label
class label 4
classes | headline
stringlengths 17
80
| text
stringlengths 1
16.8k
| headline_text
stringlengths 28
16.8k
| url
stringlengths 36
49
|
---|---|---|---|---|
0business
| የውጭ ባንኮች መግባት አገር በቀል ባንኮችን ያከስማቸዋል? ለተጠቃሚውስ ምን ይዞ ይመጣል? | የኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ለውጭ አገር ባንኮች አዲስ አይደለም። ባንኮ ዲ ሮማ እና አቢሲኒያ ባንክን መጥቀስ ይቻላል። ቢሆንም ላለፈው ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የኢትዮጵያ ገበያ እንደ ባንክ እና ቴሌኮም ያሉ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ለውጭ አገር ኢንቨስተሮችና ለግል ባለሀብቶች ዝግ አድርጎ ቆይቷል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በፈረንጆቹ 2012 በዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ቀርበው ኢትዮጵያ ባንክ እና ቴሌኮምን “ክፍት የምታደርግበት አቅም የላትም” ሲሉ ጠንከር ያለ ንግግድ አድርገው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ “አይደለም እኛ ልንቆጣጠራቸው፤ ልንረዳቸው የማንችላቸው መሳሪያዎች ነው የሚጠቀሙት። እንዴት ብለን ነው ታዲያ የምንቆጣጠራቸው? አይቻልም፤ አሁን አቅሙ የለንም” የሚል ንግግር አሰምተው ነበር። ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትሩን አቋም የሚደግፉት የመኖራቸውን ያህል ከዓለም ገበያ ተነጥለን መቆየት አንችልም ብለው የሚከራከሩም አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ በመንግሥት እጅ ያሉ ተቋማት ቤቶች ለሽያጭ ሊቀርቡ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥተው ነበር። መንግሥት ይህን ለማድረግ የወሰነው ተጨማሪ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ለመሳብ እና በግብርና ላይ የተመሰረተው የአገሪቱ ምጣኔ ሐብትን ለማዘመን በሚል እንደሆነ ይነገራል። በተጨማሪም ይህ እርምጃ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በማቀላጠፍ፣ በሥራ ፈጠራ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በማጎልበት ለምጣኔ ሐብት ዕድገት አስፈላጊ ነው ተብሎ ታምኗል። እነሆ የቴሌኮም ዘርፉ ለውጭ አገር ኢንቨስተሮች ክፍት መሆኑን ተከትሎ የባንኩ ኢንዱስትሪ ለውጭ አገር ባንኮች ክፍት እንዲሆን ተወስኗል። ባለፈው የካቲት ወር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር “ባንኮች በዘመናዊ መንገዶችና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ከዓለም ዕድገት ጋር የሚጓዝ እንዲሁም ከሌሎች አገራት ባንኮች ጋር ለመወዳደር የሚያበቃ ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል” ብለው ነበር። ብሔራዊ ባንክ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲያስችለው የባንክ ፖሊሲ፣ ሕግጋት እና ደንቦችን ሲያሻሽል ቆይቷል። ማሻሻያው የውጭ ባንኮች በቅድሚያ በሽርክና ሥራ እንዲጀምሩ የሚያስችል ዝቅተኛ ካፒታል ማዘጋጀትን ያካትታል። ለመሆኑ የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ለአገር በቀል ባንኮች ስጋት ይሆን? ለተጠቃሚውስ ምን ይዘው ይመጣሉ? በርካታ የአፍሪካ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለመዝለቅ ፍላጎት እያሳዩ እንደሆነ የማዕከላዊ ባንክ አስተዳዳሪ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ከወራት በፊት ተናግረው ነበር። ባለፉት ዓመታት የተለያዩ የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት ከፍተው የአገሪቷን ገበያ እያጤኑ እንደሆነ የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ። ‘ፋርዘር አፍሪካ’ የተባለ ድረገጽ በ2020 ባወጣው መረጃ እ.ኤ.አ ከ2015 ጀምሮ በኢትዮጵያ ዘጠኝ የውጭ ባንኮች ወኪል ጽህፈት ቤት ከፍተዋል። የፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ግሎባል ሊቀመንበር ዘመዴነህ ንጋቱ “አዋጁ ትልቅ እርምጃ ነው” ይላሉ። ዘርፉን ክፍት ያደረጉ የሌሎች አገራትን ተሞክሮ ልምድ የሚወጠቅሱት የፋይናንስ ባለሙያው፤ በአጠቃላይ አገራዊ ምርት [ጂዲፒ] ከሰሃራ በታች ከናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጥላ ሦስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ ዘርፉ መክፈቷ “ለቢዝነስ ዝግጁ መሆኗን የሚያሳይ ነው” ይላሉ። “የውጭ ባንኮች ሲመጡ ዓለም አቀፍ ልምዳቸውን ይዘው ነው የሚመጡት። የማኔጅመንት [አስተዳደር] ልምዳቸውን፣ ቴክኖሎጂያቸውን፣ እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ይዘው ይመጣሉ። ከውጭ የሚመጣን ኢንቨስተር የማስተናገድ አቅም አላቸው።” ዘመዴነህ ባንኮቹ ለደንበኞቻቸው የሚያቀርቡት አገልግሎትንም እንደ አንድ ጥቅም ያወሳሉ። “ለምሳሌ በአሜሪካ ባንኮች ደንበኞቻቸውን በጣም ይንከባከባሉ። እኛ አገር ተጠቃሚው ባንኩን ለምኖ ነው የሚጠቀመው። የተገላቢጦሽ ነው። የሚያበድሩትም ለተወሰነ ሰው ነው።” የዩናይትድ ኪንግደም የተመሰከረላቸው የሒሳብ አዋቂዎች ማኅበር አባል የሆኑት የማማከር እና ኦዲቲንግ ባለሙያው ጥላሁን ግርማ፣ በተመሳሳይ የውጭ አገር ባንኮች ወደ አገር ቤት መምጣታቸው አንደኛው ጥቅሙ የውጭ ኢንቨስተሮችን መሳባቸው ነው ይላሉ። “በሩ ለውጭ አገር ባንኮች መከፈቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እንዲስፋፉ ያደርጋል፤ አዳዲስ የባንክ አገልግሎቶች ለደንበኞች እንዲዳረሱ መንገድ ይፈጥራል፤ የአገር ውስጥ ባንኮች በቂ ፋይናንስ ይሰጡኛል ብለው የማይተማመኑ የውጭ አገር ኢንቨስተሮችን ሊጋብዝ ይችላል።” አማካሪው “ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲቲባንክ አሊያም ስታንዳርድ ቻርደተርድ ቢገባ የውጭ አገር ኢንቨስተሮች ጥናት ሲሰሩ አንደ አንድ መልካም ጎን ያዩታል” ሲሉ ያክላሉ። ነገር ግን አቶ ጥላሁን እንደሚሉት ኢትዮጵያ የባንኩን ኢንዱስትሪ ለውጭ ባንኮች የከፈትችው ከዓለም አቀፍ ተቋማት በደረሰባት ጫና ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ። “የዓለም ንግድ ድርጅት አንደኛው መመዘኛው አገራት የንግድና አገልግሎት መሣለጥን ማገድ የለባቸውም የሚል ነው። ስለዚህ ጫናው በዋናነትነ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማትና ከዓለም ንግድ ድርጅት የመጣ ነው” ሲሉ ይከራከራሉ። ዘመዴነህ፤ ዓለም አቀፍ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ከአገር በቀል ባንኮች ጋር የመሥራት ዕድል ስላላቸው ቴክኖሎጂው ይሸጋገራል ይላሉ። ቢሆንም የሒሳብ አማካሪው ጥላሁን የአገር ውስጥ ባንኮች ከቀድሞው በተሻለ የካፒታልና የቴክኖሎጂ ደረጃ ላይ ቢሆኑም ገና በጣም ብዙ እንደሚቀራቸው ይናገራሉ። ታድያ የኢትዮጵያ የግል ባንኮች ይህንን ፉክክር እንዴት መግጠም ይችላሉ? የውጭ ባንኮች እንዲገቡ መፈቀዱ ለአገር በቀል ባንኮች “መልካም አጋጣሚ” ነው የሚሉት ዘመዴነህ ንጋቱ፣ “የአገር ውስጥ ባንኮች አትራፊ ቢሆኑም በዓለም አቀፍ ደረጃ የመወዳደር ልምድ የላቸውም። እነዚህ የውጭ ባንኮች በሚመጡበት ጊዜ አብረው የመሥራት ዕድል ይኖራቸዋል” የሚል መከራከሪያ ያስቀምጣሉ። መንግሥት አገር በቀል ባንኮች አዲሱን ፖሊሲ ተከትሎ ተፎካካሪ ሆነው መቀጠል የሚሹ ከሆነ መዋሃድ አለባቸው የሚል ሐሳብ ይሰጣል። ዘመዴነህ በዚህ ሐሳብ ይስማማሉ። ለበርካታ ዓመታት ኧርንስት ኤንድ ያንግ ከተሰኘው ኩባንያ ጋር የሠሩት ዘመዴነህ፤ “ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ትልቁ የግል ባንክ የሆነው አዋሽ ባንክ በአፍሪካ ደረጃ እንኳ 83ተኛ ደረጃ ላይ ነው የተቀመጠው” በማለት ባንኮች መጣመር እንዳለባቸው ያሰምራሉ። “በዘርፉ ባንኮች የሚኖራቸው አቅም ትልቅ ዋጋ አለው። 18 ባንኮች አሉን፤ በቅርቡ ሦስት፣ አራት ሊጨመሩ ይችላሉ። 10 ገደማ ደግሞ ፈቃድ እየጠበቁ ነው። ይህ ጨርሶ አስፈላጊ አይደለም። በእኔ ግምት የዛሬ አንድ ዓመት ተኩል 5 ትላልቅ አቅም ያላቸው የግል ባንኮች ይኖራሉ።” ባንኮች ቢዋሃዱ የማበደር አቅማቸው ከፍ ይላል፣ ቴክኖሎጂያቸው ያድጋል፣ አልፎም ውጭ ባንኮች ቢመጡም የመቋቋም አቅም ይኖራቸዋል ይላሉ። ናይጄሪያን በምሳሌነት የሚጠቅሱት አማካሪ እና ኦዲተሩ ጥላሁን “መጀመሪያ በውዴታ እንዲዋሃዱ ሊደረግ ይችላል፤ አሊያም አቅም ያለው አቅም የሌለውን ሊጠቀልል ይችላል” የሚል ትንበያ አላቸው። የውጭ ባንኮች ሲገቡ አገር በቀል ባንኮች ሊከስሙ ይችላሉ የሚለውን ስጋት በተመለከተም “የኢትዮጵያ ባንኮች ይጠፋሉ የሚል ግምት የለኝም። ‘ኮርፖሬት’ ደንበኞቻቸውን ይነጠቃሉ? አዎ!” ይላሉ አቶ ጥላሁን። “መሳሳት የሌለብን እነዚህ የውጭ ባንኮች ገጠር ድረስ ዘልቀው በዝቅተኛ ደረጃ [ሪቴይል ባንኪንግ] ይሠራሉ ተብሎ አይታሰብም።” ዘመዴነህ ከባንኮች መዋሃድ በተጨማሪ ‘ጆይንት ቬንቸር’ የተሰኘው የኢኮኖሚ ሥርዓት መተግበር ቢችል አዋጭ ነው ባይ ናቸው። “ለምሳሌ ቻይና መጀመሪያ ባንኮች ሲገቡ ‘በጆይንት ቬንቸር’ እንዲገቡ ነው የፈቀደችው። ይህ ማለት የውጭ ባንኮች የተወሰነ ድርሻ ገዝተው እንዲገቡ ማድረግ ማለት ነው።” ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ባንኮች ድርሻ ገዝተው አብረው መሥራት ቢችሉ የማደግ ጥሩ ዕድል ይኖራቸዋል የሚል ሐሳብ አላቸው። አገር በቀል ባንኮች አይጠፉም ሲሉ የሚከራከሩት ጥላሁን የውጭ ባንኮች ትኩረታቸውን በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እና ሌሎች ትላልቅ ከተሞች ላይ ስለሚያደርጉ፣ አገር በቀል ባንኮች የተቀረውን ማኅበረሰብ ማገልገል ይችላሉ ይላሉ። “በፖሊሲ ካላስገደድናቸው በቀር ሥራቸውን የሚሠሩት በአንድ ዋና መሥሪያ ቤት፤ የተቀረውን ደግሞ በቴክኖሎጂ በማስተሳሰር እንጂ፣ እንደኛ ባንኮች በየመንደሩ ቅርንጫፍ ይከፍታሉ ተብሎ አይታሰብም።” አማካሪው ‘ኮርፖሬት ደንበኛ’ የተሰኘውን ሐሳብ ደጋግመው ያነሳሉ። ለመሆኑ ኮርፖሬት ደንበኛ ምን ማለት ነው? “በባንክ ኢንዱስትሪ 20/80 የሚባል ነገር አለ። 20 በመቶው ለባንኮች ትልቅ የውጭ ምንዛሬ የሚያመጡ ናቸው። የውጭ ባንኮች እነዚህን ደንበኞች ለመንጠቅ አሰፍስፈው እንደሚመጡ ምንም ጥርጥር የለኝም። ዒላማቸው ‘ኮርፖሬት’ ደንበኛ ናቸው እንጂ ታች ወርደው ብድር ይሰጣሉ ብሎ ማሰብ ስህተት ነው።” ጥላሁን፤ “ለዚህ ነው ለውድድር እንዲመቻቸው መዋሃድ ይኖርባቸዋል የምለው፤ ብሔራዊ ባንኩም ሰላሳ አርባ ባንክ መቆጣጠር አይጠበቅበትም” ይላሉ። ባለሙያው፤ የብሔራዊ ባንክ የባንኮችን ‘ካፒታል’ አሁን ካለበት በቅርቡ ከፍ ሊያደርገው የሚችል ሲሆን፣ “ይህንን ለማሟላት ደግሞ አገር በቀል ባንኮች ያላቸው አማራጭ መዋሃድ ብቻ ነው።” በምጣኔ ሃብት ጉዳዮች የተለያዩ ጽሑፎችን በማቅረብ የሚታወቁት የኩዌት ኢንስቲትዩት ፎር ሳይንቲፊክ ሪሰርች ተመራማሪው አየለ ገላን (ዶ/ር) የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ መፈቀዱን አጥብቀው ከሚቃወሙ መካከል ናቸው። “ይህ ውሳኔ የራስ ምታት ላለበት ሰው የሆድ ቁርጠት መድኃኒት እንደመስጠት ነው” የሚሉት የምጣኔ ሃብት ምሁሩ፣ የባንክ ኢንዱስትሪውን ለውጭ ባንኮች ክፍት ማድረግ “አገር ውስጥ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘብ አይደለም” ይላሉ። እንደ አየለ ገለፃ የኢትዮጵያ የባንክ እና የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ሁለት ቀንደኛ ችግሮች አሉበት። አንደኛው ‘ስትራክቸራል ኢንባላንስ’ ማለትም ትላልቅ የመንግሥት ባንኮች የሚወዳደሩት ‘ትናንሽ’ ከሚባሉት ጋር መሆኑ ነው ሲሉ ይተነትናሉ። ይህንን ለመፍታት እኒህ ትላልቅ ባንኮች ተከፋፍለው አነስተኛ ባንኮች እንዲሆኑ አሊያም የግል እንዲሆኑ ማድረግ [ፕራይቬታይዝ] ነው እንጂ የውጭ ባንኮችን ማምጣት መፍትሔ አይሆንም ይላሉ። እንደምጣኔ ሃብት ባለሙያው ገለፃ ሁለተኛው የፋይናንስ ዘርፍ ችግር ቁጥጥር (ሬጉሌሽን) ነው። የባንኮችን የብድር የወለድ መጠንን እንደምሳሌ ይጠቅሳሉ። “ከዓለም አገራት በ15 አሊያም በ18 በመቶ የወለድ መጠን ተበድሮ፣ ነግዶ፣ አትርፎ ብድሩን በመመለስ አገር ይለውጣል ማለት ዘበት ነው።» ይህ ችግር የመነጨው የመንግሥት አስተዳደር ውስጥ ያሉ አካላትና የባንክ ባለቤቶች በመስማማት በመወሰናቸው ነው ይላሉ። ነገር ግን ዘመዴነህም ሆኑ ጥላሁን የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው የወለድ መጠኑ እንዲቀንስ ያስችላል ሲሉ ይከራከራሉ። “የእነዚህ የውጭ ባንኮች መግባት ሌሎቹን የግል ባንኮች ያነቃል። ለምሳሌ የወለድ ቅናሽ ሊኖር ይችላል” ይላሉ ጥላሁን። እንደ ሌሎች አገራት የብድር ወለድ መጠን ወደ ሰባት እና ስድስት በመቶ መውረድ አለበት ብለው የሚከራከሩት አየለ ገላን (ዶ/ር) ባንኮች ትርፋቸው ሊቀንስ ቢችልም፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ከዚህ በፊት መበደር ያልቻሉ ሰዎች የብድር አቅርቦት ያገኛሉ ሲሉ ያስረዳሉ። ባለሙያው መንግሥት የውጭ ባንኮች እንዲገቡ መፍቀዱ ከላይ ከተነሱት ሁለት አበይት ችግሮች ጋር “በፍፁም አይገናኝም” ይላሉ። ተመራማሪው የውጭ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ይዘው ይመጣሉ የሚለውን ሐሳብ አጥብቀው ይተቻሉ። ይህንን ሲያብራሩም “ለዘላቂ ችግር ጊዜያዊ መፍትሔት ማበጀት ፋይዳ የለውም” የሚለውን የፈረንጅ አባባል በማውሳት ነው። “ወደ ሃገር ቤት የሚመጣው ኩባንያ ሲገባ መጀመሪያ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ይዞ ሊመጣ ይችላል። ነገር ግን ሥራ ከጀመረ በኋላ በየወሩ ዶላር ወደ ውጭ ይልካል። ዶላር ወደ ሃገር ቤት የሚመጣ ምርት ወደ ውጭ ስንልክ ነው እንጂ፣ እነዚህ ባንኮች ዶላሩን ወደ አገር ቤት አምጥተው የሚለግሱበት ምንም ምክንያት የላቸውም።” አየለ፤ የውጭ ባንኮች አዳዲስ ቴክኖሎጂ ያስተዋውቃሉ የሚለውን መከራከሪያም “ፎልስ ኢኮኖሚክስ” ነው በማለት ውድቅ ያደርጉታል። “እነዚህ ባንኮች የሚያመጡት ቴክኖሎጂ የሮኬት ሳይንስ አይደለም። ቴክኖሎጂ በሰው አአምሮ ውስጥ እንጂ በባንኮች እጅ አይደለም ያለው። የመኪና መገጣጠሚያ አሊያም የማዳበሪያ ፋብሪካ እናስገባለን ቢሉ ያስማማል” በማለት። የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ሲገቡ ምን ዓይነት ቁጥጥር ሊደርግባቸው ይገባል? የሚለው ጥያቄ ሌላኛው መከራከሪያ ነው። “ባፉት 27 ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ አንድም ባንክ አልከሰመም ሲሉ የሚናገሩት ዘመዴነህ ብሔራዊ ባንክ እስካሁን በቁጥጥር ረገድ መልካም ሥራ ሠርቷል ብለው ያምናሉ። “ነገር ግን አሁን የውጭ ባንኮች እየመጡ ስለሆነ ብሔራዊ ባንክ የቁጥጥር አቅሙን ከፍ ማድረግ አለበት። ምክንያቱም ሃገር በቀል ባንኮችን መቆጣጠር እና በጣም ውስብስብ የሆኑ ዓለም አቀፍ ባንኮችን መቆጣጠር በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው።” ጥላሁንም ‘ኮርፖሬት’ ደንበኛ ላይ አተኩረው ለሚሠሩ ባንኮች የሚሆን አዲስ ቁጥጥር በቅርቡ ሊወጣ እንደሚችል ይገምታሉ። ብሔራዊ ባንክ፤ የውጭ ሃገራት ወደ ሃገር ቤት ሲገቡ “የጤናማ ብድር መጠን ሕጉን ያስተካክላል” ብለው ያምናሉ። ነገር ግን ይላሉ፤ “አሁን እንዲገቡ እንደተፈቀደላቸው ሁሉ ሲወጡ እንዴት ነው የሚለው ሊታሰብበት ይገባል።” “ብሔራዊ ባንክ የሚያወጣቸውን መመሪያዎች መከታተል ይኖርብናል። በየዓመቱ ምን ያክል ገንዘብ ማስወጣት ይችላሉ የሚለው ነገር መመጠን ያለበት ይመስለኛል። ኢትዮጵያዊያን ድርሻ የሚገዙበትም አግባብ ሊኖር ይገባል።” | የውጭ ባንኮች መግባት አገር በቀል ባንኮችን ያከስማቸዋል? ለተጠቃሚውስ ምን ይዞ ይመጣል? የኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ለውጭ አገር ባንኮች አዲስ አይደለም። ባንኮ ዲ ሮማ እና አቢሲኒያ ባንክን መጥቀስ ይቻላል። ቢሆንም ላለፈው ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የኢትዮጵያ ገበያ እንደ ባንክ እና ቴሌኮም ያሉ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ለውጭ አገር ኢንቨስተሮችና ለግል ባለሀብቶች ዝግ አድርጎ ቆይቷል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በፈረንጆቹ 2012 በዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ቀርበው ኢትዮጵያ ባንክ እና ቴሌኮምን “ክፍት የምታደርግበት አቅም የላትም” ሲሉ ጠንከር ያለ ንግግድ አድርገው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ “አይደለም እኛ ልንቆጣጠራቸው፤ ልንረዳቸው የማንችላቸው መሳሪያዎች ነው የሚጠቀሙት። እንዴት ብለን ነው ታዲያ የምንቆጣጠራቸው? አይቻልም፤ አሁን አቅሙ የለንም” የሚል ንግግር አሰምተው ነበር። ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትሩን አቋም የሚደግፉት የመኖራቸውን ያህል ከዓለም ገበያ ተነጥለን መቆየት አንችልም ብለው የሚከራከሩም አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ በመንግሥት እጅ ያሉ ተቋማት ቤቶች ለሽያጭ ሊቀርቡ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥተው ነበር። መንግሥት ይህን ለማድረግ የወሰነው ተጨማሪ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ለመሳብ እና በግብርና ላይ የተመሰረተው የአገሪቱ ምጣኔ ሐብትን ለማዘመን በሚል እንደሆነ ይነገራል። በተጨማሪም ይህ እርምጃ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በማቀላጠፍ፣ በሥራ ፈጠራ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በማጎልበት ለምጣኔ ሐብት ዕድገት አስፈላጊ ነው ተብሎ ታምኗል። እነሆ የቴሌኮም ዘርፉ ለውጭ አገር ኢንቨስተሮች ክፍት መሆኑን ተከትሎ የባንኩ ኢንዱስትሪ ለውጭ አገር ባንኮች ክፍት እንዲሆን ተወስኗል። ባለፈው የካቲት ወር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር “ባንኮች በዘመናዊ መንገዶችና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ከዓለም ዕድገት ጋር የሚጓዝ እንዲሁም ከሌሎች አገራት ባንኮች ጋር ለመወዳደር የሚያበቃ ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል” ብለው ነበር። ብሔራዊ ባንክ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲያስችለው የባንክ ፖሊሲ፣ ሕግጋት እና ደንቦችን ሲያሻሽል ቆይቷል። ማሻሻያው የውጭ ባንኮች በቅድሚያ በሽርክና ሥራ እንዲጀምሩ የሚያስችል ዝቅተኛ ካፒታል ማዘጋጀትን ያካትታል። ለመሆኑ የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ለአገር በቀል ባንኮች ስጋት ይሆን? ለተጠቃሚውስ ምን ይዘው ይመጣሉ? በርካታ የአፍሪካ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለመዝለቅ ፍላጎት እያሳዩ እንደሆነ የማዕከላዊ ባንክ አስተዳዳሪ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ከወራት በፊት ተናግረው ነበር። ባለፉት ዓመታት የተለያዩ የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት ከፍተው የአገሪቷን ገበያ እያጤኑ እንደሆነ የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ። ‘ፋርዘር አፍሪካ’ የተባለ ድረገጽ በ2020 ባወጣው መረጃ እ.ኤ.አ ከ2015 ጀምሮ በኢትዮጵያ ዘጠኝ የውጭ ባንኮች ወኪል ጽህፈት ቤት ከፍተዋል። የፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ግሎባል ሊቀመንበር ዘመዴነህ ንጋቱ “አዋጁ ትልቅ እርምጃ ነው” ይላሉ። ዘርፉን ክፍት ያደረጉ የሌሎች አገራትን ተሞክሮ ልምድ የሚወጠቅሱት የፋይናንስ ባለሙያው፤ በአጠቃላይ አገራዊ ምርት [ጂዲፒ] ከሰሃራ በታች ከናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጥላ ሦስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ ዘርፉ መክፈቷ “ለቢዝነስ ዝግጁ መሆኗን የሚያሳይ ነው” ይላሉ። “የውጭ ባንኮች ሲመጡ ዓለም አቀፍ ልምዳቸውን ይዘው ነው የሚመጡት። የማኔጅመንት [አስተዳደር] ልምዳቸውን፣ ቴክኖሎጂያቸውን፣ እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ይዘው ይመጣሉ። ከውጭ የሚመጣን ኢንቨስተር የማስተናገድ አቅም አላቸው።” ዘመዴነህ ባንኮቹ ለደንበኞቻቸው የሚያቀርቡት አገልግሎትንም እንደ አንድ ጥቅም ያወሳሉ። “ለምሳሌ በአሜሪካ ባንኮች ደንበኞቻቸውን በጣም ይንከባከባሉ። እኛ አገር ተጠቃሚው ባንኩን ለምኖ ነው የሚጠቀመው። የተገላቢጦሽ ነው። የሚያበድሩትም ለተወሰነ ሰው ነው።” የዩናይትድ ኪንግደም የተመሰከረላቸው የሒሳብ አዋቂዎች ማኅበር አባል የሆኑት የማማከር እና ኦዲቲንግ ባለሙያው ጥላሁን ግርማ፣ በተመሳሳይ የውጭ አገር ባንኮች ወደ አገር ቤት መምጣታቸው አንደኛው ጥቅሙ የውጭ ኢንቨስተሮችን መሳባቸው ነው ይላሉ። “በሩ ለውጭ አገር ባንኮች መከፈቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እንዲስፋፉ ያደርጋል፤ አዳዲስ የባንክ አገልግሎቶች ለደንበኞች እንዲዳረሱ መንገድ ይፈጥራል፤ የአገር ውስጥ ባንኮች በቂ ፋይናንስ ይሰጡኛል ብለው የማይተማመኑ የውጭ አገር ኢንቨስተሮችን ሊጋብዝ ይችላል።” አማካሪው “ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲቲባንክ አሊያም ስታንዳርድ ቻርደተርድ ቢገባ የውጭ አገር ኢንቨስተሮች ጥናት ሲሰሩ አንደ አንድ መልካም ጎን ያዩታል” ሲሉ ያክላሉ። ነገር ግን አቶ ጥላሁን እንደሚሉት ኢትዮጵያ የባንኩን ኢንዱስትሪ ለውጭ ባንኮች የከፈትችው ከዓለም አቀፍ ተቋማት በደረሰባት ጫና ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ። “የዓለም ንግድ ድርጅት አንደኛው መመዘኛው አገራት የንግድና አገልግሎት መሣለጥን ማገድ የለባቸውም የሚል ነው። ስለዚህ ጫናው በዋናነትነ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማትና ከዓለም ንግድ ድርጅት የመጣ ነው” ሲሉ ይከራከራሉ። ዘመዴነህ፤ ዓለም አቀፍ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ከአገር በቀል ባንኮች ጋር የመሥራት ዕድል ስላላቸው ቴክኖሎጂው ይሸጋገራል ይላሉ። ቢሆንም የሒሳብ አማካሪው ጥላሁን የአገር ውስጥ ባንኮች ከቀድሞው በተሻለ የካፒታልና የቴክኖሎጂ ደረጃ ላይ ቢሆኑም ገና በጣም ብዙ እንደሚቀራቸው ይናገራሉ። ታድያ የኢትዮጵያ የግል ባንኮች ይህንን ፉክክር እንዴት መግጠም ይችላሉ? የውጭ ባንኮች እንዲገቡ መፈቀዱ ለአገር በቀል ባንኮች “መልካም አጋጣሚ” ነው የሚሉት ዘመዴነህ ንጋቱ፣ “የአገር ውስጥ ባንኮች አትራፊ ቢሆኑም በዓለም አቀፍ ደረጃ የመወዳደር ልምድ የላቸውም። እነዚህ የውጭ ባንኮች በሚመጡበት ጊዜ አብረው የመሥራት ዕድል ይኖራቸዋል” የሚል መከራከሪያ ያስቀምጣሉ። መንግሥት አገር በቀል ባንኮች አዲሱን ፖሊሲ ተከትሎ ተፎካካሪ ሆነው መቀጠል የሚሹ ከሆነ መዋሃድ አለባቸው የሚል ሐሳብ ይሰጣል። ዘመዴነህ በዚህ ሐሳብ ይስማማሉ። ለበርካታ ዓመታት ኧርንስት ኤንድ ያንግ ከተሰኘው ኩባንያ ጋር የሠሩት ዘመዴነህ፤ “ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ትልቁ የግል ባንክ የሆነው አዋሽ ባንክ በአፍሪካ ደረጃ እንኳ 83ተኛ ደረጃ ላይ ነው የተቀመጠው” በማለት ባንኮች መጣመር እንዳለባቸው ያሰምራሉ። “በዘርፉ ባንኮች የሚኖራቸው አቅም ትልቅ ዋጋ አለው። 18 ባንኮች አሉን፤ በቅርቡ ሦስት፣ አራት ሊጨመሩ ይችላሉ። 10 ገደማ ደግሞ ፈቃድ እየጠበቁ ነው። ይህ ጨርሶ አስፈላጊ አይደለም። በእኔ ግምት የዛሬ አንድ ዓመት ተኩል 5 ትላልቅ አቅም ያላቸው የግል ባንኮች ይኖራሉ።” ባንኮች ቢዋሃዱ የማበደር አቅማቸው ከፍ ይላል፣ ቴክኖሎጂያቸው ያድጋል፣ አልፎም ውጭ ባንኮች ቢመጡም የመቋቋም አቅም ይኖራቸዋል ይላሉ። ናይጄሪያን በምሳሌነት የሚጠቅሱት አማካሪ እና ኦዲተሩ ጥላሁን “መጀመሪያ በውዴታ እንዲዋሃዱ ሊደረግ ይችላል፤ አሊያም አቅም ያለው አቅም የሌለውን ሊጠቀልል ይችላል” የሚል ትንበያ አላቸው። የውጭ ባንኮች ሲገቡ አገር በቀል ባንኮች ሊከስሙ ይችላሉ የሚለውን ስጋት በተመለከተም “የኢትዮጵያ ባንኮች ይጠፋሉ የሚል ግምት የለኝም። ‘ኮርፖሬት’ ደንበኞቻቸውን ይነጠቃሉ? አዎ!” ይላሉ አቶ ጥላሁን። “መሳሳት የሌለብን እነዚህ የውጭ ባንኮች ገጠር ድረስ ዘልቀው በዝቅተኛ ደረጃ [ሪቴይል ባንኪንግ] ይሠራሉ ተብሎ አይታሰብም።” ዘመዴነህ ከባንኮች መዋሃድ በተጨማሪ ‘ጆይንት ቬንቸር’ የተሰኘው የኢኮኖሚ ሥርዓት መተግበር ቢችል አዋጭ ነው ባይ ናቸው። “ለምሳሌ ቻይና መጀመሪያ ባንኮች ሲገቡ ‘በጆይንት ቬንቸር’ እንዲገቡ ነው የፈቀደችው። ይህ ማለት የውጭ ባንኮች የተወሰነ ድርሻ ገዝተው እንዲገቡ ማድረግ ማለት ነው።” ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ባንኮች ድርሻ ገዝተው አብረው መሥራት ቢችሉ የማደግ ጥሩ ዕድል ይኖራቸዋል የሚል ሐሳብ አላቸው። አገር በቀል ባንኮች አይጠፉም ሲሉ የሚከራከሩት ጥላሁን የውጭ ባንኮች ትኩረታቸውን በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እና ሌሎች ትላልቅ ከተሞች ላይ ስለሚያደርጉ፣ አገር በቀል ባንኮች የተቀረውን ማኅበረሰብ ማገልገል ይችላሉ ይላሉ። “በፖሊሲ ካላስገደድናቸው በቀር ሥራቸውን የሚሠሩት በአንድ ዋና መሥሪያ ቤት፤ የተቀረውን ደግሞ በቴክኖሎጂ በማስተሳሰር እንጂ፣ እንደኛ ባንኮች በየመንደሩ ቅርንጫፍ ይከፍታሉ ተብሎ አይታሰብም።” አማካሪው ‘ኮርፖሬት ደንበኛ’ የተሰኘውን ሐሳብ ደጋግመው ያነሳሉ። ለመሆኑ ኮርፖሬት ደንበኛ ምን ማለት ነው? “በባንክ ኢንዱስትሪ 20/80 የሚባል ነገር አለ። 20 በመቶው ለባንኮች ትልቅ የውጭ ምንዛሬ የሚያመጡ ናቸው። የውጭ ባንኮች እነዚህን ደንበኞች ለመንጠቅ አሰፍስፈው እንደሚመጡ ምንም ጥርጥር የለኝም። ዒላማቸው ‘ኮርፖሬት’ ደንበኛ ናቸው እንጂ ታች ወርደው ብድር ይሰጣሉ ብሎ ማሰብ ስህተት ነው።” ጥላሁን፤ “ለዚህ ነው ለውድድር እንዲመቻቸው መዋሃድ ይኖርባቸዋል የምለው፤ ብሔራዊ ባንኩም ሰላሳ አርባ ባንክ መቆጣጠር አይጠበቅበትም” ይላሉ። ባለሙያው፤ የብሔራዊ ባንክ የባንኮችን ‘ካፒታል’ አሁን ካለበት በቅርቡ ከፍ ሊያደርገው የሚችል ሲሆን፣ “ይህንን ለማሟላት ደግሞ አገር በቀል ባንኮች ያላቸው አማራጭ መዋሃድ ብቻ ነው።” በምጣኔ ሃብት ጉዳዮች የተለያዩ ጽሑፎችን በማቅረብ የሚታወቁት የኩዌት ኢንስቲትዩት ፎር ሳይንቲፊክ ሪሰርች ተመራማሪው አየለ ገላን (ዶ/ር) የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ መፈቀዱን አጥብቀው ከሚቃወሙ መካከል ናቸው። “ይህ ውሳኔ የራስ ምታት ላለበት ሰው የሆድ ቁርጠት መድኃኒት እንደመስጠት ነው” የሚሉት የምጣኔ ሃብት ምሁሩ፣ የባንክ ኢንዱስትሪውን ለውጭ ባንኮች ክፍት ማድረግ “አገር ውስጥ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘብ አይደለም” ይላሉ። እንደ አየለ ገለፃ የኢትዮጵያ የባንክ እና የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ሁለት ቀንደኛ ችግሮች አሉበት። አንደኛው ‘ስትራክቸራል ኢንባላንስ’ ማለትም ትላልቅ የመንግሥት ባንኮች የሚወዳደሩት ‘ትናንሽ’ ከሚባሉት ጋር መሆኑ ነው ሲሉ ይተነትናሉ። ይህንን ለመፍታት እኒህ ትላልቅ ባንኮች ተከፋፍለው አነስተኛ ባንኮች እንዲሆኑ አሊያም የግል እንዲሆኑ ማድረግ [ፕራይቬታይዝ] ነው እንጂ የውጭ ባንኮችን ማምጣት መፍትሔ አይሆንም ይላሉ። እንደምጣኔ ሃብት ባለሙያው ገለፃ ሁለተኛው የፋይናንስ ዘርፍ ችግር ቁጥጥር (ሬጉሌሽን) ነው። የባንኮችን የብድር የወለድ መጠንን እንደምሳሌ ይጠቅሳሉ። “ከዓለም አገራት በ15 አሊያም በ18 በመቶ የወለድ መጠን ተበድሮ፣ ነግዶ፣ አትርፎ ብድሩን በመመለስ አገር ይለውጣል ማለት ዘበት ነው።» ይህ ችግር የመነጨው የመንግሥት አስተዳደር ውስጥ ያሉ አካላትና የባንክ ባለቤቶች በመስማማት በመወሰናቸው ነው ይላሉ። ነገር ግን ዘመዴነህም ሆኑ ጥላሁን የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው የወለድ መጠኑ እንዲቀንስ ያስችላል ሲሉ ይከራከራሉ። “የእነዚህ የውጭ ባንኮች መግባት ሌሎቹን የግል ባንኮች ያነቃል። ለምሳሌ የወለድ ቅናሽ ሊኖር ይችላል” ይላሉ ጥላሁን። እንደ ሌሎች አገራት የብድር ወለድ መጠን ወደ ሰባት እና ስድስት በመቶ መውረድ አለበት ብለው የሚከራከሩት አየለ ገላን (ዶ/ር) ባንኮች ትርፋቸው ሊቀንስ ቢችልም፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ከዚህ በፊት መበደር ያልቻሉ ሰዎች የብድር አቅርቦት ያገኛሉ ሲሉ ያስረዳሉ። ባለሙያው መንግሥት የውጭ ባንኮች እንዲገቡ መፍቀዱ ከላይ ከተነሱት ሁለት አበይት ችግሮች ጋር “በፍፁም አይገናኝም” ይላሉ። ተመራማሪው የውጭ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ይዘው ይመጣሉ የሚለውን ሐሳብ አጥብቀው ይተቻሉ። ይህንን ሲያብራሩም “ለዘላቂ ችግር ጊዜያዊ መፍትሔት ማበጀት ፋይዳ የለውም” የሚለውን የፈረንጅ አባባል በማውሳት ነው። “ወደ ሃገር ቤት የሚመጣው ኩባንያ ሲገባ መጀመሪያ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ይዞ ሊመጣ ይችላል። ነገር ግን ሥራ ከጀመረ በኋላ በየወሩ ዶላር ወደ ውጭ ይልካል። ዶላር ወደ ሃገር ቤት የሚመጣ ምርት ወደ ውጭ ስንልክ ነው እንጂ፣ እነዚህ ባንኮች ዶላሩን ወደ አገር ቤት አምጥተው የሚለግሱበት ምንም ምክንያት የላቸውም።” አየለ፤ የውጭ ባንኮች አዳዲስ ቴክኖሎጂ ያስተዋውቃሉ የሚለውን መከራከሪያም “ፎልስ ኢኮኖሚክስ” ነው በማለት ውድቅ ያደርጉታል። “እነዚህ ባንኮች የሚያመጡት ቴክኖሎጂ የሮኬት ሳይንስ አይደለም። ቴክኖሎጂ በሰው አአምሮ ውስጥ እንጂ በባንኮች እጅ አይደለም ያለው። የመኪና መገጣጠሚያ አሊያም የማዳበሪያ ፋብሪካ እናስገባለን ቢሉ ያስማማል” በማለት። የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ሲገቡ ምን ዓይነት ቁጥጥር ሊደርግባቸው ይገባል? የሚለው ጥያቄ ሌላኛው መከራከሪያ ነው። “ባፉት 27 ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ አንድም ባንክ አልከሰመም ሲሉ የሚናገሩት ዘመዴነህ ብሔራዊ ባንክ እስካሁን በቁጥጥር ረገድ መልካም ሥራ ሠርቷል ብለው ያምናሉ። “ነገር ግን አሁን የውጭ ባንኮች እየመጡ ስለሆነ ብሔራዊ ባንክ የቁጥጥር አቅሙን ከፍ ማድረግ አለበት። ምክንያቱም ሃገር በቀል ባንኮችን መቆጣጠር እና በጣም ውስብስብ የሆኑ ዓለም አቀፍ ባንኮችን መቆጣጠር በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው።” ጥላሁንም ‘ኮርፖሬት’ ደንበኛ ላይ አተኩረው ለሚሠሩ ባንኮች የሚሆን አዲስ ቁጥጥር በቅርቡ ሊወጣ እንደሚችል ይገምታሉ። ብሔራዊ ባንክ፤ የውጭ ሃገራት ወደ ሃገር ቤት ሲገቡ “የጤናማ ብድር መጠን ሕጉን ያስተካክላል” ብለው ያምናሉ። ነገር ግን ይላሉ፤ “አሁን እንዲገቡ እንደተፈቀደላቸው ሁሉ ሲወጡ እንዴት ነው የሚለው ሊታሰብበት ይገባል።” “ብሔራዊ ባንክ የሚያወጣቸውን መመሪያዎች መከታተል ይኖርብናል። በየዓመቱ ምን ያክል ገንዘብ ማስወጣት ይችላሉ የሚለው ነገር መመጠን ያለበት ይመስለኛል። ኢትዮጵያዊያን ድርሻ የሚገዙበትም አግባብ ሊኖር ይገባል።” | https://www.bbc.com/amharic/articles/ckv82ekpjk5o |
2health
| የዓለም ጤና ድርጅት ኮቪድ-19 ለተጨማሪ አንድ ዓመት አብሮን ሊቆይ ይችላል አለ | በመላው ዓለም የሚገኙ ድሃ አገራት የኮቪድ-19 ክትባትን በተገቢው ጊዜና መጠን እያገኙ ባለመሆናቸው ወረርሽኙ መቆየት ከሚገባው በላይ አንድ ተጨማሪ ዓመት አብሮን ይኖራል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በድርጅቱ ከፍተኛ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ብሩስ አሊዋርድ በዚሁ ችግር ምክንያት የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ እስከ አውሮፓውያኑ 2022 ድረስ ይቆያል ብለዋል። እስካሁን 5 በመቶ ብቻ የሚሆነው የአፍሪካ ሕዝብ ክትባቱን ማግኘት የቻለ ሲሆን በሌሎች አህጉራት ደግሞ እስከ 40 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ክትባቱን አግኝቷል። ዩናይትድ ኪንግደም እስካሁን 10 ሚሊዮን ክትባቶችን ለድሃ አገራት ያደረሰች ሲሆን አጠቃላይ እቅዷ 100 ሚሊዮን ክትባቶችን ማድረስ ነው። ሀብታሞቹ አገራት ክትባቱን ለማግኘት የሚያደርጉትን እሽቅድድም ገታ አድርገው ትልልቅ መድኃኒት አምራች ኩባንያዎች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገራት ላይ ትኩረታቸውን እንዲያደርጉ እንዲፈቅዱላቸው ዶክተር ብሩስ ጠይቀዋል። አክለውም "ሀብታም አገራት በያዝነው ዓመት የቡድን 7 ስብሰባ ላይ እርዳታ ለማድረግ የገቡትን ቃል መልሰው ሊቃኙት ይገባል" ብለዋል። "እውነታውን ልንገራችሁ፤ ከእቅዳችን በጣም ወደኋላ ቀርተናል። ቃል የተገባውን ገንዘብ በፍጥነት ልንጠቀምበት ይገባል። አለበለዚያ ግን ይህ ወረርሽኝ ለተጨማሪ ዓመት አብሮን እንዲቆይ ይሆናል።'' የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጥምረት የሆነው 'ፒፕልስ ቫክሲን' ባወጣው መረጃ መሰረት የበለጸጉት አገራትና ትልልቅ የመድኃኒት አምራች ድርጅቶች ለመስጠት ቃል ከገቡት የክትባት መጠን ቢያንስ ከእያንዳንዱ 7 ክትባት አንዱ ብቻ ነው ወደ ድሃ አገራት እየደረሰ የሚገኘው። በተቃራኒው ክትባቶቹ ከፍተኛ ገቢ ላላቸውና በበለጸጉት አገራት ለሚኖሩ ዜጎች ነው በስፋት እየተዳረሱ የሚገኙት። አፍሪካም ቢሆን እስካሁን ከመላው ዓለም ካለው ፍላጎት 2.6 በመቶ የሚሆነው ብቻ ነው የቀረበላት። በተጨማሪም እንደ ኦክስፋም እና ዩኤንኤይድ የመሳሰሉ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን የያዘው ጥምረት ዩናይትድ ኪንግደም እና ካናዳ በኮቫክስ በኩል የሚመጡ ክትባቶን ለዜጎቻቸው አከፋፍለዋል በማለት ተችቷል። ይፋዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ዩናይትድ ኪንግደም በኮቫክስ በኩል 536 ሺህ 370 የፋይዘር ክትባቶችን የተረከበች ሲሆን ካናዳ ደግሞ ለአንድ ሚሊዮን የቀረቡ የአስትራ ዜኔካ ክትባቶችን ወስዳለች። ኮቫክስ የኮቪድ-19 ክትባት ለደሃ አገራት እንዲደርስ የተመሰረተ ዓለም አቀፍ ጥምረት ነው። የበለጸጉት አገራት ለኮቫክስ ኢኒሺዬቲቭ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል። በተለይ ደግሞ 92 ደሃ የሚባሉ አገራት ከሌሎች 98 አቅም ካላቸው አገራት እኩል ክትባቱን እንዲቀበሉ ይደረጋል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገራት የዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ናቸው። ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ ደግሞ በኮቫክስ በኩል የተገኙ 2.2 ሚሊዮን የኮቪድ-19 ክትባቶች ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን ክትባቱም አስትራዜኔካ ሠራሽ ነው። ኮቫክስ መጀመሪያ ላይ በመላው ዓለም 2 ቢሊየን የክትባት ብልቃጦችን ለማድረስ እቅድ ይዞ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ግን ማሳካት የቻለው 371 ሚሊየን ክትባቶችን ብቻ ነው። | የዓለም ጤና ድርጅት ኮቪድ-19 ለተጨማሪ አንድ ዓመት አብሮን ሊቆይ ይችላል አለ በመላው ዓለም የሚገኙ ድሃ አገራት የኮቪድ-19 ክትባትን በተገቢው ጊዜና መጠን እያገኙ ባለመሆናቸው ወረርሽኙ መቆየት ከሚገባው በላይ አንድ ተጨማሪ ዓመት አብሮን ይኖራል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በድርጅቱ ከፍተኛ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ብሩስ አሊዋርድ በዚሁ ችግር ምክንያት የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ እስከ አውሮፓውያኑ 2022 ድረስ ይቆያል ብለዋል። እስካሁን 5 በመቶ ብቻ የሚሆነው የአፍሪካ ሕዝብ ክትባቱን ማግኘት የቻለ ሲሆን በሌሎች አህጉራት ደግሞ እስከ 40 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ክትባቱን አግኝቷል። ዩናይትድ ኪንግደም እስካሁን 10 ሚሊዮን ክትባቶችን ለድሃ አገራት ያደረሰች ሲሆን አጠቃላይ እቅዷ 100 ሚሊዮን ክትባቶችን ማድረስ ነው። ሀብታሞቹ አገራት ክትባቱን ለማግኘት የሚያደርጉትን እሽቅድድም ገታ አድርገው ትልልቅ መድኃኒት አምራች ኩባንያዎች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገራት ላይ ትኩረታቸውን እንዲያደርጉ እንዲፈቅዱላቸው ዶክተር ብሩስ ጠይቀዋል። አክለውም "ሀብታም አገራት በያዝነው ዓመት የቡድን 7 ስብሰባ ላይ እርዳታ ለማድረግ የገቡትን ቃል መልሰው ሊቃኙት ይገባል" ብለዋል። "እውነታውን ልንገራችሁ፤ ከእቅዳችን በጣም ወደኋላ ቀርተናል። ቃል የተገባውን ገንዘብ በፍጥነት ልንጠቀምበት ይገባል። አለበለዚያ ግን ይህ ወረርሽኝ ለተጨማሪ ዓመት አብሮን እንዲቆይ ይሆናል።'' የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጥምረት የሆነው 'ፒፕልስ ቫክሲን' ባወጣው መረጃ መሰረት የበለጸጉት አገራትና ትልልቅ የመድኃኒት አምራች ድርጅቶች ለመስጠት ቃል ከገቡት የክትባት መጠን ቢያንስ ከእያንዳንዱ 7 ክትባት አንዱ ብቻ ነው ወደ ድሃ አገራት እየደረሰ የሚገኘው። በተቃራኒው ክትባቶቹ ከፍተኛ ገቢ ላላቸውና በበለጸጉት አገራት ለሚኖሩ ዜጎች ነው በስፋት እየተዳረሱ የሚገኙት። አፍሪካም ቢሆን እስካሁን ከመላው ዓለም ካለው ፍላጎት 2.6 በመቶ የሚሆነው ብቻ ነው የቀረበላት። በተጨማሪም እንደ ኦክስፋም እና ዩኤንኤይድ የመሳሰሉ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን የያዘው ጥምረት ዩናይትድ ኪንግደም እና ካናዳ በኮቫክስ በኩል የሚመጡ ክትባቶን ለዜጎቻቸው አከፋፍለዋል በማለት ተችቷል። ይፋዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ዩናይትድ ኪንግደም በኮቫክስ በኩል 536 ሺህ 370 የፋይዘር ክትባቶችን የተረከበች ሲሆን ካናዳ ደግሞ ለአንድ ሚሊዮን የቀረቡ የአስትራ ዜኔካ ክትባቶችን ወስዳለች። ኮቫክስ የኮቪድ-19 ክትባት ለደሃ አገራት እንዲደርስ የተመሰረተ ዓለም አቀፍ ጥምረት ነው። የበለጸጉት አገራት ለኮቫክስ ኢኒሺዬቲቭ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል። በተለይ ደግሞ 92 ደሃ የሚባሉ አገራት ከሌሎች 98 አቅም ካላቸው አገራት እኩል ክትባቱን እንዲቀበሉ ይደረጋል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገራት የዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ናቸው። ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ ደግሞ በኮቫክስ በኩል የተገኙ 2.2 ሚሊዮን የኮቪድ-19 ክትባቶች ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን ክትባቱም አስትራዜኔካ ሠራሽ ነው። ኮቫክስ መጀመሪያ ላይ በመላው ዓለም 2 ቢሊየን የክትባት ብልቃጦችን ለማድረስ እቅድ ይዞ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ግን ማሳካት የቻለው 371 ሚሊየን ክትባቶችን ብቻ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-58991727 |
3politics
| አዲስ የሚመሰረተው መንግሥት ቁልፍ አጀንዳዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ? | የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ መስከረም 24/2014 ዓ.ም አዲሱ የፌደራል መንግሥት እንደሚመሰረት ገልጸዋል። ክልሎችም በበኩላቸው አዳዲስ መስተዳደሮቻቸውን ለማዋቀር እየተዘጋጁ ሲሆን የኦሮሚያ ምክር ቤት ቅዳሜ መስከረም 15/2014 ዓ.ም ባካሄደው ጉባኤ አዲሱን የክልሉን መንግሥት መስርቷል። በተመሳሳይ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መስከረም 19፣ የጋምቤላ፣ የአማራ እና የሲዳማ ክልሎች ደግሞ መስከረም 20 እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 21/2014 ዓ.ም መስተዳደሮቻቸውን ያዋቅራሉ። ለመሆኑ መስከረም 24/2014 ዓ.ም የሚመሰረተው የፌደራል መንግሥት ቁልፍ አጀንዳዎቹ ምን ሊሆኑ ይችላሉ? 'ያልተሰበረው የጦርነት አዙሪት' በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁር የሆኑት ውሂበእግዜር ፈረደ (ዶ/ር) አዲሱ መንግሥት የሚያስቀምጣቸውን አጀንዳዎች የመፈፀም አቅም የሚያገኘው ከሚመሰርተው መንግሥት ባህርይ ነው ይላሉ። የሚመሰረተው መንግሥት የሚኖረው ባህርይ እና አካታችነቱ ሊሰሩ ይችላሉ ተብለው የሚቀመጡ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ የራሱ አስተዋጽኦ ሊኖረው ይችላል ሲሉ ያስረዳሉ። የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው የሚመሰረተው መንግሥት ከዚህ በፊት ከነበረው "ትልቅ ሊባል የሚችል የምጣኔ ሀብት ተግዳሮት ነው ሊገጥመው ይችላል" ሲሉ ሙያዊ ግምገማቸውን ይሰጣሉ። አዲሱ መንግሥት ሲመሰረት ከዚህ በፊት በይደር የተቀመጡ፣ በተለያየ ምክንያት ሳይፈፀሙ ቀርተው ወደ ዛሬ የተንከባለሉ ጉዳዮችን እንደሚረከብ የሚጠቅሱት ውሂበእግዜር (ዶ/ር)፤ ከእነዚህ መካከል ደግሞ የኢትዮጵያውያን የዘመናት ጥያቄ የሆነው የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ጉዳይ አንዱ መሆኑን ያነሳሉ። አዲሱ መንግሥት ለዚህ የዘመናት ሕዝብ ጥያቄ ቢያንስ ቁልፍ የሆነ መሠረታዊ ጅማሮ ያሳያል ብለው እንደሚጠብቁ በማንሳትም፣ ለዚህ ደግሞ አካታች የሆነ መንግሥት መመስረት ቀዳሚውና ወሳኙ እርምጃ ነው ይላሉ። አክለውም አሁን ላይ ያጋጠሙ የሰላም መደፍረሶችን ለመፍታትና ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት መሥራት እንዳለበት፣ ይህም የአዲሱ መንግሥት ቁልፍ አጀንዳ ሊሆን እንደሚገባ ይናገራሉ። ዘላቂ መፍትሔ ተብሎ የሚቀመጠው ጉዳይ ምንድን ነው? የሚለውን ለመወሰን በወታደራዊ መንገድ ነው ወይስ በብሔራዊ መግባባት ማዕቀፍ ሊታይ ይችላል የሚለውን የሚወስነው የሚመሰረተው አዲሱ መንግሥት ይሆናል። መንግሥት የሕዝብን ጥያቄ በጠመንጃ አፈሙዝ ከመፍታት ይልቅ በተሻለ መንገድ ማስተናገድ የሚችልበት ጠንካራ ማዕቀፍ ይዞ ይመጣል የሚል ተስፋ ያላቸው ውሂበእግዜር (ደ/ር)፤ እነዚህን ጉዳዮች ለመፍታት የፖለቲካ ሪፎርሙ ሂደት እንዲሁም የብሔራዊ መግባባት ውይይቱ እነማንን ያካትታል የሚለው ወሳኝ መሆኑን ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በአገሪቱ ያሉ የፖለቲካ ተቃርኖዎች በሃሳብ የበላይነት፣ በውይይት ይፈታሉ የሚል ተስፋ ተፈጥሮ የነበረ ቢሆንም ኢትዮጵያ ዳግም የጦርነት አዙሪት ውስጥ መግባቷን ያነሳሉ። የጦርነት አዙሪትን ለመሰብርና ኢትየጵያውያንን ወደ አንድ የፖለቲካ ስበት ማዕከል ለማምጣት በአገሪቱ የሚካሄደው የለውጥ እርምጃ አካታች ሊሆን ይገባል ሲሉ ሃሳባቸዋውን ይሰነዝራሉ። የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው በዚህ ጦርት በርካታ ቁጥር ያላቸው ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት፣ እንዲሆን የግብርና ምርት ሰንሰለቶች፣ ብዙ የኢንደስትሪ ተቋማት ብዙ ባለሀብቶች እና ትልልቅ የንግድ ተቋማት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መጎዳታቸውን ያነሳሉ። በሠሜን ኢትዮጵያ ያለው ጦርነት፣ በምዕራብ እና ደቡብ ያለው አለመረጋጋት ብዙ የምጣኔ ሀብት አውታሮች እና መሰረተ ልማቶች ላይ ውድመትን አድርሷል። በዚህ በደከመ፣ በተጠቃና በተጎዳ የምጣኔ ሀብት መሠረተ ልማት አዲስ የሚመሠረተው መንግሥት ምን ያህል የሕዝቡን ፍላጎት ሊያዳርስ ይችላል የሚለው ሲታሰብ ትልቅ ፈተና ሆኖ እንደሚታይ ያስረዳሉ። የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ውሂበእግዜር ፈረደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የተጀመረውን ሪፎርም ተቋማዊ ማድረግ እንደሚገባ አስረግጠው፤ ይህም ከንግግር በዘለለ "ኢትዮጵያ ከየት ተነስታ የት እንደምትደርስ በግልጽ የሪፎርም አጀንዳው መቀመጥ አለበት" በማለት ይመክራሉ። ከዚህ ጋር አብሮ ተያይዞ ሪፎርሙን ተቋማዊ በማድረግ ሂደት ውስጥ አብሮ ሊታይ የሚገባው፣ "ሕገመንግሥቱን ማሻሻል አልያም አዲስ ሕገመንግሥት ማርቀቅ፤ የፌዴሬሽኑን ቅርጽ እና የወደፊት እጣ ፈንታ፣ የአገሪቱን የአስተዳደራዊ መዋቅር ቅርጽ እንዴት መሆን አለበት" የሚለው ሊሆን እንደሚችል ይጠቅሳሉ። ከእነዚህ ጉዳዮች በላይ ግን የብሔራዊ ውይይት (ናሽናል ዲያሎግ) እንደሚቀድም ያነሳሉ። በርካታ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ ይህንን ጉዳይ አጀንዳ አድርገው ሲወተውቱ እንደነበር ያስታወሱት ውሂበእግዜር (ዶ/ር)፣ መንግሥት በአዲሱ ዓመት ከሚመሰረተው መንግሥት ብሔራዊ መግባባትን ያመጣሉ ብሎ ያሰባቸውን ውይይቶች እንደሚጀምር ሲያነሳ መደመጡን ሳይጠቅሱ አላለፉም። ቀጠናዊ ለውጦች እና አዲሱ መንግሥት የአዲሱ መንግሥት ቁልፍ አጀንዳዎች ሲነሱ የሚታዩ ቀጠናዊ ለውጦች መኖራቸውን ያነሳሉ። ከሱዳን ጋር ያለን ግንኙነት ወደ አዲስ ትብብር የማሳደግ እና በሱዳን ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ እንድ በጎ እድል የመጠቀም እንቅስቃሴ ይኖራል ሲሉ ተስፋቸውን ውሂበእግዜር (ዶ/ር) በይናገራሉ። ሱዳን ኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ስትራቴጂካዊ ማድረግ ይቻላል የሚሉት ዶክተሩ ፣ ነገር ግን ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከሱዳን ጋር የነበራትን የሁለትዮሽ አጋርነት ዳግም የማስቀጠል ሥራ መሰራት እንደሚኖርበት አንስተዋል። በሱዳን ውስጥ የሚካሄደውን የለውጥ እንቅስቃሴዎች በበጎ መልኩ በመጠቀም ወደ ቀድሞው መልካም ግንኙትን መመለስ እንደሚያስፈልግም ይመክራሉ። ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በሱዳን ጥቅም ላይ ይህ ነው የሚባል ጉዳት እንደማያደርስ ምሁራኖቻቸውም ሆኑ ፖለቲከኞቻቸውም ያውቁታል ያሉት ውሂበእግዜር (ዶ/ር)፣ የድንበር ውዝግቡም ቢሆን ለመፍታት "በጣም ቀላል ይመስለኛል" ሲሉ ተስፋቸውን ይናገራሉ። ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ሲያስረዱም "ድንበሩን በጋራ የማልማት ስትራቴጂ መከተል አንዱ መንገድ" መሆኑን ያነሳሉ። ዋናው ከሱዳን ጋር የነበረው የድንበር ውዝግብ ችግር ውስጥ እንዲወድቅ ያደረገው በኢትዮጵያ በኩል የነበረው ዲፕሎማሲያዊ ድክመት መሆኑን ምሁሩ አንስተዋል። በኤርትራ በኩል የተጀመረው አዲስ የወንድማማችነት ሕብረት በውስጡ ይዞት የሚመጣው እድል በዘላቂነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ያድጋል የሚል ተስፋ እንዳላቸውም አክለው ተናግረዋል። "በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሚያሳድጉ ሥራዎች ይሰራሉ ብዬ እጠብቃለሁ።" ኬንያ፣ አዲሲቱ የምሥራቅ አፍሪካ ኃይል አንቀሳቃሽ ሆና ለመውጣት እየተንቀሳቀሰች መሆኑን በማንሳትም ስትራቴጂካዊ ትብብርን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል። በቀጣይ ዓመታት "ኢትዮጵያ ከቀጠናው አገራት ጋር የሚኖራትን ግንኙነት ከታክቲካል ወደ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት የማሳደግ ሂደት ውስጥ የምትገባ ይመስለኛል።" ከአገሮች ጋር ከምታደርገው ግንኙነት በተጨማሪ አዳዲስ ተቋማትን የመመስረት፣ የመገንባት፣ ኢጋድን ከማጠናከር በተጨማሪ፤ የቀይ ባሕር ጉዳይን የሚመለከት አዲስ ተቋም የመገንባት፣ በአባይ ሸለቆ ላይ ደግሞ ከዚህ በፊት ከነበረው የ'ናይል ቤዚን ኢንሼቲቭ' በመውጣት የላይኛው ተፋሰስ አገራት ጥምረትን በተመለከተ አዲስ ተቋም የምታዋቅርበት ሊኖር እንደሚችል ያስረዳሉ። ዓለም አቀፉ ግንኙነት እና አዲሱ መንግሥት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) አሜሪካ እና አውሮፓ ከዚህ በፊት በቃል ሲዝቱበት የነበረውን የምጣኔ ሀብት ማዕቀብ አሁን በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ፈርማ ወደ ተግባር እየገቡበት መሆኑን ያነሳሉ። "በተለይ ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ጋር ተጋጨን ማለት ኢትዮጵያን ከሰማይ ወደ ምድር እንደመወርወር ነው" የሚሉት ምሁሩ፣ አዲስ የሚመሰረተው መንግሥት እስከ ዛሬ ከነበሩት መንግሥታት በተለየ ትልቅ ተግዳሮቶችና ፈተናዎች ስለሚገጥሙት "ወገቡን አስሮ መጠነ ሰፊ ርብርብ ማድረግ" እንደሚጠበቅበት ይመክራሉ። ኢትዮጵያ የበጀት ድጋፍ በቀዳሚነት ከአሜሪካ፣ በመቀጠል ከእንግሊዝ፣ በሦስተኝነት ደግሞ ከተለያዩ የአውሮፓ አገራት እንደምታገኝ ዶ/ር ጉቱ ያነሳሉ። "እነዚህ ሁሉ ጀርባቸውን የሚሰጡን ከሆነ፣ አሁን የጀመሩትን ማዕቀብ የሚያስቀጥከትሉ ከሆነ፣ ኢትዮጵያ ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ውስጥ ሁሉ ልትገባ ትችላለች" ሲሉ ስጋታቸውን ይገልጻሉ። የፖለቲካ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩም በበኩላቸው የኃያላን አገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚፈጥሩት ተጽዕኖ፣ በተለይ በአሜሪካና ኢትዮጵያ ግንኙት ላይ ዲፕሎማሲውን ማጠናከር እንደሚያስፍልግ ያስረዳሉ። የአውሮፓ እና የአሜሪካ መንግሥታት በትግራይ ጦርነት ምክንያት እያሳደሩ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጫና ለመቋቋም የአዲሱ መንግሥት የትኩረት አቅጣጫ ይሆናልም ይላሉ። አዲስ የውጭ ግንኙነት መርህ እና እንቅስቃሴ ከእነማን ጋር ቢሆን የተሻለ ዘላቂ እና ስትራቴጂክ የሆነ ጥቅም ይኖረናል የሚለው ሌላኛው የትኩረት አቅጣጫ ሊሆን እንደሚችል ያስረዳሉ። "ይህንን በሚመለከት ከቀዝቃዛው ጦርነት ኢትዮጵያ ትምህርት የምትወስድ ይመስለኛል" የሚሉት ውሂበእግዜር (ዶ/ር)፣ በአሜሪካ በኩል ያለውንም ግንኙነት "ተበላሽቷል፤ የማይታከም ነው፤ የሚል ድምዳሜ ላይ ይደርሳል ብዬ አላስብም" ብለዋል። "የተጠና ዲፕሎማሲ በመጠቀም ከምዕራብም ከምሥራቅም ኃይል የማሰባሰብ ትኩረት የሚሰጠው ይመስለኛል" በማለት አሁን ያለው የዓለም አሰላለፍን በጥልቀት የመገንዘብና የመተንተን ሥራ እንደሚሰራም ያላቸውን ግምት ተናግረዋል። "ከምዕራባውያን ጋር ስንጋጭ ከውጭ ባለሃብቶች ጋር ነው የምንጋጨው። እዚህ ያለው ጠቅልሎ ይሄዳል። ሌላውም አይመጣም" ያሉት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) ቀዳሚው ነገር ከአሜሪካ ጋር መስማማት፣ መደራደር ነው ሊሆን እነደሚገባ ያሰምሩበታል። "የሚቻል ከሆነ በዲፕሎማሲ ጥበብ ለማሸነፍ መሞከር ነው።" ". . .አገር ውስጥም ይሁን በውጭ አገራት የሚገኙ ዲፕሎማቶች ከየትኛውም ጊዜ ይልጥ ሽንጣቸውን ገትረው ትልቅ የዲፕሎማሲ ጥበብ በተሞላበት ሁኔታ መስራት የሚጠበቅባቸው ጊዜ ነው" ሲሉም ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። እንደ ጉቱ (ዶ/ር) አዲሱ መንግሥት ቢያንስ ቢያንስ ማዕቀቦቹ ተግባራዊ እንዳይሆኑ ለኢትዮጵያ የእፎይታ ጊዜ በሚሰጥ ሁኔታ ላይ ሊሰራ ይገባል። ጦርነት እና አለመረጋጋት እያለ የትኛውም የምጣኔ ሀብት እርምጃ መፍትሄ አያመጣም የሚሉት ጉቱ፣ "መጠነ ሰፊ የሆነ የኢኮኖሚ መረጋጋት ለማምጣት በአገሪቱ ውስጥ ያለው ጦርነት እና አለመረጋጋት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መቆም አለበት" ይላሉ። በማጠቃላያቸውም ላይ "የሆኖ ሆኖ አሁን ከገባንበት ቀውስ ወጥተን ዘላቂ እና ፈጣን እድገት ወደ ምናስመዘግብበት ጎዳና ላይ ለመሰለፍ ከአምስት እስከ አስር ዓመት ይወስድብናል" ሲሉ ተናግረዋል። | አዲስ የሚመሰረተው መንግሥት ቁልፍ አጀንዳዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ? የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ መስከረም 24/2014 ዓ.ም አዲሱ የፌደራል መንግሥት እንደሚመሰረት ገልጸዋል። ክልሎችም በበኩላቸው አዳዲስ መስተዳደሮቻቸውን ለማዋቀር እየተዘጋጁ ሲሆን የኦሮሚያ ምክር ቤት ቅዳሜ መስከረም 15/2014 ዓ.ም ባካሄደው ጉባኤ አዲሱን የክልሉን መንግሥት መስርቷል። በተመሳሳይ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መስከረም 19፣ የጋምቤላ፣ የአማራ እና የሲዳማ ክልሎች ደግሞ መስከረም 20 እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 21/2014 ዓ.ም መስተዳደሮቻቸውን ያዋቅራሉ። ለመሆኑ መስከረም 24/2014 ዓ.ም የሚመሰረተው የፌደራል መንግሥት ቁልፍ አጀንዳዎቹ ምን ሊሆኑ ይችላሉ? 'ያልተሰበረው የጦርነት አዙሪት' በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁር የሆኑት ውሂበእግዜር ፈረደ (ዶ/ር) አዲሱ መንግሥት የሚያስቀምጣቸውን አጀንዳዎች የመፈፀም አቅም የሚያገኘው ከሚመሰርተው መንግሥት ባህርይ ነው ይላሉ። የሚመሰረተው መንግሥት የሚኖረው ባህርይ እና አካታችነቱ ሊሰሩ ይችላሉ ተብለው የሚቀመጡ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ የራሱ አስተዋጽኦ ሊኖረው ይችላል ሲሉ ያስረዳሉ። የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው የሚመሰረተው መንግሥት ከዚህ በፊት ከነበረው "ትልቅ ሊባል የሚችል የምጣኔ ሀብት ተግዳሮት ነው ሊገጥመው ይችላል" ሲሉ ሙያዊ ግምገማቸውን ይሰጣሉ። አዲሱ መንግሥት ሲመሰረት ከዚህ በፊት በይደር የተቀመጡ፣ በተለያየ ምክንያት ሳይፈፀሙ ቀርተው ወደ ዛሬ የተንከባለሉ ጉዳዮችን እንደሚረከብ የሚጠቅሱት ውሂበእግዜር (ዶ/ር)፤ ከእነዚህ መካከል ደግሞ የኢትዮጵያውያን የዘመናት ጥያቄ የሆነው የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ጉዳይ አንዱ መሆኑን ያነሳሉ። አዲሱ መንግሥት ለዚህ የዘመናት ሕዝብ ጥያቄ ቢያንስ ቁልፍ የሆነ መሠረታዊ ጅማሮ ያሳያል ብለው እንደሚጠብቁ በማንሳትም፣ ለዚህ ደግሞ አካታች የሆነ መንግሥት መመስረት ቀዳሚውና ወሳኙ እርምጃ ነው ይላሉ። አክለውም አሁን ላይ ያጋጠሙ የሰላም መደፍረሶችን ለመፍታትና ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት መሥራት እንዳለበት፣ ይህም የአዲሱ መንግሥት ቁልፍ አጀንዳ ሊሆን እንደሚገባ ይናገራሉ። ዘላቂ መፍትሔ ተብሎ የሚቀመጠው ጉዳይ ምንድን ነው? የሚለውን ለመወሰን በወታደራዊ መንገድ ነው ወይስ በብሔራዊ መግባባት ማዕቀፍ ሊታይ ይችላል የሚለውን የሚወስነው የሚመሰረተው አዲሱ መንግሥት ይሆናል። መንግሥት የሕዝብን ጥያቄ በጠመንጃ አፈሙዝ ከመፍታት ይልቅ በተሻለ መንገድ ማስተናገድ የሚችልበት ጠንካራ ማዕቀፍ ይዞ ይመጣል የሚል ተስፋ ያላቸው ውሂበእግዜር (ደ/ር)፤ እነዚህን ጉዳዮች ለመፍታት የፖለቲካ ሪፎርሙ ሂደት እንዲሁም የብሔራዊ መግባባት ውይይቱ እነማንን ያካትታል የሚለው ወሳኝ መሆኑን ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በአገሪቱ ያሉ የፖለቲካ ተቃርኖዎች በሃሳብ የበላይነት፣ በውይይት ይፈታሉ የሚል ተስፋ ተፈጥሮ የነበረ ቢሆንም ኢትዮጵያ ዳግም የጦርነት አዙሪት ውስጥ መግባቷን ያነሳሉ። የጦርነት አዙሪትን ለመሰብርና ኢትየጵያውያንን ወደ አንድ የፖለቲካ ስበት ማዕከል ለማምጣት በአገሪቱ የሚካሄደው የለውጥ እርምጃ አካታች ሊሆን ይገባል ሲሉ ሃሳባቸዋውን ይሰነዝራሉ። የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው በዚህ ጦርት በርካታ ቁጥር ያላቸው ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት፣ እንዲሆን የግብርና ምርት ሰንሰለቶች፣ ብዙ የኢንደስትሪ ተቋማት ብዙ ባለሀብቶች እና ትልልቅ የንግድ ተቋማት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መጎዳታቸውን ያነሳሉ። በሠሜን ኢትዮጵያ ያለው ጦርነት፣ በምዕራብ እና ደቡብ ያለው አለመረጋጋት ብዙ የምጣኔ ሀብት አውታሮች እና መሰረተ ልማቶች ላይ ውድመትን አድርሷል። በዚህ በደከመ፣ በተጠቃና በተጎዳ የምጣኔ ሀብት መሠረተ ልማት አዲስ የሚመሠረተው መንግሥት ምን ያህል የሕዝቡን ፍላጎት ሊያዳርስ ይችላል የሚለው ሲታሰብ ትልቅ ፈተና ሆኖ እንደሚታይ ያስረዳሉ። የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ውሂበእግዜር ፈረደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የተጀመረውን ሪፎርም ተቋማዊ ማድረግ እንደሚገባ አስረግጠው፤ ይህም ከንግግር በዘለለ "ኢትዮጵያ ከየት ተነስታ የት እንደምትደርስ በግልጽ የሪፎርም አጀንዳው መቀመጥ አለበት" በማለት ይመክራሉ። ከዚህ ጋር አብሮ ተያይዞ ሪፎርሙን ተቋማዊ በማድረግ ሂደት ውስጥ አብሮ ሊታይ የሚገባው፣ "ሕገመንግሥቱን ማሻሻል አልያም አዲስ ሕገመንግሥት ማርቀቅ፤ የፌዴሬሽኑን ቅርጽ እና የወደፊት እጣ ፈንታ፣ የአገሪቱን የአስተዳደራዊ መዋቅር ቅርጽ እንዴት መሆን አለበት" የሚለው ሊሆን እንደሚችል ይጠቅሳሉ። ከእነዚህ ጉዳዮች በላይ ግን የብሔራዊ ውይይት (ናሽናል ዲያሎግ) እንደሚቀድም ያነሳሉ። በርካታ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ ይህንን ጉዳይ አጀንዳ አድርገው ሲወተውቱ እንደነበር ያስታወሱት ውሂበእግዜር (ዶ/ር)፣ መንግሥት በአዲሱ ዓመት ከሚመሰረተው መንግሥት ብሔራዊ መግባባትን ያመጣሉ ብሎ ያሰባቸውን ውይይቶች እንደሚጀምር ሲያነሳ መደመጡን ሳይጠቅሱ አላለፉም። ቀጠናዊ ለውጦች እና አዲሱ መንግሥት የአዲሱ መንግሥት ቁልፍ አጀንዳዎች ሲነሱ የሚታዩ ቀጠናዊ ለውጦች መኖራቸውን ያነሳሉ። ከሱዳን ጋር ያለን ግንኙነት ወደ አዲስ ትብብር የማሳደግ እና በሱዳን ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ እንድ በጎ እድል የመጠቀም እንቅስቃሴ ይኖራል ሲሉ ተስፋቸውን ውሂበእግዜር (ዶ/ር) በይናገራሉ። ሱዳን ኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ስትራቴጂካዊ ማድረግ ይቻላል የሚሉት ዶክተሩ ፣ ነገር ግን ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከሱዳን ጋር የነበራትን የሁለትዮሽ አጋርነት ዳግም የማስቀጠል ሥራ መሰራት እንደሚኖርበት አንስተዋል። በሱዳን ውስጥ የሚካሄደውን የለውጥ እንቅስቃሴዎች በበጎ መልኩ በመጠቀም ወደ ቀድሞው መልካም ግንኙትን መመለስ እንደሚያስፈልግም ይመክራሉ። ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በሱዳን ጥቅም ላይ ይህ ነው የሚባል ጉዳት እንደማያደርስ ምሁራኖቻቸውም ሆኑ ፖለቲከኞቻቸውም ያውቁታል ያሉት ውሂበእግዜር (ዶ/ር)፣ የድንበር ውዝግቡም ቢሆን ለመፍታት "በጣም ቀላል ይመስለኛል" ሲሉ ተስፋቸውን ይናገራሉ። ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ሲያስረዱም "ድንበሩን በጋራ የማልማት ስትራቴጂ መከተል አንዱ መንገድ" መሆኑን ያነሳሉ። ዋናው ከሱዳን ጋር የነበረው የድንበር ውዝግብ ችግር ውስጥ እንዲወድቅ ያደረገው በኢትዮጵያ በኩል የነበረው ዲፕሎማሲያዊ ድክመት መሆኑን ምሁሩ አንስተዋል። በኤርትራ በኩል የተጀመረው አዲስ የወንድማማችነት ሕብረት በውስጡ ይዞት የሚመጣው እድል በዘላቂነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ያድጋል የሚል ተስፋ እንዳላቸውም አክለው ተናግረዋል። "በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሚያሳድጉ ሥራዎች ይሰራሉ ብዬ እጠብቃለሁ።" ኬንያ፣ አዲሲቱ የምሥራቅ አፍሪካ ኃይል አንቀሳቃሽ ሆና ለመውጣት እየተንቀሳቀሰች መሆኑን በማንሳትም ስትራቴጂካዊ ትብብርን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል። በቀጣይ ዓመታት "ኢትዮጵያ ከቀጠናው አገራት ጋር የሚኖራትን ግንኙነት ከታክቲካል ወደ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት የማሳደግ ሂደት ውስጥ የምትገባ ይመስለኛል።" ከአገሮች ጋር ከምታደርገው ግንኙነት በተጨማሪ አዳዲስ ተቋማትን የመመስረት፣ የመገንባት፣ ኢጋድን ከማጠናከር በተጨማሪ፤ የቀይ ባሕር ጉዳይን የሚመለከት አዲስ ተቋም የመገንባት፣ በአባይ ሸለቆ ላይ ደግሞ ከዚህ በፊት ከነበረው የ'ናይል ቤዚን ኢንሼቲቭ' በመውጣት የላይኛው ተፋሰስ አገራት ጥምረትን በተመለከተ አዲስ ተቋም የምታዋቅርበት ሊኖር እንደሚችል ያስረዳሉ። ዓለም አቀፉ ግንኙነት እና አዲሱ መንግሥት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) አሜሪካ እና አውሮፓ ከዚህ በፊት በቃል ሲዝቱበት የነበረውን የምጣኔ ሀብት ማዕቀብ አሁን በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ፈርማ ወደ ተግባር እየገቡበት መሆኑን ያነሳሉ። "በተለይ ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ጋር ተጋጨን ማለት ኢትዮጵያን ከሰማይ ወደ ምድር እንደመወርወር ነው" የሚሉት ምሁሩ፣ አዲስ የሚመሰረተው መንግሥት እስከ ዛሬ ከነበሩት መንግሥታት በተለየ ትልቅ ተግዳሮቶችና ፈተናዎች ስለሚገጥሙት "ወገቡን አስሮ መጠነ ሰፊ ርብርብ ማድረግ" እንደሚጠበቅበት ይመክራሉ። ኢትዮጵያ የበጀት ድጋፍ በቀዳሚነት ከአሜሪካ፣ በመቀጠል ከእንግሊዝ፣ በሦስተኝነት ደግሞ ከተለያዩ የአውሮፓ አገራት እንደምታገኝ ዶ/ር ጉቱ ያነሳሉ። "እነዚህ ሁሉ ጀርባቸውን የሚሰጡን ከሆነ፣ አሁን የጀመሩትን ማዕቀብ የሚያስቀጥከትሉ ከሆነ፣ ኢትዮጵያ ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ውስጥ ሁሉ ልትገባ ትችላለች" ሲሉ ስጋታቸውን ይገልጻሉ። የፖለቲካ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩም በበኩላቸው የኃያላን አገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚፈጥሩት ተጽዕኖ፣ በተለይ በአሜሪካና ኢትዮጵያ ግንኙት ላይ ዲፕሎማሲውን ማጠናከር እንደሚያስፍልግ ያስረዳሉ። የአውሮፓ እና የአሜሪካ መንግሥታት በትግራይ ጦርነት ምክንያት እያሳደሩ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጫና ለመቋቋም የአዲሱ መንግሥት የትኩረት አቅጣጫ ይሆናልም ይላሉ። አዲስ የውጭ ግንኙነት መርህ እና እንቅስቃሴ ከእነማን ጋር ቢሆን የተሻለ ዘላቂ እና ስትራቴጂክ የሆነ ጥቅም ይኖረናል የሚለው ሌላኛው የትኩረት አቅጣጫ ሊሆን እንደሚችል ያስረዳሉ። "ይህንን በሚመለከት ከቀዝቃዛው ጦርነት ኢትዮጵያ ትምህርት የምትወስድ ይመስለኛል" የሚሉት ውሂበእግዜር (ዶ/ር)፣ በአሜሪካ በኩል ያለውንም ግንኙነት "ተበላሽቷል፤ የማይታከም ነው፤ የሚል ድምዳሜ ላይ ይደርሳል ብዬ አላስብም" ብለዋል። "የተጠና ዲፕሎማሲ በመጠቀም ከምዕራብም ከምሥራቅም ኃይል የማሰባሰብ ትኩረት የሚሰጠው ይመስለኛል" በማለት አሁን ያለው የዓለም አሰላለፍን በጥልቀት የመገንዘብና የመተንተን ሥራ እንደሚሰራም ያላቸውን ግምት ተናግረዋል። "ከምዕራባውያን ጋር ስንጋጭ ከውጭ ባለሃብቶች ጋር ነው የምንጋጨው። እዚህ ያለው ጠቅልሎ ይሄዳል። ሌላውም አይመጣም" ያሉት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) ቀዳሚው ነገር ከአሜሪካ ጋር መስማማት፣ መደራደር ነው ሊሆን እነደሚገባ ያሰምሩበታል። "የሚቻል ከሆነ በዲፕሎማሲ ጥበብ ለማሸነፍ መሞከር ነው።" ". . .አገር ውስጥም ይሁን በውጭ አገራት የሚገኙ ዲፕሎማቶች ከየትኛውም ጊዜ ይልጥ ሽንጣቸውን ገትረው ትልቅ የዲፕሎማሲ ጥበብ በተሞላበት ሁኔታ መስራት የሚጠበቅባቸው ጊዜ ነው" ሲሉም ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። እንደ ጉቱ (ዶ/ር) አዲሱ መንግሥት ቢያንስ ቢያንስ ማዕቀቦቹ ተግባራዊ እንዳይሆኑ ለኢትዮጵያ የእፎይታ ጊዜ በሚሰጥ ሁኔታ ላይ ሊሰራ ይገባል። ጦርነት እና አለመረጋጋት እያለ የትኛውም የምጣኔ ሀብት እርምጃ መፍትሄ አያመጣም የሚሉት ጉቱ፣ "መጠነ ሰፊ የሆነ የኢኮኖሚ መረጋጋት ለማምጣት በአገሪቱ ውስጥ ያለው ጦርነት እና አለመረጋጋት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መቆም አለበት" ይላሉ። በማጠቃላያቸውም ላይ "የሆኖ ሆኖ አሁን ከገባንበት ቀውስ ወጥተን ዘላቂ እና ፈጣን እድገት ወደ ምናስመዘግብበት ጎዳና ላይ ለመሰለፍ ከአምስት እስከ አስር ዓመት ይወስድብናል" ሲሉ ተናግረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58703272 |
0business
| የኤርትራ ምጣኔ ሃብት ባለፉት 30 ዓመታት | ኤርትራ በ1992 ዓ.ም 52ኛ አፍሪካዊት አገር ስትሆን ዜጎቿና የነጻነት ጉዞዋን ሲከታተሉ የነበሩ ተንታኞች 'ኤርትራ በአጭር ጊዜ ኢኮኖሚያዊ እድገት በማስመዝገብ የአካባቢዋ ሞዴል ትሆናለች' የሚል ተስፋ ነበራቸው። ከነጻነት በኋላ የነበሩ የጊዝያዊ አስተዳደሩ ስራ አስፈጻሚዎችም "ኤርትራን ሲንጋፑር እናደርጋታለን" ሲሉ ተናግረው ነበር። አገሪቷ በ1994 ያጸደቀችው የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ በግብርና ኢንዳስትሪ፣ አሳና ጨው፣ የመሰረተ ልማቶች ግንባታ፣ ኤሌክትሪክና ውሃ ማስፋፋት፣ ትምህርት፣ ጤናና ሌሎች የማስፈጸም ተልእኮ ተሰጥቶት ስራ ተጀመረ። ሰነዱ መግቢያ ላይ "ኤርትራ ከጦርነትና ግጭት፣ ከጭቆና አገዛዝ nጻ ወጥታ ወደ አዲስ ብልጽግናና ሰላም እየገባች ነው። ይህ በመስዋእትነት የተገኘው ሰላምና መረጋጋት ፈጣን ዴሞክራሲያዊ ለውጥ እያሳየ ነው። በጦርነት የወደመው ምጣኔ ሃብትን ለመገንባትም ጥረት እየተደረገ ይገኛል" ይላል። የአፍሪካ ፖለቲካል ሳይንስ ተመራማሪ ፕሮፌሰር መንግስትአብ ኪዳነ የኤርትራ መንግሥት በግል ባለሃብቶች የሚመራ የኢንቨስትመንትና ወደ ውጪ የሚላክ ምርት ትኩረት ያደረገ ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲ እንደነደፈ ያስታውሳሉ። "መንግሥት የህግደፍ ኢኮኖሚ፣ የመንግሥት ኢኮኖሚ፣ የግል ኢንቨስትመንት ኢኮኖሚ በሚል ሦስት መንገድ የተገበረውን ፖሊሲ ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለበት መንገድ እጁ ማስገባት ስለጀመረ ብዙ ርቀት ሳይጓዝ ነው የተደናቀፈው" ይላል። በተዘበራረቀ አሰራር ምክንያት ህዝብ የመንግሥት የሆነው ንብረት ከፓርቲ ሃብት ለይቶ ማየት እንዳልቻለ የሚናገረው ፕሮፌሰር መንግስትአብ፤ "ለምሳሌ ህዝብ ማዕድን በመንግሥት ነው ወይስ በፓርቲ የሚተዳደረው የሚያውቀው ነገር አልነበረም" በማለት የአገሪቷ የምጣኔ ሃብት ስርአት የተዘበራረቀ መሆኑ ይናገራል። በሳውዝ ባንክ ዩኒቨርሲቲ ለንደን ፕሮፌሰር የሆነው ጋይም ክብረአብ በበኩሉ፤ ህዝቡ፣ በመንግስት በኩል የነበረበትን አስተዳደራዊ ችግር "ልምድ እስኪያገኙ ድረስ ነው" እያለ ጊዜ ቢሰጠውም በጊዜ ማስተካከል ባለመቻሉ የአገሪቷ ምጣኔ ሃብትና ፖለቲካ ወደ ኋላ ቀርቷል ይላል። በዚህ ምክንያት ብዙ በኢንቨስትመንት ለመሳተፍ ፍላጎት የነበራቸው ዜጎች እውቀታቸውና ገንዘባቸው ይዘው ከስደት ወደ አገራቸው ቢመለሱም፤ የግል ኢኮኖሚው ህጋዊ ግብር የማይከፍለው የፓርቲ ኢኮኖሚ ጋር መወዳደር ባለመቻሉ ቀስ በቀስ እንደከሰረ ያስረዳል። ይህ አሰራር ማን ምን እንደሚያስተዳድር ስለማይታወቅ ለሙስና የተጋለጠ እንደሆነ የሚያነሳው ፕሮፌሰር መንግስትአብ፣ በፓርቲ የሚመራው የኢኮኖሚ ተቋም በኢንዳስትሪ፣ ግንባታ፣ ትራንስፖርት፣ መሰረታዊ ሸቀጦች ሳይቀር ስለሚሳተፍ የኢኮኖሚው መተላለፊያ በመቆጣጠር ነጋዴዎች እድል ስለነፈጋቸው ኢኮኖሚው በአግባቡ መራመድ አልቻለም ይላል። "መንግሥትና ፓርቲ የውጭ ምንዛሪና ብድር ተቆጣጥረው የግል ኢንቨስትመንቱን አዳከሙት። በዚህ ላይ ወጣቱ በአገራዊ ግዳጅ ስለተጠመደ በግብርና እና የቀን ስራ የሚተዳደሩ ቤተሰቦች ሰራተኛ አጥተው ኢኮኖሚው እንዲወድቅ ሆኗል" በማለት ያስረዳል። እንዲህም ሆኖ ዜጎች በንግድና ኢንቨስትመንት ተሳትፎ ያደርጉ ስለለነበረ በ1996 የአገሪቷ ኢኮኖሚ እስከ 6.7 በመቶ እድገት እንዳስመዘገበ ፕሮፌሰር ጋይም ይናገራል። በፋይናንስ ሚኒስትር የኢኮኖሚ ኃላፊ የነበረው አቶ ክብሮም ዳፍላ በወቅቱ ከኤርትራ መገናኛ ብዙሃን ባደረገው ቆይታ እሱ ኃላፊነት ላይ በነበረበት ወቅት ያስተዳድረው የነበረው ተቋም 'ሂምቦል የውጭ ምንዛሪና ሃዋላ' ብቻ በአመት እስከ 80 ሚሊየን ዶላር ገንዘብ ይመነዘር ነበር ብሏል። በተጨማሪም በተመሳሳይ ንግድ ተሰማርተው የነበሩ ሌሎች የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለመስጠት ፍቃድ የተሰጣቸው 29 ተቋማት እንደነበሩ ገልጿል። የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትና ለ20 ዓመታት የዘለቀው ውዝግብ በአስተዳደራዊ ችግርና ጫና ለህግደፍ የንግድት ተቋማት ይሰጥ በነበረው ኢፍትሃዊ የግብርና ቀረጥ እፎይታ ሲያዘግም የነበረው ብቸኛ ኢኮኖሚ፣ ለሁለት አመታት በዘለቀው የኢትዮ ኤርትራ ግጭት ምክንያት ተንኮታኮተ። ጦርነቱ ተከትሎ ላለፉት 18 አመታት በቀጠለው ውዝግብም አብዛኛው ዜጋ በብሄራዊ አገልግሎት እንዲጠመድ ስለሆነ እንደምንም ሲንቀሳቀስ የነበረው ኢኮኖሚ በጦርነት ታግቶ እንደቆመ ፕሮፌሰር ጋይም ይናገራል። "የኤርትራ ብሄራዊ በጀት የሚመለከት ሆነ አገራዊ ኢኮኖሚያዊ ሪፖርት ስለሌለ በጦርነቱ ምክንያት ምን ያክል ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እንደደረሰ ባይገለጽም የነበረውን መባከኑን ግን ግልጽ ነው" ይላል። የኤርትራ መንግሥት ባለስልጣናት ግን "በቅድሚያ የአገር ሉአላዊነት መረጋገጥ ስላለበት አገር ሳናስጠብቅ የውስጥ ጉዳዮቻችን ላይ መነጋገር ጊዜው አይደለም" ሲሉ ቆይተዋል። የመንግሥት ኢኮኖሚያዊ ቅርጽ ሁሉንም የኢኮኖሚ አማራጮች በመቆጣጠሩ ዲሞክራሲያዊ አሰራር እንዳይኖር አድርጓል የሚለው ፕሮፌሰር መንግስተአብ በበኩሉ፤ "ፓርቲው የራሱ ኢኮኖሚ ስለገነባ ከህዝብ ጋር የሚያስተሳስረው መንገድ አይኖረውም። ለዚህም እስከ ዛሬ ለህዝብ ጥያቄ ጆሮ አልሰጠም። ህዝቡም ድምጹን የሚሰጥበት እድል ስለሌለ በድምጹ ተቃውሞ ማሰማት አልቻለም" ይላል። በዲሞክራሲያዊ አገር ፓርቲ ከአባላቶቹ በሚሰበስበው መዋጮ ነው የሚተዳደረው። በኤርትራ ግን ህገ መንግሥታዊ ስርአት ስሌለለ አገሪቷን የሚያስተዳድር ፓርቲም አንድና አንድ ብቻ ስለሆነ፤ ህግደፍ የአገሪቷን ንብረት በሙሉ እያስተዳደረ ይገኛል። የአገሪቱ ኢኮኖሚ ያላደገበት አንድ ምክንያትም ዴሞክራሲያዊ የሆነ አሰራር አለመኖሩ ነው ሲል ፕሮፌሰር ጋይም ያስረዳል። ማዕቀብ ኤርትራ እኤአ በ2009 ከሶማልያ ጋር በተያያዘ፣ በ2011 ከጅቡቲ ጋር በነበራት አለመግባባት የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክርቤት የመሳሪያ ግዢና የተወሰኑ ሰዎች ባንክ እንዳይንቀሳቀስ በማለት ማዕቀብ ጥሎባት ነበር። መንግሥት 'መሬት ላይ የሌለ ነገር በመጠቀም ኤርትራን ለማዳከም የተወሰደ ተከታታይ የአሜሪካ መንግሥታት ሴራ ነው፤ ከኢትዮጵያ ጋር በነበረው ግጭት ምክንያት በማድረግ የአፍሪካን ቀንድ ለመቆጣጠር ያሴሩት ነው' ሲል ቅሬታው ይገልጽ ነበር። በመጨረሻም ኤርትራና ኢትዮጵያ የሰላም ስምምነት ሲፈርሙ ህዳር 14 2019 ላይ ማእቀቡ ተነሳ። ሁለቱም አገራት ስምምነት ከፈረሙ በኋላ የተዘጉ ድንበሮች ሲከፈቱ የአገሪቷ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አሳይቶ ነበር። ይሁን እንጂ ድንበሮቹ ምክንያቱ በውል ባይታወቅም ተመልሰው በመዘጋታቸው የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ዳግም ማሻቀቡን የኤርትራ ምንጮች ይገልጻሉ። ፕሮፌሰር ጋይም ግን ከዚህ በፊት ኤርትራ ላይ የተደነገጉ ማዕቀቦች በአገሪቷ ኢኮኖሚ ላይ ጫና አሳድሯል የሚለው እምነት እንዳለው ተናግሯል። በሌላ በኩል መንግሥት በ2015 ህገ ወጥ የውጭ ምንዛሬ ጭማሪ ለመቆጣጠር፤ የአገሪቷን ገንዘብ በመቀየር ሁሉንም በህዝብና ነጋዴዎች እጅ የነበረው ገንዘብ ባንክ እንዲገባ ካደረገ በኋላ ታላላቅ የንግድ ልውውጥ በባንክ እንዲከናወን ትእዛዝ አስተላለፈ። ዜጎችም ከ5 ሺ ናቅፋ በላይ ከባንክ ማውጣት እንደማይችሉ የሚቆጣጠር ህግ ተግባራዊ ሆኖ እየተሰራበት ይገኛል። ይህም ምታኔ ሃብቱ እንዲዳከም ማድረጉ ፕሮፌሰሩ ያስረዳል። የኤርትራ ህዝብ ለነጻነት ሲታገሉ የነበሩ ድርጅቶች በቻለው ሁሉ እርዳታ በማድረጉ ለድል በቅቷል የሚለው ፕሮፌሰር መንግስትአብ በጣልያን እና ሌሎች አገሮች በስደት የነበሩ እናቶች ከፍተኛ የሞራልና የኢኮኖሚ ድጋፍ አድርገዋል ይላል። ከ1998 እስከ 2000 በነበረው የድንበር ግጭት ብዙ ህዝብ የአገሩን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ቦንድ በመግዛትና በጥሬ ገንዘብ በመለገስ ማገዙን የሚያነሳው ፕሮፌሰር መንግስትአብ 'አገሬ ሽልማቴ' በማለት እናቶች ሽልማታቸውን አበርክተዋል ሲል ያስታውሳል። በተጨማሪም ከጦርነቱ በኋላም ዴሞክራሲያዊ ለውጥ ሳይመጣ በአንጻሩ ለውጥ ሲጠይቁ የነበሩት ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮችና ጋዜጠኞች ያለ አግባብ ታስረው ይገኛሉ፤ እነዚህ እና ሌሎች ተያየዓዥ ምክንያቶች ተደማምረው የአገሪቱ ምጣኔ ሃብት እንዲጎዳ አድርጓል ይላል። በመሆኑም "ፖለቲካዊ ለውጥ ካልመጣ ኢኮኖሚያዊ እድገት የማይታሰብ ነው" ሲል ፕሮፌሰር ጋይም መሰረታዊ ማሻሻያ ለማድረግ የማክሮ ኢኮኖሚ መርሆዎችን ተመልሶ ማየት አስፈላጊ ነው ሲል ይመክራል። | የኤርትራ ምጣኔ ሃብት ባለፉት 30 ዓመታት ኤርትራ በ1992 ዓ.ም 52ኛ አፍሪካዊት አገር ስትሆን ዜጎቿና የነጻነት ጉዞዋን ሲከታተሉ የነበሩ ተንታኞች 'ኤርትራ በአጭር ጊዜ ኢኮኖሚያዊ እድገት በማስመዝገብ የአካባቢዋ ሞዴል ትሆናለች' የሚል ተስፋ ነበራቸው። ከነጻነት በኋላ የነበሩ የጊዝያዊ አስተዳደሩ ስራ አስፈጻሚዎችም "ኤርትራን ሲንጋፑር እናደርጋታለን" ሲሉ ተናግረው ነበር። አገሪቷ በ1994 ያጸደቀችው የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ በግብርና ኢንዳስትሪ፣ አሳና ጨው፣ የመሰረተ ልማቶች ግንባታ፣ ኤሌክትሪክና ውሃ ማስፋፋት፣ ትምህርት፣ ጤናና ሌሎች የማስፈጸም ተልእኮ ተሰጥቶት ስራ ተጀመረ። ሰነዱ መግቢያ ላይ "ኤርትራ ከጦርነትና ግጭት፣ ከጭቆና አገዛዝ nጻ ወጥታ ወደ አዲስ ብልጽግናና ሰላም እየገባች ነው። ይህ በመስዋእትነት የተገኘው ሰላምና መረጋጋት ፈጣን ዴሞክራሲያዊ ለውጥ እያሳየ ነው። በጦርነት የወደመው ምጣኔ ሃብትን ለመገንባትም ጥረት እየተደረገ ይገኛል" ይላል። የአፍሪካ ፖለቲካል ሳይንስ ተመራማሪ ፕሮፌሰር መንግስትአብ ኪዳነ የኤርትራ መንግሥት በግል ባለሃብቶች የሚመራ የኢንቨስትመንትና ወደ ውጪ የሚላክ ምርት ትኩረት ያደረገ ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲ እንደነደፈ ያስታውሳሉ። "መንግሥት የህግደፍ ኢኮኖሚ፣ የመንግሥት ኢኮኖሚ፣ የግል ኢንቨስትመንት ኢኮኖሚ በሚል ሦስት መንገድ የተገበረውን ፖሊሲ ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለበት መንገድ እጁ ማስገባት ስለጀመረ ብዙ ርቀት ሳይጓዝ ነው የተደናቀፈው" ይላል። በተዘበራረቀ አሰራር ምክንያት ህዝብ የመንግሥት የሆነው ንብረት ከፓርቲ ሃብት ለይቶ ማየት እንዳልቻለ የሚናገረው ፕሮፌሰር መንግስትአብ፤ "ለምሳሌ ህዝብ ማዕድን በመንግሥት ነው ወይስ በፓርቲ የሚተዳደረው የሚያውቀው ነገር አልነበረም" በማለት የአገሪቷ የምጣኔ ሃብት ስርአት የተዘበራረቀ መሆኑ ይናገራል። በሳውዝ ባንክ ዩኒቨርሲቲ ለንደን ፕሮፌሰር የሆነው ጋይም ክብረአብ በበኩሉ፤ ህዝቡ፣ በመንግስት በኩል የነበረበትን አስተዳደራዊ ችግር "ልምድ እስኪያገኙ ድረስ ነው" እያለ ጊዜ ቢሰጠውም በጊዜ ማስተካከል ባለመቻሉ የአገሪቷ ምጣኔ ሃብትና ፖለቲካ ወደ ኋላ ቀርቷል ይላል። በዚህ ምክንያት ብዙ በኢንቨስትመንት ለመሳተፍ ፍላጎት የነበራቸው ዜጎች እውቀታቸውና ገንዘባቸው ይዘው ከስደት ወደ አገራቸው ቢመለሱም፤ የግል ኢኮኖሚው ህጋዊ ግብር የማይከፍለው የፓርቲ ኢኮኖሚ ጋር መወዳደር ባለመቻሉ ቀስ በቀስ እንደከሰረ ያስረዳል። ይህ አሰራር ማን ምን እንደሚያስተዳድር ስለማይታወቅ ለሙስና የተጋለጠ እንደሆነ የሚያነሳው ፕሮፌሰር መንግስትአብ፣ በፓርቲ የሚመራው የኢኮኖሚ ተቋም በኢንዳስትሪ፣ ግንባታ፣ ትራንስፖርት፣ መሰረታዊ ሸቀጦች ሳይቀር ስለሚሳተፍ የኢኮኖሚው መተላለፊያ በመቆጣጠር ነጋዴዎች እድል ስለነፈጋቸው ኢኮኖሚው በአግባቡ መራመድ አልቻለም ይላል። "መንግሥትና ፓርቲ የውጭ ምንዛሪና ብድር ተቆጣጥረው የግል ኢንቨስትመንቱን አዳከሙት። በዚህ ላይ ወጣቱ በአገራዊ ግዳጅ ስለተጠመደ በግብርና እና የቀን ስራ የሚተዳደሩ ቤተሰቦች ሰራተኛ አጥተው ኢኮኖሚው እንዲወድቅ ሆኗል" በማለት ያስረዳል። እንዲህም ሆኖ ዜጎች በንግድና ኢንቨስትመንት ተሳትፎ ያደርጉ ስለለነበረ በ1996 የአገሪቷ ኢኮኖሚ እስከ 6.7 በመቶ እድገት እንዳስመዘገበ ፕሮፌሰር ጋይም ይናገራል። በፋይናንስ ሚኒስትር የኢኮኖሚ ኃላፊ የነበረው አቶ ክብሮም ዳፍላ በወቅቱ ከኤርትራ መገናኛ ብዙሃን ባደረገው ቆይታ እሱ ኃላፊነት ላይ በነበረበት ወቅት ያስተዳድረው የነበረው ተቋም 'ሂምቦል የውጭ ምንዛሪና ሃዋላ' ብቻ በአመት እስከ 80 ሚሊየን ዶላር ገንዘብ ይመነዘር ነበር ብሏል። በተጨማሪም በተመሳሳይ ንግድ ተሰማርተው የነበሩ ሌሎች የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለመስጠት ፍቃድ የተሰጣቸው 29 ተቋማት እንደነበሩ ገልጿል። የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትና ለ20 ዓመታት የዘለቀው ውዝግብ በአስተዳደራዊ ችግርና ጫና ለህግደፍ የንግድት ተቋማት ይሰጥ በነበረው ኢፍትሃዊ የግብርና ቀረጥ እፎይታ ሲያዘግም የነበረው ብቸኛ ኢኮኖሚ፣ ለሁለት አመታት በዘለቀው የኢትዮ ኤርትራ ግጭት ምክንያት ተንኮታኮተ። ጦርነቱ ተከትሎ ላለፉት 18 አመታት በቀጠለው ውዝግብም አብዛኛው ዜጋ በብሄራዊ አገልግሎት እንዲጠመድ ስለሆነ እንደምንም ሲንቀሳቀስ የነበረው ኢኮኖሚ በጦርነት ታግቶ እንደቆመ ፕሮፌሰር ጋይም ይናገራል። "የኤርትራ ብሄራዊ በጀት የሚመለከት ሆነ አገራዊ ኢኮኖሚያዊ ሪፖርት ስለሌለ በጦርነቱ ምክንያት ምን ያክል ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እንደደረሰ ባይገለጽም የነበረውን መባከኑን ግን ግልጽ ነው" ይላል። የኤርትራ መንግሥት ባለስልጣናት ግን "በቅድሚያ የአገር ሉአላዊነት መረጋገጥ ስላለበት አገር ሳናስጠብቅ የውስጥ ጉዳዮቻችን ላይ መነጋገር ጊዜው አይደለም" ሲሉ ቆይተዋል። የመንግሥት ኢኮኖሚያዊ ቅርጽ ሁሉንም የኢኮኖሚ አማራጮች በመቆጣጠሩ ዲሞክራሲያዊ አሰራር እንዳይኖር አድርጓል የሚለው ፕሮፌሰር መንግስተአብ በበኩሉ፤ "ፓርቲው የራሱ ኢኮኖሚ ስለገነባ ከህዝብ ጋር የሚያስተሳስረው መንገድ አይኖረውም። ለዚህም እስከ ዛሬ ለህዝብ ጥያቄ ጆሮ አልሰጠም። ህዝቡም ድምጹን የሚሰጥበት እድል ስለሌለ በድምጹ ተቃውሞ ማሰማት አልቻለም" ይላል። በዲሞክራሲያዊ አገር ፓርቲ ከአባላቶቹ በሚሰበስበው መዋጮ ነው የሚተዳደረው። በኤርትራ ግን ህገ መንግሥታዊ ስርአት ስሌለለ አገሪቷን የሚያስተዳድር ፓርቲም አንድና አንድ ብቻ ስለሆነ፤ ህግደፍ የአገሪቷን ንብረት በሙሉ እያስተዳደረ ይገኛል። የአገሪቱ ኢኮኖሚ ያላደገበት አንድ ምክንያትም ዴሞክራሲያዊ የሆነ አሰራር አለመኖሩ ነው ሲል ፕሮፌሰር ጋይም ያስረዳል። ማዕቀብ ኤርትራ እኤአ በ2009 ከሶማልያ ጋር በተያያዘ፣ በ2011 ከጅቡቲ ጋር በነበራት አለመግባባት የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክርቤት የመሳሪያ ግዢና የተወሰኑ ሰዎች ባንክ እንዳይንቀሳቀስ በማለት ማዕቀብ ጥሎባት ነበር። መንግሥት 'መሬት ላይ የሌለ ነገር በመጠቀም ኤርትራን ለማዳከም የተወሰደ ተከታታይ የአሜሪካ መንግሥታት ሴራ ነው፤ ከኢትዮጵያ ጋር በነበረው ግጭት ምክንያት በማድረግ የአፍሪካን ቀንድ ለመቆጣጠር ያሴሩት ነው' ሲል ቅሬታው ይገልጽ ነበር። በመጨረሻም ኤርትራና ኢትዮጵያ የሰላም ስምምነት ሲፈርሙ ህዳር 14 2019 ላይ ማእቀቡ ተነሳ። ሁለቱም አገራት ስምምነት ከፈረሙ በኋላ የተዘጉ ድንበሮች ሲከፈቱ የአገሪቷ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አሳይቶ ነበር። ይሁን እንጂ ድንበሮቹ ምክንያቱ በውል ባይታወቅም ተመልሰው በመዘጋታቸው የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ዳግም ማሻቀቡን የኤርትራ ምንጮች ይገልጻሉ። ፕሮፌሰር ጋይም ግን ከዚህ በፊት ኤርትራ ላይ የተደነገጉ ማዕቀቦች በአገሪቷ ኢኮኖሚ ላይ ጫና አሳድሯል የሚለው እምነት እንዳለው ተናግሯል። በሌላ በኩል መንግሥት በ2015 ህገ ወጥ የውጭ ምንዛሬ ጭማሪ ለመቆጣጠር፤ የአገሪቷን ገንዘብ በመቀየር ሁሉንም በህዝብና ነጋዴዎች እጅ የነበረው ገንዘብ ባንክ እንዲገባ ካደረገ በኋላ ታላላቅ የንግድ ልውውጥ በባንክ እንዲከናወን ትእዛዝ አስተላለፈ። ዜጎችም ከ5 ሺ ናቅፋ በላይ ከባንክ ማውጣት እንደማይችሉ የሚቆጣጠር ህግ ተግባራዊ ሆኖ እየተሰራበት ይገኛል። ይህም ምታኔ ሃብቱ እንዲዳከም ማድረጉ ፕሮፌሰሩ ያስረዳል። የኤርትራ ህዝብ ለነጻነት ሲታገሉ የነበሩ ድርጅቶች በቻለው ሁሉ እርዳታ በማድረጉ ለድል በቅቷል የሚለው ፕሮፌሰር መንግስትአብ በጣልያን እና ሌሎች አገሮች በስደት የነበሩ እናቶች ከፍተኛ የሞራልና የኢኮኖሚ ድጋፍ አድርገዋል ይላል። ከ1998 እስከ 2000 በነበረው የድንበር ግጭት ብዙ ህዝብ የአገሩን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ቦንድ በመግዛትና በጥሬ ገንዘብ በመለገስ ማገዙን የሚያነሳው ፕሮፌሰር መንግስትአብ 'አገሬ ሽልማቴ' በማለት እናቶች ሽልማታቸውን አበርክተዋል ሲል ያስታውሳል። በተጨማሪም ከጦርነቱ በኋላም ዴሞክራሲያዊ ለውጥ ሳይመጣ በአንጻሩ ለውጥ ሲጠይቁ የነበሩት ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮችና ጋዜጠኞች ያለ አግባብ ታስረው ይገኛሉ፤ እነዚህ እና ሌሎች ተያየዓዥ ምክንያቶች ተደማምረው የአገሪቱ ምጣኔ ሃብት እንዲጎዳ አድርጓል ይላል። በመሆኑም "ፖለቲካዊ ለውጥ ካልመጣ ኢኮኖሚያዊ እድገት የማይታሰብ ነው" ሲል ፕሮፌሰር ጋይም መሰረታዊ ማሻሻያ ለማድረግ የማክሮ ኢኮኖሚ መርሆዎችን ተመልሶ ማየት አስፈላጊ ነው ሲል ይመክራል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57140215 |
3politics
| በሱዳን የዴሞክራሲ ደጋፊ ሰልፈኞች በአደባባይ ተቃውሟቸውን ማሰማት ቀጥለዋል | የሱዳን የጸጥታ ሃይሎች በመዲናዋ ካርቱም ዴሞክራሲን እንደግፋለን የሚሉ ተቃዋሚዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ተኩሰዋል። ተቃዋሚዎቹ በሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት ቢሰበሰቡም ከፍተኛ የጸጥታ ኃይሎች አላፈናፍን ብለዋቸዋል። ወታደራዊው መንግሥት ለሰልፈኞቹ የአደባባይ ተቃውሞ አጸፋዊ ምላሽ በከተማዋ የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎቶችን ገድቦ እንደነበር ዘገባዎች አመልክተዋል። ፖርት ሱዳንን ጨምሮ በሌሎች ከተሞችም የአደባባይ ተቃውሞች ታይተዋል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በሱዳን የተፈጠረውን መፈንቅለ መንግሥት በመቃወምና የሲቪል አገዛዙ ይመለስ የሚል ጥያቄም አንግበው ወደ አደባባይ ወጥተዋል። ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ተቃውሞ ከፖሊስ ጋር በተፈጠረ ግጭት ከ100 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። ከዚህም በተጨማሪ የጸጥታ ሃይሎችም ከ12 በላይ ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የመድፈር ወንጀሎችን ፈጽመዋል የሚል ክሶች ቀርቦባቸዋል። በሱዳን ጦሩ ስልጣንን በሃይል የተቆጣጠረበትን ሁለተኛ ወር በማስመልከት፣ ኢንተርኔት ከመቋረጡ በፊት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በትናንትናው ዕለት ተከታታይ የአደባባይ ላይ የተቃውሞ ሰልፎች አቅደው ነበር። አንድ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደገለጹት የኢንተርኔት መቋረጥ የተፈጠረው ዘርፉን የሚቆጣጠረው የሱዳን ብሄራዊ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን (ኤንቲሲ) ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ነው። በመዲናዋ ተጨማሪ የጸጥታ ሃይሎች መሰማራታቸውንና ካርቱምን ከሌሎች ከተሞች ጋር የሚያገናኙት የናይል ወንዝ ድልድዮች መዘጋታቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የአደባባይ ተቃውሞው ደጋፊ የሆነው የዶክተሮች ማህበር እንዳሳወቀው የጸጥታ ሃይሎች ጉዳት የደረሰባቸውን ተቃዋሚችን እያሳደዱ እንደነበረና በሆስፒታል ውስጥ አስለቃሽ ጭስ እና ፈንጂ መተኮሳቸውን ነው። የመፈንቅለ መንግስቱ መሪ ጄኔራል አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን በጥቅምት ወር ጦሩ ስልጣንን በኃይል የተቆጣጠረው የፖለቲካ ቡድኖች ሰላማዊ ዜጎች በጸጥታ ኃይሎች ላይ እንዲነሱ ከመቀስቀሳቸው ጋር ተያይዞ ሊፈጠር የሚችለውን የእርስ በርስ ጦርነት ለመከላከል ነው ሲሉ ተሰምተዋል። ከአመት በኋላ ሊታቀድ ለተደረገው ምርጫና ወደ ሲቪል አገዛዝ ለመሸጋገር ቁርጠኛ እንደሆኑም ተናግረዋል። ነገር ግን አዲሱ ሲቪል መንግሥት በወታደራዊው ጫና ስር ስለሚውል ምን ያህል ስልጣን ይኖረዋል የሚለው ጥያቄን አጭሯል። ጄኔራሉ አሁን እየተካሄዱ ያሉ ተቃውሞዎች ሰላማዊ ዲሞክራሲያዊ ሽግግርን ሊያደናቅፍ እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል። የዲሞክራሲ ደጋፊ ተቃዋሚዎች በበኩላቸው ለረዥም ዘመን ሱዳንን የገዙትን ኦማር አልበሽር ከስልጣን እንዲወገዱ ምክንያት የሆነውን አብዮት ጦሩ ጠልፏል በማለት ይከሷቸዋል። | በሱዳን የዴሞክራሲ ደጋፊ ሰልፈኞች በአደባባይ ተቃውሟቸውን ማሰማት ቀጥለዋል የሱዳን የጸጥታ ሃይሎች በመዲናዋ ካርቱም ዴሞክራሲን እንደግፋለን የሚሉ ተቃዋሚዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ተኩሰዋል። ተቃዋሚዎቹ በሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት ቢሰበሰቡም ከፍተኛ የጸጥታ ኃይሎች አላፈናፍን ብለዋቸዋል። ወታደራዊው መንግሥት ለሰልፈኞቹ የአደባባይ ተቃውሞ አጸፋዊ ምላሽ በከተማዋ የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎቶችን ገድቦ እንደነበር ዘገባዎች አመልክተዋል። ፖርት ሱዳንን ጨምሮ በሌሎች ከተሞችም የአደባባይ ተቃውሞች ታይተዋል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በሱዳን የተፈጠረውን መፈንቅለ መንግሥት በመቃወምና የሲቪል አገዛዙ ይመለስ የሚል ጥያቄም አንግበው ወደ አደባባይ ወጥተዋል። ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ተቃውሞ ከፖሊስ ጋር በተፈጠረ ግጭት ከ100 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። ከዚህም በተጨማሪ የጸጥታ ሃይሎችም ከ12 በላይ ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የመድፈር ወንጀሎችን ፈጽመዋል የሚል ክሶች ቀርቦባቸዋል። በሱዳን ጦሩ ስልጣንን በሃይል የተቆጣጠረበትን ሁለተኛ ወር በማስመልከት፣ ኢንተርኔት ከመቋረጡ በፊት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በትናንትናው ዕለት ተከታታይ የአደባባይ ላይ የተቃውሞ ሰልፎች አቅደው ነበር። አንድ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደገለጹት የኢንተርኔት መቋረጥ የተፈጠረው ዘርፉን የሚቆጣጠረው የሱዳን ብሄራዊ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን (ኤንቲሲ) ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ነው። በመዲናዋ ተጨማሪ የጸጥታ ሃይሎች መሰማራታቸውንና ካርቱምን ከሌሎች ከተሞች ጋር የሚያገናኙት የናይል ወንዝ ድልድዮች መዘጋታቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የአደባባይ ተቃውሞው ደጋፊ የሆነው የዶክተሮች ማህበር እንዳሳወቀው የጸጥታ ሃይሎች ጉዳት የደረሰባቸውን ተቃዋሚችን እያሳደዱ እንደነበረና በሆስፒታል ውስጥ አስለቃሽ ጭስ እና ፈንጂ መተኮሳቸውን ነው። የመፈንቅለ መንግስቱ መሪ ጄኔራል አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን በጥቅምት ወር ጦሩ ስልጣንን በኃይል የተቆጣጠረው የፖለቲካ ቡድኖች ሰላማዊ ዜጎች በጸጥታ ኃይሎች ላይ እንዲነሱ ከመቀስቀሳቸው ጋር ተያይዞ ሊፈጠር የሚችለውን የእርስ በርስ ጦርነት ለመከላከል ነው ሲሉ ተሰምተዋል። ከአመት በኋላ ሊታቀድ ለተደረገው ምርጫና ወደ ሲቪል አገዛዝ ለመሸጋገር ቁርጠኛ እንደሆኑም ተናግረዋል። ነገር ግን አዲሱ ሲቪል መንግሥት በወታደራዊው ጫና ስር ስለሚውል ምን ያህል ስልጣን ይኖረዋል የሚለው ጥያቄን አጭሯል። ጄኔራሉ አሁን እየተካሄዱ ያሉ ተቃውሞዎች ሰላማዊ ዲሞክራሲያዊ ሽግግርን ሊያደናቅፍ እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል። የዲሞክራሲ ደጋፊ ተቃዋሚዎች በበኩላቸው ለረዥም ዘመን ሱዳንን የገዙትን ኦማር አልበሽር ከስልጣን እንዲወገዱ ምክንያት የሆነውን አብዮት ጦሩ ጠልፏል በማለት ይከሷቸዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59793345 |
5sports
| 'ከምንግዜም ምርጡ' የፍጻሜ ጨዋታ በኋላ ማን ምን አለ? | “እንደዚህ ዓይነት ነገር በፍጹም ደግም አናይም” ያለው የእንግሊዝ የቀድሞ ተከላካይ ሪዮ ፈርዲናንድ ነው። ፈርዲናንድ ብዙዎች ያሰቡትን ነው ቅልብጭ አድርጎ የገለጸው። ሁሉም ሙሉ የነበረበት ነው። ከዋክብቱ ሊዮኔል ሜሲ እና ክሊያን ምባፔ የተፋጠጡበት። ጨዋታው አበቃ ሲባል ድጋሚ ነፍስ የሚዘራበት አስገራሚ ምሽት። ስሜትን ሰቅዞ የሚይዝ የመለያ ምት ያለበት ጨዋታ። ማህበራዊ ሚዲያው የተጥለቀለቀበት። የስፖርት ከዋክብት የፈዘዙበት፤ በሉሳይል ስታዲም የተገኙ ደግሞ ታሪክ በዓይናቸው ያዩበት ምሽት። “ይህ ይሆናል ብዬ አልጠበቅኩም። ሁለት ግዙፍ ቡድኖች እግር በእግር የተያያዙበት ነው” ሲል ፈርዲናንድ ለቢቢሲ ዋን ገልጿል። "በሁለቱም ቡድኖች ያሉት ሁለቱ ኮከቦች ጎል በጎል ላይ ያስቆጠሩበት . . . ግሩም" ብሎታል። የቀድሞ እንግሊዝ አጥቂ አለን ሺረር ደግሞ "ትንፋሽ አጥሮናል፤ ለማመን የሚከብድ ፍጻሜ ነበር። እንደዚህ ያለ ነገር አይቼ አላውቅም። እንደገናም አያለሁ ብዬ አላስብም። በጣም አስገራሚ ነበር" ሲል ተናግሯል። የአርጀንቲናው አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ ከጨዋታው በኋላ "ተረጋግቻለሁ" ቢልም ስሜቱን ግን መደበቅ አልቻለም። "ጨዋታው ሙሉ በሙሉ እብደት ነበር። ጥሩ እንደተጫወትን አውቃለሁ። በ90 ደቂቃው ማሸነፍ እንችል ነበር" ብሏል። “ከመቼውም ጊዜ የተሻለ ጥሩ ስሜት ተፈጥሮብኛል። በጣም አስፈላጊው ነገር ይህንን ያሳካንበት መንገድ ነው" ሲል አክሏል። ከጨዋታው በፊት አብዛኛው ትኩረት አርጀንቲናዊው ሜሲ እና ፈረንሳዊው ምባፔ ላይ ነበር። ለኮከብ ጎል አግቢነት ከሚደረገው ግብግብ ሌላ ቡድናቸው ለዋንጫ የሚያበቁ መሆኑ ሲነገርላቸው ነበር። ምባፔ በመጀመርያው አጋማሽ ሜዳ ላይ መኖሩም ተረስቶ ነበር። አርጀንቲና በአሌክሲስ ማክ አሊስተር አማካኝነት የመጀመሪያውን ሙከራ ለማድረግ አራት ደቂቃ ብቻ ወሰደባት። ከዚያ በኋላም ጨዋታውን በበላይነት ተቆጣጠረች። የሜሲ ተሳትፎ የጀመረው በ23ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ፍጹም ቅጣት ምት አርጀንቲናን ቀዳሚ ሲያድርገ ነው። አንጄል ዲ ማሪያ ከ13 ደቂቃ በኋላ ሁለተኛዋን አስቆጠረ። ፈረንሳዮች ግራ ተጋብተው ነበር። ምባፔ ተሳትፎው በጣም ተገድቦ ነበር። በቃኝ ያሉት አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሾ 41ኛው ደቂቃ ሁለት ተጫዋቾችን ቀየሩ። ኦሊቪዬ ዥሩ እና ኦስማን ዴምቤሌ ወጥተው ራንዳል ኮሎ ሙዋኒ እና ማርከስ ቱራምን ተኳቸው። ለእረፍት ወደ መልበሻ ክፍል ሁለቱ ቡድኖች ሲያመሩ ፈረንሳይ ወደ ጎል ምንም ሙከራ አላደረገችም። አርጀንቲና 2 ለ 0 እየመራች ነው። ጨዋታው ተጠናቋል በሚል ጋዜጠኞች የጨዋታ ሪፖርታቸውን በማጠናቀቅ ላይ ነበሩ። ድራማው ግን ገና አልተጀመረም። የአርጀንቲናውን ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝን በ67ኛው ደቂቃ ስትፈትን እንኳን ፈረንሳይ ገና ወደ ጨዋታው አልተመለሰችም። ወዲው ግን ነገሮች በፍጥነት መቀያየር ያዙ. . . ሙአኒ በፍጹም ቅጣት ክልል ውስጥ በኒኮላስ ኦታሜንዲ ተጠልፎ ወደቀ። ምባፔ ፍጹም ቅጣት ምት ሊመታ ማርቲኔዝ ጎሉን ላለማስደፈር ተፋጠጡ። አሁን ጨዋታ ደራ። አርጀንቲና 2 ፈረንሳይ 1። አርጀንቲናዎች ትንፋሽ እንኳን ሳይሰበስቡ ምባፔ በአስደናቂው ሁኔታ ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው 2-2 ሆነ። ተጨማሪ 30 ደቂቃ ተጀመረ። የሜሲ ምሽት ነበር በ 108 ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ዋንጫዋ ወደ አርጀንቲና አዘነበለች። ምባፔ ግን ሥራውን አላጠናቀቅም። ሃትሪክ ያስቆተረበትን ጎል በ118ኛው አሳካ። ይህም ከእንግሊዙ ሰር ጂኦፍ ሁረስት (1966) በመቀጠል 3 ጎሎችን በዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ያስቆጠረ ሁለተኛው ተጫዋች አድርጎታል። አሸናፊውን ለመለየት ወደ መለያ ምት ማምራት ግድ ሆነ። በጨዋታው ሁለት ጊዜ መምራት ችላ የነበረችው አርጀንቲና ከ1986 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫ አነሳች። ማርቲኔዝ የኪንግስሌይ ኮማንን ኳስ ሲኣድን እና አውሬሊ ቹአሜኒ ደግሞ ኳሷን ወደ ው ሰዷታል። | 'ከምንግዜም ምርጡ' የፍጻሜ ጨዋታ በኋላ ማን ምን አለ? “እንደዚህ ዓይነት ነገር በፍጹም ደግም አናይም” ያለው የእንግሊዝ የቀድሞ ተከላካይ ሪዮ ፈርዲናንድ ነው። ፈርዲናንድ ብዙዎች ያሰቡትን ነው ቅልብጭ አድርጎ የገለጸው። ሁሉም ሙሉ የነበረበት ነው። ከዋክብቱ ሊዮኔል ሜሲ እና ክሊያን ምባፔ የተፋጠጡበት። ጨዋታው አበቃ ሲባል ድጋሚ ነፍስ የሚዘራበት አስገራሚ ምሽት። ስሜትን ሰቅዞ የሚይዝ የመለያ ምት ያለበት ጨዋታ። ማህበራዊ ሚዲያው የተጥለቀለቀበት። የስፖርት ከዋክብት የፈዘዙበት፤ በሉሳይል ስታዲም የተገኙ ደግሞ ታሪክ በዓይናቸው ያዩበት ምሽት። “ይህ ይሆናል ብዬ አልጠበቅኩም። ሁለት ግዙፍ ቡድኖች እግር በእግር የተያያዙበት ነው” ሲል ፈርዲናንድ ለቢቢሲ ዋን ገልጿል። "በሁለቱም ቡድኖች ያሉት ሁለቱ ኮከቦች ጎል በጎል ላይ ያስቆጠሩበት . . . ግሩም" ብሎታል። የቀድሞ እንግሊዝ አጥቂ አለን ሺረር ደግሞ "ትንፋሽ አጥሮናል፤ ለማመን የሚከብድ ፍጻሜ ነበር። እንደዚህ ያለ ነገር አይቼ አላውቅም። እንደገናም አያለሁ ብዬ አላስብም። በጣም አስገራሚ ነበር" ሲል ተናግሯል። የአርጀንቲናው አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ ከጨዋታው በኋላ "ተረጋግቻለሁ" ቢልም ስሜቱን ግን መደበቅ አልቻለም። "ጨዋታው ሙሉ በሙሉ እብደት ነበር። ጥሩ እንደተጫወትን አውቃለሁ። በ90 ደቂቃው ማሸነፍ እንችል ነበር" ብሏል። “ከመቼውም ጊዜ የተሻለ ጥሩ ስሜት ተፈጥሮብኛል። በጣም አስፈላጊው ነገር ይህንን ያሳካንበት መንገድ ነው" ሲል አክሏል። ከጨዋታው በፊት አብዛኛው ትኩረት አርጀንቲናዊው ሜሲ እና ፈረንሳዊው ምባፔ ላይ ነበር። ለኮከብ ጎል አግቢነት ከሚደረገው ግብግብ ሌላ ቡድናቸው ለዋንጫ የሚያበቁ መሆኑ ሲነገርላቸው ነበር። ምባፔ በመጀመርያው አጋማሽ ሜዳ ላይ መኖሩም ተረስቶ ነበር። አርጀንቲና በአሌክሲስ ማክ አሊስተር አማካኝነት የመጀመሪያውን ሙከራ ለማድረግ አራት ደቂቃ ብቻ ወሰደባት። ከዚያ በኋላም ጨዋታውን በበላይነት ተቆጣጠረች። የሜሲ ተሳትፎ የጀመረው በ23ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ፍጹም ቅጣት ምት አርጀንቲናን ቀዳሚ ሲያድርገ ነው። አንጄል ዲ ማሪያ ከ13 ደቂቃ በኋላ ሁለተኛዋን አስቆጠረ። ፈረንሳዮች ግራ ተጋብተው ነበር። ምባፔ ተሳትፎው በጣም ተገድቦ ነበር። በቃኝ ያሉት አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሾ 41ኛው ደቂቃ ሁለት ተጫዋቾችን ቀየሩ። ኦሊቪዬ ዥሩ እና ኦስማን ዴምቤሌ ወጥተው ራንዳል ኮሎ ሙዋኒ እና ማርከስ ቱራምን ተኳቸው። ለእረፍት ወደ መልበሻ ክፍል ሁለቱ ቡድኖች ሲያመሩ ፈረንሳይ ወደ ጎል ምንም ሙከራ አላደረገችም። አርጀንቲና 2 ለ 0 እየመራች ነው። ጨዋታው ተጠናቋል በሚል ጋዜጠኞች የጨዋታ ሪፖርታቸውን በማጠናቀቅ ላይ ነበሩ። ድራማው ግን ገና አልተጀመረም። የአርጀንቲናውን ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝን በ67ኛው ደቂቃ ስትፈትን እንኳን ፈረንሳይ ገና ወደ ጨዋታው አልተመለሰችም። ወዲው ግን ነገሮች በፍጥነት መቀያየር ያዙ. . . ሙአኒ በፍጹም ቅጣት ክልል ውስጥ በኒኮላስ ኦታሜንዲ ተጠልፎ ወደቀ። ምባፔ ፍጹም ቅጣት ምት ሊመታ ማርቲኔዝ ጎሉን ላለማስደፈር ተፋጠጡ። አሁን ጨዋታ ደራ። አርጀንቲና 2 ፈረንሳይ 1። አርጀንቲናዎች ትንፋሽ እንኳን ሳይሰበስቡ ምባፔ በአስደናቂው ሁኔታ ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው 2-2 ሆነ። ተጨማሪ 30 ደቂቃ ተጀመረ። የሜሲ ምሽት ነበር በ 108 ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ዋንጫዋ ወደ አርጀንቲና አዘነበለች። ምባፔ ግን ሥራውን አላጠናቀቅም። ሃትሪክ ያስቆተረበትን ጎል በ118ኛው አሳካ። ይህም ከእንግሊዙ ሰር ጂኦፍ ሁረስት (1966) በመቀጠል 3 ጎሎችን በዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ያስቆጠረ ሁለተኛው ተጫዋች አድርጎታል። አሸናፊውን ለመለየት ወደ መለያ ምት ማምራት ግድ ሆነ። በጨዋታው ሁለት ጊዜ መምራት ችላ የነበረችው አርጀንቲና ከ1986 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫ አነሳች። ማርቲኔዝ የኪንግስሌይ ኮማንን ኳስ ሲኣድን እና አውሬሊ ቹአሜኒ ደግሞ ኳሷን ወደ ው ሰዷታል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c4nk1d65gvzo |
2health
| ኮሮናቫይረስ ፡ በየደቂቃው በዓለም ዙሪያ ኮቪድ-19 የሚይዛቸውና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርን የሚያሳይ ካርታ | ከቻይናዋ ሁቤይ ግዛት ተነስቶ ሰው ከማይኖርበት አንታርክቲክ ውጪ ሁሉንም የዓለማችንን አህጉራትን ያዳረሰው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአሁኑ ወቅት የምድራችን ዋነኛ የጤና ስጋት ሆኗል። ኮቪድ-19 በመባል የሚታወቀው ይህ ወረርሽኝ የመተንፈሻ አካልን የሚያጠቃ ሲሆን፤ መጀመሪያ ትኩሳት ቀጥሎም ደረቅ ሳል ከሳምንት በኋላ ደግሞ የትንፋሽ ማጠርን ያስከትላል። እስካሁን በቫይረሱ ከ186 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የተያዙ ሲሆን ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል። በበሽታው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተያዙና ከሞቱ ከአንድ ዓመት በኋላ የተለያዩ አይነት ክትባቶች ተገኝተው ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ለሰዎች እየተሰጡ ይገኛሉ። ነገር ግን አሁንም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም፣ የእጅን ንጽህና በተደጋጋሚ መጠበቅና በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ በሽታውን ለመከላከል ዋነኞቹ መንገዶች መሆናቸውን ባለሙያዎች አጥብቀው ይመክራሉ። በየደቂቃው በዓለም ዙሪያ ባሉ አገራት ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ፣ ከበሽታው የሚያገግሙና በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎችን አሃዝ ቀጥሎ ከተቀመጠው ዝርዝር ላይ ይመልከቱ። የኮሮናቫይረስ ሁለት ዋነኛ ምልክቶች ከፍተኛ ትኩሳትና ደረቅ ሳል ናቸው። በአንዳንድ ታማሚዎች ላይ እነዚህ ምልክቶች ወደ ትንፋሽ ማጠር ይወስዳሉ። ደረቅ ሳል ሲባል በጣም ጠንካራ የሆነ አንዳንድ ጊዜ ለአንድ ሰዓት የሚቆይ ነው። ከዚህ በፊት ደረቅ ሳል ካለብዎ የኮሮናቫይረስ ሳል በጣም ለየት ያለና ከባድ መሆኑን ማስተዋል ይችላሉ። ከፍተኛ ትኩሳት የሚባለው ደግሞ የሰውነት ሙቀት መጠን ከ37.8 ዲግሪ ሴልሲየስ ሲልቅ ነው። ይህ ትኩሳት ሰውነት እንዲግል ወይም ደግሞ ከፍተኛ ብርድና መንቀጥቀጥ እንዲሰማን ያደርጋል። ከእነዚህ ሁለቱ ዋነኛ ስሜቶች ባለፈ ራስ ምታትና ተቅማጥ አንዳንድ የበሽታው ታማሚዎች ያሳይዋቸው ምልክቶች ናቸው። የማሽተትና የመቅመስ አቅም ማጣትም ምልክቶች ሆነው ተመዝግበዋል። ምልክቶቹ ቫይረስ ሰውነት ውስጥ በገባ በአምስት ቀናት ሊታዩ ይችላሉ። የዓለም ጤና ድርጅት ዘገባ ምልክቶቹ እስከ 14 ቀናት ድረስ ሳይታዩ ሊቆዩ እንደሚችሉ ያስረዳል። | ኮሮናቫይረስ ፡ በየደቂቃው በዓለም ዙሪያ ኮቪድ-19 የሚይዛቸውና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርን የሚያሳይ ካርታ ከቻይናዋ ሁቤይ ግዛት ተነስቶ ሰው ከማይኖርበት አንታርክቲክ ውጪ ሁሉንም የዓለማችንን አህጉራትን ያዳረሰው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአሁኑ ወቅት የምድራችን ዋነኛ የጤና ስጋት ሆኗል። ኮቪድ-19 በመባል የሚታወቀው ይህ ወረርሽኝ የመተንፈሻ አካልን የሚያጠቃ ሲሆን፤ መጀመሪያ ትኩሳት ቀጥሎም ደረቅ ሳል ከሳምንት በኋላ ደግሞ የትንፋሽ ማጠርን ያስከትላል። እስካሁን በቫይረሱ ከ186 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የተያዙ ሲሆን ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል። በበሽታው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተያዙና ከሞቱ ከአንድ ዓመት በኋላ የተለያዩ አይነት ክትባቶች ተገኝተው ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ለሰዎች እየተሰጡ ይገኛሉ። ነገር ግን አሁንም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም፣ የእጅን ንጽህና በተደጋጋሚ መጠበቅና በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ በሽታውን ለመከላከል ዋነኞቹ መንገዶች መሆናቸውን ባለሙያዎች አጥብቀው ይመክራሉ። በየደቂቃው በዓለም ዙሪያ ባሉ አገራት ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ፣ ከበሽታው የሚያገግሙና በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎችን አሃዝ ቀጥሎ ከተቀመጠው ዝርዝር ላይ ይመልከቱ። የኮሮናቫይረስ ሁለት ዋነኛ ምልክቶች ከፍተኛ ትኩሳትና ደረቅ ሳል ናቸው። በአንዳንድ ታማሚዎች ላይ እነዚህ ምልክቶች ወደ ትንፋሽ ማጠር ይወስዳሉ። ደረቅ ሳል ሲባል በጣም ጠንካራ የሆነ አንዳንድ ጊዜ ለአንድ ሰዓት የሚቆይ ነው። ከዚህ በፊት ደረቅ ሳል ካለብዎ የኮሮናቫይረስ ሳል በጣም ለየት ያለና ከባድ መሆኑን ማስተዋል ይችላሉ። ከፍተኛ ትኩሳት የሚባለው ደግሞ የሰውነት ሙቀት መጠን ከ37.8 ዲግሪ ሴልሲየስ ሲልቅ ነው። ይህ ትኩሳት ሰውነት እንዲግል ወይም ደግሞ ከፍተኛ ብርድና መንቀጥቀጥ እንዲሰማን ያደርጋል። ከእነዚህ ሁለቱ ዋነኛ ስሜቶች ባለፈ ራስ ምታትና ተቅማጥ አንዳንድ የበሽታው ታማሚዎች ያሳይዋቸው ምልክቶች ናቸው። የማሽተትና የመቅመስ አቅም ማጣትም ምልክቶች ሆነው ተመዝግበዋል። ምልክቶቹ ቫይረስ ሰውነት ውስጥ በገባ በአምስት ቀናት ሊታዩ ይችላሉ። የዓለም ጤና ድርጅት ዘገባ ምልክቶቹ እስከ 14 ቀናት ድረስ ሳይታዩ ሊቆዩ እንደሚችሉ ያስረዳል። | https://www.bbc.com/amharic/news-51868474 |
5sports
| በኳታር የዓለም ዋንጫ ከጨዋታው ቀድመው ሌሎች ጉዳዮች ለምን አነጋጋሪ ሆኑ? | የኳታሩ የዓለም ዋንጫ በጉጉት እየተጠበቀ ነው። ነገር ግን አገሪቱ ባላት የመብት አያያዝ ዙሪያ በርካታ ወቀሳ እና ተቃውሞ እየቀረበባት ነው። ይህም በውድድሩ ላይ ጥላውን ሊያጠላበት ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል። የውጭ አገር የጉልበት ሠራተኞች አያያዝ ጉዳይ፣ የመናገር መብትን እና አገሪቱ ከተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን አንጻር ያላት አቋም ኳታርን እያስወቀሱ ከሚገኙ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ። | በኳታር የዓለም ዋንጫ ከጨዋታው ቀድመው ሌሎች ጉዳዮች ለምን አነጋጋሪ ሆኑ? የኳታሩ የዓለም ዋንጫ በጉጉት እየተጠበቀ ነው። ነገር ግን አገሪቱ ባላት የመብት አያያዝ ዙሪያ በርካታ ወቀሳ እና ተቃውሞ እየቀረበባት ነው። ይህም በውድድሩ ላይ ጥላውን ሊያጠላበት ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል። የውጭ አገር የጉልበት ሠራተኞች አያያዝ ጉዳይ፣ የመናገር መብትን እና አገሪቱ ከተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን አንጻር ያላት አቋም ኳታርን እያስወቀሱ ከሚገኙ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cg6vlpg310eo |
3politics
| ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በፓርላማ ንግግራቸው ምን ምን ቁልፍ ነጥቦች አነሱ? | ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች መንግሥት በዚህ ዓመት ትኩረት በሚያደርግባቸው ጉዳዮችን በተመለከተ ንግግር አድርገዋል። ስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የሥራ ዘመኑን ሲጀምር፣ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ በንግግራቸውም ቀጣይ የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫዎችን አመልክተዋል። "ጠንከራ ፓርላማ ለመልካም አስተዳደር" ያሉት ፕሬዝዳንቷ፤ በፓርላማው የተለያዩ ሃሳቦች የሚንሸራሸሩበት፤ ተከራክረው የሚያሸንፉበት ቦታ መሆን ይጠበቅበታል ብለዋል። ፕሬዝዳንቷ ሲወሰዱ የነበሩ የምጣኔ ሀብት ማሻሻያዎች፤ ኢኮኖሚው ከነበረበት የቁልቁለት ጉዞ በመታደግ እና በማነቃቃት ከፍተኛ ውጤት አምጥተዋል ሲሉ ተናግረዋል። በ2014 በጀት ዓመት የመንግስት ገቢን 600 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማድረስ መታቀዱንና፤ ከዚህም ውስጥ 83 በመቶው የሚሆነው ገቢ በታክስ እንደሚሰበሰብ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ገለፀዋል። ጠቅላላ የሸቀጦች ንግድ ገቢም 5 ነጥብ 25 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እንደሚሰራም ተናግረዋል። ሆኖም ግን የኑሮ ውድነት እና ሥራ አጥነት የምጣኔ ሀብቱ ዋነኛ ፈተናዎች ሆነው መቀጠላቸውን እና የመንግሥት ዋነኛ የምጣኔ ሀብት ትኩረት እንደሚሆኑ ገልጸዋል። "ማይክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ይቀጥላሉ፣ የሥራ እድል ፈጠራን ማስፋፋት፣ የዋጋ ግሽበት በመቀነስ የኑሮ ውድነት እንዲስተካከል፣ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ተግዳሮቶች የገጠሙ ጉድለቶችን በማረም ሁለንተናዊ እድገት እንዲረጋገጥ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል።" እየጨመረ ለመጣው የዋጋ ግሽበት መንስኤ የሆኑ የአቅርቦት እና ፍላጎት አለመመጣጠን፣ ዝናብን መሰረት ያደረገ የግብርና ሥርዓት፣ የተዛባ ንግድ ሥርዓት ለማስተካከል በትኩረት ይሰራል ሲሉም አክለዋል። የገንዘብ እና ፊስካል ፖሊስ የትኩረት አቅጣጫ እንደሚሆንም ገልፀዋል። የአረንጓዴ አሻራ መንግሥት በቀጣይ ዓመት የደን ሀብት ቁጥርን ለመጨመር ስለማቀዱ ፕሬዝዳንቷ አመላክተዋል። በአራት ዓመት 20 ቢሊዮን ዛፎች ለመትከል የተያዘውን እቅድ በማሳካት የሕዝቡን የምግብ ዋስትና ማረጋጋጥ ይገባል ብለዋል። አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ የሥራ እድል እንዲፈጠር በትኩረት እንደሚሰራም ገልፀዋል። ከፍተኛ ማዕድን በሚገኙባቸው አካባቢዎች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮች እንዲቀረፉ በልዩ ትኩረት ይሰራል ያሉት ፕሬዝዳንቷ፤ ለባህላዊ እና አነስተኛ ማዕድን አምራቾችም ልዩ ትኩረት ይሰጣል ሲሉ ተናግረዋል። ኮንስትራክሽን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን አቅም በመገንባት አብዛኛው የአገር ውስጥ ፍላጎት በአገር በቀል ኩባንያዎች እንዲሸፈን እንደሚደረግ የተናገሩት ፕሬዝዳንቷ፣ "ኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ከፍተኛ የሥራ እድል ይፈጥራል "ብለዋል። ነባር የቱሪስት መዳረሻዎችን እና አዳዲስ መዳረሻዎች እንዲለሙ ይደረጋል። በገበታ ለአገር የተጀመሩ ጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻ የቱሪስት መዳረሻዎች በእቅዳቸው መሰረት ይከናወናሉ ሲሉም ገልፀዋል። የሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት በተጠናቀቀው ዓመት ተከናውኖ እንደነበረ ያስታወሱት ፕሬዝዳንቷ፤ የውሃው ሙሌት እንዳይከናወን ዓለም አቀፍ ጫናዎች እንደነበሩ ጠቁመዋል። ሕዳሴ ግድብ በተያዘው ዓመት "ብርሃን ይሆናል" ብለዋል ፕሬዝደንቷ። የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ስድስተኛ ዙር የሥልጣን ዘመን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት የሁለቱን ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎቻቸውን የመረጡ ሲሆን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ሰይሟል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በተመሰረተው ምክር ቤት አማካይነት ለቀጣይ አምስት ዓመታት አገሪቱን እንዲመሩ ተመርጠው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል። | ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በፓርላማ ንግግራቸው ምን ምን ቁልፍ ነጥቦች አነሱ? ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች መንግሥት በዚህ ዓመት ትኩረት በሚያደርግባቸው ጉዳዮችን በተመለከተ ንግግር አድርገዋል። ስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የሥራ ዘመኑን ሲጀምር፣ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ በንግግራቸውም ቀጣይ የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫዎችን አመልክተዋል። "ጠንከራ ፓርላማ ለመልካም አስተዳደር" ያሉት ፕሬዝዳንቷ፤ በፓርላማው የተለያዩ ሃሳቦች የሚንሸራሸሩበት፤ ተከራክረው የሚያሸንፉበት ቦታ መሆን ይጠበቅበታል ብለዋል። ፕሬዝዳንቷ ሲወሰዱ የነበሩ የምጣኔ ሀብት ማሻሻያዎች፤ ኢኮኖሚው ከነበረበት የቁልቁለት ጉዞ በመታደግ እና በማነቃቃት ከፍተኛ ውጤት አምጥተዋል ሲሉ ተናግረዋል። በ2014 በጀት ዓመት የመንግስት ገቢን 600 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማድረስ መታቀዱንና፤ ከዚህም ውስጥ 83 በመቶው የሚሆነው ገቢ በታክስ እንደሚሰበሰብ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ገለፀዋል። ጠቅላላ የሸቀጦች ንግድ ገቢም 5 ነጥብ 25 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እንደሚሰራም ተናግረዋል። ሆኖም ግን የኑሮ ውድነት እና ሥራ አጥነት የምጣኔ ሀብቱ ዋነኛ ፈተናዎች ሆነው መቀጠላቸውን እና የመንግሥት ዋነኛ የምጣኔ ሀብት ትኩረት እንደሚሆኑ ገልጸዋል። "ማይክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ይቀጥላሉ፣ የሥራ እድል ፈጠራን ማስፋፋት፣ የዋጋ ግሽበት በመቀነስ የኑሮ ውድነት እንዲስተካከል፣ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ተግዳሮቶች የገጠሙ ጉድለቶችን በማረም ሁለንተናዊ እድገት እንዲረጋገጥ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል።" እየጨመረ ለመጣው የዋጋ ግሽበት መንስኤ የሆኑ የአቅርቦት እና ፍላጎት አለመመጣጠን፣ ዝናብን መሰረት ያደረገ የግብርና ሥርዓት፣ የተዛባ ንግድ ሥርዓት ለማስተካከል በትኩረት ይሰራል ሲሉም አክለዋል። የገንዘብ እና ፊስካል ፖሊስ የትኩረት አቅጣጫ እንደሚሆንም ገልፀዋል። የአረንጓዴ አሻራ መንግሥት በቀጣይ ዓመት የደን ሀብት ቁጥርን ለመጨመር ስለማቀዱ ፕሬዝዳንቷ አመላክተዋል። በአራት ዓመት 20 ቢሊዮን ዛፎች ለመትከል የተያዘውን እቅድ በማሳካት የሕዝቡን የምግብ ዋስትና ማረጋጋጥ ይገባል ብለዋል። አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ የሥራ እድል እንዲፈጠር በትኩረት እንደሚሰራም ገልፀዋል። ከፍተኛ ማዕድን በሚገኙባቸው አካባቢዎች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮች እንዲቀረፉ በልዩ ትኩረት ይሰራል ያሉት ፕሬዝዳንቷ፤ ለባህላዊ እና አነስተኛ ማዕድን አምራቾችም ልዩ ትኩረት ይሰጣል ሲሉ ተናግረዋል። ኮንስትራክሽን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን አቅም በመገንባት አብዛኛው የአገር ውስጥ ፍላጎት በአገር በቀል ኩባንያዎች እንዲሸፈን እንደሚደረግ የተናገሩት ፕሬዝዳንቷ፣ "ኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ከፍተኛ የሥራ እድል ይፈጥራል "ብለዋል። ነባር የቱሪስት መዳረሻዎችን እና አዳዲስ መዳረሻዎች እንዲለሙ ይደረጋል። በገበታ ለአገር የተጀመሩ ጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻ የቱሪስት መዳረሻዎች በእቅዳቸው መሰረት ይከናወናሉ ሲሉም ገልፀዋል። የሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት በተጠናቀቀው ዓመት ተከናውኖ እንደነበረ ያስታወሱት ፕሬዝዳንቷ፤ የውሃው ሙሌት እንዳይከናወን ዓለም አቀፍ ጫናዎች እንደነበሩ ጠቁመዋል። ሕዳሴ ግድብ በተያዘው ዓመት "ብርሃን ይሆናል" ብለዋል ፕሬዝደንቷ። የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ስድስተኛ ዙር የሥልጣን ዘመን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት የሁለቱን ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎቻቸውን የመረጡ ሲሆን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ሰይሟል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በተመሰረተው ምክር ቤት አማካይነት ለቀጣይ አምስት ዓመታት አገሪቱን እንዲመሩ ተመርጠው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58785329 |
2health
| ቬትናም የመጀመሪያውን የኮቪድ-19 ሞት መዘገበች | የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በምታደርገው ጥረት የምትመሰገነው እስያዊቷ አገር ቬትናም የመጀመሪያውን የኮቪድ -19 ሞት መዘገበች። ይህም እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ሞት ላልመዘገበችው ቬትናም አሳዛኝ ክስተት ሆኗል። በበሽታው የሞቱት የ70 ዓመቱ ግለሰብ ከሆይ አን ከምትባል ግዛት መሆናቸውንም የአገሪቷ ሚዲያ ዘግቧል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በዳ ናንግ ሪዞርት አቅራቢያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከመመዝገባቸው በፊት ከሦስት ወራት ለሚበልጥ ጊዜ በአገሪቷ አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልነበረም። 95 ሚሊየን ሕዝብ ያላት ቬትናም፤ ወረርሽኙ ከጀመረ አንስቶ እስካሁን 509 በቫይረሱ ተይዘውባታል። ይህም ከሌሎች አገራት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ ቁጥር ነው። በእርግጥ አገሪቷ ከሌሎች አገራት በተለየ ቫይረሱን ለመከላከል እርምጃ መውሰድ የጀመረችው አንድም በቫይረሱ የተያዘ ሰው ሳይኖር ነበር። ድንበሮቿንም ወደ አገራቸው ከሚገቡ ዜጎቿ በስተቀር ለተጓዦች ዝግ ያደረገችው ቀድማ ነበር። ከዚህም ባሻገር ወደ አገሪቷ የሚገባ ማንኛውም ግለሰብ መንግሥት ባዘጋጀው ለይቶ ማቆያ ለ14 ቀናት መቆየትና መመርመር ግድ ነው። እነዚህ የጥንቃቄ እርምጃዎችም ውጤት አሳይተው ከሚያዚያ ወር አጋማሽ ጀምሮ በአገሪቷ አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልነበረም። በዚህ በወቅት በሽታውን ለመቆጣጠር ባደረገችው ጥረት እንዲሁም በቫይረሱ ተይዞ ሁለት ወራትን በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ላሳለፈው ስኮትላንዳዊ አብራሪ ላደረገችው እንክብካቤም አድናቆት ተችሯታል። ይሁን እንጂ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በታዋቂው ዳ ናንግ ሪዞርት አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የመገኘታቸው አሳዛኝ ዜና ተሰምቷል። በዚህ ወቅትም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአገሪቷ ጎብኝዎች በከተማዋ ውስጥ ነበሩ ተብሏል። መንግሥት ረቡዕ ዕለት በከተማዋ ሙሉ ለሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ከመጣሉ በፊትም ከተማዋን ለጎብኝዎች ዝግ አድርጎ ነበር። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በዳ ናንግ የተከሰተውን ወረርሽኝ ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስተር ጉየን ዡዋን ፑክ "ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በፍጥነትና በትጋት እርምጃ መውሰድ አለብን" በማለት በአገሪቷ ያሉ ግዛቶችና ከተሞችን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቃቸውን የመንግሥት ሚዲያ ዘግቧል። | ቬትናም የመጀመሪያውን የኮቪድ-19 ሞት መዘገበች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በምታደርገው ጥረት የምትመሰገነው እስያዊቷ አገር ቬትናም የመጀመሪያውን የኮቪድ -19 ሞት መዘገበች። ይህም እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ሞት ላልመዘገበችው ቬትናም አሳዛኝ ክስተት ሆኗል። በበሽታው የሞቱት የ70 ዓመቱ ግለሰብ ከሆይ አን ከምትባል ግዛት መሆናቸውንም የአገሪቷ ሚዲያ ዘግቧል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በዳ ናንግ ሪዞርት አቅራቢያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከመመዝገባቸው በፊት ከሦስት ወራት ለሚበልጥ ጊዜ በአገሪቷ አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልነበረም። 95 ሚሊየን ሕዝብ ያላት ቬትናም፤ ወረርሽኙ ከጀመረ አንስቶ እስካሁን 509 በቫይረሱ ተይዘውባታል። ይህም ከሌሎች አገራት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ ቁጥር ነው። በእርግጥ አገሪቷ ከሌሎች አገራት በተለየ ቫይረሱን ለመከላከል እርምጃ መውሰድ የጀመረችው አንድም በቫይረሱ የተያዘ ሰው ሳይኖር ነበር። ድንበሮቿንም ወደ አገራቸው ከሚገቡ ዜጎቿ በስተቀር ለተጓዦች ዝግ ያደረገችው ቀድማ ነበር። ከዚህም ባሻገር ወደ አገሪቷ የሚገባ ማንኛውም ግለሰብ መንግሥት ባዘጋጀው ለይቶ ማቆያ ለ14 ቀናት መቆየትና መመርመር ግድ ነው። እነዚህ የጥንቃቄ እርምጃዎችም ውጤት አሳይተው ከሚያዚያ ወር አጋማሽ ጀምሮ በአገሪቷ አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልነበረም። በዚህ በወቅት በሽታውን ለመቆጣጠር ባደረገችው ጥረት እንዲሁም በቫይረሱ ተይዞ ሁለት ወራትን በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ላሳለፈው ስኮትላንዳዊ አብራሪ ላደረገችው እንክብካቤም አድናቆት ተችሯታል። ይሁን እንጂ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በታዋቂው ዳ ናንግ ሪዞርት አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የመገኘታቸው አሳዛኝ ዜና ተሰምቷል። በዚህ ወቅትም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአገሪቷ ጎብኝዎች በከተማዋ ውስጥ ነበሩ ተብሏል። መንግሥት ረቡዕ ዕለት በከተማዋ ሙሉ ለሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ከመጣሉ በፊትም ከተማዋን ለጎብኝዎች ዝግ አድርጎ ነበር። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በዳ ናንግ የተከሰተውን ወረርሽኝ ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስተር ጉየን ዡዋን ፑክ "ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በፍጥነትና በትጋት እርምጃ መውሰድ አለብን" በማለት በአገሪቷ ያሉ ግዛቶችና ከተሞችን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቃቸውን የመንግሥት ሚዲያ ዘግቧል። | https://www.bbc.com/amharic/53610860 |
2health
