንደተናገሩት ቻይና በዚህ ስብሰባ ሆን ብላ የዓለም ሚዲያውን ትኩረት ለመሳብ ተዘጋጅታ ነው የመጣችው ብለዋል፡፡ ቻይና በበኩሏ ስብሰባው መክፈቻ ላይ ለ2 ደቂቃዎች ብቻ እንወቃቀስ ብንባባልም ይህን ፕሮቶኮል የጣሰችው አሜሪካ ራሷ እንጂ እኛ ቻይናዊያን አይደለንም ብለዋል፡፡ ጨምረውም አሜሪካ የቻይናን የውጭና የአገር ውስጥ ፖሊሲ በዓለም ሚዲያ ፊት ለማብጠልጠል መሞከራቸው አሳፋሪ ነው ብለዋል፡፡ ሁለቱ አገሮች በዚህ ስብሰባ በትራምፕ ዘመን አፈር ልሶ የነበረውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሻሻል እንደሚጥሩ ይጠበቃል፡፡
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር "አሜሪካ ጥቁሮች ላይ የምታደርሰውን የሰብአዊ መብት ጥሰት" እንድታቆም ጠየቁ ጆ ባይደን ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በተደረገ የቻይና-አሜሪካ የንግድ ምክክር መድረክ በሁለቱ ኃያል አገሮች ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል ውይይት እየተደረገ ሲሆን ጠጣር የሐሳብ ልውውጦች መደረጋቸው ተሰማ፡፡ በዚህ የሁለትዮሽ ስብሰባ አንዱ ሌላውን አገር ያለ ርሕራሔ እየወቀሰ ይገኛል፡፡ የቻይና ከፍተኛ ባለሥልጣናት አሜሪካን ሌሎች አገሮች ቻይና ላይ ጦር እንዲሰብቁ ታበረታታለች ሲሉ ከሰዋል፡፡ አሜሪካ በበኩሏ ቻይና በዓለም አቀፍ ደረጃ አላስፈላጊ ትኩረትን ለመሳብ ትጥራለች ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ በሁለቱ አገሮች መካከል አሁን ያለው ግንኙነት የሻከረ የሚባል እንደሆነ ዲፕሎማቶች ያወሳሉ፡፡ አሜሪካ በዚህ ስብሰባ ላይ አጨቃጫቂ የሚባሉ ጉዳዮችን እንደምታነሳ ይጠበቃል፡፡ ከነዚህ አንዱ ቤጂንግ የኡህጉሩ ሙስሊሞችን በዢንዣንግ ካምፕ ውስጥ የምታደርስባቸውን ስቃይ እንድታቆም ይጠይቃሉ ተብሏል፡፡ ይህ በቃላት ጦርነት የታጀበ የከፍተኛ ባለሥልጣናት ስብሰባ እየተካሄደ ያለው በአላስካ ሲሆን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን እና የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጄክ ሰሊቫን ተገኝተውበታል፡፡ በቻይና በኩል ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ እና የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ባለሥልጣን ያንግ ጂቺ ተሳትፈዋል፡፡ በሁለትዮሹ ስብሰባ በጠንካራ ንግግር ውይይቱን ያስጀመሩት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን አሜሪካ በዚህ ስብሰባ የሚያሳስቧትን የዢንዣንግ ሙስሊሞች አፈና፣ የሆንግ ኮንግን እና የታይዋንን ጉዳይ እንዲሁም ከቻይና የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶችን ጉዳይ ታነሳለች ብለዋል፡፡ ለዚህ ምላሽ የሰጡት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያንግ ዋሺንግተን ባላት የፋይናንስና የወታደራዊ ኃያልነት የተነሳ ሌሎችን ትደፈጥጣለች ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ አክለውም አሜሪካ በብሔራዊ ደኅንነት አደጋ ስም በርካታ የንግድ ወንጀሎን ትፈጽማለች ብለዋል፡፡ ሌሎች አገራትም ቻይና ጋር ወዳጅ እንዳይሆኑ ታስፈራራለች ሲሉም ወቅሰዋል፡፡ የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአሜሪካ የሰብአዊ መብት ጥሰት መባባሱን ጠቅሰው ጥቁሮች በጠራራ ፀሐይ እየተገደሉ ነው ሲሉ አስገራሚ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ ይህ በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ የሚደረገው መተቻቸት የዓለም ሚዲያዎች በተገኙበት እየሆነ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል፡፡ ይህ አንድ ሁለት መባባል እየተካረረ ከሄደ በኋላ አሜሪካ ቻይናን ‹የተስማማነው 2 ደቂቃ የመክፈቻ ንግግር ለማድረግ ቢሆንም በዚህ ስብሰባ ቻይና መስመር አልፋ ወቅሳኛለች ስትል ከሳታለች፡፡ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን እንደተናገሩት ቻይና በዚህ ስብሰባ ሆን ብላ የዓለም ሚዲያውን ትኩረት ለመሳብ ተዘጋጅታ ነው የመጣችው ብለዋል፡፡ ቻይና በበኩሏ ስብሰባው መክፈቻ ላይ ለ2 ደቂቃዎች ብቻ እንወቃቀስ ብንባባልም ይህን ፕሮቶኮል የጣሰችው አሜሪካ ራሷ እንጂ እኛ ቻይናዊያን አይደለንም ብለዋል፡፡ ጨምረውም አሜሪካ የቻይናን የውጭና የአገር ውስጥ ፖሊሲ በዓለም ሚዲያ ፊት ለማብጠልጠል መሞከራቸው አሳፋሪ ነው ብለዋል፡፡ ሁለቱ አገሮች በዚህ ስብሰባ በትራምፕ ዘመን አፈር ልሶ የነበረውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሻሻል እንደሚጥሩ ይጠበቃል፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-56453316
5sports
የዓለም አትሌቲክስ ሽልማት፡ ሁለት አፍሪካዊያን ለዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌቶች ሽልማት ታጩ
የዓለም አትሌቲክስ በየዓመቱ በሚያዘጋጀው ምርጥ ሴት አትሌቶች ሽልማት ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ እና ኬንያዊቷ ፔረስ ጀፕቺርቺር ከመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች ዝርዝር ውስጥ መግባታቸው ተገለፀ። የዓለም አትሌቲክስ ማክሰኞ እለት በአስሩ ዝርዝር ውስጥ ገብተው ከነበሩ አትሌቶች አምስት ለመጨረሻው ዙር መመረጣቸውን አስታውቋል። ሌሎች ሦስት አፍሪካዊያን አትሌቶች አስሩ ዝርዝር ውስጥ ተካተው የነበረ ቢሆንም 5ቱ ዝርዝር ውስጥ ግን መግባት ሳይችሉ ቀርተዋል። እነዚህ አትሌቶች ኢትዮጵያዊቷ አባበል የሻነህ፣ ኬንያዊያኖቹ ዶ ፌዝ ኪፕየጎን እና ሔለን ኦቢሪ ናቸው። ለ ሌሎቹ በአምስቱ ዝርዝር ውስጥ መካተት ያልቻሉት አትሌቶች ደግሞ የኔዘርላንዷ ፌምኬ ቦል እና እንግሊዟ ላውራ ሙር ናቸው። የዘንድሮው ዓመት የዓለም አትሌቲክስ ሽልማት ሥነ ሥርዓት በቨርቹዋል [ኢንተርኔት] በአውሮፓዊያኑ ታህሳስ 5 የሚካሄድ ሲሆን በማኅበራዊ ሚዲያም በቀጥታ ይሰራጫል ተብሏል።የዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌት 5ቱ እጩዎች ለተሰንበት ግደይ በ5000 ሜትር በ14፡06፡62 በመግባት የዓለም ክብረ ወሰንን ሰብራለች። ቫሌንሺያ በተደረገው በዚህ ውድድር በጥሩነሽ ዲባባ ለአስራ ሁለት ዓመታት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሽላለች ተብሏል። የ22 ዓመቷ ሯጭ የገባችበት ሰዓትም 14 ደቂቃ ከ6.62 ሰኮንዶች ሲሆን የጥሩነሸ ደግሞ 14 ደቂቃ ከ11.15 ሰከንዶች ነበር። በሞናኮ በተካሄደው በዋንዳ ዲያመንድ ሊግም 5000 ሜትር ሩጫ በሁለተኛ ደረጃነት አጠናቃለች። ሲፋን ሐሰን 18,930 ሜትር በአንድ ሰዓት ጊዜ በመሮጥ የዓለም ክብረ ወሰን ይዛለች። በ10 ሺህ ሜትር በ29፡36፡67 በማጠናቀቅም የአውሮፓ ክብረወሰን ያስመዘገበች ሲሆን በታሪክ አራተኛዋ ፈጣኗ ሯጭ ተብላለች። የዓለም ግማሽ ማራቶን አሸናፊ ናት። በሴቶች ውድድር 1፡ 05፡34 እና 1፡ 05፡ 16 ሰዓት በመግባት የግማሽ ማራቶን ክብረወሰንን ሁለት ጊዜ ሰብራለች። በቤት ውስጥና ከቤት ውጭ በተደረጉ አራት የርዝመት ዝላይ ውድድሮች አሸንፋለች። በቤት ውስጥ በተካሄደ የርዝመት ዝላይ ውድድር 15.43 ሜትር በመዝለል የዓለም ክብረ ወሰን ሰብራለች። በሰባት የ100 ሜትር ውድድሮች አሸንፋለች። በዓለም መሪነት 100 ሜትር በ10.85 ሰከንድ ሮጣለች። ከእነዚህ እጩዎች አሸናፊውን ለመለየት ሦስት የድምፅ አሰጣጥ መንገዶች አሉ። የዓለም አትሌቲክስ ምክር ቤት እና የዓለም አትሌቲክስ ቤተሰቦች ድምፃቸውን በኢሜይል የሚሰጡ ሲሆን አድናቂዎቻቸው ደግሞ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ድምፅ ይሰጣሉ። ከአጠቃላይ ድምፁ የምክር ቤቱ ድምፅ 50 በመቶ ይይዛል። የአትሌቲክስ ቤተሰቦችና የሕዝብ ድምፅ ደግሞ እያንዳንዳቸው 25 በመቶ ይይዛሉ።
የዓለም አትሌቲክስ ሽልማት፡ ሁለት አፍሪካዊያን ለዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌቶች ሽልማት ታጩ የዓለም አትሌቲክስ በየዓመቱ በሚያዘጋጀው ምርጥ ሴት አትሌቶች ሽልማት ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ እና ኬንያዊቷ ፔረስ ጀፕቺርቺር ከመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች ዝርዝር ውስጥ መግባታቸው ተገለፀ። የዓለም አትሌቲክስ ማክሰኞ እለት በአስሩ ዝርዝር ውስጥ ገብተው ከነበሩ አትሌቶች አምስት ለመጨረሻው ዙር መመረጣቸውን አስታውቋል። ሌሎች ሦስት አፍሪካዊያን አትሌቶች አስሩ ዝርዝር ውስጥ ተካተው የነበረ ቢሆንም 5ቱ ዝርዝር ውስጥ ግን መግባት ሳይችሉ ቀርተዋል። እነዚህ አትሌቶች ኢትዮጵያዊቷ አባበል የሻነህ፣ ኬንያዊያኖቹ ዶ ፌዝ ኪፕየጎን እና ሔለን ኦቢሪ ናቸው። ለ ሌሎቹ በአምስቱ ዝርዝር ውስጥ መካተት ያልቻሉት አትሌቶች ደግሞ የኔዘርላንዷ ፌምኬ ቦል እና እንግሊዟ ላውራ ሙር ናቸው። የዘንድሮው ዓመት የዓለም አትሌቲክስ ሽልማት ሥነ ሥርዓት በቨርቹዋል [ኢንተርኔት] በአውሮፓዊያኑ ታህሳስ 5 የሚካሄድ ሲሆን በማኅበራዊ ሚዲያም በቀጥታ ይሰራጫል ተብሏል።የዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌት 5ቱ እጩዎች ለተሰንበት ግደይ በ5000 ሜትር በ14፡06፡62 በመግባት የዓለም ክብረ ወሰንን ሰብራለች። ቫሌንሺያ በተደረገው በዚህ ውድድር በጥሩነሽ ዲባባ ለአስራ ሁለት ዓመታት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሽላለች ተብሏል። የ22 ዓመቷ ሯጭ የገባችበት ሰዓትም 14 ደቂቃ ከ6.62 ሰኮንዶች ሲሆን የጥሩነሸ ደግሞ 14 ደቂቃ ከ11.15 ሰከንዶች ነበር። በሞናኮ በተካሄደው በዋንዳ ዲያመንድ ሊግም 5000 ሜትር ሩጫ በሁለተኛ ደረጃነት አጠናቃለች። ሲፋን ሐሰን 18,930 ሜትር በአንድ ሰዓት ጊዜ በመሮጥ የዓለም ክብረ ወሰን ይዛለች። በ10 ሺህ ሜትር በ29፡36፡67 በማጠናቀቅም የአውሮፓ ክብረወሰን ያስመዘገበች ሲሆን በታሪክ አራተኛዋ ፈጣኗ ሯጭ ተብላለች። የዓለም ግማሽ ማራቶን አሸናፊ ናት። በሴቶች ውድድር 1፡ 05፡34 እና 1፡ 05፡ 16 ሰዓት በመግባት የግማሽ ማራቶን ክብረወሰንን ሁለት ጊዜ ሰብራለች። በቤት ውስጥና ከቤት ውጭ በተደረጉ አራት የርዝመት ዝላይ ውድድሮች አሸንፋለች። በቤት ውስጥ በተካሄደ የርዝመት ዝላይ ውድድር 15.43 ሜትር በመዝለል የዓለም ክብረ ወሰን ሰብራለች። በሰባት የ100 ሜትር ውድድሮች አሸንፋለች። በዓለም መሪነት 100 ሜትር በ10.85 ሰከንድ ሮጣለች። ከእነዚህ እጩዎች አሸናፊውን ለመለየት ሦስት የድምፅ አሰጣጥ መንገዶች አሉ። የዓለም አትሌቲክስ ምክር ቤት እና የዓለም አትሌቲክስ ቤተሰቦች ድምፃቸውን በኢሜይል የሚሰጡ ሲሆን አድናቂዎቻቸው ደግሞ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ድምፅ ይሰጣሉ። ከአጠቃላይ ድምፁ የምክር ቤቱ ድምፅ 50 በመቶ ይይዛል። የአትሌቲክስ ቤተሰቦችና የሕዝብ ድምፅ ደግሞ እያንዳንዳቸው 25 በመቶ ይይዛሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-55036276
5sports
የቶኪዮ ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ በመነከሱ ምክንያት በአዲስ ሊተካ ነው
የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊዋ በትውልድ ከተማዋ ከንቲባ ሜዳሊያዋ በመነከሱ ምክንያት አዲስ ሊሰጣት ነው። የጃፓኗ ናጎያ ከተማ ከንቲባ ታካሺ ካዋሙራ በአንድ ዝግጅት ላይ ጭምብላቸውን ዝቅ በማድረግ የሶፍትቦል ተወዳዳሪዋን ሚኡ ጎቶን ሜዳሊያ በመንከሳቸው በማኅበራዊ ድር አምባ ቁጣን ቀስቅሷል። ከንቲባው የኮቪድ -19 ገደቦችን ችላ በማለት እና "አክብሮት የጎደለው" በሚል ተከሰዋል። ይሁን እንጅ ከንቲባው ይቅርታ ከጠየቁ እና ለምትኩ ክፍያ እንደሚፈጽሙ ከተናገሩ በኋላ የኦሊምፒክ ባለሥልጣናት የጎቶ ሜዳልያ በአዲስ እንደሚለወጥ ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት በሴቶች የሶፍትቦል የፍጻሜ ውድድር ጃፓን በአሜሪካን ላይ ድል አግኝታለች። ከንቲባውም ይህን ድል ለማክበር ነበር ሜዳሊያውን በጥርሳቸው የያዙት፤ በኋላ ላይ ግን በድርጊታቸው ከመብጠልጠል አልዳኑም። የማኅበራዊ ድር አምባ ተጠቃሚዎች ድርጊቱ ንጽሕና የጎደለው እና ለአትሌቷ ያሳዩት ጨዋነት የጎደለው ተግባር ነው ብለዋል። "ለአትሌቶች የአክብሮት እጦት ከማሳየት ባሻገርም፤ አትሌቶች በሜዳልያ ሥነ ሥርዓቶች ወቅት ቫይረሱን ለመከላከል ሲባል ሜዳልያዎችን ራሳቸው ሲያጠልቁ ወይም ለሌሎች የቡድን አባላቶቻቸው ሲያጠልቁ ቢታዩም እሳቸው ግን ነክሰውታል። ይቅርታ፣ አልገባኝም!" ሲል የጃፓኑ የብር ሜዳልያ ተሸላሚ ዩኪ ኦታ በትዊተር ገጹ ላይ አስፍሯል። በጃፓን በማኅበራዊ ድር አምባዎች ላይ "የጀርም ሜዳሊያ" የሚል ሃሳብ በስፋት እየተንሸራሸረ እየታየ ነበር። ጎቶ የምትጫወትበት ቡድን ባለቤት የሆነው ቶዮታም ድርጊቱን "ተገቢ ያልሆነ" እና "እጅግ የሚያሳዝን" ብሎታል። የ72 ዓመቱ ከንቲባ ለድርጊቱ በኋላ ላይ ይቅርታ ጠይቀዋል። የከንቲባው ድርጊት ከ7,000 በላይ ቅሬታዎች ለከተማው ባለሥልጣናት እንዲደርስ ምክንያት ሆኗል ተብሏል። "እንደ ናጎያ አስተዳዳሪ ያለኝን ቦታ ረስቼ እጅግ ተገቢ ባልሆነ መንገድ እርምጃ ወስጄ ነበር' ሲሉ ለሚተካው ሜዳሊያ እንደሚከፍሉ ከንቲባው አስታውቀዋል። የቶኪዮ 2020 አዘጋጆች ሐሙስ ዕለት በሰጡት መግለጫ በአዲስ ሜዳሊያ በመተካቱ ዙሪያ በዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ እና በጎቶ መካከል ከስምምነት ተደርሷል። ዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ወጪዎቹን ይሸፍናልም ብሏል። ሜዳሊያዎችን መንከስ በውድድሮች ውስጥ የተለመደ ቢሆንም ብዙውን ጊዜ ግን ይህን የሚያደርጉት አሸናፊዎቹ ብቻ ናቸው። የቶኪዮ 2020 አዘጋጆች ባለፈው ሳምንት በትዊተር ገጻቸው ላይ "የ#ቶኪዮ2020 ሜዳሊያዎች የማይበሉ መሆናቸውን በይፋ ለመግለጽ እንፈልጋለን!" ሲሉ ጉዳዩን ወደ ቀልድ ወስደውት ነበር። ካዋሙራም ሆኑ ጎቶ ግን በጉዳዩ ላይ ወዲያው አስተያየት አልሰጡም።
የቶኪዮ ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ በመነከሱ ምክንያት በአዲስ ሊተካ ነው የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊዋ በትውልድ ከተማዋ ከንቲባ ሜዳሊያዋ በመነከሱ ምክንያት አዲስ ሊሰጣት ነው። የጃፓኗ ናጎያ ከተማ ከንቲባ ታካሺ ካዋሙራ በአንድ ዝግጅት ላይ ጭምብላቸውን ዝቅ በማድረግ የሶፍትቦል ተወዳዳሪዋን ሚኡ ጎቶን ሜዳሊያ በመንከሳቸው በማኅበራዊ ድር አምባ ቁጣን ቀስቅሷል። ከንቲባው የኮቪድ -19 ገደቦችን ችላ በማለት እና "አክብሮት የጎደለው" በሚል ተከሰዋል። ይሁን እንጅ ከንቲባው ይቅርታ ከጠየቁ እና ለምትኩ ክፍያ እንደሚፈጽሙ ከተናገሩ በኋላ የኦሊምፒክ ባለሥልጣናት የጎቶ ሜዳልያ በአዲስ እንደሚለወጥ ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት በሴቶች የሶፍትቦል የፍጻሜ ውድድር ጃፓን በአሜሪካን ላይ ድል አግኝታለች። ከንቲባውም ይህን ድል ለማክበር ነበር ሜዳሊያውን በጥርሳቸው የያዙት፤ በኋላ ላይ ግን በድርጊታቸው ከመብጠልጠል አልዳኑም። የማኅበራዊ ድር አምባ ተጠቃሚዎች ድርጊቱ ንጽሕና የጎደለው እና ለአትሌቷ ያሳዩት ጨዋነት የጎደለው ተግባር ነው ብለዋል። "ለአትሌቶች የአክብሮት እጦት ከማሳየት ባሻገርም፤ አትሌቶች በሜዳልያ ሥነ ሥርዓቶች ወቅት ቫይረሱን ለመከላከል ሲባል ሜዳልያዎችን ራሳቸው ሲያጠልቁ ወይም ለሌሎች የቡድን አባላቶቻቸው ሲያጠልቁ ቢታዩም እሳቸው ግን ነክሰውታል። ይቅርታ፣ አልገባኝም!" ሲል የጃፓኑ የብር ሜዳልያ ተሸላሚ ዩኪ ኦታ በትዊተር ገጹ ላይ አስፍሯል። በጃፓን በማኅበራዊ ድር አምባዎች ላይ "የጀርም ሜዳሊያ" የሚል ሃሳብ በስፋት እየተንሸራሸረ እየታየ ነበር። ጎቶ የምትጫወትበት ቡድን ባለቤት የሆነው ቶዮታም ድርጊቱን "ተገቢ ያልሆነ" እና "እጅግ የሚያሳዝን" ብሎታል። የ72 ዓመቱ ከንቲባ ለድርጊቱ በኋላ ላይ ይቅርታ ጠይቀዋል። የከንቲባው ድርጊት ከ7,000 በላይ ቅሬታዎች ለከተማው ባለሥልጣናት እንዲደርስ ምክንያት ሆኗል ተብሏል። "እንደ ናጎያ አስተዳዳሪ ያለኝን ቦታ ረስቼ እጅግ ተገቢ ባልሆነ መንገድ እርምጃ ወስጄ ነበር' ሲሉ ለሚተካው ሜዳሊያ እንደሚከፍሉ ከንቲባው አስታውቀዋል። የቶኪዮ 2020 አዘጋጆች ሐሙስ ዕለት በሰጡት መግለጫ በአዲስ ሜዳሊያ በመተካቱ ዙሪያ በዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ እና በጎቶ መካከል ከስምምነት ተደርሷል። ዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ወጪዎቹን ይሸፍናልም ብሏል። ሜዳሊያዎችን መንከስ በውድድሮች ውስጥ የተለመደ ቢሆንም ብዙውን ጊዜ ግን ይህን የሚያደርጉት አሸናፊዎቹ ብቻ ናቸው። የቶኪዮ 2020 አዘጋጆች ባለፈው ሳምንት በትዊተር ገጻቸው ላይ "የ#ቶኪዮ2020 ሜዳሊያዎች የማይበሉ መሆናቸውን በይፋ ለመግለጽ እንፈልጋለን!" ሲሉ ጉዳዩን ወደ ቀልድ ወስደውት ነበር። ካዋሙራም ሆኑ ጎቶ ግን በጉዳዩ ላይ ወዲያው አስተያየት አልሰጡም።
https://www.bbc.com/amharic/news-58168874
2health
’ኮሮናቫይረስ፡ ካልተከተቡ አይቀጠሩም’ የሚል ህግ ለአዳዲስ ሠራተኞች ተግባራዊ ሊሆን ይችላል
ኩባንያዎች አዳዲስ ሠራተኞቻቸው፣ ከመቀጠራቸው በፊት እንዲከተቡ ቢጠይቁ ህጋዊ ሊሆን ይችላል ሲሉ የእንግሊዝ የፍትህ ሚንስትር አስታወቁ። እንደሮበርት ባክላንድ ከሆነ ነባር ሠራተኞች ባላቸው ውል መሠረት ክትባቶችን እንዲወስዱ የመጠየቅ ነገር ላይኖር ይችላል። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ሰዎች በሥራቸው እንዲቀጥሉ ክትባት እንዲወስዱ ማዘዙ "አድሎአዊ" ነው ብሏል። ነገር ግን አንዳንድ ድርጅቶች ክትባቱን ለመውሰድ ፈቃደኛ ያልሆኑ አዳዲስ ሠራተኞችን እንደማይቀጥሩ ይናገራሉ፡፡ ባክላንድ ረቡዕ ዕለት ከአይቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አዳዲስ በሥራ ውል ላይ በጽሑፍ እስከቀረበ ድረስ ሠራተኞችን እንዲከተቡ ማስገደድ ይቻል ይሆናል ብለዋል፡፡ ሆኖም አሠሪዎች ምናልባት ነባር ሠራተኞች እንዲህ ዓይነቱን ትዕዛዝ እምቢ ካሉ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ ሊያስፈልጋቸው ይችላል ተብሏል። አክለውም "ያለ ክትባት ሥራ የለም" የሚሉት መስፈርት ሕጋዊነት "በቅጥርና በልዩ ውል ላይ የተንጠለጠለ ነው" ብለዋል፡፡ "በአጠቃላይ አካሄዱን ሕጋዊ ያደረጉት አሁን ያሉት የሥራ ኮንትራቶች ቢኖሩ እደነቃለሁ፡፡ እውነቱን ለመናገር ጉዳዩ መፈተሽ ያለበት ይመስለኛል" ብለዋል፡፡ መቀመጫውን ለንደን ያደረገው የፒምሊኮ ፕለምበርስ ከህክምና ጋር በተያያዘ ካልሆነ በስተቀር ክትባቱን አልፈልግም የሚሉ አዳዲስ ሠራተኞችን አልቀጥርም ካሉት ኩባንያዎች አንዱ ነው፡፡ ከቅጥር ጋር በተያያዘ የሚሠሩ የህግ ባለሙያዎች በመጀመሪያ እርምጃው ላይ ጥያቄ ቢያነሱም መስራቹ ቻርሊ ሙሊንስ ህጋዊ እንደሆነ ምክር እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ "እኛ በግልጽ ከጠበቆች ጋር የተነጋገርን ሲሆን ክትባቱ ሙሉ በሙሉ ከወጣ በኋላ ከእኛ ጋር ለሚጀምሩ ማናቸውም አዳዲስ ሠራተኞች የክትባቱ ጉዳይ በውሉ ውስጥ በመካተቱ ባለሙያዎቹ በጣም ደስተኞች ናቸው" ብለዋል ለቢቢሲ፡፡ "አዲሶቹን ኮንትራቶች ከሁለት እስከ ሶስት ወራቶች ውስጥ እንጠቀማቸዋለን፡፡ ሰዎች ከእኛ ጋር ሥራ ለመሥራት ሲመጡ ያንን በመፈረም ደስተኛ ካልሆኑ የእነሱ ምርጫ ነው። በእርግጠኝነትም ሥራው ከፒምሊኮ ፕላምበርስ አይሰጣቸውም" ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የቤት እንክብካቤ ላይ የተሠማራው ባርቸስተር ሄልዝኬርም ሁሉም አዲስ ቅጥር ሠራተኞችየመከተብ ግዴታ አለባቸው ብሏል፡፡ "ከሠራተኞቻችን ጋር በተያያዘ ፍላጎት ያላቸውን ክትባቱን እንዲያገኙ ለማበረታታት የተቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው። በተጨማሪም ሁሉም አዲስ ሠራተኞች ክትባቱን መውሰዳቸውን ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ማረጋገጥ አለብን" ያለው ድርጅቱ ደንበኞቹን እና ሠራተኞቹን ጤንነት መጠበቅን ደግሞ በምክንያትነት አስቀምጧል። 'የህግ ክፍተት' ሌዊስ ሲልኪን በሚባለው የሕግ ኩባንያ የሕግ ዳይሬክተር የሆኑት ዴቪድ ሳሙኤል እንዳሉት ድርጅቶች በአዳዲስ ቅጥር ሠራተኞቻቸው ኮንትራቶች ውስጥ "ያለ ክትባት ሥራ የለም" የሚል አንቀጽን ከማስገባት የሚያግዳቸው ሕጋዊ ማዕቀፍ የለም፡፡ አሠሪዎች እያንዳንዱን የሥራ ሚና መተንተን እና እንዲህ ዓይነቱን ሐረግ ከማስተዋወቅ በፊት የጤና እና የደህንነትን አደጋዎችን መገምገም አለባቸው ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ ይህ ባለማድረጉና አንድ ሠራተኛ ያልተከተበት ምክንያት ቢኖረው ውሉ ኢ-ፍትሃዊ ወይም አድሎአዊ ነው ብሎ ለመከራከር ያስችለዋል፡፡ ሌሎች ስጋቶችም አሉ። ለምሳሌ ፣ "ካልተከተቡ ሥራ የለም" የሚለው ፖሊሲ ክትባቱን ለመውሰድ የመጨረሻ መስመር ላይ ባሉ ወጣቶች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ የሚል ስጋት አለ፡፡ "ይህን ለማጽደቅ ከባድ ይሆናል። በተለይም በዚያ ሂደት ውስጥ ካልገቡ እና ካልሰነዱት በሕጋዊ ጥያቄ የመፈታተናቸው ዕድላቸው ሰፊ ነው" ሲሉ ሳሙኤል ለቢቢሲ ገልጸዋል፡፡ የአንዳንድ ሠራተኞች የሥራ ሁኔታ በቢሮ ወይም በፋብሪካ እንዲሠሩ የሚያስገድድ ከሆነ ድርጅታቸው እንደዚህ ዓይነት አንቀፅ ሊቀመጥ ይችላል ወይ የሚል ጥያቄ እንደደረሳቸው አክለው ገልጸዋል፡፡ "ክትባት መውሰድ ግዴታ አይደለም፤ እናም አንድ ሰው እንዲወስድ ማስገደድ አድልአዊ ነው" ብለዋል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ፡
’ኮሮናቫይረስ፡ ካልተከተቡ አይቀጠሩም’ የሚል ህግ ለአዳዲስ ሠራተኞች ተግባራዊ ሊሆን ይችላል ኩባንያዎች አዳዲስ ሠራተኞቻቸው፣ ከመቀጠራቸው በፊት እንዲከተቡ ቢጠይቁ ህጋዊ ሊሆን ይችላል ሲሉ የእንግሊዝ የፍትህ ሚንስትር አስታወቁ። እንደሮበርት ባክላንድ ከሆነ ነባር ሠራተኞች ባላቸው ውል መሠረት ክትባቶችን እንዲወስዱ የመጠየቅ ነገር ላይኖር ይችላል። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ሰዎች በሥራቸው እንዲቀጥሉ ክትባት እንዲወስዱ ማዘዙ "አድሎአዊ" ነው ብሏል። ነገር ግን አንዳንድ ድርጅቶች ክትባቱን ለመውሰድ ፈቃደኛ ያልሆኑ አዳዲስ ሠራተኞችን እንደማይቀጥሩ ይናገራሉ፡፡ ባክላንድ ረቡዕ ዕለት ከአይቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አዳዲስ በሥራ ውል ላይ በጽሑፍ እስከቀረበ ድረስ ሠራተኞችን እንዲከተቡ ማስገደድ ይቻል ይሆናል ብለዋል፡፡ ሆኖም አሠሪዎች ምናልባት ነባር ሠራተኞች እንዲህ ዓይነቱን ትዕዛዝ እምቢ ካሉ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ ሊያስፈልጋቸው ይችላል ተብሏል። አክለውም "ያለ ክትባት ሥራ የለም" የሚሉት መስፈርት ሕጋዊነት "በቅጥርና በልዩ ውል ላይ የተንጠለጠለ ነው" ብለዋል፡፡ "በአጠቃላይ አካሄዱን ሕጋዊ ያደረጉት አሁን ያሉት የሥራ ኮንትራቶች ቢኖሩ እደነቃለሁ፡፡ እውነቱን ለመናገር ጉዳዩ መፈተሽ ያለበት ይመስለኛል" ብለዋል፡፡ መቀመጫውን ለንደን ያደረገው የፒምሊኮ ፕለምበርስ ከህክምና ጋር በተያያዘ ካልሆነ በስተቀር ክትባቱን አልፈልግም የሚሉ አዳዲስ ሠራተኞችን አልቀጥርም ካሉት ኩባንያዎች አንዱ ነው፡፡ ከቅጥር ጋር በተያያዘ የሚሠሩ የህግ ባለሙያዎች በመጀመሪያ እርምጃው ላይ ጥያቄ ቢያነሱም መስራቹ ቻርሊ ሙሊንስ ህጋዊ እንደሆነ ምክር እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ "እኛ በግልጽ ከጠበቆች ጋር የተነጋገርን ሲሆን ክትባቱ ሙሉ በሙሉ ከወጣ በኋላ ከእኛ ጋር ለሚጀምሩ ማናቸውም አዳዲስ ሠራተኞች የክትባቱ ጉዳይ በውሉ ውስጥ በመካተቱ ባለሙያዎቹ በጣም ደስተኞች ናቸው" ብለዋል ለቢቢሲ፡፡ "አዲሶቹን ኮንትራቶች ከሁለት እስከ ሶስት ወራቶች ውስጥ እንጠቀማቸዋለን፡፡ ሰዎች ከእኛ ጋር ሥራ ለመሥራት ሲመጡ ያንን በመፈረም ደስተኛ ካልሆኑ የእነሱ ምርጫ ነው። በእርግጠኝነትም ሥራው ከፒምሊኮ ፕላምበርስ አይሰጣቸውም" ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የቤት እንክብካቤ ላይ የተሠማራው ባርቸስተር ሄልዝኬርም ሁሉም አዲስ ቅጥር ሠራተኞችየመከተብ ግዴታ አለባቸው ብሏል፡፡ "ከሠራተኞቻችን ጋር በተያያዘ ፍላጎት ያላቸውን ክትባቱን እንዲያገኙ ለማበረታታት የተቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው። በተጨማሪም ሁሉም አዲስ ሠራተኞች ክትባቱን መውሰዳቸውን ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ማረጋገጥ አለብን" ያለው ድርጅቱ ደንበኞቹን እና ሠራተኞቹን ጤንነት መጠበቅን ደግሞ በምክንያትነት አስቀምጧል። 'የህግ ክፍተት' ሌዊስ ሲልኪን በሚባለው የሕግ ኩባንያ የሕግ ዳይሬክተር የሆኑት ዴቪድ ሳሙኤል እንዳሉት ድርጅቶች በአዳዲስ ቅጥር ሠራተኞቻቸው ኮንትራቶች ውስጥ "ያለ ክትባት ሥራ የለም" የሚል አንቀጽን ከማስገባት የሚያግዳቸው ሕጋዊ ማዕቀፍ የለም፡፡ አሠሪዎች እያንዳንዱን የሥራ ሚና መተንተን እና እንዲህ ዓይነቱን ሐረግ ከማስተዋወቅ በፊት የጤና እና የደህንነትን አደጋዎችን መገምገም አለባቸው ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ ይህ ባለማድረጉና አንድ ሠራተኛ ያልተከተበት ምክንያት ቢኖረው ውሉ ኢ-ፍትሃዊ ወይም አድሎአዊ ነው ብሎ ለመከራከር ያስችለዋል፡፡ ሌሎች ስጋቶችም አሉ። ለምሳሌ ፣ "ካልተከተቡ ሥራ የለም" የሚለው ፖሊሲ ክትባቱን ለመውሰድ የመጨረሻ መስመር ላይ ባሉ ወጣቶች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ የሚል ስጋት አለ፡፡ "ይህን ለማጽደቅ ከባድ ይሆናል። በተለይም በዚያ ሂደት ውስጥ ካልገቡ እና ካልሰነዱት በሕጋዊ ጥያቄ የመፈታተናቸው ዕድላቸው ሰፊ ነው" ሲሉ ሳሙኤል ለቢቢሲ ገልጸዋል፡፡ የአንዳንድ ሠራተኞች የሥራ ሁኔታ በቢሮ ወይም በፋብሪካ እንዲሠሩ የሚያስገድድ ከሆነ ድርጅታቸው እንደዚህ ዓይነት አንቀፅ ሊቀመጥ ይችላል ወይ የሚል ጥያቄ እንደደረሳቸው አክለው ገልጸዋል፡፡ "ክትባት መውሰድ ግዴታ አይደለም፤ እናም አንድ ሰው እንዲወስድ ማስገደድ አድልአዊ ነው" ብለዋል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ፡
https://www.bbc.com/amharic/news-56121979
2health
በዓለም ዙሪያ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከሦስት ሚሊዮን አለፈ
በዓለም ዙሪያ በኮቪድ-19 ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከሦስት ሚሊዮን ማለፉን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ገለጸ። ይህ የተገለጸው የዓለም ጤና ድርጅት "ዓለም ወደ ከፍተኛው የኢንፌክሽን መጠን እየተቃረበ ነው" መሆኑን ባስጠነቀቀ ማግስት ነው። ብዙ ሰዎች በቫይረሱ በመያዝ ሁለተኛ የሆነችው ሕንድ ዛሬ ቅዳሜ ብቻ ከ230,000 በላይ አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን አስመዝግባለች። ወረርሽኙ ከተከሰተ ወዲህ ወደ 140 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አርብ ዕለት "በበሽታው የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በአሳሳቢ ደረጃዎች እየጨመረ ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። አክለውም "ባለፉት ሁለት ወራት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሳምንት በቫይረሱ የሚያዙ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ሊጨምር ችሏል" ብለዋል። ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ እንደገለጸው አሜሪካ፣ ሕንድ እና ብራዚል ከፍተኛ ቁጥር ያስመዘገቡ አገራት ሲሆኑ በሦስቱ አገራት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሞተዋል። ባለፈው ሳምንት በዓለም ዙሪያ በየቀኑ በአማካይ 12,000 ሰዎች መሞታቸውን የኤኤፍፒ ዜና ወኪል ዘግቧል። ይህ ስለወረርሽኙ የሚወጣው አሃዝ በዓለም ዙሪያ በብዙ አገሮች ውስጥ ስላለው የበሽታው ሁኔታ ትክክለኛውን መረጃ ላያንፀባርቅ ይችላል ተብሏል። በሕንድ ምን እየተከሰተ ነው? እስከ ጥቂት ሳምንታት በፊት ድረስ ሕንድ በአንጻራዊ ሁኔታ ወረርሽኙን በቁጥጥር ስር ያዋለች ይመስል ነበር። በጥር እና በየካቲት ወራት በአብዛኛው በቀን ከ20 ሺህ በታች አዳዲስ ታማሚዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ ይህም ከ1.3 ቢሊዮን በላይ ሕዝብ ላላት አገር ዝቅተኛ ቁጥር ነው። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ሄዶ ቅዳሜ ብቻ ለሦስተኛ ተከታታይ ቀን ክብረ ወሰን የሆነ 234,000 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል። ሆስፒታሎች የአልጋና የኦክስጂን እጥረት እያጋጠማቸው ነው። የታመሙ ሰዎች ወደ ቤት እየተመለሱ ሲሆን አንዳንድ ቤተሰቦች የሚፈልጉትን መድኃኒት ለማግኘት ወደ ጥቁር ገበያ ፊታቸውን አዙረዋል። በቢቢሲ የምርመራ ዘገባ መሠረት በሕንድ ውስጥ መድኃኒት ከመደበኛው ዋጋ በአምስት እጥፍ ለገበያ እየቀረበ ነው። ባለሥልጣናት ወረርሽኙን ለመግታት በዋና ከተማዋ ደልሂ እና በሌሎች አካባቢዎች በሳምንቱ መጨረሻ ላይ የእንቅስቃሴ እገዳዎች ተጥለዋል።
በዓለም ዙሪያ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከሦስት ሚሊዮን አለፈ በዓለም ዙሪያ በኮቪድ-19 ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከሦስት ሚሊዮን ማለፉን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ገለጸ። ይህ የተገለጸው የዓለም ጤና ድርጅት "ዓለም ወደ ከፍተኛው የኢንፌክሽን መጠን እየተቃረበ ነው" መሆኑን ባስጠነቀቀ ማግስት ነው። ብዙ ሰዎች በቫይረሱ በመያዝ ሁለተኛ የሆነችው ሕንድ ዛሬ ቅዳሜ ብቻ ከ230,000 በላይ አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን አስመዝግባለች። ወረርሽኙ ከተከሰተ ወዲህ ወደ 140 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አርብ ዕለት "በበሽታው የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በአሳሳቢ ደረጃዎች እየጨመረ ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። አክለውም "ባለፉት ሁለት ወራት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሳምንት በቫይረሱ የሚያዙ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ሊጨምር ችሏል" ብለዋል። ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ እንደገለጸው አሜሪካ፣ ሕንድ እና ብራዚል ከፍተኛ ቁጥር ያስመዘገቡ አገራት ሲሆኑ በሦስቱ አገራት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሞተዋል። ባለፈው ሳምንት በዓለም ዙሪያ በየቀኑ በአማካይ 12,000 ሰዎች መሞታቸውን የኤኤፍፒ ዜና ወኪል ዘግቧል። ይህ ስለወረርሽኙ የሚወጣው አሃዝ በዓለም ዙሪያ በብዙ አገሮች ውስጥ ስላለው የበሽታው ሁኔታ ትክክለኛውን መረጃ ላያንፀባርቅ ይችላል ተብሏል። በሕንድ ምን እየተከሰተ ነው? እስከ ጥቂት ሳምንታት በፊት ድረስ ሕንድ በአንጻራዊ ሁኔታ ወረርሽኙን በቁጥጥር ስር ያዋለች ይመስል ነበር። በጥር እና በየካቲት ወራት በአብዛኛው በቀን ከ20 ሺህ በታች አዳዲስ ታማሚዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ ይህም ከ1.3 ቢሊዮን በላይ ሕዝብ ላላት አገር ዝቅተኛ ቁጥር ነው። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ሄዶ ቅዳሜ ብቻ ለሦስተኛ ተከታታይ ቀን ክብረ ወሰን የሆነ 234,000 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል። ሆስፒታሎች የአልጋና የኦክስጂን እጥረት እያጋጠማቸው ነው። የታመሙ ሰዎች ወደ ቤት እየተመለሱ ሲሆን አንዳንድ ቤተሰቦች የሚፈልጉትን መድኃኒት ለማግኘት ወደ ጥቁር ገበያ ፊታቸውን አዙረዋል። በቢቢሲ የምርመራ ዘገባ መሠረት በሕንድ ውስጥ መድኃኒት ከመደበኛው ዋጋ በአምስት እጥፍ ለገበያ እየቀረበ ነው። ባለሥልጣናት ወረርሽኙን ለመግታት በዋና ከተማዋ ደልሂ እና በሌሎች አካባቢዎች በሳምንቱ መጨረሻ ላይ የእንቅስቃሴ እገዳዎች ተጥለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56778230
0business
በአርጀንቲና ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተቃዋሚው አሸነፉ
በኢኮኖሚ ቀውስ እየተናጠች ባለችው አርጀንቲና የግራ ዘመም ተቃዋሚ ፓርቲ መሪው አልቤርቶ ፈርናንዴዝ አሸናፊ ሆነዋል። ፈርናንዴዝ ምርጫውን ያሸነፉት ለድል የሚያበቃውን ከ45 በመቶ የሚበልጥ ድምፅ በማግኘት እንደሆነ ተገልጿል። ምርጫው ሲሶው የአርጀንቲና ህዝብ በድህነት አረንቋ ውስጥ በወደቀበት ጊዜ የተካሄደ እንደመሆኑ የድምፅ ባለቤት የሆነው ህዝብ ድምፁን የሰጠው ሙሉ በሙሉ የእጩዎችን የኢኮኖሚ አማራጭ ሃሳብ በመመዘን ነው ተብሏል። • ሊዮኔል ሜሲ እየሩሳሌም አይሄድም ፈርናንዴዝ ያሸፏቸው የአርጀንቲና ፕሬዝዳንት ሙርሲዮ ማርሲ በቅድመ ምርጫ ትንበያዎችም ሽንፈታቸውን ሰምተውት ነበር። ትናንትናም መሸነፋቸውን በማመን ተቀናቃኛቸው ፈርናንዴዝን 'እንኳን ደስ ያለዎት ሰኞ ቤተ መንግሥት ይምጡና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ስለማድረግ እንነጋገር' ብለዋቸዋል። አዲሱ ፕሬዘዳንት ፈርናንዴዝም ነገሮችን ሰላማዊ ለማድረግ ከተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ጋር በማንኛውም መንገድ እንደሚተባበሩ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ከ90 በመቶ በላይ የሚሆን ድምፅ ተቆጥሮ ፈርናንዴዝ 47.79 በመቶ ድምፅ ሲያገኙ ማርሲ ደግሞ ያገኙት 40.71 በመቶ መሆኑ ተገልጿል።
በአርጀንቲና ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተቃዋሚው አሸነፉ በኢኮኖሚ ቀውስ እየተናጠች ባለችው አርጀንቲና የግራ ዘመም ተቃዋሚ ፓርቲ መሪው አልቤርቶ ፈርናንዴዝ አሸናፊ ሆነዋል። ፈርናንዴዝ ምርጫውን ያሸነፉት ለድል የሚያበቃውን ከ45 በመቶ የሚበልጥ ድምፅ በማግኘት እንደሆነ ተገልጿል። ምርጫው ሲሶው የአርጀንቲና ህዝብ በድህነት አረንቋ ውስጥ በወደቀበት ጊዜ የተካሄደ እንደመሆኑ የድምፅ ባለቤት የሆነው ህዝብ ድምፁን የሰጠው ሙሉ በሙሉ የእጩዎችን የኢኮኖሚ አማራጭ ሃሳብ በመመዘን ነው ተብሏል። • ሊዮኔል ሜሲ እየሩሳሌም አይሄድም ፈርናንዴዝ ያሸፏቸው የአርጀንቲና ፕሬዝዳንት ሙርሲዮ ማርሲ በቅድመ ምርጫ ትንበያዎችም ሽንፈታቸውን ሰምተውት ነበር። ትናንትናም መሸነፋቸውን በማመን ተቀናቃኛቸው ፈርናንዴዝን 'እንኳን ደስ ያለዎት ሰኞ ቤተ መንግሥት ይምጡና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ስለማድረግ እንነጋገር' ብለዋቸዋል። አዲሱ ፕሬዘዳንት ፈርናንዴዝም ነገሮችን ሰላማዊ ለማድረግ ከተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ጋር በማንኛውም መንገድ እንደሚተባበሩ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ከ90 በመቶ በላይ የሚሆን ድምፅ ተቆጥሮ ፈርናንዴዝ 47.79 በመቶ ድምፅ ሲያገኙ ማርሲ ደግሞ ያገኙት 40.71 በመቶ መሆኑ ተገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/50204931
2health
ኮሮናቫይረስ፡ ሙሉ ሕዝቧን እየከተበች ያለችው እስራኤል በክትባቱ ፍቱንነት ጥርጣሬ የገባት ለምንድነው?
ሕዝቧን በብዙ ቁጥር እየከተበች ያለችው እስራኤል የክትባቱን ፈዋሽነት የሚጠራጠሩ ዜጎቿ አሳስበዋታል። ተራ ዜጎች ብቻም ሳይሆኑ የጤና ባለሙያዎቿም ስለ ክትባቱ ፈዋሽነት መጠነኛ ጥርጣሬ የገባቸው ይመስላል። እስራኤል የኮቪድ ክትባትን በብዛት በመግዛት አገሯ አከማችታለች። በርካታ ሕዝቧን ክትባቱን ለመክተብ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ትገኛለች። ዝጅግት ላይ ብቻም ሳይሆን ግማሽ ሚሊዮን ሕዝቧን ክትባት እንዲደርሰው አድርጋለች። የእስራኤል ግብ ሙሉ በሙሉ ሕዝቧን መከተብና ተህዋሲውን ታሪክ ማድረግ ነው። እንዲያው አንዳንዶች ይቺ አገር እስራኤል ሕዝቧን "የቤተሙከራ አይጥ" ልታደርገው ነው ወይ? እስከማለት ደርሰዋል። ይህን ስታደርግ ታዲያ ብዙ የጤና አዋቂ ሳይንቲስቶች ዐይናቸውን በዚያች አገር ላይ ጥለዋል። ለምን? ዋናው ምክንያት በእስራኤል የሚታየው የክትባት ውጤት ለተቀረው ዓለም ብዙ ተስፋ ስለሚኖረው ነው። ሳይንቲስቶች እስራኤል ላይ ዓይናቸውን የጣሉበት አንዱ ምክንያትም ይኸው ነው። አንድ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ክትባት ሲከተብ በዚያች አገር ተህዋሲው ምን ሊሆን ይችላል የሚለው አጓጉቷቸዋል። ይህንን የክትባቱን ዘመቻ እያስተባበሩ ከሚገኙት ዋናው ሰው የፋይዘር ክትባት እንደተባለው ፍቱን ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም በሚል ጥርጣሬ እንደገባቸው በይፋ ተናግረዋል። ይህን እንዲሉ ያደረጋቸው ታዲያ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች የፋይዘር ክትባትን ከወሰዱ በኋላም ተህዋሲው ስለተገኘባቸው ነው። ጥርጣሬው መፈጠር የጀመረውም አንድም በዚህ የተነሳ ነው። ሌሎች ሳይንቲስቶች ግን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ጊዜው ገና ነው ይላሉ። እኚህ በክትባቱ ላይ ጥርጣሬን ያነሱት ፕሮፌሰር ናችማን አሽ በጤና ጥበቃ ሚኒስትር ጥርጣሪያቸው ውድቅ ተደርጎባቸዋል። "የፕሮፌሰሩ አስተያየት ከአውድ ውጭ የተነገረና ትክክል ያልሆነ ነው" ብሏል የእስራኤል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ። "በጽኑ የሚታመሙ ዜጎቻችን ቁጥር መቀነስ አለበት ብለዋል ፕሮፌሰሩ፣ ገና 2ኛው ዙር ብልቃጥ በመሰጠት ላይ ያለው አሁን ስለሆነ ይህ ውጤቱ በቀጣይነት የሚታይ እንጂ አሁን ምንም ማለት የሚቻልበት ደረጃ ላይ አይደለንም" ብሏል ይኸው መግለጫው። እርግጥ ነው ክትባቱ የራሱ ባህሪ አለው። አንድ ሰው ክትባት ከወሰደ በኋላ ሰውነቱ የተህዋሲውን ጄኔቲክ አውቆ ወራሪ ኃይል እንደመጣ ተገንዝቦ ለዚህ የሚሆን መከላከያ ለማዘጋጀት ጊዜ ይፈልጋል። አንቲቦዲና ቲ'ሴል አምርቶ ተህዋሲውን ለመጋፈጥ ጊዜ ይፈልጋል። ይህ እስኪሆን የተከተበ ሰውም ቢሆን ሊታመም ይችላል። ቢመረመር ተህዋሲው ሊገኝበት ይችላል። ይህ ሂደት ታዲያ እስከ 2 ሳምንት ሊወስድ እንደሚችል ፕሮፌሰር ዳኔ አልትማን፣ የኢምፔሪያል ኮሌጅ ለንደን ኢሚኑሎጂስት ይናገራሉ። ክላት በእስራኤል ትልቁ የጤና ሽፋን ሰጪ ድርጅት ነው። ይህ ድርጅት በቅርቡ ባወጣው መረጃ መሰረት ከተከተቡ 200 ሺህ፣ እድሜያቸው ከ60 በላይ የሆኑት ውስጥ በዚሁ እድሜ ላይ ያሉ ክትባቱን ግን ካልወሰዱ ሰዎች ጋር በማወዳደር በሰራው ጥናት በሁለት ሳምንት ውስጥ የተከተቡትም ያልተከተቡትም ላይ ተመጣጣኝ ቁጥር ያለው ሰው በተህዋሲው መያዙን ይፋ አድርጓል። ይህ ነው በፋይዘር ክትባት ላይ ጥርጣሬ እንዲነግስ ምክንያት የሆነው። ከዚያ በኋላ ቆይቶ ግን የተከተቡት ካልተከተቡት በ33 ከመቶ ባነሰ በተህዋሲው መያዛቸው እየተስተዋለ መምጣቱ ተነግሯል። "ይህ ገና ጅምር ላይ ያለ የጥናት ውጤት ነው፤ በዚህ ደረጃ ራሱ በ33 በመቶ የተህዋሲው መዛመት ቀንሷል። ስለዚህ የሚያሳስብ ነገር የለም" ብለዋል የክላት ድርጅት የጤና መኮንን ራን ባሊቸር። በፋይዘር የክሊኒክ የሙከራ ጊዜም ቢሆን ተመሳሳይ ነገር ታይቷል። ክትባቱን በወሰዱና ባልወሰዱት መሀል በተደረገ ጥናት ግልጽ ልዩነት ለማየትና የመዛመት ፍጥነት ሲቀንስ ለመታዘብ 100 ቀናት ያስፈልጋሉ ነው የሚለው መድኃኒት አምራቹ ፋይዘር። እስራኤል ዜጎቿን መከተብ የጀመረችው በታህሣሥ 19 ነበር። አሁን የሕዝቧን 10 ከመቶ ከከተበች 2 ሳምንት አልፏታል። ዛሬ ላይ ደግሞ ከ9 ሚሊዮን ሕዝቧ ውስጥ ግማሽ ሚሊዮኑ ክትባት ደርሶታል። ነገር ግን በአገሪቱ ውስጥ በተህዋሲው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነስ በጉልህ አልታየም። ለምን? ክትባት የወሰደ ሰው የመከላከል አቅም ለማዳበር ከሚወስድበት ጊዜ አንጻር ቢያንስ ለአንድ ወራት ያህል ክትባቱ ያመጣውን ለውጥ ለማወቅ ከባድ ይሆናል ተብሏል። ፕሮፌሰር ባሊቸር ግን በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ወደ ጽኑ ሕሙማን የሚሄዱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣት አለበት ይላሉ። ፋይዘር መድኃኒት አምራች ሁለት ጠብታ ክትባቱን የወሰደ ሰው 95% በተህዋሲው ያለመያዝ እድሉ የሰፋ ነው ይላል። ነገር ግን በብዙ ክትባቶች እንደታየው ከዚህ ያነሰ መቶኛ እንኳ የፈውስ እድል ብዙ ለውጥ ያመጣል። አመታዊው የፍሉ ክትባት ለምሳሌ ፈዋሽነቱ ከ40-60% ብቻ ነው። ሆኖም በየዓመቱ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን ከሞት ይታደጋል። አንዱ አሁን እያነጋገረ ያለው አንድ ጠብታ የወሰዱ ዜጎችን ሁለተኛውን ጠብታ እየሰጡ ቀስ በቀስ ሕዝቡን ማዳረስ ነው ወይስ አንዱን ጠብታ ለሰፊው ሕዝብ ካዳረሱ በኋላ ለ2ኛው ዙር እንደገና መጀመር ይሻላል የሚለው ነው። ታላቋ ብሪታኒያ እንዳመነችው ብዙ ሰዎችን የመጀመርያውን ጠብታ ካዳረሱ በኋላ ለ2ኛው መመለስ ይሻላል የሚል ነው። በዚህ ዘዴ በተህዋሲው የሚጋለጡ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ ይቻላል ብላ አምናለች። ትንሽ ቁጥር ያለውን ሕዝብ 2 ጠብታ ሰጥቶ ትንሽ ቁጥር ያለውን ሕዝብ ከተህዋሲው በደንብ መከላከል የተሻለ ነው የሚሉም አሉ። ጠብታው መሰጠት ያለበት በ2 ሳምንት ልዩነት መሆኑም ሌላው ፈተና ነው። ምክንያቱም አንድ ሰው አንድ ጠብታ ከወሰደ በኋላ ሌላ ሁለት ሳምንት መጠበቅ ተህዋሲው ከጋረጠው ፈተና አንጻር ትእግስትን የሚፈታተን በመሆኑ ነው። ፕሮፌሰር ኢቫንስ ማጠቃለያ ሐሳብ ሲሰጡ ይህን ይላሉ፡ "ከእስራኤል አሁን የሚመጡ ሪፖርቶች ያልተሟሉ ብቻ ሳይሆን መረጃን የሚሰጡ፥ እንዲሁም አጥጋቢ ሆነው አላገኘናቸውም። በታላቋ ብሪታኒያ ሁለተኛውን ጠብታ አዘግይቶ የመጀመርያውን ጠብታ ማዳረስ የሚለውን አሰራር ሊያስቀይር የሚችል ነገርም አላገኘንባቸውም" ዞሮ ዞሮ በቀጣይ ወራት በእስራኤል ተህዋሲው ድራሹ እየጠፋ ካልመጣ ዓለም መደንገጡ አይቀርም።
ኮሮናቫይረስ፡ ሙሉ ሕዝቧን እየከተበች ያለችው እስራኤል በክትባቱ ፍቱንነት ጥርጣሬ የገባት ለምንድነው? ሕዝቧን በብዙ ቁጥር እየከተበች ያለችው እስራኤል የክትባቱን ፈዋሽነት የሚጠራጠሩ ዜጎቿ አሳስበዋታል። ተራ ዜጎች ብቻም ሳይሆኑ የጤና ባለሙያዎቿም ስለ ክትባቱ ፈዋሽነት መጠነኛ ጥርጣሬ የገባቸው ይመስላል። እስራኤል የኮቪድ ክትባትን በብዛት በመግዛት አገሯ አከማችታለች። በርካታ ሕዝቧን ክትባቱን ለመክተብ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ትገኛለች። ዝጅግት ላይ ብቻም ሳይሆን ግማሽ ሚሊዮን ሕዝቧን ክትባት እንዲደርሰው አድርጋለች። የእስራኤል ግብ ሙሉ በሙሉ ሕዝቧን መከተብና ተህዋሲውን ታሪክ ማድረግ ነው። እንዲያው አንዳንዶች ይቺ አገር እስራኤል ሕዝቧን "የቤተሙከራ አይጥ" ልታደርገው ነው ወይ? እስከማለት ደርሰዋል። ይህን ስታደርግ ታዲያ ብዙ የጤና አዋቂ ሳይንቲስቶች ዐይናቸውን በዚያች አገር ላይ ጥለዋል። ለምን? ዋናው ምክንያት በእስራኤል የሚታየው የክትባት ውጤት ለተቀረው ዓለም ብዙ ተስፋ ስለሚኖረው ነው። ሳይንቲስቶች እስራኤል ላይ ዓይናቸውን የጣሉበት አንዱ ምክንያትም ይኸው ነው። አንድ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ክትባት ሲከተብ በዚያች አገር ተህዋሲው ምን ሊሆን ይችላል የሚለው አጓጉቷቸዋል። ይህንን የክትባቱን ዘመቻ እያስተባበሩ ከሚገኙት ዋናው ሰው የፋይዘር ክትባት እንደተባለው ፍቱን ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም በሚል ጥርጣሬ እንደገባቸው በይፋ ተናግረዋል። ይህን እንዲሉ ያደረጋቸው ታዲያ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች የፋይዘር ክትባትን ከወሰዱ በኋላም ተህዋሲው ስለተገኘባቸው ነው። ጥርጣሬው መፈጠር የጀመረውም አንድም በዚህ የተነሳ ነው። ሌሎች ሳይንቲስቶች ግን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ጊዜው ገና ነው ይላሉ። እኚህ በክትባቱ ላይ ጥርጣሬን ያነሱት ፕሮፌሰር ናችማን አሽ በጤና ጥበቃ ሚኒስትር ጥርጣሪያቸው ውድቅ ተደርጎባቸዋል። "የፕሮፌሰሩ አስተያየት ከአውድ ውጭ የተነገረና ትክክል ያልሆነ ነው" ብሏል የእስራኤል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ። "በጽኑ የሚታመሙ ዜጎቻችን ቁጥር መቀነስ አለበት ብለዋል ፕሮፌሰሩ፣ ገና 2ኛው ዙር ብልቃጥ በመሰጠት ላይ ያለው አሁን ስለሆነ ይህ ውጤቱ በቀጣይነት የሚታይ እንጂ አሁን ምንም ማለት የሚቻልበት ደረጃ ላይ አይደለንም" ብሏል ይኸው መግለጫው። እርግጥ ነው ክትባቱ የራሱ ባህሪ አለው። አንድ ሰው ክትባት ከወሰደ በኋላ ሰውነቱ የተህዋሲውን ጄኔቲክ አውቆ ወራሪ ኃይል እንደመጣ ተገንዝቦ ለዚህ የሚሆን መከላከያ ለማዘጋጀት ጊዜ ይፈልጋል። አንቲቦዲና ቲ'ሴል አምርቶ ተህዋሲውን ለመጋፈጥ ጊዜ ይፈልጋል። ይህ እስኪሆን የተከተበ ሰውም ቢሆን ሊታመም ይችላል። ቢመረመር ተህዋሲው ሊገኝበት ይችላል። ይህ ሂደት ታዲያ እስከ 2 ሳምንት ሊወስድ እንደሚችል ፕሮፌሰር ዳኔ አልትማን፣ የኢምፔሪያል ኮሌጅ ለንደን ኢሚኑሎጂስት ይናገራሉ። ክላት በእስራኤል ትልቁ የጤና ሽፋን ሰጪ ድርጅት ነው። ይህ ድርጅት በቅርቡ ባወጣው መረጃ መሰረት ከተከተቡ 200 ሺህ፣ እድሜያቸው ከ60 በላይ የሆኑት ውስጥ በዚሁ እድሜ ላይ ያሉ ክትባቱን ግን ካልወሰዱ ሰዎች ጋር በማወዳደር በሰራው ጥናት በሁለት ሳምንት ውስጥ የተከተቡትም ያልተከተቡትም ላይ ተመጣጣኝ ቁጥር ያለው ሰው በተህዋሲው መያዙን ይፋ አድርጓል። ይህ ነው በፋይዘር ክትባት ላይ ጥርጣሬ እንዲነግስ ምክንያት የሆነው። ከዚያ በኋላ ቆይቶ ግን የተከተቡት ካልተከተቡት በ33 ከመቶ ባነሰ በተህዋሲው መያዛቸው እየተስተዋለ መምጣቱ ተነግሯል። "ይህ ገና ጅምር ላይ ያለ የጥናት ውጤት ነው፤ በዚህ ደረጃ ራሱ በ33 በመቶ የተህዋሲው መዛመት ቀንሷል። ስለዚህ የሚያሳስብ ነገር የለም" ብለዋል የክላት ድርጅት የጤና መኮንን ራን ባሊቸር። በፋይዘር የክሊኒክ የሙከራ ጊዜም ቢሆን ተመሳሳይ ነገር ታይቷል። ክትባቱን በወሰዱና ባልወሰዱት መሀል በተደረገ ጥናት ግልጽ ልዩነት ለማየትና የመዛመት ፍጥነት ሲቀንስ ለመታዘብ 100 ቀናት ያስፈልጋሉ ነው የሚለው መድኃኒት አምራቹ ፋይዘር። እስራኤል ዜጎቿን መከተብ የጀመረችው በታህሣሥ 19 ነበር። አሁን የሕዝቧን 10 ከመቶ ከከተበች 2 ሳምንት አልፏታል። ዛሬ ላይ ደግሞ ከ9 ሚሊዮን ሕዝቧ ውስጥ ግማሽ ሚሊዮኑ ክትባት ደርሶታል። ነገር ግን በአገሪቱ ውስጥ በተህዋሲው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነስ በጉልህ አልታየም። ለምን? ክትባት የወሰደ ሰው የመከላከል አቅም ለማዳበር ከሚወስድበት ጊዜ አንጻር ቢያንስ ለአንድ ወራት ያህል ክትባቱ ያመጣውን ለውጥ ለማወቅ ከባድ ይሆናል ተብሏል። ፕሮፌሰር ባሊቸር ግን በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ወደ ጽኑ ሕሙማን የሚሄዱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣት አለበት ይላሉ። ፋይዘር መድኃኒት አምራች ሁለት ጠብታ ክትባቱን የወሰደ ሰው 95% በተህዋሲው ያለመያዝ እድሉ የሰፋ ነው ይላል። ነገር ግን በብዙ ክትባቶች እንደታየው ከዚህ ያነሰ መቶኛ እንኳ የፈውስ እድል ብዙ ለውጥ ያመጣል። አመታዊው የፍሉ ክትባት ለምሳሌ ፈዋሽነቱ ከ40-60% ብቻ ነው። ሆኖም በየዓመቱ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን ከሞት ይታደጋል። አንዱ አሁን እያነጋገረ ያለው አንድ ጠብታ የወሰዱ ዜጎችን ሁለተኛውን ጠብታ እየሰጡ ቀስ በቀስ ሕዝቡን ማዳረስ ነው ወይስ አንዱን ጠብታ ለሰፊው ሕዝብ ካዳረሱ በኋላ ለ2ኛው ዙር እንደገና መጀመር ይሻላል የሚለው ነው። ታላቋ ብሪታኒያ እንዳመነችው ብዙ ሰዎችን የመጀመርያውን ጠብታ ካዳረሱ በኋላ ለ2ኛው መመለስ ይሻላል የሚል ነው። በዚህ ዘዴ በተህዋሲው የሚጋለጡ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ ይቻላል ብላ አምናለች። ትንሽ ቁጥር ያለውን ሕዝብ 2 ጠብታ ሰጥቶ ትንሽ ቁጥር ያለውን ሕዝብ ከተህዋሲው በደንብ መከላከል የተሻለ ነው የሚሉም አሉ። ጠብታው መሰጠት ያለበት በ2 ሳምንት ልዩነት መሆኑም ሌላው ፈተና ነው። ምክንያቱም አንድ ሰው አንድ ጠብታ ከወሰደ በኋላ ሌላ ሁለት ሳምንት መጠበቅ ተህዋሲው ከጋረጠው ፈተና አንጻር ትእግስትን የሚፈታተን በመሆኑ ነው። ፕሮፌሰር ኢቫንስ ማጠቃለያ ሐሳብ ሲሰጡ ይህን ይላሉ፡ "ከእስራኤል አሁን የሚመጡ ሪፖርቶች ያልተሟሉ ብቻ ሳይሆን መረጃን የሚሰጡ፥ እንዲሁም አጥጋቢ ሆነው አላገኘናቸውም። በታላቋ ብሪታኒያ ሁለተኛውን ጠብታ አዘግይቶ የመጀመርያውን ጠብታ ማዳረስ የሚለውን አሰራር ሊያስቀይር የሚችል ነገርም አላገኘንባቸውም" ዞሮ ዞሮ በቀጣይ ወራት በእስራኤል ተህዋሲው ድራሹ እየጠፋ ካልመጣ ዓለም መደንገጡ አይቀርም።
https://www.bbc.com/amharic/news-55745103
5sports
ኡጋንዳ ውስጥ በማንችስተር 'ደርቢ' ምክንያት አንድ ታዳጊ ተገደለ
ኡጋንዳ ውስጥ የማንችስተር ከተማ ክለቦች እግር ኳስ ጨዋታ ይተላለፍ አይተላለፍ በሚል የተነሳውን ግርግር ለማብረድ የመጣ ፖሊስ አንድ ታዳጊ ገደለ። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በማንችስተር ሲቲና በማንችስተር ዩናይትድ መካከል የነበረውን ፍልሚያ ትምህርት ቤታቸው አላሳይም በማለቱ ወደ ቅጥር ግቢው ድንጋይ ወርውረዋል። የ19 ዓመቱ ታዳጊ ከግርግሩ ለመሸሽ በሚል አንድ ዛፍ ላይ ሳለ ነበር በጥይት ተመቶ የወደቀው ሲሉ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ለቢቢሲ ተናግረዋል። 1 ሺህ ገደማ ተማሪዎች ያሉት ትምህርት ቤቱ በግድያው ምክንያት ለሁለት ሳምንት በመዘጋቱ ወደ ቤታቸው ተሸኝተዋል። የጉሉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር አዋኒ ጂሚ በሁኔታው እጅግ እንደተበሳጩ ለቢቢሲ ገልጠዋል። ዳይሬክተሩ እንዳሉት በፖሊስ ጥይት የተገደለው ታዳጊ ከሌላ ትምህርት ቤት ተዘዋውሮ ከመጣ ስድስት ሳምንት ቢሆነው ነው። ዳይሬክተሩ ታዳጊውን "ጨዋ፣ ትሁትና ጠንካራ ተማሪ" ሲሉ ገልፀውታል። አዋኒ ክስተቱን ሲያስረዱ እሑድ ዕለት የነበረው የማንችስተር 'ደርቢ' ከተማሪዎች የጥናት ክፍለ ጊዜ ጋር በመጋጨቱ ነው ጨዋታው እንዳይታይ የተከለከለው። ዳይሬክተሩ አክለው ትምህርት ቤቱ ለወትሮው ቀደም ብለው የሚጀምሩ ጨዋታዎች በተለይ ደግሞ በሃገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት ከ8-10 ሰዓት ያሉ ጨዋታዎችን ለተማሪዎች ያሳያል። ይህ የሚሆነው ተማሪዎች ምሽት 1፡30 የጥናት ፕሮግራም ስላላቸው ነው። ነገር ግን እሑድ ዕለት የማንችስተር ደርቢ ከሚያመልጠን ጥናት ይቅርብን ያሉ ተማሪዎች ግርግር በማስነሳታቸው የትምህርት ቤቱ ጥበቃዎች ሁኔታውን ለማረጋጋት ጣልቃ ይገባሉ። ሁኔታዎች እየጋለ የመጣው አንድ የአካባቢው ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ ከተኮሰ በኋላ ስልክ ደውል ከወታደራዊው ኃይል እርዳታ ከጠየቀ በኋላ ነው። "የፀጥታ ኃይሎች የወሰዱት እርምጃ ከተገቢው በላይ ነው ብዬ ነው የማስበው" ይላሉ ዳይሬክተሩ። አዋኒ ጂሚ እንደሚሉት ትምህርት ቤቱ ከተመሠረተ ጀምሮ ባሉት 30 ዓመታት እንዲህ ዓይነት ነገር አጋጥሞት አያውቅም። የጉሉ ከተማ አስተዳደር ከትምህርት ቤቱ ጋር ከመከረ በኋላ ለሁለት ሳምንት እንዲዘጋና ተማሪዎች ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ ወስኗል።
ኡጋንዳ ውስጥ በማንችስተር 'ደርቢ' ምክንያት አንድ ታዳጊ ተገደለ ኡጋንዳ ውስጥ የማንችስተር ከተማ ክለቦች እግር ኳስ ጨዋታ ይተላለፍ አይተላለፍ በሚል የተነሳውን ግርግር ለማብረድ የመጣ ፖሊስ አንድ ታዳጊ ገደለ። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በማንችስተር ሲቲና በማንችስተር ዩናይትድ መካከል የነበረውን ፍልሚያ ትምህርት ቤታቸው አላሳይም በማለቱ ወደ ቅጥር ግቢው ድንጋይ ወርውረዋል። የ19 ዓመቱ ታዳጊ ከግርግሩ ለመሸሽ በሚል አንድ ዛፍ ላይ ሳለ ነበር በጥይት ተመቶ የወደቀው ሲሉ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ለቢቢሲ ተናግረዋል። 1 ሺህ ገደማ ተማሪዎች ያሉት ትምህርት ቤቱ በግድያው ምክንያት ለሁለት ሳምንት በመዘጋቱ ወደ ቤታቸው ተሸኝተዋል። የጉሉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር አዋኒ ጂሚ በሁኔታው እጅግ እንደተበሳጩ ለቢቢሲ ገልጠዋል። ዳይሬክተሩ እንዳሉት በፖሊስ ጥይት የተገደለው ታዳጊ ከሌላ ትምህርት ቤት ተዘዋውሮ ከመጣ ስድስት ሳምንት ቢሆነው ነው። ዳይሬክተሩ ታዳጊውን "ጨዋ፣ ትሁትና ጠንካራ ተማሪ" ሲሉ ገልፀውታል። አዋኒ ክስተቱን ሲያስረዱ እሑድ ዕለት የነበረው የማንችስተር 'ደርቢ' ከተማሪዎች የጥናት ክፍለ ጊዜ ጋር በመጋጨቱ ነው ጨዋታው እንዳይታይ የተከለከለው። ዳይሬክተሩ አክለው ትምህርት ቤቱ ለወትሮው ቀደም ብለው የሚጀምሩ ጨዋታዎች በተለይ ደግሞ በሃገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት ከ8-10 ሰዓት ያሉ ጨዋታዎችን ለተማሪዎች ያሳያል። ይህ የሚሆነው ተማሪዎች ምሽት 1፡30 የጥናት ፕሮግራም ስላላቸው ነው። ነገር ግን እሑድ ዕለት የማንችስተር ደርቢ ከሚያመልጠን ጥናት ይቅርብን ያሉ ተማሪዎች ግርግር በማስነሳታቸው የትምህርት ቤቱ ጥበቃዎች ሁኔታውን ለማረጋጋት ጣልቃ ይገባሉ። ሁኔታዎች እየጋለ የመጣው አንድ የአካባቢው ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ ከተኮሰ በኋላ ስልክ ደውል ከወታደራዊው ኃይል እርዳታ ከጠየቀ በኋላ ነው። "የፀጥታ ኃይሎች የወሰዱት እርምጃ ከተገቢው በላይ ነው ብዬ ነው የማስበው" ይላሉ ዳይሬክተሩ። አዋኒ ጂሚ እንደሚሉት ትምህርት ቤቱ ከተመሠረተ ጀምሮ ባሉት 30 ዓመታት እንዲህ ዓይነት ነገር አጋጥሞት አያውቅም። የጉሉ ከተማ አስተዳደር ከትምህርት ቤቱ ጋር ከመከረ በኋላ ለሁለት ሳምንት እንዲዘጋና ተማሪዎች ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ ወስኗል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60657877
3politics
የቻይናው ፕሬዚዳንት አገራቸው በወዳጅነት ላይ የተመሰረተ ዲፕሎማሲ እንድትከተል ጥሪ አቀረቡ
የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ አገራቸው ወዳጆቿን ማብዛት እንደምትፈልግ አስታውቀዋል። ለዚህም አገራቸው የገፅታ ግንባታ ያስፈልጋታል ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ ከኮሙኒስት ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በነበራቸው ቆይታ አገራቸው "ታማኝ፣ ተወዳጅና ክብር ያላትን የቻይናን ገፅታ መፍጠር አስፈላጊ ነው ማለታቸውን የአገሪቱ የዜና ወኪል ሺኑዋ ዘግቧል። ቻይና ከምዕራባውያኑ ጋር ያላት ግንኙነት ከአመት አመት ወደ ባላንጣነት እንደተሸጋገረ የሚናገሩት ተንታኞች ቻይና ይህንን ማለቷ መሰረታዊ በሆነ መልኩ ዲፕሎማሲያዋን ልትቀይር መሆኑ አመላካች ነው። ቻይና በተለይም እንደ አሜሪካ ጋር ካሉ ታላላቅ ኃያላን አገራት ጋር የሻከረ ግንኙነት ነው ያላት። በአገሪቷ ባሉ ሙስሊም ህዝቦች ላይ በምታደርሰው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትና በሆንግ ኮንግ የዲሞክራሲ ደጋፊዎች በምታደርሰው እስሮችና እንግልቶች እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ቻይና ከፍተኛ ውግዘቶችን አስተናግዳለች። በቅርቡም አሜሪካ የኮቪድ-19 መነሻ የቻይና ቤተ ሙከራዎች ነው በሚለው ጉዳይ ላይ ምርመራ አደርጋለሁ ማለቷን ተከትሎ ቻይና በበኩሏ "የራሳቸውን ጥፋት ለመደበቅና ፖለቲካዊ ማጭበርበር" ነው በሚል አፀፋዊ ምላሽ ሰጥታለች። ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ ሰኞ እለት ከባለስልጣኖቻቸው ጋር በመከሩበት ወቅት ቻይና ታሪኳን በአዎንታዊ መልኩ ልትናገር ይገባል ብለዋል። "አጋሮችና ወዳኞች ማፍራት አስፈላጊ ነው።በአለም አቀፉ ዘንድ ያለውን ዋነኛ የህዝብ አስተያየትን ለማስቀየር የወዳጆቻችንን ቁጥር መጨመር አስፈላጊ ነው" ማለታቸውንም ሺኑዋ ዘግቧል። አክለውም አገራቸው ከአለም ጋር በምታደርገው ግንኙነት "ግልፅና በራሷ የምትተማመን እንዲሁም ራሷን ከፍ የማታደርግ" ሆና መታየት እንዳለባት አስረድተዋል። ፖርቲው በሚሰራቸው የፕሮፖጋንዳ ስራዎችም መንግሥታቸው "ለቻይና ህዝብ ደስታና ብልፅግና የሚሰራ ነው" የሚለውን አፅንኦት መስጠት ይገባቸዋል ብለዋል። የፕሬዚዳንቱን ንግግር ያጤኑ ተንታኞች መሪው ለመጀመሪያ ጊዜ የቻይናን መገለልና ብቸኝነት ያመኑበት ነው ብለዋል። ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ የቻይና ፕሬዚዳንትነትን ስልጣን የጨበጡት በአውሮፓውያኑ 2012 ሲሆን በቁርጠኝነትና በጨቋኝነት ይተቻሉ። በአገሪቱ ላይ ለሚሰነዘሩ ማንኛውም አይነት ተቃውሞዎች የአገሪቱ ዲፕሎማቶች ምላሽ ማጣጣል ወይም ደግሞ በጠብ አጫሪነት ነበር።
የቻይናው ፕሬዚዳንት አገራቸው በወዳጅነት ላይ የተመሰረተ ዲፕሎማሲ እንድትከተል ጥሪ አቀረቡ የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ አገራቸው ወዳጆቿን ማብዛት እንደምትፈልግ አስታውቀዋል። ለዚህም አገራቸው የገፅታ ግንባታ ያስፈልጋታል ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ ከኮሙኒስት ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በነበራቸው ቆይታ አገራቸው "ታማኝ፣ ተወዳጅና ክብር ያላትን የቻይናን ገፅታ መፍጠር አስፈላጊ ነው ማለታቸውን የአገሪቱ የዜና ወኪል ሺኑዋ ዘግቧል። ቻይና ከምዕራባውያኑ ጋር ያላት ግንኙነት ከአመት አመት ወደ ባላንጣነት እንደተሸጋገረ የሚናገሩት ተንታኞች ቻይና ይህንን ማለቷ መሰረታዊ በሆነ መልኩ ዲፕሎማሲያዋን ልትቀይር መሆኑ አመላካች ነው። ቻይና በተለይም እንደ አሜሪካ ጋር ካሉ ታላላቅ ኃያላን አገራት ጋር የሻከረ ግንኙነት ነው ያላት። በአገሪቷ ባሉ ሙስሊም ህዝቦች ላይ በምታደርሰው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትና በሆንግ ኮንግ የዲሞክራሲ ደጋፊዎች በምታደርሰው እስሮችና እንግልቶች እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ቻይና ከፍተኛ ውግዘቶችን አስተናግዳለች። በቅርቡም አሜሪካ የኮቪድ-19 መነሻ የቻይና ቤተ ሙከራዎች ነው በሚለው ጉዳይ ላይ ምርመራ አደርጋለሁ ማለቷን ተከትሎ ቻይና በበኩሏ "የራሳቸውን ጥፋት ለመደበቅና ፖለቲካዊ ማጭበርበር" ነው በሚል አፀፋዊ ምላሽ ሰጥታለች። ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ ሰኞ እለት ከባለስልጣኖቻቸው ጋር በመከሩበት ወቅት ቻይና ታሪኳን በአዎንታዊ መልኩ ልትናገር ይገባል ብለዋል። "አጋሮችና ወዳኞች ማፍራት አስፈላጊ ነው።በአለም አቀፉ ዘንድ ያለውን ዋነኛ የህዝብ አስተያየትን ለማስቀየር የወዳጆቻችንን ቁጥር መጨመር አስፈላጊ ነው" ማለታቸውንም ሺኑዋ ዘግቧል። አክለውም አገራቸው ከአለም ጋር በምታደርገው ግንኙነት "ግልፅና በራሷ የምትተማመን እንዲሁም ራሷን ከፍ የማታደርግ" ሆና መታየት እንዳለባት አስረድተዋል። ፖርቲው በሚሰራቸው የፕሮፖጋንዳ ስራዎችም መንግሥታቸው "ለቻይና ህዝብ ደስታና ብልፅግና የሚሰራ ነው" የሚለውን አፅንኦት መስጠት ይገባቸዋል ብለዋል። የፕሬዚዳንቱን ንግግር ያጤኑ ተንታኞች መሪው ለመጀመሪያ ጊዜ የቻይናን መገለልና ብቸኝነት ያመኑበት ነው ብለዋል። ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ የቻይና ፕሬዚዳንትነትን ስልጣን የጨበጡት በአውሮፓውያኑ 2012 ሲሆን በቁርጠኝነትና በጨቋኝነት ይተቻሉ። በአገሪቱ ላይ ለሚሰነዘሩ ማንኛውም አይነት ተቃውሞዎች የአገሪቱ ዲፕሎማቶች ምላሽ ማጣጣል ወይም ደግሞ በጠብ አጫሪነት ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/news-57333182
0business
ኢኮኖሚ ፡ የኢትዮጵያ የብር ኖት መቀየር የሚኖረው አንድምታ
ኢትዮጵያ ከሁለት አስር ዓመታት በላይ ስትገለገልባቸው የነበሩ የ10፣ የ50፣ እናየ100 የገንዘብ ዓይነቶችን ሙሉ ለሙሉ ለመተካት አዲስ የገንዘብ ኖቶች ይፋ አድርጋለች። ከአዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች ውስጥም በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜም የባለ ሁለት መቶ ብር ኖትም አሳትማለች። አገሪቷ ነባሮቹን የብር ኖቶቹን ለመቀየር ሌላ ወጪ ሳይጨምር ለህትመት ብቻ 3.7 ቢሊዮን ብር ማውጣቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አስታውቀዋል። አገሪቱ የገንዘብ ኖቶችን ለመቀየር በኢ-መደበኛ መልኩ ገንዘብ ከባንክ ውጭ በከፍተኛ ሁኔታ መንቀሳቀሱ፣ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የሚሉ ምክንያቶችን አስቀምጣለች። ከዚህ ቀደም አገሪቷ ከፋይናንስ ዘርፍ (ከባንክ) ውጭ ያለው ገንዘብ ከመደበኛው ባልተናነሰ መልኩ ከፍተኛ በመሆኑም እንዴት ይሰብሰብ የሚሉ ጥያቄዎች የባንኮች ዋና ማዕከል ሆነውም ነበር። በኢ-መደበኛ ሁኔታ ያለውን የገንዘብ ፍሰት ወደ መደበኛ ለማምጣትም ጥረቶች የተደረጉ ሲሆን በተለያየ ጊዜም የወጡ መመሪያዎችም ለዚህ ማመላከቻዎች ናቸው። በኢትዮጵያ ከባንክ ውጭ ያለው ገንዘብ በቢሊዮኖች እንደሚቆጠር ከዚህ ቀደም በፋይናንስ ዘርፉ የተሰራ ጥናት የሚያሳይ ሲሆን በባለፈው ዓመትም አገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የጥሬ ገንዘብ እጥረት (ሊኩዊዲቲ) አጋጥሟት ነበር። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክም ይህንንም ችግር ለመፍታት አንዳንድ ጊዜያዊ መፍትሄዎችን መውሰዱ የሚታወስ ነው። የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የዋጋ ግሽበት የለውጡ ዋነኛ መሰናክል ሆነው ቆይተዋል በማለትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምጣኔ ሀብቱ መዳከም ምክንያት ያሉትን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት የገንዘብ ኖት ለውጥ ማድረጓም በከፍተኛ ሁኔታ ከዘርፉ ውጭ ያለውን ገንዘብ ወደ መደበኛ የገንዘብ እንቅስቃሴ ሂደት ለማምጣትም ይረዳታል በማለት የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። የብሔራዊ ባንክ ገዢው ዶ/ር ይናገር ደሴ በበኩላቸው መንግሥት የገንዘብ ለውጥ ማድረግ ካስፈለገው ምክንያቶች መካከል ዋነኛው ከገንዘብ ጋር የተገናኙ ሕገ-ወጥ ዝውውሮችን ለመግታት እንደሆነ በብሔራዊው ቴሌቪዥን ቀርበው አስረድተዋል። የአገሪቱ ኢኮኖሚ በብዛት በጥሬ ገንዘብ ግብይት የሚካሄድበት መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ይናገር ከባንኮች ውጭ ያለው ጥሬ ገንዘብ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል። "አብዛኛው ኅብረተሰባችን ከባንክ ውጭ ነው ግብይት የሚያደርገው በዚህ ምክንያት ብዙ ጥሬ ገንዘብ ከባንክ ውጭ ይገኛል ማለት ነው። በዚህም የጥሬ ገንዘብ እጥረት ባንኮች ላይ ማጋጠም እድሉ ሰፊ ነው።ለ ገቢ አሰባሰብ አመቺ ሁኔታ ይፈጥራል የሚል እምነት ነው ያለን፤ ለአጠቃቀም የተሻለ አገልግሎት ይሰጣል፤ የህትመት ወጪንም በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል" ብለዋል። ከባንክ ውጭ ያለው ጥሬ ገንዘብ በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት አገራት ጭምር በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። "ከባንክ ውጭ የሚገኝ ገንዘብ ደግሞ ለሕገ-ወጥ ተግባራት ሲውል ነው የሚታየው፤ በተለይ በኮንትሮባንድ [ሕገ-ወጥ ንግድ] የተሰማሩ ግለሰቦች ይጠቀሙበታል" ብለዋል። ዶ/ር ይናገር ከዚህ በተጨማሪ ግለሰቦች ግብር ላለመክፈል ሲሉ ገንዘባቸውን ከባንክ ውጭ የማስቀመጥ ልማድም እየሰፋ መምጣቱን ጠቁመው አሁን ያለውን የገንዘብ ኖት መቀየር አስፈላጊ መሆኑ እንደታመነበት አስረድተዋል። ከባንክ ውጭ የተጠራቀመ ገንዘብ ጥቅም የለውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ በኋላም በአውሮፕላን ጣቢያዎችና ድንበሮች እንዲሁም በባንኮች አካባቢ ከፍተኛ ቁጥጥርም ይደረጋል ተብሏል። የፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ ገንዝብ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር ከማድረግ በተጨማሪ በሕገ ወጥ መንገድ የሚሰበሰብ ገንዘብ ካገኙ እንደሚወርሱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ከባንኮች ውጭ ያለው ገንዘብ ወደ ባንኮች ሲመለስም የሂሳብ ደብተር ተከፍቶ ባንኮች ውስጥ እንዲቀመጥ ይደረጋል። ለመሆኑ የብር ኖትን መቀየር እንደ ኮንትሮባንድ እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እንዴት ሊያስቆም ይችላል? የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ከባንክ ሥርዓት ውጭ የሚንቀሳቀስ ከ113 ቢሊየን ብር በላይ መኖሩን ይናገራሉ። ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች ያሉት ሲሆን የዋጋ ንረት ከፍተኛ በመሆኑና ባንክ ቤቶች ብር ለሚያስቀምጥ የሚሰጡት ወለድ ዝቅተኛ በመሆኑ ሰዎች ገንዘቤን በእጄ እይዛለሁ የሚል አስተሳሰብ መኖሩን እንደ አንድ ምክንያት ያነሳሉ። በሌላ በኩል በሙስናና በሌሎች ምክንያቶች "ተቋማትም ግለሰቦችም ሲዘርፉ ስለነበር ነው" ይላሉ። ለዚህ ንግግራቸውም ከለውጡ በኋላ የተከማቹ በርካታ ገንዘቦች በጆንያ እየታጨቁ እና በመኪና እየተጫኑ ሲዘዋወሩ መያዛቸውን እንደ ምሳሌም ይጠቅሳሉ። የገንዘብ ኖቶቹ ላይ ለውጥ መደረጉም ሰዎች ገንዘባቸውን ለመቀየር ባንክ በሚሄዱበት ጊዜ፤ በጤናማ የግብይት ሥርዓት ገንዘቡን ማግኘት አለማግኘታቸውን ለማረጋገጥ እድል ይሰጣል ብለዋል ባለሙያው። በመሆኑም እስካሁን የተሰሩ የሙስና ምንጮችን ለማወቅም ሆነ ከአሁን በኋላ የሚሰሩ ሙስናዎች ላይ ፍራቻ እንዲፈጥር ሊያደርግ እንደሚችልም ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምጣኔ ሀብት መምህር የሆኑት ረዳት ፐሮፌሰር ጉቱ ለገስ ደግሞ ከገንዘብ ጋር ተያይዞ ያሉ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የብር ኖቶች መቀየር አንዱ እንጂ፤ ብቸኛው መፍትሔ አለመሆኑን ያሰምሩበታል። ረዳት ፕሮፌሰር ጉቱ "አንድ ነገር ሲተዋወቅ ውጤታማ ለመሆን አለመሆኑ አንዱ ወሳኙ ነገር፤ ተቋማዊ አደረጃጃትና የመተግበር አቅም ነው። ይህ ካልሆነ ግን አዙሪት ነው የሚሆነው" ብለዋል። መንግሥት ገንዘቡን ከቀየረ በኋላ ሕገ-ወጥ ገንዘብ ይዘዋል ተብለው የሚጠረጠሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች የየራሳቸውን እርምጃ መውሰዳቸው እንደማይቀር የጠቆሙት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ መንግሥት ተቋማዊ አደረጃጀቱ ጠንካራ ሆኖ ይሄን ነገር ልብ ብሎ መከታተል እንዳለበት መክረዋል። አሁን የተወሰደው እርምጃ ቀደም ብለው የተሰሩ ሥራዎች ስላሉ ውጤታማ ይሆናል ተብሎ ይገመታልም ብለዋል። ነገር ግን "ቀድሞ የነበረው የውጭ ምንዛሬ ጋር ተያይዞ ያለው ሙስናና ደካማ አስተዳደር ካልተስተካከለ ተመልሶ ያው ነው የሚሆነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። አዲስ የ200 ብር ኖት ማስገባት ለምን ተፈለገ? በኢትዮጵያ በቅርብ አመታት ውስጥ የገንዘብ የመግዛት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ያሽቆለቆለ ሲሆን ከዚህም አንፃር ባለ ሁለት መቶ ኖቶች ወደ ገበያው ውስጥ መግባት አስፈላጊ እንደሆነም የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይናገራሉ። ረዳት ፕሮፌሰር ጉቱ የዋጋ ንረቱ በጣም ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ በተለያየ ግብይት ሂደት ውስጥ የሚሳተፈው ኅብረተሰብ ብዙ ብር ለመያዝ እየተገደደ መሆኑን በመጥቀስ ያንን ሊያስቀርላቸው እንደሚችል ይናገራሉ። ይሁን እንጂ ወደ ኤሌክትሮኒክስ የግብይት ሥርዓት እንዲገቡም እየተሰራ ያለው ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። ኢኮኖሚው ሲያድግ ወደዚያ መግባቱ እንደማይቀር በመግለፅ። አቶ ዋሲሁን በበኩላቸው የገንዘብ ኖት ከፍ እያለ ሲመጣ ገንዘቦች መግዛት አቅማቸው መዳከሙን የሚያመላክት መሆኑን ይናገራሉ። በምሳሌ ሲያስረዱም "አሁን 5 ብር ዝቅተኛው ገንዘብ እየሆነ ነው። አንድ ብርና ሁለት ብር የሚገዛቸው ነገሮች እየጠፉ ነው። ሰዎች መቶ ብርም ይዘው በፊት የሚገዙትን ያህል እቃ መግዛት አይችሉም፤ በመሆኑም ሰዎች ብዙ የወረቀት ገንዘብ ይዘው ከሚሄድ ያድናቸዋል" ይላሉ። ነገር ግን ከ20 በመቶ በላይ የዋጋ ንረት በሚመዘገብበት ሁኔታና የ100 ብርና የ200 ብር ልዩነት ብዙም ባለመሆኑ መሆን የነበረት የ500 ወይም የ1000 ብር ኖት ወደገበያው መግባት እንደነበር አቶ ዋሲሁን ሙያዊ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የገንዘብ መቀየሩን ተከትሎ ምን ሊፈጠር ይችላል? መንግሥት አሮጌ የብር ኖቶቹን ለመቀየር የሦስት ወር የጊዜ ገደብ አስቀምጧል። የምጣኔ ሀብት ባለሙያው እንደሚሉት ከሆነ አዲሱ መገበያያ ገንዘብ ይፋ መደረጉን ተከትሎ በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ ባልተለመደ መልኩ የገንዘብ ዝውውር ሊስተዋል ይችላል። "ሰዎች አዳዲስ የሒሳብ ቁጥር እየከፈቱም ሊያስቀምጡ ይችላሉ። ጥሬ ገንዘቡን ወደ ባንክ ላለማስገባትም የንብረት ግዥ ሊጧጧፍ ይችላል። መኪና፣ ቤት መግዛት ሊኖር ይችላል" ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በሌላ በኩል በሙስና የተከማቸ አሊያም ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ገንዘብ በእጃቸው የያዙ ግለሰቦች፤ የሚመጣባቸውን ጥያቄን በመፍራት በዘመድ አዝማዶቻቸው ስም በርካታ የሒሳብ ቁጥሮችን ሊከፍቱ እንደሚችሉም አመላክተዋል።
ኢኮኖሚ ፡ የኢትዮጵያ የብር ኖት መቀየር የሚኖረው አንድምታ ኢትዮጵያ ከሁለት አስር ዓመታት በላይ ስትገለገልባቸው የነበሩ የ10፣ የ50፣ እናየ100 የገንዘብ ዓይነቶችን ሙሉ ለሙሉ ለመተካት አዲስ የገንዘብ ኖቶች ይፋ አድርጋለች። ከአዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች ውስጥም በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜም የባለ ሁለት መቶ ብር ኖትም አሳትማለች። አገሪቷ ነባሮቹን የብር ኖቶቹን ለመቀየር ሌላ ወጪ ሳይጨምር ለህትመት ብቻ 3.7 ቢሊዮን ብር ማውጣቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አስታውቀዋል። አገሪቱ የገንዘብ ኖቶችን ለመቀየር በኢ-መደበኛ መልኩ ገንዘብ ከባንክ ውጭ በከፍተኛ ሁኔታ መንቀሳቀሱ፣ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የሚሉ ምክንያቶችን አስቀምጣለች። ከዚህ ቀደም አገሪቷ ከፋይናንስ ዘርፍ (ከባንክ) ውጭ ያለው ገንዘብ ከመደበኛው ባልተናነሰ መልኩ ከፍተኛ በመሆኑም እንዴት ይሰብሰብ የሚሉ ጥያቄዎች የባንኮች ዋና ማዕከል ሆነውም ነበር። በኢ-መደበኛ ሁኔታ ያለውን የገንዘብ ፍሰት ወደ መደበኛ ለማምጣትም ጥረቶች የተደረጉ ሲሆን በተለያየ ጊዜም የወጡ መመሪያዎችም ለዚህ ማመላከቻዎች ናቸው። በኢትዮጵያ ከባንክ ውጭ ያለው ገንዘብ በቢሊዮኖች እንደሚቆጠር ከዚህ ቀደም በፋይናንስ ዘርፉ የተሰራ ጥናት የሚያሳይ ሲሆን በባለፈው ዓመትም አገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የጥሬ ገንዘብ እጥረት (ሊኩዊዲቲ) አጋጥሟት ነበር። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክም ይህንንም ችግር ለመፍታት አንዳንድ ጊዜያዊ መፍትሄዎችን መውሰዱ የሚታወስ ነው። የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የዋጋ ግሽበት የለውጡ ዋነኛ መሰናክል ሆነው ቆይተዋል በማለትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምጣኔ ሀብቱ መዳከም ምክንያት ያሉትን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት የገንዘብ ኖት ለውጥ ማድረጓም በከፍተኛ ሁኔታ ከዘርፉ ውጭ ያለውን ገንዘብ ወደ መደበኛ የገንዘብ እንቅስቃሴ ሂደት ለማምጣትም ይረዳታል በማለት የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። የብሔራዊ ባንክ ገዢው ዶ/ር ይናገር ደሴ በበኩላቸው መንግሥት የገንዘብ ለውጥ ማድረግ ካስፈለገው ምክንያቶች መካከል ዋነኛው ከገንዘብ ጋር የተገናኙ ሕገ-ወጥ ዝውውሮችን ለመግታት እንደሆነ በብሔራዊው ቴሌቪዥን ቀርበው አስረድተዋል። የአገሪቱ ኢኮኖሚ በብዛት በጥሬ ገንዘብ ግብይት የሚካሄድበት መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ይናገር ከባንኮች ውጭ ያለው ጥሬ ገንዘብ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል። "አብዛኛው ኅብረተሰባችን ከባንክ ውጭ ነው ግብይት የሚያደርገው በዚህ ምክንያት ብዙ ጥሬ ገንዘብ ከባንክ ውጭ ይገኛል ማለት ነው። በዚህም የጥሬ ገንዘብ እጥረት ባንኮች ላይ ማጋጠም እድሉ ሰፊ ነው።ለ ገቢ አሰባሰብ አመቺ ሁኔታ ይፈጥራል የሚል እምነት ነው ያለን፤ ለአጠቃቀም የተሻለ አገልግሎት ይሰጣል፤ የህትመት ወጪንም በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል" ብለዋል። ከባንክ ውጭ ያለው ጥሬ ገንዘብ በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት አገራት ጭምር በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። "ከባንክ ውጭ የሚገኝ ገንዘብ ደግሞ ለሕገ-ወጥ ተግባራት ሲውል ነው የሚታየው፤ በተለይ በኮንትሮባንድ [ሕገ-ወጥ ንግድ] የተሰማሩ ግለሰቦች ይጠቀሙበታል" ብለዋል። ዶ/ር ይናገር ከዚህ በተጨማሪ ግለሰቦች ግብር ላለመክፈል ሲሉ ገንዘባቸውን ከባንክ ውጭ የማስቀመጥ ልማድም እየሰፋ መምጣቱን ጠቁመው አሁን ያለውን የገንዘብ ኖት መቀየር አስፈላጊ መሆኑ እንደታመነበት አስረድተዋል። ከባንክ ውጭ የተጠራቀመ ገንዘብ ጥቅም የለውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ በኋላም በአውሮፕላን ጣቢያዎችና ድንበሮች እንዲሁም በባንኮች አካባቢ ከፍተኛ ቁጥጥርም ይደረጋል ተብሏል። የፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ ገንዝብ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር ከማድረግ በተጨማሪ በሕገ ወጥ መንገድ የሚሰበሰብ ገንዘብ ካገኙ እንደሚወርሱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ከባንኮች ውጭ ያለው ገንዘብ ወደ ባንኮች ሲመለስም የሂሳብ ደብተር ተከፍቶ ባንኮች ውስጥ እንዲቀመጥ ይደረጋል። ለመሆኑ የብር ኖትን መቀየር እንደ ኮንትሮባንድ እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እንዴት ሊያስቆም ይችላል? የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ከባንክ ሥርዓት ውጭ የሚንቀሳቀስ ከ113 ቢሊየን ብር በላይ መኖሩን ይናገራሉ። ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች ያሉት ሲሆን የዋጋ ንረት ከፍተኛ በመሆኑና ባንክ ቤቶች ብር ለሚያስቀምጥ የሚሰጡት ወለድ ዝቅተኛ በመሆኑ ሰዎች ገንዘቤን በእጄ እይዛለሁ የሚል አስተሳሰብ መኖሩን እንደ አንድ ምክንያት ያነሳሉ። በሌላ በኩል በሙስናና በሌሎች ምክንያቶች "ተቋማትም ግለሰቦችም ሲዘርፉ ስለነበር ነው" ይላሉ። ለዚህ ንግግራቸውም ከለውጡ በኋላ የተከማቹ በርካታ ገንዘቦች በጆንያ እየታጨቁ እና በመኪና እየተጫኑ ሲዘዋወሩ መያዛቸውን እንደ ምሳሌም ይጠቅሳሉ። የገንዘብ ኖቶቹ ላይ ለውጥ መደረጉም ሰዎች ገንዘባቸውን ለመቀየር ባንክ በሚሄዱበት ጊዜ፤ በጤናማ የግብይት ሥርዓት ገንዘቡን ማግኘት አለማግኘታቸውን ለማረጋገጥ እድል ይሰጣል ብለዋል ባለሙያው። በመሆኑም እስካሁን የተሰሩ የሙስና ምንጮችን ለማወቅም ሆነ ከአሁን በኋላ የሚሰሩ ሙስናዎች ላይ ፍራቻ እንዲፈጥር ሊያደርግ እንደሚችልም ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምጣኔ ሀብት መምህር የሆኑት ረዳት ፐሮፌሰር ጉቱ ለገስ ደግሞ ከገንዘብ ጋር ተያይዞ ያሉ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የብር ኖቶች መቀየር አንዱ እንጂ፤ ብቸኛው መፍትሔ አለመሆኑን ያሰምሩበታል። ረዳት ፕሮፌሰር ጉቱ "አንድ ነገር ሲተዋወቅ ውጤታማ ለመሆን አለመሆኑ አንዱ ወሳኙ ነገር፤ ተቋማዊ አደረጃጃትና የመተግበር አቅም ነው። ይህ ካልሆነ ግን አዙሪት ነው የሚሆነው" ብለዋል። መንግሥት ገንዘቡን ከቀየረ በኋላ ሕገ-ወጥ ገንዘብ ይዘዋል ተብለው የሚጠረጠሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች የየራሳቸውን እርምጃ መውሰዳቸው እንደማይቀር የጠቆሙት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ መንግሥት ተቋማዊ አደረጃጀቱ ጠንካራ ሆኖ ይሄን ነገር ልብ ብሎ መከታተል እንዳለበት መክረዋል። አሁን የተወሰደው እርምጃ ቀደም ብለው የተሰሩ ሥራዎች ስላሉ ውጤታማ ይሆናል ተብሎ ይገመታልም ብለዋል። ነገር ግን "ቀድሞ የነበረው የውጭ ምንዛሬ ጋር ተያይዞ ያለው ሙስናና ደካማ አስተዳደር ካልተስተካከለ ተመልሶ ያው ነው የሚሆነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። አዲስ የ200 ብር ኖት ማስገባት ለምን ተፈለገ? በኢትዮጵያ በቅርብ አመታት ውስጥ የገንዘብ የመግዛት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ያሽቆለቆለ ሲሆን ከዚህም አንፃር ባለ ሁለት መቶ ኖቶች ወደ ገበያው ውስጥ መግባት አስፈላጊ እንደሆነም የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይናገራሉ። ረዳት ፕሮፌሰር ጉቱ የዋጋ ንረቱ በጣም ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ በተለያየ ግብይት ሂደት ውስጥ የሚሳተፈው ኅብረተሰብ ብዙ ብር ለመያዝ እየተገደደ መሆኑን በመጥቀስ ያንን ሊያስቀርላቸው እንደሚችል ይናገራሉ። ይሁን እንጂ ወደ ኤሌክትሮኒክስ የግብይት ሥርዓት እንዲገቡም እየተሰራ ያለው ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። ኢኮኖሚው ሲያድግ ወደዚያ መግባቱ እንደማይቀር በመግለፅ። አቶ ዋሲሁን በበኩላቸው የገንዘብ ኖት ከፍ እያለ ሲመጣ ገንዘቦች መግዛት አቅማቸው መዳከሙን የሚያመላክት መሆኑን ይናገራሉ። በምሳሌ ሲያስረዱም "አሁን 5 ብር ዝቅተኛው ገንዘብ እየሆነ ነው። አንድ ብርና ሁለት ብር የሚገዛቸው ነገሮች እየጠፉ ነው። ሰዎች መቶ ብርም ይዘው በፊት የሚገዙትን ያህል እቃ መግዛት አይችሉም፤ በመሆኑም ሰዎች ብዙ የወረቀት ገንዘብ ይዘው ከሚሄድ ያድናቸዋል" ይላሉ። ነገር ግን ከ20 በመቶ በላይ የዋጋ ንረት በሚመዘገብበት ሁኔታና የ100 ብርና የ200 ብር ልዩነት ብዙም ባለመሆኑ መሆን የነበረት የ500 ወይም የ1000 ብር ኖት ወደገበያው መግባት እንደነበር አቶ ዋሲሁን ሙያዊ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የገንዘብ መቀየሩን ተከትሎ ምን ሊፈጠር ይችላል? መንግሥት አሮጌ የብር ኖቶቹን ለመቀየር የሦስት ወር የጊዜ ገደብ አስቀምጧል። የምጣኔ ሀብት ባለሙያው እንደሚሉት ከሆነ አዲሱ መገበያያ ገንዘብ ይፋ መደረጉን ተከትሎ በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ ባልተለመደ መልኩ የገንዘብ ዝውውር ሊስተዋል ይችላል። "ሰዎች አዳዲስ የሒሳብ ቁጥር እየከፈቱም ሊያስቀምጡ ይችላሉ። ጥሬ ገንዘቡን ወደ ባንክ ላለማስገባትም የንብረት ግዥ ሊጧጧፍ ይችላል። መኪና፣ ቤት መግዛት ሊኖር ይችላል" ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በሌላ በኩል በሙስና የተከማቸ አሊያም ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ገንዘብ በእጃቸው የያዙ ግለሰቦች፤ የሚመጣባቸውን ጥያቄን በመፍራት በዘመድ አዝማዶቻቸው ስም በርካታ የሒሳብ ቁጥሮችን ሊከፍቱ እንደሚችሉም አመላክተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/54159837
5sports
የአፍሪካ ዋንጫ በየአራት ዓመቱ እንዲካሄድ ሀሳብ ቀረበ
የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ የአፍሪካ ዋንጫ በየሁለቱ ዓመቱ መካሄዱ ቀርቶ በአራት አመት አንዴ ብቻ አንዲካሄድ ለአፍሪካ እግር ኳስ ማህበር (ካፍ)ሃሳባቸውን አቅርበዋል። ኢንፋንቲኖ በሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው የካፍ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር '' በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው አፍሪካ ዋንጫ አውሮፓውያኑ ከሚያስገኙት ሲነጻጸር ገቢው በሃያ እጥፍ ያነሰ ነው። በዚህ አካሄድ በየሁለት ዓመቱ ማካሄዱ አዋጪ ነው? እስቲ በየአራት ዓመቱ ማካሄድን ከግምት ውስጥ እናስገባው'' ብለዋል። • የ2021 አፍሪካ ዋንጫ ጥር ላይ እንዲካሄድ ተወሰነ • አፍሪካ የዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት አዲስ አሰራር እንዲኖር ትፈልጋለች ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ በጎርጎሳውያኑ 2021 በካሜሩን አዘጋጅነት የሚካሄድ ሲሆን ልክ እንደ ቀድሞው ጥርና የካቲት ላይ ሀገራት ውድድር ያደርጋሉ። ባለፈው ዓመት የአፍሪካ ዋንጫ ቀድሞ ከሚካሄድበት ወቅት በተለየ መልኩ ሰኔ እና ሐምሌ ላይ ግብጽ ውስጥ ተካሂዶ ነበር። በዚሁ ውድድር ተሳታፊ ሀገራት ቁጥርም ወደ 24 ከፍ እንዲል ተደርጓል። የፊፋው ፕሬዝዳንት በንግግራቸው አክለውም ''ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ማዘጋጀት ያስፈልጋል። በእኛ በኩል ሶስት መፍትሄ የሚያስፈልጋቸው ነጥቦችን ለይተናል፤ እነሱም ዳኝነት፣ መሰረተ ልማት እና ውድድሮች ናቸው'' ብለዋል። አክለውም'' አሁን ስለአፍሪካ እግር ኳስ እድገት ብቻ የምናወራበት ሰአት ሳይሆን እርምጃ የምንወስድበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው። የትኛውም የአፍሪካ ሀገር ዓለም ዋንጫን አሸንፎ አያውቅም፤ ለምን ብለን መጠየቅም ይገባናል።'' • የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት ከዳኝነት ጋር በተያያዘ ፊፋ የተመረጡ 20 ዳኞችን በገንዘብና በስልጠና በመገደፍ ለአህጉሪቱ እግር ኳስ እድገት የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማድረግ እንዳሰበም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም የአፍሪካ እግር ኳስ አሁን ካለበት ደረጃ ከፍ በማድረግ በዓለማቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ ለማድረግ ፊፋ 1 ቢሊየን ዶላር ፈሰስ ለማድረግና በእያንዳንዱ አባል ሀገር አንድ ዘመናዊ ስታዲየም ለመገንባት እቅድ መያዙም በስብሰባው ላይ ተገልጿል።