| የዝንጀሮ ፈንጣጣ ለኢትዮጵያ ምን ያህል ስጋት ነው? | በአሁኑ ጊዜ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ ቢያንስ በ13 አገራት ከ90 በላይ ሰዎች ላይ መከሰቱ የዓለም ጤና ድርጅት አረጋግጧል። በሽታው በስፋት የታየው በአሜሪካ እና በአውሮፓ አገራት ውስጥ ነው። በንክኪ የሚተላለፈው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ከኮቪድ-19 ጋር ሲነጻጸር የመዛመት ፍጥነቱ ዝቅተኛ ቢሆንም፣ እንደ ዩናይትድ ኪንግድም ያሉ አገራት "ችላ የምንለው አይደለም" ብለው በልዩ ትኩረት እየሰሩ ነው። ለመሆኑ ይህ በሽታ ኢትዮጵያን ያሳስባታል? በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲቲዩት የበሽታዎች ቅኝት እና ምላሽ ዳይሬክተር አቶ መስፍን ወሰን የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ በኢትዮጵያ የመከሰት "ከፍተኛ ዕድል አለው ብለን እናስባለን" ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ዳይሬክተሩ የወርርሽኞች አቅም እና የመተላለፊያ መንገዶቻቸው የበሽታውን አሳሳቢነቱን እንደሚወስኑ ያብራራሉ። "ብዙ አገራትን የሚያዳርሱ በሽታዎች ብዙ ጊዜ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚዛመቱት በትንፋሽ የሚተላለፉት በሽታዎች ናቸው" የሚሉት አቶ መስፍን ቀጥሎ ያለውን ደረጃ የሚይዙት ደግሞ በንክኪ የሚተላለፉት መሆኑናቸውን ጠቁመዋል። በንክኪ የሚተላለፉ በሽታዎች በፍጥነት የመዛመት ዕድላቸው ዝቅ ያለ ነው። "ያ ማለት ግን ከአገር ወደ አገር አይተላለፍም ማለት አይደለም።" እዚህ ጋር የዝንጀሮ ፈንጣጣ በንክኪ እንደሚተላለፍ ልብ በሉ። ዳይሬክተሩ በሽታው እስካሁን በኢትዮጵያ እንዳልተከሰተ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ በታሪክም በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው ተመዝግቦ አያወቅም። ሆኖም በሽታው ከተከሰተባቸው አገራት የሚነሳ ማንኛውም ሰው የዝንጀሮ ፈንጣጣን "በቀላሉ" ወደ ኢትዮጵያ ይዞት ሊመጣ እንደሚችል ነው አቶ መስፍን የሚናገሩት። "የኢትዮጵያ ሁኔታ ከአፍሪካ አገሮች ወደ አውሮፓ እና ከአውሮፓ ወደ አፍሪካ አገራት ብዙ ትራንዚት እና ከፍተኛ የሰዎች ዝውውር ስላለ ከፍተኛ የመከሰት ዕድል አለው... ለሌሎችም አገራት ስጋት እስከሆነ ድረስ ለእኛም ስጋት መሆኑ አይቀርም፤ እኛም እየተንቀሳቀስን ያለነው ለአገራችንም ስጋት ነው ብለን ነው" ብለዋል። አቶ መስፍን ይህ በአሁኑ ጊዜ በአውሮፓ አገራት በስፋት እየታየ ያለው በሽታ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ "በተቻለ መጠን" አስፈላጊውን ተግባር እያከናወኑ መሆናቸውን አመልክተዋል። ራስ ምታት እና ከ35.5 በላይ የሆነ የሰውነት ሙቀት [ትኩሳት] ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ምልክቶች ውስጥ መካከል ይካተታሉ። በዚህም መነሻ በአገሪቱ በሁሉም ዓለምአቀፍ የየብስ እና የአየር በሮች ላይ የሙቀት ልኬት እየተከናወነ ነው። ከሚጠበቀው በላይ የሆነ የሰውነት ሙቀት ያላቸው ሰዎች ለዚሁ ዓላማ ወደተዘጋጁ የለይቶ ማቆያ ማዕከላት ተወስደው ተጨማሪ ምርመራዎች እንደሚደረግላቸው ያነሱት ኃላፊው፣ ለባለሙያዎች ሥልጣና እየተሰጠ እና በሽታው ቢያጋጥም የሚወሰዱ እርማጃዎችን በሚመለከት "የምላሽ መመሪያ" እየተዘጋጀ ነው ብለዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢከሰትስ? አቶ መስፍን እንደሚሉት በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ቢከሰት በሚል መነሻ አስፈላጊ ግብአቶችን የሟሟላት እና አቅም የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። በሁሉም ክልሎች ይህንን በሽታ የሚቆጣጠሩ ግብረ ኃይሎችን ማቋቋም፣ የተያዙ ሰዎችን ጉዳይ ለመከታተል የሚስችሉ ሥርዓቶችን ማጎልበት፣ የፈጣን ምላሽ ቡድን ማዋቀር እና የአቅም ግንባታ ተግባራትን በክልሎች ለማከናወን "የዓለም ጤና ድርጀትን ጨምሮ ከሌሎች አጋሮች ጋር እየሰራን ነው" ሲሉም አክለዋል። ወደ አገሪቱ መግቢያ እና መውጫ በሆኑ በሮች በሚደረጉ ምርመራዎች እስካሁን ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ጋር የተያያዘ አሳሳቢ ሁኔታ አለመከሰቱን ኃላፊው አመላክተዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምንድን ነው? የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ በተሰኘ ቫይረስ የሚከሰተው በሽታው 'ስሞልፎክስ' ተብሎ የሚጠራው የፈንጣጣ ዝርያ ውስጥ የሚካተት ነው። ከሰው ብቻ ሳይሆን ከእንስሳት እና ቫይረሱ ካለባቸው ቁሶች ጋር በሚኖር ንክኪ የሚተላለፈው በሽታው ለምጀመሪያ ጊዜ እንደ አውሮፓውያኑ በ1958 በዝንጀሮ ላይ የተገኘ ነው። በ1978 ደግሞ በዲሞክራቲክ ኮንንጎ በሰው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ መገኘቱ ተረጋግጧል። በገጠራማ የማዕከላዊ እና ምዕራባዊ አፍሪካ አገራት በፋት የሚያጠቃው የዝንጀሮ ፈንጣጣ እጅግ አሳሳቢ የሚባል አይደለም። በሽታውን 85 በመቶ መከላከል እንደሚችል የተረጋገጠ ክትባትም አለው። አንዳንድ ጊዜ ያለምንም ህክምና በራሱ ጊዜ ሊጠፋ የሚችል ነው ። ሆኖም በምዕራብ አፍሪካ በበሽታው ምክንያት ህይወት አልፏል። የበሽታው የሞት ምጣኔ ከ3 እስከ 6 በመቶ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጀት ይፋ ያደረገው መረጃ ያመለክታል። ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የሰውነት እብጠት፣ የጀርባ እና የጡንቻ ህመም ደግሞ የበሽታው ምልክቶች ናቸው። | የዝንጀሮ ፈንጣጣ ለኢትዮጵያ ምን ያህል ስጋት ነው? በአሁኑ ጊዜ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ ቢያንስ በ13 አገራት ከ90 በላይ ሰዎች ላይ መከሰቱ የዓለም ጤና ድርጅት አረጋግጧል። በሽታው በስፋት የታየው በአሜሪካ እና በአውሮፓ አገራት ውስጥ ነው። በንክኪ የሚተላለፈው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ከኮቪድ-19 ጋር ሲነጻጸር የመዛመት ፍጥነቱ ዝቅተኛ ቢሆንም፣ እንደ ዩናይትድ ኪንግድም ያሉ አገራት "ችላ የምንለው አይደለም" ብለው በልዩ ትኩረት እየሰሩ ነው። ለመሆኑ ይህ በሽታ ኢትዮጵያን ያሳስባታል? በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲቲዩት የበሽታዎች ቅኝት እና ምላሽ ዳይሬክተር አቶ መስፍን ወሰን የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ በኢትዮጵያ የመከሰት "ከፍተኛ ዕድል አለው ብለን እናስባለን" ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ዳይሬክተሩ የወርርሽኞች አቅም እና የመተላለፊያ መንገዶቻቸው የበሽታውን አሳሳቢነቱን እንደሚወስኑ ያብራራሉ። "ብዙ አገራትን የሚያዳርሱ በሽታዎች ብዙ ጊዜ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚዛመቱት በትንፋሽ የሚተላለፉት በሽታዎች ናቸው" የሚሉት አቶ መስፍን ቀጥሎ ያለውን ደረጃ የሚይዙት ደግሞ በንክኪ የሚተላለፉት መሆኑናቸውን ጠቁመዋል። በንክኪ የሚተላለፉ በሽታዎች በፍጥነት የመዛመት ዕድላቸው ዝቅ ያለ ነው። "ያ ማለት ግን ከአገር ወደ አገር አይተላለፍም ማለት አይደለም።" እዚህ ጋር የዝንጀሮ ፈንጣጣ በንክኪ እንደሚተላለፍ ልብ በሉ። ዳይሬክተሩ በሽታው እስካሁን በኢትዮጵያ እንዳልተከሰተ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ በታሪክም በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው ተመዝግቦ አያወቅም። ሆኖም በሽታው ከተከሰተባቸው አገራት የሚነሳ ማንኛውም ሰው የዝንጀሮ ፈንጣጣን "በቀላሉ" ወደ ኢትዮጵያ ይዞት ሊመጣ እንደሚችል ነው አቶ መስፍን የሚናገሩት። "የኢትዮጵያ ሁኔታ ከአፍሪካ አገሮች ወደ አውሮፓ እና ከአውሮፓ ወደ አፍሪካ አገራት ብዙ ትራንዚት እና ከፍተኛ የሰዎች ዝውውር ስላለ ከፍተኛ የመከሰት ዕድል አለው... ለሌሎችም አገራት ስጋት እስከሆነ ድረስ ለእኛም ስጋት መሆኑ አይቀርም፤ እኛም እየተንቀሳቀስን ያለነው ለአገራችንም ስጋት ነው ብለን ነው" ብለዋል። አቶ መስፍን ይህ በአሁኑ ጊዜ በአውሮፓ አገራት በስፋት እየታየ ያለው በሽታ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ "በተቻለ መጠን" አስፈላጊውን ተግባር እያከናወኑ መሆናቸውን አመልክተዋል። ራስ ምታት እና ከ35.5 በላይ የሆነ የሰውነት ሙቀት [ትኩሳት] ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ምልክቶች ውስጥ መካከል ይካተታሉ። በዚህም መነሻ በአገሪቱ በሁሉም ዓለምአቀፍ የየብስ እና የአየር በሮች ላይ የሙቀት ልኬት እየተከናወነ ነው። ከሚጠበቀው በላይ የሆነ የሰውነት ሙቀት ያላቸው ሰዎች ለዚሁ ዓላማ ወደተዘጋጁ የለይቶ ማቆያ ማዕከላት ተወስደው ተጨማሪ ምርመራዎች እንደሚደረግላቸው ያነሱት ኃላፊው፣ ለባለሙያዎች ሥልጣና እየተሰጠ እና በሽታው ቢያጋጥም የሚወሰዱ እርማጃዎችን በሚመለከት "የምላሽ መመሪያ" እየተዘጋጀ ነው ብለዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢከሰትስ? አቶ መስፍን እንደሚሉት በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ቢከሰት በሚል መነሻ አስፈላጊ ግብአቶችን የሟሟላት እና አቅም የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። በሁሉም ክልሎች ይህንን በሽታ የሚቆጣጠሩ ግብረ ኃይሎችን ማቋቋም፣ የተያዙ ሰዎችን ጉዳይ ለመከታተል የሚስችሉ ሥርዓቶችን ማጎልበት፣ የፈጣን ምላሽ ቡድን ማዋቀር እና የአቅም ግንባታ ተግባራትን በክልሎች ለማከናወን "የዓለም ጤና ድርጀትን ጨምሮ ከሌሎች አጋሮች ጋር እየሰራን ነው" ሲሉም አክለዋል። ወደ አገሪቱ መግቢያ እና መውጫ በሆኑ በሮች በሚደረጉ ምርመራዎች እስካሁን ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ጋር የተያያዘ አሳሳቢ ሁኔታ አለመከሰቱን ኃላፊው አመላክተዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምንድን ነው? የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ በተሰኘ ቫይረስ የሚከሰተው በሽታው 'ስሞልፎክስ' ተብሎ የሚጠራው የፈንጣጣ ዝርያ ውስጥ የሚካተት ነው። ከሰው ብቻ ሳይሆን ከእንስሳት እና ቫይረሱ ካለባቸው ቁሶች ጋር በሚኖር ንክኪ የሚተላለፈው በሽታው ለምጀመሪያ ጊዜ እንደ አውሮፓውያኑ በ1958 በዝንጀሮ ላይ የተገኘ ነው። በ1978 ደግሞ በዲሞክራቲክ ኮንንጎ በሰው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ መገኘቱ ተረጋግጧል። በገጠራማ የማዕከላዊ እና ምዕራባዊ አፍሪካ አገራት በፋት የሚያጠቃው የዝንጀሮ ፈንጣጣ እጅግ አሳሳቢ የሚባል አይደለም። በሽታውን 85 በመቶ መከላከል እንደሚችል የተረጋገጠ ክትባትም አለው። አንዳንድ ጊዜ ያለምንም ህክምና በራሱ ጊዜ ሊጠፋ የሚችል ነው ። ሆኖም በምዕራብ አፍሪካ በበሽታው ምክንያት ህይወት አልፏል። የበሽታው የሞት ምጣኔ ከ3 እስከ 6 በመቶ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጀት ይፋ ያደረገው መረጃ ያመለክታል። ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የሰውነት እብጠት፣ የጀርባ እና የጡንቻ ህመም ደግሞ የበሽታው ምልክቶች ናቸው። | https://www.bbc.com/amharic/news-61564071 |
3politics
| ቻርለስ የዩናይትድ ኪንግደም ንጉሥ መሆናቸው በይፋ ታወጀ | በሴንት ጄምስ ቤተ መንግሥት በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ቻርለስ ሳልሳዊ የዩናይትድ ኪንግደም ንጉሥ መሆናቸው ታወጀ። ቻርለስ የእናታቸው ንግሥት ኤልዛቤጥ ዳግማዊት ሞትን ተከትሎ ወዲያውኑ ንጉሥ ቢሆኑም፣ታሪካዊ በተባለለት ጉባኤ በይፋ ንጉሥነታቸው ዛሬ ቅዳሜ ተረጋግጧል። ንግሥናውን ባወጀው ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ምንም እንኳን እስካሁን የንግሥቲቱ የቀብር ሥነ ሥርዓት የሚፈጸምበት ዕለት ባይታወቅም፣ ንጉሡ የቀብሩ ዕለት ሥራ ዝግ የሚሆንበት ዕለት እንዲሆን አጽድቀዋል። ይህ ንግሥናው የጸደቀበት ጉባኤ ሥነ ሥርዓት በቴሌቪዥን ተላልፏል። ይህም በታሪክ የመጀመሪያው ነው ተብሏል። በጉባኤው መጀመሪያ ላይ ንጉሡ ያልተገኙ ሲሆን፣ ነገር ግን በሁለተኛው ክፍል ላይ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ የምክር ቤቱ አባላት እና የተለያዩ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ታድመው ነበር። የምክርቤቱ ፀሐፊ የሆኑት ሪቻርድ ቲልብሩክ “እግዚአብሔር ንጉሡን ይጠብቅ” ከማለታቸው በፊት ቻርለስን “ንጉሥ፣ የኮመንዌልዝ የበላይ፣ የእምነት ጠባቂ” በማለት አውጀዋል። በለንደንቤተ መንግሥትውስጥ ባለው አዳራሽ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ታድመው የነበሩት ከፍተኛ ፖለቲከኞች፣ ዳኞች እና ባለሥልጣናት “እግዚአብሔር ንጉሡን ይጠብቅ” ሲሉ በጋራ ተሰምተዋል። ንጉሡምበበኩላቸው “በጣም አሳዛኝ ኃላፊነት” ያሉትን የእናታቸውን ሞት አውጀዋል። ንጉሥቻርለስ “እናንተ፣ አጠቃላይ አገሩ እንዲሁም አጠቃላይ ዓለም ለደረሰብን የማይጠገን ሐዘን ያሳየንን ጥልቅ ርህራሔ አውቃለሁ። ይህም ለእህቴ እና ለወንድሞቼ ታላቅ መጽናኛ ነው” ብለዋል። ንግሥናውየታወጀበት ሥነ ሥርዓት ላይ የቀድሞዎቹን ጠቅላይ ሚኒስትሮች ቦሪስ ጆንሰንን፣ ቴሬሳ ሜይን፣ ዴቪድ ካሜሩንን፣ ጎርደን ብራውንን እና ጆን ሜጀርን ጨምሮ 200 የምክር ቤቱ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል። በኋላምከሴንት ጄምስ ቤተ መንግሥትውጪ ተሰብስቦ የነበረው ሕዝብ በጋራ “እግዚአብሔር ንጉሡን ይጠብቅ” ካሉ በኋላ የአገሪቱ ብሔራዊ መዝሙር ተዘምሯል። ይህ ሥነ ሥርዓት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በቴሌቪዥን ለሕዝብ የተላለፈ ሲሆን፣ይህንንም የወሰኑት ንጉሡ ቻርለስ ሳልሳዊ ናቸው። | ቻርለስ የዩናይትድ ኪንግደም ንጉሥ መሆናቸው በይፋ ታወጀ በሴንት ጄምስ ቤተ መንግሥት በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ቻርለስ ሳልሳዊ የዩናይትድ ኪንግደም ንጉሥ መሆናቸው ታወጀ። ቻርለስ የእናታቸው ንግሥት ኤልዛቤጥ ዳግማዊት ሞትን ተከትሎ ወዲያውኑ ንጉሥ ቢሆኑም፣ታሪካዊ በተባለለት ጉባኤ በይፋ ንጉሥነታቸው ዛሬ ቅዳሜ ተረጋግጧል። ንግሥናውን ባወጀው ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ምንም እንኳን እስካሁን የንግሥቲቱ የቀብር ሥነ ሥርዓት የሚፈጸምበት ዕለት ባይታወቅም፣ ንጉሡ የቀብሩ ዕለት ሥራ ዝግ የሚሆንበት ዕለት እንዲሆን አጽድቀዋል። ይህ ንግሥናው የጸደቀበት ጉባኤ ሥነ ሥርዓት በቴሌቪዥን ተላልፏል። ይህም በታሪክ የመጀመሪያው ነው ተብሏል። በጉባኤው መጀመሪያ ላይ ንጉሡ ያልተገኙ ሲሆን፣ ነገር ግን በሁለተኛው ክፍል ላይ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ የምክር ቤቱ አባላት እና የተለያዩ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ታድመው ነበር። የምክርቤቱ ፀሐፊ የሆኑት ሪቻርድ ቲልብሩክ “እግዚአብሔር ንጉሡን ይጠብቅ” ከማለታቸው በፊት ቻርለስን “ንጉሥ፣ የኮመንዌልዝ የበላይ፣ የእምነት ጠባቂ” በማለት አውጀዋል። በለንደንቤተ መንግሥትውስጥ ባለው አዳራሽ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ታድመው የነበሩት ከፍተኛ ፖለቲከኞች፣ ዳኞች እና ባለሥልጣናት “እግዚአብሔር ንጉሡን ይጠብቅ” ሲሉ በጋራ ተሰምተዋል። ንጉሡምበበኩላቸው “በጣም አሳዛኝ ኃላፊነት” ያሉትን የእናታቸውን ሞት አውጀዋል። ንጉሥቻርለስ “እናንተ፣ አጠቃላይ አገሩ እንዲሁም አጠቃላይ ዓለም ለደረሰብን የማይጠገን ሐዘን ያሳየንን ጥልቅ ርህራሔ አውቃለሁ። ይህም ለእህቴ እና ለወንድሞቼ ታላቅ መጽናኛ ነው” ብለዋል። ንግሥናውየታወጀበት ሥነ ሥርዓት ላይ የቀድሞዎቹን ጠቅላይ ሚኒስትሮች ቦሪስ ጆንሰንን፣ ቴሬሳ ሜይን፣ ዴቪድ ካሜሩንን፣ ጎርደን ብራውንን እና ጆን ሜጀርን ጨምሮ 200 የምክር ቤቱ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል። በኋላምከሴንት ጄምስ ቤተ መንግሥትውጪ ተሰብስቦ የነበረው ሕዝብ በጋራ “እግዚአብሔር ንጉሡን ይጠብቅ” ካሉ በኋላ የአገሪቱ ብሔራዊ መዝሙር ተዘምሯል። ይህ ሥነ ሥርዓት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በቴሌቪዥን ለሕዝብ የተላለፈ ሲሆን፣ይህንንም የወሰኑት ንጉሡ ቻርለስ ሳልሳዊ ናቸው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cqvz3j9w786o |
5sports
| ኮሮናቫይረስ፡ የበርሊን ማራቶን መቼ እንደሚካሄድ አልታወቀም | በአለማችን ከሚካሄዱ ስድስት ታላላቅ የስፖርት ውድድሮች መካከል የሆኑት የበርሊንና የለንደን ማራቶን በተያዘላቸው ጊዜ እንደማይካሄዱ ታወቀ። የበርሊን ማራቶን በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ሴፕቴምበር 27 ቀን 2020 ይካሄዳል ተብሎ የታቀደ ቢሆንም ጀርመን የእንቅስቃሴ ገደቧን እስከ ጥቅምት ወር መጨረሻ ድረስ በማራዘሟ የተነሳ እንደማይካሄድ ታውቋል። የውድድሩ አዘጋጆች በመግለጫቸው በታቀደለት ጊዜ "አይካሄድም" ከማለት ውጭ ለሌላ ጊዜ ይተላለፍ አይተላለፍ የገለፁት ነገር የለም። ቀጣዩን እርምጃ እንደሚያስተባብሩም ጨምረው ገልፀዋል። • ኢትዮጵያን ጨምሮ አስር የዓለም አገራት ከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተደቅኖባቸዋል-የዓለም ምግብ ድርጅት • በሴቶች የሚመሩ አገራት ወረርሽኙን በተሳካ ሁኔታ እንዴት ተቆጣጠሩት? • አሜሪካ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ መስጠት ልታቆም ነው የበርሊኑ ውድድር ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ከለንደኑ ማራቶን በፊት አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ሲሆን በኋላ ላይ ግን የለንደኑ ማራቶን እኤአ ወደ ኦክቶበር 4 ተገፍቷል። የለንደኑ ማራቶን በመጀመሪያ እቅዱ መሰረት በዚህ ሳምንት መጨረሻ ለመካሄድ እቅድ ተይዞ የነበረ ሲሆን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ነው ወደ ሌላ ጊዜ የተላለፈው። የበርሊን ማራቶን አዘጋጆች በቅርብ ጊዜ እንዲካሄድ የሚወስኑ ከሆነ በሕዳር ወር አጋማሽ ሊሆን ይችላል የተባለ ሲሆን በዚያ ወቅትም ግን የኒው ዮርኩ ማራቶን እንደሚካሄድ የወጣው የጊዜ ሰሌዳ ያሳያል። የበርሊን ማራቶን ፈጣን ውድድር ሲሆን ባለፉት አመታት በወንዶች ማራቶን ውድድር ሰባት ጊዜ ክብረ ወሰን ተሻሽሎበታል። እአአ በ2018 ኬንያዊው ኤሉድ ኪፕቾጌ ሁለት ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ከ39 ሰከንድ በመግባት ክብረወሰኑን በእጁ አስገብቷል። ባለፈው አመት ቀነኒሳ በቀለ ሁለተኛው ፈጣን ሰዓት ሆኖ የተመዘገበውን 2:01:41 በመግባት ያሸነፈ ሲሆን በዚህ ዓመት ከኪፕቾጌ ጋር በለንደን ማራቶን ለመፎካከር ቀጠሮ ነበራቸው። ጀርመን ከዩናይትድ ኪንግደም አንጻር አነስተኛ ሰዎች ብቻ ነው የሞቱባት። ጆንስ ሆፕኪንስ ባጠናቀረው መረጃ መሰረት በጀርመን 4,948 ሲሞቱ በዩናይትድ ኪንግደም 17,337 ሞት ተመዝግቧል። በዚህም የተነሳ ጀርመን በከፊል የእንቅስቃሴ ገደቧን አንስታለች። | ኮሮናቫይረስ፡ የበርሊን ማራቶን መቼ እንደሚካሄድ አልታወቀም በአለማችን ከሚካሄዱ ስድስት ታላላቅ የስፖርት ውድድሮች መካከል የሆኑት የበርሊንና የለንደን ማራቶን በተያዘላቸው ጊዜ እንደማይካሄዱ ታወቀ። የበርሊን ማራቶን በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ሴፕቴምበር 27 ቀን 2020 ይካሄዳል ተብሎ የታቀደ ቢሆንም ጀርመን የእንቅስቃሴ ገደቧን እስከ ጥቅምት ወር መጨረሻ ድረስ በማራዘሟ የተነሳ እንደማይካሄድ ታውቋል። የውድድሩ አዘጋጆች በመግለጫቸው በታቀደለት ጊዜ "አይካሄድም" ከማለት ውጭ ለሌላ ጊዜ ይተላለፍ አይተላለፍ የገለፁት ነገር የለም። ቀጣዩን እርምጃ እንደሚያስተባብሩም ጨምረው ገልፀዋል። • ኢትዮጵያን ጨምሮ አስር የዓለም አገራት ከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተደቅኖባቸዋል-የዓለም ምግብ ድርጅት • በሴቶች የሚመሩ አገራት ወረርሽኙን በተሳካ ሁኔታ እንዴት ተቆጣጠሩት? • አሜሪካ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ መስጠት ልታቆም ነው የበርሊኑ ውድድር ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ከለንደኑ ማራቶን በፊት አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ሲሆን በኋላ ላይ ግን የለንደኑ ማራቶን እኤአ ወደ ኦክቶበር 4 ተገፍቷል። የለንደኑ ማራቶን በመጀመሪያ እቅዱ መሰረት በዚህ ሳምንት መጨረሻ ለመካሄድ እቅድ ተይዞ የነበረ ሲሆን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ነው ወደ ሌላ ጊዜ የተላለፈው። የበርሊን ማራቶን አዘጋጆች በቅርብ ጊዜ እንዲካሄድ የሚወስኑ ከሆነ በሕዳር ወር አጋማሽ ሊሆን ይችላል የተባለ ሲሆን በዚያ ወቅትም ግን የኒው ዮርኩ ማራቶን እንደሚካሄድ የወጣው የጊዜ ሰሌዳ ያሳያል። የበርሊን ማራቶን ፈጣን ውድድር ሲሆን ባለፉት አመታት በወንዶች ማራቶን ውድድር ሰባት ጊዜ ክብረ ወሰን ተሻሽሎበታል። እአአ በ2018 ኬንያዊው ኤሉድ ኪፕቾጌ ሁለት ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ከ39 ሰከንድ በመግባት ክብረወሰኑን በእጁ አስገብቷል። ባለፈው አመት ቀነኒሳ በቀለ ሁለተኛው ፈጣን ሰዓት ሆኖ የተመዘገበውን 2:01:41 በመግባት ያሸነፈ ሲሆን በዚህ ዓመት ከኪፕቾጌ ጋር በለንደን ማራቶን ለመፎካከር ቀጠሮ ነበራቸው። ጀርመን ከዩናይትድ ኪንግደም አንጻር አነስተኛ ሰዎች ብቻ ነው የሞቱባት። ጆንስ ሆፕኪንስ ባጠናቀረው መረጃ መሰረት በጀርመን 4,948 ሲሞቱ በዩናይትድ ኪንግደም 17,337 ሞት ተመዝግቧል። በዚህም የተነሳ ጀርመን በከፊል የእንቅስቃሴ ገደቧን አንስታለች። | https://www.bbc.com/amharic/52378021 |
3politics
| የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ በቁም እስር ላይ መሆናቸው እንዳሳሰበው አምነስቲ ገለጸ | የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በቁም እስር ላይ ከአንድ ወር በላይ መቆየታቸው እንዳሳሰበው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገልጸ። ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው አቶ ዳውድ ኢብሳ ምንም አይነት ክስ ሳይቀርብባቸው በቁም አስር ላይ የሚገኙት ከሚያዝያ 25/2013 ዓ.ም ጀምሮ ነው። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አንጋፋ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅት ሲሆን አቶ ዳውድ ኢንብሳም በሊቀመንበርነት ግንባሩን በስደት ለበርካታ ዓመታት ሲመሩ ቆይተው ከሁለት ዓመት በፊት ነበር ወደ አገር ቤት የተመለሱት። በአምንስቲ ኢንተርናሽናል በአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብት አጥኚ የሆኑት አቶ ፍሰሃ ለቢቢሲ እንደገለፁት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚያዚያ ወር ጀምሮ ነው በቁም እስር ላይ የሚገኙት። ሊቀመንበሩ ከቤት መውጣት የተከለከሉት ፖሊስ ካለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መኖሪያቸውን ፈትሾ ኮምፒውተሮችናን የሞባይል ስልኮችን ጨምሮ የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተከትሎ እንደሆነ ተገልጿል። ከዚያ ቀን በኋላ ፖሊስ ማንም ሰው ከቤቱ እንዳይወጣና ወደ ቤቱም እንዳይገባ የከለከለ ሲሆን አሁን በቤቱ ውስጥ ምግብና ሌሎች መሠረታዊ ነገሮች አልቀው ወይም እያለቁ ሊሆኑ ስለሚችሉ አቶ ዳውድ ያሉበት ሁኔታና ደኅንነታቸው አሳሳቢ መሆኑን አምነስቲ አመልክቷል። እንደ አቶ ፍሰሃ ከሆነ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ይህንን መግለጫ ሲያወጣ፣ አቶ ዳውድ ከቤታቸው እንዳይወጡ ሲደረግ በስፍራው የነበሩ ሰዎችን እንዲሁም የፓርቲያቸው አመራሮችን በማናገር መሆኑን ገልፀው፣ በአሁኑ ወቅት በአቶ ዳውድ ዙሪያ የቤት ሠራተኛቸው ብቻ እንደምትገኝ ማጣራታቸውን ገልጸዋል። አስካሁን ባለሥልጣናት በኦነግ ሊቀመንበር ላይ ምንም አይነት ክስ ያላቀረቡ በመሆናቸው በአስቸኳይ ከቁም አስሩ ነጻ እንዲወጡ ጨምሮ ጠይቋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጉዳዩን በማስመልከት ለሠላማ ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ደብዳቤ የጻፈ ሲሆን፤ በዚህም የአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሕግ ውጪ በቁም አስር ላይ ለረጅም ጊዜ መቆየታቸው እንዳሳሰበው አመልክቷል። የኦነግ ቃል አቀባይን ጠቅሶ አምነስቲ እንዳሰፈረው የአቶ ዳውድ እስር እንዲሁ የተከሰተ ሳይሆን ሌሎች የግንባሩ አባላትና መሪዎች ከሕግ ውጪ በመታሰራቸውእንዲሁም በአዲስ አበባና በሌሎች ቦታዎች የሚገኙ ጽህፈት ቤቶቻቸው በመዘጋታቸው በሚቀጥለው ሳምንት ከሚካሄደው ምርጫ መውጣቱን ጠቅሷል። አምነስቲ እንዳለው ባለሥልጣናት ለአቶ ዳውድ ኢብሳ የቁም እስር የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካለማቅረባቸው በተጨማሪ ምክንያቱም ምን እንደሆነ አልተገለጸላቸውም። የአቶ ዳውድ ከሕግ ውጪ በተራዘመ የቁም እስር ላይ መሆናቸው በመንቀሳቀስና በመሰባሰብ ነጻነታቸው ላይ እቀባ እንደተጣለ ተገልጿል። አምነስቲ ጉዳዩን በማስመለከት ለሠላም ሚኒስተሯ ለወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በጻፈው ደብዳቤ ላይ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ በተቀበለችው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ግዴታ መሠረት ሃሳብን የመግለጽና የመደራጀት መብትን እንዲያከብሩና እንዲጠብቁና ጠይቋል። አምነስቲ መንግሥትን አቶ ዳውድ ኢብሳን በአስቸኳይ ከቁም አስሩ እንዲለቅ ወይም የፈጸሙት ጥፋት ካለና በቂ ማስረጃ ካለውም በተገቢው ሁኔታ ክስ እንዲመሰርት ጠይቋል። አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዚህ ቀደምም ለተወሰኑ ቀናት ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡ በጸጥታ ኃይሎች ተከልክለው እንደነበረ መዘገቡ ይታወሳል። በጉዳዩ ላይ የመንግሥት አካላትን ምላሽ ለማግኘት አምንስቲ መሞከሩን የሚናገሩት አቶ ፍሰሃ፣ ምላሽ ማግኘት መቸገራቸውን አብራርተዋል። አቶ ፍሰሃ አክለውም በርካታ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አባላት በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ እንደሚገኙ፣ ፍርድ ቤት ነጻ ያላቸውም ቢሆኑ እስካሁን ድረስ ታስረው እንዳሉ ገልጸዋል። ጨምረውም በአሁኑ ጊዜ የባልደራስ አመራር የሆኑት አቶ እስክንድር እንዲሁም በፖለቲካ ንቁ ታሳታፊ የሆኑ በርካታ ሰዎች መታሰራቸውን እንደሚያውቁ በመጥቀስ "የፖለቲካ አመራሮች በበርካታ ችግሮች ውስጥ እያለፉ እንደሚገኙ" ተናግረዋል። አምንስቲ በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና አመራሮችን የፍርድ ሂደቱ በቅርበት እየተከታተለ እና ማስረጃዎችን በሚገባ እየተመለከተ መሆኑን አክለዋል። | የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ በቁም እስር ላይ መሆናቸው እንዳሳሰበው አምነስቲ ገለጸ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በቁም እስር ላይ ከአንድ ወር በላይ መቆየታቸው እንዳሳሰበው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገልጸ። ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው አቶ ዳውድ ኢብሳ ምንም አይነት ክስ ሳይቀርብባቸው በቁም አስር ላይ የሚገኙት ከሚያዝያ 25/2013 ዓ.ም ጀምሮ ነው። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አንጋፋ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅት ሲሆን አቶ ዳውድ ኢንብሳም በሊቀመንበርነት ግንባሩን በስደት ለበርካታ ዓመታት ሲመሩ ቆይተው ከሁለት ዓመት በፊት ነበር ወደ አገር ቤት የተመለሱት። በአምንስቲ ኢንተርናሽናል በአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብት አጥኚ የሆኑት አቶ ፍሰሃ ለቢቢሲ እንደገለፁት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚያዚያ ወር ጀምሮ ነው በቁም እስር ላይ የሚገኙት። ሊቀመንበሩ ከቤት መውጣት የተከለከሉት ፖሊስ ካለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መኖሪያቸውን ፈትሾ ኮምፒውተሮችናን የሞባይል ስልኮችን ጨምሮ የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተከትሎ እንደሆነ ተገልጿል። ከዚያ ቀን በኋላ ፖሊስ ማንም ሰው ከቤቱ እንዳይወጣና ወደ ቤቱም እንዳይገባ የከለከለ ሲሆን አሁን በቤቱ ውስጥ ምግብና ሌሎች መሠረታዊ ነገሮች አልቀው ወይም እያለቁ ሊሆኑ ስለሚችሉ አቶ ዳውድ ያሉበት ሁኔታና ደኅንነታቸው አሳሳቢ መሆኑን አምነስቲ አመልክቷል። እንደ አቶ ፍሰሃ ከሆነ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ይህንን መግለጫ ሲያወጣ፣ አቶ ዳውድ ከቤታቸው እንዳይወጡ ሲደረግ በስፍራው የነበሩ ሰዎችን እንዲሁም የፓርቲያቸው አመራሮችን በማናገር መሆኑን ገልፀው፣ በአሁኑ ወቅት በአቶ ዳውድ ዙሪያ የቤት ሠራተኛቸው ብቻ እንደምትገኝ ማጣራታቸውን ገልጸዋል። አስካሁን ባለሥልጣናት በኦነግ ሊቀመንበር ላይ ምንም አይነት ክስ ያላቀረቡ በመሆናቸው በአስቸኳይ ከቁም አስሩ ነጻ እንዲወጡ ጨምሮ ጠይቋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጉዳዩን በማስመልከት ለሠላማ ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ደብዳቤ የጻፈ ሲሆን፤ በዚህም የአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሕግ ውጪ በቁም አስር ላይ ለረጅም ጊዜ መቆየታቸው እንዳሳሰበው አመልክቷል። የኦነግ ቃል አቀባይን ጠቅሶ አምነስቲ እንዳሰፈረው የአቶ ዳውድ እስር እንዲሁ የተከሰተ ሳይሆን ሌሎች የግንባሩ አባላትና መሪዎች ከሕግ ውጪ በመታሰራቸውእንዲሁም በአዲስ አበባና በሌሎች ቦታዎች የሚገኙ ጽህፈት ቤቶቻቸው በመዘጋታቸው በሚቀጥለው ሳምንት ከሚካሄደው ምርጫ መውጣቱን ጠቅሷል። አምነስቲ እንዳለው ባለሥልጣናት ለአቶ ዳውድ ኢብሳ የቁም እስር የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካለማቅረባቸው በተጨማሪ ምክንያቱም ምን እንደሆነ አልተገለጸላቸውም። የአቶ ዳውድ ከሕግ ውጪ በተራዘመ የቁም እስር ላይ መሆናቸው በመንቀሳቀስና በመሰባሰብ ነጻነታቸው ላይ እቀባ እንደተጣለ ተገልጿል። አምነስቲ ጉዳዩን በማስመለከት ለሠላም ሚኒስተሯ ለወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በጻፈው ደብዳቤ ላይ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ በተቀበለችው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ግዴታ መሠረት ሃሳብን የመግለጽና የመደራጀት መብትን እንዲያከብሩና እንዲጠብቁና ጠይቋል። አምነስቲ መንግሥትን አቶ ዳውድ ኢብሳን በአስቸኳይ ከቁም አስሩ እንዲለቅ ወይም የፈጸሙት ጥፋት ካለና በቂ ማስረጃ ካለውም በተገቢው ሁኔታ ክስ እንዲመሰርት ጠይቋል። አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዚህ ቀደምም ለተወሰኑ ቀናት ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡ በጸጥታ ኃይሎች ተከልክለው እንደነበረ መዘገቡ ይታወሳል። በጉዳዩ ላይ የመንግሥት አካላትን ምላሽ ለማግኘት አምንስቲ መሞከሩን የሚናገሩት አቶ ፍሰሃ፣ ምላሽ ማግኘት መቸገራቸውን አብራርተዋል። አቶ ፍሰሃ አክለውም በርካታ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አባላት በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ እንደሚገኙ፣ ፍርድ ቤት ነጻ ያላቸውም ቢሆኑ እስካሁን ድረስ ታስረው እንዳሉ ገልጸዋል። ጨምረውም በአሁኑ ጊዜ የባልደራስ አመራር የሆኑት አቶ እስክንድር እንዲሁም በፖለቲካ ንቁ ታሳታፊ የሆኑ በርካታ ሰዎች መታሰራቸውን እንደሚያውቁ በመጥቀስ "የፖለቲካ አመራሮች በበርካታ ችግሮች ውስጥ እያለፉ እንደሚገኙ" ተናግረዋል። አምንስቲ በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና አመራሮችን የፍርድ ሂደቱ በቅርበት እየተከታተለ እና ማስረጃዎችን በሚገባ እየተመለከተ መሆኑን አክለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57473850 |
0business
| "ከ80 ሚሊዮን ሕዝቦቼ በድህነት የሚኖሩት 17ቱ ብቻ ናቸው" የቻይናዋ ግዛት | የቻይናዋ ጂአንግሱ ግዛት ከ80 ሚሊዮን ነዋሪዎቼ በደህነት የሚኖሩት 17 ሰዎች ብቻ ናቸው አለች። የግዛቷ አስተዳዳሪዎች በግዛቷ ውስጥ በዓመት ከ863 ዶላር በታች (26ሺህ ብር ገደማ) የሚያገኙት ሰዎች ቁጥር 17 ብቻ ናቸው ብለዋል። ይህን ማሳካት የተቻለው መንግሥት ሁሉንም ተደራሽ የሚያደርጉ ውጤታማ ሥራዎችን ማከናወን በመቻሉ ነው ተብሏል። በፈረንጆቹ 2019 ማጠናቀቂያ ላይ የተገኙ አሃዞች እንደሚጠቁሙት፤ ባለፉት አራት ዓመታት 2.54 ሚሊዮን የጂአንግሱ ግዛት ነዋሪዎችን ከድህነት አረንቋ ማውጣት ተችሏል። ግዛቷ በፈረንጆቹ 2020 ድህነትን ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ አቅዳ ስትንቀሳቀስ ነበር። አሁንም በድህነት ውስጥ ነው የሚኖሩት የተባሉት 17ቱ ሰዎች፤ ተቀጥሮ ለመስራት የሚያስችል አቅም እንዳላቸው የግዛቷ ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ምንም እንኳን ቻይና ባለፉት ጥቂት አስርተ ዓመታት ኢኮኖሚዋ በፍጥነት ቢያድግም የተፈለገውን ያህል ድህነትን ከመላው ቻይና ማስወገድ አልተቻለም። ይልቁንም በድሆች እና በባለጠጎች መካከል ያለው ልዩነት እጅጉን ሰፍቶ ቆይቷል። በዚህም የቻይና መንግሥት ድህነትን ከቻይና ማራቅ የሚለው ዓላማው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ሆኗል። በቻይና 'ድህነት' ለሚለው ቃል በትክክል የሚያግባባ ትርጓሜ ማግኘት አስቸጋሪ ነው። የቻይና ግዛቶች ለድህነት የሚሰጡት ትርጓሜ እንደየደረጃቸው ይለያያል። በሃገር አቀፍ ደረጃ በዓመት ከ331 ዶላር በታች የሚያገኝ ዜጋ ድሃ ተብሎ ይፈረጃል። እንደ ጂአንግሱ ግዛት ያሉ ደግሞ ነዋሪያቸውን ድሃ የሚሉት በዓመት ከ863 ዶላር በታች የሚያገኝ ከሆነ ነው። | "ከ80 ሚሊዮን ሕዝቦቼ በድህነት የሚኖሩት 17ቱ ብቻ ናቸው" የቻይናዋ ግዛት የቻይናዋ ጂአንግሱ ግዛት ከ80 ሚሊዮን ነዋሪዎቼ በደህነት የሚኖሩት 17 ሰዎች ብቻ ናቸው አለች። የግዛቷ አስተዳዳሪዎች በግዛቷ ውስጥ በዓመት ከ863 ዶላር በታች (26ሺህ ብር ገደማ) የሚያገኙት ሰዎች ቁጥር 17 ብቻ ናቸው ብለዋል። ይህን ማሳካት የተቻለው መንግሥት ሁሉንም ተደራሽ የሚያደርጉ ውጤታማ ሥራዎችን ማከናወን በመቻሉ ነው ተብሏል። በፈረንጆቹ 2019 ማጠናቀቂያ ላይ የተገኙ አሃዞች እንደሚጠቁሙት፤ ባለፉት አራት ዓመታት 2.54 ሚሊዮን የጂአንግሱ ግዛት ነዋሪዎችን ከድህነት አረንቋ ማውጣት ተችሏል። ግዛቷ በፈረንጆቹ 2020 ድህነትን ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ አቅዳ ስትንቀሳቀስ ነበር። አሁንም በድህነት ውስጥ ነው የሚኖሩት የተባሉት 17ቱ ሰዎች፤ ተቀጥሮ ለመስራት የሚያስችል አቅም እንዳላቸው የግዛቷ ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ምንም እንኳን ቻይና ባለፉት ጥቂት አስርተ ዓመታት ኢኮኖሚዋ በፍጥነት ቢያድግም የተፈለገውን ያህል ድህነትን ከመላው ቻይና ማስወገድ አልተቻለም። ይልቁንም በድሆች እና በባለጠጎች መካከል ያለው ልዩነት እጅጉን ሰፍቶ ቆይቷል። በዚህም የቻይና መንግሥት ድህነትን ከቻይና ማራቅ የሚለው ዓላማው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ሆኗል። በቻይና 'ድህነት' ለሚለው ቃል በትክክል የሚያግባባ ትርጓሜ ማግኘት አስቸጋሪ ነው። የቻይና ግዛቶች ለድህነት የሚሰጡት ትርጓሜ እንደየደረጃቸው ይለያያል። በሃገር አቀፍ ደረጃ በዓመት ከ331 ዶላር በታች የሚያገኝ ዜጋ ድሃ ተብሎ ይፈረጃል። እንደ ጂአንግሱ ግዛት ያሉ ደግሞ ነዋሪያቸውን ድሃ የሚሉት በዓመት ከ863 ዶላር በታች የሚያገኝ ከሆነ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-51076677 |
0business
| ሩሲያ በምዕራባውያኑ ፋብሪካ የሶቪየት ኅብረት ዘመን መኪናን መልሳ ማምረት ጀመረች | በዩክሬን ላይ ከተፈጸመው ወረራ በኋላ ተዘግቶ ቆይቶ በኋላ ላይ መንግሥት ቁጥጥር ስር በገባው የቀድሞው የሬኖ መኪና ፋብሪካ የሶቪየት ዘመን ተሽከርካሪን ሩሲያ ማምረት ጀመረች። ምርት የጀመረው የጭነት ተሽከርካሪ አምራቹ “ካማዝ” እንዳስታወቀው የመጀመሪያዎቹ ምርቶቹ በቀጣይ ታኅሣሥ ወር ለሽያጭ ይቀርባሉ። ፋብሪካው ዲዛይናቸው የተሻሻሉ በሶቪት ኅብረት ዘመን በስፋት ይታወቁ የነበሩት “ሞስኮቪች” የተሽከርካሪ አይነትን መልሶ በገበያው ላይ እንዲያንሰራራ እንደሚያደርግ ተነግሯል። የፈረንሳዩ መኪና አምራች ሬኖ ሩሲያን ለቆ የወጣው የዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ ምዕራባውያን ኩባንያዎች በገፍ አገሪቱን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ ነው። ወረራውን ተከትሎ ከሩሲያ ለቀው ከወጡት ታላላቅ ስም ካላቸው የምዕራቡ ዓለም ተቋማት መካከል ማክዶናልድስ እና ስታርባክስ ይጠቀሳሉ። ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ ያጣሏቸው ማዕቀቦች አገሪቱ በዩክሬን ላይ ለከፈተችው ወረራ ምላሽ ሲሆን፣ ከቀሪው ዓለም እንድትነጠል በማድረግ ከውጪ የሚገቡ ግብአቶችን እንዳታገኝ ለማድረግ የታለመ ነው። የመኪና አምራቹ ፋብሪካ የቴክኖሎጂ አጋር ለመሆን ባለፈው ዓመት ሐምሌ ከካማዝ ጋር ስምምነት የፈረመ ሲሆን፣ በተጨማሪም የሩሲያ መንግሥት ከቻይናው የመኪና አምራች ጄኤሲ ጋር እየሰራ መሆኑን ሮይተርስ በስም ካልጠቀሳቸው ምንጮች መረጃ መግኘቱን አመልክቷል። ካማዝ ባወጣው መግለጫ እንዳለው በሂደት ለተሽከርካሪ ምርቱ የሚያስፈልጉትን ግብአቶች ለማግኘት የአገር ውስጥ አቅራቢዎችን በሂደት ለማጠናከር እንደሚያስብ ገልጾ፣ ለጊዜው ምርቱ ውስን ሊሆን እንደሚችል ጠቅሷል። ካማዝ በቀጣይ አንድ ወር ውስጥ 600 የሚደርሱ መኪኖችን አመርታለሁ ብሎ እንደሚጠብቅ ገልጿል። በቀጣይ የፈረንጆች ዓመት ውስጥ ደግሞ የምርቱን መጠን ወደ 100,000 ተሽከርካሪዎች እንዲደርስ የሚያደርግ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል የተወሰኑት በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ይሆናሉ ብሏል። በዩክሬን የሚካሄደው ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በሩሲያ የሚመረተው የተሽከርካሪዎች አጠቃላይ ቁጥር ቀንሷል። በዚህም ሳቢያ የተሽከርካሪዎች ሽያጭ መጠን ከአንድ ሚሊዮን በታች ሊያሽቆለቁል የሚችል ሲሆን፣ ይህም በዘመናዊው የሩሲያ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያጋጥም ዝቅተኛው ሽያጭ እንደሚሆን ሮይተርስ ዘግቧል። | ሩሲያ በምዕራባውያኑ ፋብሪካ የሶቪየት ኅብረት ዘመን መኪናን መልሳ ማምረት ጀመረች በዩክሬን ላይ ከተፈጸመው ወረራ በኋላ ተዘግቶ ቆይቶ በኋላ ላይ መንግሥት ቁጥጥር ስር በገባው የቀድሞው የሬኖ መኪና ፋብሪካ የሶቪየት ዘመን ተሽከርካሪን ሩሲያ ማምረት ጀመረች። ምርት የጀመረው የጭነት ተሽከርካሪ አምራቹ “ካማዝ” እንዳስታወቀው የመጀመሪያዎቹ ምርቶቹ በቀጣይ ታኅሣሥ ወር ለሽያጭ ይቀርባሉ። ፋብሪካው ዲዛይናቸው የተሻሻሉ በሶቪት ኅብረት ዘመን በስፋት ይታወቁ የነበሩት “ሞስኮቪች” የተሽከርካሪ አይነትን መልሶ በገበያው ላይ እንዲያንሰራራ እንደሚያደርግ ተነግሯል። የፈረንሳዩ መኪና አምራች ሬኖ ሩሲያን ለቆ የወጣው የዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ ምዕራባውያን ኩባንያዎች በገፍ አገሪቱን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ ነው። ወረራውን ተከትሎ ከሩሲያ ለቀው ከወጡት ታላላቅ ስም ካላቸው የምዕራቡ ዓለም ተቋማት መካከል ማክዶናልድስ እና ስታርባክስ ይጠቀሳሉ። ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ ያጣሏቸው ማዕቀቦች አገሪቱ በዩክሬን ላይ ለከፈተችው ወረራ ምላሽ ሲሆን፣ ከቀሪው ዓለም እንድትነጠል በማድረግ ከውጪ የሚገቡ ግብአቶችን እንዳታገኝ ለማድረግ የታለመ ነው። የመኪና አምራቹ ፋብሪካ የቴክኖሎጂ አጋር ለመሆን ባለፈው ዓመት ሐምሌ ከካማዝ ጋር ስምምነት የፈረመ ሲሆን፣ በተጨማሪም የሩሲያ መንግሥት ከቻይናው የመኪና አምራች ጄኤሲ ጋር እየሰራ መሆኑን ሮይተርስ በስም ካልጠቀሳቸው ምንጮች መረጃ መግኘቱን አመልክቷል። ካማዝ ባወጣው መግለጫ እንዳለው በሂደት ለተሽከርካሪ ምርቱ የሚያስፈልጉትን ግብአቶች ለማግኘት የአገር ውስጥ አቅራቢዎችን በሂደት ለማጠናከር እንደሚያስብ ገልጾ፣ ለጊዜው ምርቱ ውስን ሊሆን እንደሚችል ጠቅሷል። ካማዝ በቀጣይ አንድ ወር ውስጥ 600 የሚደርሱ መኪኖችን አመርታለሁ ብሎ እንደሚጠብቅ ገልጿል። በቀጣይ የፈረንጆች ዓመት ውስጥ ደግሞ የምርቱን መጠን ወደ 100,000 ተሽከርካሪዎች እንዲደርስ የሚያደርግ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል የተወሰኑት በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ይሆናሉ ብሏል። በዩክሬን የሚካሄደው ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በሩሲያ የሚመረተው የተሽከርካሪዎች አጠቃላይ ቁጥር ቀንሷል። በዚህም ሳቢያ የተሽከርካሪዎች ሽያጭ መጠን ከአንድ ሚሊዮን በታች ሊያሽቆለቁል የሚችል ሲሆን፣ ይህም በዘመናዊው የሩሲያ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያጋጥም ዝቅተኛው ሽያጭ እንደሚሆን ሮይተርስ ዘግቧል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cn0y2dl4vq5o |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ታንዛኒያ 'ክትባቱ ይቅርብኝ ባህላዊ መድሃኒት ይሻለኛል' አለች | ታንዛኒያ ለኮቪድ-19 የተሰሩ ክትባቶችን መጠቀም እንደማትፈልግና በምትኩ አገር በቀል መድሃኒቶች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደምትፈልግ ማስታወቋ ተገለጸ። ከኢስት አፍሪካ ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረጉት የታንዛኒያ የጤና ሚኒስትር ጄራልድ ቻሚ ከውጪ የሚገቡ ክትባቶች ላይ ከድህንነትና ከውጤታማነት አንጻር ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልጸዋል። ሚንስትሩ ክትባቶቹ የተሰሩበት ፍጥነት እንደሚያሳስባቸውም ተናግረዋል። ምንም እንኳን አሁን የተሰሩትና ጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙት ክትባቶች ሁሉንም የደህንነትና ውጤታማነት ዓለማ አቀፍ መመዘኛዎች ቢያልፉም ሚንስትሩ ግን እምብዛም አላሳመነኝም ብለዋል። በሌላ በኩል የታንዛንያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ የኮሮረናቫይረስን በተመለከተ በሚሰጧቸው አስተያየቶችና በሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎች የዓለምን ትኩረት መሳብ የቻሉ መሪ ናቸው። ኮቪድ-19 ታንዛኒያ ሲደርስ ፕሬዚዳንቱ ሰዎች በቤታቸው መቆየት የለባቸውም ብለው አጥብቀው ይከራከሩ ነበር። እንዳውም ቫይረሱ እንዲጠፋ ቤተክርስቲያን እና መስጂድ ሄደው እንዲጸልዩ አበረታትተዋል። ''ኮሮናቫይረስ እርኩስ መንፈስ ነው፤ በክርስቶስ ሰውነት ውስጥ ሊቆይ አይችልም. . . . . ወዲያውኑ ይቃጠላል'' ሲሉም ተደምጠዋል ወግ አጥባቂው ክርስቲያን መሪ ጆን ማጉፉሊ። ፕሬዝዳንቱ ከዚህ በተጨማሪ ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ስለማድረግ በተመለከተ ሲናገሩ ተግባራቱ ምንም ፋይዳ የላቸውም ሲሉም ተደምጠው ነበር። ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ጎረቤት አገራት የእንቅስቃሴ ገደብ መጣላቸውን በመተቸትም እሳቸው ግን በዚህ መልኩ ኢኮኖሚውን መጉዳት እንደማይፈልጉ በተደጋጋሚ ገልጸዋል። እንደውም ወርሃ ሰኔ ላይ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ አገራቸው ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ነጻ መሆኗን አውጀው ነበር። አነጋጋሪው ፕሬዝዳንት እንዳሉት ታንዛኒያ ከወረርሽኙ ነጻ የወጣችው በሕዝቧ ጸሎት መሆኑን ነው እንደ ምክንያት የጠቀሱት። "እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን የኮሮናቫይረስ በሽታ ተጣራርጎ ተወግዷል" ሲሉ ዶዶማ በተባለችው ከተማ ውስጥ በአንድ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው ለነበሩ ምዕመናን ተናግረዋል። ''በአገራችን በርካታ በቫይረስ የሚተላለፉ በሽታዎች አሉ፤ እንደ ኤችአይቪ ኤድስ ያሉትን መጥቀስ ይቻላል። ሁሌም ቢሆን ኢኮኖሚያችን መቅደም አለበት። ኢኮኖሚው እንዲተኛ መፍቀድ የለብንም፤ ሕይወትም መቀጠል አለባት'' ብለው ነበር ፕሬዝዳንቱ። በተጨማሪም ''ሌሎች የአፍሪካ አገራት ኢኮኖሚያቸውን ቸኩለው በመዝጋታቸው ከፍተኛ ችግር ውስጥ ስለሚገቡ በቅርብ ዓመታት ምግብ ከእኛ ለመግዛት መምጣታቸው አይቀርም'' ሲሉም ተደምጠው ነበር። ግንቦት ወር ላይ ደግሞ ታንዛኒያ ከማደጋስካር ያዘዘችውን የኮቪድ-19 'መድሃኒት' ተቀብላ ነበር። በወቅቱ የታንዛኒያው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር መድሃኒቱን ሲቀበሉ የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን በኢንስታግራም ገጻቸው ላይ የለጠፉ ሲሆን በአንዱ ፎቶ ላይ የማደጋስካሩ ሚንስትር ለታንዛኒያው አቻቸው በኮቪድ-19 'መድሃኒት' የተሞላ ካርቶን ሲሰጡ ይታያል። | ኮሮናቫይረስ፡ ታንዛኒያ 'ክትባቱ ይቅርብኝ ባህላዊ መድሃኒት ይሻለኛል' አለች ታንዛኒያ ለኮቪድ-19 የተሰሩ ክትባቶችን መጠቀም እንደማትፈልግና በምትኩ አገር በቀል መድሃኒቶች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደምትፈልግ ማስታወቋ ተገለጸ። ከኢስት አፍሪካ ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረጉት የታንዛኒያ የጤና ሚኒስትር ጄራልድ ቻሚ ከውጪ የሚገቡ ክትባቶች ላይ ከድህንነትና ከውጤታማነት አንጻር ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልጸዋል። ሚንስትሩ ክትባቶቹ የተሰሩበት ፍጥነት እንደሚያሳስባቸውም ተናግረዋል። ምንም እንኳን አሁን የተሰሩትና ጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙት ክትባቶች ሁሉንም የደህንነትና ውጤታማነት ዓለማ አቀፍ መመዘኛዎች ቢያልፉም ሚንስትሩ ግን እምብዛም አላሳመነኝም ብለዋል። በሌላ በኩል የታንዛንያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ የኮሮረናቫይረስን በተመለከተ በሚሰጧቸው አስተያየቶችና በሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎች የዓለምን ትኩረት መሳብ የቻሉ መሪ ናቸው። ኮቪድ-19 ታንዛኒያ ሲደርስ ፕሬዚዳንቱ ሰዎች በቤታቸው መቆየት የለባቸውም ብለው አጥብቀው ይከራከሩ ነበር። እንዳውም ቫይረሱ እንዲጠፋ ቤተክርስቲያን እና መስጂድ ሄደው እንዲጸልዩ አበረታትተዋል። ''ኮሮናቫይረስ እርኩስ መንፈስ ነው፤ በክርስቶስ ሰውነት ውስጥ ሊቆይ አይችልም. . . . . ወዲያውኑ ይቃጠላል'' ሲሉም ተደምጠዋል ወግ አጥባቂው ክርስቲያን መሪ ጆን ማጉፉሊ። ፕሬዝዳንቱ ከዚህ በተጨማሪ ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ስለማድረግ በተመለከተ ሲናገሩ ተግባራቱ ምንም ፋይዳ የላቸውም ሲሉም ተደምጠው ነበር። ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ጎረቤት አገራት የእንቅስቃሴ ገደብ መጣላቸውን በመተቸትም እሳቸው ግን በዚህ መልኩ ኢኮኖሚውን መጉዳት እንደማይፈልጉ በተደጋጋሚ ገልጸዋል። እንደውም ወርሃ ሰኔ ላይ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ አገራቸው ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ነጻ መሆኗን አውጀው ነበር። አነጋጋሪው ፕሬዝዳንት እንዳሉት ታንዛኒያ ከወረርሽኙ ነጻ የወጣችው በሕዝቧ ጸሎት መሆኑን ነው እንደ ምክንያት የጠቀሱት። "እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን የኮሮናቫይረስ በሽታ ተጣራርጎ ተወግዷል" ሲሉ ዶዶማ በተባለችው ከተማ ውስጥ በአንድ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው ለነበሩ ምዕመናን ተናግረዋል። ''በአገራችን በርካታ በቫይረስ የሚተላለፉ በሽታዎች አሉ፤ እንደ ኤችአይቪ ኤድስ ያሉትን መጥቀስ ይቻላል። ሁሌም ቢሆን ኢኮኖሚያችን መቅደም አለበት። ኢኮኖሚው እንዲተኛ መፍቀድ የለብንም፤ ሕይወትም መቀጠል አለባት'' ብለው ነበር ፕሬዝዳንቱ። በተጨማሪም ''ሌሎች የአፍሪካ አገራት ኢኮኖሚያቸውን ቸኩለው በመዝጋታቸው ከፍተኛ ችግር ውስጥ ስለሚገቡ በቅርብ ዓመታት ምግብ ከእኛ ለመግዛት መምጣታቸው አይቀርም'' ሲሉም ተደምጠው ነበር። ግንቦት ወር ላይ ደግሞ ታንዛኒያ ከማደጋስካር ያዘዘችውን የኮቪድ-19 'መድሃኒት' ተቀብላ ነበር። በወቅቱ የታንዛኒያው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር መድሃኒቱን ሲቀበሉ የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን በኢንስታግራም ገጻቸው ላይ የለጠፉ ሲሆን በአንዱ ፎቶ ላይ የማደጋስካሩ ሚንስትር ለታንዛኒያው አቻቸው በኮቪድ-19 'መድሃኒት' የተሞላ ካርቶን ሲሰጡ ይታያል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55346940 |
0business
| ክሪፕቶከረንሲ፡ ኢራን ከመብራት መጥፋት ጋር በተያያዘ ቢትኮይንን ለአራት ወራት አገደች | በከተሞቿ ተደጋጋሚ የመብራት መጥፋት ያጋጠማት ኢራን እንደ ቢትኮይን ያሉ እና ከፍተኛ ኃይል የሚፈልጉ የክሪፕቶከረንሲ ሥርዓቶች ላይ ለአራት ወራት እገዳ መጣሏን አስታውቃለች፡፡ ክሪፕቶከረንሲን ዲጂታል ገንዘብ ወይም መገበያያ ብለን በግርድፉ ልንተረጉመው እንችላለን። ቢትኮይን ከእነዚህ ገንዘቦች መካከል አንዱ ሲሆን አዲስ ቢትኮይን ወደ ገበያ የሚገባበት ሥርዓት ደግሞ ማይኒንግ ይባላል። ፕሬዝዳንት ሀሰን ሩሃኒ በካቢኔያቸው ስብሰባ እንደተናገሩት የመብራቱ መጥፋት ዋነኛ መንስኤ በድርቅ ምክንያት በሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ላይ ተጽዕኖ በመፈጠሩ ነው፡፡ የክሪፕቶከረንሲ ማይኒንግ (85 በመቶው ያልፈቃድ የሚሠራ ነው) በየቀኑ ከ2 ጌጋዋት በላይ ኃይል እየተጠቀመ መሆኑንም ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል፡፡ ከቢትኮይን ማይኒንግ ውስጥ 4.5 በመቶ የሚሆነው በኢራን እንደሚካሄድ ይገመታል። ኢሊፕቲክ እንደተባለው የትንታኔ ኩባንያ ከሆነ ውሳኔው አገሪቱ ማዕቀቦችን እንድታልፍ እና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመግዛት የሚያስችል በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር የክሪፕቶ-ሃብት እንድታገኝ ያስችላታል፡፡ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኑክሌር ስምምነት በመተዉ እአአ በ2018 በጣሉት ማዕቀቦች ምክንያት የኢራን ባንኮች ከዓለም የገንዘብ ሥርዓት ውጭ ሲሆኑ የነዳጅ ሽያጯም እየቀነሰ በመሄዱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እና ገቢ እንዳታገኝ አድርጓታል፡፡ ቢትኮይን እጅግ ከፍተኛ የኮምፒተር ኃይል ስለሚጠይቅ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ይጠቀማል። ኢሊፕቲክ እንደሚለው የኢራን ባለሥልጣናት እ.ኤ.አ. በ2019 ነበር የክሪፕቶከረንሲ ማይኒንግን በይፋ እውቅና የሰጡት። በኋላም በሥራው የሚሳትፉ እንዲለዩ፣ ለኤሌክትሪክ ከፍተኛ ታሪፍ እንዲከፍሉ እና ቢትኮይናቸውን ለኢራን ማዕከላዊ ባንክ እንዲሸጡ የሚያስገድድ የፈቃድ ሥርዓት ይፋ አደረጉ፡፡ ብሔራዊው የኤሌክትሪክ ኩባንያ ቅዳሜ ዕለት እንደገለጸው ፈቃድ የተሰጣቸው የክሪፕቶከረንሲ ማይንኒግ ተቋማት የኃይል መቆራረጥ ችግሩን ለማቃለል ሥራቸውን ቀድሞውኑ በፈቃደኝነት አቁመዋል፡፡ ሩሃኒ ረቡዕ ዕለት እንደተናገሩት ፈቃድ ያልተሰጣቸው ተቋማት ከስድስት እስከ ሰባት እጥፍ የሚበልጥ ኃይል እየተጠቀሙ በመሆኑ እስከ መስከረም 22 ቀን ድረስ ሁሉንም የክሪፕቶከረንሲ እንቅስቃሴዎች ለማገድ ተገደዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም የኢነርጂ ሚንስትሩ ባለፈው ሳምንት በቴህራን እና በሌሎች በርካታ ከተሞች ባልታሰበ ሁኔታ መብራት በመጥፋቱ ኢራናውያንን ይቅርታ መጠየቃቸው ትክክል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ | ክሪፕቶከረንሲ፡ ኢራን ከመብራት መጥፋት ጋር በተያያዘ ቢትኮይንን ለአራት ወራት አገደች በከተሞቿ ተደጋጋሚ የመብራት መጥፋት ያጋጠማት ኢራን እንደ ቢትኮይን ያሉ እና ከፍተኛ ኃይል የሚፈልጉ የክሪፕቶከረንሲ ሥርዓቶች ላይ ለአራት ወራት እገዳ መጣሏን አስታውቃለች፡፡ ክሪፕቶከረንሲን ዲጂታል ገንዘብ ወይም መገበያያ ብለን በግርድፉ ልንተረጉመው እንችላለን። ቢትኮይን ከእነዚህ ገንዘቦች መካከል አንዱ ሲሆን አዲስ ቢትኮይን ወደ ገበያ የሚገባበት ሥርዓት ደግሞ ማይኒንግ ይባላል። ፕሬዝዳንት ሀሰን ሩሃኒ በካቢኔያቸው ስብሰባ እንደተናገሩት የመብራቱ መጥፋት ዋነኛ መንስኤ በድርቅ ምክንያት በሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ላይ ተጽዕኖ በመፈጠሩ ነው፡፡ የክሪፕቶከረንሲ ማይኒንግ (85 በመቶው ያልፈቃድ የሚሠራ ነው) በየቀኑ ከ2 ጌጋዋት በላይ ኃይል እየተጠቀመ መሆኑንም ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል፡፡ ከቢትኮይን ማይኒንግ ውስጥ 4.5 በመቶ የሚሆነው በኢራን እንደሚካሄድ ይገመታል። ኢሊፕቲክ እንደተባለው የትንታኔ ኩባንያ ከሆነ ውሳኔው አገሪቱ ማዕቀቦችን እንድታልፍ እና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመግዛት የሚያስችል በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር የክሪፕቶ-ሃብት እንድታገኝ ያስችላታል፡፡ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኑክሌር ስምምነት በመተዉ እአአ በ2018 በጣሉት ማዕቀቦች ምክንያት የኢራን ባንኮች ከዓለም የገንዘብ ሥርዓት ውጭ ሲሆኑ የነዳጅ ሽያጯም እየቀነሰ በመሄዱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እና ገቢ እንዳታገኝ አድርጓታል፡፡ ቢትኮይን እጅግ ከፍተኛ የኮምፒተር ኃይል ስለሚጠይቅ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ይጠቀማል። ኢሊፕቲክ እንደሚለው የኢራን ባለሥልጣናት እ.ኤ.አ. በ2019 ነበር የክሪፕቶከረንሲ ማይኒንግን በይፋ እውቅና የሰጡት። በኋላም በሥራው የሚሳትፉ እንዲለዩ፣ ለኤሌክትሪክ ከፍተኛ ታሪፍ እንዲከፍሉ እና ቢትኮይናቸውን ለኢራን ማዕከላዊ ባንክ እንዲሸጡ የሚያስገድድ የፈቃድ ሥርዓት ይፋ አደረጉ፡፡ ብሔራዊው የኤሌክትሪክ ኩባንያ ቅዳሜ ዕለት እንደገለጸው ፈቃድ የተሰጣቸው የክሪፕቶከረንሲ ማይንኒግ ተቋማት የኃይል መቆራረጥ ችግሩን ለማቃለል ሥራቸውን ቀድሞውኑ በፈቃደኝነት አቁመዋል፡፡ ሩሃኒ ረቡዕ ዕለት እንደተናገሩት ፈቃድ ያልተሰጣቸው ተቋማት ከስድስት እስከ ሰባት እጥፍ የሚበልጥ ኃይል እየተጠቀሙ በመሆኑ እስከ መስከረም 22 ቀን ድረስ ሁሉንም የክሪፕቶከረንሲ እንቅስቃሴዎች ለማገድ ተገደዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም የኢነርጂ ሚንስትሩ ባለፈው ሳምንት በቴህራን እና በሌሎች በርካታ ከተሞች ባልታሰበ ሁኔታ መብራት በመጥፋቱ ኢራናውያንን ይቅርታ መጠየቃቸው ትክክል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-57230085 |
0business
| የአፍሪካ-ፈረንሳይ ስብሰባ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሦስት አገራት የብድር እፎይታ ሃሳብ በማቅረብ ተጠናቀቀ | ላለፉት ጥቂት ቀናት በፓሪስ ሲካሄድ የቆየው የፈረንሳይ-አፍሪካ ስብሰባ ብድር መክፈል ለተሳናቸው የአፍሪካ አገራት የብድር እፎይታ ሃሳብ በማቅረብ ተጠናቀቀ። የቀረበው ምክረ ሃሳብ ለኢትዮጵያ፣ ቻድ እና ዛምቢያ የብድር እፎይታ እንዲደረገ የሚጠይቅ ሲሆን ይህም ምክረ ሃሳብ በቀጣይ ወር ለጂ7 አገራት ይቀርባል ተብሏል። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ባለጸጋ አገራት ደሃ አገራት የሚጠበቅባቸውን ብድር የሚከፍሉበትን ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ ለማራዘም ተስማምተው ነበር። የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲራዘምላቸው ስምምነት ከተደረሰላቸው አገራት መካከል 40 ያክሉ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት ናቸው። በስብሰባው ላይ ከ20 በላይ የአፍሪካ አገራት መሪዎች፣ የአውሮፓ አገራት መንግሥታት፣ የአውሮፓ ሕብረት ልዑካን እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ (አይኤምኤፍ) ዳይሬክተር ተሳታፊ ሆነዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በስብሰባው መጠናቀቂያ ላይ የስብሰባው ተሳታፊዎች በኮቪድ-19 የተጎዳውን የአፍሪካ አገራት ኢኮኖሚ መልሶ እንዲያንሰራራ ተጨማሪ 100 ቢሊዮን ዶላር ለማፈላለግ ተስማምተዋል ስለማለታቸው ኤፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። ከዚህ መካከል አይኤምኤፍ የአፍሪካ አገራት ምርት ወደ አገራቸው እንዲያስገቡ እንዲረዳቸው 33 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ያደርጋል ተብሏል። ይህ ድጋፍ አገራቱ ባላቸው ሃብት ላይ ትኩረት በማድረግ በኮሮናቫይረስ ስርጭት ምክንያት የተጎዳ ምጣኔ ሃብታቸው እንዲያንሰራራ ትኩረት እንዲያደርጉ ያስችላል ተብሏል። ይህ የፈረንሳይ-አፍሪካ ውይይት የአፍሪካ አገራት የኮቪድ-19 ክትባት ስለሚያገኙበት አማራጭ ላይም መወያየቱን ሬውተርስ ዘግቧል። እንደ ኤፒ ዘገባ ከሆነ የውይይቱ ተሳታፊዎች የአፍሪካ አገራት ለዜጎቻቸው የኮቪድ-19 ክትባቶችን በራሳቸው በስፋት ማምረት እንዲቻላቸው ከአእምሮ መብት ጥበቃ ጋር የተያያዙ ክልከላዎች መላላት አለባቸው በሚል ተስማምተዋል ብለዋል ማክሮን። "የአፍሪካ አዲስ ስምምነት" የሚል መጠሪያ የሰጡት የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ የአፍሪካ አገራትን ለመደገፍ 100 ቢሊዮን ዶላር በቂ አለመሆኑን ገልጸው፤ "በቀጣይ ዋነኛ ሥራችን የሚሆነው ሌሎች አገራት እንደ ፈረንሳይ ተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ ማግባባት ነው፤ ይህም ከዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ይጀምራል" ብለዋል። የአይኤምኤፍ ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጂኦርጂቫ አይኤምኤፍ ተጨማሪ 33 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያቀርብ ይፋ አድርገው፤ ከኮሮናቫይረስ ስርጭት በኋላ የአፍሪካ አገራት እንደተቀረው ዓለም በፍጥነት ከገቡበት የምጣኔ ሃብት አጣብቂኝ ፈጥነው መውጣት አለመቻላቸው አሳሳቢ ነው ብለዋል። የተቀረው ዓለም በአማካይ የምጣኔ ሃብት እድገታቸው 6 በመቶ ሲሆን በአፍሪካ አገራት ግን የምጣኔ ሃብት እድገቱ 3.2 በመቶ ብቻ መሆኑን ዳይሬከተሯ ገልጸዋል። | የአፍሪካ-ፈረንሳይ ስብሰባ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሦስት አገራት የብድር እፎይታ ሃሳብ በማቅረብ ተጠናቀቀ ላለፉት ጥቂት ቀናት በፓሪስ ሲካሄድ የቆየው የፈረንሳይ-አፍሪካ ስብሰባ ብድር መክፈል ለተሳናቸው የአፍሪካ አገራት የብድር እፎይታ ሃሳብ በማቅረብ ተጠናቀቀ። የቀረበው ምክረ ሃሳብ ለኢትዮጵያ፣ ቻድ እና ዛምቢያ የብድር እፎይታ እንዲደረገ የሚጠይቅ ሲሆን ይህም ምክረ ሃሳብ በቀጣይ ወር ለጂ7 አገራት ይቀርባል ተብሏል። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ባለጸጋ አገራት ደሃ አገራት የሚጠበቅባቸውን ብድር የሚከፍሉበትን ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ ለማራዘም ተስማምተው ነበር። የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲራዘምላቸው ስምምነት ከተደረሰላቸው አገራት መካከል 40 ያክሉ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት ናቸው። በስብሰባው ላይ ከ20 በላይ የአፍሪካ አገራት መሪዎች፣ የአውሮፓ አገራት መንግሥታት፣ የአውሮፓ ሕብረት ልዑካን እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ (አይኤምኤፍ) ዳይሬክተር ተሳታፊ ሆነዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በስብሰባው መጠናቀቂያ ላይ የስብሰባው ተሳታፊዎች በኮቪድ-19 የተጎዳውን የአፍሪካ አገራት ኢኮኖሚ መልሶ እንዲያንሰራራ ተጨማሪ 100 ቢሊዮን ዶላር ለማፈላለግ ተስማምተዋል ስለማለታቸው ኤፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። ከዚህ መካከል አይኤምኤፍ የአፍሪካ አገራት ምርት ወደ አገራቸው እንዲያስገቡ እንዲረዳቸው 33 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ያደርጋል ተብሏል። ይህ ድጋፍ አገራቱ ባላቸው ሃብት ላይ ትኩረት በማድረግ በኮሮናቫይረስ ስርጭት ምክንያት የተጎዳ ምጣኔ ሃብታቸው እንዲያንሰራራ ትኩረት እንዲያደርጉ ያስችላል ተብሏል። ይህ የፈረንሳይ-አፍሪካ ውይይት የአፍሪካ አገራት የኮቪድ-19 ክትባት ስለሚያገኙበት አማራጭ ላይም መወያየቱን ሬውተርስ ዘግቧል። እንደ ኤፒ ዘገባ ከሆነ የውይይቱ ተሳታፊዎች የአፍሪካ አገራት ለዜጎቻቸው የኮቪድ-19 ክትባቶችን በራሳቸው በስፋት ማምረት እንዲቻላቸው ከአእምሮ መብት ጥበቃ ጋር የተያያዙ ክልከላዎች መላላት አለባቸው በሚል ተስማምተዋል ብለዋል ማክሮን። "የአፍሪካ አዲስ ስምምነት" የሚል መጠሪያ የሰጡት የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ የአፍሪካ አገራትን ለመደገፍ 100 ቢሊዮን ዶላር በቂ አለመሆኑን ገልጸው፤ "በቀጣይ ዋነኛ ሥራችን የሚሆነው ሌሎች አገራት እንደ ፈረንሳይ ተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ ማግባባት ነው፤ ይህም ከዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ይጀምራል" ብለዋል። የአይኤምኤፍ ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጂኦርጂቫ አይኤምኤፍ ተጨማሪ 33 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያቀርብ ይፋ አድርገው፤ ከኮሮናቫይረስ ስርጭት በኋላ የአፍሪካ አገራት እንደተቀረው ዓለም በፍጥነት ከገቡበት የምጣኔ ሃብት አጣብቂኝ ፈጥነው መውጣት አለመቻላቸው አሳሳቢ ነው ብለዋል። የተቀረው ዓለም በአማካይ የምጣኔ ሃብት እድገታቸው 6 በመቶ ሲሆን በአፍሪካ አገራት ግን የምጣኔ ሃብት እድገቱ 3.2 በመቶ ብቻ መሆኑን ዳይሬከተሯ ገልጸዋል። | https://www.bbc.com/amharic/57173549 |
3politics
| በኦሮሚያ ክልል ወረ ጃርሶ ወረዳ በርካታ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸው ተነገረ | በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረ ጃርሶ ወረዳ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በርካታ ሰዎችን መግደላቸውን እና ቤተሰቦች አስክሬን ተከልክለው ቀብር መፈጸም አለመቻላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የሟች ቤተሰቦች እና ነዋሪዎች ማክሰኞ ሚያዚያ 25/2014 ዓ.ም. 18 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል። የወረዳው አስተዳዳሪ በበኩላቸው የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ18 ያነሰ እና "ከጠላት ጋር የነበሩ ናቸው" ብለዋል። የክልሉ አስተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ስለ ክስተቱ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለቢቢሲ ገልጸዋል። የክልሉ መንግሥት 'ኦነግ ሸኔን የማጽዳት ዘመቻ ጀምሪያለሁ' ካለ በኋላ ባለፉት ሳምንታት ሰላማዊ ሰዎች በተለያዩ ቦታዎች መገደላቸው በስፋት እየተነገረ ነው። የሆነው ምንድነው? ነዋሪዎች እንደሚሉት ማክሰኞ ሚያዚያ 25/2014 ዓ.ም. በወረ ጃርሶ ወረዳ አዋሮ ጎልጄ ቀበሌ በዳዳ ገብርኤል ተብሎ በሚጠራ ስፍራ 18 ሰዎች ተገድለዋል። ሰዎቹ ከመገደላቸው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ማለትም ሰኞ ሚያዚያ 24/2014 ዓ.ም. ጠዋት ላይ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ወደ ወረዳዋ መምጣታቸውን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ። ልጃቸው በፀጥታ ኃይሎች እንደተገደለባቸው የሚናገሩት ስማቸውን የማንጠቅሰው አባት፤ "[ሰኞ] ጠዋት በግምት 12፡15 ላይ ከብቶች አውጥተን ቆመን ነበር። 'ኑ' ብለው ጠሩን [የፀጥታ ኃይሎች] ከዚያ 'ትክክለኛ ሸኔ አሁን አገኘን' ብለው ልጄን ያዙት። ወዲያው ኮቱን አስወልቀው እጁን ወደ ኋላ አሰሩት" ይላሉ። በቀጣይ ቀን ማክሰኞች ሚያዚያ 25 በመንግሥት ኃይሎች የተያዘባቸውን ልጃቸውን ለመጠየቅ ልብስ እና ምግብ ይዘው የመንግሥት ኃይሎች ወዳሉበት ካምፕ መሄዳቸውን እኚህ አባት ይናገራሉ። ". . . ሕግ ነው ያሰረው ብዬ ማክሰኞ ምግብ እና ልብስ ይዤ ልጄን ልጠይቀው ወደ ካምፕ ሄድኩ" ይላሉ። ይሁን እንጂ ልጃቸውን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ማክሰኞ ንጋት 11 ሰዓት ላይ መገደላቸውን ዋሻ ሚካኤል ጸበል ለመጠመቅ ከሚሄዱ ሰዎች መስማታቸውን ይናገራሉ። "መንግሥት የማያውቃቸውን ልጆቻችንን ጨረሰብን" በማለት ልጃቸው ከሕግ ፊት ሳይቀርብ መገደሉን ይናገራሉ። ልጃቸው የታጣቂ ቡድኑ አባል ወይም ከታጣቂ ቡድኑ ጋር አንዳች ግንኙነት እንዳለው የተጠየቁት አባት፤ "በጭረሽ" ሲሉ መልሰዋል። "ከእነሱ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። ከአጠገቤ ተለይቶ አያውቅም። ከሰው ጋር ተጣልቼ እጄ ተሰብሮ ከ10ኛ ክፍል አቋርጦ እኔ ለመርዳት ወደ እርሻ ተመልሶ ነበር" በማለት ይናገራሉ። 'ሦስት ዘመዶቼ ናቸው የተገሉብኝ' ሌላኛው ቢቢሲ ያነጋገረው ነዋሪ ደግሞ ወንድሙ እና ሁለት የአጎቱ ልጆች በዕለቱ መገደላቸውን ይናገራል። ሁለቱ በ20ዎቹ የእድሜ ክልሎች ውስጥ ሲገኙ ሦስተኛው ደግሞ ዕድሜው 20 መሆኑን ያስረዳል። ይህ ነዋሪ ከተገደሉት ሦስቱ መካከል ሁለቱ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ዲያቆኖች መሆናቸውን አንዱ ደግሞ ለፋሲካ በዓል ከአዲስ አበባ ወደ ከተማ የሄደ መሆኑን በመናገር ከታጣቂ ቡድኑ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የላቸውም ይላል። ሦስቱ ወጣቶች ሰኞ ተይዘው ማክሰኞ መገዳላቸውንም ይናገራል። ቢቢሲ ያነጋገረው ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ በዕለቱ ከተገደሉት 18 ሰዎች መካከል 14ቱ ከእነርሱ ጎጥ መሆናቸውን ጠቅሰው "ከእኛው አካባቢ ነው ይዘዋቸው የሄዱት። እስር ቤት ያስገቧቸዋል ብለን ስንጠብቅ ገደሏቸው። እስካሁን አልተቀበሩም" ይላሉ ነዋሪው። ይህ ነዋሪ ከሟቾች መካከል የቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ ዲያቆኖች፣ በጉልበት ሥራ የሚተዳደሩ እና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደሚገኙበት ይናገራሉ። ቢቢሲ ያነጋገራቸውን የሟች ቤተሰቦችና ዘመዶች ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸውን አይጠቅስም። ከላይ ያለው ምስልን ያጋረው 'የወረ ጃርሶ ወረዳ ብልጽግና' የፌስቡክ ገጽ ሲሆን፣ ከተለየ አቅጣጫ የተነሳ ተመሳሳይ ምስልም በወረዳው ኮሚኒኬሽን አማካይነት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተጋርቷል። ቢቢሲ ከሟች ቤተሰቦች እንደተረዳው በዚህ ምስል ላይ ከሚታዩት ሰዎች መካከል ቢያንስ ሁለቱ በፀጥታ ኃይሎች በተወሰደባቸው እርምጃ ከተገደሉት ውስጥ ናቸው። ቢቢሲ ዛሬ አርብ ሚያዚያ 28/2014 ዓ.ም. ረፋድ ላይ የቤተሰብ አባላትን መልሶ ያነጋገረ ሲሆን፤ ማክሰኞ ሚያዚያ 25/2014 ዓ.ም. ንጋት ላይ የተገደሉት ሰዎች አስክሬን እስካሁን አልተነሳም። "አስክሬን ስጡን ስንላቸው 'እናተም መጨመር ፈላጋችሁ' አሉን። . . . አውሬ እና አእዋፍ እየበላው ነው (አስክሬኑን)። ምን እናደርግ? አስክሬን ሰጥተውን ከመቅበር ውጪ ሌላ ምን እንፈልጋለን?" ሲሉ ልጃቸው የተገደለባቸው አባት ይናገራሉ። የመንግሥት ምላሽ ከግድያው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ሰኞ ሚያዚያ 24/2014 ዓ.ም. የወረ ጃርሶ ወረዳ ኮሚኒኬሽን በፌስቡክ ገጹ "የኦነግ-ሸኔ አባላት" ናቸው ያላቸው 18 ሰዎች መያዛቸውን ገልጾ ከዚህ በላይ ያለውን ምስል አጋርቷል። የወረ ጃርሶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አየለ መንግሥቱ ትናንት ሐሙስ እንደተናገሩት የተገደሉት "ከጠላት ጋር የነበሩ ናቸው" ብለዋል። "አብዛኛዎቹ የተያዙት ከጠላት ጋር የነበሩት ናቸው። ከዚያ ውጭ ደግሞ ማን አለበት የሚለውን እያጣራን ነው። ከአገር መከላከያ ጋር እያጣራን ነው" ሲሉ መልሰዋል። የሕዝብ ጥያቄን ተከትሎ የመንግሥት ፀጥታ ኃይል በወረዳው ተሰማርቶ "የማጽዳት ሥራ እየሰራ ነውም" ብለዋል። "የፀጥታ ችግር ባለበት አካባቢ ንጹሃን ሰዎች ሊጎዱ ስለሚችሉ" ከተገደሉት ሰዎች መካከል ንጹሃን ሰዎች ስለመኖራቸው እየተመረመረ ነው ብለዋል። አቶ አየለ፤ "18 አይደርሱም [የተገደሉት ሰዎች ቁጥር] ግን የተገደሉ ሰዎች አሉ" በማለት ተናግረዋል። ቢቢሲ ተጨማሪም ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ክልሉ የአስተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ስልክ ደውሎ ነበር። ኮሎኔል አበበ ስለጉዳዩ "አላውቀም" ሲሉ አጭር ምላሸ ሰጥተዋል። መሰል ድርጊት ከእርሳቸው እውቅና ውጪ ሊፈጸም እንደሚችል ቢቢሲ ላቀረበላቸው ጥያቄ፤ "እኔ እንደዚህ አይነት ትዕዛዝ አልሰጠሁም፤ አላውቀም" ሲሉ መልሰዋል። "ሸኔን የማጽዳት ዘመቻ" ከሰሞኑ መንግሥት 'ሸኔ' ብሎ የሚጠራውን ታጣቂ ቡድን "የማጽዳት ዘመቻ" ጀምሬያለሁ ካለ በኋላ በሁለቱ አካላት መካከል የሚደረገው ግጭት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ይህን ተከትሎ ባለፉት ሳምንታት በተለይ በምዕራብ ሸዋ ዞን በሚገኙ አካባቢዎች በርካታ ሰዎች ስለመገደላቸው በስፋት ተዘግቧል። ከእነዚህ መካከል አርብ ሚያዚያ 21/2014 ዓ.ም. ምዕራብ ሸዋ ዞን አደአ በርጋ ወረዳ የተገደሉት ሰዎች ይገኙበታል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በዕለቱ ከ20 የማያንሱ ነዋሪዎች በወረዳው ጂማታ ተብላ በምትጠራ ቦታ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት መገደላቸውን ተናግረው ነበር። ይህ ግድያ የተከሰተው በክልሉ ልዩ ኃይል አባላት ላይ በአካባቢው የነበሩ ታጠቂዎች ጥቃት ሰንዝረው ግድያ ከፈጸሙ በኋላ መሆኑንም ነዋሪዎች ገልጸዋል። | በኦሮሚያ ክልል ወረ ጃርሶ ወረዳ በርካታ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸው ተነገረ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረ ጃርሶ ወረዳ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በርካታ ሰዎችን መግደላቸውን እና ቤተሰቦች አስክሬን ተከልክለው ቀብር መፈጸም አለመቻላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የሟች ቤተሰቦች እና ነዋሪዎች ማክሰኞ ሚያዚያ 25/2014 ዓ.ም. 18 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል። የወረዳው አስተዳዳሪ በበኩላቸው የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ18 ያነሰ እና "ከጠላት ጋር የነበሩ ናቸው" ብለዋል። የክልሉ አስተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ስለ ክስተቱ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለቢቢሲ ገልጸዋል። የክልሉ መንግሥት 'ኦነግ ሸኔን የማጽዳት ዘመቻ ጀምሪያለሁ' ካለ በኋላ ባለፉት ሳምንታት ሰላማዊ ሰዎች በተለያዩ ቦታዎች መገደላቸው በስፋት እየተነገረ ነው። የሆነው ምንድነው? ነዋሪዎች እንደሚሉት ማክሰኞ ሚያዚያ 25/2014 ዓ.ም. በወረ ጃርሶ ወረዳ አዋሮ ጎልጄ ቀበሌ በዳዳ ገብርኤል ተብሎ በሚጠራ ስፍራ 18 ሰዎች ተገድለዋል። ሰዎቹ ከመገደላቸው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ማለትም ሰኞ ሚያዚያ 24/2014 ዓ.ም. ጠዋት ላይ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ወደ ወረዳዋ መምጣታቸውን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ። ልጃቸው በፀጥታ ኃይሎች እንደተገደለባቸው የሚናገሩት ስማቸውን የማንጠቅሰው አባት፤ "[ሰኞ] ጠዋት በግምት 12፡15 ላይ ከብቶች አውጥተን ቆመን ነበር። 'ኑ' ብለው ጠሩን [የፀጥታ ኃይሎች] ከዚያ 'ትክክለኛ ሸኔ አሁን አገኘን' ብለው ልጄን ያዙት። ወዲያው ኮቱን አስወልቀው እጁን ወደ ኋላ አሰሩት" ይላሉ። በቀጣይ ቀን ማክሰኞች ሚያዚያ 25 በመንግሥት ኃይሎች የተያዘባቸውን ልጃቸውን ለመጠየቅ ልብስ እና ምግብ ይዘው የመንግሥት ኃይሎች ወዳሉበት ካምፕ መሄዳቸውን እኚህ አባት ይናገራሉ። ". . . ሕግ ነው ያሰረው ብዬ ማክሰኞ ምግብ እና ልብስ ይዤ ልጄን ልጠይቀው ወደ ካምፕ ሄድኩ" ይላሉ። ይሁን እንጂ ልጃቸውን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ማክሰኞ ንጋት 11 ሰዓት ላይ መገደላቸውን ዋሻ ሚካኤል ጸበል ለመጠመቅ ከሚሄዱ ሰዎች መስማታቸውን ይናገራሉ። "መንግሥት የማያውቃቸውን ልጆቻችንን ጨረሰብን" በማለት ልጃቸው ከሕግ ፊት ሳይቀርብ መገደሉን ይናገራሉ። ልጃቸው የታጣቂ ቡድኑ አባል ወይም ከታጣቂ ቡድኑ ጋር አንዳች ግንኙነት እንዳለው የተጠየቁት አባት፤ "በጭረሽ" ሲሉ መልሰዋል። "ከእነሱ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። ከአጠገቤ ተለይቶ አያውቅም። ከሰው ጋር ተጣልቼ እጄ ተሰብሮ ከ10ኛ ክፍል አቋርጦ እኔ ለመርዳት ወደ እርሻ ተመልሶ ነበር" በማለት ይናገራሉ። 'ሦስት ዘመዶቼ ናቸው የተገሉብኝ' ሌላኛው ቢቢሲ ያነጋገረው ነዋሪ ደግሞ ወንድሙ እና ሁለት የአጎቱ ልጆች በዕለቱ መገደላቸውን ይናገራል። ሁለቱ በ20ዎቹ የእድሜ ክልሎች ውስጥ ሲገኙ ሦስተኛው ደግሞ ዕድሜው 20 መሆኑን ያስረዳል። ይህ ነዋሪ ከተገደሉት ሦስቱ መካከል ሁለቱ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ዲያቆኖች መሆናቸውን አንዱ ደግሞ ለፋሲካ በዓል ከአዲስ አበባ ወደ ከተማ የሄደ መሆኑን በመናገር ከታጣቂ ቡድኑ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የላቸውም ይላል። ሦስቱ ወጣቶች ሰኞ ተይዘው ማክሰኞ መገዳላቸውንም ይናገራል። ቢቢሲ ያነጋገረው ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ በዕለቱ ከተገደሉት 18 ሰዎች መካከል 14ቱ ከእነርሱ ጎጥ መሆናቸውን ጠቅሰው "ከእኛው አካባቢ ነው ይዘዋቸው የሄዱት። እስር ቤት ያስገቧቸዋል ብለን ስንጠብቅ ገደሏቸው። እስካሁን አልተቀበሩም" ይላሉ ነዋሪው። ይህ ነዋሪ ከሟቾች መካከል የቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ ዲያቆኖች፣ በጉልበት ሥራ የሚተዳደሩ እና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደሚገኙበት ይናገራሉ። ቢቢሲ ያነጋገራቸውን የሟች ቤተሰቦችና ዘመዶች ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸውን አይጠቅስም። ከላይ ያለው ምስልን ያጋረው 'የወረ ጃርሶ ወረዳ ብልጽግና' የፌስቡክ ገጽ ሲሆን፣ ከተለየ አቅጣጫ የተነሳ ተመሳሳይ ምስልም በወረዳው ኮሚኒኬሽን አማካይነት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተጋርቷል። ቢቢሲ ከሟች ቤተሰቦች እንደተረዳው በዚህ ምስል ላይ ከሚታዩት ሰዎች መካከል ቢያንስ ሁለቱ በፀጥታ ኃይሎች በተወሰደባቸው እርምጃ ከተገደሉት ውስጥ ናቸው። ቢቢሲ ዛሬ አርብ ሚያዚያ 28/2014 ዓ.ም. ረፋድ ላይ የቤተሰብ አባላትን መልሶ ያነጋገረ ሲሆን፤ ማክሰኞ ሚያዚያ 25/2014 ዓ.ም. ንጋት ላይ የተገደሉት ሰዎች አስክሬን እስካሁን አልተነሳም። "አስክሬን ስጡን ስንላቸው 'እናተም መጨመር ፈላጋችሁ' አሉን። . . . አውሬ እና አእዋፍ እየበላው ነው (አስክሬኑን)። ምን እናደርግ? አስክሬን ሰጥተውን ከመቅበር ውጪ ሌላ ምን እንፈልጋለን?" ሲሉ ልጃቸው የተገደለባቸው አባት ይናገራሉ። የመንግሥት ምላሽ ከግድያው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ሰኞ ሚያዚያ 24/2014 ዓ.ም. የወረ ጃርሶ ወረዳ ኮሚኒኬሽን በፌስቡክ ገጹ "የኦነግ-ሸኔ አባላት" ናቸው ያላቸው 18 ሰዎች መያዛቸውን ገልጾ ከዚህ በላይ ያለውን ምስል አጋርቷል። የወረ ጃርሶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አየለ መንግሥቱ ትናንት ሐሙስ እንደተናገሩት የተገደሉት "ከጠላት ጋር የነበሩ ናቸው" ብለዋል። "አብዛኛዎቹ የተያዙት ከጠላት ጋር የነበሩት ናቸው። ከዚያ ውጭ ደግሞ ማን አለበት የሚለውን እያጣራን ነው። ከአገር መከላከያ ጋር እያጣራን ነው" ሲሉ መልሰዋል። የሕዝብ ጥያቄን ተከትሎ የመንግሥት ፀጥታ ኃይል በወረዳው ተሰማርቶ "የማጽዳት ሥራ እየሰራ ነውም" ብለዋል። "የፀጥታ ችግር ባለበት አካባቢ ንጹሃን ሰዎች ሊጎዱ ስለሚችሉ" ከተገደሉት ሰዎች መካከል ንጹሃን ሰዎች ስለመኖራቸው እየተመረመረ ነው ብለዋል። አቶ አየለ፤ "18 አይደርሱም [የተገደሉት ሰዎች ቁጥር] ግን የተገደሉ ሰዎች አሉ" በማለት ተናግረዋል። ቢቢሲ ተጨማሪም ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ክልሉ የአስተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ስልክ ደውሎ ነበር። ኮሎኔል አበበ ስለጉዳዩ "አላውቀም" ሲሉ አጭር ምላሸ ሰጥተዋል። መሰል ድርጊት ከእርሳቸው እውቅና ውጪ ሊፈጸም እንደሚችል ቢቢሲ ላቀረበላቸው ጥያቄ፤ "እኔ እንደዚህ አይነት ትዕዛዝ አልሰጠሁም፤ አላውቀም" ሲሉ መልሰዋል። "ሸኔን የማጽዳት ዘመቻ" ከሰሞኑ መንግሥት 'ሸኔ' ብሎ የሚጠራውን ታጣቂ ቡድን "የማጽዳት ዘመቻ" ጀምሬያለሁ ካለ በኋላ በሁለቱ አካላት መካከል የሚደረገው ግጭት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ይህን ተከትሎ ባለፉት ሳምንታት በተለይ በምዕራብ ሸዋ ዞን በሚገኙ አካባቢዎች በርካታ ሰዎች ስለመገደላቸው በስፋት ተዘግቧል። ከእነዚህ መካከል አርብ ሚያዚያ 21/2014 ዓ.ም. ምዕራብ ሸዋ ዞን አደአ በርጋ ወረዳ የተገደሉት ሰዎች ይገኙበታል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በዕለቱ ከ20 የማያንሱ ነዋሪዎች በወረዳው ጂማታ ተብላ በምትጠራ ቦታ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት መገደላቸውን ተናግረው ነበር። ይህ ግድያ የተከሰተው በክልሉ ልዩ ኃይል አባላት ላይ በአካባቢው የነበሩ ታጠቂዎች ጥቃት ሰንዝረው ግድያ ከፈጸሙ በኋላ መሆኑንም ነዋሪዎች ገልጸዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-61343985 |
0business
| ቻይና በ2060 ከካርበን ልቀት ነጻ እሆናለሁ አለች | ቻይና በ2060 ከካርበን ልቀት ነጻ እንደምትሆን ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ ይፋ አደረጉ። ፕሬዝደንቱ አገራቸው የካርበን ልቀት ምጠንን ዜሮ የምታስገባበት ጠንከር ያሉ ቅድመ ተከተሎች እንደሚኖሩ በተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል። ይህ የቻይና ውሳኔ በካርበን ልቀጥ መጠን እየጨመረ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥን ወደተሻለ ደረጃ ይወስዳል ተብሎ ታምኖበታል። ቻይና ከጠቅላላ የካርበን ልቀት የ28 በመቶ ድርሻን በመያዝ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲከሰት ዋነኛዋ አገር ናት። በዓለም አቀፍ ደረጃ የካርበን ልቀት መጠንን ለመቀነስ የሚደረጉ ስምምነቶች አዎንታዊ ለውጥ ሳያሳዩ በመቅረታቸው ቻይና ከዚህ መሰል ውሳኔ የመድረሷ ዜና ያልተጠበቀ ነበር። ፕሬዝደንት ዢ አገራቸው የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት ቆርጣ መነሳቷን ለተባበሩት መንግስታት አባል አገራት ካረጋገጡ በኋላ ሌሎች አገራት የቻይናን ተምሳሌት እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል። ሺ ዢንፒንግ እንዳሉት ቻይና ከ2030 በኋላ የካርበን ልቀቷ በተከታታይ መቀነስ ከጀመረ በኋላ ነው በ2060 የካርበን ልቀት መጠኑ ዜሮ የሚሆነው። ምንም እንኳ ቻይና እአአ 2018 እና 2019 ላይ የካርበን ልቀት መጠኗ መጨመርን ቢያሳይም በኮቪድ-19 ምክንያት በ2020 የካርበን ልቀቷ መቀነስን አሳይቶ ነበር። አሁን ላይ ዳግም ቻይና የድንጋይ ከሰል አጠቃቀሟ ላይ ማሻሻያ ባለማድረጓ የካርበን ልቀት መጨመር ምልክት እየታየ ነው። የቻይናው ፕሬዝደንት ይህን የአገራቸውን ውሳኔ ይፋ ያደረጉት አሜሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ ግዴለሽነት እያሳየች ባለችበት ወቅት ነው። እአአ 2015 ላይ ፕሬዝደንት ዢ እና የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ፓሪስ ላይ የካርበን ልቀት መጠንን ለመቀነስ ተስማምተው እንደነበረ ይታወሳል። ሺ ዢንፒንግ ይፋ ባደረጉት የቻይና ውሳኔ ዙሪያ አሁንም ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች አሉ። ለምሳሌ ቻይና የካርበን ልቀቷን ዜሮ ለማድረስ የምትወስዳቸው እርምጃዎች ምንድናቸው የሚለው አልተመለሰም። | ቻይና በ2060 ከካርበን ልቀት ነጻ እሆናለሁ አለች ቻይና በ2060 ከካርበን ልቀት ነጻ እንደምትሆን ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ ይፋ አደረጉ። ፕሬዝደንቱ አገራቸው የካርበን ልቀት ምጠንን ዜሮ የምታስገባበት ጠንከር ያሉ ቅድመ ተከተሎች እንደሚኖሩ በተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል። ይህ የቻይና ውሳኔ በካርበን ልቀጥ መጠን እየጨመረ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥን ወደተሻለ ደረጃ ይወስዳል ተብሎ ታምኖበታል። ቻይና ከጠቅላላ የካርበን ልቀት የ28 በመቶ ድርሻን በመያዝ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲከሰት ዋነኛዋ አገር ናት። በዓለም አቀፍ ደረጃ የካርበን ልቀት መጠንን ለመቀነስ የሚደረጉ ስምምነቶች አዎንታዊ ለውጥ ሳያሳዩ በመቅረታቸው ቻይና ከዚህ መሰል ውሳኔ የመድረሷ ዜና ያልተጠበቀ ነበር። ፕሬዝደንት ዢ አገራቸው የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት ቆርጣ መነሳቷን ለተባበሩት መንግስታት አባል አገራት ካረጋገጡ በኋላ ሌሎች አገራት የቻይናን ተምሳሌት እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል። ሺ ዢንፒንግ እንዳሉት ቻይና ከ2030 በኋላ የካርበን ልቀቷ በተከታታይ መቀነስ ከጀመረ በኋላ ነው በ2060 የካርበን ልቀት መጠኑ ዜሮ የሚሆነው። ምንም እንኳ ቻይና እአአ 2018 እና 2019 ላይ የካርበን ልቀት መጠኗ መጨመርን ቢያሳይም በኮቪድ-19 ምክንያት በ2020 የካርበን ልቀቷ መቀነስን አሳይቶ ነበር። አሁን ላይ ዳግም ቻይና የድንጋይ ከሰል አጠቃቀሟ ላይ ማሻሻያ ባለማድረጓ የካርበን ልቀት መጨመር ምልክት እየታየ ነው። የቻይናው ፕሬዝደንት ይህን የአገራቸውን ውሳኔ ይፋ ያደረጉት አሜሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ ግዴለሽነት እያሳየች ባለችበት ወቅት ነው። እአአ 2015 ላይ ፕሬዝደንት ዢ እና የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ፓሪስ ላይ የካርበን ልቀት መጠንን ለመቀነስ ተስማምተው እንደነበረ ይታወሳል። ሺ ዢንፒንግ ይፋ ባደረጉት የቻይና ውሳኔ ዙሪያ አሁንም ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች አሉ። ለምሳሌ ቻይና የካርበን ልቀቷን ዜሮ ለማድረስ የምትወስዳቸው እርምጃዎች ምንድናቸው የሚለው አልተመለሰም። | https://www.bbc.com/amharic/news-54262908 |
5sports
| ታዳጊዋ የአሜሪካ 'ስፔሊንግ ቢ' በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ጥቁር አሜሪካዊት ሆነች | ድንቅ የቅርጫት ኳስ ችሎታ ያላት ታዳጊ የአሜሪካን ብሔራዊ 'ስፔሊንግ ቢ' ያሸነፈነች የመጀመሪያው አፍሪካ-አሜሪካዊ ሆናለች። ስፔሊንግ ቢ ተወዳዳሪዎች የሚነገራቸውን ቃላት ትክክለኛ ፊደላት እየተናገሩ የሚፎካከሩበት መድረክ ነው። የሉዊዚያና ኒው ኦርሊያንስ ነዋሪ የሆነችው የ14 ዓመቷ ዛይላ አቫንት-ጋርድ “ሙራያ” (murraya) የሚለው ቃል ትክለኛ ፊደላት ተናግራ ነው ያሸነፈችው። ሙራያ በሞቃታማ አካባቢ የሚገኝ የዛፍ ዓይነት ነው። ወደዚህ ደረጃ ለመድረስ “querimonious” እና “solidungulate” የተሰኙትን ቃላት ፊደላት በትክክል መናገር ነበረባት። ምንም እንኳን በቀን እስከ ሰባት ሰዓታት ያህል ብትለማመድም የቃለት ፊደልን መናገርን የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ አድርጋ ነው የምትመለከተው። ዛይላ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ለመሆን ነው ፍላጎቷ። በአንድ ጊዜ በርካታ ኳሶችን በማንጠር ሦስት የዓለም ክብረወሰኖችን ስትይዝ ከናሽናል ባስኬትቦል አሶስዬሽን (ኤንቢኤ) ኮከቡ ስቴፈን ከሪ ጋር ማስታወቂያ የመሥራት እድልም አግኝታለች። ዛይላ ሐሙስ ዕለት ከአስራ አንድ የመጨረሻ ተወዳዳሪዎች ጋር ተፎካክራ አሸናፊ ሆናለች። በፍሎሪዳ ኦርላንዶ የተካሄደውን ዝግጅት በማሸነፏም 50,000 ዶላር አግኝታለች። በመጨረሻው ዙር የፍሪስኮ ቴክሳስዋን ነዋሪ እና የ 12 ዓመቷን ቻይትራ ቱማላን አሸንፋለች። እአአ ከ 2008 ወዲህ የእስያ ዝርያ የሌለው/የሌላት አሸናፊ ወይም ከአሸናፊዎቹ መካከል አንዱ/ዷ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለድል ሳይሆኑ የቀሩበት መድረክ መሆኑን አሶሺዬትድ ፕሬስ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡ ዛይላ በፍጻሜው ቀን ‘ኔፓታ’ (የሚንት ዝርያ ነው) በሚለው ቃል ላይ ያመነታች ቢሆንም በትክክል ፊደሉን መጥራት ችላለች፡፡ በቤት ውስጥ የምትማረው ታዳጊ ለኒው ኦርሊያንስ ጋዜጣ ታይምስ-ፒካዩን “አብዛኛውን ጊዜ ወደ 13,000 ቃላት [በየቀኑ] ለማጥናት እሞክራለሁ። ይህ ደግሞ እስከ ሰባት ሰዓት ወይም ተቀራራቢ ጊዜ ይወስዳል” ብላለች። “በእርግጥ ከመጠን በላይ በሆነ መንገድ እንዲሄድ አንፈቅድም። ትምህርት እና ቅርጫት ኳስም አለብኝ።“ ዛይላ ውድድሩን ያሸነፈች ሁለተኛዋ ጥቁር ታዳጊ ሆናለች። የጃማይካዋ ተወላጅ ጆዲ አን ማክስዌል እአአ በ1998 በ12 ዓመቷ ሻምፒዮን ሆናለች፡፡ በ2019 ስምንት ሕጻናት በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋራ አሸናፊ ለመሆን በቅተዋል። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ውድድሩ ባለፈው ዓመት ተቋርጦ ነበር። | ታዳጊዋ የአሜሪካ 'ስፔሊንግ ቢ' በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ጥቁር አሜሪካዊት ሆነች ድንቅ የቅርጫት ኳስ ችሎታ ያላት ታዳጊ የአሜሪካን ብሔራዊ 'ስፔሊንግ ቢ' ያሸነፈነች የመጀመሪያው አፍሪካ-አሜሪካዊ ሆናለች። ስፔሊንግ ቢ ተወዳዳሪዎች የሚነገራቸውን ቃላት ትክክለኛ ፊደላት እየተናገሩ የሚፎካከሩበት መድረክ ነው። የሉዊዚያና ኒው ኦርሊያንስ ነዋሪ የሆነችው የ14 ዓመቷ ዛይላ አቫንት-ጋርድ “ሙራያ” (murraya) የሚለው ቃል ትክለኛ ፊደላት ተናግራ ነው ያሸነፈችው። ሙራያ በሞቃታማ አካባቢ የሚገኝ የዛፍ ዓይነት ነው። ወደዚህ ደረጃ ለመድረስ “querimonious” እና “solidungulate” የተሰኙትን ቃላት ፊደላት በትክክል መናገር ነበረባት። ምንም እንኳን በቀን እስከ ሰባት ሰዓታት ያህል ብትለማመድም የቃለት ፊደልን መናገርን የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ አድርጋ ነው የምትመለከተው። ዛይላ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ለመሆን ነው ፍላጎቷ። በአንድ ጊዜ በርካታ ኳሶችን በማንጠር ሦስት የዓለም ክብረወሰኖችን ስትይዝ ከናሽናል ባስኬትቦል አሶስዬሽን (ኤንቢኤ) ኮከቡ ስቴፈን ከሪ ጋር ማስታወቂያ የመሥራት እድልም አግኝታለች። ዛይላ ሐሙስ ዕለት ከአስራ አንድ የመጨረሻ ተወዳዳሪዎች ጋር ተፎካክራ አሸናፊ ሆናለች። በፍሎሪዳ ኦርላንዶ የተካሄደውን ዝግጅት በማሸነፏም 50,000 ዶላር አግኝታለች። በመጨረሻው ዙር የፍሪስኮ ቴክሳስዋን ነዋሪ እና የ 12 ዓመቷን ቻይትራ ቱማላን አሸንፋለች። እአአ ከ 2008 ወዲህ የእስያ ዝርያ የሌለው/የሌላት አሸናፊ ወይም ከአሸናፊዎቹ መካከል አንዱ/ዷ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለድል ሳይሆኑ የቀሩበት መድረክ መሆኑን አሶሺዬትድ ፕሬስ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡ ዛይላ በፍጻሜው ቀን ‘ኔፓታ’ (የሚንት ዝርያ ነው) በሚለው ቃል ላይ ያመነታች ቢሆንም በትክክል ፊደሉን መጥራት ችላለች፡፡ በቤት ውስጥ የምትማረው ታዳጊ ለኒው ኦርሊያንስ ጋዜጣ ታይምስ-ፒካዩን “አብዛኛውን ጊዜ ወደ 13,000 ቃላት [በየቀኑ] ለማጥናት እሞክራለሁ። ይህ ደግሞ እስከ ሰባት ሰዓት ወይም ተቀራራቢ ጊዜ ይወስዳል” ብላለች። “በእርግጥ ከመጠን በላይ በሆነ መንገድ እንዲሄድ አንፈቅድም። ትምህርት እና ቅርጫት ኳስም አለብኝ።“ ዛይላ ውድድሩን ያሸነፈች ሁለተኛዋ ጥቁር ታዳጊ ሆናለች። የጃማይካዋ ተወላጅ ጆዲ አን ማክስዌል እአአ በ1998 በ12 ዓመቷ ሻምፒዮን ሆናለች፡፡ በ2019 ስምንት ሕጻናት በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋራ አሸናፊ ለመሆን በቅተዋል። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ውድድሩ ባለፈው ዓመት ተቋርጦ ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/news-57773978 |
0business
| ፈረንሳይ ምርቶቿ ላይ ማዕቀብ እንዳይጣል የመካከለኛው ምሥራቅ አገራትን ጠየቀች | ፈረንሳይ የተለያዩ ቁሳቁሶቿ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የሚደረጉ ቅስቀሳዎችን የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት እንዲያስቆሙ ጠየቀች። ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ ነብዩ መሐመድን የሚያሳዩ ካርቱኖችን መሣል ይቻላል የሚል አቋም ማንጸባረቃቸውን ተከትሎ የፈረንሳይ እቃዎች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ጥሪ እየተደረገ ነው። በኩዌት፣ ጆርዳን እና ካታር የሚገኙ አንዳንድ መደብሮች የፈረንሳይ ምርቶችን ማስወገድ ጀምረዋል። በሊቢያ፣ ሶርያ እና የጋዛ ሰርጥ ተቃውሞ ተካሂዷል። ፈረንሳያዊ መምህር ሳሙኤል ፓቲ፤ የነብዩ መሐመድን የካርቱን ሥዕል ለተማሪዎቹ ካሳየ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉ ይታወሳል። ክስተቱን ተከትሎ ፕሬዘዳንት ማክሮን "ኢስላሚስቶች ነጋችንን መቆጣጠር ይፈልጋሉ። ፈረንሳይ ግን ካርቱን መሥራት አታቆምም" ብለው ነበር። የነብዩ መሐመድን እንዲሁም የአላህን ምስል ማሳየት በእስልምና የተከለከለ ነው። የማክሮን ንግግርም ቁጣ ቀስቅስሷል። . በፈረንሳይ አንገቱን ለተቀላው መምህር በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ድጋፋቸውን አሳዩ . ቻርሊ ሄብዶ መፅሄት አወዛጋቢውን የነብዩ መሐመድ ካርቱንን እንደገና አተመ ፈረንሳይ ከሃይማኖት ጣልቃ ገብነት ነጻ የሆነች አገር እንደሆነች ትገልጻለች። የአንድ ማኅበረሰብን ስሜት ላለመጉዳት በመጠንቀቅ ውስጥ የንግግር ነጻነት መገደብ የለበትም የሚል አቋም ታንጸባርቃለች። ማክሮን "መቼም ቢሆን እጅ አንሰጥም" ሲሉ ትዊት አድርገዋል። በቱርክ እና በፓኪስታን ያሉ የፖለቲካ መሪዎች ማክሮንን ተችተዋል። የሃይማኖት ነጻነትን እየተጋፉ እንዲሁም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ፈረንሳይ የሚኖሩ ሙስሊሞችን እያገለሉ እንደሆነም ገልጸዋል። የቱርኩ ፕሬዘዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ማክሮን ስለ እስልምና ያላቸውን አቋም በተመለከተ "አእምሯቸውን ይመርመሩ" ብለዋል። ፈረንሳይ ቱርክ ከሚገኙ አምባሳደሯ ጋር ለመምከር ወደ ፈረንሳይ ጠርታቸዋለች። የፓኪስታኑ መሪ ኢምራን ከሀን "እስልምናን ሳይገነዘቡ ሃይማኖቱን እያጥላሉ ነው" ብለዋል። በወሩ በባቻ ላይ ማክሮን "እስላማዊ ገንጣይ" ያሏቸው ቡድኖች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረው ነበር። የምዕራብ አውሮፓ ትልቁ የሙስሊም ማኅበረሰብ ማክሮን፤ ሃይማኖታዊ ጫና እያደረጉባቸው እንደሆነና እንቅስቃሴያቸው ሙስሊም ጠል እንደሆነ ተናግረዋል። እአአ 2015 ላይ የፈረንሳዩ ሽሙጥ አዘል መጽሔት ቻርሊ ሄድቦ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸው አይዘነጋም። መጽሔቱ የነብዩ መሐመድን ካርቱን አትሞ ነበር። ባሳለፍነው እሑድ በጆርዳን፣ ካታር እና ኩዌት ያሉ አንዳንድ መደብሮች የፈረንሳይ ምርቶችን አስወግደዋል። የፈረንሳይ ውበት መጠበቂያ ምርቶች ከመደርደሪያ ተነስተዋል። ክዌት ውስጥ ትልቁ የአከፋፋዮች ማኅበር የፈረንሳይ ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል አዟል። የሸማቾች ማኅበርም በተደጋጋሚ ነብዩ መሐመድን የሚያጥላሉ አስተያየቶች በመሰንዘራቸው ተመሳሳይ ትዕዛዝ አስተላልፏል። የፈረንሳይ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ባወጣው መግለጫ "ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የተደረገው ጥሪ መሠረተ ቢስ ነው። ይህ ጥሪና በጥቂት አክራሪዎች የሚጫሩ አገሪቱ ላይ የሚቃጡ ጥቃቶች መገታት አለባቸው" ብሏል። በሳኡዲ አረቢያ እንዲሁም በሌሎች የአረብ አገራትም የፈረንሳይ ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የሚጠይቁ የበይነ መረብ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል። የፈረንሳዩ መደብር ካርፉር እንዲዘጋ የሚጠይቀው ሀሽታግ፤ በሳኡዲ የትዊተር ተጠቃሚዎች ዘንድ ከነበሩ አነጋጋሪ ጉዳዮች ሁለተኛውን ደረጃ ይዟል። በሊቢያ፣ ጋዛ እና ሶርያ ፈረንሳይን የሚያወግዙ ተቃውሞዎች ተካሂደዋል። | ፈረንሳይ ምርቶቿ ላይ ማዕቀብ እንዳይጣል የመካከለኛው ምሥራቅ አገራትን ጠየቀች ፈረንሳይ የተለያዩ ቁሳቁሶቿ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የሚደረጉ ቅስቀሳዎችን የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት እንዲያስቆሙ ጠየቀች። ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ ነብዩ መሐመድን የሚያሳዩ ካርቱኖችን መሣል ይቻላል የሚል አቋም ማንጸባረቃቸውን ተከትሎ የፈረንሳይ እቃዎች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ጥሪ እየተደረገ ነው። በኩዌት፣ ጆርዳን እና ካታር የሚገኙ አንዳንድ መደብሮች የፈረንሳይ ምርቶችን ማስወገድ ጀምረዋል። በሊቢያ፣ ሶርያ እና የጋዛ ሰርጥ ተቃውሞ ተካሂዷል። ፈረንሳያዊ መምህር ሳሙኤል ፓቲ፤ የነብዩ መሐመድን የካርቱን ሥዕል ለተማሪዎቹ ካሳየ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉ ይታወሳል። ክስተቱን ተከትሎ ፕሬዘዳንት ማክሮን "ኢስላሚስቶች ነጋችንን መቆጣጠር ይፈልጋሉ። ፈረንሳይ ግን ካርቱን መሥራት አታቆምም" ብለው ነበር። የነብዩ መሐመድን እንዲሁም የአላህን ምስል ማሳየት በእስልምና የተከለከለ ነው። የማክሮን ንግግርም ቁጣ ቀስቅስሷል። . በፈረንሳይ አንገቱን ለተቀላው መምህር በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ድጋፋቸውን አሳዩ . ቻርሊ ሄብዶ መፅሄት አወዛጋቢውን የነብዩ መሐመድ ካርቱንን እንደገና አተመ ፈረንሳይ ከሃይማኖት ጣልቃ ገብነት ነጻ የሆነች አገር እንደሆነች ትገልጻለች። የአንድ ማኅበረሰብን ስሜት ላለመጉዳት በመጠንቀቅ ውስጥ የንግግር ነጻነት መገደብ የለበትም የሚል አቋም ታንጸባርቃለች። ማክሮን "መቼም ቢሆን እጅ አንሰጥም" ሲሉ ትዊት አድርገዋል። በቱርክ እና በፓኪስታን ያሉ የፖለቲካ መሪዎች ማክሮንን ተችተዋል። የሃይማኖት ነጻነትን እየተጋፉ እንዲሁም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ፈረንሳይ የሚኖሩ ሙስሊሞችን እያገለሉ እንደሆነም ገልጸዋል። የቱርኩ ፕሬዘዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ማክሮን ስለ እስልምና ያላቸውን አቋም በተመለከተ "አእምሯቸውን ይመርመሩ" ብለዋል። ፈረንሳይ ቱርክ ከሚገኙ አምባሳደሯ ጋር ለመምከር ወደ ፈረንሳይ ጠርታቸዋለች። የፓኪስታኑ መሪ ኢምራን ከሀን "እስልምናን ሳይገነዘቡ ሃይማኖቱን እያጥላሉ ነው" ብለዋል። በወሩ በባቻ ላይ ማክሮን "እስላማዊ ገንጣይ" ያሏቸው ቡድኖች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረው ነበር። የምዕራብ አውሮፓ ትልቁ የሙስሊም ማኅበረሰብ ማክሮን፤ ሃይማኖታዊ ጫና እያደረጉባቸው እንደሆነና እንቅስቃሴያቸው ሙስሊም ጠል እንደሆነ ተናግረዋል። እአአ 2015 ላይ የፈረንሳዩ ሽሙጥ አዘል መጽሔት ቻርሊ ሄድቦ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸው አይዘነጋም። መጽሔቱ የነብዩ መሐመድን ካርቱን አትሞ ነበር። ባሳለፍነው እሑድ በጆርዳን፣ ካታር እና ኩዌት ያሉ አንዳንድ መደብሮች የፈረንሳይ ምርቶችን አስወግደዋል። የፈረንሳይ ውበት መጠበቂያ ምርቶች ከመደርደሪያ ተነስተዋል። ክዌት ውስጥ ትልቁ የአከፋፋዮች ማኅበር የፈረንሳይ ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል አዟል። የሸማቾች ማኅበርም በተደጋጋሚ ነብዩ መሐመድን የሚያጥላሉ አስተያየቶች በመሰንዘራቸው ተመሳሳይ ትዕዛዝ አስተላልፏል። የፈረንሳይ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ባወጣው መግለጫ "ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የተደረገው ጥሪ መሠረተ ቢስ ነው። ይህ ጥሪና በጥቂት አክራሪዎች የሚጫሩ አገሪቱ ላይ የሚቃጡ ጥቃቶች መገታት አለባቸው" ብሏል። በሳኡዲ አረቢያ እንዲሁም በሌሎች የአረብ አገራትም የፈረንሳይ ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የሚጠይቁ የበይነ መረብ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል። የፈረንሳዩ መደብር ካርፉር እንዲዘጋ የሚጠይቀው ሀሽታግ፤ በሳኡዲ የትዊተር ተጠቃሚዎች ዘንድ ከነበሩ አነጋጋሪ ጉዳዮች ሁለተኛውን ደረጃ ይዟል። በሊቢያ፣ ጋዛ እና ሶርያ ፈረንሳይን የሚያወግዙ ተቃውሞዎች ተካሂደዋል። | https://www.bbc.com/amharic/54689433 |
0business
| በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ግሽበት ወዴት እያመራ ነው? መፍትሔውስ ምንድነው? | ሰናይት ‘ሱዙኪ ዲዛዬር’ የተሰኘች 1200 ‘ሲሲ’ ያላትን መኪና ባለፈው ግንቦት የገዛችው 1.38 ሚሊዮን ብር ነበር። ከአምስት ወር በኋላ ተሽከርካሪዋ 2.2 ሚሊዮን ብር እየተሸጠች እንደሆነ ቢቢሲ አዲስ አበባ ከሚገኙ መኪና ሻጮች መረዳት ችሏል። በአገረ ሕንድ የምትመረተው ዲዛዬር ሦስተኛ ምርት (ሰርድ ጄነሬሽን) መኪና ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ ለገበያ ውላለች። የመኪናዋ ዋጋ በአሜሪካ ዶላር ሲሰላ 10 ሺህ ዶላር ገደማ ነው። ይህ አሁን ባለው የባንክ ምንዛሪ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ይሆናል። ይህ ዋጋ በጎረቤት አገር ኬንያ ከ1.3 እስከ 1.4 ሚሊዮን ሽልንግ ይገመታል። ይህ ወደ ዶላር ሲመታ 11 ሺህ ዶላር ይጠጋል። በኡጋንዳ ደግሞ መኪናዋ በካምፓላ ገበያ በ43 ሚሊዮን የኡጋንዳ ሽልንግ ትሸጣለች። ይህም በዶላር ወደ 11 ሺህ ገደማ ይመነዘራል። ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ባለፈው ዓመት መጋቢት ባወጣው ዘገባ በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር በ34.7 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ገልጦ ነበር። የዋጋ ንረቱ ለምግብነት በሚውሉ አትክልት እና ፍራፍሬ፣ ጥራጥሬ እና እህሎች፣ ቅመማ ቅመም እና ዘይት፣ ቅቤ እና ቡና ላይ ይጠነክራል። ሄኖክ የልጁን አንደኛ ዓመት ልደት “አነስ ባለ ድግስ” ለማክበር 40 ሺህ ብር ገደማ እንዳወጣ ለቢቢሲ ገልጿል። “ከባለቤቴ ጋር ብዙ ሰው አንጠራም ብለን ተስማማተን ቤተሰብ ብቻ ነው ልደቱን የታደመው” ይላል። “ዲኮር ብቻ 6 ሺህ ብር የፈጀው። ዲኮር ስልህ ፊኛና ‘ዲም ላይት’ እንጂ ሌላ ምንም አልነበረውም። ለባለቤቴ ባሕላዊ ቀሚስ፤ ለእኔና ለሁለት ልጆቼ ደግሞ ከላይ የሚለበስ ልብስ 10 ሺህ ብር፤ ስጋና ሽንኩርት እንዲሁም ዘይትና አትክልት 11 ሺህ ብር ገደማ፤ ኬክ 3 ሺህ አውጥቻለሁ።” ሄኖክ ከልጁ ልደት በኋላ ትራንስፖርትን ጨምሮ ለሌሎች ጥቃቅን ወጪዎች ያወጣውን ሲያሰላ 40 ሺህ እንደደረሰ ሲረዳ ግራ እንደተጋባ ይናገራል። ይህ ብቻ አይደለም ለትልቁ ልጁ ደብተር ሊገዛ ወጥቶ ከብዙ አሰሳ በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ ስሙ የገነነ ደብተር አንዱን ደርዘን 880 ብር አውጥቶ ሸምቶ ተመልሷል። የዋጋ ግሽበት ጉዳይ በማኅበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ዘንድም ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል። በአዲስ አበባ ከተማ የአትክልትና ፍራፍሬ ገበያ ተብሎ በሚታወቀው ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በንግድ ሥራ ላይ የተሠማራ አንድ ወጣት፣ ከቅርብ ወራት ወዲህ በተለይ የቲማቲም እና የነጭ ሽንኩርት ዋጋ እጅግ መናሩን ለቢቢሲ ይናገራል። “አንድ ኪሎ ቲማቲም በችርቻሮ ዋጋ እንደ ጥራቱ ከ55 አስከ 70 ብር፤ ነጭ ሽንኩርት ደግሞ እስከ 250 ብር በኪሎ ይሸጣል።” የዋጋ ግሽበት የአንድ ሸቀጥ አሊያም አገልግሎት ዋጋ መናር ነው። ቬኒዝዌላ በዓለም ትልቁ የዋጋ ግሽበት ያለባት አገር ናት። በዚህ ዓመት መጀመሪያ (2022) በአገሪቷ የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት 1198.0 በመቶ ነበር። በዚህ ምክንያት በገበያ የሚታየው የዋጋ ጭማሪ በፍጥነት የሚቀያየር በመሆኑ የንግድ ተቋማት የሚያቀርቧቸውን ምርቶች ዋጋ መተመን ትተው ደንበኞች በየቀኑ የሚኖረውን ዋጋ እንዲጠይቁ ብለው ነበር። እንዲህ ዓይነት የዋጋ ንረት፤ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አሊያም ‘ሃይፐር ኢንፍሌሽን’ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የመንግሥት ወጪ ከልክ በላይ ሲሆን እና መንግሥት ወጪዎቹን ለመሸፈን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በብዛት ሲያትም የሚከሰት ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ነው። ‘ሃይፐር ኢንፍሌሽን’ ብዙውን ጊዜ በጦርነት፣ በሥርዓት ለውጥ ወይም ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተከትሎ የሚመጣ ነው። ቬኒዝዌላ፤ ከደቡብ አሜሪካ አገራት ከፍተኛ የነፍስ ወከፍ ገቢ የነበራት ነበረች። አብዛኛው የአገሪቱ ገቢ ከነዳጅ ንግድ የሚገኝ ስለነበረ በ80 እና 90ዎቹ የነዳጅ ዋጋ ሲዋዥቅ ኢኮኖሚዋን ለአደጋ አጋለጠው። የአንድ በርሜል ነዳጅ ዋጋ በ2014 ከነበረው 100 ዶላር በ2016 ከ30 ዶላር በታች ሲወርድ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ትልቅ ኪሳራ ደረሰበት። ከአፍሪካ አገራት ሱዳን፤ በባለፈው ዓመት አጋማሽ ላይ 340.0 በመቶ የዋጋ ንረት ተመዝግቦባታል። በዚህ ምክንያት በዓለም ሁለተኛ ትልቁ የዋጋ ንረት ያለባት አገር ሆናለች። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሱዳን የምግብና መጠጥ ዋጋ መናሩ እንዲሁም ዶላር በጥቁር ገበያ ያለው ምንዛሪ መናሩ የዋጋ ግሽብቱ ከፍተኛ ደረጃ ጭማሪ እያሳየ ነው። ይህ የዋጋ ንረት የወለደው የሱዳን ተቃውሞ የቀድሞው ፕሬዝደንት ኦማር አል-ባሽር በ2019 ከስልጣናቸው እንዲነሱ ምክንያት ሆኗል። በአጠቃላይ ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ወደ 12.2 በመቶ ያደገ ሲሆን አብዛኛዎቹ አገራት ጠንካራ የማዕከዊ ባንክ ሥርዓት ስለሌላቸው ነው ይላል ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ። የዋጋ ግሽበት፤ በስሪ ላንካ የነበረው ፖለቲከዊ አለመረጋጋት እንዲጋጋል ከማድረጉም በላይ ሕዝባዊ ተቃውሞውን ተከትሎ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ከሥልጣናቸው ወርደዋል። የዋጋ ግሽበት በአሁኑ ወቅት በርካታ የዓለም አገራትን እየፈተነ ሲሆን የኤነርጂ (ኃይል አቅርቦት) ዋጋ መጨመር፣ የምግብ እና የሌሎች ግብዓቶች አቅርቦት እጥረት እንዲሁም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለዚህ መባባስ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ይነገራል። በኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት 37.2 በመቶ ነበር። ይህ በፈረንጆቹ 2011 በኋላ ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ነው። የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሪፖርት እንደሚያመለክተው ነሐሴ 2014 ዓ.ም. የተመዘገበው ዓመታዊ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 32.5 በመቶ ደርሷል። ኤጀንሲው በዚህ ወር የዋጋ ግሽበቱ መጠን ዝቅ ያለበት ምክንያት የምግብ ዋጋ ግሽበት አንጻራዊ መረጋጋት ስላሳየ ነው ይላል። ሆኖም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ካላቸው አገራት ተርታ ትገኛለች። በአፍሪካ ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት የተመዘገበባት አገር ዚምባብዌ ስትሆን ይህም 285 በመቶ ነው። በተከታይነት ደግሞ በፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ የምትገኘው ሱዳን በ125 በመቶ የሸቀጦች የዋጋ ሁለተኛ ናት። የፋይናንስ አማካሪው እና የኦዲት ባለሙያው ጥላሁን ግርማ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የዋጋ ግሽበት “በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተከሰተው ጋር የሚያያዝ ነው” ይላሉ። ባለሙያው “ዓለም እንዲህ ያለ የዋጋ ግሽበት አይታ አታውቅም” ሲሉ የዓለም አገራት ችግር ላይ እንደወደቁ ያስገነዝባሉ። በሩሲያና በዩክሬን መካከል እየተካሄድ ያለው ጦርነት እንደ ነዳጅ፣ ስንዴ፣ ዘይትና ሌሎች መሠረታዊ ፍጆታዎች ዋጋ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል ይላሉ። የነዳጅ ዋጋ በዓለም አቀፍ ደረጃ በጨመረበት ወቅት “የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ ነዳጅ ላይ ያደርግ የነበረውን ድጎማ ማንሳቱ ችግሩ የበለጠ እንዲባባስ አድርጓል” ይላሉ። “በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ የነዳጅ ዋጋ በሚጨምርበት ወቅት የሁሉም ምርቶች ዋጋ ከፍ ይላል። ከነዳጅ ጋር በቀጥታ ጋር የሚገናኙ ዘርፎች ብቻ ሳይሆን የማይመለከታቸውም መጨመራቸው አይቀርም።” አቶ ጥላሁን አክለው በሰሜን ኢትዮጵያ እየተሄድ ያለው የእርስ በርስ ጦርነት “ለኑሮ ውድነት መባባስ ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል” በማለት ግጭቱ በጊዜ ካልተቋጨ ሁኔታው እንደሚባባስ ያሳስባሉ። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በፍጥነት እየጨመረ የሄደውን የተሽከርካሪዎች ዋጋ መናር እንደምሳሌ የሚጠቅሱት ባለሙያው የዶላር እጥረት ትልቅ ድርሻ አለው ይላሉ። “ወደ አገር ቤት መኪና የሚያስገቡ አስመጪዎች እንደሚፈልጉት ዶላር እየተፈቀደላቸው አይደለም። ተፈቅዶላቸው ዶላር አግኝተው ሲያስገቡ ደግሞ ትልቅ ትርፍ በማግኘት ነው የሚሸጡት።” የተሽከርካሪዎች ብቻ ሳይሆን የሌሎች ቁሳቁሶች ዋጋ መናር ዶላር በጥቁር ገበያ ካለው ዋጋ ጋር እንደሚገናኝ አቶ ጥላሁን ያስረዳሉ። “አንድ የአሜሪካን ዶላር ጥቁር ገበያው ላይ እስከ 90 ብር እየተመነዘረ ነው። መንግሥት ደግሞ በ53 ብር ተምኖታል። መኪና የሚያስገቡ አስመጪዎች ዶላር ከባንክ የሚጠይቁት ለይምሰል ነው እንጂ ዶላር ከጥቁር ገበያው እየገዙ ነው መኪና የሚያስገቡት። ታዲያ ይህንን የጥቁር ገበያ ዋጋ ነው ለገዢዎች የሚያስተላልፉት።” የቢዝነስ ድረ-ገፁ ብሉምበርግ ረቡዕ ዕለት ባወጣው ዘገባ በኢትዮጵያ ጥቁር ገበያ አንድ የአሜሪካን ዶላር እስከ 92 ብር እየተመነዘረ ነው ሲል ስማቸውን ያልተጠቀሱ ምንጮችን በመጥቀስ አስነብቧል። በተቃራኒው ባንኮች አንድ ዶላር በ52.5 ብር እየመነዘሩ እንደሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ብሉምበርግ፤ ዶላር በጥቁር ገበያውና በባንክ መካከል ላለው ልዩነት ትልቁ ምክንያት የሰሜን ኢትዮጵያው የእርስ በርስ ጦርነት ነው ሲል የማዕከላዊ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ዋና የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ፍቃዱ ድጋፌን ዋቢ በማድረግ ፅፏል። ኢትዮጵያ በዋጋ ንረት ከአፍሪካ አገራት በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሸቀጦች ዋጋ ግሽበት የተመዘገበው በምግብ እና በምግብ ነክ ቁሳቁሶች እንዲሁም በግንባታ ግብአቶች ላይ ነው። መንግሥት በተለያዩ ወቅቶች ለሸቀጦች እና ለቁሳቁሶች የዋጋ ተመን ቢያወጣም መሰል ፖሊሲዎች ከጥቂት ሳምንት በላይ ተግባራዊ አይሆኑም። ለምሳሌ በቅርቡ የሲሚንቶ ዋጋ መናርን ተከትሎ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አዲስ የዋጋ ተመን ማውጣቱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ሲሚንቶ ከፋብሪካ የሚወጣበት አዲሱ የዋጋ ተመን ዝቅተኛው 510 ብር ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ 683 ብር ከ44 ሳንቲም እንዲሆን ሚኒስቴሩ ወስኗል። ነገር ግን ይህ አዲስ ተመን ከወጣ በኋላ ሲሚንቶ እስከ 1050 ብር እየተሸጠ እንዳለ አንድ ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ ደላላ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የውጭ አገር ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንዲሠሩ መንግሥት መፍቀዱን ተከትሎ ያናገርናቸው የፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ሊቀ-መንበር ዘመዴነህ ንጋቱ ባንኮቹ ዶላር ይዘው መምጣታቸው ችግሩን ሊያቃልል እንደሚችል ያምናሉ። “እንደ አጭር ጊዜ መፍትሔ መንግሥት፤ ሕዝቡ በየቀኑ መሠረታዊ ፍጆታዎች ላይ ድጎማ ማድረግ አለበት” የሚሉት የፋይናንስ አማካሪው አቶ ጥላሁን ደግሞ “ነገር ግን ለዋጋ ግሽበት ዋናው መፍትሔ የግብር አሰባሰብ።” “ለምሳሌ እኔ ለተሽከርካሪዬ የመድን ፈንድ ለመክፈል በቅርቡ ሄጄ ነበር። ለአንድ ዓመት 125 ብር ብቻ ነው ያስከፈሉኝ። ይህ ምን ያደርግላቸዋል?” በማለት በግብር አሰባሰብ ሂደቱ ላይ ጥያቄ ያነሳሉ። “የግብር አሰባሰብ ሂደቱ በደንብ መታየት አለበት። ግብር ማለት ካለው ላይ ሰብስበህ ለሌለው እንደመስጠት ነው። በዚህ ላይ መንግሥት ጠንክሮ መሥራት አለበት።” ከዚህ ቀደም የዋጋ ግሽበትን አስመልክቶ ያናገርናቸው የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) “ችግሩ እጅግ ውስብስብ ስለሆነ” የአጭር ጊዜ መፍትሔ አለው ብለው እንደማያምኑ ገልጠዋል። ለንዶን የሚኖሩት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አብዱልመናን መሐመድ ደግሞ “መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ የሚበደረውን ገንዘብ መቀነስና አስፈላጊነታቸው ጥያቄ ውስጥ ያሉ ፕሮጀክቶችን ማቆም፣ አስፈላጊ የሚባሉ ፕሮጀክቶችንም ቢሆን ለጊዜው መፍትሔ እስኪገኝ ማዘግየት አለበት” ሲሉ መክረዋል። “የኢትዮጵያን ብር የመግዛት አቅም ከውጭ ምንዛሪ ጋር በተያያዘ የማውረድ እንቅስቃሴ ወደ አገር ቤት የሚገቡ እቃዎችን ስለሚያንር በአስቸኳይ መቆም አለበት፤ መንግሥት እነዚህን እርምጃዎች የሚወስድ ከሆነ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ውጤት ማየት ይቻላል” ይላሉ አብዱልመናን። የዓለም ባንክ፤ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ያስመዘገቡ አገራት የሕዝባቸውን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ላይ መትጋት አለባቸው ሲል ይመክራል። | በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ግሽበት ወዴት እያመራ ነው? መፍትሔውስ ምንድነው? ሰናይት ‘ሱዙኪ ዲዛዬር’ የተሰኘች 1200 ‘ሲሲ’ ያላትን መኪና ባለፈው ግንቦት የገዛችው 1.38 ሚሊዮን ብር ነበር። ከአምስት ወር በኋላ ተሽከርካሪዋ 2.2 ሚሊዮን ብር እየተሸጠች እንደሆነ ቢቢሲ አዲስ አበባ ከሚገኙ መኪና ሻጮች መረዳት ችሏል። በአገረ ሕንድ የምትመረተው ዲዛዬር ሦስተኛ ምርት (ሰርድ ጄነሬሽን) መኪና ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ ለገበያ ውላለች። የመኪናዋ ዋጋ በአሜሪካ ዶላር ሲሰላ 10 ሺህ ዶላር ገደማ ነው። ይህ አሁን ባለው የባንክ ምንዛሪ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ይሆናል። ይህ ዋጋ በጎረቤት አገር ኬንያ ከ1.3 እስከ 1.4 ሚሊዮን ሽልንግ ይገመታል። ይህ ወደ ዶላር ሲመታ 11 ሺህ ዶላር ይጠጋል። በኡጋንዳ ደግሞ መኪናዋ በካምፓላ ገበያ በ43 ሚሊዮን የኡጋንዳ ሽልንግ ትሸጣለች። ይህም በዶላር ወደ 11 ሺህ ገደማ ይመነዘራል። ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ባለፈው ዓመት መጋቢት ባወጣው ዘገባ በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር በ34.7 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ገልጦ ነበር። የዋጋ ንረቱ ለምግብነት በሚውሉ አትክልት እና ፍራፍሬ፣ ጥራጥሬ እና እህሎች፣ ቅመማ ቅመም እና ዘይት፣ ቅቤ እና ቡና ላይ ይጠነክራል። ሄኖክ የልጁን አንደኛ ዓመት ልደት “አነስ ባለ ድግስ” ለማክበር 40 ሺህ ብር ገደማ እንዳወጣ ለቢቢሲ ገልጿል። “ከባለቤቴ ጋር ብዙ ሰው አንጠራም ብለን ተስማማተን ቤተሰብ ብቻ ነው ልደቱን የታደመው” ይላል። “ዲኮር ብቻ 6 ሺህ ብር የፈጀው። ዲኮር ስልህ ፊኛና ‘ዲም ላይት’ እንጂ ሌላ ምንም አልነበረውም። ለባለቤቴ ባሕላዊ ቀሚስ፤ ለእኔና ለሁለት ልጆቼ ደግሞ ከላይ የሚለበስ ልብስ 10 ሺህ ብር፤ ስጋና ሽንኩርት እንዲሁም ዘይትና አትክልት 11 ሺህ ብር ገደማ፤ ኬክ 3 ሺህ አውጥቻለሁ።” ሄኖክ ከልጁ ልደት በኋላ ትራንስፖርትን ጨምሮ ለሌሎች ጥቃቅን ወጪዎች ያወጣውን ሲያሰላ 40 ሺህ እንደደረሰ ሲረዳ ግራ እንደተጋባ ይናገራል። ይህ ብቻ አይደለም ለትልቁ ልጁ ደብተር ሊገዛ ወጥቶ ከብዙ አሰሳ በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ ስሙ የገነነ ደብተር አንዱን ደርዘን 880 ብር አውጥቶ ሸምቶ ተመልሷል። የዋጋ ግሽበት ጉዳይ በማኅበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ዘንድም ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል። በአዲስ አበባ ከተማ የአትክልትና ፍራፍሬ ገበያ ተብሎ በሚታወቀው ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በንግድ ሥራ ላይ የተሠማራ አንድ ወጣት፣ ከቅርብ ወራት ወዲህ በተለይ የቲማቲም እና የነጭ ሽንኩርት ዋጋ እጅግ መናሩን ለቢቢሲ ይናገራል። “አንድ ኪሎ ቲማቲም በችርቻሮ ዋጋ እንደ ጥራቱ ከ55 አስከ 70 ብር፤ ነጭ ሽንኩርት ደግሞ እስከ 250 ብር በኪሎ ይሸጣል።” የዋጋ ግሽበት የአንድ ሸቀጥ አሊያም አገልግሎት ዋጋ መናር ነው። ቬኒዝዌላ በዓለም ትልቁ የዋጋ ግሽበት ያለባት አገር ናት። በዚህ ዓመት መጀመሪያ (2022) በአገሪቷ የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት 1198.0 በመቶ ነበር። በዚህ ምክንያት በገበያ የሚታየው የዋጋ ጭማሪ በፍጥነት የሚቀያየር በመሆኑ የንግድ ተቋማት የሚያቀርቧቸውን ምርቶች ዋጋ መተመን ትተው ደንበኞች በየቀኑ የሚኖረውን ዋጋ እንዲጠይቁ ብለው ነበር። እንዲህ ዓይነት የዋጋ ንረት፤ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አሊያም ‘ሃይፐር ኢንፍሌሽን’ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የመንግሥት ወጪ ከልክ በላይ ሲሆን እና መንግሥት ወጪዎቹን ለመሸፈን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በብዛት ሲያትም የሚከሰት ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ነው። ‘ሃይፐር ኢንፍሌሽን’ ብዙውን ጊዜ በጦርነት፣ በሥርዓት ለውጥ ወይም ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተከትሎ የሚመጣ ነው። ቬኒዝዌላ፤ ከደቡብ አሜሪካ አገራት ከፍተኛ የነፍስ ወከፍ ገቢ የነበራት ነበረች። አብዛኛው የአገሪቱ ገቢ ከነዳጅ ንግድ የሚገኝ ስለነበረ በ80 እና 90ዎቹ የነዳጅ ዋጋ ሲዋዥቅ ኢኮኖሚዋን ለአደጋ አጋለጠው። የአንድ በርሜል ነዳጅ ዋጋ በ2014 ከነበረው 100 ዶላር በ2016 ከ30 ዶላር በታች ሲወርድ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ትልቅ ኪሳራ ደረሰበት። ከአፍሪካ አገራት ሱዳን፤ በባለፈው ዓመት አጋማሽ ላይ 340.0 በመቶ የዋጋ ንረት ተመዝግቦባታል። በዚህ ምክንያት በዓለም ሁለተኛ ትልቁ የዋጋ ንረት ያለባት አገር ሆናለች። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሱዳን የምግብና መጠጥ ዋጋ መናሩ እንዲሁም ዶላር በጥቁር ገበያ ያለው ምንዛሪ መናሩ የዋጋ ግሽብቱ ከፍተኛ ደረጃ ጭማሪ እያሳየ ነው። ይህ የዋጋ ንረት የወለደው የሱዳን ተቃውሞ የቀድሞው ፕሬዝደንት ኦማር አል-ባሽር በ2019 ከስልጣናቸው እንዲነሱ ምክንያት ሆኗል። በአጠቃላይ ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ወደ 12.2 በመቶ ያደገ ሲሆን አብዛኛዎቹ አገራት ጠንካራ የማዕከዊ ባንክ ሥርዓት ስለሌላቸው ነው ይላል ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ። የዋጋ ግሽበት፤ በስሪ ላንካ የነበረው ፖለቲከዊ አለመረጋጋት እንዲጋጋል ከማድረጉም በላይ ሕዝባዊ ተቃውሞውን ተከትሎ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ከሥልጣናቸው ወርደዋል። የዋጋ ግሽበት በአሁኑ ወቅት በርካታ የዓለም አገራትን እየፈተነ ሲሆን የኤነርጂ (ኃይል አቅርቦት) ዋጋ መጨመር፣ የምግብ እና የሌሎች ግብዓቶች አቅርቦት እጥረት እንዲሁም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለዚህ መባባስ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ይነገራል። በኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት 37.2 በመቶ ነበር። ይህ በፈረንጆቹ 2011 በኋላ ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ነው። የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሪፖርት እንደሚያመለክተው ነሐሴ 2014 ዓ.ም. የተመዘገበው ዓመታዊ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 32.5 በመቶ ደርሷል። ኤጀንሲው በዚህ ወር የዋጋ ግሽበቱ መጠን ዝቅ ያለበት ምክንያት የምግብ ዋጋ ግሽበት አንጻራዊ መረጋጋት ስላሳየ ነው ይላል። ሆኖም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ካላቸው አገራት ተርታ ትገኛለች። በአፍሪካ ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት የተመዘገበባት አገር ዚምባብዌ ስትሆን ይህም 285 በመቶ ነው። በተከታይነት ደግሞ በፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ የምትገኘው ሱዳን በ125 በመቶ የሸቀጦች የዋጋ ሁለተኛ ናት። የፋይናንስ አማካሪው እና የኦዲት ባለሙያው ጥላሁን ግርማ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የዋጋ ግሽበት “በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተከሰተው ጋር የሚያያዝ ነው” ይላሉ። ባለሙያው “ዓለም እንዲህ ያለ የዋጋ ግሽበት አይታ አታውቅም” ሲሉ የዓለም አገራት ችግር ላይ እንደወደቁ ያስገነዝባሉ። በሩሲያና በዩክሬን መካከል እየተካሄድ ያለው ጦርነት እንደ ነዳጅ፣ ስንዴ፣ ዘይትና ሌሎች መሠረታዊ ፍጆታዎች ዋጋ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል ይላሉ። የነዳጅ ዋጋ በዓለም አቀፍ ደረጃ በጨመረበት ወቅት “የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ ነዳጅ ላይ ያደርግ የነበረውን ድጎማ ማንሳቱ ችግሩ የበለጠ እንዲባባስ አድርጓል” ይላሉ። “በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ የነዳጅ ዋጋ በሚጨምርበት ወቅት የሁሉም ምርቶች ዋጋ ከፍ ይላል። ከነዳጅ ጋር በቀጥታ ጋር የሚገናኙ ዘርፎች ብቻ ሳይሆን የማይመለከታቸውም መጨመራቸው አይቀርም።” አቶ ጥላሁን አክለው በሰሜን ኢትዮጵያ እየተሄድ ያለው የእርስ በርስ ጦርነት “ለኑሮ ውድነት መባባስ ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል” በማለት ግጭቱ በጊዜ ካልተቋጨ ሁኔታው እንደሚባባስ ያሳስባሉ። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በፍጥነት እየጨመረ የሄደውን የተሽከርካሪዎች ዋጋ መናር እንደምሳሌ የሚጠቅሱት ባለሙያው የዶላር እጥረት ትልቅ ድርሻ አለው ይላሉ። “ወደ አገር ቤት መኪና የሚያስገቡ አስመጪዎች እንደሚፈልጉት ዶላር እየተፈቀደላቸው አይደለም። ተፈቅዶላቸው ዶላር አግኝተው ሲያስገቡ ደግሞ ትልቅ ትርፍ በማግኘት ነው የሚሸጡት።” የተሽከርካሪዎች ብቻ ሳይሆን የሌሎች ቁሳቁሶች ዋጋ መናር ዶላር በጥቁር ገበያ ካለው ዋጋ ጋር እንደሚገናኝ አቶ ጥላሁን ያስረዳሉ። “አንድ የአሜሪካን ዶላር ጥቁር ገበያው ላይ እስከ 90 ብር እየተመነዘረ ነው። መንግሥት ደግሞ በ53 ብር ተምኖታል። መኪና የሚያስገቡ አስመጪዎች ዶላር ከባንክ የሚጠይቁት ለይምሰል ነው እንጂ ዶላር ከጥቁር ገበያው እየገዙ ነው መኪና የሚያስገቡት። ታዲያ ይህንን የጥቁር ገበያ ዋጋ ነው ለገዢዎች የሚያስተላልፉት።” የቢዝነስ ድረ-ገፁ ብሉምበርግ ረቡዕ ዕለት ባወጣው ዘገባ በኢትዮጵያ ጥቁር ገበያ አንድ የአሜሪካን ዶላር እስከ 92 ብር እየተመነዘረ ነው ሲል ስማቸውን ያልተጠቀሱ ምንጮችን በመጥቀስ አስነብቧል። በተቃራኒው ባንኮች አንድ ዶላር በ52.5 ብር እየመነዘሩ እንደሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ብሉምበርግ፤ ዶላር በጥቁር ገበያውና በባንክ መካከል ላለው ልዩነት ትልቁ ምክንያት የሰሜን ኢትዮጵያው የእርስ በርስ ጦርነት ነው ሲል የማዕከላዊ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ዋና የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ፍቃዱ ድጋፌን ዋቢ በማድረግ ፅፏል። ኢትዮጵያ በዋጋ ንረት ከአፍሪካ አገራት በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሸቀጦች ዋጋ ግሽበት የተመዘገበው በምግብ እና በምግብ ነክ ቁሳቁሶች እንዲሁም በግንባታ ግብአቶች ላይ ነው። መንግሥት በተለያዩ ወቅቶች ለሸቀጦች እና ለቁሳቁሶች የዋጋ ተመን ቢያወጣም መሰል ፖሊሲዎች ከጥቂት ሳምንት በላይ ተግባራዊ አይሆኑም። ለምሳሌ በቅርቡ የሲሚንቶ ዋጋ መናርን ተከትሎ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አዲስ የዋጋ ተመን ማውጣቱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ሲሚንቶ ከፋብሪካ የሚወጣበት አዲሱ የዋጋ ተመን ዝቅተኛው 510 ብር ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ 683 ብር ከ44 ሳንቲም እንዲሆን ሚኒስቴሩ ወስኗል። ነገር ግን ይህ አዲስ ተመን ከወጣ በኋላ ሲሚንቶ እስከ 1050 ብር እየተሸጠ እንዳለ አንድ ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ ደላላ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የውጭ አገር ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንዲሠሩ መንግሥት መፍቀዱን ተከትሎ ያናገርናቸው የፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ሊቀ-መንበር ዘመዴነህ ንጋቱ ባንኮቹ ዶላር ይዘው መምጣታቸው ችግሩን ሊያቃልል እንደሚችል ያምናሉ። “እንደ አጭር ጊዜ መፍትሔ መንግሥት፤ ሕዝቡ በየቀኑ መሠረታዊ ፍጆታዎች ላይ ድጎማ ማድረግ አለበት” የሚሉት የፋይናንስ አማካሪው አቶ ጥላሁን ደግሞ “ነገር ግን ለዋጋ ግሽበት ዋናው መፍትሔ የግብር አሰባሰብ።” “ለምሳሌ እኔ ለተሽከርካሪዬ የመድን ፈንድ ለመክፈል በቅርቡ ሄጄ ነበር። ለአንድ ዓመት 125 ብር ብቻ ነው ያስከፈሉኝ። ይህ ምን ያደርግላቸዋል?” በማለት በግብር አሰባሰብ ሂደቱ ላይ ጥያቄ ያነሳሉ። “የግብር አሰባሰብ ሂደቱ በደንብ መታየት አለበት። ግብር ማለት ካለው ላይ ሰብስበህ ለሌለው እንደመስጠት ነው። በዚህ ላይ መንግሥት ጠንክሮ መሥራት አለበት።” ከዚህ ቀደም የዋጋ ግሽበትን አስመልክቶ ያናገርናቸው የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) “ችግሩ እጅግ ውስብስብ ስለሆነ” የአጭር ጊዜ መፍትሔ አለው ብለው እንደማያምኑ ገልጠዋል። ለንዶን የሚኖሩት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አብዱልመናን መሐመድ ደግሞ “መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ የሚበደረውን ገንዘብ መቀነስና አስፈላጊነታቸው ጥያቄ ውስጥ ያሉ ፕሮጀክቶችን ማቆም፣ አስፈላጊ የሚባሉ ፕሮጀክቶችንም ቢሆን ለጊዜው መፍትሔ እስኪገኝ ማዘግየት አለበት” ሲሉ መክረዋል። “የኢትዮጵያን ብር የመግዛት አቅም ከውጭ ምንዛሪ ጋር በተያያዘ የማውረድ እንቅስቃሴ ወደ አገር ቤት የሚገቡ እቃዎችን ስለሚያንር በአስቸኳይ መቆም አለበት፤ መንግሥት እነዚህን እርምጃዎች የሚወስድ ከሆነ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ውጤት ማየት ይቻላል” ይላሉ አብዱልመናን። የዓለም ባንክ፤ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ያስመዘገቡ አገራት የሕዝባቸውን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ላይ መትጋት አለባቸው ሲል ይመክራል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cw9dvwvnrv0o |