የአፍሪካ ዋንጫ በየአራት ዓመቱ እንዲካሄድ ሀሳብ ቀረበ የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ የአፍሪካ ዋንጫ በየሁለቱ ዓመቱ መካሄዱ ቀርቶ በአራት አመት አንዴ ብቻ አንዲካሄድ ለአፍሪካ እግር ኳስ ማህበር (ካፍ)ሃሳባቸውን አቅርበዋል። ኢንፋንቲኖ በሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው የካፍ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር '' በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው አፍሪካ ዋንጫ አውሮፓውያኑ ከሚያስገኙት ሲነጻጸር ገቢው በሃያ እጥፍ ያነሰ ነው። በዚህ አካሄድ በየሁለት ዓመቱ ማካሄዱ አዋጪ ነው? እስቲ በየአራት ዓመቱ ማካሄድን ከግምት ውስጥ እናስገባው'' ብለዋል። • የ2021 አፍሪካ ዋንጫ ጥር ላይ እንዲካሄድ ተወሰነ • አፍሪካ የዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት አዲስ አሰራር እንዲኖር ትፈልጋለች ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ በጎርጎሳውያኑ 2021 በካሜሩን አዘጋጅነት የሚካሄድ ሲሆን ልክ እንደ ቀድሞው ጥርና የካቲት ላይ ሀገራት ውድድር ያደርጋሉ። ባለፈው ዓመት የአፍሪካ ዋንጫ ቀድሞ ከሚካሄድበት ወቅት በተለየ መልኩ ሰኔ እና ሐምሌ ላይ ግብጽ ውስጥ ተካሂዶ ነበር። በዚሁ ውድድር ተሳታፊ ሀገራት ቁጥርም ወደ 24 ከፍ እንዲል ተደርጓል። የፊፋው ፕሬዝዳንት በንግግራቸው አክለውም ''ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ማዘጋጀት ያስፈልጋል። በእኛ በኩል ሶስት መፍትሄ የሚያስፈልጋቸው ነጥቦችን ለይተናል፤ እነሱም ዳኝነት፣ መሰረተ ልማት እና ውድድሮች ናቸው'' ብለዋል። አክለውም'' አሁን ስለአፍሪካ እግር ኳስ እድገት ብቻ የምናወራበት ሰአት ሳይሆን እርምጃ የምንወስድበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው። የትኛውም የአፍሪካ ሀገር ዓለም ዋንጫን አሸንፎ አያውቅም፤ ለምን ብለን መጠየቅም ይገባናል።'' • የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት ከዳኝነት ጋር በተያያዘ ፊፋ የተመረጡ 20 ዳኞችን በገንዘብና በስልጠና በመገደፍ ለአህጉሪቱ እግር ኳስ እድገት የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማድረግ እንዳሰበም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም የአፍሪካ እግር ኳስ አሁን ካለበት ደረጃ ከፍ በማድረግ በዓለማቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ ለማድረግ ፊፋ 1 ቢሊየን ዶላር ፈሰስ ለማድረግና በእያንዳንዱ አባል ሀገር አንድ ዘመናዊ ስታዲየም ለመገንባት እቅድ መያዙም በስብሰባው ላይ ተገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/news-51346280
5sports
የሊቨርፑል ተጫዋቾች የአሜሪካውን ግድያ ተቃወሙ
የሊቨርፑል ተጫዋቾች በአፍሪካ አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ላይ በፖሊስ የተፈጸመውን ግድያ በመቃወም በልምምድ ሜዳቸው ማሃል ላይ ክብ ሰርተው በጉልበታቸው ተንበርክከው አጋርነታቸውን አሳዩ። 29 የሊቨርፑል ተጫዋቾችን ተንበርክከው የሚያሳየው ፎቶግራፍ የወጣው "አንድነት ኃይል ነው" ከሚል የፎቶ መግለጫ ጋር ነው። ተጫዋቾቹ ፎቶውን የተነሱት ዛሬ ሰኞ በነበራቸው ልምምድ ላይ ሲሆን፤ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾቹ ማርከስ ራሽፎርድ እና ጃደን ሳንቾም በዓለም ዙሪያ እየተስተጋባ ባለው ጸረ ዘረኝነት ተቃውሞ ላይ ድምጻቸውን በማሰማት ተሳትፈዋል። የማንችስተር ዩናይትድ እና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቹ ማርከስ ራሽፎርድ በበኩሉ ክስተቱ ለመቀበል እንደተቸገረ እንዲህ ሲል ተናግሯል "በምድራችን ላይ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ለመረዳት እየሞከርኩ ነው።" ጨምሮም "ሰዎች አንድ ላይ እንዲሆኑ፣ አብረው በመስራት ህብረት እንዲፈጥሩ በሚጠየቅበት ጊዜ፤ ከሌላው ጊዜ በበለጠ ተከፋፍለን እንገኛለን። "በዚህም ሰዎች እየተጎዱ ነው ምላሽን ይሻሉ። ስለጥቁሮች ሕይወት ግድ ይለናል። ስለጥቁሮች ባሕል ያገባናል። ስለጥቁሮች ማኅበረሰብ ግድ ይለናል። እኛም ድርሻ አለን። [ብላክ ላይቭስ ማተርስ]" ብሏል። ከሳምንት በፊት ጆርጅ ፍሎይድ ሚኒያፖሊስ ውስጥ ዴሪክ ቾቪን የተባለ ፖሊስ መሬት ላይ በደረቱ እንዲተኛ አድርጎት በጉልበቱ አንገቱ ላይ ለደቂቃዎች በመጫን ትንፋሽ እንዲያጥረው በማድረግ ካሰቃየው በኋላ ህይወቱ በማለፉ አሁን ድረስ መላዋን አሜሪካ ያናወጠ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው። የፖሊስ መኮንኑ በዚህ ድርጊቱ ከሥራው የተባረረ ሲሆን በግድያ ወንጀልም ክስ ተመስርቶበታል።
የሊቨርፑል ተጫዋቾች የአሜሪካውን ግድያ ተቃወሙ የሊቨርፑል ተጫዋቾች በአፍሪካ አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ላይ በፖሊስ የተፈጸመውን ግድያ በመቃወም በልምምድ ሜዳቸው ማሃል ላይ ክብ ሰርተው በጉልበታቸው ተንበርክከው አጋርነታቸውን አሳዩ። 29 የሊቨርፑል ተጫዋቾችን ተንበርክከው የሚያሳየው ፎቶግራፍ የወጣው "አንድነት ኃይል ነው" ከሚል የፎቶ መግለጫ ጋር ነው። ተጫዋቾቹ ፎቶውን የተነሱት ዛሬ ሰኞ በነበራቸው ልምምድ ላይ ሲሆን፤ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾቹ ማርከስ ራሽፎርድ እና ጃደን ሳንቾም በዓለም ዙሪያ እየተስተጋባ ባለው ጸረ ዘረኝነት ተቃውሞ ላይ ድምጻቸውን በማሰማት ተሳትፈዋል። የማንችስተር ዩናይትድ እና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቹ ማርከስ ራሽፎርድ በበኩሉ ክስተቱ ለመቀበል እንደተቸገረ እንዲህ ሲል ተናግሯል "በምድራችን ላይ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ለመረዳት እየሞከርኩ ነው።" ጨምሮም "ሰዎች አንድ ላይ እንዲሆኑ፣ አብረው በመስራት ህብረት እንዲፈጥሩ በሚጠየቅበት ጊዜ፤ ከሌላው ጊዜ በበለጠ ተከፋፍለን እንገኛለን። "በዚህም ሰዎች እየተጎዱ ነው ምላሽን ይሻሉ። ስለጥቁሮች ሕይወት ግድ ይለናል። ስለጥቁሮች ባሕል ያገባናል። ስለጥቁሮች ማኅበረሰብ ግድ ይለናል። እኛም ድርሻ አለን። [ብላክ ላይቭስ ማተርስ]" ብሏል። ከሳምንት በፊት ጆርጅ ፍሎይድ ሚኒያፖሊስ ውስጥ ዴሪክ ቾቪን የተባለ ፖሊስ መሬት ላይ በደረቱ እንዲተኛ አድርጎት በጉልበቱ አንገቱ ላይ ለደቂቃዎች በመጫን ትንፋሽ እንዲያጥረው በማድረግ ካሰቃየው በኋላ ህይወቱ በማለፉ አሁን ድረስ መላዋን አሜሪካ ያናወጠ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው። የፖሊስ መኮንኑ በዚህ ድርጊቱ ከሥራው የተባረረ ሲሆን በግድያ ወንጀልም ክስ ተመስርቶበታል።
https://www.bbc.com/amharic/news-52883363
3politics
ግብፅ የመስኖ እና የውሃ ሚኒስትርን ጨምሮ 13 አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾመች
የፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ ጥያቄን ተከትሎ የግብፅ ፓርላማ በአገሪቱ የካቢኔ ሚኒስትሮች ላይ ዋነኛ ለውጥ በማድረግ አዳዲስ ሹመቶችን አፀደቀ። ፕሬዝዳንቱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመመካከር በአገሪቱ የካቢኔ አባላት ላይ ከፍተኛ የተባለውን ለውጥ ለማድረግ በእረፍት ላይ የነበረው ፓርላማ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲያደረግ የጠየቁት ባለፈው አርብ ነበር። በዚህም መሠረት አብዛኞቹ ሚኒስትሮች በአዲስ የተተኩበት የአገሪቱ የካቢኔ ሚኒስትሮች ስብስብ 13 አዳዲስ ሚኒስትሮች ተካተውበት ለምክር ቤቱ ቀርቦ ዕሁድ ዕለት መጽደቁ ተዘግቧል። በአዲሱ የግብፅ ካቢኔ ውስጥ ዋነኛ የሚባሉት የመስኖ እና የውሃ ሚኒስትርን ጨምሮ 13 ሚኒስትሮች በአዲስ ሲተኩ፣ የገንዘብ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በቦታቸው ቀጥለዋል። የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ በሚኒስተሮቻቸው ላይ ለውጥ ያስፈለገበትን ምክንያት በማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መድረኮች ላይ እንደገለጹት “በአገር ውስጥና በውጪ የአገሪቱን ጥቅም በማስጠበቅና ለዜጎች የሚሰጠውን አገልግሎት የበለጠ በማጎልበት የመንግሥትን የአፈጻጸም ብቃት ለማጠናከር ነው” ብለዋል። ለዚህም በመስከረም ወር መጨረሻ ላይ ሥራውን ለመጀመር ለሦስት ወራት ዕረፍት ተዘግቶ የነበረው የግብፅ ፓርላማ አባላትም “ለአስቸኳይ ጉዳይ” በሚል ለቅዳሜ እንዲሰበሰቡ ተጠርተው አዲስ የቀረቡትን ሚኒስትሮች ሹመት አጽድቀውታል። ዕሁድ ዕለትም ተሿሚዎቹ ሚኒስትሮች ሥራ ለመጀመር በፕሬዝዳንቱ ፊት ቃለ መሐላ ፈጽመዋል። ግብፅ ከፍተኛ ትኩረት ከምትሰጣቸው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶቿ መከከል አንዱ የሆነውን እና ኢትዮጵያ ልታጠናቅቀው የተቃረበችውን የታላቁ የኢትየጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይን ለዓመታት በቅርበት ሲከታተሉ የነበሩት የመስኖ እና የውሃ ሚኒስትሩ ሞሐመድ አብደል አቲ በአዲስ ተተክተዋል። ባለፈው ሳምንት በሁለተኛ ተርባይን ኃይል ማመንጨት የጀመረውና ሦስተኛው ዙር የውሃ ሙሌቱን ያከናወነው በአፍሪካ ግዙፉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ የኢትዮጵያ ግድብ ላይ ግብፅ ለዓመታት ተቃውሞዋን ስታሰማ መቆየቷ ይታወቃል። የግብፅን የመስኖ እና ውሃ ሚኒስትርነት ቦታን የተረከቡት አዲሱ ተሿሚ ሃኒ ሴዊላም ሲሆኑ፣ አዲሱ ሚኒስትር በዘርፉ ሦስት አስርት ዓመታት የሚጠጋ ዕውቀትና ልምድ ያካበቱ መሆናቸው ተነግሯል። ሃኒ ሴዊላም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በአውሮፓውያኑ 1991 እዚያው ግብፅ ውስጥ ከሚገኘው ዛግዚግ ዩኒቨርስቲ የምህንድስና ፋክልቲ በውሃ እና በአካባቢ መህንድስና አግኝተዋል። ሴዊላም ካይሮ ውስጥ በሚገኘው የአሜሪካ ዩኒቨርስቲ በዘላቂ ልማት እና በውሃ ሃብት አስተዳደር ዘርፍ ቋሚ ፕሮፌሰር ሆነው አገለግለዋል። በዩኒቨርስቲው ውስጥም ሁለት ዘርፎችን በመመስረት እና በዳይሬክተርነት በመምራት አገልግለዋል። በተጨማሪም በጀርመን ዩኒቨርስቲ ውስጥ በሃይድሮሎጂ ምህንድስና አካዳሚክ ዳይሬክተር ሆነው ሰርተዋል እንዲሁም የዩኔስኮ የውሃ እና የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ዋና ዳይሬክተርም ነበሩ። ሃኒ ሴዊላም በዘላቂ ልማት፣ በውሃ ሀብት፣ በውሃ - በኃይል - በምግብ ተያያዥ ጉዳዮች እንዲሁም በደለል እና በሌሎችም የውሃ አስተዳደር ዘርፎች ከ25 ዓመታት በላይ የዘለቀ የማስተማርና የተግባር ልምድ እንዳላቸው ይነገራል። መንግሥታዊው አል አህራም እንዳለው አዲሱ የግብፅ የመስኖ እና የውሃ ሚኒስትር የሚጠብቃቸው ቀዳሚ ሥራ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለው የሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ይሆናል። ኢትዮጵያ ግብፅ እና ሱዳን በሕዳሴው ግድብ የውሃ አሞላልና አጠቃላይ አስተዳደር ዙሪያ ለዓመታት ሲያደርጉት የነበረው ድርድር ምንም አይነት ስምምነትን ሳያስገኝ ግድቡ ወደ መጠናቀቁ እየተቃረበ ነው። ምንም እንኳን ግብፅና ሱዳን አስገዳጅ ሕጋዊ ስምምነት ላይ ሳይደረስ ኢትዮጵያ የግድቡን ውሃ የመሙላት ሥራ እንዳትጀመር ግፊት ቢያደርጉም፣ ይህንን ዓመት ጨምሮ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ግድቡ በውሃ መሞላቱን ኢትዮጵያ አስታውቃለች። ባለፈው ሳምንትም ኢትዮጵያ ግድቡ ከሚኖሩት 13 የኃይል ማመንጫ ተርባይኖች መካከል ሁለተኛውን ሥራ በማስጀመር፣ ቀደም ሲል በየካቲት ወር ኃይል ማመንጨት ከጀመረው ጋር በመሆን ከ500 ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ከሕዳሴው ግድብ መመንጨት መጀመሩ ታውቋል። ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን በግድቡ ዙሪያ ሲያደርጉት የነበረው ድርድር ከተቋረጠ የቆየ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ድርድሩ እንዲቀጥል በተደጋጋሚ ስትጠይቅ ቆይታለች። ባለፈው ሳምንትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሁለተኛውን የኃይል ማመንጫ ተርባይንን ሥራ ባስጀመሩት ወቅት በግድቡ የውሃ ሙሌትና አጠቃላይ ሥራ ላይ ተቃውሞ እያሰሙ ካሉት ከግብፅ እና ከሱዳን ጋር ኢትዮጵያ ድርድር ለመቀጠል ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ኢትዮጵያ የታችኛው የአባይ ተፋሰስ አገራትን የመጉዳት ፍላጎት እንደሌላት በመጥቀስ “ከድርድር ውጪ ያሉ አማራጮች የግድቡን ግንባታ አያስቆሙትም” በማለት በአገራቱ መካከል ሲካሄድ የነበረውና የተቋረጠው ንግግር እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። ከሳምንት በፊት ኢትዮጵያ የሕዳሴው ግድብ ሦስተኛው ዙር የውሃ ሙሌትን እንደምታከናውን እንደተገለጸላት በመጥቀስ ግብፅ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አቤቱታ አቅርባ ነበር። ግብፅ ለመንግሥታቱ ድርጅት በጻፈችው ደብዳቤ ላይ ኢትዮጵያ ከስምምነት ላይ ሳይደርስ በተናጠል የግድቡን የውሃ ሙሌት ማከናወን የለባትም በሚል ተቃውሞዋን አስመዝግባለች። ኢትዮጵያ ግን የግድቡ ግንባታም ሆነ የውሃው ሙሌት በታችኛው ተፋሰስ አገራት ላይ የሚያስከትለው የጎላ ጉዳት የለም በማለት ግንባታውን እና የውሃ ሙሌቱን ወደ ማጠናቀቅ እየተቃረበች ነው።
ግብፅ የመስኖ እና የውሃ ሚኒስትርን ጨምሮ 13 አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾመች የፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ ጥያቄን ተከትሎ የግብፅ ፓርላማ በአገሪቱ የካቢኔ ሚኒስትሮች ላይ ዋነኛ ለውጥ በማድረግ አዳዲስ ሹመቶችን አፀደቀ። ፕሬዝዳንቱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመመካከር በአገሪቱ የካቢኔ አባላት ላይ ከፍተኛ የተባለውን ለውጥ ለማድረግ በእረፍት ላይ የነበረው ፓርላማ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲያደረግ የጠየቁት ባለፈው አርብ ነበር። በዚህም መሠረት አብዛኞቹ ሚኒስትሮች በአዲስ የተተኩበት የአገሪቱ የካቢኔ ሚኒስትሮች ስብስብ 13 አዳዲስ ሚኒስትሮች ተካተውበት ለምክር ቤቱ ቀርቦ ዕሁድ ዕለት መጽደቁ ተዘግቧል። በአዲሱ የግብፅ ካቢኔ ውስጥ ዋነኛ የሚባሉት የመስኖ እና የውሃ ሚኒስትርን ጨምሮ 13 ሚኒስትሮች በአዲስ ሲተኩ፣ የገንዘብ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በቦታቸው ቀጥለዋል። የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ በሚኒስተሮቻቸው ላይ ለውጥ ያስፈለገበትን ምክንያት በማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መድረኮች ላይ እንደገለጹት “በአገር ውስጥና በውጪ የአገሪቱን ጥቅም በማስጠበቅና ለዜጎች የሚሰጠውን አገልግሎት የበለጠ በማጎልበት የመንግሥትን የአፈጻጸም ብቃት ለማጠናከር ነው” ብለዋል። ለዚህም በመስከረም ወር መጨረሻ ላይ ሥራውን ለመጀመር ለሦስት ወራት ዕረፍት ተዘግቶ የነበረው የግብፅ ፓርላማ አባላትም “ለአስቸኳይ ጉዳይ” በሚል ለቅዳሜ እንዲሰበሰቡ ተጠርተው አዲስ የቀረቡትን ሚኒስትሮች ሹመት አጽድቀውታል። ዕሁድ ዕለትም ተሿሚዎቹ ሚኒስትሮች ሥራ ለመጀመር በፕሬዝዳንቱ ፊት ቃለ መሐላ ፈጽመዋል። ግብፅ ከፍተኛ ትኩረት ከምትሰጣቸው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶቿ መከከል አንዱ የሆነውን እና ኢትዮጵያ ልታጠናቅቀው የተቃረበችውን የታላቁ የኢትየጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይን ለዓመታት በቅርበት ሲከታተሉ የነበሩት የመስኖ እና የውሃ ሚኒስትሩ ሞሐመድ አብደል አቲ በአዲስ ተተክተዋል። ባለፈው ሳምንት በሁለተኛ ተርባይን ኃይል ማመንጨት የጀመረውና ሦስተኛው ዙር የውሃ ሙሌቱን ያከናወነው በአፍሪካ ግዙፉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ የኢትዮጵያ ግድብ ላይ ግብፅ ለዓመታት ተቃውሞዋን ስታሰማ መቆየቷ ይታወቃል። የግብፅን የመስኖ እና ውሃ ሚኒስትርነት ቦታን የተረከቡት አዲሱ ተሿሚ ሃኒ ሴዊላም ሲሆኑ፣ አዲሱ ሚኒስትር በዘርፉ ሦስት አስርት ዓመታት የሚጠጋ ዕውቀትና ልምድ ያካበቱ መሆናቸው ተነግሯል። ሃኒ ሴዊላም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በአውሮፓውያኑ 1991 እዚያው ግብፅ ውስጥ ከሚገኘው ዛግዚግ ዩኒቨርስቲ የምህንድስና ፋክልቲ በውሃ እና በአካባቢ መህንድስና አግኝተዋል። ሴዊላም ካይሮ ውስጥ በሚገኘው የአሜሪካ ዩኒቨርስቲ በዘላቂ ልማት እና በውሃ ሃብት አስተዳደር ዘርፍ ቋሚ ፕሮፌሰር ሆነው አገለግለዋል። በዩኒቨርስቲው ውስጥም ሁለት ዘርፎችን በመመስረት እና በዳይሬክተርነት በመምራት አገልግለዋል። በተጨማሪም በጀርመን ዩኒቨርስቲ ውስጥ በሃይድሮሎጂ ምህንድስና አካዳሚክ ዳይሬክተር ሆነው ሰርተዋል እንዲሁም የዩኔስኮ የውሃ እና የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ዋና ዳይሬክተርም ነበሩ። ሃኒ ሴዊላም በዘላቂ ልማት፣ በውሃ ሀብት፣ በውሃ - በኃይል - በምግብ ተያያዥ ጉዳዮች እንዲሁም በደለል እና በሌሎችም የውሃ አስተዳደር ዘርፎች ከ25 ዓመታት በላይ የዘለቀ የማስተማርና የተግባር ልምድ እንዳላቸው ይነገራል። መንግሥታዊው አል አህራም እንዳለው አዲሱ የግብፅ የመስኖ እና የውሃ ሚኒስትር የሚጠብቃቸው ቀዳሚ ሥራ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለው የሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ይሆናል። ኢትዮጵያ ግብፅ እና ሱዳን በሕዳሴው ግድብ የውሃ አሞላልና አጠቃላይ አስተዳደር ዙሪያ ለዓመታት ሲያደርጉት የነበረው ድርድር ምንም አይነት ስምምነትን ሳያስገኝ ግድቡ ወደ መጠናቀቁ እየተቃረበ ነው። ምንም እንኳን ግብፅና ሱዳን አስገዳጅ ሕጋዊ ስምምነት ላይ ሳይደረስ ኢትዮጵያ የግድቡን ውሃ የመሙላት ሥራ እንዳትጀመር ግፊት ቢያደርጉም፣ ይህንን ዓመት ጨምሮ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ግድቡ በውሃ መሞላቱን ኢትዮጵያ አስታውቃለች። ባለፈው ሳምንትም ኢትዮጵያ ግድቡ ከሚኖሩት 13 የኃይል ማመንጫ ተርባይኖች መካከል ሁለተኛውን ሥራ በማስጀመር፣ ቀደም ሲል በየካቲት ወር ኃይል ማመንጨት ከጀመረው ጋር በመሆን ከ500 ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ከሕዳሴው ግድብ መመንጨት መጀመሩ ታውቋል። ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን በግድቡ ዙሪያ ሲያደርጉት የነበረው ድርድር ከተቋረጠ የቆየ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ድርድሩ እንዲቀጥል በተደጋጋሚ ስትጠይቅ ቆይታለች። ባለፈው ሳምንትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሁለተኛውን የኃይል ማመንጫ ተርባይንን ሥራ ባስጀመሩት ወቅት በግድቡ የውሃ ሙሌትና አጠቃላይ ሥራ ላይ ተቃውሞ እያሰሙ ካሉት ከግብፅ እና ከሱዳን ጋር ኢትዮጵያ ድርድር ለመቀጠል ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ኢትዮጵያ የታችኛው የአባይ ተፋሰስ አገራትን የመጉዳት ፍላጎት እንደሌላት በመጥቀስ “ከድርድር ውጪ ያሉ አማራጮች የግድቡን ግንባታ አያስቆሙትም” በማለት በአገራቱ መካከል ሲካሄድ የነበረውና የተቋረጠው ንግግር እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። ከሳምንት በፊት ኢትዮጵያ የሕዳሴው ግድብ ሦስተኛው ዙር የውሃ ሙሌትን እንደምታከናውን እንደተገለጸላት በመጥቀስ ግብፅ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አቤቱታ አቅርባ ነበር። ግብፅ ለመንግሥታቱ ድርጅት በጻፈችው ደብዳቤ ላይ ኢትዮጵያ ከስምምነት ላይ ሳይደርስ በተናጠል የግድቡን የውሃ ሙሌት ማከናወን የለባትም በሚል ተቃውሞዋን አስመዝግባለች። ኢትዮጵያ ግን የግድቡ ግንባታም ሆነ የውሃው ሙሌት በታችኛው ተፋሰስ አገራት ላይ የሚያስከትለው የጎላ ጉዳት የለም በማለት ግንባታውን እና የውሃ ሙሌቱን ወደ ማጠናቀቅ እየተቃረበች ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cz9krey24dko
0business
ከአሜሪካ ወደ አዲስ አበባ ሊጓዙ የነበሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን 27 ሺህ ዶላር ተወረሰባቸው
የአሜሪካ የጉምሩክ እና ድንበር ጥበቃ ወደ አዲስ አበባ ሊጓዙ ከነበሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቤተሰብ አባላት 27 ሺህ የአሜሪካ ዶላር መውረሱን አስታወቀ። የአገሪቱ ጉምሩክና ድንበር ጥበቃ ተቋም እንዳስታወቀው እሁድ ሐምሌ 03/2014 ዓ.ም. ከቤተሰብ አባላቱ 27 ሺህ 330 ዶላር የወረሰው የቤተሰብ አባላቱ የያዙትን የገንዘብ መጠን ይፋ ባለማድረጋቸው ነው ብሏል። የጉምሩክ እና ድንበር ጥበቃ እንደገለጸው፤ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አዲስ አበባ በረራ ለማድረግ አምስቱ የቤተሰብ አባላት ዋሽንግተን ደለስ ዓለም አቀፍ አውሮእፓለን ማረፊያ ተገኝተው ነበር። የቤተሰብ አባላቱ አውሮፕላን መሳፈሪያ በር ላይ እንደደረሱ ምን ያክል ገንዘብ እንደያዙ በጉምሩክ እና ድንበረ ጥበቃ መኮንኖች እንዲያሳውቁ ተጠይቀው ነበር። ትውልደ ኢትዮጵያዊ እና የአሜሪካ ዜግነት ያለው አባት 8 ሺህ ዶላር ገደማ እንደያዙ በቃል ምላሽ ሰጥቷል። በመቀጠል የጉምሩክ እና ድንበር ጥበቃ ባለሥልጣናት ተጓዞቹ በጉዞ ወቅት የያዙት ገንዘብ በተመለከተ ሪፖርት ስለማድረግ የአገሪቱን ሕግ ለተጓዦች አስታውሰዋል። በአሜሪካ ሕግ መሠረት ተጓዦች ወደ አገር ውስጥ ይዘው በሚገቡትም ሆነ በሚወጡት የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ የለም። ይሁን እንጂ አንድ ተጓዥ ከ10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወይም ተመጣጣኝ የሌላ አገር ገንዘብ በላይ ከያዘ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ቅጽ ላይ አሳውቆ ለአሜሪካ ጉምሩክ ባለሥልጣን ሠራተኛ ማሳወቅ ይኖርበታል። የጉምሩክ እና የድንበር ጥበቃ ባወጣው ሪፖርት መሠረት፤ 8 ሺህ ዶላር ገደማ ብቻ መያዙን የተናገረው አባት፤ የተጠየቀውን ቅጽ እየሞላ ሳለ፤ በእድሜ ትልቁ የሆነው ልጅ ሌላ 8 ሺህ ዶላር መያዙን ለባለሥልጣናቱ ተናግሯል። በመቀጠል የጉምሩክ እና ድንበር ጥበቃ መኮንኖቹ የቤተሰብ አባላቱ ሻንጣዎች ላይ ፍተሻ ካደረጉ በኋላ ያገኙትን 27 ሺህ 330 የአሜሪካ ዶላር ወርሰዋል። “ይህን በተደጋጋሚ ተናግረናል። ተጓዦች የፈለጉትን ያክል ገንዘብ ከአሜሪካ ይዘው መውጣት እና መግባት ይችላሉ፤ ይሁን እንጂ የአሜሪካ ፌደራል ሕግ ተጓዦች ከ10ሺህ ዶላር በላይ ከያዙ ማሳወቅ እንዳለባቸው ያስገድዳል። ይህ በጣም ቀላል ነው” ሲሉ የአካባቢው የጉምሩክ እና ድንበር ባለሥልጣን ዳንኤል ኤስኮቤዶ ተናግረዋል። የጉምሩክ እና የድንበር ጥበቃ ባለሙያዎች ለቤተሰብ አባላቱ 830 ዶላር ከመለሱ በኋላ ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ አሰናብቷቸዋል። ይሁን እንጂ በረራው አምልጧቸው የነበሩት የቤተሰብ አባላት፤ ሌላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ቲኬት ተቆርጦ ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ ተደርጓል። የጉምሩክ እና የድንበር ጥበቃ ገንዘብ የተወረሰባቸው ሰዎች በወንጀል ስላልተከሰሱ የማናቸውንም ስም ይፋ እንደማያደርግ ጨምሮ ገልጿል።
ከአሜሪካ ወደ አዲስ አበባ ሊጓዙ የነበሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን 27 ሺህ ዶላር ተወረሰባቸው የአሜሪካ የጉምሩክ እና ድንበር ጥበቃ ወደ አዲስ አበባ ሊጓዙ ከነበሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቤተሰብ አባላት 27 ሺህ የአሜሪካ ዶላር መውረሱን አስታወቀ። የአገሪቱ ጉምሩክና ድንበር ጥበቃ ተቋም እንዳስታወቀው እሁድ ሐምሌ 03/2014 ዓ.ም. ከቤተሰብ አባላቱ 27 ሺህ 330 ዶላር የወረሰው የቤተሰብ አባላቱ የያዙትን የገንዘብ መጠን ይፋ ባለማድረጋቸው ነው ብሏል። የጉምሩክ እና ድንበር ጥበቃ እንደገለጸው፤ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አዲስ አበባ በረራ ለማድረግ አምስቱ የቤተሰብ አባላት ዋሽንግተን ደለስ ዓለም አቀፍ አውሮእፓለን ማረፊያ ተገኝተው ነበር። የቤተሰብ አባላቱ አውሮፕላን መሳፈሪያ በር ላይ እንደደረሱ ምን ያክል ገንዘብ እንደያዙ በጉምሩክ እና ድንበረ ጥበቃ መኮንኖች እንዲያሳውቁ ተጠይቀው ነበር። ትውልደ ኢትዮጵያዊ እና የአሜሪካ ዜግነት ያለው አባት 8 ሺህ ዶላር ገደማ እንደያዙ በቃል ምላሽ ሰጥቷል። በመቀጠል የጉምሩክ እና ድንበር ጥበቃ ባለሥልጣናት ተጓዞቹ በጉዞ ወቅት የያዙት ገንዘብ በተመለከተ ሪፖርት ስለማድረግ የአገሪቱን ሕግ ለተጓዦች አስታውሰዋል። በአሜሪካ ሕግ መሠረት ተጓዦች ወደ አገር ውስጥ ይዘው በሚገቡትም ሆነ በሚወጡት የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ የለም። ይሁን እንጂ አንድ ተጓዥ ከ10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወይም ተመጣጣኝ የሌላ አገር ገንዘብ በላይ ከያዘ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ቅጽ ላይ አሳውቆ ለአሜሪካ ጉምሩክ ባለሥልጣን ሠራተኛ ማሳወቅ ይኖርበታል። የጉምሩክ እና የድንበር ጥበቃ ባወጣው ሪፖርት መሠረት፤ 8 ሺህ ዶላር ገደማ ብቻ መያዙን የተናገረው አባት፤ የተጠየቀውን ቅጽ እየሞላ ሳለ፤ በእድሜ ትልቁ የሆነው ልጅ ሌላ 8 ሺህ ዶላር መያዙን ለባለሥልጣናቱ ተናግሯል። በመቀጠል የጉምሩክ እና ድንበር ጥበቃ መኮንኖቹ የቤተሰብ አባላቱ ሻንጣዎች ላይ ፍተሻ ካደረጉ በኋላ ያገኙትን 27 ሺህ 330 የአሜሪካ ዶላር ወርሰዋል። “ይህን በተደጋጋሚ ተናግረናል። ተጓዦች የፈለጉትን ያክል ገንዘብ ከአሜሪካ ይዘው መውጣት እና መግባት ይችላሉ፤ ይሁን እንጂ የአሜሪካ ፌደራል ሕግ ተጓዦች ከ10ሺህ ዶላር በላይ ከያዙ ማሳወቅ እንዳለባቸው ያስገድዳል። ይህ በጣም ቀላል ነው” ሲሉ የአካባቢው የጉምሩክ እና ድንበር ባለሥልጣን ዳንኤል ኤስኮቤዶ ተናግረዋል። የጉምሩክ እና የድንበር ጥበቃ ባለሙያዎች ለቤተሰብ አባላቱ 830 ዶላር ከመለሱ በኋላ ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ አሰናብቷቸዋል። ይሁን እንጂ በረራው አምልጧቸው የነበሩት የቤተሰብ አባላት፤ ሌላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ቲኬት ተቆርጦ ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ ተደርጓል። የጉምሩክ እና የድንበር ጥበቃ ገንዘብ የተወረሰባቸው ሰዎች በወንጀል ስላልተከሰሱ የማናቸውንም ስም ይፋ እንደማያደርግ ጨምሮ ገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c51wd1793nyo