3politics
| በምሥራቅ ዩክሬን ዶንባስ የሚደረገው ጦርነት ደም አፋሳሽ እንዳይሆን ተፈርቷል | የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ወደ 2ኛ ወሩ እየተጠጋ ነው፡፡ ሩሲያ በሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮችን አጥታለች፡፡ በርካታ ጄኔራሎችም ተገድለውባታል፡፡ ዋና ከተማ ኪየቭን በአጭር ቀናት የመቆጣጠሩ ነገር አልሆነላትም፡፡ አሁን ኪየቭን የከበበው የሩሲያ ጦር ሙሉ በሙሉ ለቋል፡፡ ቭላድሚር ፑቲን፣ ከዚህ በኋላ ትኩረታችን በምሥራቅ ዩክሬን ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አዲስ ጄኔራልም ሾመዋል፡፡ ይህን ተከትሎም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊታቸው ወደ ምሥራቅ ዩክሬን እየገሰገሰ ነው፡፡ የዶንባስ ክልል አካል የሆነችው ቁልፏ የወደብ ከተማ ማሪዮፖል አልህ አስጨራሽ ጦርነት እየተደረገባት ይገኛል፡፡ በቀጣይ ቀናት በሩሲያ እጅ ልትወድቅ ትችላለች የሚሉ በርካታ ናቸው፡፡ በዚያ የሚገኙ የዩክሬን ተዋጊዎች ወደ 4ሺህ የሚጠጉ ሲሆን የሩሲያ ጦር ግን የዚህን ሦስት እጥፍ ይሆናል፡፡ የማሪዮፖል ከንቲባ በዚያች ከተማ በሩሲያ ወታደሮች የተገደሉ ሰላማዊ ሰዎች ቁጥር 21ሺህ ይጠጋል ሲሉ ትናንት ተናግረዋል፡፡ በዘግናኝና ኢሰብአዊ ሁኔታ የተገደሉ ዩክሬናዊያንም ሬሳዎቻቸው በድበቅ ቦታ በጅምላ እየተቀበረ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ማሪዮፖል እንደተፈራው በቀጣይ ቀናት በሩሲያ እጅ ከወደቀች ዶንባስ ክልል ዙርያውን ከበባ ውስጥ ይገባል የሚል ፍርሃት አለ፡፡ ዞሮ ዞሮ በቀጣይ ቀናት እና ሳምንታት በምሥራቃዊ ዩክሬን የሚኖረው ጦርነት ከእስከዛሬው ሁሉ የከፋና እልህ አስጨራሽ እንዲሁም ደም አፋሳሽ እንደሚሆን ከወዲሁ እየተነገረ ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል ዩክሬናዊያን ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ከዶንባስ ክልል ለመሸሽ እየተሸቀዳደሙ ያሉት፡፡ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ዉሾች እንኳ የሚሆነውን የተረዱ ይመስላሉ፡፡ ከርቀት የተኩስ ድምጽ በሰሙ ቁጥር ጩኸታቸው ያሰማሉ፤ ያላዝናሉ፡፡ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩት ዩክሬናዊያን ምሥራቁን ክፍል ጥለው እየሸሹ ያሉት በብዛት ወደ ምዕራብ ዩክሬን ነው፡፡ እስከአሁን ወደ 4.6 ሚሊዮን የሚጠጉ ዩክሬናዊያን ውድ አገራቸውን ጥለው ተሰደዋል፡፡ በዚህ ወቅት የሳተላይት ምሥሎች እንዳረጋገጡት የሩሲያ ሰራዊት በረዥም ሰልፍ ወደ ምሥራቅ እየተመመ ነው፡፡ የዩክሬን ሰራዊትም ሳይቀደም ለመቅደም ብረት ለበስ ተሸከርካሪዎችን፣ አየር መቃወሚያዎችን እና ሌሎች ከምዕራብ አገራት የተገኙ ውስብስብ የጦር መሣሪያዎችን ወደ ምሥራቅ በማጓጓዝ ተጠምዷል፡፡ ነገር ግን ከሩሲያ ሰራዊት ጋር ሲወዳደር ቁጥሩ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ በርካታ የጦር አዋቂዎች እንደሚሉት የምሥራቁ ጦርነት ወሳኝና አሸናፊ የሚኖር ከሆነም ያንኑ የሚለይ ይሆናል፡፡ ሁሉንም ተንታኞች ያስማማው ነጥብ ግን ይህ ጦርነት የዋዛ ጦርነት እንደማይሆን ነው፡፡ እጅግ ዘግናኝና ደማ አፋሳሹ ጦርነት ይኸው የምሥራቁ ጦርነት ነው ተብሎ ተፈርቷል፡፡ ቢቢሲ በዩክሬን ወታደሮች ፈቃድ የመከላከያ ምሽጎችን መመልከት የቻለ ሲሆን ወደ ስፍራው መድረስ የሚቻልበት ብቸኛው መንገድ ብረት ለበስ ተሽከርካሪን በመጠቀም ነው፡፡ ቢቢሲ በስፍራው እንዳይቀርጽ የተከለከላቸው በርካታ የአየር መቃወሚያዎችን፣ ራዳርና ሮኬቶችንም ተመልክቷል፡፡ ሩሲያ ጄት ወይም ድሮኖችን ከላከች በሚል እነሱን ለመምታት የተፈበረኩና ከምዕራብ አገራት ለዩክሬን የተለገሱ ውስብስብ መሣሪያዎችንም ቢቢሲ ለመመልከት ችሏል፡፡ ሩሲያ እስከዛሬ በነበረው ጦርነት በአየር ኃይል የበላይነት ብትይዝም ይህ ግን ከዚህ በኋላ ዘላቂ ላይሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡ ምክንያቱም አሁን ያገኘቻቸው መሣሪያዎች ዓይነትና ብዛት ነው፡፡ ሩሲያና ዩክሬን አሁን በስፍራው እያንዳንዳቸው ከ30 እስከ 40 ሺህ ሰራዊት እንደሚያሰልፉ ይጠበቃል፡፡ ሆኖም አንዳንድ ተንታኞች ሩሲያ በቅርብ ጊዜ ይህን የሰራዊት ቁጥር በሦስት እጥፍ እንደምታሳድግ ይናገራሉ፡፡ ሩሲያ ባለፉት ሳምንታት በተደረጉ ጦርነቶች የሰራዊቷን 20 ከመቶ አጥታለች የሚሉ ተንታኞች አሉ፡፡ በዚህም የተነሳ የሩሲያ ወታደሮች ላይ ብርታትና መነቃቃት አይታይም፤ እንደ ዩክሬናዊያን ለመዋጋት ሞራል የላቸውም ይላሉ የምዕራቡ ዓለም የጦር አዋቂዎች፡፡ የዩክሬናዊያን ወታደሮች ሞራልና የመዋጋት ፍላጎት በአንጻሩ ከፍ ያለ ነው፡፡ በጦርነቱ መሀል የምዕራብ አገራት አሜሪካን ጨምሮ ከፍተኛ የስለላና ደኅንነት ቁልፍ መረጃዎችን ወዲያውኑ ከዩክሬን ያቀብላሉ፡፡ ቢቢሲ ይህ እውነት ስለመሆኑ ከዩክሬንም ሆነ ከምዕራብ አገራቱ ማረጋገጫ አግኝቷል፡፡ ይህም ማለት የሩሲያ ሰራዊት እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል ለዩክሬን ወቅታዊ መረጃዎች እንዲደርሷት አውሮጳና አሜሪካ ተግተው ይሠራሉ፡፡ ይልቅ ለዩክሬናዊያን ራስ ምታት የሆኑት ሩሲያ ያሰማራቻቸው ሰላዮችና አሻጥረኞች ናቸው፡፡ ቢቢሲ በክራማቶር ከተማ አንድ ፖሊስ ጣቢያ በርካታ የሩሲያ አሻጥረኞች ናቸው የተባሉ እስረኞችን ለመመልከት ችሏል፡፡ በዩክሬን ለሩሲያ ስስ ልብ ያላቸው በርካታ ዩክሬናዊያን በብዛት የሚገኙት በዚህ ዶንባስ ክልል ነው፡፡ ለዚህም ነው ፖሊስ በየመንገዱ ነዋሪዎችን እያስቆመ ተደጋጋሚ ፍተሻን የሚያደርገው፡፡ ፑቲን ትናንት ከቤላሩሱ አጋራቸው አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ጋር ተገናኝተው መክረዋል፡፡ አገራቸው በዚህ ጦርነት ድል እንደምታስመዘግብም ተናግረዋል፡፡ የሰላም ተስፋ እንደሌለም ጠቁመዋል፡፡ ሉካሼንኮ በበኩላቸው ቤላሩስ ምንጊዜም ከሩሲያ ጎን ትቆማለች ብለዋል፡፡ በቀጣዮቹ ሳምንታት ምናልባትም በአውሮጳ ታሪክ ከ2ኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ፈጽሞ ያልታየ እልቂት ሊኖር ይችላል እየተባለ ነው፡፡ | በምሥራቅ ዩክሬን ዶንባስ የሚደረገው ጦርነት ደም አፋሳሽ እንዳይሆን ተፈርቷል የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ወደ 2ኛ ወሩ እየተጠጋ ነው፡፡ ሩሲያ በሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮችን አጥታለች፡፡ በርካታ ጄኔራሎችም ተገድለውባታል፡፡ ዋና ከተማ ኪየቭን በአጭር ቀናት የመቆጣጠሩ ነገር አልሆነላትም፡፡ አሁን ኪየቭን የከበበው የሩሲያ ጦር ሙሉ በሙሉ ለቋል፡፡ ቭላድሚር ፑቲን፣ ከዚህ በኋላ ትኩረታችን በምሥራቅ ዩክሬን ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አዲስ ጄኔራልም ሾመዋል፡፡ ይህን ተከትሎም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊታቸው ወደ ምሥራቅ ዩክሬን እየገሰገሰ ነው፡፡ የዶንባስ ክልል አካል የሆነችው ቁልፏ የወደብ ከተማ ማሪዮፖል አልህ አስጨራሽ ጦርነት እየተደረገባት ይገኛል፡፡ በቀጣይ ቀናት በሩሲያ እጅ ልትወድቅ ትችላለች የሚሉ በርካታ ናቸው፡፡ በዚያ የሚገኙ የዩክሬን ተዋጊዎች ወደ 4ሺህ የሚጠጉ ሲሆን የሩሲያ ጦር ግን የዚህን ሦስት እጥፍ ይሆናል፡፡ የማሪዮፖል ከንቲባ በዚያች ከተማ በሩሲያ ወታደሮች የተገደሉ ሰላማዊ ሰዎች ቁጥር 21ሺህ ይጠጋል ሲሉ ትናንት ተናግረዋል፡፡ በዘግናኝና ኢሰብአዊ ሁኔታ የተገደሉ ዩክሬናዊያንም ሬሳዎቻቸው በድበቅ ቦታ በጅምላ እየተቀበረ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ማሪዮፖል እንደተፈራው በቀጣይ ቀናት በሩሲያ እጅ ከወደቀች ዶንባስ ክልል ዙርያውን ከበባ ውስጥ ይገባል የሚል ፍርሃት አለ፡፡ ዞሮ ዞሮ በቀጣይ ቀናት እና ሳምንታት በምሥራቃዊ ዩክሬን የሚኖረው ጦርነት ከእስከዛሬው ሁሉ የከፋና እልህ አስጨራሽ እንዲሁም ደም አፋሳሽ እንደሚሆን ከወዲሁ እየተነገረ ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል ዩክሬናዊያን ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ከዶንባስ ክልል ለመሸሽ እየተሸቀዳደሙ ያሉት፡፡ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ዉሾች እንኳ የሚሆነውን የተረዱ ይመስላሉ፡፡ ከርቀት የተኩስ ድምጽ በሰሙ ቁጥር ጩኸታቸው ያሰማሉ፤ ያላዝናሉ፡፡ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩት ዩክሬናዊያን ምሥራቁን ክፍል ጥለው እየሸሹ ያሉት በብዛት ወደ ምዕራብ ዩክሬን ነው፡፡ እስከአሁን ወደ 4.6 ሚሊዮን የሚጠጉ ዩክሬናዊያን ውድ አገራቸውን ጥለው ተሰደዋል፡፡ በዚህ ወቅት የሳተላይት ምሥሎች እንዳረጋገጡት የሩሲያ ሰራዊት በረዥም ሰልፍ ወደ ምሥራቅ እየተመመ ነው፡፡ የዩክሬን ሰራዊትም ሳይቀደም ለመቅደም ብረት ለበስ ተሸከርካሪዎችን፣ አየር መቃወሚያዎችን እና ሌሎች ከምዕራብ አገራት የተገኙ ውስብስብ የጦር መሣሪያዎችን ወደ ምሥራቅ በማጓጓዝ ተጠምዷል፡፡ ነገር ግን ከሩሲያ ሰራዊት ጋር ሲወዳደር ቁጥሩ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ በርካታ የጦር አዋቂዎች እንደሚሉት የምሥራቁ ጦርነት ወሳኝና አሸናፊ የሚኖር ከሆነም ያንኑ የሚለይ ይሆናል፡፡ ሁሉንም ተንታኞች ያስማማው ነጥብ ግን ይህ ጦርነት የዋዛ ጦርነት እንደማይሆን ነው፡፡ እጅግ ዘግናኝና ደማ አፋሳሹ ጦርነት ይኸው የምሥራቁ ጦርነት ነው ተብሎ ተፈርቷል፡፡ ቢቢሲ በዩክሬን ወታደሮች ፈቃድ የመከላከያ ምሽጎችን መመልከት የቻለ ሲሆን ወደ ስፍራው መድረስ የሚቻልበት ብቸኛው መንገድ ብረት ለበስ ተሽከርካሪን በመጠቀም ነው፡፡ ቢቢሲ በስፍራው እንዳይቀርጽ የተከለከላቸው በርካታ የአየር መቃወሚያዎችን፣ ራዳርና ሮኬቶችንም ተመልክቷል፡፡ ሩሲያ ጄት ወይም ድሮኖችን ከላከች በሚል እነሱን ለመምታት የተፈበረኩና ከምዕራብ አገራት ለዩክሬን የተለገሱ ውስብስብ መሣሪያዎችንም ቢቢሲ ለመመልከት ችሏል፡፡ ሩሲያ እስከዛሬ በነበረው ጦርነት በአየር ኃይል የበላይነት ብትይዝም ይህ ግን ከዚህ በኋላ ዘላቂ ላይሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡ ምክንያቱም አሁን ያገኘቻቸው መሣሪያዎች ዓይነትና ብዛት ነው፡፡ ሩሲያና ዩክሬን አሁን በስፍራው እያንዳንዳቸው ከ30 እስከ 40 ሺህ ሰራዊት እንደሚያሰልፉ ይጠበቃል፡፡ ሆኖም አንዳንድ ተንታኞች ሩሲያ በቅርብ ጊዜ ይህን የሰራዊት ቁጥር በሦስት እጥፍ እንደምታሳድግ ይናገራሉ፡፡ ሩሲያ ባለፉት ሳምንታት በተደረጉ ጦርነቶች የሰራዊቷን 20 ከመቶ አጥታለች የሚሉ ተንታኞች አሉ፡፡ በዚህም የተነሳ የሩሲያ ወታደሮች ላይ ብርታትና መነቃቃት አይታይም፤ እንደ ዩክሬናዊያን ለመዋጋት ሞራል የላቸውም ይላሉ የምዕራቡ ዓለም የጦር አዋቂዎች፡፡ የዩክሬናዊያን ወታደሮች ሞራልና የመዋጋት ፍላጎት በአንጻሩ ከፍ ያለ ነው፡፡ በጦርነቱ መሀል የምዕራብ አገራት አሜሪካን ጨምሮ ከፍተኛ የስለላና ደኅንነት ቁልፍ መረጃዎችን ወዲያውኑ ከዩክሬን ያቀብላሉ፡፡ ቢቢሲ ይህ እውነት ስለመሆኑ ከዩክሬንም ሆነ ከምዕራብ አገራቱ ማረጋገጫ አግኝቷል፡፡ ይህም ማለት የሩሲያ ሰራዊት እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል ለዩክሬን ወቅታዊ መረጃዎች እንዲደርሷት አውሮጳና አሜሪካ ተግተው ይሠራሉ፡፡ ይልቅ ለዩክሬናዊያን ራስ ምታት የሆኑት ሩሲያ ያሰማራቻቸው ሰላዮችና አሻጥረኞች ናቸው፡፡ ቢቢሲ በክራማቶር ከተማ አንድ ፖሊስ ጣቢያ በርካታ የሩሲያ አሻጥረኞች ናቸው የተባሉ እስረኞችን ለመመልከት ችሏል፡፡ በዩክሬን ለሩሲያ ስስ ልብ ያላቸው በርካታ ዩክሬናዊያን በብዛት የሚገኙት በዚህ ዶንባስ ክልል ነው፡፡ ለዚህም ነው ፖሊስ በየመንገዱ ነዋሪዎችን እያስቆመ ተደጋጋሚ ፍተሻን የሚያደርገው፡፡ ፑቲን ትናንት ከቤላሩሱ አጋራቸው አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ጋር ተገናኝተው መክረዋል፡፡ አገራቸው በዚህ ጦርነት ድል እንደምታስመዘግብም ተናግረዋል፡፡ የሰላም ተስፋ እንደሌለም ጠቁመዋል፡፡ ሉካሼንኮ በበኩላቸው ቤላሩስ ምንጊዜም ከሩሲያ ጎን ትቆማለች ብለዋል፡፡ በቀጣዮቹ ሳምንታት ምናልባትም በአውሮጳ ታሪክ ከ2ኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ፈጽሞ ያልታየ እልቂት ሊኖር ይችላል እየተባለ ነው፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-61090526 |
2health
| አውሮጳ፡ የፖርቹጋሉ ፕሬዚደንት በባህር ማዕበል ሲናወጡ የነበሩ ሁለት ሴቶችን ታደጉ | የፖርቹጋሉ ፕሬዚደንት ማርሴሎ ሬቤሎ ደ ሶውሳ በአልጋርቭ የባህር ዳርቻ የሽርሽር ጀልባቸው ተገልብጣባቸው ነፍሳቸውን ለማትረፍ ሲታገሉ የነበሩ ሁለት ሴቶችን ሕይወት መታደጋቸው ተገለፀ። የ71 ዓመቱ ፕሬዚደንት ቅዳሜ እለት በማዕበል እየተናወጡ የነበሩ ሴቶችን ለመታደግ ወደ ጀልባዋ ሲዋኙ የሚያሳይ ምስሎች ወጥተዋል። ፕሬዚደንት ሬቤሎ ዲ ሶውሳ በእረፍት ላይ የነበሩ ሲሆን፣ ጊዜያቸውን ቱሪዝምን ለማስተዋወቅ የተለያዩ ቦታዎችን በመጎብኘት እያሳለፉ እንደሆነ ተገልጿል። በወቅቱም በአልጋርቭ የባህር ዳርቻ ነበሩ። ሴቶቹ ከውሃው ለመውጣት ሲታገሉ የተመለከቱትም ከጋዜጠኞች ጋር እየተነጋገሩ ባለበት ጊዜ እንደነበር የጠቀሱት ፕሬዚደንቱ፤ በአቅራቢያ ካለ የባህር ዳርቻ በማዕበል ተገፍተው እንደመጡም በኋላ ላይ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። በመገናኛ ብዙኀን ይፋ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎችም ፕሬዚደንቱ ሴቶቹን ለመርዳት እየዋኙ ሲሄዱ አሳይተዋል። ሲደርሱ ግን ሌላ ሰው ቀድሟቸው እነርሱን ለመርዳት እየሞከረ ነበር ያገኙት። ከዚያም ሌላ ግለሰብ የሞተር ጀልባ ይዞ እርዳታ ለመስጠት በሥፍራው ደርሷል። የሞተር ጀልባ ይዞ የደረሰው ግለሰብም ጀልባዋን ወደ ባህር ዳርቻው ማውጣት ችሏል። እርሳቸውም ጀልባዋን ወደ ነበረችበት ለመመለስ ፈታኝ እንደነበር ገልፀው፤ የሞተር ጀልባ የያዘው ግለሰብ እርዳታ እንዳደረገላቸው ተናግረዋል። ለወደፊቱ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሴቶቹን አሳስበዋቸዋል። ፖርቹጋል በርካታ እንግሊዛዊያን ጎብኝዎች ያሏት ሲሆን በዓመት ከ3 ሚሊየን በላይ ጎብኝዎች የሚጎርፉትም ከዩናይትድ ኪንግደም ነው። ከዩናይትድ ኪንግደም የሚመጡ ጎብኝዎችም በአብዛኛው የሚሄዱት ወደ አልጋርቭ ባህር ዳርቻዎች ነው። ፖርቹጋል በዋናነት ኢኮኖሚዋ የተመሰረተው በቱሪዝም ኢንዱስትሪ ላይ ቢሆንም በዘንድሮው ዓመት ግን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ዘርፉ ከፍተኛ ተፅዕኖ ደርሶባታል። | አውሮጳ፡ የፖርቹጋሉ ፕሬዚደንት በባህር ማዕበል ሲናወጡ የነበሩ ሁለት ሴቶችን ታደጉ የፖርቹጋሉ ፕሬዚደንት ማርሴሎ ሬቤሎ ደ ሶውሳ በአልጋርቭ የባህር ዳርቻ የሽርሽር ጀልባቸው ተገልብጣባቸው ነፍሳቸውን ለማትረፍ ሲታገሉ የነበሩ ሁለት ሴቶችን ሕይወት መታደጋቸው ተገለፀ። የ71 ዓመቱ ፕሬዚደንት ቅዳሜ እለት በማዕበል እየተናወጡ የነበሩ ሴቶችን ለመታደግ ወደ ጀልባዋ ሲዋኙ የሚያሳይ ምስሎች ወጥተዋል። ፕሬዚደንት ሬቤሎ ዲ ሶውሳ በእረፍት ላይ የነበሩ ሲሆን፣ ጊዜያቸውን ቱሪዝምን ለማስተዋወቅ የተለያዩ ቦታዎችን በመጎብኘት እያሳለፉ እንደሆነ ተገልጿል። በወቅቱም በአልጋርቭ የባህር ዳርቻ ነበሩ። ሴቶቹ ከውሃው ለመውጣት ሲታገሉ የተመለከቱትም ከጋዜጠኞች ጋር እየተነጋገሩ ባለበት ጊዜ እንደነበር የጠቀሱት ፕሬዚደንቱ፤ በአቅራቢያ ካለ የባህር ዳርቻ በማዕበል ተገፍተው እንደመጡም በኋላ ላይ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። በመገናኛ ብዙኀን ይፋ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎችም ፕሬዚደንቱ ሴቶቹን ለመርዳት እየዋኙ ሲሄዱ አሳይተዋል። ሲደርሱ ግን ሌላ ሰው ቀድሟቸው እነርሱን ለመርዳት እየሞከረ ነበር ያገኙት። ከዚያም ሌላ ግለሰብ የሞተር ጀልባ ይዞ እርዳታ ለመስጠት በሥፍራው ደርሷል። የሞተር ጀልባ ይዞ የደረሰው ግለሰብም ጀልባዋን ወደ ባህር ዳርቻው ማውጣት ችሏል። እርሳቸውም ጀልባዋን ወደ ነበረችበት ለመመለስ ፈታኝ እንደነበር ገልፀው፤ የሞተር ጀልባ የያዘው ግለሰብ እርዳታ እንዳደረገላቸው ተናግረዋል። ለወደፊቱ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሴቶቹን አሳስበዋቸዋል። ፖርቹጋል በርካታ እንግሊዛዊያን ጎብኝዎች ያሏት ሲሆን በዓመት ከ3 ሚሊየን በላይ ጎብኝዎች የሚጎርፉትም ከዩናይትድ ኪንግደም ነው። ከዩናይትድ ኪንግደም የሚመጡ ጎብኝዎችም በአብዛኛው የሚሄዱት ወደ አልጋርቭ ባህር ዳርቻዎች ነው። ፖርቹጋል በዋናነት ኢኮኖሚዋ የተመሰረተው በቱሪዝም ኢንዱስትሪ ላይ ቢሆንም በዘንድሮው ዓመት ግን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ዘርፉ ከፍተኛ ተፅዕኖ ደርሶባታል። | https://www.bbc.com/amharic/53803506 |
0business
| በአፍሪካ አየር ላይ ‘የአንበሳውን ድርሻ’ እየያዘ ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ | 75 ዓመታት በሙሉ ስመ ገናና ሆኖ ዘልቋል-የኢትዮጵያ አየር መንገድ። ለስመ ገናናነቱም መገለጫ ከሆነው አንዱ ከበርካታ አየር መንገዶች ልቆ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደጋጋሚ ሽልማቶችን መቀዳጀቱ ነው። የአውሮፕላን ጭነት ዘርፍ የደንበኞች መስተንግዶ ሽልማትን በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜም ያሸነፈው በቅርቡ ነው። አየር መንገዱ የዘንድሮውን፣ የ2022 የአፔክስ ክልላዊ የመንገደኞች ምርጫ ሽልማት ላይ በአፍሪካ ምርጥ አገልግሎትን በመስጠት 'Best Entertainment ' እና 'Best cabin service ' በሚል ዘርፎች አሸናፊም ሆኗል። ለተወዳዳሪነቱ በርካቶች የሚመሰክሩለት አየር መንገዱ የኢትዮጵያ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የዘርፈ ብዙ ሽልማቶች ተሸላሚና በአፍሪካ ትልቁ የአየር ዕቃ ጭነት አገልግሎት ሰጪም ነው። በርካታ ሽልማቶችን በማሸነፍ በዓለም ላይ ስመ ጥርና በአቪየሽን ኢንዱስትሩው ዘርፍም ከሚጠቀሱት አንዱ አድርጎታል። ከሰባት አስርት ዓመታት በላይ ወደ ኋላ ታሪክን ስንዳስስ አየር መንገዱ ሲ-47 በተባሉ ቀደምት አውሮፕላኖች በአውሮፓውያኑ 1946 ሥራውን መጀመሩን ከድረ ገጹ ላይ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። በወቅቱም ካይሮ፣ ጅቡቲ እና ኤደን ከመጀመሪያ መዳረሻዎቹ መካከል መሆናቸው ተጠቅሷል። ጅማ ደግሞ ቀዳሚዋ የአገር ውስጥ መዳረሻ ነበረች። ሥራውን ሲጀምር የነበሩት ሲ-47 አውሮፕላኖች ቁጥር በዚያው ዓመት ዘጠኝ ደረሱ። እነዚህ አውሮፕላኖች ቀደም ሲል ለአሜሪካ ጦር ግልጋሎት የሰጡ ሲሆን ተጣጣፊ መቀመጫዎችም የተገጠሙላቸው ነበሩ። ከሸራ ከተሰሩት መቀመጫዎች በተጨማሪ የተሳፋሪዎችን ዕቃ ለመጫን መተላለፊያዎቹ ጥቅም ላይ ይውሉ ነበር። ፊት ለፊት ‘ተፋጠው’ የሚሄዱባቸው መቀመጫዎች የተገጠሙላቸው አውሮፕላኖችም ነበሩት። በመቀጠልም መዳረሻዎቹን በማሳደግ አየር መንገዱ ወደ ናይሮቢ፣ ፖርት ሱዳን እና ቦምቤይ በረራዎችን ማድረግ ጀመረ። በዚህ መንገድ ወደ ስኬት መንደርደር የጀመረው አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት ከ22 በላይ የአገር ውስጥ መዳረሻዎች አሉት። ከ130 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችንም ያካልላል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ቀዳሚ ከሆኑት አየር መንገዶች አንዱ ነው። በአህጉሩ ያለውን ተቀባይነት ለማስፋትም ደፋ ቀና እያለ ሲሆን በዋነኝነትም በአህጉሪቱ ውስጥ በሚገኙ የአየር መንገዶች ድርሻ መግዛትን ተያይዟል። አየር መንገዱ በዘርፉ የአህጉሩን ‘የአንበሳ ድርሻ’ ለመያዝ እንደቻለም አስታውቋል ። በተለያዩ የአህጉሪቱ አየር መንገዶች ድርሻ በመያዝም ስድስት የሚበልጡ የአፍሪካ አገራትን ደርሷል። በአውሮፓውያኑ 2025 ቀዳሚው የአፍሪካ አየር መንገድ ለመሆን ዕቅድ አውጥቶ እየተገበረም ነው። ይህንን እቅድ ለማሳካት ደግሞ ከአንዳንድ የአፍሪካ አየር መንገዶች ጋር በሽርክና በመሥራት ላይ ይገኛል። በአስተዳደራዊ እና በስትራቴጂክ አጋርነት ከእነዚህ አገራት አየር መንገዶች ጋር ይሠራል። በተጨማሪም በአንዳንድ አገራት ያሉ አየር መንገዶችን ድርሻ እስከ መግዛትም ደርሷል። በአንዳንድ በረራዎች ወቅት የተለያዩ አየር መንገዶች ስም እና አርማ ባረፉባቸው አውሮፕላኖች በረው ይሆናል። እነዚህ አውሮፕላኖች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በሽርክና የሚሠሩ አየር መንገዶች ሊሆኑም ይችላሉ። ለመሆኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ያለው ተሳትፎ ምን ይመስላል? የተወሰኑትን እንመልከት። 'ኤይር ኮንጎ' የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አየር መንገድ ሲሆን ከፍተኛ ባለቤትነቱን የአገሪቱ መንግሥት ነው የተቆጣጠረው። የአገሪቱ መንግሥት ከአየር መንገዱ ድርሻ 51 በመቶውን ይይዛል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ ቀሪውን 49 በመቶ በመያዝ ሥራቸውን በጋራ ያከናውናሉ።\n'ኤይር ኮንጎ' ከአስር የሚበልጡ አውሮፕላኖች ባለቤት ነው። ከእነዚህም ውስጥ ዳሽ 8-400፣ ቦይንግ 737 እና ቦይንግ 787 ተጠቃሽ ናቸው። ለአየር መንገዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ተጨማሪ አውሮፕላኖችን ያቀርባል። የዛምቢያ አየር መንገድ የዛምቢያ ሪፐብሊክ አየር መንገድ መሆኑን ከድረ ገጹ የተገኘው መረጃ የሚያስረዳ ሲሆን መቀመጫውም ሉሳካ ነው። በቅርቡ ሥራ ከጀመረው አየር መንገድ 45 በመቶ ድርሻው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው። ቀሪው ድርሻ የአገሪቱ ነው። ሥራቸውንም በቦምባርዲየር ኪው-400 ጀምረዋል። አየር መንገዱ ቀደምት ከሚባሉት አንዱ የነበረ ሲሆን የኋላ ኋላ ግን በደረሰበት ኪሳራ ከሥራ ውጭ ሆኖ ነበር። በሞዛምቢክ የሚገኘው አየር መንገድ- የኢትዮጵያ ሞዛምቢክ አየር መንገድ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። ይህ ጥምረት የተጀመረው በአውሮፓውያኑ 2018 ነበር። ሥራው ሲጀመር በዋናነት የአገር ውስጥ በረራ ላይ ትኩረት አድርጎ ነው። በአገር ውስጥ ከዘጠኝ በላይ መዳረሻዎች ነበሩት። ለእነዚህ በረራዎች ኪው 400 የሚባሉ አውሮፕላኖችን ይጠቀማል። የኮቪድ ወረርሽኝ ከፍተኛ ደረጃ በደረሰበት ወቅት ሥራቸው ተቋርጦ ቢቆይም በኋላም ወደ በረራ ገብተዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ 99 በመቶ የሚደርስ ድርሻ እንዳለው ታውቋል። መቀመጫውን ማፑቶ ሞዛምቢክ አድርጓል። የዓለም አቀፍ በረራዎቹን በቅብብሎሽ በአዲስ አበባ በኩል ነው የሚያደርግ ይሆናል። 'ኤስካይ' ዋና መቀመጫውን ቶጎ ሎሜ ያደረገ አየር መንገድ ነው። ኤስካይ በዋናነት ትኩረቱን በምዕራብ እና በመካከለኛው አፍሪካ አገራት ላይ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በምዕራብ አፍሪካ ለሚሰጠው አገልግሎት ድጋፍ ያደርጋል። ሁለቱ አየር መንገዶች በጋራ ለመስራት ከስምምነት ደርሰዋል። ይህ ስምምነት የቴክኒክ እና የስተራቴጂያዊ አጋርነት መሆኑ ተጠቅሷል። አየር መንገዶቹ መንገደኞችን በመለዋወጥም አብረው ይሠራሉ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ አቅንቶም አገልግሎቱን አስፋፍቶ በመስራት ላይ ይገኛል። ማላዊ አየር መንገድ የሃገሪቱ ንብረት ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዚህን አየር መንገድ 49 በመቶ ድርሻ ይዟል። የአየር መንገዱን አስተዳደር ሥራዎችንም ያከናውናል። ስምምነቱ በኢትዮጵያ እና በማላዊ አየር መንገድ መካከል በአውሮፓውያኑ ሐምሌ 11/2007 ተፈረመ። በዚህ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና አዲስ የተቋቋመው የማላዊ አየር መንገድ የበረራ መርሃ ግብራቸውን በማጣጣም ለመንገደኞች ምርጥ አማራጮችን ያቀርባሉ ተብሏል። አየር መንገዱ በኪው 400 እና ቦይንግ ቢ737-700 በተሰኙ አውሮፕላኖች የበረራ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አየር መንገድ ለመመስረት ከቻድ መንግሥት ጋር የተስማማው በአውሮፓውያኑ ነሐሴ 2018 ነበር። 'ቻዲያ' አየር መንገድ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። 49 በመቶ ድርሻ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲሆን መቀመጫውንም በቻድ ዋና ከተማ አድርጓል። ሥራው የተጀመረው ስምምነቱ በተፈረመበት ዓመት በአገር ውስጥ በረራ ነው። በአዲስ አበባ በኩል ደግሞ ከመካከለኛው ምሥራቅ እና ከተቀረው ዓለም ጋር ይገናኛል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኢኳቶሪያል ጊኒው ሲ2-ሲዬባ ኢንተርኮንቲኔንታል ጋርም ውል አለው። አየር መንገዱ መቀመጫውን ኢኳቶሪያል ጊኒ ማላቦ አድርጓል። ሁለቱ አየር መንገዶች አስተዳደራዊ ስምምነት የደረሱት በአውሮፓውያኑ የካቲት 2018 ነው። ለዓለም አቀፍ በረራዎች አዲስ አበባ ማዕከል ሆና ታገለግላለች። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጨማሪ ከሌሎች የአፍሪካ አየር መንገዶች ጋር ውል በመፈጸም በጋራ ይሰራል። በዚህም በአህጉሪቱ ውስጥ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ አልሟል። ባወጣው የ15 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ በአውሮፓውያኑ 2025 የአህጉሪቱ ተቀዳሚ አየር መንገድ ለመሆን በመሥራት ላይ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዳዲስ አውሮፕላኖችን በማስገባትም ይታወቃል። ከአንድ ወር በፊት አምስት ቦይንግ ቢ777 የጭነት አውሮፕላኖችን ለመግዛት አዟል። አየር መንገዱ ከ80 በላይ የቦይንግ አውሮፕላኖችን በመጠቀም ላይ ይገኛል። በአፍሪካ ትርፋማ ከሆኑ አየር መንገዶችም ቀዳሚው በመሆን ይታወቃል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮሮና ወረርሽኝ በፊት በነበሩት ሰባት ተከታታይ ዓመታትም 25 በመቶ ዕድገት ማስመዝገብ ችሏል። | በአፍሪካ አየር ላይ ‘የአንበሳውን ድርሻ’ እየያዘ ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 75 ዓመታት በሙሉ ስመ ገናና ሆኖ ዘልቋል-የኢትዮጵያ አየር መንገድ። ለስመ ገናናነቱም መገለጫ ከሆነው አንዱ ከበርካታ አየር መንገዶች ልቆ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደጋጋሚ ሽልማቶችን መቀዳጀቱ ነው። የአውሮፕላን ጭነት ዘርፍ የደንበኞች መስተንግዶ ሽልማትን በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜም ያሸነፈው በቅርቡ ነው። አየር መንገዱ የዘንድሮውን፣ የ2022 የአፔክስ ክልላዊ የመንገደኞች ምርጫ ሽልማት ላይ በአፍሪካ ምርጥ አገልግሎትን በመስጠት 'Best Entertainment ' እና 'Best cabin service ' በሚል ዘርፎች አሸናፊም ሆኗል። ለተወዳዳሪነቱ በርካቶች የሚመሰክሩለት አየር መንገዱ የኢትዮጵያ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የዘርፈ ብዙ ሽልማቶች ተሸላሚና በአፍሪካ ትልቁ የአየር ዕቃ ጭነት አገልግሎት ሰጪም ነው። በርካታ ሽልማቶችን በማሸነፍ በዓለም ላይ ስመ ጥርና በአቪየሽን ኢንዱስትሩው ዘርፍም ከሚጠቀሱት አንዱ አድርጎታል። ከሰባት አስርት ዓመታት በላይ ወደ ኋላ ታሪክን ስንዳስስ አየር መንገዱ ሲ-47 በተባሉ ቀደምት አውሮፕላኖች በአውሮፓውያኑ 1946 ሥራውን መጀመሩን ከድረ ገጹ ላይ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። በወቅቱም ካይሮ፣ ጅቡቲ እና ኤደን ከመጀመሪያ መዳረሻዎቹ መካከል መሆናቸው ተጠቅሷል። ጅማ ደግሞ ቀዳሚዋ የአገር ውስጥ መዳረሻ ነበረች። ሥራውን ሲጀምር የነበሩት ሲ-47 አውሮፕላኖች ቁጥር በዚያው ዓመት ዘጠኝ ደረሱ። እነዚህ አውሮፕላኖች ቀደም ሲል ለአሜሪካ ጦር ግልጋሎት የሰጡ ሲሆን ተጣጣፊ መቀመጫዎችም የተገጠሙላቸው ነበሩ። ከሸራ ከተሰሩት መቀመጫዎች በተጨማሪ የተሳፋሪዎችን ዕቃ ለመጫን መተላለፊያዎቹ ጥቅም ላይ ይውሉ ነበር። ፊት ለፊት ‘ተፋጠው’ የሚሄዱባቸው መቀመጫዎች የተገጠሙላቸው አውሮፕላኖችም ነበሩት። በመቀጠልም መዳረሻዎቹን በማሳደግ አየር መንገዱ ወደ ናይሮቢ፣ ፖርት ሱዳን እና ቦምቤይ በረራዎችን ማድረግ ጀመረ። በዚህ መንገድ ወደ ስኬት መንደርደር የጀመረው አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት ከ22 በላይ የአገር ውስጥ መዳረሻዎች አሉት። ከ130 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችንም ያካልላል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ቀዳሚ ከሆኑት አየር መንገዶች አንዱ ነው። በአህጉሩ ያለውን ተቀባይነት ለማስፋትም ደፋ ቀና እያለ ሲሆን በዋነኝነትም በአህጉሪቱ ውስጥ በሚገኙ የአየር መንገዶች ድርሻ መግዛትን ተያይዟል። አየር መንገዱ በዘርፉ የአህጉሩን ‘የአንበሳ ድርሻ’ ለመያዝ እንደቻለም አስታውቋል ። በተለያዩ የአህጉሪቱ አየር መንገዶች ድርሻ በመያዝም ስድስት የሚበልጡ የአፍሪካ አገራትን ደርሷል። በአውሮፓውያኑ 2025 ቀዳሚው የአፍሪካ አየር መንገድ ለመሆን ዕቅድ አውጥቶ እየተገበረም ነው። ይህንን እቅድ ለማሳካት ደግሞ ከአንዳንድ የአፍሪካ አየር መንገዶች ጋር በሽርክና በመሥራት ላይ ይገኛል። በአስተዳደራዊ እና በስትራቴጂክ አጋርነት ከእነዚህ አገራት አየር መንገዶች ጋር ይሠራል። በተጨማሪም በአንዳንድ አገራት ያሉ አየር መንገዶችን ድርሻ እስከ መግዛትም ደርሷል። በአንዳንድ በረራዎች ወቅት የተለያዩ አየር መንገዶች ስም እና አርማ ባረፉባቸው አውሮፕላኖች በረው ይሆናል። እነዚህ አውሮፕላኖች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በሽርክና የሚሠሩ አየር መንገዶች ሊሆኑም ይችላሉ። ለመሆኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ያለው ተሳትፎ ምን ይመስላል? የተወሰኑትን እንመልከት። 'ኤይር ኮንጎ' የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አየር መንገድ ሲሆን ከፍተኛ ባለቤትነቱን የአገሪቱ መንግሥት ነው የተቆጣጠረው። የአገሪቱ መንግሥት ከአየር መንገዱ ድርሻ 51 በመቶውን ይይዛል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ ቀሪውን 49 በመቶ በመያዝ ሥራቸውን በጋራ ያከናውናሉ።\n'ኤይር ኮንጎ' ከአስር የሚበልጡ አውሮፕላኖች ባለቤት ነው። ከእነዚህም ውስጥ ዳሽ 8-400፣ ቦይንግ 737 እና ቦይንግ 787 ተጠቃሽ ናቸው። ለአየር መንገዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ተጨማሪ አውሮፕላኖችን ያቀርባል። የዛምቢያ አየር መንገድ የዛምቢያ ሪፐብሊክ አየር መንገድ መሆኑን ከድረ ገጹ የተገኘው መረጃ የሚያስረዳ ሲሆን መቀመጫውም ሉሳካ ነው። በቅርቡ ሥራ ከጀመረው አየር መንገድ 45 በመቶ ድርሻው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው። ቀሪው ድርሻ የአገሪቱ ነው። ሥራቸውንም በቦምባርዲየር ኪው-400 ጀምረዋል። አየር መንገዱ ቀደምት ከሚባሉት አንዱ የነበረ ሲሆን የኋላ ኋላ ግን በደረሰበት ኪሳራ ከሥራ ውጭ ሆኖ ነበር። በሞዛምቢክ የሚገኘው አየር መንገድ- የኢትዮጵያ ሞዛምቢክ አየር መንገድ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። ይህ ጥምረት የተጀመረው በአውሮፓውያኑ 2018 ነበር። ሥራው ሲጀመር በዋናነት የአገር ውስጥ በረራ ላይ ትኩረት አድርጎ ነው። በአገር ውስጥ ከዘጠኝ በላይ መዳረሻዎች ነበሩት። ለእነዚህ በረራዎች ኪው 400 የሚባሉ አውሮፕላኖችን ይጠቀማል። የኮቪድ ወረርሽኝ ከፍተኛ ደረጃ በደረሰበት ወቅት ሥራቸው ተቋርጦ ቢቆይም በኋላም ወደ በረራ ገብተዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ 99 በመቶ የሚደርስ ድርሻ እንዳለው ታውቋል። መቀመጫውን ማፑቶ ሞዛምቢክ አድርጓል። የዓለም አቀፍ በረራዎቹን በቅብብሎሽ በአዲስ አበባ በኩል ነው የሚያደርግ ይሆናል። 'ኤስካይ' ዋና መቀመጫውን ቶጎ ሎሜ ያደረገ አየር መንገድ ነው። ኤስካይ በዋናነት ትኩረቱን በምዕራብ እና በመካከለኛው አፍሪካ አገራት ላይ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በምዕራብ አፍሪካ ለሚሰጠው አገልግሎት ድጋፍ ያደርጋል። ሁለቱ አየር መንገዶች በጋራ ለመስራት ከስምምነት ደርሰዋል። ይህ ስምምነት የቴክኒክ እና የስተራቴጂያዊ አጋርነት መሆኑ ተጠቅሷል። አየር መንገዶቹ መንገደኞችን በመለዋወጥም አብረው ይሠራሉ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ አቅንቶም አገልግሎቱን አስፋፍቶ በመስራት ላይ ይገኛል። ማላዊ አየር መንገድ የሃገሪቱ ንብረት ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዚህን አየር መንገድ 49 በመቶ ድርሻ ይዟል። የአየር መንገዱን አስተዳደር ሥራዎችንም ያከናውናል። ስምምነቱ በኢትዮጵያ እና በማላዊ አየር መንገድ መካከል በአውሮፓውያኑ ሐምሌ 11/2007 ተፈረመ። በዚህ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና አዲስ የተቋቋመው የማላዊ አየር መንገድ የበረራ መርሃ ግብራቸውን በማጣጣም ለመንገደኞች ምርጥ አማራጮችን ያቀርባሉ ተብሏል። አየር መንገዱ በኪው 400 እና ቦይንግ ቢ737-700 በተሰኙ አውሮፕላኖች የበረራ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አየር መንገድ ለመመስረት ከቻድ መንግሥት ጋር የተስማማው በአውሮፓውያኑ ነሐሴ 2018 ነበር። 'ቻዲያ' አየር መንገድ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። 49 በመቶ ድርሻ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲሆን መቀመጫውንም በቻድ ዋና ከተማ አድርጓል። ሥራው የተጀመረው ስምምነቱ በተፈረመበት ዓመት በአገር ውስጥ በረራ ነው። በአዲስ አበባ በኩል ደግሞ ከመካከለኛው ምሥራቅ እና ከተቀረው ዓለም ጋር ይገናኛል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኢኳቶሪያል ጊኒው ሲ2-ሲዬባ ኢንተርኮንቲኔንታል ጋርም ውል አለው። አየር መንገዱ መቀመጫውን ኢኳቶሪያል ጊኒ ማላቦ አድርጓል። ሁለቱ አየር መንገዶች አስተዳደራዊ ስምምነት የደረሱት በአውሮፓውያኑ የካቲት 2018 ነው። ለዓለም አቀፍ በረራዎች አዲስ አበባ ማዕከል ሆና ታገለግላለች። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጨማሪ ከሌሎች የአፍሪካ አየር መንገዶች ጋር ውል በመፈጸም በጋራ ይሰራል። በዚህም በአህጉሪቱ ውስጥ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ አልሟል። ባወጣው የ15 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ በአውሮፓውያኑ 2025 የአህጉሪቱ ተቀዳሚ አየር መንገድ ለመሆን በመሥራት ላይ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዳዲስ አውሮፕላኖችን በማስገባትም ይታወቃል። ከአንድ ወር በፊት አምስት ቦይንግ ቢ777 የጭነት አውሮፕላኖችን ለመግዛት አዟል። አየር መንገዱ ከ80 በላይ የቦይንግ አውሮፕላኖችን በመጠቀም ላይ ይገኛል። በአፍሪካ ትርፋማ ከሆኑ አየር መንገዶችም ቀዳሚው በመሆን ይታወቃል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮሮና ወረርሽኝ በፊት በነበሩት ሰባት ተከታታይ ዓመታትም 25 በመቶ ዕድገት ማስመዝገብ ችሏል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cd15revlryqo |
3politics
| ምርጫ ቦርድ በአቶ ዳውድ ኢብሳ ላይ የተጣለው የመንቀሳቀስ ገደብ በአስቸኳይ እንዲነሳ ጠየቀ | የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የረጅም ጊዜ ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳ አንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ከቤታቸው እንዳይወጡ ተከልክለው በቁም እስር ላይ እንደቆዩ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባደረገው ማጣራት ማረጋገጡን ገለጸ። ይህም ድርጊት ከሕግ ውጪ በመሆኑ በአቶ ዳውድ ኢብሳ ላይ የተጣለው የመንቀሳቀስ ገደብ በአፋጣኝ እንዲነሳ ቦርዱ ለፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን እና ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በደብዳቤ ጠይቋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ለሁለቱ የፀጥታ ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ ላይ እንዳመለከተው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር ለረጅም ጊዜ ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ የቀረበውን አቤቱታ አጣሪዎችን በማሰማራት ማረጋገጡን ገልጿል። በዚህም መሠረት ከቦርዱ የተላኩት አጣሪዎች የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ ወደ ሚገኘው የአቶ ዳውድ ኢብሳ መኖሪያ በሄዱበት ጊዜ ሲቪል የለበሱ የፀጥታ ሠራተኞች በር እንደከፈቱላቸውና ማንም ሰው መግባት እንደማይችል መረዳታቸውን ደብዳቤው አመልክቷል። ወደ መኖሪያ ቤቱ በመግባት ሊቀመንበሩን ለማግኘትም ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸው፣ በዚህም መሠረት አጣሪዎቹ ከየት እንደመጡና ማንነታቸውን ተጠይቀው አቶ ዳውድን እንዲጎበኙ እንደተፈቀደላቸው ገልጸዋል። የኦነግ ሊቀመንበርን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ከማግኘታቸው በፊትም በፀጥታ ሠራተኞቹ ቦርሳቸው መፈተሹ እንዲሁም ስልክ ይዘው መግባት እንደማይችሉ እንደተነገራቸውና ይህንኑ በማድረግ በመጨረሻ አቶ ዳውድን እንዳገኙ ቦርዱ በደዳቤው ላይ ጠቅሷል። አጣሪዎቹ ከኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ጋር ባደረጉት ውይይት ከመጋቢት 24፣ 2013 ዓ.ም በቤታቸው እንዲገደቡና እንዳይወጡ መከልከላቸውን አስረድተዋል። የታጠቁ ሰዎች በመኖሪያ ቤታቸው ግቢ ተመድበውም እንደከለክሏቸውም ምርጫ ቦርድ በመግለጫው አስፍሯል። ከዚህም በመነሳት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ የመንቀሳቀስ መብት ተገድቦ በቁም እስር በቤታቸው ውስጥ እንዳይወጡ መደረጋቸውን መገንዘቡን በደብዳቤው ላይ አመልክቷል። በመሆኑም ቦርዱ በአቶ ዳውድ ኢብሳ ላይ የተፈጸመው ይህ የመንቀሳቀስ ገደብ በየትኛውም ሕግ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በመግለጽ ያሉበት የቁም አስር በአፋጣኝ እንዲነሳ ጠይቋል። ቦርዱ ፌደራል ፖሊስ እና ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በጻፈው ደብዳቤ በሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ ቤት የተመደቡት ጥበቃዎች በአስቸኳይ እንዲነሱና የግለሰቡ የመንቀሳቀስ መብታቸው እንዲከበር አድርገው ለቦርዱ በአስቸኳይ እንዲያሳውቁ ጠይቋል። ከዚህ ቀደም የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በቁም እስር ላይ መሆናቸው እንዳሳሰበው የመብት ተቆርቋሪው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ማስታወቁ ይታወሳል። ሊቀ መንበሩ ምንም አይነት ክስ ሳይቀርብባቸው በቁም አስር ላይ የሚገኙት ከሚያዝያ 25/2013 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑንም ገልጾ ነበር። አቶ ዳውድ ከቤት መውጣት የተከለከሉት ፖሊስ ካለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መኖሪያቸውን ፈትሾ ኮምፒውተሮችናን የሞባይል ስልኮችን ጨምሮ የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተከትሎ እንደሆነ ተገልጿል። ከዚያ ቀን በኋላ ፖሊስ ማንም ሰው ከቤቱ እንዳይወጣና ወደ ቤቱም እንዳይገባ የከለከለ ሲሆን አሁን በቤቱ ውስጥ ምግብና ሌሎች መሠረታዊ ነገሮች አልቀው ወይም እያለቁ ሊሆኑ ስለሚችሉ አቶ ዳውድ ያሉበት ሁኔታና ደኅንነታቸው አሳሳቢ መሆኑን አምነስቲ አመልክቷል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጉዳዩን በማስመልከት በወቅቱ የሰላም ሚኒስትር ለነበሩት ሙፈሪያት ካሚል ደብዳቤ የጻፈ ሲሆን፤ በዚህም የአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሕግ ውጪ በቁም አስር ላይ ለረጅም ጊዜ መቆየታቸው እንዳሳሰበው አመልክቷል። አምነስቲ በዚሁ ደብዳቤ ላይ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ በተቀበለችው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ግዴታ መሠረት ሃሳብን የመግለጽና የመደራጀት መብትን እንዲያከብሩና እንዲጠብቁና ጠይቋል። አምነስቲ መንግሥትን አቶ ዳውድ ኢብሳን በአስቸኳይ ከቁም አስሩ እንዲለቅ ወይም የፈጸሙት ጥፋት ካለና በቂ ማስረጃ ካለውም በተገቢው ሁኔታ ክስ እንዲመሰርት ጠይቆ ነበር። አቶ ዳውድ ኢብሳ ለረጅም ዓመታት የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን በሊቀመንበርነት ሲመሩ የቆዩ ሲሆን ግንባሩ በሽብርተኛ ቡድንነት በተፈረጀበት ጊዜ መቀመጫቸውን ኤርትራ ውስጥ በማድረግ የትጥቅ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ ወደ ሥልጣን መጥተው ፖለቲካዊ ለውጥ በአገሪቱ ሲደረግ በኦነግ ላይ ተጥሎ የነበረው የሽብርተኛ ድርጅትነት ፍረጃ ተነስቶለት በአገሪቱ ፖለቲካዊ መድረክ ውስጥ ለመሳተፍ መሪዎቹ ወደ አገር ቤት ሲመለሱ የተወሰነው የቡድኑ ተዋጊም ወደ ተሃድሶ መግባቱ ይታወሳል። በግንባሩ ውስጥ በተደጋጋሚ መከፋፈል ያጋጠመ ሲሆን አቶ ዳውድ ወደ አዲስ አበባ ከተመለሱ በኋላ የተወሰኑ የቡድኑ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ሳይፈቱ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል። በተለይ በምዕራብ ኦሮሚያ በስፋት የሚንቀሰቀሰው መንግሥት ሸኔ የሚለውና እራሱን የአሮሞ ነጻነት ጦር የሚለው ቡድን በሚፈጽማቸው ጥቃቶች ምክንያት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ቡድን ተብሎ ተሰይሟል። ከቡድኑ ታጣቂ ኃይል በተጨማሪ አዲስ አበባ በገቡት የፖለቲካ አመራሮች መካከል ልዩነት ተፈጥሮ በግንባሩ የመሪነት ሚና ላይ መከፋፈል መፈጠሩ ይታወቃል። ከአቶ ዳውድ ኢብሳ የተለየውን ቡድን የሚመሩት አካላት ትክክለኛው የኦነግ መሪዎች መሆናቸውን በመግለጽ ባለፈው ዓመት በተካሄደው ምርጫ ለመሳተፍ ሙከራ አድርገው ነበር። ይህ በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራውን ኦነግ እውቅና የነፈገውና የግንባሩ ትክክለኛ አመራር መሆኑን የሚገልጸው አካል ባለፈው ዓመት ከተካሄደው ምርጫ በኋላ መንግሥት ተቃዋሚዎችን በሚመሰርተው መንግሥት ውስጥ ለማሳተፍ በገባው ቃል መሠረት የተወሰኑት በኦሮሚያና በፌደራል መንግሥቱ ውስጥ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል። | ምርጫ ቦርድ በአቶ ዳውድ ኢብሳ ላይ የተጣለው የመንቀሳቀስ ገደብ በአስቸኳይ እንዲነሳ ጠየቀ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የረጅም ጊዜ ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳ አንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ከቤታቸው እንዳይወጡ ተከልክለው በቁም እስር ላይ እንደቆዩ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባደረገው ማጣራት ማረጋገጡን ገለጸ። ይህም ድርጊት ከሕግ ውጪ በመሆኑ በአቶ ዳውድ ኢብሳ ላይ የተጣለው የመንቀሳቀስ ገደብ በአፋጣኝ እንዲነሳ ቦርዱ ለፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን እና ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በደብዳቤ ጠይቋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ለሁለቱ የፀጥታ ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ ላይ እንዳመለከተው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር ለረጅም ጊዜ ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ የቀረበውን አቤቱታ አጣሪዎችን በማሰማራት ማረጋገጡን ገልጿል። በዚህም መሠረት ከቦርዱ የተላኩት አጣሪዎች የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ ወደ ሚገኘው የአቶ ዳውድ ኢብሳ መኖሪያ በሄዱበት ጊዜ ሲቪል የለበሱ የፀጥታ ሠራተኞች በር እንደከፈቱላቸውና ማንም ሰው መግባት እንደማይችል መረዳታቸውን ደብዳቤው አመልክቷል። ወደ መኖሪያ ቤቱ በመግባት ሊቀመንበሩን ለማግኘትም ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸው፣ በዚህም መሠረት አጣሪዎቹ ከየት እንደመጡና ማንነታቸውን ተጠይቀው አቶ ዳውድን እንዲጎበኙ እንደተፈቀደላቸው ገልጸዋል። የኦነግ ሊቀመንበርን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ከማግኘታቸው በፊትም በፀጥታ ሠራተኞቹ ቦርሳቸው መፈተሹ እንዲሁም ስልክ ይዘው መግባት እንደማይችሉ እንደተነገራቸውና ይህንኑ በማድረግ በመጨረሻ አቶ ዳውድን እንዳገኙ ቦርዱ በደዳቤው ላይ ጠቅሷል። አጣሪዎቹ ከኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ጋር ባደረጉት ውይይት ከመጋቢት 24፣ 2013 ዓ.ም በቤታቸው እንዲገደቡና እንዳይወጡ መከልከላቸውን አስረድተዋል። የታጠቁ ሰዎች በመኖሪያ ቤታቸው ግቢ ተመድበውም እንደከለክሏቸውም ምርጫ ቦርድ በመግለጫው አስፍሯል። ከዚህም በመነሳት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ የመንቀሳቀስ መብት ተገድቦ በቁም እስር በቤታቸው ውስጥ እንዳይወጡ መደረጋቸውን መገንዘቡን በደብዳቤው ላይ አመልክቷል። በመሆኑም ቦርዱ በአቶ ዳውድ ኢብሳ ላይ የተፈጸመው ይህ የመንቀሳቀስ ገደብ በየትኛውም ሕግ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በመግለጽ ያሉበት የቁም አስር በአፋጣኝ እንዲነሳ ጠይቋል። ቦርዱ ፌደራል ፖሊስ እና ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በጻፈው ደብዳቤ በሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ ቤት የተመደቡት ጥበቃዎች በአስቸኳይ እንዲነሱና የግለሰቡ የመንቀሳቀስ መብታቸው እንዲከበር አድርገው ለቦርዱ በአስቸኳይ እንዲያሳውቁ ጠይቋል። ከዚህ ቀደም የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በቁም እስር ላይ መሆናቸው እንዳሳሰበው የመብት ተቆርቋሪው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ማስታወቁ ይታወሳል። ሊቀ መንበሩ ምንም አይነት ክስ ሳይቀርብባቸው በቁም አስር ላይ የሚገኙት ከሚያዝያ 25/2013 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑንም ገልጾ ነበር። አቶ ዳውድ ከቤት መውጣት የተከለከሉት ፖሊስ ካለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መኖሪያቸውን ፈትሾ ኮምፒውተሮችናን የሞባይል ስልኮችን ጨምሮ የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተከትሎ እንደሆነ ተገልጿል። ከዚያ ቀን በኋላ ፖሊስ ማንም ሰው ከቤቱ እንዳይወጣና ወደ ቤቱም እንዳይገባ የከለከለ ሲሆን አሁን በቤቱ ውስጥ ምግብና ሌሎች መሠረታዊ ነገሮች አልቀው ወይም እያለቁ ሊሆኑ ስለሚችሉ አቶ ዳውድ ያሉበት ሁኔታና ደኅንነታቸው አሳሳቢ መሆኑን አምነስቲ አመልክቷል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጉዳዩን በማስመልከት በወቅቱ የሰላም ሚኒስትር ለነበሩት ሙፈሪያት ካሚል ደብዳቤ የጻፈ ሲሆን፤ በዚህም የአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሕግ ውጪ በቁም አስር ላይ ለረጅም ጊዜ መቆየታቸው እንዳሳሰበው አመልክቷል። አምነስቲ በዚሁ ደብዳቤ ላይ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ በተቀበለችው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ግዴታ መሠረት ሃሳብን የመግለጽና የመደራጀት መብትን እንዲያከብሩና እንዲጠብቁና ጠይቋል። አምነስቲ መንግሥትን አቶ ዳውድ ኢብሳን በአስቸኳይ ከቁም አስሩ እንዲለቅ ወይም የፈጸሙት ጥፋት ካለና በቂ ማስረጃ ካለውም በተገቢው ሁኔታ ክስ እንዲመሰርት ጠይቆ ነበር። አቶ ዳውድ ኢብሳ ለረጅም ዓመታት የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን በሊቀመንበርነት ሲመሩ የቆዩ ሲሆን ግንባሩ በሽብርተኛ ቡድንነት በተፈረጀበት ጊዜ መቀመጫቸውን ኤርትራ ውስጥ በማድረግ የትጥቅ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ ወደ ሥልጣን መጥተው ፖለቲካዊ ለውጥ በአገሪቱ ሲደረግ በኦነግ ላይ ተጥሎ የነበረው የሽብርተኛ ድርጅትነት ፍረጃ ተነስቶለት በአገሪቱ ፖለቲካዊ መድረክ ውስጥ ለመሳተፍ መሪዎቹ ወደ አገር ቤት ሲመለሱ የተወሰነው የቡድኑ ተዋጊም ወደ ተሃድሶ መግባቱ ይታወሳል። በግንባሩ ውስጥ በተደጋጋሚ መከፋፈል ያጋጠመ ሲሆን አቶ ዳውድ ወደ አዲስ አበባ ከተመለሱ በኋላ የተወሰኑ የቡድኑ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ሳይፈቱ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል። በተለይ በምዕራብ ኦሮሚያ በስፋት የሚንቀሰቀሰው መንግሥት ሸኔ የሚለውና እራሱን የአሮሞ ነጻነት ጦር የሚለው ቡድን በሚፈጽማቸው ጥቃቶች ምክንያት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ቡድን ተብሎ ተሰይሟል። ከቡድኑ ታጣቂ ኃይል በተጨማሪ አዲስ አበባ በገቡት የፖለቲካ አመራሮች መካከል ልዩነት ተፈጥሮ በግንባሩ የመሪነት ሚና ላይ መከፋፈል መፈጠሩ ይታወቃል። ከአቶ ዳውድ ኢብሳ የተለየውን ቡድን የሚመሩት አካላት ትክክለኛው የኦነግ መሪዎች መሆናቸውን በመግለጽ ባለፈው ዓመት በተካሄደው ምርጫ ለመሳተፍ ሙከራ አድርገው ነበር። ይህ በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራውን ኦነግ እውቅና የነፈገውና የግንባሩ ትክክለኛ አመራር መሆኑን የሚገልጸው አካል ባለፈው ዓመት ከተካሄደው ምርጫ በኋላ መንግሥት ተቃዋሚዎችን በሚመሰርተው መንግሥት ውስጥ ለማሳተፍ በገባው ቃል መሠረት የተወሰኑት በኦሮሚያና በፌደራል መንግሥቱ ውስጥ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60622088 |
0business
| ጫንጮ አቅራቢያ ገንዘብ በጠየቁ አጋቾች እጅ የቆዩት የሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች ተለቀቁ | ከአዲስ አበባ በስተሰሜን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ለበርካታ ሳምንታት በታጣቂዎች ታግተው የነበሩት የኢትዮ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች መለቀቃቸውን የአካባቢው ባለሥልጣን ለቢቢሲ ገለጹ። ከአዲስ አበባ በ47 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ጫንጮ ከተማ አቅራቢያ ከሚገኘው የሲሚንቶ ፋብሪካ የምርት ግብዓት ማውጫ ስፍራ በታጣቂዎች ተይዘው የቆዩ ዘጠኝ ግለሰቦች ነበሩ ተብሏል። የሱሉልታ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ግርማ ወዬሳ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በታጣቂዎቹ ታግተው የማስለቀቂያ ገንዘብ ተጠይቆባቸው የቆዩት ዘጠኙ ግለሰቦች ተለቅቀዋል። ለሳምንታት በዘለቀው በዚህ እገታ በቅድሚያ 27 ሰዎች የሲሚንቶ ፋብሪካው ሠራተኞች ተይዘው የነበረ ሲሆን፣ 18ቱ ከሁለት ሳምንታት በፊት መለቀቃቸውን ተዘግቧል። በታጣቂዎቹ ተለይተው ከቀሩት መካከል ስድስቱ የሕንድ ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ፣ ሦስቱ አስተርጓሚዎቻቸው እንደነበሩም በወቅቱ ተዘግቦ ነበር። አቶ ግርማ ታጋቾቹ ተለቅቀው ቀጣሪያቸው ኢትዮ-ሲሚንቶ ፋብሪካ ወደሚገኝበት የጫንጮ ከተማ መመለሳቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የግለሰቦቹ እገታ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ለመሰብሰብ አላማ ያደረገ እንደነበረ የተነገረ ሲሆን፣ አሁን ታጋቾቹ በምን ሁኔታ እንደተለቀቁ ቢቢሲ ከአካባቢው አስተዳዳሪ ማብራሪያ ቢጠይቅም ስለተለቀቁበት ሁኔታ መረጃው እንደሌላቸው ተናግረዋል። ቢቢሲ በታጠቂዎች እገታ ስር የቆዩት ግለሰቦች ቀጣሪ የሆነውን ኢትዮ-ሲሚንቶን በጉዳዩ ላይ ለማነጋገር በተደጋጋሚ ስልክ ቢደውልም ምለሽ ሳያገኝ ቀርቷል። "ሕብረተሰቡን በማወያየት እና የፀጥታ ኃይሉን በማጠናከር እንዲህ አይነት ተግባራትን ለማስቆም ጠንካራ ሥራ እየሰራን ነው" ሲሉ ኃላፊው ተናግረዋል። የሲሚንቶ ፋብሪካው ሠራተኞች በታጣቂዎች ከተያዙ በኋላ ከአጎራባች ወረዳዎች ጋር በመሆን ጥበቃ ሲደርግ ብሎም ታጋቾቹን ለማግኘት መንግሥት የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል። አክለውም ተመሳሳይ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ የፀጥታ ኃይሉ በአካባቢው ተጠናከረ ክትትልና ጥበቃ እያደረገ መሆኑንም አስተዳዳሪው አቶ ግርማ ወዬሳ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ተመሳሳይ እገታና ጥቃቶች ማንነታቸው ባልተገለጸ ታጣቂዎች እንደሚፈጸም ሲዘገብ ቆይቷል። እንዲህ አይነት ድርጊቶች እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራውና መንግሥት 'ሸኔ' የሚለው በሽብርተኝነት የተፈረጀ ድርጅት የሚፈጽመው መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣንት ቢናገሩም፣ ቡድኑ ግን በእንዲህ ያለው ድርጊት ውስጥ እጁ እንደሌለ ያስተባብላል። | ጫንጮ አቅራቢያ ገንዘብ በጠየቁ አጋቾች እጅ የቆዩት የሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች ተለቀቁ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ለበርካታ ሳምንታት በታጣቂዎች ታግተው የነበሩት የኢትዮ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች መለቀቃቸውን የአካባቢው ባለሥልጣን ለቢቢሲ ገለጹ። ከአዲስ አበባ በ47 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ጫንጮ ከተማ አቅራቢያ ከሚገኘው የሲሚንቶ ፋብሪካ የምርት ግብዓት ማውጫ ስፍራ በታጣቂዎች ተይዘው የቆዩ ዘጠኝ ግለሰቦች ነበሩ ተብሏል። የሱሉልታ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ግርማ ወዬሳ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በታጣቂዎቹ ታግተው የማስለቀቂያ ገንዘብ ተጠይቆባቸው የቆዩት ዘጠኙ ግለሰቦች ተለቅቀዋል። ለሳምንታት በዘለቀው በዚህ እገታ በቅድሚያ 27 ሰዎች የሲሚንቶ ፋብሪካው ሠራተኞች ተይዘው የነበረ ሲሆን፣ 18ቱ ከሁለት ሳምንታት በፊት መለቀቃቸውን ተዘግቧል። በታጣቂዎቹ ተለይተው ከቀሩት መካከል ስድስቱ የሕንድ ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ፣ ሦስቱ አስተርጓሚዎቻቸው እንደነበሩም በወቅቱ ተዘግቦ ነበር። አቶ ግርማ ታጋቾቹ ተለቅቀው ቀጣሪያቸው ኢትዮ-ሲሚንቶ ፋብሪካ ወደሚገኝበት የጫንጮ ከተማ መመለሳቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የግለሰቦቹ እገታ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ለመሰብሰብ አላማ ያደረገ እንደነበረ የተነገረ ሲሆን፣ አሁን ታጋቾቹ በምን ሁኔታ እንደተለቀቁ ቢቢሲ ከአካባቢው አስተዳዳሪ ማብራሪያ ቢጠይቅም ስለተለቀቁበት ሁኔታ መረጃው እንደሌላቸው ተናግረዋል። ቢቢሲ በታጠቂዎች እገታ ስር የቆዩት ግለሰቦች ቀጣሪ የሆነውን ኢትዮ-ሲሚንቶን በጉዳዩ ላይ ለማነጋገር በተደጋጋሚ ስልክ ቢደውልም ምለሽ ሳያገኝ ቀርቷል። "ሕብረተሰቡን በማወያየት እና የፀጥታ ኃይሉን በማጠናከር እንዲህ አይነት ተግባራትን ለማስቆም ጠንካራ ሥራ እየሰራን ነው" ሲሉ ኃላፊው ተናግረዋል። የሲሚንቶ ፋብሪካው ሠራተኞች በታጣቂዎች ከተያዙ በኋላ ከአጎራባች ወረዳዎች ጋር በመሆን ጥበቃ ሲደርግ ብሎም ታጋቾቹን ለማግኘት መንግሥት የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል። አክለውም ተመሳሳይ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ የፀጥታ ኃይሉ በአካባቢው ተጠናከረ ክትትልና ጥበቃ እያደረገ መሆኑንም አስተዳዳሪው አቶ ግርማ ወዬሳ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ተመሳሳይ እገታና ጥቃቶች ማንነታቸው ባልተገለጸ ታጣቂዎች እንደሚፈጸም ሲዘገብ ቆይቷል። እንዲህ አይነት ድርጊቶች እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራውና መንግሥት 'ሸኔ' የሚለው በሽብርተኝነት የተፈረጀ ድርጅት የሚፈጽመው መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣንት ቢናገሩም፣ ቡድኑ ግን በእንዲህ ያለው ድርጊት ውስጥ እጁ እንደሌለ ያስተባብላል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60906446 |
3politics
| የዩኬው ጠቅላይ ሚኒስትር የኮሮናቫይረስ መመሪያን በመተላለፋቸው ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተጠየቁ | የዩኬው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ኮሮናቫይረስን ተከትሎ የተጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ በመተላለፍ አንድ የመጠጥ ድግስ ላይ መታደማቸውን ካመኑ በኋላ በርካቶች ከኃላፊነታቸውን እንዲነሱ እየወተወቱ ነው። ምንም እንኳን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአውሮፓውያኑ 2020 ላይ ላደረጉት ነገር ይቅርታ ቢጠይቁም ሰሚ አላገኙም። ''በዚህ ምክንያት በርካቶች ቢቆጡ አልፈርድባቸውም'' ብለዋል ጠቅላዩ። የካቢኔ አባል የሆኑት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን ቆመዋል። ነገር ግን የስኮትላንድ ካቢኔ መሪው ዳግላስ ሮስ እና ሌሎቹ የእንደራሴ ምክር ቤት አባላት ዊሊያም ራግ፣ ካሮሊን ኖክስ እና ሮጀር ጌል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ጠይቀዋል። ትናንት ረቡዕ ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ይቅርታ ከጠይቁ በኋላ የስኮትላንድ ካቢኔ መሪው ዳግላስ ሮስ ''አስቸጋሪ ውይይት'' ነበር ብለዋል። መሪው አክለውም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ያላቸው እምነት መሸርሸሩን የሚገልጽ ደብዳቤ መሰል ጉዳዮችን ወደሚከታተለው ምክር ቤት እንደሚጽፉ አስታውቀዋል። ''እሱኮ ጠቅላይ ሚኒስትር ነው፤ የእሱ መንግስት ነው እነኚህን መመሪያዎች ያስቀመጠው፤ ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሰራው ስህተት ተጠያቂ መሆን አለበት'' ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ወግ አጥባቂዎቹ 54 የህዝብ እንደራሴዎች በአውሮፓውያኑ 1922 ለተቋቋመው ኮሚቴ ግልጽ ደብዳቤ የሚጽፉ ከሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትልቅ ፈተና ሊገጥማቸው ይችላል። በርካታ የዩኬ ሚኒስትሮች በበኩላቸው የህዝብ እንደራሴዎቹ በሲቪል አገልጋይ ሱ ግሬይ የሚመራው መርማሪ ቡድን መረጃ እስነከሚያጠናቅር ድረስ ትንሽ እንዲታገሱ የጠየቁ ሲሆን ግኝቱ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግም አስታውቀዋል። ነገር ግን የእንደራሴ ምክር ቤት አባሉ ዊሊያም ራግ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እራሳቸውን መከላከል የማይችሉበት ሁኔታ ላይ ነው የሚገኙት ብለዋል። '' የጠቅላይ ሚኒስትሩ እጣ ፈንታ በመርማሪው ኮሚቴ ግኝት ላይ ብቻ የተንጠለጠለ መሆን የለበትም'' በማለት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ሌላኛዋ የህዝብ እንደራሴ ቶሪ ካሮላይን በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መላውን ወግ አጥባቂ ቡድን እየጎዱ ስለሆነ በፍጥነት ከስልጣናቸው መልቀቅ አለባቸው ሲሉ ተደምጠዋል። ከዚህ በፊትም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የሰላ ትችት ይሰነዝሩ የነበሩት የህዝብ እንደራሴዋ በአይቲቪ ላይ በቀረቡበት ወቅት ''በትክክል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደካማ ጎናችን ናቸው'' ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋ ይቅርታ መጠየቃቸው ከምህረት ይልቅ ትልቅ ቀውስ ነው ይዞባቸው የመጣው። ሌላው ቀርቶ ጥቂት የማይባሉ የእርሳቸው ደጋፊ የህዝብ እንደራሴዎች ጭምር ቦሪስ ጆንሰን ከኃላፊነታቸው ይነሱ እያሉ ይገኛሉ። | የዩኬው ጠቅላይ ሚኒስትር የኮሮናቫይረስ መመሪያን በመተላለፋቸው ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተጠየቁ የዩኬው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ኮሮናቫይረስን ተከትሎ የተጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ በመተላለፍ አንድ የመጠጥ ድግስ ላይ መታደማቸውን ካመኑ በኋላ በርካቶች ከኃላፊነታቸውን እንዲነሱ እየወተወቱ ነው። ምንም እንኳን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአውሮፓውያኑ 2020 ላይ ላደረጉት ነገር ይቅርታ ቢጠይቁም ሰሚ አላገኙም። ''በዚህ ምክንያት በርካቶች ቢቆጡ አልፈርድባቸውም'' ብለዋል ጠቅላዩ። የካቢኔ አባል የሆኑት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን ቆመዋል። ነገር ግን የስኮትላንድ ካቢኔ መሪው ዳግላስ ሮስ እና ሌሎቹ የእንደራሴ ምክር ቤት አባላት ዊሊያም ራግ፣ ካሮሊን ኖክስ እና ሮጀር ጌል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ጠይቀዋል። ትናንት ረቡዕ ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ይቅርታ ከጠይቁ በኋላ የስኮትላንድ ካቢኔ መሪው ዳግላስ ሮስ ''አስቸጋሪ ውይይት'' ነበር ብለዋል። መሪው አክለውም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ያላቸው እምነት መሸርሸሩን የሚገልጽ ደብዳቤ መሰል ጉዳዮችን ወደሚከታተለው ምክር ቤት እንደሚጽፉ አስታውቀዋል። ''እሱኮ ጠቅላይ ሚኒስትር ነው፤ የእሱ መንግስት ነው እነኚህን መመሪያዎች ያስቀመጠው፤ ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሰራው ስህተት ተጠያቂ መሆን አለበት'' ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ወግ አጥባቂዎቹ 54 የህዝብ እንደራሴዎች በአውሮፓውያኑ 1922 ለተቋቋመው ኮሚቴ ግልጽ ደብዳቤ የሚጽፉ ከሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትልቅ ፈተና ሊገጥማቸው ይችላል። በርካታ የዩኬ ሚኒስትሮች በበኩላቸው የህዝብ እንደራሴዎቹ በሲቪል አገልጋይ ሱ ግሬይ የሚመራው መርማሪ ቡድን መረጃ እስነከሚያጠናቅር ድረስ ትንሽ እንዲታገሱ የጠየቁ ሲሆን ግኝቱ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግም አስታውቀዋል። ነገር ግን የእንደራሴ ምክር ቤት አባሉ ዊሊያም ራግ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እራሳቸውን መከላከል የማይችሉበት ሁኔታ ላይ ነው የሚገኙት ብለዋል። '' የጠቅላይ ሚኒስትሩ እጣ ፈንታ በመርማሪው ኮሚቴ ግኝት ላይ ብቻ የተንጠለጠለ መሆን የለበትም'' በማለት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ሌላኛዋ የህዝብ እንደራሴ ቶሪ ካሮላይን በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መላውን ወግ አጥባቂ ቡድን እየጎዱ ስለሆነ በፍጥነት ከስልጣናቸው መልቀቅ አለባቸው ሲሉ ተደምጠዋል። ከዚህ በፊትም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የሰላ ትችት ይሰነዝሩ የነበሩት የህዝብ እንደራሴዋ በአይቲቪ ላይ በቀረቡበት ወቅት ''በትክክል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደካማ ጎናችን ናቸው'' ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋ ይቅርታ መጠየቃቸው ከምህረት ይልቅ ትልቅ ቀውስ ነው ይዞባቸው የመጣው። ሌላው ቀርቶ ጥቂት የማይባሉ የእርሳቸው ደጋፊ የህዝብ እንደራሴዎች ጭምር ቦሪስ ጆንሰን ከኃላፊነታቸው ይነሱ እያሉ ይገኛሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-59976252 |
2health
| በአሜሪካ የኮቪድ ክትባት ያልተከተበው ግለሰብ የልብ ንቅለ ተከላ ተሰረዘ | በአሜሪካ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ታካሚው የኮቪድ-19 ክትባት ባለመውሰዱ የልብ ንቅለ ተከላውን ሰረዘ። ዲጄ ፈርጉሰን የተሰኘው የ31 ዓመት ታካሚ አንገብጋቢ የሆነ የልብ ንቅለ ተከላ የሚያስፈልገው ቢሆንም በቦስተን የሚገኘው ሆስፒታል ግን ግለሰቡን ከታካሚዎች ዝርዝር ውስጥ አስወጥቶታል። የብሪንግሃም እና የሴቶች ሆስፒታል የልብ ንቅለ ተከላውን የሰረዘው ታካሚው የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ባለመውሰዱ ነው። የታካሚው ወላጅ አባት ዴቪክ፤ የኮቪድ ክትባት ከልጃቸው መሠረታዊ መርሆች ጋር የሚቃረን መሆኑን በመግለጽ ልጃቸው በክትባት እንደማያምን ገልጸዋል። ሆስፒታሉ በበኩሉ ንቅለ ተከላውን የሰረዝኩት መመሪያ በመከተል ነው ብሏል። "በውስጥ አካላት ጉዳት ምክንያት በንቅለ ተከላ አዲስ የውስጥ አካል የተቀበለ ታካሚ በሕይወት የመትረፍ እድሉ ከፍተኛ እንዲሆን የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን" ሲል የብሪግሃም እና የሴቶች ሆስፒታል ለቢቢሲ ገልጿል። የሆስፒታሉ ቃል አቀባይ ሆስፒታላቸው የታካሚዎችን በሽታ የመከላከል አቅም ከግምት በማስገባት ንቅለ ተከላው የመሳካት እድሉን እና ታካሚዎች ከቀዶ ጥገናው በኋላ የመትረፍ እድላቸው ከፍ ለማድረግ ከንቅለ ተከላ በፊት የኮቪድ-19 ክትባት እና የአኗኗር ዘይቤዎችን እንደሚመለከቱ ገልጸዋል። በሆስፒታሉ የአካል ክፍሎችን ለመተካት በተጠባባቂ መዝገብ ውስጥ ከሚገኙት 100,000 ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በአምስት ዓአመት ጊዜ ውስጥ የውስጥ አካል እንደማያገኙ እና የአካል ክፍሎች እጥረት ከፍተኛ መሆኑንም ገልጿል። የሁለት ልጆች አባት የሆነው ፈርጉሰን ባጋጠመው የልብ ሕመም ምክንያት ላለፉት አራት ወራት ሆስፒታል ተኝቶ በመታከም ላይ ይገኛል። ለግለሰቡ ገንዘብ ለማሰባሰብ በተዘጋጀው የጎ ፈንድ ሚ አካውንት ላይ አዘጋጆቹ እንደገለጹት ፈርጉሰን ክትባቱን ከወሰደ በልቡ ላይ ተጨማሪ ሕመሞች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ሰግተዋል። የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ኤጄንሲ ሲዲሲ በበኩሉ የንቅለ ተከላ ተቀባዮች እና በአቅራቢያቸው ያሉ ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንዲከተቡ እንዲሁም ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባት እንዲወስዱ ያበረታታል። ዶ/ር አርተር ካፕላን በኒዩ ግሮስማን የሕክምና ትምህርት ቤት የሕክምና ሥነ ምግባር ኃላፊ ናቸው። ለሲቢኤስ ኒውስ እንደተናገሩት፤ ማንኛውም የሰውነት አካል ከተቀየረ በኋላ የታካሚው በሽታ የመከላከል ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ይዘጋል። በተጨማሪም በተራ ጉንፋን እንኳን ለሞት ሊዳርግ ይችላል። "የውስጥ አካል ክፍሎቹ በጣም አነስተኛ ቁጥር ስላላቸው አናሳ የመዳን እድል ላለው ሰው ላለመስጠት እንሞክራለን። ሌሎች ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሰዎች ከንቅለ ተከላው በኋላ የመዳን እድላቸው ከፍተኛ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ወላጅ አባቱም ልጃቸው በራሱ ሰውነት ላይ የመወሰን መብት እንዳለው እና ሕመሙንም በጀግንነት እየታገለ እንደሆነ ተናግረዋል። በዚህ አስቸጋሪ ግዜ ውስጥ ባሳየው ቁርጠኝነትም ለልጃቸው ያላቸው ክብር መጨመሩን ተናግረዋል። | በአሜሪካ የኮቪድ ክትባት ያልተከተበው ግለሰብ የልብ ንቅለ ተከላ ተሰረዘ በአሜሪካ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ታካሚው የኮቪድ-19 ክትባት ባለመውሰዱ የልብ ንቅለ ተከላውን ሰረዘ። ዲጄ ፈርጉሰን የተሰኘው የ31 ዓመት ታካሚ አንገብጋቢ የሆነ የልብ ንቅለ ተከላ የሚያስፈልገው ቢሆንም በቦስተን የሚገኘው ሆስፒታል ግን ግለሰቡን ከታካሚዎች ዝርዝር ውስጥ አስወጥቶታል። የብሪንግሃም እና የሴቶች ሆስፒታል የልብ ንቅለ ተከላውን የሰረዘው ታካሚው የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ባለመውሰዱ ነው። የታካሚው ወላጅ አባት ዴቪክ፤ የኮቪድ ክትባት ከልጃቸው መሠረታዊ መርሆች ጋር የሚቃረን መሆኑን በመግለጽ ልጃቸው በክትባት እንደማያምን ገልጸዋል። ሆስፒታሉ በበኩሉ ንቅለ ተከላውን የሰረዝኩት መመሪያ በመከተል ነው ብሏል። "በውስጥ አካላት ጉዳት ምክንያት በንቅለ ተከላ አዲስ የውስጥ አካል የተቀበለ ታካሚ በሕይወት የመትረፍ እድሉ ከፍተኛ እንዲሆን የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን" ሲል የብሪግሃም እና የሴቶች ሆስፒታል ለቢቢሲ ገልጿል። የሆስፒታሉ ቃል አቀባይ ሆስፒታላቸው የታካሚዎችን በሽታ የመከላከል አቅም ከግምት በማስገባት ንቅለ ተከላው የመሳካት እድሉን እና ታካሚዎች ከቀዶ ጥገናው በኋላ የመትረፍ እድላቸው ከፍ ለማድረግ ከንቅለ ተከላ በፊት የኮቪድ-19 ክትባት እና የአኗኗር ዘይቤዎችን እንደሚመለከቱ ገልጸዋል። በሆስፒታሉ የአካል ክፍሎችን ለመተካት በተጠባባቂ መዝገብ ውስጥ ከሚገኙት 100,000 ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በአምስት ዓአመት ጊዜ ውስጥ የውስጥ አካል እንደማያገኙ እና የአካል ክፍሎች እጥረት ከፍተኛ መሆኑንም ገልጿል። የሁለት ልጆች አባት የሆነው ፈርጉሰን ባጋጠመው የልብ ሕመም ምክንያት ላለፉት አራት ወራት ሆስፒታል ተኝቶ በመታከም ላይ ይገኛል። ለግለሰቡ ገንዘብ ለማሰባሰብ በተዘጋጀው የጎ ፈንድ ሚ አካውንት ላይ አዘጋጆቹ እንደገለጹት ፈርጉሰን ክትባቱን ከወሰደ በልቡ ላይ ተጨማሪ ሕመሞች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ሰግተዋል። የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ኤጄንሲ ሲዲሲ በበኩሉ የንቅለ ተከላ ተቀባዮች እና በአቅራቢያቸው ያሉ ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንዲከተቡ እንዲሁም ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባት እንዲወስዱ ያበረታታል። ዶ/ር አርተር ካፕላን በኒዩ ግሮስማን የሕክምና ትምህርት ቤት የሕክምና ሥነ ምግባር ኃላፊ ናቸው። ለሲቢኤስ ኒውስ እንደተናገሩት፤ ማንኛውም የሰውነት አካል ከተቀየረ በኋላ የታካሚው በሽታ የመከላከል ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ይዘጋል። በተጨማሪም በተራ ጉንፋን እንኳን ለሞት ሊዳርግ ይችላል። "የውስጥ አካል ክፍሎቹ በጣም አነስተኛ ቁጥር ስላላቸው አናሳ የመዳን እድል ላለው ሰው ላለመስጠት እንሞክራለን። ሌሎች ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሰዎች ከንቅለ ተከላው በኋላ የመዳን እድላቸው ከፍተኛ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ወላጅ አባቱም ልጃቸው በራሱ ሰውነት ላይ የመወሰን መብት እንዳለው እና ሕመሙንም በጀግንነት እየታገለ እንደሆነ ተናግረዋል። በዚህ አስቸጋሪ ግዜ ውስጥ ባሳየው ቁርጠኝነትም ለልጃቸው ያላቸው ክብር መጨመሩን ተናግረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60136750 |
3politics
| አንቶኒ ብሊንከን፡ አዲሱ ከፍተኛ የአሜሪካ ዲፕሎማት ማን ናቸው? | በአሜሪካ ጆ ባይደን አዲስ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ አዳዲስ ተሿሚዎችም የኃላፊነት ቦታቸውን ተቀብለዋል፤ ከነዚህም ውስጥ አንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ናቸው። አዲሱ ከፍተኛ የአሜሪካ ዲፕሎማት ማን ናቸው? የቢቢሲ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ልዩ ዘጋቢ ባርባራ ፕሌት አሸር በአንደበቷ ትነግረናለች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ተሿሚዎችን ሹመት ስታደም ለሶስተኛ ጊዜዬ ነው። አስታውሳለሁ የዶናልድ ትራምፕ ልዑካን ሬክስ ቲለርሰንና ማይክ ፖምፒዮ ሹመት ወቅት መረማመጃውም ሆነ አዳራሹ በሰው ተሞልቶ ነበር። በርካቶችም ደስታቸውን፣ ተስፋቸውን እንዲሁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቶች የተዥጎደጎዱበት ወቅት ነበር። ለአዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሹመት ግን ሁሉ ፀጥ ረጭ ብሏል። ለዚህም ዋነኛው የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት በወጣው መመሪያ ምክንያት ነው። ነገር ግን በርካቶች በዓለ ሲመታቸውን ባይታደሙም፤ ፊት ለፊት ተገኝተው እንኳን ደስ አለዎት ባይሉም በዲፕሎማቱ ማህበረሰብ ውስጥ የእፎይታ ስሜት ተፈጥሯል። "ብዙዎች በብሊንከን መምጣት ከመጠን በላይ በፈንጠዝያ ላይ ናቸው፤ በሱ መምጣት ብቻ ሳይሆን የቀድሞው ቡድን ቢሮውን ለቆ በመውጣቱ" በማለት አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣን በቤታቸው በዓለ ሲመቱን እየተመለከቱ ባሉበት ነግረውኛል። ብሊንከን አንጋፋ የሚባሉ ዲፕሎማት ናቸው። ለበርካታ አመታት በዘርፉ ላቅ ያለ ልምድን አካብተዋል። ነገር ግን በርካታ ሁኔታዎች ተቀይረዋል፤ "እምነትንና ሞራልና ለመመለስ የሚገጥማቸው ፈተና ቀላል ላይሆን ይችላል" ይላሉ እኚሁ ባለስልጣን። በትራምፕ አስተዳደር ወቅት ሁኔታውን መቀበል ያቃታቸው 1 ሺህ ሰራተኞች ለቅቀዋል። በሃሳብ ብንለያይም ከአስተዳደሩ ጋር እንቀጥላለን ያሉ ደግሞ በቀድሞው ፕሬዚዳንት ዲፕሎማሲያዊ ያልሆነ አካሄድ ወደ ጎን በመገፋት፣ በሬክስ ቲለርሰን አጉል አሰራር በመሰላቸት እንዲሁ የትራምፕ ቀንደኛ ደጋፊ በሆኑት ማይክ ፖምፒዮ ፖለቲካ ገሸሽ እንዲደረጉ ሆኗል። "ሁላችንም ቢሆን በአለም ላይ ያለን ገፅታ መቀየሩ ከፍተኛ ደስታ ይሰጠናል" ይላሉ ባለስልጣኑ። "በአራት አመቱ የትራምፕ አስተዳደር ገሽሽ ተደርጎ የነበረው ሁሉ ወደ ስራ ለመግባትና ነገሮችን ለመቀየር እየሞከረ ነው" በማለት ያክላሉ። የፕሬስ ፅህፈት ቤቱ መተላለፊያ የነበረው የማይክ ፖምፒዮ ፎቶ ተነስቶ በምትኩ የተለያዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ፎቶ እንዲሰቀል ተደርጓል። ከዚህም በተጨማሪ የሥራ አስፈላጊነትና ባለሙያነት ጋር የተያያዘ በማይክ ፖምፒዮ የተፃፈ ትልቅ ቢልቦርድ የጆ ባይደን በዓለ ሲመትን ተከትሎ እንዲወርድ ተደርጓል። አዲሱ የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች ላይ የረዥም አመት ልምድን አካብተዋል፤ ለዘመናትም የባይደን ቅርብ አማካሪ በመሆን ጠንከር ያለ ግንኙነትን መስርተዋል። በሹመታቸው ወቅት ለዘብ ባለ ንግግግራቸው የትራምፕን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በመቀልበስ እንደገና እንደሚፅፉት ያስገነዘቡ ሲሆን ከፍተኛ ድጋፍም ተችሯቸዋል። የአሜሪካ እንደራሴዎችም ቢሆን ይህንን ከሌሎች አገሮች ጋር መጋተሩንና "አሜሪካ ትቅደም" የሚለውን አካሄድ ወደኋላ መተው ይፈልጋሉ። ብሊንከን መጀመሪያ አከናውናቸዋለሁ ብለው ቃል የገቧቸው ጉዳዮች ቢኖሩ የሩሲያ ሳይበር ጥቃትና የምርጫ ጣልቃ መግባት ምላሽ፣ ሳዑዲ በየመን የምታደርገውን የአየር ጥቃት ማስቆም፣ በትራምፕ አስተዳደር አሸባሪ ተብለው የተፈረጁትን የሁቲ አማፅያን ሁኔታ እንደገና መገምገም የሚሉ ናቸው። የሁቲ አማፅያን በአሸባሪነት መፈረጅ በየመን ያለውን የሰብዓዊ እርዳታዎች ላይ እክል ሊፈጥር ይችላል ተብሎ ይታመናል። ኢራንን በተመለከተ ብሊንከን ባይደን ቃል የገቡትን የደገሙ ሲሆን ይኸም የ2015ቱን የኢራን የኒውክሊየር ስምምነትን መመለስ ነው። ባራክ ኦባማ በስልጣን ዘመናቸው ወቅት አሳክተዋቸዋል ከሚባሉት ጉዳዮች ውስጥ (JCPOA) ተብሎ የሚጠራው የኢራን የኒውክሊየር ፕሮግራም ሲሆን ፕሬዚዳንት ትራምፕ በ2018 ስምምነቱን አፍርሰዋል። ወደ ስምምነቱ እንዲመለሱ ግን ኢራን የገባችውን ቃል ስታከብር እንደሆነና ይህ የማይሆን ከሆነ በጥንቃቄ ሊታይ ይገባል ይላሉ። ቻይናን በተመለከተ ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጠንከር ያለ አስተያየትና አካሄድ ጋር ይስማማሉ። ቻይናን ለማዳከም ትራምፕ ውድቅ ካደረጓቸው የዲሞክራሲ ደጋፊዎችና አለም አቀፍ ተቋማት ጋር መተባበር ያስፈልጋል በማለት አፅንኦት ይሰጣሉ። የአዲሱ ከፍተኛ ዲፕሎማት ዋነኛ አላማና ተልዕኮ የአሜሪካን መሪነት ቦታ እንደገና በዚያ መንገድ መመለስ ነው። ነገር ግን በተሾሙበት ቀን ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ውይይት በመጥፎ ይታይ ከነበረው የአሜሪካ አስተዳደር ጋር ተያይዞ እንዴት የቀድሞ አጋሮቿ ያምኗታል የሚል ነበር ። ነገር ግን ብሊንከን አሜሪካ ወደቀደመ ስፍራዋ ለመመለስ ያለው ፍላጎት ከአጋሮቿም በኩል የመጣ ነው ይላሉ። በመጀመሪያ ቀናቸው ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ውይይት ከሚዲያውና ከጋዜጠኞች ጋር ለመስራት ያላቸውን ቀናነት በግልፅ አሳይተዋል። ይህ አካሄድ ደግሞ ከቀድሞው አስተዳደደር ተቃራኒ ነው። ማይክ ፖምፒዮ እንደ አለቃቸው ሚዲያን አይወዱም አያዳምጡም፤ አንዳንድ ጊዜም ሲያወግዙ ይሰማሉ። ለጥያቄዎቻችን ኢሜይል መልስ ለማግኘት በጣም ፈታኝ ነበር። ደፈር ያሉ የኮሚዪኒኬሽን ቡድኑ አባላት ምንም የምንለው የለም የሚል መልስ ይሰጡን ነበር። የብሊንከን አካሄድ ልታይ ልታይ ይሉ ከነበሩት የማይክ ፖምፒዮ ሁኔታ ተቃራኒ ነው። ሆኖም በአሁኑ ወቅት በአዲሱ አስተዳደር የፕሬዚዳንቱ የአየር ንብረት ለውጥ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑትና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነታቸው ከፍተኛ ስፍራ የተጎናፀፉት የቀድሞ አለቃቸው ጆን ኬሪ ጋር ይወዳደራሉ። ነገር ግን ብሊንከንም ቢሆኑ ለየት ያለ ባለታሪካቸው የተጎናፀፉት ማንነት አለ። አያታቸው በሩሲያ የነበረውን የፀረ- ይሁዲዎች ነውጥ ፈርተው ወደ አሜሪካ በስደት መጡ፤ ፖላንዳዊ እንጀራ አባታቸው እንዲሁ በናዚዎች ከተቃጣባቸው ግድያ በአሜሪካውያን ወታደሮች የዳኑ ናቸው። "ማንነታችን ይኼ ነው። በአለም ላይ የምንወክለውም ይህንኑ ነው። እንደ ሰው ጉድለቶች ቢኖሩንብንም ምርጥ ለመሆን እንሞክራለን" ብለዋል። በአሁኑ ወቅት አሜሪካ አሁንም ቢሆን ጠቃሚነቷን ማረጋገጥ የስራቸው ማዕከል እንደሆነ ያስባሉ። | አንቶኒ ብሊንከን፡ አዲሱ ከፍተኛ የአሜሪካ ዲፕሎማት ማን ናቸው? በአሜሪካ ጆ ባይደን አዲስ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ አዳዲስ ተሿሚዎችም የኃላፊነት ቦታቸውን ተቀብለዋል፤ ከነዚህም ውስጥ አንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ናቸው። አዲሱ ከፍተኛ የአሜሪካ ዲፕሎማት ማን ናቸው? የቢቢሲ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ልዩ ዘጋቢ ባርባራ ፕሌት አሸር በአንደበቷ ትነግረናለች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ተሿሚዎችን ሹመት ስታደም ለሶስተኛ ጊዜዬ ነው። አስታውሳለሁ የዶናልድ ትራምፕ ልዑካን ሬክስ ቲለርሰንና ማይክ ፖምፒዮ ሹመት ወቅት መረማመጃውም ሆነ አዳራሹ በሰው ተሞልቶ ነበር። በርካቶችም ደስታቸውን፣ ተስፋቸውን እንዲሁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቶች የተዥጎደጎዱበት ወቅት ነበር። ለአዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሹመት ግን ሁሉ ፀጥ ረጭ ብሏል። ለዚህም ዋነኛው የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት በወጣው መመሪያ ምክንያት ነው። ነገር ግን በርካቶች በዓለ ሲመታቸውን ባይታደሙም፤ ፊት ለፊት ተገኝተው እንኳን ደስ አለዎት ባይሉም በዲፕሎማቱ ማህበረሰብ ውስጥ የእፎይታ ስሜት ተፈጥሯል። "ብዙዎች በብሊንከን መምጣት ከመጠን በላይ በፈንጠዝያ ላይ ናቸው፤ በሱ መምጣት ብቻ ሳይሆን የቀድሞው ቡድን ቢሮውን ለቆ በመውጣቱ" በማለት አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣን በቤታቸው በዓለ ሲመቱን እየተመለከቱ ባሉበት ነግረውኛል። ብሊንከን አንጋፋ የሚባሉ ዲፕሎማት ናቸው። ለበርካታ አመታት በዘርፉ ላቅ ያለ ልምድን አካብተዋል። ነገር ግን በርካታ ሁኔታዎች ተቀይረዋል፤ "እምነትንና ሞራልና ለመመለስ የሚገጥማቸው ፈተና ቀላል ላይሆን ይችላል" ይላሉ እኚሁ ባለስልጣን። በትራምፕ አስተዳደር ወቅት ሁኔታውን መቀበል ያቃታቸው 1 ሺህ ሰራተኞች ለቅቀዋል። በሃሳብ ብንለያይም ከአስተዳደሩ ጋር እንቀጥላለን ያሉ ደግሞ በቀድሞው ፕሬዚዳንት ዲፕሎማሲያዊ ያልሆነ አካሄድ ወደ ጎን በመገፋት፣ በሬክስ ቲለርሰን አጉል አሰራር በመሰላቸት እንዲሁ የትራምፕ ቀንደኛ ደጋፊ በሆኑት ማይክ ፖምፒዮ ፖለቲካ ገሸሽ እንዲደረጉ ሆኗል። "ሁላችንም ቢሆን በአለም ላይ ያለን ገፅታ መቀየሩ ከፍተኛ ደስታ ይሰጠናል" ይላሉ ባለስልጣኑ። "በአራት አመቱ የትራምፕ አስተዳደር ገሽሽ ተደርጎ የነበረው ሁሉ ወደ ስራ ለመግባትና ነገሮችን ለመቀየር እየሞከረ ነው" በማለት ያክላሉ። የፕሬስ ፅህፈት ቤቱ መተላለፊያ የነበረው የማይክ ፖምፒዮ ፎቶ ተነስቶ በምትኩ የተለያዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ፎቶ እንዲሰቀል ተደርጓል። ከዚህም በተጨማሪ የሥራ አስፈላጊነትና ባለሙያነት ጋር የተያያዘ በማይክ ፖምፒዮ የተፃፈ ትልቅ ቢልቦርድ የጆ ባይደን በዓለ ሲመትን ተከትሎ እንዲወርድ ተደርጓል። አዲሱ የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች ላይ የረዥም አመት ልምድን አካብተዋል፤ ለዘመናትም የባይደን ቅርብ አማካሪ በመሆን ጠንከር ያለ ግንኙነትን መስርተዋል። በሹመታቸው ወቅት ለዘብ ባለ ንግግግራቸው የትራምፕን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በመቀልበስ እንደገና እንደሚፅፉት ያስገነዘቡ ሲሆን ከፍተኛ ድጋፍም ተችሯቸዋል። የአሜሪካ እንደራሴዎችም ቢሆን ይህንን ከሌሎች አገሮች ጋር መጋተሩንና "አሜሪካ ትቅደም" የሚለውን አካሄድ ወደኋላ መተው ይፈልጋሉ። ብሊንከን መጀመሪያ አከናውናቸዋለሁ ብለው ቃል የገቧቸው ጉዳዮች ቢኖሩ የሩሲያ ሳይበር ጥቃትና የምርጫ ጣልቃ መግባት ምላሽ፣ ሳዑዲ በየመን የምታደርገውን የአየር ጥቃት ማስቆም፣ በትራምፕ አስተዳደር አሸባሪ ተብለው የተፈረጁትን የሁቲ አማፅያን ሁኔታ እንደገና መገምገም የሚሉ ናቸው። የሁቲ አማፅያን በአሸባሪነት መፈረጅ በየመን ያለውን የሰብዓዊ እርዳታዎች ላይ እክል ሊፈጥር ይችላል ተብሎ ይታመናል። ኢራንን በተመለከተ ብሊንከን ባይደን ቃል የገቡትን የደገሙ ሲሆን ይኸም የ2015ቱን የኢራን የኒውክሊየር ስምምነትን መመለስ ነው። ባራክ ኦባማ በስልጣን ዘመናቸው ወቅት አሳክተዋቸዋል ከሚባሉት ጉዳዮች ውስጥ (JCPOA) ተብሎ የሚጠራው የኢራን የኒውክሊየር ፕሮግራም ሲሆን ፕሬዚዳንት ትራምፕ በ2018 ስምምነቱን አፍርሰዋል። ወደ ስምምነቱ እንዲመለሱ ግን ኢራን የገባችውን ቃል ስታከብር እንደሆነና ይህ የማይሆን ከሆነ በጥንቃቄ ሊታይ ይገባል ይላሉ። ቻይናን በተመለከተ ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጠንከር ያለ አስተያየትና አካሄድ ጋር ይስማማሉ። ቻይናን ለማዳከም ትራምፕ ውድቅ ካደረጓቸው የዲሞክራሲ ደጋፊዎችና አለም አቀፍ ተቋማት ጋር መተባበር ያስፈልጋል በማለት አፅንኦት ይሰጣሉ። የአዲሱ ከፍተኛ ዲፕሎማት ዋነኛ አላማና ተልዕኮ የአሜሪካን መሪነት ቦታ እንደገና በዚያ መንገድ መመለስ ነው። ነገር ግን በተሾሙበት ቀን ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ውይይት በመጥፎ ይታይ ከነበረው የአሜሪካ አስተዳደር ጋር ተያይዞ እንዴት የቀድሞ አጋሮቿ ያምኗታል የሚል ነበር ። ነገር ግን ብሊንከን አሜሪካ ወደቀደመ ስፍራዋ ለመመለስ ያለው ፍላጎት ከአጋሮቿም በኩል የመጣ ነው ይላሉ። በመጀመሪያ ቀናቸው ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ውይይት ከሚዲያውና ከጋዜጠኞች ጋር ለመስራት ያላቸውን ቀናነት በግልፅ አሳይተዋል። ይህ አካሄድ ደግሞ ከቀድሞው አስተዳደደር ተቃራኒ ነው። ማይክ ፖምፒዮ እንደ አለቃቸው ሚዲያን አይወዱም አያዳምጡም፤ አንዳንድ ጊዜም ሲያወግዙ ይሰማሉ። ለጥያቄዎቻችን ኢሜይል መልስ ለማግኘት በጣም ፈታኝ ነበር። ደፈር ያሉ የኮሚዪኒኬሽን ቡድኑ አባላት ምንም የምንለው የለም የሚል መልስ ይሰጡን ነበር። የብሊንከን አካሄድ ልታይ ልታይ ይሉ ከነበሩት የማይክ ፖምፒዮ ሁኔታ ተቃራኒ ነው። ሆኖም በአሁኑ ወቅት በአዲሱ አስተዳደር የፕሬዚዳንቱ የአየር ንብረት ለውጥ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑትና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነታቸው ከፍተኛ ስፍራ የተጎናፀፉት የቀድሞ አለቃቸው ጆን ኬሪ ጋር ይወዳደራሉ። ነገር ግን ብሊንከንም ቢሆኑ ለየት ያለ ባለታሪካቸው የተጎናፀፉት ማንነት አለ። አያታቸው በሩሲያ የነበረውን የፀረ- ይሁዲዎች ነውጥ ፈርተው ወደ አሜሪካ በስደት መጡ፤ ፖላንዳዊ እንጀራ አባታቸው እንዲሁ በናዚዎች ከተቃጣባቸው ግድያ በአሜሪካውያን ወታደሮች የዳኑ ናቸው። "ማንነታችን ይኼ ነው። በአለም ላይ የምንወክለውም ይህንኑ ነው። እንደ ሰው ጉድለቶች ቢኖሩንብንም ምርጥ ለመሆን እንሞክራለን" ብለዋል። በአሁኑ ወቅት አሜሪካ አሁንም ቢሆን ጠቃሚነቷን ማረጋገጥ የስራቸው ማዕከል እንደሆነ ያስባሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-55829616 |
3politics
| የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ሶስተኛ የስልጣን ዘመናቸውን አወጁ | የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ለሶስተኛ ጊዜ አገሪቷን ሊመሩ ነው። ዢ ዢንፒንግ የቻይናው ገዥ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ባደረገው ጉበኤ ዋና ጸሓፊ አድርጎ መምረጡን ተከትሎም ነው ለሶስተኛ ጊዜ ስልጣናቸው የተራዘመው። የፓርቲው ዋና ጸሃፊ በሃገሪቱ የመሪነት ቦታ የሚያስገኝ ሲሆን መጋቢት በሚደረገውም የብሄራዊ ህዝቦች ጉባኤ በይፋ ስልጣናቸው ይጸድቃል። ፓርቲው በተጨማሪም 25 አባላት ያሉትን የፖሊት ቢሮ እንዲሁም ሰባት አባላት ያሉትን ቋሚ የፖሊት ቢሮን መርጧል። ፕሬዚዳንቱ ከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸውንም ያስተዋወቁ ሲሆን ከነዚህም መካከል የቀድሞው የሻንጋይ ፓርቲ መሪ ይገኙበታል። ሊ ኪያንግ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም ይሆናሉ። ዢ ጂንፒንግ በዛሬው ዕለት አዲሱን የፖሊት ቢሮ ቋሚ ኮሚቴንም እየመሩ ወደ መድረክ መጥተዋል። ፕሬዚዳንቱ ለመገናኛ ብዙኃንም ፓርቲያቸው በትናንትናው ዕለት ያደረገውን ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዳጠናቀቀና ገልጸው “ጥንካሬያችንን በማሰባሰብ በአንድነት ወደፊት እንቀጥላለን” ብለዋል። አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጉባኤውን በከፍተኛ ፍላጎት ሲከታተል መቆየቱን ጠቅሰው የሀገር መሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክትና ደብዳቤ መላካቸውን በመግለጽ ለሁሉም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ከዚያም አዲሱን የፖሊት ቢሮ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በማስተዋወቅ “ሁሉንም በደንብ ታውቋቸዋላችሁ” በማለት ተናግረዋል። ዢ ሶስተኛ የስልጣን ዘመናቸውን አውጀው አዲሱ የአመራር ቡድናቸውን ካስተዋወቁ በኋላም ንግግር አድርገዋል። በዚህ ንግግራቸው ቻይናን የምትመራበት አቅጣጫ በተመለከተ ፍንጭ ሰጥተዋል። ሃገሪቱ ለአለም ኢኮኖሚ በሯን እየዘጋጀች ነው የሚል ስጋት በጨመረበት ወቅት ፕሬዚዳንቱ “ ቻይና ያለተቀረው አለም ማደግ አትችልም እናም አለምም ቻይናን ይፈልጋል” ብለዋል። አክለውም “ከአርባ ዓመታት በላይ ባደረግነው የለውጥ እንቅስቃሴ ሁለት ተአምራትን መፍጠር ችለናል። ፈጣን የኢኮኖሚ ልማት እና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ማህበራዊ መረጋጋት ነው” ብለዋል | የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ሶስተኛ የስልጣን ዘመናቸውን አወጁ የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ለሶስተኛ ጊዜ አገሪቷን ሊመሩ ነው። ዢ ዢንፒንግ የቻይናው ገዥ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ባደረገው ጉበኤ ዋና ጸሓፊ አድርጎ መምረጡን ተከትሎም ነው ለሶስተኛ ጊዜ ስልጣናቸው የተራዘመው። የፓርቲው ዋና ጸሃፊ በሃገሪቱ የመሪነት ቦታ የሚያስገኝ ሲሆን መጋቢት በሚደረገውም የብሄራዊ ህዝቦች ጉባኤ በይፋ ስልጣናቸው ይጸድቃል። ፓርቲው በተጨማሪም 25 አባላት ያሉትን የፖሊት ቢሮ እንዲሁም ሰባት አባላት ያሉትን ቋሚ የፖሊት ቢሮን መርጧል። ፕሬዚዳንቱ ከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸውንም ያስተዋወቁ ሲሆን ከነዚህም መካከል የቀድሞው የሻንጋይ ፓርቲ መሪ ይገኙበታል። ሊ ኪያንግ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም ይሆናሉ። ዢ ጂንፒንግ በዛሬው ዕለት አዲሱን የፖሊት ቢሮ ቋሚ ኮሚቴንም እየመሩ ወደ መድረክ መጥተዋል። ፕሬዚዳንቱ ለመገናኛ ብዙኃንም ፓርቲያቸው በትናንትናው ዕለት ያደረገውን ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዳጠናቀቀና ገልጸው “ጥንካሬያችንን በማሰባሰብ በአንድነት ወደፊት እንቀጥላለን” ብለዋል። አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጉባኤውን በከፍተኛ ፍላጎት ሲከታተል መቆየቱን ጠቅሰው የሀገር መሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክትና ደብዳቤ መላካቸውን በመግለጽ ለሁሉም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ከዚያም አዲሱን የፖሊት ቢሮ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በማስተዋወቅ “ሁሉንም በደንብ ታውቋቸዋላችሁ” በማለት ተናግረዋል። ዢ ሶስተኛ የስልጣን ዘመናቸውን አውጀው አዲሱ የአመራር ቡድናቸውን ካስተዋወቁ በኋላም ንግግር አድርገዋል። በዚህ ንግግራቸው ቻይናን የምትመራበት አቅጣጫ በተመለከተ ፍንጭ ሰጥተዋል። ሃገሪቱ ለአለም ኢኮኖሚ በሯን እየዘጋጀች ነው የሚል ስጋት በጨመረበት ወቅት ፕሬዚዳንቱ “ ቻይና ያለተቀረው አለም ማደግ አትችልም እናም አለምም ቻይናን ይፈልጋል” ብለዋል። አክለውም “ከአርባ ዓመታት በላይ ባደረግነው የለውጥ እንቅስቃሴ ሁለት ተአምራትን መፍጠር ችለናል። ፈጣን የኢኮኖሚ ልማት እና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ማህበራዊ መረጋጋት ነው” ብለዋል | https://www.bbc.com/amharic/articles/cx8w5pxrz4vo |
5sports
| የኢትዮጵያ ታሪክ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና | በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያና ሜዳሊያ የተገናኙት ገና ከጅምሩ ፊንላንድ ሄልሲንኪ በተደረገው የመጀመሪያው ውድድር ነበር። በዚህ የመጀመሪያው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ለኢትዮጵያ እንዲሁም ለአፍሪካ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ያስገኘው አትሌት ከበደ ባልቻ ነው። ከበደ በማራቶን ውድድር ሁለተኛ ወጥቶ የብር ሜዳሊያ በማጥለቅ ችቦውን አቀጣጠለ። ነገር ግን ቀጥሎ በጣሊያኗ ከተማ ሮም በተካሄደው ሁለተኛው ውድድር ኢትዮጵያ አልተሳተፈችም ነበር። በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በርካታ ሜዳሊያ በመሰብሰብ አሜሪካንን የሚደርስባት የለም። ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ደግሞ ጎረቤት አገር ኬንያ ናት። ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር እስካሁን ባከማቻቸው ሜዳሊያዎች ከዓለም ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ተሾመ ቀዲዳ የ2022 የኦሬገን ሻምፒዮናን ሳይጨምር ኢትዮጵያ 85 ሜዳሊያዎች አሏት ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። “ኢትዮጵያ በዓለም ቻምፒዮና ታሪክ 29 ወርቅ፣ 30 ብር እንዲሁም 26 የነሐስ ሜዳሊያዎች፤ በአጠቃላይ 85 ሜዳሊያ አላት።” በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የተለየ ታሪክ አላት የሚለው ጋዜጠኛው፣ አትሌት ከበደ ባልቻም በማራቶን መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ የብር ሜዳሊያ ያስገኘ አፍሪካዊ መሆኑን ያወሳል። በፈር ቀዳጁ ውድድር ኢትዮጵያ በከበደ ባልቻ ነሐስ ሜዳሊያ ከዓለም 15ኛ ሆና አጠናቃለች። ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት የቻለች ብቸኛዋ አፍሪካዊት አገር ናት። በወቅቱ ምሥራቅ ጀመርን [ጀርመን አንድ ከመሆኗ በፊት] 19 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ አንደኛ ሆና ስታጠናቅቅ፣ የውድድሩ ኃያል አገር አሜሪካ ደግሞ ሁለተኛ ሆና ነበር። በጣልያኗ ሮም በተካሄደው ሁለተኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና “የአትሌቲክስ ቡድን እየመራ የሚጓዝ አሠልጣኝ ባለመገኘቱ ነው ኢትዮጵያ ያልተሳተፈችው” ይላል ጋዜጠኛ ተሾመ። ኢትዮጵያ በዚህ ታላቅ የአትሌቲክስ መድረክ የመጀመሪያውን ወርቅ ያገኘችው በአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ አማካይነት ነው። ኃይሌ የጀርመኗ ስቱትጋርት ባዘጋጀችው አራተኛው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር ወርቅ ማምጣት ችሏል። አትሌቱ በዚህ ሳይገታ በ5 ሺህ ውድድር ደግሞ የነሐስ ሜዳሊያ ለአገሩ አስገኝቷል። አትሌት ፊጣ ባይሳ ደግሞ ሌላ ነሐስ አክሎ ኢትዮጵያ በሦስት ሜዳሊያ አሸብርቃ ተመለሰች። ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መድረክ በስዊድኗ ጉተምበርግ ከተማ እስከተሰናዳው ውድድር ድረስ ከአፍሪካ አንደኛ ሆና ስታጠናቅቅ ቆየች። ነገር ግን በጉተምበርግ በተካሄደው ውድድር ኬንያ ወደ ኃይልነት መጣች። በዚህ ውድድር ኬንያ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ጨምሮ ስድስት ሜዳሊያ በመሰብሰብ ስሟን ከፍ አደረገች። በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያና ኬንያ ከጉተምበርጉ ፍልሚያ በኋላ ፉክክራቸው እየበረታ መጣ። በፈረንጆቹ 2003 በተካሄደው የፓሪሱ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 3 ወርቅ፣ 2 ብርና 2 ነሐስ በማምጣት ከዓለም አራተኛ ሆና ያጠናቀቀችበት መድረክ የሚረሳ አይደለም ይላል ጋዜጠኛ ተሾመ። በሄልሲንኪ የተካሄደው 10ኛው ሻምፒዮና ግን ልዩ ነበር ሲል ያክላል። ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር ከአሜሪካና ከሩሲያ በመቀጠል በ3 ወርቅ፣ በ4 ብርና በ2 ነሐስ ከዓለም ሦስተኛ ሆና አጠናቀቀች። ይህ የሄልሲንኪው ውድድር “አረንጓዴው ጎርፍ” ተብሎ ይጠራል። አረንጓዴው ጎርፍ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሦስት ተከታትለው በመግባት ዓለምን አጀብ ያሰኙበት ዘመን ነው። አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ 2 ወርቅ ባጠለቅችበት በዚህ ውድድር የአረንጓዴው ጎርፍ አርማዎቹ መሠረት ደፋር፣ ብርሃኔ አደሬ እና እጅጋየሁ ዲባባ የነበራቸው ተሳትፎ የሚዘነጋ አይደለም። በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ደግሞ ቀነኒሳ በቀለና ስለሺ ስህን ተከታትለው በመግባት ሄልሲንኪን የማይረሳ አድረጓት። ከሁለት ዓመታት በኋላ ግን ጃፓን ኦሳካ ባሰናዳችው ውድድር ድል ወደ ኬንያ ዞረ። ኬንያ በዚህ ሻምፒዮና 5 ወርቅን ጨምሮ 15 ሜዳሊያዎች አሸነፈች። ከዚያ በኋላ በነበሩት የበርሊን፣ ዴጎ፣ ሞስኮ፣ ቤይጂንግ፣ ለንዶን፣ ዶሃ ላይ ኬንያ በሜዳሊያ ብዛት ኢትዮጵያን እየመራች ቆይታለች። ደራርቱ ቱሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ሻምፒዮና የተሳተፈችው በፈረንጆቹ 1991 ቶኪዮ በተዘጋጀው ውድድር ነበር። ምንም እንኳ ደራርቱ በተሳተፈተችበት የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ሜዳሊያ ባታመጣም በቀጣዩ ዓመት ባርሴሎና በተዘጋጀው ኦሊምፒክ ላይ ወርቅ ማጥለቅ ችላለች። የአገሯን ስም በተለያዩ መድረኮች ያስጠራችው ደራርቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆና ከተመረጠች በኋላ ለውጥ ማምጣት ችላለች ቢባል ማጋነን አይሆንም። ነገር ግን ለደራርቱ ሁኔታዎች ሁሉ የተመቻቹ ነበሩ ማለት ከባድ ነው። ደራርቱ ፌዴሬሽኑን መምራት ከጀመረች ወዲህ ሁለት ጊዜ በዓለም ሻምፒዮና፤ አንድ ጊዜ በኦሊምፒክ መድረክ፤ አንድ ጊዜ ደግሞ በዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ተሳትፋለች። በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ በተሰናደው የ2019 የዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለት ወርቅ፣ አምስት ብርና አንድ ነሐስ ይዛ ተመልሳለች። በዚህ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች በሚታወቁበት የመካከለኛና ረዥም ርቀት ውድድር የተለመደውን ወርቅ ማስመዝገብ ባይችሉም ተስፋ ያላቸው አትሌቶች ታይተዋል። ኢትዮጵያ በመድረኩ በስምንት ሜዳሊያ አምስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቀቀች። ከዚህ በኋላ በደራርቱ የተመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ታላቅ ወደ ሚባለው የኦሊምፒክ መድረክ ነው ያቀናው። በ2022 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ ያገኘችው ሜዳሊያ ብዛት አራት ነው። ይህ ውጤት ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ መድረክ ካመጣቻቸው ዝቅተኛ ከተባሉት የሚመደብ ነው። ቀጥሎ ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት ዓለም አቀፍ መድረክ ባለፈው መጋቢት የተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ፍልሚያ ነው። ይህ መድረክ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ደምቀው የታዩበት ነበር። ኢትዮጵያ፤ በአራት ወርቅ፣ በሦስት ብርና በሁለት የነሐስ አሜሪካን አስከትላ ከዓለም ቁንጮ ሆና አጠናቃለች። በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት እየተካሄደ ባለው የዘንድሮው የዓለም ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ውጤት ከጅምሩ አመርቂ መሆን ችሏል። በተለይ በመድረኩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የምንጊዜም ተቀናቃኝ የሆነችው ኬንያ በምትታወቅባቸው ሩጫዎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ብቅ ብቅ ማለታቸው አነጋጋሪ ሆኗል። ኬንያና ኢትዮጵያ ድንበር ብቻ አይደለም የሚጋሩት። ሜዳሊያ የሚታደልበት የአትሌቲክስ መድረክንም ጭምር እንጂ። በተለይ በረዥም ርቀት የሩጫ ውድድር ሁለቱ አገራት በየመድረኩ አንገት ለአንገት ሲተናነቁ ማየት አዲስ አይደለም። ኃይሌና ፖልቴርጋን በሚሊ ሜትር ተቀዳድመው ሲገቡ የነበረውን ትዕይንት ማን ይዘነጋል። ቀነኒሳና ኪፕቾጌ በሁለት ሰከንድ ልዩነት የጨበጡት የማራቶን ክብረ ወሰንም እንዲሁም ተመዝገቦ የሚኖር ነው። ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በመካከለኛ ርቀት ማለትም በ5 ሺህና በ10 ሺህ ሜትር፤ ኬንያ ደግሞ በአጭርና በመካከለኛ የ800፣ የ1500 እና የ3000 ሜትር ርቀቶች ሲነግሱ ማየት የተለመደ ነው። ነገር ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኬንያዊያን በመካከለኛ ርቀት ኢትዮጵያን ሲፋለሙ ተመልክተናል። ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ደግሞ በ1500 እና 3000 ሜትር መሰናክል ውድድሮች ኬንያዊያንን መፈተን ይዘዋል። ለምሳሌ በ2019 የዶሃ ዓለም ሻምፒዮና በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ኬንያዊው ኪፕሩቶ ታዳጊው ኢትዮጵያዊ ሌሜቻ ግርማን በሚሊ ሜትር ቀድሞ ወርቅ ያጠለቀበት ውድድር የሚዘነጋ አይደለም። ለሜቻ ግርማ በ3000 መሰናክል ለኢትዮጵያ ሜዳሊያ ያስገኘ የመጀመሪያው ወንድ አትሌት ነው። አትሌት ሶፊያ አሰፋ በ2013 ሞስኮ ላይ ያገኘችው ነሐስ በርቀቱ ብቸኛው የኢትዮጵያ ሜዳሊያ ነበር። በዘንድሮው የኦሪገን ዓለም ሻምፒዮና የታየውም ይህ ነው። ለሜቻ ግርማ በርቀቱ ሁለተኛ ብሩን በተከታታይ አጥልቋል። ጉዳፍ ፀጋይ ደግሞ በ1500 ሜትር ለአገሯ ብር አስገኝታለች። ኬንያዊቷ ፌይዝ ኪፕየጎን ለአገሯ ብቸኛውን ወርቅ አስገኝታለች። የኬንያ መገናኛ ብዙኃን በዘንድሮው የኦሪገን ውጤት ደስተኛ አለመሆናቸውን እየገለጡ ነው። ኬንያ ባለፈው የዓለም ሻምፒዮናም ሆነ በኦሊምፒክ መድረክ ከኢትዮጵያ ልቃ ብታጠናቅቅም በዓለም የቤት ውስጥ ውድድርና በአሜሪካው የዓለም ሻምፒዮና የተመዘገበው ውጤት አመርቂ ሆኖ አልተገኘም። በአሜሪካዋ ኦሪገን ግዛት እየተካሄደ የሚገኘው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መጪው እሁድ ይጠናቀቃል። በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ በወንዶች እና ሴቶች ከ800 ሜትር እስከ ማራቶን ባሉ የውድድር ዘርፎች እየተሳተፈች ትገኛለች። በዚህ ውድድር እስከ አሁን ሦስት የወርቅ ሜዳሊያ፣ አራት ብር እና አንድ የነሃስ ሜዳልያ በማምጣት ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ እሑድ እለት የሚካሄዱት የ800 እና 5000 ሜትር ውድድሮች በጉጉት ይጠበቃሉ። ኢትዮጵያ እስከ አሁን በዚህ ውድድር ካገኘቻቸው ስምንት ሜዳሊያዎች አምስቱ በሴት አትሌቶች የተገኙ ናቸው። የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በፈረንጆቹ ከ1983 ጀምሮ በየሁለት ዓመት ልዩነት መካሄድ የጀመረ ሲሆን፤ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በ5000 እና በ10000 ሜትር ውድድሮች ስመ ጥር ሆነውበታል። ቀደም ሲል በ10 ሺህ ሜትር፣ በ5 ሺህ ሜትር እና በግማሽ ማራቶን፤ ሦስት የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነችው አትሌት ለተሰንበት ግደይ በዚህ ታላቅ መድረክ አሸናፊነቷን አስጠብቃለች። ለተሰንበት ከውድድሩ በኋላ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጠችው አስተያየት “ህልሜ እውን ሆኗል። ይህ ድል ከዓለም ክብረወሰን በበለጠ ለእኔ ትልቅ ነው። በውጤቱ በጣም ደስተኛ ነኝ” ብላለች። አትሌት ጎተይቶም ገብረሥላሴም በሴቶች ማራቶች የሻምፒዮናውን ክብረ ወሰን በመስበር አሸናፊ መሆኗ ይታወሳል። በኦሪገን መድረክ ደግሞ በማራቶን ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች። ከዚህ በፊት ማሬ ዲባባ በ2015 ቤይጂንግ በተካሄደው የዓለም ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆና ነበር። ኢትዮጵያ፤ በተለይ በፈረንጆቹ ከ1999 እስከ 2007 ባሉት ዓመታት በ10 ሺህ እና በ5 ሺህ ሜትር ከአንድ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ውድድሩን በማሸነፍ በርካታ ሜዳሊያ አካብታለች። ጌጤ ዋሚ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ወርቅነሽ ኪዳኔ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ ብርሃኔ አደሬ፣ አልማዝ አያና እና ሌሎች በአትሌቲክሱ ዓለም አገራቸውና ያስጠሩ ሴት አትሌቶች ናቸው። አሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ ያለውን ውድድርን ሳይጨምር ኢትዮጵያ በተሳተፈችባቸው የአትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች 85 ሜዳሊያዎችን ስታስመዘገብ፣ ከዚህ ውስጥ ደግሞ ወደ ግማሽ የሚጠጋው የተገኘው በሴቶች ነው። በዚህም 38ቱ ሜዳሊያዎች በ1500፣ በ3000፣ 5000 እና በ10000 ሜትር እንዲሁም 2 ሜዳሊያዎች በማራቶን ውድድሮች ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች ያሰነፉት ሲሆን በአጠቃላይም 40 ሜዳሊያዎችን አስገኝተዋል። | የኢትዮጵያ ታሪክ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያና ሜዳሊያ የተገናኙት ገና ከጅምሩ ፊንላንድ ሄልሲንኪ በተደረገው የመጀመሪያው ውድድር ነበር። በዚህ የመጀመሪያው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ለኢትዮጵያ እንዲሁም ለአፍሪካ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ያስገኘው አትሌት ከበደ ባልቻ ነው። ከበደ በማራቶን ውድድር ሁለተኛ ወጥቶ የብር ሜዳሊያ በማጥለቅ ችቦውን አቀጣጠለ። ነገር ግን ቀጥሎ በጣሊያኗ ከተማ ሮም በተካሄደው ሁለተኛው ውድድር ኢትዮጵያ አልተሳተፈችም ነበር። በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በርካታ ሜዳሊያ በመሰብሰብ አሜሪካንን የሚደርስባት የለም። ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ደግሞ ጎረቤት አገር ኬንያ ናት። ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር እስካሁን ባከማቻቸው ሜዳሊያዎች ከዓለም ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ተሾመ ቀዲዳ የ2022 የኦሬገን ሻምፒዮናን ሳይጨምር ኢትዮጵያ 85 ሜዳሊያዎች አሏት ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። “ኢትዮጵያ በዓለም ቻምፒዮና ታሪክ 29 ወርቅ፣ 30 ብር እንዲሁም 26 የነሐስ ሜዳሊያዎች፤ በአጠቃላይ 85 ሜዳሊያ አላት።” በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የተለየ ታሪክ አላት የሚለው ጋዜጠኛው፣ አትሌት ከበደ ባልቻም በማራቶን መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ የብር ሜዳሊያ ያስገኘ አፍሪካዊ መሆኑን ያወሳል። በፈር ቀዳጁ ውድድር ኢትዮጵያ በከበደ ባልቻ ነሐስ ሜዳሊያ ከዓለም 15ኛ ሆና አጠናቃለች። ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት የቻለች ብቸኛዋ አፍሪካዊት አገር ናት። በወቅቱ ምሥራቅ ጀመርን [ጀርመን አንድ ከመሆኗ በፊት] 19 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ አንደኛ ሆና ስታጠናቅቅ፣ የውድድሩ ኃያል አገር አሜሪካ ደግሞ ሁለተኛ ሆና ነበር። በጣልያኗ ሮም በተካሄደው ሁለተኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና “የአትሌቲክስ ቡድን እየመራ የሚጓዝ አሠልጣኝ ባለመገኘቱ ነው ኢትዮጵያ ያልተሳተፈችው” ይላል ጋዜጠኛ ተሾመ። ኢትዮጵያ በዚህ ታላቅ የአትሌቲክስ መድረክ የመጀመሪያውን ወርቅ ያገኘችው በአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ አማካይነት ነው። ኃይሌ የጀርመኗ ስቱትጋርት ባዘጋጀችው አራተኛው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር ወርቅ ማምጣት ችሏል። አትሌቱ በዚህ ሳይገታ በ5 ሺህ ውድድር ደግሞ የነሐስ ሜዳሊያ ለአገሩ አስገኝቷል። አትሌት ፊጣ ባይሳ ደግሞ ሌላ ነሐስ አክሎ ኢትዮጵያ በሦስት ሜዳሊያ አሸብርቃ ተመለሰች። ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መድረክ በስዊድኗ ጉተምበርግ ከተማ እስከተሰናዳው ውድድር ድረስ ከአፍሪካ አንደኛ ሆና ስታጠናቅቅ ቆየች። ነገር ግን በጉተምበርግ በተካሄደው ውድድር ኬንያ ወደ ኃይልነት መጣች። በዚህ ውድድር ኬንያ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ጨምሮ ስድስት ሜዳሊያ በመሰብሰብ ስሟን ከፍ አደረገች። በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያና ኬንያ ከጉተምበርጉ ፍልሚያ በኋላ ፉክክራቸው እየበረታ መጣ። በፈረንጆቹ 2003 በተካሄደው የፓሪሱ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 3 ወርቅ፣ 2 ብርና 2 ነሐስ በማምጣት ከዓለም አራተኛ ሆና ያጠናቀቀችበት መድረክ የሚረሳ አይደለም ይላል ጋዜጠኛ ተሾመ። በሄልሲንኪ የተካሄደው 10ኛው ሻምፒዮና ግን ልዩ ነበር ሲል ያክላል። ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር ከአሜሪካና ከሩሲያ በመቀጠል በ3 ወርቅ፣ በ4 ብርና በ2 ነሐስ ከዓለም ሦስተኛ ሆና አጠናቀቀች። ይህ የሄልሲንኪው ውድድር “አረንጓዴው ጎርፍ” ተብሎ ይጠራል። አረንጓዴው ጎርፍ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሦስት ተከታትለው በመግባት ዓለምን አጀብ ያሰኙበት ዘመን ነው። አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ 2 ወርቅ ባጠለቅችበት በዚህ ውድድር የአረንጓዴው ጎርፍ አርማዎቹ መሠረት ደፋር፣ ብርሃኔ አደሬ እና እጅጋየሁ ዲባባ የነበራቸው ተሳትፎ የሚዘነጋ አይደለም። በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ደግሞ ቀነኒሳ በቀለና ስለሺ ስህን ተከታትለው በመግባት ሄልሲንኪን የማይረሳ አድረጓት። ከሁለት ዓመታት በኋላ ግን ጃፓን ኦሳካ ባሰናዳችው ውድድር ድል ወደ ኬንያ ዞረ። ኬንያ በዚህ ሻምፒዮና 5 ወርቅን ጨምሮ 15 ሜዳሊያዎች አሸነፈች። ከዚያ በኋላ በነበሩት የበርሊን፣ ዴጎ፣ ሞስኮ፣ ቤይጂንግ፣ ለንዶን፣ ዶሃ ላይ ኬንያ በሜዳሊያ ብዛት ኢትዮጵያን እየመራች ቆይታለች። ደራርቱ ቱሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ሻምፒዮና የተሳተፈችው በፈረንጆቹ 1991 ቶኪዮ በተዘጋጀው ውድድር ነበር። ምንም እንኳ ደራርቱ በተሳተፈተችበት የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ሜዳሊያ ባታመጣም በቀጣዩ ዓመት ባርሴሎና በተዘጋጀው ኦሊምፒክ ላይ ወርቅ ማጥለቅ ችላለች። የአገሯን ስም በተለያዩ መድረኮች ያስጠራችው ደራርቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆና ከተመረጠች በኋላ ለውጥ ማምጣት ችላለች ቢባል ማጋነን አይሆንም። ነገር ግን ለደራርቱ ሁኔታዎች ሁሉ የተመቻቹ ነበሩ ማለት ከባድ ነው። ደራርቱ ፌዴሬሽኑን መምራት ከጀመረች ወዲህ ሁለት ጊዜ በዓለም ሻምፒዮና፤ አንድ ጊዜ በኦሊምፒክ መድረክ፤ አንድ ጊዜ ደግሞ በዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ተሳትፋለች። በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ በተሰናደው የ2019 የዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለት ወርቅ፣ አምስት ብርና አንድ ነሐስ ይዛ ተመልሳለች። በዚህ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች በሚታወቁበት የመካከለኛና ረዥም ርቀት ውድድር የተለመደውን ወርቅ ማስመዝገብ ባይችሉም ተስፋ ያላቸው አትሌቶች ታይተዋል። ኢትዮጵያ በመድረኩ በስምንት ሜዳሊያ አምስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቀቀች። ከዚህ በኋላ በደራርቱ የተመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ታላቅ ወደ ሚባለው የኦሊምፒክ መድረክ ነው ያቀናው። በ2022 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ ያገኘችው ሜዳሊያ ብዛት አራት ነው። ይህ ውጤት ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ መድረክ ካመጣቻቸው ዝቅተኛ ከተባሉት የሚመደብ ነው። ቀጥሎ ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት ዓለም አቀፍ መድረክ ባለፈው መጋቢት የተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ፍልሚያ ነው። ይህ መድረክ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ደምቀው የታዩበት ነበር። ኢትዮጵያ፤ በአራት ወርቅ፣ በሦስት ብርና በሁለት የነሐስ አሜሪካን አስከትላ ከዓለም ቁንጮ ሆና አጠናቃለች። በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት እየተካሄደ ባለው የዘንድሮው የዓለም ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ውጤት ከጅምሩ አመርቂ መሆን ችሏል። በተለይ በመድረኩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የምንጊዜም ተቀናቃኝ የሆነችው ኬንያ በምትታወቅባቸው ሩጫዎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ብቅ ብቅ ማለታቸው አነጋጋሪ ሆኗል። ኬንያና ኢትዮጵያ ድንበር ብቻ አይደለም የሚጋሩት። ሜዳሊያ የሚታደልበት የአትሌቲክስ መድረክንም ጭምር እንጂ። በተለይ በረዥም ርቀት የሩጫ ውድድር ሁለቱ አገራት በየመድረኩ አንገት ለአንገት ሲተናነቁ ማየት አዲስ አይደለም። ኃይሌና ፖልቴርጋን በሚሊ ሜትር ተቀዳድመው ሲገቡ የነበረውን ትዕይንት ማን ይዘነጋል። ቀነኒሳና ኪፕቾጌ በሁለት ሰከንድ ልዩነት የጨበጡት የማራቶን ክብረ ወሰንም እንዲሁም ተመዝገቦ የሚኖር ነው። ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በመካከለኛ ርቀት ማለትም በ5 ሺህና በ10 ሺህ ሜትር፤ ኬንያ ደግሞ በአጭርና በመካከለኛ የ800፣ የ1500 እና የ3000 ሜትር ርቀቶች ሲነግሱ ማየት የተለመደ ነው። ነገር ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኬንያዊያን በመካከለኛ ርቀት ኢትዮጵያን ሲፋለሙ ተመልክተናል። ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ደግሞ በ1500 እና 3000 ሜትር መሰናክል ውድድሮች ኬንያዊያንን መፈተን ይዘዋል። ለምሳሌ በ2019 የዶሃ ዓለም ሻምፒዮና በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ኬንያዊው ኪፕሩቶ ታዳጊው ኢትዮጵያዊ ሌሜቻ ግርማን በሚሊ ሜትር ቀድሞ ወርቅ ያጠለቀበት ውድድር የሚዘነጋ አይደለም። ለሜቻ ግርማ በ3000 መሰናክል ለኢትዮጵያ ሜዳሊያ ያስገኘ የመጀመሪያው ወንድ አትሌት ነው። አትሌት ሶፊያ አሰፋ በ2013 ሞስኮ ላይ ያገኘችው ነሐስ በርቀቱ ብቸኛው የኢትዮጵያ ሜዳሊያ ነበር። በዘንድሮው የኦሪገን ዓለም ሻምፒዮና የታየውም ይህ ነው። ለሜቻ ግርማ በርቀቱ ሁለተኛ ብሩን በተከታታይ አጥልቋል። ጉዳፍ ፀጋይ ደግሞ በ1500 ሜትር ለአገሯ ብር አስገኝታለች። ኬንያዊቷ ፌይዝ ኪፕየጎን ለአገሯ ብቸኛውን ወርቅ አስገኝታለች። የኬንያ መገናኛ ብዙኃን በዘንድሮው የኦሪገን ውጤት ደስተኛ አለመሆናቸውን እየገለጡ ነው። ኬንያ ባለፈው የዓለም ሻምፒዮናም ሆነ በኦሊምፒክ መድረክ ከኢትዮጵያ ልቃ ብታጠናቅቅም በዓለም የቤት ውስጥ ውድድርና በአሜሪካው የዓለም ሻምፒዮና የተመዘገበው ውጤት አመርቂ ሆኖ አልተገኘም። በአሜሪካዋ ኦሪገን ግዛት እየተካሄደ የሚገኘው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መጪው እሁድ ይጠናቀቃል። በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ በወንዶች እና ሴቶች ከ800 ሜትር እስከ ማራቶን ባሉ የውድድር ዘርፎች እየተሳተፈች ትገኛለች። በዚህ ውድድር እስከ አሁን ሦስት የወርቅ ሜዳሊያ፣ አራት ብር እና አንድ የነሃስ ሜዳልያ በማምጣት ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ እሑድ እለት የሚካሄዱት የ800 እና 5000 ሜትር ውድድሮች በጉጉት ይጠበቃሉ። ኢትዮጵያ እስከ አሁን በዚህ ውድድር ካገኘቻቸው ስምንት ሜዳሊያዎች አምስቱ በሴት አትሌቶች የተገኙ ናቸው። የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በፈረንጆቹ ከ1983 ጀምሮ በየሁለት ዓመት ልዩነት መካሄድ የጀመረ ሲሆን፤ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በ5000 እና በ10000 ሜትር ውድድሮች ስመ ጥር ሆነውበታል። ቀደም ሲል በ10 ሺህ ሜትር፣ በ5 ሺህ ሜትር እና በግማሽ ማራቶን፤ ሦስት የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነችው አትሌት ለተሰንበት ግደይ በዚህ ታላቅ መድረክ አሸናፊነቷን አስጠብቃለች። ለተሰንበት ከውድድሩ በኋላ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጠችው አስተያየት “ህልሜ እውን ሆኗል። ይህ ድል ከዓለም ክብረወሰን በበለጠ ለእኔ ትልቅ ነው። በውጤቱ በጣም ደስተኛ ነኝ” ብላለች። አትሌት ጎተይቶም ገብረሥላሴም በሴቶች ማራቶች የሻምፒዮናውን ክብረ ወሰን በመስበር አሸናፊ መሆኗ ይታወሳል። በኦሪገን መድረክ ደግሞ በማራቶን ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች። ከዚህ በፊት ማሬ ዲባባ በ2015 ቤይጂንግ በተካሄደው የዓለም ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆና ነበር። ኢትዮጵያ፤ በተለይ በፈረንጆቹ ከ1999 እስከ 2007 ባሉት ዓመታት በ10 ሺህ እና በ5 ሺህ ሜትር ከአንድ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ውድድሩን በማሸነፍ በርካታ ሜዳሊያ አካብታለች። ጌጤ ዋሚ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ወርቅነሽ ኪዳኔ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ ብርሃኔ አደሬ፣ አልማዝ አያና እና ሌሎች በአትሌቲክሱ ዓለም አገራቸውና ያስጠሩ ሴት አትሌቶች ናቸው። አሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ ያለውን ውድድርን ሳይጨምር ኢትዮጵያ በተሳተፈችባቸው የአትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች 85 ሜዳሊያዎችን ስታስመዘገብ፣ ከዚህ ውስጥ ደግሞ ወደ ግማሽ የሚጠጋው የተገኘው በሴቶች ነው። በዚህም 38ቱ ሜዳሊያዎች በ1500፣ በ3000፣ 5000 እና በ10000 ሜትር እንዲሁም 2 ሜዳሊያዎች በማራቶን ውድድሮች ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች ያሰነፉት ሲሆን በአጠቃላይም 40 ሜዳሊያዎችን አስገኝተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c51dx3qnynpo |
2health
| ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መጨመር እንዳሳሰባት ገለፀች | በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ደቡብ ሱዳን እንዳሳሰባት ገልፃለች። መጋቢት ወር ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጀምሮ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመጣባት ኢትዮጵያ በባለፉት ሳምንታት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደቡብ ሱዳኗ መዲና ጁባ በየቀኑ ከአዲስ አበባ በረራ የሚያደርግ ሲሆን ይሄም ሁኔታ አስጊ ነው በማለት የጤና ባለስልጣናቱ ተናግረዋል። "በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመር በእርግጥ ሊያሳስበን ይገባል፤ ስለዚህ የመከላከያ መንገዶቻችንንም ልናጠናክር ይገባል" በማለት የጤና ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ዶክተር ቶው ሎይ ሲንጎት በጁባ ለሚገኙ ሪፖርተሮች ተናግረዋል። ሆኖም ከአዲስ አበባ ወደ ጁባ በየቀኑ የሚደረጉት በረራዎችም እንደሚቀጥሉ የተናገሩት ቃለ አቀባይ ሁሉም አገራት ለዜጎቹ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት እንደሚደረገው ከፍተኛ ጥንቃቄን ተግባራዊ እናደርጋለን ብለዋል። "ከአዲስ አበባ የሚደረጉ የየቀኑ በረራዎች የሚቀጥሉ ይሆናል። አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ካልሆነ አይቆምም" ብለዋል ዶክተር ቶው ሎይ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 59 ሺህ 648 ደርሷል፤ ከነዚህም ውስጥ 21 ሺህ 789 ያገገሙ ሲሆን 933 ህይወታቸው እንዳለፈ በትናንትናው ዕለት የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጋራ መግለጫ አስፍሯል። | ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መጨመር እንዳሳሰባት ገለፀች በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ደቡብ ሱዳን እንዳሳሰባት ገልፃለች። መጋቢት ወር ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጀምሮ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመጣባት ኢትዮጵያ በባለፉት ሳምንታት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደቡብ ሱዳኗ መዲና ጁባ በየቀኑ ከአዲስ አበባ በረራ የሚያደርግ ሲሆን ይሄም ሁኔታ አስጊ ነው በማለት የጤና ባለስልጣናቱ ተናግረዋል። "በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመር በእርግጥ ሊያሳስበን ይገባል፤ ስለዚህ የመከላከያ መንገዶቻችንንም ልናጠናክር ይገባል" በማለት የጤና ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ዶክተር ቶው ሎይ ሲንጎት በጁባ ለሚገኙ ሪፖርተሮች ተናግረዋል። ሆኖም ከአዲስ አበባ ወደ ጁባ በየቀኑ የሚደረጉት በረራዎችም እንደሚቀጥሉ የተናገሩት ቃለ አቀባይ ሁሉም አገራት ለዜጎቹ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት እንደሚደረገው ከፍተኛ ጥንቃቄን ተግባራዊ እናደርጋለን ብለዋል። "ከአዲስ አበባ የሚደረጉ የየቀኑ በረራዎች የሚቀጥሉ ይሆናል። አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ካልሆነ አይቆምም" ብለዋል ዶክተር ቶው ሎይ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 59 ሺህ 648 ደርሷል፤ ከነዚህም ውስጥ 21 ሺህ 789 ያገገሙ ሲሆን 933 ህይወታቸው እንዳለፈ በትናንትናው ዕለት የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጋራ መግለጫ አስፍሯል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54068173 |
2health
| ከአምስት ወራት በኋላ የሕክምና መገልገያዎች ዛሬ ትግራይ መድረሳቸውን ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል አስታወቀ | በጦርነት ክፉኛ ለተጎዳችው ትግራይ ከአምስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው ዕለት ጥር 18/2014 ዓ.ም ህይወት አድን የህክምና መገልገያዎችን ማድረሱን ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ገለጸ። ከ15 ወራት በላይ በዘለቀው ጦርነት መድኃኒትና ምግብን ጨምሮ በመሰረታዊ ቁሳቁሶች እጥረት እየተሰቃየችው ላለችውም ትግራይ ይህ ዜና የተስፋ ጭላንጭል ነው ተብሏል። በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የጤና አስተባባሪ አፖሎ ባራሳ "የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ ወደ ትግራይ ሆስፒታሎች መድረሱ ትልቅ እፎይታ ነው። ድጋፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ማስቀጠል የሚያስችል ነው" ብለዋል። በዛሬው ዕለት ጥር 18/2014 ዓ.ም አስፈላጊ መድኃኒቶችን የያዘ አውሮፕላን ወደ ትግራይ መዲና መቀለ እንደደረሱም ተገልጿል። በመጪዎቹ ቀናትም ተጨማሪ በረራዎች እንዲሁም እርዳታ የጫኑ መኪኖችንም እንደሚልክ ድርጅቱ አስታውቋል። ይህም ተፈጻሚ የሆነው መንግሥት በህወሓት ቁጥጥር ስር ለምትገኘው የትግራይ ክልል አስፈላጊ የሆኑ የምግብ እና የሕክምና አቅርቦቶችን በአየር ለማጓጓዝ ለማመቻቸት የገባውን ቃል ተከትሎ ነው። ሆኖም በትግራይ እና አፋር ክልሎች አዋሳኝ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እርዳታውን በጭነት መኪኖች ለማድረስ የበለጠ ሊያወሳስበው እንደሚችልም እየተገለጸ ነው። ድርጅቱ ቀደም ሲል በትግራይ ያለው የመድኃኒት እና ሌሎች የህይወት አድን ቁሳቁሶች እጥረት የህክምና ባለሙያዎች ጓንቶችን እንደገና አጥበው እንዲጠቀሙ አስገድዷቸዋልም ብሏል። የዓለም ጤና ድርጅት በትግራይ ክልል ካለፈው ዓመት ሐምሌ አጋማሽ የሕክምና ቁሳቁሶች ለማቅረብ በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ሊፈቀድለት እንዳልቻለ ገልጾ ነበር። ሆኖም በጦርነቱ ለተጎዱት አማራና አፋር ክልሎች የሕክምና ቁሳቁሶች ማድረስ መቻሉን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበኩሉ በቅርቡ በትግራይ አንዳንድ የጤና አገልግሎቶች በአስፈላጊ መድኃኒት እጥረት ሳቢያ ሥራ አቁመዋል ብሏል። በትግራይ ክልል የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች ህፃናትን ጨምሮ ህሙማን በከፍተኛ መድኃኒት እጥረት ምክንት እየሞቱ መሆናቸውን ከሰሞኑ ባወጡት መግለጫ እንዲሁ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት ከተጣለው እገዳ ጋር ተያይዞ መድኃኒት እና ሌሎች የህይወት አድን ቁሳቁሶች ወደ ሆስፒታሎች ባለመድረሳቸው እንደሆነ ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ለገሰ ቱሉ መንግሥት ምንም አይነት እገዳ በትግራይ ላይ እንዳልጣለና በአሁኑ ወቅት ለተፈጠረው ችግር ህወሓትን ተጠያቂ አድርገዋል። በክልሉ መዲና መቀለ በሚገኘው ትልቁ የጤና ተቋም የሚገኙ ዶክተሮች እንደተናገሩት በቀዶ ህክምና ወቅት የሚያስፈልጉ በደም ስር የሚሰጡ እና የሰመመን መስጫ መድኃኒቶች ባለመኖራቸው ቀዶ ህክምና ማድረግ አለመቻላቸውን ነው። የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ሠራተኞች ባወጡት መግለጫ በተደጋጋሚ የሚከሰተው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እና ያልተሟላ የኦክስጂን አቅርቦት ለታካሚዎች ሞት ምክንያት ነው ብለዋል። ጓንቶች፣ በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉ አንቲባዮቲክ መድኃኒቶች፣ የህመም ማስታገሻዎች፣ በምጥ ላይ ላሉ ሴቶች ወሳኝ መድኃኒቶች እንዲሁም ለተለያዩ የአዕምሮ ህመም የሚውሉ መድኃኒቶችና መሰረታዊ የላብራቶሪ ምርመራዎች በሌሉበት ሁኔታ በሆስፒታሉ ውስጥ እንዲሰሩ መገደዳቸውን ጠቅሰዋል። የህክምና ባለሙያዎቹ የመገልገያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶች እንደሚጠቀሙና ያለውም ብቸኛ አማራጭ እሱ በመሆኑ አሁንም አስቸኳይ እንክብካቤ ለሚያስፈልጋቸው ህሙማንም በቻሉት መጠን እየተንከባከቡ እንደሆነ አስፍረዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት እና የህወሓት ባለሥልጣናት የህክምና ቁሳቁሶችን ጨምሮ የእርዳታ አቅርቦትን በማደናቀፍ እርስ በእርሳቸው ሲወቃቀሱ ይሰማል። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በትግራይ ክልል መሰረታዊ የሚባሉ አገልግሎቶች መብራት፣ ውሃ፣ ስልክ፣ ትራንስፖርትና የባንክ አገልግሎቶች አሁንም እንደተቋረጡ ናቸው። ባለፈው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ ትግራይ ውስጥ ተከስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሺዎችን በመቅጠፍና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀል መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ አድርሷል። ከአስራ አራት ወራት በላይ ያስቆጠረው ይህ ጦርነት እንዲቋጭ አሜሪካን ጨምሮ የአፍሪካ ሕብረት እንዲሁም የሕብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ እና ሌሎች አጋሮች ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥታቸው ከትግራይ ኃይሎች ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን መናገራቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ የዜና ወኪል (ኤፒ) ዘግቧል። | ከአምስት ወራት በኋላ የሕክምና መገልገያዎች ዛሬ ትግራይ መድረሳቸውን ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል አስታወቀ በጦርነት ክፉኛ ለተጎዳችው ትግራይ ከአምስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው ዕለት ጥር 18/2014 ዓ.ም ህይወት አድን የህክምና መገልገያዎችን ማድረሱን ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ገለጸ። ከ15 ወራት በላይ በዘለቀው ጦርነት መድኃኒትና ምግብን ጨምሮ በመሰረታዊ ቁሳቁሶች እጥረት እየተሰቃየችው ላለችውም ትግራይ ይህ ዜና የተስፋ ጭላንጭል ነው ተብሏል። በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የጤና አስተባባሪ አፖሎ ባራሳ "የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ ወደ ትግራይ ሆስፒታሎች መድረሱ ትልቅ እፎይታ ነው። ድጋፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ማስቀጠል የሚያስችል ነው" ብለዋል። በዛሬው ዕለት ጥር 18/2014 ዓ.ም አስፈላጊ መድኃኒቶችን የያዘ አውሮፕላን ወደ ትግራይ መዲና መቀለ እንደደረሱም ተገልጿል። በመጪዎቹ ቀናትም ተጨማሪ በረራዎች እንዲሁም እርዳታ የጫኑ መኪኖችንም እንደሚልክ ድርጅቱ አስታውቋል። ይህም ተፈጻሚ የሆነው መንግሥት በህወሓት ቁጥጥር ስር ለምትገኘው የትግራይ ክልል አስፈላጊ የሆኑ የምግብ እና የሕክምና አቅርቦቶችን በአየር ለማጓጓዝ ለማመቻቸት የገባውን ቃል ተከትሎ ነው። ሆኖም በትግራይ እና አፋር ክልሎች አዋሳኝ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እርዳታውን በጭነት መኪኖች ለማድረስ የበለጠ ሊያወሳስበው እንደሚችልም እየተገለጸ ነው። ድርጅቱ ቀደም ሲል በትግራይ ያለው የመድኃኒት እና ሌሎች የህይወት አድን ቁሳቁሶች እጥረት የህክምና ባለሙያዎች ጓንቶችን እንደገና አጥበው እንዲጠቀሙ አስገድዷቸዋልም ብሏል። የዓለም ጤና ድርጅት በትግራይ ክልል ካለፈው ዓመት ሐምሌ አጋማሽ የሕክምና ቁሳቁሶች ለማቅረብ በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ሊፈቀድለት እንዳልቻለ ገልጾ ነበር። ሆኖም በጦርነቱ ለተጎዱት አማራና አፋር ክልሎች የሕክምና ቁሳቁሶች ማድረስ መቻሉን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበኩሉ በቅርቡ በትግራይ አንዳንድ የጤና አገልግሎቶች በአስፈላጊ መድኃኒት እጥረት ሳቢያ ሥራ አቁመዋል ብሏል። በትግራይ ክልል የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች ህፃናትን ጨምሮ ህሙማን በከፍተኛ መድኃኒት እጥረት ምክንት እየሞቱ መሆናቸውን ከሰሞኑ ባወጡት መግለጫ እንዲሁ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት ከተጣለው እገዳ ጋር ተያይዞ መድኃኒት እና ሌሎች የህይወት አድን ቁሳቁሶች ወደ ሆስፒታሎች ባለመድረሳቸው እንደሆነ ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ለገሰ ቱሉ መንግሥት ምንም አይነት እገዳ በትግራይ ላይ እንዳልጣለና በአሁኑ ወቅት ለተፈጠረው ችግር ህወሓትን ተጠያቂ አድርገዋል። በክልሉ መዲና መቀለ በሚገኘው ትልቁ የጤና ተቋም የሚገኙ ዶክተሮች እንደተናገሩት በቀዶ ህክምና ወቅት የሚያስፈልጉ በደም ስር የሚሰጡ እና የሰመመን መስጫ መድኃኒቶች ባለመኖራቸው ቀዶ ህክምና ማድረግ አለመቻላቸውን ነው። የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ሠራተኞች ባወጡት መግለጫ በተደጋጋሚ የሚከሰተው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እና ያልተሟላ የኦክስጂን አቅርቦት ለታካሚዎች ሞት ምክንያት ነው ብለዋል። ጓንቶች፣ በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉ አንቲባዮቲክ መድኃኒቶች፣ የህመም ማስታገሻዎች፣ በምጥ ላይ ላሉ ሴቶች ወሳኝ መድኃኒቶች እንዲሁም ለተለያዩ የአዕምሮ ህመም የሚውሉ መድኃኒቶችና መሰረታዊ የላብራቶሪ ምርመራዎች በሌሉበት ሁኔታ በሆስፒታሉ ውስጥ እንዲሰሩ መገደዳቸውን ጠቅሰዋል። የህክምና ባለሙያዎቹ የመገልገያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶች እንደሚጠቀሙና ያለውም ብቸኛ አማራጭ እሱ በመሆኑ አሁንም አስቸኳይ እንክብካቤ ለሚያስፈልጋቸው ህሙማንም በቻሉት መጠን እየተንከባከቡ እንደሆነ አስፍረዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት እና የህወሓት ባለሥልጣናት የህክምና ቁሳቁሶችን ጨምሮ የእርዳታ አቅርቦትን በማደናቀፍ እርስ በእርሳቸው ሲወቃቀሱ ይሰማል። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በትግራይ ክልል መሰረታዊ የሚባሉ አገልግሎቶች መብራት፣ ውሃ፣ ስልክ፣ ትራንስፖርትና የባንክ አገልግሎቶች አሁንም እንደተቋረጡ ናቸው። ባለፈው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ ትግራይ ውስጥ ተከስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሺዎችን በመቅጠፍና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀል መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ አድርሷል። ከአስራ አራት ወራት በላይ ያስቆጠረው ይህ ጦርነት እንዲቋጭ አሜሪካን ጨምሮ የአፍሪካ ሕብረት እንዲሁም የሕብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ እና ሌሎች አጋሮች ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥታቸው ከትግራይ ኃይሎች ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን መናገራቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ የዜና ወኪል (ኤፒ) ዘግቧል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60144165 |
3politics
| ፖለቲከኞች በአዲሱ ዓመት ሰላም እንዲያሰፍኑ 24 የሲቪል ማኅበራት ጠየቁ | በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እየተካሄዱ ባሉ ግጭቶች ምክንያት እየደረሰ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ አሳስቦናል ያሉ 24 አገር በቀል የሲቪል ማኅበራት በግጭቶቹ ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው አካላት በአዲሱ ዓመት ሰላም እንዲያወርዱ ጠየቁ። አስር ነጥቦች ባለው በዚሁ ጥሪያቸው፤ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ቀውሶቹ በውይይት እንዲፈቱ የተደረጉ ጥረቶች እስካሁን ድረስ መፍትሔ አለማምጣታቸውን ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ ሚዲያ ሴቶች ማኅበር፣ ኢንተር አፍሪካ ግሩፕ፣ ሴታዊት ንቅናቄ፣ ሴንተር ፎር ጀስቲስ፣ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር፣ ኢኒሺዬቲቭ አፍሪካ፣ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት እና የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል ከተቋማቱ ውስጥ ይገኙበታል። "ጦርነት እና ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ደኅንነት ጉዳይ ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ በተለይም ሕፃናት፣ ሴቶች እና አረጋውያን ለከፍተኛ አደጋ መጋለጣቸው አሳስቦናል" ሲሉ ተቋማቱ ገልጸዋል። እንዲሁም ለጦርነት መንስኤ የሆኑ የተለያዩ የፖለቲካ ችግሮች በጦርነት በዘላቂነት ሊፈቱ አይችሉም የሚል እምነት አለን ያሉት የሲቪል ተቋማቱ፤ በጦርነት ለመፍታት የሚደረግ ጥረት ዋናው ዋጋ ከፋይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ብለዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩትን ከቀያቸው አፈናቅሎ በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብን ለረሃብ አደጋ አጋልጧል። ይህ ጦርነት በተለይም በወጣቱ የማኅበረሰብ ክፍል ላይ እያስከተለ ያለው እልቂት፣ የምጣኔ ሀብት ውድመት እንዲሁም የከፋ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በዓለም አቀፍ ሕጎች የተወገዘ ብሎም በአገሪቷ መጻኢ እድል ላይ መጠነ ሰፊ ጫና የሚያስከትል ሆኖ እንዳገኙት ማኅበራቱ ገልጸዋል። የዚህ ጦርነት ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራዎች ከአገር አቀፍ ጉዳት አልፎ ወደ ቀጠናዊ ቀውስ ሊያመራ የሚችልበት እድል በመኖሩ እንዲሁም ጦርነቱ በመሠረተ ልማቶች ውድመት በማስከተል ኢትዮጵያን ወደ ከፋ ድህነት የሚጎትት ሆኖ በማግኘታቸው የሰላም ጥሪ እንዳደረጉ አስታውቀዋል። ከምጣኔ ሀብታዊ ብሎም ከፖለቲካዊ ኪሳራዎች ባሻገር ይህ ጦርነት በማኅበራዊ ግንኙነት ላይ እያስከተለ የመጣው ጫና አሳሰቢ ነው ያሉት ተቋማቱ፤ በምዕራብና በደቡብ ኦሮሚያ፣ በሶማሊ፣ በአፋር፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በደቡብ ክልሎች የሚካሄዱ ግጭቶችም እንዳሳሰቧቸው ተናግረዋል። "ሕፃናት ልጆቻችን፣ በዕድሜ የገፉ ወገኖቻችን እና ሴቶቻችን በተለየ ሁኔታ ለመከራ ተጋላጭ እየሆኑ፣ ጾታዊ ጥቃትንና ግድያን ጨምሮ የተለያዩ የሰብዓዊ ጥሰቶች ሰለባ በመሆን ላይ ናቸው" ሲል ጥሪው ያስነብባል። "ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት የምንጠቀምባቸው የሽምግልና እና የዕርቅ ባህላዊና ማኅበራዊ አቅሞቻችንን ለመጠቀም እያደረግን ያለነው ሁለገብ ጥረት እስካሁን ሰላምን ሊያረጋጋጥልን አልቻለም። በመሆኑም ሕዝባችንን ለዘመናት ደግፈው ያቆዩ ማኅበራዊ እሴቶቻችን ሳይቀሩ አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ" ሲሉም ማኅበራቱ ስጋታቸውን ገልጸዋል። በእነዚህ ግጭቶች ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ የፖለቲካ ብሎም የጦር ኃይሎች በመጪው ዓመት ቆም ብሎ በማሰብ የሰላም አማራጭን እንዲመርጡ ጠይቀዋል። | ፖለቲከኞች በአዲሱ ዓመት ሰላም እንዲያሰፍኑ 24 የሲቪል ማኅበራት ጠየቁ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እየተካሄዱ ባሉ ግጭቶች ምክንያት እየደረሰ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ አሳስቦናል ያሉ 24 አገር በቀል የሲቪል ማኅበራት በግጭቶቹ ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው አካላት በአዲሱ ዓመት ሰላም እንዲያወርዱ ጠየቁ። አስር ነጥቦች ባለው በዚሁ ጥሪያቸው፤ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ቀውሶቹ በውይይት እንዲፈቱ የተደረጉ ጥረቶች እስካሁን ድረስ መፍትሔ አለማምጣታቸውን ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ ሚዲያ ሴቶች ማኅበር፣ ኢንተር አፍሪካ ግሩፕ፣ ሴታዊት ንቅናቄ፣ ሴንተር ፎር ጀስቲስ፣ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር፣ ኢኒሺዬቲቭ አፍሪካ፣ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት እና የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል ከተቋማቱ ውስጥ ይገኙበታል። "ጦርነት እና ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ደኅንነት ጉዳይ ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ በተለይም ሕፃናት፣ ሴቶች እና አረጋውያን ለከፍተኛ አደጋ መጋለጣቸው አሳስቦናል" ሲሉ ተቋማቱ ገልጸዋል። እንዲሁም ለጦርነት መንስኤ የሆኑ የተለያዩ የፖለቲካ ችግሮች በጦርነት በዘላቂነት ሊፈቱ አይችሉም የሚል እምነት አለን ያሉት የሲቪል ተቋማቱ፤ በጦርነት ለመፍታት የሚደረግ ጥረት ዋናው ዋጋ ከፋይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ብለዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩትን ከቀያቸው አፈናቅሎ በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብን ለረሃብ አደጋ አጋልጧል። ይህ ጦርነት በተለይም በወጣቱ የማኅበረሰብ ክፍል ላይ እያስከተለ ያለው እልቂት፣ የምጣኔ ሀብት ውድመት እንዲሁም የከፋ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በዓለም አቀፍ ሕጎች የተወገዘ ብሎም በአገሪቷ መጻኢ እድል ላይ መጠነ ሰፊ ጫና የሚያስከትል ሆኖ እንዳገኙት ማኅበራቱ ገልጸዋል። የዚህ ጦርነት ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራዎች ከአገር አቀፍ ጉዳት አልፎ ወደ ቀጠናዊ ቀውስ ሊያመራ የሚችልበት እድል በመኖሩ እንዲሁም ጦርነቱ በመሠረተ ልማቶች ውድመት በማስከተል ኢትዮጵያን ወደ ከፋ ድህነት የሚጎትት ሆኖ በማግኘታቸው የሰላም ጥሪ እንዳደረጉ አስታውቀዋል። ከምጣኔ ሀብታዊ ብሎም ከፖለቲካዊ ኪሳራዎች ባሻገር ይህ ጦርነት በማኅበራዊ ግንኙነት ላይ እያስከተለ የመጣው ጫና አሳሰቢ ነው ያሉት ተቋማቱ፤ በምዕራብና በደቡብ ኦሮሚያ፣ በሶማሊ፣ በአፋር፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በደቡብ ክልሎች የሚካሄዱ ግጭቶችም እንዳሳሰቧቸው ተናግረዋል። "ሕፃናት ልጆቻችን፣ በዕድሜ የገፉ ወገኖቻችን እና ሴቶቻችን በተለየ ሁኔታ ለመከራ ተጋላጭ እየሆኑ፣ ጾታዊ ጥቃትንና ግድያን ጨምሮ የተለያዩ የሰብዓዊ ጥሰቶች ሰለባ በመሆን ላይ ናቸው" ሲል ጥሪው ያስነብባል። "ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት የምንጠቀምባቸው የሽምግልና እና የዕርቅ ባህላዊና ማኅበራዊ አቅሞቻችንን ለመጠቀም እያደረግን ያለነው ሁለገብ ጥረት እስካሁን ሰላምን ሊያረጋጋጥልን አልቻለም። በመሆኑም ሕዝባችንን ለዘመናት ደግፈው ያቆዩ ማኅበራዊ እሴቶቻችን ሳይቀሩ አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ" ሲሉም ማኅበራቱ ስጋታቸውን ገልጸዋል። በእነዚህ ግጭቶች ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ የፖለቲካ ብሎም የጦር ኃይሎች በመጪው ዓመት ቆም ብሎ በማሰብ የሰላም አማራጭን እንዲመርጡ ጠይቀዋል። | https://www.bbc.com/amharic/58511480 |
5sports
| ሩሲያ ከሁሉም ስፖርታዊ ውድድሮች ልትታገድ ትችላለች | የዓለማ አቀፉ የጸረ አበረታች መድሃኒቶች ኤጀንሲ (ዋዳ) ከሩሲያ ላቦራቶሪዎች የተገኙት መረጃዎች ወጥ ስላልሆኑ ሃገሪቱ ከማንኛውም ስፖርታዊ ውድድሮች ልትታገድ ትችለች ብሏል። ሩሲያ ጉዳዩን በአግባቡ ለማስረዳት ሶስት ሳምንታት የተሰጣት ሲሆን አጥጋቢ ምላሽ የማትሰጥ ከሆነ ግን ከኦሎምፒክና የዓለም ሻምፒየንሺፕ ውድድሮች መታገዷ እንደማይቀር ኤጀንሲው አስታውቋል። በተጨማሪም ማንኛውም አይነት ውድድሮች ከማዘጋጀትም ልትታደግ እንደምትችል አስጠንቅቋል። • አባታቸውን የገደሉት እህትማማቾች እንዲለቀቁ ፊርማ እየተሰበሰበ ነው • ሩሲያዊው ቄስ በባለቤታቸው "ሀጥያት" ለስደት ተዳረጉ ''ከላቦራቶሪ ውጤቶቹ መካከል ብዙዎቹ መጥፋታቸውን አረጋግጠናል'' ሲሉ ጆናታን ታይለር የተባሉ የዓለማ አቀፉ የጸረ አበረታች መድሃኒቶች ኤጀንሲ ከፍተኛ ሃላፊ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ሩሲያ ተመሳሳይ ክስ ቀርቦባት ለሶስት ዓመታት የተጣለባትን እገዳ ከጨረሰች በኋላ ነበር ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ የላቦራቶሪ ውጤቶቹን ለዋዳ ያስረከበችው። የዋዳ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሰኞ ዕለት እንዳስታወቁት መረጃዎቹ ወጥነት ስለሚጎድላቸውን ሆን ተብሎ የጠፉም ስላሉ ይፋዊ የሆነ ምርመራ ተጀምሯል። ሩሲያ ጥፋተኛ ሆና ከተገኘች ከሁሉም ስፖርታዊ ውድድሮች ልትታገድ የምትችል ሲሆን ቅሬታ ካላት ደግሞ ለዓለማ አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማለት እንደምትችል ኮሚቴው ገልጿል። የዓለማ አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በዋዳ ቀርቦለት የነበረውን ሩሲያን ከ2016ቱ የሪዮ ኦሎምፒክ የማገድ ሃሳብ ወደጎን ብሎት የነበረ ሲሆን በ2018 በፒዮንግያንግ በተካሄደው የክረምት ኦሎምፒክ ግን ሩሲያ እንዳትሳተፍ ማድረጉ ይታወሳል። የዓለማ አቀፉ አትሌቲክስ ሻምፒየንሺፕ ከአራት ቀናት በኋላ በኳታር ዶሃ የሚጀመር ሲሆን የሩሲያ ተሳታፊዎች ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል አልታወቀም። ''ወጣም ወረደ ሩሲያ ለመደበቅ የሞከረቸው መረጃ ካለ በቀጣዩ ዓመት በቶክዮ ከሚዘጋጀው የቶክዮ ኦሎምፒክና ከ2022 ዓለም ዋንጫ መታገዷ አይቀርም'' ብለዋል ጆናታን ታይለር። • የ56 ዓመቷ ሩሲያዊት በአሳሞች ተበላች የሩሲያው ስፖርት ሚኒስትር ፓቬል ኮሎብኮቭ ''ምን አይነት የመረጃ መለያየት እንደተፈጠረ ሊነግሩን ይገባል፤ ልዩነቶቹ ከምን ጋር የተያያዙ መሆናቸውም ግልጽ መደረግ አለበት'' ማለታቸውን 'ታስ' የተባለው የዜና ወኪል ዘግቧል። ''የዲጂታል ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ከሁለቱም በኩል በትብብር እየሰሩ ነው። በእኛ በኩል ማንኛውም አይነት ትብብርና እርዳታ ለማድረግ ዝግጁ ነን'' ብለዋል። ሩሲያ ባለፈው ዓመት የላቦራቶሪ ውጤቶቹን ለዋዳ ስታስረክብ የተቀመጠላትን ቀነ ገደብ አሳልፋ ነበር። ይህ ደግሞ ብዙ ጥርጣሬዎች እንዲፈጠሩ አድርጎ ነበር። | ሩሲያ ከሁሉም ስፖርታዊ ውድድሮች ልትታገድ ትችላለች የዓለማ አቀፉ የጸረ አበረታች መድሃኒቶች ኤጀንሲ (ዋዳ) ከሩሲያ ላቦራቶሪዎች የተገኙት መረጃዎች ወጥ ስላልሆኑ ሃገሪቱ ከማንኛውም ስፖርታዊ ውድድሮች ልትታገድ ትችለች ብሏል። ሩሲያ ጉዳዩን በአግባቡ ለማስረዳት ሶስት ሳምንታት የተሰጣት ሲሆን አጥጋቢ ምላሽ የማትሰጥ ከሆነ ግን ከኦሎምፒክና የዓለም ሻምፒየንሺፕ ውድድሮች መታገዷ እንደማይቀር ኤጀንሲው አስታውቋል። በተጨማሪም ማንኛውም አይነት ውድድሮች ከማዘጋጀትም ልትታደግ እንደምትችል አስጠንቅቋል። • አባታቸውን የገደሉት እህትማማቾች እንዲለቀቁ ፊርማ እየተሰበሰበ ነው • ሩሲያዊው ቄስ በባለቤታቸው "ሀጥያት" ለስደት ተዳረጉ ''ከላቦራቶሪ ውጤቶቹ መካከል ብዙዎቹ መጥፋታቸውን አረጋግጠናል'' ሲሉ ጆናታን ታይለር የተባሉ የዓለማ አቀፉ የጸረ አበረታች መድሃኒቶች ኤጀንሲ ከፍተኛ ሃላፊ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ሩሲያ ተመሳሳይ ክስ ቀርቦባት ለሶስት ዓመታት የተጣለባትን እገዳ ከጨረሰች በኋላ ነበር ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ የላቦራቶሪ ውጤቶቹን ለዋዳ ያስረከበችው። የዋዳ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሰኞ ዕለት እንዳስታወቁት መረጃዎቹ ወጥነት ስለሚጎድላቸውን ሆን ተብሎ የጠፉም ስላሉ ይፋዊ የሆነ ምርመራ ተጀምሯል። ሩሲያ ጥፋተኛ ሆና ከተገኘች ከሁሉም ስፖርታዊ ውድድሮች ልትታገድ የምትችል ሲሆን ቅሬታ ካላት ደግሞ ለዓለማ አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማለት እንደምትችል ኮሚቴው ገልጿል። የዓለማ አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በዋዳ ቀርቦለት የነበረውን ሩሲያን ከ2016ቱ የሪዮ ኦሎምፒክ የማገድ ሃሳብ ወደጎን ብሎት የነበረ ሲሆን በ2018 በፒዮንግያንግ በተካሄደው የክረምት ኦሎምፒክ ግን ሩሲያ እንዳትሳተፍ ማድረጉ ይታወሳል። የዓለማ አቀፉ አትሌቲክስ ሻምፒየንሺፕ ከአራት ቀናት በኋላ በኳታር ዶሃ የሚጀመር ሲሆን የሩሲያ ተሳታፊዎች ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል አልታወቀም። ''ወጣም ወረደ ሩሲያ ለመደበቅ የሞከረቸው መረጃ ካለ በቀጣዩ ዓመት በቶክዮ ከሚዘጋጀው የቶክዮ ኦሎምፒክና ከ2022 ዓለም ዋንጫ መታገዷ አይቀርም'' ብለዋል ጆናታን ታይለር። • የ56 ዓመቷ ሩሲያዊት በአሳሞች ተበላች የሩሲያው ስፖርት ሚኒስትር ፓቬል ኮሎብኮቭ ''ምን አይነት የመረጃ መለያየት እንደተፈጠረ ሊነግሩን ይገባል፤ ልዩነቶቹ ከምን ጋር የተያያዙ መሆናቸውም ግልጽ መደረግ አለበት'' ማለታቸውን 'ታስ' የተባለው የዜና ወኪል ዘግቧል። ''የዲጂታል ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ከሁለቱም በኩል በትብብር እየሰሩ ነው። በእኛ በኩል ማንኛውም አይነት ትብብርና እርዳታ ለማድረግ ዝግጁ ነን'' ብለዋል። ሩሲያ ባለፈው ዓመት የላቦራቶሪ ውጤቶቹን ለዋዳ ስታስረክብ የተቀመጠላትን ቀነ ገደብ አሳልፋ ነበር። ይህ ደግሞ ብዙ ጥርጣሬዎች እንዲፈጠሩ አድርጎ ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/news-49806815 |
3politics
| የዩክሬን ጦርነት ክራይሚያ ነጻ ወጥታ መጠናቀቅ አለበት ሲሉ ዜለንስኪ ተናገሩ | የዩክሬን ጦርነት በክራይሚያ የተጀመረ በመሆኑ ጦርነቱ ሲጠናቀቅም ክራይሚያን ነፃን በማውጣት መሆን አለበት ሲሉ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ ይህንን የተናገሩት የሩሲያ አየር ኃይል መሰረት በሆነ ቦታ ላይ ፍንዳታዎች ከተከሰቱ እና የአንድ ሰው ሕይወት ካለፈ ከሰዓታት በኋላ ነበር። ዜለንስኪ በንግግራቸው ስለ ፍንዳታዎቹ ምንም ባይሉም የምሽት መግለጫቸውን ክራይሚያ ላይ ያተኮረ ነበር። “ክሪሚያ የዩክሬን ስለሆነ እኛም በፍጹም አሳልፈን አንሰጥም’’ ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። ሩሲያ ፍንዳታውን አቅልላ የተመለከተች ሲሆን አንድ ከፍተኛ የዩክሬን አማካሪ ዩክሬን ለፍንዳታው ኃላፊነቱን እንደማትወስድ ተናግረዋል። ክሬይሚያ የዩክሬን አካል የነበረች ሲሆን ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ሕገ-ወጥ ባለው ሕዝበ ውሳኔ ከ2014 ጀምሮ ሩሲያ አካል ነች በማለት ጠቅልላ ይዛለች። ብዙ ዩክሬናውያን ይህንን የክራይሚያን ጉዳይ ሩሲያ ከአገራቸው ጋር ለጀመረችው ጦርነት የመጀመሪያ እርምጃ አድርገው ይመለከቱታል። ትላንት ማክሰኞ ከክራሚያ በስተ ምዕራብ በሚገኘው በኖቮፌዶሪቭካ አቅራቢያ በሚገኘው ሳኪ በተሰኘው የሩሲያ የጦር ሰፈር በሩሲያ ቱሪስቶች ተወዳጅ በሆኑ የባህር ዳርቻዎች አቅራቢያ በርካታ ፍንዳታዎች ተከስተዋል። በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የተዘዋወሩ ምስሎች በባሕር ዳርቻው ላይ የሚዝናኑ ሰዎች ፍንዳታዎቹን ተከትሎ ሲሯሯጡ አሳይተዋል። የዓይን እማኞች ቢያንስ 12 ፍንዳታዎችን እንደሰሙ ተናግረዋል። በክራይሚያ የሚገኝ የሩሲያ የጤና ባለስጣን አንድ ሲቪል ሰው ሲገደል ሌሎች ስምንት ሰዎች ቆስለዋል ብሏል። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ፍንዳታዎቹ በአንድ የጦር መሳሪያዎች ማቆያ ውስጥ የተቀመጡ ጥይቶች ፈንድተው የተከሰተ ነው ሲል ቢናገርም እስካሁን ድረስ የተረጋገጠ ነገር የለም። የዩክሬን ፕሬዝዳንት ረዳት የሆኑት ማይካሂሎ ፖዶሊያክ ዩክሬን ከፍንዳታው ጀርባ የለችም ሲሉ ያጣጣሉ ሲሆን ለዶዝድ ኦንላይን የቴሌቪዥን ጣቢያ "በፍጹም፣ እኛ ከዚህ ጋር ምን አገናኘን?’’ ሲሉም ተደምጠዋል። ፕሬዘዳንት ዜለንስኪም ማክሰኞ ዕለት ባደረጉት ንግግር ፍንዳታውን በቀጥታ ባይጠቅሱም ስለ ክራይሚያ ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል። “የሩሲያ ጦርነት በዩክሬን ላይ የተጀመረው ክራይሚያን በመውረር መሆኑን አንዘነጋም። ይህ የሩሲያ ጦርነት... ክሪሚያ ጋር ተጀምሮ በክራይሚያን ነፃ በማውጣት ማብቃት አለበት" ብለዋል። | የዩክሬን ጦርነት ክራይሚያ ነጻ ወጥታ መጠናቀቅ አለበት ሲሉ ዜለንስኪ ተናገሩ የዩክሬን ጦርነት በክራይሚያ የተጀመረ በመሆኑ ጦርነቱ ሲጠናቀቅም ክራይሚያን ነፃን በማውጣት መሆን አለበት ሲሉ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ ይህንን የተናገሩት የሩሲያ አየር ኃይል መሰረት በሆነ ቦታ ላይ ፍንዳታዎች ከተከሰቱ እና የአንድ ሰው ሕይወት ካለፈ ከሰዓታት በኋላ ነበር። ዜለንስኪ በንግግራቸው ስለ ፍንዳታዎቹ ምንም ባይሉም የምሽት መግለጫቸውን ክራይሚያ ላይ ያተኮረ ነበር። “ክሪሚያ የዩክሬን ስለሆነ እኛም በፍጹም አሳልፈን አንሰጥም’’ ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። ሩሲያ ፍንዳታውን አቅልላ የተመለከተች ሲሆን አንድ ከፍተኛ የዩክሬን አማካሪ ዩክሬን ለፍንዳታው ኃላፊነቱን እንደማትወስድ ተናግረዋል። ክሬይሚያ የዩክሬን አካል የነበረች ሲሆን ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ሕገ-ወጥ ባለው ሕዝበ ውሳኔ ከ2014 ጀምሮ ሩሲያ አካል ነች በማለት ጠቅልላ ይዛለች። ብዙ ዩክሬናውያን ይህንን የክራይሚያን ጉዳይ ሩሲያ ከአገራቸው ጋር ለጀመረችው ጦርነት የመጀመሪያ እርምጃ አድርገው ይመለከቱታል። ትላንት ማክሰኞ ከክራሚያ በስተ ምዕራብ በሚገኘው በኖቮፌዶሪቭካ አቅራቢያ በሚገኘው ሳኪ በተሰኘው የሩሲያ የጦር ሰፈር በሩሲያ ቱሪስቶች ተወዳጅ በሆኑ የባህር ዳርቻዎች አቅራቢያ በርካታ ፍንዳታዎች ተከስተዋል። በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የተዘዋወሩ ምስሎች በባሕር ዳርቻው ላይ የሚዝናኑ ሰዎች ፍንዳታዎቹን ተከትሎ ሲሯሯጡ አሳይተዋል። የዓይን እማኞች ቢያንስ 12 ፍንዳታዎችን እንደሰሙ ተናግረዋል። በክራይሚያ የሚገኝ የሩሲያ የጤና ባለስጣን አንድ ሲቪል ሰው ሲገደል ሌሎች ስምንት ሰዎች ቆስለዋል ብሏል። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ፍንዳታዎቹ በአንድ የጦር መሳሪያዎች ማቆያ ውስጥ የተቀመጡ ጥይቶች ፈንድተው የተከሰተ ነው ሲል ቢናገርም እስካሁን ድረስ የተረጋገጠ ነገር የለም። የዩክሬን ፕሬዝዳንት ረዳት የሆኑት ማይካሂሎ ፖዶሊያክ ዩክሬን ከፍንዳታው ጀርባ የለችም ሲሉ ያጣጣሉ ሲሆን ለዶዝድ ኦንላይን የቴሌቪዥን ጣቢያ "በፍጹም፣ እኛ ከዚህ ጋር ምን አገናኘን?’’ ሲሉም ተደምጠዋል። ፕሬዘዳንት ዜለንስኪም ማክሰኞ ዕለት ባደረጉት ንግግር ፍንዳታውን በቀጥታ ባይጠቅሱም ስለ ክራይሚያ ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል። “የሩሲያ ጦርነት በዩክሬን ላይ የተጀመረው ክራይሚያን በመውረር መሆኑን አንዘነጋም። ይህ የሩሲያ ጦርነት... ክሪሚያ ጋር ተጀምሮ በክራይሚያን ነፃ በማውጣት ማብቃት አለበት" ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c0jw41zwn25o |
0business
| የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት አውሮፕላናቸውን ሸጠው ሕገ-ወጥ ስደትን ሊቀንሱ አስበዋል | የሜክሲኮው ፕሬዝዳንት አንድሬ ማኑዌል ሎፔዝ ኦብራዶር አውሮፕላናቸውን ሸጠው የሚያገኙትን ትርፍ ሕገ-ወጥ ስደትን ሊከላከሉበት እንደሆነ አሳውቀዋል። ፕሬዝዳንቱ ሃሳቡን ያመጡት ሃገራቸው ሜክሲኮ ከአሜሪካ ጋር በደረሱት ስምምነት መሠረት ሲሆን ስምምነቱ ሜክሲኮ ከማዕከላዊ ወደ አሜሪካ የሚደረገውን ጉዞ መግታት የምትችል ከሆነ የዶናልድ ትራምፕ መንግሥት ሜክሲኮ ላይ የጫነውን ቀረጥ እንደሚቀንስ ያትታል። ፕሬዝዳንቱ በምረጡኝ ቅስቀሳቸው ወቅት የፕሬዝዳንቱን አውሮፕላን ሸጬ ደሃ ሜክሲኳዊያንን ሕዝብ እረዳለሁ ሲሉ ቃል ገብተው ነበር። • ከፍተኛ መጠን ያለው ዕፅ በአሜሪካና ሜክሲኮ ድንበር ተያዘ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር የተሰኘው የፕሬዝዳንቱ አውሮፕላን 150 ሚሊዮን ዶላር [ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ገደማ] ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል። ስማቸው የረዘመባቸው የሃገሪቱ ሰዎች 'አምሎ' ብለው የሚጠሯቸው ፕሬዝዳንት ሎፔዝ አውሮፕላኑን ሸጨ እኔ ከሕዝብ ጋር ተጋፍቼ እሄዳለሁ ሲሉ ነበር ቃል የገቡት። አውሮፕላኑ ላለፉት ጥቂት ወራት ካሊፎርኒያ የሚገኝ አንድ መጋዘን ውስጥ ለሻጮች ክፍት ሆኖ ቆይቷል። ሜክሲኮ የፕሬዝዳንቱን አውሮፕላን አክሎ ሌሎች 60 የመንግሥት አውሮፕላኖችንና 70 ሄሊኮፕተሮችን ለመሸጥ ቆርጣ ተነስታለች። • "አቶ ጌታቸው አሰፋን ሜክሲኮ አግኝቻቸው ነበር" ነጋ ዘርዑ ሜክሲኮ ሶስተኛዋ ሃያል የአሜሪካ የንግድ አጋር ስትሆን ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በነበራት እሰጥ-አገባ ምክንያት ከሜክሲኮ የሚመጡ ምርቶች ላይ ቀረጥ ተጭኖ ነበር። ሜክሲኮ አውሮፕላኗን ከመሸጥ አልፋ 6 ሺህ ገደማ ፖሊሶችን ወደ ጓቲማላ ልካ ሕገ-ወጥ ስድትን ለመግታት ቃል ገብታለች። የፕሬዝዳንቱ አውሮፕላን መሸጥ ለበርካታ ሜክሲኳውያን የተዋጠ አይመስልም፤ በሕዝብ ገንዘብ የተገዛ ንብረትን እንዴት ተደርጎ? እያሉም ይገኛሉ። • አሜሪካና ሜክሲኮን የሚለየው ግንብ መገንባት ተጀመረ | የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት አውሮፕላናቸውን ሸጠው ሕገ-ወጥ ስደትን ሊቀንሱ አስበዋል የሜክሲኮው ፕሬዝዳንት አንድሬ ማኑዌል ሎፔዝ ኦብራዶር አውሮፕላናቸውን ሸጠው የሚያገኙትን ትርፍ ሕገ-ወጥ ስደትን ሊከላከሉበት እንደሆነ አሳውቀዋል። ፕሬዝዳንቱ ሃሳቡን ያመጡት ሃገራቸው ሜክሲኮ ከአሜሪካ ጋር በደረሱት ስምምነት መሠረት ሲሆን ስምምነቱ ሜክሲኮ ከማዕከላዊ ወደ አሜሪካ የሚደረገውን ጉዞ መግታት የምትችል ከሆነ የዶናልድ ትራምፕ መንግሥት ሜክሲኮ ላይ የጫነውን ቀረጥ እንደሚቀንስ ያትታል። ፕሬዝዳንቱ በምረጡኝ ቅስቀሳቸው ወቅት የፕሬዝዳንቱን አውሮፕላን ሸጬ ደሃ ሜክሲኳዊያንን ሕዝብ እረዳለሁ ሲሉ ቃል ገብተው ነበር። • ከፍተኛ መጠን ያለው ዕፅ በአሜሪካና ሜክሲኮ ድንበር ተያዘ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር የተሰኘው የፕሬዝዳንቱ አውሮፕላን 150 ሚሊዮን ዶላር [ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ገደማ] ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል። ስማቸው የረዘመባቸው የሃገሪቱ ሰዎች 'አምሎ' ብለው የሚጠሯቸው ፕሬዝዳንት ሎፔዝ አውሮፕላኑን ሸጨ እኔ ከሕዝብ ጋር ተጋፍቼ እሄዳለሁ ሲሉ ነበር ቃል የገቡት። አውሮፕላኑ ላለፉት ጥቂት ወራት ካሊፎርኒያ የሚገኝ አንድ መጋዘን ውስጥ ለሻጮች ክፍት ሆኖ ቆይቷል። ሜክሲኮ የፕሬዝዳንቱን አውሮፕላን አክሎ ሌሎች 60 የመንግሥት አውሮፕላኖችንና 70 ሄሊኮፕተሮችን ለመሸጥ ቆርጣ ተነስታለች። • "አቶ ጌታቸው አሰፋን ሜክሲኮ አግኝቻቸው ነበር" ነጋ ዘርዑ ሜክሲኮ ሶስተኛዋ ሃያል የአሜሪካ የንግድ አጋር ስትሆን ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በነበራት እሰጥ-አገባ ምክንያት ከሜክሲኮ የሚመጡ ምርቶች ላይ ቀረጥ ተጭኖ ነበር። ሜክሲኮ አውሮፕላኗን ከመሸጥ አልፋ 6 ሺህ ገደማ ፖሊሶችን ወደ ጓቲማላ ልካ ሕገ-ወጥ ስድትን ለመግታት ቃል ገብታለች። የፕሬዝዳንቱ አውሮፕላን መሸጥ ለበርካታ ሜክሲኳውያን የተዋጠ አይመስልም፤ በሕዝብ ገንዘብ የተገዛ ንብረትን እንዴት ተደርጎ? እያሉም ይገኛሉ። • አሜሪካና ሜክሲኮን የሚለየው ግንብ መገንባት ተጀመረ | https://www.bbc.com/amharic/news-48619205 |
0business
| የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌና ላልይበላ በረራዎችን ሰረዘ | የኢትዮጵያ አየር መንገድ መቀሌና ላልይበላ ጨምሮ በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍሎች ዛሬ ሊያደርጋቸው የነበሩ በረራዎችን ባጋጠመው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት መሰረዙን አስታወቀ። አየር መንገዱ ጨምሮም በተመሳሳይ ወደ ጎንደር፣ አክሱምና ሽሬ ሊያደርጋቸው የነበሩ በረራዎችም ዛሬ ጠዋት በነበረው አመቺ ያልሆነ የአየር ሁኔታ ሳቢያ መስተጓጎሉን አመልክቷል። በዛሬው ዕለት የተሰረዙትን በረራዎች ያለው የአየር ሁኔታ መሻሻሉን በተመለከተ ከብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት የሚገኝን መረጃ መሰረት በማድረግ እንዲቀጥል የሚደረግ መሆኑን ገልጿል። ነገር ግን አሁን ከብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በረራዎችን ያስተጓጎለው የአየር ሁኔታ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ውስጥም ሊቀጥል እንደሚችል አመልክቷል። በተያያዘ ዜና ከአርብ ከሰዓት ጀምሮ ቅዳሜ ዕለትም የባህር ዳር ከተማ ሰማይ በአቧራ ጭጋግ ተሸፍኖ እንደነበር ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል። ይህንን ክስተት በተመለከተ የምዕራብ አማራ የሜቲዮሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል የትንተናና ትንበያ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ቡድን አስተባባሪ የሆኑት አቶ ጥላሁን ውቡ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት "ጠንካራ የአቧራ ጭጋግ ተከስቷል።" ይህ የአቧራ ጭጋግ የሚከሰተው በደረቅ አካባቢዎች የሚከሰትን አውሎ ነፋስ ተከትሎ ነው የሚሉት ባለሙያው፤ በባህር ዳር ላይ የታየው የአቧራ አውሎ ነፋስ ሱዳን ላይ በተከሰተ ዝቅተኛ የአየር ግፊት ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ። ይህ የአቧራ ጭጋግ የተከሰተው በባህር ዳር ከተማ ብቻ አለመሆኑን የሚናገሩት ባለሙያው ጎንደር ላይም መታየቱን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ክስተቱ ብዙ ጊዜ ለረዥም ሰዓት አይቆይም የሚሉት አቶ ጥላሁን ቶሎ ሊጠፋ እንደሚችል ያስረዳሉ። ነገር ግን በእንዲህ ዓይነት የአየር ሁኔታ አውሮፕላኖች ለመነሳትም ሆነ ለማረፍ እይታን ስለሚጋርድ ለበረራ አስቸጋሪ እንደሚሆን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ ግን በረራዎች ከተስተጓጎሉባቸው ከተሞች ውስጥ የአቧራ ጭጋጉ የተከሰተባት የባህር ዳር ከተማ የለችበትም። ባለሙያው ጨምረውም እንዲህ አይነት አቧራ ጭጋግ የመተንፈሻ አካል ችግር በተለይ አስም ላለባቸው ሰዎች አስቸጋሪ እንደሚሆን አስታውሰው፤ እንዲሁም ክስተቱ የማጅራት ገትር በሽታ መንስዔም ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ባህር ዳር የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ እንዳረጋገጠው የአቧራ ጭጋጉ ዛሬ በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ቢሆንም የተወሰኑ ምልክቶች ግን እንዳሉ አመልክቷል። | የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌና ላልይበላ በረራዎችን ሰረዘ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መቀሌና ላልይበላ ጨምሮ በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍሎች ዛሬ ሊያደርጋቸው የነበሩ በረራዎችን ባጋጠመው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት መሰረዙን አስታወቀ። አየር መንገዱ ጨምሮም በተመሳሳይ ወደ ጎንደር፣ አክሱምና ሽሬ ሊያደርጋቸው የነበሩ በረራዎችም ዛሬ ጠዋት በነበረው አመቺ ያልሆነ የአየር ሁኔታ ሳቢያ መስተጓጎሉን አመልክቷል። በዛሬው ዕለት የተሰረዙትን በረራዎች ያለው የአየር ሁኔታ መሻሻሉን በተመለከተ ከብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት የሚገኝን መረጃ መሰረት በማድረግ እንዲቀጥል የሚደረግ መሆኑን ገልጿል። ነገር ግን አሁን ከብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በረራዎችን ያስተጓጎለው የአየር ሁኔታ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ውስጥም ሊቀጥል እንደሚችል አመልክቷል። በተያያዘ ዜና ከአርብ ከሰዓት ጀምሮ ቅዳሜ ዕለትም የባህር ዳር ከተማ ሰማይ በአቧራ ጭጋግ ተሸፍኖ እንደነበር ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል። ይህንን ክስተት በተመለከተ የምዕራብ አማራ የሜቲዮሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል የትንተናና ትንበያ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ቡድን አስተባባሪ የሆኑት አቶ ጥላሁን ውቡ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት "ጠንካራ የአቧራ ጭጋግ ተከስቷል።" ይህ የአቧራ ጭጋግ የሚከሰተው በደረቅ አካባቢዎች የሚከሰትን አውሎ ነፋስ ተከትሎ ነው የሚሉት ባለሙያው፤ በባህር ዳር ላይ የታየው የአቧራ አውሎ ነፋስ ሱዳን ላይ በተከሰተ ዝቅተኛ የአየር ግፊት ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ። ይህ የአቧራ ጭጋግ የተከሰተው በባህር ዳር ከተማ ብቻ አለመሆኑን የሚናገሩት ባለሙያው ጎንደር ላይም መታየቱን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ክስተቱ ብዙ ጊዜ ለረዥም ሰዓት አይቆይም የሚሉት አቶ ጥላሁን ቶሎ ሊጠፋ እንደሚችል ያስረዳሉ። ነገር ግን በእንዲህ ዓይነት የአየር ሁኔታ አውሮፕላኖች ለመነሳትም ሆነ ለማረፍ እይታን ስለሚጋርድ ለበረራ አስቸጋሪ እንደሚሆን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ ግን በረራዎች ከተስተጓጎሉባቸው ከተሞች ውስጥ የአቧራ ጭጋጉ የተከሰተባት የባህር ዳር ከተማ የለችበትም። ባለሙያው ጨምረውም እንዲህ አይነት አቧራ ጭጋግ የመተንፈሻ አካል ችግር በተለይ አስም ላለባቸው ሰዎች አስቸጋሪ እንደሚሆን አስታውሰው፤ እንዲሁም ክስተቱ የማጅራት ገትር በሽታ መንስዔም ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ባህር ዳር የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ እንዳረጋገጠው የአቧራ ጭጋጉ ዛሬ በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ቢሆንም የተወሰኑ ምልክቶች ግን እንዳሉ አመልክቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-51894638 |
2health
| ኮሮናቫይረስ ፡ የካናዳው ሚኒስትር በኮቪድ-19 ወቅት ሽርሽር በመሄዳቸው ምክንያት ሥልጣናቸውን ለቀቁ | የካናዳዋ ኦንታሪዮ ግዛት የገንዘብ ሚኒስትር የሆኑት ግለሰብ በኮቪድ-19 ወቅት ለመዝናናት ወደ ካሪቢያን በመጓዛቸው ምክንያት ሥራ ለቀዋል። የግዛቲቱ ገዥ ዶግ ፎርድ የገንዘብ ሚኒስትራቸው ሥልጣን እንዲለቁ ያደረጉት ኦንታሪዮ የእንቅስቃሴ ገደብ ላይ እያለች ሽርሽር ብለው በመጓዛቸው ነው። ሚኒስትር ሮድ ፊሊፕስ ይቅርታ ጠይቀዋል። ጉዟቸውንም "የሞኝ ሥራ" ብለውታል። የግዛቲቱ አስተዳዳሪ እንዳሉት "የፋይናንስ ሚኒስትሩ ሥልጣን መልቀቃቸው መንግሥታቸው ኃላፊነትን በአግባቡ የማይወጡ ሰዎችን እንደማይምር ማሳያ ነው" ብለዋል። በካናዳ ብዙ ሕዝብ የሚኖርባት የኦንታሪዬ ግዛት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ጠበቅ ያለ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሏ ይታወቃል። የፕሮግረሲቭ ኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ አባል የሆኑት ሚኒስትር ሴይንት ባርትስ ወደ ተሰኘችው የካሬቢያን ደሴት ለሽርሽር የሄዱት በዚህ በታኅሣስ ወር ነው። በወቅቱ የኦንታሪዮ የጤና ባለሥልጣናት በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁትሩ በመጨመሩ ምክንያት ነዋሪዎች ከቤታቸው ንቅንቅ እንዳይሉ አዘው ነበር። ኦንታሪዮ ከቀናት በፊት እንደ አዲስ ጠበቅ ያለ የኮቪድ-19 ሕግ አውጥታለች። ባለፈው ሐሙስ ብቻ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከገባ በበሽታው የተያዙ ከፍተኛው የተባለው ቁጥር [3328] ተመዝግቧል። 56 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ከሆነ በካናዳ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ582 ሺህ በላይ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 15 ሺህ 600 ደርሷል። ሚኒስትሩ ከሽርሽር ሲመለሱ ሥራቸውን ለመቀጠል አስበው የነበረ ቢሆንም የግዛቲቱ አስተዳደር ሥልጣናቸውን ቢለቁ የተሻለ እንደሆነ ነግረዋቸዋል። "እንምታዩት በጣም ከባድ ስህተት ፈፅሜያለሁ። ተጠያቂ መሆን ደግሞ አለብኝ። መሄድ በሌለብኝ ወቅት ነው የተጓዝኩት። ምንም ምክንያት መደርደር አይጠበቅብኝም" ብለዋል ስልጣናቸውን የለቀቁት ሚኒስትር። የኦንታሪዮ አስተዳዳሪ ሥልጣን በለቀቁት ሚኒስትር ምትክ ሌላ ሰው በጊዜያዊነት ሾመዋል። | ኮሮናቫይረስ ፡ የካናዳው ሚኒስትር በኮቪድ-19 ወቅት ሽርሽር በመሄዳቸው ምክንያት ሥልጣናቸውን ለቀቁ የካናዳዋ ኦንታሪዮ ግዛት የገንዘብ ሚኒስትር የሆኑት ግለሰብ በኮቪድ-19 ወቅት ለመዝናናት ወደ ካሪቢያን በመጓዛቸው ምክንያት ሥራ ለቀዋል። የግዛቲቱ ገዥ ዶግ ፎርድ የገንዘብ ሚኒስትራቸው ሥልጣን እንዲለቁ ያደረጉት ኦንታሪዮ የእንቅስቃሴ ገደብ ላይ እያለች ሽርሽር ብለው በመጓዛቸው ነው። ሚኒስትር ሮድ ፊሊፕስ ይቅርታ ጠይቀዋል። ጉዟቸውንም "የሞኝ ሥራ" ብለውታል። የግዛቲቱ አስተዳዳሪ እንዳሉት "የፋይናንስ ሚኒስትሩ ሥልጣን መልቀቃቸው መንግሥታቸው ኃላፊነትን በአግባቡ የማይወጡ ሰዎችን እንደማይምር ማሳያ ነው" ብለዋል። በካናዳ ብዙ ሕዝብ የሚኖርባት የኦንታሪዬ ግዛት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ጠበቅ ያለ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሏ ይታወቃል። የፕሮግረሲቭ ኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ አባል የሆኑት ሚኒስትር ሴይንት ባርትስ ወደ ተሰኘችው የካሬቢያን ደሴት ለሽርሽር የሄዱት በዚህ በታኅሣስ ወር ነው። በወቅቱ የኦንታሪዮ የጤና ባለሥልጣናት በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁትሩ በመጨመሩ ምክንያት ነዋሪዎች ከቤታቸው ንቅንቅ እንዳይሉ አዘው ነበር። ኦንታሪዮ ከቀናት በፊት እንደ አዲስ ጠበቅ ያለ የኮቪድ-19 ሕግ አውጥታለች። ባለፈው ሐሙስ ብቻ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከገባ በበሽታው የተያዙ ከፍተኛው የተባለው ቁጥር [3328] ተመዝግቧል። 56 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ከሆነ በካናዳ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ582 ሺህ በላይ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 15 ሺህ 600 ደርሷል። ሚኒስትሩ ከሽርሽር ሲመለሱ ሥራቸውን ለመቀጠል አስበው የነበረ ቢሆንም የግዛቲቱ አስተዳደር ሥልጣናቸውን ቢለቁ የተሻለ እንደሆነ ነግረዋቸዋል። "እንምታዩት በጣም ከባድ ስህተት ፈፅሜያለሁ። ተጠያቂ መሆን ደግሞ አለብኝ። መሄድ በሌለብኝ ወቅት ነው የተጓዝኩት። ምንም ምክንያት መደርደር አይጠበቅብኝም" ብለዋል ስልጣናቸውን የለቀቁት ሚኒስትር። የኦንታሪዮ አስተዳዳሪ ሥልጣን በለቀቁት ሚኒስትር ምትክ ሌላ ሰው በጊዜያዊነት ሾመዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55505118 |
0business
| የዓለማችን ግዙፉ ባለሁለት ሞተር ቦይንግ አውሮፕላን የሙከራ በረራውን አደረገ | ቦይንግ 777ኤክስ የተሰኘው የዓለማችን ግዙፉ ባለሁለት ሞተር አውሮፕላን የሙከራ በራራውን በድል አጠናቋል። ቦይንግ የተሰኘው አውሮፕላን ፈብራኪ ድርጅት 737 ማክስ በተሰኙ አውሮፕላኖቹ ላይ በደረሰ እክል ምክንያት የሰው ሕይወት ከጠፋ በኋላ ገበያ ለማግኘት ሲዳክር ከርሟል። የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢንዶኔዢያ አቻው ንብረት የሆኑ ሁለት አውሮፕላኖች በወራት ልዩነት ተከስክሰው በድምሩ 346 ሰዎች ሞተዋል። ከአደጋዎቹ በኋላ የተቀሩትን 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከበረራ ያገደው ቦይንግ እነሆ ግዙፍ አውሮፕላን ይዞ ብቅ ብሏል። ለአራት ሰዓትታ የዘለቀው የሙከራ በረራ ሲያትል የተሰኘችው የአሜሪካ ከተማ አቅራቢያ ነው የተከወነው። የተሳካው በረራ ከመካሄዱ በፊት ሁለት ጊዜ በአየር ፀባይ ምክንያት በረራዎች እንዲቋረጡ ተደርገዋል። 252 ጫማ [76 ሜትር] የሚረዝመው አውሮፕላን የዓለማችን ግዙፉ ባለሁለት ሞተር የንግድ አውሮፕላን ነው ተብሎለታል። ቦይንግ እስካሁን 309 777ኤክስ አውሮፕላኖች ሸጫለሁ የአንዱ ዋጋ ደግሞ 442 ሚሊዮን ዶላር ነው ብሏል። የድርጅቱ ግብይት ባለሙያ ዌንዲ ሶወርስ "ድርጅታችን ትልቅ ነገር ማድረግ እንደሚችል ያሳየ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። አውሮፕላኑ 360 ሰዎች የመጫን አቅም ካለው ኤርባስ ኤ350-1000 ጋር ተመሳሳይ ባሕሪ አለው ተብሏል። ቦይንግ አደጋ የጠናባቸውን 737 ማክስ አውሮፕላኖች ሲያመርት ለደህንነት የሰጠው ዋጋ ዝቅ ያለ ነው ተብሎ ብዙ ወቀሳ ደርሶባታል። እንዳይበሩ የታገዱት አውሮፕላኖች እንደገና ተፈትሸው ወደ ሰማይ ይወጣሉ ሲል ድርጅቱ ማሳወቁ አይዘነጋም። ማክስ 737 የቦይንግ እጅግ በብዛት የተሸጡ አውሮፕላኖች ሲሆን አውሮፕላኖቹ እንዳይበሩ በመተጋዳቸው ምክንያት ቦይንግ 9 ቢሊዮን ዶላር እንደከሰረ ይገመታል። | የዓለማችን ግዙፉ ባለሁለት ሞተር ቦይንግ አውሮፕላን የሙከራ በረራውን አደረገ ቦይንግ 777ኤክስ የተሰኘው የዓለማችን ግዙፉ ባለሁለት ሞተር አውሮፕላን የሙከራ በራራውን በድል አጠናቋል። ቦይንግ የተሰኘው አውሮፕላን ፈብራኪ ድርጅት 737 ማክስ በተሰኙ አውሮፕላኖቹ ላይ በደረሰ እክል ምክንያት የሰው ሕይወት ከጠፋ በኋላ ገበያ ለማግኘት ሲዳክር ከርሟል። የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢንዶኔዢያ አቻው ንብረት የሆኑ ሁለት አውሮፕላኖች በወራት ልዩነት ተከስክሰው በድምሩ 346 ሰዎች ሞተዋል። ከአደጋዎቹ በኋላ የተቀሩትን 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከበረራ ያገደው ቦይንግ እነሆ ግዙፍ አውሮፕላን ይዞ ብቅ ብሏል። ለአራት ሰዓትታ የዘለቀው የሙከራ በረራ ሲያትል የተሰኘችው የአሜሪካ ከተማ አቅራቢያ ነው የተከወነው። የተሳካው በረራ ከመካሄዱ በፊት ሁለት ጊዜ በአየር ፀባይ ምክንያት በረራዎች እንዲቋረጡ ተደርገዋል። 252 ጫማ [76 ሜትር] የሚረዝመው አውሮፕላን የዓለማችን ግዙፉ ባለሁለት ሞተር የንግድ አውሮፕላን ነው ተብሎለታል። ቦይንግ እስካሁን 309 777ኤክስ አውሮፕላኖች ሸጫለሁ የአንዱ ዋጋ ደግሞ 442 ሚሊዮን ዶላር ነው ብሏል። የድርጅቱ ግብይት ባለሙያ ዌንዲ ሶወርስ "ድርጅታችን ትልቅ ነገር ማድረግ እንደሚችል ያሳየ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። አውሮፕላኑ 360 ሰዎች የመጫን አቅም ካለው ኤርባስ ኤ350-1000 ጋር ተመሳሳይ ባሕሪ አለው ተብሏል። ቦይንግ አደጋ የጠናባቸውን 737 ማክስ አውሮፕላኖች ሲያመርት ለደህንነት የሰጠው ዋጋ ዝቅ ያለ ነው ተብሎ ብዙ ወቀሳ ደርሶባታል። እንዳይበሩ የታገዱት አውሮፕላኖች እንደገና ተፈትሸው ወደ ሰማይ ይወጣሉ ሲል ድርጅቱ ማሳወቁ አይዘነጋም። ማክስ 737 የቦይንግ እጅግ በብዛት የተሸጡ አውሮፕላኖች ሲሆን አውሮፕላኖቹ እንዳይበሩ በመተጋዳቸው ምክንያት ቦይንግ 9 ቢሊዮን ዶላር እንደከሰረ ይገመታል። | https://www.bbc.com/amharic/news-51253933 |
0business
| ቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎቼን አሜሪካ "በማን አለብኝነት እያስፈራራቸው" ነው አለች | የቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ቲክቶክ፣ ዊቻት በአሜሪካ መታገዳቸውን ተከትሎ ቻይና ኩባንያዎቿ ግልፅ የሆነ "የማስፈራሪያ ጥቃት" በአሜሪካ እየደረሰባቸው ነው ብላለች። የቻይና መንግሥትም "በአሜሪካ የበላይነትና ማን አለብኝነት" ብሎ በጠራው የተፈጠረውን ጫና ለማስተካካልም የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የሚገዛ አለም አቀፍ መመሪያዎችን አውጥታለች። በአዲሱ ጅማሮ መሰረት የዜጎችን የግል መረጃ በህገወጥ መንገድ መሰብሰም ሆነ በዜጎች ላይ የሚደረግ ከፍተኛ ስለላና ክትትል ህጋዊ አይደለም በማለት አስምሯል። በባለፈው ወርም እንዲሁ መረጃዎችን ከመጠበቅና ደህንነት ጋር ተያይዞም አሜሪካ "ክሊን ኔትወርክ" (ከማንም ነፃ የሆነ ኔትወርክ) የሚል እሳቤን አስተዋውቃለች። የመረጃን ደህንንነት በተመለከተ እሰጣገባ የገቡት አሜሪካና ቻይና ፤ ቲክቶክ፣ ሁዋዌና ዊ ቻትም መወዛገቢያ ሆነዋል። በቅርብ ወራትም የትራምፕ አስተዳደር የቻይና የቴሌኮም አገልግሎት ሰጭና ተንቀሳቃሽ ስልኮች አምራች ሁዋዌን ጨምሮ የማህበራዊ ሚዲያዎቹን ቲክቶክና ዊቻት ብሄራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ ይጥላሉ በሚል አግዷል። "አንዳንድ ሃገራት በማን አለብኝነትና በትምክህተኝነት አገራትን ሲያዋርዱ ይታያሉ። መረጃን በመጠበቅና ደህነነት በሚል ሽፋንም በአለም እየመሩ ያሉ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን ለማጥቃት አነጣጥረዋል" በማለት የቻይና መንግሥት አማካሪ ዋንግ ይ ተናግረዋል። "ይሄ ግልፅ ያለ ማስፈራራትና ጉልቤነት ነው። ልንቃወመው ይገባል" ብለዋል። ዋንግ በዛሬው እለት እንደተናገሩት ቻይና ያወጣቻቸው አዳዲስ መመሪያዎች ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የግል መረጃዎቻቸውንና አገልግሎታቸውን ለተለያዩ ኩባንያዎች አስተላልፈው እንዳይሰጡም ጥሪ አድርጓል። አሜሪካ በበኩሏ የቻይናው ቴሌኮም አገልግሎት ሰጭና ተንቀሳቃሽ ስልኮች አምራች ኩባንያ ሁዋዌ በስልኮቹ ላይ መረጃዎችን አሳልፎ የሚሰጥ የተገጠመ ማሽን አለው በማለት ትወነጅላለች። "የአለም አቀፉ መረጃ ደህንነት ሁሉም አገራት በመከባበር፣ በመተሳሰብና አለም አቀፍ ተሳትፎን መሰረት ያደረገ ነው" በማለት ዋንግ አስረድተዋል። | ቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎቼን አሜሪካ "በማን አለብኝነት እያስፈራራቸው" ነው አለች የቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ቲክቶክ፣ ዊቻት በአሜሪካ መታገዳቸውን ተከትሎ ቻይና ኩባንያዎቿ ግልፅ የሆነ "የማስፈራሪያ ጥቃት" በአሜሪካ እየደረሰባቸው ነው ብላለች። የቻይና መንግሥትም "በአሜሪካ የበላይነትና ማን አለብኝነት" ብሎ በጠራው የተፈጠረውን ጫና ለማስተካካልም የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የሚገዛ አለም አቀፍ መመሪያዎችን አውጥታለች። በአዲሱ ጅማሮ መሰረት የዜጎችን የግል መረጃ በህገወጥ መንገድ መሰብሰም ሆነ በዜጎች ላይ የሚደረግ ከፍተኛ ስለላና ክትትል ህጋዊ አይደለም በማለት አስምሯል። በባለፈው ወርም እንዲሁ መረጃዎችን ከመጠበቅና ደህንነት ጋር ተያይዞም አሜሪካ "ክሊን ኔትወርክ" (ከማንም ነፃ የሆነ ኔትወርክ) የሚል እሳቤን አስተዋውቃለች። የመረጃን ደህንንነት በተመለከተ እሰጣገባ የገቡት አሜሪካና ቻይና ፤ ቲክቶክ፣ ሁዋዌና ዊ ቻትም መወዛገቢያ ሆነዋል። በቅርብ ወራትም የትራምፕ አስተዳደር የቻይና የቴሌኮም አገልግሎት ሰጭና ተንቀሳቃሽ ስልኮች አምራች ሁዋዌን ጨምሮ የማህበራዊ ሚዲያዎቹን ቲክቶክና ዊቻት ብሄራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ ይጥላሉ በሚል አግዷል። "አንዳንድ ሃገራት በማን አለብኝነትና በትምክህተኝነት አገራትን ሲያዋርዱ ይታያሉ። መረጃን በመጠበቅና ደህነነት በሚል ሽፋንም በአለም እየመሩ ያሉ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን ለማጥቃት አነጣጥረዋል" በማለት የቻይና መንግሥት አማካሪ ዋንግ ይ ተናግረዋል። "ይሄ ግልፅ ያለ ማስፈራራትና ጉልቤነት ነው። ልንቃወመው ይገባል" ብለዋል። ዋንግ በዛሬው እለት እንደተናገሩት ቻይና ያወጣቻቸው አዳዲስ መመሪያዎች ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የግል መረጃዎቻቸውንና አገልግሎታቸውን ለተለያዩ ኩባንያዎች አስተላልፈው እንዳይሰጡም ጥሪ አድርጓል። አሜሪካ በበኩሏ የቻይናው ቴሌኮም አገልግሎት ሰጭና ተንቀሳቃሽ ስልኮች አምራች ኩባንያ ሁዋዌ በስልኮቹ ላይ መረጃዎችን አሳልፎ የሚሰጥ የተገጠመ ማሽን አለው በማለት ትወነጅላለች። "የአለም አቀፉ መረጃ ደህንነት ሁሉም አገራት በመከባበር፣ በመተሳሰብና አለም አቀፍ ተሳትፎን መሰረት ያደረገ ነው" በማለት ዋንግ አስረድተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54068170 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ሳይታወቅ ለዓመታት በሌሊት ወፎች ውስጥ ነበር | የሰው ልጆች ላይ ጉዳት እያስከተለ ያለው ኮሮናቫይረስ ለበርካታ ዓመታት ሳይታወቅ በሌሊት ወፎች ሰውነት ውስጥ እንደነበር ጥናቶች ያሳያሉ። ኮቪድ-19ን የሚያስከትለው ቫይረስ በሌሊት ወፎች ላይ ከታየ ከ40 እስከ 70 ዓመታት አልፈዋል። ወደ ሰው ልጆች ከተሻረገ ጥቂት ጊዜው መሆኑን ሳይንቲስቶች ይናገራሉ። መረጃው፤ ኮቪድ-19 በሰው የተሠራና ከቤተ ሙከራ አምልጦ የወጣ ነው የሚለው የሴራ ትንተና ላይ እውነትን የተመረኮዘ ስለመሆኑ ጥያቄ ያጭራል። ፕ/ር ዴቪድ ሮበርትሰን በግላስጎው ዩኒቨርስቲ ነው የሚሠሩት። የሳቸው ጥናት ‘ኔቸር ማይክሮባዮሎጂ’ በተባለ መጽሔት ላይ ታትሟል። ፕ/ር ዴቪድ እንደሚናገሩት፤ ሳርስ-ኮቭ-2 ከሌሊት ወፎች ቫይረስ ጋር የዘረ መል ተመሳሳይነት ቢኖረውም፤ አንዳቸው ከሌላቸው የበርካታ ዓሠርታት ልዩነት አላቸው። “እነዚህ ሰውን ሊይዙ የሚችሉ ቫይረሶች ዘለግ ላለ ጊዜ እንደኖሩ ጥናቱ ያሳያል” ይላሉ። ቫይረሱ መቼ እና እንዴት ወደ ሰው ልጆች እንደተሸጋገረ መታወቅ እንዳለበት ተመራማሪው ያስረዳሉ። “በሌሊት ወፎች ላይ ቫይረሱ እንዳለ ካወቅን ለመቆጣጠር መሞከር አለብን።” ለወደፊቱ ወረርሽኞች እንዳይቀሰቀሱ፤ ሰዎች የሚገጥሟቸው ህመሞች የቅርብ ክትትል እንደሚያሻቸው ጥናቱ ያሳያል። ከዱር የሌሊት ወፎች ላይ ናሙና ተወስዶ ምርመራ መካሄድም አለበት። ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት፤ “እነዚህ ቫይረሶች ዓመታት አስቆጥረዋል ማለት ሰዎችን ጨምሮ ሌላም መኖሪያቸው የሚያደርጉት አካል አግኝተዋል ማለት ነው።” በጥናቱ፤ የሳርስ-ኮቭ-2 ዘረ መል ተቀራራቢው ከሆኑ የሌሊት ወፍ ላይ ያሉ ቫይረሶች ማለትም አርኤቲጂ13 እንዲሁም ከሌሎች ጋር ንጽጽር ተደርጓል። ሁለቱ አይነቶች በምን ወቅት ላይ ተመሳሳይ የዘር ግንድ እንደነበራቸውም ተጠንቷል። በዚህ መሠረትም ሁሉቱ ዓይነቶች ከአስርታት በፊት በተለያየ የእድገት ሁኔታ ማለፋቸው ተደርሶበታል። በሪዲንግ ዩኒቨርስቲ የሚሠሩት ፕ/ር ማርክ ፓጌል በጥናቱ ባይሳተፉም፤ ሰዎችን ሊጎዱ የሚችሉ ኮሮናቫይረሶች ሳይታወቁ በሌሊት ወፎች ላይ ከ40 እስከ 70 ዓመታት መኖራቸውን ምርምሩ እንደሚያሳይ ይስማማሉ። “ከእንስሳት ወደ ሰዎች የሚተላለፉ በሽታዎች ምን ያህል አደገኛ እንደሆኑ ጥናቱ ያሳያል። እንስሳት ውስጥ በጥገኝነት የሚኖሩና ለሰው ልጅ ጎጂ የሆኑ፤ እስካሁን ድረስ ግን ያልታወቁ ሌሎች ቫይረሶችም ሊኖሩ ይችላሉ።” ቫይረሶቹ ወደ ሌሎች የዱር እንስሳት ተላልፈው ሊሆን ይችላል። በተለይም በሕገ ወጥ የእንስሳት ዝውውር ሳቢያ እርስ በእርስ የተቀራረቡ እንስሳት የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። እስካሁን ድረስ ያለው መረጃ እንደሚያሳየው ግን የቫይረስ ዋነኛ ተሸካሚ የሆኑት የሌሊት ወፎች ናቸው። ከዚህ ቀደም የሰሠሩ ጥናቶች ፓንጎሎኖች ለሳርስ-ኮቭ-2 ዝግመተ ለውጥ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ ያሳያል። አሁን ግን ይህ ትክክል እንዳልሆነ ተደርሶበታል። ቻይናን መዳረሻው ባደረገ ሕገ ወጥ የዱር እንስሳት ንግድ ወቅት ፓንጎሊኖች ከሌሎች እንስሳት ጋር ንክኪ ነበራቸው። ስለዚህም ፓንጎሊኖች ለቫይረሱ የተጋለጡት በቅርቡ ነው። | ኮሮናቫይረስ፡ ሳይታወቅ ለዓመታት በሌሊት ወፎች ውስጥ ነበር የሰው ልጆች ላይ ጉዳት እያስከተለ ያለው ኮሮናቫይረስ ለበርካታ ዓመታት ሳይታወቅ በሌሊት ወፎች ሰውነት ውስጥ እንደነበር ጥናቶች ያሳያሉ። ኮቪድ-19ን የሚያስከትለው ቫይረስ በሌሊት ወፎች ላይ ከታየ ከ40 እስከ 70 ዓመታት አልፈዋል። ወደ ሰው ልጆች ከተሻረገ ጥቂት ጊዜው መሆኑን ሳይንቲስቶች ይናገራሉ። መረጃው፤ ኮቪድ-19 በሰው የተሠራና ከቤተ ሙከራ አምልጦ የወጣ ነው የሚለው የሴራ ትንተና ላይ እውነትን የተመረኮዘ ስለመሆኑ ጥያቄ ያጭራል። ፕ/ር ዴቪድ ሮበርትሰን በግላስጎው ዩኒቨርስቲ ነው የሚሠሩት። የሳቸው ጥናት ‘ኔቸር ማይክሮባዮሎጂ’ በተባለ መጽሔት ላይ ታትሟል። ፕ/ር ዴቪድ እንደሚናገሩት፤ ሳርስ-ኮቭ-2 ከሌሊት ወፎች ቫይረስ ጋር የዘረ መል ተመሳሳይነት ቢኖረውም፤ አንዳቸው ከሌላቸው የበርካታ ዓሠርታት ልዩነት አላቸው። “እነዚህ ሰውን ሊይዙ የሚችሉ ቫይረሶች ዘለግ ላለ ጊዜ እንደኖሩ ጥናቱ ያሳያል” ይላሉ። ቫይረሱ መቼ እና እንዴት ወደ ሰው ልጆች እንደተሸጋገረ መታወቅ እንዳለበት ተመራማሪው ያስረዳሉ። “በሌሊት ወፎች ላይ ቫይረሱ እንዳለ ካወቅን ለመቆጣጠር መሞከር አለብን።” ለወደፊቱ ወረርሽኞች እንዳይቀሰቀሱ፤ ሰዎች የሚገጥሟቸው ህመሞች የቅርብ ክትትል እንደሚያሻቸው ጥናቱ ያሳያል። ከዱር የሌሊት ወፎች ላይ ናሙና ተወስዶ ምርመራ መካሄድም አለበት። ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት፤ “እነዚህ ቫይረሶች ዓመታት አስቆጥረዋል ማለት ሰዎችን ጨምሮ ሌላም መኖሪያቸው የሚያደርጉት አካል አግኝተዋል ማለት ነው።” በጥናቱ፤ የሳርስ-ኮቭ-2 ዘረ መል ተቀራራቢው ከሆኑ የሌሊት ወፍ ላይ ያሉ ቫይረሶች ማለትም አርኤቲጂ13 እንዲሁም ከሌሎች ጋር ንጽጽር ተደርጓል። ሁለቱ አይነቶች በምን ወቅት ላይ ተመሳሳይ የዘር ግንድ እንደነበራቸውም ተጠንቷል። በዚህ መሠረትም ሁሉቱ ዓይነቶች ከአስርታት በፊት በተለያየ የእድገት ሁኔታ ማለፋቸው ተደርሶበታል። በሪዲንግ ዩኒቨርስቲ የሚሠሩት ፕ/ር ማርክ ፓጌል በጥናቱ ባይሳተፉም፤ ሰዎችን ሊጎዱ የሚችሉ ኮሮናቫይረሶች ሳይታወቁ በሌሊት ወፎች ላይ ከ40 እስከ 70 ዓመታት መኖራቸውን ምርምሩ እንደሚያሳይ ይስማማሉ። “ከእንስሳት ወደ ሰዎች የሚተላለፉ በሽታዎች ምን ያህል አደገኛ እንደሆኑ ጥናቱ ያሳያል። እንስሳት ውስጥ በጥገኝነት የሚኖሩና ለሰው ልጅ ጎጂ የሆኑ፤ እስካሁን ድረስ ግን ያልታወቁ ሌሎች ቫይረሶችም ሊኖሩ ይችላሉ።” ቫይረሶቹ ወደ ሌሎች የዱር እንስሳት ተላልፈው ሊሆን ይችላል። በተለይም በሕገ ወጥ የእንስሳት ዝውውር ሳቢያ እርስ በእርስ የተቀራረቡ እንስሳት የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። እስካሁን ድረስ ያለው መረጃ እንደሚያሳየው ግን የቫይረስ ዋነኛ ተሸካሚ የሆኑት የሌሊት ወፎች ናቸው። ከዚህ ቀደም የሰሠሩ ጥናቶች ፓንጎሎኖች ለሳርስ-ኮቭ-2 ዝግመተ ለውጥ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ ያሳያል። አሁን ግን ይህ ትክክል እንዳልሆነ ተደርሶበታል። ቻይናን መዳረሻው ባደረገ ሕገ ወጥ የዱር እንስሳት ንግድ ወቅት ፓንጎሊኖች ከሌሎች እንስሳት ጋር ንክኪ ነበራቸው። ስለዚህም ፓንጎሊኖች ለቫይረሱ የተጋለጡት በቅርቡ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-53600806 |
2health
| ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት ገበያ እንዲወጣ የተባለው የአፕል ጭማቂ | በደቡብ አፍሪካ የሚመረተው ሲረስ የተባለው ታሸገ ጭማቂ ከፍተኛ መጠን ያለው ለጤና ጎጂ የሆነ ንጥረ ነገር በውስጡ በመገኘቱ ከሰባት የአፍሪካ አገራት ገበያ እንዲሰበሰብ መደረጉ ተዘግቧል። የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በበኩሉ ሲረስ አፕል ጁስ የተሰኘው ጭማቂ "በውስጡ ጎጂ የሆነ ከሻጋታ የመነጨ መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት" ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀም ማሳሰቢያ አውጥቷል። ባለስልጣኑ ስለተገኘው መርዛማ ንጥረ ነገር በአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በኩል በሰጠው ማብራሪያ በፍራፍሬዎች ላይ የሚከሰት ማይኮቶክሲን ከሚባል ከሻጋታ የሚመነጭ መሆኑን አመልክቶ ኅብተሰቡ የተጠቀሰውን ምርት እንዳይጠቀም መክሯል። በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተመርቶ ወደ ተለያዩ የአፍሪካ አገራት የሚሰራጨው ሲረስ የአፕል ጭማቂ በመበስበስና በመሻገት የሚከሰተው ፓቱሊን የተባለው ጎጂ ንጥረ ነገር ስለተገኘበት ከገበያ እንዲወጣ እየተደረገ ነው። በጭማቂው ላይ በተደረገ ቤተ ሙከራ ፍተሻ እንደተረጋገጠው ሲረስ በተባለው የአፕል ምርት ላይ በአንድ ሊትር ውስጥ እንዲኖረው ከተፈቀደው 50 ማይክሮ ግራም ከፍ ያለ መጠን መገኘቱ ተገልጿል። ይህ የማይኮቶክሲን ውጤት የሆነው ፓቱሊን የተባለው ጎጂ ንጥረ ነገር በአፕል እና በአፕል ምርቶች ውስጥ በሚከሰቱ በተለያዩ ሻጋታዎች አማካይነት የሚፈጠረው። በጭማቂው ውስጥ የተገኘው ንጥረ ነገር ፓቱሊን በተጠቃሚዎች ላይ ማቅለሽለሽና ማስታወክን በማስከተል ጤናን ሊያውክ ይችላል ተብሏል። ይህ ሲረስ የተባለው የአፕል ጭማቂ በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን አመልክቶ ኅብረተሰቡ እንዳይ ጠቀመውና በገበያ ላይ ከተገኘም ጥቆማ እንዲሰጠው ጥሪ አቅርቧል። ምርቱ በተጨማሪም በኬንያ፣ በዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ በዛምቢያ፣ ዚምብብዌ፣ ኡጋንዳ፣ ሲሸልስ እና ሞሪሺየስ ገበያዎች ውስጥ ተሰራጭቶ እንደሚገን ተነግሯል። የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ የንግድ ቀጠና (ኮሜሳ) የንግድ ውድድር ኮሚሽን በአገራቱ ውስጥ ያሉ የምርቱ ተጠቃሚዎች ባለፈው ሰኔ ወር ተመርተው የተሰራጩ የሲረስአፕል ጭማቂ ምርቶችን ከገበያ አስወጥተው ለአምራቹ እንዲመልሱ ጥሪ አቅርቧል። | ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት ገበያ እንዲወጣ የተባለው የአፕል ጭማቂ በደቡብ አፍሪካ የሚመረተው ሲረስ የተባለው ታሸገ ጭማቂ ከፍተኛ መጠን ያለው ለጤና ጎጂ የሆነ ንጥረ ነገር በውስጡ በመገኘቱ ከሰባት የአፍሪካ አገራት ገበያ እንዲሰበሰብ መደረጉ ተዘግቧል። የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በበኩሉ ሲረስ አፕል ጁስ የተሰኘው ጭማቂ "በውስጡ ጎጂ የሆነ ከሻጋታ የመነጨ መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት" ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀም ማሳሰቢያ አውጥቷል። ባለስልጣኑ ስለተገኘው መርዛማ ንጥረ ነገር በአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በኩል በሰጠው ማብራሪያ በፍራፍሬዎች ላይ የሚከሰት ማይኮቶክሲን ከሚባል ከሻጋታ የሚመነጭ መሆኑን አመልክቶ ኅብተሰቡ የተጠቀሰውን ምርት እንዳይጠቀም መክሯል። በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተመርቶ ወደ ተለያዩ የአፍሪካ አገራት የሚሰራጨው ሲረስ የአፕል ጭማቂ በመበስበስና በመሻገት የሚከሰተው ፓቱሊን የተባለው ጎጂ ንጥረ ነገር ስለተገኘበት ከገበያ እንዲወጣ እየተደረገ ነው። በጭማቂው ላይ በተደረገ ቤተ ሙከራ ፍተሻ እንደተረጋገጠው ሲረስ በተባለው የአፕል ምርት ላይ በአንድ ሊትር ውስጥ እንዲኖረው ከተፈቀደው 50 ማይክሮ ግራም ከፍ ያለ መጠን መገኘቱ ተገልጿል። ይህ የማይኮቶክሲን ውጤት የሆነው ፓቱሊን የተባለው ጎጂ ንጥረ ነገር በአፕል እና በአፕል ምርቶች ውስጥ በሚከሰቱ በተለያዩ ሻጋታዎች አማካይነት የሚፈጠረው። በጭማቂው ውስጥ የተገኘው ንጥረ ነገር ፓቱሊን በተጠቃሚዎች ላይ ማቅለሽለሽና ማስታወክን በማስከተል ጤናን ሊያውክ ይችላል ተብሏል። ይህ ሲረስ የተባለው የአፕል ጭማቂ በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን አመልክቶ ኅብረተሰቡ እንዳይ ጠቀመውና በገበያ ላይ ከተገኘም ጥቆማ እንዲሰጠው ጥሪ አቅርቧል። ምርቱ በተጨማሪም በኬንያ፣ በዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ በዛምቢያ፣ ዚምብብዌ፣ ኡጋንዳ፣ ሲሸልስ እና ሞሪሺየስ ገበያዎች ውስጥ ተሰራጭቶ እንደሚገን ተነግሯል። የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ የንግድ ቀጠና (ኮሜሳ) የንግድ ውድድር ኮሚሽን በአገራቱ ውስጥ ያሉ የምርቱ ተጠቃሚዎች ባለፈው ሰኔ ወር ተመርተው የተሰራጩ የሲረስአፕል ጭማቂ ምርቶችን ከገበያ አስወጥተው ለአምራቹ እንዲመልሱ ጥሪ አቅርቧል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58919812 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ክትባት ለመከተብ አጭበርብረዋል የተባሉ ኃላፊ ከስራቸው ለቀቁ | ከ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የካዚኖ ቁማር ኩባንያ የሚመሩት ዋና ስራ አስፈፃሚ የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት አጭብርብረዋል መባሉን ተከትሎ ከስራቸው ለቀቁ። ኃላፈውና ባለቤታቸው ባለስልጣናቱን አታለዋል በሚል ተከሰዋል። ግሬት ካናዲያን ጌሚንግ የተባለ የካዚኖ ቁማር ድርጅት የሚመሩት ሮድ ቤከርና ባለቤታቸው ኢካትሪና ገጠራማ ወደሆነው ዩኮን ግዛት ክትባት ለመከተብ አቅንተው ነበር። ግዛቱ የቀደምት ካናዳውያን መኖሪያ ሲሆን ከሌሎች የካናዳ ክፍሎች በበለጠ ፈጣን የሆነ የክትባት አሰጣጥ ስርአት እንዳለው መረጃዎች ያሳያሉ። ባለትዳሮቹ ወደ ቦታው ሲያመሩም የሆቴል ሰራተኞች ነን በሚል ሽፋን ነው። በባለፈው ሳምንት በግዛቲቱ ውስጥ በምትገኝ ቢቨር ክሪክ በምትባል መንደር ውስጥ ተከትበው ከጨረሱ በኋላ ወደ አየር ማረፊያ ውሰዱን ማለታቸውን ተከትሎ ነው የተጋለጡት። " በዚህ ራስ ወዳድ በሆነ ባህርያቸው በጣም ተበሳጭቻለሁ" በማለት የዩኮን ማህበረሰብ አገልግሎት ሚኒስትር ጆን ስትሬይከር ተናግረዋል። "በዚህ መንገድ ሰው አጭበርብሮ እንዲህ አይነት ተግባር ይፈፅማል የሚል ነገር በጭራሽ አላሰብንም" ብለዋል አክለውም። ከዚሁ ጋር ተያያይዞ የዋይት ሪቨር ፈርስት ኔሽን፣ የአካባቢው የቀደምት ህዝቦች ኃላፊ አንጄላ ዴሚት በበኩላቸው "የእድሜ ባለፀጎቻችንና ተጋላጭ ማህበረሰቦቻችንን ስጋት ውስጥ የሚከቱ የአንዳንድ ግለሰቦች ድርጊት በጣም አሳስቦናል። ተራን ባለመጠበቅ እንዲህ አይነት አስነዋሪ ስራ መፈፀም ራስ ወዳድነት ነው" ብለዋል። ሮድ ቤከርና ባለቤታቸው ከቫንኮቨር ግዛት ወደ ዩኮን በሄዱበት ወቅት አስገዳጅ የሆነውን የ14 ቀናት ለይቶ ማቆያ ባለማክበር ተቀጥተዋል። | ኮሮናቫይረስ፡ክትባት ለመከተብ አጭበርብረዋል የተባሉ ኃላፊ ከስራቸው ለቀቁ ከ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የካዚኖ ቁማር ኩባንያ የሚመሩት ዋና ስራ አስፈፃሚ የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት አጭብርብረዋል መባሉን ተከትሎ ከስራቸው ለቀቁ። ኃላፈውና ባለቤታቸው ባለስልጣናቱን አታለዋል በሚል ተከሰዋል። ግሬት ካናዲያን ጌሚንግ የተባለ የካዚኖ ቁማር ድርጅት የሚመሩት ሮድ ቤከርና ባለቤታቸው ኢካትሪና ገጠራማ ወደሆነው ዩኮን ግዛት ክትባት ለመከተብ አቅንተው ነበር። ግዛቱ የቀደምት ካናዳውያን መኖሪያ ሲሆን ከሌሎች የካናዳ ክፍሎች በበለጠ ፈጣን የሆነ የክትባት አሰጣጥ ስርአት እንዳለው መረጃዎች ያሳያሉ። ባለትዳሮቹ ወደ ቦታው ሲያመሩም የሆቴል ሰራተኞች ነን በሚል ሽፋን ነው። በባለፈው ሳምንት በግዛቲቱ ውስጥ በምትገኝ ቢቨር ክሪክ በምትባል መንደር ውስጥ ተከትበው ከጨረሱ በኋላ ወደ አየር ማረፊያ ውሰዱን ማለታቸውን ተከትሎ ነው የተጋለጡት። " በዚህ ራስ ወዳድ በሆነ ባህርያቸው በጣም ተበሳጭቻለሁ" በማለት የዩኮን ማህበረሰብ አገልግሎት ሚኒስትር ጆን ስትሬይከር ተናግረዋል። "በዚህ መንገድ ሰው አጭበርብሮ እንዲህ አይነት ተግባር ይፈፅማል የሚል ነገር በጭራሽ አላሰብንም" ብለዋል አክለውም። ከዚሁ ጋር ተያያይዞ የዋይት ሪቨር ፈርስት ኔሽን፣ የአካባቢው የቀደምት ህዝቦች ኃላፊ አንጄላ ዴሚት በበኩላቸው "የእድሜ ባለፀጎቻችንና ተጋላጭ ማህበረሰቦቻችንን ስጋት ውስጥ የሚከቱ የአንዳንድ ግለሰቦች ድርጊት በጣም አሳስቦናል። ተራን ባለመጠበቅ እንዲህ አይነት አስነዋሪ ስራ መፈፀም ራስ ወዳድነት ነው" ብለዋል። ሮድ ቤከርና ባለቤታቸው ከቫንኮቨር ግዛት ወደ ዩኮን በሄዱበት ወቅት አስገዳጅ የሆነውን የ14 ቀናት ለይቶ ማቆያ ባለማክበር ተቀጥተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55807191 |
2health
| እህል በአፏ የማይዞረው ታዋቂዋ ምግብ አብሳይ | ሎሬታ ሃርሜስ ለስድስት ዓመታት ምግብ የሚባል ነገር ወደ አፏ አላስጠጋችም። ምግብ ከማብሰል የሚያግዳት ግን አልሆነም። ሎሬታ የምትሠራው ምግብ ጨው ይብዛው ይነሰው መቅመስ ባትችልም በኢንስታግራም መድረክ በርካታ ወዳጆች አፍርታለች። ሎሬታ ቀቅላ የጠበሰችውን ድንች በሹካ እየፈረካከሰች እንፋሎቱን ትምጋለች። ሎሬታና እናቷ ጁሊ ይህን ማዕድ በጥንቃቄ ያበሰሉት ምናልባትም ይህ የመጨረሻዋ ይሆናል ብለው አስበው ነው። በደቂቃዎች ውስጥ አንድ ከበድ ያለ ስቃይ ሆዷን እየቦረቦረ እንደሚገባ ታውቀዋለች። ይህን ለምዳዋለች። እህልና ፈሳሽ ወደ አፏ ሄዱ ማለት ስቃይ ነው ትርፉ። ነገር ግን የመጣው ይምጣ ብላ ስቃይዋን ተቀብላ በቤተሰቦቿ ኩችና ወንበር ላይ ትውላለች። ኩችናው ማብሰል የተማረችበት አስኳላ ነው። "ከእናቴና እህቴ ጋር አንድ አፍታ ቁጭ ብሎ መመገብ የሚሰጠው ደስታ ለየት ያለ ነው።" ጊዜው በፈረንጆቹ 2015 ነበር። የ23 ዓመቷ ሎሬታ ለዓመታት በፈሳሽ መልክ በሚሰጣት ምግብ ነው የምትንቀሳቀሰው። ቤተሰቦቿ ለእራት ጠረጴዛ ሲከቡ እሷ ተለይታ ክፍሏ ውስጥ ከመቀመጥ ያለፈ ዕጣ አልነበራትም። በነጭ ሽንኩርትና ሎሚ ያበደውን የዶሮ ሥጋ አንስቶ መግመጥ ይቅርና ቢላና ሹካ ማንሳት ራሱ ብርቅ ነው የሚሆንባት። ነገር ግን ይኸው ዛሬ አንድ ጊዜ እንኳ ከቀረበላት ማዕድ ላይ ምግብ አንስታ እንድትበላ ሆነች። ይህን ያደረገው አንድ ባለሙያ ነው። ባለሙያው ሎሬታ ለምን ምግብ ስትበላ እንደሚያማት፣ ለምንስ ሽንት ቤት መጎብኘት እንደማትችል ለመመርመር ነው ዕቅዱ። ሎሬታ የዚያን ቀን ጠዋት ለንደን ወደ ሚገኘው ቅዱስ ማርቆስ ሆስፒታል አቅንታ በአፍንጫዋ ወደታች በተላከ አንድ ቀጭን ቱቦ የትንሹ አንጀቷን ጤንነት ተመርምራ መጥታለች። ሎሬታ ጨቅላ ሳለች በቴሌቪዥን መስኮት የሚታዩ የምግብ ዝግጅት ቅንብሮችን አስመስላ ለቤተሰቦቿ ታቀርብ ነበር። ምግብ ማብሰል መክሊቷ ነው ብንል ማጋነን አይሆንም። የ11 ዓመት ታዳጊ ሳለች ዘወትር ማክሰኞ እናቷ ከሥራ አምሽታ እንደምትመጣ ስለምታውቅ እራት አሰናድታ ትጠብቃት ነበር። እናቷ ጁሊ እንደምትለው ሎሬታ ማብሰል የጀመረችው በቲማቲም ስልስ የተቀመመ ፓስታ በመሥራት ነው። ነገር ግን ትንሽ ቆይታ ከበድ ያሉ ምግቦችን ማሰናዳት ተያያዘችው። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን እየተከታተለች ሳለ የምግብ ማብሰል ውድድር ላይ ተሳትፋ አሸንፋለች። ከትምህርት ቤት አልፋ በሌሎች ውድድሮች ላይ ታላላቆቹን ሳይቀር ረትታ ዋንጫ ይዛ መጥታለች። "የሎሬታ ትልቁ ብቃቷ ኩችና ውስጥ ባለው ነገር የሆነ ምግብ መሥራት መቻሏ ነው" ትላለች እናቷ ጁሊ። 15 ዓመት ሲሞላት የምግብ መብላት መመሰቃቀል የሚያስከትለው 'ኢቲንግ ዲስኦርደር' የተሰኘው በሽታ አገኛት። ነገር ግን እሷ እንደምትለው በሽታው ከአንድ ዓመት በላይ አልቆየም። ቢሆንም በታዳጊነት ዘመኗ የምግብ አለመፈጨት በጣም ያስቸግራት እንደነበር ታስውሳለች። ይህ ምግብ በበላች ቁጥር የሚጎረብጣት ስሜት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ መጣ። የሆነ ሆኖ ይህን ስሜት እየታገለች ምግብ ማብሰሏንና መመገቧን ቀጠለች። ሎሬታ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን እንደጨረሰች ለንደን ውስጥ ያለ አንድ ትልቅ የምግብ ዝግጅት ጥበብ ኮሌጅን ተቀላቀለች። ነገር ግን የሦስቱን ዓመት ኮርስ መማር የቻለችው ለአንድ ዓመት ብቻ ነው። ለዚህ ተጠያቂው ደግሞ የጤናዋ ሁኔታ ነበር። በ19 ዓመቷ ትምህርቷን አቋርጣ፣ ከምትወደው ኩችና ተነጥላ አልጋዋ ላይ ስቃይዋን እያስታመመች መኖር ሆነ ሥራዋ። በሽታው ሥጋዋን መጦ ከሰውነት ተራ እንድትወጣ አደረጋት። አልፎም የአእምሮ ጤናዋ ተቃወሰ። ሎሬታ በአንድ ወቅት ክብደቷ ሲለካ መመዘኛው ላይ የሚታየውን ብዙዎች ማመን አልቻሉም። 25 ኪሎ ይላል። ይህ ደግሞ ለሕይወቷ ጭምር አስጊ እንደሆነ ዶክተሯ በተደጋጋሚ አስጠንቅቀዋል። ምንም እንኳ ስቃዩ ለጠላቷ የማትመኘው ቢሆንም እየቻለችውን መመገብና ክብደቷን ማስተካከል እንዳለባት አመነች። ሎሬታ የአመጋገብ መመሰቃቀል ያመጣባትን ጫና ተከትሎ የአእምሮ ጤናዋም ይዳከም ጀመር። በርካታ ጊዜ ራሷን ለማጥፋት ሙከራ እንዳደረገች ትናገራለች። እርዳታ እንድታገኝ የተላከችበት ካምፕ ውስጥ ስድስት ጊዜ መመገብ ግዴታ ነው። ሦስት ጊዜ ዳጎስ ያለ ምግብ፤ ሦስቱን ደግሞ ብስኩት የመሳሰሉ ቀለል ያሉ ምግቦችን መብላት ግድ ነበር። ታማሚዎች የቀረበላቸውን ምግብ በተመደበላቸው ደቂቃ የመጨረስ ግዴታ አለባቸው። ሎሬታ ግን ብዙ ጊዜ ራሷን የምታገኘው ምግቡ ላይ ስታፈጥ ምግቡም ሲያፈጥባት ነው። እሷ ማዕዷን ሳታገባድ ማንም ሰው ከጠረጴዛው ላይ እንዲነሳ አይፈቀድለትም። በዚህ ምክንያት ብዙዎቹ ታማሚዎች ቂም ይቋጥሩባታል። ሁሉም ታካሚዎች ምግብ ከበሉ በኋላ ለአንድ ሰዓት ያክል ቁጥጥር ይደርግላቸዋል። ምክንያቱ ደግሞ ዞር ብለው ጣታቸውን ከተው እንዳያወጡት በሚል ነው። ከዓመታት ምርምርና ጥናት በኋላ የሎሬታ ሆድ ዕቃ በግማሽ ከጥቅም ውጭ እንደሆነ ተደረሰበት። በሽታው በዘር የሚመጣ እንደሆነም ሐኪሞች አወቁበት። ሎሬታ እንድትበላ ማስገደድ ምንም ዋጋ እንደሌለው የተደረሰበት ይሄኔ ነው። ሎሬታ ከምግብ አለመብላት ጋር ከባድ የራስ ምታት፣ ድካምና የልብ በፍጥነት መምታት ያጋጥሟት ነበር። ይህ በሽታ እስኪደረስበት ድረስ ከ10 እስከ 14 ዓመት ድረስ ሊወስድበት እንደሚችል ዶክተር አላን ሐኪም ይናገራሉ። ሎሬታ ምግብ በአፏ ከዞረ ስድስት ዓመታት አልፈዋል። ከዚህ በኋላ ድጋሚ እህልም ሆነ ፈሳሽ ወደ አፏ እንደማታስገባ ታውቀዋለች። አሁን ምግብ የምታገኘው በቀን ለ18 ሰዓታት አንጠልጥላ በምትዞረው ቱቦ አማካይነት ነው። ቱቦው በደረቷ በኩል ገብቶ ወደ ደም ዝውውሯ በፈሳሽ መልክ ምግብ ያሰራጫል። ሎሬታ ይህን ሁሉ አልፋ፤ አሁን ምግብ ለማብሰል ያላትን ፍቅር የማትበላውን ኧረ እንደውም የማትቀምሰውን ማዕድ በማሰናዳት እየተወጣች ነው። የምትሠራውን ምግብ የማትቀምስ አብሳይ መሆኗ በኢንስታግራም ተጠቃሚዎች ዘንድ ታዋቂነትን አትርፎላታል። ሁሌም ከጎኗ የሆኑት እናቷና እህቷ እንዲሁም አብራት የምትኖረው ባልንጀራዋ የሎሬታን ጣት የሚያስቆረጥሙ ምግቦች በፍቅር ይጎርሳሉ። ሎሬታ ግን ሕይወቷን በቱቦ በሚተላለፍ ምግብ ትገፋለች። | እህል በአፏ የማይዞረው ታዋቂዋ ምግብ አብሳይ ሎሬታ ሃርሜስ ለስድስት ዓመታት ምግብ የሚባል ነገር ወደ አፏ አላስጠጋችም። ምግብ ከማብሰል የሚያግዳት ግን አልሆነም። ሎሬታ የምትሠራው ምግብ ጨው ይብዛው ይነሰው መቅመስ ባትችልም በኢንስታግራም መድረክ በርካታ ወዳጆች አፍርታለች። ሎሬታ ቀቅላ የጠበሰችውን ድንች በሹካ እየፈረካከሰች እንፋሎቱን ትምጋለች። ሎሬታና እናቷ ጁሊ ይህን ማዕድ በጥንቃቄ ያበሰሉት ምናልባትም ይህ የመጨረሻዋ ይሆናል ብለው አስበው ነው። በደቂቃዎች ውስጥ አንድ ከበድ ያለ ስቃይ ሆዷን እየቦረቦረ እንደሚገባ ታውቀዋለች። ይህን ለምዳዋለች። እህልና ፈሳሽ ወደ አፏ ሄዱ ማለት ስቃይ ነው ትርፉ። ነገር ግን የመጣው ይምጣ ብላ ስቃይዋን ተቀብላ በቤተሰቦቿ ኩችና ወንበር ላይ ትውላለች። ኩችናው ማብሰል የተማረችበት አስኳላ ነው። "ከእናቴና እህቴ ጋር አንድ አፍታ ቁጭ ብሎ መመገብ የሚሰጠው ደስታ ለየት ያለ ነው።" ጊዜው በፈረንጆቹ 2015 ነበር። የ23 ዓመቷ ሎሬታ ለዓመታት በፈሳሽ መልክ በሚሰጣት ምግብ ነው የምትንቀሳቀሰው። ቤተሰቦቿ ለእራት ጠረጴዛ ሲከቡ እሷ ተለይታ ክፍሏ ውስጥ ከመቀመጥ ያለፈ ዕጣ አልነበራትም። በነጭ ሽንኩርትና ሎሚ ያበደውን የዶሮ ሥጋ አንስቶ መግመጥ ይቅርና ቢላና ሹካ ማንሳት ራሱ ብርቅ ነው የሚሆንባት። ነገር ግን ይኸው ዛሬ አንድ ጊዜ እንኳ ከቀረበላት ማዕድ ላይ ምግብ አንስታ እንድትበላ ሆነች። ይህን ያደረገው አንድ ባለሙያ ነው። ባለሙያው ሎሬታ ለምን ምግብ ስትበላ እንደሚያማት፣ ለምንስ ሽንት ቤት መጎብኘት እንደማትችል ለመመርመር ነው ዕቅዱ። ሎሬታ የዚያን ቀን ጠዋት ለንደን ወደ ሚገኘው ቅዱስ ማርቆስ ሆስፒታል አቅንታ በአፍንጫዋ ወደታች በተላከ አንድ ቀጭን ቱቦ የትንሹ አንጀቷን ጤንነት ተመርምራ መጥታለች። ሎሬታ ጨቅላ ሳለች በቴሌቪዥን መስኮት የሚታዩ የምግብ ዝግጅት ቅንብሮችን አስመስላ ለቤተሰቦቿ ታቀርብ ነበር። ምግብ ማብሰል መክሊቷ ነው ብንል ማጋነን አይሆንም። የ11 ዓመት ታዳጊ ሳለች ዘወትር ማክሰኞ እናቷ ከሥራ አምሽታ እንደምትመጣ ስለምታውቅ እራት አሰናድታ ትጠብቃት ነበር። እናቷ ጁሊ እንደምትለው ሎሬታ ማብሰል የጀመረችው በቲማቲም ስልስ የተቀመመ ፓስታ በመሥራት ነው። ነገር ግን ትንሽ ቆይታ ከበድ ያሉ ምግቦችን ማሰናዳት ተያያዘችው። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን እየተከታተለች ሳለ የምግብ ማብሰል ውድድር ላይ ተሳትፋ አሸንፋለች። ከትምህርት ቤት አልፋ በሌሎች ውድድሮች ላይ ታላላቆቹን ሳይቀር ረትታ ዋንጫ ይዛ መጥታለች። "የሎሬታ ትልቁ ብቃቷ ኩችና ውስጥ ባለው ነገር የሆነ ምግብ መሥራት መቻሏ ነው" ትላለች እናቷ ጁሊ። 15 ዓመት ሲሞላት የምግብ መብላት መመሰቃቀል የሚያስከትለው 'ኢቲንግ ዲስኦርደር' የተሰኘው በሽታ አገኛት። ነገር ግን እሷ እንደምትለው በሽታው ከአንድ ዓመት በላይ አልቆየም። ቢሆንም በታዳጊነት ዘመኗ የምግብ አለመፈጨት በጣም ያስቸግራት እንደነበር ታስውሳለች። ይህ ምግብ በበላች ቁጥር የሚጎረብጣት ስሜት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ መጣ። የሆነ ሆኖ ይህን ስሜት እየታገለች ምግብ ማብሰሏንና መመገቧን ቀጠለች። ሎሬታ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን እንደጨረሰች ለንደን ውስጥ ያለ አንድ ትልቅ የምግብ ዝግጅት ጥበብ ኮሌጅን ተቀላቀለች። ነገር ግን የሦስቱን ዓመት ኮርስ መማር የቻለችው ለአንድ ዓመት ብቻ ነው። ለዚህ ተጠያቂው ደግሞ የጤናዋ ሁኔታ ነበር። በ19 ዓመቷ ትምህርቷን አቋርጣ፣ ከምትወደው ኩችና ተነጥላ አልጋዋ ላይ ስቃይዋን እያስታመመች መኖር ሆነ ሥራዋ። በሽታው ሥጋዋን መጦ ከሰውነት ተራ እንድትወጣ አደረጋት። አልፎም የአእምሮ ጤናዋ ተቃወሰ። ሎሬታ በአንድ ወቅት ክብደቷ ሲለካ መመዘኛው ላይ የሚታየውን ብዙዎች ማመን አልቻሉም። 25 ኪሎ ይላል። ይህ ደግሞ ለሕይወቷ ጭምር አስጊ እንደሆነ ዶክተሯ በተደጋጋሚ አስጠንቅቀዋል። ምንም እንኳ ስቃዩ ለጠላቷ የማትመኘው ቢሆንም እየቻለችውን መመገብና ክብደቷን ማስተካከል እንዳለባት አመነች። ሎሬታ የአመጋገብ መመሰቃቀል ያመጣባትን ጫና ተከትሎ የአእምሮ ጤናዋም ይዳከም ጀመር። በርካታ ጊዜ ራሷን ለማጥፋት ሙከራ እንዳደረገች ትናገራለች። እርዳታ እንድታገኝ የተላከችበት ካምፕ ውስጥ ስድስት ጊዜ መመገብ ግዴታ ነው። ሦስት ጊዜ ዳጎስ ያለ ምግብ፤ ሦስቱን ደግሞ ብስኩት የመሳሰሉ ቀለል ያሉ ምግቦችን መብላት ግድ ነበር። ታማሚዎች የቀረበላቸውን ምግብ በተመደበላቸው ደቂቃ የመጨረስ ግዴታ አለባቸው። ሎሬታ ግን ብዙ ጊዜ ራሷን የምታገኘው ምግቡ ላይ ስታፈጥ ምግቡም ሲያፈጥባት ነው። እሷ ማዕዷን ሳታገባድ ማንም ሰው ከጠረጴዛው ላይ እንዲነሳ አይፈቀድለትም። በዚህ ምክንያት ብዙዎቹ ታማሚዎች ቂም ይቋጥሩባታል። ሁሉም ታካሚዎች ምግብ ከበሉ በኋላ ለአንድ ሰዓት ያክል ቁጥጥር ይደርግላቸዋል። ምክንያቱ ደግሞ ዞር ብለው ጣታቸውን ከተው እንዳያወጡት በሚል ነው። ከዓመታት ምርምርና ጥናት በኋላ የሎሬታ ሆድ ዕቃ በግማሽ ከጥቅም ውጭ እንደሆነ ተደረሰበት። በሽታው በዘር የሚመጣ እንደሆነም ሐኪሞች አወቁበት። ሎሬታ እንድትበላ ማስገደድ ምንም ዋጋ እንደሌለው የተደረሰበት ይሄኔ ነው። ሎሬታ ከምግብ አለመብላት ጋር ከባድ የራስ ምታት፣ ድካምና የልብ በፍጥነት መምታት ያጋጥሟት ነበር። ይህ በሽታ እስኪደረስበት ድረስ ከ10 እስከ 14 ዓመት ድረስ ሊወስድበት እንደሚችል ዶክተር አላን ሐኪም ይናገራሉ። ሎሬታ ምግብ በአፏ ከዞረ ስድስት ዓመታት አልፈዋል። ከዚህ በኋላ ድጋሚ እህልም ሆነ ፈሳሽ ወደ አፏ እንደማታስገባ ታውቀዋለች። አሁን ምግብ የምታገኘው በቀን ለ18 ሰዓታት አንጠልጥላ በምትዞረው ቱቦ አማካይነት ነው። ቱቦው በደረቷ በኩል ገብቶ ወደ ደም ዝውውሯ በፈሳሽ መልክ ምግብ ያሰራጫል። ሎሬታ ይህን ሁሉ አልፋ፤ አሁን ምግብ ለማብሰል ያላትን ፍቅር የማትበላውን ኧረ እንደውም የማትቀምሰውን ማዕድ በማሰናዳት እየተወጣች ነው። የምትሠራውን ምግብ የማትቀምስ አብሳይ መሆኗ በኢንስታግራም ተጠቃሚዎች ዘንድ ታዋቂነትን አትርፎላታል። ሁሌም ከጎኗ የሆኑት እናቷና እህቷ እንዲሁም አብራት የምትኖረው ባልንጀራዋ የሎሬታን ጣት የሚያስቆረጥሙ ምግቦች በፍቅር ይጎርሳሉ። ሎሬታ ግን ሕይወቷን በቱቦ በሚተላለፍ ምግብ ትገፋለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-56795578 |
0business
| በዘይት እጦት እየተንገፈገፉ ያሉት አልጄሪያውያን | በሰሜናዊቷ አፍሪካ አገር አልጄሪያ የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ሲሆን ለዚህም የአንበሳ ድርሻውን የያዘው በአገሪቱ የተከሰተው የዘይት እጥረት ነው። በገበያ ውስጥ ያለው ዘይትና እና ወተት ምርቶች በጣም አናሳ በመሆኑ ምክንያት ሸማቾች በመደብሮች ውስጥ በሚገበዩበት ወቅት ነጋዴዎችን መለማመጥ እንዲሁም ማሞካሸት ይጠበቅባቸዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት ተጥለው የነበሩ መመሪያዎች እንዲሁም በቅርቡ የተከሰተው የዩክሬን ጦርነት ተደማምሮ እጥረቱን ያባባሰው ሲሆን ለሸማቾችም ህይወትን ፈታኝ አድርጓታል። "መድኃኒት የመግዛት አይነት ስሜት አለው" ትላለች የ31 አመቷ ሳሚሃ ሳመር በንዴትና በምጸት በተቀላቀለው ድምጸት። ለቤተሰቦቿና ጓደኞቿ ኬክ መስራት ትወድ የነበረችው ሳሚሃ በዚህም ገቢም ታገኝ ነበር በአሁኑ ወቅት ግን ለኬክ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ማግኘት አልቻለችም። "ከየትኛውም መደብር ዘይት ለመግዛት የሱቁ ባለቤት ጋር ወዳጅነት ወይም ትውውቅ መኖር አለበት" በማለት ሁኔታውን ታስረዳለች። የግብይይት ሁኔታውም የሚከናወነው ሚስጥራዊ በሆነ ሁኔታ ነው። ዘይት እንደማንኛውም እቃ መደብሩ መደርደሪያ ፊት ለፊት ላይ አይታይም፤ ሻጮች መደብሮች ውስጥ ደብቀው ነው የሚያስቀምጡት። እንደ በርካታ አልጄሪያውያን የኮሮናቫይረስ መመሪያዎች ከፍተኛ ጫና ሲያደርሱና በርካታ ነገሮችን ሲቀይሩ የተመለከተችው ባለፈው ዓመት ነበር። የሙስሊሞች ረመዳን ፆም ሊጀምር በተቃረበበት በአሁኑ ወቅትና ቅዱስ ወር ተብሎ በሚጠራው በዚህ ወር ለሚሰሩ የተለያዩ ዓይነት ምግቦች ግብዓት የሚሆነውን ዘይት ለመሸመት ነዋሪዎች ፍለጋቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። ሳሚሃ አንዳንድ ጊዜ ፍራፍሬ እና አትክልቶችን ለመግዛትም ከምትኖርበት ከተማ ቢልዳ ረከስ ወዳለባትና ወደ አቅራቢያዋ ወደምትገኘው ኮሊያ ሄዳ መሸመት ይኖርባታል። ሌሎች የምግብ ሸቀጦችም እንዲሁ ዋጋቸው ንሯል። ለምሳሌ ድንችን ብንወስድ ከጥቂት ወራት በፊት ከነበረው ከ30 በመቶ በበለጠ አሻቅቧል። ወተት ለመግዛት ነዋሪዎች ጸሃይ ከመውጣቷ በፊት ወደ መደብሮች በማቅናት ረጅም ወረፋ መጠበቅ ይኖርባቸዋል። "ወተት ለማግኘት የተሰለፉ ሰዎችን መግፋት አንዳንዴም መጣላት ስለሚያጋጥም አሁን አቁሜያለሁ" በማለት የአስተዳደሩ ጸሃፊ ይናገራሉ። "በጣም የሚያዋርድ ተግባር ነው " የሚሉት ጸሃፊዋ እነዚህን ሰልፎች መራቅ ግን ዋጋ አስከፍሏቸዋል። ከህዝብ ጋር እየተገፋፉና ረጅም ወረፋ መጠበቅንም በመተው ከውጭ አገር ለሚገባ አንድ ኪሎ የዱቄት ወተት 2.90 ዶላር አካባቢ መክፈል ይጠበቅባቸዋል። በመንግሥት ድጎማ የሚደረግለት ወተት ዋጋ 17 ሳንቲም ዶላር ነው። አልጄሪያ ወተት ብታመርትም ነገር ግን መጠኑ በጣም አናሳ ነው። ለዓመታትም ከፈረንሳይ፣ ከሌሎች የአውሮፓ ህብረት ሃገራት እንዲሁም በቅርብ ጊዜ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሚመጣ ወተት ጥገኛ ናት። የሚገባው ወተት በዱቄት መልክ ሲሆን ለሸማቾች ከመድረሱ በፊት ፋብሪካዎች ወደ ፈሳሽነት ይቀይሩታል። ወተት እጥረት ቢኖርም በርካታ አልጄሪያውያንን እያስጨነቀ ያለው የዘይት ዋጋ መናር ነው። እንደ ወተት ዘይትም ቢሆን በመንግሥት ድጎማ ቢደረግለትም በቅርቡ ከተከሰተው ቀውስ በፊትም ቢሆን ውድ ነበር። በዚያን ጊዜም የአምስት ሊትር ዘይት ዋጋ 4.20 ዶላር ወይም 216 ብር ነበር። የአልጄሪያውያን ወርሃዊ ደመወዝ በአማካይ በግሉ ዘርፍ 240 ዶላር እንዲሁም የመንግሥት ሰራተኞች ደግሞ 410 ዶላር ሲሆን ባለስልጣናቱም በናረው የሸቀጥ ዋጋ ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ጫና ቢፈጠርባቸው ብዙም አያስገርምም። በአገሪቷ ኢኮኖሚ ሳቢያ ምግብ ማከማቸት እንዲሁም ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ ማንሰራራቱን የፓርላማው ኮሚቴ በሪፖርቱ ይፋ አድርጓል። በፓርላማው የተመረጠው ኮሚቴ አባል የሆኑት ሂሻም ሳፋር ለቢቢሲ እንደተናገሩት የዘይት ነጋዴዎች ከመንግሥት ተጨማሪ ገንዘብን ለመጠየቅ በሚል ድጎማ የተደረገለት ዘይት ላይ ሰው ሰራሽ የሆነ የዋጋ ንረት እየፈጠሩ ይገኛሉ። ባለፈው ዓመት ወደ 150 ሺህ የሚጠጉ ጥሰቶች ለባለስልጣናቱ ሪፖርት የተደረጉ ሲሆን አብዛኞች ፍርድ ቤት ቀርበዋል እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ የንግድ ፈቃዶች ተነጥቀዋል። ከዚህም ጋር በተያያዘ በአገሪቷ ድጎማ የተደረገላቸው ሸቀጦች በደቡባዊ ድንበር አቋርጦ በጎረቤት ሃገራት በህገወጥ መንገዶች እየተሸጡ ይገኛሉ። ይህም መጠነ ሰፊ እንደሆነ የፓርላማ ኮሚሽኑ መጠነ ሰፊ እንደሆነም አመልክቷል። ምንም እንኳን ይፋ የሆነ አሃዝ ባይኖርም ምንጮች ለቢቢሲ እንደተናገሩት 12 የሚሆን የጭነት መኪና ዘይት ወደ ማሊና ኒጀር በድብቅ ይወሰዳል። ህገወጥ ነጋዴዎቹ በመንግሥት ድጎማ የተደረገለትን ዘይት በመቸብቸብ በአንድ ጭነት መኪና እስከ 17 ሺህ 800 ዶላር ትርፍ እንደሚያገኙም ምንጮቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔ ከውጭ የመጡ ምርቶች ወይም ግብዓታቸው ከውጭ የመጣ እንደ ዘይት፣ ስኳር፣ ፓስታ፣ ሰሞሊና እና የስንዴ ምርቶች ወደ ውጭ እንዳይላኩ አግደዋል። ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ፕሬዚዳንቱ መሰል ድርጊቶች ሆን ብሎ የአገሪቱ ምጣኔን ሆን ብሎ ለማደናቀፍ የተሸረበ ሴራ ስለሆነ ከፍተኛ ቅጣት እንዲጣልባቸው ይፈልጋሉ። ነገር ግን በአልጄሪያ ለተነሳው ቀውስ ጥልቅ መንስኤዎችን ለማወቅ ወደ ኋላ መለስ ብሎ መመልከት እንደሚያስፈልግ ባለሙያዎች ይናገራሉ። "አገሪቷ በማፍያ ተዘርፋለች" የአገሪቷ ምጣኔ ኃብት መሰረቱ ጋዝ እና ድፍድፍ ነዳጅ መሆኑ እንዲሁም የመንግሥት ገቢ ምንጭም በነዚህ ምርቶች ላይ ጥገኛ መሆኑ በርካታ ችግሮችን ፈጥሯል ይላሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አብዳል ራህማን ሀዴፍ። በዘርፉ ላይ የሚደረጉ ስምምነቶች መልካም አስተዳደር ጉድለት የሚታዩበትና ከፍተኛ ገንዘብ የሚወጣባቸው መሆናቸውንም አብዳል ይናገራሉ። የኢኮኖሚው ችግር ወደ ከፋ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ሊያመራ ይችላል የሚል ስጋትም ፈጥሯል። የዋጋ ንረቱ "በህዝቡ እና በአስተደዳሩ መካከከል መካከል ያለው ደካማ ግንኙነት ሊፈርስ የሚችልበት ደረጃ ላይ ሊያደርሰው ይችላል፣ ይህም በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ቅሬታን ይፈጥራል" ሲሉ የሶሺዮሎጂ ባለሙያ ፕሮፌሰር ራቺድ ሃማዶቼ ያስጠነቅቃሉ። የቀድሞው ፕሬዝዳንት አብደላዚዝ ቡተፍሊካ በአውሮፓውያኑ 2019 የተነሳውን ሰፊ ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ተገደዋል። ተተኪው ፕሬዚዳንት በአንድ ወቅት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ቅርብ አጋር የነበሩ ሲሆን በቡተፍሊካ መሪነት "የሀገሪቱን ካዝና የዘረፈውን ማፍያ" ደጋግመው ሲያወግዙም ተዘሰምቷል። የፕሬዝዳንቱ ለውጥ ቢኖርም በርካታ ወጣቶች ለውጥ ባለመኖሩ ቅር እንደተሰኙ ነው ከዚህም ጋር ተያይዞ የኮሮናቫይረስ ወረረርሽኝ እስከተከሰተበት ድረስ በርካታ የአደባባይ ተቃውሞዎች አድርገዋል። የአገሪቱ ሶስት አራተኛ ህዝብ ከ37 አመት በታች ነው፣ ስራ አጥነት 11 በመቶ ደርሷል፤ ይባስ ብሎ በርካታ ስራ አጦች የዩኒቨርስቲ ምሩቃን ናቸው። መንግሥት የህዝቡን እሮሮ በጊዜያዊነት ለማስታገስ በሚመስል መልኩ በንቃት ስራ እየፈለጉ መሆናቸውን ማረጋገጥ የሚችሉ ስራ አጥ ዜጎች 90 ዶላር የሚጠጋ ወርሃዊ አበል እንደሚሰጣቸው ተናግሯል። በዩክሬን ጦርነት ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታየው የነዳጅ ዋጋ መጨመር ሁኔታውን ቀለል የሚያደርግላቸው ሲሆን ለባለሥልጣናቱ ይህንን ገንዘብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመክፈል ያስችላቸዋል ተብሏል። ነገር ግን አልጄሪያ በዚህ አጋጣሚ የተገኘው የነዳጅ ገቢን ማባከን እንደማትችል የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች አጥብቀው ይከራከራሉ ። አሁን ግን እንደ ሳመር ያሉ ሸማቾች በአሁኑ ወቅት ወዳጅ የሚሆናቸውም ባለመደብርና የተደበቀ ዘይት ላይ ተስፋቸውን ጥለዋል። | በዘይት እጦት እየተንገፈገፉ ያሉት አልጄሪያውያን በሰሜናዊቷ አፍሪካ አገር አልጄሪያ የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ሲሆን ለዚህም የአንበሳ ድርሻውን የያዘው በአገሪቱ የተከሰተው የዘይት እጥረት ነው። በገበያ ውስጥ ያለው ዘይትና እና ወተት ምርቶች በጣም አናሳ በመሆኑ ምክንያት ሸማቾች በመደብሮች ውስጥ በሚገበዩበት ወቅት ነጋዴዎችን መለማመጥ እንዲሁም ማሞካሸት ይጠበቅባቸዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት ተጥለው የነበሩ መመሪያዎች እንዲሁም በቅርቡ የተከሰተው የዩክሬን ጦርነት ተደማምሮ እጥረቱን ያባባሰው ሲሆን ለሸማቾችም ህይወትን ፈታኝ አድርጓታል። "መድኃኒት የመግዛት አይነት ስሜት አለው" ትላለች የ31 አመቷ ሳሚሃ ሳመር በንዴትና በምጸት በተቀላቀለው ድምጸት። ለቤተሰቦቿና ጓደኞቿ ኬክ መስራት ትወድ የነበረችው ሳሚሃ በዚህም ገቢም ታገኝ ነበር በአሁኑ ወቅት ግን ለኬክ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ማግኘት አልቻለችም። "ከየትኛውም መደብር ዘይት ለመግዛት የሱቁ ባለቤት ጋር ወዳጅነት ወይም ትውውቅ መኖር አለበት" በማለት ሁኔታውን ታስረዳለች። የግብይይት ሁኔታውም የሚከናወነው ሚስጥራዊ በሆነ ሁኔታ ነው። ዘይት እንደማንኛውም እቃ መደብሩ መደርደሪያ ፊት ለፊት ላይ አይታይም፤ ሻጮች መደብሮች ውስጥ ደብቀው ነው የሚያስቀምጡት። እንደ በርካታ አልጄሪያውያን የኮሮናቫይረስ መመሪያዎች ከፍተኛ ጫና ሲያደርሱና በርካታ ነገሮችን ሲቀይሩ የተመለከተችው ባለፈው ዓመት ነበር። የሙስሊሞች ረመዳን ፆም ሊጀምር በተቃረበበት በአሁኑ ወቅትና ቅዱስ ወር ተብሎ በሚጠራው በዚህ ወር ለሚሰሩ የተለያዩ ዓይነት ምግቦች ግብዓት የሚሆነውን ዘይት ለመሸመት ነዋሪዎች ፍለጋቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። ሳሚሃ አንዳንድ ጊዜ ፍራፍሬ እና አትክልቶችን ለመግዛትም ከምትኖርበት ከተማ ቢልዳ ረከስ ወዳለባትና ወደ አቅራቢያዋ ወደምትገኘው ኮሊያ ሄዳ መሸመት ይኖርባታል። ሌሎች የምግብ ሸቀጦችም እንዲሁ ዋጋቸው ንሯል። ለምሳሌ ድንችን ብንወስድ ከጥቂት ወራት በፊት ከነበረው ከ30 በመቶ በበለጠ አሻቅቧል። ወተት ለመግዛት ነዋሪዎች ጸሃይ ከመውጣቷ በፊት ወደ መደብሮች በማቅናት ረጅም ወረፋ መጠበቅ ይኖርባቸዋል። "ወተት ለማግኘት የተሰለፉ ሰዎችን መግፋት አንዳንዴም መጣላት ስለሚያጋጥም አሁን አቁሜያለሁ" በማለት የአስተዳደሩ ጸሃፊ ይናገራሉ። "በጣም የሚያዋርድ ተግባር ነው " የሚሉት ጸሃፊዋ እነዚህን ሰልፎች መራቅ ግን ዋጋ አስከፍሏቸዋል። ከህዝብ ጋር እየተገፋፉና ረጅም ወረፋ መጠበቅንም በመተው ከውጭ አገር ለሚገባ አንድ ኪሎ የዱቄት ወተት 2.90 ዶላር አካባቢ መክፈል ይጠበቅባቸዋል። በመንግሥት ድጎማ የሚደረግለት ወተት ዋጋ 17 ሳንቲም ዶላር ነው። አልጄሪያ ወተት ብታመርትም ነገር ግን መጠኑ በጣም አናሳ ነው። ለዓመታትም ከፈረንሳይ፣ ከሌሎች የአውሮፓ ህብረት ሃገራት እንዲሁም በቅርብ ጊዜ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሚመጣ ወተት ጥገኛ ናት። የሚገባው ወተት በዱቄት መልክ ሲሆን ለሸማቾች ከመድረሱ በፊት ፋብሪካዎች ወደ ፈሳሽነት ይቀይሩታል። ወተት እጥረት ቢኖርም በርካታ አልጄሪያውያንን እያስጨነቀ ያለው የዘይት ዋጋ መናር ነው። እንደ ወተት ዘይትም ቢሆን በመንግሥት ድጎማ ቢደረግለትም በቅርቡ ከተከሰተው ቀውስ በፊትም ቢሆን ውድ ነበር። በዚያን ጊዜም የአምስት ሊትር ዘይት ዋጋ 4.20 ዶላር ወይም 216 ብር ነበር። የአልጄሪያውያን ወርሃዊ ደመወዝ በአማካይ በግሉ ዘርፍ 240 ዶላር እንዲሁም የመንግሥት ሰራተኞች ደግሞ 410 ዶላር ሲሆን ባለስልጣናቱም በናረው የሸቀጥ ዋጋ ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ጫና ቢፈጠርባቸው ብዙም አያስገርምም። በአገሪቷ ኢኮኖሚ ሳቢያ ምግብ ማከማቸት እንዲሁም ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ ማንሰራራቱን የፓርላማው ኮሚቴ በሪፖርቱ ይፋ አድርጓል። በፓርላማው የተመረጠው ኮሚቴ አባል የሆኑት ሂሻም ሳፋር ለቢቢሲ እንደተናገሩት የዘይት ነጋዴዎች ከመንግሥት ተጨማሪ ገንዘብን ለመጠየቅ በሚል ድጎማ የተደረገለት ዘይት ላይ ሰው ሰራሽ የሆነ የዋጋ ንረት እየፈጠሩ ይገኛሉ። ባለፈው ዓመት ወደ 150 ሺህ የሚጠጉ ጥሰቶች ለባለስልጣናቱ ሪፖርት የተደረጉ ሲሆን አብዛኞች ፍርድ ቤት ቀርበዋል እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ የንግድ ፈቃዶች ተነጥቀዋል። ከዚህም ጋር በተያያዘ በአገሪቷ ድጎማ የተደረገላቸው ሸቀጦች በደቡባዊ ድንበር አቋርጦ በጎረቤት ሃገራት በህገወጥ መንገዶች እየተሸጡ ይገኛሉ። ይህም መጠነ ሰፊ እንደሆነ የፓርላማ ኮሚሽኑ መጠነ ሰፊ እንደሆነም አመልክቷል። ምንም እንኳን ይፋ የሆነ አሃዝ ባይኖርም ምንጮች ለቢቢሲ እንደተናገሩት 12 የሚሆን የጭነት መኪና ዘይት ወደ ማሊና ኒጀር በድብቅ ይወሰዳል። ህገወጥ ነጋዴዎቹ በመንግሥት ድጎማ የተደረገለትን ዘይት በመቸብቸብ በአንድ ጭነት መኪና እስከ 17 ሺህ 800 ዶላር ትርፍ እንደሚያገኙም ምንጮቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔ ከውጭ የመጡ ምርቶች ወይም ግብዓታቸው ከውጭ የመጣ እንደ ዘይት፣ ስኳር፣ ፓስታ፣ ሰሞሊና እና የስንዴ ምርቶች ወደ ውጭ እንዳይላኩ አግደዋል። ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ፕሬዚዳንቱ መሰል ድርጊቶች ሆን ብሎ የአገሪቱ ምጣኔን ሆን ብሎ ለማደናቀፍ የተሸረበ ሴራ ስለሆነ ከፍተኛ ቅጣት እንዲጣልባቸው ይፈልጋሉ። ነገር ግን በአልጄሪያ ለተነሳው ቀውስ ጥልቅ መንስኤዎችን ለማወቅ ወደ ኋላ መለስ ብሎ መመልከት እንደሚያስፈልግ ባለሙያዎች ይናገራሉ። "አገሪቷ በማፍያ ተዘርፋለች" የአገሪቷ ምጣኔ ኃብት መሰረቱ ጋዝ እና ድፍድፍ ነዳጅ መሆኑ እንዲሁም የመንግሥት ገቢ ምንጭም በነዚህ ምርቶች ላይ ጥገኛ መሆኑ በርካታ ችግሮችን ፈጥሯል ይላሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አብዳል ራህማን ሀዴፍ። በዘርፉ ላይ የሚደረጉ ስምምነቶች መልካም አስተዳደር ጉድለት የሚታዩበትና ከፍተኛ ገንዘብ የሚወጣባቸው መሆናቸውንም አብዳል ይናገራሉ። የኢኮኖሚው ችግር ወደ ከፋ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ሊያመራ ይችላል የሚል ስጋትም ፈጥሯል። የዋጋ ንረቱ "በህዝቡ እና በአስተደዳሩ መካከከል መካከል ያለው ደካማ ግንኙነት ሊፈርስ የሚችልበት ደረጃ ላይ ሊያደርሰው ይችላል፣ ይህም በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ቅሬታን ይፈጥራል" ሲሉ የሶሺዮሎጂ ባለሙያ ፕሮፌሰር ራቺድ ሃማዶቼ ያስጠነቅቃሉ። የቀድሞው ፕሬዝዳንት አብደላዚዝ ቡተፍሊካ በአውሮፓውያኑ 2019 የተነሳውን ሰፊ ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ተገደዋል። ተተኪው ፕሬዚዳንት በአንድ ወቅት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ቅርብ አጋር የነበሩ ሲሆን በቡተፍሊካ መሪነት "የሀገሪቱን ካዝና የዘረፈውን ማፍያ" ደጋግመው ሲያወግዙም ተዘሰምቷል። የፕሬዝዳንቱ ለውጥ ቢኖርም በርካታ ወጣቶች ለውጥ ባለመኖሩ ቅር እንደተሰኙ ነው ከዚህም ጋር ተያይዞ የኮሮናቫይረስ ወረረርሽኝ እስከተከሰተበት ድረስ በርካታ የአደባባይ ተቃውሞዎች አድርገዋል። የአገሪቱ ሶስት አራተኛ ህዝብ ከ37 አመት በታች ነው፣ ስራ አጥነት 11 በመቶ ደርሷል፤ ይባስ ብሎ በርካታ ስራ አጦች የዩኒቨርስቲ ምሩቃን ናቸው። መንግሥት የህዝቡን እሮሮ በጊዜያዊነት ለማስታገስ በሚመስል መልኩ በንቃት ስራ እየፈለጉ መሆናቸውን ማረጋገጥ የሚችሉ ስራ አጥ ዜጎች 90 ዶላር የሚጠጋ ወርሃዊ አበል እንደሚሰጣቸው ተናግሯል። በዩክሬን ጦርነት ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታየው የነዳጅ ዋጋ መጨመር ሁኔታውን ቀለል የሚያደርግላቸው ሲሆን ለባለሥልጣናቱ ይህንን ገንዘብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመክፈል ያስችላቸዋል ተብሏል። ነገር ግን አልጄሪያ በዚህ አጋጣሚ የተገኘው የነዳጅ ገቢን ማባከን እንደማትችል የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች አጥብቀው ይከራከራሉ ። አሁን ግን እንደ ሳመር ያሉ ሸማቾች በአሁኑ ወቅት ወዳጅ የሚሆናቸውም ባለመደብርና የተደበቀ ዘይት ላይ ተስፋቸውን ጥለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60904242 |
0business
| በርካታ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርሶች በአነስተኛ ዋጋ በበይነ መረብ ላይ ለሽያጭ ቀረቡ | በርካታ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርሶች እንደ ኢቤይ እና አማዞን ባሉ የኢንተርኔት መገበያያ ገጾች ላይ በአነስተኛ ዋጋ ለሽያጭ ቀረቡ። እነዚህ ከኢትዮጵያ የተወሰዱ እንደሆኑ የተገመቱ ቅርሶች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በብዛት በበይነ መረብ የግብይት መድረኮች ርካሽ በሚባል ዋጋ እየተሸጡ እንደሆነ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ይገኛሉ። ከእነዚህ ቅርሶች ውስጥ በርከት የሚሉት "ኢቤይ" በተሰኘው የበይነመረብ ገበያ ላይ እንደቀረቡ መመልከት ይቻላል። ይህ በድንገት በርካታ የኢትዮጵያ ቅርሶች ወደ ገበያ መውጣት ምናልባት በጦርነቱ ወቅት ከትግራይ የተዘረፉ ናቸው የሚለውን ጥርጣሬ አጭሯል። በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀውስን ጦርነት ተከትሎ በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በክርስትና እና እስልምና የሃይማኖት ተቋማት ላይ ጥቃት ስለማድረሳቸው ከዚህ ቀደም ተዘግቧል። በሃይማኖት ተቋማት ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ ጥንታዊ ቅርሶች ስለመዘረፋቸው ተገልጿል። በጉዳዩ ላይ የፌደራል ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣንን ምላሽና ማብራሪያን ለማግኘት ቢቢሲ በተደጋጋሚ ያደረገው የስልክ ጥሪ ባለመነሳቱ ለጊዜው ሳይሳካ ቀርቷል። የቢቢሲ ኒውስዴይ ፕሮግራም በጉዳዩ ዙርያ ያነጋገራቸው የቋንቋ ታሪክ ተመራማሪ እና በሐምቡርግ ዩኒቨርስቲ የድኅረ ዶክትሬት ተማሪ የሆኑት ሐጎስ አብረሃ (ዶ/ር) በጦርነቱ ወቅት "ከበርካታ የትግራይ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናትን ቅርሶች መዘረፋቸውን አረጋግጫለሁ" ይላሉ። ሐጎስ (ዶ/ር) በወቅቱ ከተዘረፉት ቅርሶች አንዳንዶቹ ጥንታዊና እጅግ ብርቅዬ የነበሩ ናቸው ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ተመራማሪው ከኢትዮጵያ የተዘረፉት ቅርሶች በብዛት እየተሸጡ ያሉበት ዋጋ እጅግ ርካሽ የሚባል እንደሆነ ለቢቢሲ ገልጠዋል። በዚህ ወቅት እንዴት ተዘርፈው ከአገር ሊወጡ እንደቻሉ ማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ በሱዳንና ኬንያ በኩል ሊሆን እንደሚችል ግን ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በኢቤይ የበየነመረብ የግብይት መድረክ ላይ ባለፉት ጥቂት ወራት በርካታ ከኢትዮጵያ የሆኑ ጥንታዊ ሃይማኖታዊ ቅርሶችን ለሽያጭ ካቀረቡት ሻጮች መካከል አንዱ ዎርሌይ ኢንተርፕራይስ ኢንተርናሽናል ኤልኤልሲ (Worley Enterprises International LLC) የተሰኘው ሻጭ ይገኝበታል። ይህ ነጋዴ ለሽያጭ ካቀረባቸው የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርጾች መካከል አንዱ ከ15ኛው አስከ 17ኛ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ በእጅ የተጻፈ ሃይማኖታዊ መጽሐፍ ይገኝበታል። ይህ በእንስሳት ቆዳ ላይ በግዕዝ ቋንቋ የተጻፈ ጽሑፍ ጥር 12/2014 ዓ.ም. በ240 የአሜሪካ ዶላር ለገበያ ቀርቧል። ሌላኛው ከ15ኛው አስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን ባሉት ዓመታት በግዕዝ ቋንቋ ሳይጻፍ አይቀርም የተባለለት መጽሐፍ በ1250 የአሜሪካ ዶላር በዚሁ ገጽ አማካይነት ለገበያ ቀርቧል። እንደ ኢቤይ ባሉ የኢንተርኔት ገበያዎች ላይ ግለሰቦች ምዝገባ አድርገው መግለጫ እና ፎቶ በማያያዝ እቃዎችን ለገበያ ያቀርባሉ። ዎርሌይ ኢንተርፕራይስ ኢንተርናሽናል ኤልኤልሲ ያስተዋወቃቸው መነሻቸው ከኢትዮጵያ የሆኑ ቅርሶች "መቶ በመቶ ትክክለኛ" ስለመሆናቸው በመግለጽ፤ ገዢዎች "ይህ መልካም እድል እንዳያመልጣችሁ" በማለት ሰዎች ቅርሶቹን እንዲገዙ ያበረታታል። ይህ ሻጭ ለሽያጭ በሚያቀርባቸው እቃዎች መግለጫ ላይ፤ መሰል ጥንታዊ እቃዎችን ለሽያጭ የሚያቀርበው ሰዎች እቃዎቹን እንዲሸጡለት ከሰጡት በኋላ እንደሆነ ይገልጻል። ከዚህ በተጨማሪም እራሱ በተለያዩ ወቅቶች ከሰበሰባቸው ክምችቶቹ አልያም ከሌሎች ስፍራዎች ገዝቶ ኢቤይ ላይ መልሶ ለሽያጭ እንደሚያቀርብ ያትታል። ለ15 ወራት ያክል የዘለቀው የኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት በእምነት ስፍራዎች ላይ ካደረሰው ጉዳት ባሻገር፣ ከባድ የሚባል ውድመትን እንዲሁም ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስን አስከትሏል። በጦርነቱ ሳቢያ ቁጥራቸው አስካሁን በውል ባይታወቅም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለሞት የተዳረጉ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩት ደግሞ ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገልጿል። በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ውስጥ ተቀስቅሶ ወደ አጎራባቾቹ የአማራና የአፋር ክልሎች የተስፋፋው ጦርነት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትን ለከፋ ረሀብ ያጋለጠ ሲሆን፣ ወደ 10 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችን ሰብዓዊ እርዳታን እንዲጠብቁ መገደዳቸውን ድርጅቱ አመልክቷል። | በርካታ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርሶች በአነስተኛ ዋጋ በበይነ መረብ ላይ ለሽያጭ ቀረቡ በርካታ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርሶች እንደ ኢቤይ እና አማዞን ባሉ የኢንተርኔት መገበያያ ገጾች ላይ በአነስተኛ ዋጋ ለሽያጭ ቀረቡ። እነዚህ ከኢትዮጵያ የተወሰዱ እንደሆኑ የተገመቱ ቅርሶች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በብዛት በበይነ መረብ የግብይት መድረኮች ርካሽ በሚባል ዋጋ እየተሸጡ እንደሆነ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ይገኛሉ። ከእነዚህ ቅርሶች ውስጥ በርከት የሚሉት "ኢቤይ" በተሰኘው የበይነመረብ ገበያ ላይ እንደቀረቡ መመልከት ይቻላል። ይህ በድንገት በርካታ የኢትዮጵያ ቅርሶች ወደ ገበያ መውጣት ምናልባት በጦርነቱ ወቅት ከትግራይ የተዘረፉ ናቸው የሚለውን ጥርጣሬ አጭሯል። በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀውስን ጦርነት ተከትሎ በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በክርስትና እና እስልምና የሃይማኖት ተቋማት ላይ ጥቃት ስለማድረሳቸው ከዚህ ቀደም ተዘግቧል። በሃይማኖት ተቋማት ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ ጥንታዊ ቅርሶች ስለመዘረፋቸው ተገልጿል። በጉዳዩ ላይ የፌደራል ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣንን ምላሽና ማብራሪያን ለማግኘት ቢቢሲ በተደጋጋሚ ያደረገው የስልክ ጥሪ ባለመነሳቱ ለጊዜው ሳይሳካ ቀርቷል። የቢቢሲ ኒውስዴይ ፕሮግራም በጉዳዩ ዙርያ ያነጋገራቸው የቋንቋ ታሪክ ተመራማሪ እና በሐምቡርግ ዩኒቨርስቲ የድኅረ ዶክትሬት ተማሪ የሆኑት ሐጎስ አብረሃ (ዶ/ር) በጦርነቱ ወቅት "ከበርካታ የትግራይ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናትን ቅርሶች መዘረፋቸውን አረጋግጫለሁ" ይላሉ። ሐጎስ (ዶ/ር) በወቅቱ ከተዘረፉት ቅርሶች አንዳንዶቹ ጥንታዊና እጅግ ብርቅዬ የነበሩ ናቸው ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ተመራማሪው ከኢትዮጵያ የተዘረፉት ቅርሶች በብዛት እየተሸጡ ያሉበት ዋጋ እጅግ ርካሽ የሚባል እንደሆነ ለቢቢሲ ገልጠዋል። በዚህ ወቅት እንዴት ተዘርፈው ከአገር ሊወጡ እንደቻሉ ማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ በሱዳንና ኬንያ በኩል ሊሆን እንደሚችል ግን ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በኢቤይ የበየነመረብ የግብይት መድረክ ላይ ባለፉት ጥቂት ወራት በርካታ ከኢትዮጵያ የሆኑ ጥንታዊ ሃይማኖታዊ ቅርሶችን ለሽያጭ ካቀረቡት ሻጮች መካከል አንዱ ዎርሌይ ኢንተርፕራይስ ኢንተርናሽናል ኤልኤልሲ (Worley Enterprises International LLC) የተሰኘው ሻጭ ይገኝበታል። ይህ ነጋዴ ለሽያጭ ካቀረባቸው የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርጾች መካከል አንዱ ከ15ኛው አስከ 17ኛ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ በእጅ የተጻፈ ሃይማኖታዊ መጽሐፍ ይገኝበታል። ይህ በእንስሳት ቆዳ ላይ በግዕዝ ቋንቋ የተጻፈ ጽሑፍ ጥር 12/2014 ዓ.ም. በ240 የአሜሪካ ዶላር ለገበያ ቀርቧል። ሌላኛው ከ15ኛው አስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን ባሉት ዓመታት በግዕዝ ቋንቋ ሳይጻፍ አይቀርም የተባለለት መጽሐፍ በ1250 የአሜሪካ ዶላር በዚሁ ገጽ አማካይነት ለገበያ ቀርቧል። እንደ ኢቤይ ባሉ የኢንተርኔት ገበያዎች ላይ ግለሰቦች ምዝገባ አድርገው መግለጫ እና ፎቶ በማያያዝ እቃዎችን ለገበያ ያቀርባሉ። ዎርሌይ ኢንተርፕራይስ ኢንተርናሽናል ኤልኤልሲ ያስተዋወቃቸው መነሻቸው ከኢትዮጵያ የሆኑ ቅርሶች "መቶ በመቶ ትክክለኛ" ስለመሆናቸው በመግለጽ፤ ገዢዎች "ይህ መልካም እድል እንዳያመልጣችሁ" በማለት ሰዎች ቅርሶቹን እንዲገዙ ያበረታታል። ይህ ሻጭ ለሽያጭ በሚያቀርባቸው እቃዎች መግለጫ ላይ፤ መሰል ጥንታዊ እቃዎችን ለሽያጭ የሚያቀርበው ሰዎች እቃዎቹን እንዲሸጡለት ከሰጡት በኋላ እንደሆነ ይገልጻል። ከዚህ በተጨማሪም እራሱ በተለያዩ ወቅቶች ከሰበሰባቸው ክምችቶቹ አልያም ከሌሎች ስፍራዎች ገዝቶ ኢቤይ ላይ መልሶ ለሽያጭ እንደሚያቀርብ ያትታል። ለ15 ወራት ያክል የዘለቀው የኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት በእምነት ስፍራዎች ላይ ካደረሰው ጉዳት ባሻገር፣ ከባድ የሚባል ውድመትን እንዲሁም ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስን አስከትሏል። በጦርነቱ ሳቢያ ቁጥራቸው አስካሁን በውል ባይታወቅም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለሞት የተዳረጉ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩት ደግሞ ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገልጿል። በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ውስጥ ተቀስቅሶ ወደ አጎራባቾቹ የአማራና የአፋር ክልሎች የተስፋፋው ጦርነት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትን ለከፋ ረሀብ ያጋለጠ ሲሆን፣ ወደ 10 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችን ሰብዓዊ እርዳታን እንዲጠብቁ መገደዳቸውን ድርጅቱ አመልክቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60335006 |
3politics