5sports
የዓለም ዋንጫ አሸናፊን ቀድሞ ለመገመት ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ መንገዶች
ኳታር እያስተናገደችው ያለውን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን የትኛው አገር ይወስዳል? የበርካቶች ጥያቄ ነው። አንዳንዶች ስፖርታዊ ትንታኔን ተከትለው ለመገመት ይሞክራሉ። ሌሎች ደግሞ ‘ጠቋሚ ምልክት’ ይፈልጋሉ። ተስፋቸውን ‘አስማት’ ላይ የጣሉ፣ በሰው ሠራሽ አስተውሎት (አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ኤአይ) የሚታገዙም አሉ። የኳስ ውጤት መገመት በእርግጥ ቀላል አይደለም። ምክንያታዊ ግምት ቢከተሉም በቁማር ገንዘብ የሚበሉ የበዙትም ለዚያ ይሆናል። የፋይናንስ ተቋማት የወደፊቱን የሚገምት ሞዴል ቢያዘጋጁም፣ የኳስ ውጤት ባልተጠበቀ ሁኔታ መለዋወጡ ለኪሳራ ሲዳርጋቸው ታይቷል። ‘አስማታዊ ኃይል’ ተጠቅመው የወደፊቱን መተበይ እንደሚችሉ የሚያምኑ፣ የኳስ ውጤትን ለመገመት ሲሞክሩ ይስተዋላል። ለምሳሌ ብራዚላዊው አቶስ ሳሎሜን እንውሰድ። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንደሚነሳና፣ ሩሲያ ዩክሬንን እንደምትወር ቀድሞ እንዳወቀ ይናገራል። ምናልባት የዓለም ዋንጫ አሸናፊውንም ይተነብያል። ኳስ ተጫዋቾች፣ አሠልጣኞች እና ጋዜጠኞች ተሰባስበው በመወያየት አሸናፊውን ይገምታሉ። ብዙውን ጊዜ ግምታቸው ስህተት ይሆናል። የዓለም ዋንጫ እጅግ በጉጉት ከሚጠበቁ ሁነቶች አንዱ ነው። የዘንድሮው የኳታር የዓለም ዋንጫ አምስት ቢሊዮን ተመልካቾች እንዳሉት ፊፋ አስታውቋል። በዩናይትድ ኪንግደም የምጣኔ ሀብት ተንታኙ ፕሮፌሰር ሮበርት ሳይመንስ “ሰዎች በተለይም ገንዘብ የሚያገኙ ከሆነ በቁማር ይደሰታሉ” ይላል። የዓለም ዋንጫ ለመገመት አዳጋች ቢሆንም፣ ተመልካቾች ከመቆመር ወደኋላ አላሉም። ለምሳሌ ሳዑዲ አረቢያ አርጀንቲናን፣ ጃፓን ጀርመንን ያሸንፋሉ ብሎ ለመገመት ከባድ ነበር። የዓለም ዋንጫ አሸናፊን ለመገመት ተመልካቾች የሚጠቀሙባቸውን አስደናቂ መንገዶች እንዲህ ቃኝተናል። የኮምፒውተር ቀመር እና ሰው ሠራሽ አስተውሎት ቀመር በመጠቀም የዓለም ዋንጫ አሸናፊን ለመገመት እየተሞከረ ነው። የዩናይትድ ኪንግደሙ (ዩኬ) አለን ተሪንግ ተቋም ምርምር ከሚያደርጉት መካከል ይገኝበታል። ሳይንቲስቶች 64 የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎችን በመጠቀም 100,000 የኮምፒውተር ስሌቶች ሠርተዋል። ለዚህ የተጠቀሙት የቀደሚ ውጤቶችን ነው። አንደኛ ደረጃ ግምት የተሰጠው ለአምስት ጊዜ ባለ ድሏ ብራዚል ነው። በመቀጠልም ቤልጄየም እና ሁለት ጊዜ ያሸነፉት አርጀንቲ እና እና ፈረንሳይ ለዋንጫ ይጠበቃሉ ብሎ ነበር፤ ነገር ግን ቤልጂየም ከምድብ ውድድሩ ባሻገር ማለፍ አልቻለችም። ተቋሙ በኮምፒውተር ስሌት የታገዘ ግምቱን ቢያስቀምጥም “የእኛን ግምት ተከትሎ ማንም ሰው እንዳይቆምር። ምክንያቱን ኳስ ለመገመት አዳጋች ነው” ሲል አስጠንቅቋል። ከዚህ በፊት ጎልድማን ሳችስ፣ ዩቢኤስ፣ አይኤንጂ የተባሉ ተቋማት በሁለት የዓለም ዋንጫዎች ግምታቸው ሳይሳካ ቀርቷል። ለንደን የሚገኘው ሊብሪየም ካፒታል የ2014 እና የ2018 አሸናፊዎችን በትክክል መገመት ችሏል። ነገር ግን ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ ግምት መስጠት እንደማይቻል ያምናል። ክሌመንት የተባለው ተቋም እንዳለው፣ አንድ ቡድን የማሸነፍ ዕድሉን 45 በመቶ መገመት ቢችልም የተቀረው 55 በመቶ የቡድኑ ዕድል ላይ የተመሠረተ ይሆናል። የዓለም ዋንጫ አሸናፊን መገመት እንደሚችሉ የሚነገርላቸው ‘አስማተኛ’ እንስሳት አሉ። ፓንዳዎች፣ ግመሎች እና ኦክቶፐስ የተባለው የዓሣ ዝርያ ይጠቀሳሉ። ‘ፖል ዘ ኦክትፑስ’ የተባለው ዓሣ የ2010 የዓለም ዋንጫ አሸናፊን በትክክል ከገመተ ወዲህ ሌሎች የዓለም ዋንጫ አሸናፊዎችንም በትክክል ይገምታል ተብሎ ይታሰባል። ዓሣው ሁለት የአገራት ሰንደቅ አላማ ያለው ሳጥን ይቀርብለታል። ሁለቱም ሳጥን ውስጥ ምግብ ይቀመጣል። ያሸንፋል የሚለው አገር ሰንደቅ አላማ ከተቀባው ሳጥን ይመገባል። 14 ጊዜ ሙከራ ተደርጎ 12ቱ የዓሣው ግምቶች ትክክል ሆነዋል። ይህ ዓሣ አሁን ሕይወቱ አልፏል። ሳይንቲስቶች እንደሚሉት፣ ዓሣው እግር ኳስ ማን እንደሚያሸንፍ የሚያውቅበት ‘አስማታዊ’ ኃይል የለውም። ዓሣ በተፈጥሮው ከአግድም መስመር ቀጥተኛ መስመር ያለበትን ምሥል ይመርጣል። ከቀረቡለት የሰንደቅ አላማ ምርጫዎች ቀጥተኞቹን የመረጠውም ለዚያ ይሆናል። ሳይንቲስቶች ቁማርን አያበረታቱም። ፕሮፌሰር ሳይመንስ እንደሚሉት፣ ምክንያታዊ ግምት በማስቀመጥ ቁማርን የሚያሳልጡ ባለሙያዎች (ቡክሜከርስ) የተሻለ አማራጭ ናቸው። እነዚህ ባለሙያዎች ግምታቸው ትክክል ካልሆነ ገንዘብ ስለሚከፍሉ፣ ትክክለኛ ግምት ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። በእርግጥ ግምት የተሰጣቸው ቡድኖች ሊያሸኝፉም ሊሸነፉም ይችላሉ። ነገር ግን ምክንያታዊ ግምት የማሸነፍ ዕድልን ከፍ ያደርጋል ተብሎ ይታመናል። የዓለም ዋንጫ በ1930 በኡራጓይ ከተጀመረ ወዲህ ብዙ ተለውጧል። ባለፉት ዓመታት በውድድሩ ከቀረቡ 79 አገራት መካከል ያሸነፉት ስምንት ብቻ ናቸው። ብራዚል (አምስት ጊዜ)፣ ጣልያን እና ጀርመን (አራት ጊዜ)፣ ፈረንሳይ፣ ኡራጓይ እና አርጀንቲና (ሁለት ጊዜ) እንዲሁም ስፔን (አንድ ጊዜ)። ከ1978 ወዲህ ዋንጫውን ያልወሰዱና የጨዋታቸውን የመጨረሻ ዙር የተቀላቀሉ አገራት ሦስት ናቸው። ከአህጉራቸው ውጭ ዋንጫውን የወሰዱ አገራት ብራዚል፣ ጀርመን እና ስፔን ናቸው። እስከ መጨረሻው ዙር የተጓዘ አፍሪካዊ አገር የለም። ከእስያ ለግማሽ ፍጻሜ የደረሰችው ደቡብ ኮርያ ብቻ ናት። ከ1982 ወዲህ ከጀርመን ወይም ከጣልያን አንድ ተጫዋች ያልተሳተፈበት የዓለም ዋንጫ የለም። ለዚህ ነው በዓለም ዋንጫ የባየር ሙኒክ እና ኢንተር ሚላን ስም በተደጋጋሚ የሚነሳው። በኳታር የዓለም ዋንጫ ባየር ሙኒክ 17 ተጫዋዎች አሰልፏል። ኢንተር ሚላን ደግሞ ስድስት ተጫዋቾች አሉት። ታዲያ የኳታሩን የዓለም ዋንጫ ማን ይወስድ ይሆን?
የዓለም ዋንጫ አሸናፊን ቀድሞ ለመገመት ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ መንገዶች ኳታር እያስተናገደችው ያለውን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን የትኛው አገር ይወስዳል? የበርካቶች ጥያቄ ነው። አንዳንዶች ስፖርታዊ ትንታኔን ተከትለው ለመገመት ይሞክራሉ። ሌሎች ደግሞ ‘ጠቋሚ ምልክት’ ይፈልጋሉ። ተስፋቸውን ‘አስማት’ ላይ የጣሉ፣ በሰው ሠራሽ አስተውሎት (አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ኤአይ) የሚታገዙም አሉ። የኳስ ውጤት መገመት በእርግጥ ቀላል አይደለም። ምክንያታዊ ግምት ቢከተሉም በቁማር ገንዘብ የሚበሉ የበዙትም ለዚያ ይሆናል። የፋይናንስ ተቋማት የወደፊቱን የሚገምት ሞዴል ቢያዘጋጁም፣ የኳስ ውጤት ባልተጠበቀ ሁኔታ መለዋወጡ ለኪሳራ ሲዳርጋቸው ታይቷል። ‘አስማታዊ ኃይል’ ተጠቅመው የወደፊቱን መተበይ እንደሚችሉ የሚያምኑ፣ የኳስ ውጤትን ለመገመት ሲሞክሩ ይስተዋላል። ለምሳሌ ብራዚላዊው አቶስ ሳሎሜን እንውሰድ። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንደሚነሳና፣ ሩሲያ ዩክሬንን እንደምትወር ቀድሞ እንዳወቀ ይናገራል። ምናልባት የዓለም ዋንጫ አሸናፊውንም ይተነብያል። ኳስ ተጫዋቾች፣ አሠልጣኞች እና ጋዜጠኞች ተሰባስበው በመወያየት አሸናፊውን ይገምታሉ። ብዙውን ጊዜ ግምታቸው ስህተት ይሆናል። የዓለም ዋንጫ እጅግ በጉጉት ከሚጠበቁ ሁነቶች አንዱ ነው። የዘንድሮው የኳታር የዓለም ዋንጫ አምስት ቢሊዮን ተመልካቾች እንዳሉት ፊፋ አስታውቋል። በዩናይትድ ኪንግደም የምጣኔ ሀብት ተንታኙ ፕሮፌሰር ሮበርት ሳይመንስ “ሰዎች በተለይም ገንዘብ የሚያገኙ ከሆነ በቁማር ይደሰታሉ” ይላል። የዓለም ዋንጫ ለመገመት አዳጋች ቢሆንም፣ ተመልካቾች ከመቆመር ወደኋላ አላሉም። ለምሳሌ ሳዑዲ አረቢያ አርጀንቲናን፣ ጃፓን ጀርመንን ያሸንፋሉ ብሎ ለመገመት ከባድ ነበር። የዓለም ዋንጫ አሸናፊን ለመገመት ተመልካቾች የሚጠቀሙባቸውን አስደናቂ መንገዶች እንዲህ ቃኝተናል። የኮምፒውተር ቀመር እና ሰው ሠራሽ አስተውሎት ቀመር በመጠቀም የዓለም ዋንጫ አሸናፊን ለመገመት እየተሞከረ ነው። የዩናይትድ ኪንግደሙ (ዩኬ) አለን ተሪንግ ተቋም ምርምር ከሚያደርጉት መካከል ይገኝበታል። ሳይንቲስቶች 64 የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎችን በመጠቀም 100,000 የኮምፒውተር ስሌቶች ሠርተዋል። ለዚህ የተጠቀሙት የቀደሚ ውጤቶችን ነው። አንደኛ ደረጃ ግምት የተሰጠው ለአምስት ጊዜ ባለ ድሏ ብራዚል ነው። በመቀጠልም ቤልጄየም እና ሁለት ጊዜ ያሸነፉት አርጀንቲ እና እና ፈረንሳይ ለዋንጫ ይጠበቃሉ ብሎ ነበር፤ ነገር ግን ቤልጂየም ከምድብ ውድድሩ ባሻገር ማለፍ አልቻለችም። ተቋሙ በኮምፒውተር ስሌት የታገዘ ግምቱን ቢያስቀምጥም “የእኛን ግምት ተከትሎ ማንም ሰው እንዳይቆምር። ምክንያቱን ኳስ ለመገመት አዳጋች ነው” ሲል አስጠንቅቋል። ከዚህ በፊት ጎልድማን ሳችስ፣ ዩቢኤስ፣ አይኤንጂ የተባሉ ተቋማት በሁለት የዓለም ዋንጫዎች ግምታቸው ሳይሳካ ቀርቷል። ለንደን የሚገኘው ሊብሪየም ካፒታል የ2014 እና የ2018 አሸናፊዎችን በትክክል መገመት ችሏል። ነገር ግን ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ ግምት መስጠት እንደማይቻል ያምናል። ክሌመንት የተባለው ተቋም እንዳለው፣ አንድ ቡድን የማሸነፍ ዕድሉን 45 በመቶ መገመት ቢችልም የተቀረው 55 በመቶ የቡድኑ ዕድል ላይ የተመሠረተ ይሆናል። የዓለም ዋንጫ አሸናፊን መገመት እንደሚችሉ የሚነገርላቸው ‘አስማተኛ’ እንስሳት አሉ። ፓንዳዎች፣ ግመሎች እና ኦክቶፐስ የተባለው የዓሣ ዝርያ ይጠቀሳሉ። ‘ፖል ዘ ኦክትፑስ’ የተባለው ዓሣ የ2010 የዓለም ዋንጫ አሸናፊን በትክክል ከገመተ ወዲህ ሌሎች የዓለም ዋንጫ አሸናፊዎችንም በትክክል ይገምታል ተብሎ ይታሰባል። ዓሣው ሁለት የአገራት ሰንደቅ አላማ ያለው ሳጥን ይቀርብለታል። ሁለቱም ሳጥን ውስጥ ምግብ ይቀመጣል። ያሸንፋል የሚለው አገር ሰንደቅ አላማ ከተቀባው ሳጥን ይመገባል። 14 ጊዜ ሙከራ ተደርጎ 12ቱ የዓሣው ግምቶች ትክክል ሆነዋል። ይህ ዓሣ አሁን ሕይወቱ አልፏል። ሳይንቲስቶች እንደሚሉት፣ ዓሣው እግር ኳስ ማን እንደሚያሸንፍ የሚያውቅበት ‘አስማታዊ’ ኃይል የለውም። ዓሣ በተፈጥሮው ከአግድም መስመር ቀጥተኛ መስመር ያለበትን ምሥል ይመርጣል። ከቀረቡለት የሰንደቅ አላማ ምርጫዎች ቀጥተኞቹን የመረጠውም ለዚያ ይሆናል። ሳይንቲስቶች ቁማርን አያበረታቱም። ፕሮፌሰር ሳይመንስ እንደሚሉት፣ ምክንያታዊ ግምት በማስቀመጥ ቁማርን የሚያሳልጡ ባለሙያዎች (ቡክሜከርስ) የተሻለ አማራጭ ናቸው። እነዚህ ባለሙያዎች ግምታቸው ትክክል ካልሆነ ገንዘብ ስለሚከፍሉ፣ ትክክለኛ ግምት ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። በእርግጥ ግምት የተሰጣቸው ቡድኖች ሊያሸኝፉም ሊሸነፉም ይችላሉ። ነገር ግን ምክንያታዊ ግምት የማሸነፍ ዕድልን ከፍ ያደርጋል ተብሎ ይታመናል። የዓለም ዋንጫ በ1930 በኡራጓይ ከተጀመረ ወዲህ ብዙ ተለውጧል። ባለፉት ዓመታት በውድድሩ ከቀረቡ 79 አገራት መካከል ያሸነፉት ስምንት ብቻ ናቸው። ብራዚል (አምስት ጊዜ)፣ ጣልያን እና ጀርመን (አራት ጊዜ)፣ ፈረንሳይ፣ ኡራጓይ እና አርጀንቲና (ሁለት ጊዜ) እንዲሁም ስፔን (አንድ ጊዜ)። ከ1978 ወዲህ ዋንጫውን ያልወሰዱና የጨዋታቸውን የመጨረሻ ዙር የተቀላቀሉ አገራት ሦስት ናቸው። ከአህጉራቸው ውጭ ዋንጫውን የወሰዱ አገራት ብራዚል፣ ጀርመን እና ስፔን ናቸው። እስከ መጨረሻው ዙር የተጓዘ አፍሪካዊ አገር የለም። ከእስያ ለግማሽ ፍጻሜ የደረሰችው ደቡብ ኮርያ ብቻ ናት። ከ1982 ወዲህ ከጀርመን ወይም ከጣልያን አንድ ተጫዋች ያልተሳተፈበት የዓለም ዋንጫ የለም። ለዚህ ነው በዓለም ዋንጫ የባየር ሙኒክ እና ኢንተር ሚላን ስም በተደጋጋሚ የሚነሳው። በኳታር የዓለም ዋንጫ ባየር ሙኒክ 17 ተጫዋዎች አሰልፏል። ኢንተር ሚላን ደግሞ ስድስት ተጫዋቾች አሉት። ታዲያ የኳታሩን የዓለም ዋንጫ ማን ይወስድ ይሆን?
https://www.bbc.com/amharic/articles/cekv1p424jro
5sports
በርካታ ተጫዋቾች በኮቪድና በጉዳት ያላሰለፉት ሌስተሮች ሊቨርፑልን አሸነፉ
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ትናንት ማክሰኞ ምሽት በሊቨርፑልና ሌስተር ሲቲ መካከል የተደረገው ተጠባቂ ጨዋታ አዴማላ ሉክማን ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ በሌስተር አሸናፊነት ተጠናቋል። በዚህም ሊቨርፑሎች በደረጃ ሰንጠረዡ ከማንቸስተር ሲቲ በስድስት ነጥብ ርቀው ሁለተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል። ሊቨርፑሎች በመጀመሪያው አጋማሽ 15ኛው ደቂቃ ላይ የፍጹም ቅጣት ምት አግኝተው የነበረ ቢሆንም ግብፃዊው ሞሐመድ ሳላህ ወደ ግብነት መቀየር ሳይችል ቀርቷል። የጨዋታው ኮከብ ተጨዋች ተብሎ የተመረጠው የሌስተሩ ግብ ጠባቂ ካስፐር ሹማይክል ኳሷን ከመረብ እንዳትገናኝ አድርጓል። ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔም ቢሆን በርካታ የግብ ዕድሎችን ቢያገኝም ግብ ማስቆጠር ግን አልቻለም። አብዛኛውን የጨዋታ ጊዜ ወደ ግብ ክልላቸው ተስበው ለመከላከል ተገድደው የነበሩት ሌስተሮች 59ኛው ደቂቃ ላይ ያገኙትን ዕድል በአግባቡ ተጠቅመዋል። የቀድሞው የኤቨርተን የፊት መስመር ተጫዋች አዴማላ ሉክማን ተቀይሮ በገባ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ኪረን ደውስብሪ ያሻማለትን ኳስ ወደ ግብነት መቀየር ችሏል። በርካታ የመጀመሪያ ቡድን ተጫዋቾችን በጉዳትና በኮቪድ ምክንያት ያጡት ሌስተሮች በተደጋጋሚ ሊቨርፑሎች ሲያደርጉት የነበረው የማጥቃት ጨዋታ ተቋቁመው አምሽተዋል። ከስድስት ቀናት በፊት በካራባዎ ዋንጫ ሁለቱ ቡድኖች ተገናኝተው የነበረ ሲሆን ሌስተር ሲቲ ቀድሞ 3 ለ 0 መምራት ችሎ ነበር። ነገር ግን በተከታታይ ባስተናገዱት ሦስት ግብ ምክንያት ጨዋታው አቻ ተጠናቆ በፍጹም ቅጣት ምት ሊቨርፑል ማሸነፍ ችሏል። ፕሪምየር ሊጉ ከተጀመረ ሁለተኛ ሽንፈታቸውን ያስተናገዱት ሊቨርፑሎች ከሊጉ መሪ ማንቸስተር ሲቲ በስድስት ነጥብ ርቀው በ41 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በሌላ በኩል ከሰባት ጨዋታዎች ሁለቱን ብቻ ማሸነፍ የቻሉት ሌስተሮች ትናንት ምሽት ሦስት ሙሉ ነጥብ ማግኘታቸውን ተከትሎ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል። በጉዳት ምከንያት ተከላካዮቻቸውን ያጡት ሌስተሮች የመሀል ክፍል ተጫዋቹ ዊልፍሬድ ንዲዲን በተከላካይ መስመር ለማሰለፍ ተገድደው ነበር። ንዲዲም ሞሐመድ ሳላህ ላይ በፈጸመው ጥፋት ቡድኑ ላይ የፍጹም ቅጣት ምት አስሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ግብ ጠባቂው ግን ኳሷ ግብ እንዳትሆን አድርጓል። የሌስተሩ አጥቂ ጄሚ ቫርዲ ምሽቱን ሙሉ ያገኘውን ኳስ ወደ ሊቨርፑል ግብ ክልል ይዞ በመግባት ትልቅ ፈተና ሆኖ አምሽቷል። በመጀመሪያው አጋማሽም ያገኘውን ኳስ ወደ ግብ ቢመታም ተከላካዩ ጆዌል ማቲፕ ተደርቦ ግብ ከመሆን አድኖበታል። ሊቨርፑሎች ከሜዳቸው ውጪ ካደረጓቸው 29 ጨዋታዎች በትናንቱ ጨዋታ ላይ ብቻ ነው ግብ ማስቆጠር ያልቻሉት። የፊታችን እሁድ ከቼልሲ ጋር የሚፋለሙት ሊቨርፑሎች በደረጃ ሰንጠረዡ ከማንቸስተር ሲቲ ያላቸውን ልዩነት ለማጥበብ የሞት የሽረት ትግል እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፉት የሊቨርፑሎቹ ሞሐመድ ሳላህ፣ ሳዲዮ ማኔ እና ናቢ ኬታ ወደ ውድድሩ ከመሄዳቸው በፊት የቼልሲው ጨዋታ የመጨረሻቸው ይሆናል። ትናንት በተካሄዱ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በጥሩ አቋም ላይ የሚገኙት ቶተንሀሞች ከሳውዝሀምፕተን ጋር አንድ አቻ ሲለያዩ ዌስት ሀም ደግሞ ዋትፎርድን 4 ለ1 በማሸነፍ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል መመለስ ችለዋል። በቀድሞው አርሰናል ተጫዋች ፓትሪክ ቪዬራ የሚመሩት ክሪስታል ፓላሶች ደግሞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኙት ኖርዊቾችን ሶስት ለባዶ አሸንፈዋል። ሰኞ ምሽት የተደረገው የማንቸስተር ዩናይርድና የኒውካስል ጨዋታ አንድ አቻ መጠናቀቁ የሚታወስ ነው። ዛሬ ምሽት ደግሞ ቼልሲ ከብራይተን እንዲሁም የሊጉ መሪ ማንቸስተር ሲቲተ ከብሬንትፎር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
በርካታ ተጫዋቾች በኮቪድና በጉዳት ያላሰለፉት ሌስተሮች ሊቨርፑልን አሸነፉ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ትናንት ማክሰኞ ምሽት በሊቨርፑልና ሌስተር ሲቲ መካከል የተደረገው ተጠባቂ ጨዋታ አዴማላ ሉክማን ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ በሌስተር አሸናፊነት ተጠናቋል። በዚህም ሊቨርፑሎች በደረጃ ሰንጠረዡ ከማንቸስተር ሲቲ በስድስት ነጥብ ርቀው ሁለተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል። ሊቨርፑሎች በመጀመሪያው አጋማሽ 15ኛው ደቂቃ ላይ የፍጹም ቅጣት ምት አግኝተው የነበረ ቢሆንም ግብፃዊው ሞሐመድ ሳላህ ወደ ግብነት መቀየር ሳይችል ቀርቷል። የጨዋታው ኮከብ ተጨዋች ተብሎ የተመረጠው የሌስተሩ ግብ ጠባቂ ካስፐር ሹማይክል ኳሷን ከመረብ እንዳትገናኝ አድርጓል። ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔም ቢሆን በርካታ የግብ ዕድሎችን ቢያገኝም ግብ ማስቆጠር ግን አልቻለም። አብዛኛውን የጨዋታ ጊዜ ወደ ግብ ክልላቸው ተስበው ለመከላከል ተገድደው የነበሩት ሌስተሮች 59ኛው ደቂቃ ላይ ያገኙትን ዕድል በአግባቡ ተጠቅመዋል። የቀድሞው የኤቨርተን የፊት መስመር ተጫዋች አዴማላ ሉክማን ተቀይሮ በገባ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ኪረን ደውስብሪ ያሻማለትን ኳስ ወደ ግብነት መቀየር ችሏል። በርካታ የመጀመሪያ ቡድን ተጫዋቾችን በጉዳትና በኮቪድ ምክንያት ያጡት ሌስተሮች በተደጋጋሚ ሊቨርፑሎች ሲያደርጉት የነበረው የማጥቃት ጨዋታ ተቋቁመው አምሽተዋል። ከስድስት ቀናት በፊት በካራባዎ ዋንጫ ሁለቱ ቡድኖች ተገናኝተው የነበረ ሲሆን ሌስተር ሲቲ ቀድሞ 3 ለ 0 መምራት ችሎ ነበር። ነገር ግን በተከታታይ ባስተናገዱት ሦስት ግብ ምክንያት ጨዋታው አቻ ተጠናቆ በፍጹም ቅጣት ምት ሊቨርፑል ማሸነፍ ችሏል። ፕሪምየር ሊጉ ከተጀመረ ሁለተኛ ሽንፈታቸውን ያስተናገዱት ሊቨርፑሎች ከሊጉ መሪ ማንቸስተር ሲቲ በስድስት ነጥብ ርቀው በ41 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በሌላ በኩል ከሰባት ጨዋታዎች ሁለቱን ብቻ ማሸነፍ የቻሉት ሌስተሮች ትናንት ምሽት ሦስት ሙሉ ነጥብ ማግኘታቸውን ተከትሎ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል። በጉዳት ምከንያት ተከላካዮቻቸውን ያጡት ሌስተሮች የመሀል ክፍል ተጫዋቹ ዊልፍሬድ ንዲዲን በተከላካይ መስመር ለማሰለፍ ተገድደው ነበር። ንዲዲም ሞሐመድ ሳላህ ላይ በፈጸመው ጥፋት ቡድኑ ላይ የፍጹም ቅጣት ምት አስሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ግብ ጠባቂው ግን ኳሷ ግብ እንዳትሆን አድርጓል። የሌስተሩ አጥቂ ጄሚ ቫርዲ ምሽቱን ሙሉ ያገኘውን ኳስ ወደ ሊቨርፑል ግብ ክልል ይዞ በመግባት ትልቅ ፈተና ሆኖ አምሽቷል። በመጀመሪያው አጋማሽም ያገኘውን ኳስ ወደ ግብ ቢመታም ተከላካዩ ጆዌል ማቲፕ ተደርቦ ግብ ከመሆን አድኖበታል። ሊቨርፑሎች ከሜዳቸው ውጪ ካደረጓቸው 29 ጨዋታዎች በትናንቱ ጨዋታ ላይ ብቻ ነው ግብ ማስቆጠር ያልቻሉት። የፊታችን እሁድ ከቼልሲ ጋር የሚፋለሙት ሊቨርፑሎች በደረጃ ሰንጠረዡ ከማንቸስተር ሲቲ ያላቸውን ልዩነት ለማጥበብ የሞት የሽረት ትግል እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፉት የሊቨርፑሎቹ ሞሐመድ ሳላህ፣ ሳዲዮ ማኔ እና ናቢ ኬታ ወደ ውድድሩ ከመሄዳቸው በፊት የቼልሲው ጨዋታ የመጨረሻቸው ይሆናል። ትናንት በተካሄዱ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በጥሩ አቋም ላይ የሚገኙት ቶተንሀሞች ከሳውዝሀምፕተን ጋር አንድ አቻ ሲለያዩ ዌስት ሀም ደግሞ ዋትፎርድን 4 ለ1 በማሸነፍ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል መመለስ ችለዋል። በቀድሞው አርሰናል ተጫዋች ፓትሪክ ቪዬራ የሚመሩት ክሪስታል ፓላሶች ደግሞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኙት ኖርዊቾችን ሶስት ለባዶ አሸንፈዋል። ሰኞ ምሽት የተደረገው የማንቸስተር ዩናይርድና የኒውካስል ጨዋታ አንድ አቻ መጠናቀቁ የሚታወስ ነው። ዛሬ ምሽት ደግሞ ቼልሲ ከብራይተን እንዲሁም የሊጉ መሪ ማንቸስተር ሲቲተ ከብሬንትፎር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59802875
0business
ዚምባብዌ የመገበያያ ገንዘቧ መዳከምን ለመቋቋም የወርቅ ሳንቲሞችን ልታስተዋውቅ ነው
ዚምባብዌ የመገበያያ ገንዘቧ ከውጭ ምንዛሬ አንፃር ማሽቆልቆልንና በአገሪቱ የተከሰተውን የዋጋ ግሽበት ለመግታት የወርቅ ሳንቲሞችን ለመገበያያነት እንዲውል ልታደርግ ነው። በተጨማሪም የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ የአሜሪካ ዶላርን ለሚቀጥሉት አምስት አመታት ህጋዊ መገበያያ ለማድረግም ማቀዱን አስታውቋል። አመታዊው የአገሪቱ የዋጋ ግሽበት 190 በመቶ በላይ ከፍ ማለቱን ተከትሎ የማዕከላዊ ባንክ ዋና የወለድ ምጣኔ በዚህ ወር ከእጥፍ በላይ ወደ 200 በመቶ አድጓል። የዚምባብዌ የመገበያያ ገንዘብ ዶላር በዚህ አመት ከሌሎች ከውጭ አገር መገበያያ ገንዘቦች አንፃር በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆል አሳይቷል። አንድ ትሮይ አውንስ ብዛት ያላቸው 22 ካራት ወርቅ የሆኑ የወርቅ ሳንቲሞች በያዝነው ወር መጨረሻ በገበያ ላይ እንደሚውሉ የዚምባብዌ ሪዘርቭ ባንክ ገዥ የሆኑት ጆን ፒ ማንጉዲያ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ትሮይ አውንስ የከበረ ማዕድናትን እንደ ወርቅ፣ ብር እና ፕላቲኒየም የመሳሰሉትን ለመመዘን የሚያገለግል የመለኪያ አሃድ ነው። መለኪያው ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ የነበረ ሲሆን አንድ ትሮይ አውንስ ከ31.10 ግራም ጋር እኩል ነው። “የወርቅ ሳንቲሞቹ በአለም አቀፍ የወርቅ ዋጋ እና በተመረተበት ዋጋም በበመስረት ለህዝቡ በአገር ውስጥ ምንዛሬ፣ በዶላር እና በሌሎች አገራት የውጭ ምንዛሬዎች ለሽያጭ ይቀርባሉ" ብለዋል ማንጉዲያ መግለጫው በተጨማሪም ለእያንዳንዱ የወርቅ ሳንቲም መለያ ቁጥር የሚሰጣቸው ሲሆንም ሳንቲሞቹንም  በቀላሉ ወደ ጥሬ ገንዘብ በአገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ እንደሚለወጥም ገልጿል። በዚምባብዌ እና ዛምቢያ አዋሳኝ ላይ የሚገኘውን የቪክቶሪያ ፏፏቴንም ስያሜ በመውሰድ "ሞሲ-ኦአ-ቱኒያ” የወርቅ ሳንቲም" የሚል ስም ተሰጥቶታል። የወርቅ ሳንቲሞቹ ወደ ገበያ መምጣት የዚምባብዌ መንግስት የሀገሪቱን የመገበያያ ገንዘብ ቀውስ ለመቅረፍ የወሰደው እርምጃ አካል ነው።
ዚምባብዌ የመገበያያ ገንዘቧ መዳከምን ለመቋቋም የወርቅ ሳንቲሞችን ልታስተዋውቅ ነው ዚምባብዌ የመገበያያ ገንዘቧ ከውጭ ምንዛሬ አንፃር ማሽቆልቆልንና በአገሪቱ የተከሰተውን የዋጋ ግሽበት ለመግታት የወርቅ ሳንቲሞችን ለመገበያያነት እንዲውል ልታደርግ ነው። በተጨማሪም የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ የአሜሪካ ዶላርን ለሚቀጥሉት አምስት አመታት ህጋዊ መገበያያ ለማድረግም ማቀዱን አስታውቋል። አመታዊው የአገሪቱ የዋጋ ግሽበት 190 በመቶ በላይ ከፍ ማለቱን ተከትሎ የማዕከላዊ ባንክ ዋና የወለድ ምጣኔ በዚህ ወር ከእጥፍ በላይ ወደ 200 በመቶ አድጓል። የዚምባብዌ የመገበያያ ገንዘብ ዶላር በዚህ አመት ከሌሎች ከውጭ አገር መገበያያ ገንዘቦች አንፃር በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆል አሳይቷል። አንድ ትሮይ አውንስ ብዛት ያላቸው 22 ካራት ወርቅ የሆኑ የወርቅ ሳንቲሞች በያዝነው ወር መጨረሻ በገበያ ላይ እንደሚውሉ የዚምባብዌ ሪዘርቭ ባንክ ገዥ የሆኑት ጆን ፒ ማንጉዲያ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ትሮይ አውንስ የከበረ ማዕድናትን እንደ ወርቅ፣ ብር እና ፕላቲኒየም የመሳሰሉትን ለመመዘን የሚያገለግል የመለኪያ አሃድ ነው። መለኪያው ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ የነበረ ሲሆን አንድ ትሮይ አውንስ ከ31.10 ግራም ጋር እኩል ነው። “የወርቅ ሳንቲሞቹ በአለም አቀፍ የወርቅ ዋጋ እና በተመረተበት ዋጋም በበመስረት ለህዝቡ በአገር ውስጥ ምንዛሬ፣ በዶላር እና በሌሎች አገራት የውጭ ምንዛሬዎች ለሽያጭ ይቀርባሉ" ብለዋል ማንጉዲያ መግለጫው በተጨማሪም ለእያንዳንዱ የወርቅ ሳንቲም መለያ ቁጥር የሚሰጣቸው ሲሆንም ሳንቲሞቹንም  በቀላሉ ወደ ጥሬ ገንዘብ በአገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ እንደሚለወጥም ገልጿል። በዚምባብዌ እና ዛምቢያ አዋሳኝ ላይ የሚገኘውን የቪክቶሪያ ፏፏቴንም ስያሜ በመውሰድ "ሞሲ-ኦአ-ቱኒያ” የወርቅ ሳንቲም" የሚል ስም ተሰጥቶታል። የወርቅ ሳንቲሞቹ ወደ ገበያ መምጣት የዚምባብዌ መንግስት የሀገሪቱን የመገበያያ ገንዘብ ቀውስ ለመቅረፍ የወሰደው እርምጃ አካል ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cw83xygz5x6o
2health
ከፍተኛው እራስን የማጥፋት ቁጥር በአፍሪካ እንደተመዘገበ የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ
በመላው ዓለም ከሚመዘገበው እራስን የማጥፋት ክስተት ከፍተኛ ቁጥር ያለው አፍሪካ አህጉር ውስጥ እንደሚፈጸም የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸ። እንደ ድርጅቱ መግለጫ ከሆነ በዓለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር ከተመዘገበባቸው አስር አገራት ስድስቱ የሚገኙት በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ነው። በአህጉሪቱ የሥነ አእምሮ ህክም እና ድጋፍ የሚሰጡ ባለሙያዎች ቁጥርም እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ገልጿል። በዚህም በአፍሪካ ውስጥ አንድ ሳይኪያትሪስት ሐኪም ለግማሽ ሚሊዮን ያህል ሰዎች አገልግሎት ይሰጣል። ይህ ደግሞ የዓለም ጤና ድርጅት ከሚያስቀምጠው የባለሙያና የተጠቃሚዎች ምጥጥን አሃዝ በአንድ መቶ እጥፍ ያነሰ ነው። በአፍሪካ ከሚኖሩ 100,000 ሰዎች ውስጥ 11 ሰዎች እራሳቸውን ያጠፋሉ ተብሎ የተመዘገበ ሲሆን፣ ይህ ቁጥር በዓለም ላይ አማካይ ነው ተብሎ ከተቀመጠው ከ100,000 ሺህ ዘጠኝ ሰዎች እራሳቸውን የማጥፋት ክስተት አኳያ ከፍተኛው እንደሆነ የመንግሥታቱ ድርጅት የጤና ተቋም ገልጿል። ለሰዎች እራስን የማጥፋት ድርጊት እንደምክንያት በቀዳሚነት የተቀመጠው የአእምሮ ጤና ችግር ሲሆን፣ ይህም አስከ 11 በመቶ ለሚሆኑት ሰበብ እንደሆነ ተነግሯል። የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው በአፍሪካ አህጉር ውስጥ የአእምሮ ጤና ባለሙያዎች በአብዛኛው የሚገኙት በከተሞች አካባቢ ስለሚሆን፣ በገጠሩ ክፍል ያሉ ነዋሪዎች አገለግሎቱን የማግኘት ዕድላቸውን ያጠበዋል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ክልል ዳይሬክተር የሆኑት ማስሂዲሶ ሞኤቲ እንደሚሉት፣ በአገራት የጤና ፕሮግራሞች ውስጥ የአእምሮ ጤና ችግሮችን የመከላከሉ አማራጭ ቅድሚያ ስለማይሰጠው እራስን የማጥፋት ሁኔታ ዋነኛ የኅብረተሰብ ጤና እክል ሆኗል። እራስን የማጥፋትን ክስተቶች ለመከላከል ግንዛቤን ለመፍጠርና እርምጃዎች እንዲወሰዱ ለማበረታታት የዓለም የጤና ድርጅት በአሁኑ ወቅት በአህጉሪቱ ውስጥ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እኣካሄደ ነው። ይህ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የተጀመረው በመጪው መስከረም 30 ከሚከበረው የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን ቀደም ብሎ ነው። በዚህም ዘመቻው የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ አህጉር ውስጥ 10 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ጋር መልዕክቱን ለማድረስ አቅዶ እየሰራ ነው።