| መንግሥትና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጦርነቱን አቁመው ልዩነታቸውን በድርድር እንዲፈቱ ኦፌኮ ጠየቀ | በኢትዮጵያ መንግሥትና በአሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት እንዲቆምና ልዩነታቸውን በድርድር እንዲፈቱ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ጥሪ አቀረበ። በሁለቱ አካላት መካከል ያለው ግጭት መንስዔው "ፖለቲካዊ ነው ያለው" ኦፌኮ መፍትሄውም "ፖለቲካዊ" መሆን እንዳለበትም በትናንትናው ዕለት ሚያዝያ 3፣ 2014 ዓ.ም የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የኦሮሚያ ክልል ከቀናት በፊት "አሸባሪ" ብሎ የጠራውን የ"ሸኔን ኃይል" ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ የሚያስችል ጠንካራ ዘመቻ ተጀምሯል ብሏል። በመንግሥት ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኑ መካከል ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ቃለ አቀባይ ኦዳ ተርቢ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። በአሁኑ ወቅት ጦርነቱ ከመፋፋሙና እንደ አዲስ ዘመቻ ከመጀመሩ ጋርም ተያይዞ ኦፌኮ ይህ ሁኔታ የኦሮሚያን ክልልን እንዲሁም አገሪቱን ለተጨማሪ አደጋ የሚዳርግ መሆኑንም አፅንኦት ሰጥቷል። "መንግሥት ሰሞኑን በአዲስ መልኩ ያወጀው ዘመቻ በጥቂቱ ፈንጥቆ የነበረውን የሰላም ጭላንጭል መልሶ የሚያደበዝዝ፤ኦሮሚያና አገሪቱን ለተጨማሪ አደጋ የሚያጋልጥ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ እንደማያስገኝ ደጋግመን ማሳሰብ እንፈልጋለን። " ብሏል ከሰሞኑ የኦሮሚያ ክልል የፌደራል ኃይሎች እና የክልል ኃይሎች በቅንጅት በወለጋ፣ በጉጂ፣ በምዕራብ እና ሰሜን ሸዋ በሚንቀሳቀሱ የታጣቂዎቹ አባላት ላይ እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸውን ገልጿል። መግለጫው መንግሥት "ሸኔን" እደመስሳለሁ የሚለውን ሁኔታውን አቁሞ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እንደተጀመረው የሰላም አካሄድ እንዲከተልም ጥሪ አቅርቧል። "መንግስት 'ሸኔን ማጥፋት' ከሚለው ውጤት አልባ የዘመቻ አዙሪት ወጥቶ በሰሜኑ ያገራችን ክፍል እንደጀመረው ሁሉ በኦሮሚያ ክልል ያለውን አለመግባባትም ተመሳሳይ በሆነ ሰላማዊ አካሄድ እንዲፈታ በድጋሜ ጥሪ እናደርጋለን፡፡" በማለት አስፍሯል። ስራ አስፈፃሚው ኮሚቴ ሚያዝያ 1፣ 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በተጨማሪ ያነሳው ሃሳብ ከአማራ ክልል የመጡ ያላቸው ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል እየፈጠሩት ያለውን የጸጥታ ችግር አስመልክቶ ነው። እነዚህ ታጣቂዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል በመግባት " የመሬት ወረራና የግዛት ማስፋፋት እየፈጸሙ እንዲሁም ሰላማዊ ሰዎችን እየገደሉ፣ አርሷአደሮችን ከመሬታቸው በማፈናቀል የኦሮሚያ ክልልን ወደማያባራ የግጭት ቀጠና እየለወጡት ነው" ብሏል። "የጦር ዘመቻና የመሬት ወራራ" እየተፈጸመ እንደሆነ ያሰፈረው ይህ መግለጫ ይህም ሁኔታ በምስራቅ ወለጋ፤ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፤ሰሜን ሸዋ፤ ምዕራብ ሸዋና በምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ በተቀናጀ አኳኋን እየተካሔደ እንደሆነ መረዳቱንም ጠቅሷል። ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በተጨማሪ አገሪቱ የተፈጠረው የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነትን አንስቶ በመወያየት መንስዔውም የርስ በርስ ጦርነቱ እንደሆነና መፍትሄው "ሀገሪቱን በሁሉም አቅጣጫ እያመሰ ያለውን የርስ በርስ ጦርነት ወደሚያስቆም ውይይትና ድርድር ፊትን ማዞር ብቻ ነው" ብሏል። ጦርነቱ የውስጥና የውጪ ንግድ እንዲቀዛቀዝ፣ የግብርናና ፋብሪካዎች ምርታማነት እንዲቀንስ፣ የውጪ ኢንቨስትመንት እንዲዳከም እንዲሁም በማዕቀቡ ምክንያት በእርዳታና በብድር ወደ አገር ይገባ የነበረ ገንዘብ እንዲቀንስ ወይም እንዲቋረጥ በማድረጉ የአገሪቱ ምጣኔ ኃብት ላይ ከፍተኛ ጫና አሳርፏል ይላል የኦፌኮ መግለጫ በአጠቃላይ በአገሪቱ እየተከሰቱ ያሉ የጸጥታ ችግሮችም ሆነ የኑሮ ውድነቱን ችግር ለመፍታት በተለያዩ ስፍራዎች ያሉ ግጭቶችን ማስቆምና የፖለቲካ ልዩነቶችን በምክክር መፍታት አስፈላጊ ነው ሲል አሳስቧል። "መንግሥትም ሆነ ማንኛውም ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ኃይል ወደምክክር መድረክ በመመለስ፤ የኢኮኖሚ ውድቀት፤ በህዝብ ላይ የተጫነውን መከራ፤ እንዲሁም አገሪቱን ከብተና እንዲያድኑ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡" በማለት መግለጫው አስፍሯል። | መንግሥትና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጦርነቱን አቁመው ልዩነታቸውን በድርድር እንዲፈቱ ኦፌኮ ጠየቀ በኢትዮጵያ መንግሥትና በአሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት እንዲቆምና ልዩነታቸውን በድርድር እንዲፈቱ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ጥሪ አቀረበ። በሁለቱ አካላት መካከል ያለው ግጭት መንስዔው "ፖለቲካዊ ነው ያለው" ኦፌኮ መፍትሄውም "ፖለቲካዊ" መሆን እንዳለበትም በትናንትናው ዕለት ሚያዝያ 3፣ 2014 ዓ.ም የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የኦሮሚያ ክልል ከቀናት በፊት "አሸባሪ" ብሎ የጠራውን የ"ሸኔን ኃይል" ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ የሚያስችል ጠንካራ ዘመቻ ተጀምሯል ብሏል። በመንግሥት ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኑ መካከል ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ቃለ አቀባይ ኦዳ ተርቢ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። በአሁኑ ወቅት ጦርነቱ ከመፋፋሙና እንደ አዲስ ዘመቻ ከመጀመሩ ጋርም ተያይዞ ኦፌኮ ይህ ሁኔታ የኦሮሚያን ክልልን እንዲሁም አገሪቱን ለተጨማሪ አደጋ የሚዳርግ መሆኑንም አፅንኦት ሰጥቷል። "መንግሥት ሰሞኑን በአዲስ መልኩ ያወጀው ዘመቻ በጥቂቱ ፈንጥቆ የነበረውን የሰላም ጭላንጭል መልሶ የሚያደበዝዝ፤ኦሮሚያና አገሪቱን ለተጨማሪ አደጋ የሚያጋልጥ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ እንደማያስገኝ ደጋግመን ማሳሰብ እንፈልጋለን። " ብሏል ከሰሞኑ የኦሮሚያ ክልል የፌደራል ኃይሎች እና የክልል ኃይሎች በቅንጅት በወለጋ፣ በጉጂ፣ በምዕራብ እና ሰሜን ሸዋ በሚንቀሳቀሱ የታጣቂዎቹ አባላት ላይ እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸውን ገልጿል። መግለጫው መንግሥት "ሸኔን" እደመስሳለሁ የሚለውን ሁኔታውን አቁሞ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እንደተጀመረው የሰላም አካሄድ እንዲከተልም ጥሪ አቅርቧል። "መንግስት 'ሸኔን ማጥፋት' ከሚለው ውጤት አልባ የዘመቻ አዙሪት ወጥቶ በሰሜኑ ያገራችን ክፍል እንደጀመረው ሁሉ በኦሮሚያ ክልል ያለውን አለመግባባትም ተመሳሳይ በሆነ ሰላማዊ አካሄድ እንዲፈታ በድጋሜ ጥሪ እናደርጋለን፡፡" በማለት አስፍሯል። ስራ አስፈፃሚው ኮሚቴ ሚያዝያ 1፣ 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በተጨማሪ ያነሳው ሃሳብ ከአማራ ክልል የመጡ ያላቸው ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል እየፈጠሩት ያለውን የጸጥታ ችግር አስመልክቶ ነው። እነዚህ ታጣቂዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል በመግባት " የመሬት ወረራና የግዛት ማስፋፋት እየፈጸሙ እንዲሁም ሰላማዊ ሰዎችን እየገደሉ፣ አርሷአደሮችን ከመሬታቸው በማፈናቀል የኦሮሚያ ክልልን ወደማያባራ የግጭት ቀጠና እየለወጡት ነው" ብሏል። "የጦር ዘመቻና የመሬት ወራራ" እየተፈጸመ እንደሆነ ያሰፈረው ይህ መግለጫ ይህም ሁኔታ በምስራቅ ወለጋ፤ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፤ሰሜን ሸዋ፤ ምዕራብ ሸዋና በምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ በተቀናጀ አኳኋን እየተካሔደ እንደሆነ መረዳቱንም ጠቅሷል። ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በተጨማሪ አገሪቱ የተፈጠረው የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነትን አንስቶ በመወያየት መንስዔውም የርስ በርስ ጦርነቱ እንደሆነና መፍትሄው "ሀገሪቱን በሁሉም አቅጣጫ እያመሰ ያለውን የርስ በርስ ጦርነት ወደሚያስቆም ውይይትና ድርድር ፊትን ማዞር ብቻ ነው" ብሏል። ጦርነቱ የውስጥና የውጪ ንግድ እንዲቀዛቀዝ፣ የግብርናና ፋብሪካዎች ምርታማነት እንዲቀንስ፣ የውጪ ኢንቨስትመንት እንዲዳከም እንዲሁም በማዕቀቡ ምክንያት በእርዳታና በብድር ወደ አገር ይገባ የነበረ ገንዘብ እንዲቀንስ ወይም እንዲቋረጥ በማድረጉ የአገሪቱ ምጣኔ ኃብት ላይ ከፍተኛ ጫና አሳርፏል ይላል የኦፌኮ መግለጫ በአጠቃላይ በአገሪቱ እየተከሰቱ ያሉ የጸጥታ ችግሮችም ሆነ የኑሮ ውድነቱን ችግር ለመፍታት በተለያዩ ስፍራዎች ያሉ ግጭቶችን ማስቆምና የፖለቲካ ልዩነቶችን በምክክር መፍታት አስፈላጊ ነው ሲል አሳስቧል። "መንግሥትም ሆነ ማንኛውም ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ኃይል ወደምክክር መድረክ በመመለስ፤ የኢኮኖሚ ውድቀት፤ በህዝብ ላይ የተጫነውን መከራ፤ እንዲሁም አገሪቱን ከብተና እንዲያድኑ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡" በማለት መግለጫው አስፍሯል። | https://www.bbc.com/amharic/news-61077377 |
3politics
| የኢትዮጵያ ምርጫ 2013፡ የትኞቹ ፓርቲዎች ጠንካራ ተፎካካሪ ሊሆኑ ይችላሉ? | በግንቦት ወር መጨረሻና በሰኔ ወር መጀመሪያ ከትግራይ ክልል ውጪ በመላው ኢትዮጵያ ለማካሄድ በታቀደው 6ኛው አገራዊ ምርጫ 52 የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል። ቢቢሲ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የኋላ ታሪክ፣ የመሪዎቻቸውን ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና አሁናዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን መነሻ በማድረግ በፌዴራሉና በክልሎች እንዲሁም በከተማ መስተዳድሮች ምክር ቤቶች ድምጽ የማግኘት እድል ሊኖራቸው እንደሚችል የሚገመቱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንደሚከተለው ዘርዝሯል። ፓርቲዎቹ የተዘረዘሩት በእንግሊዘኛ መጠሪያቸው ሆሄያት ቅደም ተከተል መሠረት ነው። አብን ረዥም የፖለቲካ የትግል ታሪክ ባይኖረውም በወቅቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ ውስጥ ተጽዕኖው ቀላል የሚባል አይደለም። በብሔር ተኮር የፓለቲካ እንቅስቃሴ የአማራ ብሔርተኝነትን በመወከል የሚንቀሳቀሰው አብን የተመሠረተው በ2010 ዓ.ም ነው። ንቅናቄው ዋነኛ ዓላማዬ "የአማራ ህዝብን ጥቅምና መብት ማስከበር ነው" የሚል ሲሆን ከምስረታው በኋላ ባሉት ሦስት ዓመታት ጎልቶ መምጣት ችሏል። ፓርቲው በአማራ ክልል በወጣቱ ዘንድ ተቀባይነት እንዳለው ይታመናል። በክልሉ በርካታ ስፍራዎችም ቢሮዎችን ከፍቶ ይንቀሳቀሳል። ከአምስት ወራት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ከሚቀርቡ ፓርቲዎች መካከል አብን አንዱ እንደሚሆን ይጠበቃል። በቅርቡ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ቆይታ የነበራቸው የንቅናቄው ሊቀ መንበር አቶ በለጠ ሞላ፤ ለምርጫው ሰፊ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆናውን ገልጸዋል። "በሕዝብ ለመዳኘትና ውጤቱን በጸጋ ለመቀበል" ዝግጁ ስለመሆናቸውም ተናገረዋል። አብን ከአማራ ክልል ውጪም የአማራ ተወላጆች በብዛት በሚኖሩባቸው በተለያዩ የኢትዮጰያ ክፍሎች ጽህፈት ቤቶችን እያደራጀ ሲሆን ይህም በምርጫው ጠንካራ ተፎካካሪ ሊያደርገው እንደሚችል ይታመናል። ባልደራስ በቀድሞው ጉምቱ ጋዜጠኛ እና የመብት ተሟጋች በዛሬው ፖለቲከኛ አቶ እስክንድር ነገ የሚመራ ፓርቲ ነው። አቶ እስክንድር በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስና ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ተሳትፎ አለው። ባልደራስ "የአዲስ አበባን ጥቅም ለማስከበር" ያስጀመረው እንቅስቃሴ ሲሆን፤ እንቅስቃሴው አድጎ አዲስ አበባን መሠረት በማድረግ ወደ ፓለቲካ ፓርቲነት አድጓል። የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር በተያያዘ መሪው አቶ እስክንድር የታሰርበት ባልደራስ፤ በከተማ አስተዳደሩ ይሰራሉ ያላቸውን 'ሕገ ወጥ' ተግባራት እንደሚታገል ሲገልጽ ቆይቷል። ባልደራስ በተለያዩ ወቅቶች የሚጠራቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎችና ሰልፎች ግልጽ ባልሆኑ ምክንያቶች ሲሰረዙ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። ፓርቲው በአዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ውስጥ በፈጠረው ተጽዕኖ እና አቶ እስክንድር በፖለቲካው ውስጥ ባለው 'የገዘፈ' ስም ምክንያት፤ ባልደራስ በመጪው ምርጫ አዲስ አበባ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። ኢዜማ በምርጫ 97 ተሳትፏቸው የታወቁ እውቅ ፖለቲከኞችን ያቀፈ ነው። በመላው አገሪቱ ሊባል በሚያስችል መልኩ ከ400 በላይ የምርጫ ወረዳ ጽህፈት ቤቶችን ከፍቷል። ከብሔር ፖለቲካ በተለየ "ዜግነትን መሰረት ያደረገ" ፖለቲካን እንደሚያራምድ የሚገልጸው ፓርቲው፤ በኢትዮጵያ ማህበራዊ ፍትህን ማረጋገጥ ቀዳሚ ግቤ ነው ይላል። ፓርቲው ከሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለየ መልኩ፤ በአገሪቱ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊና የውጪ ግንኙነት ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ 40 የፖሊሲ ሰነዶችን እንዳዘጋጀም ገልጿል። ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ሕገ ወጥ ነው ያለውን የመሬትና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ወረራ በተመለከተ ያወጣው የጥናት ሪፖርት የበርካቶች መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። በ97ቱ ምርጫ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከነበሩ ፖለቲከኞች መካከል ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የፓርቲው መሪ፤ አቶ አንዱአለም አራጌ ደግሞ የፓርቲው ምክት መሪ ናቸው። ከጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን መምጣት ቀደም ብሎ የጎላ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የነበረውን ሰማያዊ ፓርቲ ሲመሩ የነበሩት አቶ የሺዋስ አሰፋን ሊቀ መንበር ያደረገው ኢዜማ፤ 6 ፓርቲዎች ከስመው የመሰረቱት ነው። ከእነዚህ ውስጥ ነፍጥ አንግቦ ሲታገል የነበረው አርበኞች ግንቦት 7 ተጠቃሽ ነው። ይህ ድርጅት በውጪና በአገር ውስጥ ቀላል የማይባል ደጋፊዎች እንዳሉት ይገለጻል። ታዲያ የዚህ ሁሉ ድምር ኢዜማን በምርጫ 2013 ለውጤት ከሚጠበቁ ፓርቲዎች አንዱ አድርጎታል። ኦብነግ በፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ረዥም እድሜ ያስቆጠረ ድርጅት ነው። ከ37 ዓመታት በፊት የተመሠረተው ኦብነግ መሰረቱን በሶማሌ ክልል ያደረገ ነው። ከ1986 እሰከ 2010 ዓ. ም በትጥቅ ትግል የቆየው የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር፤ ከ1983-87 የነበረው የሽግግር መንግሥት አካል ነበር። በ1984 በተከናወነው የአካባቢ ምርጫ 87 በመቶ የሚሆነውን ድምጽ በማሸነፍ የሶማሌ ክልልን ለሁለት ዓመታት አስተዳድሯል። ሆኖም በኦብነግና ማዕከላዊ መንግሥቱ መካከል የተፈጠረው ቅራኔ ግንባሩ ወደ ትጥቅ ትግል እንዲገባ አድርጎታል። በዚህም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 'አሸባሪ' ተብሎ ተፈርጆ ነበር። በ2010 የጠቅላይ ሚኒሰትር ዐብይን ወደ ሥልጣን መምጣት ተከተሎ ከሽብር መዝገብ ተሰርዞ በሕጋዊ ፓርቲነት ተመዝግቧል። የሶማሌ ክልል ሕዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ማረጋገጥ ዋነኛ ዓላማዬ ነው የሚለው ፓርቲው፤ በቀጣዩ ምርጫ በሶማሌ ክልል ብርቱ ተፎካካሪ እንደሚሆን ይጠበቃል። የፓርቲው አመራሮች በ2011 ወደ አገር ቤት በገቡበት ወቅት የተደረገላቸው 'ሞቅ' ያለ አቀባበል ግንባሩ አሁንም ያለውን ተቀባይነት ብቻ ሳይሆን ለቀጣዩ ምርጫ ያለውንም ተስፋ የሚያመላክት ይመስላል። በኢትዮጵያ ፖለቲካ የረዥም ዘመን ተሳትፎ ያላቸው መረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር) የሚመሩት ኦፌኮ፤ ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች ተሳታፊ ነበር። ሊቀ መንበሩ መረራ (ፕሮፌሰር) በፌዴራሉ የፓርላማ አባል ሆነው በቆዩባቸው ዓመታት በፓርላማ ውስጥ በሚሰጧቸው አስተያየቶች በበርካቶች ዘንድ ይታወሳሉ። በተደጋጋሚ የታሰሩ ሲሆን ለመጫረሻ ጊዜ ከእስር ሲፈቱ በርካታ ደጋፊዎቻቸው አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን ገልጸዋል። በተመሳሳይ አሁን እስር ቤት የሚገኙት ምክትል ሊቀ መንበሩ አቶ በቀለ ገርባ የዳበረ የፖለቲካ ልምድ ያላቸው ናቸው። በኦሮሚያ በተለይም በወጣቱ ዘንድ ተቀባይነት ያለው አቶ ጀዋር መሐመድ ፓርቲውን መቀላቀሉ የኦፌኮን ተጽዕኖ ከፍ እንዳደረገው ይታመናል። መረራ (ፕሮፌሰር)፣ አቶ በቀለ እና አቶ ጀዋር ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት በኦሮሚያ የተለያዩ አከባቢዎች በተጓዙበት ወቅት የተደረገላቸው አቀባል ኦፌኮ በምርጫ 2013 ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ እንደሚቀርብ ያመላከተ ነበር። በኢትዮጵያ የምርጫ ስርዓት ልምድ ያካበቱ ጉምቱ ፖለቲከኞችን መያዙ [ምንም እንኳን በእስር ላይ የሚገኙ ቢኖሩም] ኦፌኮን በቀጣዩ ምርጫ ለውጤት የሚጠበቅ ፓርቲ አድርጎታል። ከተመሠረቱ ብዙ ዓመታት ካስቆጠሩት የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል አንዱ ኦነግ ነው። በበርካታ የኦሮሚያ አከባቢዎች የነጻነት አርማ ተደርጎ የሚቆጠረው ኦነግ በ1965 ዓ. ም ነበር የተመሠረተው። ግንባሩ የ1983ቱ የሽግግር መንግሥት አካል የነበረ ሲሆን ብዙም ሳይቆይ ግን አማጺ ቡድን ሆኖ ጫካ ገባ። እናም ለዓመታት በትጥቅ ትግል ቆይቶ ከ3 ዓመታት በፊት የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይን ወደ ሥልጣን መምጣት ተከትሎ ወደ አገር ቤት ተመልሷል። ከበርካታ ዓመታት የትጥቅ ትግል በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ ለመወዳደር የተዘጋጀው ፓርቲው፤ በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከፍተኛ ግምት ከሚሰጣቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ ነው። ፓርቲው በውስጣዊ ችግሮቹ እና በፓርቲ አመራሮች እስር ታጅቦ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ያለውን የገዘፈ ስምና የትጥቅ ትግል ታሪክ ይዞ ምርጫው እየተጠባበቀ ነው። ፓርቲው በመንግሥት ይደርስብኛል በሚለው ጫናና በአመራሮቹ መካከል የተፈጠረው ቅራኔ በምርጫ ተሳትፎው ላይ ተጽዕኖ ካላደረገበት በስተቀር በኦሮሚያ ክልል ብርቱ ተፎካካሪ መሆኑ የሚቀር አይመስልም። ብልጽግና፤ ያለፉትን 5 አገራዊ ምርጫዎች 'አሸንፊያለሁ' ያለውና አገሪቱን ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ሲያስተዳድር የቆየው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢሕአዴግ/ ውጤት ነው። ብልጽግና ከኢሕአዴግ መክሰም በኋላ አንዳንድ ለውጦችን እንዳደረገ ቢነገርም፤ ህወሓት ብቻ የተቀነሰበት የቀድሞው ኢሕአዴግ ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከህወሓት ውጪ ግንባሩን ከ 'አጋሮቹ' ጋር በመዋሃድ ብልጽግና የተሰኘ አዲስ ፓርቲ ፈጥረዋል። የቀድሞውን ኢሕአዴግ ሀብት እና ንብረቶች ጠቅልሏል። አብዮታዊ ዲሞክራሲ ጽንሰ ሃሳብን ሽሮ መደመር በተሰኘ የፓርቲው ፕሬዝዳንትና በአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እሳቤ ተክቷል። ፓርቲው በመላው ሀገሪቱ አለኝ ከሚለው በሚሊዮን የሚቆጠር አባላት እንዲሆም ረጅም አመታት ያሰቆጠር ጠንካራ መዋቅር በቀጣዩ ምርጫ ተጠባቂ እንዲሆን አርጎታል። የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዐቢይ (ዶ/ር) አምጥተውታል የሚባለው ለውጥና በአገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች ያላቸው ድጋፍ እንዲሁም ፓርቲው በክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች ተጽዕኖ ፈጣሪ አመራሮችን መያዙ በምርጫው ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ እንዲገመት አድርጎታል። ከላይ የተጠቀሱት አንዳንድ ፓርቲዎች በተለያዩ ምክንያቶች በቀጣዩ ምርጫ ላይሳተፉ እንደሚችሉ እየገለጹ ቢሆንም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ይኖራቸዋል ተብሎ የሚጠበቀው ፍክክር ምርጫ 2013 ከባለፉት በተሻለ ዓይን የሚጣልበት እንዲሆን አድርጎታል። | የኢትዮጵያ ምርጫ 2013፡ የትኞቹ ፓርቲዎች ጠንካራ ተፎካካሪ ሊሆኑ ይችላሉ? በግንቦት ወር መጨረሻና በሰኔ ወር መጀመሪያ ከትግራይ ክልል ውጪ በመላው ኢትዮጵያ ለማካሄድ በታቀደው 6ኛው አገራዊ ምርጫ 52 የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል። ቢቢሲ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የኋላ ታሪክ፣ የመሪዎቻቸውን ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና አሁናዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን መነሻ በማድረግ በፌዴራሉና በክልሎች እንዲሁም በከተማ መስተዳድሮች ምክር ቤቶች ድምጽ የማግኘት እድል ሊኖራቸው እንደሚችል የሚገመቱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንደሚከተለው ዘርዝሯል። ፓርቲዎቹ የተዘረዘሩት በእንግሊዘኛ መጠሪያቸው ሆሄያት ቅደም ተከተል መሠረት ነው። አብን ረዥም የፖለቲካ የትግል ታሪክ ባይኖረውም በወቅቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ ውስጥ ተጽዕኖው ቀላል የሚባል አይደለም። በብሔር ተኮር የፓለቲካ እንቅስቃሴ የአማራ ብሔርተኝነትን በመወከል የሚንቀሳቀሰው አብን የተመሠረተው በ2010 ዓ.ም ነው። ንቅናቄው ዋነኛ ዓላማዬ "የአማራ ህዝብን ጥቅምና መብት ማስከበር ነው" የሚል ሲሆን ከምስረታው በኋላ ባሉት ሦስት ዓመታት ጎልቶ መምጣት ችሏል። ፓርቲው በአማራ ክልል በወጣቱ ዘንድ ተቀባይነት እንዳለው ይታመናል። በክልሉ በርካታ ስፍራዎችም ቢሮዎችን ከፍቶ ይንቀሳቀሳል። ከአምስት ወራት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ከሚቀርቡ ፓርቲዎች መካከል አብን አንዱ እንደሚሆን ይጠበቃል። በቅርቡ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ቆይታ የነበራቸው የንቅናቄው ሊቀ መንበር አቶ በለጠ ሞላ፤ ለምርጫው ሰፊ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆናውን ገልጸዋል። "በሕዝብ ለመዳኘትና ውጤቱን በጸጋ ለመቀበል" ዝግጁ ስለመሆናቸውም ተናገረዋል። አብን ከአማራ ክልል ውጪም የአማራ ተወላጆች በብዛት በሚኖሩባቸው በተለያዩ የኢትዮጰያ ክፍሎች ጽህፈት ቤቶችን እያደራጀ ሲሆን ይህም በምርጫው ጠንካራ ተፎካካሪ ሊያደርገው እንደሚችል ይታመናል። ባልደራስ በቀድሞው ጉምቱ ጋዜጠኛ እና የመብት ተሟጋች በዛሬው ፖለቲከኛ አቶ እስክንድር ነገ የሚመራ ፓርቲ ነው። አቶ እስክንድር በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስና ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ተሳትፎ አለው። ባልደራስ "የአዲስ አበባን ጥቅም ለማስከበር" ያስጀመረው እንቅስቃሴ ሲሆን፤ እንቅስቃሴው አድጎ አዲስ አበባን መሠረት በማድረግ ወደ ፓለቲካ ፓርቲነት አድጓል። የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር በተያያዘ መሪው አቶ እስክንድር የታሰርበት ባልደራስ፤ በከተማ አስተዳደሩ ይሰራሉ ያላቸውን 'ሕገ ወጥ' ተግባራት እንደሚታገል ሲገልጽ ቆይቷል። ባልደራስ በተለያዩ ወቅቶች የሚጠራቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎችና ሰልፎች ግልጽ ባልሆኑ ምክንያቶች ሲሰረዙ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። ፓርቲው በአዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ውስጥ በፈጠረው ተጽዕኖ እና አቶ እስክንድር በፖለቲካው ውስጥ ባለው 'የገዘፈ' ስም ምክንያት፤ ባልደራስ በመጪው ምርጫ አዲስ አበባ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። ኢዜማ በምርጫ 97 ተሳትፏቸው የታወቁ እውቅ ፖለቲከኞችን ያቀፈ ነው። በመላው አገሪቱ ሊባል በሚያስችል መልኩ ከ400 በላይ የምርጫ ወረዳ ጽህፈት ቤቶችን ከፍቷል። ከብሔር ፖለቲካ በተለየ "ዜግነትን መሰረት ያደረገ" ፖለቲካን እንደሚያራምድ የሚገልጸው ፓርቲው፤ በኢትዮጵያ ማህበራዊ ፍትህን ማረጋገጥ ቀዳሚ ግቤ ነው ይላል። ፓርቲው ከሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለየ መልኩ፤ በአገሪቱ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊና የውጪ ግንኙነት ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ 40 የፖሊሲ ሰነዶችን እንዳዘጋጀም ገልጿል። ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ሕገ ወጥ ነው ያለውን የመሬትና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ወረራ በተመለከተ ያወጣው የጥናት ሪፖርት የበርካቶች መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። በ97ቱ ምርጫ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከነበሩ ፖለቲከኞች መካከል ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የፓርቲው መሪ፤ አቶ አንዱአለም አራጌ ደግሞ የፓርቲው ምክት መሪ ናቸው። ከጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን መምጣት ቀደም ብሎ የጎላ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የነበረውን ሰማያዊ ፓርቲ ሲመሩ የነበሩት አቶ የሺዋስ አሰፋን ሊቀ መንበር ያደረገው ኢዜማ፤ 6 ፓርቲዎች ከስመው የመሰረቱት ነው። ከእነዚህ ውስጥ ነፍጥ አንግቦ ሲታገል የነበረው አርበኞች ግንቦት 7 ተጠቃሽ ነው። ይህ ድርጅት በውጪና በአገር ውስጥ ቀላል የማይባል ደጋፊዎች እንዳሉት ይገለጻል። ታዲያ የዚህ ሁሉ ድምር ኢዜማን በምርጫ 2013 ለውጤት ከሚጠበቁ ፓርቲዎች አንዱ አድርጎታል። ኦብነግ በፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ረዥም እድሜ ያስቆጠረ ድርጅት ነው። ከ37 ዓመታት በፊት የተመሠረተው ኦብነግ መሰረቱን በሶማሌ ክልል ያደረገ ነው። ከ1986 እሰከ 2010 ዓ. ም በትጥቅ ትግል የቆየው የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር፤ ከ1983-87 የነበረው የሽግግር መንግሥት አካል ነበር። በ1984 በተከናወነው የአካባቢ ምርጫ 87 በመቶ የሚሆነውን ድምጽ በማሸነፍ የሶማሌ ክልልን ለሁለት ዓመታት አስተዳድሯል። ሆኖም በኦብነግና ማዕከላዊ መንግሥቱ መካከል የተፈጠረው ቅራኔ ግንባሩ ወደ ትጥቅ ትግል እንዲገባ አድርጎታል። በዚህም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 'አሸባሪ' ተብሎ ተፈርጆ ነበር። በ2010 የጠቅላይ ሚኒሰትር ዐብይን ወደ ሥልጣን መምጣት ተከተሎ ከሽብር መዝገብ ተሰርዞ በሕጋዊ ፓርቲነት ተመዝግቧል። የሶማሌ ክልል ሕዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ማረጋገጥ ዋነኛ ዓላማዬ ነው የሚለው ፓርቲው፤ በቀጣዩ ምርጫ በሶማሌ ክልል ብርቱ ተፎካካሪ እንደሚሆን ይጠበቃል። የፓርቲው አመራሮች በ2011 ወደ አገር ቤት በገቡበት ወቅት የተደረገላቸው 'ሞቅ' ያለ አቀባበል ግንባሩ አሁንም ያለውን ተቀባይነት ብቻ ሳይሆን ለቀጣዩ ምርጫ ያለውንም ተስፋ የሚያመላክት ይመስላል። በኢትዮጵያ ፖለቲካ የረዥም ዘመን ተሳትፎ ያላቸው መረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር) የሚመሩት ኦፌኮ፤ ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች ተሳታፊ ነበር። ሊቀ መንበሩ መረራ (ፕሮፌሰር) በፌዴራሉ የፓርላማ አባል ሆነው በቆዩባቸው ዓመታት በፓርላማ ውስጥ በሚሰጧቸው አስተያየቶች በበርካቶች ዘንድ ይታወሳሉ። በተደጋጋሚ የታሰሩ ሲሆን ለመጫረሻ ጊዜ ከእስር ሲፈቱ በርካታ ደጋፊዎቻቸው አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን ገልጸዋል። በተመሳሳይ አሁን እስር ቤት የሚገኙት ምክትል ሊቀ መንበሩ አቶ በቀለ ገርባ የዳበረ የፖለቲካ ልምድ ያላቸው ናቸው። በኦሮሚያ በተለይም በወጣቱ ዘንድ ተቀባይነት ያለው አቶ ጀዋር መሐመድ ፓርቲውን መቀላቀሉ የኦፌኮን ተጽዕኖ ከፍ እንዳደረገው ይታመናል። መረራ (ፕሮፌሰር)፣ አቶ በቀለ እና አቶ ጀዋር ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት በኦሮሚያ የተለያዩ አከባቢዎች በተጓዙበት ወቅት የተደረገላቸው አቀባል ኦፌኮ በምርጫ 2013 ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ እንደሚቀርብ ያመላከተ ነበር። በኢትዮጵያ የምርጫ ስርዓት ልምድ ያካበቱ ጉምቱ ፖለቲከኞችን መያዙ [ምንም እንኳን በእስር ላይ የሚገኙ ቢኖሩም] ኦፌኮን በቀጣዩ ምርጫ ለውጤት የሚጠበቅ ፓርቲ አድርጎታል። ከተመሠረቱ ብዙ ዓመታት ካስቆጠሩት የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል አንዱ ኦነግ ነው። በበርካታ የኦሮሚያ አከባቢዎች የነጻነት አርማ ተደርጎ የሚቆጠረው ኦነግ በ1965 ዓ. ም ነበር የተመሠረተው። ግንባሩ የ1983ቱ የሽግግር መንግሥት አካል የነበረ ሲሆን ብዙም ሳይቆይ ግን አማጺ ቡድን ሆኖ ጫካ ገባ። እናም ለዓመታት በትጥቅ ትግል ቆይቶ ከ3 ዓመታት በፊት የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይን ወደ ሥልጣን መምጣት ተከትሎ ወደ አገር ቤት ተመልሷል። ከበርካታ ዓመታት የትጥቅ ትግል በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ ለመወዳደር የተዘጋጀው ፓርቲው፤ በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከፍተኛ ግምት ከሚሰጣቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ ነው። ፓርቲው በውስጣዊ ችግሮቹ እና በፓርቲ አመራሮች እስር ታጅቦ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ያለውን የገዘፈ ስምና የትጥቅ ትግል ታሪክ ይዞ ምርጫው እየተጠባበቀ ነው። ፓርቲው በመንግሥት ይደርስብኛል በሚለው ጫናና በአመራሮቹ መካከል የተፈጠረው ቅራኔ በምርጫ ተሳትፎው ላይ ተጽዕኖ ካላደረገበት በስተቀር በኦሮሚያ ክልል ብርቱ ተፎካካሪ መሆኑ የሚቀር አይመስልም። ብልጽግና፤ ያለፉትን 5 አገራዊ ምርጫዎች 'አሸንፊያለሁ' ያለውና አገሪቱን ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ሲያስተዳድር የቆየው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢሕአዴግ/ ውጤት ነው። ብልጽግና ከኢሕአዴግ መክሰም በኋላ አንዳንድ ለውጦችን እንዳደረገ ቢነገርም፤ ህወሓት ብቻ የተቀነሰበት የቀድሞው ኢሕአዴግ ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከህወሓት ውጪ ግንባሩን ከ 'አጋሮቹ' ጋር በመዋሃድ ብልጽግና የተሰኘ አዲስ ፓርቲ ፈጥረዋል። የቀድሞውን ኢሕአዴግ ሀብት እና ንብረቶች ጠቅልሏል። አብዮታዊ ዲሞክራሲ ጽንሰ ሃሳብን ሽሮ መደመር በተሰኘ የፓርቲው ፕሬዝዳንትና በአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እሳቤ ተክቷል። ፓርቲው በመላው ሀገሪቱ አለኝ ከሚለው በሚሊዮን የሚቆጠር አባላት እንዲሆም ረጅም አመታት ያሰቆጠር ጠንካራ መዋቅር በቀጣዩ ምርጫ ተጠባቂ እንዲሆን አርጎታል። የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዐቢይ (ዶ/ር) አምጥተውታል የሚባለው ለውጥና በአገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች ያላቸው ድጋፍ እንዲሁም ፓርቲው በክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች ተጽዕኖ ፈጣሪ አመራሮችን መያዙ በምርጫው ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ እንዲገመት አድርጎታል። ከላይ የተጠቀሱት አንዳንድ ፓርቲዎች በተለያዩ ምክንያቶች በቀጣዩ ምርጫ ላይሳተፉ እንደሚችሉ እየገለጹ ቢሆንም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ይኖራቸዋል ተብሎ የሚጠበቀው ፍክክር ምርጫ 2013 ከባለፉት በተሻለ ዓይን የሚጣልበት እንዲሆን አድርጎታል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56027522 |
0business
| ምጣኔ ኃብት፡ ከመቶ ሺህ ብር በላይ ያላቸው በአንድ ወር መቀየር እንዳለባቸው ተገለፀ | አዲሱ የብር ኖት ቅየራ በዛሬው ዕለት፣ መስከረም 6/2012 ዓ.ም ከሰዓት መጀመሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስኪያጅ አቶ አልሰን አሰፋ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በዝግጅቱ ላይም የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ የተገኙ ሲሆን፤ ዛሬ ከቀኑ 9፡30 ጀምሮም በአዲስ አበባ አካባቢ ባሉ ባንኮች ብር መቀየር ተጀምሯል ብለዋል ሥራ አስኪያጁ። በመሆኑም የብሔራዊ ባንክ ባስቀመጠው መመሪያ መሠረት፤ 100 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ገንዘብ በእጃቸው ላይ ያለ ግለሰቦችና አካላት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ወደ ባንክ በመሄድ ገንዘቡን መቀየር እንደሚችሉም አቶ አልሰን ገልፀዋል። አገልግሎቱ በማንኛውም የባንክ ቅርንጫፍ እንደሚሰጥ የጠቆሙት ሥራ አስኪያጁ፤ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች እጃቸው ላይ ያለውን ብር ወደ አዲሱ መቀየር አሊያም ከሒሳብ ቁጥራቸው አዲሱን የብር ኖት ማውጣት እንደሚችሉ ተናግረዋል። እጃቸው ላይ ከ100 ሺህ ብር በታች ያላቸው ግለሰቦችም እስከ 2 ወር ከግማሽ ድረስ ገንዘባቸው እንዲቀይሩ ቀነ ገደብ ተቀምጧል ብለዋል። ከ100 ሺህ ብር በላይ ያላቸው ግን በዚህ አንድ ወር ብቻ ቅየራውን ማጠናቀቅ ያለባቸው ሲሆን፤ ከዚያ በኋላ የሚመጣ በየትኛውም ባንክ እንደማይስተናገድ ሥራ አስኪያጁ አስጠንቅቀዋል። በመሆኑም በዚህ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ራሳቸውን ከኮሮና በመጠበቅ እጃቸው ላይ ገንዘባቸው በአዲሱ የብር ኖት እንዲለውጡ አሳስበዋል። ከዚያ በታች የገንዘብ መጠን ያላቸው ሰዎች የተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ እስከ ሁለት ወር ከግማሽ ቢሆንም በዚህ ወር ውስጥም ግን መቀየር እንደሚችሉ አቶ አልሰን ጠቁመዋል። 10 ሺህ እና ከዚያ በላይ እጃቸው ላይ ያለ ሰዎች ደግሞ ገንዘባቸው አካውንታቸው ላይ ማስገባት የሚጠበቅባቸው ሲሆን የሒሳብ ቁጥር ከሌላቸውም መታወቂያ እና ጉርድ ፎቶግራፍ በመያዝ የሒሳብ ቁጥር ከፍተው ገንዘባቸው እዚያ ማስቀመጥ ይችላሉም ተብሏል። በተቀመጠው ጊዜም ከባንክ ውጪ የሚገኙ ገንዘቦች የሚሰበሰቡበት ሁኔታዎች መመቻቸታቸውንም ሥራ አስኪያጁ አክለዋል። አቶ አልሰን እንዳሉት ገንዘቡን ለመሰብሰብ የተሰጠው አጠቃላይ ጊዜ ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ሦስት ወራት ውስጥ ነው። በዚህ ጊዜም ከባንክ ውጭ አለ ተብሎ የሚገመተው ወደ 113 ቢሊየን ብር ወደ ባንክ ይገባል ተብሎ እንደሚጠበቅም ኃላፊው ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ኢትዮጵያ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ስትገለገልባቸው የነበሩ የ10፣ የ50 እና የ100 የገንዘብ ኖቶችን ሙሉ ለሙሉ ለመተካት አዲስ የገንዘብ ኖቶችን ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል። ከአዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች ውስጥም በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የባለ ሁለት መቶ ብር ኖትም አሳትማለች። አገሪቷ ነባሮቹን የብር ኖቶች ለመቀየር ሌላ ወጪን ሳይጨምር ለህትመት ብቻ 3.7 ቢሊየን ብር ማውጣቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስታውቀዋል። | ምጣኔ ኃብት፡ ከመቶ ሺህ ብር በላይ ያላቸው በአንድ ወር መቀየር እንዳለባቸው ተገለፀ አዲሱ የብር ኖት ቅየራ በዛሬው ዕለት፣ መስከረም 6/2012 ዓ.ም ከሰዓት መጀመሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስኪያጅ አቶ አልሰን አሰፋ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በዝግጅቱ ላይም የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ የተገኙ ሲሆን፤ ዛሬ ከቀኑ 9፡30 ጀምሮም በአዲስ አበባ አካባቢ ባሉ ባንኮች ብር መቀየር ተጀምሯል ብለዋል ሥራ አስኪያጁ። በመሆኑም የብሔራዊ ባንክ ባስቀመጠው መመሪያ መሠረት፤ 100 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ገንዘብ በእጃቸው ላይ ያለ ግለሰቦችና አካላት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ወደ ባንክ በመሄድ ገንዘቡን መቀየር እንደሚችሉም አቶ አልሰን ገልፀዋል። አገልግሎቱ በማንኛውም የባንክ ቅርንጫፍ እንደሚሰጥ የጠቆሙት ሥራ አስኪያጁ፤ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች እጃቸው ላይ ያለውን ብር ወደ አዲሱ መቀየር አሊያም ከሒሳብ ቁጥራቸው አዲሱን የብር ኖት ማውጣት እንደሚችሉ ተናግረዋል። እጃቸው ላይ ከ100 ሺህ ብር በታች ያላቸው ግለሰቦችም እስከ 2 ወር ከግማሽ ድረስ ገንዘባቸው እንዲቀይሩ ቀነ ገደብ ተቀምጧል ብለዋል። ከ100 ሺህ ብር በላይ ያላቸው ግን በዚህ አንድ ወር ብቻ ቅየራውን ማጠናቀቅ ያለባቸው ሲሆን፤ ከዚያ በኋላ የሚመጣ በየትኛውም ባንክ እንደማይስተናገድ ሥራ አስኪያጁ አስጠንቅቀዋል። በመሆኑም በዚህ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ራሳቸውን ከኮሮና በመጠበቅ እጃቸው ላይ ገንዘባቸው በአዲሱ የብር ኖት እንዲለውጡ አሳስበዋል። ከዚያ በታች የገንዘብ መጠን ያላቸው ሰዎች የተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ እስከ ሁለት ወር ከግማሽ ቢሆንም በዚህ ወር ውስጥም ግን መቀየር እንደሚችሉ አቶ አልሰን ጠቁመዋል። 10 ሺህ እና ከዚያ በላይ እጃቸው ላይ ያለ ሰዎች ደግሞ ገንዘባቸው አካውንታቸው ላይ ማስገባት የሚጠበቅባቸው ሲሆን የሒሳብ ቁጥር ከሌላቸውም መታወቂያ እና ጉርድ ፎቶግራፍ በመያዝ የሒሳብ ቁጥር ከፍተው ገንዘባቸው እዚያ ማስቀመጥ ይችላሉም ተብሏል። በተቀመጠው ጊዜም ከባንክ ውጪ የሚገኙ ገንዘቦች የሚሰበሰቡበት ሁኔታዎች መመቻቸታቸውንም ሥራ አስኪያጁ አክለዋል። አቶ አልሰን እንዳሉት ገንዘቡን ለመሰብሰብ የተሰጠው አጠቃላይ ጊዜ ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ሦስት ወራት ውስጥ ነው። በዚህ ጊዜም ከባንክ ውጭ አለ ተብሎ የሚገመተው ወደ 113 ቢሊየን ብር ወደ ባንክ ይገባል ተብሎ እንደሚጠበቅም ኃላፊው ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ኢትዮጵያ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ስትገለገልባቸው የነበሩ የ10፣ የ50 እና የ100 የገንዘብ ኖቶችን ሙሉ ለሙሉ ለመተካት አዲስ የገንዘብ ኖቶችን ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል። ከአዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች ውስጥም በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የባለ ሁለት መቶ ብር ኖትም አሳትማለች። አገሪቷ ነባሮቹን የብር ኖቶች ለመቀየር ሌላ ወጪን ሳይጨምር ለህትመት ብቻ 3.7 ቢሊየን ብር ማውጣቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስታውቀዋል። | https://www.bbc.com/amharic/54183500 |
3politics
| የጋዳፊ ልጅ ከፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ታገዱ | የቀድሞ የሊቢያ መሪ ሙአመር ጋዳፊ ልጅ ሰይፍ ጋዳፊ ከሳምንታት በኋላ በሀገሪቱ ከሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውድድር ውጪ ሆነዋል። የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ሰይፍ አል ኢስላም ጋዳፊን ጨምሮ በርካታ እጩዎችን "በህጋዊ ምክንያቶች" በምርጫው እንዳይሳተፉ እንዳገደ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። አል ኢስላም ጋዳፊን አባቱ የሰሜናዊቷን አፍሪካዊ ሀገር ሊቢያን በሚያስተዳደሩበት ወቅት በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በጦር ወንጀል እና በነፍስ ግድያ የሚፈለግ ሰው ነበር። በዚህም ሳቢያ የጋዳፊ ልጅ ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደሩ ከተሰማ በኋላ ውዝግብ አስነስቷል። በአሜሪካ ፍርድ ቤቶች የወንጀል ክስ የቀረበባቸው ዝነኛው ካሊፍ ሃፍታር ለምርጫ ለመወዳደር መዘጋጃታቸው በሀገሪቱ ውስጥ ውዥንብር ፈጥሯል። ነገር ግን ምርጫ ኮሚሽኑ ከፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ያድርጋቸው አይድርጋቸው የታወቀ ነገር የለም። የሊቢያ ወታደራዊ አቃብያነ ህግ የጋዳፊ ልጅ እና የሃፍታር በቀረበባቸው ክስ ላይ ተገቢ መልስ እስኪያቀርቡ ድረስ የምርጫ ኮሚሽኑን በእጩነት ለማሳተፍ የሚያደርገውን ሂደት እንዲያቆም ጠይቀው ነበር። ሰኞ በተጠናቀቀው የእጩዎች ምዝገባ ስልሳ ሰዎች ሊቢያን በፕሬዝዳንት ለመምራት የተመዘገቡ ሲሆን የ46 ዓመቷ የሴቶች መብት ተሟጋች ሊላ ቤን ካሊፋ ብቸኛዋ ሴት ተወዳዳሪ ናቸው። | የጋዳፊ ልጅ ከፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ታገዱ የቀድሞ የሊቢያ መሪ ሙአመር ጋዳፊ ልጅ ሰይፍ ጋዳፊ ከሳምንታት በኋላ በሀገሪቱ ከሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውድድር ውጪ ሆነዋል። የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ሰይፍ አል ኢስላም ጋዳፊን ጨምሮ በርካታ እጩዎችን "በህጋዊ ምክንያቶች" በምርጫው እንዳይሳተፉ እንዳገደ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። አል ኢስላም ጋዳፊን አባቱ የሰሜናዊቷን አፍሪካዊ ሀገር ሊቢያን በሚያስተዳደሩበት ወቅት በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በጦር ወንጀል እና በነፍስ ግድያ የሚፈለግ ሰው ነበር። በዚህም ሳቢያ የጋዳፊ ልጅ ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደሩ ከተሰማ በኋላ ውዝግብ አስነስቷል። በአሜሪካ ፍርድ ቤቶች የወንጀል ክስ የቀረበባቸው ዝነኛው ካሊፍ ሃፍታር ለምርጫ ለመወዳደር መዘጋጃታቸው በሀገሪቱ ውስጥ ውዥንብር ፈጥሯል። ነገር ግን ምርጫ ኮሚሽኑ ከፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ያድርጋቸው አይድርጋቸው የታወቀ ነገር የለም። የሊቢያ ወታደራዊ አቃብያነ ህግ የጋዳፊ ልጅ እና የሃፍታር በቀረበባቸው ክስ ላይ ተገቢ መልስ እስኪያቀርቡ ድረስ የምርጫ ኮሚሽኑን በእጩነት ለማሳተፍ የሚያደርገውን ሂደት እንዲያቆም ጠይቀው ነበር። ሰኞ በተጠናቀቀው የእጩዎች ምዝገባ ስልሳ ሰዎች ሊቢያን በፕሬዝዳንት ለመምራት የተመዘገቡ ሲሆን የ46 ዓመቷ የሴቶች መብት ተሟጋች ሊላ ቤን ካሊፋ ብቸኛዋ ሴት ተወዳዳሪ ናቸው። | https://www.bbc.com/amharic/59406242 |
3politics
| አሜሪካ ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የሚያደርጉ ልዩ መልዕክተኛ ሾመች | አሜሪካ በኢትዮጵያና በአካባቢዋ ባሉ አገራት ውስጥ ስላሉ ጉዳዮች በቅርበት የሚከታተሉላትን ልዩ መልዕክተኛ መሾሟን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አስታወቀ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ይፋ እንዳደረጉት በተለይ ኢትዮጵያ ለምትገኝበት የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ጄፍሪ ፌልትማንን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አድርገው መሾማቸውን ገልጸዋል። አሜሪካ አዲስ የሾመቻቸው የአፍሪካ ቀንድ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን በተለይ በኢትዮጵያና በዙሪያዋ ስላሉ ሁኔታዎች የተለየ ትኩረት እንደሚሰጡ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አመልክቷል። በዚህም መሠረት በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል ትግራይ ክልል ውስጥ ያለውን ግጭት ጨምሮ በአገሪቱ ያለው ተለዋወጭ ሁኔታ፣ ከሱዳን ጋር ያለውን የድንበር አለመግባባት እንዲሁም በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለው ውዝግብ የልዩ ልዑኩ ቀዳሚ ሥራ እንደሚሆን ተገልጿል። የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ በመግለጫው ላይ እናዳለው ቁልፍ በሆነው የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ "በአሁኑ ጊዜ መሠረታዊ ለውጥ እየተካሄደበት ነው" ብሏል። የአዲሱን ልዩ መልዕክተኛ አስፈላጊነት በተመለከተም በአካባቢው "በትውልዶች ውስጥ አንድ ጊዜ ለሚያጋጥም የለውጥ ዕድል አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የግጭት ስጋትን ለማስቀረት በከፍተኛ የሥልጣን ደረጃ የአሜሪካ ተሳትፎ አስፈላጊ" በመሆኑ ነው ብሏል። ይህ የልዩ መልዕክተኛ ሹመት የባይደን አስተዳደር በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለውን ተያያዥ የሆኑትን ፖለቲካዊ፣ የደኅንነትና የሰብአዊ ጉዳዮች ምፍትሔ እንዲያገኙ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ጥረቶችን ለመምራት ያለውን ቁርጠኝነት ያመለክታል ተብሏል። በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጥና በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ በከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ የሰሩት ጄፍሪ ፌልትማን በአፍሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች ላይ ለረጅም ዘመን ልምድ እንዳላቸው ተገልጿል። በተጨማሪም ፌልትማን በርካታ አገራትን ባካተቱ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሚደረጉ ድርድሮችና ሽምግልናዎች ውስጥ የአሜሪካንን ተያያዥ ስትራቴጂን በማስፈጸም ልምድ አላቸው ብሏል ሹመታቸውን ያሳወቀው መግለጫ። በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤትና በተባበሩት መንግሥት ውስጥ በተለያዩ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ላይ በመሥራት ሠፊ ልምድ እንዳላቸው የሚነገርላቸው የ62 ዓመቱ ጄፍሪ ፌልትማን በዓለም አቀፍ ፖለቲካ የጥናት ተቋማት ውስጥ እጉልህ ሚና አላቸው። ፌልትማን በድርድርና የሽምግልና ጉዳዮች ላይ ጥናትን በማካሄድና በአደራዳሪነትም ከፍ ያለ ልምድ እንዳላቸው ይነገራል። ፌልትማን በፖለቲካዊና በውጭ ጉዳዳ ፖሊሲዎች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቀድሞውንና የአሁኑን ሊቃነ መናብርት ባን ኪሙን እና አንቶኒዮ ጉቱሬዝን ያማከሩ ሲሆን፤ ለጸጥታው ምክር ቤት በሠላምና በደኅንነት ጉዳዮች ማብራሪያዎችን በመስጠት ይታወቃሉ። በተባበሩት መንግሥታት ቆይታቸው ወቅትም በልዩ መልዕክተኝነት አገልግለዋል፤ በተጨማሪም በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጥ ለ26 ዓመታት ያገለገሉት ፌልትማን በሌባኖስ፣ በኢራቅ፣ በእስራኤል፣ በቱኒዚያ፣ በሃንጋሪና በሄይቲ ከፍተኛ ዲፕሎማት ሆነው አገልግለዋል። አሜሪካ በትግራይ ክልል ውስጥ ወታደራዊ ግጭት ከመከሰቱ በፊት በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ድርድር ውስጥ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አማካይነት ጭምር ስትሳተፍ መቆየቷ ይታወሳል። በተለይ በትግራይ ክልል ውስጥ የተከሰተውን ቀውስ ተከትሎ ከፍተኛ የአገሪቱ ባለስልጣንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ጨምሮ ከሌሎች የኢትዮጵያው ባለሥልጣናት ጋር በተደጋጋሚ መወያየታቸው ሲነገር ቆይቷል። ባለፈው መጋቢት ወርም የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ሴናተር ክሪስ ኩንስ ለቀናት የቆየ ጉብኝት በአዲስ አበባ አድርገው ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር ተወያይተው ነበር። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ትግራይ ውስጥ ስላለው ግጭትና የሰብአዊ ጉዳዮች ሁኔታ በተደጋጋሚ ጠንከር ያሉ መግለጫዎችና ንግግር ማድረጋቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃውሞ ማሰማቱ ይታወሳል። | አሜሪካ ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የሚያደርጉ ልዩ መልዕክተኛ ሾመች አሜሪካ በኢትዮጵያና በአካባቢዋ ባሉ አገራት ውስጥ ስላሉ ጉዳዮች በቅርበት የሚከታተሉላትን ልዩ መልዕክተኛ መሾሟን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አስታወቀ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ይፋ እንዳደረጉት በተለይ ኢትዮጵያ ለምትገኝበት የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ጄፍሪ ፌልትማንን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አድርገው መሾማቸውን ገልጸዋል። አሜሪካ አዲስ የሾመቻቸው የአፍሪካ ቀንድ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን በተለይ በኢትዮጵያና በዙሪያዋ ስላሉ ሁኔታዎች የተለየ ትኩረት እንደሚሰጡ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አመልክቷል። በዚህም መሠረት በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል ትግራይ ክልል ውስጥ ያለውን ግጭት ጨምሮ በአገሪቱ ያለው ተለዋወጭ ሁኔታ፣ ከሱዳን ጋር ያለውን የድንበር አለመግባባት እንዲሁም በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለው ውዝግብ የልዩ ልዑኩ ቀዳሚ ሥራ እንደሚሆን ተገልጿል። የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ በመግለጫው ላይ እናዳለው ቁልፍ በሆነው የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ "በአሁኑ ጊዜ መሠረታዊ ለውጥ እየተካሄደበት ነው" ብሏል። የአዲሱን ልዩ መልዕክተኛ አስፈላጊነት በተመለከተም በአካባቢው "በትውልዶች ውስጥ አንድ ጊዜ ለሚያጋጥም የለውጥ ዕድል አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የግጭት ስጋትን ለማስቀረት በከፍተኛ የሥልጣን ደረጃ የአሜሪካ ተሳትፎ አስፈላጊ" በመሆኑ ነው ብሏል። ይህ የልዩ መልዕክተኛ ሹመት የባይደን አስተዳደር በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለውን ተያያዥ የሆኑትን ፖለቲካዊ፣ የደኅንነትና የሰብአዊ ጉዳዮች ምፍትሔ እንዲያገኙ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ጥረቶችን ለመምራት ያለውን ቁርጠኝነት ያመለክታል ተብሏል። በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጥና በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ በከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ የሰሩት ጄፍሪ ፌልትማን በአፍሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች ላይ ለረጅም ዘመን ልምድ እንዳላቸው ተገልጿል። በተጨማሪም ፌልትማን በርካታ አገራትን ባካተቱ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሚደረጉ ድርድሮችና ሽምግልናዎች ውስጥ የአሜሪካንን ተያያዥ ስትራቴጂን በማስፈጸም ልምድ አላቸው ብሏል ሹመታቸውን ያሳወቀው መግለጫ። በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤትና በተባበሩት መንግሥት ውስጥ በተለያዩ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ላይ በመሥራት ሠፊ ልምድ እንዳላቸው የሚነገርላቸው የ62 ዓመቱ ጄፍሪ ፌልትማን በዓለም አቀፍ ፖለቲካ የጥናት ተቋማት ውስጥ እጉልህ ሚና አላቸው። ፌልትማን በድርድርና የሽምግልና ጉዳዮች ላይ ጥናትን በማካሄድና በአደራዳሪነትም ከፍ ያለ ልምድ እንዳላቸው ይነገራል። ፌልትማን በፖለቲካዊና በውጭ ጉዳዳ ፖሊሲዎች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቀድሞውንና የአሁኑን ሊቃነ መናብርት ባን ኪሙን እና አንቶኒዮ ጉቱሬዝን ያማከሩ ሲሆን፤ ለጸጥታው ምክር ቤት በሠላምና በደኅንነት ጉዳዮች ማብራሪያዎችን በመስጠት ይታወቃሉ። በተባበሩት መንግሥታት ቆይታቸው ወቅትም በልዩ መልዕክተኝነት አገልግለዋል፤ በተጨማሪም በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጥ ለ26 ዓመታት ያገለገሉት ፌልትማን በሌባኖስ፣ በኢራቅ፣ በእስራኤል፣ በቱኒዚያ፣ በሃንጋሪና በሄይቲ ከፍተኛ ዲፕሎማት ሆነው አገልግለዋል። አሜሪካ በትግራይ ክልል ውስጥ ወታደራዊ ግጭት ከመከሰቱ በፊት በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ድርድር ውስጥ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አማካይነት ጭምር ስትሳተፍ መቆየቷ ይታወሳል። በተለይ በትግራይ ክልል ውስጥ የተከሰተውን ቀውስ ተከትሎ ከፍተኛ የአገሪቱ ባለስልጣንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ጨምሮ ከሌሎች የኢትዮጵያው ባለሥልጣናት ጋር በተደጋጋሚ መወያየታቸው ሲነገር ቆይቷል። ባለፈው መጋቢት ወርም የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ሴናተር ክሪስ ኩንስ ለቀናት የቆየ ጉብኝት በአዲስ አበባ አድርገው ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር ተወያይተው ነበር። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ትግራይ ውስጥ ስላለው ግጭትና የሰብአዊ ጉዳዮች ሁኔታ በተደጋጋሚ ጠንከር ያሉ መግለጫዎችና ንግግር ማድረጋቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃውሞ ማሰማቱ ይታወሳል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56867423 |
2health
| ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መጨመር እንዳሳሰባት ገለፀች | በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ደቡብ ሱዳን እንዳሳሰባት ገልፃለች። መጋቢት ወር ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጀምሮ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመጣባት ኢትዮጵያ በባለፉት ሳምንታት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደቡብ ሱዳኗ መዲና ጁባ በየቀኑ ከአዲስ አበባ በረራ የሚያደርግ ሲሆን ይሄም ሁኔታ አስጊ ነው በማለት የጤና ባለስልጣናቱ ተናግረዋል። "በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመር በእርግጥ ሊያሳስበን ይገባል፤ ስለዚህ የመከላከያ መንገዶቻችንንም ልናጠናክር ይገባል" በማለት የጤና ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ዶክተር ቶው ሎይ ሲንጎት በጁባ ለሚገኙ ሪፖርተሮች ተናግረዋል። ሆኖም ከአዲስ አበባ ወደ ጁባ በየቀኑ የሚደረጉት በረራዎችም እንደሚቀጥሉ የተናገሩት ቃለ አቀባይ ሁሉም አገራት ለዜጎቹ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት እንደሚደረገው ከፍተኛ ጥንቃቄን ተግባራዊ እናደርጋለን ብለዋል። "ከአዲስ አበባ የሚደረጉ የየቀኑ በረራዎች የሚቀጥሉ ይሆናል። አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ካልሆነ አይቆምም" ብለዋል ዶክተር ቶው ሎይ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 59 ሺህ 648 ደርሷል፤ ከነዚህም ውስጥ 21 ሺህ 789 ያገገሙ ሲሆን 933 ህይወታቸው እንዳለፈ በትናንትናው ዕለት የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጋራ መግለጫ አስፍሯል። | ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መጨመር እንዳሳሰባት ገለፀች በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ደቡብ ሱዳን እንዳሳሰባት ገልፃለች። መጋቢት ወር ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጀምሮ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመጣባት ኢትዮጵያ በባለፉት ሳምንታት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደቡብ ሱዳኗ መዲና ጁባ በየቀኑ ከአዲስ አበባ በረራ የሚያደርግ ሲሆን ይሄም ሁኔታ አስጊ ነው በማለት የጤና ባለስልጣናቱ ተናግረዋል። "በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመር በእርግጥ ሊያሳስበን ይገባል፤ ስለዚህ የመከላከያ መንገዶቻችንንም ልናጠናክር ይገባል" በማለት የጤና ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ዶክተር ቶው ሎይ ሲንጎት በጁባ ለሚገኙ ሪፖርተሮች ተናግረዋል። ሆኖም ከአዲስ አበባ ወደ ጁባ በየቀኑ የሚደረጉት በረራዎችም እንደሚቀጥሉ የተናገሩት ቃለ አቀባይ ሁሉም አገራት ለዜጎቹ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት እንደሚደረገው ከፍተኛ ጥንቃቄን ተግባራዊ እናደርጋለን ብለዋል። "ከአዲስ አበባ የሚደረጉ የየቀኑ በረራዎች የሚቀጥሉ ይሆናል። አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ካልሆነ አይቆምም" ብለዋል ዶክተር ቶው ሎይ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 59 ሺህ 648 ደርሷል፤ ከነዚህም ውስጥ 21 ሺህ 789 ያገገሙ ሲሆን 933 ህይወታቸው እንዳለፈ በትናንትናው ዕለት የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጋራ መግለጫ አስፍሯል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54068173 |
5sports
| በአሜሪካ ታዋቂ አትሌቶች የወሲብ ጥቃቶችን ችላ በማለት ኤፍቢአይን ሊከሱ ነው | በአሜሪካ የብሔራዊ የጂምናስቲክ ቡድን ዶክተር የወሲብ ጥቃት ደርሶብናል ያሉ አትሌቶች ኤፍቢአይን በ1 ቢሊዮን ዶላር ካሳ ሊከሱ ነው። ቅሬታ አቅራቢዎቹ የአሜሪካ ፌደራል የምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) በሕክምና ባለሙያው ላሪ ናሳር የተፈጸሙ የወሲብ ጥቃቶች ላይ ተዓማኒነት ያላቸው መረጃዎች ቢቀርቡም በአግባቡ አላስተናገደም ብለዋል። ከከሳሾቹም መካከል የኦሎምሊክ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዎቹ ሲሞን ባይልስ፣ አሊ ሬይስማን እና ማኬይላ ማሮኒ ይገኙበታል። ዶክተር ላሪ ናስር የጂምናስቲክ ስፖርተኞቹ ላይ ትንኮሳ እንዲሁም ወሲባዊ ጥቃቶችን በማድረስ ወንጀል የ175 ዓመት እስራት ተፈርዶበት በእስር ላይ ይገኛል። የኤፍቢአይ የበላይ ጠባቂ በበኩሉ ኤፍቢአይ ስለ ዶክተሩ የቀረበውን ክስ ችላ ማለቱንና የምርመራው ጅማሮ ላይም ስህተቶችን መሥራቱን አጋልጧል። ባለፈው ዓመት በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአሜሪካ የፍትሕ ዲፓርትመንት የዋና ኢንስፔክተር ጽሕፈት ቤት ሪፖርት ኤፍቢአይ በዶክተሩ ላይ ስላከናወነው ምርመራ ግምገማ ሰጥቷል። በሪፖርቱ መሠረት በአውሮፓውያኑ 2015 ዶክተሩ ፈፅሟቸዋል በተባሉ ጥቃቶች ላይ ምርመራ ቢጀመርም ምንም ነገር ሳይደረግ ከአንድ ዓመት በላይ እንዲቀጥል ተደርጓል ይላል። ለዚህም የኤፍቢአይ ወኪሎች ስህተቶችን በመፈጸም እንዲሁም ሆን ብለው ለመሸፋፈን እንደሞከሩ ሪፖርቱ አመልክቷል። ለኤፍቢአይ ሪፖርት ከተደረገ በኋላም ዶክተሩ ወሲባዊ ጥቃት እንዳደረሰባቸው ተከሳሾቹ አጋልጠዋል። አብዘኞቹ የአሜሪካ ብሔራዊ የጂምናስቲክ ፕሮግራም አካል እንዲሁም በሚቺጋን ዩኒቨርስቲ በሚገኘው የዶክተሩ ክሊኒክ ሕክምና ይከታተሉ የነበሩ አትሌቶች ናቸው። ሪፖርት የተደረገላቸው የኤፍቢአይ መርማሪዎች እዚህ ግባ የማይባል እርምጃ እንደወሰዱ እና ምርመራ በማከናወን ዘርፉ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አላደረጉም እንዲሁም ሌሎች ባለሥልጣናትን አላስጠነቀቁም ተብሏል። “የነዚህ ወሲባዊ ጥቃቶች ሰለባ የሆንን አትሌቶች እኛን ሊጠብቁን በሚገቡ ሁሉም ተቋማት ማለትም በአሜሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ በአሜሪካ ጂምናስቲክስ፣ በኤፍቢአይ እንዲሁም በፍትሕ ዲፓርትመንቱ ተክደናል” በማለት የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነችው ኬይላ ማሮኒ በሰጠችው መግለጫ ተናግራለች። ከሁለት ሳምንት በፊት የአሜሪካ የፍትሕ ዲፓርትመንት ኤፍቢአይ ምርመራውን በተሳሳተ መንገድ ይዘውታል የተባሉ ሁለት የኤፍቢአይ ወኪሎች ላይ ክስ ላለመመሥረት ወስኗል። ከሳሾቹ አትሌቶች ተቋሙ ላደረሰው ጉዳት ካሳ የጠየቁ ሲሆን ይህም ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚሆን ይጠበቃል። | በአሜሪካ ታዋቂ አትሌቶች የወሲብ ጥቃቶችን ችላ በማለት ኤፍቢአይን ሊከሱ ነው በአሜሪካ የብሔራዊ የጂምናስቲክ ቡድን ዶክተር የወሲብ ጥቃት ደርሶብናል ያሉ አትሌቶች ኤፍቢአይን በ1 ቢሊዮን ዶላር ካሳ ሊከሱ ነው። ቅሬታ አቅራቢዎቹ የአሜሪካ ፌደራል የምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) በሕክምና ባለሙያው ላሪ ናሳር የተፈጸሙ የወሲብ ጥቃቶች ላይ ተዓማኒነት ያላቸው መረጃዎች ቢቀርቡም በአግባቡ አላስተናገደም ብለዋል። ከከሳሾቹም መካከል የኦሎምሊክ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዎቹ ሲሞን ባይልስ፣ አሊ ሬይስማን እና ማኬይላ ማሮኒ ይገኙበታል። ዶክተር ላሪ ናስር የጂምናስቲክ ስፖርተኞቹ ላይ ትንኮሳ እንዲሁም ወሲባዊ ጥቃቶችን በማድረስ ወንጀል የ175 ዓመት እስራት ተፈርዶበት በእስር ላይ ይገኛል። የኤፍቢአይ የበላይ ጠባቂ በበኩሉ ኤፍቢአይ ስለ ዶክተሩ የቀረበውን ክስ ችላ ማለቱንና የምርመራው ጅማሮ ላይም ስህተቶችን መሥራቱን አጋልጧል። ባለፈው ዓመት በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአሜሪካ የፍትሕ ዲፓርትመንት የዋና ኢንስፔክተር ጽሕፈት ቤት ሪፖርት ኤፍቢአይ በዶክተሩ ላይ ስላከናወነው ምርመራ ግምገማ ሰጥቷል። በሪፖርቱ መሠረት በአውሮፓውያኑ 2015 ዶክተሩ ፈፅሟቸዋል በተባሉ ጥቃቶች ላይ ምርመራ ቢጀመርም ምንም ነገር ሳይደረግ ከአንድ ዓመት በላይ እንዲቀጥል ተደርጓል ይላል። ለዚህም የኤፍቢአይ ወኪሎች ስህተቶችን በመፈጸም እንዲሁም ሆን ብለው ለመሸፋፈን እንደሞከሩ ሪፖርቱ አመልክቷል። ለኤፍቢአይ ሪፖርት ከተደረገ በኋላም ዶክተሩ ወሲባዊ ጥቃት እንዳደረሰባቸው ተከሳሾቹ አጋልጠዋል። አብዘኞቹ የአሜሪካ ብሔራዊ የጂምናስቲክ ፕሮግራም አካል እንዲሁም በሚቺጋን ዩኒቨርስቲ በሚገኘው የዶክተሩ ክሊኒክ ሕክምና ይከታተሉ የነበሩ አትሌቶች ናቸው። ሪፖርት የተደረገላቸው የኤፍቢአይ መርማሪዎች እዚህ ግባ የማይባል እርምጃ እንደወሰዱ እና ምርመራ በማከናወን ዘርፉ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አላደረጉም እንዲሁም ሌሎች ባለሥልጣናትን አላስጠነቀቁም ተብሏል። “የነዚህ ወሲባዊ ጥቃቶች ሰለባ የሆንን አትሌቶች እኛን ሊጠብቁን በሚገቡ ሁሉም ተቋማት ማለትም በአሜሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ በአሜሪካ ጂምናስቲክስ፣ በኤፍቢአይ እንዲሁም በፍትሕ ዲፓርትመንቱ ተክደናል” በማለት የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነችው ኬይላ ማሮኒ በሰጠችው መግለጫ ተናግራለች። ከሁለት ሳምንት በፊት የአሜሪካ የፍትሕ ዲፓርትመንት ኤፍቢአይ ምርመራውን በተሳሳተ መንገድ ይዘውታል የተባሉ ሁለት የኤፍቢአይ ወኪሎች ላይ ክስ ላለመመሥረት ወስኗል። ከሳሾቹ አትሌቶች ተቋሙ ላደረሰው ጉዳት ካሳ የጠየቁ ሲሆን ይህም ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚሆን ይጠበቃል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c4nwddg511go |
5sports
| በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. | በጋ ፈረንጆቹን ያፈካቸዋል። ኮምጫጫ አውሮፓዊ ለማያውቀው መንገደኛ ሳይቀር ፈገግታ የሚመጸውትበት ጊዜ ነው። ለሀበሾችስ ቢሆን? በጋው የፌሽታ ነው። በረዶ ያቆፈነው በጓንት የተጀቦነ እጅ እንጀራ ለመጠቅለል የሚፍታታበት ወቅት ነው። ካፖርታና ጋቢ ወዲያ የሚሽቀነጠርበት ወቅት ነው። በከፊል ዕርቃን መዘነጥ የሚያስችል በቂ ንዳድ አለ። ከሁሉ በላይ ዓመታዊው የባህልና ስፖርት አውደፌሽታ አለ። ቁርጥ አለ፤ በቂቤ ያበደ ሽሮ አለ፤ ጎረድ ጎረድ አለ። ቡናው ይንከሸከሻል…እጣኑ ይንቦለቦላል…፤ የአገር ሰው ከዚህ በላይ ምን ይሻል? ይህ አገር ቤት እየኖረ እንግሊዝኛ ለሚቀናው ሰው ‹‹ሶ ዋት?›› የሚያስብል ሊሆን ይችላል። ከአገር ለራቀ ሰው ግን ትርጉሙ ራስ ዳሽን ነው። ለዚህም ነው ለዓመታዊው የሐበሾች ‹‹መካ›› በየዓመቱ በሺዎች የሚተሙት፡፡ ዘንድሮ ተረኛዋ ዙሪክ ነበረች። እጅግ አምሮባት ተኩላ ነበር እንግዶቿን የጠበቀችው። እርግጥ ነው በነዚህ መድረኮች ላይ ሀበሾቹ የሚገናኙት ለሳቅ ለጨዋታ ነው። የሚጠራሩት ለእስክስታና ፌሽታ ነው። ሆኖም ክትፎና ቁርጥ ቀማምሰው ሲጨርሱ ቡጢ ይቀማመሳሉ። መነሻው ምንም ሊሆን ይችላል። በሐበሾች መንደር ግን ጸብ ጠፍቶ አያውቅም። በዙሪክ ይህ ባይሰተዋልም በስቱትጋርት ሆኗል። •"እናቴ ካልመጣች አልመረቅም" ኢዛና ሐዲስ ከማንችስተር ዩኒቨርስቲ እንዴት እጅግ የተነፋፈቀ የአገር ልጅ ለያውም በሰው አገር፣ ለያውም ለሳቅ ለጨዋታ ተጠራርቶ ቡጢ እንደሚሰነዛዘር መተንተን የቻለ ሊቅ ለጊዜው አልተገኘም። ብቻ የአገር ልጆች በየዓመቱ ተሰባስበው የ‹‹ፍቅር ቡጢ››ን እንካ ቅመስ-እንቺ ቅመሽ ሲባባሉ ዓመታት አስቆጥረዋል። ለምሳሌ የዛሬ ዓመት የፌሽታው አስተናጅ ስቱትጋርት ነበረች። ቴዲ አፍሮ መጥቶ አፍሮ ተመልሷል፤ ሳይዘፍን። ንብረት ወድሟል። የአዳራሽ መስታወት እንዳልነበር ሆኗል። የጀመርን ፖሊስ ‹‹ኤሎሄ! ዘንድሮ ምን ጉድ ላ'ክብን›› ብሏል። ጸቡ ከእኛም አልፎ ወንድም ኤርትራዊያንን ያሳተፈ ነበር። የቢራ ጠርሙስ ከአንድ ኢትዮጵያዊ እጅ ተምዘግዝጎ ሌላ ኢትዮጵያ የራስ ቅል ላይ አርፏል። ሀበሾች ሲገናኙ ‹‹አብሿቸው›› ይነሳል መሰለኝ ፍቅራቸው በጸብ ካልደመቀ…። ኢትዮጵያዊያኑ ወደ ዙሪክ የከተሙት ይህንኑ የጸብ ትዝታ ይዘው ነበር። ዙሪክ አላሳፈረቻቸውም። ለሰላሙ ቅድሚያ ሰጥታ አጫውታ፣ አዝናንታ አፋቅራ ሸኝታቸዋለች። በአሉታዊነቱ ስቱትጋርት እንደ ምሳሌ ተነሳ እንጂ፣ ሮም በ2012 ‹‹የፌዴሬሽኑን ገንዘብ ይዘው ተሰውረዋል›› በሚሉና ‹‹እንዲያውም አዘጋጅተን ከሰርን›› በሚሉት መሀል መራር ጸብ ነበር። ደግነቱ የሮም ጸበኞች ዘንድሮ በዙሪክ ይቅር ለእግዛብሔር ተባብለዋል። በ2014 ሙኒክ ላይም ምክንያቱ መናኛ የሆነ ዱላ መማዘዝ ነበር። ‹‹ሐበሻ ድሮም አብሮ መብላት እንጂ…አብሮ መሥራት…›› የሚል ተረት የሚያስተርቱ አጋጣሚዎች በርካታ ነበሩ። ሆኖም ይህን ሁሉ ዓመት ከጸብና መወነጃጀል መራቅ ለምን አልተቻለም? የሚለው ጥያቄ ዛሬም ሙሉ በሙሉ ምላሽ አላገኘም። አንድ ሁለት ምክንያቶችን መዘርዘር ግን ይቻላል። አንዱ በየዝግጅቶቹ ውስጥ የአገር ቤቱ ፖለቲካ የሚያጠላው ጥላ ሰፊ መሆኑ ነው። ሌላው በጎ ፈቃድ እንጂ የአመራር ክህሎት በሌላቸው ሰዎች ትልቅ ድግስ መሰናዳቱ የሚፈጥረው ትርምስ ነው። ሦስተኛው ለጥቅም መንሰፍሰፍ ነው። •የጄኔራል ደምሴ ቡልቶ ልጅ 'መራር' ትዝታ ‹‹እንዲህ ዓይነቱን ሺህዎች የሚታደሙበት አውደ ፌሽታ ለማሰናዳት ከመቶ እስከ ሁለት መቶ ሺህ ዩሮ ፈሰስ መደረጉ አይቀርም›› ይላሉ ወጪውን የሚያውቁት። ይህንን ወጪ ለመመለስ፣ ብሎም በትርፍ ለመንበሽበሽ አድብቶ የሚጠብቀው ብዙ ነው፤ በዚህ መሀል ትርምስ ይፈጠራል። ከፍተኛ የጥቅም ግጭት ይነሳል። ‹‹ስልጡን አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሰለጠነ መንገድ መነጋገር ይሳናቸዋል። በሰለጠነ መንገድ ሂሳብ ኦዲት አያስደርጉም። በሰለጠነ መንገድ ወጪና ገቢ አያሰሉም። መጨረሻው የማያምረው ለዚህ ይመስለኛል›› ይላል በዓመታት ውስጥ ባየው ነገር ተስፋ ቆርጦ ራሱን ከአዘጋጅነት ተሳትፎ ያገለለ ወጣት ለቢቢሲ። የዙሪኩ መሰናዶ ግን በሁሉም መለኪያ የተሻለና የተዋጣለት መሆኑ ለብዙዎች መልካም ስሜትን ፈጥሯል። ለሌሎች ቀጣይ አዘጋጅ ቡድኖችና ከተሞችም ምሳሌ መሆን የሚችል ነበር። ከደርግ ጀምሮ ከዚያም ቀደም ብሎ ከአገር የወጡ ኢትዮጵያዊያን አሉ። በአውሮፓ የሚኖሩ የድሮ የብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ብዛታቸው ለጉድ ነው። ይህ ዓመታዊ አውደ ፌሽታ ታዲያ ለአንዳንዶች የፌሽታ ያህል ፌዝ አይደለም። የምር ጉዳይ ነው። የአገር ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያን ናፍቀው ኢትዮጵያ መግባት የማይችሉ በርካታ ዜጎች ነበሩ። በፖለቲካም ይሁን በያዙት የስደተኛ ወረቀት ምክንያት። ስለዚህ ኢትዮጵያዊን ባይረግጡም ‹‹የኢትዮጵያን ኮፒ›› መርገጥ ይፈልጋሉ። በአውሮፓ የኢትዮጵያ ኮፒ ደግሞ ይህ ዓመታዊ አውደ ፌሽታ ብቻ ነው። በዚህ ምክንያት ዝግጅቱን እንደዋዛ አያዩትም። በማንከሽከሻ የሚቆላ ቡና…እጅ የሚያስቆረጥም ቁርጥ…ምራቅ የሚያስውጥ ክትፎ፣ ከሸክላ የሚንቆረቆር አገርኛ ሙዚቃ…ከኢትዮጵያ ብዙ ሚሊየን ማይሎች ርቆ ለሚኖር ሰው ቀልድ አይደለም፡፡ መዝናኛ ብቻ አይደለም። አገር የመግባት ያህል ነው። ለነዚህ ኢትዮጵያዊያ የአገርን፣ የአገር ልጅን ናፍቆትም ለመወጣት ሁነኛ ሥፍራ ይኸው መድረክ የሆነውም ለዚሁ ነው። ጎረቤታሞች ቡና ሊጠራሩ ቀርቶ በማይተያዩበት፣ በሁለት ሦስት ሥራ ደፋ ቀና ካላሉ ሕይወት በማይገፋበት፣ ጥሬ ሥጋ መጉረስ ዜና በሚሆንበት አውሮፓ ኢትዮጵያዊያንን የሚያገናኘው ፌስቲቫል ከተጀመረ ዘንድሮ 17ኛ ዓመቱን ይዟል። አውሮፓ ውስጥ ኢትዮጵያውያን የሚገናኙበት ምናልባትም ብቸኛው ፌስቲቫል ነው። ለዚህም ነው ጁላይ 31 እስከ ኦገስት 2! ብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን በቀን መቁጠሪያቸው ላይ በደማቅ ቀለም ያከበቡት። ቀኑ ሲደርስ ራቅ ካሉቱ እንደ ኖርዌይ እና ስዊዲን በጢያራ በረሩ። ቀረብ ካሉቱ ከጀርመን፣ ከፈረንሳይ፣ ከእንግሊዝ…በአውቶቡስ ተሳፈሩ፣ የባቡር ትኬት ቆረጡ፣ የመኪናቸውን ሞተር ቀሰቀሱ። ሆኖም ድንበር ሲደርሱ ስዊዘርላንድ ‹‹የማይደረገውን!?›› አለች። ስዊዘርላንድ ከተቀሩት የአውሮፓ አገሮች የድንበሯን ነገር በዋዛ ባለመመልከት ትታወቃለች። በቂ የጉዞ ሰነድ የላቸውም ያለቻቸውን ኢትዮጵያዊያንን ወደመጡበት መልሳቸዋለች። ከእነዚህ መካከል በዙሪክ ለመጫወት የተንቀሳቀሱት የፈረንሳዩ ኢትዮ-ማርሴይ የእግር ኳስ ቡድን እና ከኢትዮ-ፍራንክፈርት ሁለት ቡድኖች አንዱ፣ እንዲሁም የጀመርኑ ዳርምሽታት የእግር ኳስ ቡድን አባላት በከፊል ይገኙበታል። አብዛኞቹ በሚኖሩበት አገር ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ ተሰጥቷቸው የዜግነት ማረጋገጫ ወረቀት የሚጠብቁ ወይም የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበው ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ወይም ጭርሱኑ ያላገኙ ናቸው። የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ አሳየኸኝ ጥላሁን ለቢቢሲ እንደተናገሩት እንግሊዝ ከ40ሺ የሚልቁ ኢትዮጵያዊያን የሚገኙባት አገር ሆኖ ነገር ግን ይህ ፌስቲቫል እንግሊዝ የማይዘጋጅበት አንዱ ምክንያት እንዲህ ዓይነቱ ችግር እንዳያጋጥምና ኢትዮጵያዊያኑ እንዳይንገላቱ በመስጋት እንደነበር ያስረዳሉ። ‹‹ይህ ዝግጅት ለብዙ ኢትዮጵያዊያን ዓመታዊ የሥነ ልቦና ቴራፒ የሚያገኙበት ነው። በጉጉት የሚጠብቁት ነው፤ ከድንበር መመለሳቸው ያሳዘነን ጉዳይ ነው›› ይላሉ አቶ አሳየኸኝ። ፌስቲቫሉ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2001 ላይ ሲጀመር ከአንድ ቀን የእግር ኳስ ግጥሚያ የዘለለ አልነበረም። 2003 ላይ ግን የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቾች ማለትም ግርማ ሳህሌ፣ ዩሀንስ መሰለ፣ ከበደ ኃይሌና ሌሎችም፤ በተዋቀረ ሁኔታ የሚንቀሳቀስ ፌደሬሽን መመሥረታቸውን በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የባህልና የስፓርት ፌደሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ብስራት ይናገራል። ፌስቲቫሉ በተጀመረበት ወቅት አውሮፓ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እንደዛሬው አልተበራከቱም ነበር። የእግር ኳስ ቡድኖቹ በቂ ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ስለማያገኙ አውሮፓውያንን ያካትታሉ። ያኔ ፌስቲቫሉ እንደዛሬው ብዙ ኢትዮጵያውያን ታዳሚዎችም አልነበሩትም። "ከ2007 ወዲህ የሊቢያ መንገድ ሲከፈት ወጣቱ ግልብጥ ብሎ ወደ አውሮፓ መጣ። እዚያ የሚኖሩ ህጻናትም እያደጉ የእግር ኳስ ቡድኖችን መቀላቀል ጀመሩ። በጣም ጠንካራ ኳስ መጫወት የተጀመረው ከዚያ ወዲህ ነው" ይላል ዳንኤል። ባለፈው ዓመት ፌስቲቫሉ የተካሄደው በጀርመኗ ስቱትጋርት ነበር። ከዚያ በፊት ሮም፣ ጄኔቭ፣ ስቶኮልም፣ አምስተርዳምና ሌሎችም የአውሮፓ ከተሞች ፌስቲቫሉን አስተናግደዋል። አውሮፓ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ባቋቋሟቸው ቡድኖች መካከል የሚካሄድ የእግር ኳስ ግጥሚያ ፌስቲቫሉን ደማቅ ያደርገዋል። ዘንድሮ አበበ ቢቂላ፣ ሻላ እና ቡና የተባሉ የጤና ቡድኖች መቀመጫቸውን አውሮፓ ካደረጉት ቡድኖች ጋር ለመፋለም ከኢትዮጵያ ወደ ዙሪክ አቅንተዋል። በስም ከሚታወቁት የቀድሞ ተጨዋቾች መካከል ሳሙኤል ደምሴ (ኩኩሻ)፣ ስንታየሁ ጌታቸው (ቆጬ)፣ ተክሌ ብርሃኔ፣ ቴዎድሮስ ቦካንዴ፣ ሃብቶም ብርሃኔ፣ ሰይፈ ውብሸት፣ ጌታቸው ካሳ (ቡቡ)፣ ኃይሉ አድማሱ (ቻይና)፣ግርማ ሳህሌ ይጠቀሳሉ። በነዚህ ጨዋታዎች በየዓመቱ ይገኛሉ። በዘንድሮው የሦስት ቀን ፌስቲቫል ከአምስት ሺህ እስከ አስር ሺህ ሰዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የፌስቲቫሉ አዘጋጅ የሆነው ኢትዮ-ዙሪክ ቡድን ፕሬዘዳንት ሙሉጌታ በየነ በመክፈቻው ዕለት ለቢቢሲ ተናግረዋል። በፌስቲቫሉ ላይ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያን ባህል የሚወዱ የሌሎች አገሮች ዜጎችም ይገኛሉ። ኢትዮጵያዊያንን ያገቡ ዜጎች ይህ ዝግጅት ነፍሳቸው ነው። ከሰሜን አሜሪካው ፌስቲቫል ቀጥሎ ኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ ውጪ የሚገናኙበት ፌስቲቫል እንደመሆኑ ፍቅርና አንድነትን የሚያስተጋቡ ሙዚቀኞች መጋበዛቸውን ሙሉጌታ ይገልጻል። ዘንድሮ ጋሽ ማሕሙድና ስለሺ ደምሴ (ጋሽ አበራ ሞላን) ጨምሮ በርካታ ስመ ገናና ድምጻዊያን ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ራስ ምታት ከኢትዮጵያ ውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵዊያን ትኩሳት ይለቅባቸዋል።አሰላለፋቸው ያሸብራል። ልዩነታቸው የሀበሻ ሬስቶራንት ድረስ ይዘልቃል። የእንቶኔ ብሔር በቀነጠሰው በርበሬ የተሰራ ዶሮ ወጥ በአፌም አይዞር እስከማለት… በፖለቲካ አሰላለፍ ጎራ ተለይቶ መራኮት ዕለታዊ በሆነበት አውሮፓ 'አንዲት ኢትዮጵያ' በሚል ፌስቲቫል ማዘጋጀት ምን ይመስል ይሆን? የየወቅቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታስ ፌስቲቫሉ ላይ ጥላውን አላጠላም? ብለን አቶ ዳንኤልን ጠይቀነው ነበር። "…ፖለቲካው ፌስቲቫሉን ሊያፈርስ የደረሰበት ወቅትም ነበር" ሲል መልሷል። የእግር ኳስ ቡድኖች የመንግሥት ተቃዋሚና ደጋፊ በሚል እንደሚከፋፈሉ ካስታወሰ በኋላ በተለይ በምርጫ 97 ሰሞን የተካሄደውን የእግር ኳስ ግጥሚያ ያሸነፈው ቡድን አባላት በፖለቲካ አቋም ልዩነት ምክንያት አኩርፈው ዋንጫ ሳይቀበሉ ወደ መጡበት አገር መመለሳቸውን እንደ አብነት ያነሳል። "ከፖለቲካ ጋር ግንኙነት ያላቸው መገናኛ ብዙኃን ሲመጡ እንደ ፌደሬሽን የማስተናገድ ግዴታ አለብን ስንል የሚቃወሙ አካላት አሉ። ሜዳ ላይ ያለውን መንፈስ ይረብሻል። እነ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ፣ ታማኝ በየነ፣ ተስፋዬ ገብረአብ ይመጡ ነበር። ያ አንዳንዶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊፈጥር ይችላል። ግን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የመምጣት መብት አለው። አትምጡ ልንላቸው አንችልም›› ይላል፤ ያም ሆኖ መድረኩ ከፖለቲካ የጸዳ የባህልና የስፖርት ፌስቲቫል ብቻ እንዲሆን አዘጋጆቹ ይተጋሉ። ፌስቲቫሉን በየዓመቱ ማን ያዘጋጀው በሚለው ላይ ሁለት ተሞክሮዎች እንዳሉ አቶ ዳንኤል ያብራራል። እንደ ሰሜን አሜሪካው ውድድር ፌዴሬሽኑ ያሰናዳው ወይስ አዘጋጅ አገር? 2017 ላይ የፌስቲቫሉ አዘጋጅ ፌደሬሽኑ እንዲሆን ተወስኖ ጣልያን ውስጥ ፌስቲቫሉን ለማካሄድ መሰናዶ ተጀምሮ ነበር። ሆኖም የፌደሬሽኑ አመራሮች ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ እሰጣ ገባ መፈጠሩን ይናገራል። ከዚህ የሮሙ ክስተት በኋላ ፌስቲቫሉ በየዓመቱ በተለያዩ የእግር ኳስ ቡድኖች እንዲዘጋጅ ውሳኔ ተላለፈ። በዚህም መሠረት የዘንድሮውን ፌስቲቫል ያዘጋጀው ኢትዮ-ዙሪክ ቡድን ነው። የኢትዮ ዙሪክ ቡድኑ ፕሬዝዳንት ሙሉጌታ፤ ፖለቲካው ለጊዜው እንዲቆይ ይማጸናል። ወደ ፌስቲቫሉ የሚሄዱ ሰዎች "ፖለቲካን ማሰብ የለባቸውም። እንዲያውም እዚያ ሜዳ ላይ ፌስቡክን አጥፍቶ፤ ሰላም ተባብሎ መጫወት፣ መብላት፣ መጠጣት፣ መሳቅን ነው ማየት የምንፈልገው" ሲል በበዓሉ መክፈቻ ዕለት ለቢቢሲ ምኞቹን አጋርቷል። የኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ፌስቲቫል አውሮፓ ውስጥ የተወለዱ የኢትዮጵያ ልጆች እነሱን ከሚመስሉ ልጆች ጋር የሚገናኙበትም መድረክ ነው። ብዙዎቹ ታዲያ በግማሽ ኢትዮጵያዊ ካልሆኑ ወላጆች የተገኙ ናቸው። በተለይ ኢትዮጵያን ረግጠው የማያውቁ የኢትዮጵያዊያን ልጆች በእናት በአባታቸው ቋንቋ እየተኮላተፉ ሲያወሩ መስማት አንዳች ልዩ ስሜት ያጭራል። በየዓመቱ የሚጋበዙት ኢትዮጵያዊያን ሙዚቀኞች ታዳጊዎቹን ከአገሪቱ ባህል ጋር በመጠኑም ቢሆን ያስተዋውቋቸዋል። ‹‹ፌስቲቫሉ የአዋቂዎች ብቻ መሆን የለበትም፤ ለነዚህ ሕጻናት በቂ ትኩረት መሰጠት አለበት›› ይላል ለዚሁ መሰናዶ ዙሪክ የሚገኘው ጋሽ አበራ ሞላ። የእግር ኳስ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊዎች ዕድለኛ ከሆኑ ለተለያዩ አገራት ብሔራዊ ቡድኖችና ክለቦች ሊታጩ የሚችሉትም በዚሁ ፌስቲቫል ላይ ነው። በደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ዋንጫ ብሔራዊ ቡድናችን ላይ የተሰለፈው ዩሱፍ ሳሊህ ከዚሁ መድረክ የተገኘ ነው። ፌስቲቫሉን ለመታደም በዙሪክ፣ ክሎተን ስቴድየም ከተገኙ ኢትዮጵያዊያን አንዷ የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ ቅድስት በላይ ናት። በልጆች ክፍለ ጊዜ መርሀ ግብር የምትታወቀው ቅድስት የምትኖረው ስዊዘርላንድ ሲሆን፤ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል ላይ ስትሳተፍ የዘንድሮው የመጀመሪያዋ ነው። ፌስቲቫሉ፤ አውሮፓ ውስጥ ተወልደው በምዕራባውያን ባህል የሚያድጉ ልጆች ስለ ኢትዮጵያ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ትናገራለች። "ስብስቡ ማኅበራዊ ትስስሩን ያጠነክራል። ልጆችም በጣም ደስተኛ ይሆናሉ። ለምሳሌ የጓደኛዬ ቤተሰቦች ከኖርዌይ መጥተው ከሌሎች ልጆች ጋር ስለ ስዊዝና ኖርዌይ ባህል ሲያወሩ ነበር።" ኢትዮጵያዊያን በብዛት በሌሉበት አካባቢ ለሚኖሩ ልጆች፣ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በሚውለበለብበት፣ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በሚነገሩበት፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦች በሚበሉበት ቦታ መገኘትን የሚተካ ነገር እንደሌለም ቅድስት ታስረዳለች። አውሮፓ በሮቿን ለስደተኞች ባትዘጋም ከጊዜ ወደ ጊዜ ሽንቁሩ እየጠበበ ይመስላል። ምናልባትም ለወደፊት ወደ አውሮፓ የሚሄዱ ኢትዮጵዊያን ቁጥር ያሽቆለቁል ይሆናል። ይህ መላ ምት፤ አሁን በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የጀመሩትን ፌስቲቫል ለወደፊት የሚረከባቸው ይኖራልን? የሚል ጥያቄ ማጫሩ አይቀርም። ከኢትዮጵያዊያን እና ከሌሎች አገሮች ዜጎች የሚወለዱ ህጻናት እየተበራከቱ መጥተዋል። እነዚህ በከፊል ብቻ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ልጆች ከኢትዮጵያዊ ማንነታቸው ጋር የሚያስተሳስራቸው ፌስቲቫል አስፈላጊነት የሚታያቸው እስከ መቼ ነው? ሌላው ጥያቄ ነው። ዳንኤል የፌስቲቫሉ ቀጣይነት አያጠራጥርም ይላል። አንድም "በቀጣይ ለሚመጣው ትውልድ ብቸኛ መገናኛው ይህ ፌስቲቫል ነው" ሲል ያስረዳል። በልጅነታቸው ወደ አውሮፓ ቢሄዱም የእግር ኳስ ፌደሬሽኑን ለዓመታት ያገለገሉ ወጣቶች መኖራቸውም ተስፋ ይሰጠዋል። ዳንኤል፤ አውሮፓ ተወልደው ያደጉ ልጆች በፌስቲቫሉ ድምቀት በመማረክ ከዓመት ዓመት ቀጠሮ ሲይዙ አስተውሏል። ለነጭ ጓደኞቻቸው 'የኢትዮጵያ ፌስቲቫል ሄጄ ነበር' ብለው በኩራት እንደሚያወሩም ሰምቷል። እነዚህ ልጆች አሁን ያለውን ሥርዓት እንዲረከቡ ከተደረገ የፌስቲቫሉ ዕድሜ እንደሚረዝም ያምናል።የቡናው መዓዛ ሳይጠፋ…እስክስታው ሳይለዝዝ፣ ቁርጡ ሳይወደር፣ ሙዚቃው ሳይጎትት የዛሬ ዐሥር፣ ሀያ፣ ሠላሳ ዓመት ኢትዮጵያዊያኑ ይገናኙ ይሆን? ከብዙ ፍቅርና ከትንሽ ቡጢ ጋ'ም ቢሆን… | በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. በጋ ፈረንጆቹን ያፈካቸዋል። ኮምጫጫ አውሮፓዊ ለማያውቀው መንገደኛ ሳይቀር ፈገግታ የሚመጸውትበት ጊዜ ነው። ለሀበሾችስ ቢሆን? በጋው የፌሽታ ነው። በረዶ ያቆፈነው በጓንት የተጀቦነ እጅ እንጀራ ለመጠቅለል የሚፍታታበት ወቅት ነው። ካፖርታና ጋቢ ወዲያ የሚሽቀነጠርበት ወቅት ነው። በከፊል ዕርቃን መዘነጥ የሚያስችል በቂ ንዳድ አለ። ከሁሉ በላይ ዓመታዊው የባህልና ስፖርት አውደፌሽታ አለ። ቁርጥ አለ፤ በቂቤ ያበደ ሽሮ አለ፤ ጎረድ ጎረድ አለ። ቡናው ይንከሸከሻል…እጣኑ ይንቦለቦላል…፤ የአገር ሰው ከዚህ በላይ ምን ይሻል? ይህ አገር ቤት እየኖረ እንግሊዝኛ ለሚቀናው ሰው ‹‹ሶ ዋት?›› የሚያስብል ሊሆን ይችላል። ከአገር ለራቀ ሰው ግን ትርጉሙ ራስ ዳሽን ነው። ለዚህም ነው ለዓመታዊው የሐበሾች ‹‹መካ›› በየዓመቱ በሺዎች የሚተሙት፡፡ ዘንድሮ ተረኛዋ ዙሪክ ነበረች። እጅግ አምሮባት ተኩላ ነበር እንግዶቿን የጠበቀችው። እርግጥ ነው በነዚህ መድረኮች ላይ ሀበሾቹ የሚገናኙት ለሳቅ ለጨዋታ ነው። የሚጠራሩት ለእስክስታና ፌሽታ ነው። ሆኖም ክትፎና ቁርጥ ቀማምሰው ሲጨርሱ ቡጢ ይቀማመሳሉ። መነሻው ምንም ሊሆን ይችላል። በሐበሾች መንደር ግን ጸብ ጠፍቶ አያውቅም። በዙሪክ ይህ ባይሰተዋልም በስቱትጋርት ሆኗል። •"እናቴ ካልመጣች አልመረቅም" ኢዛና ሐዲስ ከማንችስተር ዩኒቨርስቲ እንዴት እጅግ የተነፋፈቀ የአገር ልጅ ለያውም በሰው አገር፣ ለያውም ለሳቅ ለጨዋታ ተጠራርቶ ቡጢ እንደሚሰነዛዘር መተንተን የቻለ ሊቅ ለጊዜው አልተገኘም። ብቻ የአገር ልጆች በየዓመቱ ተሰባስበው የ‹‹ፍቅር ቡጢ››ን እንካ ቅመስ-እንቺ ቅመሽ ሲባባሉ ዓመታት አስቆጥረዋል። ለምሳሌ የዛሬ ዓመት የፌሽታው አስተናጅ ስቱትጋርት ነበረች። ቴዲ አፍሮ መጥቶ አፍሮ ተመልሷል፤ ሳይዘፍን። ንብረት ወድሟል። የአዳራሽ መስታወት እንዳልነበር ሆኗል። የጀመርን ፖሊስ ‹‹ኤሎሄ! ዘንድሮ ምን ጉድ ላ'ክብን›› ብሏል። ጸቡ ከእኛም አልፎ ወንድም ኤርትራዊያንን ያሳተፈ ነበር። የቢራ ጠርሙስ ከአንድ ኢትዮጵያዊ እጅ ተምዘግዝጎ ሌላ ኢትዮጵያ የራስ ቅል ላይ አርፏል። ሀበሾች ሲገናኙ ‹‹አብሿቸው›› ይነሳል መሰለኝ ፍቅራቸው በጸብ ካልደመቀ…። ኢትዮጵያዊያኑ ወደ ዙሪክ የከተሙት ይህንኑ የጸብ ትዝታ ይዘው ነበር። ዙሪክ አላሳፈረቻቸውም። ለሰላሙ ቅድሚያ ሰጥታ አጫውታ፣ አዝናንታ አፋቅራ ሸኝታቸዋለች። በአሉታዊነቱ ስቱትጋርት እንደ ምሳሌ ተነሳ እንጂ፣ ሮም በ2012 ‹‹የፌዴሬሽኑን ገንዘብ ይዘው ተሰውረዋል›› በሚሉና ‹‹እንዲያውም አዘጋጅተን ከሰርን›› በሚሉት መሀል መራር ጸብ ነበር። ደግነቱ የሮም ጸበኞች ዘንድሮ በዙሪክ ይቅር ለእግዛብሔር ተባብለዋል። በ2014 ሙኒክ ላይም ምክንያቱ መናኛ የሆነ ዱላ መማዘዝ ነበር። ‹‹ሐበሻ ድሮም አብሮ መብላት እንጂ…አብሮ መሥራት…›› የሚል ተረት የሚያስተርቱ አጋጣሚዎች በርካታ ነበሩ። ሆኖም ይህን ሁሉ ዓመት ከጸብና መወነጃጀል መራቅ ለምን አልተቻለም? የሚለው ጥያቄ ዛሬም ሙሉ በሙሉ ምላሽ አላገኘም። አንድ ሁለት ምክንያቶችን መዘርዘር ግን ይቻላል። አንዱ በየዝግጅቶቹ ውስጥ የአገር ቤቱ ፖለቲካ የሚያጠላው ጥላ ሰፊ መሆኑ ነው። ሌላው በጎ ፈቃድ እንጂ የአመራር ክህሎት በሌላቸው ሰዎች ትልቅ ድግስ መሰናዳቱ የሚፈጥረው ትርምስ ነው። ሦስተኛው ለጥቅም መንሰፍሰፍ ነው። •የጄኔራል ደምሴ ቡልቶ ልጅ 'መራር' ትዝታ ‹‹እንዲህ ዓይነቱን ሺህዎች የሚታደሙበት አውደ ፌሽታ ለማሰናዳት ከመቶ እስከ ሁለት መቶ ሺህ ዩሮ ፈሰስ መደረጉ አይቀርም›› ይላሉ ወጪውን የሚያውቁት። ይህንን ወጪ ለመመለስ፣ ብሎም በትርፍ ለመንበሽበሽ አድብቶ የሚጠብቀው ብዙ ነው፤ በዚህ መሀል ትርምስ ይፈጠራል። ከፍተኛ የጥቅም ግጭት ይነሳል። ‹‹ስልጡን አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሰለጠነ መንገድ መነጋገር ይሳናቸዋል። በሰለጠነ መንገድ ሂሳብ ኦዲት አያስደርጉም። በሰለጠነ መንገድ ወጪና ገቢ አያሰሉም። መጨረሻው የማያምረው ለዚህ ይመስለኛል›› ይላል በዓመታት ውስጥ ባየው ነገር ተስፋ ቆርጦ ራሱን ከአዘጋጅነት ተሳትፎ ያገለለ ወጣት ለቢቢሲ። የዙሪኩ መሰናዶ ግን በሁሉም መለኪያ የተሻለና የተዋጣለት መሆኑ ለብዙዎች መልካም ስሜትን ፈጥሯል። ለሌሎች ቀጣይ አዘጋጅ ቡድኖችና ከተሞችም ምሳሌ መሆን የሚችል ነበር። ከደርግ ጀምሮ ከዚያም ቀደም ብሎ ከአገር የወጡ ኢትዮጵያዊያን አሉ። በአውሮፓ የሚኖሩ የድሮ የብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ብዛታቸው ለጉድ ነው። ይህ ዓመታዊ አውደ ፌሽታ ታዲያ ለአንዳንዶች የፌሽታ ያህል ፌዝ አይደለም። የምር ጉዳይ ነው። የአገር ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያን ናፍቀው ኢትዮጵያ መግባት የማይችሉ በርካታ ዜጎች ነበሩ። በፖለቲካም ይሁን በያዙት የስደተኛ ወረቀት ምክንያት። ስለዚህ ኢትዮጵያዊን ባይረግጡም ‹‹የኢትዮጵያን ኮፒ›› መርገጥ ይፈልጋሉ። በአውሮፓ የኢትዮጵያ ኮፒ ደግሞ ይህ ዓመታዊ አውደ ፌሽታ ብቻ ነው። በዚህ ምክንያት ዝግጅቱን እንደዋዛ አያዩትም። በማንከሽከሻ የሚቆላ ቡና…እጅ የሚያስቆረጥም ቁርጥ…ምራቅ የሚያስውጥ ክትፎ፣ ከሸክላ የሚንቆረቆር አገርኛ ሙዚቃ…ከኢትዮጵያ ብዙ ሚሊየን ማይሎች ርቆ ለሚኖር ሰው ቀልድ አይደለም፡፡ መዝናኛ ብቻ አይደለም። አገር የመግባት ያህል ነው። ለነዚህ ኢትዮጵያዊያ የአገርን፣ የአገር ልጅን ናፍቆትም ለመወጣት ሁነኛ ሥፍራ ይኸው መድረክ የሆነውም ለዚሁ ነው። ጎረቤታሞች ቡና ሊጠራሩ ቀርቶ በማይተያዩበት፣ በሁለት ሦስት ሥራ ደፋ ቀና ካላሉ ሕይወት በማይገፋበት፣ ጥሬ ሥጋ መጉረስ ዜና በሚሆንበት አውሮፓ ኢትዮጵያዊያንን የሚያገናኘው ፌስቲቫል ከተጀመረ ዘንድሮ 17ኛ ዓመቱን ይዟል። አውሮፓ ውስጥ ኢትዮጵያውያን የሚገናኙበት ምናልባትም ብቸኛው ፌስቲቫል ነው። ለዚህም ነው ጁላይ 31 እስከ ኦገስት 2! ብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን በቀን መቁጠሪያቸው ላይ በደማቅ ቀለም ያከበቡት። ቀኑ ሲደርስ ራቅ ካሉቱ እንደ ኖርዌይ እና ስዊዲን በጢያራ በረሩ። ቀረብ ካሉቱ ከጀርመን፣ ከፈረንሳይ፣ ከእንግሊዝ…በአውቶቡስ ተሳፈሩ፣ የባቡር ትኬት ቆረጡ፣ የመኪናቸውን ሞተር ቀሰቀሱ። ሆኖም ድንበር ሲደርሱ ስዊዘርላንድ ‹‹የማይደረገውን!?›› አለች። ስዊዘርላንድ ከተቀሩት የአውሮፓ አገሮች የድንበሯን ነገር በዋዛ ባለመመልከት ትታወቃለች። በቂ የጉዞ ሰነድ የላቸውም ያለቻቸውን ኢትዮጵያዊያንን ወደመጡበት መልሳቸዋለች። ከእነዚህ መካከል በዙሪክ ለመጫወት የተንቀሳቀሱት የፈረንሳዩ ኢትዮ-ማርሴይ የእግር ኳስ ቡድን እና ከኢትዮ-ፍራንክፈርት ሁለት ቡድኖች አንዱ፣ እንዲሁም የጀመርኑ ዳርምሽታት የእግር ኳስ ቡድን አባላት በከፊል ይገኙበታል። አብዛኞቹ በሚኖሩበት አገር ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ ተሰጥቷቸው የዜግነት ማረጋገጫ ወረቀት የሚጠብቁ ወይም የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበው ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ወይም ጭርሱኑ ያላገኙ ናቸው። የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ አሳየኸኝ ጥላሁን ለቢቢሲ እንደተናገሩት እንግሊዝ ከ40ሺ የሚልቁ ኢትዮጵያዊያን የሚገኙባት አገር ሆኖ ነገር ግን ይህ ፌስቲቫል እንግሊዝ የማይዘጋጅበት አንዱ ምክንያት እንዲህ ዓይነቱ ችግር እንዳያጋጥምና ኢትዮጵያዊያኑ እንዳይንገላቱ በመስጋት እንደነበር ያስረዳሉ። ‹‹ይህ ዝግጅት ለብዙ ኢትዮጵያዊያን ዓመታዊ የሥነ ልቦና ቴራፒ የሚያገኙበት ነው። በጉጉት የሚጠብቁት ነው፤ ከድንበር መመለሳቸው ያሳዘነን ጉዳይ ነው›› ይላሉ አቶ አሳየኸኝ። ፌስቲቫሉ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2001 ላይ ሲጀመር ከአንድ ቀን የእግር ኳስ ግጥሚያ የዘለለ አልነበረም። 2003 ላይ ግን የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቾች ማለትም ግርማ ሳህሌ፣ ዩሀንስ መሰለ፣ ከበደ ኃይሌና ሌሎችም፤ በተዋቀረ ሁኔታ የሚንቀሳቀስ ፌደሬሽን መመሥረታቸውን በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የባህልና የስፓርት ፌደሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ብስራት ይናገራል። ፌስቲቫሉ በተጀመረበት ወቅት አውሮፓ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እንደዛሬው አልተበራከቱም ነበር። የእግር ኳስ ቡድኖቹ በቂ ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ስለማያገኙ አውሮፓውያንን ያካትታሉ። ያኔ ፌስቲቫሉ እንደዛሬው ብዙ ኢትዮጵያውያን ታዳሚዎችም አልነበሩትም። "ከ2007 ወዲህ የሊቢያ መንገድ ሲከፈት ወጣቱ ግልብጥ ብሎ ወደ አውሮፓ መጣ። እዚያ የሚኖሩ ህጻናትም እያደጉ የእግር ኳስ ቡድኖችን መቀላቀል ጀመሩ። በጣም ጠንካራ ኳስ መጫወት የተጀመረው ከዚያ ወዲህ ነው" ይላል ዳንኤል። ባለፈው ዓመት ፌስቲቫሉ የተካሄደው በጀርመኗ ስቱትጋርት ነበር። ከዚያ በፊት ሮም፣ ጄኔቭ፣ ስቶኮልም፣ አምስተርዳምና ሌሎችም የአውሮፓ ከተሞች ፌስቲቫሉን አስተናግደዋል። አውሮፓ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ባቋቋሟቸው ቡድኖች መካከል የሚካሄድ የእግር ኳስ ግጥሚያ ፌስቲቫሉን ደማቅ ያደርገዋል። ዘንድሮ አበበ ቢቂላ፣ ሻላ እና ቡና የተባሉ የጤና ቡድኖች መቀመጫቸውን አውሮፓ ካደረጉት ቡድኖች ጋር ለመፋለም ከኢትዮጵያ ወደ ዙሪክ አቅንተዋል። በስም ከሚታወቁት የቀድሞ ተጨዋቾች መካከል ሳሙኤል ደምሴ (ኩኩሻ)፣ ስንታየሁ ጌታቸው (ቆጬ)፣ ተክሌ ብርሃኔ፣ ቴዎድሮስ ቦካንዴ፣ ሃብቶም ብርሃኔ፣ ሰይፈ ውብሸት፣ ጌታቸው ካሳ (ቡቡ)፣ ኃይሉ አድማሱ (ቻይና)፣ግርማ ሳህሌ ይጠቀሳሉ። በነዚህ ጨዋታዎች በየዓመቱ ይገኛሉ። በዘንድሮው የሦስት ቀን ፌስቲቫል ከአምስት ሺህ እስከ አስር ሺህ ሰዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የፌስቲቫሉ አዘጋጅ የሆነው ኢትዮ-ዙሪክ ቡድን ፕሬዘዳንት ሙሉጌታ በየነ በመክፈቻው ዕለት ለቢቢሲ ተናግረዋል። በፌስቲቫሉ ላይ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያን ባህል የሚወዱ የሌሎች አገሮች ዜጎችም ይገኛሉ። ኢትዮጵያዊያንን ያገቡ ዜጎች ይህ ዝግጅት ነፍሳቸው ነው። ከሰሜን አሜሪካው ፌስቲቫል ቀጥሎ ኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ ውጪ የሚገናኙበት ፌስቲቫል እንደመሆኑ ፍቅርና አንድነትን የሚያስተጋቡ ሙዚቀኞች መጋበዛቸውን ሙሉጌታ ይገልጻል። ዘንድሮ ጋሽ ማሕሙድና ስለሺ ደምሴ (ጋሽ አበራ ሞላን) ጨምሮ በርካታ ስመ ገናና ድምጻዊያን ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ራስ ምታት ከኢትዮጵያ ውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵዊያን ትኩሳት ይለቅባቸዋል።አሰላለፋቸው ያሸብራል። ልዩነታቸው የሀበሻ ሬስቶራንት ድረስ ይዘልቃል። የእንቶኔ ብሔር በቀነጠሰው በርበሬ የተሰራ ዶሮ ወጥ በአፌም አይዞር እስከማለት… በፖለቲካ አሰላለፍ ጎራ ተለይቶ መራኮት ዕለታዊ በሆነበት አውሮፓ 'አንዲት ኢትዮጵያ' በሚል ፌስቲቫል ማዘጋጀት ምን ይመስል ይሆን? የየወቅቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታስ ፌስቲቫሉ ላይ ጥላውን አላጠላም? ብለን አቶ ዳንኤልን ጠይቀነው ነበር። "…ፖለቲካው ፌስቲቫሉን ሊያፈርስ የደረሰበት ወቅትም ነበር" ሲል መልሷል። የእግር ኳስ ቡድኖች የመንግሥት ተቃዋሚና ደጋፊ በሚል እንደሚከፋፈሉ ካስታወሰ በኋላ በተለይ በምርጫ 97 ሰሞን የተካሄደውን የእግር ኳስ ግጥሚያ ያሸነፈው ቡድን አባላት በፖለቲካ አቋም ልዩነት ምክንያት አኩርፈው ዋንጫ ሳይቀበሉ ወደ መጡበት አገር መመለሳቸውን እንደ አብነት ያነሳል። "ከፖለቲካ ጋር ግንኙነት ያላቸው መገናኛ ብዙኃን ሲመጡ እንደ ፌደሬሽን የማስተናገድ ግዴታ አለብን ስንል የሚቃወሙ አካላት አሉ። ሜዳ ላይ ያለውን መንፈስ ይረብሻል። እነ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ፣ ታማኝ በየነ፣ ተስፋዬ ገብረአብ ይመጡ ነበር። ያ አንዳንዶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊፈጥር ይችላል። ግን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የመምጣት መብት አለው። አትምጡ ልንላቸው አንችልም›› ይላል፤ ያም ሆኖ መድረኩ ከፖለቲካ የጸዳ የባህልና የስፖርት ፌስቲቫል ብቻ እንዲሆን አዘጋጆቹ ይተጋሉ። ፌስቲቫሉን በየዓመቱ ማን ያዘጋጀው በሚለው ላይ ሁለት ተሞክሮዎች እንዳሉ አቶ ዳንኤል ያብራራል። እንደ ሰሜን አሜሪካው ውድድር ፌዴሬሽኑ ያሰናዳው ወይስ አዘጋጅ አገር? 2017 ላይ የፌስቲቫሉ አዘጋጅ ፌደሬሽኑ እንዲሆን ተወስኖ ጣልያን ውስጥ ፌስቲቫሉን ለማካሄድ መሰናዶ ተጀምሮ ነበር። ሆኖም የፌደሬሽኑ አመራሮች ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ እሰጣ ገባ መፈጠሩን ይናገራል። ከዚህ የሮሙ ክስተት በኋላ ፌስቲቫሉ በየዓመቱ በተለያዩ የእግር ኳስ ቡድኖች እንዲዘጋጅ ውሳኔ ተላለፈ። በዚህም መሠረት የዘንድሮውን ፌስቲቫል ያዘጋጀው ኢትዮ-ዙሪክ ቡድን ነው። የኢትዮ ዙሪክ ቡድኑ ፕሬዝዳንት ሙሉጌታ፤ ፖለቲካው ለጊዜው እንዲቆይ ይማጸናል። ወደ ፌስቲቫሉ የሚሄዱ ሰዎች "ፖለቲካን ማሰብ የለባቸውም። እንዲያውም እዚያ ሜዳ ላይ ፌስቡክን አጥፍቶ፤ ሰላም ተባብሎ መጫወት፣ መብላት፣ መጠጣት፣ መሳቅን ነው ማየት የምንፈልገው" ሲል በበዓሉ መክፈቻ ዕለት ለቢቢሲ ምኞቹን አጋርቷል። የኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ፌስቲቫል አውሮፓ ውስጥ የተወለዱ የኢትዮጵያ ልጆች እነሱን ከሚመስሉ ልጆች ጋር የሚገናኙበትም መድረክ ነው። ብዙዎቹ ታዲያ በግማሽ ኢትዮጵያዊ ካልሆኑ ወላጆች የተገኙ ናቸው። በተለይ ኢትዮጵያን ረግጠው የማያውቁ የኢትዮጵያዊያን ልጆች በእናት በአባታቸው ቋንቋ እየተኮላተፉ ሲያወሩ መስማት አንዳች ልዩ ስሜት ያጭራል። በየዓመቱ የሚጋበዙት ኢትዮጵያዊያን ሙዚቀኞች ታዳጊዎቹን ከአገሪቱ ባህል ጋር በመጠኑም ቢሆን ያስተዋውቋቸዋል። ‹‹ፌስቲቫሉ የአዋቂዎች ብቻ መሆን የለበትም፤ ለነዚህ ሕጻናት በቂ ትኩረት መሰጠት አለበት›› ይላል ለዚሁ መሰናዶ ዙሪክ የሚገኘው ጋሽ አበራ ሞላ። የእግር ኳስ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊዎች ዕድለኛ ከሆኑ ለተለያዩ አገራት ብሔራዊ ቡድኖችና ክለቦች ሊታጩ የሚችሉትም በዚሁ ፌስቲቫል ላይ ነው። በደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ዋንጫ ብሔራዊ ቡድናችን ላይ የተሰለፈው ዩሱፍ ሳሊህ ከዚሁ መድረክ የተገኘ ነው። ፌስቲቫሉን ለመታደም በዙሪክ፣ ክሎተን ስቴድየም ከተገኙ ኢትዮጵያዊያን አንዷ የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ ቅድስት በላይ ናት። በልጆች ክፍለ ጊዜ መርሀ ግብር የምትታወቀው ቅድስት የምትኖረው ስዊዘርላንድ ሲሆን፤ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል ላይ ስትሳተፍ የዘንድሮው የመጀመሪያዋ ነው። ፌስቲቫሉ፤ አውሮፓ ውስጥ ተወልደው በምዕራባውያን ባህል የሚያድጉ ልጆች ስለ ኢትዮጵያ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ትናገራለች። "ስብስቡ ማኅበራዊ ትስስሩን ያጠነክራል። ልጆችም በጣም ደስተኛ ይሆናሉ። ለምሳሌ የጓደኛዬ ቤተሰቦች ከኖርዌይ መጥተው ከሌሎች ልጆች ጋር ስለ ስዊዝና ኖርዌይ ባህል ሲያወሩ ነበር።" ኢትዮጵያዊያን በብዛት በሌሉበት አካባቢ ለሚኖሩ ልጆች፣ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በሚውለበለብበት፣ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በሚነገሩበት፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦች በሚበሉበት ቦታ መገኘትን የሚተካ ነገር እንደሌለም ቅድስት ታስረዳለች። አውሮፓ በሮቿን ለስደተኞች ባትዘጋም ከጊዜ ወደ ጊዜ ሽንቁሩ እየጠበበ ይመስላል። ምናልባትም ለወደፊት ወደ አውሮፓ የሚሄዱ ኢትዮጵዊያን ቁጥር ያሽቆለቁል ይሆናል። ይህ መላ ምት፤ አሁን በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የጀመሩትን ፌስቲቫል ለወደፊት የሚረከባቸው ይኖራልን? የሚል ጥያቄ ማጫሩ አይቀርም። ከኢትዮጵያዊያን እና ከሌሎች አገሮች ዜጎች የሚወለዱ ህጻናት እየተበራከቱ መጥተዋል። እነዚህ በከፊል ብቻ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ልጆች ከኢትዮጵያዊ ማንነታቸው ጋር የሚያስተሳስራቸው ፌስቲቫል አስፈላጊነት የሚታያቸው እስከ መቼ ነው? ሌላው ጥያቄ ነው። ዳንኤል የፌስቲቫሉ ቀጣይነት አያጠራጥርም ይላል። አንድም "በቀጣይ ለሚመጣው ትውልድ ብቸኛ መገናኛው ይህ ፌስቲቫል ነው" ሲል ያስረዳል። በልጅነታቸው ወደ አውሮፓ ቢሄዱም የእግር ኳስ ፌደሬሽኑን ለዓመታት ያገለገሉ ወጣቶች መኖራቸውም ተስፋ ይሰጠዋል። ዳንኤል፤ አውሮፓ ተወልደው ያደጉ ልጆች በፌስቲቫሉ ድምቀት በመማረክ ከዓመት ዓመት ቀጠሮ ሲይዙ አስተውሏል። ለነጭ ጓደኞቻቸው 'የኢትዮጵያ ፌስቲቫል ሄጄ ነበር' ብለው በኩራት እንደሚያወሩም ሰምቷል። እነዚህ ልጆች አሁን ያለውን ሥርዓት እንዲረከቡ ከተደረገ የፌስቲቫሉ ዕድሜ እንደሚረዝም ያምናል።የቡናው መዓዛ ሳይጠፋ…እስክስታው ሳይለዝዝ፣ ቁርጡ ሳይወደር፣ ሙዚቃው ሳይጎትት የዛሬ ዐሥር፣ ሀያ፣ ሠላሳ ዓመት ኢትዮጵያዊያኑ ይገናኙ ይሆን? ከብዙ ፍቅርና ከትንሽ ቡጢ ጋ'ም ቢሆን… | https://www.bbc.com/amharic/49220661 |
3politics
| ምርጫ 2013 ፡ የስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ተስፋ እና ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው? | ኢትዮጵያ ስድስተኛውን አጠቃላይ ምርጫ ለማካሄድ ለግንቦት 28 እና ሰኔ 5 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ይዛለች። ለዚህም ፓርቲያቸውን ወክለው የሚወዳደሩ የተለያዩ ዕጩዎች ምዝገባም በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ፣ በቤኒሻንጉል፣ በሃረሪ፣ በጋምቤላ እና ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልሎች ከየካቲት 08 ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል። በእነዚህ አካባቢዎች የእጩዎች ምዝገባ የሚጠናቀቀው የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑንም በምርጫ ቦርድ ተገልጿል። በአፋር፣ አማራ፣ ሲዳማ ፣ ደቡብ ሕዝቦች እና ሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥቶች ደግሞ ከየካቲት 15 እስከ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. የዕጩዎች ምዝገባ የሚከናወንበት ጊዜ እንደሚሆን ቦርዱ አሳውቋል። በምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመራጮች ምዝገባ የሚካሄደው ከዛሬ ሰኞ የካቲት 22/2013 ዓ.ም ጀምሮ ይሆናል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ እና ኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አመራሮች አባላቶቻቸውና መሪዎቻቸው መታሰራቸውን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ቢሮዎቻቸው መዘጋታቸውን በመግለጽ ይህም በምርጫ ተሳትፏቸው ላይ ጥላ ማጥላቱን ገልፀዋል። አባላቶቻቸው ፍርድ ቤት የዋስትና መብታቸውን አክብሮላቸው እንኳ አለመፈታታቸውን በመግለጽም ተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ለሚመለከታቸው አካላት አቅርበዋል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ወደ ምርጫ መግባት ያሳስበናል ሲሉ ተናግረዋል። ከቀደሙት ምርጫዎች የተለየ ምርጫ ሊሆን ይችላል? በማክስ ፕላንክ ተቋም የፖስት ዶክቶራል ፌሎ የሆኑት ዶ/ር በሪሁን አዱኛ በሕገመንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ በርካታ ጥናቶችን ሰርተዋል። ስድስተኛው አጠቃላይ ምርጫ ኢትዮጵያ ካካሄደቻቸው ካለፉት አምስት ምርጫዎች ልዩ የሚያደርገው አገሪቱ አሁን ያለችበት ሁኔታ መሆኑን በመግለጽ ይጀምራሉ። በርካቶች ይህንን ምርጫ እንደ ከዚህ ቀደሙ የዲሞክራሲ፣ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር ብቻ ሳይሆን፣ አገሪቱ ያለችበትን ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ቅራኔዎች ይፈታል ብለው መጠበቃቸው፤ አገራዊ መሠረታዊ ለውጥ ያስፈልጋል የሚለው ላይ የጋራ መግባባት መኖሩም ለየት እንደሚያደርገው ይናገራሉ። ዶ/ር በሪሁን ይህ ምርጫ መሠረታዊ ምርጫ መሆኑን መንግሥት ማሰብ ይኖርበታል ሲሉም ይመክራሉ። ይህ ምርጫ እንደከዚህ ቀደሞቹ ዓይነት ምርጫ ካልሆነ እና መሠረታዊ ምርጫ ከሆነ ደግሞ "ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር አብሮ መሥራት አለበት፤ ብቻውን ሊያደርገው የሚችለው ነገር አይደለም" ሲሉ አክለዋል። የባለፉት አምስት ምርጫዎች ኢህአዴግ በሚባል ፓርቲ ማዕቀፍ ውስጥ የተደረገ ነው በማለት ይሄኛው ስድስተኛ አገራዊ ምርጫ ግን በአዲስ ብልጽግና በሚባል ፓርቲ መዋቅር ስር የሚደረግ መሆኑን በራሱ ልዩ እንደሚያደርገው ያስረዳሉ። ሌላው ለዶ/ር በሪሁን ይህ ምርጫ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ምርጫዎች በመላው አገሪቱ የሚካሄድ አለመሆኑም ለየት ያደርገዋል። በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ መደፍረስ ይህንን ምርጫ ስጋትና ተስፋ ይዞ እንዲካሄድ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል አንዱ መሆኑንም ይናገራሉ። የፖለቲካ ለውጥ እና የፖለቲካ ሽግግር ወሬ በሚሰማበት ወቅት የሚደረግ ምርጫ መሆኑ ደግሞ ይህንን ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ለየት እንደሚያደርገው ይስታውሳሉ። ሆኖም ግን ይላሉ ዶ/ር በሪሁን ይህንን ምርጫ ከዚህ በፊት ከነበሩት ምርጫዎች የተለየ ነው ወይንም አይደለም የሚለውን የሚወስነው የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያቀርቡት ሃሳብ ነው ይላሉ። ከዘንድሮው ምርጫ ምን ይጠበቃል? እንደከዚህ ቀደሙ የዲሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎችን ብቻ ይዞ እነርሱን ለመፍታት የሚደረግ የምርጫ ውድድር ከሆነ ካለፉት በብዙ ላይለይ ይችላል ሲሉ ይገልጻሉ። ነገር ግን አሁን አገሪቱ ላይ ያሉትን የማኅበራዊ እና የፖለቲካዊ ችግሮችን በመሰረታዊ መልኩ ለመፍታት የሚደረግ እና በዚያ እሳቤ ለመፍታት የሚካሄድ ምርጫ ከሆነ ደግሞ ካለፉት ምርጫዎች የተለየ ሊሆን ይችላል ብለዋል። በተደጋጋሚ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የመንግሥትን እርምጃዎች በመተቸት የሚታወቁት አቶ እያስፔድ ተስፋዬ በበኩላቸው ይህ አገራዊ ምርጫ ከዚህ በፊት ሲካሄዱ ከነበሩ አምስት ተከታታይ ምርጫዎች የተለየ ይሆናል ብለው አያስቡም። ይህንን ሃሳቡን ሲያብራሩም ኢህአዴግ ከዚህ በፊት በአውራ ፓርቲነት ከመራቸውና ከተሳተፈባቸው አምስት ተከታታይ ምርጫዎች የተለየ የፖለቲካ ባህል በዚህኛው ምርጫ አለማስተዋላቸውን ይጠቅሳሉ። ከዚህ ቀደም የተካሄዱት ምርጫዎች ከምርጫ በፊት፣ በኋላ እና በምርጫ ወቅት የተለያዩ ጉድለቶች እንደሚስተዋልባቸው የሚጠቅሱት አቶ እያስፔድ፤ ለዚህም ማሳያዎች ፓርቲዎች እንዳይንቀሰቅሱ ማድረግ፣ አባላቶቻቸውን ማሰር፣ ቢሯቸውን መዝጋት መሆናቸውን ይገልጻሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ሥልጣን በመጡበት ወቅት ቀጣዩ ምርጫ ከዚህ በፊት ከተደረጉት አምስት ምርጫዎች ሁሉ የተለየ ይሆናል የሚል ተስፋ እንደነበራቸው የገለፁት አቶ እያስፔድ፤ ይህ ግን በሂደት መጥፋቱን ይናገራል። በወቅቱ ተስፋ አድርገው የነበሩበትንም ምክንያት ሲያስረዱ፣ የፖለቲካ ምሕዳሩ ከዚህ በፊት ከነበረው ጊዜ ሁሉ የተሻለ መስፋቱን እና በእስር ቤት የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና አመራሮች መፈታታቸው መሆኑን ያስታውሳሉ። ከዚህ በተጨማሪም ደግሞ የመገናኛ ብዙሃን እንደ ልባቸው ተንቀሳቅሰው ያሻቸውን ያለ ተጽዕኖ የሚሰሩበት እድል ተመቻችቶ እንደነበርም አልዘነጉም። ከምርጫ እና ዲሞክራሲ ጋር ተያይዞ ያሉ ተቋማትን የሚመሩ ሰዎችንም በሚመለከት በሕዝቡም ሆነ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ዘንድ ከሞላ ጎደል እምነት የሚጣልባቸውን ግለሰቦች ወደ አመራርነት ማምጣት መቻሉን በማንሳት ቀጣዩ ምርጫ ተስፋ አለው ብለው እንደነበር ለቢቢሲ ገልፀዋል። "ግን እነዚህ ነገሮች እንዳለ ተቀልብሰው ወደ ነበርንበት ተመልሰናል" የሚሉት አቶ እያስፔድ የፖለቲካ ምሕዳሩ መጥበብ ብቻ ሳይሆን በርካቶች እስር ቤት እንደሚገኙም ይጠቅሳሉ። ዛሬም ፍርድ ቤት ንፁህ መሆናቸውን ገልጾ የታሰሩ መኖራቸውን በተለያዩ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርቶች ላይ መገለፁን የሚያነሱት አቶ እያስፔድ፤ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት የዋስትና መብታቸውን አክብሮላቸው ነገር ግን ፖሊስ ከመልቀቅ ይልቅ አሁንም ከተማ እና ፍርድ ቤት እየቀያየረ የተለያየ ክስ የሚመሰርትባቸው መኖራቸውን ይገልጻሉ። የባልደራስ አባላት እንዲሁም የተለያዩ የኦሮሞ ተቃዋሚ ፓርቲ አባላት መታሰር ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም የቤንሻንጉል ጉሙዝ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የምርጫ ቦርድ ግቢ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ መታገታቸውን ራሱ የምርጫ ቦርድ የገለፀው መሆኑን በማንሳት በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ የፖለቲካ ምሕዳሩ ጠብቦ "ፍትሃዊና የተለየ ምርጫ ይደረጋል ብሎ ማሰብ የማይታሰብ ነው" ይላሉ። ጋዜጠኞችን በሚመለከትም ሲናገሩ ሲፒጄ ዶ/ር አብይ ወደ ሥልጣን በመጡበት ወቅት አንድም ጋዜጠኛ ያልታሰረባት አገር ያላት ኢትዮጵያ፣ በአሁኑ ሰዓት ግን ከቤላሩስ በመቀጠል በፍጥነት ጋዜጠኞችን በማሰር ሁለተኛዋ አገር በሚል እንደፈረጃት ይጠቅሳሉ። ዶ/ር በሪሁን በበኩላቸው ፖለቲከኞች እስር ቤት ውስጥ ሆነው የሚካሄድ ምርጫ የቅርብ እና የሩቅ ጊዜ ተጽዕኖ እንዳለው ይናገራሉ። በቅርብ ምርጫውን በሰላማዊ መንገድ ለማካሄድ አለመቻል ሲሆን፣ አርቆ ሲመለከቱት ደግሞ ከምርጫ በኋላ ለሚመጣው የፖለቲካ ሥርዓት አሉታዊ ተጽዕኖ አለው ሲሉም ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። ፓርቲዎች ይደርስብናል ያሏቸው ችግሮች ከአሁኑ መፍታት አለመቻል በኋላ ላይ ምርጫውን ለማከናወን የሰላም እና የደኅንነት ችግር ሊፈጥር ይችላል ሲሉም አክለዋል። ምርጫውም ካለፈ በኋላ ምርጫውን ያሸነፈው ፓርቲ የተለያዩ ፖሊሲዎችና ሕጎችን ቢያወጣ፣ የሕገመንግሥት ማሻሻያ ማድረግ ቢፈልግ የሚወሰነው ፓርላማ ባሉ ፓርቲዎች እና ሰዎች በመሆኑ፣ ከዚህ ውጪ የሆኑ የአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎችን በአጠቃላይ ትርጉም ባለው መልኩ የማያሳትፍ ይሆናል ሲሉ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። የምርጫው ነጻና ፍትሃዊነት ዶ/ር በሪሁን በምርጫ ቦርድ አካባቢ የማይካዱ የአስተዳደር እና የሕግ ለውጦች መካሄዳቸውን ይገልጻሉ። የምርጫ ቦርድ አመራሮች ቀጣዩን ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ ለማድረግ ቁርጠኝነቱ እንዳላቸው "እንደ ግለሰብ ግምት አለኝ" የሚሉት ዶ/ር በሪሁን አጠቃላይ ሁኔታው ሲታይ ግን ያለው ችግር ከእነርሱ በላይ ነው ይላሉ። ምርጫ ቦርድ በራሱ ብቻ ማስፈፀም የሚችለው ነገር የለም በማለትም መንግሥት፣ ፍርድ ቤቶች፣ የፀጥታና ደኅንነት አካላት ሁሉም የየራሳቸው ድርሻ አላቸው ብለዋል። አሁን ያለው ጉዳዩ ከምርጫ ቦርድ በላይ ነው የሚሉት ዶ/ር በሪሁን፣ ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ ለማድረግ "ዝም ብሎ በምርጫ ቦርድ ላይ ብቻ የምንንጠለጠል አይሆንም" ይላሉ። መንግሥት፣ ተቃዋሚዎች፣ ሕዝቡ፣ የፍትህ አካላት ሁሉም በትብብር ካልሰሩ አንዱ ተቋም ብቻ ይህንን ምርጫ በሥነ ሥርዓት ማድረግ ይችላል ማለት ከባድ ነው ሲሉ ያክላሉ። ዶ/ር በሪሁን ይህንን ሁሉ ከግንዛቤ አስገብተው ምርጫ ቦርድ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ ይችላል ለሚለው ጥያቄ "መልሴ አይችሉም ነው" ይላሉ። አቶ እያስፔድ የምርጫ ቦርድ ፍትሃዊነት ላይ ያላቸው እምነት እየተሸረሸረ መምጣቱን ገልፀው የኦነግ እና ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ቢሮዎች በተለያዩ አካባቢዎች ተዘግተው፣ ፓርቲዎቹ ምርጫ ላይ እንዴት መሳተፍ ይችላሉ በማለት፣ ምርጫ ቦርድ ይህንን የፓርቲዎቹን ችግር እንኳ ለመፍታት ቁርጠኝነት እንዳልታየበት ያስረዳሉ። እርሳቸው እና ሌሎች ግለሰቦች በጋራ በመሆን ባካሄዱት የማኅበራዊ ድረ ገጽ ዘመቻ የኦነግና ኦፌኮ ቢሮዎች የት የት ቦታ እንደተዘጉ አቅማቸው በፈቀደ በአካል በመሄድ፣ ሌሎቹን ደግሞ ከፓርቲው መረጃ በመሰብሰብ በፌስቡክና ትዊተር ላይ ማስፈራቸውን ያስታውሳሉ። ፓርቲዎቹም ቢሆኑ ይህንኑ ጉዳይ ለቦርዱ በደብዳቤ በተደጋጋሚ ማሳወቃቸውን አቶ እያስፔድ አክለዋል። ምርጫ ቦርድ ግን "ኦነግም ሆነ ኦፌኮ ቢሮዎቻቸው የት የት ቦታ እንደተዘጉባቸው በትክክል ስላላቀረቡላቸው መቸገራቸውን" ሲናገር መስማታቸውን ይጠቅሳሉ። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ከፓርቲዎች የሚቀርቡለትን ቅሬታዎችና አቤቱታዎችን በመቀበል ምላሽና መፍትሔ እንዲያገኙ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ጥረት እንደሚያደርግ በተለያዩ ጊዜያት መግለጹ ይታወሳል። ምርጫውን የሚያሸንፍ ፓርቲ መሠረታዊ የፖለቲካ ለውጥ ማምጣት የሚፈልግ ከሆነ አሁን ከምርጫ በፊት ቁጭ ብሎ "በተለይ ኦሮሚያ ውስጥ ካሉ እና ሌሎችም ፓርቲዎች ጋር መነጋገር፤ በተለይ መንግሥትን ለሚያስተዳድረው፣ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በይበልጥ ፓርቲ ለብልጽግና ይጠቅማል ብዬ አስባለሁ" ይላሉ። ስጋቶች እና ተስፋዎች ኢትዮጵያ ይህንን ምርጫ የምታካሄደው በተለያዩ የደኅንነት እና የፀጥታ ስጋቶች ውስጥ ሆና ነው። የሕዳሴ ግድብ ድርድር ጉዳይ፣ ከሱዳን ጋር ያለው የድንበር ይገባኛል ውዝግብ፣ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የፀጥታ ችግሮች ቢኖሩም አገሪቱ ያለችባቸውን የተለያዩ ችግሮች ለመፍታት "ቢዘገይም ምርጫ ማካሄድ አማራጭ የሌለው ነገር ነው" ዶ/ር በሪሁን ይላሉ። መንግሥት የሕዝቡን ይሁንታ ማግኘት እንዲችል የሚያወጣቸውን ፖሊሲዎች እና ሕጎች ተቀባይነትና ተፈጻሚነት እንዲያገኙ ምርጫ ማድረጉ አማራጭ የለውም ሲሉም ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። ከዶ/ር በሪሁን ጋር ተመሳሳይ አስተያየት ያላቸው አቶ እያስፔድ ይህንን ቀጣይ አገራዊ ምርጫ እስር ቤት ካሉ የፖለቲካ አመራሮች ጋር እውነተኛ የሆነ ድርድር ሳያካሄዱ ማከናወን ከዚህ ቀደም "አገሪቱ የሄደችበትን መንገድ መድገም" ይሆናል ሲሉ ይናገራሉ። አምስተኛው አገራዊ ምርጫ ኢህአዴግ መቶ በመቶ ማሸነፉን ያስታወሱት አቶ እያስፔድ፣ አሁን የተወሰኑ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች በሰላማዊ ሁኔታ እንዳይንቀሳቀሱ እድሎችን መዝጋት ወደሌላ አማራጭ ሊያመራ እንደሚችል ስጋታቸውን ይገልጻሉ። ውይይትና ድርድር እንደሚያስፈልግ የሚናገሩት አቶ እያስፔድ የመራጮች ምዝገባ እየተጠናቀቀ መሆኑ ግን ይህንን ተስፋቸውን እያመነመነው መሆኑን ተናግረዋል። ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል የሚሉት አቶ እያስፔድ፣ ሕዝቦች በተለያየ ምክንያት ተወካዮቻቸው ባልተሳተፉበት እና በሌሉበት ምክር ቤት ለሚወጡ ሕጎች ተገዢ ይሆናሉ ብሎ ማሰብ ከባድ መሆኑን ከዚህ ቀደም የተደረጉ ተቃውሞዎችን በማስረጃነት በመጥቀስ ይናገራሉ። ዶ/ር በሪሁን ምርጫ ማለት አገሪቱን ለቀጣይ አምስት ዓመት ማን ያስተዳድራት በሚል የሚከናወን መሆኑን በማንሳት አሁን ግን ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ፣ የሕግ እና ሌሎች በርካታ ልዩነቶች ያሉበት መሆኑን ጠቅሰው ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ለየት እንደሚል ተናግረዋል። አሁን ኢትዮጵያን እያስተዳደረ ያለው ፓርቲም ሆነ የሚመረጠው ፓርቲ አገሪቱ ያለችበትን ችግሮች ሁሉ ብቻውን የሚፈታቸው አይደሉም የሚሉት ዶ/ር በሪሁን፣ ከምርጫውም በፊት ሆነ በኋላ መነጋገር አስፈላጊ መሆኑን ያሰምሩበታል። ስለምርጫውና ከምርጫው በኋላ ምን ማድረግ እንችላለን፣ የቆዩ መሠረታዊ ጥያቄዎችንና ልዩነቶችን እንዴት መፍታት እንደሚቻል ማሰብ፣ አገሪቱ የምትፈልገውን መሠረታዊ ለውጥ ታሳቢ ያደረገ ውይይት ያስፈልጋል ሲሉም ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። ዶ/ር በሪሁን ላለፉት ሁለት ዓመታት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የእንነጋገር ጥያቄ ሲያቀርቡ እንደነበር ገልፀው አሁንም ግን ጊዜ መኖሩን ይናገራሉ። ለዚህም ረዥም ርቀት መሄድ ያለበት መንግሥት መሆኑን ይናገራሉ። ምርጫው በተለያዩ ልዩነት መንፈሶች ውስጥ የሚካሄድ መሆኑንም በማንሳት፣ ውይይቶች እና ንግግሮች ከምርጫው በፊትም ሆነ በኋላ መደረግ እንዳለባቸው ያሰረዳሉ። አለበለዚያ ግን ከሰኔው ምርጫ በኋላ መንግሥት ችግሮችን ካልፈታ እንደ ከዚህ ቀደሙ ከምርጫ በኋላ ቀውስ ላለመከተሉ ማረጋገጫ የለም ሲሉ ያስጠነቅቃሉ። | ምርጫ 2013 ፡ የስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ተስፋ እና ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው? ኢትዮጵያ ስድስተኛውን አጠቃላይ ምርጫ ለማካሄድ ለግንቦት 28 እና ሰኔ 5 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ይዛለች። ለዚህም ፓርቲያቸውን ወክለው የሚወዳደሩ የተለያዩ ዕጩዎች ምዝገባም በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ፣ በቤኒሻንጉል፣ በሃረሪ፣ በጋምቤላ እና ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልሎች ከየካቲት 08 ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል። በእነዚህ አካባቢዎች የእጩዎች ምዝገባ የሚጠናቀቀው የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑንም በምርጫ ቦርድ ተገልጿል። በአፋር፣ አማራ፣ ሲዳማ ፣ ደቡብ ሕዝቦች እና ሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥቶች ደግሞ ከየካቲት 15 እስከ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. የዕጩዎች ምዝገባ የሚከናወንበት ጊዜ እንደሚሆን ቦርዱ አሳውቋል። በምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመራጮች ምዝገባ የሚካሄደው ከዛሬ ሰኞ የካቲት 22/2013 ዓ.ም ጀምሮ ይሆናል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ እና ኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አመራሮች አባላቶቻቸውና መሪዎቻቸው መታሰራቸውን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ቢሮዎቻቸው መዘጋታቸውን በመግለጽ ይህም በምርጫ ተሳትፏቸው ላይ ጥላ ማጥላቱን ገልፀዋል። አባላቶቻቸው ፍርድ ቤት የዋስትና መብታቸውን አክብሮላቸው እንኳ አለመፈታታቸውን በመግለጽም ተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ለሚመለከታቸው አካላት አቅርበዋል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ወደ ምርጫ መግባት ያሳስበናል ሲሉ ተናግረዋል። ከቀደሙት ምርጫዎች የተለየ ምርጫ ሊሆን ይችላል? በማክስ ፕላንክ ተቋም የፖስት ዶክቶራል ፌሎ የሆኑት ዶ/ር በሪሁን አዱኛ በሕገመንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ በርካታ ጥናቶችን ሰርተዋል። ስድስተኛው አጠቃላይ ምርጫ ኢትዮጵያ ካካሄደቻቸው ካለፉት አምስት ምርጫዎች ልዩ የሚያደርገው አገሪቱ አሁን ያለችበት ሁኔታ መሆኑን በመግለጽ ይጀምራሉ። በርካቶች ይህንን ምርጫ እንደ ከዚህ ቀደሙ የዲሞክራሲ፣ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር ብቻ ሳይሆን፣ አገሪቱ ያለችበትን ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ቅራኔዎች ይፈታል ብለው መጠበቃቸው፤ አገራዊ መሠረታዊ ለውጥ ያስፈልጋል የሚለው ላይ የጋራ መግባባት መኖሩም ለየት እንደሚያደርገው ይናገራሉ። ዶ/ር በሪሁን ይህ ምርጫ መሠረታዊ ምርጫ መሆኑን መንግሥት ማሰብ ይኖርበታል ሲሉም ይመክራሉ። ይህ ምርጫ እንደከዚህ ቀደሞቹ ዓይነት ምርጫ ካልሆነ እና መሠረታዊ ምርጫ ከሆነ ደግሞ "ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር አብሮ መሥራት አለበት፤ ብቻውን ሊያደርገው የሚችለው ነገር አይደለም" ሲሉ አክለዋል። የባለፉት አምስት ምርጫዎች ኢህአዴግ በሚባል ፓርቲ ማዕቀፍ ውስጥ የተደረገ ነው በማለት ይሄኛው ስድስተኛ አገራዊ ምርጫ ግን በአዲስ ብልጽግና በሚባል ፓርቲ መዋቅር ስር የሚደረግ መሆኑን በራሱ ልዩ እንደሚያደርገው ያስረዳሉ። ሌላው ለዶ/ር በሪሁን ይህ ምርጫ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ምርጫዎች በመላው አገሪቱ የሚካሄድ አለመሆኑም ለየት ያደርገዋል። በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ መደፍረስ ይህንን ምርጫ ስጋትና ተስፋ ይዞ እንዲካሄድ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል አንዱ መሆኑንም ይናገራሉ። የፖለቲካ ለውጥ እና የፖለቲካ ሽግግር ወሬ በሚሰማበት ወቅት የሚደረግ ምርጫ መሆኑ ደግሞ ይህንን ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ለየት እንደሚያደርገው ይስታውሳሉ። ሆኖም ግን ይላሉ ዶ/ር በሪሁን ይህንን ምርጫ ከዚህ በፊት ከነበሩት ምርጫዎች የተለየ ነው ወይንም አይደለም የሚለውን የሚወስነው የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያቀርቡት ሃሳብ ነው ይላሉ። ከዘንድሮው ምርጫ ምን ይጠበቃል? እንደከዚህ ቀደሙ የዲሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎችን ብቻ ይዞ እነርሱን ለመፍታት የሚደረግ የምርጫ ውድድር ከሆነ ካለፉት በብዙ ላይለይ ይችላል ሲሉ ይገልጻሉ። ነገር ግን አሁን አገሪቱ ላይ ያሉትን የማኅበራዊ እና የፖለቲካዊ ችግሮችን በመሰረታዊ መልኩ ለመፍታት የሚደረግ እና በዚያ እሳቤ ለመፍታት የሚካሄድ ምርጫ ከሆነ ደግሞ ካለፉት ምርጫዎች የተለየ ሊሆን ይችላል ብለዋል። በተደጋጋሚ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የመንግሥትን እርምጃዎች በመተቸት የሚታወቁት አቶ እያስፔድ ተስፋዬ በበኩላቸው ይህ አገራዊ ምርጫ ከዚህ በፊት ሲካሄዱ ከነበሩ አምስት ተከታታይ ምርጫዎች የተለየ ይሆናል ብለው አያስቡም። ይህንን ሃሳቡን ሲያብራሩም ኢህአዴግ ከዚህ በፊት በአውራ ፓርቲነት ከመራቸውና ከተሳተፈባቸው አምስት ተከታታይ ምርጫዎች የተለየ የፖለቲካ ባህል በዚህኛው ምርጫ አለማስተዋላቸውን ይጠቅሳሉ። ከዚህ ቀደም የተካሄዱት ምርጫዎች ከምርጫ በፊት፣ በኋላ እና በምርጫ ወቅት የተለያዩ ጉድለቶች እንደሚስተዋልባቸው የሚጠቅሱት አቶ እያስፔድ፤ ለዚህም ማሳያዎች ፓርቲዎች እንዳይንቀሰቅሱ ማድረግ፣ አባላቶቻቸውን ማሰር፣ ቢሯቸውን መዝጋት መሆናቸውን ይገልጻሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ሥልጣን በመጡበት ወቅት ቀጣዩ ምርጫ ከዚህ በፊት ከተደረጉት አምስት ምርጫዎች ሁሉ የተለየ ይሆናል የሚል ተስፋ እንደነበራቸው የገለፁት አቶ እያስፔድ፤ ይህ ግን በሂደት መጥፋቱን ይናገራል። በወቅቱ ተስፋ አድርገው የነበሩበትንም ምክንያት ሲያስረዱ፣ የፖለቲካ ምሕዳሩ ከዚህ በፊት ከነበረው ጊዜ ሁሉ የተሻለ መስፋቱን እና በእስር ቤት የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና አመራሮች መፈታታቸው መሆኑን ያስታውሳሉ። ከዚህ በተጨማሪም ደግሞ የመገናኛ ብዙሃን እንደ ልባቸው ተንቀሳቅሰው ያሻቸውን ያለ ተጽዕኖ የሚሰሩበት እድል ተመቻችቶ እንደነበርም አልዘነጉም። ከምርጫ እና ዲሞክራሲ ጋር ተያይዞ ያሉ ተቋማትን የሚመሩ ሰዎችንም በሚመለከት በሕዝቡም ሆነ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ዘንድ ከሞላ ጎደል እምነት የሚጣልባቸውን ግለሰቦች ወደ አመራርነት ማምጣት መቻሉን በማንሳት ቀጣዩ ምርጫ ተስፋ አለው ብለው እንደነበር ለቢቢሲ ገልፀዋል። "ግን እነዚህ ነገሮች እንዳለ ተቀልብሰው ወደ ነበርንበት ተመልሰናል" የሚሉት አቶ እያስፔድ የፖለቲካ ምሕዳሩ መጥበብ ብቻ ሳይሆን በርካቶች እስር ቤት እንደሚገኙም ይጠቅሳሉ። ዛሬም ፍርድ ቤት ንፁህ መሆናቸውን ገልጾ የታሰሩ መኖራቸውን በተለያዩ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርቶች ላይ መገለፁን የሚያነሱት አቶ እያስፔድ፤ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት የዋስትና መብታቸውን አክብሮላቸው ነገር ግን ፖሊስ ከመልቀቅ ይልቅ አሁንም ከተማ እና ፍርድ ቤት እየቀያየረ የተለያየ ክስ የሚመሰርትባቸው መኖራቸውን ይገልጻሉ። የባልደራስ አባላት እንዲሁም የተለያዩ የኦሮሞ ተቃዋሚ ፓርቲ አባላት መታሰር ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም የቤንሻንጉል ጉሙዝ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የምርጫ ቦርድ ግቢ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ መታገታቸውን ራሱ የምርጫ ቦርድ የገለፀው መሆኑን በማንሳት በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ የፖለቲካ ምሕዳሩ ጠብቦ "ፍትሃዊና የተለየ ምርጫ ይደረጋል ብሎ ማሰብ የማይታሰብ ነው" ይላሉ። ጋዜጠኞችን በሚመለከትም ሲናገሩ ሲፒጄ ዶ/ር አብይ ወደ ሥልጣን በመጡበት ወቅት አንድም ጋዜጠኛ ያልታሰረባት አገር ያላት ኢትዮጵያ፣ በአሁኑ ሰዓት ግን ከቤላሩስ በመቀጠል በፍጥነት ጋዜጠኞችን በማሰር ሁለተኛዋ አገር በሚል እንደፈረጃት ይጠቅሳሉ። ዶ/ር በሪሁን በበኩላቸው ፖለቲከኞች እስር ቤት ውስጥ ሆነው የሚካሄድ ምርጫ የቅርብ እና የሩቅ ጊዜ ተጽዕኖ እንዳለው ይናገራሉ። በቅርብ ምርጫውን በሰላማዊ መንገድ ለማካሄድ አለመቻል ሲሆን፣ አርቆ ሲመለከቱት ደግሞ ከምርጫ በኋላ ለሚመጣው የፖለቲካ ሥርዓት አሉታዊ ተጽዕኖ አለው ሲሉም ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። ፓርቲዎች ይደርስብናል ያሏቸው ችግሮች ከአሁኑ መፍታት አለመቻል በኋላ ላይ ምርጫውን ለማከናወን የሰላም እና የደኅንነት ችግር ሊፈጥር ይችላል ሲሉም አክለዋል። ምርጫውም ካለፈ በኋላ ምርጫውን ያሸነፈው ፓርቲ የተለያዩ ፖሊሲዎችና ሕጎችን ቢያወጣ፣ የሕገመንግሥት ማሻሻያ ማድረግ ቢፈልግ የሚወሰነው ፓርላማ ባሉ ፓርቲዎች እና ሰዎች በመሆኑ፣ ከዚህ ውጪ የሆኑ የአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎችን በአጠቃላይ ትርጉም ባለው መልኩ የማያሳትፍ ይሆናል ሲሉ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። የምርጫው ነጻና ፍትሃዊነት ዶ/ር በሪሁን በምርጫ ቦርድ አካባቢ የማይካዱ የአስተዳደር እና የሕግ ለውጦች መካሄዳቸውን ይገልጻሉ። የምርጫ ቦርድ አመራሮች ቀጣዩን ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ ለማድረግ ቁርጠኝነቱ እንዳላቸው "እንደ ግለሰብ ግምት አለኝ" የሚሉት ዶ/ር በሪሁን አጠቃላይ ሁኔታው ሲታይ ግን ያለው ችግር ከእነርሱ በላይ ነው ይላሉ። ምርጫ ቦርድ በራሱ ብቻ ማስፈፀም የሚችለው ነገር የለም በማለትም መንግሥት፣ ፍርድ ቤቶች፣ የፀጥታና ደኅንነት አካላት ሁሉም የየራሳቸው ድርሻ አላቸው ብለዋል። አሁን ያለው ጉዳዩ ከምርጫ ቦርድ በላይ ነው የሚሉት ዶ/ር በሪሁን፣ ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ ለማድረግ "ዝም ብሎ በምርጫ ቦርድ ላይ ብቻ የምንንጠለጠል አይሆንም" ይላሉ። መንግሥት፣ ተቃዋሚዎች፣ ሕዝቡ፣ የፍትህ አካላት ሁሉም በትብብር ካልሰሩ አንዱ ተቋም ብቻ ይህንን ምርጫ በሥነ ሥርዓት ማድረግ ይችላል ማለት ከባድ ነው ሲሉ ያክላሉ። ዶ/ር በሪሁን ይህንን ሁሉ ከግንዛቤ አስገብተው ምርጫ ቦርድ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ ይችላል ለሚለው ጥያቄ "መልሴ አይችሉም ነው" ይላሉ። አቶ እያስፔድ የምርጫ ቦርድ ፍትሃዊነት ላይ ያላቸው እምነት እየተሸረሸረ መምጣቱን ገልፀው የኦነግ እና ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ቢሮዎች በተለያዩ አካባቢዎች ተዘግተው፣ ፓርቲዎቹ ምርጫ ላይ እንዴት መሳተፍ ይችላሉ በማለት፣ ምርጫ ቦርድ ይህንን የፓርቲዎቹን ችግር እንኳ ለመፍታት ቁርጠኝነት እንዳልታየበት ያስረዳሉ። እርሳቸው እና ሌሎች ግለሰቦች በጋራ በመሆን ባካሄዱት የማኅበራዊ ድረ ገጽ ዘመቻ የኦነግና ኦፌኮ ቢሮዎች የት የት ቦታ እንደተዘጉ አቅማቸው በፈቀደ በአካል በመሄድ፣ ሌሎቹን ደግሞ ከፓርቲው መረጃ በመሰብሰብ በፌስቡክና ትዊተር ላይ ማስፈራቸውን ያስታውሳሉ። ፓርቲዎቹም ቢሆኑ ይህንኑ ጉዳይ ለቦርዱ በደብዳቤ በተደጋጋሚ ማሳወቃቸውን አቶ እያስፔድ አክለዋል። ምርጫ ቦርድ ግን "ኦነግም ሆነ ኦፌኮ ቢሮዎቻቸው የት የት ቦታ እንደተዘጉባቸው በትክክል ስላላቀረቡላቸው መቸገራቸውን" ሲናገር መስማታቸውን ይጠቅሳሉ። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ከፓርቲዎች የሚቀርቡለትን ቅሬታዎችና አቤቱታዎችን በመቀበል ምላሽና መፍትሔ እንዲያገኙ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ጥረት እንደሚያደርግ በተለያዩ ጊዜያት መግለጹ ይታወሳል። ምርጫውን የሚያሸንፍ ፓርቲ መሠረታዊ የፖለቲካ ለውጥ ማምጣት የሚፈልግ ከሆነ አሁን ከምርጫ በፊት ቁጭ ብሎ "በተለይ ኦሮሚያ ውስጥ ካሉ እና ሌሎችም ፓርቲዎች ጋር መነጋገር፤ በተለይ መንግሥትን ለሚያስተዳድረው፣ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በይበልጥ ፓርቲ ለብልጽግና ይጠቅማል ብዬ አስባለሁ" ይላሉ። ስጋቶች እና ተስፋዎች ኢትዮጵያ ይህንን ምርጫ የምታካሄደው በተለያዩ የደኅንነት እና የፀጥታ ስጋቶች ውስጥ ሆና ነው። የሕዳሴ ግድብ ድርድር ጉዳይ፣ ከሱዳን ጋር ያለው የድንበር ይገባኛል ውዝግብ፣ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የፀጥታ ችግሮች ቢኖሩም አገሪቱ ያለችባቸውን የተለያዩ ችግሮች ለመፍታት "ቢዘገይም ምርጫ ማካሄድ አማራጭ የሌለው ነገር ነው" ዶ/ር በሪሁን ይላሉ። መንግሥት የሕዝቡን ይሁንታ ማግኘት እንዲችል የሚያወጣቸውን ፖሊሲዎች እና ሕጎች ተቀባይነትና ተፈጻሚነት እንዲያገኙ ምርጫ ማድረጉ አማራጭ የለውም ሲሉም ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። ከዶ/ር በሪሁን ጋር ተመሳሳይ አስተያየት ያላቸው አቶ እያስፔድ ይህንን ቀጣይ አገራዊ ምርጫ እስር ቤት ካሉ የፖለቲካ አመራሮች ጋር እውነተኛ የሆነ ድርድር ሳያካሄዱ ማከናወን ከዚህ ቀደም "አገሪቱ የሄደችበትን መንገድ መድገም" ይሆናል ሲሉ ይናገራሉ። አምስተኛው አገራዊ ምርጫ ኢህአዴግ መቶ በመቶ ማሸነፉን ያስታወሱት አቶ እያስፔድ፣ አሁን የተወሰኑ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች በሰላማዊ ሁኔታ እንዳይንቀሳቀሱ እድሎችን መዝጋት ወደሌላ አማራጭ ሊያመራ እንደሚችል ስጋታቸውን ይገልጻሉ። ውይይትና ድርድር እንደሚያስፈልግ የሚናገሩት አቶ እያስፔድ የመራጮች ምዝገባ እየተጠናቀቀ መሆኑ ግን ይህንን ተስፋቸውን እያመነመነው መሆኑን ተናግረዋል። ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል የሚሉት አቶ እያስፔድ፣ ሕዝቦች በተለያየ ምክንያት ተወካዮቻቸው ባልተሳተፉበት እና በሌሉበት ምክር ቤት ለሚወጡ ሕጎች ተገዢ ይሆናሉ ብሎ ማሰብ ከባድ መሆኑን ከዚህ ቀደም የተደረጉ ተቃውሞዎችን በማስረጃነት በመጥቀስ ይናገራሉ። ዶ/ር በሪሁን ምርጫ ማለት አገሪቱን ለቀጣይ አምስት ዓመት ማን ያስተዳድራት በሚል የሚከናወን መሆኑን በማንሳት አሁን ግን ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ፣ የሕግ እና ሌሎች በርካታ ልዩነቶች ያሉበት መሆኑን ጠቅሰው ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ለየት እንደሚል ተናግረዋል። አሁን ኢትዮጵያን እያስተዳደረ ያለው ፓርቲም ሆነ የሚመረጠው ፓርቲ አገሪቱ ያለችበትን ችግሮች ሁሉ ብቻውን የሚፈታቸው አይደሉም የሚሉት ዶ/ር በሪሁን፣ ከምርጫውም በፊት ሆነ በኋላ መነጋገር አስፈላጊ መሆኑን ያሰምሩበታል። ስለምርጫውና ከምርጫው በኋላ ምን ማድረግ እንችላለን፣ የቆዩ መሠረታዊ ጥያቄዎችንና ልዩነቶችን እንዴት መፍታት እንደሚቻል ማሰብ፣ አገሪቱ የምትፈልገውን መሠረታዊ ለውጥ ታሳቢ ያደረገ ውይይት ያስፈልጋል ሲሉም ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። ዶ/ር በሪሁን ላለፉት ሁለት ዓመታት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የእንነጋገር ጥያቄ ሲያቀርቡ እንደነበር ገልፀው አሁንም ግን ጊዜ መኖሩን ይናገራሉ። ለዚህም ረዥም ርቀት መሄድ ያለበት መንግሥት መሆኑን ይናገራሉ። ምርጫው በተለያዩ ልዩነት መንፈሶች ውስጥ የሚካሄድ መሆኑንም በማንሳት፣ ውይይቶች እና ንግግሮች ከምርጫው በፊትም ሆነ በኋላ መደረግ እንዳለባቸው ያሰረዳሉ። አለበለዚያ ግን ከሰኔው ምርጫ በኋላ መንግሥት ችግሮችን ካልፈታ እንደ ከዚህ ቀደሙ ከምርጫ በኋላ ቀውስ ላለመከተሉ ማረጋገጫ የለም ሲሉ ያስጠነቅቃሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-56224264 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ስንት የኮቪድ-19 ክትባቶች አሉ? ለኢትዮጵያስ የትኛው ይደርሳታል? | ኮሮናቫይረስ ተከስቶ የዓለምን አጠቃላይ ገጽታ መቀየር ከጀመረ እንሆ አንድ ዓመት ሊሞላው ተቃርቧል። በዚህ ጊዜም ከ71 ሚሊዮን በላይ የምድራችን ነዋሪ በበሽታው መያዙ የተረጋገጠ ሲሆን ከ1.6 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሰበብ ህይወታቸውን አጥተዋል። በሽታው ያላዳረሰው የዓለም ክፍል የሌለ ሲሆን እንደተሰጋው የከፋ ጉዳትን ባያደርስም በአፍሪካ አገራት ውስጥም ከ2.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታው ሲያዙ ከ56 ሺህ በላይ ድግሞ ለሞት ተዳርገዋል። ከዚህ ውስጥ ደግሞ በኢትዮጵያ ከ116 ሺህ ሰዎች በላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ከ1 ሺህ 880 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ከዓለም ዙሪያ የተሰባሰቡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በበሽታው መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ከበሽታው ያገገሙ ቢሆንም አስካሁን ፈዋሽነቱ የተረጋገጠ መድኃኒት ለቫይረሱ አልተገኘም። በሽታው ቻይና ውስጥ መከሰቱ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ አገራት ለበሽታው መከላከያ የሚሆን ክትባት እንዲሁም የተያዙ ሰዎችን ለማከም የሚያገለግል መድኃኒት ለማግኘት ሊቃውንት ቀን ከሌት እየጣሩ ይገኛሉ። እስካሁን በተደረጉ ምርምሮችና ሙከራዎች በርካታ ተስፋ ሰጪ የክትባት ውጤቶች መገኘታቸው ከመነገሩ ባሻገር፤ በሽታውን ለመከላከል ያስችላሉ የተባሉ ጥቂት ክትባቶችም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ለበሽታው ተጋላጭ ናቸው ለተባሉ ሰዎች መሰጠት ተጀምሯል። በዚህ ረገድ ቀዳሚውን የተጠቃሚነት ዕድል ያገኙት ባለጸጋ አገራት ሲሆኑ የዓለም ጤና ድርጅት ደግሞ ክትባቶቹ ለሁሉም እንዲዳረስ ጥረት እያደረገ መሆኑን አመልክቷል። አገራትም ለዜጎቻቸው ክትባቱን ለማቅረብ ባላቸው አማራጮች ሁሉ እየሞከሩ ነው። ኢትዮጵያም እንዲሁ ኮቫክስ ከተሰኘው ዓለም አቀፍ የክትባት ድጋፍ ሰጪና እቅራቢ በኩል ለአገልግሎት ከሚቀርቡት የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ጥያቄ እንዳቀረበች የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ባለፈው ሳምንት ገልጸዋል። ሚኒስትሯ ጨምረውም ለአገልግሎት ብቁ ከሆኑ የክትባት አይነቶች መካከል ኢትዮጵያም እንድታገኝ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረው፤ በኮቫክስ በኩል ክትባቱን በፍጥነት ለማግኘትና በቅድሚያ መከተብ ለሚገባቸው ወገኖች እንዲደርስ እንደሚደረግ ገልጸዋል። ለመሆኑ የትኞቹ ክትባቶች ጥቅም ላይ ውለዋል? በአሁኑ ጊዜ በርካታ መድኃኒት አምራች ኩባንያዎችና አገራት ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሚሆን ክትባት በማበልጸግ ላይ ሲሆኑ ጥቂቶቹም በስራ ላይ መዋል ጀምረዋል። ፋይዘር/ባዮንቴክ ኮሮናቫይረስን በመከላከል 90 በመቶ ውጤታማ ነው የተባለው ይህ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ይፋ የሆነው በፈረንጆቹ ሕዳር 9/2020 ላይ ነበር። በወቅቱ ክትባቱን ይፋ ያደረጉት ፋይዘር እና ባዮኤንቴክ ኩባንያዎች ግኝቱ ለሳይንስና ለሰው ልጅ ትልቅ እድል ነው ብለዋል። የአሜሪካ እና የጀርመን ኩባንያ የሆኑት ፋይዘር እና ባዮንቴክ በስድስት የተለያዩ ሃገራት 43 ሺህ 500 ሰዎች ላይ መሞከራቸውን የገለፁ ሲሆን አንድም ጊዜ አሳሳቢ የጤና ችግር አልታየም ብለዋል። ፋይዘርና ባዮንቴክ ክትባቱን በፈረንጆቹ የህዳር ወር መጨረሻ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥያቄ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎም ዩናይትድ ኪንግደም ክትባቱ ጥቅም ላይ እንዲውል በመፍቀድ ከዓለማችን ቀዳሚዋ አገር ሆናለች። ዩናይትድ ኪንግደም ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ክትባትን ማክሰኞ ዕለት ለዜጎቿ መስጠት የጀመረች ሲሆን የዘጠና ዓመቷ አዛውንት የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባትን በመውሰድ በዓለም የመጀመሪያዋ ሰው ሆነዋል። በመላው ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የሚገኙ ከ70 በላይ የሚሆኑ ሆስፒታሎች እድሜያቸው ከ80 ዓመት በላይ ለሆኑ አዛውንቶች እና ለጤና ባለሙያዎች ክትባቱን ለመስጠት መዘጋጀታቸው ተገልጿል። የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር መስሪያ ቤትን (ኤፍዲኤ) የሚያማክሩ ባለሙያዎች በፋይዘር/ባዮንቴክ የበለጸገው የኮሮናቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ሀሳብ ማቅረባቸውም ተገልጿል። ባለሙያዎቹ ይህን ምክረ ሃሳብ የሰጡት 23 አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ክትባቱ ሊፈጥረው የሚችለው ስጋት ከሚሰጠው ጥቅም አንጻር ምን ሊመስል እንደሚችል ምክክር ካደረጉ በኋላ ነው ተብሏል። የአሜሪካ የጤና ሚንስትር አሌክስ ረቡዕ ዕለት ''በሚቀጥሉት ቀናት ክትባቱ በእጃችን ሊገባ ይችላል፤ በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ እጅግ ተጋላጭ የሆኑትን ዜጎች መከተብ ልንጀምር እንችላል'' ብለዋል። የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባት እስካሁን በዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳ፣ ባህሬን እና ሳኡዲ አረቢያ ጥቅም ላይ ለመዋል ፍቃድ አግኝቷል። ሞደርና የዩናይትድ ስቴትስ መድኃኒት አምራች ኩባንያ የሆነው 'ሞደርና' ከኮሮናቫይረስ 95 በመቶ የሚከላከል አዲስ ክትባት ማግኘቱን ይፋ ካደረገ ሰነባብቷል። በአሁኑ ሰአትም ከአውሮፓና አሜሪካ ፈቃድ ሰጪዎች ክትባቱን ለመጠቀም የሚያስችል ፈቃድ ጠይቆ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። ሞደርና የምርምር ውጤቱን ይፋ ያደረገበትን ዕለት 'ታላቅ ቀን' በማለት ሐሴቱን የገለፀ ሲሆን፤ በቅርብ ሳምንታትም ክትባቱን ለመጠቀም ፈቃድ እንደሚያገኝ አስታውቋል። የቤተ ሙከራ ሂደቶች እንደሚያሳዩት ኤምአርኤንኤ የተሰኘው ክትባት 94 በመቶ ውጤታማና ሰዎችን ከኮሮናቫይረስ የሚያድን ነው። የክትባቱ ሙከራ አሜሪካ ውስጥ ያሉ 30 ሺህ ሰዎችን ያሳተፈ ሲሆን፤ ግማሾቹ በየአራት ሳምንቱ ክትባቱ ሲሰጣቸው ግማሾቹ ደግሞ ጥቅምና ጉዳት የሌለው መርፌ ተወግተው ውጤቱን ለመለየት ተሞክሯል። ከዚህ ሙከራ በተገኘ ውጤት መሠረት 94.5 በመቶ ሰዎች በክትባቱ ምክንያት ለኮሮናቫይረስ ሳይጋለጡ ቀርተዋል ተብሏል። ስለ ክትባቱ ውጤቱ የቀረበው ዘገባ ጨምሮም፤ ሙከራ ከተደረገባቸው መካከል 11 በኮቪድ-19 ክፉኛ የታመሙ ሰዎች የመከላከል አቅም አዳብረዋል ይላል። ስፑትኒክ 5 ይህ ሩሲያ ሰራሽ ክትባት ይፋ በተደረገ ጊዜ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአገር ውስጥ በተደረገ ምርምር አገር በቀል ክትባት አግኝተናል፤ ለሰዎች አገልግሎት እንዲውልም ይፋዊና ብሔራዊ ፍቃድ ሰጥተናል ብለው ነበር። በዓለም የመጀመርያው የተባለው ይህ ስፑትኒክ-5 ክትባት ሞስኮ የሚገኘው ጋማሊያ ኢንስቲትዩት ነው ያመረተው። ክትባቱ ይፋ የተደረገውም ነሀሴ ወር ላይ ነበር። ኢንስቲትዩቱ እንደሚለው ክትባቱ አስተማማኝ የመከላከል አቅም ይሰጣል። ፑቲን በበኩላቸው ገና ቀደም ብሎ "ይህ ክትባት አስተማማኝ እንደነበር አውቅ ነበር" ብለዋል። "ሁሉንም ሳይንሳዊ ሂደቶችን በአስተማማኝ ሁኔታ ማለፍ ችሏል" ሲሉም አስረግጠው ተናግረዋል። ፑቲን ከልጆቻቸው ለአንዷ ክትባቱ ተሰጥቷት ትንሽ አተኮሳት እንጂ ምንም አልሆነችም ብለዋል። ፑቲን የትኛዋ ልጃቸው ክትባቱን ወስዳ እንዳተኮሳት ግን በስም አልገለጹም። የሩሲያ ሳይንቲስቶች የመጀመሪያ ዙር ሙከራዎች ተደርገው ሁሉም ድንቅ ውጤት አስመዝግበዋል ብለዋል። ሳንቲስቶቹ ሰዎች ላይ ጉንፋንን የሚያመጣው አዲኖቫይረስ የተሰኘውን የተላመደ የተህዋስ ቅንጣት ተጠቅመው ነው ክትባት ሰራን ያሉት። ይህን ለማዳ ተህዋሲ አዳክመው ወደ ሰውነት በማስገባት ሕዋስ በማቀበል ክትባቱ ሰውነት ኮቪድ-19 ተህዋሲ ሲገባ ነቅቶ እንዲዋጋ ያደርገዋል ብለዋል። በአውሮፓውያኑ ታሕሳስ 5/2020 ላይ ደግሞ ይሄው ክትባት በሩሲያዋ መዲና ሞስኮ መሰጠት ተጀምሯል። በመጀመሪያው ዙር ክትባቱን ለመውሰድ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተመዝግበዋል። ሩሲያ ምን ያህል ክትባት ማምረት እንደምትችል ግልጽ ባይሆንም፤ አምራቾች እስከ ዓመቱ መገባደጃ ሁለት ሚሊዮን ጠብታ እንዲያዘጋጁ ይጠበቃል። 13 ሚሊዮን ሰዎች የሚኖሩባት የሞስኮ ከተማ ከንቲባ ሰርጌ ሶቢያን እንዳሉት፤ ክትባቱ ለማኅበረሰብ አገልግሎት ሰጪዎች፣ ለጤና ባለሙያዎች እና ለትምህርት ቤት ሠራተኞች ይሰጣል። ተጨማሪ ክትባቶች ሲመረቱ ለተቀረው ማኅበረሰብ እንደሚዳረስ ከንቲባው ጠቁመዋል። ከላይ በተዘረዘሩት የሙያ መስኮች የተሰማሩና እድሜያቸው ከ18 እስከ 60 የሆኑ ዜጎች በድረ ገጽ ተመዝግበዋል። በሞስኮ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት የክትባቱን አገልግሎት የሚሠጡ 70 ማዕከሎች ተከፍተዋል። ክትባቱ የተሰጣቸው ባለፉት 30 ቀናት የመተንፈሻ አካል ህመም የገጠማቸው፣ የከፋ የጤና እክል ያለባቸው፣ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች እንደሚለዩ ተገልጿል። ሲኖቫክ መላው ዓለም ለኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ደፋ ቀና ሲል ቻይናም እጇን አጣጥፋ አልተቀመጠችም። ሲኖቫክ የተባለ ክትባት መስራት ከጀመረች ሰነባብታለች። እንደውም በጎ ፈቃደⶉችን መከተብ ከጀመረች ቆየት ብላለች። በቻይና በሙከራ ላይ የሚገኘው የኮቪድ-19 ክትባት አመርቂ የሚባል ውጤት እያስገኘ ነውም ተብሏል። ሆኖም ክትባቱ አመርቂ ውጤት ያስገኘው በረዥም የሙከራ ሂደት ውስጥ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ሳይሆን፣ መካከለኛ ምዕራፍ በሚባለው ክፍል ነው። ተመራማሪዎች እንዳረጋገጡት ከቻይና ሰራሽ ክትባቶች አንዱና ታዋቂ እየሆነ የመጣው በሲኖቫክ ባዮቴክ የተመረተው ሲኖቫክ ክትባት በ700 ሰዎች ላይ ተሞክሮ ይበል የሚያሰኝ ውጤት አስገኝቷል። ክትባቱ የተሞከረባቸው ሰዎች በሽታን የመከላከያ ህዋሳቸውን አንቅቶ ቫይረሱን መመከት እንደቻለ ተደርሶበታል። ላንሴት በሚባለው ሥመ ጥር የሳይንስ ጆርናል ላይ ይህንን ክትባት በተመለከተ የተዘገበው፤ ክትባቱ ለጊዜው በምዕራፍ አንድና ሁለት ያስመዘገበው ውጤት እንጂ አሁን ያለበትን ደረጃ አይገልጽም። በተጨማሪም የስኬት ምጣኔው ምን ያህል እንደሆነ ይፋ አልተደረገም። በዚህ ጆርናል ላይ ስለዚህ ቻይና ሰራሹ ክትባት ከጻፉት ተመራማሪዎች አንዱ የሆኑት ዙ ፋንቻይ እንደሚሉት፤ በምዕራፍ አንድ እና በምዕራፍ 2 ሙከራዎች 600 ሰዎች ላይ ጥናት ተደርጎ ክትባቱ ለአስቸኳይ ሕክምና አገልግሎት ላይ መዋል ይችላል የሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሷል። ነገር ግን ወሳኝ በሚባው በምዕራፍ ሦስት ሙከራ ላይ ይህ የቻይና ክትባት ስላስገኘው ውጤት በተጨባጭ ተአማኒ ሳይንሳዊ ጆርናል ላይ የተጻፈ ዘገባ የለም። በቻይና በአሁን ሰዓት ሙሉ በሙሉ ሊባል በተቃረበ ደረጃ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በቁጥጥር ሥር የዋለበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ሆኖም ቻይና ለዜጎቿ ይህንን ክትባት መስጠቷን ቀጥላበታለች። በአሁኑ ሰአት ደግሞ መቀመጫውን ቤዢንግ ያደረገው የክትባት አምራቹ ኩባንያ ያዘዛቸው በርካታ የህክምና ቁሳቁሶች ከኢንዶኔዢያ መግባት ጀምረዋል። ይህ ደግሞ አገሪቱ በቅርቡ ዜጎቿን በይፋ መከተብ ልትጀምር እንደሆነ ማሳያ ነው ተብሏል። በዓለም ላይ ኮቪድ-19 ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰባቸው አገራት ተርታ የምትመደው የደቡብ አሜሪካዋ ትልቅ አገር ብራዚል በበኩሏ ቻይና ሰራሽ ክትባት ለሕዝቤ አድላለሁ ማለቷ የሚታወስ ነው። የሳኦ ፖሎ ገዥ ጃዎ ዶሪያ እንዳሉት የፌዴራል መንግሥት 46 ሚሊዮን ጠብታዎችን ለመግዛት ስምምነት ላይ ደርሷል። የክትባት ዘመቻው መቼ ይጀመራል በሚል የተጠየቁት የሳኦ ፖሎ ገዥ በፈረንጆች አዲሱ ዓመት የመጀመርያ ወር ላይ ሊሆን ይችላል ብለዋል። አስትራዜኒካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ አስትራዜኒካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ እያበለፀጉ ያሉት ክትባት ከፍተኛ ተስፋ ከተጣለባቸው ክትባቶች መካከል ነው። ይሄው ክትባት በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሙከራ መልክ ተሰጥቷል። ደቡብ አፍሪካ ለዚህ የክትባት ሙከራ የተመረጠችው በዘርፉ ባሏት ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ በርካታ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ያሉባትና ወረርሽኙም በፍጥነት እየተስፋፋባት በመሆኑ ነው። ይህ የክትባት ሙከራ ኦኤክስ1ኮቪድ-19 ክትባት የሚባል ሲሆን፤ ኮሮናቫይረስን የሚያስከትለው ሳርስ-ኮቪ-2 በተባለው ቫይረስ ሰዎች እንዳይያዙ ለመከላከል የታለመ ነው። በደቡብ አፍሪካ የሚደረገው የክትባት ሙከራ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ጥልቅ ፍተሻ ተደርጎበት በደቡብ አፍሪካ መንግሥት የጤና ምርቶች ተቆጣጣሪ ተቋምና በዊትስ ዩኒቨርስቲ ፈቃድ ተሰጥቶታል ተብሏል። ይህ ክትባት ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ከአራት ሺህ ሰዎች በላይ የተሳተፉበት ክሊኒካል ሙከራ የተደረገበት ሲሆን፤ በደቡብ አፍሪካ ከሚደረገው ሙከራ ጋር ተመሳሳይና ተዛማጅ የሆነ ሙከራ ብራዚል ውስጥ ሊጀመር እንደሆነ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም ከሁሉም የላቀ ቁጥር ያላቸው ሰዎች የሚሳተፉበት የዚህ ክትባት ሙከራ አሜሪካ ውስጥ በ30 ሺህ ሰዎች ላይ ለማካሄድ ዕቅድ ተይዟል። በሌሎች ድርጅቶች የሚሠሩ እና በሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ክትባቶች ሙከራ ተጨማሪ ውጤቶች በሚቀጥሉት ሳምንታት እና ወራቶች ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በአሁኑ ሰአትም የመጨረሻው የሙከራ ደረጃ ላይ የሚገኙ በርካታ ተጨማሪ ክትባቶች አሉ። ከነዚህም መካከል ከታች የተዘረዘሩት የሚጠቀሱ ናቸው። የክትባቶቹ ደኅንነትስ? ክትባቱ እስካሁን በደኅንነት ጉዳይ ይህ ነው የሚባል ነገር አልተነሳበትም። ነገር ግን የትኛውም መድኃኒት መቶ በመቶ እንከን አልባ ሊሆን አይችልም። አንዳንድ ተሳታፊዎች ክትባቱን የወሰዱ ሰሞን መጠነኛ ድካም፣ ራስ ምታትና ሕመም እንደተሰማቸው አስታውቀዋል። የሞደርና እና የፋይዘር ክትባት ከ90 በመቶ በላይ ውጤታማ መሆናቸው ተነግሯል። ነገር ግን የሁለቱም ድርጅቶች ውጤት የመጨረሻ ደረጃ ላይ አልደረሰም። ውጤታማነቱም ሊቀየር ይችላል ተብሏል። ቢሆንም የሞደርና ክትባት ማቀዝቀዣ ውስጥ ለማስቀመጥ ከሌሎቹ ክትባቶች በተለየ ቀላል እንደሆነ ተነግሯል። የሞደርና ክትባት ማቀዝቀዣ ውስጥ እስከ አንድ ወር መቆየት ሲችል የፋይዘር ግን ለአምስት ቀናት ብቻ ነው የሚቆየው። ሩስያ የለቀቀችው ስፑትኒክ 5 የተሰኘው ክትባትም 92 በመቶ የመከላከል አቅም እንዳለው ተነግሯል። | ኮሮናቫይረስ፡ ስንት የኮቪድ-19 ክትባቶች አሉ? ለኢትዮጵያስ የትኛው ይደርሳታል? ኮሮናቫይረስ ተከስቶ የዓለምን አጠቃላይ ገጽታ መቀየር ከጀመረ እንሆ አንድ ዓመት ሊሞላው ተቃርቧል። በዚህ ጊዜም ከ71 ሚሊዮን በላይ የምድራችን ነዋሪ በበሽታው መያዙ የተረጋገጠ ሲሆን ከ1.6 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሰበብ ህይወታቸውን አጥተዋል። በሽታው ያላዳረሰው የዓለም ክፍል የሌለ ሲሆን እንደተሰጋው የከፋ ጉዳትን ባያደርስም በአፍሪካ አገራት ውስጥም ከ2.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታው ሲያዙ ከ56 ሺህ በላይ ድግሞ ለሞት ተዳርገዋል። ከዚህ ውስጥ ደግሞ በኢትዮጵያ ከ116 ሺህ ሰዎች በላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ከ1 ሺህ 880 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ከዓለም ዙሪያ የተሰባሰቡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በበሽታው መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ከበሽታው ያገገሙ ቢሆንም አስካሁን ፈዋሽነቱ የተረጋገጠ መድኃኒት ለቫይረሱ አልተገኘም። በሽታው ቻይና ውስጥ መከሰቱ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ አገራት ለበሽታው መከላከያ የሚሆን ክትባት እንዲሁም የተያዙ ሰዎችን ለማከም የሚያገለግል መድኃኒት ለማግኘት ሊቃውንት ቀን ከሌት እየጣሩ ይገኛሉ። እስካሁን በተደረጉ ምርምሮችና ሙከራዎች በርካታ ተስፋ ሰጪ የክትባት ውጤቶች መገኘታቸው ከመነገሩ ባሻገር፤ በሽታውን ለመከላከል ያስችላሉ የተባሉ ጥቂት ክትባቶችም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ለበሽታው ተጋላጭ ናቸው ለተባሉ ሰዎች መሰጠት ተጀምሯል። በዚህ ረገድ ቀዳሚውን የተጠቃሚነት ዕድል ያገኙት ባለጸጋ አገራት ሲሆኑ የዓለም ጤና ድርጅት ደግሞ ክትባቶቹ ለሁሉም እንዲዳረስ ጥረት እያደረገ መሆኑን አመልክቷል። አገራትም ለዜጎቻቸው ክትባቱን ለማቅረብ ባላቸው አማራጮች ሁሉ እየሞከሩ ነው። ኢትዮጵያም እንዲሁ ኮቫክስ ከተሰኘው ዓለም አቀፍ የክትባት ድጋፍ ሰጪና እቅራቢ በኩል ለአገልግሎት ከሚቀርቡት የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ጥያቄ እንዳቀረበች የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ባለፈው ሳምንት ገልጸዋል። ሚኒስትሯ ጨምረውም ለአገልግሎት ብቁ ከሆኑ የክትባት አይነቶች መካከል ኢትዮጵያም እንድታገኝ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረው፤ በኮቫክስ በኩል ክትባቱን በፍጥነት ለማግኘትና በቅድሚያ መከተብ ለሚገባቸው ወገኖች እንዲደርስ እንደሚደረግ ገልጸዋል። ለመሆኑ የትኞቹ ክትባቶች ጥቅም ላይ ውለዋል? በአሁኑ ጊዜ በርካታ መድኃኒት አምራች ኩባንያዎችና አገራት ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሚሆን ክትባት በማበልጸግ ላይ ሲሆኑ ጥቂቶቹም በስራ ላይ መዋል ጀምረዋል። ፋይዘር/ባዮንቴክ ኮሮናቫይረስን በመከላከል 90 በመቶ ውጤታማ ነው የተባለው ይህ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ይፋ የሆነው በፈረንጆቹ ሕዳር 9/2020 ላይ ነበር። በወቅቱ ክትባቱን ይፋ ያደረጉት ፋይዘር እና ባዮኤንቴክ ኩባንያዎች ግኝቱ ለሳይንስና ለሰው ልጅ ትልቅ እድል ነው ብለዋል። የአሜሪካ እና የጀርመን ኩባንያ የሆኑት ፋይዘር እና ባዮንቴክ በስድስት የተለያዩ ሃገራት 43 ሺህ 500 ሰዎች ላይ መሞከራቸውን የገለፁ ሲሆን አንድም ጊዜ አሳሳቢ የጤና ችግር አልታየም ብለዋል። ፋይዘርና ባዮንቴክ ክትባቱን በፈረንጆቹ የህዳር ወር መጨረሻ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥያቄ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎም ዩናይትድ ኪንግደም ክትባቱ ጥቅም ላይ እንዲውል በመፍቀድ ከዓለማችን ቀዳሚዋ አገር ሆናለች። ዩናይትድ ኪንግደም ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ክትባትን ማክሰኞ ዕለት ለዜጎቿ መስጠት የጀመረች ሲሆን የዘጠና ዓመቷ አዛውንት የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባትን በመውሰድ በዓለም የመጀመሪያዋ ሰው ሆነዋል። በመላው ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የሚገኙ ከ70 በላይ የሚሆኑ ሆስፒታሎች እድሜያቸው ከ80 ዓመት በላይ ለሆኑ አዛውንቶች እና ለጤና ባለሙያዎች ክትባቱን ለመስጠት መዘጋጀታቸው ተገልጿል። የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር መስሪያ ቤትን (ኤፍዲኤ) የሚያማክሩ ባለሙያዎች በፋይዘር/ባዮንቴክ የበለጸገው የኮሮናቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ሀሳብ ማቅረባቸውም ተገልጿል። ባለሙያዎቹ ይህን ምክረ ሃሳብ የሰጡት 23 አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ክትባቱ ሊፈጥረው የሚችለው ስጋት ከሚሰጠው ጥቅም አንጻር ምን ሊመስል እንደሚችል ምክክር ካደረጉ በኋላ ነው ተብሏል። የአሜሪካ የጤና ሚንስትር አሌክስ ረቡዕ ዕለት ''በሚቀጥሉት ቀናት ክትባቱ በእጃችን ሊገባ ይችላል፤ በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ እጅግ ተጋላጭ የሆኑትን ዜጎች መከተብ ልንጀምር እንችላል'' ብለዋል። የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባት እስካሁን በዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳ፣ ባህሬን እና ሳኡዲ አረቢያ ጥቅም ላይ ለመዋል ፍቃድ አግኝቷል። ሞደርና የዩናይትድ ስቴትስ መድኃኒት አምራች ኩባንያ የሆነው 'ሞደርና' ከኮሮናቫይረስ 95 በመቶ የሚከላከል አዲስ ክትባት ማግኘቱን ይፋ ካደረገ ሰነባብቷል። በአሁኑ ሰአትም ከአውሮፓና አሜሪካ ፈቃድ ሰጪዎች ክትባቱን ለመጠቀም የሚያስችል ፈቃድ ጠይቆ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። ሞደርና የምርምር ውጤቱን ይፋ ያደረገበትን ዕለት 'ታላቅ ቀን' በማለት ሐሴቱን የገለፀ ሲሆን፤ በቅርብ ሳምንታትም ክትባቱን ለመጠቀም ፈቃድ እንደሚያገኝ አስታውቋል። የቤተ ሙከራ ሂደቶች እንደሚያሳዩት ኤምአርኤንኤ የተሰኘው ክትባት 94 በመቶ ውጤታማና ሰዎችን ከኮሮናቫይረስ የሚያድን ነው። የክትባቱ ሙከራ አሜሪካ ውስጥ ያሉ 30 ሺህ ሰዎችን ያሳተፈ ሲሆን፤ ግማሾቹ በየአራት ሳምንቱ ክትባቱ ሲሰጣቸው ግማሾቹ ደግሞ ጥቅምና ጉዳት የሌለው መርፌ ተወግተው ውጤቱን ለመለየት ተሞክሯል። ከዚህ ሙከራ በተገኘ ውጤት መሠረት 94.5 በመቶ ሰዎች በክትባቱ ምክንያት ለኮሮናቫይረስ ሳይጋለጡ ቀርተዋል ተብሏል። ስለ ክትባቱ ውጤቱ የቀረበው ዘገባ ጨምሮም፤ ሙከራ ከተደረገባቸው መካከል 11 በኮቪድ-19 ክፉኛ የታመሙ ሰዎች የመከላከል አቅም አዳብረዋል ይላል። ስፑትኒክ 5 ይህ ሩሲያ ሰራሽ ክትባት ይፋ በተደረገ ጊዜ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአገር ውስጥ በተደረገ ምርምር አገር በቀል ክትባት አግኝተናል፤ ለሰዎች አገልግሎት እንዲውልም ይፋዊና ብሔራዊ ፍቃድ ሰጥተናል ብለው ነበር። በዓለም የመጀመርያው የተባለው ይህ ስፑትኒክ-5 ክትባት ሞስኮ የሚገኘው ጋማሊያ ኢንስቲትዩት ነው ያመረተው። ክትባቱ ይፋ የተደረገውም ነሀሴ ወር ላይ ነበር። ኢንስቲትዩቱ እንደሚለው ክትባቱ አስተማማኝ የመከላከል አቅም ይሰጣል። ፑቲን በበኩላቸው ገና ቀደም ብሎ "ይህ ክትባት አስተማማኝ እንደነበር አውቅ ነበር" ብለዋል። "ሁሉንም ሳይንሳዊ ሂደቶችን በአስተማማኝ ሁኔታ ማለፍ ችሏል" ሲሉም አስረግጠው ተናግረዋል። ፑቲን ከልጆቻቸው ለአንዷ ክትባቱ ተሰጥቷት ትንሽ አተኮሳት እንጂ ምንም አልሆነችም ብለዋል። ፑቲን የትኛዋ ልጃቸው ክትባቱን ወስዳ እንዳተኮሳት ግን በስም አልገለጹም። የሩሲያ ሳይንቲስቶች የመጀመሪያ ዙር ሙከራዎች ተደርገው ሁሉም ድንቅ ውጤት አስመዝግበዋል ብለዋል። ሳንቲስቶቹ ሰዎች ላይ ጉንፋንን የሚያመጣው አዲኖቫይረስ የተሰኘውን የተላመደ የተህዋስ ቅንጣት ተጠቅመው ነው ክትባት ሰራን ያሉት። ይህን ለማዳ ተህዋሲ አዳክመው ወደ ሰውነት በማስገባት ሕዋስ በማቀበል ክትባቱ ሰውነት ኮቪድ-19 ተህዋሲ ሲገባ ነቅቶ እንዲዋጋ ያደርገዋል ብለዋል። በአውሮፓውያኑ ታሕሳስ 5/2020 ላይ ደግሞ ይሄው ክትባት በሩሲያዋ መዲና ሞስኮ መሰጠት ተጀምሯል። በመጀመሪያው ዙር ክትባቱን ለመውሰድ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተመዝግበዋል። ሩሲያ ምን ያህል ክትባት ማምረት እንደምትችል ግልጽ ባይሆንም፤ አምራቾች እስከ ዓመቱ መገባደጃ ሁለት ሚሊዮን ጠብታ እንዲያዘጋጁ ይጠበቃል። 13 ሚሊዮን ሰዎች የሚኖሩባት የሞስኮ ከተማ ከንቲባ ሰርጌ ሶቢያን እንዳሉት፤ ክትባቱ ለማኅበረሰብ አገልግሎት ሰጪዎች፣ ለጤና ባለሙያዎች እና ለትምህርት ቤት ሠራተኞች ይሰጣል። ተጨማሪ ክትባቶች ሲመረቱ ለተቀረው ማኅበረሰብ እንደሚዳረስ ከንቲባው ጠቁመዋል። ከላይ በተዘረዘሩት የሙያ መስኮች የተሰማሩና እድሜያቸው ከ18 እስከ 60 የሆኑ ዜጎች በድረ ገጽ ተመዝግበዋል። በሞስኮ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት የክትባቱን አገልግሎት የሚሠጡ 70 ማዕከሎች ተከፍተዋል። ክትባቱ የተሰጣቸው ባለፉት 30 ቀናት የመተንፈሻ አካል ህመም የገጠማቸው፣ የከፋ የጤና እክል ያለባቸው፣ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች እንደሚለዩ ተገልጿል። ሲኖቫክ መላው ዓለም ለኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ደፋ ቀና ሲል ቻይናም እጇን አጣጥፋ አልተቀመጠችም። ሲኖቫክ የተባለ ክትባት መስራት ከጀመረች ሰነባብታለች። እንደውም በጎ ፈቃደⶉችን መከተብ ከጀመረች ቆየት ብላለች። በቻይና በሙከራ ላይ የሚገኘው የኮቪድ-19 ክትባት አመርቂ የሚባል ውጤት እያስገኘ ነውም ተብሏል። ሆኖም ክትባቱ አመርቂ ውጤት ያስገኘው በረዥም የሙከራ ሂደት ውስጥ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ሳይሆን፣ መካከለኛ ምዕራፍ በሚባለው ክፍል ነው። ተመራማሪዎች እንዳረጋገጡት ከቻይና ሰራሽ ክትባቶች አንዱና ታዋቂ እየሆነ የመጣው በሲኖቫክ ባዮቴክ የተመረተው ሲኖቫክ ክትባት በ700 ሰዎች ላይ ተሞክሮ ይበል የሚያሰኝ ውጤት አስገኝቷል። ክትባቱ የተሞከረባቸው ሰዎች በሽታን የመከላከያ ህዋሳቸውን አንቅቶ ቫይረሱን መመከት እንደቻለ ተደርሶበታል። ላንሴት በሚባለው ሥመ ጥር የሳይንስ ጆርናል ላይ ይህንን ክትባት በተመለከተ የተዘገበው፤ ክትባቱ ለጊዜው በምዕራፍ አንድና ሁለት ያስመዘገበው ውጤት እንጂ አሁን ያለበትን ደረጃ አይገልጽም። በተጨማሪም የስኬት ምጣኔው ምን ያህል እንደሆነ ይፋ አልተደረገም። በዚህ ጆርናል ላይ ስለዚህ ቻይና ሰራሹ ክትባት ከጻፉት ተመራማሪዎች አንዱ የሆኑት ዙ ፋንቻይ እንደሚሉት፤ በምዕራፍ አንድ እና በምዕራፍ 2 ሙከራዎች 600 ሰዎች ላይ ጥናት ተደርጎ ክትባቱ ለአስቸኳይ ሕክምና አገልግሎት ላይ መዋል ይችላል የሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሷል። ነገር ግን ወሳኝ በሚባው በምዕራፍ ሦስት ሙከራ ላይ ይህ የቻይና ክትባት ስላስገኘው ውጤት በተጨባጭ ተአማኒ ሳይንሳዊ ጆርናል ላይ የተጻፈ ዘገባ የለም። በቻይና በአሁን ሰዓት ሙሉ በሙሉ ሊባል በተቃረበ ደረጃ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በቁጥጥር ሥር የዋለበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ሆኖም ቻይና ለዜጎቿ ይህንን ክትባት መስጠቷን ቀጥላበታለች። በአሁኑ ሰአት ደግሞ መቀመጫውን ቤዢንግ ያደረገው የክትባት አምራቹ ኩባንያ ያዘዛቸው በርካታ የህክምና ቁሳቁሶች ከኢንዶኔዢያ መግባት ጀምረዋል። ይህ ደግሞ አገሪቱ በቅርቡ ዜጎቿን በይፋ መከተብ ልትጀምር እንደሆነ ማሳያ ነው ተብሏል። በዓለም ላይ ኮቪድ-19 ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰባቸው አገራት ተርታ የምትመደው የደቡብ አሜሪካዋ ትልቅ አገር ብራዚል በበኩሏ ቻይና ሰራሽ ክትባት ለሕዝቤ አድላለሁ ማለቷ የሚታወስ ነው። የሳኦ ፖሎ ገዥ ጃዎ ዶሪያ እንዳሉት የፌዴራል መንግሥት 46 ሚሊዮን ጠብታዎችን ለመግዛት ስምምነት ላይ ደርሷል። የክትባት ዘመቻው መቼ ይጀመራል በሚል የተጠየቁት የሳኦ ፖሎ ገዥ በፈረንጆች አዲሱ ዓመት የመጀመርያ ወር ላይ ሊሆን ይችላል ብለዋል። አስትራዜኒካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ አስትራዜኒካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ እያበለፀጉ ያሉት ክትባት ከፍተኛ ተስፋ ከተጣለባቸው ክትባቶች መካከል ነው። ይሄው ክትባት በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሙከራ መልክ ተሰጥቷል። ደቡብ አፍሪካ ለዚህ የክትባት ሙከራ የተመረጠችው በዘርፉ ባሏት ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ በርካታ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ያሉባትና ወረርሽኙም በፍጥነት እየተስፋፋባት በመሆኑ ነው። ይህ የክትባት ሙከራ ኦኤክስ1ኮቪድ-19 ክትባት የሚባል ሲሆን፤ ኮሮናቫይረስን የሚያስከትለው ሳርስ-ኮቪ-2 በተባለው ቫይረስ ሰዎች እንዳይያዙ ለመከላከል የታለመ ነው። በደቡብ አፍሪካ የሚደረገው የክትባት ሙከራ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ጥልቅ ፍተሻ ተደርጎበት በደቡብ አፍሪካ መንግሥት የጤና ምርቶች ተቆጣጣሪ ተቋምና በዊትስ ዩኒቨርስቲ ፈቃድ ተሰጥቶታል ተብሏል። ይህ ክትባት ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ከአራት ሺህ ሰዎች በላይ የተሳተፉበት ክሊኒካል ሙከራ የተደረገበት ሲሆን፤ በደቡብ አፍሪካ ከሚደረገው ሙከራ ጋር ተመሳሳይና ተዛማጅ የሆነ ሙከራ ብራዚል ውስጥ ሊጀመር እንደሆነ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም ከሁሉም የላቀ ቁጥር ያላቸው ሰዎች የሚሳተፉበት የዚህ ክትባት ሙከራ አሜሪካ ውስጥ በ30 ሺህ ሰዎች ላይ ለማካሄድ ዕቅድ ተይዟል። በሌሎች ድርጅቶች የሚሠሩ እና በሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ክትባቶች ሙከራ ተጨማሪ ውጤቶች በሚቀጥሉት ሳምንታት እና ወራቶች ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በአሁኑ ሰአትም የመጨረሻው የሙከራ ደረጃ ላይ የሚገኙ በርካታ ተጨማሪ ክትባቶች አሉ። ከነዚህም መካከል ከታች የተዘረዘሩት የሚጠቀሱ ናቸው። የክትባቶቹ ደኅንነትስ? ክትባቱ እስካሁን በደኅንነት ጉዳይ ይህ ነው የሚባል ነገር አልተነሳበትም። ነገር ግን የትኛውም መድኃኒት መቶ በመቶ እንከን አልባ ሊሆን አይችልም። አንዳንድ ተሳታፊዎች ክትባቱን የወሰዱ ሰሞን መጠነኛ ድካም፣ ራስ ምታትና ሕመም እንደተሰማቸው አስታውቀዋል። የሞደርና እና የፋይዘር ክትባት ከ90 በመቶ በላይ ውጤታማ መሆናቸው ተነግሯል። ነገር ግን የሁለቱም ድርጅቶች ውጤት የመጨረሻ ደረጃ ላይ አልደረሰም። ውጤታማነቱም ሊቀየር ይችላል ተብሏል። ቢሆንም የሞደርና ክትባት ማቀዝቀዣ ውስጥ ለማስቀመጥ ከሌሎቹ ክትባቶች በተለየ ቀላል እንደሆነ ተነግሯል። የሞደርና ክትባት ማቀዝቀዣ ውስጥ እስከ አንድ ወር መቆየት ሲችል የፋይዘር ግን ለአምስት ቀናት ብቻ ነው የሚቆየው። ሩስያ የለቀቀችው ስፑትኒክ 5 የተሰኘው ክትባትም 92 በመቶ የመከላከል አቅም እንዳለው ተነግሯል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55273576 |
0business
| የመንግሥት ድርጅቶችን 'ፕራይቬታይዝ' ጉዳይ እጅግ አከራካሪ ሆኗል | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን የመጡ ሰሞን ነበር ከኤርትራ ጋር ሰላም እንደሚያሰፍኑ፤ በመንግሥት ስር ያሉ ግዙፍ የኢኮኖሚ ተቋማት ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ወደ ግል እንዲሸጋጋሩ ለማድረግ እንደሚሰሩ ይፋ አደረጉ። በወቅቱ ሁለቱም አበይት ጉዳዮች አነጋጋሪ ነበሩ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀዳሚ ሥራ የነበረው ግን የኤርትራ ጉዳይ ነበር። 'የፕራይቬታይዜሽኑ' ጉዳይ በይደር ተቀምጦ ቆይቷል። ጉዳዩ ለሕዝብ ጆሮ ከደረሰ ከአንድ ዓመት በኋላ አሁን እንደ አዲስ ተነስቶ መናጋገሪያ ሆኗል። ሐሙስ እለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዉጭ ኩባንያዎች በቴሌኮሙኑኬሽን ዘርፍ መዋዕለ ነዋይ እንዲያፈሱ የሚፈቅድ ረቂቅ ሕግ አፅድቋል። ምክር ቤቱ ገለልተኛ የኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን መስሪያ ቤትን ለማቋቋም የሚያስችል አዋጅም እንዳጸደቀ የተከበሩ ዶ/ር ሙሉጌታ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ባለስልጣኑ የቴሌኮም ዋጋ ትመናን፣ የኮምኒኬሽን ፖሊሲዎችን ማስፈጸምና የኮምኒኬሽን ድርጅቶችን፣ ኢንተርኔትንና የሬዲዮ ሞገዶችን ይቆጣጠራል ሲሉም ያብራራሉ። • «አማካሪ አያስፈልገኝም ብሎ የሚያስብ መሪ አልገባውም ማለት ነው» ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ 'ፕራይቬታይዜሽን' ወይንም የመንግሥት ድርጅቶችን ለግል ይዞታነት የማዞር ጉዳይ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎችንና ፖለቲከኞችን በሦስት ጎራ ከፋፍሏል። አንደኛው ጎራ 'አዎ መሸጥ አለባቸው፤ እኒህ ድርጅቶች ገበያውን በሞኖፖል ይዘውት እስከመቼ?' የሚል ሃሳብ የሚያነሱ ግለሰቦች ስብስብ ነው። ሁለተኛው ደግሞ 'ይህ ሃገር ከመሸጥ አይተናነስም፤ የመወዳደር አቅም ሳይኖረን እንዴት ሃብታሞች ሃገራችን እንዲገቡ እንፈቅዳለን?' ሲሉ ይሞግታሉ። ሦስተኛው 'መሸጥ ያለባቸው እና የለሌባቸው አሉ' ሲሉ የሚመክሩ ናቸው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ከሁለቱ ፅንፍ ሃሳቦች መሃል ላይ ናቸው። «ይህንን ፖሊሲ የሚያስፈፅሙ ሰዎች ሁሉም ነገር ፕራይቬታይዝ ይደረጋል ብለው ማሰብ የለባቸውም። መደረግ ያለባቸው አሉ፤ መደረግ የሌለባቸው አሉ። ለምሳሌ በምንም መሥፈርት የኢትዮጵያ አየር መንገድ መደረግ የለበትም። በፖለቲካም በኢኮኖሚም መሥፈርት መደረግ የለበትም። ከሃገር ጥቅምም አንፃር መደረግ የሌለበት ነው" በማለት አጥብቀው ይከራከራሉ። ነገር ግን ይላሉ ፕሮፌሰር አለማየሁ «ሌሎቹን ለምሳሌ ስኳር ፋብሪካን ፕራቬታይዝ ብታደርገው፤ ብትሸጠው አዋጭ ነው። ኢትዮ-ቴሌኮም ላይ ስትመጣ ደግሞ አብዛኛውን ድርሻ እኛ ይዘነው ለምሳሌ 70 በመቶውን ከያዝነው በኋላ ሌላውን መሸጥ አዋጭ ነው። ቀሪውን ድርሻ የሚይዘው ደግሞ አፍሪካዊ ድርጅት ቢሆን ይመረጣል፤ በዚያውም የቀጠናውን ጥምረት ለማጠናከር።» • ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት? መሸጡ የግድ ቢሆን እንኳ 'ሬጉላቶሪ ቦዲ' [ተቆጣጣሪ አካል] ማቋቋም ሊውል ሊያድር የሚገባው ጉዳይ እንዳልሆነ ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ። «ለምሳሌ መንግሥት 60 በመቶ ገቢ ያገኘው ከቴሌ ነው። ሌላው 30 በመቶ ከንግድ ባንክ ነው። ስለዚህ ንግድ ባንክን፤ ቴሌን ሸጥክ ማለት ባዶ እጅህን ነው አራት ኪሎ ቁጭ የምትለው። ስለዚህ ምጣኔ ሃብታዊ ውሳኔ ለመወሰን ምንም ዓይነት 'ኢንቨስትመንት' የለህም ማለት ነው። አሁን መንግሥት ማድረግ ያለበት፤ በተለይ እንደ ቴሌ ላሉት የተወሰነውን ሽጦ ሲያበቃ የመቆጣጠር አቅሙ ሲጎለብት ለሌሎች ክፍት ማድረግ ነው።» የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የነበሩት ፖለቲከኛው ዮናታን ተስፋዬ የመንግሥትን 'ፕራቬታይዜሽን' ዕቅድ ከሚደግፉት መካከል አንዱ ናቸው። «ፕራቬታይዝ የማድረጉ አንደኛ ጥቅም 'ሞኖፖሊ' እንዳይኖር ማድረጉ ነው። ሁለተኛ የፉክክር ገበያ ይኖራል፤ ይህ ደግሞ ሕብረተሰቡ የተሻለ ምርትና አገልግሎት እንዲያገኝ ያደርጋል።» ምጣኔ ሃብታዊውን ትንታኔ ለባለሙያዎች ልትወው፤ የሚሉት አቶ ዮናታን «የመንግሥት ድርጅቶች በመንግሥት ቁጥጥር ሥር መሆን አምባገነንነትን ያበረታታል» ባይ ናቸው። «'እኔ ነኝ አሳቢ፤ እኔ የተሻለ ለማሕበረሰቡ እጨነቃለሁ' የሚል ሥነ-ልቡናን እያሳደረ ነው የሚሄደው። ይህ አስተሳሰብ ደግሞ ሥር በሰደደ ቁጥር ሌሎች ተፎካካሪ ኃይሎችን እንደ ሥልጣን ተቀናቃኝ ነው የሚያየው፤ ምክንያቱም ራሱ ነጋዴው መንግሥት እየሆነ ስለሚመጣ። ስለዚህ ፖለቲካዊ ብልሽትን ይፈጥራል፤ ነፃ ገበያ እና ፉክክር የሌለበት፤ አንድ ወገን ብቻ እሴት የሚጨምርበት በጣም ደካማ የገበያ ሥርዓት እንዲኖር ነው የሚያደርገው።» • ኢትዮጵያ ኢንትርኔትን ስታቋርጥ በየቀኑ 4.5 ሚሊዮን ዶላር ታጣለች የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች 'ዘ ቢግ ፋይቭ' ይሏቸዋል፤ አየር መንገድ፣ ቴሌኮም፣ ባንክ፣ ባቡር እና ስኳር ፋብሪካዎች። መንግሥት እነዚህን ድርጅቶች ለግል ባለሃብቶች ሲሸጥ ሕዝብን ማማከር አለበት የሚሉ ሃሳቦች በአለፍ ገደም እያሉ ይደመጣሉ። አቶ ዮናታን «ይሄ እኮ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው. . .» ይላሉ። «ይሄ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው። የኢኮኖሚ ጉዳይ ደግሞ በባለሙያዎች ጥናት ተደርጎ፤ በዚያ ጥናት ላይ ተመርኩዞ፤ ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ይሄ ያዋጣል ብለን የምንወስነው ነገር ነው እንጂ ልክ እንደባንዲራ ጉዳይ ወይም የክልል እንሁን ጥያቄ ሕዝበ-ውሳኔ የሚደረግበት አይደለም። በየትኛውም ዓለም ላይ ሕዝብ በእንደዚህ ዓይነት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ቀጥተኛ የሆነ ውሳኔ ማሳለፍ አይችልም።» መሰል የፖሊሲ ለውጦች የሕዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ ባይኖራቸው እንኳ ምርጫ እስኪመጣ መጠበቅ አይቻልም ወይ? በርካቶች የሚያነሱት ጥያቄ ነው። እርግጥ ነው አቶ ዮናታን በዚህ ጉዳይ ይስማማል። ግን እሱ አልሆነም፤ አሁን ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ለሃገሪቱ ይጠቅማል የሚለውን ፖሊሲ የማፅደቅ መብት አለው ይላል። «አሁን ባለንበት ወቅት ኢኮኖሚው እየወደቀ ነው። ለዚህ ደግሞ አንድ ትልቅ ድርሻ የሚወስዱት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ናቸው። እነዚህ የልማት ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ ስላልሆኑ አሁን ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ምንም ሊቋቋመው የሚችለው አይደለም። የውጭ ባለሃብቶችን መሳብ የሚቻለው ደግሞ የኢኮኖሚ ፖሊሲውን መቀየር ሲቻል ነው።» ነዋሪነቱን እንግሊዝ ያደረገው የምጣኔ ሃብት ምሁሩ እዮብ ባልቻ፤ አዲሱ የፕራቬታይዜሽን አጀንዳ በግለሰቦች የሚመራ ነው ሲል ይሞግታል። እንደ እዮብ ትንተና አሁን ጠቅላይ ሚኒስትሩን በምጣኔ ሃብት ጉዳይ የሚያማክሩ ግለሰቦች ከዓለም ባንክና እና ዓለም አቀፉ ገንዘብ ድርጅት ጋር በቀጥታም ሆነ ተዘዋዋሪ ቁርኝት ያላቸው ናቸው። ምንም እንኳ የእዮብ ትንታኔ ግለሰቦቹ ላሳኩት ግብ ምስጋና ቢሰጥም በፕራቬታይዜሽን ጉዳይ ላይ ያላቸው አቋም አያስተማምንም ይላል። ፕሮፌሰር አለማየሁም ቢሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሥር ጫና እንዳሉና ያንን ጫና ለመቋቋም የሚያስችል የምጣኔ ሃብት አቅም የላቸውም ባይ ናቸው። ለፕሮፌሰሩ የመንግሥት ድርጅቶችን ለገበያ የማቅረብ ጊዜው አሁን አይደለም። ትርፉ ከመንግሥት ሞኖፖሊ ወደ ግለሰብ ሞኖፖሊ መሸጋገር ነው ይላሉ። • ወሳኝ ምጣኔ ሃብታዊ እርምጃዎች በ100 ቀናት «ለምሳሌ ቴሌን በ5 ወይም 10 ቢሊዮን ዶላር ሸጥነው እንበል። ነገ ያ ድርጅት የሚያተርፈውን አትርፎ የቀረውን ይዞ ሹልክ ይላል። በኢትዮጵያ ሕግ ደግሞ ያተረፍከውን ገንዘብ 'እክስፓትረየት' [ይዘህ መውጣት] ማድረግ ትችላለህ፤ የፈለግከውን። መሰል ስትራቴጂክ ነገሮችን ስታስብ መንግሥት ለፕራቬታይዜሽን መጣደፍ የለበትም። መንግሥትም ስለጨነቀውና ዶላር ስላጠረው እንጂ ፈልጎት አይመስለኝም» ይላሉ። ለአቶ ዮናታን ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው። መከራከሪያው ደግሞ ኢኮኖሚያችን እየደቀቀ ነው የሚል። ፕሮፌሰር አለማየሁ ደግሞ ጉዳዩን በሁለት ከፍለው ያዩታል። «አንደኛው ፖለቲካዊ ነው፤ ማለት አንድ መንግሥት ይህንን ፖሊሲ አስተዋውቆ የሕዝቡን ይሁንታ ካገኘ ሊያስፈፅመው ይችላል። ምክንያቱም እነዚህ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ የሚቆጣጠሩ ተቋማት ናቸው» ይላሉ። • የስኳር ፋብሪካዎችን ለግል ባለሃብቶች የመስጠት ፋይዳና ፈተናዎቹ ስለዚህ ትክክለኛው ጊዜ መንግሥት የሕዝቡን ፖለቲካዊ ውክልና ባገኘበት ጊዜ መሆን እንዳለበት የሚጠቅሱት ፕሮፌሰር አለማየሁ «በኢኮኖሚ መነፅር ስናየው ግን አሁን ባለው ሁኔታ በእኔ ግምት ትክክል አይደለም። ምክንያቱም መንግሥትም አልተረጋጋም፤ ሃገሩም አልተረጋጋም። ግን ደግሞ መንግሥት ብር የለውም። ከጀርባቸው ጠንካራ ኃይሎች ካልሸጣችሁ እይሏቸው ይሆናል። ስለዚህ ያለው አማራጭ ቅድም ያነሳሁት ሃሳብ ነው። የተወሰነውን ፕራይቬታይዝ ማድረግ።» | የመንግሥት ድርጅቶችን 'ፕራይቬታይዝ' ጉዳይ እጅግ አከራካሪ ሆኗል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን የመጡ ሰሞን ነበር ከኤርትራ ጋር ሰላም እንደሚያሰፍኑ፤ በመንግሥት ስር ያሉ ግዙፍ የኢኮኖሚ ተቋማት ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ወደ ግል እንዲሸጋጋሩ ለማድረግ እንደሚሰሩ ይፋ አደረጉ። በወቅቱ ሁለቱም አበይት ጉዳዮች አነጋጋሪ ነበሩ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀዳሚ ሥራ የነበረው ግን የኤርትራ ጉዳይ ነበር። 'የፕራይቬታይዜሽኑ' ጉዳይ በይደር ተቀምጦ ቆይቷል። ጉዳዩ ለሕዝብ ጆሮ ከደረሰ ከአንድ ዓመት በኋላ አሁን እንደ አዲስ ተነስቶ መናጋገሪያ ሆኗል። ሐሙስ እለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዉጭ ኩባንያዎች በቴሌኮሙኑኬሽን ዘርፍ መዋዕለ ነዋይ እንዲያፈሱ የሚፈቅድ ረቂቅ ሕግ አፅድቋል። ምክር ቤቱ ገለልተኛ የኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን መስሪያ ቤትን ለማቋቋም የሚያስችል አዋጅም እንዳጸደቀ የተከበሩ ዶ/ር ሙሉጌታ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ባለስልጣኑ የቴሌኮም ዋጋ ትመናን፣ የኮምኒኬሽን ፖሊሲዎችን ማስፈጸምና የኮምኒኬሽን ድርጅቶችን፣ ኢንተርኔትንና የሬዲዮ ሞገዶችን ይቆጣጠራል ሲሉም ያብራራሉ። • «አማካሪ አያስፈልገኝም ብሎ የሚያስብ መሪ አልገባውም ማለት ነው» ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ 'ፕራይቬታይዜሽን' ወይንም የመንግሥት ድርጅቶችን ለግል ይዞታነት የማዞር ጉዳይ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎችንና ፖለቲከኞችን በሦስት ጎራ ከፋፍሏል። አንደኛው ጎራ 'አዎ መሸጥ አለባቸው፤ እኒህ ድርጅቶች ገበያውን በሞኖፖል ይዘውት እስከመቼ?' የሚል ሃሳብ የሚያነሱ ግለሰቦች ስብስብ ነው። ሁለተኛው ደግሞ 'ይህ ሃገር ከመሸጥ አይተናነስም፤ የመወዳደር አቅም ሳይኖረን እንዴት ሃብታሞች ሃገራችን እንዲገቡ እንፈቅዳለን?' ሲሉ ይሞግታሉ። ሦስተኛው 'መሸጥ ያለባቸው እና የለሌባቸው አሉ' ሲሉ የሚመክሩ ናቸው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ከሁለቱ ፅንፍ ሃሳቦች መሃል ላይ ናቸው። «ይህንን ፖሊሲ የሚያስፈፅሙ ሰዎች ሁሉም ነገር ፕራይቬታይዝ ይደረጋል ብለው ማሰብ የለባቸውም። መደረግ ያለባቸው አሉ፤ መደረግ የሌለባቸው አሉ። ለምሳሌ በምንም መሥፈርት የኢትዮጵያ አየር መንገድ መደረግ የለበትም። በፖለቲካም በኢኮኖሚም መሥፈርት መደረግ የለበትም። ከሃገር ጥቅምም አንፃር መደረግ የሌለበት ነው" በማለት አጥብቀው ይከራከራሉ። ነገር ግን ይላሉ ፕሮፌሰር አለማየሁ «ሌሎቹን ለምሳሌ ስኳር ፋብሪካን ፕራቬታይዝ ብታደርገው፤ ብትሸጠው አዋጭ ነው። ኢትዮ-ቴሌኮም ላይ ስትመጣ ደግሞ አብዛኛውን ድርሻ እኛ ይዘነው ለምሳሌ 70 በመቶውን ከያዝነው በኋላ ሌላውን መሸጥ አዋጭ ነው። ቀሪውን ድርሻ የሚይዘው ደግሞ አፍሪካዊ ድርጅት ቢሆን ይመረጣል፤ በዚያውም የቀጠናውን ጥምረት ለማጠናከር።» • ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት? መሸጡ የግድ ቢሆን እንኳ 'ሬጉላቶሪ ቦዲ' [ተቆጣጣሪ አካል] ማቋቋም ሊውል ሊያድር የሚገባው ጉዳይ እንዳልሆነ ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ። «ለምሳሌ መንግሥት 60 በመቶ ገቢ ያገኘው ከቴሌ ነው። ሌላው 30 በመቶ ከንግድ ባንክ ነው። ስለዚህ ንግድ ባንክን፤ ቴሌን ሸጥክ ማለት ባዶ እጅህን ነው አራት ኪሎ ቁጭ የምትለው። ስለዚህ ምጣኔ ሃብታዊ ውሳኔ ለመወሰን ምንም ዓይነት 'ኢንቨስትመንት' የለህም ማለት ነው። አሁን መንግሥት ማድረግ ያለበት፤ በተለይ እንደ ቴሌ ላሉት የተወሰነውን ሽጦ ሲያበቃ የመቆጣጠር አቅሙ ሲጎለብት ለሌሎች ክፍት ማድረግ ነው።» የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የነበሩት ፖለቲከኛው ዮናታን ተስፋዬ የመንግሥትን 'ፕራቬታይዜሽን' ዕቅድ ከሚደግፉት መካከል አንዱ ናቸው። «ፕራቬታይዝ የማድረጉ አንደኛ ጥቅም 'ሞኖፖሊ' እንዳይኖር ማድረጉ ነው። ሁለተኛ የፉክክር ገበያ ይኖራል፤ ይህ ደግሞ ሕብረተሰቡ የተሻለ ምርትና አገልግሎት እንዲያገኝ ያደርጋል።» ምጣኔ ሃብታዊውን ትንታኔ ለባለሙያዎች ልትወው፤ የሚሉት አቶ ዮናታን «የመንግሥት ድርጅቶች በመንግሥት ቁጥጥር ሥር መሆን አምባገነንነትን ያበረታታል» ባይ ናቸው። «'እኔ ነኝ አሳቢ፤ እኔ የተሻለ ለማሕበረሰቡ እጨነቃለሁ' የሚል ሥነ-ልቡናን እያሳደረ ነው የሚሄደው። ይህ አስተሳሰብ ደግሞ ሥር በሰደደ ቁጥር ሌሎች ተፎካካሪ ኃይሎችን እንደ ሥልጣን ተቀናቃኝ ነው የሚያየው፤ ምክንያቱም ራሱ ነጋዴው መንግሥት እየሆነ ስለሚመጣ። ስለዚህ ፖለቲካዊ ብልሽትን ይፈጥራል፤ ነፃ ገበያ እና ፉክክር የሌለበት፤ አንድ ወገን ብቻ እሴት የሚጨምርበት በጣም ደካማ የገበያ ሥርዓት እንዲኖር ነው የሚያደርገው።» • ኢትዮጵያ ኢንትርኔትን ስታቋርጥ በየቀኑ 4.5 ሚሊዮን ዶላር ታጣለች የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች 'ዘ ቢግ ፋይቭ' ይሏቸዋል፤ አየር መንገድ፣ ቴሌኮም፣ ባንክ፣ ባቡር እና ስኳር ፋብሪካዎች። መንግሥት እነዚህን ድርጅቶች ለግል ባለሃብቶች ሲሸጥ ሕዝብን ማማከር አለበት የሚሉ ሃሳቦች በአለፍ ገደም እያሉ ይደመጣሉ። አቶ ዮናታን «ይሄ እኮ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው. . .» ይላሉ። «ይሄ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው። የኢኮኖሚ ጉዳይ ደግሞ በባለሙያዎች ጥናት ተደርጎ፤ በዚያ ጥናት ላይ ተመርኩዞ፤ ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ይሄ ያዋጣል ብለን የምንወስነው ነገር ነው እንጂ ልክ እንደባንዲራ ጉዳይ ወይም የክልል እንሁን ጥያቄ ሕዝበ-ውሳኔ የሚደረግበት አይደለም። በየትኛውም ዓለም ላይ ሕዝብ በእንደዚህ ዓይነት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ቀጥተኛ የሆነ ውሳኔ ማሳለፍ አይችልም።» መሰል የፖሊሲ ለውጦች የሕዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ ባይኖራቸው እንኳ ምርጫ እስኪመጣ መጠበቅ አይቻልም ወይ? በርካቶች የሚያነሱት ጥያቄ ነው። እርግጥ ነው አቶ ዮናታን በዚህ ጉዳይ ይስማማል። ግን እሱ አልሆነም፤ አሁን ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ለሃገሪቱ ይጠቅማል የሚለውን ፖሊሲ የማፅደቅ መብት አለው ይላል። «አሁን ባለንበት ወቅት ኢኮኖሚው እየወደቀ ነው። ለዚህ ደግሞ አንድ ትልቅ ድርሻ የሚወስዱት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ናቸው። እነዚህ የልማት ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ ስላልሆኑ አሁን ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ምንም ሊቋቋመው የሚችለው አይደለም። የውጭ ባለሃብቶችን መሳብ የሚቻለው ደግሞ የኢኮኖሚ ፖሊሲውን መቀየር ሲቻል ነው።» ነዋሪነቱን እንግሊዝ ያደረገው የምጣኔ ሃብት ምሁሩ እዮብ ባልቻ፤ አዲሱ የፕራቬታይዜሽን አጀንዳ በግለሰቦች የሚመራ ነው ሲል ይሞግታል። እንደ እዮብ ትንተና አሁን ጠቅላይ ሚኒስትሩን በምጣኔ ሃብት ጉዳይ የሚያማክሩ ግለሰቦች ከዓለም ባንክና እና ዓለም አቀፉ ገንዘብ ድርጅት ጋር በቀጥታም ሆነ ተዘዋዋሪ ቁርኝት ያላቸው ናቸው። ምንም እንኳ የእዮብ ትንታኔ ግለሰቦቹ ላሳኩት ግብ ምስጋና ቢሰጥም በፕራቬታይዜሽን ጉዳይ ላይ ያላቸው አቋም አያስተማምንም ይላል። ፕሮፌሰር አለማየሁም ቢሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሥር ጫና እንዳሉና ያንን ጫና ለመቋቋም የሚያስችል የምጣኔ ሃብት አቅም የላቸውም ባይ ናቸው። ለፕሮፌሰሩ የመንግሥት ድርጅቶችን ለገበያ የማቅረብ ጊዜው አሁን አይደለም። ትርፉ ከመንግሥት ሞኖፖሊ ወደ ግለሰብ ሞኖፖሊ መሸጋገር ነው ይላሉ። • ወሳኝ ምጣኔ ሃብታዊ እርምጃዎች በ100 ቀናት «ለምሳሌ ቴሌን በ5 ወይም 10 ቢሊዮን ዶላር ሸጥነው እንበል። ነገ ያ ድርጅት የሚያተርፈውን አትርፎ የቀረውን ይዞ ሹልክ ይላል። በኢትዮጵያ ሕግ ደግሞ ያተረፍከውን ገንዘብ 'እክስፓትረየት' [ይዘህ መውጣት] ማድረግ ትችላለህ፤ የፈለግከውን። መሰል ስትራቴጂክ ነገሮችን ስታስብ መንግሥት ለፕራቬታይዜሽን መጣደፍ የለበትም። መንግሥትም ስለጨነቀውና ዶላር ስላጠረው እንጂ ፈልጎት አይመስለኝም» ይላሉ። ለአቶ ዮናታን ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው። መከራከሪያው ደግሞ ኢኮኖሚያችን እየደቀቀ ነው የሚል። ፕሮፌሰር አለማየሁ ደግሞ ጉዳዩን በሁለት ከፍለው ያዩታል። «አንደኛው ፖለቲካዊ ነው፤ ማለት አንድ መንግሥት ይህንን ፖሊሲ አስተዋውቆ የሕዝቡን ይሁንታ ካገኘ ሊያስፈፅመው ይችላል። ምክንያቱም እነዚህ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ የሚቆጣጠሩ ተቋማት ናቸው» ይላሉ። • የስኳር ፋብሪካዎችን ለግል ባለሃብቶች የመስጠት ፋይዳና ፈተናዎቹ ስለዚህ ትክክለኛው ጊዜ መንግሥት የሕዝቡን ፖለቲካዊ ውክልና ባገኘበት ጊዜ መሆን እንዳለበት የሚጠቅሱት ፕሮፌሰር አለማየሁ «በኢኮኖሚ መነፅር ስናየው ግን አሁን ባለው ሁኔታ በእኔ ግምት ትክክል አይደለም። ምክንያቱም መንግሥትም አልተረጋጋም፤ ሃገሩም አልተረጋጋም። ግን ደግሞ መንግሥት ብር የለውም። ከጀርባቸው ጠንካራ ኃይሎች ካልሸጣችሁ እይሏቸው ይሆናል። ስለዚህ ያለው አማራጭ ቅድም ያነሳሁት ሃሳብ ነው። የተወሰነውን ፕራይቬታይዝ ማድረግ።» | https://www.bbc.com/amharic/news-48619211 |
0business
| አሜሪካ በጦር መሳሪያ ንግድ ቀዳሚነቷን ስታስጠብቅ ሽያጯም ከፍ ብሏል | ባለፉት አምስት ዓመታት አሜሪካ ለሌሎች አገራት የምታቀርበው የጦር መሳሪያ መጠን በ37 በመቶ መጨመሩን አንድ በስዊዲን የሚገኝ የምርምር ተቋም አስታወቀ። ከአሜሪካ በተጨማሪ ፈረንሳይና ጀርመን ለሌሎች አገራት በሽያጭ የሚያቀርቡት የጦር መሳሪያ መጠን መጨመር በሩሲያና በቻይና አቅርቦት ምክንያት የተፈጠረውን ክፈተት የሚሞላ ነው ተብሏል። በአሁኑ ጊዜ የአገራት የጦር መሳሪያ ግዢና ሽያጭ መጠን ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ ከፍተኛ ከሚባለው ደረጃ ላይ የሚገኝ ቢሆንም፤ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሰበብ ለውጥ ሊኖር ይችላል ተብሎ ይገመታል። በዓለም ላይ ከታየው የጦር መሳሪያ ግዢ ውስጥ ከፍተኛው የተመዘገበው በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ነው ተብሏል። የጦር መሳሪያዎች ግዢና ሽያጭን በተመለከተ ምርምሩን የሰራው የስቶክሆልም የሠላም ጥናት ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ፒተር ዊዝማን "ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የታየው ፈጣን የጦር መሳሪያ ግብይት አብቅቷል ለማለት ጊዜው ገና ነው" ብለዋል። ባለሙያው ጨምረውም የኮሮናቫይረስ የሚያስከትለው የምጣኔ ሀብት ተጽዕኖ አገራት በቀጣይ ዓመታት ውስጥ የሚገዙትን የጦር መሳሪያ መጠን መለስ ብለው እንዲቃኙ ሳያደርጋቸው አይቀርም። "ወረርሽኙ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ባለፈው ዓመት እንኳን፣ በርካታ አገራት ወሳኝ የሚባሉ ጦር መሳሪያዎችን ለመግዛት ከፍተኛ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።" የጥናት ተቋሙ እንዳመለከተው ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ቀደም ሲል ከነበረው ዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ጋር ሲነጻጸር በነበረበት የመርጋት ሁኔታ አሳይቶ ነበር። አሜሪካ ወደ ውጭ ከምትልከው የጦር መሳሪያ ወደ ግማሽ የሚጠጋው፣ ማለትም 47 በመቶው፣ ለመካከለኛው ምሥራቅ አገራት የቀረበ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥም ሳዑዲ አረቢያ ብቻዋን ከአጠቃላዩ የአሜሪካ የመሳሪያ ሽያጭ 24 በመቶውን ትወስዳለች። ባለፉት አምስት ዓመታት የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ድርሻ በጨመረበት ጊዜ 96 አገራት ደንበኞቿ ሆነዋል። ከአሜሪካ በመከተል የፈረንሳይ የጦር መሳሪያ ሽያጭ በ44 በመቶ ሲጨምር የጀርመን ደግሞ በ21 በመቶ ከፍ ብሏል። ከእነዚህ በተጨማሪም እስራኤልና ደቡብ ኮሪያ ምንም እንኳን ከዋነኞቹ ጋር ሲነጻጸር የሚያቀርቡት የጦር መሳሪያ መጠን ዝቅተኛ ቢሆንም በዚህ ወቅት ሽያጫቸው በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል። ግጭትና ውጥረት በማይለየው መካከለኛው ምሥራቅ የጦር መሳሪያ ግዢ ፍላጎት በፍጥነት እያደገ ይገኛል። በዚህም ባለፉት አምስት ዓመታት ወደዚህ አካባቢ የተሸጠው የጦር መሳሪያ መጠን ቀደም ሲል ከነበሩት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር በ25 በመቶ ከፍ ብሏል። ከፍተኛው የጦር መሳሪያ ግዢ የተከናወነውም በሳዑዲ አረቢያ ሲሆን በዚህም ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ከተላከው 61 በመቶውን ገዝታለች። በተከታይነት ግብጽና ኳታር ይጠቀሳሉ። የእስያና የኢዢያ አገራት ቀደም ሲል 42 በመቶ የሚሆነውን ከፍተኛ መጠን ያለውን ዋነኛ የጦር መሳሪያዎችን በመሸመት ቀዳሚ ነበሩ። በአካባቢው ሕንድ፣ አውስትራሊያ፣ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያና ፓኪስታን ዋነኞቹ የጦር መሳሪያ ሸማች አገራት ነበሩ። ምንም እንኳን አሁንም ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገራት ዋነኛ የጦር መሳሪያ አቅራቢዎች ቢሆኑም፤ ቀደም ሲል ከዋነኞቹ የጦር መሳሪያ ላኪዎች መካከል የነበሩት ሩሲያና ቻይና ሽያጫቸው ቀንሷል። በዚህም ሳቢያ ሩሲያ ወደ ውጭ አገራት የምትልከው መሳሪያ በ22 በመቶ የቀነሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ወደ ሕንድ የምትልከው 53 በመቶ የሚሆነው ነበር። የዓለም ትልቋ አምስተኛ የጦር መሳሪያ አቅራቢ የሆነችው ቻይና ሽያጯ በ7.8 በመቶ ቀንሷል። ፓኪስታን፣ ባንግላዲሽና አልጄሪያ ዋነኞቹ የቻይና ጦር መሳሪያ ገዢዎች ነበሩ። | አሜሪካ በጦር መሳሪያ ንግድ ቀዳሚነቷን ስታስጠብቅ ሽያጯም ከፍ ብሏል ባለፉት አምስት ዓመታት አሜሪካ ለሌሎች አገራት የምታቀርበው የጦር መሳሪያ መጠን በ37 በመቶ መጨመሩን አንድ በስዊዲን የሚገኝ የምርምር ተቋም አስታወቀ። ከአሜሪካ በተጨማሪ ፈረንሳይና ጀርመን ለሌሎች አገራት በሽያጭ የሚያቀርቡት የጦር መሳሪያ መጠን መጨመር በሩሲያና በቻይና አቅርቦት ምክንያት የተፈጠረውን ክፈተት የሚሞላ ነው ተብሏል። በአሁኑ ጊዜ የአገራት የጦር መሳሪያ ግዢና ሽያጭ መጠን ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ ከፍተኛ ከሚባለው ደረጃ ላይ የሚገኝ ቢሆንም፤ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሰበብ ለውጥ ሊኖር ይችላል ተብሎ ይገመታል። በዓለም ላይ ከታየው የጦር መሳሪያ ግዢ ውስጥ ከፍተኛው የተመዘገበው በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ነው ተብሏል። የጦር መሳሪያዎች ግዢና ሽያጭን በተመለከተ ምርምሩን የሰራው የስቶክሆልም የሠላም ጥናት ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ፒተር ዊዝማን "ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የታየው ፈጣን የጦር መሳሪያ ግብይት አብቅቷል ለማለት ጊዜው ገና ነው" ብለዋል። ባለሙያው ጨምረውም የኮሮናቫይረስ የሚያስከትለው የምጣኔ ሀብት ተጽዕኖ አገራት በቀጣይ ዓመታት ውስጥ የሚገዙትን የጦር መሳሪያ መጠን መለስ ብለው እንዲቃኙ ሳያደርጋቸው አይቀርም። "ወረርሽኙ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ባለፈው ዓመት እንኳን፣ በርካታ አገራት ወሳኝ የሚባሉ ጦር መሳሪያዎችን ለመግዛት ከፍተኛ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።" የጥናት ተቋሙ እንዳመለከተው ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ቀደም ሲል ከነበረው ዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ጋር ሲነጻጸር በነበረበት የመርጋት ሁኔታ አሳይቶ ነበር። አሜሪካ ወደ ውጭ ከምትልከው የጦር መሳሪያ ወደ ግማሽ የሚጠጋው፣ ማለትም 47 በመቶው፣ ለመካከለኛው ምሥራቅ አገራት የቀረበ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥም ሳዑዲ አረቢያ ብቻዋን ከአጠቃላዩ የአሜሪካ የመሳሪያ ሽያጭ 24 በመቶውን ትወስዳለች። ባለፉት አምስት ዓመታት የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ድርሻ በጨመረበት ጊዜ 96 አገራት ደንበኞቿ ሆነዋል። ከአሜሪካ በመከተል የፈረንሳይ የጦር መሳሪያ ሽያጭ በ44 በመቶ ሲጨምር የጀርመን ደግሞ በ21 በመቶ ከፍ ብሏል። ከእነዚህ በተጨማሪም እስራኤልና ደቡብ ኮሪያ ምንም እንኳን ከዋነኞቹ ጋር ሲነጻጸር የሚያቀርቡት የጦር መሳሪያ መጠን ዝቅተኛ ቢሆንም በዚህ ወቅት ሽያጫቸው በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል። ግጭትና ውጥረት በማይለየው መካከለኛው ምሥራቅ የጦር መሳሪያ ግዢ ፍላጎት በፍጥነት እያደገ ይገኛል። በዚህም ባለፉት አምስት ዓመታት ወደዚህ አካባቢ የተሸጠው የጦር መሳሪያ መጠን ቀደም ሲል ከነበሩት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር በ25 በመቶ ከፍ ብሏል። ከፍተኛው የጦር መሳሪያ ግዢ የተከናወነውም በሳዑዲ አረቢያ ሲሆን በዚህም ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ከተላከው 61 በመቶውን ገዝታለች። በተከታይነት ግብጽና ኳታር ይጠቀሳሉ። የእስያና የኢዢያ አገራት ቀደም ሲል 42 በመቶ የሚሆነውን ከፍተኛ መጠን ያለውን ዋነኛ የጦር መሳሪያዎችን በመሸመት ቀዳሚ ነበሩ። በአካባቢው ሕንድ፣ አውስትራሊያ፣ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያና ፓኪስታን ዋነኞቹ የጦር መሳሪያ ሸማች አገራት ነበሩ። ምንም እንኳን አሁንም ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገራት ዋነኛ የጦር መሳሪያ አቅራቢዎች ቢሆኑም፤ ቀደም ሲል ከዋነኞቹ የጦር መሳሪያ ላኪዎች መካከል የነበሩት ሩሲያና ቻይና ሽያጫቸው ቀንሷል። በዚህም ሳቢያ ሩሲያ ወደ ውጭ አገራት የምትልከው መሳሪያ በ22 በመቶ የቀነሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ወደ ሕንድ የምትልከው 53 በመቶ የሚሆነው ነበር። የዓለም ትልቋ አምስተኛ የጦር መሳሪያ አቅራቢ የሆነችው ቻይና ሽያጯ በ7.8 በመቶ ቀንሷል። ፓኪስታን፣ ባንግላዲሽና አልጄሪያ ዋነኞቹ የቻይና ጦር መሳሪያ ገዢዎች ነበሩ። | https://www.bbc.com/amharic/news-56398435 |
5sports
| የእንግሊዝ እግር ኳስ ክለቦች ማሕበራዊ ሚድያን ጥለው ሊወጡ ነው | የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ፣ እንግሊሽ ፉትቦል ሊግ እና የሴቶች ሱፐር ሊግ ክለቦች ለአራት ቀናት ከማሕበራዊ ድር አምባዎች ራሳቸውን ሊያገሉ ነው። ክለቦች ከዚህ ውሳኔ የደረሱት ማሕበራዊ ድር አምባዎች ላይ የሚታዩ ብዘበዛዎችና ማግለሎችን በመቃወም ነው። አድማው የሚጀምረው ከአምስት ቀናት በኋላ ሚያዚያ 22 ነው። የእግር ኳስ ማሕበር፣ እንዲሁም ሌሎች ይመለከተናል የሚሉ መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ ኪክ ኢት ኦፍ የተባለው ፀረ-ማግለል ድርጅት በዚህ አድማ ላይ ይሳተፋሉ። የኪክ ኢት ኦፍ ሊቀመንበር ሳንጃይ ባንዳሪ "ይህ አድማ ምን ያክል እንደመረረን የሚያሳይ ነው" ይላሉ። "ማሕበራዊ ድር አምባ አሁን አሁን በጣም መርዛማ ለሆኑ ብዝበዛዎች የተጋለጠ ሆኗል ።" እኛ አንድ ላይ ሆነን ይህን አድማ የምንመታው ሥልጣኑ ላላቸው መልዕክት ለማስተላለፍ ነው። እርምጃ እንድትወስዱ እንፈልጋለን። ለውጥ እንድታመጡ እንሻለን።" ሊቀ መንበሩ ማሕበራዊ ድር አምባዎች ፊታቸውን ደብቀው ለሚበዘብዙ ሳይሆን ለእግር ኳሱ ቤተሰቡ ነው የተመቸ ሊሆን የሚገባው ሲሉ ይሞግታሉ። ባለፈው ዓመት የቆዳ ቀለሙን አስመልክቶ ብዝበዛ የደረሰበት የሼፊልድ ዩናይትዱ ዴቪድ ማክጎልድሪክ "ጊዜው አሁን ነው" ይላል። "በእኔ ላይ የደረሰው በሌሎች በርካታ ተጫዋቾች ላይ ደርሷል። የሆነ ነገር ሊፈጠር ይገባዋል። የቆዳ ቀለምን መሠረት አድርጎ ጥቃት ማድረስ ለብዙዎች ቀላል ነው።" ጎልድሪክ ትላንት [ቅዳሜ] ምሽት ከብራይተን ጋር በነበረው ጨዋታ አንድ ጎል አስቆጥሮ ቡድኑ እንዲያሸንፍ አስችሏል። ተጫዋቹ ከግጥሚያው በኋላ በሰጠው አስተያየት "ሱፐር ሊግን በ48 ሰዓታት አስወገድን። ዘረኝነት መርታት ያቃተን ለምንድነው?" ሲል ጠይቋል። የብራይተኑ ፈረንሳዊ አጥቂ ኒል ሞፔም በተመሳሳይ ማሕበራዊ ድር አምባው ላይ ጥቃት ደርሶበታል። ተጫዋቹ ለስካይ ስፖርት በሰጠው ድምፅ "አድማው ትክክለኛ ነው" ሲል ተደምጧል። "ተጫዋቾች በይነ መረብ ላይ ብዙ ጥቃት ይደርስባቸዋል። ይህን መዋጋት አለብን። አሁን አንድ ላይ መሆናችን መልካም ነገር ነው።" ክለቦችን ጨምሮ አስተዳዳሪ አካላት እንዲሁም የእግር ኳስ ዳኞች ማሕበር ከትዊተር፣ ፌስቡክና ኢንስታግራም ራሳቸውን ለአምስት ቀናት ለማግለል ተስማምተዋል። ከሳምንታት በፊት ስዋንሲ ሲቲ የተሰኘው ቡድን ተጫዋቾቹ ላይ በደረሰው ጥቃት ምክንያት የአንድ ሳምንት አድማ አድርጎ ነበር። ሌላኛው የቻምፒዮንሺፕ ቡድን በርሚንግሃም ሲቲና የስኮትላንዱ ሬንጀርስም ማሕበራ ድር አምባው ላይ አድማ መትተው ነበር። የቀድሞው የአርሰናል ተጫዋች ፈረንሳዊው ቲዬሪ ሄንሪ በዘረኝነትና በሌሎች ጥቃቶች ሳቢያ ከማሕበራዊ ድር አምባዎች ራሱን ሙለ በሙሉ ማግለሉን ማስታወቁ አይዘነጋም። ከቢቢሲ ጋር ቆይታ የነበረው የ43 ዓመቱ ሄንሪ "በቃ ማለት በቃ ነው" ሲል ተቃውሞውን ገልጿል። ሊቨርፑል ሶስቱ ጥቁር ተጫዋቾቹ አሌክሳንደር-አርኖልድ፣ ናቢ ኬታና ሳዲዮ ማኔ ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ ቁጣውን መግለፁ ይታወሳል። አድማ መቺዎች ዓላማቸው ማሕበራዊ ድር-አምባዎች ጥላቻን እንዲያስወግዱና ትምህርትም እንዲሰጡ መሆኑን በመግለጫቸው አትተዋል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ትላልቅ የማሕበራዊ ድር አምባ ኩባንያዎች ችግሩን መቅረፍ ካልቻሉ ቅጣት እንደሚጥል ዝቶ ነበር። ፌስቡክ የካቲት ላይ ከበድ ያሉ እርምጃዎችን ለመውሰድ እንዳሰበ አስታውቆ ነበር። በፌስቡክ የሚተዳደረው ኢንስታግራም ደግሞ ባለፈው ሳምንት ተጠቃሚዎች ጓደኞቻቸው ያልሆኑ ሰዎች መልዕክት እንዳይልኩላቸው የሚያስችል መንገድ አምጥቻለሁ ብሏል። | የእንግሊዝ እግር ኳስ ክለቦች ማሕበራዊ ሚድያን ጥለው ሊወጡ ነው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ፣ እንግሊሽ ፉትቦል ሊግ እና የሴቶች ሱፐር ሊግ ክለቦች ለአራት ቀናት ከማሕበራዊ ድር አምባዎች ራሳቸውን ሊያገሉ ነው። ክለቦች ከዚህ ውሳኔ የደረሱት ማሕበራዊ ድር አምባዎች ላይ የሚታዩ ብዘበዛዎችና ማግለሎችን በመቃወም ነው። አድማው የሚጀምረው ከአምስት ቀናት በኋላ ሚያዚያ 22 ነው። የእግር ኳስ ማሕበር፣ እንዲሁም ሌሎች ይመለከተናል የሚሉ መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ ኪክ ኢት ኦፍ የተባለው ፀረ-ማግለል ድርጅት በዚህ አድማ ላይ ይሳተፋሉ። የኪክ ኢት ኦፍ ሊቀመንበር ሳንጃይ ባንዳሪ "ይህ አድማ ምን ያክል እንደመረረን የሚያሳይ ነው" ይላሉ። "ማሕበራዊ ድር አምባ አሁን አሁን በጣም መርዛማ ለሆኑ ብዝበዛዎች የተጋለጠ ሆኗል ።" እኛ አንድ ላይ ሆነን ይህን አድማ የምንመታው ሥልጣኑ ላላቸው መልዕክት ለማስተላለፍ ነው። እርምጃ እንድትወስዱ እንፈልጋለን። ለውጥ እንድታመጡ እንሻለን።" ሊቀ መንበሩ ማሕበራዊ ድር አምባዎች ፊታቸውን ደብቀው ለሚበዘብዙ ሳይሆን ለእግር ኳሱ ቤተሰቡ ነው የተመቸ ሊሆን የሚገባው ሲሉ ይሞግታሉ። ባለፈው ዓመት የቆዳ ቀለሙን አስመልክቶ ብዝበዛ የደረሰበት የሼፊልድ ዩናይትዱ ዴቪድ ማክጎልድሪክ "ጊዜው አሁን ነው" ይላል። "በእኔ ላይ የደረሰው በሌሎች በርካታ ተጫዋቾች ላይ ደርሷል። የሆነ ነገር ሊፈጠር ይገባዋል። የቆዳ ቀለምን መሠረት አድርጎ ጥቃት ማድረስ ለብዙዎች ቀላል ነው።" ጎልድሪክ ትላንት [ቅዳሜ] ምሽት ከብራይተን ጋር በነበረው ጨዋታ አንድ ጎል አስቆጥሮ ቡድኑ እንዲያሸንፍ አስችሏል። ተጫዋቹ ከግጥሚያው በኋላ በሰጠው አስተያየት "ሱፐር ሊግን በ48 ሰዓታት አስወገድን። ዘረኝነት መርታት ያቃተን ለምንድነው?" ሲል ጠይቋል። የብራይተኑ ፈረንሳዊ አጥቂ ኒል ሞፔም በተመሳሳይ ማሕበራዊ ድር አምባው ላይ ጥቃት ደርሶበታል። ተጫዋቹ ለስካይ ስፖርት በሰጠው ድምፅ "አድማው ትክክለኛ ነው" ሲል ተደምጧል። "ተጫዋቾች በይነ መረብ ላይ ብዙ ጥቃት ይደርስባቸዋል። ይህን መዋጋት አለብን። አሁን አንድ ላይ መሆናችን መልካም ነገር ነው።" ክለቦችን ጨምሮ አስተዳዳሪ አካላት እንዲሁም የእግር ኳስ ዳኞች ማሕበር ከትዊተር፣ ፌስቡክና ኢንስታግራም ራሳቸውን ለአምስት ቀናት ለማግለል ተስማምተዋል። ከሳምንታት በፊት ስዋንሲ ሲቲ የተሰኘው ቡድን ተጫዋቾቹ ላይ በደረሰው ጥቃት ምክንያት የአንድ ሳምንት አድማ አድርጎ ነበር። ሌላኛው የቻምፒዮንሺፕ ቡድን በርሚንግሃም ሲቲና የስኮትላንዱ ሬንጀርስም ማሕበራ ድር አምባው ላይ አድማ መትተው ነበር። የቀድሞው የአርሰናል ተጫዋች ፈረንሳዊው ቲዬሪ ሄንሪ በዘረኝነትና በሌሎች ጥቃቶች ሳቢያ ከማሕበራዊ ድር አምባዎች ራሱን ሙለ በሙሉ ማግለሉን ማስታወቁ አይዘነጋም። ከቢቢሲ ጋር ቆይታ የነበረው የ43 ዓመቱ ሄንሪ "በቃ ማለት በቃ ነው" ሲል ተቃውሞውን ገልጿል። ሊቨርፑል ሶስቱ ጥቁር ተጫዋቾቹ አሌክሳንደር-አርኖልድ፣ ናቢ ኬታና ሳዲዮ ማኔ ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ ቁጣውን መግለፁ ይታወሳል። አድማ መቺዎች ዓላማቸው ማሕበራዊ ድር-አምባዎች ጥላቻን እንዲያስወግዱና ትምህርትም እንዲሰጡ መሆኑን በመግለጫቸው አትተዋል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ትላልቅ የማሕበራዊ ድር አምባ ኩባንያዎች ችግሩን መቅረፍ ካልቻሉ ቅጣት እንደሚጥል ዝቶ ነበር። ፌስቡክ የካቲት ላይ ከበድ ያሉ እርምጃዎችን ለመውሰድ እንዳሰበ አስታውቆ ነበር። በፌስቡክ የሚተዳደረው ኢንስታግራም ደግሞ ባለፈው ሳምንት ተጠቃሚዎች ጓደኞቻቸው ያልሆኑ ሰዎች መልዕክት እንዳይልኩላቸው የሚያስችል መንገድ አምጥቻለሁ ብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56877326 |
0business
| በስህተት የጣለውን ቢትኮይን በ13 ሚሊዮን ዶላር እያፈላለገ ያለው ግለሰብ | ከ10 ዓመታት በፊት ነው። ጄምስ ሃዌልስ ያስቀመጠውን ቢትኮይን ረስቶ የኮምፒውተሩን የመረጃ ቋት (ሃርድ ድራይቭ) አውጥቶ ጣለው። ጄምስ ተዝናግቶ የወረወረው ቢትኮይን ዘንድሮ ባለው ገበያ 184 ሚሊዮን ዶላር ሊያወጣ ይችላል። ይህ የከነከነው ጄምስ ከዓመታት በፊት የጣለውን ቢትኮይን ሚሊዮን ዶላር ከፍሎ ሊያስቆፍረው አስቧል። የሰውዬው ‘ሃርድ ድራይቭ’ ኒውፖርት በተሰኘችው የዩናይትድ ኪንግደም ከተማ ቆሻሻ መጣያ ሥፍራ ይኖራል ተብሎ ተገምቷል። ጄምስ ይህ ውድ ቁስ ከተገኘለት ከቢትኮይኑ 10 በመቶውን ቆንጥሮ ከተማዋን የክሪፕቶከረንሲ ማዕከል ለማድረግ ቃል ገብቷል። ነገር ግን የከተማዋ ምክር ቤት የቆሻሻ መጣያውን መቆፈር ሥነ-ምኅዳራዊ (ኢኮሎጂካል) ቀውስ ያስከትላል እያለ ነው። የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (አይቲ) ባለሙያው ጄምስ ከዘጠኝ ዓመት በፊት በፈረንጆቹ 2013 ነበር፤ 8 ሺህ ቢትኮይን ያቀፈውን ሃርድ ድራይቭ ጠርጎ የጣለው። ወቅቱም ቢትኮይን የተሰኘው ዲጂታል የመገበያያ ገንዘብ ብቅ ብቅ ማለት የጀመረበት ነበር። ቢትኮይን ገበያው ላይ የሚታወቀው በሚዋዥው ዋጋው ነው። ለምሳሌ የጄምስ ቢትኮይን ዋጋ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት [2021] 256 ሚሊዮን ዶላር ደርሶለት ነበር። ነገር ግን ከዘንድሮው ዓመት መባቻ ጀምሮ ዋጋው አሽቆልቁሏል። ጄምስ በተደጋጋሚ ለኒውፖርት ከተማ ምክር ቤት ቆሻሻ ማከማቻው ይቆፈርልኝ ብሎ ቢያመልክትም ጥያቄው ሰሚ አጥቷል። ይህ ያታከተው ግለሰብ አሁን ሃርድ ድራይቩ ከተገኘ 10 በመቶ ገቢውን ለከተማዋ የክሪፕቶከረንሲ ማስፋፊያ ለመስጠት ወስኗል። ነገር ግን የጄምስን መዳፍ የምታክል ቁስ ለማግኘት ሲል ከተማ አስተዳደሩ በርካታ ወጪ አውጥቶ ለዓመታት የተከማቸውን ቆሻሻ ይቆፍር እንደሁ አልታወቀም። ከተማ አስተዳደሩ የቆሻሻ ማከማቻውን ማመስ አካባቢውን ሊበክለው ይችላል የሚል ስጋት አለው። ጄምስ ደግሞ “እኔ ማከማቻውን የማስቆፈር አቅም እንዲሁም አደጋ ሳያደርስ የሚያስስ ባለሙያ አለኝ” ይላል። “እርግጥ ነው ቆሻሻ ማከማቻ መቆፈር ራሱን የቻለ ትልቅ ሥራ ነው” ይላል ጄምስ። “ነገር ግን ማስቆፈሪያ ወጪውን እችላለሁ። የሰው-ሠራሽ ልኅቀት [አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ] ባለሙያ አስመጥተናል። ሃርድ ድራይቩን ነቅሎ የሚያወጣ ቴክኖሎጂ አለ።” ግለሰቡ ይህ ብቻ ሳይሆን ከበቢያዊ አደጋን የሚመረምር ቡድን ማዘጋጀቱን ይገልጣል። “በሁሉም ዘርፍ የተካኑ ልምድ ያላቸው ሙያተኞች ይዣለሁ። ከተፈቀደላቸው ይህንን ሥራ በብቃት መከውን የሚችሉ ናቸው።” ነገር ግን ሃርድ ድራቩን ማግኘት ብቸኛው ሥራ አይደለም። ይህ የመረጃ ማከማቻ ቁስ ቢገኝ እንኳ ለመሥራቱ ማስተማመኛ የለም። ይህ በርካታ ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ቢትኮይን ያቀፈው ቁስ ቢገኝ ጄምስ ሚሊየነር ይሆናል። ነገር ግን የቢትኮይንን የገበያ ዋጋ መገመት ከባድ ነው። ቢሆንም የ37 ዓመቱ ግለሰብ የበርካታ ሚሊዮን ዶላሮች ባለቤት ሊሆን ይችላል። ጄምስ ገንዘቡ ተቆፍሮ ይውጣለት እንጂ፣ ያደገባትን ከተማ የክሪፕቶከረንሲ ማዕከል ለማድረግ ቆርጦ ተነስቷል። “ሕብረተሰቡን የሚጠቅም ሥራ ለመሥራት የሚያስችል ዕቅድ አስቀምጫለሁ” ይላል። “አንደኛው ሥራ የቆሻሻ ማከማቻውን ማዘመን ነው። ከተቻለ በአካባቢው በነፋስ ኃይል የሚሠራ የኤሌክትሪክ ማመንጫ እንገነባለን።” የኒውፖርት ማኅበረሰብ የሚጠቀምበት የክሪፕቶከረንሲ ገበያ ለመዘርጋት ነው የጄምስ ዓላማ። ለእያንዳንዱ የኒውፖርት ነዋሪ 61 ዶላር ዋጋ ያለው ቢትኮይን ለመስጠትም ቃል ገብቷል። በተከማዋ ዋና ዋና ቦታዎች ደግሞ ክሪፕቶ ላይ የተመሠረቱ ፌርማታዎች ለመግንባትም አስቧል። የኒውፖርት ከተማ ምክር ቤት ግን በተደጋጋሚ የሰውዬውን ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል። የከተማዋ ቃል አቀባይ “ቆሻሻ ማከማቻን በተለመከተ የተቀመጠ ሕግ አለን። ይህን ሕግ መከተል አለብን” ብለዋል። “አንደኛው ጉዳይ ይህ የቆሻሻ ማከማቻ ከተቆፈረ በአካባቢው ማኅበረሰብ ላይ የሚያደርሰው ሥነ ምኅዳራዊ አደጋ ነው። የጄምስ ዕቅድ ደግሞ ይህን አደጋ የሚያስከትል ነው። ይህን ልንቀበለው አንችልም። በሕጉ መሠረት እንዲያውም ከግምት ውስጥ ልናስገባው የምንችለው ሐሳብ አይደለም።” | በስህተት የጣለውን ቢትኮይን በ13 ሚሊዮን ዶላር እያፈላለገ ያለው ግለሰብ ከ10 ዓመታት በፊት ነው። ጄምስ ሃዌልስ ያስቀመጠውን ቢትኮይን ረስቶ የኮምፒውተሩን የመረጃ ቋት (ሃርድ ድራይቭ) አውጥቶ ጣለው። ጄምስ ተዝናግቶ የወረወረው ቢትኮይን ዘንድሮ ባለው ገበያ 184 ሚሊዮን ዶላር ሊያወጣ ይችላል። ይህ የከነከነው ጄምስ ከዓመታት በፊት የጣለውን ቢትኮይን ሚሊዮን ዶላር ከፍሎ ሊያስቆፍረው አስቧል። የሰውዬው ‘ሃርድ ድራይቭ’ ኒውፖርት በተሰኘችው የዩናይትድ ኪንግደም ከተማ ቆሻሻ መጣያ ሥፍራ ይኖራል ተብሎ ተገምቷል። ጄምስ ይህ ውድ ቁስ ከተገኘለት ከቢትኮይኑ 10 በመቶውን ቆንጥሮ ከተማዋን የክሪፕቶከረንሲ ማዕከል ለማድረግ ቃል ገብቷል። ነገር ግን የከተማዋ ምክር ቤት የቆሻሻ መጣያውን መቆፈር ሥነ-ምኅዳራዊ (ኢኮሎጂካል) ቀውስ ያስከትላል እያለ ነው። የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (አይቲ) ባለሙያው ጄምስ ከዘጠኝ ዓመት በፊት በፈረንጆቹ 2013 ነበር፤ 8 ሺህ ቢትኮይን ያቀፈውን ሃርድ ድራይቭ ጠርጎ የጣለው። ወቅቱም ቢትኮይን የተሰኘው ዲጂታል የመገበያያ ገንዘብ ብቅ ብቅ ማለት የጀመረበት ነበር። ቢትኮይን ገበያው ላይ የሚታወቀው በሚዋዥው ዋጋው ነው። ለምሳሌ የጄምስ ቢትኮይን ዋጋ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት [2021] 256 ሚሊዮን ዶላር ደርሶለት ነበር። ነገር ግን ከዘንድሮው ዓመት መባቻ ጀምሮ ዋጋው አሽቆልቁሏል። ጄምስ በተደጋጋሚ ለኒውፖርት ከተማ ምክር ቤት ቆሻሻ ማከማቻው ይቆፈርልኝ ብሎ ቢያመልክትም ጥያቄው ሰሚ አጥቷል። ይህ ያታከተው ግለሰብ አሁን ሃርድ ድራይቩ ከተገኘ 10 በመቶ ገቢውን ለከተማዋ የክሪፕቶከረንሲ ማስፋፊያ ለመስጠት ወስኗል። ነገር ግን የጄምስን መዳፍ የምታክል ቁስ ለማግኘት ሲል ከተማ አስተዳደሩ በርካታ ወጪ አውጥቶ ለዓመታት የተከማቸውን ቆሻሻ ይቆፍር እንደሁ አልታወቀም። ከተማ አስተዳደሩ የቆሻሻ ማከማቻውን ማመስ አካባቢውን ሊበክለው ይችላል የሚል ስጋት አለው። ጄምስ ደግሞ “እኔ ማከማቻውን የማስቆፈር አቅም እንዲሁም አደጋ ሳያደርስ የሚያስስ ባለሙያ አለኝ” ይላል። “እርግጥ ነው ቆሻሻ ማከማቻ መቆፈር ራሱን የቻለ ትልቅ ሥራ ነው” ይላል ጄምስ። “ነገር ግን ማስቆፈሪያ ወጪውን እችላለሁ። የሰው-ሠራሽ ልኅቀት [አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ] ባለሙያ አስመጥተናል። ሃርድ ድራይቩን ነቅሎ የሚያወጣ ቴክኖሎጂ አለ።” ግለሰቡ ይህ ብቻ ሳይሆን ከበቢያዊ አደጋን የሚመረምር ቡድን ማዘጋጀቱን ይገልጣል። “በሁሉም ዘርፍ የተካኑ ልምድ ያላቸው ሙያተኞች ይዣለሁ። ከተፈቀደላቸው ይህንን ሥራ በብቃት መከውን የሚችሉ ናቸው።” ነገር ግን ሃርድ ድራቩን ማግኘት ብቸኛው ሥራ አይደለም። ይህ የመረጃ ማከማቻ ቁስ ቢገኝ እንኳ ለመሥራቱ ማስተማመኛ የለም። ይህ በርካታ ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ቢትኮይን ያቀፈው ቁስ ቢገኝ ጄምስ ሚሊየነር ይሆናል። ነገር ግን የቢትኮይንን የገበያ ዋጋ መገመት ከባድ ነው። ቢሆንም የ37 ዓመቱ ግለሰብ የበርካታ ሚሊዮን ዶላሮች ባለቤት ሊሆን ይችላል። ጄምስ ገንዘቡ ተቆፍሮ ይውጣለት እንጂ፣ ያደገባትን ከተማ የክሪፕቶከረንሲ ማዕከል ለማድረግ ቆርጦ ተነስቷል። “ሕብረተሰቡን የሚጠቅም ሥራ ለመሥራት የሚያስችል ዕቅድ አስቀምጫለሁ” ይላል። “አንደኛው ሥራ የቆሻሻ ማከማቻውን ማዘመን ነው። ከተቻለ በአካባቢው በነፋስ ኃይል የሚሠራ የኤሌክትሪክ ማመንጫ እንገነባለን።” የኒውፖርት ማኅበረሰብ የሚጠቀምበት የክሪፕቶከረንሲ ገበያ ለመዘርጋት ነው የጄምስ ዓላማ። ለእያንዳንዱ የኒውፖርት ነዋሪ 61 ዶላር ዋጋ ያለው ቢትኮይን ለመስጠትም ቃል ገብቷል። በተከማዋ ዋና ዋና ቦታዎች ደግሞ ክሪፕቶ ላይ የተመሠረቱ ፌርማታዎች ለመግንባትም አስቧል። የኒውፖርት ከተማ ምክር ቤት ግን በተደጋጋሚ የሰውዬውን ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል። የከተማዋ ቃል አቀባይ “ቆሻሻ ማከማቻን በተለመከተ የተቀመጠ ሕግ አለን። ይህን ሕግ መከተል አለብን” ብለዋል። “አንደኛው ጉዳይ ይህ የቆሻሻ ማከማቻ ከተቆፈረ በአካባቢው ማኅበረሰብ ላይ የሚያደርሰው ሥነ ምኅዳራዊ አደጋ ነው። የጄምስ ዕቅድ ደግሞ ይህን አደጋ የሚያስከትል ነው። ይህን ልንቀበለው አንችልም። በሕጉ መሠረት እንዲያውም ከግምት ውስጥ ልናስገባው የምንችለው ሐሳብ አይደለም።” | https://www.bbc.com/amharic/articles/c4n347241vro |
5sports
| ሳሙኤል ኤቶ እግር ኳስ ሊያቆም ነው | አራት ጊዜ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ መመረጥ የቻለው ካሜሩናዊው ሳሙኤል ኤቶ ከ22 ዓመታት የእግር ኳስ ህይወት በኋላ ጫማውን ሊሰቅል ስለመሆኑ ጠቁሟል። የ38 ዓመቱ የቀድሞው የካሜሩን ብሄራዊ ቡድንና የባርሴሎናው አጥቂ በኢንስታግራም ገጹ ላይ ባሰፈረው መልእክት ''ተፈጸመ፤ ወደ ሌላ የፈተና ጉዞ ተጀመረ'' ሲል ጽፏል። • “በአምስት የዓለም ዋንጫዎች ወርቅ እንዲመጣ ምክንያት ነኝ” አትሌት ገብረእግዚአብሔር • በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. ኤቶ ለሃገሩ ካሜሩን በ118 ጨዋታዎች 56 ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በኤልሲና በኤቨርተን ተጫውቷል። ባለፈው ዓመት ደግሞ ለቱርኩ ኮንያስፖር ለአጭር ጊዜ ከተጫወተ በኋላ የኳታሩን ስፖርት ክለብ ተቀላቅሏል። እ.አ.አ. ገና የ16 ዓመት ታዳጊ እያለ የስፔኑን ሪያል ማድሪድ በ1996 ቢቀላቀልም መጫወት የቻለው ሶስት ጨዋታዎችን ብቻ ነበር። ከዛም በውሰት ለሌጋኔዝ፣ ኤስፓኞል እና ማሎርካ ተጫውቷል። በ2000 ለማሎርካ በ133 ጨዋታዎች 54 ግቦችን በማስቆጠር የቡድኑ የምን ጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን ታሪክ ሰርቷል። በ2004 ደግሞ ባርሴሎናን ከተቀላቀለ በኋላ ሶስት ጊዜ የስፔን ላሊጋን ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በ2006 እና በ2009 ቡድኑ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ እንዲሆን አስችሏል። በሁለቱም የፍጻሜ ጨዋታዎችም ግብ አስቆጥሮ ነበር። በ2006 የውድድር ዘመን ለባርሴሎና በ34 ጨዋታዎች 26 ግቦችን ካስቆጠረ በኋላ በሊጉ የወርቅ ጫማ ማሸነፍ የቻለ ብቸኛው አፍሪካዊ ተጫዋች መሆን ችሏል። በአጠቃላይ በ144 ጨዋታዎች 108 ግቦችን ለባርሴሎና ያስቆጠረው ኤቶ በ2009 ወደ ኢንተር ሚላን በመሄድ ለሶስተኛ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማንሳት ችሏል። የጣሊያን ሴሪ አ እና የፊፋ ክለቦች የዓለም ዋንጫዎችን ከቡድኑ ጋር አንስቷል። በመቀጠል ኤቶ ያመራው ወደ ራሺያ ነበር። አንዚ ማካቻካላ ከሚባለው ቡድን ጋርም ለሁለት ዓመታት ከቆየ በኋላ በ2013 ቼልሲን ተቀላቀለ። ኤቨርተን፣ ሳምፕዶሪያ እና አንታሊያስፖር ደግሞ የተጫወተባቸው ሌሎች ቡድኖች ናቸው። ለካሜሩን ብሄራዊ ብድን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጫወት ሳሙኤል ኤቶ ገና የ17 ዓመት ታዳጊ ነበር። በ1998 በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ሃገሩ ከኮስታሪካ ስትጫወት በመሰለፍ የጀመረው ኤቶ በውድድሩ ትንሹ ተጫዋች ተብሎ ነበር። • "አንድ አትሌት በህይወቱ የሚያስደስተው የአለም ሪከርድን መስበር ነው" ዮሚፍ ቀጀልቻ ከብሄራዊ ቡድን እራሱን እስካገለለበት ጊዜ ድረስ ሃገሩን ወክሎ በአራት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ ተሳትፏል። በ2000 እና በ2002 የተካሄዱትን ተከታታይ የአፍሪካ ዋንጫዎችንም ከሃገሩ ጋር አንስቷል። በውድድሮቹም 18 ጎሎችን በማስቆጠር ኮኮብ ግብ አግቢ ሆኖ መጨረስ ችሎ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ በ2000 በተካሄደው ኦሎምፒክ ከቡድን አጋሮቹ ጋር በመሆን ለሃግሩ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል። | ሳሙኤል ኤቶ እግር ኳስ ሊያቆም ነው አራት ጊዜ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ መመረጥ የቻለው ካሜሩናዊው ሳሙኤል ኤቶ ከ22 ዓመታት የእግር ኳስ ህይወት በኋላ ጫማውን ሊሰቅል ስለመሆኑ ጠቁሟል። የ38 ዓመቱ የቀድሞው የካሜሩን ብሄራዊ ቡድንና የባርሴሎናው አጥቂ በኢንስታግራም ገጹ ላይ ባሰፈረው መልእክት ''ተፈጸመ፤ ወደ ሌላ የፈተና ጉዞ ተጀመረ'' ሲል ጽፏል። • “በአምስት የዓለም ዋንጫዎች ወርቅ እንዲመጣ ምክንያት ነኝ” አትሌት ገብረእግዚአብሔር • በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. ኤቶ ለሃገሩ ካሜሩን በ118 ጨዋታዎች 56 ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በኤልሲና በኤቨርተን ተጫውቷል። ባለፈው ዓመት ደግሞ ለቱርኩ ኮንያስፖር ለአጭር ጊዜ ከተጫወተ በኋላ የኳታሩን ስፖርት ክለብ ተቀላቅሏል። እ.አ.አ. ገና የ16 ዓመት ታዳጊ እያለ የስፔኑን ሪያል ማድሪድ በ1996 ቢቀላቀልም መጫወት የቻለው ሶስት ጨዋታዎችን ብቻ ነበር። ከዛም በውሰት ለሌጋኔዝ፣ ኤስፓኞል እና ማሎርካ ተጫውቷል። በ2000 ለማሎርካ በ133 ጨዋታዎች 54 ግቦችን በማስቆጠር የቡድኑ የምን ጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን ታሪክ ሰርቷል። በ2004 ደግሞ ባርሴሎናን ከተቀላቀለ በኋላ ሶስት ጊዜ የስፔን ላሊጋን ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በ2006 እና በ2009 ቡድኑ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ እንዲሆን አስችሏል። በሁለቱም የፍጻሜ ጨዋታዎችም ግብ አስቆጥሮ ነበር። በ2006 የውድድር ዘመን ለባርሴሎና በ34 ጨዋታዎች 26 ግቦችን ካስቆጠረ በኋላ በሊጉ የወርቅ ጫማ ማሸነፍ የቻለ ብቸኛው አፍሪካዊ ተጫዋች መሆን ችሏል። በአጠቃላይ በ144 ጨዋታዎች 108 ግቦችን ለባርሴሎና ያስቆጠረው ኤቶ በ2009 ወደ ኢንተር ሚላን በመሄድ ለሶስተኛ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማንሳት ችሏል። የጣሊያን ሴሪ አ እና የፊፋ ክለቦች የዓለም ዋንጫዎችን ከቡድኑ ጋር አንስቷል። በመቀጠል ኤቶ ያመራው ወደ ራሺያ ነበር። አንዚ ማካቻካላ ከሚባለው ቡድን ጋርም ለሁለት ዓመታት ከቆየ በኋላ በ2013 ቼልሲን ተቀላቀለ። ኤቨርተን፣ ሳምፕዶሪያ እና አንታሊያስፖር ደግሞ የተጫወተባቸው ሌሎች ቡድኖች ናቸው። ለካሜሩን ብሄራዊ ብድን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጫወት ሳሙኤል ኤቶ ገና የ17 ዓመት ታዳጊ ነበር። በ1998 በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ሃገሩ ከኮስታሪካ ስትጫወት በመሰለፍ የጀመረው ኤቶ በውድድሩ ትንሹ ተጫዋች ተብሎ ነበር። • "አንድ አትሌት በህይወቱ የሚያስደስተው የአለም ሪከርድን መስበር ነው" ዮሚፍ ቀጀልቻ ከብሄራዊ ቡድን እራሱን እስካገለለበት ጊዜ ድረስ ሃገሩን ወክሎ በአራት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ ተሳትፏል። በ2000 እና በ2002 የተካሄዱትን ተከታታይ የአፍሪካ ዋንጫዎችንም ከሃገሩ ጋር አንስቷል። በውድድሮቹም 18 ጎሎችን በማስቆጠር ኮኮብ ግብ አግቢ ሆኖ መጨረስ ችሎ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ በ2000 በተካሄደው ኦሎምፒክ ከቡድን አጋሮቹ ጋር በመሆን ለሃግሩ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-49625124 |
5sports
| ወልቂጤ ከነማ 'የጨዋታ መጭበርበር ነበር' በሚል ቅሬታ አቀረበ | እየተገባደደ በሚገኘው በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ በድሬዳዋ ከነማ እና ፋሲል ከነማ መካከል የተደረገው ጨዋታ ተጭበርብሯል ሲል ወልቂጤ ከነማ ቅሬታውን ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን አቀረበ። ከትላንት በስቲያ ግንቦት 9፣ 2013 ዓ.ም በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም 9 ሰዓት ላይ በነበረው ጨዋታ የዘንድሮው የዋንጫ ባለድል ፋሲል ከነማ በድሬ ዳዋ ከነማ 3 ለ 1 ተረትቷል። ከዚህ ጨዋታ በኋላ ወራጅ ቀጠና የሚገኘው ወልቂጤ ከነማ ጨዋታው ተጭበርብሯል ሲል ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን ቅሬታውን አቅርቧል። የደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉዳዩን እንዲያጣሩለት ለሊግ አወዳዳሪው ኩባንያ እና ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን ደብዳቤ መጻፉን ምክትል ፕሬዝዳንት ሸረፋ ደልቾ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በሊጉ አዳማ ከነማ እና ጅማ አባጅፋር መውረዳቸው ሲታወቅ በሦስተኛነት ላለመውረድ ከሚጫወቱ ክለቦች መካከል ድሬዳዋ ከነማ፣ ወልቂጤ ከነማ እና ሲዳማ ቡና ይገኙባቸዋል። ጨዋታው በመጭበርበሩ "ድሬ ዳዋ ከነማን ይጠቅማል፣ ወልቂጤ ከነማ ላይ ጉዳት ያደርሳል" ብለዋል ምክትል ኮሚሽነሩ። "በ24ኛው ሳምንት ትላንት በነበረው የ9 ሰዓት ጨዋታ ላይ ድሬዳዋ ከነማ ከፋሲል ከነማ ጋር ጨዋታ ነበራቸው። በጨዋታው ፋሲል ከነማ ከአቅም በታች ተጫውቷል። የጨዋታ የማጭበርበር ሥራ ተሰርቶብኛል ብሎ ነው ወልቂጤ ከነማ ቅሬታ ያቀረበው። ይህ ደግሞ በክልሉ እግር ኳስ ፌደሬሽንም በኩል በበቂ ሁኔታ ታምኖበት የክልሉ እግር ኳስ ፌደሬሽንም ይህንን ቅሬታ ለሚመለከታቸው አካላት አቅርቧል" ብለዋል። የክልሉ እግርኳስ ፌደሬሽን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጻፈው ደብዳቤ በጨዋታው ከፍተኛ የጨዋታ ማጭበርበር እንደተፈጸመ እና ይህንንም ፌደሬሽኑ ባደራጀው የቴክኒክ ኮሚቴ አካላት ሪፖርት እንደቀረበለት አስታውቋል። "የወልቂጤ እግር ኳስ ክለብ ላይ የተፈጸመው በደል እና የጨዋታ ማጭበርበር ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ዕድገት ጸር ነው" ያለው ደብዳቤው የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ የእርምት እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቋል። ከበፊት ጀምሮ ጨዋታዎች 'ሊጭበረበሩ ይችላሉ' የሚሉ የተወሰኑ መረጃዎች ስለነበሩ ፌደሬሽኑ የተወሰኑ ባለሙያዎችንም አሰማርቶ ሁኔታውን ይከታተለው ነበር ብለዋል። "ቅሬታው ዛሬ ነው የቀረበው አወዳዳሪው አካልም ሆነ እግር ኳስ ፌደሬሽኑ መልስ እኛም ክለቡም ይጠብቃል" ሲሉ ገልጸዋል። ጥያቄያቸው በዋነኝነት የጨዋታው ሂደት በገለልተኛ አካል ይገምገም የሚል መሆኑን ጠቅሰው "የጨዋታውን ሂደት የሚገመገምበት ብዙ ፓራሜትሮች ስላሉ ብዙ የሚያስቸግር አይደልም" ሲሉ አክለዋል። ፋሲል ከነማ ቀደም ሲል የነበረው እንቅስቃሴ [ፐርፎርማንስ]፣ ያሰለፋቸው ተጫዋቾች እና አጠቃላይ የነበረውን ሂደት በገለልተኛ አካል እንዲታይ ተጠይቋል ብለዋል። ፋሲል ዋንጫ በማንሳቱ ተጫዋቾች መቀየሩ አንዱ ግምት ሊሆን ይችላል። "በዚህ ጨዋታ ብቻ ሳይሆን በጥቅሉ ይህ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ከፍተኛ ጥንቃቀቄ ለማድርግ ጥረት ሲደረግ እንደነበር እናውቃልን" ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ "ለሁሉም በሚገባ ጥብቅ መመሪያ እና ትዕዛዝ እንደተላለፈ መረጃዎች አሉ" ብለዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቃል አቀባይ ባህሩ ጥላሁን በበኩላቸው ደብዳቤው እንደደረሳቸውና ቅሬታውን የመመልከት ሥልጣን ያለው ሊግ አወዳዳሪው ኩባንያ እንደሆነ ነገር ግን ከኩባንያው አቅም በላይ ከሆነ ፌዴሬሽኑ እንደሚመለከተው ገልጸዋል። ፋሲል ከነማ 22 ጨዋታ ተጫውቶ በ52 ነጥብ ሻምፒዮን መሆኑን ባረጋገጠበት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና እና ሀዲያ ሆሳዕና ይከተላሉ። የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስር በ27 ጎሎች የሊጉን የምንግዜም ከፍተኛ አግቢነት ክብረወሰን በመስበር ጭመር ሲመራ ሙጂብ ቃሲም በ20 እንዲሁም ጌታነህ ከበደ በ12 ጎሎች ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል። | ወልቂጤ ከነማ 'የጨዋታ መጭበርበር ነበር' በሚል ቅሬታ አቀረበ እየተገባደደ በሚገኘው በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ በድሬዳዋ ከነማ እና ፋሲል ከነማ መካከል የተደረገው ጨዋታ ተጭበርብሯል ሲል ወልቂጤ ከነማ ቅሬታውን ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን አቀረበ። ከትላንት በስቲያ ግንቦት 9፣ 2013 ዓ.ም በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም 9 ሰዓት ላይ በነበረው ጨዋታ የዘንድሮው የዋንጫ ባለድል ፋሲል ከነማ በድሬ ዳዋ ከነማ 3 ለ 1 ተረትቷል። ከዚህ ጨዋታ በኋላ ወራጅ ቀጠና የሚገኘው ወልቂጤ ከነማ ጨዋታው ተጭበርብሯል ሲል ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን ቅሬታውን አቅርቧል። የደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉዳዩን እንዲያጣሩለት ለሊግ አወዳዳሪው ኩባንያ እና ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን ደብዳቤ መጻፉን ምክትል ፕሬዝዳንት ሸረፋ ደልቾ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በሊጉ አዳማ ከነማ እና ጅማ አባጅፋር መውረዳቸው ሲታወቅ በሦስተኛነት ላለመውረድ ከሚጫወቱ ክለቦች መካከል ድሬዳዋ ከነማ፣ ወልቂጤ ከነማ እና ሲዳማ ቡና ይገኙባቸዋል። ጨዋታው በመጭበርበሩ "ድሬ ዳዋ ከነማን ይጠቅማል፣ ወልቂጤ ከነማ ላይ ጉዳት ያደርሳል" ብለዋል ምክትል ኮሚሽነሩ። "በ24ኛው ሳምንት ትላንት በነበረው የ9 ሰዓት ጨዋታ ላይ ድሬዳዋ ከነማ ከፋሲል ከነማ ጋር ጨዋታ ነበራቸው። በጨዋታው ፋሲል ከነማ ከአቅም በታች ተጫውቷል። የጨዋታ የማጭበርበር ሥራ ተሰርቶብኛል ብሎ ነው ወልቂጤ ከነማ ቅሬታ ያቀረበው። ይህ ደግሞ በክልሉ እግር ኳስ ፌደሬሽንም በኩል በበቂ ሁኔታ ታምኖበት የክልሉ እግር ኳስ ፌደሬሽንም ይህንን ቅሬታ ለሚመለከታቸው አካላት አቅርቧል" ብለዋል። የክልሉ እግርኳስ ፌደሬሽን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጻፈው ደብዳቤ በጨዋታው ከፍተኛ የጨዋታ ማጭበርበር እንደተፈጸመ እና ይህንንም ፌደሬሽኑ ባደራጀው የቴክኒክ ኮሚቴ አካላት ሪፖርት እንደቀረበለት አስታውቋል። "የወልቂጤ እግር ኳስ ክለብ ላይ የተፈጸመው በደል እና የጨዋታ ማጭበርበር ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ዕድገት ጸር ነው" ያለው ደብዳቤው የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ የእርምት እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቋል። ከበፊት ጀምሮ ጨዋታዎች 'ሊጭበረበሩ ይችላሉ' የሚሉ የተወሰኑ መረጃዎች ስለነበሩ ፌደሬሽኑ የተወሰኑ ባለሙያዎችንም አሰማርቶ ሁኔታውን ይከታተለው ነበር ብለዋል። "ቅሬታው ዛሬ ነው የቀረበው አወዳዳሪው አካልም ሆነ እግር ኳስ ፌደሬሽኑ መልስ እኛም ክለቡም ይጠብቃል" ሲሉ ገልጸዋል። ጥያቄያቸው በዋነኝነት የጨዋታው ሂደት በገለልተኛ አካል ይገምገም የሚል መሆኑን ጠቅሰው "የጨዋታውን ሂደት የሚገመገምበት ብዙ ፓራሜትሮች ስላሉ ብዙ የሚያስቸግር አይደልም" ሲሉ አክለዋል። ፋሲል ከነማ ቀደም ሲል የነበረው እንቅስቃሴ [ፐርፎርማንስ]፣ ያሰለፋቸው ተጫዋቾች እና አጠቃላይ የነበረውን ሂደት በገለልተኛ አካል እንዲታይ ተጠይቋል ብለዋል። ፋሲል ዋንጫ በማንሳቱ ተጫዋቾች መቀየሩ አንዱ ግምት ሊሆን ይችላል። "በዚህ ጨዋታ ብቻ ሳይሆን በጥቅሉ ይህ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ከፍተኛ ጥንቃቀቄ ለማድርግ ጥረት ሲደረግ እንደነበር እናውቃልን" ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ "ለሁሉም በሚገባ ጥብቅ መመሪያ እና ትዕዛዝ እንደተላለፈ መረጃዎች አሉ" ብለዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቃል አቀባይ ባህሩ ጥላሁን በበኩላቸው ደብዳቤው እንደደረሳቸውና ቅሬታውን የመመልከት ሥልጣን ያለው ሊግ አወዳዳሪው ኩባንያ እንደሆነ ነገር ግን ከኩባንያው አቅም በላይ ከሆነ ፌዴሬሽኑ እንደሚመለከተው ገልጸዋል። ፋሲል ከነማ 22 ጨዋታ ተጫውቶ በ52 ነጥብ ሻምፒዮን መሆኑን ባረጋገጠበት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና እና ሀዲያ ሆሳዕና ይከተላሉ። የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስር በ27 ጎሎች የሊጉን የምንግዜም ከፍተኛ አግቢነት ክብረወሰን በመስበር ጭመር ሲመራ ሙጂብ ቃሲም በ20 እንዲሁም ጌታነህ ከበደ በ12 ጎሎች ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57164707 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ መምህር በቫይረሱ ሕይወታቸው አለፈ | በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሕብረተሰብ ጤና ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ዶ/ር ፍሰሃየ አለምሰገድ በኮሮናቫይረስ ተይዘው የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይተው ዛሬ ሕይወታቸው ማለፉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ ለቢቢሲ ገለፁ። ሕክምና እየተከታተሉ በሚገኙበት የመቀለ የኮሮና ታማሚዎች ማገገሚያ ማዕከል ሕይወታቸው ማለፉንም የገለፁት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት፤ ከእርሳቸው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላት አንድ ግለሰብም በቫይረሱ መያዟ ተረጋግጦ ሕክምና እየተደረገላት እንደሚገኝ አክለዋል። በዩኒቨርስቲው የተለያዩ ግቢዎች በሚገኙ ለይቶ ማቆያዎች የሚሰሩ 1 ሹፌር፣ 2 የፀረ ተህዋስ ኬሚካል ርጭት ባለሙያዎች፣ 23 የፅዳት ሰራተኞች እና 10 የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸውን በዩኒቨርሲቲው ኮርፖሬት ኮሚኒኬሽንና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተወካይ ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ዘ ሚካኤል ገልፀውልናል። ዶ/ር ፍሰሃየ ከመምህርነት ባሻገር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የኮሮናቫይረስ ፈጣን ግብረ መልስ ቡድን መሪ በመሆን እንዲሁም በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ በኮሮናቫይረስ መረጃ ትንተና እና ትንበያ ክፍል እየሰሩ እንደነበር ዶ/ር ኪሮስ ገልፀውልናል። ዶ/ር ፍሰሃየ አለምሰገድ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመምህርነት፣ በተመራማሪነትና በሙያ አማካሪነት ለ17 ዓመታት አገልግለዋል። ከመስከረም 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በመዛወር በዩኒቨርሲቲው የሕብረተሰብ ጤና ትምህርት ክፍል ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ፍሰሃየ በእናቶችና ህፃናት ህክምና፣ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች፣ በስነ-ምግብ፣ በወባ፣ በኤች አይቪ ኤድስና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ጨምሮ በሌሎች የሕብረተሰብ ጤና ዘርፎች ከ50 በላይ ችግር ፈቺ ጥናቶችን በታዋቂ ጆርናሎች ማሳተማቸውን አክለዋል። የቀብር ሥነ ስርዓታቸውም ነገ በመቀለ ከተማ እንደሚፈፀም ዶ/ር ኪሮስ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በትግራይ ክልል እስካሁን በተደረገ 25 ሺህ 579 ናሙናዎች ተመርምረው 1016 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን የ5 ሰዎች ሕይወት አልፏል። | ኮሮናቫይረስ፡ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ መምህር በቫይረሱ ሕይወታቸው አለፈ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሕብረተሰብ ጤና ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ዶ/ር ፍሰሃየ አለምሰገድ በኮሮናቫይረስ ተይዘው የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይተው ዛሬ ሕይወታቸው ማለፉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ ለቢቢሲ ገለፁ። ሕክምና እየተከታተሉ በሚገኙበት የመቀለ የኮሮና ታማሚዎች ማገገሚያ ማዕከል ሕይወታቸው ማለፉንም የገለፁት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት፤ ከእርሳቸው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላት አንድ ግለሰብም በቫይረሱ መያዟ ተረጋግጦ ሕክምና እየተደረገላት እንደሚገኝ አክለዋል። በዩኒቨርስቲው የተለያዩ ግቢዎች በሚገኙ ለይቶ ማቆያዎች የሚሰሩ 1 ሹፌር፣ 2 የፀረ ተህዋስ ኬሚካል ርጭት ባለሙያዎች፣ 23 የፅዳት ሰራተኞች እና 10 የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸውን በዩኒቨርሲቲው ኮርፖሬት ኮሚኒኬሽንና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተወካይ ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ዘ ሚካኤል ገልፀውልናል። ዶ/ር ፍሰሃየ ከመምህርነት ባሻገር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የኮሮናቫይረስ ፈጣን ግብረ መልስ ቡድን መሪ በመሆን እንዲሁም በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ በኮሮናቫይረስ መረጃ ትንተና እና ትንበያ ክፍል እየሰሩ እንደነበር ዶ/ር ኪሮስ ገልፀውልናል። ዶ/ር ፍሰሃየ አለምሰገድ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመምህርነት፣ በተመራማሪነትና በሙያ አማካሪነት ለ17 ዓመታት አገልግለዋል። ከመስከረም 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በመዛወር በዩኒቨርሲቲው የሕብረተሰብ ጤና ትምህርት ክፍል ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ፍሰሃየ በእናቶችና ህፃናት ህክምና፣ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች፣ በስነ-ምግብ፣ በወባ፣ በኤች አይቪ ኤድስና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ጨምሮ በሌሎች የሕብረተሰብ ጤና ዘርፎች ከ50 በላይ ችግር ፈቺ ጥናቶችን በታዋቂ ጆርናሎች ማሳተማቸውን አክለዋል። የቀብር ሥነ ስርዓታቸውም ነገ በመቀለ ከተማ እንደሚፈፀም ዶ/ር ኪሮስ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በትግራይ ክልል እስካሁን በተደረገ 25 ሺህ 579 ናሙናዎች ተመርምረው 1016 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን የ5 ሰዎች ሕይወት አልፏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-53699944 |
5sports
| ኢትዮጵያ የቶኪዮ ኦሎምፒክስ የአትሌቲክስ ተወዳዳሪዎቿን ይፋ አደረገች | በቅርቡ በኔዘርላንድስ ሄንግሎ በተካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ የአትሌቲክስ ማጣሪያ ውድድሮች ከአንድ እስከ ሶስተኛ የወጡ አሸናፊዎች በቶኪዮ ኦሎምፒክስ አገራቸውን ወክለው እንደሚወዳደሩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። በዚህም መሰረት ከ800-10 ሺህ ሜትር ባሉ ውድድሮች እንዲሁም 3000 ሜትር መሰናክልን ጨምሮ በአምስት ውድድሮች በሁለቱም ፆታ አገራቸውን የሚወክሉ አትሌቶች በውጤታቸው መሰረት ተሰላፊዎቹና ተጠባባቂዎቹ ተለይተዋል። ከቀናት በፊት በነበረው የ10 ሺህ የሴቶች ማጣሪያ ውድድር ለተሰንበት ግደይከሁለት ቀናት በፊት በሲፋን ሀሰን ተሰብሮ የነበረውን የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር አሸናፊ መሆን ችላለች። በዚህ በ29 ደቂቃ ከ1.03 አሸናፊ በሆነችበት ውድድር ፅጌ ገብረ ሰላማ በሁለተኝነት፣ ፀሃይ ገመቹ በሶስተኝነት አሸናፊ ሆነዋል። በቀጣዩ የቶኪዮ ኦሎምፒክ በ10 ሺህ ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩት ለተሰንበት ግደይ፣ ፅጌ ገብረሰላማ፣ ፀኀይ ገመቹና በተጠባባቂነት ያለም ዘርፍ የኋላው ናቸው። በቶኪዮ ኦሎምፒክስ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩ አትሌቶች ዝርዝር በ800 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች በ1500 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች በ5000 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች በ1000 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች በ3000 ሜትር መሰናክል የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች በወንዶች 10ሺህ ሜትር ማጣሪያ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ አራተኛ ደረጃ የያዙ ሲሆን አትሌት ሰለሞን ባረጋ በ26 ደቂቃ 49 ሰከንድ ከ51 ማይክሮሰከንድ በሆነ ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ መሆን ችሏል። እሱን በመከተል ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ በሪሁ አረጋዊ እና ሀጎስ ገብረህይወት ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። በ1500 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ወንድ ተወዳዳሪዎች በ5000 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ወንድ ተወዳዳሪዎች በ10000 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ወንድ ተወዳዳሪዎች በ3000 ሜትር መሰናክል የቶኪዮ ኦሎምፒክ ወንድ ተወዳዳሪዎች የቶክዮ ኦሎምፒክ 2020/2021 ከሐምሌ 16- ነሐሴ 2 ድረስ ይካሄዳል። | ኢትዮጵያ የቶኪዮ ኦሎምፒክስ የአትሌቲክስ ተወዳዳሪዎቿን ይፋ አደረገች በቅርቡ በኔዘርላንድስ ሄንግሎ በተካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ የአትሌቲክስ ማጣሪያ ውድድሮች ከአንድ እስከ ሶስተኛ የወጡ አሸናፊዎች በቶኪዮ ኦሎምፒክስ አገራቸውን ወክለው እንደሚወዳደሩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። በዚህም መሰረት ከ800-10 ሺህ ሜትር ባሉ ውድድሮች እንዲሁም 3000 ሜትር መሰናክልን ጨምሮ በአምስት ውድድሮች በሁለቱም ፆታ አገራቸውን የሚወክሉ አትሌቶች በውጤታቸው መሰረት ተሰላፊዎቹና ተጠባባቂዎቹ ተለይተዋል። ከቀናት በፊት በነበረው የ10 ሺህ የሴቶች ማጣሪያ ውድድር ለተሰንበት ግደይከሁለት ቀናት በፊት በሲፋን ሀሰን ተሰብሮ የነበረውን የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር አሸናፊ መሆን ችላለች። በዚህ በ29 ደቂቃ ከ1.03 አሸናፊ በሆነችበት ውድድር ፅጌ ገብረ ሰላማ በሁለተኝነት፣ ፀሃይ ገመቹ በሶስተኝነት አሸናፊ ሆነዋል። በቀጣዩ የቶኪዮ ኦሎምፒክ በ10 ሺህ ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩት ለተሰንበት ግደይ፣ ፅጌ ገብረሰላማ፣ ፀኀይ ገመቹና በተጠባባቂነት ያለም ዘርፍ የኋላው ናቸው። በቶኪዮ ኦሎምፒክስ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩ አትሌቶች ዝርዝር በ800 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች በ1500 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች በ5000 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች በ1000 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች በ3000 ሜትር መሰናክል የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች በወንዶች 10ሺህ ሜትር ማጣሪያ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ አራተኛ ደረጃ የያዙ ሲሆን አትሌት ሰለሞን ባረጋ በ26 ደቂቃ 49 ሰከንድ ከ51 ማይክሮሰከንድ በሆነ ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ መሆን ችሏል። እሱን በመከተል ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ በሪሁ አረጋዊ እና ሀጎስ ገብረህይወት ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። በ1500 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ወንድ ተወዳዳሪዎች በ5000 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ወንድ ተወዳዳሪዎች በ10000 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ወንድ ተወዳዳሪዎች በ3000 ሜትር መሰናክል የቶኪዮ ኦሎምፒክ ወንድ ተወዳዳሪዎች የቶክዮ ኦሎምፒክ 2020/2021 ከሐምሌ 16- ነሐሴ 2 ድረስ ይካሄዳል። | https://www.bbc.com/amharic/57444933 |
2health
| ሕንድ ውስጥ በርካቶች ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ታመው ሆስፒታል ገቡ | በሕንድ ውስጥ በሚገኝ አንድ ግዛት ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ታመው ሆስፒታል መግባተቸው ተነገረ። የአገሪቱ ባለስልጣናት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ 140 ሰዎችን ሆስፒታል እንዲገቡ ያደረገው በሽታን ምንነት ለማወቅ ምርምራ እያካሄዱ ነው። የህክምና ተመራማሪዎችም የዚህን በሽታ ምንነት ለመለየት እና የሕመሙን መንስኤ ለማወቅ ጥረት መጀመራቸው አስታውቀዋል። አንድራ ፕራዴሽ ከሚባለው ግዛት የመጡት ታማሚዎች በርካታ የተለያዩ የሕመም ምልክቶች ሲያሳዩ የነበረ ሲሆን፤ ከምልክቶቹ ውስጥም ማቅለሽለሽ እና እራስን ስቶ ተዝለፍልፎ መውደቅ ደግሞ አብዛኛዎቹ ላይ የተስተዋለ እንደሆነ ዶክተሮች ገልጸዋል። ኢሉሩ የተባለው የመንግሥት ሆስፒታል ደግሞ ምናልባት ተጨማሪ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ታማሚዎች ከመጡ በሚል በርካታ አልጋዎች ነጻ ሆነው እንዲጠባበቁም ተደርጓል ተብሏል። ሕንድ የኮሮናቫይረስ ተጽእኖን ለመቀነስ እና ስርጭቱን ለመቆጣጠር ደፋ ቀና በምትልበት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ምንነቱ ያልታወቀ ሕመም መከሰቱ በርካቶችን አሳስቧል። የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ደግሞ ሁሉም ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ታማሚዎች የኮሮናቫይረስ ምርምራ የተደረገላቸው ሲሆን ማናቸውም ግን በቫይረሱ አልተያዙም። በኢሉሩ የመንግሥት ሆስፒታል የሚሰራ አንድ የጤና ባለሙያ ለኢንዲያን ኤክስፕረስ ሲናገር '''አይናችን አካባቢ ማቃጠል ይሰማናል' ብለው ወደ ሆስፒታላችን ከመጡት መካከል በተለይ ደግሞ ሕጻናቱ ወዲያው ማስመለስ ጀመሩ። አንዳንዶቹ እራሳቸውን የሳቱ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ቅዝቃዜ ተሰምቷቸው ይንቀጠቀጡ ነበር'' ብሏል። ወደ ሆስፒታል ከተወሰዱት ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ ሲሆን አንዳንዶቹም ተሽሏቸው ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል። የአንድራ ፕራዳሽ የጤና ሚኒስትር አላ ካሊ ካሊ ክሪሽና እንዳሉት ደግሞ ከሁሉም ታማሚዎች ላይ የደም ናሙና የተወሰደ ቢሆንም ምንም አይነት የቫይረስ ኢንፌክሽን ምልክት ግን አልታየባቸውም። ''ባለሙያዎቻችን የሰዎቹን መኖሪያ አካባቢ ከጎበኙ በኋላ በምርመራችን የአየር እና የውሃ ብክለት አለመሆኑን ደርሰንበታል። ምስጢራዊ የሆነ ሕመም ይመስላል፤ የትኛውም የላብራቶሪ ምርመራ ምክንያቱን ሊያውቀው አልቻለም'' ብለዋል የጤና ሚንስትሩ። | ሕንድ ውስጥ በርካቶች ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ታመው ሆስፒታል ገቡ በሕንድ ውስጥ በሚገኝ አንድ ግዛት ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ታመው ሆስፒታል መግባተቸው ተነገረ። የአገሪቱ ባለስልጣናት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ 140 ሰዎችን ሆስፒታል እንዲገቡ ያደረገው በሽታን ምንነት ለማወቅ ምርምራ እያካሄዱ ነው። የህክምና ተመራማሪዎችም የዚህን በሽታ ምንነት ለመለየት እና የሕመሙን መንስኤ ለማወቅ ጥረት መጀመራቸው አስታውቀዋል። አንድራ ፕራዴሽ ከሚባለው ግዛት የመጡት ታማሚዎች በርካታ የተለያዩ የሕመም ምልክቶች ሲያሳዩ የነበረ ሲሆን፤ ከምልክቶቹ ውስጥም ማቅለሽለሽ እና እራስን ስቶ ተዝለፍልፎ መውደቅ ደግሞ አብዛኛዎቹ ላይ የተስተዋለ እንደሆነ ዶክተሮች ገልጸዋል። ኢሉሩ የተባለው የመንግሥት ሆስፒታል ደግሞ ምናልባት ተጨማሪ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ታማሚዎች ከመጡ በሚል በርካታ አልጋዎች ነጻ ሆነው እንዲጠባበቁም ተደርጓል ተብሏል። ሕንድ የኮሮናቫይረስ ተጽእኖን ለመቀነስ እና ስርጭቱን ለመቆጣጠር ደፋ ቀና በምትልበት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ምንነቱ ያልታወቀ ሕመም መከሰቱ በርካቶችን አሳስቧል። የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ደግሞ ሁሉም ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ታማሚዎች የኮሮናቫይረስ ምርምራ የተደረገላቸው ሲሆን ማናቸውም ግን በቫይረሱ አልተያዙም። በኢሉሩ የመንግሥት ሆስፒታል የሚሰራ አንድ የጤና ባለሙያ ለኢንዲያን ኤክስፕረስ ሲናገር '''አይናችን አካባቢ ማቃጠል ይሰማናል' ብለው ወደ ሆስፒታላችን ከመጡት መካከል በተለይ ደግሞ ሕጻናቱ ወዲያው ማስመለስ ጀመሩ። አንዳንዶቹ እራሳቸውን የሳቱ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ቅዝቃዜ ተሰምቷቸው ይንቀጠቀጡ ነበር'' ብሏል። ወደ ሆስፒታል ከተወሰዱት ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ ሲሆን አንዳንዶቹም ተሽሏቸው ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል። የአንድራ ፕራዳሽ የጤና ሚኒስትር አላ ካሊ ካሊ ክሪሽና እንዳሉት ደግሞ ከሁሉም ታማሚዎች ላይ የደም ናሙና የተወሰደ ቢሆንም ምንም አይነት የቫይረስ ኢንፌክሽን ምልክት ግን አልታየባቸውም። ''ባለሙያዎቻችን የሰዎቹን መኖሪያ አካባቢ ከጎበኙ በኋላ በምርመራችን የአየር እና የውሃ ብክለት አለመሆኑን ደርሰንበታል። ምስጢራዊ የሆነ ሕመም ይመስላል፤ የትኛውም የላብራቶሪ ምርመራ ምክንያቱን ሊያውቀው አልቻለም'' ብለዋል የጤና ሚንስትሩ። | https://www.bbc.com/amharic/news-55211959 |
0business
| ሊባኖስ፡ ለመሠረታዊ ሸቀጦች የሚደረገው ድጎማ እንዳይነሳ ቤይሩት ውስጥ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ | በአንዳንድ መሠረታዊ ሸቀጦች ላይ መንግሥት ያደርገው የነበረው ድጎማ ሊቀነስ መሆኑን በመቃወም በሊባኖሷ መዲና ቤይሩት ውስጥ ተቃዋሚዎች መንገዶችን መዝጋታቸው ተነገረ። የድጎማውን መቀነስ በተመለከተ የወጡ መረጃዎችን ተከትሎ እርምጃውን የተቃወሙ ሰልፈኞች በማዕከላዊ ቤይሩት መንገዶች ላይ ጎማዎችን ያቃጠሉ ሲሆን አንዳንዶቹም ቁጣቸውን ለመግለጽ ወደ አገሪቱ ፓርላማ ህንጻ አምርተዋል ተብሏል። የአገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ ኃላፊ መንግሥት በዱቄት፣ በነዳጅና በመድኃኒቶች ላይ ያደርግ የነበረው ድጎማ ከቀጣዮቹ ሁለት ወራት በኋላ ሊቀጥሉ እንደማይችሉ ተናግረው ነበር። በአገሪቱ ውስጥ በተከሰተው የኢኮኖሚ ድቀት ሳቢያ በተለይ ድሃ ቤተሰቦች ላይ ከባድ ማኅበራዊ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ተቋማት አስጠንቅቀዋል። ከሰኞ ጀምሮ የሌባኖስ ዜጎች በመሠረታዊ ሸቀጦች ላይ መንግሥት ያደርግ የነበረው ድጎማ ለማንሳት ማሰቡን በተመለከተ በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ ከሰኞ ጀምሮ ከፍተኛ ዘመቻ እያካሄዱ ነው። ሊባኖስ ለተራዘመ ጊዜ እያሰቃያት ባለው የምጣኔ ሐብት ቀውስ ምክንያት የአገሪቱ ገንዘብ የመግዛት አቅም በከፍተኛ ደረጃ በመዳከሙ ማዕከላዊው ባንክ ዱቄትና ነዳጅን የመሳሰሉ ምርቶች ከውጭ ለሚያስገቡ አስመጪዎች የውጭ ምንዛሪ በቅናሽ እያቀረበ ቆይቷል። የምጣኔ ሐብት ቀውሱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሊባኖሳዊያንን ወደ ድህነት የከተተ ሲሆን፤ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ደግሞ ቀውሱን የበለጠ አባብሶታል። ባለፈው ዓመት ነሐሴ ላይ በቤይሩት ወደብ ላይ ተከስቶ ከ200 በላይ ሰዎችን የገደለውና በሺዎች ያቆሰለውን ከባድ ፍንዳታ ተከትሎ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰልፈኞች በዋና ከተማዋ ያሉትን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጥሰው ገብተው እንደነበር ይታወሳል። ለፍንዳታው ምክንያት የሆነውን ወደቡ ውስጥ በሚገኝ አንድ መጋዘን ውስጥ ለረጅም ጊዜ ተከማችቶ የነበረውን ሁለት ሺህ ቶን የሚደርስ የአሙኒየም ናይትሬት አደገኛ ንጥረ ነገር እንዳይፈነዳና ጉዳት እንዳያደርስ ባለስልጣናት ለማድረግ አልቻሉም በሚል በወቅቱ በርካታ የሊባኖስ ዜጎች ቁጣቸውን ገልጸው ነበር። በደረሰው ከባድ ጉዳትና በተቀሰቀሰው ከባድ ተቃውሞ ምክንያት አገሪቱን ያስተዳድር የነበረው የሊባኖስ መንግሥት ስልጣኑን እንዲለቅ ተገዶ ነበር። | ሊባኖስ፡ ለመሠረታዊ ሸቀጦች የሚደረገው ድጎማ እንዳይነሳ ቤይሩት ውስጥ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ በአንዳንድ መሠረታዊ ሸቀጦች ላይ መንግሥት ያደርገው የነበረው ድጎማ ሊቀነስ መሆኑን በመቃወም በሊባኖሷ መዲና ቤይሩት ውስጥ ተቃዋሚዎች መንገዶችን መዝጋታቸው ተነገረ። የድጎማውን መቀነስ በተመለከተ የወጡ መረጃዎችን ተከትሎ እርምጃውን የተቃወሙ ሰልፈኞች በማዕከላዊ ቤይሩት መንገዶች ላይ ጎማዎችን ያቃጠሉ ሲሆን አንዳንዶቹም ቁጣቸውን ለመግለጽ ወደ አገሪቱ ፓርላማ ህንጻ አምርተዋል ተብሏል። የአገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ ኃላፊ መንግሥት በዱቄት፣ በነዳጅና በመድኃኒቶች ላይ ያደርግ የነበረው ድጎማ ከቀጣዮቹ ሁለት ወራት በኋላ ሊቀጥሉ እንደማይችሉ ተናግረው ነበር። በአገሪቱ ውስጥ በተከሰተው የኢኮኖሚ ድቀት ሳቢያ በተለይ ድሃ ቤተሰቦች ላይ ከባድ ማኅበራዊ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ተቋማት አስጠንቅቀዋል። ከሰኞ ጀምሮ የሌባኖስ ዜጎች በመሠረታዊ ሸቀጦች ላይ መንግሥት ያደርግ የነበረው ድጎማ ለማንሳት ማሰቡን በተመለከተ በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ ከሰኞ ጀምሮ ከፍተኛ ዘመቻ እያካሄዱ ነው። ሊባኖስ ለተራዘመ ጊዜ እያሰቃያት ባለው የምጣኔ ሐብት ቀውስ ምክንያት የአገሪቱ ገንዘብ የመግዛት አቅም በከፍተኛ ደረጃ በመዳከሙ ማዕከላዊው ባንክ ዱቄትና ነዳጅን የመሳሰሉ ምርቶች ከውጭ ለሚያስገቡ አስመጪዎች የውጭ ምንዛሪ በቅናሽ እያቀረበ ቆይቷል። የምጣኔ ሐብት ቀውሱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሊባኖሳዊያንን ወደ ድህነት የከተተ ሲሆን፤ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ደግሞ ቀውሱን የበለጠ አባብሶታል። ባለፈው ዓመት ነሐሴ ላይ በቤይሩት ወደብ ላይ ተከስቶ ከ200 በላይ ሰዎችን የገደለውና በሺዎች ያቆሰለውን ከባድ ፍንዳታ ተከትሎ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰልፈኞች በዋና ከተማዋ ያሉትን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጥሰው ገብተው እንደነበር ይታወሳል። ለፍንዳታው ምክንያት የሆነውን ወደቡ ውስጥ በሚገኝ አንድ መጋዘን ውስጥ ለረጅም ጊዜ ተከማችቶ የነበረውን ሁለት ሺህ ቶን የሚደርስ የአሙኒየም ናይትሬት አደገኛ ንጥረ ነገር እንዳይፈነዳና ጉዳት እንዳያደርስ ባለስልጣናት ለማድረግ አልቻሉም በሚል በወቅቱ በርካታ የሊባኖስ ዜጎች ቁጣቸውን ገልጸው ነበር። በደረሰው ከባድ ጉዳትና በተቀሰቀሰው ከባድ ተቃውሞ ምክንያት አገሪቱን ያስተዳድር የነበረው የሊባኖስ መንግሥት ስልጣኑን እንዲለቅ ተገዶ ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/news-55226709 |
0business
| የቻይናን የለውጥ ሂደት ለ40 ዓመታት በካሜራው የሰነደው ግለሰብ | በሐምሌ ወር የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ 100ኛ የምስረታ ዓመቱን ያከብራል። በማኦ ዜዱንግ የተቀረጸው ፖሊሲ በ1950ዎቹ እና 60ዎቹ ረሃብ እና ቀውስ አስከትሎ ነበር። የእርሳቸውን ሞት ተከትሎ በቻይና ሰፊ የሚባል ለውጥ መጥቷል። ያን ዢጋንግ የተባለ ቻይናዊ ታዲያ ለ40 ዓመታት የቻይና ጎዳናዎችን በካሜራ እየቀረጸ ለውጡን ሰንዷል። | የቻይናን የለውጥ ሂደት ለ40 ዓመታት በካሜራው የሰነደው ግለሰብ በሐምሌ ወር የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ 100ኛ የምስረታ ዓመቱን ያከብራል። በማኦ ዜዱንግ የተቀረጸው ፖሊሲ በ1950ዎቹ እና 60ዎቹ ረሃብ እና ቀውስ አስከትሎ ነበር። የእርሳቸውን ሞት ተከትሎ በቻይና ሰፊ የሚባል ለውጥ መጥቷል። ያን ዢጋንግ የተባለ ቻይናዊ ታዲያ ለ40 ዓመታት የቻይና ጎዳናዎችን በካሜራ እየቀረጸ ለውጡን ሰንዷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57677744 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ የለንደን ፖሊስ ክልከላዎችን በመተላለፍ ሰልፍ የወጡ ሰዎችን አሰረ | በለንደን ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ የተጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ ለመቃወም ከወጡ ሰዎች መካካል 18 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ። ውሳኔውን የተቃወሙ በርካታ ሰዎች ከዩናይትድ ኪንግደም ንጉሳውያን መኖሪያ በሆነው ባኪንግሃም ቤተ-መንግስት ፊትለፊት ተሰባስበው ነበር። በመቀጠል ተቃዋሚ ሰልፈኞች ወደ ትራፋልጋር አደባባይ አምርተዋል። ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች በኮቪድ ምክንያት የተነጠቅነው ነጻነት ይመለስልን ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል። የሜትሮፖሊታን ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ እንዲበተኑ የተደረገ ቢሆንም ዜጎች ግን አሁንም ቢሆን አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል። በዌስትሚኒስተር ድልድይ ላይ ደግሞ ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ለመበተን ጥረት በሚያደርግበት ወቅት አንዳንድ ችግሮች ተፈጥረው ነበር ተብሏል። የፖሊስ አባላት ቀላል የሚባል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፖሊስ ሰልፈኞቹ በቁጥጥር ሥር ያዋልኩት የተለያዩ ሕግጋቶችን በመተላለፍ ነው ብሏል። ከጥፋቶቹ መካከልም የኮሮረናቫይረስ ሕጎችን በመጣስ፣ የአደጋ ጊዜ ሰራተኛ ላይ ጉዳት ማድረስና ነውጠኝነት በዋነኛነት ተጠቃሽ ናቸው። ለንደን በያዝነው ሳምንት ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ጠበቅ ያሉ ገደቦች ተጥለውባታል። ''ሰዎች በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ሲገኙ አካላዊ ርቀታቸውን አለመጠበቃቸውና የተቀመጡ ሕግና ደንቦችን አለማክበራቸው በእጅጉ አሳስቦናል'' ብለዋል የሜርሮፖሊታን ፖሊስ አዛዡ ኮማንደር አዴ አዴሌካን። አክለውም ''የተቃውሞ ሰልፉ አዘጋጆች የሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ በቂ ዝግጅት አላደረጉም። በዚህ ሰአት ነው የህብረተሰቡን ደህንነት ለማረጋገጥ በማሰብ ፖሊሶች የተሰበሰቡትን ሰዎች ለመበተን የተንቀሳቀሱት'' ብለዋል። ''አብዛኛዎቹ የተሰበሰቡት ሰዎች የፖሊስ አባላቱ የነገሯቸውን በመስማታቸውና አካባቢውን ቶሎ በመልቀቃቸው ደስተኞች ነን። ነገር ግን ጥቂቶች ተባባሪ ለመሆን ፈቃደኛ አልነበሩም። ሆነ ብለው ፖሊሶች የሚነግሯቸው ነገር ችላ ሲሉ ነበር። ዌስትሚኒስተር ድልድይንም ዘግተው ነበር'' ብለዋል። | ኮሮናቫይረስ፡ የለንደን ፖሊስ ክልከላዎችን በመተላለፍ ሰልፍ የወጡ ሰዎችን አሰረ በለንደን ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ የተጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ ለመቃወም ከወጡ ሰዎች መካካል 18 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ። ውሳኔውን የተቃወሙ በርካታ ሰዎች ከዩናይትድ ኪንግደም ንጉሳውያን መኖሪያ በሆነው ባኪንግሃም ቤተ-መንግስት ፊትለፊት ተሰባስበው ነበር። በመቀጠል ተቃዋሚ ሰልፈኞች ወደ ትራፋልጋር አደባባይ አምርተዋል። ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች በኮቪድ ምክንያት የተነጠቅነው ነጻነት ይመለስልን ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል። የሜትሮፖሊታን ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ እንዲበተኑ የተደረገ ቢሆንም ዜጎች ግን አሁንም ቢሆን አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል። በዌስትሚኒስተር ድልድይ ላይ ደግሞ ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ለመበተን ጥረት በሚያደርግበት ወቅት አንዳንድ ችግሮች ተፈጥረው ነበር ተብሏል። የፖሊስ አባላት ቀላል የሚባል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፖሊስ ሰልፈኞቹ በቁጥጥር ሥር ያዋልኩት የተለያዩ ሕግጋቶችን በመተላለፍ ነው ብሏል። ከጥፋቶቹ መካከልም የኮሮረናቫይረስ ሕጎችን በመጣስ፣ የአደጋ ጊዜ ሰራተኛ ላይ ጉዳት ማድረስና ነውጠኝነት በዋነኛነት ተጠቃሽ ናቸው። ለንደን በያዝነው ሳምንት ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ጠበቅ ያሉ ገደቦች ተጥለውባታል። ''ሰዎች በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ሲገኙ አካላዊ ርቀታቸውን አለመጠበቃቸውና የተቀመጡ ሕግና ደንቦችን አለማክበራቸው በእጅጉ አሳስቦናል'' ብለዋል የሜርሮፖሊታን ፖሊስ አዛዡ ኮማንደር አዴ አዴሌካን። አክለውም ''የተቃውሞ ሰልፉ አዘጋጆች የሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ በቂ ዝግጅት አላደረጉም። በዚህ ሰአት ነው የህብረተሰቡን ደህንነት ለማረጋገጥ በማሰብ ፖሊሶች የተሰበሰቡትን ሰዎች ለመበተን የተንቀሳቀሱት'' ብለዋል። ''አብዛኛዎቹ የተሰበሰቡት ሰዎች የፖሊስ አባላቱ የነገሯቸውን በመስማታቸውና አካባቢውን ቶሎ በመልቀቃቸው ደስተኞች ነን። ነገር ግን ጥቂቶች ተባባሪ ለመሆን ፈቃደኛ አልነበሩም። ሆነ ብለው ፖሊሶች የሚነግሯቸው ነገር ችላ ሲሉ ነበር። ዌስትሚኒስተር ድልድይንም ዘግተው ነበር'' ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54681599 |
3politics
| ከስድስት ዓመታት በላይ በአማፂያን ታግተው የነበሩት ኮሎምቢያዊት ለፕሬዚዳንትነት ሊወዳደሩ ነው | የቀድሞዋ የኮሎምቢያ ሴናተርና ከ20 አመታት በፊት በግራ ክንፍ አማፂያን ታግተው የነበሩት ኢንግሪድ ቤንታኮርት ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደሩ አስታወቁ። ኢንግሪድ በአውሮፓውያኑ 2002 በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ቅስቀሳ እያደረጉ በነበረበት ወቅት በፋርክ አማፂያን ተወስደው ከስድስት ዓመታት በላይ ታግተው ቆይተዋል። ፖለቲከኛዋ በመጪው ግንቦት ወር የሚደረገውን ምርጫ ካሸነፉ ሙስናን እና ድህነትን ለመቅረፍ ቃል ገብተዋል። "በአሁኑ ወቅት ልወዳደር የመጣሁት የጀመርኩትን ለመጨረስ ነው" ሲሉ በሃገሪቱ መዲና ቦጎታ ላሉ ደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል። "እኔ ፊታችሁ የተገኘሁት ፍትህ የማያገኙ 51 ሚሊዮን ኮሎምቢያውያንን መብት ለመጠየቅ ነው፤ ምክንያቱም የምንኖረው ወንጀለኞችን ለመሸለም በተዘጋጀ ስርአት ውስጥ ነው" ሲሉም ተደምጠዋል። የፋርክ አማፅያን ከ50 ዓመታት በላይ ከኮሎምቢያ መንግሥት ጋር ደም አፋሳሽ ጦርነት ያካሄዱ የማርክሲስት ቡድን ነበሩ። በመጨረሻም በአውሮፓውያኑ 2016 የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ተደረሰ። በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ መጪው ሰኔ ለሚደረገው ምርጫ ከ20 በላይ እጩዎች እንደሚወዳደሩ ታውቋል። የቦጎታ የቀድሞ ከንቲባ እና ኤም- 19 የተባለው የአብዮታዊ ሽምቅ ተዋጊ ቡድን አባል የነበሩት ጉስታቮ ፔትሮ በአሁኑ ጊዜ በህዝብ የምርጫ አስተያየት መስረት በግንባር ቀደምትነት እየመሩ ነው። በርካታ ኮሎምቢያውያን በአሁኑ ጊዜ አገሪቱን እየመሩ ካሉትና ተወዳጅነታቸው እያሽቆለቆለ ከመጣው የቀኝ ክንፍ ፖለቲከኛው ፕሬዚዳንት ኢቫን ዱክ የተሻለ አማራጭ አድርገው ያዩዋቸዋል ጉስታቮ ፔትሮን። ፕሬዚዳንት ኢቫን ዱክ በጊዜ ገደብ ምክንያት በዘንድሮው ምርጫ መወዳደር አይችሉም። ኢንግሪድ ቤንታኮርት በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂነት ቢኖራቸውም በአውሮፓውያኑ 2008 በኮሎምቢያ ወታደራዊ ሃይሎች አማካኝነት ከተለቀቁ በኋላ ድምፃቸው አይሰማም። በአሁኑ ወቅትም ፓርቲያቸውን ኦክስጅንን ጨምሮ በተዋቀረው ሴንትሪስት በተባለው ጥምረት እጩነትን ለማሸነፍ ከባድ ፈተና ይገጥማቸዋል። የመጀመሪያ ደረጃ ምርጫ ሁለት ወራት ብቻ በቀረውና ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በግጭት ሰለባ ሆነው በመንግሥት በተመዘገቡባት ሀገር ራሳቸውን እንደ አስታራቂ እጩ አድርገው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ኢንግሪድ ቤንታኮርት በፋርክ አማፂያን የታገቱት ሳን ቪሰንቴ ዴል ካጉዋን በምትባል ከተማ የነበራቸውን የምርጫ ቅስቀሳ አጠናቀው ሲመለሱ መንገድ ላይ ነው። በኮሎምቢያ ጫካ ውስጥ በቆዩባቸው ስድስት ዓመታት ውስጥ በአጋቾቻቸው ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል። በፋርክ አማፂያን ውስጥ የነበሩ ሰርጎ ገብ የኮሎምቢያ ጦር አባላትም ተቀናጅተው ነው በአውሮፓውያኑ 2008 ያስለቀቋቸው። ከተለቀቁም በኋላ በርካታ አመታትን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው በፈረንሳይ ነው የኖሩት። የፋርክ አማጽያን ከ50 ዓመታት በላይ ከመንግሥት ጋር ባደረጉት የእርስ በርስ ጦርነት ከ200 ሺህ ሰዎች በላይ ተገድለዋል። ቡድኑ በአውሮፓውያኑ 2016 የሰላም ስምምነት ከማዕከላዊው መንግሥት ጋር ተፈራርመው የተወሰኑት ወደ ፓርላማ ሲገቡ የቀሩት ደግሞ በጦርነቱ ቀጥለዋል። | ከስድስት ዓመታት በላይ በአማፂያን ታግተው የነበሩት ኮሎምቢያዊት ለፕሬዚዳንትነት ሊወዳደሩ ነው የቀድሞዋ የኮሎምቢያ ሴናተርና ከ20 አመታት በፊት በግራ ክንፍ አማፂያን ታግተው የነበሩት ኢንግሪድ ቤንታኮርት ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደሩ አስታወቁ። ኢንግሪድ በአውሮፓውያኑ 2002 በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ቅስቀሳ እያደረጉ በነበረበት ወቅት በፋርክ አማፂያን ተወስደው ከስድስት ዓመታት በላይ ታግተው ቆይተዋል። ፖለቲከኛዋ በመጪው ግንቦት ወር የሚደረገውን ምርጫ ካሸነፉ ሙስናን እና ድህነትን ለመቅረፍ ቃል ገብተዋል። "በአሁኑ ወቅት ልወዳደር የመጣሁት የጀመርኩትን ለመጨረስ ነው" ሲሉ በሃገሪቱ መዲና ቦጎታ ላሉ ደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል። "እኔ ፊታችሁ የተገኘሁት ፍትህ የማያገኙ 51 ሚሊዮን ኮሎምቢያውያንን መብት ለመጠየቅ ነው፤ ምክንያቱም የምንኖረው ወንጀለኞችን ለመሸለም በተዘጋጀ ስርአት ውስጥ ነው" ሲሉም ተደምጠዋል። የፋርክ አማፅያን ከ50 ዓመታት በላይ ከኮሎምቢያ መንግሥት ጋር ደም አፋሳሽ ጦርነት ያካሄዱ የማርክሲስት ቡድን ነበሩ። በመጨረሻም በአውሮፓውያኑ 2016 የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ተደረሰ። በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ መጪው ሰኔ ለሚደረገው ምርጫ ከ20 በላይ እጩዎች እንደሚወዳደሩ ታውቋል። የቦጎታ የቀድሞ ከንቲባ እና ኤም- 19 የተባለው የአብዮታዊ ሽምቅ ተዋጊ ቡድን አባል የነበሩት ጉስታቮ ፔትሮ በአሁኑ ጊዜ በህዝብ የምርጫ አስተያየት መስረት በግንባር ቀደምትነት እየመሩ ነው። በርካታ ኮሎምቢያውያን በአሁኑ ጊዜ አገሪቱን እየመሩ ካሉትና ተወዳጅነታቸው እያሽቆለቆለ ከመጣው የቀኝ ክንፍ ፖለቲከኛው ፕሬዚዳንት ኢቫን ዱክ የተሻለ አማራጭ አድርገው ያዩዋቸዋል ጉስታቮ ፔትሮን። ፕሬዚዳንት ኢቫን ዱክ በጊዜ ገደብ ምክንያት በዘንድሮው ምርጫ መወዳደር አይችሉም። ኢንግሪድ ቤንታኮርት በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂነት ቢኖራቸውም በአውሮፓውያኑ 2008 በኮሎምቢያ ወታደራዊ ሃይሎች አማካኝነት ከተለቀቁ በኋላ ድምፃቸው አይሰማም። በአሁኑ ወቅትም ፓርቲያቸውን ኦክስጅንን ጨምሮ በተዋቀረው ሴንትሪስት በተባለው ጥምረት እጩነትን ለማሸነፍ ከባድ ፈተና ይገጥማቸዋል። የመጀመሪያ ደረጃ ምርጫ ሁለት ወራት ብቻ በቀረውና ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በግጭት ሰለባ ሆነው በመንግሥት በተመዘገቡባት ሀገር ራሳቸውን እንደ አስታራቂ እጩ አድርገው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ኢንግሪድ ቤንታኮርት በፋርክ አማፂያን የታገቱት ሳን ቪሰንቴ ዴል ካጉዋን በምትባል ከተማ የነበራቸውን የምርጫ ቅስቀሳ አጠናቀው ሲመለሱ መንገድ ላይ ነው። በኮሎምቢያ ጫካ ውስጥ በቆዩባቸው ስድስት ዓመታት ውስጥ በአጋቾቻቸው ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል። በፋርክ አማፂያን ውስጥ የነበሩ ሰርጎ ገብ የኮሎምቢያ ጦር አባላትም ተቀናጅተው ነው በአውሮፓውያኑ 2008 ያስለቀቋቸው። ከተለቀቁም በኋላ በርካታ አመታትን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው በፈረንሳይ ነው የኖሩት። የፋርክ አማጽያን ከ50 ዓመታት በላይ ከመንግሥት ጋር ባደረጉት የእርስ በርስ ጦርነት ከ200 ሺህ ሰዎች በላይ ተገድለዋል። ቡድኑ በአውሮፓውያኑ 2016 የሰላም ስምምነት ከማዕከላዊው መንግሥት ጋር ተፈራርመው የተወሰኑት ወደ ፓርላማ ሲገቡ የቀሩት ደግሞ በጦርነቱ ቀጥለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60034973 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ 33 ሚሊዮን ፓውንድ ያሰባሰቡት የ100 አመቱ ሽማግሌ በኮቪድ-19 ሞቱ | በእንግሊዝ ለጤና ባለሙያዎች ያላቸውን ክብር ለመቸር 33 ሚሊዮን ፓውንድ በማሰባሰብ ከፍተኛ ስም ያተረፉት ካፕቴን ቶም ሙር በመቶ አመታቸው በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው አልፏል። 33 ሚሊዮን ፓውንድ ለአገሪቱ ብሔራዊ ጤና አገልግሎት ወይም ኤንኤችኤስ ማሰባሰብ የቻሉት የ100 አመቱ የዕድሜ ባለፀጋ በባለፈው ሳምንት መጨረሻ እሁድ ከመተንፈሻ እክል ጋር በተያያዘ ቤድፎርድ ወደተባለ ሆስፒታል ተወስደው ነበር። ልጃቸው፣ ሃና ኢንግራም ሙር በባለፉት ሳምንታት በሳንባ ምች ህመም ሲሰቃዩ እንደነበርና በዚህ ሳምንት በኮሮናቫይረስ እንደተያዙ ተናግራለች። ግለሰቡ የ2ኛው የዓለም ጦርነት ተዋጊ ሲሆኑ ከቤታቸው ጓሮ በሚገኘው ሜዳ 100 ዙር በመሮጥም ነው የእርዳታ ገንዘብ ያሰባሰቡት። ይህንንም ያደረጉት ከመቶኛ አመት ልደታቸው በፊት ነው። ልጆቻቸው ሃና ኢንግራም ሙርና ሉሲ ቲየክሴራ እንዳሉት "ውድ አባታችን ካፕቴን ሰር ቶም ሙር መሞታቸውን በታላቅ ሃዘን ነው የምንናገረው" ብለዋል። በመጨረሻው ሰዓትም ከአባታቸው ጎን በመሆናቸው ትልቅ ክብር እንደነበር ገልፀዋል። "ለሰዓታት ያልህ ስለ ልጅነታችን፣ ስለ ውዷ እናታችን ስናወራ ነበር። ረዥም ሰዓት ሳቅን፣ አለቀስን። አባታችን በባለፈው አመት አስቦትና አልሞት የማያውቀው ነገር ተሳክቶለታል። "ብለዋል አክለውም "ምንም እንኳን ለአጭር ወቅት ቢሆን በብዙዎች ልቦና ዘንድ የማይረሳ ነገርን ጥሏል። ለኛ አስደናቂ አባት፣ አያት ነው፤ ሁልጊዜም ቢሆን በልባችን ይኖራል" በማለት ኃዘናቸውን አጋርተዋል። የብሔራዊ ጤና አገልግሎት ለአባታቸው ያደረጉላቸውን እንክብካቤ አድንቀዋል። | ኮሮናቫይረስ፡ 33 ሚሊዮን ፓውንድ ያሰባሰቡት የ100 አመቱ ሽማግሌ በኮቪድ-19 ሞቱ በእንግሊዝ ለጤና ባለሙያዎች ያላቸውን ክብር ለመቸር 33 ሚሊዮን ፓውንድ በማሰባሰብ ከፍተኛ ስም ያተረፉት ካፕቴን ቶም ሙር በመቶ አመታቸው በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው አልፏል። 33 ሚሊዮን ፓውንድ ለአገሪቱ ብሔራዊ ጤና አገልግሎት ወይም ኤንኤችኤስ ማሰባሰብ የቻሉት የ100 አመቱ የዕድሜ ባለፀጋ በባለፈው ሳምንት መጨረሻ እሁድ ከመተንፈሻ እክል ጋር በተያያዘ ቤድፎርድ ወደተባለ ሆስፒታል ተወስደው ነበር። ልጃቸው፣ ሃና ኢንግራም ሙር በባለፉት ሳምንታት በሳንባ ምች ህመም ሲሰቃዩ እንደነበርና በዚህ ሳምንት በኮሮናቫይረስ እንደተያዙ ተናግራለች። ግለሰቡ የ2ኛው የዓለም ጦርነት ተዋጊ ሲሆኑ ከቤታቸው ጓሮ በሚገኘው ሜዳ 100 ዙር በመሮጥም ነው የእርዳታ ገንዘብ ያሰባሰቡት። ይህንንም ያደረጉት ከመቶኛ አመት ልደታቸው በፊት ነው። ልጆቻቸው ሃና ኢንግራም ሙርና ሉሲ ቲየክሴራ እንዳሉት "ውድ አባታችን ካፕቴን ሰር ቶም ሙር መሞታቸውን በታላቅ ሃዘን ነው የምንናገረው" ብለዋል። በመጨረሻው ሰዓትም ከአባታቸው ጎን በመሆናቸው ትልቅ ክብር እንደነበር ገልፀዋል። "ለሰዓታት ያልህ ስለ ልጅነታችን፣ ስለ ውዷ እናታችን ስናወራ ነበር። ረዥም ሰዓት ሳቅን፣ አለቀስን። አባታችን በባለፈው አመት አስቦትና አልሞት የማያውቀው ነገር ተሳክቶለታል። "ብለዋል አክለውም "ምንም እንኳን ለአጭር ወቅት ቢሆን በብዙዎች ልቦና ዘንድ የማይረሳ ነገርን ጥሏል። ለኛ አስደናቂ አባት፣ አያት ነው፤ ሁልጊዜም ቢሆን በልባችን ይኖራል" በማለት ኃዘናቸውን አጋርተዋል። የብሔራዊ ጤና አገልግሎት ለአባታቸው ያደረጉላቸውን እንክብካቤ አድንቀዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55909539 |
2health
| ኮሮናቫይረስ : አዲሱ የቫይረስ ዝርያ በመላው ዓለም ሊሰራጭ ይችላል ተባለ | አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በመላው ዓለም ሊሰራጭ ይችላል ተባለ። ኬንት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው የኮሮናቫይረስ ዝርያ በዓለም ላይ በስርጭቱ ቀዳሚው ሊሆን ይችላል ሲሉ የዩናይትድ ኪንግደም የዘረ መል ክትትል መርሃ ግብር ኃላፊ ገልጸዋል። ኃላፊው ፕሮፌሰር ሻሮን ፒኮክ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አዲሱ ዝርያ "በአገሪቱ የተሰራጨ" ሲሆን "በመላው ዓለም የመሰራጭ ዕድሎችም" አሉት ብለዋል፡፡ በኬንት የተገኘው ዝርያ ከ50 በላይ በሆኑ አገራት ውስጥ ተሰራጭቶ ይገኛል። የኮሮናቫይረስ ዝርያ በደቡብ ምስራቅ እንግሊዝ በጎርጎሮሳዊያኑ መስከረም 2020 ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘ ሲሆን፤ በቀጣይ ወራት በፍጥነት ተስፋፍቶ በጥር ወር በመላው ዩናይትድ ኪንግደም አዲስ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል ምክንያት ሆኗል። ፕሮፌሰር ፒኮክ "በእውነቱ ከሆነ እኛን በመጉዳት ላይ የሚገኘው በከፍተኛ ፍጥነት መተላለፉ ነው" ብለዋል። ለኮሮናቫይረስ የተሠሩ ክትባቶች ቀደም ሲል ለነበረው የቫይረሱ ዙሪያ የተመረቱ ቢሆንም ሳይንቲስቶች አሁንም ቢሆን በአዲሱም ዝርያ ላይ ይሠራሉ ብለው ያምናሉ። ውጤታማነታቸውን ግን ጥሩ ላይሆን ይችላል። በዩናይትድ ኪንግደም ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተፈቀደላቸው ክትባቶች በአገሪቱ ውስጥ ባሉ የቫይረስ ዓይነቶች ላይ በጥሩ ሁኔታ የሚሠሩ ይመስላሉ ብለዋል ፕሮፌሰር ፒኮክ። | ኮሮናቫይረስ : አዲሱ የቫይረስ ዝርያ በመላው ዓለም ሊሰራጭ ይችላል ተባለ አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በመላው ዓለም ሊሰራጭ ይችላል ተባለ። ኬንት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው የኮሮናቫይረስ ዝርያ በዓለም ላይ በስርጭቱ ቀዳሚው ሊሆን ይችላል ሲሉ የዩናይትድ ኪንግደም የዘረ መል ክትትል መርሃ ግብር ኃላፊ ገልጸዋል። ኃላፊው ፕሮፌሰር ሻሮን ፒኮክ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አዲሱ ዝርያ "በአገሪቱ የተሰራጨ" ሲሆን "በመላው ዓለም የመሰራጭ ዕድሎችም" አሉት ብለዋል፡፡ በኬንት የተገኘው ዝርያ ከ50 በላይ በሆኑ አገራት ውስጥ ተሰራጭቶ ይገኛል። የኮሮናቫይረስ ዝርያ በደቡብ ምስራቅ እንግሊዝ በጎርጎሮሳዊያኑ መስከረም 2020 ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘ ሲሆን፤ በቀጣይ ወራት በፍጥነት ተስፋፍቶ በጥር ወር በመላው ዩናይትድ ኪንግደም አዲስ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል ምክንያት ሆኗል። ፕሮፌሰር ፒኮክ "በእውነቱ ከሆነ እኛን በመጉዳት ላይ የሚገኘው በከፍተኛ ፍጥነት መተላለፉ ነው" ብለዋል። ለኮሮናቫይረስ የተሠሩ ክትባቶች ቀደም ሲል ለነበረው የቫይረሱ ዙሪያ የተመረቱ ቢሆንም ሳይንቲስቶች አሁንም ቢሆን በአዲሱም ዝርያ ላይ ይሠራሉ ብለው ያምናሉ። ውጤታማነታቸውን ግን ጥሩ ላይሆን ይችላል። በዩናይትድ ኪንግደም ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተፈቀደላቸው ክትባቶች በአገሪቱ ውስጥ ባሉ የቫይረስ ዓይነቶች ላይ በጥሩ ሁኔታ የሚሠሩ ይመስላሉ ብለዋል ፕሮፌሰር ፒኮክ። | https://www.bbc.com/amharic/news-56027521 |
0business
| የአሜሪካ ኢኮኖሚ በኮሮናቫይረስ ሰበብ በ30 በመቶ ያሽቆለቁላል ተባለ | የአሜሪካ ኢኮኖሚ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከ20 እስከ 30 በመቶ ሊያሽቆለቁል እንደሚችል የፌደራል መንግሥቱ ግምጃ ቤት ሊቀ መንበር ተናገሩ። ጄሮም ፓውል ለሲቢሲ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ እንዳመለከቱት የኢኮኖሚ መቀዛቀዙ በወራት ውስጥ የሚያበቃ ብቻ ሳይሆን እስከ ቀጣዩ የፈረንጆች ዓመትም ሊዘልቅ እንደሚችል ገልጸዋል። ምናልባትም የአገሪቱ ኢኮኖሚ ከወደቀበት ተነስቶ ወደነበረበት ለመመለስ ለወረርሽኙ ክትባት እስኪገኝ ድረስ መቆየት ሊያስፈልገው እንደሚችልም ጠቁመዋል። በዚህም ምክንያት የግምጃ ቤት ሊቀመንበሩ ፓውል ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች ተጨማሪ የኢኮኖሚ ማነቃቂያና እርዳታ እንዲያጸድቁ ጥሪ አቅርበው ነበር። የኮሮናቫይረስ ባስከተለው ጫና ምክንያት ከመጋቢት ወር አጋማሽ ወዲህ ከ36 ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያን ሥራቸውን በማጣታቸው ምክንያት የመንግሥትን ድጋፍ ለማግኘት አመልክተዋል። ጄሮም ፓውል ጨምረውም "የአሁኑ ወቅት ከባድ ችግር ያጋጠመን ጊዜ ነው። ዜጎች ያሉበትን ስቃይ በቃላት ለመግለጽ ያስቸግራል። ቢሆንም ግን ጊዜ ሊወስድ ይችላል እንጂ ኢኮኖሚው ማገገሙ አይቀርም" በማለት እስከ ቀጣይ ዓመት ድረስ ችግሩ ሊቀጥል እንደሚችል አመልክተዋል። እስካሁን ያለው የሥራ አጦች ቁጥር እስከ 25 በመቶ ሊድረስ እንደሚችልና ተጎጂዎቹም "ዝቅተኛ ክፍያ የሚያገኙ ሰዎች" እንደሚሆኑና በተለይ ደግሞ ሴቶች በኢኮኖሚ ቀውሱ ክፉኛ ተጎድተዋል ብለዋል። ነገር ግን የአገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ጤናማ በመሆኑና ወረርሽኙም ከኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውጪ ያጋጠመ "ውጫዊ ክስተት" በመሆኑ አሜሪካ የኢኮኖሚ ድቀት እንደማይገጥማት ተናግረዋል። ሊቀ መንበሩ አክለውም ባለፉት ሦስት ወራት ኢኮኖሚው እስከ 30 በመቶ ቢያሽቆቁልም፤ ወረርሽኙ ለሁለተኛ ዙር ተመልሶ ጉዳት ካላስከተለ በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ውስጥ "በፍጥነት የማገገም ዕድል አለ" ብለዋል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ የተመታችው አሜሪካ ከዓለም አገራት ሁሉ የላቀ ቁጥር ያለቸው ሰዎች በሽታው ከመያዛቸው በተጨማሪ ከፍተኛውን የሟቾች ቁጥር መዝግባለች። በአንዳንድ ግዛቶቿ በእንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው ዕገደ ከመላላቱ ጋር ተያይዞ በሸታው ተመልሶ ለሁለተኛ ጊዜ ሊያገረሽ ይችላል የሚል ስጋት ተፈጥሯል። | የአሜሪካ ኢኮኖሚ በኮሮናቫይረስ ሰበብ በ30 በመቶ ያሽቆለቁላል ተባለ የአሜሪካ ኢኮኖሚ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከ20 እስከ 30 በመቶ ሊያሽቆለቁል እንደሚችል የፌደራል መንግሥቱ ግምጃ ቤት ሊቀ መንበር ተናገሩ። ጄሮም ፓውል ለሲቢሲ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ እንዳመለከቱት የኢኮኖሚ መቀዛቀዙ በወራት ውስጥ የሚያበቃ ብቻ ሳይሆን እስከ ቀጣዩ የፈረንጆች ዓመትም ሊዘልቅ እንደሚችል ገልጸዋል። ምናልባትም የአገሪቱ ኢኮኖሚ ከወደቀበት ተነስቶ ወደነበረበት ለመመለስ ለወረርሽኙ ክትባት እስኪገኝ ድረስ መቆየት ሊያስፈልገው እንደሚችልም ጠቁመዋል። በዚህም ምክንያት የግምጃ ቤት ሊቀመንበሩ ፓውል ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች ተጨማሪ የኢኮኖሚ ማነቃቂያና እርዳታ እንዲያጸድቁ ጥሪ አቅርበው ነበር። የኮሮናቫይረስ ባስከተለው ጫና ምክንያት ከመጋቢት ወር አጋማሽ ወዲህ ከ36 ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያን ሥራቸውን በማጣታቸው ምክንያት የመንግሥትን ድጋፍ ለማግኘት አመልክተዋል። ጄሮም ፓውል ጨምረውም "የአሁኑ ወቅት ከባድ ችግር ያጋጠመን ጊዜ ነው። ዜጎች ያሉበትን ስቃይ በቃላት ለመግለጽ ያስቸግራል። ቢሆንም ግን ጊዜ ሊወስድ ይችላል እንጂ ኢኮኖሚው ማገገሙ አይቀርም" በማለት እስከ ቀጣይ ዓመት ድረስ ችግሩ ሊቀጥል እንደሚችል አመልክተዋል። እስካሁን ያለው የሥራ አጦች ቁጥር እስከ 25 በመቶ ሊድረስ እንደሚችልና ተጎጂዎቹም "ዝቅተኛ ክፍያ የሚያገኙ ሰዎች" እንደሚሆኑና በተለይ ደግሞ ሴቶች በኢኮኖሚ ቀውሱ ክፉኛ ተጎድተዋል ብለዋል። ነገር ግን የአገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ጤናማ በመሆኑና ወረርሽኙም ከኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውጪ ያጋጠመ "ውጫዊ ክስተት" በመሆኑ አሜሪካ የኢኮኖሚ ድቀት እንደማይገጥማት ተናግረዋል። ሊቀ መንበሩ አክለውም ባለፉት ሦስት ወራት ኢኮኖሚው እስከ 30 በመቶ ቢያሽቆቁልም፤ ወረርሽኙ ለሁለተኛ ዙር ተመልሶ ጉዳት ካላስከተለ በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ውስጥ "በፍጥነት የማገገም ዕድል አለ" ብለዋል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ የተመታችው አሜሪካ ከዓለም አገራት ሁሉ የላቀ ቁጥር ያለቸው ሰዎች በሽታው ከመያዛቸው በተጨማሪ ከፍተኛውን የሟቾች ቁጥር መዝግባለች። በአንዳንድ ግዛቶቿ በእንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው ዕገደ ከመላላቱ ጋር ተያይዞ በሸታው ተመልሶ ለሁለተኛ ጊዜ ሊያገረሽ ይችላል የሚል ስጋት ተፈጥሯል። | https://www.bbc.com/amharic/news-52703735 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ኩባ የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማምረት የምታደርገው ጥረት ይሳካ ይሆን? | በኩባዋ ዋና ከተማ ሃቫና የሚገኘው ፊንሌይ የክትባት ኢንስቲትዩት ምናልባት ከሌሎች የዓለማችን ማዕከላት አንጻር ሲታይ ያረጀና ጊዜ ያለፈበት ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን በዚህ ማዕከል የሚሰራው የምርምር ሥራ እጅግ ዘመናዊ ነው። የአገሪቱ ከፍተኛ ተመራማሪዎች እረፍት አልባ ረጅም ፈረቃዎችን ጭምር በመስራት ለኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ መፍትሄ ለማግኘት ደፋ ቀና እያሉ ነው። የክትባቱ ስም 'ሶቤሬና 2' የሚባል ሲሆን በኩባ ተመራማሪዎች ኩባ ውስጥ የተሰራ ነው። ይህ ክትባት በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በጎ ፈቃደኞች ላይ ይሞከራል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ባለፉት ሳምንታት በተደረጉ ክሊኒካዊ ሙከራዎች በጣም አመርቂ የሚባል ውጤት የተመዘገበ ሲሆን ይህ አገሪቱ ክትባቱን ለማግኘት በምታደርገው ጥረት ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የኢንስቲትይቱ ዳይሬክተር ዶክተር ቪሴንቴ ቬሬዝ ቤንኮሞ ገልጸዋል። በኩባ መንግሥት እቅድ መሰረት ክትባቱ ክሊኒካዊ ሙከራውን ከጨረሰ በኋላ በያዝነው የአውሮፓውያኑ ዓመት መጨረሻ አካባቢ ለሁሉም ዜጎች መሰጠት ይጀመራል። "የእኛ እቅድ በመጀመሪያ ሕዝባችንን መከተብ ነው'' ይላሉ ዶክተር ቪሴንቴ። "ከሕዝባችን በኋላ ምናልባት ለሌሎች አገራት መላክ ልንጀምር እንችላለን። ከ2021 መጨረሻ በኋላ ምናልባት 100 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን አምርተን ሕዝባችን ሙሉ በሙሉ ለመከተብ እቅድ ይዘናል።" ይህ ክትባት የአሜሪካም ሆነ የየትኛውም አገር እርዳታ አልተደረገለትም። ኩባ በባዮቴክኖሎጂ ከ30 ዓመታት በላይ ልምድ ያላት አገር እንደመሆኗ ይህ ምንም የሚገርም ነገር አይደለም። በ1980ዎቹ መጨረሻ አካባቢ የኩባ ሳይንቲስቶች ለማጅራት ገትር ቢ (ሚኒንጃይተስ) ክትባት ካመረቱ የመጀመሪያዎቹ ሲሆኑ የወቅቱ የአገሪቱ መሪ ፊደል ካስትሮ መሰል ሥራዎችን ለማበረታታት ነበር ፊንሌይ የክትባት ኢንስቲትዩት እንዲቋቋም ያደረጉት። በአሜሪካ መድኃኒት አምራች ኩባንያዎች የሚሰሩ መድኃኒቶች ወደ ኩባ እንዳይገቡ ሲደረግ አገሪቱ በራሷ መንገድ መድኃኒቶቹን ማምረት ትችላለች በማለት ፊደል ካስትሮ ይከራከሩ ነበር። ነገር ግን አሁን ባለው ቴክኖሎጂ እና ዘመናዊ አሰራር እንኳን ያለ ሌሎች አገራት ድጋፍና እርዳታ 100 ሚሊዮን የክትባት ብልቃጦችን አምርቶ ሕዝቡን መከተብ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። "ክትባቱን በማምረት ሂደቱ ላይ ግንኙነት የፈጠርነው ከአውሮፓ አገራትና እና ካናዳ ጋር ነው። ከጣልያን እና ፈረንሳይ የመጡ ተመራማሪዎችም በሂደቱ ላይ ይሳተፋሉ" ብለዋል ዶክተር ቪሴንቴ ቬሬዝ። አክለውም "በሚያሳዝን ሁኔታ እስካሁን ድረስ ምንም አይነት የአሜሪካ ተሳትፎ የለም። ምናልባት ወደፊት በመሰል ሂደቶች ላይ ትብብር ሊኖረን እንደሚችል ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል። እንደ ፓን አሜሪካን ሄልዝ ኦርጋናይዜሽን መሰል ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ኩባ ለኮሮረናቫይረስ የሚሆነውን ክትባት በማግኘት የመጀመሪያዋ የላቲን አሜሪካ አገር እንደምትሆን ተስፋ ያደርጋሉ። "ኩባ ክትባቱን እንደምታገኝ ተስፋ እናደርጋለን'' ይላሉ በኩባ የድርጅቱ ተወካይ ዶክተር ሆዜ ሞቫ። ''የሶብሬና 2 ክትባት ሁለተኛ ደረጃ ሙከራ ውጤትን ከሰማን በኋላ ሂደቱን በቅርበት ስንከታተለው ነበር። ካለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ ኩባ የክትባቱን ውጤታማነትና ደኅንነት ስትመረምር እንደነበርም እናውቃለን።'' በአሁኑ ጊዜ በክትባቱ ዙሪያ ያለው ጉጉት ትልቅ ነው። በመጀመሪያ አገሪቱ በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ነው። ወረርሽኙ በጀመረበት የመጀመሪያዎቹ ወራት ውስጥ በየቀኑ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ የነበረ ሲሆን ከብራዚልና ሜክሲኮ ጋር ሲነጻጸር ግን ቁጥሩ ብዙም አስፈሪ አይደለም። ነገር ግን የአገሪቱን የጤና ሥርዓት በእጅጉ ፈትኖታል። ባሳለፍነው የአውሮፓውያኑ ዓመት አጋማሽ ላይ ኩባ የወረርሽኙን ስርጭት መግታት ችላ ነበር። በዋነኛነት አየር ማረፊያዎችን በመዝጋትና የማኅበረሰቡን እንቅስቃሴ በመገደብ ነበር ይህንን ማሳካት የቻለችው። ሐምሌ እና ነሐሴ ላይ በጣም ዝቅተኛ የሚባል ስርጭትና ሞት ነበር የተመዘገበው። የፓን አሜሪካን ሄልዝ ኦርጋናይዜሽን ተወካዩ በአሁኑ ጊዜ ያለው የቫይረሱ ስርጭት መቆጣጠር ከማይቻልበት ደረጃ ላይ አልደረሰም ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ኩባ ውስጥ በወረርሽኙ ምክንያት በርካታ እንቅስቃሴዎች በመገደባቸው በጣም ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ መላሸቅ አጋጥሟታል። እንደውም ከቀዝቃዛው ጦርነት በኋላ ከፍተኛው የኢኮኖሚ መድቀቅ ነው እየተባለ ነው። ክትባቱ በአገር ውስጥ የሚገኝ ከሆነ ደግሞ ሕዝቡን ከመክተብ ባለፈ ከሽያጭ ሊገኝ የሚችለው ገቢ ኢኮኖሚውን በከፍተኛ ሁኔታ ሊረዳው ይችላል ተብሎ ይታመናል። በተጨማሪም ከትባቱን ከሌሎች አገራት ማስመጣት ሊያስከትለው የሚችለውን ወጪ ይቀንሳል። ኮሮረናቫይረስን ተከትሎ በኩባ በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ባለፈው ዓመት ብቻ ኢኮኖሚው 11 በመቶ ኪሳራ አጋጥሞታል። በተጨማሪም የምግብ ሱቆችና ሱፐር ማርኬቶች አካባቢ ከፍተኛ ሰልፍና ግፊያም ታይቷል። በዚህ ወቅት ሁሉም ህጻናት ከትምህርት ቤት ቀርተዋል፣ የንግድ እንቅስቃሴዎች በእጅጉ ተቀዛቅዘዋል፣ የእንቅስቃሴ ገደቦችም ቢሆን የዜጎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ አስቸጋሪ አድርጎታል። ስለዚህ የክትባቱ ዜና በርካቶች በጉጉት እንዲጠብቁት አድርጓቸዋል። የዚህ ክትባት ውጤታማ መሆን የዜጎችን ጤንነት ከመጠበቅ ባለፈ ለጎረቤት አገራት ከሚደረገው ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ኢኮኖሚውን እንደሚያነቃቃው ይታመናል። | ኮሮናቫይረስ፡ ኩባ የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማምረት የምታደርገው ጥረት ይሳካ ይሆን? በኩባዋ ዋና ከተማ ሃቫና የሚገኘው ፊንሌይ የክትባት ኢንስቲትዩት ምናልባት ከሌሎች የዓለማችን ማዕከላት አንጻር ሲታይ ያረጀና ጊዜ ያለፈበት ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን በዚህ ማዕከል የሚሰራው የምርምር ሥራ እጅግ ዘመናዊ ነው። የአገሪቱ ከፍተኛ ተመራማሪዎች እረፍት አልባ ረጅም ፈረቃዎችን ጭምር በመስራት ለኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ መፍትሄ ለማግኘት ደፋ ቀና እያሉ ነው። የክትባቱ ስም 'ሶቤሬና 2' የሚባል ሲሆን በኩባ ተመራማሪዎች ኩባ ውስጥ የተሰራ ነው። ይህ ክትባት በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በጎ ፈቃደኞች ላይ ይሞከራል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ባለፉት ሳምንታት በተደረጉ ክሊኒካዊ ሙከራዎች በጣም አመርቂ የሚባል ውጤት የተመዘገበ ሲሆን ይህ አገሪቱ ክትባቱን ለማግኘት በምታደርገው ጥረት ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የኢንስቲትይቱ ዳይሬክተር ዶክተር ቪሴንቴ ቬሬዝ ቤንኮሞ ገልጸዋል። በኩባ መንግሥት እቅድ መሰረት ክትባቱ ክሊኒካዊ ሙከራውን ከጨረሰ በኋላ በያዝነው የአውሮፓውያኑ ዓመት መጨረሻ አካባቢ ለሁሉም ዜጎች መሰጠት ይጀመራል። "የእኛ እቅድ በመጀመሪያ ሕዝባችንን መከተብ ነው'' ይላሉ ዶክተር ቪሴንቴ። "ከሕዝባችን በኋላ ምናልባት ለሌሎች አገራት መላክ ልንጀምር እንችላለን። ከ2021 መጨረሻ በኋላ ምናልባት 100 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን አምርተን ሕዝባችን ሙሉ በሙሉ ለመከተብ እቅድ ይዘናል።" ይህ ክትባት የአሜሪካም ሆነ የየትኛውም አገር እርዳታ አልተደረገለትም። ኩባ በባዮቴክኖሎጂ ከ30 ዓመታት በላይ ልምድ ያላት አገር እንደመሆኗ ይህ ምንም የሚገርም ነገር አይደለም። በ1980ዎቹ መጨረሻ አካባቢ የኩባ ሳይንቲስቶች ለማጅራት ገትር ቢ (ሚኒንጃይተስ) ክትባት ካመረቱ የመጀመሪያዎቹ ሲሆኑ የወቅቱ የአገሪቱ መሪ ፊደል ካስትሮ መሰል ሥራዎችን ለማበረታታት ነበር ፊንሌይ የክትባት ኢንስቲትዩት እንዲቋቋም ያደረጉት። በአሜሪካ መድኃኒት አምራች ኩባንያዎች የሚሰሩ መድኃኒቶች ወደ ኩባ እንዳይገቡ ሲደረግ አገሪቱ በራሷ መንገድ መድኃኒቶቹን ማምረት ትችላለች በማለት ፊደል ካስትሮ ይከራከሩ ነበር። ነገር ግን አሁን ባለው ቴክኖሎጂ እና ዘመናዊ አሰራር እንኳን ያለ ሌሎች አገራት ድጋፍና እርዳታ 100 ሚሊዮን የክትባት ብልቃጦችን አምርቶ ሕዝቡን መከተብ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። "ክትባቱን በማምረት ሂደቱ ላይ ግንኙነት የፈጠርነው ከአውሮፓ አገራትና እና ካናዳ ጋር ነው። ከጣልያን እና ፈረንሳይ የመጡ ተመራማሪዎችም በሂደቱ ላይ ይሳተፋሉ" ብለዋል ዶክተር ቪሴንቴ ቬሬዝ። አክለውም "በሚያሳዝን ሁኔታ እስካሁን ድረስ ምንም አይነት የአሜሪካ ተሳትፎ የለም። ምናልባት ወደፊት በመሰል ሂደቶች ላይ ትብብር ሊኖረን እንደሚችል ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል። እንደ ፓን አሜሪካን ሄልዝ ኦርጋናይዜሽን መሰል ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ኩባ ለኮሮረናቫይረስ የሚሆነውን ክትባት በማግኘት የመጀመሪያዋ የላቲን አሜሪካ አገር እንደምትሆን ተስፋ ያደርጋሉ። "ኩባ ክትባቱን እንደምታገኝ ተስፋ እናደርጋለን'' ይላሉ በኩባ የድርጅቱ ተወካይ ዶክተር ሆዜ ሞቫ። ''የሶብሬና 2 ክትባት ሁለተኛ ደረጃ ሙከራ ውጤትን ከሰማን በኋላ ሂደቱን በቅርበት ስንከታተለው ነበር። ካለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ ኩባ የክትባቱን ውጤታማነትና ደኅንነት ስትመረምር እንደነበርም እናውቃለን።'' በአሁኑ ጊዜ በክትባቱ ዙሪያ ያለው ጉጉት ትልቅ ነው። በመጀመሪያ አገሪቱ በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ነው። ወረርሽኙ በጀመረበት የመጀመሪያዎቹ ወራት ውስጥ በየቀኑ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ የነበረ ሲሆን ከብራዚልና ሜክሲኮ ጋር ሲነጻጸር ግን ቁጥሩ ብዙም አስፈሪ አይደለም። ነገር ግን የአገሪቱን የጤና ሥርዓት በእጅጉ ፈትኖታል። ባሳለፍነው የአውሮፓውያኑ ዓመት አጋማሽ ላይ ኩባ የወረርሽኙን ስርጭት መግታት ችላ ነበር። በዋነኛነት አየር ማረፊያዎችን በመዝጋትና የማኅበረሰቡን እንቅስቃሴ በመገደብ ነበር ይህንን ማሳካት የቻለችው። ሐምሌ እና ነሐሴ ላይ በጣም ዝቅተኛ የሚባል ስርጭትና ሞት ነበር የተመዘገበው። የፓን አሜሪካን ሄልዝ ኦርጋናይዜሽን ተወካዩ በአሁኑ ጊዜ ያለው የቫይረሱ ስርጭት መቆጣጠር ከማይቻልበት ደረጃ ላይ አልደረሰም ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ኩባ ውስጥ በወረርሽኙ ምክንያት በርካታ እንቅስቃሴዎች በመገደባቸው በጣም ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ መላሸቅ አጋጥሟታል። እንደውም ከቀዝቃዛው ጦርነት በኋላ ከፍተኛው የኢኮኖሚ መድቀቅ ነው እየተባለ ነው። ክትባቱ በአገር ውስጥ የሚገኝ ከሆነ ደግሞ ሕዝቡን ከመክተብ ባለፈ ከሽያጭ ሊገኝ የሚችለው ገቢ ኢኮኖሚውን በከፍተኛ ሁኔታ ሊረዳው ይችላል ተብሎ ይታመናል። በተጨማሪም ከትባቱን ከሌሎች አገራት ማስመጣት ሊያስከትለው የሚችለውን ወጪ ይቀንሳል። ኮሮረናቫይረስን ተከትሎ በኩባ በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ባለፈው ዓመት ብቻ ኢኮኖሚው 11 በመቶ ኪሳራ አጋጥሞታል። በተጨማሪም የምግብ ሱቆችና ሱፐር ማርኬቶች አካባቢ ከፍተኛ ሰልፍና ግፊያም ታይቷል። በዚህ ወቅት ሁሉም ህጻናት ከትምህርት ቤት ቀርተዋል፣ የንግድ እንቅስቃሴዎች በእጅጉ ተቀዛቅዘዋል፣ የእንቅስቃሴ ገደቦችም ቢሆን የዜጎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ አስቸጋሪ አድርጎታል። ስለዚህ የክትባቱ ዜና በርካቶች በጉጉት እንዲጠብቁት አድርጓቸዋል። የዚህ ክትባት ውጤታማ መሆን የዜጎችን ጤንነት ከመጠበቅ ባለፈ ለጎረቤት አገራት ከሚደረገው ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ኢኮኖሚውን እንደሚያነቃቃው ይታመናል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56088539 |
3politics
| ከ‘ትግራይን እከላከላለሁ’ እስከ ‘ናይሮቢን እቆጣጠራለሁ’ የሚሉት አወዛጋቢው ጄኔራል | የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ እና የኡጋንዳ ጦር ከፍተኛ መኮንን የሆኑት ሌ/ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ አነጋጋሪ የሆኑ አስተያየቶችን መስጠታቸውን ቀጥለዋል። የኡጋንዳ የምድር ጦር አዛዥ የሆኑት ሌ/ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ አገራትንና መሪዎችን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በመጻፍ ቅሬታን ሲፈጥሩ ቆይተዋል። በተለይ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነትን ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሯቸው መልዕክቶች ምክንያት በኢትዮጵያውያን ዘንድ መነጋገሪያ ለመሆን በቅተዋል። ሌ/ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ ከሁለት ቀናት በፊት በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ላይ፣ “. . . ትግራይን እከላከላለሁ” ብለው ካሰፈሩ ከሰዓታት በኋላ “ዳግማዊ ሚኒሊክ አያታችን ናቸው” በማለት ኢትዮጵያን የተመለከተ ሌላ ትዊት ለጥፈው ነበር። በአፍሪካ በሥልጣን ላይ ለረጅም ዓመታት በመቆየት ከሚጠቀሱት አንዱ የሆኑትን አባታቸውን ዩዌሪ ሙሴቬኒን በመተካት ቀጣይ የኡጋንዳ መሪ ሊሆኑ ይችላሉ የሚባሉት የጦር መሪ ሰኞ ዕለት በኬንያውያን ዘንድ መነጋገሪያ ሆነዋል። ጄኔራሉ ምንም ባልተፈጠረበት ድንገት ብድግ ብለው “እኔ እና ሠራዊቴ የኬንያን መዲና ናይሮቢ ለመያዝ ሁለት ሳምንታት ይበቃናል” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል። ሌ/ጄኔራል ካይኒሩጋባ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ስለ ኢትዮጵያ እና ኬንያ እያነሱ መጻፋቸው ከአገራቸው መንግሥት አቋም ጋር የሚያያዝ ስለመሆኑ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም አነጋጋሪ በመሆን ትኩረትን ስበዋል። ይህንንም ተከትሎ የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማክሰኞ መስከረም 24/2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ላይ የጄኔራሉን የትዊተር መልዕክት በቀጥታ ሳይጠቅስ፣ ከጎረቤት ኬንያ ጋር ለሚኖር ሰላም እና ትብብር ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል። እሁድ መስከረም 22/2015 ዓ.ም. በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሳፈሩት ጽሑፍ፤ “ትግራይ ሁሌም በልቤ አለች! ትግራይን እንድወድ እና እንድከላከል ከፈጣሪዬ ከእየሱስ ክርስቶስ የመጣ ትዕዛዝ ነው” ብለዋል። በተመሳሳይ ዕለት ከሰዓታት በኋላ ደግሞ ጄኔራሉ ኢትዮጵያን በተመለከተ ባሰፈሩት ሌላኛው ጽሑፍ፤ “ዳግማዊ ሚኒሊክ አያታችን ናቸው። ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ አካል ናት። እንድትወድም አንፈቅድም። ሁሉንም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንወዳለን!” ሲሉ ጽፈዋል። የ48 ዓመቱ ጎልማሳ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያን የተመለከተ በተለይ ደግሞ ከትግራይ ጋር የተያያዙ አስተያየቶችን ሲሰጡ ነበር። ጄኔራሉ የኢትዮጵያው የእርስ በእርስ ጦርነት አንድ ዓመት በደፈነበት ጥቅምት 2014 ዓ.ም. ላይ የትግራይ ኃይሎችን ደግፈው ትዊት አድርገው ነበር። “የትግራይ መከላከያ ኃይሎች . . . የቆማችሁበትን ዓላማ እደግፋለሁ። የትግራይ እህቶቻችንን የደፈሩ እና ወንድሞቻችንን የገደሉ መቀጣት አለባቸው” ሲሉ ጽፈው ነበር። ይህን የሌ/ጀነራል ሙሆዚ ትዊት ተከትሎ የኡጋንዳ መንግሥት አስተያየቱ የጄኔራሉ እንጂ የጦሩን አቋም አይወክልም የሚል ማስተባበያን ሰጥቶ ነበር። በተጨማሪም ጄኔራሉ ከአገራቸው ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ከጥቂት ወራት በፊት ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋርም ተገናኝተው ነበር። የኡጋንዳ የምድር ጦር አዛዥ የሆኑት ሌ/ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ የጎረቤት አገር ኬንያ መዲና ናይሮቢን በተመለከተ በትዊተር ገጻቸው ላይ የለጠፉት ሐሳብ ስላቅ ይሁን ጽኑ ፍላጎት ኬንያውያን ያስደሰተ አልነበረም። ጄኔራሉ “እኔ እና ሠራዊቴ ናይሮቢን ለመያዝ ሁለት ሳምንት ቢወስድብን ነው” ብለዋል። ቀጠል አድርገውም “ጦራችን ናይሮቢን ከቆጣጠረ በኋላ የት መኖር መጀመር አለብኝ? ዌስትላንድስ ወይስ ሪቨርሳይድ?” ሲሉ የናይሮቢ አካባቢዎችን በመጥቀስ ትዊት አድርገዋል። ይህ የጄኔራሉ ትዊት ግን ኬንያውያንን ያስቆጣ ሆኗል። አንዳንዶች ሙሴቪኒ የሰፋቸውን ሙሉ ልብስ ለብሰው የሚያሳይ ምስል በማያያዝ “ቅደሚያ የአባትህን ልብ ሰፊ ተቆጣጠር” በሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ከሰኞ ጀምሮ ኬንያውያን በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ የጄኔራሉን ጉዳይ በማንሳት ትችት እየሰነዘሩ ሲሆን፣ አንዳንዶችም ጄኔራሉ እንደሚባለው የአባታቸውን ሥልጣን የሚረከቡ ከሆነ ለአገራቸው ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ ጽፈዋል። ሌሎች ደግሞ በኬንያ እና ኡጋንዳ መካከል ያለውን ዴሞክራሲ በማነጻጸር የሙሴቪኒ ቤተሰብ ኡጋንዳውያንን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ነፍገዋል ሲሉ ተችተዋል። ይህን የጄኔራሉን አስተያየት ተከትሎ የኬንያ መንግሥትም ሆነ የኡጋንዳ ባለሥልጣንት በይፋ ያሉት ነገር የለም። ሌ/ጄኔራል ካይኒሩጋባ ኬንያን በተመለከተ ሌላ ጸሁፋቸው ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ያለኝ ብቸኛው ችግር ለሦስተኛ ዙር አለመወዳደራቸው ነው ብሏል። በኬንያ ሕገ-መንግሥት መሠረት አንድ ፕሬዝዳንት አገር መምራት የሚችለው ለሁለት የሥልጣን ዘመን ብቻ ነው። በዚህ መሠረት ኡሁሩ ከሁለት ወራት በፊት በተካሄደው ምርጫ ሳይሳተፉ ሥልጣን አስረክበው መንበራቸውን ለቀዋል። ሌ/ጄኔራል ካይኒሩጋባ ግን “ከተወዳጁ ትልቁ ወንድሜ ጋር ያለኝ ብቸኛ ችግር ለሦስተኛ ዙር አለመወዳደሩ ነው። በቀላሉ ማሸነፍ እንችል ነበር” ሲሉ ጽፈዋል። የምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ የምድር ጦር አዛዡ በሌላኛው አነጋገሪ ጽሑፋቸው ደግሞ ቀጣይዋን የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር የተመለከተ ነው። ባለፈው ሳምንት በተደረገ ምርጫ ፓርቲያቸው በማሸነፉ የጣሊያን መሪ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ሰፊ ግምት ለተሰጣቸው ሴት ፖለቲከኛ ጂዮርጂ ሜሎኒ ጥሎሽ የመስጠት ፍላጎት እንዳላቸው አመልክተዋል። “ለቀጣይዋ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ስንት ከብቶችን ልትሰጡ ትችላለችሁ?” ሲሉ ትዊተር ላይ የጠየቁት ጄኔራሉ፤ “አውሮፓውያን ለሚወዷቸው ሴቶች አበባ ይሰጣሉ፤ በአገሬ ባህል ግን ለምንወዳቸው ሴቶች የምንሰጠው ከብቶችን ነው” በማለት ባለ ግዙፍ ቀንድ ከብቶችን ምስል አያይዘው ትዊተር ላይ ለጥፈዋል። ቀደም ብሎ ደግሞ በኡጋንዳ የጣሊያን አምባሳደር የጥሎሽ ዋጋ እንዲደራደሩ ሽማግሌ አድርጌ መርጫለሁ ሲሉ ጽፈው ነበር። አነጋጋሪው ጄኔራል በኡጋንዳ ጦር ሠራዊት ውስጥ ከፍተኛ ሥልጣን ያላቸው ሲሆን፣ የሚሰጧቸው አስተያየቶችም መነጋገሪያ ከመሆን አልፈው ቁጣን እያስከተሉ ነው። ሌ/ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ በተለይ በትዊተር ላይ የሚያሰፍሯቸው አነጋጋሪ እና አወዛጋቢ ፖለቲካዊ አስተያየቶች፣ በርካታ ተከታዮችን እያፈራለቸው ነው። ከዚህ አንጻር ግባቸው መነጋገሪያ በመሆን በርካታ ተከታዮችን ማግኘት ነው የሚሉ ሰዎች አሉ። የኡጋንዳ መንግሥት ጄኔራሉ ትዊተር ላይ በሚያሰፍሯቸው መልዕክቶች ዙሪያ ብዙ ጊዜ ዝምታን የሚመርጥ ሲሆን፣ አንዳንድ ጊዜ ግን የጄኔራሉ ሐሳብ የአገሪቱ መንግሥት አቋም ሳይሆን የግለሰቡ አስተያየት ነው በማለት ያስተባብላል። አሁንም ኬንያውያን ከጄኔራሉ ሳይሆን የኡጋንዳ መንግሥት በይፋ የጄኔራሉን ጽሁፍ የሚያስተባብል ምላሽ እንዲሰጥ እንደሚፈልጉ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየጠየቁ የነበሩ ሲሆን ይፋዊ መግለጫም ወጥቷል። የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጄኔራሉን የትዊተር መልዕክት ሳይጠቅስ በተዘዋዋሪ የተሰነዘረው ሐሳብ የመንግሥት እንዳልሆነ ገልጿል። በዚህም የኡጋንዳ መንግሥት ከየትኛውም አገር ጋር የሚኖረው ግንኙነትን በተመለከተ ከማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሚገኙ እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያዎች በኩል በሚተላለፉ መልዕክቶች አማካይነት አይሆኑም ብሏል። ጨምሮም ኡጋንዳ ከኬንያ መንግሥት እና ሕዝብ ጋር ላለው ግንኙነትን ከፍተኛ ዋጋ እንደምትሰጥና ይህም የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንደምትፈልግ ገልጿል። ጄኔራሉ ግን በትዊተር ላይ ያሰፈሩት መልዕክት የቀሰቀሰውን ቁጣ ተከትሎ ማስተባበያ፣ ምላሽ ወይም ማብራሪያ ሳይሰጡ ሌሎች ጉዳዮችን በማንሳት ትዊት ማድረግ መቀጠላቸው በርካቶችን ግራ አጋብቷል። | ከ‘ትግራይን እከላከላለሁ’ እስከ ‘ናይሮቢን እቆጣጠራለሁ’ የሚሉት አወዛጋቢው ጄኔራል የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ እና የኡጋንዳ ጦር ከፍተኛ መኮንን የሆኑት ሌ/ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ አነጋጋሪ የሆኑ አስተያየቶችን መስጠታቸውን ቀጥለዋል። የኡጋንዳ የምድር ጦር አዛዥ የሆኑት ሌ/ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ አገራትንና መሪዎችን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በመጻፍ ቅሬታን ሲፈጥሩ ቆይተዋል። በተለይ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነትን ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሯቸው መልዕክቶች ምክንያት በኢትዮጵያውያን ዘንድ መነጋገሪያ ለመሆን በቅተዋል። ሌ/ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ ከሁለት ቀናት በፊት በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ላይ፣ “. . . ትግራይን እከላከላለሁ” ብለው ካሰፈሩ ከሰዓታት በኋላ “ዳግማዊ ሚኒሊክ አያታችን ናቸው” በማለት ኢትዮጵያን የተመለከተ ሌላ ትዊት ለጥፈው ነበር። በአፍሪካ በሥልጣን ላይ ለረጅም ዓመታት በመቆየት ከሚጠቀሱት አንዱ የሆኑትን አባታቸውን ዩዌሪ ሙሴቬኒን በመተካት ቀጣይ የኡጋንዳ መሪ ሊሆኑ ይችላሉ የሚባሉት የጦር መሪ ሰኞ ዕለት በኬንያውያን ዘንድ መነጋገሪያ ሆነዋል። ጄኔራሉ ምንም ባልተፈጠረበት ድንገት ብድግ ብለው “እኔ እና ሠራዊቴ የኬንያን መዲና ናይሮቢ ለመያዝ ሁለት ሳምንታት ይበቃናል” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል። ሌ/ጄኔራል ካይኒሩጋባ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ስለ ኢትዮጵያ እና ኬንያ እያነሱ መጻፋቸው ከአገራቸው መንግሥት አቋም ጋር የሚያያዝ ስለመሆኑ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም አነጋጋሪ በመሆን ትኩረትን ስበዋል። ይህንንም ተከትሎ የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማክሰኞ መስከረም 24/2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ላይ የጄኔራሉን የትዊተር መልዕክት በቀጥታ ሳይጠቅስ፣ ከጎረቤት ኬንያ ጋር ለሚኖር ሰላም እና ትብብር ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል። እሁድ መስከረም 22/2015 ዓ.ም. በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሳፈሩት ጽሑፍ፤ “ትግራይ ሁሌም በልቤ አለች! ትግራይን እንድወድ እና እንድከላከል ከፈጣሪዬ ከእየሱስ ክርስቶስ የመጣ ትዕዛዝ ነው” ብለዋል። በተመሳሳይ ዕለት ከሰዓታት በኋላ ደግሞ ጄኔራሉ ኢትዮጵያን በተመለከተ ባሰፈሩት ሌላኛው ጽሑፍ፤ “ዳግማዊ ሚኒሊክ አያታችን ናቸው። ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ አካል ናት። እንድትወድም አንፈቅድም። ሁሉንም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንወዳለን!” ሲሉ ጽፈዋል። የ48 ዓመቱ ጎልማሳ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያን የተመለከተ በተለይ ደግሞ ከትግራይ ጋር የተያያዙ አስተያየቶችን ሲሰጡ ነበር። ጄኔራሉ የኢትዮጵያው የእርስ በእርስ ጦርነት አንድ ዓመት በደፈነበት ጥቅምት 2014 ዓ.ም. ላይ የትግራይ ኃይሎችን ደግፈው ትዊት አድርገው ነበር። “የትግራይ መከላከያ ኃይሎች . . . የቆማችሁበትን ዓላማ እደግፋለሁ። የትግራይ እህቶቻችንን የደፈሩ እና ወንድሞቻችንን የገደሉ መቀጣት አለባቸው” ሲሉ ጽፈው ነበር። ይህን የሌ/ጀነራል ሙሆዚ ትዊት ተከትሎ የኡጋንዳ መንግሥት አስተያየቱ የጄኔራሉ እንጂ የጦሩን አቋም አይወክልም የሚል ማስተባበያን ሰጥቶ ነበር። በተጨማሪም ጄኔራሉ ከአገራቸው ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ከጥቂት ወራት በፊት ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋርም ተገናኝተው ነበር። የኡጋንዳ የምድር ጦር አዛዥ የሆኑት ሌ/ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ የጎረቤት አገር ኬንያ መዲና ናይሮቢን በተመለከተ በትዊተር ገጻቸው ላይ የለጠፉት ሐሳብ ስላቅ ይሁን ጽኑ ፍላጎት ኬንያውያን ያስደሰተ አልነበረም። ጄኔራሉ “እኔ እና ሠራዊቴ ናይሮቢን ለመያዝ ሁለት ሳምንት ቢወስድብን ነው” ብለዋል። ቀጠል አድርገውም “ጦራችን ናይሮቢን ከቆጣጠረ በኋላ የት መኖር መጀመር አለብኝ? ዌስትላንድስ ወይስ ሪቨርሳይድ?” ሲሉ የናይሮቢ አካባቢዎችን በመጥቀስ ትዊት አድርገዋል። ይህ የጄኔራሉ ትዊት ግን ኬንያውያንን ያስቆጣ ሆኗል። አንዳንዶች ሙሴቪኒ የሰፋቸውን ሙሉ ልብስ ለብሰው የሚያሳይ ምስል በማያያዝ “ቅደሚያ የአባትህን ልብ ሰፊ ተቆጣጠር” በሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ከሰኞ ጀምሮ ኬንያውያን በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ የጄኔራሉን ጉዳይ በማንሳት ትችት እየሰነዘሩ ሲሆን፣ አንዳንዶችም ጄኔራሉ እንደሚባለው የአባታቸውን ሥልጣን የሚረከቡ ከሆነ ለአገራቸው ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ ጽፈዋል። ሌሎች ደግሞ በኬንያ እና ኡጋንዳ መካከል ያለውን ዴሞክራሲ በማነጻጸር የሙሴቪኒ ቤተሰብ ኡጋንዳውያንን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ነፍገዋል ሲሉ ተችተዋል። ይህን የጄኔራሉን አስተያየት ተከትሎ የኬንያ መንግሥትም ሆነ የኡጋንዳ ባለሥልጣንት በይፋ ያሉት ነገር የለም። ሌ/ጄኔራል ካይኒሩጋባ ኬንያን በተመለከተ ሌላ ጸሁፋቸው ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ያለኝ ብቸኛው ችግር ለሦስተኛ ዙር አለመወዳደራቸው ነው ብሏል። በኬንያ ሕገ-መንግሥት መሠረት አንድ ፕሬዝዳንት አገር መምራት የሚችለው ለሁለት የሥልጣን ዘመን ብቻ ነው። በዚህ መሠረት ኡሁሩ ከሁለት ወራት በፊት በተካሄደው ምርጫ ሳይሳተፉ ሥልጣን አስረክበው መንበራቸውን ለቀዋል። ሌ/ጄኔራል ካይኒሩጋባ ግን “ከተወዳጁ ትልቁ ወንድሜ ጋር ያለኝ ብቸኛ ችግር ለሦስተኛ ዙር አለመወዳደሩ ነው። በቀላሉ ማሸነፍ እንችል ነበር” ሲሉ ጽፈዋል። የምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ የምድር ጦር አዛዡ በሌላኛው አነጋገሪ ጽሑፋቸው ደግሞ ቀጣይዋን የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር የተመለከተ ነው። ባለፈው ሳምንት በተደረገ ምርጫ ፓርቲያቸው በማሸነፉ የጣሊያን መሪ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ሰፊ ግምት ለተሰጣቸው ሴት ፖለቲከኛ ጂዮርጂ ሜሎኒ ጥሎሽ የመስጠት ፍላጎት እንዳላቸው አመልክተዋል። “ለቀጣይዋ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ስንት ከብቶችን ልትሰጡ ትችላለችሁ?” ሲሉ ትዊተር ላይ የጠየቁት ጄኔራሉ፤ “አውሮፓውያን ለሚወዷቸው ሴቶች አበባ ይሰጣሉ፤ በአገሬ ባህል ግን ለምንወዳቸው ሴቶች የምንሰጠው ከብቶችን ነው” በማለት ባለ ግዙፍ ቀንድ ከብቶችን ምስል አያይዘው ትዊተር ላይ ለጥፈዋል። ቀደም ብሎ ደግሞ በኡጋንዳ የጣሊያን አምባሳደር የጥሎሽ ዋጋ እንዲደራደሩ ሽማግሌ አድርጌ መርጫለሁ ሲሉ ጽፈው ነበር። አነጋጋሪው ጄኔራል በኡጋንዳ ጦር ሠራዊት ውስጥ ከፍተኛ ሥልጣን ያላቸው ሲሆን፣ የሚሰጧቸው አስተያየቶችም መነጋገሪያ ከመሆን አልፈው ቁጣን እያስከተሉ ነው። ሌ/ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ በተለይ በትዊተር ላይ የሚያሰፍሯቸው አነጋጋሪ እና አወዛጋቢ ፖለቲካዊ አስተያየቶች፣ በርካታ ተከታዮችን እያፈራለቸው ነው። ከዚህ አንጻር ግባቸው መነጋገሪያ በመሆን በርካታ ተከታዮችን ማግኘት ነው የሚሉ ሰዎች አሉ። የኡጋንዳ መንግሥት ጄኔራሉ ትዊተር ላይ በሚያሰፍሯቸው መልዕክቶች ዙሪያ ብዙ ጊዜ ዝምታን የሚመርጥ ሲሆን፣ አንዳንድ ጊዜ ግን የጄኔራሉ ሐሳብ የአገሪቱ መንግሥት አቋም ሳይሆን የግለሰቡ አስተያየት ነው በማለት ያስተባብላል። አሁንም ኬንያውያን ከጄኔራሉ ሳይሆን የኡጋንዳ መንግሥት በይፋ የጄኔራሉን ጽሁፍ የሚያስተባብል ምላሽ እንዲሰጥ እንደሚፈልጉ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየጠየቁ የነበሩ ሲሆን ይፋዊ መግለጫም ወጥቷል። የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጄኔራሉን የትዊተር መልዕክት ሳይጠቅስ በተዘዋዋሪ የተሰነዘረው ሐሳብ የመንግሥት እንዳልሆነ ገልጿል። በዚህም የኡጋንዳ መንግሥት ከየትኛውም አገር ጋር የሚኖረው ግንኙነትን በተመለከተ ከማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሚገኙ እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያዎች በኩል በሚተላለፉ መልዕክቶች አማካይነት አይሆኑም ብሏል። ጨምሮም ኡጋንዳ ከኬንያ መንግሥት እና ሕዝብ ጋር ላለው ግንኙነትን ከፍተኛ ዋጋ እንደምትሰጥና ይህም የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንደምትፈልግ ገልጿል። ጄኔራሉ ግን በትዊተር ላይ ያሰፈሩት መልዕክት የቀሰቀሰውን ቁጣ ተከትሎ ማስተባበያ፣ ምላሽ ወይም ማብራሪያ ሳይሰጡ ሌሎች ጉዳዮችን በማንሳት ትዊት ማድረግ መቀጠላቸው በርካቶችን ግራ አጋብቷል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cz7derezj88o |
3politics
| ለፈረንሳይ ፕሬዝደንትነት ማክሮን እና ማሪን ሌ ፔን ለፍጻሜ ቀረቡ | በፈረንሳይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እየተደረገ ነው፡፡ 12 ተፎካካሪዎች በቀረቡበት የመጀመርያ ድምጽ አሰጣጥ ሁለቱ ከፍተኛ ድምጽ ያገኙት ዕጩዎች ተለይተዋል፡፡ ለ2ኛ ጊዜ ፈረንሳይን ለመምራት የሚወዳደሩት ኢማኑኤል ማክሮን ሁነኛ ተፎካካሪያቸውን ለይተዋል፡፡ የቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪ ማሪን ሌ ፔን የኢማኑኤል ማክሮን ቀንደኛ ተቀናቃኝ ሆነው ቀርበዋል፡፡ ሁለቱ እጩዎች ለፕሬዝዳንትነት እጩ ሆነው ሲቀርቡ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ቀኝ አክራሪዋ ማሪን ሌ ፔን ለፕሬዝዳንትነት ሲወዳደሩ ይህ ለ3ኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ በኋላ ከተሸነፉ ምናልባትም የፖለቲካ ሕይወታቸው መጨረሻ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡ የትናንቱን የድምጽ አሰጣጥ ተከትሎ ከፍተኛ ድምጽ ያገኙት ማክሮን፣ ‹‹በፍጹም እንዳትሳሳቱ፣ ምንም እርግጠኛ የሆነ ነገር የለም፡፡›› ሲሉ ለደጋፊዎቻቸው በስሜት የተሞላ ንግግር አድርገዋል፡፡ በፈረንሳይ ትናንት በተደረገ የመጀመርያ ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማክሮን ከፍተኛውን ድምጽ ያገኙ ሲሆን ሌ ፔን 2ኛውን ከፍተኛ ድምጽ በማግኘታቸው ነው ወደ 2ኛ ዙር ምርጫ እየተኬደ ያለው፡፡ ትናንት በተደረገው ድምጽ አሰጣጥ 97 ከመቶ ድምጽ ቆጠራ ተጠናቋል፡፡ በዚህም መሠረት ከጠቅላላ ድምጽ ሰጪዎች 27.35% ለማክሮን ድምጻቸውን ሰጥተዋል፡፡ ስደተኛ-ጠል ናቸው የሚባሉት ቀኝ አክራሪ ፓርቲን የሚመሩት ማሪን ሌ ፔን 23.97% ድምጽ በማግኘት 2ኛ ሆነዋል፡፡ ግራ ዘመም ፓርቲን የሚመሩትና ስሜት የሚኮረኩር ንግግር በማድረግ የተዋጣላቸው ዣን ሉክ ሚሌቾን 21.7% ከመቶ ድምጽ በማግኘት 3ኛ ሆነዋል፡፡ ዣን ሉክ ፈረንሳዊያን በፍጹም ድምጻቸውን ለቀኝ አክራሪዋ ሌ ፔን እንዳይሰጡ አሳስበዋል፡፡ ትናንትና ለፕሬዝዳንትነት እጩ ሆነው የቀረቡት ማክሮንን ጨምሮ 12 ፖለቲከኞች ነበሩ፡፡ ሆኖም የድምጽ ሰጪውን 10 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ድምጽ ማግኘት የቻሉት ሦስቱ ፓርቲዎች ብቻ ናቸው፡፡ አሸናፊውን ለመለየት ማክሮን እና ማሪን ሌ ፔን ለፍጻሜ ቀርበዋል፡፡ ሌ ፔን እና ማክሮን ከወዲሁ ከፍተኛ የምረጡኝ ቅስቀሳ ውስጥ ገብተዋል፡፡ የቀኝ አክራሪዋ ላ ፔን ከማክሮን ደጋፊዎች ውጭ ያሉ ፈረንሳዊያን በሙሉ ድምጻቸውን ለሳቸው እንዲሰጡ ተማጽነዋል፡፡ ትንንሽ ድምጽ ያገኙ ፓርቲዎችና ደጋፊዎቻቸው ድጋፋቸውን ለማሪን ሌ ፔን ከሰጡ ማክሮን የማሸነፍ ዕድላቸው አጣብቂኝ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል ተገምቷል፡፡ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በፈረንሳይ ታሪክ በወጣትነት ዕድሜ ፕሬዝዳንትነትን የተቆናጠጡ መሪ ናቸው፡፡ ሥልጣን ሲረከቡ 39 ዓመታቸው ነበር፡፡ ለዚህኛው ምርጫ በቂ ቅስቀሳ እንዳላደረጉ የተነገረ ሲሆን ለምርጫው 8 ቀናት ሲቀሩት ብቻ ነው ሞቅ ወዳለ ቅስቀሳ የገቡት ተብሏል፡፡ ይህም የሆነው በዋናነት በዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት ጉዳይ በመጠመዳቸው ነው ተብሏል፡፡ የሁለተኛ ዙር ድምጽ አሰጣጡ የሚደረገው ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚያዚያ 24 ነው፡፡ ማዳም ማሪን ሌ ፔን በፈረንሳይ ቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪነት ዘለግ ላለ ጊዜ የቆዩ ናቸው፡፡ ለመጤዎች በጎ አመለካከት የሌላቸው ሲሆን በአደባባይ ኢስላማዊ ሒጃብ እንዳይለበስ ሕግ እደነግጋለሁ ብለዋል፡፡ ከዚህም ሌላ ፈረንሳይ ከአውሮጳ ኅብረት እንድትወጣ ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ይፈልጋሉ፡፡ ወደ ፈረንሳይ የሚገቡ ስደተኞችን ቁጥር በእጅጉ ለመቀነስና ድንበርን ለመዝጋትም ፍላጎት አላቸው፡፡ | ለፈረንሳይ ፕሬዝደንትነት ማክሮን እና ማሪን ሌ ፔን ለፍጻሜ ቀረቡ በፈረንሳይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እየተደረገ ነው፡፡ 12 ተፎካካሪዎች በቀረቡበት የመጀመርያ ድምጽ አሰጣጥ ሁለቱ ከፍተኛ ድምጽ ያገኙት ዕጩዎች ተለይተዋል፡፡ ለ2ኛ ጊዜ ፈረንሳይን ለመምራት የሚወዳደሩት ኢማኑኤል ማክሮን ሁነኛ ተፎካካሪያቸውን ለይተዋል፡፡ የቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪ ማሪን ሌ ፔን የኢማኑኤል ማክሮን ቀንደኛ ተቀናቃኝ ሆነው ቀርበዋል፡፡ ሁለቱ እጩዎች ለፕሬዝዳንትነት እጩ ሆነው ሲቀርቡ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ቀኝ አክራሪዋ ማሪን ሌ ፔን ለፕሬዝዳንትነት ሲወዳደሩ ይህ ለ3ኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ በኋላ ከተሸነፉ ምናልባትም የፖለቲካ ሕይወታቸው መጨረሻ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡ የትናንቱን የድምጽ አሰጣጥ ተከትሎ ከፍተኛ ድምጽ ያገኙት ማክሮን፣ ‹‹በፍጹም እንዳትሳሳቱ፣ ምንም እርግጠኛ የሆነ ነገር የለም፡፡›› ሲሉ ለደጋፊዎቻቸው በስሜት የተሞላ ንግግር አድርገዋል፡፡ በፈረንሳይ ትናንት በተደረገ የመጀመርያ ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማክሮን ከፍተኛውን ድምጽ ያገኙ ሲሆን ሌ ፔን 2ኛውን ከፍተኛ ድምጽ በማግኘታቸው ነው ወደ 2ኛ ዙር ምርጫ እየተኬደ ያለው፡፡ ትናንት በተደረገው ድምጽ አሰጣጥ 97 ከመቶ ድምጽ ቆጠራ ተጠናቋል፡፡ በዚህም መሠረት ከጠቅላላ ድምጽ ሰጪዎች 27.35% ለማክሮን ድምጻቸውን ሰጥተዋል፡፡ ስደተኛ-ጠል ናቸው የሚባሉት ቀኝ አክራሪ ፓርቲን የሚመሩት ማሪን ሌ ፔን 23.97% ድምጽ በማግኘት 2ኛ ሆነዋል፡፡ ግራ ዘመም ፓርቲን የሚመሩትና ስሜት የሚኮረኩር ንግግር በማድረግ የተዋጣላቸው ዣን ሉክ ሚሌቾን 21.7% ከመቶ ድምጽ በማግኘት 3ኛ ሆነዋል፡፡ ዣን ሉክ ፈረንሳዊያን በፍጹም ድምጻቸውን ለቀኝ አክራሪዋ ሌ ፔን እንዳይሰጡ አሳስበዋል፡፡ ትናንትና ለፕሬዝዳንትነት እጩ ሆነው የቀረቡት ማክሮንን ጨምሮ 12 ፖለቲከኞች ነበሩ፡፡ ሆኖም የድምጽ ሰጪውን 10 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ድምጽ ማግኘት የቻሉት ሦስቱ ፓርቲዎች ብቻ ናቸው፡፡ አሸናፊውን ለመለየት ማክሮን እና ማሪን ሌ ፔን ለፍጻሜ ቀርበዋል፡፡ ሌ ፔን እና ማክሮን ከወዲሁ ከፍተኛ የምረጡኝ ቅስቀሳ ውስጥ ገብተዋል፡፡ የቀኝ አክራሪዋ ላ ፔን ከማክሮን ደጋፊዎች ውጭ ያሉ ፈረንሳዊያን በሙሉ ድምጻቸውን ለሳቸው እንዲሰጡ ተማጽነዋል፡፡ ትንንሽ ድምጽ ያገኙ ፓርቲዎችና ደጋፊዎቻቸው ድጋፋቸውን ለማሪን ሌ ፔን ከሰጡ ማክሮን የማሸነፍ ዕድላቸው አጣብቂኝ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል ተገምቷል፡፡ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በፈረንሳይ ታሪክ በወጣትነት ዕድሜ ፕሬዝዳንትነትን የተቆናጠጡ መሪ ናቸው፡፡ ሥልጣን ሲረከቡ 39 ዓመታቸው ነበር፡፡ ለዚህኛው ምርጫ በቂ ቅስቀሳ እንዳላደረጉ የተነገረ ሲሆን ለምርጫው 8 ቀናት ሲቀሩት ብቻ ነው ሞቅ ወዳለ ቅስቀሳ የገቡት ተብሏል፡፡ ይህም የሆነው በዋናነት በዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት ጉዳይ በመጠመዳቸው ነው ተብሏል፡፡ የሁለተኛ ዙር ድምጽ አሰጣጡ የሚደረገው ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚያዚያ 24 ነው፡፡ ማዳም ማሪን ሌ ፔን በፈረንሳይ ቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪነት ዘለግ ላለ ጊዜ የቆዩ ናቸው፡፡ ለመጤዎች በጎ አመለካከት የሌላቸው ሲሆን በአደባባይ ኢስላማዊ ሒጃብ እንዳይለበስ ሕግ እደነግጋለሁ ብለዋል፡፡ ከዚህም ሌላ ፈረንሳይ ከአውሮጳ ኅብረት እንድትወጣ ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ይፈልጋሉ፡፡ ወደ ፈረንሳይ የሚገቡ ስደተኞችን ቁጥር በእጅጉ ለመቀነስና ድንበርን ለመዝጋትም ፍላጎት አላቸው፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-61064285 |
3politics
| ፑቲን በዩክሬን ጦርነት ጣልቃ የሚገባ አገር ላይ መብረቃዊ ጥቃት እንደሚፈጽሙ ዛቱ | የሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ጦርነት እጁን የሚያስገባ ማንኛውም አገር ላይ መብረቃዊ ጥቃት እንደሚፈጸምበት አስጠነቀቁ፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ አገራቸው ሩሲያ አቅምም ብቃትም አላት ብለዋል፡፡ ‹‹ማንም አገር አለኝ የማይለው የጦር መሣሪያ አለን፡፡…አስፈላጊ ከሆነ እንጠቀመዋለን›› ሲሉ ብዙዎችን ያሳሰበ ንግግር አድርገዋል፡፡ አንዳንድ ተንታኞች ፑቲን በዚህ ንግግራቸው ለመጠቆም የሞከሩት ባለስቲክ ሚሳኤልና የኑክሊየር መሣሪያን ነው በማለት ግምት ወስደዋል፡፡ ፑቲን ወረራውን በጀመሩ ማግስት ለጦር ሹማምንቶቻቸው የኑክሊየር መሣሪያ በተጠንቀቅ እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡ ይህ የፑቲን መራር ንግግር የተሰማው ደግሞ ምዕራባዊያን ለዩክሬን እጅግ ውስብስብና ዘመናዊ መሣሪያዎችን በመስጠት በተጠመዱበት ማግስት ነው፡፡ በተለይም ባለፉት ቀናት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ኦስቲን በኪየቭ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ በዚህ ጉብኝታቸውም ለዩክሬን ወደ 700 ሚሊዮን ዶላር የተጠጋ እርዳታን ይፋ አድርገዋል፡፡ ከትናንት በስቲያ ደግሞ የምዕራብ አገራት በጀርመን ተሰብስበው ለዩክሬን የሚደረገውን የጦር መሣሪያ እርዳታ እንዴት ከዚህም በላቀ መልኩ ማሳደግ ይቻላል በሚል ተወያይተው ነበር፡፡ በጦርነት ጣልቃ ያለመግባት ጥብቅ ፖሊሲን ትከተል የነበረችው ጀርመን ሳይቀር ያልተጠበቀ የፖሊሲ ለውጥ በማድረግ ለዩክሬን 50 የአየር መቃወሚያ ታንኮችን እሰጣለሁ ብላለች፡፡ በአሁን ጊዜ ጦርነቱ ተፋፍሞ የቀጠለ ቢሆንም የምዕራብ አገር ተንታኞች ሩሲያ በምሥራቅ ዩክሬን ልታደርገው ያሰበችው መጠነ ሰፊ ጥቃት እንደተስተጓጎለባት እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ ሩሲያ ከዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ከበባ ወደ ኋላ እንድታፈገፍግ ከተደረገች በኋላ ትኩረቷን ወደ ደቡብ ምሥራቅ ዩክሬን በተለይም ዶንባስ በሚባለው ክልል ለማድረግ ወስና ነበር፡፡ ይሁንና በምሥራቅ ግንባር ሩሲያ ያሰበችውን ግስጋሴ አላሳካችም፡፡ ከዩክሬናዊያን ያልጠበቀችው መከላከል ገጥሟታል፡፡በርካታ ወታደሮችም ተገድለውባታል፡፡ ይህ በአንዲህ እያለ የአውሮጳ ኅብረት ሩሲያ ለፖላንድና ቡልጋሪያ ጋዝ አልሸጥም ማለቷን አውግዟል፡፡ የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሊየን እንዳሉት ይህ የሚያሳየው ሩሲያ የማታስተማምን የንግድ አቅራቢ መሆኗን ነው፡፡ ሩሲያ በበኩሏ ይህን እርምጃ የወሰድኩት ወዳጅ ያልሆኑ አገራት ለማቀርብላቸው ጋዝ ክፍያቸውን በሩብል እንዲያደርጉ ያሳለፍኩትን ውሳኔ ፖላንድና ቡልጋሪያ ስላላከበሩት ነው ብላለች፡፡ | ፑቲን በዩክሬን ጦርነት ጣልቃ የሚገባ አገር ላይ መብረቃዊ ጥቃት እንደሚፈጽሙ ዛቱ የሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ጦርነት እጁን የሚያስገባ ማንኛውም አገር ላይ መብረቃዊ ጥቃት እንደሚፈጸምበት አስጠነቀቁ፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ አገራቸው ሩሲያ አቅምም ብቃትም አላት ብለዋል፡፡ ‹‹ማንም አገር አለኝ የማይለው የጦር መሣሪያ አለን፡፡…አስፈላጊ ከሆነ እንጠቀመዋለን›› ሲሉ ብዙዎችን ያሳሰበ ንግግር አድርገዋል፡፡ አንዳንድ ተንታኞች ፑቲን በዚህ ንግግራቸው ለመጠቆም የሞከሩት ባለስቲክ ሚሳኤልና የኑክሊየር መሣሪያን ነው በማለት ግምት ወስደዋል፡፡ ፑቲን ወረራውን በጀመሩ ማግስት ለጦር ሹማምንቶቻቸው የኑክሊየር መሣሪያ በተጠንቀቅ እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡ ይህ የፑቲን መራር ንግግር የተሰማው ደግሞ ምዕራባዊያን ለዩክሬን እጅግ ውስብስብና ዘመናዊ መሣሪያዎችን በመስጠት በተጠመዱበት ማግስት ነው፡፡ በተለይም ባለፉት ቀናት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ኦስቲን በኪየቭ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ በዚህ ጉብኝታቸውም ለዩክሬን ወደ 700 ሚሊዮን ዶላር የተጠጋ እርዳታን ይፋ አድርገዋል፡፡ ከትናንት በስቲያ ደግሞ የምዕራብ አገራት በጀርመን ተሰብስበው ለዩክሬን የሚደረገውን የጦር መሣሪያ እርዳታ እንዴት ከዚህም በላቀ መልኩ ማሳደግ ይቻላል በሚል ተወያይተው ነበር፡፡ በጦርነት ጣልቃ ያለመግባት ጥብቅ ፖሊሲን ትከተል የነበረችው ጀርመን ሳይቀር ያልተጠበቀ የፖሊሲ ለውጥ በማድረግ ለዩክሬን 50 የአየር መቃወሚያ ታንኮችን እሰጣለሁ ብላለች፡፡ በአሁን ጊዜ ጦርነቱ ተፋፍሞ የቀጠለ ቢሆንም የምዕራብ አገር ተንታኞች ሩሲያ በምሥራቅ ዩክሬን ልታደርገው ያሰበችው መጠነ ሰፊ ጥቃት እንደተስተጓጎለባት እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ ሩሲያ ከዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ከበባ ወደ ኋላ እንድታፈገፍግ ከተደረገች በኋላ ትኩረቷን ወደ ደቡብ ምሥራቅ ዩክሬን በተለይም ዶንባስ በሚባለው ክልል ለማድረግ ወስና ነበር፡፡ ይሁንና በምሥራቅ ግንባር ሩሲያ ያሰበችውን ግስጋሴ አላሳካችም፡፡ ከዩክሬናዊያን ያልጠበቀችው መከላከል ገጥሟታል፡፡በርካታ ወታደሮችም ተገድለውባታል፡፡ ይህ በአንዲህ እያለ የአውሮጳ ኅብረት ሩሲያ ለፖላንድና ቡልጋሪያ ጋዝ አልሸጥም ማለቷን አውግዟል፡፡ የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሊየን እንዳሉት ይህ የሚያሳየው ሩሲያ የማታስተማምን የንግድ አቅራቢ መሆኗን ነው፡፡ ሩሲያ በበኩሏ ይህን እርምጃ የወሰድኩት ወዳጅ ያልሆኑ አገራት ለማቀርብላቸው ጋዝ ክፍያቸውን በሩብል እንዲያደርጉ ያሳለፍኩትን ውሳኔ ፖላንድና ቡልጋሪያ ስላላከበሩት ነው ብላለች፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-61245799 |
5sports
| እግር ኳስ፡ የአፍሪካ ዋንጫ ካይሮ ውስጥ ጠፋ | የአፍሪካ ዋንጫን ጨምሮ በርካታ ዋንጫዎች ካይሮ ከሚገኘው ከግብጽ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዋና መስሪያ ቤት መጥፋታቸው ተነገረ። የግብጽ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም በጉዳዩ ላይ ይፋዊ ምርመራ ጀምሪያለሁ ብሏል። ግብጽ እአአ 2010 ተከታታይ ሶስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ መሆኗን ተከትሎ ነበር ዋንጫው ግብጽ እንድትወስደው የተደረገው። ግብጽ የአፍሪካ ዋንጫን ለተከታታይ ሶስት ጊዜ ያሸነፈችው በ2006፣ 2008 እና 2010 በተደረጉት ውድድሮች ነበር። አርብ ዕለት የግብጽ እግር ኳን ፌደሬሽን በርካታ ዋንጫዎች መጥፋታቸውን ተከትሎ ይፋዊ ምረመራ መጀመሩን አስታውቋል። ''ፌደሬሽኑ ዋና መስሪይ ቤቱን በማደስና ወደ ሙዚየምነት ለመቀየር እየተሯሯጠ ባለበት ወቅት የዋንጫዎቹ መጥፋት አመራሩን በጣም አስደንግጦታል'' ብሏል ፌደሬሽኑ ባወጣው መግለጫ። የቀድሞው የግብጽ እግር ኳስ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት አህመድ ሾቢር በበኩላቸው ከጠፉት ዋንጫዎች መካከል የ2010ሩ ዋንጫም እንደሚገኝበት ተናግረዋል። በአውሮፓውያኑ 2013 የግብጽ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዋና መስሪያ ቤት ጥቃት ከተፈጸመበት በኋላ ዋንጫዎቹ ወደ ሌላ ማቆያ ስፍራ እንዲወሰዱ ተደርጎ ነበር። ነገር ግን የፌደሬሽኑ ባለስልጣናት የመስሪያ ቤቱን መግቢያና መውጫ በሮች በማስተካከል ጎብኚዎች ዋንጫዎቹን እንዲጎበኙ ለማድረግ እድሳት በሚሰሩበት ወቅት ነው ዋንጫዎቹ መጥፋታቸውን ይተነገረው። በአፍሪካ አግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ወይንም ካፍ ሕግ መሰረት አንዲት አገር ዋንጫውን ለሶስት ተከታታይ ጊዜ ካሸነፈች ዋንጫውን ማስቀረት ትችላለች። በዚህም ሕግ መሰረት ነው ግብጽ ዋንጫውን በአገሯ ያስቀረችው። በአፍሪካ ዋንጫ ታሪክ ለሶስት ተከታታይ ጊዜ ማሸነፍ የቻለችው ሌላኛዋ አገር ጋና ስትሆን ሶስተኛውን ዋንጫ ያነሳችው በአውሮፓውያኑ 1978 ላይ ነበር። | እግር ኳስ፡ የአፍሪካ ዋንጫ ካይሮ ውስጥ ጠፋ የአፍሪካ ዋንጫን ጨምሮ በርካታ ዋንጫዎች ካይሮ ከሚገኘው ከግብጽ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዋና መስሪያ ቤት መጥፋታቸው ተነገረ። የግብጽ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም በጉዳዩ ላይ ይፋዊ ምርመራ ጀምሪያለሁ ብሏል። ግብጽ እአአ 2010 ተከታታይ ሶስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ መሆኗን ተከትሎ ነበር ዋንጫው ግብጽ እንድትወስደው የተደረገው። ግብጽ የአፍሪካ ዋንጫን ለተከታታይ ሶስት ጊዜ ያሸነፈችው በ2006፣ 2008 እና 2010 በተደረጉት ውድድሮች ነበር። አርብ ዕለት የግብጽ እግር ኳን ፌደሬሽን በርካታ ዋንጫዎች መጥፋታቸውን ተከትሎ ይፋዊ ምረመራ መጀመሩን አስታውቋል። ''ፌደሬሽኑ ዋና መስሪይ ቤቱን በማደስና ወደ ሙዚየምነት ለመቀየር እየተሯሯጠ ባለበት ወቅት የዋንጫዎቹ መጥፋት አመራሩን በጣም አስደንግጦታል'' ብሏል ፌደሬሽኑ ባወጣው መግለጫ። የቀድሞው የግብጽ እግር ኳስ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት አህመድ ሾቢር በበኩላቸው ከጠፉት ዋንጫዎች መካከል የ2010ሩ ዋንጫም እንደሚገኝበት ተናግረዋል። በአውሮፓውያኑ 2013 የግብጽ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዋና መስሪያ ቤት ጥቃት ከተፈጸመበት በኋላ ዋንጫዎቹ ወደ ሌላ ማቆያ ስፍራ እንዲወሰዱ ተደርጎ ነበር። ነገር ግን የፌደሬሽኑ ባለስልጣናት የመስሪያ ቤቱን መግቢያና መውጫ በሮች በማስተካከል ጎብኚዎች ዋንጫዎቹን እንዲጎበኙ ለማድረግ እድሳት በሚሰሩበት ወቅት ነው ዋንጫዎቹ መጥፋታቸውን ይተነገረው። በአፍሪካ አግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ወይንም ካፍ ሕግ መሰረት አንዲት አገር ዋንጫውን ለሶስት ተከታታይ ጊዜ ካሸነፈች ዋንጫውን ማስቀረት ትችላለች። በዚህም ሕግ መሰረት ነው ግብጽ ዋንጫውን በአገሯ ያስቀረችው። በአፍሪካ ዋንጫ ታሪክ ለሶስት ተከታታይ ጊዜ ማሸነፍ የቻለችው ሌላኛዋ አገር ጋና ስትሆን ሶስተኛውን ዋንጫ ያነሳችው በአውሮፓውያኑ 1978 ላይ ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/news-54039405 |
5sports
| አርጀንቲና፣ ቺሊ፣ ኡራጓይና ፓራጓይ የዓለም ዋንጫን በጥምረት ለማዘጋጀት ጠየቁ | አርጀንቲና፣ ቺሊ፣ ኡራጓይ እና ፓራጓይ በአውሮፓውያኑ 2030 ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫን በጋራ ለማዘጋጀት ጥያቄ አቀረቡ። የአለም ዋንጫ የመጀመሪያውን ውድድር በአውሮፓውያኑ 1930 ያስተናገደችው ኡራጓይ የአለም ዋንጫ መቶኛ አመቱን ሲያከብር ወደተጀመረባት አገር ማምጣት እንደምትፈልግ አስታውቃለች። የደቡብ አሜሪካዎቹ አገራት የአለም ዋንጫን በጋራ ለማዘጋጅት መጠየቃቸውንም አስመልክቶ “ ይህ የአንድ አህጉር ህልም ነው” በማለት የደቡብ አሜሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ኮንሜቦል) ፕሬዝዳንት አሌሃንድሮ ዶሚኒጌዝ ተናግረዋል። ከደቡብ አሜሪካዎቹ አገራት በተጨማሪ የአውሮፓ ሃገራቱ ስፔን እና ፖርቹጋል በጋራ ለማዘጋጀት ውድድሩ ላይ ቀርበዋል። ሞንቴቪዲዮ ሴንቴናሪዮ ስታዲየም በተደረገው የመጀመሪያው የአለም ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ ኡራጓይ አርጀንቲናን ያሸነፈች ሲሆን ፕሬዚዳንት አሌሃንድሮ ዶሚኒጌዝ በዚህ ስታዲየም ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። “ተጨማሪ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ይኖራሉ ፣ ነገር ግን የዓለም ዋንጫ ጨዋታ 100 አመቱን የሚያከብረው አንድ ጊዜ ብቻ ነው ስለዚህ ወደተጀመረበት ወደ ቤቱ መምጣት አለበት” ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል። ቺሊ የዓለም ዋንጫን በአውሮፖውያኑ 1962 ስታስተናግድ፣ አርጀንቲና ደግሞ በአውሮፓውያኑ 1978 አዘጋጅታለች። "የአለም ዋንጫ ውድድር ከ100 አመት በኋላ በተጀመረበት ቦታ መካሄዱ ትክክለኛ ነው" በማለት የኡራጓይ እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት ኢግናሲዮ አሎንሶ ተናግረዋል። የ2022 የአለም ዋንጫ በኳታር የሚካሄድ ሲሆን ካናዳ፣ሜክሲኮ እና አሜሪካ የ2026 የጋራ አስተናጋጅ ይሆናሉ። ፊፋ የ2030 አስተናጋጅን ከሁለት አመት በኋላ፣ በ2024 ለመምረጥ እቅድ ይዟል። የዩናይትድ ኪንግደም እና የአየርላንድ ሪፐብሊክ የእግር ኳስ ማህበራት ለ2030ው የአለም ዋንጫ አስተናጋጅነት ላለመወዳደር እና በምትኩ ዩሮ 2028ን በጋራ ለማዘጋጀት በሚደረገው ጥረት ላይ ለማተኮር ተስማምተዋል። | አርጀንቲና፣ ቺሊ፣ ኡራጓይና ፓራጓይ የዓለም ዋንጫን በጥምረት ለማዘጋጀት ጠየቁ አርጀንቲና፣ ቺሊ፣ ኡራጓይ እና ፓራጓይ በአውሮፓውያኑ 2030 ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫን በጋራ ለማዘጋጀት ጥያቄ አቀረቡ። የአለም ዋንጫ የመጀመሪያውን ውድድር በአውሮፓውያኑ 1930 ያስተናገደችው ኡራጓይ የአለም ዋንጫ መቶኛ አመቱን ሲያከብር ወደተጀመረባት አገር ማምጣት እንደምትፈልግ አስታውቃለች። የደቡብ አሜሪካዎቹ አገራት የአለም ዋንጫን በጋራ ለማዘጋጅት መጠየቃቸውንም አስመልክቶ “ ይህ የአንድ አህጉር ህልም ነው” በማለት የደቡብ አሜሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ኮንሜቦል) ፕሬዝዳንት አሌሃንድሮ ዶሚኒጌዝ ተናግረዋል። ከደቡብ አሜሪካዎቹ አገራት በተጨማሪ የአውሮፓ ሃገራቱ ስፔን እና ፖርቹጋል በጋራ ለማዘጋጀት ውድድሩ ላይ ቀርበዋል። ሞንቴቪዲዮ ሴንቴናሪዮ ስታዲየም በተደረገው የመጀመሪያው የአለም ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ ኡራጓይ አርጀንቲናን ያሸነፈች ሲሆን ፕሬዚዳንት አሌሃንድሮ ዶሚኒጌዝ በዚህ ስታዲየም ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። “ተጨማሪ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ይኖራሉ ፣ ነገር ግን የዓለም ዋንጫ ጨዋታ 100 አመቱን የሚያከብረው አንድ ጊዜ ብቻ ነው ስለዚህ ወደተጀመረበት ወደ ቤቱ መምጣት አለበት” ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል። ቺሊ የዓለም ዋንጫን በአውሮፖውያኑ 1962 ስታስተናግድ፣ አርጀንቲና ደግሞ በአውሮፓውያኑ 1978 አዘጋጅታለች። "የአለም ዋንጫ ውድድር ከ100 አመት በኋላ በተጀመረበት ቦታ መካሄዱ ትክክለኛ ነው" በማለት የኡራጓይ እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት ኢግናሲዮ አሎንሶ ተናግረዋል። የ2022 የአለም ዋንጫ በኳታር የሚካሄድ ሲሆን ካናዳ፣ሜክሲኮ እና አሜሪካ የ2026 የጋራ አስተናጋጅ ይሆናሉ። ፊፋ የ2030 አስተናጋጅን ከሁለት አመት በኋላ፣ በ2024 ለመምረጥ እቅድ ይዟል። የዩናይትድ ኪንግደም እና የአየርላንድ ሪፐብሊክ የእግር ኳስ ማህበራት ለ2030ው የአለም ዋንጫ አስተናጋጅነት ላለመወዳደር እና በምትኩ ዩሮ 2028ን በጋራ ለማዘጋጀት በሚደረገው ጥረት ላይ ለማተኮር ተስማምተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cw9753j3191o |
3politics
| ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ሆኑ | የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን የቀረቡ አስራ አንድ ዕጩዎችን ሲሾም፣ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ሆነው ተሰየሙ። ምክር ቤቱ ዛሬ ሰኞ የካቲት 14/2014 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው በአፈ ጉባኤው ታገሰ ጫፎ በቀረቧቸው 11 ዕጩ ተሿሚዎች ላይ ድምጽ ተሰጥቶ ሹመታቸው ጸድቋል። ከአስራ አንዱ የኮሚሽነሮች መካከል በሰብሳቢነት ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ሲሾሙ፣ ወይዘሮ ሂሩት ገብረሥላሴ ደግሞ የኮሚሽኑ ምክትል ሰብሳቢ ሆነዋል። ከምክር ቤቱ አባላት 335 አባላት በተገኙበት በተሰጠው ድምጽ፣ አምስቱ ድምጸ ታዕቅቦ ያደረጉ ሲሆን ቀሪዎቹ እንደራሴዎች ሹመቱን ደግፈው አጽድቀውታል። ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ መሠረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር በማድረግና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችል ሂደትን የሚመራና የሚያስተባብር አካል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካይነት ለማቋቋም ጥቆማ መካሄዱ ይታወሳል። ከጥቂት ወራት በፊት ለሕዝብ በቀረበ ጥሪ መሠረት 632 ዕጩዎች ለኮሚሽኑ አባልነት በተለያዩ ወገኖች ተጠቁመው ከእነዚህ መካከልም ኮሚሽኑን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ መስፈርቶች መሠረት 42ቱ ተለይተው ኅብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ዝርዝራቸው ይፋ መድረጉ ይታወሳል። ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን በኮሚሽነርነት ከቀረቡት ከ42ቱ ዕጩ ተጠቋሚዎች መካከል መስፈርቱን በከፍተኛ ደረጃ አሟልተዋል የተባሉት ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ተሹመዋል። በዚህ መሠረትም፦ 1. ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ 2. ወይዘሮ ሂሩት ገብረሥላሴ 3. ዶክተር ተገኘወርቅ ጌቱ 4. አምባሳደር ዶክተር አይሮሪት መሐመድ 5. ዶክተር አምባዬ ኦጋቶ 6. ዶክተር ዮናስ አዳዬ 7. አምባሳደር መሐሙድ ድሪር 8. ወይዘሮ ብሌን ገብረመድኅን 9. አቶ ዘገየ አስፋው 10. አቶ መላኩ ወልደማሪያም 11. አቶ ሙሉጌታ አጎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስራ አንዱን ኮሚሽነሮች ከመሰየሙ በፊት ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት የተጠቆሙትን የ42ቱን ግለሰቦች ዝርዝር ከአጭር የትምህርትና የሥራ መግለጫ ጋር በድረ ገጹ ላይ ይፋ አድርጎ ሕዝቡም አስተያየት እንዲሰጥባቸው ጥያቄ አቅርቦ ነበር። ከዚህ ሂደት በኋላም በተጠቋሚ ዕጩዎቹ ላይ በተዘጋጀው መስፈርት መሠረት ከሕዝብ የሚቀርበው አስተያየት ተገምግሞ የመጨረሻዎቹ 11 ዕጩ ኮሚሽነሮች ተለይተው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ እንዲሾሙ አድርጓል። ኮሚሽኑ በአገሪቱ ለዘመናት የቆዩ ናቸው በተባሉ የተለያዩ አወዛጋቢና ጉዳዮች ላይ የሚመለከታቸው ወገኖችንና ኃይሎችን በማቀራረብ ውይይት ተደርጓ መግባባት ላይ እንዲደረስ ለማድረግ የሚያስችሉ ምክክሮችን ይመራል ተብሎ ይጠበቃል። | ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ሆኑ የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን የቀረቡ አስራ አንድ ዕጩዎችን ሲሾም፣ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ሆነው ተሰየሙ። ምክር ቤቱ ዛሬ ሰኞ የካቲት 14/2014 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው በአፈ ጉባኤው ታገሰ ጫፎ በቀረቧቸው 11 ዕጩ ተሿሚዎች ላይ ድምጽ ተሰጥቶ ሹመታቸው ጸድቋል። ከአስራ አንዱ የኮሚሽነሮች መካከል በሰብሳቢነት ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ሲሾሙ፣ ወይዘሮ ሂሩት ገብረሥላሴ ደግሞ የኮሚሽኑ ምክትል ሰብሳቢ ሆነዋል። ከምክር ቤቱ አባላት 335 አባላት በተገኙበት በተሰጠው ድምጽ፣ አምስቱ ድምጸ ታዕቅቦ ያደረጉ ሲሆን ቀሪዎቹ እንደራሴዎች ሹመቱን ደግፈው አጽድቀውታል። ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ መሠረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር በማድረግና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችል ሂደትን የሚመራና የሚያስተባብር አካል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካይነት ለማቋቋም ጥቆማ መካሄዱ ይታወሳል። ከጥቂት ወራት በፊት ለሕዝብ በቀረበ ጥሪ መሠረት 632 ዕጩዎች ለኮሚሽኑ አባልነት በተለያዩ ወገኖች ተጠቁመው ከእነዚህ መካከልም ኮሚሽኑን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ መስፈርቶች መሠረት 42ቱ ተለይተው ኅብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ዝርዝራቸው ይፋ መድረጉ ይታወሳል። ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን በኮሚሽነርነት ከቀረቡት ከ42ቱ ዕጩ ተጠቋሚዎች መካከል መስፈርቱን በከፍተኛ ደረጃ አሟልተዋል የተባሉት ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ተሹመዋል። በዚህ መሠረትም፦ 1. ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ 2. ወይዘሮ ሂሩት ገብረሥላሴ 3. ዶክተር ተገኘወርቅ ጌቱ 4. አምባሳደር ዶክተር አይሮሪት መሐመድ 5. ዶክተር አምባዬ ኦጋቶ 6. ዶክተር ዮናስ አዳዬ 7. አምባሳደር መሐሙድ ድሪር 8. ወይዘሮ ብሌን ገብረመድኅን 9. አቶ ዘገየ አስፋው 10. አቶ መላኩ ወልደማሪያም 11. አቶ ሙሉጌታ አጎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስራ አንዱን ኮሚሽነሮች ከመሰየሙ በፊት ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት የተጠቆሙትን የ42ቱን ግለሰቦች ዝርዝር ከአጭር የትምህርትና የሥራ መግለጫ ጋር በድረ ገጹ ላይ ይፋ አድርጎ ሕዝቡም አስተያየት እንዲሰጥባቸው ጥያቄ አቅርቦ ነበር። ከዚህ ሂደት በኋላም በተጠቋሚ ዕጩዎቹ ላይ በተዘጋጀው መስፈርት መሠረት ከሕዝብ የሚቀርበው አስተያየት ተገምግሞ የመጨረሻዎቹ 11 ዕጩ ኮሚሽነሮች ተለይተው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ እንዲሾሙ አድርጓል። ኮሚሽኑ በአገሪቱ ለዘመናት የቆዩ ናቸው በተባሉ የተለያዩ አወዛጋቢና ጉዳዮች ላይ የሚመለከታቸው ወገኖችንና ኃይሎችን በማቀራረብ ውይይት ተደርጓ መግባባት ላይ እንዲደረስ ለማድረግ የሚያስችሉ ምክክሮችን ይመራል ተብሎ ይጠበቃል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60461921 |
5sports
| ከወሳኝ የምድብ ጨዋታቸው በፊት ኢራን በአሜሪካ ላይ ለፊፋ ክስ አቀረበች | የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአሜሪካን ቡድን በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቹ ላይ ካወጣው የኢራን ሰንደቅ ዓላማ ጋር በተያያዘ ለፊፋ ክስ አቀረበ። የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ለዓለም አቀፉ የእግር ኳስ የበላይ አካል አቤቱታ ያረበው የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የኢራን ብሎ ያወጣው ሰንደቅ ዓላማ እስላማዊ ሪፐብሊኳን የሚወክለውን አርማ አንስቶታል የሚል ነው። ኢራን እና አሜሪካ ነገ ማክሰኞ ከሚኖራቸው የዓለም ዋንጫ የምድብ ግጥሚያ በፊት፣ የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን በትዊተር፣ በፌስቡክ እና በኢንስታ ግራም ላይ ከለጠፈው የኢራን ባንዲራ ላይ የአገሪቱ መለያ አርማ አልተካተተም። አሜሪካ ለዚህ ክስ በሰጠችው ምላሽ በአገሪቱ ውስጥ እየተካሄዱ ካሉት ፀረ መንግሥት ተቃውሞዎች ጋር በተያያዘ “በኢራን መሠረታዊ መብቶች እንዲከበሩ እየታገሉ ላሉት ሴቶች ድጋፈችንን ለመግለጽ” የአገሪቱን ይፋዊ ሰንደቅ ዓላማ ላለመጠቀም መወሰኑን ገልጻለች። በኢራን ውስጥ ማህሳ አሚኒ የተባለች የ22 ዓመት ወጣት ሂጃብ በአግባቡ አልለበሰችም በሚል በአገሪቱ የሥነ ምግባር ፖሊሶች ተይዛ ከታሰረች በኋላ መሞቷን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው። “ሙያዊነት በጎደለው ተግባር፣ የአሜሪካ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢንስታግራም ገጽ በሰንደቅ ዓላማው ላይ ያለውን የአላህ ምልክትን አስወግዶታል” ሲል የኢራን መንግሥት ዜና ወኪል ኢርና ገልጸወል። ይህንንም ተከትሎ “የኢራን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የእግር ኳስ የበላይ አስተዳዳሪው አካል ፊፋ ለአሜሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠንካራ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ኢሜይል ልኳል።” በኋላ ላይ ግን አንድ የአሜሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቃል አቀባይ እንዳሉት፣ ቅሬታ የቀረበበት የሰንደቅ ዓላማ ምስል ከማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ እንዲነሱ መደረጋቸውንና በምትካቸውም ትክክለኛው የኢራን ሰንደቅ ዓላማ እንዲወጣ መደረጉን ገልጸዋል። ነገር ግን “አሁንም የኢራን ሴቶችን እንደግፋለን” ብለዋል። ኢራን አሜሪካንን እና ሌሎች ባላንጣዎቿን በአገሯ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ በማባባስ የምትከስ ሲሆን፣ የኢራን መንግሥት በተቃዋሚዎች ላይ እየወሰደ ካለው እርምጃ ጋር ተያይዞ አሜሪካ በአገሪቱ ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ነው። በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ላይ በምድብ ለ ከእንግሊዝ፣ ከአሜሪካ እና ከዌልስ ጋር የተደለደለችው ኢራን ሦስት ነጥብ ይዛ ከእንግሊዝ በመከተል በምድቡ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በእግሊዝ 6 ለ 2 ተሸንፋ ዌልስን 2 ለ 0 ያሸነፈችው ኢራን የምድቡ ወሳኝ ጨዋታዋን ነገ ማክሰኞ ኅዳር 20/2015 ዓ.ም. ከአሜሪካ ጋር ታደርጋለች። ኢራን ታካሂደዋለች በሚባለው የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ግንባታ ፕሮጀክት የተነሳ ለዓመታት እየተወዛገበቻት ከምትገኘው ከአሜሪካ ጋር በአንድ ምድብ ተደልድለው ከጨዋታቸው ቀደም ብሎ ከሰንደቅ ዓላማዋ ጋር በተያያዘ ቅሬታዋን አቅርባለች። አሜሪካ እና ኢራን በአይነ ቁራኛ የሚጠባበቁ ባላንጣዎች ሲሆኑ፣ የዲፕሎማቲክ ግንኙነታቸውን ካቋረጡ ከአርባ ዓመታት በላይ ሆኗቸዋል። | ከወሳኝ የምድብ ጨዋታቸው በፊት ኢራን በአሜሪካ ላይ ለፊፋ ክስ አቀረበች የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአሜሪካን ቡድን በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቹ ላይ ካወጣው የኢራን ሰንደቅ ዓላማ ጋር በተያያዘ ለፊፋ ክስ አቀረበ። የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ለዓለም አቀፉ የእግር ኳስ የበላይ አካል አቤቱታ ያረበው የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የኢራን ብሎ ያወጣው ሰንደቅ ዓላማ እስላማዊ ሪፐብሊኳን የሚወክለውን አርማ አንስቶታል የሚል ነው። ኢራን እና አሜሪካ ነገ ማክሰኞ ከሚኖራቸው የዓለም ዋንጫ የምድብ ግጥሚያ በፊት፣ የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን በትዊተር፣ በፌስቡክ እና በኢንስታ ግራም ላይ ከለጠፈው የኢራን ባንዲራ ላይ የአገሪቱ መለያ አርማ አልተካተተም። አሜሪካ ለዚህ ክስ በሰጠችው ምላሽ በአገሪቱ ውስጥ እየተካሄዱ ካሉት ፀረ መንግሥት ተቃውሞዎች ጋር በተያያዘ “በኢራን መሠረታዊ መብቶች እንዲከበሩ እየታገሉ ላሉት ሴቶች ድጋፈችንን ለመግለጽ” የአገሪቱን ይፋዊ ሰንደቅ ዓላማ ላለመጠቀም መወሰኑን ገልጻለች። በኢራን ውስጥ ማህሳ አሚኒ የተባለች የ22 ዓመት ወጣት ሂጃብ በአግባቡ አልለበሰችም በሚል በአገሪቱ የሥነ ምግባር ፖሊሶች ተይዛ ከታሰረች በኋላ መሞቷን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው። “ሙያዊነት በጎደለው ተግባር፣ የአሜሪካ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢንስታግራም ገጽ በሰንደቅ ዓላማው ላይ ያለውን የአላህ ምልክትን አስወግዶታል” ሲል የኢራን መንግሥት ዜና ወኪል ኢርና ገልጸወል። ይህንንም ተከትሎ “የኢራን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የእግር ኳስ የበላይ አስተዳዳሪው አካል ፊፋ ለአሜሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠንካራ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ኢሜይል ልኳል።” በኋላ ላይ ግን አንድ የአሜሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቃል አቀባይ እንዳሉት፣ ቅሬታ የቀረበበት የሰንደቅ ዓላማ ምስል ከማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ እንዲነሱ መደረጋቸውንና በምትካቸውም ትክክለኛው የኢራን ሰንደቅ ዓላማ እንዲወጣ መደረጉን ገልጸዋል። ነገር ግን “አሁንም የኢራን ሴቶችን እንደግፋለን” ብለዋል። ኢራን አሜሪካንን እና ሌሎች ባላንጣዎቿን በአገሯ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ በማባባስ የምትከስ ሲሆን፣ የኢራን መንግሥት በተቃዋሚዎች ላይ እየወሰደ ካለው እርምጃ ጋር ተያይዞ አሜሪካ በአገሪቱ ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ነው። በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ላይ በምድብ ለ ከእንግሊዝ፣ ከአሜሪካ እና ከዌልስ ጋር የተደለደለችው ኢራን ሦስት ነጥብ ይዛ ከእንግሊዝ በመከተል በምድቡ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በእግሊዝ 6 ለ 2 ተሸንፋ ዌልስን 2 ለ 0 ያሸነፈችው ኢራን የምድቡ ወሳኝ ጨዋታዋን ነገ ማክሰኞ ኅዳር 20/2015 ዓ.ም. ከአሜሪካ ጋር ታደርጋለች። ኢራን ታካሂደዋለች በሚባለው የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ግንባታ ፕሮጀክት የተነሳ ለዓመታት እየተወዛገበቻት ከምትገኘው ከአሜሪካ ጋር በአንድ ምድብ ተደልድለው ከጨዋታቸው ቀደም ብሎ ከሰንደቅ ዓላማዋ ጋር በተያያዘ ቅሬታዋን አቅርባለች። አሜሪካ እና ኢራን በአይነ ቁራኛ የሚጠባበቁ ባላንጣዎች ሲሆኑ፣ የዲፕሎማቲክ ግንኙነታቸውን ካቋረጡ ከአርባ ዓመታት በላይ ሆኗቸዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c4n6exxx0e9o |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ የአስትራዜንካን ክትባት ተጠቀሙ- የዓለም ጤና ድርጅት | በርካታ የአውሮፓ ሃገራት የኮሮናቫይረስ መከላከያ የሆነውን አስትራዜንካ ክትባት ማገዳቸውን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት ክትባቱን እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርቧል። ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያንና ስፔይንን ጨምሮ ሌሎች አገራት የኦክስፎርዱ አስትራዜንካ ክትባት ደም መርጋት በተያያዘ ችግር አለበት በሚል ክትባቱ እንዳይሰጥ አግደውታል። የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ደም መርጋት ስለማስከተሉ ምንም አይነት ማስረጃ የለም ይላል። የድርጅቱ የክትባት ደህንነት ልሂቃንም በዛሬው ዕለት ተሰብስበው ስለ ክትባቱ ይመክራሉ ተብሏል። የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲም እንዲሁ ስለ ክትባቱ በዛሬው ዕለት የሚወያዩ ሲሆን በያዝነው ሃሙስም የደረሱበትን ማጠቃለያ ለህዝብ ያሳውቃሉ ተብሏል። ሆኖም ኤጀንሲው ክትባቱን ተጠቀሙ ብሏል። በአውሮፓ ክትባቱን ከተከተቡ በኋላ የደም መርጋት ችግር ያጋጠማቸው ሰዎች አሉ ብሏል። ነገር ግን ባለሙያዎቹ እንደሚሉት በአጠቃላይ ከህዝብ ብዛቱ ጋር ሲነፃፀር የደም መርጋት ያጋጠማቸው ሰዎች ድንገተኛ መጨመር አላሳየም ይላሉ ። በአውሮፓ ህብረት አባላት አገራትና ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ 17 ሚሊዮን ሰዎች የአስትራዜንካ ክትባትን መከተባቸውና ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ 40ዎቹ የደም መርጋት ችግር እንዳጋጠማቸው አስትራዜንካ አስታውቋል። እየተወሰዱ ያሉ ጥንቃቄዎች ይህንንም ተከትሎ የጀርመን ጤና ሚኒስቴር በያዝነው ሳምንት ሰኞ ዕለት አስትራዜንካ ክትባት መስጠት በአስቸኳይ እንዲቆም ትዕዛዝ አስተላልፏል። ክትባቱ የአዕምሮ ደም መርጋት ወይም ሴሬብራል ቬይን ቶርምቦሲስ ችግር ጋር መገናኘቱን አይተናል ብለዋል። የጤና ሚኒስትሩ ጄንስ ስፋን እንዳሉት ውሳኔ "ፖለቲካዊ" እንዳልሆነ ነው። "ሁላችንም ቢሆን ይህ ውሳኔ ሊያስከትለው የሚችለውን ጉዳት እንረዳለን። በቀላሉም የደረስንበት አይደለም" ብለዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እንዲሁ የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲ ውሳኔውን እስኪያሳውቅ ድረስ አገራቸው ክትባቱን ታግዳለች ብለዋል። "ቀለል ያለ መመሪያ ነው ያለን፤ ሳይንስንና በዘርፉ ላይ ዕውቀት ያላቸውን የጤና ባለስልጣናት ምክር ነው የምንከተለው፤ ይህም የአውሮፓ ስትራቴጂ ምን መምሰል አለበት የሚለውን የሚጠቁም ይሆናል" ብለዋል። የጣልያን መድኃኒት ኤጀንሲም እንዲሁ የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲ የሚደርስበትን ማጠቃለያ እጠብቃለሁ በማለት አግዳዋለች። የስፔን ጤና ሚኒስትር ካሮሊና ዳሪያስ በበኩላቸው ክትባቱ ለመጪው ሁለት ሳምንት ይታገዳል ብለዋል። አየርላንድ፣ ፖርቹጋል፣ዴንማርክ፣ ኖርዌይ፣ ቡልጋሪያ፣ አይስላንድ፣ ስሎቬኒያ ክትባቱን በጊዜያዊነት ያገዱ ሲሆን ዲሞክራቲክ ኮንጎና ኢንዶኔዥያ የክትባት መስጪያ ጊዜያቸውን አራዝመውታል። ኦስትሪያን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ አገራት ለጥንቃቄ ሲሊ ቢያግዱትም ቤልጂየም፣ ፖላንድና ቼክ ሪፐብሊክ ክትባቱን እየሰጡ ነው። የቤልጂየም ጤና ሚኒስትር ፍራንክ ቫንደንብራውኬ እንዳስታወቁት ቤልጂየም ካላት ከፍተኛ የኮሮናቫይረስ ህሙማን ቁጥርን በማየት ክትባቱን አለመስጠት አትችልም ብለዋል። የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በበኩላቸው አስትራዜንካን ጨምሮ በአገሪቱ እየተሰጡ ያሉ ክትባቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን የጤና ባለስልጣናቱ ነግረውኛል ብለዋል። | ኮሮናቫይረስ፡ የአስትራዜንካን ክትባት ተጠቀሙ- የዓለም ጤና ድርጅት በርካታ የአውሮፓ ሃገራት የኮሮናቫይረስ መከላከያ የሆነውን አስትራዜንካ ክትባት ማገዳቸውን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት ክትባቱን እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርቧል። ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያንና ስፔይንን ጨምሮ ሌሎች አገራት የኦክስፎርዱ አስትራዜንካ ክትባት ደም መርጋት በተያያዘ ችግር አለበት በሚል ክትባቱ እንዳይሰጥ አግደውታል። የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ደም መርጋት ስለማስከተሉ ምንም አይነት ማስረጃ የለም ይላል። የድርጅቱ የክትባት ደህንነት ልሂቃንም በዛሬው ዕለት ተሰብስበው ስለ ክትባቱ ይመክራሉ ተብሏል። የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲም እንዲሁ ስለ ክትባቱ በዛሬው ዕለት የሚወያዩ ሲሆን በያዝነው ሃሙስም የደረሱበትን ማጠቃለያ ለህዝብ ያሳውቃሉ ተብሏል። ሆኖም ኤጀንሲው ክትባቱን ተጠቀሙ ብሏል። በአውሮፓ ክትባቱን ከተከተቡ በኋላ የደም መርጋት ችግር ያጋጠማቸው ሰዎች አሉ ብሏል። ነገር ግን ባለሙያዎቹ እንደሚሉት በአጠቃላይ ከህዝብ ብዛቱ ጋር ሲነፃፀር የደም መርጋት ያጋጠማቸው ሰዎች ድንገተኛ መጨመር አላሳየም ይላሉ ። በአውሮፓ ህብረት አባላት አገራትና ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ 17 ሚሊዮን ሰዎች የአስትራዜንካ ክትባትን መከተባቸውና ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ 40ዎቹ የደም መርጋት ችግር እንዳጋጠማቸው አስትራዜንካ አስታውቋል። እየተወሰዱ ያሉ ጥንቃቄዎች ይህንንም ተከትሎ የጀርመን ጤና ሚኒስቴር በያዝነው ሳምንት ሰኞ ዕለት አስትራዜንካ ክትባት መስጠት በአስቸኳይ እንዲቆም ትዕዛዝ አስተላልፏል። ክትባቱ የአዕምሮ ደም መርጋት ወይም ሴሬብራል ቬይን ቶርምቦሲስ ችግር ጋር መገናኘቱን አይተናል ብለዋል። የጤና ሚኒስትሩ ጄንስ ስፋን እንዳሉት ውሳኔ "ፖለቲካዊ" እንዳልሆነ ነው። "ሁላችንም ቢሆን ይህ ውሳኔ ሊያስከትለው የሚችለውን ጉዳት እንረዳለን። በቀላሉም የደረስንበት አይደለም" ብለዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እንዲሁ የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲ ውሳኔውን እስኪያሳውቅ ድረስ አገራቸው ክትባቱን ታግዳለች ብለዋል። "ቀለል ያለ መመሪያ ነው ያለን፤ ሳይንስንና በዘርፉ ላይ ዕውቀት ያላቸውን የጤና ባለስልጣናት ምክር ነው የምንከተለው፤ ይህም የአውሮፓ ስትራቴጂ ምን መምሰል አለበት የሚለውን የሚጠቁም ይሆናል" ብለዋል። የጣልያን መድኃኒት ኤጀንሲም እንዲሁ የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲ የሚደርስበትን ማጠቃለያ እጠብቃለሁ በማለት አግዳዋለች። የስፔን ጤና ሚኒስትር ካሮሊና ዳሪያስ በበኩላቸው ክትባቱ ለመጪው ሁለት ሳምንት ይታገዳል ብለዋል። አየርላንድ፣ ፖርቹጋል፣ዴንማርክ፣ ኖርዌይ፣ ቡልጋሪያ፣ አይስላንድ፣ ስሎቬኒያ ክትባቱን በጊዜያዊነት ያገዱ ሲሆን ዲሞክራቲክ ኮንጎና ኢንዶኔዥያ የክትባት መስጪያ ጊዜያቸውን አራዝመውታል። ኦስትሪያን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ አገራት ለጥንቃቄ ሲሊ ቢያግዱትም ቤልጂየም፣ ፖላንድና ቼክ ሪፐብሊክ ክትባቱን እየሰጡ ነው። የቤልጂየም ጤና ሚኒስትር ፍራንክ ቫንደንብራውኬ እንዳስታወቁት ቤልጂየም ካላት ከፍተኛ የኮሮናቫይረስ ህሙማን ቁጥርን በማየት ክትባቱን አለመስጠት አትችልም ብለዋል። የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በበኩላቸው አስትራዜንካን ጨምሮ በአገሪቱ እየተሰጡ ያሉ ክትባቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን የጤና ባለስልጣናቱ ነግረውኛል ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56411232 |
5sports
| ቅርጫት ኳስ ፡ የኦባማ እና የጆርዳን የቅርጫት ኳስ መለያዎች በከፍተኛ ገንዘብ በጨረታ ተሸጡ | በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማና በታዋቂው የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ኮከብ ማይክል ጆርዳን የተለበሱ ሁለት የቅርጫት ኳስ መለያዎች አርብ ዕለት ሎስ አንጀለስ ከተማ ውስጥ በተካሄደ ጨረታ ክብረ ወሰን ነው በተባለ ከፍተኛ ገንዘብ ተሸጡ። ታዋቂው የቅርጫት ኳስ ኮከብ ማይክል ጆርዳን በ1984 (እአአ) ለቺካጎ ቡልስ ቡድን ለመጫወት በፈረመበት ጊዜ የለበሰው ባለ 23 ቁጥር መለያ ለጨረታ ቀርቦ 320 ሺህ ዶላር ተሽጧል። ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ለትምህርት ቤታቸው ፑናሁ ቡድን በተጫወቱበት ጊዜ ለብሰውት የነበረው መለያ ደግሞ በ192 ሺህ ዶላር ሲሸጥ፤ ይህም በጨረታ ከተሸጡ የተማሪዎች መለያ ከፍተኛውን ዋጋ አውጥቷል። ባለፈው ዓመት በተካሄደ ጨረታ ኦባማ ተማሪ ሳሉ ለብሰውት የነበረ ሌላ የቅርጫት ኳስ መለያ በ120 ሺህ ዶላር ተሽጦ ነበር። በከፍተኛ ዋጋ የተሸጠው የኦባማ መለያ የትምህርት ቤታቸው ቡድን በ1979 (እአአ) የሃዋይ የቅርጫት ኳስ ውድድርን ባሸነፈበት ጊዜ ለብሰውት የነበረው ባለ 23 ቁጥር መለያ ነው። የቀድሞው ፕሬዝደንት ለቅርጫት ኳስ ስፖርት ከፍተኛ ፍቅር ያላቸው ሲሆን፤ በቅርቡ ባሳተሙት መጽሐፋቸው ላይ የተፎካካሪ ቡድን አባላት ወላጆች ተገቢ ያልሆነ የበላይነትን እንዲያገኙ አድርገዋል በሚል ቅሬታ በማሰማታቸው ልጃቸው ሳሻ የምትጫወትበትን የቅርጫት ኳስ ቡድን ማሰልጠን እንደተዉ ጽፈዋል። የመጀመሪያው ቢሊየነር ስፖርተኛ የሆነው ኮከቡ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ጆርዳን ቡድኑ ቺካጎ ቡልስ በአሜሪካ የቅርጫት ኳስ ውድድር የበላይ ሆኖ ስድስት ጊዜ አሸናፊ ለመሆን አስችሎታል። የጆርዳን መለያዎች በተለያዩ ጊዜያት በጨረታ የተሸጡ ሲሆን፤ ከዚህ በፊት ከተሸጡ 23 ቁጥር መለያዎች ከፍተኛው 288,000 ዶላር ነበር። | ቅርጫት ኳስ ፡ የኦባማ እና የጆርዳን የቅርጫት ኳስ መለያዎች በከፍተኛ ገንዘብ በጨረታ ተሸጡ በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማና በታዋቂው የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ኮከብ ማይክል ጆርዳን የተለበሱ ሁለት የቅርጫት ኳስ መለያዎች አርብ ዕለት ሎስ አንጀለስ ከተማ ውስጥ በተካሄደ ጨረታ ክብረ ወሰን ነው በተባለ ከፍተኛ ገንዘብ ተሸጡ። ታዋቂው የቅርጫት ኳስ ኮከብ ማይክል ጆርዳን በ1984 (እአአ) ለቺካጎ ቡልስ ቡድን ለመጫወት በፈረመበት ጊዜ የለበሰው ባለ 23 ቁጥር መለያ ለጨረታ ቀርቦ 320 ሺህ ዶላር ተሽጧል። ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ለትምህርት ቤታቸው ፑናሁ ቡድን በተጫወቱበት ጊዜ ለብሰውት የነበረው መለያ ደግሞ በ192 ሺህ ዶላር ሲሸጥ፤ ይህም በጨረታ ከተሸጡ የተማሪዎች መለያ ከፍተኛውን ዋጋ አውጥቷል። ባለፈው ዓመት በተካሄደ ጨረታ ኦባማ ተማሪ ሳሉ ለብሰውት የነበረ ሌላ የቅርጫት ኳስ መለያ በ120 ሺህ ዶላር ተሽጦ ነበር። በከፍተኛ ዋጋ የተሸጠው የኦባማ መለያ የትምህርት ቤታቸው ቡድን በ1979 (እአአ) የሃዋይ የቅርጫት ኳስ ውድድርን ባሸነፈበት ጊዜ ለብሰውት የነበረው ባለ 23 ቁጥር መለያ ነው። የቀድሞው ፕሬዝደንት ለቅርጫት ኳስ ስፖርት ከፍተኛ ፍቅር ያላቸው ሲሆን፤ በቅርቡ ባሳተሙት መጽሐፋቸው ላይ የተፎካካሪ ቡድን አባላት ወላጆች ተገቢ ያልሆነ የበላይነትን እንዲያገኙ አድርገዋል በሚል ቅሬታ በማሰማታቸው ልጃቸው ሳሻ የምትጫወትበትን የቅርጫት ኳስ ቡድን ማሰልጠን እንደተዉ ጽፈዋል። የመጀመሪያው ቢሊየነር ስፖርተኛ የሆነው ኮከቡ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ጆርዳን ቡድኑ ቺካጎ ቡልስ በአሜሪካ የቅርጫት ኳስ ውድድር የበላይ ሆኖ ስድስት ጊዜ አሸናፊ ለመሆን አስችሎታል። የጆርዳን መለያዎች በተለያዩ ጊዜያት በጨረታ የተሸጡ ሲሆን፤ ከዚህ በፊት ከተሸጡ 23 ቁጥር መለያዎች ከፍተኛው 288,000 ዶላር ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/news-55156386 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ በፈረንሳይ ከተሞች የሰዓት እላፊ ታወጀ | የፈረንሳይ መዲና ፓሪስን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች የሰዓት እላፊ ታወጀ። የሰዓት እላፊ የታወጀው እየጨመረ የመጣውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ነው። ፈረንሳይ ከአውሮፓ የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ከሆኑባቸው አገራት መካከል አንዷ ናት። የሰዓት እላፊ በታወጀባቸው ከተሞች የሚኖሩ ዜጎች ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ ከቤት መውጣት አይችሉም። የሰዓት እላፊው ከታወጀባቸው ከተሞች መካከል ፓሪስ፣ ማርሴል፣ ሊዮን እና ሊል ይገኙበታል። 20 ሚሊዮን ፈረንሳውያን የሰዓት እላፊው አዋጅ ይተገበርባቸዋል። የፈረንሳይ መንግሥት የሰዓት እላፊ አዋጁ መተግበሩን የሚያረጋግጡ 12ሺህ የፖሊስ አባላት እንደሚያሰማራ አስታውቋል። ከምሽቱ 3 ሰዓት በፊት ምግብ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ ካፊቴሪያዎች እና ሲኒማ ቤቶች መዘጋት ይኖርባቸዋል። የሰዓት እላፊውን ተላልፎ የሚገኝ ሰው 135 ዩሮ የሚቀጣ ሲሆን፤ ዳግም ተላልፎ የተገኘ ደግሞ የስድስት ወራት እስር እና የ3ሺህ 700 ዩሮ ቅጣት ይጠብቀዋል። እንደ ሰርግ ያሉ ማህበራዊ ሰብስቦች ክልክል ናቸው። በፈረንሳይ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ከ32ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ኮሮናቫይረስ በሌሎች የአውሮፓ አገራት የስፔን መንግሥት በማድሪድ እና አካባቢዋ ለ15 ቀናት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል። 7ሺህ ፖሊስ አባላት አዋጁን ያስፈጽማሉ። መሠረታዊ ላልሆኑ ጉዳዮች ከማድሪድ መውጣትም ሆነ መግባት ክልክል ነው። ሆቴሎች እና ምግብ ቤቶች መያዝ ከሚችሉት አቅማቸው ግማሹን ብቻ ነው ማስተናገድ የሚችሉት። በኔዘርላንድስ የቫይረሱ ስርጭት ዳግም እያገረሸ ይገኛል። በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍልም በከፊል የእንቅስቃሴ ገደቦች እየተጣሉ ይገኛሉ። በአምስተርዳም መጠጥ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች እየተዘጉ ነው። በጀርመንም በተመሳሳይ የቫይረሱ ስርጭት እየጨመረ ይገኛል። በቀን ከ7ሺህ በላይ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እየተመዘገቡ ይገኛል። ጀርመን አንዳንድ ጎረቤት አገራትን የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ደረጃ ደርሶባቸዋል ስትል አውጃለች። ከእነዚህም መካከል ፈረንሳይ እና ኔዘርላንድስ ተጠቃሽ ናቸው። ከእነዚህ አገራት ወደ ጀርመን የሚገባ ተጓዥ ራሱን ለይቶ የማቆየት ግዴታ ይኖርበታል። አየርላንድ በበኩሏ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የተለያዩ ገደቦችን ከጣለች አራት ሳምንታት አልፈዋታል። በመኖሪያ ቤት ሄዶ ወዳጅ ዘመድ መጠየቅ ከተከለከለ ሰነባብቷል። | ኮሮናቫይረስ፡ በፈረንሳይ ከተሞች የሰዓት እላፊ ታወጀ የፈረንሳይ መዲና ፓሪስን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች የሰዓት እላፊ ታወጀ። የሰዓት እላፊ የታወጀው እየጨመረ የመጣውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ነው። ፈረንሳይ ከአውሮፓ የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ከሆኑባቸው አገራት መካከል አንዷ ናት። የሰዓት እላፊ በታወጀባቸው ከተሞች የሚኖሩ ዜጎች ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ ከቤት መውጣት አይችሉም። የሰዓት እላፊው ከታወጀባቸው ከተሞች መካከል ፓሪስ፣ ማርሴል፣ ሊዮን እና ሊል ይገኙበታል። 20 ሚሊዮን ፈረንሳውያን የሰዓት እላፊው አዋጅ ይተገበርባቸዋል። የፈረንሳይ መንግሥት የሰዓት እላፊ አዋጁ መተግበሩን የሚያረጋግጡ 12ሺህ የፖሊስ አባላት እንደሚያሰማራ አስታውቋል። ከምሽቱ 3 ሰዓት በፊት ምግብ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ ካፊቴሪያዎች እና ሲኒማ ቤቶች መዘጋት ይኖርባቸዋል። የሰዓት እላፊውን ተላልፎ የሚገኝ ሰው 135 ዩሮ የሚቀጣ ሲሆን፤ ዳግም ተላልፎ የተገኘ ደግሞ የስድስት ወራት እስር እና የ3ሺህ 700 ዩሮ ቅጣት ይጠብቀዋል። እንደ ሰርግ ያሉ ማህበራዊ ሰብስቦች ክልክል ናቸው። በፈረንሳይ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ከ32ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ኮሮናቫይረስ በሌሎች የአውሮፓ አገራት የስፔን መንግሥት በማድሪድ እና አካባቢዋ ለ15 ቀናት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል። 7ሺህ ፖሊስ አባላት አዋጁን ያስፈጽማሉ። መሠረታዊ ላልሆኑ ጉዳዮች ከማድሪድ መውጣትም ሆነ መግባት ክልክል ነው። ሆቴሎች እና ምግብ ቤቶች መያዝ ከሚችሉት አቅማቸው ግማሹን ብቻ ነው ማስተናገድ የሚችሉት። በኔዘርላንድስ የቫይረሱ ስርጭት ዳግም እያገረሸ ይገኛል። በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍልም በከፊል የእንቅስቃሴ ገደቦች እየተጣሉ ይገኛሉ። በአምስተርዳም መጠጥ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች እየተዘጉ ነው። በጀርመንም በተመሳሳይ የቫይረሱ ስርጭት እየጨመረ ይገኛል። በቀን ከ7ሺህ በላይ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እየተመዘገቡ ይገኛል። ጀርመን አንዳንድ ጎረቤት አገራትን የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ደረጃ ደርሶባቸዋል ስትል አውጃለች። ከእነዚህም መካከል ፈረንሳይ እና ኔዘርላንድስ ተጠቃሽ ናቸው። ከእነዚህ አገራት ወደ ጀርመን የሚገባ ተጓዥ ራሱን ለይቶ የማቆየት ግዴታ ይኖርበታል። አየርላንድ በበኩሏ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የተለያዩ ገደቦችን ከጣለች አራት ሳምንታት አልፈዋታል። በመኖሪያ ቤት ሄዶ ወዳጅ ዘመድ መጠየቅ ከተከለከለ ሰነባብቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54581080 |
0business
| የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ከፍተኛ መጠን ያለው የስንዴና ዘይት ግዢ መፈጸሙ ተገለጸ | በኢትዮጵያ ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት 4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴና 12.5 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። ግዢው የተፈጸመው በጥቅምትና ኅዳር ወራት ሲሆን ከተገዛው 4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኩንታል ስንዴ ወደ አገር ውስጥ መግባቱም ተገልጿል። የተቀረውም ስንዴ በተቻለ ፍጥነት ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት በሂደት ላይ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ የስንዴ ዋጋንም ከፍ እንዳይል የራሱ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብሏል ገንዘብ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ዛሬ ታኅሣሥ 26/2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ። ግዢ የተፈጸመበት 12.5 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት በሂደት ላይ መሆኑንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል። ከፍተኛ መጠን ያለው ስንዴና ዘይት ግዢ መፈጸሙ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠርና የገበያ ዋጋን በማረጋጋት ረገድ ፋይዳ እንዳለው የተገለጸ ሲሆን የተረጋጋ ማክሮ ምጣኔ ሀብት ከማስፈን አንፃርም ሚና ይጫወታል ተብሏል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማት የመቶ ቀን እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በተካሄደበት ወቅት ነውም ይህንን የገለጸው። በተጨማሪም ዘይትና ዱቄት አስመጪዎች በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ እንዲያስገቡ በመደረጉ የሸቀጦች ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል አስችሏልም ተብሏል። በሰሜኑ ጦርነትና በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት የዋጋ ግሽበት አስከትሎባታል በተባለችው ኢትዮጵያ በተወሰነ መልኩ መቀነስም አሳይቷል ተብሏል። በያዝነው ዓመት ጥቅምት ወር 34.2 በመቶ የነበረው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በኅዳር ወር ወደ 33.0 በመቶ ዝቅ ብሏል። በተጨማሪም በ2014 በኅዳር ወር የምግብ ዋጋ ግሽበት ከጥቅምት ወር ጋር ሲነጻጸር በ1.8 በመቶ የቀነሰ ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት 1.0 ከመቶ የጨመረ መሆኑን መረጃው ጠቁሟል። | የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ከፍተኛ መጠን ያለው የስንዴና ዘይት ግዢ መፈጸሙ ተገለጸ በኢትዮጵያ ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት 4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴና 12.5 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። ግዢው የተፈጸመው በጥቅምትና ኅዳር ወራት ሲሆን ከተገዛው 4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኩንታል ስንዴ ወደ አገር ውስጥ መግባቱም ተገልጿል። የተቀረውም ስንዴ በተቻለ ፍጥነት ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት በሂደት ላይ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ የስንዴ ዋጋንም ከፍ እንዳይል የራሱ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብሏል ገንዘብ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ዛሬ ታኅሣሥ 26/2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ። ግዢ የተፈጸመበት 12.5 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት በሂደት ላይ መሆኑንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል። ከፍተኛ መጠን ያለው ስንዴና ዘይት ግዢ መፈጸሙ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠርና የገበያ ዋጋን በማረጋጋት ረገድ ፋይዳ እንዳለው የተገለጸ ሲሆን የተረጋጋ ማክሮ ምጣኔ ሀብት ከማስፈን አንፃርም ሚና ይጫወታል ተብሏል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማት የመቶ ቀን እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በተካሄደበት ወቅት ነውም ይህንን የገለጸው። በተጨማሪም ዘይትና ዱቄት አስመጪዎች በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ እንዲያስገቡ በመደረጉ የሸቀጦች ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል አስችሏልም ተብሏል። በሰሜኑ ጦርነትና በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት የዋጋ ግሽበት አስከትሎባታል በተባለችው ኢትዮጵያ በተወሰነ መልኩ መቀነስም አሳይቷል ተብሏል። በያዝነው ዓመት ጥቅምት ወር 34.2 በመቶ የነበረው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በኅዳር ወር ወደ 33.0 በመቶ ዝቅ ብሏል። በተጨማሪም በ2014 በኅዳር ወር የምግብ ዋጋ ግሽበት ከጥቅምት ወር ጋር ሲነጻጸር በ1.8 በመቶ የቀነሰ ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት 1.0 ከመቶ የጨመረ መሆኑን መረጃው ጠቁሟል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59868390 |