ከፍተኛው እራስን የማጥፋት ቁጥር በአፍሪካ እንደተመዘገበ የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ በመላው ዓለም ከሚመዘገበው እራስን የማጥፋት ክስተት ከፍተኛ ቁጥር ያለው አፍሪካ አህጉር ውስጥ እንደሚፈጸም የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸ። እንደ ድርጅቱ መግለጫ ከሆነ በዓለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር ከተመዘገበባቸው አስር አገራት ስድስቱ የሚገኙት በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ነው። በአህጉሪቱ የሥነ አእምሮ ህክም እና ድጋፍ የሚሰጡ ባለሙያዎች ቁጥርም እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ገልጿል። በዚህም በአፍሪካ ውስጥ አንድ ሳይኪያትሪስት ሐኪም ለግማሽ ሚሊዮን ያህል ሰዎች አገልግሎት ይሰጣል። ይህ ደግሞ የዓለም ጤና ድርጅት ከሚያስቀምጠው የባለሙያና የተጠቃሚዎች ምጥጥን አሃዝ በአንድ መቶ እጥፍ ያነሰ ነው። በአፍሪካ ከሚኖሩ 100,000 ሰዎች ውስጥ 11 ሰዎች እራሳቸውን ያጠፋሉ ተብሎ የተመዘገበ ሲሆን፣ ይህ ቁጥር በዓለም ላይ አማካይ ነው ተብሎ ከተቀመጠው ከ100,000 ሺህ ዘጠኝ ሰዎች እራሳቸውን የማጥፋት ክስተት አኳያ ከፍተኛው እንደሆነ የመንግሥታቱ ድርጅት የጤና ተቋም ገልጿል። ለሰዎች እራስን የማጥፋት ድርጊት እንደምክንያት በቀዳሚነት የተቀመጠው የአእምሮ ጤና ችግር ሲሆን፣ ይህም አስከ 11 በመቶ ለሚሆኑት ሰበብ እንደሆነ ተነግሯል። የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው በአፍሪካ አህጉር ውስጥ የአእምሮ ጤና ባለሙያዎች በአብዛኛው የሚገኙት በከተሞች አካባቢ ስለሚሆን፣ በገጠሩ ክፍል ያሉ ነዋሪዎች አገለግሎቱን የማግኘት ዕድላቸውን ያጠበዋል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ክልል ዳይሬክተር የሆኑት ማስሂዲሶ ሞኤቲ እንደሚሉት፣ በአገራት የጤና ፕሮግራሞች ውስጥ የአእምሮ ጤና ችግሮችን የመከላከሉ አማራጭ ቅድሚያ ስለማይሰጠው እራስን የማጥፋት ሁኔታ ዋነኛ የኅብረተሰብ ጤና እክል ሆኗል። እራስን የማጥፋትን ክስተቶች ለመከላከል ግንዛቤን ለመፍጠርና እርምጃዎች እንዲወሰዱ ለማበረታታት የዓለም የጤና ድርጅት በአሁኑ ወቅት በአህጉሪቱ ውስጥ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እኣካሄደ ነው። ይህ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የተጀመረው በመጪው መስከረም 30 ከሚከበረው የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን ቀደም ብሎ ነው። በዚህም ዘመቻው የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ አህጉር ውስጥ 10 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ጋር መልዕክቱን ለማድረስ አቅዶ እየሰራ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cerdy21nxvgo
0business
በአፍሪካ የነዳጅ ዋጋ ሊጨምር እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ
የዓለም ነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ተከትሎ በቀጣይ ሳምንታት በአፍሪካ የነዳጃ ዋጋ በተመሳሳይ ሊጨምር እንደሚችል ባለሙያዎች አመለከቱ። ትናንት ማክሰኞ የአንድ ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በበርሜል 80 የአሜሪካ ዶላር ደርሶ ነበር። ይህም ከሦስት ዓመት ወዲህ የተመዘገበ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ነው ተብሏል። ዓለም ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጫናዎች መላቀቅ ስትጀምር የምጣኔ ሐብት እንቅስቃሴዎች እየተነቃቁ ነው። ይህን ተከትሎም የነዳጅ ፍላጎት ጣራ እየነካ ነው። የዘርፉ ባለሙያዎች አሁን ላይ ለታየው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አንዱ ምክንያት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ የምጣኔ ሐብት እንቅስቃሴዎች መጨመሩ ነው ይላሉ። የምጣኔ ሐብት ባለሙያው ፓትሪክ ኦባታ፤ የነዳጅ ፍላጎቱ በተለየ በአሜሪካ እና አውሮፓ እየጨመረ ስለሚቀጥል የዋጋ ጭማሪው ለወራት ሊዘልቅ እንደሚችል ያስረዳሉ። በዚህም ምክንያት ነዳጅ አምራች ያልሆኑ አገራት የኃይል ምንጫቸውን ፍላጎት ለማስተካከል በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ሊያደርጉ ይችላሉ ይላሉ። ሌላኛው የምጣኔ ሐብት ባለሙያ ኬን ጊቺንጋ፤ በምጣኔ ሐብት እድገት ውስጥ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ሚና ስላለው የነዳጅ ዋጋ ሲጨመር የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋም አብሮ ይጨምራል በማለት ያስረዳሉ። የነዳጅ አምራች እና ላኪ አገራት ጥምረት የሆነው ኦፔክ በቀጣይ ሳምንት ይመክራል ተብሏል። የኦፔክ አባላት በቀጣይ ሳምንት ውይይታቸው የነዳጅ አቅርቦትን መጠን ከፍ ለማድረግ ከውሳኔ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። የምጣኔ ሐብት ባለሙያው ማይክል ፋሞሮቲ በቀጣይ ለዓለም ገበያ የሚቀርበው የነዳጅ መጠን በኦፔክ አባላት የሚወሰን ይሆናል ይላሉ። ነዳጅ አምራች እና ላኪ አገራት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ተከትሎ ተቀዛቅዞ የነበረውን የነዳጅ አቅርቦት መጠን፤ አምራች አገራት የምርት መጠናቸውን ከፍ እንዲያደርጉ በመፍቀድ የነዳጅ ዋጋ እንዲረጋጋ ሊያደርጉ ይችላሉ ሲሉ ይተነብያሉ። "ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት ኦፔክ ጠንከር ያለ እርምጃ ይወስዳል ብዬ እጠብቃለሁ" ብለዋል የምጣኔ ሐብት ባለሙያው ማይክል ፋሞሮቲ።
በአፍሪካ የነዳጅ ዋጋ ሊጨምር እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ የዓለም ነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ተከትሎ በቀጣይ ሳምንታት በአፍሪካ የነዳጃ ዋጋ በተመሳሳይ ሊጨምር እንደሚችል ባለሙያዎች አመለከቱ። ትናንት ማክሰኞ የአንድ ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በበርሜል 80 የአሜሪካ ዶላር ደርሶ ነበር። ይህም ከሦስት ዓመት ወዲህ የተመዘገበ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ነው ተብሏል። ዓለም ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጫናዎች መላቀቅ ስትጀምር የምጣኔ ሐብት እንቅስቃሴዎች እየተነቃቁ ነው። ይህን ተከትሎም የነዳጅ ፍላጎት ጣራ እየነካ ነው። የዘርፉ ባለሙያዎች አሁን ላይ ለታየው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አንዱ ምክንያት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ የምጣኔ ሐብት እንቅስቃሴዎች መጨመሩ ነው ይላሉ። የምጣኔ ሐብት ባለሙያው ፓትሪክ ኦባታ፤ የነዳጅ ፍላጎቱ በተለየ በአሜሪካ እና አውሮፓ እየጨመረ ስለሚቀጥል የዋጋ ጭማሪው ለወራት ሊዘልቅ እንደሚችል ያስረዳሉ። በዚህም ምክንያት ነዳጅ አምራች ያልሆኑ አገራት የኃይል ምንጫቸውን ፍላጎት ለማስተካከል በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ሊያደርጉ ይችላሉ ይላሉ። ሌላኛው የምጣኔ ሐብት ባለሙያ ኬን ጊቺንጋ፤ በምጣኔ ሐብት እድገት ውስጥ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ሚና ስላለው የነዳጅ ዋጋ ሲጨመር የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋም አብሮ ይጨምራል በማለት ያስረዳሉ። የነዳጅ አምራች እና ላኪ አገራት ጥምረት የሆነው ኦፔክ በቀጣይ ሳምንት ይመክራል ተብሏል። የኦፔክ አባላት በቀጣይ ሳምንት ውይይታቸው የነዳጅ አቅርቦትን መጠን ከፍ ለማድረግ ከውሳኔ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። የምጣኔ ሐብት ባለሙያው ማይክል ፋሞሮቲ በቀጣይ ለዓለም ገበያ የሚቀርበው የነዳጅ መጠን በኦፔክ አባላት የሚወሰን ይሆናል ይላሉ። ነዳጅ አምራች እና ላኪ አገራት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ተከትሎ ተቀዛቅዞ የነበረውን የነዳጅ አቅርቦት መጠን፤ አምራች አገራት የምርት መጠናቸውን ከፍ እንዲያደርጉ በመፍቀድ የነዳጅ ዋጋ እንዲረጋጋ ሊያደርጉ ይችላሉ ሲሉ ይተነብያሉ። "ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት ኦፔክ ጠንከር ያለ እርምጃ ይወስዳል ብዬ እጠብቃለሁ" ብለዋል የምጣኔ ሐብት ባለሙያው ማይክል ፋሞሮቲ።
https://www.bbc.com/amharic/news-58723014
2health
ቦሪስ ጆንሰን ክትባቱ በመላው ዓለም እንዲዳረስ ኃያላን አገራት ላይ ጫና ሊያደርጉ ነው
የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እስከ ቀጣዩ የአውሮፓዊያን ዓመት መጨረሻ ድረስ በመላው ዓለም የኮሮናቫይረስ ክትባት እንዲዳረስ ጫና ለማድረግ መዘጋጀታቸው ተሰማ። በመጪው አርብ በአገራቸው በሚደረገው የቡድን ሰባት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ይህንን እቅዳቸውን ያቀርባሉ ተብሎም ይጠበቃል። አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣልያን እና ጃፓን ለዓለም አቀፉ የፍትሃዊ የክትባት ማከፋፈያ ፕሮግራም ኮቫክስ ምን ያህል ክትባት እንደሚያጋሩ ይፋ አድርገዋል። እንግሊዝ እና ካናዳ ግን ምን ያህል አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉ እስካሁን ይፋ አላደረጉም። ከኮሮናቫይረስ ጋር እየተደረገ ያለውን ፍልሚያ በስኬት ለማጠናቀቅ እስከሚቀጥለው ዓመት መጨረሻ በመላው ዓለም ክትባቱን ለማዳረስ ቦሪስ ለመሪዎቹ በኮርንዌሉ ጉባኤ ላይ ጥሪ ያቀርባሉ። እንዲህ ዓይነቱ ስኬት ‹‹በሕክምና ታሪክ ውስጥ ብቸኛና ታላቁ›› ይሆናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ። አገራቸው ዩናይትድ ኪንግደም ክትባቱን የማምረት ምጣኔን እንዴት ከፍ ማድረግ እንደሚቻል የሚደረጉ ውይይቶችን እንደምታበረታታም ተገልጿል። የቡድን ሰባት የመሪዎች ጉባኤ ከወረርሺኙ መከሰት በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ ገፅ ለገፅ የሚደረግ ሲሆን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ከተረከቡ በኋላ ወደ እንግሊዝ የሚያደርጉት የመጀመሪያ ጉብኝት ይሆናል ። እንግሊዝ ምን ያህል ክትባት ለኮቫክስ እንደምታበረክት በጉባኤው ላይ ይፋ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል። ባለፈው ሳምንት የፓርላማ አባላት ብሎም የአገራት መሪዎች እንግሊዝ የተያዘው የፈረንጆች አመት እስከሚጠናቀቅ ድረስ ቢያንስ 100 ሚሊዮን ክትባት እንድታበረክት ደብዳቤዎችን እንደፃፉላቸው ይታወሳል። የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር በበኩላቸው ‹‹እውነታው›› መንግስታት ‹‹የራሳቸውን ሰዎች የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው››፤ ሁል ጊዜም ለራሳቸው ዜጎች ክትባት ቅድሚያ ይሰጣሉ ሲሉ መናገራቸውም ይታወሳል። አክለውም በዚህ ጉዳይ ፍፁም መሆን አይቻልም፤ ከመዳረሱ በፊትም የተወሰነ ክትባት መለግስ ይቻላልም ብለዋል።
ቦሪስ ጆንሰን ክትባቱ በመላው ዓለም እንዲዳረስ ኃያላን አገራት ላይ ጫና ሊያደርጉ ነው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እስከ ቀጣዩ የአውሮፓዊያን ዓመት መጨረሻ ድረስ በመላው ዓለም የኮሮናቫይረስ ክትባት እንዲዳረስ ጫና ለማድረግ መዘጋጀታቸው ተሰማ። በመጪው አርብ በአገራቸው በሚደረገው የቡድን ሰባት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ይህንን እቅዳቸውን ያቀርባሉ ተብሎም ይጠበቃል። አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣልያን እና ጃፓን ለዓለም አቀፉ የፍትሃዊ የክትባት ማከፋፈያ ፕሮግራም ኮቫክስ ምን ያህል ክትባት እንደሚያጋሩ ይፋ አድርገዋል። እንግሊዝ እና ካናዳ ግን ምን ያህል አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉ እስካሁን ይፋ አላደረጉም። ከኮሮናቫይረስ ጋር እየተደረገ ያለውን ፍልሚያ በስኬት ለማጠናቀቅ እስከሚቀጥለው ዓመት መጨረሻ በመላው ዓለም ክትባቱን ለማዳረስ ቦሪስ ለመሪዎቹ በኮርንዌሉ ጉባኤ ላይ ጥሪ ያቀርባሉ። እንዲህ ዓይነቱ ስኬት ‹‹በሕክምና ታሪክ ውስጥ ብቸኛና ታላቁ›› ይሆናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ። አገራቸው ዩናይትድ ኪንግደም ክትባቱን የማምረት ምጣኔን እንዴት ከፍ ማድረግ እንደሚቻል የሚደረጉ ውይይቶችን እንደምታበረታታም ተገልጿል። የቡድን ሰባት የመሪዎች ጉባኤ ከወረርሺኙ መከሰት በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ ገፅ ለገፅ የሚደረግ ሲሆን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ከተረከቡ በኋላ ወደ እንግሊዝ የሚያደርጉት የመጀመሪያ ጉብኝት ይሆናል ። እንግሊዝ ምን ያህል ክትባት ለኮቫክስ እንደምታበረክት በጉባኤው ላይ ይፋ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል። ባለፈው ሳምንት የፓርላማ አባላት ብሎም የአገራት መሪዎች እንግሊዝ የተያዘው የፈረንጆች አመት እስከሚጠናቀቅ ድረስ ቢያንስ 100 ሚሊዮን ክትባት እንድታበረክት ደብዳቤዎችን እንደፃፉላቸው ይታወሳል። የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር በበኩላቸው ‹‹እውነታው›› መንግስታት ‹‹የራሳቸውን ሰዎች የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው››፤ ሁል ጊዜም ለራሳቸው ዜጎች ክትባት ቅድሚያ ይሰጣሉ ሲሉ መናገራቸውም ይታወሳል። አክለውም በዚህ ጉዳይ ፍፁም መሆን አይቻልም፤ ከመዳረሱ በፊትም የተወሰነ ክትባት መለግስ ይቻላልም ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57381197
5sports
የቺሊ ብሔራዊ ቡድን ሊሰልለኝ ነበር ያለውን ድሮን ቢጥልም ስህተት መሥራቱ ታወቀ
በሩጫው የስፖርት መስክ ኢትዮጵያና ኬንያ ተቀናቃኞች እንደሆኑት ሁሉ የደቡብ አሜሪካ አገራት የሆኑት ቺሊና አርጀንቲና ደግሞ ለዘመናት በእግር ኳስ ውድድር ተቀናቃኝነታቸው ይታወቃሉ። ለዚህም ነው ሁለቱ አገራት ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዛሬ ሐሙስ ከሚያደርጉት ግጥሚያ ቀደም ብሎ የቺሊ ብሔራዊ ቡድን ልምምድ በሚያደርግበት ሜዳ ላይ አንዲት ድሮን ስታንጃብብ ጥርጣሬ የተፈጠረው። በዚህ ጊዜ የቺሉ ቡድን የገመተው አርጀንቲናውያኑ ተቀናቃኞቻቸው ድሮን አሰማርተው እየሰለሏቸው እንደሆነ ነበር። በምላሹም የእራሳቸውን ድሮን ልከው "ሊሰልለን መጥቷል" ያሉትን ድሮን በቁጥጥር ስር አዋሉት። ነገር ግን ድሮኑ እነሱ እንደጠረጠሩት የአርጀንቲናውያን ሳይሆን የአንድ የአገራቸው የኃይል አቅራቢ ኩባንያ ንብረት ሆኖ አግኝተውታል። ይህ የተከሰተው ቺሊና አርጀንቲና ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ሐሙስ ዕለት ከሚያደርጉት ጨዋታ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ነበር። የቺሊ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ለዛሬው ውድድር ለመዘጋጀት በዋና ከተማዋ ሳንቲያጎ ውስጥ በሚገኝ ስታዲየም ልምምድ እያደረጉ ሳለ ነበር "የስለላ" ነው ያሉት ድሮንን የተመለከቱት። የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት የቡድኑ አሰልጣኝ ማርቲን ላዛርቴ ናቸው የአጠራጣሪውን ድሮን ምንነት ለማወቅ የራሳቸውን ድሮን በማብረር እርምጃ የወሰዱት። በዚህም ሁለቱ ድሮኖች አየር ላይ ተጋጩ በስፍራው የነበሩ ጋዜጠኞች እንደተናገሩት ሆን ተብሎ የተፈጠረ ግጭት ነበር። በዚህም ሰላይ የተባለው ድሮን ወደ መሬት ወደቀ። ሲጣራም ድሮኑ አርጀንቲናውያን የቺሊን ብሔራዊ ቡድን ለመሰለል ያሰማሩት ሳይሆን 'ኤኔል' የተባለው ኩባንያ በአካባቢው ለሥራ ያሰማራው እንደሆነ ተደረሰበት። በድሮን አማካይነት በእግር ኳስ ቡድኖች ላይ የሚደረግ ስለላን በተመለከተ ሲነገር ይህ የመጀመሪያው አይደለም። አሰልጣኞችም በዚህ ዙሪያ ቀደም ሲል ቅሬታ አሰምተዋል። ከእነዚህም መካከል ከስድስት ዓመታት በፊት የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበረው ዲዲየ ዴሾ ብራዚል ውስጥ በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ወቅት ቡድኑ ከሆንዱራስ ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት በልምምድ ስፍራ ላይ ሲንዣብብ የነበረን ድሮን በተመለከተ ፊፋ ምርመራ እንዲያደርግ ጠይቆ ነበር። በተመሳሳይ እአአ 2017 ላይ ሆንዱራስ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በምትዘጋጅበት ጊዜ አውስትራሊያ ድሮን አሰማርታ ቡድኔን እየሰለለች ነው በማለት ክስ አቅርባ ነበር። በተጨማሪም ቡድኑ ክስተቱን የሚያሳይ ቪዲዮ በትዊተር ላይ አሰራጭቶ ነበር። ከአገራት ብሔራዊ ቡድኖች በተጨማሪም ታላላቅ ክለቦች ተመሳሳይ ነገር እንዳጋጠማቸው ተነግሯል። የጀርመኑ ወርደ ብሬመን ክለብ ከሦስት ዓመት በፊት በተቀናቃኙ ሆፈንሃይም ቡድን የልምምድ ሜዳ ላይ ድሮን እንዲያንዣብብ ማድረጉን አምኖ ለድርጊቱ ይቅርታ ጠይቆ ነበር። አሁን አሁን በድሮን አማካይነት በቡድኖች ላይ የሚደረግ ስለላን በተመለከተ የሚቀርቡ ክሶች እየተለመዱ የመጡ ሲሆን፤ አንዳንድ የቡድን አሰልጣኞች ግን አሁንም የቆየውን ተቀናቃኞቻቸውን የመሰለል መንገድን እየተጠቀሙ እንደሆነ ይነገራል። ከሁለት ዓመት በፊት በአውሮፓውያኑ 2019 የእንግሊዙ ሊድስ ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ማርሴሎ ቢየልሳ ተቀናቃኛቸው የሆነውን ደርቢ ካውንቲ እንዲሰልልላቸው አንድ የቡድኑን አባል ወደ ልምምድ ሜዳ መላካቸውን ተከትሎ ቡድኑ ይቅርታ መጠየቁ ይታወሳል።
የቺሊ ብሔራዊ ቡድን ሊሰልለኝ ነበር ያለውን ድሮን ቢጥልም ስህተት መሥራቱ ታወቀ በሩጫው የስፖርት መስክ ኢትዮጵያና ኬንያ ተቀናቃኞች እንደሆኑት ሁሉ የደቡብ አሜሪካ አገራት የሆኑት ቺሊና አርጀንቲና ደግሞ ለዘመናት በእግር ኳስ ውድድር ተቀናቃኝነታቸው ይታወቃሉ። ለዚህም ነው ሁለቱ አገራት ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዛሬ ሐሙስ ከሚያደርጉት ግጥሚያ ቀደም ብሎ የቺሊ ብሔራዊ ቡድን ልምምድ በሚያደርግበት ሜዳ ላይ አንዲት ድሮን ስታንጃብብ ጥርጣሬ የተፈጠረው። በዚህ ጊዜ የቺሉ ቡድን የገመተው አርጀንቲናውያኑ ተቀናቃኞቻቸው ድሮን አሰማርተው እየሰለሏቸው እንደሆነ ነበር። በምላሹም የእራሳቸውን ድሮን ልከው "ሊሰልለን መጥቷል" ያሉትን ድሮን በቁጥጥር ስር አዋሉት። ነገር ግን ድሮኑ እነሱ እንደጠረጠሩት የአርጀንቲናውያን ሳይሆን የአንድ የአገራቸው የኃይል አቅራቢ ኩባንያ ንብረት ሆኖ አግኝተውታል። ይህ የተከሰተው ቺሊና አርጀንቲና ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ሐሙስ ዕለት ከሚያደርጉት ጨዋታ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ነበር። የቺሊ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ለዛሬው ውድድር ለመዘጋጀት በዋና ከተማዋ ሳንቲያጎ ውስጥ በሚገኝ ስታዲየም ልምምድ እያደረጉ ሳለ ነበር "የስለላ" ነው ያሉት ድሮንን የተመለከቱት። የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት የቡድኑ አሰልጣኝ ማርቲን ላዛርቴ ናቸው የአጠራጣሪውን ድሮን ምንነት ለማወቅ የራሳቸውን ድሮን በማብረር እርምጃ የወሰዱት። በዚህም ሁለቱ ድሮኖች አየር ላይ ተጋጩ በስፍራው የነበሩ ጋዜጠኞች እንደተናገሩት ሆን ተብሎ የተፈጠረ ግጭት ነበር። በዚህም ሰላይ የተባለው ድሮን ወደ መሬት ወደቀ። ሲጣራም ድሮኑ አርጀንቲናውያን የቺሊን ብሔራዊ ቡድን ለመሰለል ያሰማሩት ሳይሆን 'ኤኔል' የተባለው ኩባንያ በአካባቢው ለሥራ ያሰማራው እንደሆነ ተደረሰበት። በድሮን አማካይነት በእግር ኳስ ቡድኖች ላይ የሚደረግ ስለላን በተመለከተ ሲነገር ይህ የመጀመሪያው አይደለም። አሰልጣኞችም በዚህ ዙሪያ ቀደም ሲል ቅሬታ አሰምተዋል። ከእነዚህም መካከል ከስድስት ዓመታት በፊት የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበረው ዲዲየ ዴሾ ብራዚል ውስጥ በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ወቅት ቡድኑ ከሆንዱራስ ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት በልምምድ ስፍራ ላይ ሲንዣብብ የነበረን ድሮን በተመለከተ ፊፋ ምርመራ እንዲያደርግ ጠይቆ ነበር። በተመሳሳይ እአአ 2017 ላይ ሆንዱራስ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በምትዘጋጅበት ጊዜ አውስትራሊያ ድሮን አሰማርታ ቡድኔን እየሰለለች ነው በማለት ክስ አቅርባ ነበር። በተጨማሪም ቡድኑ ክስተቱን የሚያሳይ ቪዲዮ በትዊተር ላይ አሰራጭቶ ነበር። ከአገራት ብሔራዊ ቡድኖች በተጨማሪም ታላላቅ ክለቦች ተመሳሳይ ነገር እንዳጋጠማቸው ተነግሯል። የጀርመኑ ወርደ ብሬመን ክለብ ከሦስት ዓመት በፊት በተቀናቃኙ ሆፈንሃይም ቡድን የልምምድ ሜዳ ላይ ድሮን እንዲያንዣብብ ማድረጉን አምኖ ለድርጊቱ ይቅርታ ጠይቆ ነበር። አሁን አሁን በድሮን አማካይነት በቡድኖች ላይ የሚደረግ ስለላን በተመለከተ የሚቀርቡ ክሶች እየተለመዱ የመጡ ሲሆን፤ አንዳንድ የቡድን አሰልጣኞች ግን አሁንም የቆየውን ተቀናቃኞቻቸውን የመሰለል መንገድን እየተጠቀሙ እንደሆነ ይነገራል። ከሁለት ዓመት በፊት በአውሮፓውያኑ 2019 የእንግሊዙ ሊድስ ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ማርሴሎ ቢየልሳ ተቀናቃኛቸው የሆነውን ደርቢ ካውንቲ እንዲሰልልላቸው አንድ የቡድኑን አባል ወደ ልምምድ ሜዳ መላካቸውን ተከትሎ ቡድኑ ይቅርታ መጠየቁ ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57306934
2health
ሲዲሲ የኮቪድ-19 ክትባት የሚሰራጭበት መንገድ ላይ የአሜሪካ ግዛቶች ቀድመው እንዲዘጋጁ አሳሰበ
የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) የአሜሪካ ግዛቶች የጤና ኃላፊዎች የኮሮናቫይረስ ክትባት የበለጠ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ቀድሞ የሚታደልበት አማራጭ ላይ ቀድመው እንዲዘጋጁ ማሳሰቡ ተነገረ። ሲዲሲ ትናንት በድረ-ገጹ ላይ ባወጣው ጽሑፍ ላይ ክትባቱ ለበሽታው የበለጠ ተጋለጭ ለሆኑ ሰዎች እስከ ጥቅምት አጋማሽ ሊሰራጭ እንደሚችል ጠቁሟል። “ሲዲሲ ግዛቶች ቀድመው እንዲዘጋጁ በማሰብ ዝግጁ ሊሆን የሚችል የክትባት መጠን እና ጊዜን ለግዛቶች አሳውቋል። ከጥቅምት አጋማሽ እስከ ሕዳር መጨረሻ ድረስ መጠናቸው አነስተኛ ቢሆንም የክትባት ስርጭት ሊኖር ይችላል” ሲሉ የሲዲሲ ቃል አቀባይ ለሬውተርስ ተናግረዋል። ኒው ዮርክ ታይመስ ደግሞ ቀደም ሲል ሲዲሲ ከሁሉም 50 የአሜሪካ ግዛቶች እና አምስት ግዙፍ ከተሞች ከስርጭት ጋር ተያይዞ ያሉ የእቅድ መረጃዎችን ጠይቋል። በኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ ላይ ሲዲሲ ጥቅምት አጋማሽ ላይ በቁጥር አነስተኛ የሆኑ አንድ ወይም ሁለት የኮቪድ-19 ክትባቶች ለስርጭት ዝግጁ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁሟል። ለበሽታው የበለጠ ተጋላጭ ናቸው ለተባሉ እንደ የጤና ባለሙያዎች፣ ለደህንነት ሰራተኞች እና እድሜያቸው የገፉ ሰዎችን የሚንከባከቡ ነርሶች እና ባልደረቦች ክትባቱ ያለ ክፍያ ይሰጣቸዋል ይላል የሲዲሲው ዶክመንት። የተላላፊ በሽታዎች ባለሙያው ዶ/ር አንቶኒዮ ፋውቺ ለኤምኤስኤንቢሲ ቴሌቪዥን ትናንት ሲናገሩ፤ ለኮቪድ-19 ክትባት ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥርን ከግምት በማስገባት እስከ ሕዳር ወር ድረስ የትኛው የኮቪድ-19 ክትባት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ እንደሚሆን መለየት ይቻላል ብለዋል። ሞደርና፣ አስትራዜኔካ እና ፐፊዘር የተሰኙ መድሃኒት አምራቾች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ የሆነ የኮቪድ-19 ክትባት ለማዘጋጀት ጥረት ላይ ይገኛሉ።
ሲዲሲ የኮቪድ-19 ክትባት የሚሰራጭበት መንገድ ላይ የአሜሪካ ግዛቶች ቀድመው እንዲዘጋጁ አሳሰበ የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) የአሜሪካ ግዛቶች የጤና ኃላፊዎች የኮሮናቫይረስ ክትባት የበለጠ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ቀድሞ የሚታደልበት አማራጭ ላይ ቀድመው እንዲዘጋጁ ማሳሰቡ ተነገረ። ሲዲሲ ትናንት በድረ-ገጹ ላይ ባወጣው ጽሑፍ ላይ ክትባቱ ለበሽታው የበለጠ ተጋለጭ ለሆኑ ሰዎች እስከ ጥቅምት አጋማሽ ሊሰራጭ እንደሚችል ጠቁሟል። “ሲዲሲ ግዛቶች ቀድመው እንዲዘጋጁ በማሰብ ዝግጁ ሊሆን የሚችል የክትባት መጠን እና ጊዜን ለግዛቶች አሳውቋል። ከጥቅምት አጋማሽ እስከ ሕዳር መጨረሻ ድረስ መጠናቸው አነስተኛ ቢሆንም የክትባት ስርጭት ሊኖር ይችላል” ሲሉ የሲዲሲ ቃል አቀባይ ለሬውተርስ ተናግረዋል። ኒው ዮርክ ታይመስ ደግሞ ቀደም ሲል ሲዲሲ ከሁሉም 50 የአሜሪካ ግዛቶች እና አምስት ግዙፍ ከተሞች ከስርጭት ጋር ተያይዞ ያሉ የእቅድ መረጃዎችን ጠይቋል። በኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ ላይ ሲዲሲ ጥቅምት አጋማሽ ላይ በቁጥር አነስተኛ የሆኑ አንድ ወይም ሁለት የኮቪድ-19 ክትባቶች ለስርጭት ዝግጁ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁሟል። ለበሽታው የበለጠ ተጋላጭ ናቸው ለተባሉ እንደ የጤና ባለሙያዎች፣ ለደህንነት ሰራተኞች እና እድሜያቸው የገፉ ሰዎችን የሚንከባከቡ ነርሶች እና ባልደረቦች ክትባቱ ያለ ክፍያ ይሰጣቸዋል ይላል የሲዲሲው ዶክመንት። የተላላፊ በሽታዎች ባለሙያው ዶ/ር አንቶኒዮ ፋውቺ ለኤምኤስኤንቢሲ ቴሌቪዥን ትናንት ሲናገሩ፤ ለኮቪድ-19 ክትባት ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥርን ከግምት በማስገባት እስከ ሕዳር ወር ድረስ የትኛው የኮቪድ-19 ክትባት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ እንደሚሆን መለየት ይቻላል ብለዋል። ሞደርና፣ አስትራዜኔካ እና ፐፊዘር የተሰኙ መድሃኒት አምራቾች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ የሆነ የኮቪድ-19 ክትባት ለማዘጋጀት ጥረት ላይ ይገኛሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-54012503
3politics
ባይደን በመሪዎች ስብሰባ ላይ አሜሪካ ለአፍሪካ የቢሊዮን ዶላሮችን ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቁ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዩኤስ-አፍሪካ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ለአህጉሪቱ በድጋፍ እና በኢንቨስትመንት መልክ ቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ አገራቸው ፈሰስ እንደምታደርግ አስታውቁ። ባይደን አሜሪካ ለአፍሪካ የወደፊት ተስፋ ሙሉ ትኩረቷን እንደምትሰጥ በመሪዎች ውይይት ላይ ለመሳተፍ ዋሽንግተን ለተገኙ የ49 አገራት መሪዎች ተናግረዋል። አሜሪካ መሰል የመሪዎች ውይይትን ስታካሂድ ይህ በስምንት ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያው ነው። አሜሪካ ይህን ስብሰባ የጠራችው በአፍሪካ እያደገ ለመጣው የቻይና ተጽእኖ መልስ ለመስጠት ያለመ ተደርጎ ተወስዷል። ከዚህ በተጨማሪ ዶናልድ ትራምፕ በአራት ዓመታት የሥልጣን ዘመናቸው አፍሪካውያን መሪዎችን ገሸሽ ከማድረግ አልፈው፣ አፍሪካውያን አገራትን በማንቋሸሽ በመጥራት የአሜሪካ እና አፍሪካ ግንኙነት አሻክረዋል። ጆ ባይደን ግን ከዚህ በተለየ መልኩ አገራቸው ከአፍሪካ አህጉር ጋር የበለጠ ቅርብ እንድትሆን ፍላጎታቸው መሆኑን ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ ለተሰበሰቡት የአፍሪካ መሪዎች “አፍሪካ ስኬታማ ስትሆን፤ ዩናይትድ ስቴትስም ስኬታማ ትሆናለች። እውነት ለመናገር፤ መላው ዓለም ጭምር ስኬታማ ይሆናል” ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ ዓለም በአሁኑ ወቅት ከገባችበት ቀውስ ለመውጣት የአፍሪካ መሪዎች የመሪነት ጥበብ እና ሃሳብን ትፈልጋለች ብለዋል። የፕሬዝዳንቱ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጃክ ሰሊቫን አሜሪካ በቀጣይ ሦስት ዓመታት በድጋፍ እና በኢንቨስትመንት 55 ቢሊዮን ዶላር በአፍሪካ ፈሰስ እንደምታደርግ ገልጸዋል። ፕሬዝዳንት ባይደን ረቡዕ ዕለት ሲናገሩ በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ቤኒን የትራንስፖርት ወጪን ለመቀነስ 500 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት ታደርጋለች ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም በአህጉሪቱ የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለማሳደግ 350 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚደረግ ጠቅሰዋል። አሜሪካ ከአፍሪካ አገራት ጋር በዓለም ትልቅ የሆነውን የአፍሪካ አህጉር ነጻ የንግድ ቀጠና ለመፍጠር የመግባቢያ ሰነድ እንደምትፈራረም ጨምረው ተናግራል። ከዚህ ስብሰባ ጎን ለጎን ባይደን በእአአ 2023 ምርጫ ከሚያካሂዱ ስድስት የአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። ፕሬዝዳንቱ ከመሪዎቹ ጋር ውይይት ያደረጉት የሚካሄዱት ምርጫዎች ነጻ እና ፍትሐዊ እንዲሆኑ ጫና ለመፍጠር ነው ተብሏል። ባይደን በእአአ 2023 ላይ ወደ አፍሪካ ለሥራ ጉብኝት ሊጓዙ እንደሚችሉ ይፋ ሊያደርጉ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ የአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ስብሰባ ለሦስተ ቀናት ተካሂዶ ዛሬ ሐሙስ ታኅሣሥ 06/2015 ዓ.ም. ይጠናቀቃል።
ባይደን በመሪዎች ስብሰባ ላይ አሜሪካ ለአፍሪካ የቢሊዮን ዶላሮችን ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቁ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዩኤስ-አፍሪካ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ለአህጉሪቱ በድጋፍ እና በኢንቨስትመንት መልክ ቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ አገራቸው ፈሰስ እንደምታደርግ አስታውቁ። ባይደን አሜሪካ ለአፍሪካ የወደፊት ተስፋ ሙሉ ትኩረቷን እንደምትሰጥ በመሪዎች ውይይት ላይ ለመሳተፍ ዋሽንግተን ለተገኙ የ49 አገራት መሪዎች ተናግረዋል። አሜሪካ መሰል የመሪዎች ውይይትን ስታካሂድ ይህ በስምንት ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያው ነው። አሜሪካ ይህን ስብሰባ የጠራችው በአፍሪካ እያደገ ለመጣው የቻይና ተጽእኖ መልስ ለመስጠት ያለመ ተደርጎ ተወስዷል። ከዚህ በተጨማሪ ዶናልድ ትራምፕ በአራት ዓመታት የሥልጣን ዘመናቸው አፍሪካውያን መሪዎችን ገሸሽ ከማድረግ አልፈው፣ አፍሪካውያን አገራትን በማንቋሸሽ በመጥራት የአሜሪካ እና አፍሪካ ግንኙነት አሻክረዋል። ጆ ባይደን ግን ከዚህ በተለየ መልኩ አገራቸው ከአፍሪካ አህጉር ጋር የበለጠ ቅርብ እንድትሆን ፍላጎታቸው መሆኑን ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ ለተሰበሰቡት የአፍሪካ መሪዎች “አፍሪካ ስኬታማ ስትሆን፤ ዩናይትድ ስቴትስም ስኬታማ ትሆናለች። እውነት ለመናገር፤ መላው ዓለም ጭምር ስኬታማ ይሆናል” ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ ዓለም በአሁኑ ወቅት ከገባችበት ቀውስ ለመውጣት የአፍሪካ መሪዎች የመሪነት ጥበብ እና ሃሳብን ትፈልጋለች ብለዋል። የፕሬዝዳንቱ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጃክ ሰሊቫን አሜሪካ በቀጣይ ሦስት ዓመታት በድጋፍ እና በኢንቨስትመንት 55 ቢሊዮን ዶላር በአፍሪካ ፈሰስ እንደምታደርግ ገልጸዋል። ፕሬዝዳንት ባይደን ረቡዕ ዕለት ሲናገሩ በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ቤኒን የትራንስፖርት ወጪን ለመቀነስ 500 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት ታደርጋለች ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም በአህጉሪቱ የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለማሳደግ 350 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚደረግ ጠቅሰዋል። አሜሪካ ከአፍሪካ አገራት ጋር በዓለም ትልቅ የሆነውን የአፍሪካ አህጉር ነጻ የንግድ ቀጠና ለመፍጠር የመግባቢያ ሰነድ እንደምትፈራረም ጨምረው ተናግራል። ከዚህ ስብሰባ ጎን ለጎን ባይደን በእአአ 2023 ምርጫ ከሚያካሂዱ ስድስት የአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። ፕሬዝዳንቱ ከመሪዎቹ ጋር ውይይት ያደረጉት የሚካሄዱት ምርጫዎች ነጻ እና ፍትሐዊ እንዲሆኑ ጫና ለመፍጠር ነው ተብሏል። ባይደን በእአአ 2023 ላይ ወደ አፍሪካ ለሥራ ጉብኝት ሊጓዙ እንደሚችሉ ይፋ ሊያደርጉ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ የአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ስብሰባ ለሦስተ ቀናት ተካሂዶ ዛሬ ሐሙስ ታኅሣሥ 06/2015 ዓ.ም. ይጠናቀቃል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cekv71zl2gpo
5sports
የማንችስተር ሲቲና የአርሰናል ግጥሚያ በኮሮናቫይረስ ስጋት ለሌላ ጊዜ ተላለፈ
ማንችስተር ሲቲ ከአርሰናል ጋር ዛሬ እሮብ፤ ሊያደርግ የነበረው የፕሮሪሚየር ሊግ ጨዋታ "ቅድመ ጥንቃቄ" በሚልና በርካታ የአርሰናል ተጫዋቾች ራሳቸውን ለይተው በመቀመጣቸው የተነሳ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ። የመድፈኞቹ ተጫዋቾች ራሳቸውን አግልለው በር ዘግተው የተቀመጡት የኦሎምፒያኮስ ባለቤት የሆኑት ኢቫንጀሎስ ማሪናኪስ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ ነው። አርሰናል እንዳለው ከሆነ ማሪናኪስ ከሁለት ሳምንት በፊት በነበረው አውሮፓ ሊግ ጨዋታ ወቅት በርካታ ተጫዋቾችን አግኝተው ነበር። የ52 ዓመቱ ማሪናኪስ በኮቪድ 19 [ኮሮናቫይረስ] መያዛቸውን የተናገሩት ማክሰኞ ዕለት ነበር። ኦሎምፒያኮስ በአውሮፓ ሊግ ዎልቭስን ሐሙስ ዕለት የሚያስተናግድ ሲሆን፤ ዎልቭስ ግን አስቀድሞ ጨዋታው እንዲራዘምለት ጠይቆ የነበረ ቢሆንም ተከልክሏል። የፕሪሚየር ሊግ የበላይ ኃላፊዎች ግን ከእንግዲህ ወዲህ ምንም ዓይነት ጨዋታ የማራዘም ሃሳብ እንደሌላቸው ገልፀው "አስፈላጊው ጥንቃቄ ሁሉ ተወስዷል" ሲሉ ተናግረዋል። ብራይተን በበኩሉ ከአርሰናል ጋር ያላቸው ግጥሚያ ቅዳሜ እለት በተያዘለት ሰዓት እንደሚካሄድ አስታውቋል። "ተጫዋቾቹ ራሳቸውን ነጥለው የሚያቆዩበት ጊዜ የሚያበቃው ሐሙስ በመሆኑ አደጋው እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነው" ብለዋል። በዩናይትድ ኪንግደም እስካሁን ድረስ 382 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ስድስት ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። የኮሮናቫይረስ የስፖርት ውድድሮችን በከፍተኛ ሁኔታ የጎዳ ሲሆን የጣሊያን ሴሪ አ ሲቋረጥ የፈረንሳይና የስፔን ጨዋታዎች በዝግ ስታዲየም እንዲካሄዱ ተወስኗል። ማንችስተር ዩናይትድን፣ ሬንጀርስንና ቼልሲን የሚያሳትፈው የአውሮፓ ዋንጫም በሚቀጥሉት ቀናት በኦስትሪያ እና በጀርመን በዝግ ስታዲየሞች ይካሄዳሉ። በዩናይትድ ኪንግደም ግን ስፖርት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሲስተጓጎል ይህ የመጀመሪያው ጨዋታ ነው።
የማንችስተር ሲቲና የአርሰናል ግጥሚያ በኮሮናቫይረስ ስጋት ለሌላ ጊዜ ተላለፈ ማንችስተር ሲቲ ከአርሰናል ጋር ዛሬ እሮብ፤ ሊያደርግ የነበረው የፕሮሪሚየር ሊግ ጨዋታ "ቅድመ ጥንቃቄ" በሚልና በርካታ የአርሰናል ተጫዋቾች ራሳቸውን ለይተው በመቀመጣቸው የተነሳ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ። የመድፈኞቹ ተጫዋቾች ራሳቸውን አግልለው በር ዘግተው የተቀመጡት የኦሎምፒያኮስ ባለቤት የሆኑት ኢቫንጀሎስ ማሪናኪስ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ ነው። አርሰናል እንዳለው ከሆነ ማሪናኪስ ከሁለት ሳምንት በፊት በነበረው አውሮፓ ሊግ ጨዋታ ወቅት በርካታ ተጫዋቾችን አግኝተው ነበር። የ52 ዓመቱ ማሪናኪስ በኮቪድ 19 [ኮሮናቫይረስ] መያዛቸውን የተናገሩት ማክሰኞ ዕለት ነበር። ኦሎምፒያኮስ በአውሮፓ ሊግ ዎልቭስን ሐሙስ ዕለት የሚያስተናግድ ሲሆን፤ ዎልቭስ ግን አስቀድሞ ጨዋታው እንዲራዘምለት ጠይቆ የነበረ ቢሆንም ተከልክሏል። የፕሪሚየር ሊግ የበላይ ኃላፊዎች ግን ከእንግዲህ ወዲህ ምንም ዓይነት ጨዋታ የማራዘም ሃሳብ እንደሌላቸው ገልፀው "አስፈላጊው ጥንቃቄ ሁሉ ተወስዷል" ሲሉ ተናግረዋል። ብራይተን በበኩሉ ከአርሰናል ጋር ያላቸው ግጥሚያ ቅዳሜ እለት በተያዘለት ሰዓት እንደሚካሄድ አስታውቋል። "ተጫዋቾቹ ራሳቸውን ነጥለው የሚያቆዩበት ጊዜ የሚያበቃው ሐሙስ በመሆኑ አደጋው እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነው" ብለዋል። በዩናይትድ ኪንግደም እስካሁን ድረስ 382 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ስድስት ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። የኮሮናቫይረስ የስፖርት ውድድሮችን በከፍተኛ ሁኔታ የጎዳ ሲሆን የጣሊያን ሴሪ አ ሲቋረጥ የፈረንሳይና የስፔን ጨዋታዎች በዝግ ስታዲየም እንዲካሄዱ ተወስኗል። ማንችስተር ዩናይትድን፣ ሬንጀርስንና ቼልሲን የሚያሳትፈው የአውሮፓ ዋንጫም በሚቀጥሉት ቀናት በኦስትሪያ እና በጀርመን በዝግ ስታዲየሞች ይካሄዳሉ። በዩናይትድ ኪንግደም ግን ስፖርት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሲስተጓጎል ይህ የመጀመሪያው ጨዋታ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-51830172
5sports
የቻይና ቴሌቪዢን በኦዚል ምክንያት የአርሰናልን የቀጥታ ጨዋታ አቋረጠ
የቻይናው የዜና ተቋም ሲሲቲቪ እሁድ የተካሄደውን የአርሰናልና የማንቸስተር ሲቲ ጨዋታን እንዳይተላለፍ አግዶታል። ምክንያቱ ደግሞ የአርሰናሉ ሜሱት አዚል በቻይና ስለሚገኙ ሙስሊሞች በማህበራዊ ሚዲያ አስተያየቱን በመስጠቱ ነው። ኦዚል በቻይና ስለሚገኙ ኡጉር ሙስሊሞች የሰጠው አስተያየት መነጋገሪያ ከመሆን አልፎ ቡድኑ አርሰናል ጉዳዩ እኔን አይመለከተኝም የሚል መግለጫ እንዲያወጣም አስገድዶት ነበር። የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ''አርሰናል እንደ ድርጅት ከፖለቲካ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም'' ብሏል። • የአርሰናሉ ሜሱት ኦዚል ስለ ቻይና ሙስሊሞች የሰጠው አስተያየት ክርክር አስነሳ • ለወሲብ ባርነት ወደ ቻይና የሚወሰዱት ሴቶች አክሎም '' ሜሱት ኦዚል በማህበራዊ ሚዲያ ያስተላለፈውን መልእክት ተከትሎ የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ጉዳዩ እንደማይመለከተውና የኦዚል የግል ሃሳብ መሆኑን መግለጽ እንፈልጋለን'' ብሏል። የቻይና እግር ኳስ ማህበር በበኩሉ የአርሰናሉ ተጫዋች የሰጠው አስተያየት ተቀባይነት የሌለውና የበርካታ ቻይናውያን ኳስ አፍቃሪዎችን ስሜት የጎዳ ነው ብሏል። ሲሲቲቪ ጣቢያም እሁድ የተካሄደውና የባለፈው ዓመት ሻምፒዮኖቹ ማንቸስተር ሲቲዎች አርሰናልን 3 ለባዶ ያሸነፉበትን ጨዋታ በመተው ቶተንሃምና ዎልቭስ ያደረጉትን ጨዋታ አስተላልፏል። ሜሱት ኦዚል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰፈረው መልእክት የኡጉር ሙስሊሞችን ''እስራትና ስቃይን መቋቋም የሚችሉ ተዋጊዎች'' ብሎ በማድነቅ፤ ቻይና እና ዝምታን መርጠዋል ያላቸው ሌሎች ሙስሊሞችን ተችቷል። • የቻይና ሙስሊሞች ምድራዊ 'ጀሐነም' ሲጋለጥ • ቻይና ሙስሊም ዜጎቿን እየሰለለች ነው ተባለ ቻይና በሚሊየን የሚቆጠሩ የኡጉር ሙስሊም ማህበረሰቦችን ያለፍርድቤት ትእዛዝ አስራለች፤ በማጎሪያ ካምፖችም ታሳቃያቸዋለች በማለት አንዳንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ይከሳሉ። ቻይና ማዕከላቱ ሀይማኖታዊ አክራሪነትን ለመዋጋት የሚረዱ የቴክኒክና ስልጠና ማስተማሪያዎች እንጂ ማጎሪያ ካምፖች አይደሉም በማለት በተደጋጋሚ ገልጻለች።
የቻይና ቴሌቪዢን በኦዚል ምክንያት የአርሰናልን የቀጥታ ጨዋታ አቋረጠ የቻይናው የዜና ተቋም ሲሲቲቪ እሁድ የተካሄደውን የአርሰናልና የማንቸስተር ሲቲ ጨዋታን እንዳይተላለፍ አግዶታል። ምክንያቱ ደግሞ የአርሰናሉ ሜሱት አዚል በቻይና ስለሚገኙ ሙስሊሞች በማህበራዊ ሚዲያ አስተያየቱን በመስጠቱ ነው። ኦዚል በቻይና ስለሚገኙ ኡጉር ሙስሊሞች የሰጠው አስተያየት መነጋገሪያ ከመሆን አልፎ ቡድኑ አርሰናል ጉዳዩ እኔን አይመለከተኝም የሚል መግለጫ እንዲያወጣም አስገድዶት ነበር። የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ''አርሰናል እንደ ድርጅት ከፖለቲካ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም'' ብሏል። • የአርሰናሉ ሜሱት ኦዚል ስለ ቻይና ሙስሊሞች የሰጠው አስተያየት ክርክር አስነሳ • ለወሲብ ባርነት ወደ ቻይና የሚወሰዱት ሴቶች አክሎም '' ሜሱት ኦዚል በማህበራዊ ሚዲያ ያስተላለፈውን መልእክት ተከትሎ የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ጉዳዩ እንደማይመለከተውና የኦዚል የግል ሃሳብ መሆኑን መግለጽ እንፈልጋለን'' ብሏል። የቻይና እግር ኳስ ማህበር በበኩሉ የአርሰናሉ ተጫዋች የሰጠው አስተያየት ተቀባይነት የሌለውና የበርካታ ቻይናውያን ኳስ አፍቃሪዎችን ስሜት የጎዳ ነው ብሏል። ሲሲቲቪ ጣቢያም እሁድ የተካሄደውና የባለፈው ዓመት ሻምፒዮኖቹ ማንቸስተር ሲቲዎች አርሰናልን 3 ለባዶ ያሸነፉበትን ጨዋታ በመተው ቶተንሃምና ዎልቭስ ያደረጉትን ጨዋታ አስተላልፏል። ሜሱት ኦዚል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰፈረው መልእክት የኡጉር ሙስሊሞችን ''እስራትና ስቃይን መቋቋም የሚችሉ ተዋጊዎች'' ብሎ በማድነቅ፤ ቻይና እና ዝምታን መርጠዋል ያላቸው ሌሎች ሙስሊሞችን ተችቷል። • የቻይና ሙስሊሞች ምድራዊ 'ጀሐነም' ሲጋለጥ • ቻይና ሙስሊም ዜጎቿን እየሰለለች ነው ተባለ ቻይና በሚሊየን የሚቆጠሩ የኡጉር ሙስሊም ማህበረሰቦችን ያለፍርድቤት ትእዛዝ አስራለች፤ በማጎሪያ ካምፖችም ታሳቃያቸዋለች በማለት አንዳንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ይከሳሉ። ቻይና ማዕከላቱ ሀይማኖታዊ አክራሪነትን ለመዋጋት የሚረዱ የቴክኒክና ስልጠና ማስተማሪያዎች እንጂ ማጎሪያ ካምፖች አይደሉም በማለት በተደጋጋሚ ገልጻለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-50805305
3politics
ምርጫ፡ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ መደበኛ ሥራቸዉ ለመመለስ ዝግጁ ናቸው ተባለ
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ መደበኛ ሥራቸው ለመመለስ ዝግጁ መሆናቸውን ሐኪሞቻቸው ተናገሩ። በኮሮናቫይረስ የተያዙት የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮቪድ-19 ሕክምናቸውን መጨረሳቸውን በመግለጽ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ወደ ሥራቸው መመለስ እንደሚችሉ ሐኪማቸው ተናግረዋል። ዶ/ር ሼን ኮንሌይ፤ ፕሬዝዳንቱ ለወሰዷቸው መድሃኒቶች ጥሩ ምላሽ መስጠታቸውንና የጤና ሁኔታቸው አስተማማኝ መሆኑን ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕም ይህንን የሐኪማቸውን አስተያየት ተከትሎ ዛሬ ሌላ የኮቪድ-19 ምርመራ ካደረጉ በኋላ በሳምንቱ መጨረሻ የምረጡኝ ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። በመሆኑም ለመጨረሻ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ከተደረገላቸው በኋላ ከነገ ጀምሮ ወደ መደበኛ ሥራቸዉ መመለስና ህዝባዊ ክንውኖች ላይ መሳተፍ ይችላሉ ተብሏል። ፕሬዝዳንቱ በሚቀጥለው ሳምንት ሐሙስ ከተፎካካሪያቸው ጆ ባይደን ጋር በቀጥታ በቴሌቪዥን ከሚካሄደው የምርጫ ክርክር ራሳቸውን ማግለላቸው ይታወሳል። የክርክሩ አዘጋጆች የትራምፕን በኮቪድ-19 መያዝ ካወቁ በኋላ በቴሌቪዥን የሚካሄደው የምረጡኝ ክርክሩ 'ቨርቹዋል' በሆነ መንገድ በርቀት ይከናወናል ማለታቸውን ተከትሎ ዶናልድ ትራምፕ " በቨርቹዋል ለሚደረግ ክርክር ጊዜዬን አላባክንም" ብለዋል። የግል ሀኪማቸዉ ዶ/ር ሼን ኮንሌይ፤ አሁን ላይ ፕሬዝዳንቱ ከኮቪድ-19 ጋር ተያይዞ የሚሰጣቸዉን ህክምና ማጠናቀቃቸዉንና በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በኮሮናቫይረስ በተያዙ ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ ገበታቸው ተመልሰው መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል። ፕሬዚደንቱ ለ24 ሰዓታት ያህል የኮቪድ-19 ምልክት ያልታየባቸው ሲሆን ለተከታታይ አራት ቀናትም ትኩሳት እንዳልነበራቸው የግል ሐኪማቸው ሼን ኮንሊይ ተናግረዋል። ትራምፕ ረቡዕ ዕለት ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት ደህንነት ይሰማቸው እንደነበር ገልፀው፤ "ይህ በፈጣሪ መባረክ ነው" ብለዋል። በንግግራቸውም ሁሉም አሜሪካዊያን ለእርሳቸው የተሰጠውን መድሃኒት እንዲያገኙ እንደሚፈልጉ ተናግረው ነበር። በመሆኑም በወቅቱ በመድሃኒት አምራቹ ሬጀኔሮን የተመረተውን መድሃኒት በነፃ ለመስጠት ፕሬዚደንቱ ቃል ገብተዋል። ፕሬዚደንቱ አክለውም ባለፈው ሳምንት የተሰጣቸው በሙከራ ላይ ያለው የሰውነት በሽታ መከላከል አቅምን የሚጨምረው አንቲቦዲ ማገገሚያ ብቻ ሳይሆን ፈዋሽ ነው በማለትም በመቶ ሺዎች የሚቆጠር መጠን [ዶዝ] ያለው መድሃኒት እየተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል። ይሁን እንጅ ድርጅቱ የሚያመርተው መድሃኒት በፌደራል የመድሃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን የተረጋገጠ አይደለም።
ምርጫ፡ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ መደበኛ ሥራቸዉ ለመመለስ ዝግጁ ናቸው ተባለ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ መደበኛ ሥራቸው ለመመለስ ዝግጁ መሆናቸውን ሐኪሞቻቸው ተናገሩ። በኮሮናቫይረስ የተያዙት የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮቪድ-19 ሕክምናቸውን መጨረሳቸውን በመግለጽ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ወደ ሥራቸው መመለስ እንደሚችሉ ሐኪማቸው ተናግረዋል። ዶ/ር ሼን ኮንሌይ፤ ፕሬዝዳንቱ ለወሰዷቸው መድሃኒቶች ጥሩ ምላሽ መስጠታቸውንና የጤና ሁኔታቸው አስተማማኝ መሆኑን ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕም ይህንን የሐኪማቸውን አስተያየት ተከትሎ ዛሬ ሌላ የኮቪድ-19 ምርመራ ካደረጉ በኋላ በሳምንቱ መጨረሻ የምረጡኝ ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። በመሆኑም ለመጨረሻ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ከተደረገላቸው በኋላ ከነገ ጀምሮ ወደ መደበኛ ሥራቸዉ መመለስና ህዝባዊ ክንውኖች ላይ መሳተፍ ይችላሉ ተብሏል። ፕሬዝዳንቱ በሚቀጥለው ሳምንት ሐሙስ ከተፎካካሪያቸው ጆ ባይደን ጋር በቀጥታ በቴሌቪዥን ከሚካሄደው የምርጫ ክርክር ራሳቸውን ማግለላቸው ይታወሳል። የክርክሩ አዘጋጆች የትራምፕን በኮቪድ-19 መያዝ ካወቁ በኋላ በቴሌቪዥን የሚካሄደው የምረጡኝ ክርክሩ 'ቨርቹዋል' በሆነ መንገድ በርቀት ይከናወናል ማለታቸውን ተከትሎ ዶናልድ ትራምፕ " በቨርቹዋል ለሚደረግ ክርክር ጊዜዬን አላባክንም" ብለዋል። የግል ሀኪማቸዉ ዶ/ር ሼን ኮንሌይ፤ አሁን ላይ ፕሬዝዳንቱ ከኮቪድ-19 ጋር ተያይዞ የሚሰጣቸዉን ህክምና ማጠናቀቃቸዉንና በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በኮሮናቫይረስ በተያዙ ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ ገበታቸው ተመልሰው መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል። ፕሬዚደንቱ ለ24 ሰዓታት ያህል የኮቪድ-19 ምልክት ያልታየባቸው ሲሆን ለተከታታይ አራት ቀናትም ትኩሳት እንዳልነበራቸው የግል ሐኪማቸው ሼን ኮንሊይ ተናግረዋል። ትራምፕ ረቡዕ ዕለት ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት ደህንነት ይሰማቸው እንደነበር ገልፀው፤ "ይህ በፈጣሪ መባረክ ነው" ብለዋል። በንግግራቸውም ሁሉም አሜሪካዊያን ለእርሳቸው የተሰጠውን መድሃኒት እንዲያገኙ እንደሚፈልጉ ተናግረው ነበር። በመሆኑም በወቅቱ በመድሃኒት አምራቹ ሬጀኔሮን የተመረተውን መድሃኒት በነፃ ለመስጠት ፕሬዚደንቱ ቃል ገብተዋል። ፕሬዚደንቱ አክለውም ባለፈው ሳምንት የተሰጣቸው በሙከራ ላይ ያለው የሰውነት በሽታ መከላከል አቅምን የሚጨምረው አንቲቦዲ ማገገሚያ ብቻ ሳይሆን ፈዋሽ ነው በማለትም በመቶ ሺዎች የሚቆጠር መጠን [ዶዝ] ያለው መድሃኒት እየተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል። ይሁን እንጅ ድርጅቱ የሚያመርተው መድሃኒት በፌደራል የመድሃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን የተረጋገጠ አይደለም።
https://www.bbc.com/amharic/54475144
5sports
ሳዲዮ ማኔ ሴኔጋልን ለአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ አደረሳት
በትናንትናው ዕለት ሴኔጋል ቡርኪናፋሶን 3 ለ1 በመርታት ለሶስተኛዋ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ፍጻሜ አልፋለች፤ በዚህም ስኬት ከፍተኛ ሚናን የተጫወተው ሳዲዮ ማኔ ነው። የሚገርሙ ክስተቶች ተስተናግደውበታል በተባለው ጨዋታ ሁለት ፍፁም ቅጣት ምቶች በቪዲዮ ድጋፍ አማካኝነት ሴኔጋል የተከለከለች ሲሆን በመጀመሪያውም ክስተት የቡርኪናፋሶው ግብ ጠባቂ ሄርቬ ኮፊ ተጎድቶ በፋሪድ ኦድራጎ እንዲተካ ሆኗል። የሴኔጋሎቹ አብዱ ዲያሎ እና ኢድሪሳ ጉዬ ሴኔጋል እንድትመራ ያስቻላትን ሁለት ጎሎች ያስቆጠሩ ሲሆን የቡርኪናፋሶው ብላቲ ቱሬ አንድ ጎል በማስቆጠር ልዩነቱን ማጥበብ ችሎ ነበር። ነገር ግን አገሩ የውድድሩ አሸናፊ የሆነችበት ጎል በሳዲዮ ማኔ ተቆጠረች። ለማኔ ለአገሩ ያስቆጠራት 29ኛ ጎል ስትሆን ከሄንሪ ካማራም ጋር የምንግዜም ጎል አስቆጣሪዎች በሚል በአንደኛ ደረጃነት እንዲቀመጥ አድርጎታል። እሁድ በሚጠናቀቀው በአፍሪካ ዋንጫ ሴኔጋል፣ ግብፅን ወይም ካሜሩንን ትገጥማለች። ቡርኪናፋሶ ለሶስተኛነት ወይም ለአራተኛነት በሚደረገው ፍልሚያ በመጪው ቅዳሜ ጨዋታዋን ታደርጋለች። "ይህ የደረስንበትን ወቅት ያሳያል። በሁለት ተከታታይ የአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ መድረስ ቀላል እንደማይሆን እናውቅ ነበር፤ ነገር ግን አድርገነዋል። በአሁኑ ወቅት ለኛ መሰረታዊው ጉዳይ ማንም ይሁን ማን ይግጠመን ተፋልመን ማሸነፍ ነው" ብሏል ማኔ። ማኔ የቡርኪናፋሶ ቡድን በጣም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደነበርና በጣም ከብዷቸውም እንደነበር አልደበቀም። "በጣም ከባድ ጨዋታ ጠብቀን ነበር። አዎ ፈታኝ ነበር፤ ነገር ግን ተረጋግተን ብዙ እድሎችን ፈጥረናል። ማሸነፍ ይገባናል ብዬም አስባለሁ" በማለት ተናግሯል። "ምን ያህል ደስተኛ እንደሆንኩኝ ፊቴ ላይ የምታዩት ይመስለኛል፣ ይህ ለኔ የተለመደ ነው። በግሌ እኮራለሁ፣ እናም ለራሴ፣ ለቡድን ጓደኞቼ እና ለአገሬ በጣም ደስተኛ ነኝ።" ብሏል ማኔ
ሳዲዮ ማኔ ሴኔጋልን ለአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ አደረሳት በትናንትናው ዕለት ሴኔጋል ቡርኪናፋሶን 3 ለ1 በመርታት ለሶስተኛዋ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ፍጻሜ አልፋለች፤ በዚህም ስኬት ከፍተኛ ሚናን የተጫወተው ሳዲዮ ማኔ ነው። የሚገርሙ ክስተቶች ተስተናግደውበታል በተባለው ጨዋታ ሁለት ፍፁም ቅጣት ምቶች በቪዲዮ ድጋፍ አማካኝነት ሴኔጋል የተከለከለች ሲሆን በመጀመሪያውም ክስተት የቡርኪናፋሶው ግብ ጠባቂ ሄርቬ ኮፊ ተጎድቶ በፋሪድ ኦድራጎ እንዲተካ ሆኗል። የሴኔጋሎቹ አብዱ ዲያሎ እና ኢድሪሳ ጉዬ ሴኔጋል እንድትመራ ያስቻላትን ሁለት ጎሎች ያስቆጠሩ ሲሆን የቡርኪናፋሶው ብላቲ ቱሬ አንድ ጎል በማስቆጠር ልዩነቱን ማጥበብ ችሎ ነበር። ነገር ግን አገሩ የውድድሩ አሸናፊ የሆነችበት ጎል በሳዲዮ ማኔ ተቆጠረች። ለማኔ ለአገሩ ያስቆጠራት 29ኛ ጎል ስትሆን ከሄንሪ ካማራም ጋር የምንግዜም ጎል አስቆጣሪዎች በሚል በአንደኛ ደረጃነት እንዲቀመጥ አድርጎታል። እሁድ በሚጠናቀቀው በአፍሪካ ዋንጫ ሴኔጋል፣ ግብፅን ወይም ካሜሩንን ትገጥማለች። ቡርኪናፋሶ ለሶስተኛነት ወይም ለአራተኛነት በሚደረገው ፍልሚያ በመጪው ቅዳሜ ጨዋታዋን ታደርጋለች። "ይህ የደረስንበትን ወቅት ያሳያል። በሁለት ተከታታይ የአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ መድረስ ቀላል እንደማይሆን እናውቅ ነበር፤ ነገር ግን አድርገነዋል። በአሁኑ ወቅት ለኛ መሰረታዊው ጉዳይ ማንም ይሁን ማን ይግጠመን ተፋልመን ማሸነፍ ነው" ብሏል ማኔ። ማኔ የቡርኪናፋሶ ቡድን በጣም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደነበርና በጣም ከብዷቸውም እንደነበር አልደበቀም። "በጣም ከባድ ጨዋታ ጠብቀን ነበር። አዎ ፈታኝ ነበር፤ ነገር ግን ተረጋግተን ብዙ እድሎችን ፈጥረናል። ማሸነፍ ይገባናል ብዬም አስባለሁ" በማለት ተናግሯል። "ምን ያህል ደስተኛ እንደሆንኩኝ ፊቴ ላይ የምታዩት ይመስለኛል፣ ይህ ለኔ የተለመደ ነው። በግሌ እኮራለሁ፣ እናም ለራሴ፣ ለቡድን ጓደኞቼ እና ለአገሬ በጣም ደስተኛ ነኝ።" ብሏል ማኔ
https://www.bbc.com/amharic/news-60239919
5sports
የቻምፒዮንስ ሊጉ ዋንጫ ወደ ማንችስተር ሲቲ ወይስ ቼልሲ?