3politics
| የኢትዮጵያን ምጣኔ ሀብታዊ እመርታ ስጋት ላይ የጣለው ጦርነት | ባለፉት አስር ወራት የተደረገው ጦርነት ኢትዮጵያን ከፍተኛ ሰብዓዊ ኪሳራ ውስጥ ከቷታል። በሺዎች የሚቆጠሩ ተገድለዋል፤ ሚሊዮኖች ተፈናቅለዋል እንዲሁም ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው በርካቶች ናቸው። ጦርነቱ በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ በሆነችው ኢትዮጵያ እያደረሰው ያለው ጉዳት ይህ ብቻ አይደለም። ከፍተኛ የሆነ ምጣኔ ሀብታዊ ወጪን አስከትሏል፤ ይህንንም ለመጠገን ዓመታት ሊወስድ ይችላል። በመዲናዋ አዲስ አበባ ነዋሪ የሆነችውና ሙሉ ስሟ እንዳይጠቀስ የጠየቀችው የ26 ዓመቷ ትዕግስት ወርሃዊ ወጪዋ በሁለት ምክንያቶች በእጥፍ ጨምሯል ትላለች። እነዚህም በጥቅምት ወር ወር በሠሜናዊ ትግራይ ክልል የተቀሰቀሰው ጦርነት እና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ናቸው። "ከኮቪድ-19 እና ከግጭቱ በፊት መሠረታዊ ሸቀጦችን ለመሸመት በየወሩ አንድ ሺህ ብር አወጣ ነበር። በአሁኑ ወቅት ግን ይህ ወጪ ተመንድጎ ሁለት ሺህ ብር ሆኗል" ትላለች። አክላም "አሁን በርካታ ነገሮች ዋጋቸው የማይቀመስ ሆኗል ለምሳሌ - ስልኮች፣ ምግብ እና አልባሳት።" ይፋዊ የሆነውን ስታቲስቲክስ በምንመለከትበትም ወቅት የመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ዋጋ በእርግጥም በኢትዮጵያ ጨምሯል። በዚህም ከአንድ ዓመት በፊት በሐምሌ ወር የነበረውና የዘንድሮው ዋጋ ሲነፃፀር በአማካይ ሩብ ያህል ውድ ሆኗል። ትግስት ቤተሰቦቿን ለመደገፍ በትልቅ የገበያ መደብር (ሱፐርማርኬት) ውስጥ በገንዘብ ተቀባይነት ተቀጥራ ትሰራለች። ወንድሟ የቤት ኪራዩን የሚሸፍን ሲሆን የምግቡ ወጪ ደግሞ የእሷ ኃላፊነት ነው። "የዶላር ምንዛሪ ጥሩ አይደለም ለምሳሌ ባለፈው ዓመት 1 ዶላር በ35 ብር ሲመነዘር የነበረ ሲሆን በአሁ ወቅት ግን የአንድ ዶላር ምንዛሬ ወደ 45 ብር አሻቅቧል" ትላለች። የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ ተንታኝ የሆኑትና መቀመጫቸውን በአሜሪካ ያደረጉት ፋይሰል ሮብሌ አገሪቷ በጦርነት ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰሷ "በእውነቱ ኢትዮጵያ ዶላር የማግኘት አቅሟ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል" እና የምንዛሪው ተመንም እንዲባባስ ምክንያት ሆኗል ይላሉ። ጦርነቱ አገሪቱን ምን ያህል እንዳስወጣ እስካሁን ግልፅ አይደለም ነገር ግን በትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ ትንበያ መሰረት ወታደራዊ ወጪዋ በመጪው ታኅሣሥ ወር መጨረሻ ላይ ወደ 502 ሚሊዮን ዶላር ሊደርስ ይችላል ብሏል። በባለፈው ዓመት 460 ሚሊዮን ዶላር ነበር። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ባለፈው ሳምንት ጦርነቱ "ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ከአገሪቱ ካዝና አስወጥቷል" ብለዋል። ከዓለም አቀፉ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እና ከጦርነቱ በፊት የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት በቀጠናው በፍጥነት በማደግ ላይ ከነበሩ አንዱ ነበር። ከዓለም ባንክ የተገኘውም መረጃም አገሪቱ ከሁለት ዓመት በፊት በነበረው አስር ዓመታት ውስጥ እድገቷ በዓመት በአማካይ 10 በመቶ ነበር። ትዕግስት የጠቀሰቸው በባንኮች የሚመነዘረውን የውጭ ምንዛሪ ሲሆን መደበኛ ባልሆነው ገበያ ውስጥ ግን የብር ዋጋ በእጅጉ አሽቆልቁሎ ወደ አንድ ዶላር 65 ብር እንደሚመነዘር ፋይሰል ተናግሯል። ጨምሮም በአገሪቱ ያሉ የነጋዴዎች ጦርነቱ ከትግራይ ተሻግሮ ወደ አጎራባቾቹ የአፋርና የአማራ ክልሎች በመስፋፋቱ እያሽቆቆለ ያለው የደኅንነት ሁኔታ በእጅጉ ያሳስባቸዋል። በርካቶቹም ከአካውንታቸው ገንዘባቸውን እያወጡ እራሷን ነጻ አገር አድርጋ ወዳወጀችው ሶማሌላንድ በማሻገር በመቀየር የብር የመግዛት አቅምን የበለጠ እንዲዳከም እያደረገው መሆኑን ፋይሳል ይገልጻል። በትግራይ የባንኮች መዘጋት የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ መክሰምና የምርጫ መራዘምን ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሚመራው አስተዳርና በህወሓት መካከል የነበረው አለመግባባት ተካሮ በነበረበት ጊዜ በፌደራሉ ወታደራዊ የጦር ሰፈር ላይ ትግራይ ውስጥ ጥቃት ሲሰነዘር ነበር ጦርነቱ የተቀሰቀሰው። ከጥቅምት ወር ማብቂያ ጀምሮ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የኤርታራ ወታደሮች፣ የክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሻዎች ከትግራይ ኃይሎች ጋር ደም አፋሳሽ ጦርነት አካሂደዋል። በዚህም ጊዜ አስገድዶ መድፈርና የሰላማዊ ሰዎች የጅምላ ግድያን ጨምሮ ጭፍጨፋዎችን በመፈጸም ሁሉም ወገኖች ሲከሰሱ ቆይተዋል። ባለፈው ሰኔ ወር አማጺያኑ የክልሉን ዋና ከተማ መልሰው ከያዙ በኋላ በትግራይ ውስጥ የፌደራል መንግሥቱ የቴሌኮሚዩኒኬሽንና ባንኮችን አገልግሎቶችን ጨምሮ መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ አድርጓል። ትግራይ ሙሉ በሙሉ ተዘግታለች። በትግራይ ከ 400 ሺህ በላይ ሰዎች በረሃብ አፋፍ ላይ ናቸው። የእርዳታ ስርጭቱ በከፍተኛ ሁኔታ ተመናምኖ የኤሌክትሪክ እና የነዳጅ አቅርቦቶች ባለመኖሩም የሸቀጦች ዋጋ እንዲንር አድርጎታል። የመቀለ ነዋሪ የሆነው ፊልሞን ብርሃኔ ለቢቢሲ ትግርኛ እንደተናገረው ምግብና ኪራይ ሰሞኑን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተናግሯል። "ሁሉም ባንኮች ተዘግተው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ደመወዝ ስለማይከፍሉ ገንዘብ የለም" ይላል። የቴሌኮም ጨረታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጦርነቱ ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ባላት ስም ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያሳደረ ነው ሲሉ የኤን.ኬ.ሲ የአፍሪካ ኢኮኖሚ አማካሪ ቡድን የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ኢርማጋርድ ኢራስመስ ይናገራሉ። "ሸማቾ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ጫና ካጋጠማቸው በአሜሪካ ወይም በዩሮ ዞን እንደምናየው በሸማቾች የሚመራ ዕድገት አያዩም" ይላሉ። "ይህም ማለት በአጠቃላይ የምጣኔ ሀብት እድገቱ የሚመራው በውጭ ኢንቨስትመንት ይሆናል፤ ነገር ግን ይህ ሁኔታም ባለው የኢትዮጵያ አሉታዊ ስም እየተጎዳ ነው" በማለት ይጠቅሳሉ። ኢርማጋርድ በቅርቡ የደቡብ አፍሪካው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ኤምቲኤንን ጨምሮ በርካታ አገልግሎት አቅራቢዎችን ፍላጎት የሳበውን የኢትዮጵያን የቴሌኮም ዘርፍ ፈቃድ ይጠቅሳሉ። ምንም እንኳን በመጀመሪያ ዙር በርካታ ዓለም አቀፍና ስመ ጥር ኩባንያዎች ፍላጎት ቢያሳዩም በመጨረሻ ግን ለሁለት የቴሌኮም ፈቃድ የወጣው ጨረታ አንዱ ብቻ ነው የተሳካው። በዚህም በኬንያው ሳፋሪኮም የሚመራው ጥምረት 850 ሚሊዮን ዶላር በማቅረብ ማሸነፍ ችሏል። የሞባይል ገንዘብ ሥርዓትን እንዳይሠሩ የሚገድቡ ሕጎች ከፈቃዱ ጋር በተያያዘ አሉታዊ ጫና ነበረባቸው ቢባልም የኩባንያዎቹ ፍላጎት የቀነሰው ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ እንደሆነ የኢንዱስትሪው ምንጮች ያስረዳሉ። ጦርነቱ እንዲቆም እየተደረገ ያለ ጫና የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት ባለፈው ዓመት በ2020 ከነበረበት 6 በመቶ በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት በ2021 ሁለት በመቶ ብቻ እንደሚያድግ ተገምቷል። ይህም በሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ከታየው በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ የአይኤምኤፍ መረጃ ያሳያል። አገሪቱ በዓመት ወደ 14 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ እቃዎችን ከውጭ የምታስገባ ሲሆን 3.4 ቢሊዮን ዶላር ብቻ የሚያወጣ ምርቶችን ወደ ውጪ ትልካለች። ከዚህም በተጨማሪ የአገሪቱ ብሔራዊ ዕዳ በዚህ ዓመት 60 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) 70 በመቶ ይደርሳል ከመባሉ ጋር ተያይዞ በርካታ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የሚያሳስብ ነው ይላሉ። "ይህ ዝቅ ተደርጎ በተደረገ ግምገማ የቀረበ ግምት ነው" ያሉት ባለለሙያዋ "የኢትዮጵያ ወታደራዊ ወጪ ከተገመተው በላይ ሊሆን ይችላል እና ቀደም ሲል ሪፖርት ያልተደረገ ዕዳም አለበት" ይላሉ። አሜሪካ በጦርነቱ ተሳታፊ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ባለስልጣናት ላይ አንዳንድ የቪዛ ገደቦችን ስትጥል እና የተወሰነ ድጋፍን ብትከለክልም፣ እስካሁን ድረስ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በመንግሥት ላይ ከፍተኛውን የኢኮኖሚ ጫና ለማሳረፍ ወይም ከፍተኛ የእርዳታ ፕሮግራሞችን ለመቋረጥ ፈቃደኛ አይደለም። በአገሪቱ ሩብ ገደማ የሚሆነው ሕዝብ ከብሔራዊ የድህነት ወለል በታች የሚኖር ሲሆን አማካይ ዓመታዊ ገቢ በአንድ ሰው 850 ዶላር ብቻ ነው። "ከሁለት ዓመታት በፊት የኖቤል የሰላም ሽልማትን ያሸነፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ግጭቱን ማስቆም ካልቻሉ ማዕቀቡን የማስፋት ሁኔታ እንዳለም" በዋሽንግተን የቲንክ ታንክ ፌሎው ዊትኒ ሽኔይድማን ይናገራሉ። የባይደን አስተዳደር አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ የገባው ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ከዓለም ሳትገለል ጦርነቱ እንዲቆም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ላይ በቂ ጫና ማሳደር ነው ይላሉ። "ሁሉም አማራጮች ጠረጴዛው ላይ ናቸው። ነገርን በአገሪቷ ከ110 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ አለ። ከዚያም በተጨማሪ አገሪቷ ጠቃሚ፣ አስፈላጊ እንዲሁም በጣሙን ስትራቴጂካዊ ናት" ይላሉ። | የኢትዮጵያን ምጣኔ ሀብታዊ እመርታ ስጋት ላይ የጣለው ጦርነት ባለፉት አስር ወራት የተደረገው ጦርነት ኢትዮጵያን ከፍተኛ ሰብዓዊ ኪሳራ ውስጥ ከቷታል። በሺዎች የሚቆጠሩ ተገድለዋል፤ ሚሊዮኖች ተፈናቅለዋል እንዲሁም ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው በርካቶች ናቸው። ጦርነቱ በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ በሆነችው ኢትዮጵያ እያደረሰው ያለው ጉዳት ይህ ብቻ አይደለም። ከፍተኛ የሆነ ምጣኔ ሀብታዊ ወጪን አስከትሏል፤ ይህንንም ለመጠገን ዓመታት ሊወስድ ይችላል። በመዲናዋ አዲስ አበባ ነዋሪ የሆነችውና ሙሉ ስሟ እንዳይጠቀስ የጠየቀችው የ26 ዓመቷ ትዕግስት ወርሃዊ ወጪዋ በሁለት ምክንያቶች በእጥፍ ጨምሯል ትላለች። እነዚህም በጥቅምት ወር ወር በሠሜናዊ ትግራይ ክልል የተቀሰቀሰው ጦርነት እና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ናቸው። "ከኮቪድ-19 እና ከግጭቱ በፊት መሠረታዊ ሸቀጦችን ለመሸመት በየወሩ አንድ ሺህ ብር አወጣ ነበር። በአሁኑ ወቅት ግን ይህ ወጪ ተመንድጎ ሁለት ሺህ ብር ሆኗል" ትላለች። አክላም "አሁን በርካታ ነገሮች ዋጋቸው የማይቀመስ ሆኗል ለምሳሌ - ስልኮች፣ ምግብ እና አልባሳት።" ይፋዊ የሆነውን ስታቲስቲክስ በምንመለከትበትም ወቅት የመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ዋጋ በእርግጥም በኢትዮጵያ ጨምሯል። በዚህም ከአንድ ዓመት በፊት በሐምሌ ወር የነበረውና የዘንድሮው ዋጋ ሲነፃፀር በአማካይ ሩብ ያህል ውድ ሆኗል። ትግስት ቤተሰቦቿን ለመደገፍ በትልቅ የገበያ መደብር (ሱፐርማርኬት) ውስጥ በገንዘብ ተቀባይነት ተቀጥራ ትሰራለች። ወንድሟ የቤት ኪራዩን የሚሸፍን ሲሆን የምግቡ ወጪ ደግሞ የእሷ ኃላፊነት ነው። "የዶላር ምንዛሪ ጥሩ አይደለም ለምሳሌ ባለፈው ዓመት 1 ዶላር በ35 ብር ሲመነዘር የነበረ ሲሆን በአሁ ወቅት ግን የአንድ ዶላር ምንዛሬ ወደ 45 ብር አሻቅቧል" ትላለች። የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ ተንታኝ የሆኑትና መቀመጫቸውን በአሜሪካ ያደረጉት ፋይሰል ሮብሌ አገሪቷ በጦርነት ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰሷ "በእውነቱ ኢትዮጵያ ዶላር የማግኘት አቅሟ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል" እና የምንዛሪው ተመንም እንዲባባስ ምክንያት ሆኗል ይላሉ። ጦርነቱ አገሪቱን ምን ያህል እንዳስወጣ እስካሁን ግልፅ አይደለም ነገር ግን በትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ ትንበያ መሰረት ወታደራዊ ወጪዋ በመጪው ታኅሣሥ ወር መጨረሻ ላይ ወደ 502 ሚሊዮን ዶላር ሊደርስ ይችላል ብሏል። በባለፈው ዓመት 460 ሚሊዮን ዶላር ነበር። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ባለፈው ሳምንት ጦርነቱ "ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ከአገሪቱ ካዝና አስወጥቷል" ብለዋል። ከዓለም አቀፉ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እና ከጦርነቱ በፊት የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት በቀጠናው በፍጥነት በማደግ ላይ ከነበሩ አንዱ ነበር። ከዓለም ባንክ የተገኘውም መረጃም አገሪቱ ከሁለት ዓመት በፊት በነበረው አስር ዓመታት ውስጥ እድገቷ በዓመት በአማካይ 10 በመቶ ነበር። ትዕግስት የጠቀሰቸው በባንኮች የሚመነዘረውን የውጭ ምንዛሪ ሲሆን መደበኛ ባልሆነው ገበያ ውስጥ ግን የብር ዋጋ በእጅጉ አሽቆልቁሎ ወደ አንድ ዶላር 65 ብር እንደሚመነዘር ፋይሰል ተናግሯል። ጨምሮም በአገሪቱ ያሉ የነጋዴዎች ጦርነቱ ከትግራይ ተሻግሮ ወደ አጎራባቾቹ የአፋርና የአማራ ክልሎች በመስፋፋቱ እያሽቆቆለ ያለው የደኅንነት ሁኔታ በእጅጉ ያሳስባቸዋል። በርካቶቹም ከአካውንታቸው ገንዘባቸውን እያወጡ እራሷን ነጻ አገር አድርጋ ወዳወጀችው ሶማሌላንድ በማሻገር በመቀየር የብር የመግዛት አቅምን የበለጠ እንዲዳከም እያደረገው መሆኑን ፋይሳል ይገልጻል። በትግራይ የባንኮች መዘጋት የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ መክሰምና የምርጫ መራዘምን ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሚመራው አስተዳርና በህወሓት መካከል የነበረው አለመግባባት ተካሮ በነበረበት ጊዜ በፌደራሉ ወታደራዊ የጦር ሰፈር ላይ ትግራይ ውስጥ ጥቃት ሲሰነዘር ነበር ጦርነቱ የተቀሰቀሰው። ከጥቅምት ወር ማብቂያ ጀምሮ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የኤርታራ ወታደሮች፣ የክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሻዎች ከትግራይ ኃይሎች ጋር ደም አፋሳሽ ጦርነት አካሂደዋል። በዚህም ጊዜ አስገድዶ መድፈርና የሰላማዊ ሰዎች የጅምላ ግድያን ጨምሮ ጭፍጨፋዎችን በመፈጸም ሁሉም ወገኖች ሲከሰሱ ቆይተዋል። ባለፈው ሰኔ ወር አማጺያኑ የክልሉን ዋና ከተማ መልሰው ከያዙ በኋላ በትግራይ ውስጥ የፌደራል መንግሥቱ የቴሌኮሚዩኒኬሽንና ባንኮችን አገልግሎቶችን ጨምሮ መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ አድርጓል። ትግራይ ሙሉ በሙሉ ተዘግታለች። በትግራይ ከ 400 ሺህ በላይ ሰዎች በረሃብ አፋፍ ላይ ናቸው። የእርዳታ ስርጭቱ በከፍተኛ ሁኔታ ተመናምኖ የኤሌክትሪክ እና የነዳጅ አቅርቦቶች ባለመኖሩም የሸቀጦች ዋጋ እንዲንር አድርጎታል። የመቀለ ነዋሪ የሆነው ፊልሞን ብርሃኔ ለቢቢሲ ትግርኛ እንደተናገረው ምግብና ኪራይ ሰሞኑን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተናግሯል። "ሁሉም ባንኮች ተዘግተው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ደመወዝ ስለማይከፍሉ ገንዘብ የለም" ይላል። የቴሌኮም ጨረታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጦርነቱ ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ባላት ስም ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያሳደረ ነው ሲሉ የኤን.ኬ.ሲ የአፍሪካ ኢኮኖሚ አማካሪ ቡድን የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ኢርማጋርድ ኢራስመስ ይናገራሉ። "ሸማቾ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ጫና ካጋጠማቸው በአሜሪካ ወይም በዩሮ ዞን እንደምናየው በሸማቾች የሚመራ ዕድገት አያዩም" ይላሉ። "ይህም ማለት በአጠቃላይ የምጣኔ ሀብት እድገቱ የሚመራው በውጭ ኢንቨስትመንት ይሆናል፤ ነገር ግን ይህ ሁኔታም ባለው የኢትዮጵያ አሉታዊ ስም እየተጎዳ ነው" በማለት ይጠቅሳሉ። ኢርማጋርድ በቅርቡ የደቡብ አፍሪካው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ኤምቲኤንን ጨምሮ በርካታ አገልግሎት አቅራቢዎችን ፍላጎት የሳበውን የኢትዮጵያን የቴሌኮም ዘርፍ ፈቃድ ይጠቅሳሉ። ምንም እንኳን በመጀመሪያ ዙር በርካታ ዓለም አቀፍና ስመ ጥር ኩባንያዎች ፍላጎት ቢያሳዩም በመጨረሻ ግን ለሁለት የቴሌኮም ፈቃድ የወጣው ጨረታ አንዱ ብቻ ነው የተሳካው። በዚህም በኬንያው ሳፋሪኮም የሚመራው ጥምረት 850 ሚሊዮን ዶላር በማቅረብ ማሸነፍ ችሏል። የሞባይል ገንዘብ ሥርዓትን እንዳይሠሩ የሚገድቡ ሕጎች ከፈቃዱ ጋር በተያያዘ አሉታዊ ጫና ነበረባቸው ቢባልም የኩባንያዎቹ ፍላጎት የቀነሰው ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ እንደሆነ የኢንዱስትሪው ምንጮች ያስረዳሉ። ጦርነቱ እንዲቆም እየተደረገ ያለ ጫና የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት ባለፈው ዓመት በ2020 ከነበረበት 6 በመቶ በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት በ2021 ሁለት በመቶ ብቻ እንደሚያድግ ተገምቷል። ይህም በሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ከታየው በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ የአይኤምኤፍ መረጃ ያሳያል። አገሪቱ በዓመት ወደ 14 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ እቃዎችን ከውጭ የምታስገባ ሲሆን 3.4 ቢሊዮን ዶላር ብቻ የሚያወጣ ምርቶችን ወደ ውጪ ትልካለች። ከዚህም በተጨማሪ የአገሪቱ ብሔራዊ ዕዳ በዚህ ዓመት 60 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) 70 በመቶ ይደርሳል ከመባሉ ጋር ተያይዞ በርካታ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የሚያሳስብ ነው ይላሉ። "ይህ ዝቅ ተደርጎ በተደረገ ግምገማ የቀረበ ግምት ነው" ያሉት ባለለሙያዋ "የኢትዮጵያ ወታደራዊ ወጪ ከተገመተው በላይ ሊሆን ይችላል እና ቀደም ሲል ሪፖርት ያልተደረገ ዕዳም አለበት" ይላሉ። አሜሪካ በጦርነቱ ተሳታፊ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ባለስልጣናት ላይ አንዳንድ የቪዛ ገደቦችን ስትጥል እና የተወሰነ ድጋፍን ብትከለክልም፣ እስካሁን ድረስ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በመንግሥት ላይ ከፍተኛውን የኢኮኖሚ ጫና ለማሳረፍ ወይም ከፍተኛ የእርዳታ ፕሮግራሞችን ለመቋረጥ ፈቃደኛ አይደለም። በአገሪቱ ሩብ ገደማ የሚሆነው ሕዝብ ከብሔራዊ የድህነት ወለል በታች የሚኖር ሲሆን አማካይ ዓመታዊ ገቢ በአንድ ሰው 850 ዶላር ብቻ ነው። "ከሁለት ዓመታት በፊት የኖቤል የሰላም ሽልማትን ያሸነፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ግጭቱን ማስቆም ካልቻሉ ማዕቀቡን የማስፋት ሁኔታ እንዳለም" በዋሽንግተን የቲንክ ታንክ ፌሎው ዊትኒ ሽኔይድማን ይናገራሉ። የባይደን አስተዳደር አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ የገባው ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ከዓለም ሳትገለል ጦርነቱ እንዲቆም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ላይ በቂ ጫና ማሳደር ነው ይላሉ። "ሁሉም አማራጮች ጠረጴዛው ላይ ናቸው። ነገርን በአገሪቷ ከ110 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ አለ። ከዚያም በተጨማሪ አገሪቷ ጠቃሚ፣ አስፈላጊ እንዲሁም በጣሙን ስትራቴጂካዊ ናት" ይላሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-58374340 |
3politics
| የብሪታኒያ መንግሥት በኢትዮጵያ ያሉ ዜጎቹ በአስቸኳይ እንዲወጡ ጠየቀ | የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር በኩል ረቡዕ ምሽት ባወጣው ማሳሰቢያ ዜጎቹ የንግድ በረራዎችን በመጠቀም "አሁን" ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ጠየቀ። ሚኒስትሯ ቪኪ ፎርድ እንዳሉት ግጭቱ እየተባባሰ በመሄዱ "ጦርነቱ ወደ አዲስ አበባ እየቀረበ ሊመጣ ከቻለ ከኢትዮጵያ ለመውጣት ያሉ አማራጮች ውስን ሊሆኑ ይችላሉ" ብለዋል። ስለዚህም ሁሉም የብሪታኒያ ዜጎች በረራዎች ባሉበትና የቦሌ አየር ማረፊያ ክፍት ሆኖ እየሰራበት ባለበት ጊዜ በአስቸኳይ እንዲወጡ፣ ገንዘብ ለሌላቸውም የአየር ትኬት ብድር መመቻቸቱንም ገልጸዋል። ጨምረውም "ከኢትዮጵያ ለመውጣት የማይፈልጉ ከሆነም በሚቀጥሉት ሳምንታት ለደኅንነታቸው አስተማማኝ በሆነ ስፍራ እንዲቆዩ" መክረዋል። ቀደም ሲልም ጀርመን እና ፈረንሳይ ዜጎቻቸው አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የመከሩ ሲሆን ሌሎች አገራትም በተመሳሳይ ዜጎቻቸው ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ የመከሩ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም አንዳንድ ሠራተኞቹን በጊዜያዊነት ማዛወሩን ገልጿል። አገራቱ ይህንን ጥሪ እያቀረቡ ያሉት የትግራይ ተዋጊዎች ወደ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እያመሩ መሆናቸውን ባስታወቁበትና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አማፂያኑን ለመዋጋት ወደ ጦር ግንባር በመሄድ ሠራዊቱን እመራለሁ ባሉበት ወቅት ነው። በትግራይ ተቀስቅሶ ወደ አጎራባቾቹ አማራና አፋር ክልል የተዛመተው ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሰብዓዊ ቀውሶችን ማስከተሉን ቀጥሏል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በረሃብ አፋፍ ላይ ሲሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታትና የእርዳታ ድርጅቶች አመልክተዋል። የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄዎች ላይ መሻሻሎች ቢታዩም መሬት ላይ ያለው ጦርነት መባባስ ሁኔታውን ስጋት ላይ ጥሎታል ብለዋል። ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች በወታደራዊ ድል አፋፍ ላይ መሆናቸውን ያመኑ ይመስላሉ ብለዋል ልዩ መልዕክተኛው። ፌልትማን አማጽያኑ ወደ አዲስ አበባ የሚጠጉ ከሆነ ተቀባይነት የሌለው እና አስከፊ እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል። ከጦር ግንባሩ የሚወጡ ዘገባዎች ለማጣራት ቢከብዱም ህወሓት ተዋጊዎቹ ከአዲስ አበባ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማን መቆጣጠራቸውን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት ቀደም ሲል የአማጺያኑን ድል ዘገባን አስተባብሏል። "ግንባር ላይ እንገናኝ" የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎቿ አማራጭ የንግድ በረራዎችን በመጠቀም መውጣት አለባቸው ሲል ፈረንሣይ በበኩሏ ዜጎቿ "ሳይዘዩ" አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አሳስባለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጣዊ የደኅንነት ሰነድ "ብቁ የሆኑ የዓለም አቀፍ ሠራተኞች ቤተሰብ አባላት" እስከ ኅዳር 16/2014 ዓ.ም ድረስ አገሪቱን ለቀው መውጣት አለባቸው ብሏል። ቀደም ሲል አሜሪካና ዩናይትድ ኪንግደም አስፈላጊ ያልሆኑ የዲፕሎማቲክ ሠራተኞች እያስወጡ መሆኑን አስታውቀው ሌሎች በአገሪቱ የሚገኙ ዜጎቻቸውም አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ከጥቂት ዓመታት በፊት የኖቤል የሰላም ሽልማት ያገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ሰኞ ማምሻውን ባስተላለፉት መልዕክት የመከላከያ ሠራዊቱን ለመምራት ወደ ጦር ግንባር እንደሚሄዱ ገልጸዋል። "ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን የምታስቡ ሁሉ ለሀገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሡ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ" በማለት ሌሎችም የእሳቸውን አርአያ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ድላቸውን ያገኙት የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ተከትሎ ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀው ውጥረት ማክተሚያ መፍትሄ በመሆናቸው ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩን ወደ ግንባር በመሄድ ጦሩን እመራለሁ ማለታቸውን የህወሓት ቃለ አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ አጣጥለውታል። "የእኛ ኃይሎች በሕዝባችን ላይ ያለውን (የዐብይን) ማነቆ ለማብቃት እያደረጉት ካለው ግስጋሴ አይመለሱም" ብለዋል አቶ ጌታቸው። ጦርነቱ በድርድር እንዲቋጭ የአፍሪካ ሕብረት ጥረቶችን እያደረገ ቢሆንም ሁለቱም ወገኖች ለውይይት ቁርጠኛ አይደሉም። ለጦርነቱ ዋነኛ መነሻ የሆነው በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ እና ትግራይን ብቻ ሳይሆን መላ አገሪቷን በበላይነት ይመራ በነበረው ህወሓት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን መምጣት ተከትሎ የፖለቲካ ምህዳሩን ከማስፋት በተጨማሪ ለረጅም ጊዜ በጠላትነት ሲተያዩ ከነበሩት ኤርትራ ጋር እርቅ መፍጠርና ሌሎች ማሻሻያዎችን አካሂደዋል። በዚህ ወቅት ህወሓት ወደ ጎን ገሸሽ ተደርጓል። በህወሓትና በጠቅላይ ሚኒስትሩ መካከል የከረመው መሻከርም ወደ ጦርነት አምርቷል። ከዓመት በፊት የህወሓት ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈፅመዋል እንዲሁም መሳሪያ ዘርፈዋል በሚልም የፌደራል መንግሥቱ ወታደራዊ ምላሽ ሰጥቷል። | የብሪታኒያ መንግሥት በኢትዮጵያ ያሉ ዜጎቹ በአስቸኳይ እንዲወጡ ጠየቀ የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር በኩል ረቡዕ ምሽት ባወጣው ማሳሰቢያ ዜጎቹ የንግድ በረራዎችን በመጠቀም "አሁን" ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ጠየቀ። ሚኒስትሯ ቪኪ ፎርድ እንዳሉት ግጭቱ እየተባባሰ በመሄዱ "ጦርነቱ ወደ አዲስ አበባ እየቀረበ ሊመጣ ከቻለ ከኢትዮጵያ ለመውጣት ያሉ አማራጮች ውስን ሊሆኑ ይችላሉ" ብለዋል። ስለዚህም ሁሉም የብሪታኒያ ዜጎች በረራዎች ባሉበትና የቦሌ አየር ማረፊያ ክፍት ሆኖ እየሰራበት ባለበት ጊዜ በአስቸኳይ እንዲወጡ፣ ገንዘብ ለሌላቸውም የአየር ትኬት ብድር መመቻቸቱንም ገልጸዋል። ጨምረውም "ከኢትዮጵያ ለመውጣት የማይፈልጉ ከሆነም በሚቀጥሉት ሳምንታት ለደኅንነታቸው አስተማማኝ በሆነ ስፍራ እንዲቆዩ" መክረዋል። ቀደም ሲልም ጀርመን እና ፈረንሳይ ዜጎቻቸው አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የመከሩ ሲሆን ሌሎች አገራትም በተመሳሳይ ዜጎቻቸው ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ የመከሩ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም አንዳንድ ሠራተኞቹን በጊዜያዊነት ማዛወሩን ገልጿል። አገራቱ ይህንን ጥሪ እያቀረቡ ያሉት የትግራይ ተዋጊዎች ወደ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እያመሩ መሆናቸውን ባስታወቁበትና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አማፂያኑን ለመዋጋት ወደ ጦር ግንባር በመሄድ ሠራዊቱን እመራለሁ ባሉበት ወቅት ነው። በትግራይ ተቀስቅሶ ወደ አጎራባቾቹ አማራና አፋር ክልል የተዛመተው ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሰብዓዊ ቀውሶችን ማስከተሉን ቀጥሏል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በረሃብ አፋፍ ላይ ሲሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታትና የእርዳታ ድርጅቶች አመልክተዋል። የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄዎች ላይ መሻሻሎች ቢታዩም መሬት ላይ ያለው ጦርነት መባባስ ሁኔታውን ስጋት ላይ ጥሎታል ብለዋል። ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች በወታደራዊ ድል አፋፍ ላይ መሆናቸውን ያመኑ ይመስላሉ ብለዋል ልዩ መልዕክተኛው። ፌልትማን አማጽያኑ ወደ አዲስ አበባ የሚጠጉ ከሆነ ተቀባይነት የሌለው እና አስከፊ እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል። ከጦር ግንባሩ የሚወጡ ዘገባዎች ለማጣራት ቢከብዱም ህወሓት ተዋጊዎቹ ከአዲስ አበባ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማን መቆጣጠራቸውን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት ቀደም ሲል የአማጺያኑን ድል ዘገባን አስተባብሏል። "ግንባር ላይ እንገናኝ" የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎቿ አማራጭ የንግድ በረራዎችን በመጠቀም መውጣት አለባቸው ሲል ፈረንሣይ በበኩሏ ዜጎቿ "ሳይዘዩ" አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አሳስባለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጣዊ የደኅንነት ሰነድ "ብቁ የሆኑ የዓለም አቀፍ ሠራተኞች ቤተሰብ አባላት" እስከ ኅዳር 16/2014 ዓ.ም ድረስ አገሪቱን ለቀው መውጣት አለባቸው ብሏል። ቀደም ሲል አሜሪካና ዩናይትድ ኪንግደም አስፈላጊ ያልሆኑ የዲፕሎማቲክ ሠራተኞች እያስወጡ መሆኑን አስታውቀው ሌሎች በአገሪቱ የሚገኙ ዜጎቻቸውም አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ከጥቂት ዓመታት በፊት የኖቤል የሰላም ሽልማት ያገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ሰኞ ማምሻውን ባስተላለፉት መልዕክት የመከላከያ ሠራዊቱን ለመምራት ወደ ጦር ግንባር እንደሚሄዱ ገልጸዋል። "ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን የምታስቡ ሁሉ ለሀገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሡ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ" በማለት ሌሎችም የእሳቸውን አርአያ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ድላቸውን ያገኙት የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ተከትሎ ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀው ውጥረት ማክተሚያ መፍትሄ በመሆናቸው ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩን ወደ ግንባር በመሄድ ጦሩን እመራለሁ ማለታቸውን የህወሓት ቃለ አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ አጣጥለውታል። "የእኛ ኃይሎች በሕዝባችን ላይ ያለውን (የዐብይን) ማነቆ ለማብቃት እያደረጉት ካለው ግስጋሴ አይመለሱም" ብለዋል አቶ ጌታቸው። ጦርነቱ በድርድር እንዲቋጭ የአፍሪካ ሕብረት ጥረቶችን እያደረገ ቢሆንም ሁለቱም ወገኖች ለውይይት ቁርጠኛ አይደሉም። ለጦርነቱ ዋነኛ መነሻ የሆነው በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ እና ትግራይን ብቻ ሳይሆን መላ አገሪቷን በበላይነት ይመራ በነበረው ህወሓት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን መምጣት ተከትሎ የፖለቲካ ምህዳሩን ከማስፋት በተጨማሪ ለረጅም ጊዜ በጠላትነት ሲተያዩ ከነበሩት ኤርትራ ጋር እርቅ መፍጠርና ሌሎች ማሻሻያዎችን አካሂደዋል። በዚህ ወቅት ህወሓት ወደ ጎን ገሸሽ ተደርጓል። በህወሓትና በጠቅላይ ሚኒስትሩ መካከል የከረመው መሻከርም ወደ ጦርነት አምርቷል። ከዓመት በፊት የህወሓት ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈፅመዋል እንዲሁም መሳሪያ ዘርፈዋል በሚልም የፌደራል መንግሥቱ ወታደራዊ ምላሽ ሰጥቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59384118 |
2health
| “የጥርሴ ቢጫ መሆን ሕልሜን አመከነው” | በልጅነት ፍሎራይድ የበዛበትን ውሃ መጠቀም የጥርስ ቀለምን ወደ ቢጫ እንዲቀየር እና እንዲበልዝ ያደርጋል። ይህ ሁኔታም ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ውስጥ ያጋጥማል። ፍሎራይድ የጥርስን የላይኛውን ክፍል በመጉዳት ቀለሙ እንዲቀየር እና እንዲሸራረፍ ምክንያት ይሆናል። በዚህም ሳቢያ በርካታ ሰዎች በጥርሳቸው ቀለም እፍረት እና መገለል ይገጥማቸዋል። የወደፊት ዕቅዳቸው ተሰናክሎብናል የሚሉም አሉ። የታንዛኒያዋ አሩሻ በውሃ ውስጥ ከፍተኛ የፍሎራይድ መጠን ካለባቸው ስፍራዎች መካከል አንዷ ስትሆን፣ እዚያ የአሩሻ ነዋሪ የሆኑ ሁለት ወጣት ሴቶች ስለገጠማቸው ችግር ይናገራሉ። ሁለቱ ወጣቶች በጥርሳቸው ቀለም መቀየር ምክንያት መድሎ እንደሚደርስባቸው ገልጸዋል። መፍትሔ ይኖረው ይሆን የጥርስን ቀለም የሚቀይረውን ከፍተኛ የፍሎራይድ መጠን ያለውን ውሃ ማጣራት እጅግ ከባድና ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ነው። አሁን ግን ቀላል የውሃ ጣሪያ ዘዴ ተፈጥሯል። | “የጥርሴ ቢጫ መሆን ሕልሜን አመከነው” በልጅነት ፍሎራይድ የበዛበትን ውሃ መጠቀም የጥርስ ቀለምን ወደ ቢጫ እንዲቀየር እና እንዲበልዝ ያደርጋል። ይህ ሁኔታም ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ውስጥ ያጋጥማል። ፍሎራይድ የጥርስን የላይኛውን ክፍል በመጉዳት ቀለሙ እንዲቀየር እና እንዲሸራረፍ ምክንያት ይሆናል። በዚህም ሳቢያ በርካታ ሰዎች በጥርሳቸው ቀለም እፍረት እና መገለል ይገጥማቸዋል። የወደፊት ዕቅዳቸው ተሰናክሎብናል የሚሉም አሉ። የታንዛኒያዋ አሩሻ በውሃ ውስጥ ከፍተኛ የፍሎራይድ መጠን ካለባቸው ስፍራዎች መካከል አንዷ ስትሆን፣ እዚያ የአሩሻ ነዋሪ የሆኑ ሁለት ወጣት ሴቶች ስለገጠማቸው ችግር ይናገራሉ። ሁለቱ ወጣቶች በጥርሳቸው ቀለም መቀየር ምክንያት መድሎ እንደሚደርስባቸው ገልጸዋል። መፍትሔ ይኖረው ይሆን የጥርስን ቀለም የሚቀይረውን ከፍተኛ የፍሎራይድ መጠን ያለውን ውሃ ማጣራት እጅግ ከባድና ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ነው። አሁን ግን ቀላል የውሃ ጣሪያ ዘዴ ተፈጥሯል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c4n023lnxdqo |
5sports
| ፔንግ ሹዋይ፡ በጾታዊ ጥቃት ሳቢያ በቻይና የሚደረጉ የቴኒስ ውድድሮች ታገዱ | የቻይናዊቷ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ፔንግ ሹዋይ ጉዳይ ያሳሰበው የሴቶች ቴኒስ ማኅበር (ደብሊውቲኤ) በቻይና የሚደረጉ ሁሉንም ውድድሮች በአስቸኳይ ማገዱን አስታውቋል። የ35 ዓመቷ ፔንግ የቻይናን ከፍተኛ ባለሥልጣን በጾታዊ ጥቃት ከከሰሰች በኋላ ለሦስት ሳምንታት ከሕዝብ ዕይታ ጠፍታለች። የማኅበሩ ዋና ኃላፊ ስቲቭ ሳይመን እንዳሉት ፔንግ "ነጻ፣ ደህንነቷ የተጠበቀ እና ለማስፈራሪያ ያልታጋለጠች ስለመሆኑ ከባድ ጥርጣሬዎች አሉን" ብለዋል። "በጥሩ ህሊና ስፖርተኞቻችን እዚያ እንዲወዳደሩ እንዴት እንደምጠይቅ አይታየኝም" ብለዋል ኃላፊው። ማኅበሩ በፔንግ ክሶች ዙሪያ ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ ደጋግሞ ጠይቋል። የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዣንግ ጋዎሊን በጾታዊ ጥቃት ከከሰሰች በኋላ በፔንግ ጉዳይ ስጋት ተፈጥሯል። በኅዳር ወር ከዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ቶማስ ባህ ጋር ባደረችው የቪዲዮ ጥሪ "ደህና" መሆኗን ተናግራለች። ማኅበሩ ግን ቪዲዮው ስለፔንግ "ደህንነት በቂ ማስረጃ አይደለም" ብሏል። ሳይመን በ2022 በቻይና ውድድሮች ቢደረጉ ተጫዋቾቹ እና ባልደረቦቻቸው ሊያጋጥሟቸው ስለሚችለው አደጋ "በጣም አሳስቦኛል" ብሏል። "በቻይና ያለው አመራር በዚህ አሳሳቢ ጉዳይ ላይ በምንም መልኩ ሊታመን አይችልም" ብለዋል። "ታላላቅ ሰዎች የሴቶችን ድምጽ ማፈን እና የጾታዊ ጥቃትን ውንጀላን ማጥፋት ካልቻሉ ማኅበሩ ከተመሠረተበት የሴቶች እኩልነት ዓላማ ትልቅ እንቅፋት ይገጥመዋል።" ሲሉም ስጋታቸውን ገልጸዋል። "ይህ በማኅበሩ እና በተጫዋቾቹ ላይ እንዲደርስም እንዲሆንም አልፈቅድም" ብለዋል። እገዳው በሆንግ ኮንግ የሚካሄዱ ውድድሮችንም ያካትታል። የቀድሞዋ የዓለም ቁጥር አንድ ቴኒስ ተጫዋች እና የማህኅበሩ መስራች ቢሊ ዣን ኪንግ ድርጅቱ ጠንካራ አቋም መያዙን አድንቃለች። ኪንግ በትዊተር ላይ "ይህ የሴቶች ቴኒስ በሴቶች ስፖርት ውስጥ መሪ የሚሆንበት ሌላው ምክንያት ነው።" ብላለች። "ደብሊውቲኤ ተጫዋቾቻችንን በመደገፍ በታሪክ ጎን ቆሟል።" ስትልም አክላለች። የሁለት ጊዜ የዊምብልደን ሻምፒዮናዋ ፔትራ ክቪቶቫ እና የዩኤስ ኦፕን የሩብ ፍጻሜ ተወዳዳሪ የነበረችው ሼልቢ ሮጀርስን ጨምሮ በርካታ ተጫዋቾች ለውሳኔው ድጋፋቸውን በትዊተር ገልጸዋል። የፔንግ ጉዳይ 'ከሥራ ይበልጣል' - ሳይመን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ላለፉት ሁለት ዓመታት በቻይና ምንም አይነት የማኅበሩ ውድድሮች አልተካሄዱም። ይሁን እንጂ የበላይ አካሉ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ባደረጋቸው ውድድሮች በቻይና ኢንቨስትመንቶች ላይ በእጅጉ ከመንጠላጠሉም በላይ በአገሪቱ በርካታ ውድድሮች እንዲካሄዱ አድርጓል። ቻይና እአአ በ2019 የውድድር ዓመት ዘመን ውድድሮችን አስተናግዳለች። የውድድር ዘመኑ ማብቂያ ለሆነው የማኅበሩን የፍጻሜ ውድድርን ጨምሮ በድምሩ 30.4 ሚሊዮን ዶላር በሽልማት ሰጥታለች። ሳይመን በቻይና ያለመጫወት የሚያስከትለው የፋይናንስ ችግር እንዳሳሰበው ለቢቢሲ ስፖርት ገልጸው የፔንግ ጉዳይ ግን "ከሥራም የበለጠ ነው" ብለዋል። "ይህ በቀላሉ ልንወጣው የማንችለው ነገር ነው" ሲሉ ገልጸዋል። "ከጠየቅነው ነገር ርቀን ከሄድን ለዓለም እየነገርነው ያለው ወሲባዊ ጥቃትን እና አሳሳቢነት አለመመልከት በመሆኑ አይሆንም።" ብለዋል። "እኛ እንዲሆን መፍቀድ የማንችለው እና ከዚያ መሸሽ የማንችለው ነገር ነው" ሲሉም አክለዋል። በድርብ ውድድር የቀድሞዋ የዓለም ቁጥር አንድ የነበረችው ፔንግ በቻይና ማኅበራዊ ድር አምባ ዌይቦ ላይ ከዣንግ ጋር ጾታዊ ግንኙነት እንድትፈጽም መገደዷን ገልጻለች። ጽሁፉ ከደቂቃዎች በኋላ የተነሳ ሲሆን ፔንግ ለተወሰነ ጊዜ በአደባባይ አልታየችም። በርካታ የቴኒስ ተጫዋቾች በትዊተር ላይ #WhereisPengShuai (ፔንግ ሹዋን የታለች) የሚለውን ሃሽታግ ተጠቅመው ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ አድርገዋል። ሳይመን በወንዶች ውድድር ላይ የወንድ ቴኒስ ተጫዋቾች ማኅበር ተመሳሳይ አቋም እንዲይዝ እንደማይጠይቁ ለቢቢሲ ስፖርት ተናግረዋል። የማኅበሩ የበላይ አካል ግን አቋማቸውን እንደሚደግፍ ተናግሯል። "[የወንዶቹ ማኅበር ውድድሮችን አለማቋረጡ] አቋማችንን የሚጎዳው አይመስለኝም" ብለዋል። "የእኛ አቋም ለደብሊውቲኤ እና ለሴቶች ስፖርተኞች የተሻለው ነገር ነው እና እኛ በዚያ አቋም እንቀጥላለን።" ሲሉም አቋማቸውን ገልጸዋል። "ሌሎች ለእነሱ ተስማሚ ናቸው ብለው ያሰቡትን ውሳኔ ያሳልፋሉ።" ብለዋል ሳይመን። የቻይና ባለሥልጣናት የፔንግን ጥያቄዎች "በሕጋዊ መንገድ ለመፍታት" እርምጃዎችን እንደሚወስዱ ተስፋ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል። 'ምርጫ የለም' ሳይመን አክለውም "እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱ በጣም አዝኛለሁ። የቻይና መሪዎች ግን ማኅበሩ ምንም አማራጭ እንዳይኖረው አድርገዋል።" ይላሉ። "ቻይና የጠየቅናቸውን እርምጃዎች እስካልወሰደች ድረስ በቻይና ውድድሮችን በማድረግ ተጫዋቾቻችንን እና ሠራተኞቻችንን አደጋ ላይ መጣል አንችልም።" ብለዋል። ቻይና በጥቅምት ወር ባወጣችው መግለጫ "ሰዎች ሆን ብለው ይህንን ጉዳይ ፖለቲካዊ ማድረግ ይቅርና [ጉዳዩንም] ማበረታታቸውን ማቆም አለባቸው" ብላለች። እአአ በ2018 ከመንግሥት ሥራቸው ጡረታ የወጡት ዣንግ ጋዎሊ ስለቀረበባቸው ክስ እስካሁን ምላሽ አልሰጡም። የ2022 የክረምት ኦሎምፒክ እና ፓራሊምፒክ በቤጂንግ በየካቲት እና በመጋቢት ወር ሊካሄድ ታቅዷል። | ፔንግ ሹዋይ፡ በጾታዊ ጥቃት ሳቢያ በቻይና የሚደረጉ የቴኒስ ውድድሮች ታገዱ የቻይናዊቷ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ፔንግ ሹዋይ ጉዳይ ያሳሰበው የሴቶች ቴኒስ ማኅበር (ደብሊውቲኤ) በቻይና የሚደረጉ ሁሉንም ውድድሮች በአስቸኳይ ማገዱን አስታውቋል። የ35 ዓመቷ ፔንግ የቻይናን ከፍተኛ ባለሥልጣን በጾታዊ ጥቃት ከከሰሰች በኋላ ለሦስት ሳምንታት ከሕዝብ ዕይታ ጠፍታለች። የማኅበሩ ዋና ኃላፊ ስቲቭ ሳይመን እንዳሉት ፔንግ "ነጻ፣ ደህንነቷ የተጠበቀ እና ለማስፈራሪያ ያልታጋለጠች ስለመሆኑ ከባድ ጥርጣሬዎች አሉን" ብለዋል። "በጥሩ ህሊና ስፖርተኞቻችን እዚያ እንዲወዳደሩ እንዴት እንደምጠይቅ አይታየኝም" ብለዋል ኃላፊው። ማኅበሩ በፔንግ ክሶች ዙሪያ ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ ደጋግሞ ጠይቋል። የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዣንግ ጋዎሊን በጾታዊ ጥቃት ከከሰሰች በኋላ በፔንግ ጉዳይ ስጋት ተፈጥሯል። በኅዳር ወር ከዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ቶማስ ባህ ጋር ባደረችው የቪዲዮ ጥሪ "ደህና" መሆኗን ተናግራለች። ማኅበሩ ግን ቪዲዮው ስለፔንግ "ደህንነት በቂ ማስረጃ አይደለም" ብሏል። ሳይመን በ2022 በቻይና ውድድሮች ቢደረጉ ተጫዋቾቹ እና ባልደረቦቻቸው ሊያጋጥሟቸው ስለሚችለው አደጋ "በጣም አሳስቦኛል" ብሏል። "በቻይና ያለው አመራር በዚህ አሳሳቢ ጉዳይ ላይ በምንም መልኩ ሊታመን አይችልም" ብለዋል። "ታላላቅ ሰዎች የሴቶችን ድምጽ ማፈን እና የጾታዊ ጥቃትን ውንጀላን ማጥፋት ካልቻሉ ማኅበሩ ከተመሠረተበት የሴቶች እኩልነት ዓላማ ትልቅ እንቅፋት ይገጥመዋል።" ሲሉም ስጋታቸውን ገልጸዋል። "ይህ በማኅበሩ እና በተጫዋቾቹ ላይ እንዲደርስም እንዲሆንም አልፈቅድም" ብለዋል። እገዳው በሆንግ ኮንግ የሚካሄዱ ውድድሮችንም ያካትታል። የቀድሞዋ የዓለም ቁጥር አንድ ቴኒስ ተጫዋች እና የማህኅበሩ መስራች ቢሊ ዣን ኪንግ ድርጅቱ ጠንካራ አቋም መያዙን አድንቃለች። ኪንግ በትዊተር ላይ "ይህ የሴቶች ቴኒስ በሴቶች ስፖርት ውስጥ መሪ የሚሆንበት ሌላው ምክንያት ነው።" ብላለች። "ደብሊውቲኤ ተጫዋቾቻችንን በመደገፍ በታሪክ ጎን ቆሟል።" ስትልም አክላለች። የሁለት ጊዜ የዊምብልደን ሻምፒዮናዋ ፔትራ ክቪቶቫ እና የዩኤስ ኦፕን የሩብ ፍጻሜ ተወዳዳሪ የነበረችው ሼልቢ ሮጀርስን ጨምሮ በርካታ ተጫዋቾች ለውሳኔው ድጋፋቸውን በትዊተር ገልጸዋል። የፔንግ ጉዳይ 'ከሥራ ይበልጣል' - ሳይመን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ላለፉት ሁለት ዓመታት በቻይና ምንም አይነት የማኅበሩ ውድድሮች አልተካሄዱም። ይሁን እንጂ የበላይ አካሉ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ባደረጋቸው ውድድሮች በቻይና ኢንቨስትመንቶች ላይ በእጅጉ ከመንጠላጠሉም በላይ በአገሪቱ በርካታ ውድድሮች እንዲካሄዱ አድርጓል። ቻይና እአአ በ2019 የውድድር ዓመት ዘመን ውድድሮችን አስተናግዳለች። የውድድር ዘመኑ ማብቂያ ለሆነው የማኅበሩን የፍጻሜ ውድድርን ጨምሮ በድምሩ 30.4 ሚሊዮን ዶላር በሽልማት ሰጥታለች። ሳይመን በቻይና ያለመጫወት የሚያስከትለው የፋይናንስ ችግር እንዳሳሰበው ለቢቢሲ ስፖርት ገልጸው የፔንግ ጉዳይ ግን "ከሥራም የበለጠ ነው" ብለዋል። "ይህ በቀላሉ ልንወጣው የማንችለው ነገር ነው" ሲሉ ገልጸዋል። "ከጠየቅነው ነገር ርቀን ከሄድን ለዓለም እየነገርነው ያለው ወሲባዊ ጥቃትን እና አሳሳቢነት አለመመልከት በመሆኑ አይሆንም።" ብለዋል። "እኛ እንዲሆን መፍቀድ የማንችለው እና ከዚያ መሸሽ የማንችለው ነገር ነው" ሲሉም አክለዋል። በድርብ ውድድር የቀድሞዋ የዓለም ቁጥር አንድ የነበረችው ፔንግ በቻይና ማኅበራዊ ድር አምባ ዌይቦ ላይ ከዣንግ ጋር ጾታዊ ግንኙነት እንድትፈጽም መገደዷን ገልጻለች። ጽሁፉ ከደቂቃዎች በኋላ የተነሳ ሲሆን ፔንግ ለተወሰነ ጊዜ በአደባባይ አልታየችም። በርካታ የቴኒስ ተጫዋቾች በትዊተር ላይ #WhereisPengShuai (ፔንግ ሹዋን የታለች) የሚለውን ሃሽታግ ተጠቅመው ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ አድርገዋል። ሳይመን በወንዶች ውድድር ላይ የወንድ ቴኒስ ተጫዋቾች ማኅበር ተመሳሳይ አቋም እንዲይዝ እንደማይጠይቁ ለቢቢሲ ስፖርት ተናግረዋል። የማኅበሩ የበላይ አካል ግን አቋማቸውን እንደሚደግፍ ተናግሯል። "[የወንዶቹ ማኅበር ውድድሮችን አለማቋረጡ] አቋማችንን የሚጎዳው አይመስለኝም" ብለዋል። "የእኛ አቋም ለደብሊውቲኤ እና ለሴቶች ስፖርተኞች የተሻለው ነገር ነው እና እኛ በዚያ አቋም እንቀጥላለን።" ሲሉም አቋማቸውን ገልጸዋል። "ሌሎች ለእነሱ ተስማሚ ናቸው ብለው ያሰቡትን ውሳኔ ያሳልፋሉ።" ብለዋል ሳይመን። የቻይና ባለሥልጣናት የፔንግን ጥያቄዎች "በሕጋዊ መንገድ ለመፍታት" እርምጃዎችን እንደሚወስዱ ተስፋ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል። 'ምርጫ የለም' ሳይመን አክለውም "እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱ በጣም አዝኛለሁ። የቻይና መሪዎች ግን ማኅበሩ ምንም አማራጭ እንዳይኖረው አድርገዋል።" ይላሉ። "ቻይና የጠየቅናቸውን እርምጃዎች እስካልወሰደች ድረስ በቻይና ውድድሮችን በማድረግ ተጫዋቾቻችንን እና ሠራተኞቻችንን አደጋ ላይ መጣል አንችልም።" ብለዋል። ቻይና በጥቅምት ወር ባወጣችው መግለጫ "ሰዎች ሆን ብለው ይህንን ጉዳይ ፖለቲካዊ ማድረግ ይቅርና [ጉዳዩንም] ማበረታታቸውን ማቆም አለባቸው" ብላለች። እአአ በ2018 ከመንግሥት ሥራቸው ጡረታ የወጡት ዣንግ ጋዎሊ ስለቀረበባቸው ክስ እስካሁን ምላሽ አልሰጡም። የ2022 የክረምት ኦሎምፒክ እና ፓራሊምፒክ በቤጂንግ በየካቲት እና በመጋቢት ወር ሊካሄድ ታቅዷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59501635 |
5sports
| ግሌዘሮች ለክለቡ 'ደንታ የላቸውም’፤ ኔቪል እና ሩኒ ጓደኞቼ አይደሉም- ሮናልዶ | የማንቸስተር ዩናይትዱ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የክለቡ ባለቤቶች የሆኑት የግሌዘር ቤተሰቦች ከስፖርት አኳያ ከታየ “ስለክለቡ ምንም ደንታ የላቸውም” ሲል ገለጸ። ሮናልዶ ክለቤ “ከዳኝ” ብሎ ለቶክ ቲቪ የሰጠው ቃለ መጠይቅ መነጋገሪያ ሆኗል። የቃለ ምልልሱ ሌላኛው ክፍል ሰኞ ምሽት ተለቋል። "ማንችስተር ንግድ ክለብ ነው፤ ከገበያ ገንዘብ ያገኛሉ" ሲል ተናግሯል። "በሚቀጥሉት ሁለት እና ሦስት ዓመታት ማንቸስተር ሜዳ ላይ የበላይ ለመሆን ከባድ ይሆንበታል" ብሏል። በዘንድሮው የውድድር ዘመን አንድ ግብ ብቻ ያስቆጠረው የ37 ዓመቱ ፖርቱጋላዊ የፊት መስመር ተጫዋች "የክለቡ ባለቤቶች የሆኑት ግሌዘሮች ስለ ክለቡ ደንታ የላቸውም" ብሏል። ሮናልዶ አክሎም በ2005 ክለቡን ከተረከቡት የግሌዘር ቤተሰብ አባለት ጋር ተገናኝቶ እንደማያውቅም ተናግሯል። ዩናይትድ ለሮናልዶ ቃለ መጠይቅ ሰኞ ዕለት ምላሽ ሰጧል። ክለቡ "ማንቸስተር ዩናይትድ የክርስቲያኖ ሮናልዶን ቃለ መጠይቅ አስመልክቶ የሚዲያ ዘገባዎችን ተከታትሏል። ክለቡ ሙሉ መረጃዎች ከወጡ በኋላ የሚሰጠውን ምላሽ ግምት ውስጥ ያስገባል” ብሏል። "ትኩረታችን ለሁለተኛው የውድድር አጋማሽ መዘጋጀት እና በተጫዋቾች፣ በአሰልጣኞች፣ በሠራተኞች እና በደጋፊዎች መካከል እየተገነባ ያለውን መነሳሳት፣ እምነት እና አንድነት ማስቀጠል ላይ ነው" ሲልም ክለቡ አክሏል። እአአ በ2017 ለመጨረሻ ጊዜ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ያነሳውን ክለብ ባለቤቶች በመቃወም ደጋፊዎች በርካታ ተቃውሞዎችን አካሂደዋል። የፖርቹጋሉ አምበል ሮናልዶ አክሎም "ደጋፊዎቹ ሁሌም ትክክል ናቸው። እውነታውን ማወቅ አለባቸው። ተጫዋቾቹ ለክለቡ ጥሩ ነገር ይፈልጋሉ። እኔም ለክለቡ ጥሩ ነገር እመኛለሁ። ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ የመጣሁትም ለዚህ ነው። ለዚህም ነው ይህንን ክለብ የምወደው” ብሏል። “ማንቸስተር እንደ ሲቲ፣ ሊቨርፑል እና አሁን ደግሞ እንደ አርሴናል ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዳይደርስ የሚያደርጉ አንዳንድ ነገሮች በክለቡ ውስጥ አሉ።“ "ውስብስብ ነው። ከባድ ነው። በጣም ከባድ ነው።" "ኔቪልና ሩኒ ጓደኞቼ አይደሉም" በእሑዱ ቃለ ምልልስ ወቅት ሮናልዶ የቀድሞው የዩናይትድ የቡድን አጋሩ ዋይኒ ሩኒ ስለተቸው ተበሳጭቶ እንደሆን ተጠይቆ ነበር። ሮናልዶ "ምናልባት በሠላሳዎቹ ዕድሜው ጫማውን ስለሰቀለ ይሆናል። እኔ አሁንም በትልቅ ደረጃ እየተጫወትኩ ነው። ከሱ የተሻልኩ ነኝ አልልም። ምክንያቱም እውነት ነው. . .።" አሁን ደግሞ ትኩረቱን ወደ ሌላ የቀድሞ የዩናይትድ አጋሩ ጋሪ ኔቪል አዙሯል። የቀድሞ የእንግሊዝ የቀኝ መስመር ተከላካይ በቅርቡ ለስካይ ስፖርት ተንታኝ ሆኖ ሲሠራ ሮናልዶ ሠላም ሳይለው ቀርቷል። "ከአንተ ጋር ከተጫወቱ ሰዎች እንዲህ ዓይነቱን ትችት እና አሉታዊነት ማዳመጥ በጣም ከባድ ነው። ለምሳሌ ጋሪ ኔቪል። ሁለቱም ጓደኞቼ አይደሉም" ሲል ሮናልዶ ተናግሯል። "መተቸት ቀላል ነው። በቴሌቪዥን ሠርቶ የበለጠ ታዋቂ ለመሆን መተቸት ግዴታ ይሁንባቸው አላውቅም። በእርግጥም አልገባኝም።“ "ሞኞች ስላልሆኑ (የእኔን ስም) የሚያነሱት ሊጠቀሙበት ይመስለኛል። ከአንተ ጋር በአንድ መልበሻ ክፍል የነበሩ ሰዎች በዚያ መንገድ ሲተቹ ማየት በጣም ከባድ ነው" ብሏል። ከዚህ በፊት ምን ተፈጠረ? ቀደም ሲል በተለቀቀው የቃለ ምልልሱ ክፍል በሳምንት 500 ሺህ ፓውንድ የሚከፈለው ሮናልዶ ክለቡ አስገድዶ ሊያስወጣው እየሞከረ መሆኑን እና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግን እንደማያከብር ተናግሯል። ሮናልዶ ከአውሮፓውያኑ 2003 እና 2009 ለዩናይትድ 118 ጎሎችን አስቆጥሯል። በ2021 ክረምት ወደ ክለቡ በድጋሚ የተመለሰው በክለቡ ደጋፊዎች ዘንድ በአክብሮት ነበር። በዚህ ሳምንት የሚተላለፈው ሙሉው ቃለ መጠይቅ ብዙ ደጋፊዎችን ከእሱ እንደሚያርቅ ይጠበቃል። ሮናልዶ አሁን በኳታር ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ከፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። | ግሌዘሮች ለክለቡ 'ደንታ የላቸውም’፤ ኔቪል እና ሩኒ ጓደኞቼ አይደሉም- ሮናልዶ የማንቸስተር ዩናይትዱ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የክለቡ ባለቤቶች የሆኑት የግሌዘር ቤተሰቦች ከስፖርት አኳያ ከታየ “ስለክለቡ ምንም ደንታ የላቸውም” ሲል ገለጸ። ሮናልዶ ክለቤ “ከዳኝ” ብሎ ለቶክ ቲቪ የሰጠው ቃለ መጠይቅ መነጋገሪያ ሆኗል። የቃለ ምልልሱ ሌላኛው ክፍል ሰኞ ምሽት ተለቋል። "ማንችስተር ንግድ ክለብ ነው፤ ከገበያ ገንዘብ ያገኛሉ" ሲል ተናግሯል። "በሚቀጥሉት ሁለት እና ሦስት ዓመታት ማንቸስተር ሜዳ ላይ የበላይ ለመሆን ከባድ ይሆንበታል" ብሏል። በዘንድሮው የውድድር ዘመን አንድ ግብ ብቻ ያስቆጠረው የ37 ዓመቱ ፖርቱጋላዊ የፊት መስመር ተጫዋች "የክለቡ ባለቤቶች የሆኑት ግሌዘሮች ስለ ክለቡ ደንታ የላቸውም" ብሏል። ሮናልዶ አክሎም በ2005 ክለቡን ከተረከቡት የግሌዘር ቤተሰብ አባለት ጋር ተገናኝቶ እንደማያውቅም ተናግሯል። ዩናይትድ ለሮናልዶ ቃለ መጠይቅ ሰኞ ዕለት ምላሽ ሰጧል። ክለቡ "ማንቸስተር ዩናይትድ የክርስቲያኖ ሮናልዶን ቃለ መጠይቅ አስመልክቶ የሚዲያ ዘገባዎችን ተከታትሏል። ክለቡ ሙሉ መረጃዎች ከወጡ በኋላ የሚሰጠውን ምላሽ ግምት ውስጥ ያስገባል” ብሏል። "ትኩረታችን ለሁለተኛው የውድድር አጋማሽ መዘጋጀት እና በተጫዋቾች፣ በአሰልጣኞች፣ በሠራተኞች እና በደጋፊዎች መካከል እየተገነባ ያለውን መነሳሳት፣ እምነት እና አንድነት ማስቀጠል ላይ ነው" ሲልም ክለቡ አክሏል። እአአ በ2017 ለመጨረሻ ጊዜ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ያነሳውን ክለብ ባለቤቶች በመቃወም ደጋፊዎች በርካታ ተቃውሞዎችን አካሂደዋል። የፖርቹጋሉ አምበል ሮናልዶ አክሎም "ደጋፊዎቹ ሁሌም ትክክል ናቸው። እውነታውን ማወቅ አለባቸው። ተጫዋቾቹ ለክለቡ ጥሩ ነገር ይፈልጋሉ። እኔም ለክለቡ ጥሩ ነገር እመኛለሁ። ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ የመጣሁትም ለዚህ ነው። ለዚህም ነው ይህንን ክለብ የምወደው” ብሏል። “ማንቸስተር እንደ ሲቲ፣ ሊቨርፑል እና አሁን ደግሞ እንደ አርሴናል ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዳይደርስ የሚያደርጉ አንዳንድ ነገሮች በክለቡ ውስጥ አሉ።“ "ውስብስብ ነው። ከባድ ነው። በጣም ከባድ ነው።" "ኔቪልና ሩኒ ጓደኞቼ አይደሉም" በእሑዱ ቃለ ምልልስ ወቅት ሮናልዶ የቀድሞው የዩናይትድ የቡድን አጋሩ ዋይኒ ሩኒ ስለተቸው ተበሳጭቶ እንደሆን ተጠይቆ ነበር። ሮናልዶ "ምናልባት በሠላሳዎቹ ዕድሜው ጫማውን ስለሰቀለ ይሆናል። እኔ አሁንም በትልቅ ደረጃ እየተጫወትኩ ነው። ከሱ የተሻልኩ ነኝ አልልም። ምክንያቱም እውነት ነው. . .።" አሁን ደግሞ ትኩረቱን ወደ ሌላ የቀድሞ የዩናይትድ አጋሩ ጋሪ ኔቪል አዙሯል። የቀድሞ የእንግሊዝ የቀኝ መስመር ተከላካይ በቅርቡ ለስካይ ስፖርት ተንታኝ ሆኖ ሲሠራ ሮናልዶ ሠላም ሳይለው ቀርቷል። "ከአንተ ጋር ከተጫወቱ ሰዎች እንዲህ ዓይነቱን ትችት እና አሉታዊነት ማዳመጥ በጣም ከባድ ነው። ለምሳሌ ጋሪ ኔቪል። ሁለቱም ጓደኞቼ አይደሉም" ሲል ሮናልዶ ተናግሯል። "መተቸት ቀላል ነው። በቴሌቪዥን ሠርቶ የበለጠ ታዋቂ ለመሆን መተቸት ግዴታ ይሁንባቸው አላውቅም። በእርግጥም አልገባኝም።“ "ሞኞች ስላልሆኑ (የእኔን ስም) የሚያነሱት ሊጠቀሙበት ይመስለኛል። ከአንተ ጋር በአንድ መልበሻ ክፍል የነበሩ ሰዎች በዚያ መንገድ ሲተቹ ማየት በጣም ከባድ ነው" ብሏል። ከዚህ በፊት ምን ተፈጠረ? ቀደም ሲል በተለቀቀው የቃለ ምልልሱ ክፍል በሳምንት 500 ሺህ ፓውንድ የሚከፈለው ሮናልዶ ክለቡ አስገድዶ ሊያስወጣው እየሞከረ መሆኑን እና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግን እንደማያከብር ተናግሯል። ሮናልዶ ከአውሮፓውያኑ 2003 እና 2009 ለዩናይትድ 118 ጎሎችን አስቆጥሯል። በ2021 ክረምት ወደ ክለቡ በድጋሚ የተመለሰው በክለቡ ደጋፊዎች ዘንድ በአክብሮት ነበር። በዚህ ሳምንት የሚተላለፈው ሙሉው ቃለ መጠይቅ ብዙ ደጋፊዎችን ከእሱ እንደሚያርቅ ይጠበቃል። ሮናልዶ አሁን በኳታር ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ከፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c980grz0n04o |
0business
| ዩክሬን ውስጥ እዳቸውን መክፈል ያልቻሉ ሰዎች የውስጥ ልብስ ለጨረታ ቀረበ | ዩክሬን ወስጥ እዳቸውን መክፈል ያልቻሉ ሰዎች የውስጥ ልብስ ጭምር ለጨረታ መቅረቡ በርካቶችን አስገርሟል። በዩክሬን ማዕከላዊ ከተማ ክሪይቪ ሪህ የተለያዩ አልባሳት እና ጫማዎች በአገሪቱ የፍትህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ይፋዊ ድረ ገጽ ላይ ለሽያጭ ቀርበዋል። የአልባሳቱ መነሻ የመሸጫ ዋጋ ደግሞ 70 ሳንቲም ዶላር እንደሆነ ተገልጿል። መስሪያ ቤቱ ከአልባሳት በተጨማሪ ላሞችና በጎችንም ጭምር ለሽያጭ አቅርቧል። የ ኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ እስከ 2 ሚሊየን የሚደርሱ ዩክሬናውያን ከመንግሰት አበዳሪ ተቋማት የተለያዩ የብድር አይነቶችን ወስደዋል። ቢቢሲ ከአንድ ዩክሬን መስሪያ ቤት ባገኘው መረጃ መሰረት ባለፈው ዓመት ብቻ የተበዳሪዎች ቁጥር በ300 ሺ ጨምሯል። ባለፈው ዓመት በአንድ ወቅት በማህበራዊ ሚዲያ በተሰራጨ መልዕክት ሁለት የቤት እንስሳ የሆኑ ውሻዎች ለሽያጭ ቀርበው በርካቶች ተቃውሟቸው ን ሲገልጹ ነበር። አንድ የሕዝብ እንደራሴ ደግሞ እዳዋን መክፈል ያልቻለች አንዲት ጡረተኛ ውሻዎቿን ሸጣም ቢሆን እዳዋን መክፈል አለባት ብለው ነበር። በወቅቱም በርካቶች ተቃውሟቸውን ገልጸው ነበር። የፍትህ ሚኒስትሩ ዴኒስ ማሊዩስካ ወደኋላ ላይ ግን የቤት እንሳስቱን መሸጥ እምብዛም አዋጪ ነገር እንዳልሆነና ቢቻል በጥሩ ገንዘብ ሊሸጡ የሚችሉ ንብረቶች ላይ ትኩረት ቢደረግ ይሻላል ብለዋል። ኦኢሲዲ የተባለው አንድ ተቋም ባለፈው ወር ባወጣው ሪፖርት መሰረት የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ዩክሬን ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ሊያጋጥማት የሚችል ሲሆን ይህም ባለፉት 10 ኣመታት ከታየው በጣም ትልቁ ነው። ወረርሽኙን ተከትሎም አገሪቱ ካላት 41 ሚሊዮን ዜጎች ውስጥ 9 ሚሊዮን የሚሆኑት እጅግ በከፋ ድህነት ውስጥ ይኖራሉ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰራው ጥናት መሰረት ደግሞ ከኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ ከአጠቃላይ ህዝቡ 40 በመቶ የሚሆኑ ቤተሰቦች በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የቤተሰብ አባላቸው ስራ አጥቷል። ዩክሬን ውስጥ እዳቸውን መክፈል ያልቻሉ ሰዎችን ንብረት ለሽያጭ የሚያቀርበው ድረ ገጽ የተቋቋመው በአውሮፓውያኑ 2015 ነበር። የፍትህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደሚለው እስካሁን 506 ሚሊየን ዶላር ከሽያጩ ተገኝቷል። ከዘህ በተጨማሪም መስሪያ ቤቱ እዳቸውን መክፈል ካልቻሉ ሰዎች የተወሰዱ ንብረቶችን ለወላጅ አልባ ህጻናት፣ ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎች በነጻ እንዲሰጡ እንደሚደረግ ተገልጿል። | ዩክሬን ውስጥ እዳቸውን መክፈል ያልቻሉ ሰዎች የውስጥ ልብስ ለጨረታ ቀረበ ዩክሬን ወስጥ እዳቸውን መክፈል ያልቻሉ ሰዎች የውስጥ ልብስ ጭምር ለጨረታ መቅረቡ በርካቶችን አስገርሟል። በዩክሬን ማዕከላዊ ከተማ ክሪይቪ ሪህ የተለያዩ አልባሳት እና ጫማዎች በአገሪቱ የፍትህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ይፋዊ ድረ ገጽ ላይ ለሽያጭ ቀርበዋል። የአልባሳቱ መነሻ የመሸጫ ዋጋ ደግሞ 70 ሳንቲም ዶላር እንደሆነ ተገልጿል። መስሪያ ቤቱ ከአልባሳት በተጨማሪ ላሞችና በጎችንም ጭምር ለሽያጭ አቅርቧል። የ ኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ እስከ 2 ሚሊየን የሚደርሱ ዩክሬናውያን ከመንግሰት አበዳሪ ተቋማት የተለያዩ የብድር አይነቶችን ወስደዋል። ቢቢሲ ከአንድ ዩክሬን መስሪያ ቤት ባገኘው መረጃ መሰረት ባለፈው ዓመት ብቻ የተበዳሪዎች ቁጥር በ300 ሺ ጨምሯል። ባለፈው ዓመት በአንድ ወቅት በማህበራዊ ሚዲያ በተሰራጨ መልዕክት ሁለት የቤት እንስሳ የሆኑ ውሻዎች ለሽያጭ ቀርበው በርካቶች ተቃውሟቸው ን ሲገልጹ ነበር። አንድ የሕዝብ እንደራሴ ደግሞ እዳዋን መክፈል ያልቻለች አንዲት ጡረተኛ ውሻዎቿን ሸጣም ቢሆን እዳዋን መክፈል አለባት ብለው ነበር። በወቅቱም በርካቶች ተቃውሟቸውን ገልጸው ነበር። የፍትህ ሚኒስትሩ ዴኒስ ማሊዩስካ ወደኋላ ላይ ግን የቤት እንሳስቱን መሸጥ እምብዛም አዋጪ ነገር እንዳልሆነና ቢቻል በጥሩ ገንዘብ ሊሸጡ የሚችሉ ንብረቶች ላይ ትኩረት ቢደረግ ይሻላል ብለዋል። ኦኢሲዲ የተባለው አንድ ተቋም ባለፈው ወር ባወጣው ሪፖርት መሰረት የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ዩክሬን ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ሊያጋጥማት የሚችል ሲሆን ይህም ባለፉት 10 ኣመታት ከታየው በጣም ትልቁ ነው። ወረርሽኙን ተከትሎም አገሪቱ ካላት 41 ሚሊዮን ዜጎች ውስጥ 9 ሚሊዮን የሚሆኑት እጅግ በከፋ ድህነት ውስጥ ይኖራሉ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰራው ጥናት መሰረት ደግሞ ከኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ ከአጠቃላይ ህዝቡ 40 በመቶ የሚሆኑ ቤተሰቦች በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የቤተሰብ አባላቸው ስራ አጥቷል። ዩክሬን ውስጥ እዳቸውን መክፈል ያልቻሉ ሰዎችን ንብረት ለሽያጭ የሚያቀርበው ድረ ገጽ የተቋቋመው በአውሮፓውያኑ 2015 ነበር። የፍትህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደሚለው እስካሁን 506 ሚሊየን ዶላር ከሽያጩ ተገኝቷል። ከዘህ በተጨማሪም መስሪያ ቤቱ እዳቸውን መክፈል ካልቻሉ ሰዎች የተወሰዱ ንብረቶችን ለወላጅ አልባ ህጻናት፣ ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎች በነጻ እንዲሰጡ እንደሚደረግ ተገልጿል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56090926 |
5sports
| ሁለት ሜትር ከሃያ አምስት ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ሴኔጋላዊ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች | ሴኔጋላዊው ታኮ ፎል ወደ ቅርጫት ኳሱ ዓለም የተቀላቀለው ገና ከሰባት ዓመታት በፊት ቢሆንም የ2.25 ሜትር ርዝማኔ ያለው ይህ ተጫዋች በአሜሪካ ቅርጫት ኳስ (ኤንቢኤ) ከፍተኛ ስፍራ እያገኘ ነው። ከዓለም ረዥሙ የቀድሞው የእግር ኳስ ተጫዋች ሮማኒያዊው ጆርጅ ሙሬሳን በ6.3 ሴንቲ ሜትር የሚያጥረው የ23 አመቱ ታኮ፤ የታዋቂው የቦስተን ሴልቲክስ ከቋሚዎቹ አስራ አምስት ተጫዋቾች አንዱ ለመሆንም ጥረት ላይ ነው። • የደቡብ አፍሪካ ባሕር ጠላቂዎች በኬንያ አስክሬን ፍለጋ ላይ ሊሰማሩ ነው • የካቶሊክ ቄሶች ማግባት ይፈቀድላቸው ይሆን? • በአሜሪካዊቷ ፖሊስ የፍርድ ሂደት ምስክርነት የሰጠው የዐይን እማኝ ተገደለ ሴልቲክስ ታኮ ፎልን የመረጠበት ምክንያትም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቡ እንደሆነም ተገልጿል። በሴኔጋሏ መዲና ዳካር የተወለደው ታኮ፤ ወደ አሜሪካ የሄደው በ16 ዓመቱ ሲሆን፤ በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሴንትራል ፍሎሪዳ ቅርጫት ኳስ ይጫወት ነበር። ታኮ ለቢቢሲ እንደተናገረው፤ ዩኒቨርስቲው ውስጥ ብዙዎች ሙያውን እንዲያሳድግ ድጋፍ አድርገውለታል። ታዳጊ ሳለ ብዙም ስለ ቅርጫት ኳስ እንደማያውቅ ይናገራል። ጊዜውን ያሳልፍ የነበረው ካርቱን ፊልሞች በማየት ነበር። የአያቱ ቅርጫት ኳስ መውደድ ስፖርቱ ላይ ፍቅር እንዲያሳድር አድርጎታል። ወደ አሜሪካ ከሄደ በኋላ ሙሉ ትኩረቱን ወደ ቅርጫት ኳስ አድርጓል። ጉዞው ግን አልጋ በአልጋ አልነበረም። "ቅርጫት ኳስ መጫወት አልችልም ነበር። ብዙ ነገር መማር ይጠበቅብኝ ነበር። እድለኛ ሆኜ ብዙ ሰዎች ራሴን እንዳሻሽል ረድተውኛል" ይላል። ሂውስተን አንድ ዓመት ከቆየ በኋላ ወደ ቴኒሲ፣ ጂዎርጂያ እና ፍሎሪዳ አቅንቷል። በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሴንትራል ፍሎሪዳ ሁለት ዓመት ቆይቷል። "አንድ ሴኔጋላዊ ታዳጊ ነበርኩ። ቅርጫት ኳስ መጫወት የጀመርኩትም ከስድስት ዓመት በፊት ነበር። ኤንቢኤ ውስጥ ለመጫወት ብዙ ለፍቻለሁ። በጣም እድለኛ እንደሆንኩ ይሰማኛል። ቅርጫት ኳስ ሕይወቴ ነው። አንድ ቀን እንኳን ሳልጫወት ባልፍ አዝናለሁ" ሲል ይናገራል። | ሁለት ሜትር ከሃያ አምስት ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ሴኔጋላዊ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ሴኔጋላዊው ታኮ ፎል ወደ ቅርጫት ኳሱ ዓለም የተቀላቀለው ገና ከሰባት ዓመታት በፊት ቢሆንም የ2.25 ሜትር ርዝማኔ ያለው ይህ ተጫዋች በአሜሪካ ቅርጫት ኳስ (ኤንቢኤ) ከፍተኛ ስፍራ እያገኘ ነው። ከዓለም ረዥሙ የቀድሞው የእግር ኳስ ተጫዋች ሮማኒያዊው ጆርጅ ሙሬሳን በ6.3 ሴንቲ ሜትር የሚያጥረው የ23 አመቱ ታኮ፤ የታዋቂው የቦስተን ሴልቲክስ ከቋሚዎቹ አስራ አምስት ተጫዋቾች አንዱ ለመሆንም ጥረት ላይ ነው። • የደቡብ አፍሪካ ባሕር ጠላቂዎች በኬንያ አስክሬን ፍለጋ ላይ ሊሰማሩ ነው • የካቶሊክ ቄሶች ማግባት ይፈቀድላቸው ይሆን? • በአሜሪካዊቷ ፖሊስ የፍርድ ሂደት ምስክርነት የሰጠው የዐይን እማኝ ተገደለ ሴልቲክስ ታኮ ፎልን የመረጠበት ምክንያትም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቡ እንደሆነም ተገልጿል። በሴኔጋሏ መዲና ዳካር የተወለደው ታኮ፤ ወደ አሜሪካ የሄደው በ16 ዓመቱ ሲሆን፤ በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሴንትራል ፍሎሪዳ ቅርጫት ኳስ ይጫወት ነበር። ታኮ ለቢቢሲ እንደተናገረው፤ ዩኒቨርስቲው ውስጥ ብዙዎች ሙያውን እንዲያሳድግ ድጋፍ አድርገውለታል። ታዳጊ ሳለ ብዙም ስለ ቅርጫት ኳስ እንደማያውቅ ይናገራል። ጊዜውን ያሳልፍ የነበረው ካርቱን ፊልሞች በማየት ነበር። የአያቱ ቅርጫት ኳስ መውደድ ስፖርቱ ላይ ፍቅር እንዲያሳድር አድርጎታል። ወደ አሜሪካ ከሄደ በኋላ ሙሉ ትኩረቱን ወደ ቅርጫት ኳስ አድርጓል። ጉዞው ግን አልጋ በአልጋ አልነበረም። "ቅርጫት ኳስ መጫወት አልችልም ነበር። ብዙ ነገር መማር ይጠበቅብኝ ነበር። እድለኛ ሆኜ ብዙ ሰዎች ራሴን እንዳሻሽል ረድተውኛል" ይላል። ሂውስተን አንድ ዓመት ከቆየ በኋላ ወደ ቴኒሲ፣ ጂዎርጂያ እና ፍሎሪዳ አቅንቷል። በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሴንትራል ፍሎሪዳ ሁለት ዓመት ቆይቷል። "አንድ ሴኔጋላዊ ታዳጊ ነበርኩ። ቅርጫት ኳስ መጫወት የጀመርኩትም ከስድስት ዓመት በፊት ነበር። ኤንቢኤ ውስጥ ለመጫወት ብዙ ለፍቻለሁ። በጣም እድለኛ እንደሆንኩ ይሰማኛል። ቅርጫት ኳስ ሕይወቴ ነው። አንድ ቀን እንኳን ሳልጫወት ባልፍ አዝናለሁ" ሲል ይናገራል። | https://www.bbc.com/amharic/news-49960041 |
3politics
| ቦርዱ የኦነግን ጠቅላላ ጉባኤና በምርጫ የመሳተፍ ጥያቄን ውድቅ አደረገ | በቅርቡ አዲስ የአመራር አባላትን መርጫለሁ ያለው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ክንፍ ያካሄደው ጠቅላላ ጉባኤና በምርጫ ለመሳተፍ ያቀረበው ጥያቄ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ውድቅ ተደረገበት። በኦነግ ከፍተኛ የአመራር አባላት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ሳቢያ ግንባሩ በሁለት ወገኖች መካከል ተከፍሎ በቀጣዩ ምርጫ ለመሳተፍ የዕጩዎች ምዝገባ ሳያከናውን የጊዜ ገደቡ ጊዜ እንዳለፈው ይታወሳል። ቦርዱ ውሳኔውን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ላይ እንደጠቀሰው በግንባሩ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን ክፍፍልና ውዝግብን ተከትሎ ከሁለቱም ወገን አቤቱታዎችና የማሳወቂያ ደብዳቤዎችን ሲቀበል መቆየቱ በመግለጽ ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝ የበኩሉን ጥረት ማድረጉን ገልጿል። ግንባሩ በቀደምት ሊቀመንበሩ በአቶ ዳውድ ኢብሳና ምክትላቸው በነበሩት በአቶ አራርሶ ቢቂላ መካከል ለሁለት ተከፍሎ የተለያየ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ውሳኔዎችን እየሰጠ ነው። በአቶ ዳውድ የሚመራው ቡድን በግንባሩ ላይ የተለያዩ ጫናዎች እየደረሱ ነው በሚል በምርጫው ላይ እንደማይሳተፍ ቢገልጽም የአቶ አራርሶ ቡድን ግን ተገቢውን ማስተካከያ እንዳደረገ በመግለጽ በምርጫው የመሳተፍ ፍላጎቱን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አቅርቦ ነበር። በግንባሩ ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታትም ሁለቱ ወገኖችን በተናጠል እንዲሁም የፓርቲውን የሥነ ሥርዓት እና የቁጥጥር ኮሚቴን በማነጋገር ያሉ አስተዳደራዊና ሕጋዊ መንገዶች ሁሉ በመጠቀም መፍትሔ ለመስጠት ጥረት ማድረጉን ቦርዱ ገልጿል። በመጨረሻም የግንባሩን ጠቅላላ ጉባኤ መጥራት ፓርቲው ለገጠመው ችግር ብቸኛ መፍትሔ መሆኑን በማስረዳት በውዝግብ ውስጥ ያሉ አመራሮችም ይህንኑ ሃሳብ በመቀበል የተፈጠረውን ችግር በጠቅላላ ጉባኤ እንዲፈታ መወሰኑ የምርጫ ቦርድ መግለጫ አስታውሷል። በዚህም የግንባሩ አንደኛ ወገን ጠቅላላ ጉባኤ በማካሄድ አዲስ የአመራር አባላት መምረጡን በመግለጽ፣ "በውስጥ ችግሩ ምክንያት የጠቅላላ ጉባኤ ሳያካሂድ በመቆየቱ የነበረበትን ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት የምልክት መረጣና የዕጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዲያደርግ እንዲፈቅድለት ጠቅላላ ጉባኤውንም እንዲጸድቅለት" መጠየቁን ምርጫ ቦርድ አመልክቷል። ቦርዱም የቀረቡለትን ሰነዶች መርምሮ በጠቅላላ ጉባኤው አካሄድና ተሳታፊዎች በኩል የግንባሩን ሕገ ደንብ ባከበረ መንገድ አለመካሄዱን የሚያመለክቱ አምስት ነጥቦችን በማስቀመት የቀረበለትን የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔና በምርጫ የመሳተፍ ጥያቄን እንዳልተቀበለው ገልጿል። ስለዚህም በመጪው ግንቦት ወር ማብቂያ ላይ በሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎቱን ገልጾ የነበረው በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው የኦነግ አንድ ክፍል ያካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። ባለፈው ሳምንት በአገሪቱ ምክር ቤት ቀርበው ለተነሱ ጥያቄዎች መልስና ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በምርጫው ለመሳተፍ ፍላጎት ያለው ፓርቲን አሁንም ቦርዱ ቢቀበለው እንደሚደግፉ ገልጸው ነበር። በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው ኦነግ በምርጫው የመሳተፉ ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ የቆየ ቢሆንም አሁን በገጠመው ችግር ምክንያት ከምርጫው ውድድር ውጪ ሆኗል። ከዚህ ቀደምም የኦሮሞ ፌደራሊስte ኮንግረስ በአባላቱ መታሰርና በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ጽህፈት ቤቶቹ መዘጋትን እንደምክንያት በማቅረብ በምርጫው ላይ ለመሳተፍ እንደሚቸገር መግለጹ ይታወሳል። የብልጽግና ፓርቲ ሕዝብ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ፓርቲዎቹ መንግሥት ጫና ያደርስብናል፣ አባላቶቻችንን ያስራል፣ ጽህፈት ቤታችንን ዘግቷል ሲሉ የሚያቀርቡትን ውንጀላ "መሰረት የሌለው" ሲሉ ከዚህ በፊት ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። በመጪው ግንቦት ወር መጨረሻና በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ከትግራይ ክልል በስተቀር በቀሪው የአገሪቱ አካባቢዎች በሚካሄደው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ላይ የሚወዳደሩ 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም 125 የግል ዕጩዎች ለመወዳደር ተመዝግበዋል። ባለፈው ሳምንት ደግሞ ሁለት ወር ያህል በቀረው ምርጫ ላይ ድምጽ የሚሰጡ የመራጮች ዝገባ መጀመሩን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳውቋል። | ቦርዱ የኦነግን ጠቅላላ ጉባኤና በምርጫ የመሳተፍ ጥያቄን ውድቅ አደረገ በቅርቡ አዲስ የአመራር አባላትን መርጫለሁ ያለው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ክንፍ ያካሄደው ጠቅላላ ጉባኤና በምርጫ ለመሳተፍ ያቀረበው ጥያቄ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ውድቅ ተደረገበት። በኦነግ ከፍተኛ የአመራር አባላት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ሳቢያ ግንባሩ በሁለት ወገኖች መካከል ተከፍሎ በቀጣዩ ምርጫ ለመሳተፍ የዕጩዎች ምዝገባ ሳያከናውን የጊዜ ገደቡ ጊዜ እንዳለፈው ይታወሳል። ቦርዱ ውሳኔውን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ላይ እንደጠቀሰው በግንባሩ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን ክፍፍልና ውዝግብን ተከትሎ ከሁለቱም ወገን አቤቱታዎችና የማሳወቂያ ደብዳቤዎችን ሲቀበል መቆየቱ በመግለጽ ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝ የበኩሉን ጥረት ማድረጉን ገልጿል። ግንባሩ በቀደምት ሊቀመንበሩ በአቶ ዳውድ ኢብሳና ምክትላቸው በነበሩት በአቶ አራርሶ ቢቂላ መካከል ለሁለት ተከፍሎ የተለያየ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ውሳኔዎችን እየሰጠ ነው። በአቶ ዳውድ የሚመራው ቡድን በግንባሩ ላይ የተለያዩ ጫናዎች እየደረሱ ነው በሚል በምርጫው ላይ እንደማይሳተፍ ቢገልጽም የአቶ አራርሶ ቡድን ግን ተገቢውን ማስተካከያ እንዳደረገ በመግለጽ በምርጫው የመሳተፍ ፍላጎቱን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አቅርቦ ነበር። በግንባሩ ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታትም ሁለቱ ወገኖችን በተናጠል እንዲሁም የፓርቲውን የሥነ ሥርዓት እና የቁጥጥር ኮሚቴን በማነጋገር ያሉ አስተዳደራዊና ሕጋዊ መንገዶች ሁሉ በመጠቀም መፍትሔ ለመስጠት ጥረት ማድረጉን ቦርዱ ገልጿል። በመጨረሻም የግንባሩን ጠቅላላ ጉባኤ መጥራት ፓርቲው ለገጠመው ችግር ብቸኛ መፍትሔ መሆኑን በማስረዳት በውዝግብ ውስጥ ያሉ አመራሮችም ይህንኑ ሃሳብ በመቀበል የተፈጠረውን ችግር በጠቅላላ ጉባኤ እንዲፈታ መወሰኑ የምርጫ ቦርድ መግለጫ አስታውሷል። በዚህም የግንባሩ አንደኛ ወገን ጠቅላላ ጉባኤ በማካሄድ አዲስ የአመራር አባላት መምረጡን በመግለጽ፣ "በውስጥ ችግሩ ምክንያት የጠቅላላ ጉባኤ ሳያካሂድ በመቆየቱ የነበረበትን ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት የምልክት መረጣና የዕጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዲያደርግ እንዲፈቅድለት ጠቅላላ ጉባኤውንም እንዲጸድቅለት" መጠየቁን ምርጫ ቦርድ አመልክቷል። ቦርዱም የቀረቡለትን ሰነዶች መርምሮ በጠቅላላ ጉባኤው አካሄድና ተሳታፊዎች በኩል የግንባሩን ሕገ ደንብ ባከበረ መንገድ አለመካሄዱን የሚያመለክቱ አምስት ነጥቦችን በማስቀመት የቀረበለትን የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔና በምርጫ የመሳተፍ ጥያቄን እንዳልተቀበለው ገልጿል። ስለዚህም በመጪው ግንቦት ወር ማብቂያ ላይ በሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎቱን ገልጾ የነበረው በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው የኦነግ አንድ ክፍል ያካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። ባለፈው ሳምንት በአገሪቱ ምክር ቤት ቀርበው ለተነሱ ጥያቄዎች መልስና ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በምርጫው ለመሳተፍ ፍላጎት ያለው ፓርቲን አሁንም ቦርዱ ቢቀበለው እንደሚደግፉ ገልጸው ነበር። በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው ኦነግ በምርጫው የመሳተፉ ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ የቆየ ቢሆንም አሁን በገጠመው ችግር ምክንያት ከምርጫው ውድድር ውጪ ሆኗል። ከዚህ ቀደምም የኦሮሞ ፌደራሊስte ኮንግረስ በአባላቱ መታሰርና በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ጽህፈት ቤቶቹ መዘጋትን እንደምክንያት በማቅረብ በምርጫው ላይ ለመሳተፍ እንደሚቸገር መግለጹ ይታወሳል። የብልጽግና ፓርቲ ሕዝብ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ፓርቲዎቹ መንግሥት ጫና ያደርስብናል፣ አባላቶቻችንን ያስራል፣ ጽህፈት ቤታችንን ዘግቷል ሲሉ የሚያቀርቡትን ውንጀላ "መሰረት የሌለው" ሲሉ ከዚህ በፊት ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። በመጪው ግንቦት ወር መጨረሻና በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ከትግራይ ክልል በስተቀር በቀሪው የአገሪቱ አካባቢዎች በሚካሄደው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ላይ የሚወዳደሩ 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም 125 የግል ዕጩዎች ለመወዳደር ተመዝግበዋል። ባለፈው ሳምንት ደግሞ ሁለት ወር ያህል በቀረው ምርጫ ላይ ድምጽ የሚሰጡ የመራጮች ዝገባ መጀመሩን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳውቋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56555595 |
0business
| የተትረፈረፈ ቢመስልም የአሸዋ እጥረት ዓለም ላይ ተፈጥሯል | በተለይም በበረሃና በባህር ዳርቻዎች የሚገኘው አሸዋ የትም የሚገኝ ቢመስልም በዓለም ላይ ሰዎች እጅጉን እየተጠቀሟቸው ካሉ ነገሮች ሁለተኛው ነው። ባለፈው መስከረም ወር ብቻ ደቡብ አፍሪካዊ ሥራ ፈጣሪ፣ ሁለት ህንዳዊያን እንዲሁም ሜክሲኳዊ የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ብዙ ዋጋ ባልተሰጠው ነገር ግን በጣም አስፈላጊ በሆነው አሸዋ ምክንያት ተገድለዋል። • እየጨመረ የመጣው የአሸዋ ፍላጎት ወንዞችን እያጠፋ ነው • አሸዋ የሰረቁ ፈረንሳያውያን ጥንዶች ለእስር ተዳረጉ ብዙም ባይመስልም አሸዋ እጅጉን አስፈላጊ ነገር ነው። በጥቅሉ ለከተሞች ግንባታ ወሳኝ ግብአት ነው- አሸዋ። የገበያ ማዕከሎች፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ የአስፓልት መንገዶች ግንባታ ያለ አሸዋ የሚታሰብ አደለም። በየቦታው የሚታዩት የመስታወት መስኮቶች፤ የስማርት ስልኮች ስክሪን ጭምር ከቀለጠ አሸዋ የሚሰሩ ናቸው። በስልኮቻችን እንዲሁም በኮምፒውተሮቻችን ውስጥ ያሉ ሲልከን ቺፖችም ከቀለጠ አሸዋ የተሰሩ ናቸው። ይህም ብቻ አይደለም በመኖሪያ ቤቶቻችን ለሚገኙ የኤሌክትሪክ መገልገያ እቃዎች ስሪትም አሸዋ ግብአት ነው። ምንም እኳ ከሰሃራ እስከ አሪዞና ባሉ ሰፋፊ በርሃዎችና በባህር ዳርቻዎች ቢገኝም፤ በአቅራቢያ ከሚገኝ መደብር በቀላሉ ልንገዛው የምንችለው ነገር ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ዓለም ላይ የአሸዋ እጥረት አጋጥሟል። • ሳናውቀው እያለቁብን ያሉ ስድስት ነገሮች ለመሆኑ በዓለም ላይ የትም ቦታ የሚገኝ ነገር እንዴት እጥረት ሊፈጠርበት ይችላል? በዓመት 50 ቢሊዮን ቶን አሸዋ በሰዎች ጥቅም ላይ ይውላል። ይህ የአሸዋ መጠን መላዋን እንግሊዝ ሊያለብስ የሚችል ነው። አጥኚዎቹ እንደሚሉት ችግሩ ያለው ጥቅም ላይ እየዋለ ባለው አሸዋ አይነት ምክንያት እንደሆነ እየተናገሩ ነው። ከላይ ለተጠቀሱት አገልግሎቶች ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ለስላሳውና በቀላሉ በንፋስ የሚበነው የበረሃ አሸዋ አይደለም። ይህ በጣም ደቃቅ የበረሃ አሸዋ ለኮንክሪት የሚሆን አይደለም። ይልቁንም ለሰዎች አስፈላጊ የሆነው ባለ ማእዘኑ እና በወንዞች እና በሃይቆች የሚገኘው ነው። ስለዚህም ይህኛውን አሸዋ ለማግኘት በወንዞች መድረሻ፣ በእርሻ ማሳዎ እንዲሁም በጫካዎች ውስጥ ሕገ ወጥ ፍለጋ ይካሄዳል። ጥቂት በማይባሉ አገራትም የወንጀለኛ ቡድኖች በዚህ የአሸዋ ንግድ ላይ ተሰማርተዋል፤ በዚህ ሳቢያ ደግሞ የአሸዋ ጥቁር ገበያም ተስፋፍቷል። • ኢትዮጵያ አርባ በመቶ ዕፀዋቶቿን ልታጣ እንደምትችል ተነገረ "የአሸዋ እጥረት ጉዳይ ብዙዎች እያስገረመ ነው ግን ሊያስገርም አይገባም። ያለ ምንም አካባቢያዊ ተፅዕኖ የአንድን ተፈጥሯዊ ሃብት 50 ቢሊዮን ቶን የሚያክል ነገር ማውጣት የሚቻል ነገር አይደለም" ይላሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም ተመራማሪው ፓስካል ፔዱዚ። | የተትረፈረፈ ቢመስልም የአሸዋ እጥረት ዓለም ላይ ተፈጥሯል በተለይም በበረሃና በባህር ዳርቻዎች የሚገኘው አሸዋ የትም የሚገኝ ቢመስልም በዓለም ላይ ሰዎች እጅጉን እየተጠቀሟቸው ካሉ ነገሮች ሁለተኛው ነው። ባለፈው መስከረም ወር ብቻ ደቡብ አፍሪካዊ ሥራ ፈጣሪ፣ ሁለት ህንዳዊያን እንዲሁም ሜክሲኳዊ የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ብዙ ዋጋ ባልተሰጠው ነገር ግን በጣም አስፈላጊ በሆነው አሸዋ ምክንያት ተገድለዋል። • እየጨመረ የመጣው የአሸዋ ፍላጎት ወንዞችን እያጠፋ ነው • አሸዋ የሰረቁ ፈረንሳያውያን ጥንዶች ለእስር ተዳረጉ ብዙም ባይመስልም አሸዋ እጅጉን አስፈላጊ ነገር ነው። በጥቅሉ ለከተሞች ግንባታ ወሳኝ ግብአት ነው- አሸዋ። የገበያ ማዕከሎች፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ የአስፓልት መንገዶች ግንባታ ያለ አሸዋ የሚታሰብ አደለም። በየቦታው የሚታዩት የመስታወት መስኮቶች፤ የስማርት ስልኮች ስክሪን ጭምር ከቀለጠ አሸዋ የሚሰሩ ናቸው። በስልኮቻችን እንዲሁም በኮምፒውተሮቻችን ውስጥ ያሉ ሲልከን ቺፖችም ከቀለጠ አሸዋ የተሰሩ ናቸው። ይህም ብቻ አይደለም በመኖሪያ ቤቶቻችን ለሚገኙ የኤሌክትሪክ መገልገያ እቃዎች ስሪትም አሸዋ ግብአት ነው። ምንም እኳ ከሰሃራ እስከ አሪዞና ባሉ ሰፋፊ በርሃዎችና በባህር ዳርቻዎች ቢገኝም፤ በአቅራቢያ ከሚገኝ መደብር በቀላሉ ልንገዛው የምንችለው ነገር ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ዓለም ላይ የአሸዋ እጥረት አጋጥሟል። • ሳናውቀው እያለቁብን ያሉ ስድስት ነገሮች ለመሆኑ በዓለም ላይ የትም ቦታ የሚገኝ ነገር እንዴት እጥረት ሊፈጠርበት ይችላል? በዓመት 50 ቢሊዮን ቶን አሸዋ በሰዎች ጥቅም ላይ ይውላል። ይህ የአሸዋ መጠን መላዋን እንግሊዝ ሊያለብስ የሚችል ነው። አጥኚዎቹ እንደሚሉት ችግሩ ያለው ጥቅም ላይ እየዋለ ባለው አሸዋ አይነት ምክንያት እንደሆነ እየተናገሩ ነው። ከላይ ለተጠቀሱት አገልግሎቶች ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ለስላሳውና በቀላሉ በንፋስ የሚበነው የበረሃ አሸዋ አይደለም። ይህ በጣም ደቃቅ የበረሃ አሸዋ ለኮንክሪት የሚሆን አይደለም። ይልቁንም ለሰዎች አስፈላጊ የሆነው ባለ ማእዘኑ እና በወንዞች እና በሃይቆች የሚገኘው ነው። ስለዚህም ይህኛውን አሸዋ ለማግኘት በወንዞች መድረሻ፣ በእርሻ ማሳዎ እንዲሁም በጫካዎች ውስጥ ሕገ ወጥ ፍለጋ ይካሄዳል። ጥቂት በማይባሉ አገራትም የወንጀለኛ ቡድኖች በዚህ የአሸዋ ንግድ ላይ ተሰማርተዋል፤ በዚህ ሳቢያ ደግሞ የአሸዋ ጥቁር ገበያም ተስፋፍቷል። • ኢትዮጵያ አርባ በመቶ ዕፀዋቶቿን ልታጣ እንደምትችል ተነገረ "የአሸዋ እጥረት ጉዳይ ብዙዎች እያስገረመ ነው ግን ሊያስገርም አይገባም። ያለ ምንም አካባቢያዊ ተፅዕኖ የአንድን ተፈጥሯዊ ሃብት 50 ቢሊዮን ቶን የሚያክል ነገር ማውጣት የሚቻል ነገር አይደለም" ይላሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም ተመራማሪው ፓስካል ፔዱዚ። | https://www.bbc.com/amharic/news-50555337 |
0business
| የኢትዮጵያ ከአግዋ መታገድ በሥራ ዕድል እና በውጭ ምንዛሪ ምን ያጎድልባታል? | የአሜሪካ መንግሥት ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገራት የዘረጋው ከቀረጥ ነጻ ዕድል ተጠቃሚ የነበረችው ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ ከዚህ ዕድል መታገዷ ተሰምቷል። በ2005 ዓ.ም የአግዋ ፎረምን ያስተናገደችው ኢትዮጵያ በአግዋ በኩል ለሁለት አስርት ዓመታት የተለያዩ ምርቶችን [በስፋት ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት] ለአሜሪካ ገበያ በማቅረብ ለመቶ ሺዎች የሥራ ዕድል በመፍጠር በሚሊዮኖች የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ ስታገኝ ቆይታለች። እንደ አውሮፓውያኑ በ2000 ይፋ በተደረገው በዚህ የቀረጥ ነጻ ዕድል ተጠቃሚ ከሆኑ 38 አገራት አንዷ የነበረችው ኢትዮጵያ የተለያዩ ምርቶችን ለአሜሪካ ገበያ ስታቀርብ ቆይታ ከዚህ ተጠቃሚነት መታገዷ የውጭ ምንዛሪ ማጣትንና የሥራ ዕድል ማጥበብን ጨምሮ በርካታ ጉዳቶችን እንደሚያስከትልባት ይታመናል። ኢትዮጵያ ከጆ ባይደን አስተዳደር ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎች በኋላ የአግዋ ዕድልን የተነጠቀች ሲሆን በኢትዮጵያ ያለው ችግር አሳሳቢ ነው የምትለው አሜሪካ አገሪቱ በሚቀጥሉት 60 ቀናት ውስጥ የሚጠበቅባትን የምታከናውን ከሆነ ወደ አግዋ ዳግም ልትመለስ እንደምትችል አስታውቃለች። አግዋ ምንድን ነው? The African Growth and Opportunity Act [በግርድፍ ትርጉሙ የአፍሪካ ዕድገት እና ዕድል ድንጋጌ] ወይም አግዋ በአሜሪካ የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉና ከሰሃራ በታች ለሚገኙ አገራት ምርቶቻቸውን ከቀረጥ ነጻ ለአሜሪካ ገበያ እንዲያቀርቡ የሚያስችል ዕድል ወይም ችሮታ ነው። በአግዋ የተካተተ ማንኛውም አገር የሕግ የበላይነትን ለማስፈን መስራት፣ የሰብአዊ እና የሠራተኛ መብቶችን ማክበር፣ ፖለቲካዊ ብዝሃነትን ማስተናገድ፣ ገበያ መር ኢኮኖሚን መከተል ወይም ለመከተል መስራትን ጨምሮ የተለያዩ መስፈርቶች የተቀመጡ ሲሆን መስፈርቶቹ የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን እና በዕድሉ ለመቆየት የሚያስችሉ እንደሆነ በአዋጁ ተቀምጧል። አግዋ እንደ አውሮፓውያኑ በግንቦት 18/2000 በአሜሪካ ኮንግረንስ የጸደቀ ሲሆን በ2025 ክለሳ ይደረግበታል። ይህ የንግድ ዕድል ሥርዓት እንደ አውሮፓውያኑ ከ2000 እስከ 2008 እንዲተገበር ታስቦ የተጀመረ ቢሆንም፣ በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳት የነበሩት ጆርጅ ቡሽ እስከ 2015 እንዲራዘም ፈርመዋል። በ2015 ላይ ደግሞ ይህ ዕድል እስከ 2025 እንዲራዘም የያኔው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በፊርማቸው አጽደቀዋል። በአሜሪካ መንግሥት ችሮታ የቀረበውና አፍሪካን በሚመለከት የአገሪቱ የንግድ ፖሊስ አካል የሆነው አግዋ ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት እና በአሜሪካ መካከል የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስርን ማበረታታት፤ በአገራቱ ያሉ ንግዶችን ለአሜሪካ ኢንቬስተሮች ክፍት ማድረግ እንዲሁም ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያን እና ዕድገትን መደገፍ ቀዳሚ ግቦቹ ናቸው። ኢትዮጵያ ከአግዋ ምን ተጠቀመች? እንድ አውሮፓውያኑ በ2019 በአግዋ ሥርዓት አማካኝነት አሜሪካ 8.4 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን ማስገባቷን የአሜሪካ ፌዴራል መንግሥት የንግድ ጉዳዮች አማካሪ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ይህ ተቋም ባወጣው መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ በዚያው ዓመት 246 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን በአግዋ አማካኝነት ወደ አሜሪካ ልካለች። ከተላኩት ምርቶች አብዛኛውን የሚሸፍኑት አልባሳት፣ አበባ እና ጫማን የመሳሰሉ ናቸው። ናይጄሪያ በአግዋ ዕድል 3.1 ቢሊዮን ዶላር የሚገመቱ ምርቶችን [በብዛት ድፍድፍ ነዳጅ] በመላክ የዚያ ዓመት የዕድሉ ቀዳሚ ተጠቃሚ ነበረች። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢኮኖሚ አማካሪ ማሞ ምህረቱ (ዶ/ር) ፎሬይን ፖሊስ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ኢትዮጵያ በአግዋ ሥርዓት በኩል እንደ ለአሜሪካ ገበያ ያቀረበችው ምርት ወደ 150 ሚሊዮን ዶላር ማደጉን አስፍረዋል። ይህም ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ከላከችው አጠቃላይ ምርት ግማሹን የሚሸፍን ነው። አግዋ ይፋ በሆነበት ዓመት ከኢትዮጵያ የተላከው ምርት 28 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ሲሆን ከ20 ዓመታት በኋላ የተላከው ምርት ከአምስት እጥፍ የላቀ ነው። ሂደቱም ለኢትዮጵያ ዘላቂ የሆነ የውጭ ምንዛሪ ግኝት እና የዜጎች የሥራ ዕድል ምንጭ ሆኖ ቆይቷል። ማሞ ምህረቱ በጽሁፋቸው በአግዋ ዕድል አማካኝነት ኢትዮጵያ ከምትልካቸው ምርቶች አልባሳትና የቆዳ ምርቶች ኢንዱስትሪ ብቻቸውን ለ200 ሺህ ዜጎች ቀጥተኛ የሥራ ዕድል መፍጠሩን ገልጸው ከተጠቃሚዎቹ 80 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። አማካሪው 30 ሺህ ሠራተኞች ያሉትን የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ለአብነት በማንሳት 95 በመቶ የሚሆኑት ሠራተኞች ሴት መሆናቸው እና የሥራ ልምድ ለሌላቸው ወጣቶች ዕድል መፍጠሩን አስረድተዋል። አጠቃላይ የኢንዱስትሪ ማዕቀፉ ደግሞ እንደ ትራንስፖርትና ሆቴል ካሉ አነስተኛ ቢዝነሶች እስከ ጥሬ ዕቃ አቅራቢ ባለው ትስስር ከአንድ ሚሊዮን ለሚልቅ ዜጋ የገቢ ምንጭ መሆኑን አስረድተዋል። በሌላ በኩል የኢንቨስትመንት ኮሚሽነሯ ሌሊሴ ነሜ ለአሜሪካ መንግሥት በጻፉትና በኮሚሽኑ ማኅበራዊ ገጾች በተሰራጨ ግልጽ ደብዳቤ፣ አግዋ አሜሪካን ጨምሮ ታላላቅ የዓለም ኩባንያዎች ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ዕድል መስጠቱን አስታውሰዋል። በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚመረቱ ጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት 80 በመቶ በአግዋ በኩል የገበያ መዳረሻቸው አሜሪካ እንደሆነ ያነሱት ኮሚሽነሯ፣ አግዋ በከተሞች ዙሪያ ለሚኖሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ዜጎች የገቢ ምንጭ ሆኖ ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉ እያገዘ እንደሆነ ገልጸዋል። በተጨማሪም ከገጠር ወደ ከተማ ሥራ ፍለጋ ለሚፈልሱና በርካታ ሴቶች የእንጀራ ገመድ መሆኑንም በደብዳቤያቸው አስፍረዋል። ኢትዮጵያ ከአግዋ ዕድል መታገዷ ከመገለጹ ከሳምንታት በፊት በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው ስለ አግዋ አስተያየት የሰጡት ማሞ ምህረቱ አግዋ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪን እንድታስፋፋ አስተዋፅኦ እንደነበረው ጠቁመዋል። "ከጥቂት ዓመታት በፊት የነበረን የኢንዱስትሪ ፓርክ አንድ ብቻ ነበር። አሁን ግን በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የኢንዱስትሪ ፓርኮችን መገንባት ችለናል። ያንንም ተከትሎ ብዙ ሠራተኞች ቀጥረናል ያንንም ተከትሎ የወጪ ንግዳችንን ማስፋት ችለናል በግብርና ላይ መሰረት ያደረገው ኢኮኖሚ ሌሎች የኢኮኖሚ ሴክተሮችንም ለማበረታታት አግዋ የራሱ የሆነ አስተዎፅኦ አበርክቷል" ብለዋል። የኢትዮጵያ ከአግዋ መታግድ ምን ጉዳት ያስከትላል? ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ከኢንቨስትመንት ኮሚሽነሯ ተማጽኖ በተቃራኒ የአሜሪካ መንግሥት ኢትዮጵያን ከአግዋ አግዷል። ይህም አገሪቱን ከአግዋ የምታገኘውን ጥቅም በሙሉ እንድታጣ ያደርጋታል። የኢንቨስትመንት ኮሚሽነሯ በደብዳቤያቸው ኢትዮጵያ ከአግዋ የምትታገድ ከሆነ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ ኢንቨስተሮችም ተጎጂ እንደሚሆኑ አንስተዋል። ማሞ ምህረቱ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ሲናገሩ በኢትዮጵያ ያለው አስተዳደር የተሻለ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ሁኔታ እየፈጠረ መሆኑን ገልጸው ኢትዮጵያ በአግዋ ለመቆየት የሚስያችሏት መስፈርቶችን "ከመቼውም ጊዜ በላይ" ያሟላችበት ወቅት ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በስፋት እንዲገነቡና ሰፊ የሥራ እድል እንዲፈጠር ምክንያት ከሆኑ ጉዳዮች አግዋ አንዱ እንደሆነ ያነሱት ማሞ "የአግዋ እድል በሚቀርበት ጊዜ ይሄ ሁሉ ነገር ይቀራል ማለት አይደለም። ግን አሉታዊ ውጤት ይኖረዋል ማለት ነው። .... አግዋ ቢሄድም እንኳን እነዚህ ኢንቨስተሮች ነቅለው ይሄዳሉ ማለት አይደለም" ሲሉ ገልጸዋል። ሆኖም የኢትዮጵያ ከአግዋ ዕድል መታገድ ዋነኛ ተጠቂ የሚያደርገው ከማንም በላይ የፋብሪካዎች ሠራተኞችን ቢሆንም ከእነሱ ጋር ተያይዘው የሚጎዱ ተጠቃሚዎች መኖራቸውን አመልክተዋል። "በተለይ ሴት ሠራተኞች ይጎዳሉ። በተጨማሪም በኢንዱስትሪ ፓርኮች አካባቢ ሌሎች በተዘዋዋሪ መልኩ የሥራ እድል የፈጠሩ ሰዎችንም ይጎዳል" በማለት የምግብ፣ የትራንስፖርት፣ የትምህርት፣ የቤት ኪራይ እና መሰል አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ ሰዎች ተጎጂ እንደሚሆኑ አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ከቀናት በፊት የተነጠቀችው የአግዋ ዕድል በቀጥታና በተዘዋዋሪ የሥራ ዕድል ያገኙ ዜጎች ላይ ጫና ከማሳረፍ እና የውጭ ምንዛሪ ግኝቷን ከመቀነስ ባሻገር በጦርነት፣ በኮቪድ 19 ወርርሽኝና በሌሎች ምክንያቶች ለተፈተነው ምጣኔ ሀብቷ ሌላ መስናክል መሆኑ አይቀርም። | የኢትዮጵያ ከአግዋ መታገድ በሥራ ዕድል እና በውጭ ምንዛሪ ምን ያጎድልባታል? የአሜሪካ መንግሥት ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገራት የዘረጋው ከቀረጥ ነጻ ዕድል ተጠቃሚ የነበረችው ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ ከዚህ ዕድል መታገዷ ተሰምቷል። በ2005 ዓ.ም የአግዋ ፎረምን ያስተናገደችው ኢትዮጵያ በአግዋ በኩል ለሁለት አስርት ዓመታት የተለያዩ ምርቶችን [በስፋት ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት] ለአሜሪካ ገበያ በማቅረብ ለመቶ ሺዎች የሥራ ዕድል በመፍጠር በሚሊዮኖች የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ ስታገኝ ቆይታለች። እንደ አውሮፓውያኑ በ2000 ይፋ በተደረገው በዚህ የቀረጥ ነጻ ዕድል ተጠቃሚ ከሆኑ 38 አገራት አንዷ የነበረችው ኢትዮጵያ የተለያዩ ምርቶችን ለአሜሪካ ገበያ ስታቀርብ ቆይታ ከዚህ ተጠቃሚነት መታገዷ የውጭ ምንዛሪ ማጣትንና የሥራ ዕድል ማጥበብን ጨምሮ በርካታ ጉዳቶችን እንደሚያስከትልባት ይታመናል። ኢትዮጵያ ከጆ ባይደን አስተዳደር ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎች በኋላ የአግዋ ዕድልን የተነጠቀች ሲሆን በኢትዮጵያ ያለው ችግር አሳሳቢ ነው የምትለው አሜሪካ አገሪቱ በሚቀጥሉት 60 ቀናት ውስጥ የሚጠበቅባትን የምታከናውን ከሆነ ወደ አግዋ ዳግም ልትመለስ እንደምትችል አስታውቃለች። አግዋ ምንድን ነው? The African Growth and Opportunity Act [በግርድፍ ትርጉሙ የአፍሪካ ዕድገት እና ዕድል ድንጋጌ] ወይም አግዋ በአሜሪካ የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉና ከሰሃራ በታች ለሚገኙ አገራት ምርቶቻቸውን ከቀረጥ ነጻ ለአሜሪካ ገበያ እንዲያቀርቡ የሚያስችል ዕድል ወይም ችሮታ ነው። በአግዋ የተካተተ ማንኛውም አገር የሕግ የበላይነትን ለማስፈን መስራት፣ የሰብአዊ እና የሠራተኛ መብቶችን ማክበር፣ ፖለቲካዊ ብዝሃነትን ማስተናገድ፣ ገበያ መር ኢኮኖሚን መከተል ወይም ለመከተል መስራትን ጨምሮ የተለያዩ መስፈርቶች የተቀመጡ ሲሆን መስፈርቶቹ የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን እና በዕድሉ ለመቆየት የሚያስችሉ እንደሆነ በአዋጁ ተቀምጧል። አግዋ እንደ አውሮፓውያኑ በግንቦት 18/2000 በአሜሪካ ኮንግረንስ የጸደቀ ሲሆን በ2025 ክለሳ ይደረግበታል። ይህ የንግድ ዕድል ሥርዓት እንደ አውሮፓውያኑ ከ2000 እስከ 2008 እንዲተገበር ታስቦ የተጀመረ ቢሆንም፣ በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳት የነበሩት ጆርጅ ቡሽ እስከ 2015 እንዲራዘም ፈርመዋል። በ2015 ላይ ደግሞ ይህ ዕድል እስከ 2025 እንዲራዘም የያኔው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በፊርማቸው አጽደቀዋል። በአሜሪካ መንግሥት ችሮታ የቀረበውና አፍሪካን በሚመለከት የአገሪቱ የንግድ ፖሊስ አካል የሆነው አግዋ ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት እና በአሜሪካ መካከል የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስርን ማበረታታት፤ በአገራቱ ያሉ ንግዶችን ለአሜሪካ ኢንቬስተሮች ክፍት ማድረግ እንዲሁም ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያን እና ዕድገትን መደገፍ ቀዳሚ ግቦቹ ናቸው። ኢትዮጵያ ከአግዋ ምን ተጠቀመች? እንድ አውሮፓውያኑ በ2019 በአግዋ ሥርዓት አማካኝነት አሜሪካ 8.4 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን ማስገባቷን የአሜሪካ ፌዴራል መንግሥት የንግድ ጉዳዮች አማካሪ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ይህ ተቋም ባወጣው መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ በዚያው ዓመት 246 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን በአግዋ አማካኝነት ወደ አሜሪካ ልካለች። ከተላኩት ምርቶች አብዛኛውን የሚሸፍኑት አልባሳት፣ አበባ እና ጫማን የመሳሰሉ ናቸው። ናይጄሪያ በአግዋ ዕድል 3.1 ቢሊዮን ዶላር የሚገመቱ ምርቶችን [በብዛት ድፍድፍ ነዳጅ] በመላክ የዚያ ዓመት የዕድሉ ቀዳሚ ተጠቃሚ ነበረች። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢኮኖሚ አማካሪ ማሞ ምህረቱ (ዶ/ር) ፎሬይን ፖሊስ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ኢትዮጵያ በአግዋ ሥርዓት በኩል እንደ ለአሜሪካ ገበያ ያቀረበችው ምርት ወደ 150 ሚሊዮን ዶላር ማደጉን አስፍረዋል። ይህም ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ከላከችው አጠቃላይ ምርት ግማሹን የሚሸፍን ነው። አግዋ ይፋ በሆነበት ዓመት ከኢትዮጵያ የተላከው ምርት 28 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ሲሆን ከ20 ዓመታት በኋላ የተላከው ምርት ከአምስት እጥፍ የላቀ ነው። ሂደቱም ለኢትዮጵያ ዘላቂ የሆነ የውጭ ምንዛሪ ግኝት እና የዜጎች የሥራ ዕድል ምንጭ ሆኖ ቆይቷል። ማሞ ምህረቱ በጽሁፋቸው በአግዋ ዕድል አማካኝነት ኢትዮጵያ ከምትልካቸው ምርቶች አልባሳትና የቆዳ ምርቶች ኢንዱስትሪ ብቻቸውን ለ200 ሺህ ዜጎች ቀጥተኛ የሥራ ዕድል መፍጠሩን ገልጸው ከተጠቃሚዎቹ 80 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። አማካሪው 30 ሺህ ሠራተኞች ያሉትን የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ለአብነት በማንሳት 95 በመቶ የሚሆኑት ሠራተኞች ሴት መሆናቸው እና የሥራ ልምድ ለሌላቸው ወጣቶች ዕድል መፍጠሩን አስረድተዋል። አጠቃላይ የኢንዱስትሪ ማዕቀፉ ደግሞ እንደ ትራንስፖርትና ሆቴል ካሉ አነስተኛ ቢዝነሶች እስከ ጥሬ ዕቃ አቅራቢ ባለው ትስስር ከአንድ ሚሊዮን ለሚልቅ ዜጋ የገቢ ምንጭ መሆኑን አስረድተዋል። በሌላ በኩል የኢንቨስትመንት ኮሚሽነሯ ሌሊሴ ነሜ ለአሜሪካ መንግሥት በጻፉትና በኮሚሽኑ ማኅበራዊ ገጾች በተሰራጨ ግልጽ ደብዳቤ፣ አግዋ አሜሪካን ጨምሮ ታላላቅ የዓለም ኩባንያዎች ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ዕድል መስጠቱን አስታውሰዋል። በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚመረቱ ጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት 80 በመቶ በአግዋ በኩል የገበያ መዳረሻቸው አሜሪካ እንደሆነ ያነሱት ኮሚሽነሯ፣ አግዋ በከተሞች ዙሪያ ለሚኖሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ዜጎች የገቢ ምንጭ ሆኖ ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉ እያገዘ እንደሆነ ገልጸዋል። በተጨማሪም ከገጠር ወደ ከተማ ሥራ ፍለጋ ለሚፈልሱና በርካታ ሴቶች የእንጀራ ገመድ መሆኑንም በደብዳቤያቸው አስፍረዋል። ኢትዮጵያ ከአግዋ ዕድል መታገዷ ከመገለጹ ከሳምንታት በፊት በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው ስለ አግዋ አስተያየት የሰጡት ማሞ ምህረቱ አግዋ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪን እንድታስፋፋ አስተዋፅኦ እንደነበረው ጠቁመዋል። "ከጥቂት ዓመታት በፊት የነበረን የኢንዱስትሪ ፓርክ አንድ ብቻ ነበር። አሁን ግን በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የኢንዱስትሪ ፓርኮችን መገንባት ችለናል። ያንንም ተከትሎ ብዙ ሠራተኞች ቀጥረናል ያንንም ተከትሎ የወጪ ንግዳችንን ማስፋት ችለናል በግብርና ላይ መሰረት ያደረገው ኢኮኖሚ ሌሎች የኢኮኖሚ ሴክተሮችንም ለማበረታታት አግዋ የራሱ የሆነ አስተዎፅኦ አበርክቷል" ብለዋል። የኢትዮጵያ ከአግዋ መታግድ ምን ጉዳት ያስከትላል? ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ከኢንቨስትመንት ኮሚሽነሯ ተማጽኖ በተቃራኒ የአሜሪካ መንግሥት ኢትዮጵያን ከአግዋ አግዷል። ይህም አገሪቱን ከአግዋ የምታገኘውን ጥቅም በሙሉ እንድታጣ ያደርጋታል። የኢንቨስትመንት ኮሚሽነሯ በደብዳቤያቸው ኢትዮጵያ ከአግዋ የምትታገድ ከሆነ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ ኢንቨስተሮችም ተጎጂ እንደሚሆኑ አንስተዋል። ማሞ ምህረቱ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ሲናገሩ በኢትዮጵያ ያለው አስተዳደር የተሻለ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ሁኔታ እየፈጠረ መሆኑን ገልጸው ኢትዮጵያ በአግዋ ለመቆየት የሚስያችሏት መስፈርቶችን "ከመቼውም ጊዜ በላይ" ያሟላችበት ወቅት ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በስፋት እንዲገነቡና ሰፊ የሥራ እድል እንዲፈጠር ምክንያት ከሆኑ ጉዳዮች አግዋ አንዱ እንደሆነ ያነሱት ማሞ "የአግዋ እድል በሚቀርበት ጊዜ ይሄ ሁሉ ነገር ይቀራል ማለት አይደለም። ግን አሉታዊ ውጤት ይኖረዋል ማለት ነው። .... አግዋ ቢሄድም እንኳን እነዚህ ኢንቨስተሮች ነቅለው ይሄዳሉ ማለት አይደለም" ሲሉ ገልጸዋል። ሆኖም የኢትዮጵያ ከአግዋ ዕድል መታገድ ዋነኛ ተጠቂ የሚያደርገው ከማንም በላይ የፋብሪካዎች ሠራተኞችን ቢሆንም ከእነሱ ጋር ተያይዘው የሚጎዱ ተጠቃሚዎች መኖራቸውን አመልክተዋል። "በተለይ ሴት ሠራተኞች ይጎዳሉ። በተጨማሪም በኢንዱስትሪ ፓርኮች አካባቢ ሌሎች በተዘዋዋሪ መልኩ የሥራ እድል የፈጠሩ ሰዎችንም ይጎዳል" በማለት የምግብ፣ የትራንስፖርት፣ የትምህርት፣ የቤት ኪራይ እና መሰል አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ ሰዎች ተጎጂ እንደሚሆኑ አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ከቀናት በፊት የተነጠቀችው የአግዋ ዕድል በቀጥታና በተዘዋዋሪ የሥራ ዕድል ያገኙ ዜጎች ላይ ጫና ከማሳረፍ እና የውጭ ምንዛሪ ግኝቷን ከመቀነስ ባሻገር በጦርነት፣ በኮቪድ 19 ወርርሽኝና በሌሎች ምክንያቶች ለተፈተነው ምጣኔ ሀብቷ ሌላ መስናክል መሆኑ አይቀርም። | https://www.bbc.com/amharic/news-59151040 |
3politics
| በምዕራብ ወለጋ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 28 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ | በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት 28 ሰዎች መገደላቸውን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ገለጸ። ማክሰኞ መጋቢት 21/2013 ዓ.ም በዞኑ ውስጥ በሚገኘው ባቦ ገንቤል ወረዳ በቦኔ ቀበሌ የተፈጸመውን ጥቃት ኦነግ-ሸኔ የተባለው ቡድን እንደፈጸመው የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል አራርሳ መርዳሳ አመልክተዋል። ቡድኑ በጥቃቱ ዕለት ከምሽቱ ሦሰት ሰዓት ላይ ከ50 በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎችን ሰብስቦ "ጭፍጨፋ ፈፅሟል" ሲሉ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። በጥቃቱ ከተገደሉት 28 ሰዎች መካከል 16ቱ ወንዶች ሲሆኑ 12ቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን የተናገሩት በተጨማሪ 12 ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል። ጥቃቱን በተመለከተ መግለጫ ያወጣው የኦሮሚያ ክልል መንግሥትም "አሰቃቂና ዘግናኝ" ያለውን ጥቃት የፈጸመው ኦነግ-ሸኔ እንደሆነ አመልክቷል። የፖሊስ ኮሚሽነሩ አራርሳ መርዳሳም ከጥቃቱ በኋላ የክልሉ ፖሊስ በአካባቢው በወሰደው እርምጃ የታጣቂው ቡድን አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል። የክልሉ መንግሥት መግለጫ በጥቃቱ ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉና የጸጥታ አካላት በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ በጥቃት ፈጻሚዎቹ ላይ ስለደረሰ ጉዳት ያለው ነገር የለም። ጨምሮም ቡድኑን የህወሓት ተላላኪ በመሆን በአካባቢው የመንግሥት መዋቅርን በማፍረስ በገጠርና በከተማ በመንግሥት አመራሮችና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከዚህ በፊት "ዘግናኝ የሽብር ጥቃቶችን ሲፈፅም ቆይቷል" ብሏል። ቡድኑ በሚፈጽመው ጥቃት የቀበሌና የክልል አመራሮችን ጨምሮ በርካታ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን ያመለከተው የክልሉ መንግሥት መግለጫ፤ በጥቃቶቹ የግልና የመንግሥት ንብረቶች መውደማቸውንም ገልጿል። መንግሥት "የኦነግ ሸኔ እኩይ ተግባር ለማስወገድ በወሰደው የሕግ የበላይነትን የማስከበር እርምጃ" ቡድኑ እየተዳከመ መሆኑን በመጥቀስ ነገር ግን "በሞትና በህይወት መካከል ሆኖ የጥፋት ሴራውንና እርምጃውን ቀጥሏል" ብሏል። በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ውስጥ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተለይቶ የወጣውና መንግሥት ኦነግ-ሸኔ የሚለው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን እንደሚንቀሳቀስ ይነገራል። በዚህ አካባቢ በተለያዩ ጊዜያት በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሠላማዊ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ ሲዘገብ ቆይቷል። በተጨማሪም በአካባቢው ባሉ የመንግሥት መዋቅሮች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎችና፣ የጸጥታ አካላትና አመራሮች በተለያዩ ጊዜያት በተፈጸሙ ጥቃቶች ሰለባ ሆነዋል። ለእነዚህ ጥቃቶችም መንግሥት በኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) ይመራል የሚባለው ኦነግ-ሸኔን ተጠያቂ ሲያደርግ ቡድኑ ግን ግድያዎቹን አለመፈጸሙን ሲያስተባብል ቆይቷል። መንግሥት ታጣቂ ቡድኑን ከአካባቢው ለማስወገድ በተለያዩ ጊዜያት በወሰዳቸው እርምጃዎች በርካታ አባላቱን መግደሉንና መማረኩን ሲገልጽ መቆየቱ ይታወሳል። የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር እንዳሉት ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የጸጥታ አካላት በኦነግ-ሸኔ ላይ በተወሰዱት እርምጃ 1947 አባላቱ ሲገደሉ 489ቱ ደግሞ መማረካቸውን ተናግረዋል። በዚህም ከጥቂት ወራት በፊትም የቡድኑ መሪ የሆነው ኩምሳ ድሪባ በጸጥታ ኃይሎች መገደሉ የተነገረ ቢሆንም ከቀናት በፊት በአልጀዚራ ቴሌቪዥን ላይ መታየቱ አነጋጋሪ ሆኗል። | በምዕራብ ወለጋ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 28 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት 28 ሰዎች መገደላቸውን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ገለጸ። ማክሰኞ መጋቢት 21/2013 ዓ.ም በዞኑ ውስጥ በሚገኘው ባቦ ገንቤል ወረዳ በቦኔ ቀበሌ የተፈጸመውን ጥቃት ኦነግ-ሸኔ የተባለው ቡድን እንደፈጸመው የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል አራርሳ መርዳሳ አመልክተዋል። ቡድኑ በጥቃቱ ዕለት ከምሽቱ ሦሰት ሰዓት ላይ ከ50 በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎችን ሰብስቦ "ጭፍጨፋ ፈፅሟል" ሲሉ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። በጥቃቱ ከተገደሉት 28 ሰዎች መካከል 16ቱ ወንዶች ሲሆኑ 12ቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን የተናገሩት በተጨማሪ 12 ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል። ጥቃቱን በተመለከተ መግለጫ ያወጣው የኦሮሚያ ክልል መንግሥትም "አሰቃቂና ዘግናኝ" ያለውን ጥቃት የፈጸመው ኦነግ-ሸኔ እንደሆነ አመልክቷል። የፖሊስ ኮሚሽነሩ አራርሳ መርዳሳም ከጥቃቱ በኋላ የክልሉ ፖሊስ በአካባቢው በወሰደው እርምጃ የታጣቂው ቡድን አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል። የክልሉ መንግሥት መግለጫ በጥቃቱ ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉና የጸጥታ አካላት በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ በጥቃት ፈጻሚዎቹ ላይ ስለደረሰ ጉዳት ያለው ነገር የለም። ጨምሮም ቡድኑን የህወሓት ተላላኪ በመሆን በአካባቢው የመንግሥት መዋቅርን በማፍረስ በገጠርና በከተማ በመንግሥት አመራሮችና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከዚህ በፊት "ዘግናኝ የሽብር ጥቃቶችን ሲፈፅም ቆይቷል" ብሏል። ቡድኑ በሚፈጽመው ጥቃት የቀበሌና የክልል አመራሮችን ጨምሮ በርካታ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን ያመለከተው የክልሉ መንግሥት መግለጫ፤ በጥቃቶቹ የግልና የመንግሥት ንብረቶች መውደማቸውንም ገልጿል። መንግሥት "የኦነግ ሸኔ እኩይ ተግባር ለማስወገድ በወሰደው የሕግ የበላይነትን የማስከበር እርምጃ" ቡድኑ እየተዳከመ መሆኑን በመጥቀስ ነገር ግን "በሞትና በህይወት መካከል ሆኖ የጥፋት ሴራውንና እርምጃውን ቀጥሏል" ብሏል። በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ውስጥ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተለይቶ የወጣውና መንግሥት ኦነግ-ሸኔ የሚለው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን እንደሚንቀሳቀስ ይነገራል። በዚህ አካባቢ በተለያዩ ጊዜያት በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሠላማዊ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ ሲዘገብ ቆይቷል። በተጨማሪም በአካባቢው ባሉ የመንግሥት መዋቅሮች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎችና፣ የጸጥታ አካላትና አመራሮች በተለያዩ ጊዜያት በተፈጸሙ ጥቃቶች ሰለባ ሆነዋል። ለእነዚህ ጥቃቶችም መንግሥት በኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) ይመራል የሚባለው ኦነግ-ሸኔን ተጠያቂ ሲያደርግ ቡድኑ ግን ግድያዎቹን አለመፈጸሙን ሲያስተባብል ቆይቷል። መንግሥት ታጣቂ ቡድኑን ከአካባቢው ለማስወገድ በተለያዩ ጊዜያት በወሰዳቸው እርምጃዎች በርካታ አባላቱን መግደሉንና መማረኩን ሲገልጽ መቆየቱ ይታወሳል። የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር እንዳሉት ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የጸጥታ አካላት በኦነግ-ሸኔ ላይ በተወሰዱት እርምጃ 1947 አባላቱ ሲገደሉ 489ቱ ደግሞ መማረካቸውን ተናግረዋል። በዚህም ከጥቂት ወራት በፊትም የቡድኑ መሪ የሆነው ኩምሳ ድሪባ በጸጥታ ኃይሎች መገደሉ የተነገረ ቢሆንም ከቀናት በፊት በአልጀዚራ ቴሌቪዥን ላይ መታየቱ አነጋጋሪ ሆኗል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56569258 |
0business
| በቻይና ተጠቃሚዎች የሚያዙት የምግብ መጠን ላይ ገደብ ሊበጅ ነው | ቻይና የምግብ ብክነትን ለማስቀረት ቆርጣ እንደተነሳችና በርካታ እርምጃዎችን ለመውሰድ መዘጋጀቷን አስታውቃለች። ፕሬዝዳንት ሺ ዢን ፒንግ በአገሪቱ የሚስተዋለውን የምግብ ብክነት '' አስደንጋጭና አሳዛኝ'' ሲሉ ገልጸውታል። 'ክሊን ፕሌት ካምፔይን' ወይም በአማርኛ ንፁህ የምግብ ሰሀን እንቅስቃሴ የተጀመረው ፐሬዝዳንቱ ከኮቪድ-19 በኋላ የምግብ ብክነት ቁልጭ ብሎ ታይቷል ማለታቸውን ተከትሎ ነው። ፕሬዝዳንቱ አክለውም '' የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ ይህንን ጉዳይ ልንከታተለው ይገባል'' ብለዋል። በተጨማሪም በቻይና ለሳምንታት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በርካታ የደቡባዊ የአገሪቱ ክፍሎች በጎርፍ መመታታቸውን ተከትሎ በቶኖች የሚቆጠር የገበሬዎች ምርት እንዳልንበር ሆኗል። ነገር ግን የቻይናው ብሄራዊ የዜና ተቋም 'ግሎባል ታይምስ' እነዚህ ምክንያቶች የምግብ እጥረት የሚያስከትሉ አይደሉም ካለ በኋላ የምግብ ብክነት በራሱ ግን እንደ ትልቅ ጉዳይ ሊታይ እንደሚገባው ገልጿል። የቴሌቪዥን ጣቢያው በበይነ መረብ አማካይነት በርካታ ምግቦችን ሲመገቡ በቀጥታ የሚያስተላልፉ ሰዎች ላይም ወቀሳ መሰል አስተያየት ሰጥቷል። የሺ ዢን ፒንግን ንግግር ተከትሎም የዉሃን የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሩ ማህበር ምግብ ቤቶች ለተጠቃሚዎች የሚያቀርቡት የምግብ ቁጥር ላይ ገደብ እንዲያስቀምጡ እየወተወተ ነው። በዚህም መሰረት በቡድን የሚመጡ ሰዎች ካላቸው ቁጥር በአንድ ያነሰ የምግብ አይነት ብቻ ነው ማዘዝ የሚችሉት። አራት ሰዎች ወደ አንድ ምግብ ቤት ጎራ ብለው አራት ምግብ ማዘዝ አይችሉም ማለት ነው። ስለዚህ አዝዘው መመገብ የሚችሉት ሶስት ምግብ ብቻ ይሆናል። ነገር ግን ይህ አሰራር ወደ ማህበረሰቡ ዘልቆ እስከሚገባ ብዙ ጊዜ ሊፈጅ እንደሚችል ተገምቷል። በቻይናውያን ባህል መሰረት ደግሞ ከሚመገቡት ምግብ በላይ ማዘዝ እንደ ጥሩ ነገር የሚቆጠር ነው። ሰዎች በቡድን ሆነው ሲመገቡ ሰሀኖችና ትሪዎች ባዶ ሆነው ከታዩ አስተናጋጁ ግለሰብ ወይም ድርጅት እንደ መጥፎ እንግዳ ተቀባይ ነው የሚቆጠረው። 'ኤን-1' የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ሀሳብ በበርካቶች ትችትን አስተናግዷል። "በጣም አስጨናቂ ነገር ነው" ብለው የተከራከሩም አልጠፉም። '' አንድ ሰው ብቻውን ወደ ምግብ ቤት ቢሄድስ? ምን ያክል ምግብ ነው ማዘዝ የሚችለው? ምንም?'' ሲል አንድ ግለሰብ በአንድ የቻይና ማህበራዊ ሚዲያ በኩል ሀሳቡን አስፍሯል። ሌሎች ደግሞ አብዛኛዎቹ ምግብ ቤቶች ምግብ እንዲባክን አያደርጉም፤ እንደውም በርካታ የመንግስት ባለስልጣናት ናቸው በየአጋጣሚው ምግብ እንዲባክን የሚያደርጉት ብለዋል። የቻይናው የዜና ወኪል ሲሲቲቪ በበኩሉ በቀጥታ ስርጭት በአንድ ጊዜ ብዙ ምግብ በአፍ የመጉረስ ትእይንት የሚያሳዩ ግለሰቦችም ለዚህ ብክነት አስተዋጽኦ እያደረጉ እንደሆነ ገልጿል። ''ሙክባንግ' በመባል የሚታወቁት እነዚህ የቀጥታ ስርጭቶች በብዙ የቻይና አካባቢዎችና እስያ አገራት ተወዳጅ ናቸው። ቻይና ይህን መሰል የምግብ ብክንትን የመከላከል እንቅስቃሴ ስትጀምር ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም። በአውሮፓውያኑ 2013 እጅግ የተጋነኑ የምግብ ድግሶችን እና የባለስልጣናት ግብዣዎችን ለማስቀረት ስራዎችን አከናውና ነበር። አንድ ቻይና ውስጥ የሚንቀሳቀስና አካባቢ ጥበቃ ላይ የሚሰራ ድርጅት እንዳስታወቀው በአውሮፓውያኑ 2015 በአገሪቱ ከ17 እስከ 18 ሚሊዮን ቶን ምግብ ተርፎ ተደፍቷል። | በቻይና ተጠቃሚዎች የሚያዙት የምግብ መጠን ላይ ገደብ ሊበጅ ነው ቻይና የምግብ ብክነትን ለማስቀረት ቆርጣ እንደተነሳችና በርካታ እርምጃዎችን ለመውሰድ መዘጋጀቷን አስታውቃለች። ፕሬዝዳንት ሺ ዢን ፒንግ በአገሪቱ የሚስተዋለውን የምግብ ብክነት '' አስደንጋጭና አሳዛኝ'' ሲሉ ገልጸውታል። 'ክሊን ፕሌት ካምፔይን' ወይም በአማርኛ ንፁህ የምግብ ሰሀን እንቅስቃሴ የተጀመረው ፐሬዝዳንቱ ከኮቪድ-19 በኋላ የምግብ ብክነት ቁልጭ ብሎ ታይቷል ማለታቸውን ተከትሎ ነው። ፕሬዝዳንቱ አክለውም '' የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ ይህንን ጉዳይ ልንከታተለው ይገባል'' ብለዋል። በተጨማሪም በቻይና ለሳምንታት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በርካታ የደቡባዊ የአገሪቱ ክፍሎች በጎርፍ መመታታቸውን ተከትሎ በቶኖች የሚቆጠር የገበሬዎች ምርት እንዳልንበር ሆኗል። ነገር ግን የቻይናው ብሄራዊ የዜና ተቋም 'ግሎባል ታይምስ' እነዚህ ምክንያቶች የምግብ እጥረት የሚያስከትሉ አይደሉም ካለ በኋላ የምግብ ብክነት በራሱ ግን እንደ ትልቅ ጉዳይ ሊታይ እንደሚገባው ገልጿል። የቴሌቪዥን ጣቢያው በበይነ መረብ አማካይነት በርካታ ምግቦችን ሲመገቡ በቀጥታ የሚያስተላልፉ ሰዎች ላይም ወቀሳ መሰል አስተያየት ሰጥቷል። የሺ ዢን ፒንግን ንግግር ተከትሎም የዉሃን የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሩ ማህበር ምግብ ቤቶች ለተጠቃሚዎች የሚያቀርቡት የምግብ ቁጥር ላይ ገደብ እንዲያስቀምጡ እየወተወተ ነው። በዚህም መሰረት በቡድን የሚመጡ ሰዎች ካላቸው ቁጥር በአንድ ያነሰ የምግብ አይነት ብቻ ነው ማዘዝ የሚችሉት። አራት ሰዎች ወደ አንድ ምግብ ቤት ጎራ ብለው አራት ምግብ ማዘዝ አይችሉም ማለት ነው። ስለዚህ አዝዘው መመገብ የሚችሉት ሶስት ምግብ ብቻ ይሆናል። ነገር ግን ይህ አሰራር ወደ ማህበረሰቡ ዘልቆ እስከሚገባ ብዙ ጊዜ ሊፈጅ እንደሚችል ተገምቷል። በቻይናውያን ባህል መሰረት ደግሞ ከሚመገቡት ምግብ በላይ ማዘዝ እንደ ጥሩ ነገር የሚቆጠር ነው። ሰዎች በቡድን ሆነው ሲመገቡ ሰሀኖችና ትሪዎች ባዶ ሆነው ከታዩ አስተናጋጁ ግለሰብ ወይም ድርጅት እንደ መጥፎ እንግዳ ተቀባይ ነው የሚቆጠረው። 'ኤን-1' የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ሀሳብ በበርካቶች ትችትን አስተናግዷል። "በጣም አስጨናቂ ነገር ነው" ብለው የተከራከሩም አልጠፉም። '' አንድ ሰው ብቻውን ወደ ምግብ ቤት ቢሄድስ? ምን ያክል ምግብ ነው ማዘዝ የሚችለው? ምንም?'' ሲል አንድ ግለሰብ በአንድ የቻይና ማህበራዊ ሚዲያ በኩል ሀሳቡን አስፍሯል። ሌሎች ደግሞ አብዛኛዎቹ ምግብ ቤቶች ምግብ እንዲባክን አያደርጉም፤ እንደውም በርካታ የመንግስት ባለስልጣናት ናቸው በየአጋጣሚው ምግብ እንዲባክን የሚያደርጉት ብለዋል። የቻይናው የዜና ወኪል ሲሲቲቪ በበኩሉ በቀጥታ ስርጭት በአንድ ጊዜ ብዙ ምግብ በአፍ የመጉረስ ትእይንት የሚያሳዩ ግለሰቦችም ለዚህ ብክነት አስተዋጽኦ እያደረጉ እንደሆነ ገልጿል። ''ሙክባንግ' በመባል የሚታወቁት እነዚህ የቀጥታ ስርጭቶች በብዙ የቻይና አካባቢዎችና እስያ አገራት ተወዳጅ ናቸው። ቻይና ይህን መሰል የምግብ ብክንትን የመከላከል እንቅስቃሴ ስትጀምር ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም። በአውሮፓውያኑ 2013 እጅግ የተጋነኑ የምግብ ድግሶችን እና የባለስልጣናት ግብዣዎችን ለማስቀረት ስራዎችን አከናውና ነበር። አንድ ቻይና ውስጥ የሚንቀሳቀስና አካባቢ ጥበቃ ላይ የሚሰራ ድርጅት እንዳስታወቀው በአውሮፓውያኑ 2015 በአገሪቱ ከ17 እስከ 18 ሚሊዮን ቶን ምግብ ተርፎ ተደፍቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-53762650 |