ዛሬ በእንግሊዝ ቡድኖች መካከል የሚደረግ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ነው። የዛሬ ምሽቱን የአውሮፓ ቻምፒዮንነት ዘውድ የሚጭነው ማንችስተር ሲቲ ወይስ ቼልሲ? የፕሪሚየር ሊጉ ቻምፒዮን ማንችስተር ሲቲ ባለ ትልቁን ጆሮ ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማንሳት ይፎካከራል፡፡ የ2012 የአውሮፓ ቻምፒዮኑ ቼልሲ የፔፕ ጋርዲዮላን ቡድን ዘንድሮ በሊጉ እና በኤፍኤ ካፕ ሁለት ጊዜ ማሸነፍ ችሏል። በፖርቶ ስታዲዮ ዶ ድራጋዎ የሚደረገውን ጨዋታ ለመመልከት እስከ 16,500 ታዳሚዎች እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ ምንም እንኳን አርብ በተደረገው ልምምድ ላይ የሲቲው አማካይ ኢካይ ጉንዶጋን ከፈርናንድኒሆ ጋር ተጋጭቶ ትንሽ ጉዳት ያስተናገደ ቢመስልም የሁለቱም ቡድኖች ተጫዋቾች በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ። አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ "መጫወት የምንፈልገውን መንገድ እና ከማን ጋር እንደምንጫወት ስለምናውቅ ብዙ እንደማላስቸግራቸው አውቃለሁ" ብሏል፡፡ "እዚህ መገኘት አስገራሚ ተሞክሮ ነው፡፡ ምን እንደምነግራቸው በትክክልም አውቃለሁ፡፡ የተጨነቁ እና የተደናገጡ ካሉ የተለመደ ነገር እንደሆነ እነግራቸዋለሁ" ሲል ሐሳቡን ሰጥቷል። በተጨማሪም "የፍፃሜ ጨዋታውን ለማሸነፍ እንደምንሰቃይ እርግጠኛ ነኝ፡፡ [በጨዋታው] ተዝናኑበት ማለት ጥሩ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ አይቻልም፡፡ ጽናት እና ማስተካከያ ማድረግ ያስፈልጋል" ብሏል፡፡ የሲቲው አማካይ ኬቪን ደ ብሩይን በበኩሉ "ካሸነፍክ ጀግና ነህ፣ ከተሸነፍክ ደግሞ ወድቀሀል ማለት ነው። ወደዚህ ደረጃ መምጣት ለቡድኑ አስደናቂ ቢሆንም ዋንጫውን አለማሸነፍ ግን ልምድ አይደለም" ሲል ገልጿል፡፡ "ከክለቡ እና ከተጫዋቾች ግቦች አንዱ ነው፡፡ እዚህ መድረስ መቻል እና በዓለም ላይ ከፍተኛ በሆነው መድረክ ላይ መጫወት መቻል ትልቅ ዕድል ነው፡፡" የሲቲው ስፔናዊ አለቃ ጋርዲዮላ በ2009 እና 2011 ከባርሴሎና ጋር ድሉን ከተቀዳጀ በኋላ ሻምፒዮንስ ሊጉን ለሦስተኛ ጊዜ ለማሸነፍ ይጫወታል፡፡ የቼልሲው አለቃ ቶማስ ቱቼል የመጀመሪያውን የቻምፒየንስ ሊግ ስኬት ለማስመዝገብ ይጫወታል፡፡ ባለፈው የውድድር ዘመን ጀርመናዊው ፓሪስ ሴንት ዠርሜንን ይዞ በባየር ሙኒክ 1-0 ተሸንፎ ዋንጫውን አጥቷል፡፡ "ሁሉም እንደሚፈልገው ሙሉ እምነት አለኝ፡፡ የድል ረሀብ አለ። እናም ሁልጊዜ በስፖርቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ምን ያህል ፍላጎት አለ የሚለው ነው ዋናው ነገር። በዚህ ሳምንት በጣም የተጠናከርን፣ ትኩረት እና ሥነምግባር ያለን ሆኖ ተሰምቶኛል" ብሏል ቱቼል፡፡ "ፔፕ የያዘውን ሲቲ፣ ባየርን ወይም ባርሴሎናን መግጠም ሁልጊዜም ከባድ ነው፡፡ እሱ ትልቅ እምነት እና ስኬት ከመፍጠር ባለፈ ትልቅ የማሸነፍ አስተሳሰብ አለው" ሲል ገልጿል፡፡ "ምናልባትም በአሁኑ ወቅት በአውሮፓ ብሎም በዓለም በጣም ጠንካራው ቡድን ነው። በሊጉ በመካከላችን ትልቅ ክፍተት ቢኖርም በዌምብሌይ እና በማንችስተር ክፍተቱን ዘግተናል" ብሏል፡፡ የዋንጫው ጨዋታ በ90 ደቂቃ የሚወሰን ሲሆን ካልሆነ 30 ደቂቃዎች ተጨማሪ ጊዜ እና አስፈላጊ ከሆነም ወደ ፍጹም ቅጣት ምት ያመራል፡፡ በመደበኛው ክፍለ ጊዜ ቡድኖቹ አምስት ተጫዋቾችን የሚቀይሩ ሲሆን ወደተጨማሪ ሰዓት ካመሩ ደግሞ ተጨማሪ አንድ ተጫዋች የመምረጥ መብት አላቸው፡፡ ቱቼል "በፍጹም ቅጣት ምት በኩል [የዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ] ከመቺዎች ጥራት አንፃር ድንቅ ነበር፡፡ 20 ፍጹም ቅጣት ምት ሳይሳት ሲቆጠር የመሰለን ነገር ያየሁ አይመስለኝም" ብሏል። "ቅጣት ምቱን የሚመቱትን ለይተናል። ነገር ግን በመጨረሻው ሜዳ ላይ ማን እንደሚቆይ አላውቅም። ስለዚህ በደንብ ማወቅ አለብን። ወደ ቅጣት ምት ከሄድን አብረን እንሄዳለን እና አብረን እንወጣለን፡፡" የቪድዮ ረዳት ዳኛ (ቫር) ጥቅም ላይ ይውላል። ሲቲ ደግሞ 'በሜዳው የሚጫወተው' ቡድን ተብሎ የተሰየመ ሲሆን፤ በዚህም በተለመደው ሰማያዊ እና ነጭ መለያው ይጫወታል፡፡ የዘንድሮው ፍጻሜ በዓለም ዙሪያ ባሉ ከ200 በላይ አገራት ይተላለፋል። የአውሮፓ ክለቦች ትልቁ ጨዋታ ከመጀመሩ 10 ደቂቃ በፊት የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ይደረጋል፡፡
የቻምፒዮንስ ሊጉ ዋንጫ ወደ ማንችስተር ሲቲ ወይስ ቼልሲ? ዛሬ በእንግሊዝ ቡድኖች መካከል የሚደረግ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ነው። የዛሬ ምሽቱን የአውሮፓ ቻምፒዮንነት ዘውድ የሚጭነው ማንችስተር ሲቲ ወይስ ቼልሲ? የፕሪሚየር ሊጉ ቻምፒዮን ማንችስተር ሲቲ ባለ ትልቁን ጆሮ ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማንሳት ይፎካከራል፡፡ የ2012 የአውሮፓ ቻምፒዮኑ ቼልሲ የፔፕ ጋርዲዮላን ቡድን ዘንድሮ በሊጉ እና በኤፍኤ ካፕ ሁለት ጊዜ ማሸነፍ ችሏል። በፖርቶ ስታዲዮ ዶ ድራጋዎ የሚደረገውን ጨዋታ ለመመልከት እስከ 16,500 ታዳሚዎች እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ ምንም እንኳን አርብ በተደረገው ልምምድ ላይ የሲቲው አማካይ ኢካይ ጉንዶጋን ከፈርናንድኒሆ ጋር ተጋጭቶ ትንሽ ጉዳት ያስተናገደ ቢመስልም የሁለቱም ቡድኖች ተጫዋቾች በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ። አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ "መጫወት የምንፈልገውን መንገድ እና ከማን ጋር እንደምንጫወት ስለምናውቅ ብዙ እንደማላስቸግራቸው አውቃለሁ" ብሏል፡፡ "እዚህ መገኘት አስገራሚ ተሞክሮ ነው፡፡ ምን እንደምነግራቸው በትክክልም አውቃለሁ፡፡ የተጨነቁ እና የተደናገጡ ካሉ የተለመደ ነገር እንደሆነ እነግራቸዋለሁ" ሲል ሐሳቡን ሰጥቷል። በተጨማሪም "የፍፃሜ ጨዋታውን ለማሸነፍ እንደምንሰቃይ እርግጠኛ ነኝ፡፡ [በጨዋታው] ተዝናኑበት ማለት ጥሩ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ አይቻልም፡፡ ጽናት እና ማስተካከያ ማድረግ ያስፈልጋል" ብሏል፡፡ የሲቲው አማካይ ኬቪን ደ ብሩይን በበኩሉ "ካሸነፍክ ጀግና ነህ፣ ከተሸነፍክ ደግሞ ወድቀሀል ማለት ነው። ወደዚህ ደረጃ መምጣት ለቡድኑ አስደናቂ ቢሆንም ዋንጫውን አለማሸነፍ ግን ልምድ አይደለም" ሲል ገልጿል፡፡ "ከክለቡ እና ከተጫዋቾች ግቦች አንዱ ነው፡፡ እዚህ መድረስ መቻል እና በዓለም ላይ ከፍተኛ በሆነው መድረክ ላይ መጫወት መቻል ትልቅ ዕድል ነው፡፡" የሲቲው ስፔናዊ አለቃ ጋርዲዮላ በ2009 እና 2011 ከባርሴሎና ጋር ድሉን ከተቀዳጀ በኋላ ሻምፒዮንስ ሊጉን ለሦስተኛ ጊዜ ለማሸነፍ ይጫወታል፡፡ የቼልሲው አለቃ ቶማስ ቱቼል የመጀመሪያውን የቻምፒየንስ ሊግ ስኬት ለማስመዝገብ ይጫወታል፡፡ ባለፈው የውድድር ዘመን ጀርመናዊው ፓሪስ ሴንት ዠርሜንን ይዞ በባየር ሙኒክ 1-0 ተሸንፎ ዋንጫውን አጥቷል፡፡ "ሁሉም እንደሚፈልገው ሙሉ እምነት አለኝ፡፡ የድል ረሀብ አለ። እናም ሁልጊዜ በስፖርቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ምን ያህል ፍላጎት አለ የሚለው ነው ዋናው ነገር። በዚህ ሳምንት በጣም የተጠናከርን፣ ትኩረት እና ሥነምግባር ያለን ሆኖ ተሰምቶኛል" ብሏል ቱቼል፡፡ "ፔፕ የያዘውን ሲቲ፣ ባየርን ወይም ባርሴሎናን መግጠም ሁልጊዜም ከባድ ነው፡፡ እሱ ትልቅ እምነት እና ስኬት ከመፍጠር ባለፈ ትልቅ የማሸነፍ አስተሳሰብ አለው" ሲል ገልጿል፡፡ "ምናልባትም በአሁኑ ወቅት በአውሮፓ ብሎም በዓለም በጣም ጠንካራው ቡድን ነው። በሊጉ በመካከላችን ትልቅ ክፍተት ቢኖርም በዌምብሌይ እና በማንችስተር ክፍተቱን ዘግተናል" ብሏል፡፡ የዋንጫው ጨዋታ በ90 ደቂቃ የሚወሰን ሲሆን ካልሆነ 30 ደቂቃዎች ተጨማሪ ጊዜ እና አስፈላጊ ከሆነም ወደ ፍጹም ቅጣት ምት ያመራል፡፡ በመደበኛው ክፍለ ጊዜ ቡድኖቹ አምስት ተጫዋቾችን የሚቀይሩ ሲሆን ወደተጨማሪ ሰዓት ካመሩ ደግሞ ተጨማሪ አንድ ተጫዋች የመምረጥ መብት አላቸው፡፡ ቱቼል "በፍጹም ቅጣት ምት በኩል [የዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ] ከመቺዎች ጥራት አንፃር ድንቅ ነበር፡፡ 20 ፍጹም ቅጣት ምት ሳይሳት ሲቆጠር የመሰለን ነገር ያየሁ አይመስለኝም" ብሏል። "ቅጣት ምቱን የሚመቱትን ለይተናል። ነገር ግን በመጨረሻው ሜዳ ላይ ማን እንደሚቆይ አላውቅም። ስለዚህ በደንብ ማወቅ አለብን። ወደ ቅጣት ምት ከሄድን አብረን እንሄዳለን እና አብረን እንወጣለን፡፡" የቪድዮ ረዳት ዳኛ (ቫር) ጥቅም ላይ ይውላል። ሲቲ ደግሞ 'በሜዳው የሚጫወተው' ቡድን ተብሎ የተሰየመ ሲሆን፤ በዚህም በተለመደው ሰማያዊ እና ነጭ መለያው ይጫወታል፡፡ የዘንድሮው ፍጻሜ በዓለም ዙሪያ ባሉ ከ200 በላይ አገራት ይተላለፋል። የአውሮፓ ክለቦች ትልቁ ጨዋታ ከመጀመሩ 10 ደቂቃ በፊት የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ይደረጋል፡፡
https://www.bbc.com/amharic/57291566
2health
አፍሪካ በኤድስ የሚከሰት ሞትን ለመግታት ወደ ኋላ ቀርታለች ተባለ
የአፍሪካ አገራት በ2030 በኤችአይቪ ኤድስ አማካኝነት የሚከሰት ሞትን ለማስቀረት የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ወደ ኋላ መቅረታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት አመለከተ። ነገ ሐሙስ ተከብሮ የሚውለውን የዓለም የኤድስ ቀንን በማስመልከት በድርጅቱ ይፋ የሆነው ሪፖርት እንዳመላከተው በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጭቆና ብሎም አግላይ ሕጎች ለዕቅዱ መጓተት እንደምክንያት ተጠቅሷል። ተመድ 90 በመቶ የሚሆኑ ኤችአይቪ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች ተመርምረው ውጤታቸውን እንዲያውቁ፣ ብሎም ከዚህ ውስጥ 90 በመቶው የፀረኤችአይቪ መድኃኒት እንዲጀምሩ እና ከዚህ ውስጥ ደግሞ 90 በመቶው በደማቸው ውስጥ የሚገኘውን የቫይረስ መጠን ከ200 በታች የማድረግ ዕቅድ አለው። ከሰሃራ በታች በሉ የአፍሪካ አገራት ውስጥ የሚኖሩ እድሜያቸው ከ15 እስከ 24 የሆኑ ሴቶች እና ልጃገረዶች ከወንዶች ጋር ሲነጻጸር፣ በሦስት እጥፍ ለኤችአይቪ የመጋለጥ ዕድል ሲኖራቸው በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ 5000 አዳዲስ ሴቶች በቫይረሱ ይያዛሉ። “የአፍሪካ አገራት የሥነ ተዋልዶ ትምህርትን፣ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች የሚሰጥ አገልግሎት፣ ብሎም የኤችአይቪ አገልግሎቶችን በጋራ በማጣመር መስጠት ይኖርባቸዋል። ይህም በጋራ ተጣምረው የሴቶችን ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት ሊሰጡ ይገባል” ሲሉ የተመድ የኤችአይቪ ኤድስ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ዊኒ ባያኒማ ተናግረዋል። ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም መንግሥታት የቫይረሱን ሥርጭት ለመቀነስ እንደ እንቅፋት የተጠቀሱ ሕጎቻቸውን እንዲያነሱም ጠይቀዋል። “አግላይ ሕጎች ሰዎች ኤችአይቪን የሚመለከቱ አገልግሎቶችን እንዳያገኙ ብሎም የኤችአይቪ ተጋላጭነትን በመጨመር ከፍተኛ ሚና አላቸው። እነዚህ ሕጎች የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን ግንኙነትን፣ የወሲብ ንግድን፣ የፀረ ኤችአይቪ መድኃኒት መጠቀምን ወንጀል የሚያደርጉ ሕጎች ይጠቀሳሉ” ሲሉም አክለዋል። ለኤችአይቪ ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸውን ሰዎች በወንጀል የሚጠይቁ አገራት በምርመራ እና በህክምናው ሂደት ላይ ዝቅተኛ ውጤት የሚያሳዩ ሲሆን፣ በርካታ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች ተመርምረው ውጤታቸውን ሳያውቁ ይኖራሉ።
አፍሪካ በኤድስ የሚከሰት ሞትን ለመግታት ወደ ኋላ ቀርታለች ተባለ የአፍሪካ አገራት በ2030 በኤችአይቪ ኤድስ አማካኝነት የሚከሰት ሞትን ለማስቀረት የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ወደ ኋላ መቅረታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት አመለከተ። ነገ ሐሙስ ተከብሮ የሚውለውን የዓለም የኤድስ ቀንን በማስመልከት በድርጅቱ ይፋ የሆነው ሪፖርት እንዳመላከተው በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጭቆና ብሎም አግላይ ሕጎች ለዕቅዱ መጓተት እንደምክንያት ተጠቅሷል። ተመድ 90 በመቶ የሚሆኑ ኤችአይቪ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች ተመርምረው ውጤታቸውን እንዲያውቁ፣ ብሎም ከዚህ ውስጥ 90 በመቶው የፀረኤችአይቪ መድኃኒት እንዲጀምሩ እና ከዚህ ውስጥ ደግሞ 90 በመቶው በደማቸው ውስጥ የሚገኘውን የቫይረስ መጠን ከ200 በታች የማድረግ ዕቅድ አለው። ከሰሃራ በታች በሉ የአፍሪካ አገራት ውስጥ የሚኖሩ እድሜያቸው ከ15 እስከ 24 የሆኑ ሴቶች እና ልጃገረዶች ከወንዶች ጋር ሲነጻጸር፣ በሦስት እጥፍ ለኤችአይቪ የመጋለጥ ዕድል ሲኖራቸው በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ 5000 አዳዲስ ሴቶች በቫይረሱ ይያዛሉ። “የአፍሪካ አገራት የሥነ ተዋልዶ ትምህርትን፣ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች የሚሰጥ አገልግሎት፣ ብሎም የኤችአይቪ አገልግሎቶችን በጋራ በማጣመር መስጠት ይኖርባቸዋል። ይህም በጋራ ተጣምረው የሴቶችን ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት ሊሰጡ ይገባል” ሲሉ የተመድ የኤችአይቪ ኤድስ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ዊኒ ባያኒማ ተናግረዋል። ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም መንግሥታት የቫይረሱን ሥርጭት ለመቀነስ እንደ እንቅፋት የተጠቀሱ ሕጎቻቸውን እንዲያነሱም ጠይቀዋል። “አግላይ ሕጎች ሰዎች ኤችአይቪን የሚመለከቱ አገልግሎቶችን እንዳያገኙ ብሎም የኤችአይቪ ተጋላጭነትን በመጨመር ከፍተኛ ሚና አላቸው። እነዚህ ሕጎች የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን ግንኙነትን፣ የወሲብ ንግድን፣ የፀረ ኤችአይቪ መድኃኒት መጠቀምን ወንጀል የሚያደርጉ ሕጎች ይጠቀሳሉ” ሲሉም አክለዋል። ለኤችአይቪ ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸውን ሰዎች በወንጀል የሚጠይቁ አገራት በምርመራ እና በህክምናው ሂደት ላይ ዝቅተኛ ውጤት የሚያሳዩ ሲሆን፣ በርካታ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች ተመርምረው ውጤታቸውን ሳያውቁ ይኖራሉ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/ckknl16ln2yo
3politics
ኔታኒያሁ ጥምር መንግሥት መመሠረት ለእስራኤል አደጋ ነው አሉ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጥቂት ቀናት ውስጥ ይዋቀራል ተብሎ የሚጠበቀው አዲስ የጥምር መንግሥት ለአገሪቱ "የደህንነት አደጋ" እንደሚሆን አስጠነቀቁ። የአክራሪ-ብሔርተኝነት መሪ የሆኑት ናፍታሊ ቤኔት መሃል ሰፋሪ ከሚባሉት ያየር ላፒድ ጋር ድርድሩን እንደሚቀላቀሉ ከተናገሩ በኋላ ነው ኔታኒያሁ ለቀኝ ክንፍ ፖለቲከኞች ስምምነቱን እንዳይደግፉ ጥሪ ያቀረቡት። ላፒድ አዲስ የጥምር መንግሥት ለማቋቋም እስከ ረቡዕ ድረስ ቀን ያላቸው ሲሆን ከተሳካላቸው በአገሪቱ ታሪክ ለረጅም ግዜ በጠቅላይ ሚኒስቴርነት የቆዩት የኔታኒያሁ የስልጣን ዘመን ያበቃል። በማጭበርበር ክስ ፍርድ ቤት የቀረቡት ኔታንያሁ እ.ኤ.አ. በመጋቢት ወር በተካሄደው አጠቃላይ ምርጫ አብላጫ ድምፅ ማግኘት አልቻሉም ነበር። በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ አራት ግዜ አጠቃላይ ምርጫ ቢካሄድም ኔታኒያሁ አብላጫ ድምፅ ማግኘትም ሆነ የጥምር መንግሥት ለመመስረት የሚሆን ስምምነት ማድረግ ሳይችሉ ቆይተዋል። "የግራ ዘመም የጥምር መንግሥት አትመስርቱ፣ ይህ ለእስራኤል ደህንነት አደገኛ ነው" ሲሉ የ 71 ዓመቱ ኔታኒያሁ ተናግረዋል። ኔታኒያሁ ለ12 ዓመታት በስልጣን ላይ የቆዩ መሪ ሲሆኑ፤ የአንድ ትውልድ እድሜ ላለው ግዜ የእስራኤል ፖለቲከ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ይዘው ቆይተዋል። የ49 ዓመቱ ቤኔት በበኩላቸው ፓርቲያቸው የጥምር መንግሥት ለመመስረት የሚደረገውን ድርድር እንደሚቀላቀል በቴሌቪዢን በተላለፈ መልክታቸው ላይ አስታውቀዋል። "ኔታንያሁ ከዚህ በኋላ ቀኝ ዘመም መንግሥት ለማቋቋም አይሞክርም፣ ምክንያቱም እንደሌለ ስለሚያውቀው ነው" ያሉት ቤኔት፤ "የእስራኤል ብሔረተኛ ቡድንን እንዲሁም መላው አገሪቱን ከግሉ አቋም ጎን ለማሰለፍ እየሞከረ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ቤኔት መግለጫውን ከመስጠታቸው በፊት የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን በተዘረዘሩት የስምምነት ነጥቦች መሠረት ቤኔት ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁን እንደሚተኩ እና በኋላም ለ57 ዓመቱ ለማ ላፒድ በቀጣይ ዙር ስልጣኑን እንደሚሰጧቸው ተዘግቧል። ስለ ስምምነቱ በይፋ የተባለ ነገር የለም። ለስምምነት የቀረበው ጥመረት ከቀኝ ፣ ግራ እና ማሃል ሰፋሪ የሆኑ ፖለቲከኞችን ይሰበስባል። ፓርቲዎቹ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ብዙም የሚያመሳስላቸው ነገር ባይኖርም፣ ቤኒያሚን ኔታንያሁ የስልጣን ዘመናቸው እንዲጠናቀቅ ባላቸው ፍላጎት ላይ ግን ይስማማሉ።
ኔታኒያሁ ጥምር መንግሥት መመሠረት ለእስራኤል አደጋ ነው አሉ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጥቂት ቀናት ውስጥ ይዋቀራል ተብሎ የሚጠበቀው አዲስ የጥምር መንግሥት ለአገሪቱ "የደህንነት አደጋ" እንደሚሆን አስጠነቀቁ። የአክራሪ-ብሔርተኝነት መሪ የሆኑት ናፍታሊ ቤኔት መሃል ሰፋሪ ከሚባሉት ያየር ላፒድ ጋር ድርድሩን እንደሚቀላቀሉ ከተናገሩ በኋላ ነው ኔታኒያሁ ለቀኝ ክንፍ ፖለቲከኞች ስምምነቱን እንዳይደግፉ ጥሪ ያቀረቡት። ላፒድ አዲስ የጥምር መንግሥት ለማቋቋም እስከ ረቡዕ ድረስ ቀን ያላቸው ሲሆን ከተሳካላቸው በአገሪቱ ታሪክ ለረጅም ግዜ በጠቅላይ ሚኒስቴርነት የቆዩት የኔታኒያሁ የስልጣን ዘመን ያበቃል። በማጭበርበር ክስ ፍርድ ቤት የቀረቡት ኔታንያሁ እ.ኤ.አ. በመጋቢት ወር በተካሄደው አጠቃላይ ምርጫ አብላጫ ድምፅ ማግኘት አልቻሉም ነበር። በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ አራት ግዜ አጠቃላይ ምርጫ ቢካሄድም ኔታኒያሁ አብላጫ ድምፅ ማግኘትም ሆነ የጥምር መንግሥት ለመመስረት የሚሆን ስምምነት ማድረግ ሳይችሉ ቆይተዋል። "የግራ ዘመም የጥምር መንግሥት አትመስርቱ፣ ይህ ለእስራኤል ደህንነት አደገኛ ነው" ሲሉ የ 71 ዓመቱ ኔታኒያሁ ተናግረዋል። ኔታኒያሁ ለ12 ዓመታት በስልጣን ላይ የቆዩ መሪ ሲሆኑ፤ የአንድ ትውልድ እድሜ ላለው ግዜ የእስራኤል ፖለቲከ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ይዘው ቆይተዋል። የ49 ዓመቱ ቤኔት በበኩላቸው ፓርቲያቸው የጥምር መንግሥት ለመመስረት የሚደረገውን ድርድር እንደሚቀላቀል በቴሌቪዢን በተላለፈ መልክታቸው ላይ አስታውቀዋል። "ኔታንያሁ ከዚህ በኋላ ቀኝ ዘመም መንግሥት ለማቋቋም አይሞክርም፣ ምክንያቱም እንደሌለ ስለሚያውቀው ነው" ያሉት ቤኔት፤ "የእስራኤል ብሔረተኛ ቡድንን እንዲሁም መላው አገሪቱን ከግሉ አቋም ጎን ለማሰለፍ እየሞከረ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ቤኔት መግለጫውን ከመስጠታቸው በፊት የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን በተዘረዘሩት የስምምነት ነጥቦች መሠረት ቤኔት ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁን እንደሚተኩ እና በኋላም ለ57 ዓመቱ ለማ ላፒድ በቀጣይ ዙር ስልጣኑን እንደሚሰጧቸው ተዘግቧል። ስለ ስምምነቱ በይፋ የተባለ ነገር የለም። ለስምምነት የቀረበው ጥመረት ከቀኝ ፣ ግራ እና ማሃል ሰፋሪ የሆኑ ፖለቲከኞችን ይሰበስባል። ፓርቲዎቹ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ብዙም የሚያመሳስላቸው ነገር ባይኖርም፣ ቤኒያሚን ኔታንያሁ የስልጣን ዘመናቸው እንዲጠናቀቅ ባላቸው ፍላጎት ላይ ግን ይስማማሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-57305762